የወዳጅ ሀገራት እህት ፓርቲ ተወካዮች የመዲናዋን የመስህብ ስፍራዎች ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2017(ኢዜአ)፦ ለብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የመጡ የወዳጅ ሀገራት የእህት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ብሔራዊ ቤተ-መንግስትን ጨምሮ የተለያዩ የመስህብ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።

የሀገራት እህት ፓርቲዎች አመራሮች በብሔራዊ ቤተ-መንግስት፣ በእንጦጦ ፓርክ፣ በአንድነት ፓርክና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የፓርቲው አመራር አባላት፣ የአፍሪካና የብሪክስ አባል ሀገራት የእህት ፓርቲዎች የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሳቢያ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም