ከናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር አልሀጅ አሊቡካር ዳሎሪ መልዕክቶች

👉ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በመከባበር እና በጋራ እሴት ላይ የፀና ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።

👉 ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲ፣ ንግድ እና ባህል ጨምሮ በተለያዩ መስኮች አጋርነት አላቸው።

👉 ሁለቱ ሀገራት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥማቸውም ችግሮችን ለመፍታት ያለው ብቸኛ አማርጭ ትብብር እና አጋርነት ነው።

👉 ኤፒሲ እና ብልጽግና ፓርቲ የጋራ ግብ ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው።

👉 ሁለቱም ፓርቲዎች ልማትን ለማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እና የበለጸገ ሀገር ለመፍጠር እየሰሩ መሆናቸው ያላቸውን የአላማ አንድነት ያሳያል።

👉 የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ልማትና አንድነትን ለማምጣት ያለንን ቁርጠኝነት በጋራ የምናወድስበት ነው።

👉 የናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም