የተርኪዬ ኤኬ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዛፈር ሲራካያ ምን አሉ

 

👉 ኢትዮጵያ ከዓለማችን ጥንታዊ ስልጣኔዎች አንዷ ናት። ኢትዮጵያ በአፍሪካ የታሪክ ገጾች ውስጥ ጉልህ ታሪክ የጻፈች እንዲሁም በባህል፣ በታሪክ፣ በብዝሃነት፣ በእምነት፣ በቋንቋና ቅርስ የበለጸገችና በፈተናዎች ሳትበገር ዘመናትን የተሻገረች ሀገር ናት።

👉 ተርኪዬና ኢትዮጵያ የነጻነትና ሉዓላዊነት የአይበገሬነት መንፈስ የሚጋሩ ሀገራት ናቸው። ኢትዮጵያ እና ተርኪዬ በታሪክ ጥብቅ ቁርኝነት አላቸው። ተርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች።

👉 ኢትዮጵያ እና ተርኪዬ በዘመናት መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸው እና ትብብራቸው እያደገ መምጣቱንና በርካታ ስኬቶች እያስመዘገበ ይገኛል።

👉 ተርኪዬ ለቀጣናው ሰላምና ልማት መረጋገጥ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች።

👉 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ሃሳቦች ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ቀጣናውና የአፍሪካን ብልፅግናን ዕውን ማድረግ የሚያስችሉ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም