ነጋሪ 24

1

ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 24 ሰኔ 2015 ዓ.ም ዋጋ 15 ብር

ወርቃማ ዕድል በአዲስ ከፍታ



2

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ



3



4

የዳቦ ቅርጫት

አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11 +251-11-56-39-31 +251-11-56-52-21

ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09 enanegari@gmail.comበኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት

ማውጫ

መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች

ሣይንስን ከጥበብ

ያቆራኘ ሙዚየም 24

32

የዓይን ብርሃን

74



5

ዋና አዘጋጅ አብዱራህማን ናስር

ም/ ዋና አዘጋጆች ጌታቸው ሠናይ የሺመቤት ደመቀ

ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ

አዘጋጅ መንገሻ ገ/ሚካኤል

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com

ፎቶግራፍ በሃይሉ አስፋው

እርምት ባለሙያ ትዝታ ሁሴን

መልዕክትሙሉ ማዕድ!

እነሆ!

ነጋሪ ቁጥር 24 ከአንባቢዎቿ እጅ ስትገባ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥልቀት ያላቸው ዘገባዎች ይዛ ነው። እያንዳንዳቸው ርዕሰ ጉዳዮች በተለያዩ አተያዮች ተቀብበው፣ ምልከታዎችን ለማስፋት የሚያስችሉ ነጥቦችን አንስተዋል።

“ሁሉን ማያው ዲጂታል ሚዲያ” በርዕሰ ጉዳይነት ተነስቷል። ይህ ሚዲያ በአዎንታዊና በአሉታዊ መልኩ የሚያሳድረውን ተጽእኖ የሚያመላክቱ ነጥቦች ተጠቅሰዋል። በእያንዳንዳችን የዕለት ተዕለት የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ዲጂታል ሚዲያ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ እያሳረፈ መምጣቱ ይስተዋላል። ይህን በአግባቡ መጠቀምና ለአዎንታዊ አስተሳሰብ ግንባታ የሚውልበትን መንገድ መፈለግ መልካም እርምጃ መሆኑን የሚያመላክቱ ሀሳቦች ለማንሳት ተሞክሯል።

ነጋሪ “በህገ መንግስት፤ ሕገ መንግስታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት” በሚል ርዕስ ስር የቀረበው ትንታኔ የህገ መንግስትንና የፌዴራል ሥርዓትን በሚገባ የዳሰሰ ነው። ሥርዓቱ በዓለም ላይ ያለው ገጽታና ቱርፋቶቹን የሚያብራራ ሰፋ ያለ ግንዛቤ የሚሰጥ ነው። አገሮች የፌዴራል ሥርዓትን የሚመርጡበት ምክንያት፣ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ፣ ለህግ የበላይነት እውን መሆንና መብት መከበር ያለው አንደምታ በነጥብነት በማንሳት ትንታኔ ከተሰጠባቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ሕገ-መንግሥት፤ ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት እጅግ የተቆራኙ እና አንዱን ከአንዱ ለይቶ እንደማይታይ በጽሁፉ መነሻ ጉዳይ ተደርጎ ተጠቅሷል። የፌዴራላዊ ሥርዓት ዋነኛው መገለጫ የራስ እና የጋራ አስተዳዳር ማዕከል ያደረገ በመሆኑ የሥልጣን ክፍፍል እንዳለው ተንትኗል። ይህም ሕገ መንግሥትን መሰረት እንደሚያደርግም ያትታል። የሥልጣን ክፍፍል የሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ተከትሎ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም ያብራራል።

የፌዴራል ሥርዓቱ አባል መንግሥታት የአንዱን ሥልጣን ሌላው በማክበር በቅንጅት እና በመተባባር እየተንቀሳቀሱ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እና ነፃነቶች በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታት ለማክበር እና ለማስከበር፤ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው ፌዴራላዊ የአስተዳደር ሥርዓት እየገነቡ ለመሄድ ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊነት በፌዴራል ሥርዓት የተለየ ባህሪ እንዳላቸው የዳሰሰ ጽሁፍ ነውና አንብቡት።

የመገናኛ ብዙሃን ለአገር ግንባታ ያላቸው አዎንታዊ ሚና በተገለጸበት ጽሁፍ ውስጥ መገናኛ ብዙሃን፣ ለብሄራዊ ጥቅም መከበር፣ ሰላምና ደህንነት እውን መሆን አስፈላጊነቱን የሚያሳዩ አንኳር ነጥቦች ተነስተውበታል። መገናኛ ብዙሃን በማንኛውም ጊዜ ለብሄራዊ ጥቅም በመቆም አገራቸውን ከፍ የማድረግ አስፈላጊነትን አጽንኦት ተሰጥቶበታል። በተለይ ሰላምን ለማስፈንና ደህንነት ለማረጋገጥ የመገናኛ ብዙሃን የማይተካ ሚና አላቸው፤ ይህን ሚናቸውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን አሰራር መከተል ከብሄራዊ ጥቅም አኳያ ፋይዳው ላቅ ያለ መሆኑን “መገናኛ ብዙሃን በአገር ግንባታ” በሚል ርዕስ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ተብራርቷል፤ ጋብዘናችኋል።

“የአዲስ አበባን ወርቃማ ዕድል ወደ አዲስ ከፍታ” በሚለው ጽሁፍ ውስጥ አዲስ አበባ የአገር፣ የአህጉርና የዓለምአቀፍ መዲናነቷን ተከትለው የመጡ መልካም እድሎችን እንደወርቅ የማየት አስፈላጊነት ተጠቅሷል። እነዚህ ወርቃማ እድሎችን በአግባቡ በመጠቀምና ከተማዋን በማሳደግ የዲፕሎማሲ ከፍታ ላይ ማድረስ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ስለመሆኑ የተተነተነበት ጽሁፍ ነው። ከተማዋ የዓለምአቀፍ መዲናነቷን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መንቀሳቀስ፣ ዘመኑን በሚመጥን የዘመናዊነት ዘዬ መንቀሳቀስ እንዳለባት ርዕሰ ጉዳዩ እንደአንድ ወሳኝ ነጥብ ጠቅሷል።

በዚህ ዕትም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መሰረት ያደረጉ አንኳር ነጥቦች ለአንባቢያን አቅርበናል።

መልካም ንባብ!

ሁሉን ማያው - ዲጂታል ሚዲያ

6 ሕገ መንግሥት፤ ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት

12

መገናኛ ብዙሃን በአገር ግንባታ

18 የአዲስ አበባን ወርቃማ ዕድል

ወደ አዲስ ከፍታ 40

መጪውን ዘመን በጥበብ መራመድ መንገድ የቀየሰ -

ዩኒቨርሲቲ 50

ዋናው መድኃኒት ቤት 58

የጤናን ጉዳይ - በወፍ በረር 62

68



6

ሁሉን ማያው - ዲጂታል ሚዲያ

ማህበራዊ



7

ሁሉን ማያው - ዲጂታል ሚዲያ

ሙሴ መለሰ መረጃ

መረጃና የሰው ልጅ ሊበጠስ በማይችል ጠንካራ ትስስር የተጋመዱ ናቸው፡፡ የሰው ልጅ መልዕክትን በቃል ከመለዋወጥ አንስቶ ፊደል ቀርጾ ብራና ላይ ወደ መጻፍ ከዚያም ወደ ህትመት ውጤቶች በማደግ ብዙኃንን ለመድረስ ተግቷል፡፡ መጽሐፍ፣ ጋዜጣና መጽሔት እውቀትን በመላው ዓለም በማሰራጨት የሰዎችን የአስተሳሰብ አድማስ ከማስፋታቸው ባሻገር የመረጃ ፍሰት ተቋማዊ ሆኖ በግልጽ ሙያዊ መርህ (መለኪያ) እንዲሰራ የጋዜጠኝነት ጽንሰ ሀሳብን አዋልደዋል፡፡ የሬዲዮና የቴሌቪዥን መምጣትም የመገናኛ ብዙሃን ተደራሽነትን ከማስፋቱ ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበረውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ተዓማኒነት በእጅጉ አሳድጎት ነበር፡፡ ኢንተርኔት መጥቶ “ሁሉም ሰው” ጸሐፊና ተንታኝ እስኪሆን ድረስ ከሬዲዮ አሊያም ከቴሌቪዥን መስማት ከእውነት ከራሷ የመስማት ያህል እርግጥ ተደርጎ ይወሰድ እንደነበርም የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ኢንተርኔት

ኢንተርኔት የዓለምን ተጨባጭ ሁኔታ መከተል በሚያዳግት ፍጥነት እየለወጣት ይገኛል፡፡ ከዓለም መፈጠር አንስቶ በጊዜ እና በቦታ ተወስኖ የኖረው የሰው ልጅ በኢንተርኔት አማካኝነት ዓለምን ወደ ትንሽ መንደርነት ለውጧታል፡፡ ያለንበት ዘመን ሰዎች በየትኛውም የዓለም ጫፍ ቢኖሩ በቀላሉ መገናኘት፣ በጋራ መማር ወይንም መስራት፣ ጉባዔዎችን እንዲሁም የመዝናኛ መርሃግብሮችን



8

በአንድነት መታደም ወዘተ… የሚችሉበት ነው፡፡ ኢንተርኔት በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በትራንስፖርት፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በሕክምና፣ በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበትን ቆጥቦ ምርታማነትን በከፍተኛ ሁኔታ ቢያሳድግም በሀሰተኛና በተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ግን ዓለምን ክፉኛ እየፈተነ ይገኛል፡፡

ለበርካታ ዓመታት በዓለማችን ብቸኛ የመረጃ ምንጮች ሆነው የኖሩት የህትመት ውጤቶች (ጋዜጣ፣ መጽሔትና መጽሐፍ፣) እንዲሁም ሬዲዮና ቴሌቪዥን በዲጂታል ሚዲያዎች አማካኝነት ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸው እየተመናመነ መጥቷል፡፡

የዲጂታል ሚዲያ አስፈላጊነት

ዓለም ወደ ዲጂታላይዜሽን እያደረገች ባለው ግስጋሴ በርካታ አዎንታዊና አሉታዊ ለውጦች እየተስተናገዱ ሲሆን፤ ለውጦቹ ከሰው ልጅ ህልውና፣ ከሰብዓዊነት፣ ከግብረገብ እንዲሁም ከባህል አኳያ ቀውስ እንዳይፈጥሩ በማረቅ ለአገር እድገትና ለዜጎች ሕይወት መሻሻል መጠቀም ይገባል፡፡ ግብርናን ጨምሮ ለዘመናት በሰው ጉልበት ሲከወኑ የቆዩ ሁሉም ዘርፎች ለማለት በሚያስደፍር ልክ አሰራራቸውን ኮምፒዩተር ተኮር ወደ ማድረግ እየቀየሩ ነው፡፡ የአምራች፣ የአገልግሎት፣ የትምህርት፣ የንግድ፣ የመዝናኛ እና ሌሎችም ዘርፎች በኢንተርኔት ከመታገዝ አልፈው በሰው ሰራሽ አስተውህሎ አማካኝነት በሮቦት ወደ መስራት ጭምር እየተሸጋገሩ መሆኑን መረዳት ራስን ከጊዜው ጋራ ለማራመድ የቤት ስራዎችን ለመስራት ያነቃል፡ ፡ ዲጂታል ሚዲያ ካሉት በርካታ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡፡

ቀልጣፋና ሰፊ የመረጃ ተደራሽነት

በዲጂታል ሚዲያዎች መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ ለምሣሌ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት ዜናና ትንታኔ የሚሰሩ ድረ ገጾች፣ የፌስቡክ ገጾች፣ የዩቲዩብ ቻናሎች እና በተለያየ መንገድ ሰዎች ጋር የሚደርሱ ብሎጎች በአገሪቷ ያሉትን ዓበይት ክስተቶች ፈልፍለው በማውጣት ለሕዝቡ ያደርሳሉ፡፡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት ለማግኘትም እነዚህ የኦንላየን ሚዲያዎች ሁነኛ አማራጮች ናቸው፡ ፡ ኢትዮጵያን ለማወቅ የፈለገ ሰው ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህል፣ መልክዓ ምድር፣ ሕዝቦች፤ ፖለቲካ ወይንም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በዚህ ዙሪያ ከሚሰሩ ዲጂታል ሚዲያዎች በብዙ አማራጮች

ማግኘት ይችላል፡፡

ማኅበራዊ መስተጋብርን ማጠናከር

ዲጂታል ሚዲያዎች ሰዎች ተቀራርበው ሃሳብ እንዲለዋወጡ ድልድይ ሆነው በማገናኘት ላይ ናቸው፡፡ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ሰዎች በዩቲዩብ የቀጥታ ስርጭት ውይይቶችን ሲያካሂዱ፣ በፌስቡክ ገጾች ላይ በተለቀቁ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ሲሰጡ፣ የጋራ በሚያደርጉ ርዕሶች ጥላ ስር ኅብረት ሲፈጥሩ ማየት ዲጂታል ሚዲያው የራቀውንና የተበተነውን ምን ያህል የማቅረብና የመሰብሰብ ጉልበት እንዳለው ለመረዳት ያስችላል፡፡

ለምሣሌ ያህል ፌስቡክ ላይ የ’90ዎች ልጆች’ በሚል ስያሜ የተከፈተ ከ625 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ቡድን አለ። በዚህ ቡድን ላይ የልጅነትና የጉርምስና ጊዜያቸውን በ1990ዎቹ ያሳለፉ ወጣቶችና ጎልማሶች በዚያ ዘመን ስለተጫወቷቸው የጨዋታ ዓይነቶች፣ ስላነበቧቸው መጽሐፍት፣ ያዳምጧቸው የነበሩ ሙዚቃዎች እና ያይዋቸው ስለነበሩ ፊልሞች፣ ይመገቧቸው ስለነበሩ የምግብ ዓይነቶች፣ ስለ አካባቢያቸው፣ ስለ ትምህርታቸው ወዘተ… የቆዩ ምስሎችንና ትዝታዎቻቸውን በማጋራት አባል ከሆኑ የትውልድ አቻዎቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት ከመፍጠር ባለፈ በቡድኑ አስተባባሪዎች አማካኝነት በአካል በመገናኘት የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴዎች ላይ ይሳተፋሉ፡፡

በተመሳሳይ ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ጠቃሚ መረጃዎችን ከሚቀባበሉባቸው የቴሌግራም ቡድኖች መካከልም አንዱን እንመልከት - የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፡፡ ከ1 ሺህ 200 በላይ አባላት ያሉት ይህ ቡድን ጋዜጠኞች ለስራዎቻቸው ግብዓት የሚሆኑ ጉዳዮችን የሚጋሩበት ነው፡፡ ለአብነት ለመጥቀስ በአንድ ማህበራዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ላይ ፕሮግራም መስራት የፈለገ ጋዜጠኛ የርዕሱን ይዘት በመግለጽ በምን መንገድ ቢሰራ ይበልጥ ጠቃሚ እንደሚሆን፣ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን እንዲሁም ሙያዊ ማብራሪያ ሊሰጡ የሚችሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን አድራሻ ጠይቆ መረጃውን በቀላሉ ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥራል።

ለሃሳብ ነጻነት የተሻለ ዕድል መስጠት

ጋዜጠኝነት ግልጽነት፣ ተዓማኒነት፣ ገለልተኝነት፣ ተጠያቂነትና ቅድሚያ ለሰብዓዊነት የሚሉ መሰረታዊ የሙያ ስነ-ምግባሮች አሉት። እነዚህን ሥነ ምግባሮች ሳይሸራርፉ ፍጹም ለሙያው



9

አድረው የሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትም ይኖራሉ፡፡ መገናኛ ብዙሃን የሚመሩበት የዓላማ መርህ (ኤዲቶሪያል ፖሊሲ) ሲኖራቸው ይህም በዚያ ተቋም ውስጥ የሚከናወኑ ስራዎችን ይዘት በሙሉ ይቃኛል፡፡ እውነትንና ሙያዊ ስነ-ምግባርን መሰረት አድርገው ለመስራት የሚውተረተሩና የሚፈለገውን ውጤት ለማስገኘት የሚተጉ ጥቂቶች መሆናቸው ይስተዋላል። ብዙዎቹ ጠንካራ ጉዳዮችን ማዕከል አድርጎ መስራት አልደፈሩም። ከዚህ ይልቅ የመዝናኛ መገናኛ ብዙሃን (የሙዚቃ፣ የፊልምና የስፖርት) በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ያልጠሩና ያልተረጋገጡ መረጃዎች አብረው ቢሰራጩም

ኅብረተሰቡ በሌላኛው ጫፍ ያለውን እውነት እንዲያይ እነዚህ የዲጂታል ሚዲያዎች የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ ዲጂታል ሚዲያ መምጣት በሌላው ዘንድ ያለውን ሀሳብና መረጃ ለመረዳት እድል ፈጥሯል ማለት ይቻላል።

የትምህርት ዕድል

ባለንበት ዘመን ዕውቀትን የሚሻ ሰው ራሱን አስተምሮ ማብቃት የሚችልባቸው ሰፊ አማራጮች አሉ፡፡ እንግሊዘኛ ቋንቋ መማር የፈለገ ሰው የመናገር፣ የመስማትና የመጻፍ ችሎታውን ሊያጎለብቱ የሚችሉ የማስተማሪያ (ቱቶሪያል) ቪዲዮዎችን ዩቲዩብ ላይ ማግኘት ይችላል፡፡ እነኚህ ቪዲዮዎች ጀማሪ፣

መካከለኛና ከፍተኛ በሚሉ ደረጃዎች የሚዘጋጁ በመሆናቸው በቋንቋ እውቀቱ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ካለው አንስቶ እስከ ጥሩ ተናጋሪ ድረስ ጠቃሚ ክህሎቶችን የሚቀስሙበት ነው፡፡

በዚህ መንገድ ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ዓረብኛ፣ ራሺያኛ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ቋንቋዎችን መማር ይቻላል፡፡

ዲጂታል ሚዲያዎች ከማዝናናትና መረጃ ከመስጠት ባሻገር የዕውቀት መድረክ በመሆናቸው የስነ-ጽሁፍ፣ የጋዜጠኝነት፣ የሂሳብ፣ የትወና፣ የምግብ ማብሰል፣ የንግድ፣ የግራፊክስ፣ የስፖርት፣ የአይሲቲ፤ የውበትና የሌሎች ሙያዎች ባለቤት መሆን ለሚፈልጉ እና ሙያው ኖሯቸው ሙያቸውን ማሳደግ ለሚሹ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የትምህርት ዕድሎችን ይዘው መጥተዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዕድል ከዩቱዩብ በተጨማሪ በሌሎቹም የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ይገኛል። ለአብነት ከፌስቡክ መንደር ሁለት ማሳያዎችን እናንሳ - ‘የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግና አመጋገብ’ ቡድን እና ‘ታሪካችን’ የፌስቡክ ገጽ፡፡

የእናቶች ወግ ስለ ልጆች አስተዳደግና አመጋገብ

ከ548 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ይህ ቡድን እናቶች በልጆች አስተዳደግ ላይ የእርስ በእርስ ምክክር የሚያደርጉበት ሲሆን፤ በተለይም አዲስ እናቶች ከልጆች አመጋገብ፣ ጤናና ባህሪይ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጽሁፍና በፎቶ በመልቀቅ ልምድ ካላቸው እናቶች ምክር የሚያገኙበት ነው፡፡ ይህም እናቶች እርስ በእርስ በመደጋገፍ በአካልና በአዕምሮ ጤናማ ልጆችን እንዲያሳድጉ የመረዳጃ ድልድይ በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡

ታሪካችን

ይህ የፌስቡክ ገጽ ምንም እንኳን በተከታዮች ብዛት አነስተኛ ሊባል የሚችል ቁጥር ቢኖረውም (25 ሺህ ገደማ) የተለያዩ ታሪካዊ ሰነዶችን በማገላበጥ እንደ ልብ የማይገኙ ታሪካዊ ፎቶግራፎችን ለተከታዮቹ ያጋራል፡፡ ፎቶግራፎቹ ስለተነሱበት ጊዜና ስለሚያሳዩት ጉዳይ አጭር ሀተታ ያላቸው በመሆናቸው ታሪክን ማወቅ ለሚሹ እንደ ጥሩ አማራጭ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ ሌሎችም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በቲክቶክ፣ በቴሌግራም እንዲሁም በድረ ገጽ ጠቅላላ እውቀትን የሚያሰፉና በአንድ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ትምህርቶችን የሚሰጡ የዲጂታል ሚዲያዎች አሉ፡፡



10

ተጨማሪ ገቢ

ድረ ገጾችን ጨምሮ አብዛኞቹ ማኅበራዊ የትስስር ገጾች ከማስታወቂያ የሚገኝ እንዲሁም በመታየት (በመጎብኘት) ድግግሞሽ ተሰልቶ በዶላር የሚከፈል ክፍያ አላቸው፡፡ በዚህ ክፍያ ኑሯቸውን ያሻሻሉ እንዲሁም ወደ ባለሃብትነት ያደጉ ቀላል ቁጥር የሌላቸው ፌስቡከሮች፣ ዩቲዩበሮች እና ቲክ ቶከሮች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ዲጂታል ሚዲያ ገቢን ከማሳደግ ባሻገር ወደ እውቅና ለመውጣትም ቀላል መሰላል በመሆን ለበርካታ ሰዎች የስኬት በር ከፍቷል፡፡

የዲጂታል ሚዲያ አሉታዊ ተጽዕኖ

“ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በጎደለው አጠቃቀም የተነሳ በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት በአገራችንም ሆነ በዓለማችን እጅግ አስከፊ ግጭቶች ሲፈጠሩና ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት፣ አካል መጉደልና ንብረት መውደም ምክንያት ሲሆኑ ተመልክተናል፡፡ ኃላፊነት የጎደላቸው ዲጂታል ሚዲያዎች የግጭት መነሾ ከመሆን በመለስ ግጭት የሚያባብሱ፣ ያልተረጋገጡና የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት ቀውስ ላይ ነዳጅ ሲያርከፈክፉ መመልከት የተለመደ ሆኗል፡፡ በአገራችን በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዘር፣ ሀይማኖትና የፖለቲካ አስተሳሰብን ማዕከል ያደረጉ አስከፊ ውጤቶችን ያስከተሉ መልዕክቶች በዲጂታል ሚዲያዎች ሲተላለፉ ተስተውሏል፡፡ በጥቅሉ ኃላፊነት የጎደለው የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከትላቸው ሦስት መሰረታዊ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሐሰተኛ/የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት

በአሁኑ ወቅት መገናኛ ብዙሃን ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያወጧቸው ዘገባዎች የተሳሳቱ፣ የተዛቡ፣ ከፊል እውነት ያላቸው፣ የተጋነኑና ሐሰተኛ መረጃዎችን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ። በተለይ የሐሰት/የተዛቡ መረጃዎች ሆን ተብሎ አሊያም ተገቢውን ማጣራት ባለማድረግ ወደ ሕዝብ የሚደርሱ ሲሆኑ፤ በአብዛኛው ከእውነት በራቀ ወይንም በተጋነነ መረጃ የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሟላት ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት መረጃዎች ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋ ለመቀነስ ዲጂታል ሚዲያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ብዙኃኑ ጋር የሚደርሱ መረጃዎችን ስርጭት የሚቆጣጠርና

ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የሕግ ማዕቀፍ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየካቲት 2012 ዓ.ም የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል አዋጅ ቁጥር 1185/2012 በሚል ማፅደቁ ይታወቃል።

አዋጁ በመግቢያው “ሰብዓዊ ክብርን የሚገረስሱና ሆን ተብሎ የሚሰራጩ ሐሰተኛ ንግግሮችን በሕግ መከልከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ፤ የጥላቻ ንግግርና የሐስተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉት ግጭትና ጉዳት ለእኩልነት፣ ለሠላም፣ ለዴሞክራሲና ለሕዝቦች አንድነት ትልቅ ጠንቅ በመሆኑ፤ መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚጣሉ ገደቦች በሕግ የተደነገጉ፣ በዴሞክራሲያዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውን ዓላማ ለማስፈጸም የሚወጡና ተመጣጣኝ መሆን እንዳለባቸው በመገንዘብ” መዘጋጀቱን ያትታል፡፡

የጥላቻ ንግግርን ሲያብራራም የጥላቻ ንግግር ማለት “የሌላን ግለሰብ፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማኅበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ውጪያዊ ገጽታን መሰረት በማድረግ ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው” ካለ በኋላ የሐሰተኛ መረጃን ትርጉም ደግሞ “የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት የሆነና ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ ዕድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ ንግግር ነው” በማለት ይበይነዋል፡፡ የአዋጁ አፈጻጸም ላይ በተለይ ከዜጎች የሃሳብ ነጻነት እቀባ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎች ቢኖሩም አዋጁ መኖሩ በራሱ በሕግ አግባብ የሚሰሩትን ለመጠበቅ ሕገወጦችንም በሕግ ለመጠይቅ እንደሚያግዝ የታመነ ነው፡፡

ስም ማጥፋት (Defamation)

“ተዋናይ እከሌ የአርቲስት እከሊትን ጉድ ዘረገፈው”፣ “ድምጻዊት እከሊት የድምጻዊ እከሌን ቅሌት አደባባይ አሰጣችው”፣ “መምህር እከሌ ስለእነከሌ ግፍ ዝምታውን ሰበረ”፣ “ፖለቲከኛ እከሌ በእከሌ ላይ ዘመተ” ወይም “በድብቅ ተቀርጾ/አፈትልኮ የወጣ” የሚል ርዕስ ያላቸው ሰዎችን ለማየት የሚያነሳሱ የስም ማጥፋት ቪዲዮዎች ዲጂታል ሚዲያውን በተለይ



11

ዩቲዩብን በእጅጉ አጨናንቀውታል፡፡ በዚህም ከግለሰቦች እስከ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ከታዋቂ ሰዎች እስከ ሃይማኖት አባቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች እስከ ከፍተኛ የአገር መሪዎች በሐሰተኛ መረጃዎች ከፍ ዝቅ ይደረጋሉ፣ ይብጠለጠላሉ፡ ፡ ስም ማጥፋት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑ ተረስቶ ሰዎችን በማታለል በሚገኝ እይታ ጥሩ ገንዘብ የሚሰራበት ሁነኛ ስልት ተደርጎ ከመወሰዱም ባሻገር እንደ አገር አለመረጋጋት ለመፍጠር ጥቅም ላይ ሲውል እንመለከታለን፡፡

ለአብነት በግንቦት 2013 ዓ.ም መቀመጫቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ዲጂታል ሚዲያዎች “ሾልኮ የወጣ የጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ አህመድ ንግግር” በሚል አንድ የድምጽ ቅጂ አሰራጭተው ነበር፡፡ ድምጹ ጠቅላይ ሚንስትሩ በዚያን ሰሞን በተካሄደ የብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ላይ የመዝጊያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት በድብቅ የተቀዳ በማስመሰል በዩቲዩብ ቻናል የተሰራጨ ነበር፡፡ ነገር ግን ድምጹ የሐሰት የሆነ፣ ከስብሰባው የተወሰደ አንድም ቃል የሌለው፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንት በተለያዩ ጊዜያት ካደረጓቸው ንግግሮች እየተቀነጨቡ የተወሰዱ ቃላትን በመገጣጠም የተቀናበረ ነበር። ይህ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያነገበ የስም ማጥፋት ብልጽግና ፓርቲና የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ዘገባው የሀሰተኛና የተዛባ መረጃ መሆኑን በመግለጽ መግለጫ እስከማስወጣት ያደረሰ እንደነበር ማስተዋል ይቻላል። ይህ በራሱ ዲጂታል ሚዲያው ስም በማጉደፍ ቀውሶችን የመፍጠር ቀላል የማይባል አቅም እንዳለው ማሳያ ይሆናል።

የጊዜ ብክነትና ሱሰኝነት

ኢንተርኔት የራቀውን የማቅረቡን ያህል የቀረበውን አራርቆ በቤተሰብና በጓደኛሞች መካከል የነበረውን ግንኙነት እያላላው መጥቷል፡፡ የአብዛኞች ሰዎች ግንኙነት ተሰብስቦ ከመጫወት ይልቅ ተሰብስቦ ስልክ ላይ ወደማቀርቀር እየተለወጠ በመምጣቱ ለሕይወት የሚበጁ ቁምነገሮች ላይ ሃሳብ መለዋወጥ እያዳገተ ነው፡፡ በዚህም ፍቅረኛሞች፣ ባለትዳሮች፣ የስራ ባልደረቦች፣ ለስራ የተገናኙ ሰዎች ወዘተ… ሞባይል ስልክ አስቀምጦ በሙሉ ትኩረት መነጋገር አቅቷቸው ለግጭት ከመዳረጋቸውም በላይ ብዙ ቁምነገር ሊሰራበት የሚችል ውድ ጊዜ በእንቶፈንቶ የማኅበራዊ

የትስስር ገጾች ወሬና በዲጂታል ሚዲያዎች መረጃ ያልፋል፡፡

በተለይ በማኅበራዊ ድረገጾች የሚተላለፉ መረጃዎች ሰዎችን በማስገረም፣ በማስደንገጥ፣ ግራ በማጋባትና በማዝናናት ልዩ ልዩ ስልቶች ተከሽነው የሚቀርቡ በመሆናቸው ሰዎች ሳያስቡት እየደጋገሙ እንዲጎበኟቸው በማድረግ ጊዜ፣ ገንዘብና ትኩረትን ያስገብራሉ፡፡ ከልክ በላይ ዲጂታል ሚዲያዎችን መጠቀም ሕይወትን ጣዕም አልባ በማድረግ ደስታ እንደሚያሳጣ እንዲሁም ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዘው በሚለቀቁ ተግተልታይ፣ አሳዛኝና አስጨናቂ መረጃዎች በርካታ ሰዎች ለአዕምሮ መረበሽ እንደሚዳረጉ ዓለም አቀፍ ጥናቶች ያመላክታሉ፡ ፡

ዲጂታል ሚዲያዎችን አብዝቶ የሚጠቀም ሰው ደጋግሞ ሊመለከታቸው ከሚችሉ ጉዳዮች መካከል የጦርነት፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የሽብር፣ የኑሮ ውድነት፣ የተቃውሞ፣ የስራ አጥነትና መሰል ዜናዎች እንዲሁም ታሪክን፣ ማንነትንና የፖለቲካ አቋምን መሰረት ያደረጉ ትንታኔዎች በስፋት የሚገኙ ሲሆን፤ እነዚህም ከድግግሞሽ ብዛት አዕምሮን ወደ ማስጨነቅ የመውሰድ አቅም አላቸው፡፡ በአጠቃላይ ብልሃት የጎደለው የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀም ከስራና ከትምህርት ከማናጠብ አንስቶ ዓለምን በስክሪን ውስጥ ባይዋት መልክ እስከመፈረጅ የሚደርስ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሲጠቃለል

ዲጂታል ሚዲያን ኃላፊነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አግባብ መጠቀም መረጃን በፍጥነት ከማድረስ በተጓዳኝ ገንቢ ሃሳቦችን ለመለዋወጥም ይጠቅማል፡፡ ኅብረተሰቡም የሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን አስከፊነት በመገንዘብ አጠራጣሪ መረጃዎችን ተዓማኒ ከሆኑ (በአንጻራዊነት) የሚዲያ ተቋማት የማረጋገጥ ባሕሉን ሊያሳድግ ይገባል፡፡ እውነትን ማጣራት ላይ አተኩረው የሚሰሩ ተቋማትን በማብዛት በቁጥርም፣ በሰው ኃይልም፣ በቴክኖሎጂም እንዲጠናከሩ ማድረግ መልካም ይሆናል፡፡



12

ሕገ መንግሥት፤ ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት

ፖለቲካ



13

ዶክተር ኃይለየሱስ ታዬ

መግቢያ

ሕገ-መንግሥት፤ ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት እጅግ የተቆራኙ እና አንዱን ከአንዱ ለይቶ ማየት የማይቻል ነው። ለዚህም ነው የዚህ ማጠንጠኛ መነሻ ሃሳብ ተደርጎ የተወሰደው። የፌዴራላዊ ሥርዓት ዋነኛው መገለጫ የራስ እና የጋራ አስተዳዳር (self rule and shared rule) ማዕከል ያደረገ የሥልጣን ክፍፍል ሲሆን፤ ለዚህም ሕገ መንግሥትን መሰረት ያደርጋል። ይህ የሥልጣን ክፍፍል የሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን ተከትሎ ተግባራዊ የሚደረግ ነው። በዚህም የፌዴራል ሥርዓቱ አባል መንግሥታት ለራሳቸው በተናጥል፣ የተሰጣቸውን በጣምራ እና በጋራ የተሰጣቸውን፤ እንዲሁም ቀሪ ሥልጣን የተሰጠው አካል በሕግ የተሰጣቸውን የሥልጣን ገደብ ተከትለው ሕግ እና ሕግን መሰረት አድርገው የአንዱን ሥልጣን ሌላው በማክበር በቅንጅት እና በመተባባር ለመንቀሳቀስ እና የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እና ነፃነቶች በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታት ለማክበር እና ለማስከበር፤ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው ፌዴራላዊ የአስተዳደር ሥርዓት እየገነቡ ለመሄድ ሕገ መንግሥት

ሕገ መንግሥት፤ ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት



14

እና ሕገ መንግሥታዊነት በፌዴራል ሥርዓት የተለየ ባህሪ አላቸው። ስለዚህ ሕገ መንግሥት፤ የፌዴራላዊ ሥርዓት እና ሕገ መንግሥታዊነት ይህን ገጽታ በሚያንጸባርቅ መልኩ ተዳሷል።

ፌዴራሊዝም እንደ ፍልስፍና ፌዴራላዊ ሥርዓት ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግሥታዊነት ይዘትና ልዩ ትስስር ከማንሳታችን በፊት ስለ ፌዴራሊዝም የተወሰኑ ሃሳቦች ማንሳት ጠቃሚ ይሆናል።

የፌዴራሊዝም ፍልስፍና አንድ ማኅበረሰብ እንደ አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በጋራ ለመቀጠል ሲወስን የራሱ እና የጋራ ጉዳዮቹን አጣምሮ ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ለማስተናገድ የሚያስችል ሥርዓት መፍጠር ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህን አስተሳሰብ እና አስተሳሰቡ የሚገለጽባቸው እሴቶችን የመያዝ፣ የመደገፍ እንዲሁም በተግባር የመግለፅ ጉዳይን ያካትታል።

የፌዴራሊዝም ፍልስፍና ትንሽ አገር ከመሆን እና የተማከለ ትልቅ አገር ከመሆን ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቀነስ የሁለቱንም ጥንካሬዎች ለማስቀጠል የሚያስብ ፍልስፍና ነው። የፌዴራሊዝም ፍልስፍና ብዝሃነትን ያቀፈ የአንድነት ፍልስፍና ነው። ከመነሻው ፌዴራሊዝም የሚታሰበው የአብሮነት እና የአንድነት እሳቤ ሲኖር ነው። ይህ ሁሉንም ያካተተ፣ የብዝሃነት እና አንድነት ሚዛን ጠብቆ የሚተገበር ነው። በዚህ አንዱ አንዱን ሳይውጥ አብረው ተጣምረው የሚቀጥሉበት የአንድነት ፍልስፍና ነው።

ይህን ፍልስፍና የሚጋሩ የተለያዩ የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት አደረጃጀቶች አሉ። በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የፌዴሬሽን ቅርጽ ያለው የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት ነው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ 2022 ድረስ የፌዴራል ሥርዓት የሚከተሉ 28 አገሮች አሉ። በነዚህ አገሮች ከዓለም ሕዝብ መካከል 41 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆነው ይኖርባቸዋል። የዓለምን 44 ነጥብ 4 በመቶ የቆዳ ስፋት የሚሸፍኑ እና 48 ነጥብ 5 በመቶ የዓለም የአገር ውስጥ ምርት (GDP) የያዙ መሆናቸውን መረጃዎች ያረጋግጣሉ። ከፌዴሬሽን ሌላ የፌዴራሊዝምን እሳቤ የሚጋሩ ሌሎች የፌዴራል ፖለቲካ ሥርዓት አደረጃጀቶች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

የፌዴራሊዝም አጥኝዎች ኮንፌዴሬሽን፣ ዩኒየን፣ ሊግ፣ አሶሸትድስቴትስ፣ ኮንዶሚኒየም፣ ያልተማከለ አሃዳዊ ሥርዓት እሳቤውን የሚጋሩ አደረጃጀቶች ተደርገው ይወስዳሉ።

ሕገ መንግሥት እና ፌዴራላዊ ሥርዓት

የፌዴራላዊ ሥርዓት ዋነኛ መገለጫ ባህሪው ቢያንስ የሁለት መንግሥታት መኖር ነው። በእነዚህ መንግሥታት መካከል ሕገመንግሥታዊ የሆነ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሥልጣን ወሰን፣ የመንግሥታቱ አደረጃጀት፣ የመንግሥታቱ እርስ በእርስ እና ከማኅበረሰቡ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት የሚወስን ሕገ መንግሥት መኖር የግድ ይላል። የሕገ መንግሥቱም መነሻ የሕዝቦች የሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤትነት ነው። እነዚህ የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት የሆኑ ሕዝቦች በራስ አስተዳደራቸው እና አገራዊ በሆነ የጋራ አስተዳደራቸው የከባቢያዊ ፍላጎት እና አቅም ከአገራዊ ፍላጎትና አቅም ዴሞክራያሲያዊ በሆነ አግባብ አጣምረው የሚያስተዳድሩበት ሥርዓት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት የሚያደረጁት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነው። ይህ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት የፌዴራላዊ ሥርዓት ዋና ምሰሶ ሆኖ የሚያገለግል ነው። የሕገ መንግሥቱ ይዘት፣ ሕገ መንግሥቱ የተዘጋጀበት እና የፀደቀበት ሂደት እንዲሁም የሚሻሻልበት አግባብ ከፌዴራል ሥርዓት እና ከሕገ መንግሥት ጋር ተያይዘው የሚታዩ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው።

በፌዴራላዊ ሥርዓት ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ያስቀመጠው ድንጋጌ በራሱ በቂ አይደለም። ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሂደት የፌዴራል ሥርዓቱ የሚከተለውን አቅጣጫ የሚያመላክት ዋና ወሳኝ ጉዳዩ በመሆኑ ነው። የፌዴራል ሥርዓቱ በርግጥ “የፌዴራል ሥርዓት ነው ወይስ የፌዴራል ሥርዓት በቅርጽ እንጅ በይዘት ግን ይበልጥ የተማከለ ወይንም ይበልጥ ያልተማከለ” የሚለውን ለማየት ፌዴራላዊ ሂደቱን መመልከት ተገቢ ነው።

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሂደቱ አካታች፣ ሁሉም አካላት በተለይም ዝቅተኛ ቁጥር ያላቸው ማኅበረሰቦች ድምጽ የሚሰማበትና የሚሳተፉበት መሆን ይኖርበታል። ይህ በተለይ በባለ ብዙ ብሄር፣ ባህል፣ ቋንቋ ወዘተ…. በሆኑ ፌዴሬሽኖች ውስጥ ወሳኝ ጉዳይ ይሆናል። የአመለካከት፣ የአስተሳሰብም ሆነ የባህል፣ የቋንቋ፣ የብሄር ብዝሃነት በማካተት ሁሉንም የፌዴራል ስምምነቱ አካል ማድረግ ጠቃሚ

ነው።

የፌዴራል ሕገ-መንግሥታዊ አወቃቀር ፍልስፍና በፌዴራላዊ ሕገ መንግሥት የተሳሰሩ አባል መንግሥታቱ “ትስስራቸውን የሚያዩት እንደ ኮንትራት፣ ኮቪናንት ወይም ኮሚፓክት ነው ወይ?” የሚለው የራሱ አንድምታ ይኖረዋል። ኮንትራት ብዙ ጊዜ የግል ባህሪ (private) ይዘት ሲኖረው ኮቪናንት እና ኮምፓክት ግን የሕዝብ (Public) ባህሪ ያላቸው ናቸው። በዚህም የተስስሩ ዓይነት እና አረዳድም የፌዴሬሽኑ አካላት ትስስራቸውን የሚያዩበት አንድምታ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ያሳድራል። ለአብነት ኮቪናንት ከሌሎች የሚለየው የሞራላዊ ትስስሩ ገፅታ ከሕጋዊ ትስስሩ ገፅታ ቅድሚያ የሚያዝ ነው።

አንድ ማኅበረሰብ እንደ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በጋራ ለመቀጠል የወሰነባቸው አግባቦች በሁሉም ዘንድ እንዲከበሩ በሕገ-መንግሥት ቀርጾ በውይይት ሂደት ወቅት ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ ነው። ሆኖም በሕገ- መንግሥቱ ስምምነት የተደረሰባቸውን የሥልጣን፣ የሃብት፣ የወጭ እና ገቢ፣ የተናተጠል እና የጋራ ሥልጣን ክፍፍሎችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚኖሩ ግንኙነቶች ዙሪያ ተገቢውን አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ሊነሱ የሚችሉ አለመግባባቶችን የሚፈቱበት ሂደት፣ የሕገ-መንግሥቱ የበላይነት ጉዳይ ወዘተ በሕገ-መንግሥቱ የሚመላከቱ ይሆናሉ። በርግጥ አፈፃፀማቸው የፌዴራል ሥርዓቱ ሲፈጠር እና እያደገ በሚሄድ የጋራ መተማመን፣ የፌዴራላዊ አስተሳሰብ እና እሴት መዳበር፣ በሥርዓቱ ሕዝቡ እኩል የመጠቀም ዕድል እያገኘ ይሄዳል። በተለይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ሥርዓቱን በሚያጠናክር መልኩ በየወቅቱ በውይይትና በምክክር እየፈቱ መሄድ አስፈላጊ ነው። የፖለቲካ ልሂቃን የፌዴራል ሥርዓቱ ድንጋጌዎች ለመጠበቅ ባላቸው ፍላጎት እና ፍላጎቱ እንዲያድርባቸው በሚፈጠሩ እድሎች እና ገፊ ምክንያቶች ላይ የሚወሰን ነው።

ፌዴራሊዝም ከሕገ መንግሥታዊ የመንግሥት አወቃቀር በዘለለ የፖለቲካ ኑሮ ዘይቤ ከሆነ ሕግና የሕግ የበላይነት የዕለት ከዕለት ኑሮ አካል ማድረግ ያስችላል። ፌዴራላዊ የፖለቲካ የኑሮ ዘይቤ የሁሉንም መብት ማክበር እና መጠበቅ የሚጠይቅ የኑሮ ዘይቤ ነው። የሕግ የበላይነት አንድ መገለጫ ነጻነት የመጠበቅ እና የማጎናፀፍ ሲሆን፤ በፌዴራላዊ አወቃቀር በጋራ ለመኖር የመረጡ ሕዝቦች ነፃነታቸው ተጠብቆ በጋራ ለመኖር ስለወሰኑ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋግጡበት ዕድል ሰፊ ነው።



15

ሕገ መንግሥታዊነት እና የፌዴራል ሥርዓት

ሕገ መንግሥታዊነት በአጭሩ ሲብራራ ለሕገ መንግሥት ያለ ታማኝነት እና እምነት ነው። በዚህ መሰረት ሕገ መንግሥታዊነት የመንግሥት አካላትና ባለሥልጣናት በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ መሰረታዊ መርሆዎችን እና እሴቶችን በሙሉ ልብ በመቀበል፣ በዕለት ተዕለት ስራቸው ተግባራዊ የሚያደርጉትና የሚገለገሉበት መሆኑን የሚያመለክት ፅንሰ ሀሳብ ነው። እንደዚሁም ሕገመንግሥቱን ለማክበርም ሆነ ለማስከበር በእምነትና በቁርጠኝነት የሚሰሩ መሆናቸውን እንዲሁ። በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ በተሰጣቸው ሥልጣን ልክ ተገድበው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ይገልፃል። ሕገ መንግሥታዊነት በአንዲት አገር በሕገ መንግሥትነት የታወጀ ሰነድ ከመኖሩ ባሻገር መንግሥት፣ የተለያዩ ማህበሮችና የፖለቲካ ድርጅቶች እና ሕብረተሰቡ የሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎችን የማክበርና ተገዥ ሆነው መገኘትን ያመለክታል። ሕገ መንግሥታዊነት ሕገ መንግሥት መኖር ብቻ ሳይሆን በተግባር የመዋልን ሁኔታ ያሳያል።

ሕገ መንግሥታዊነት መነሻውም መድረሻውም ሕገ መንግሥቱ ነው። የሕገ መንግሥታዊ ፅንሰ ሀሳብም ከሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ጋር አብሮ የዳበረ ነው። ሕገ መንግሥት ያለ ሕገ መንግሥታዊነት በሰነድ ደረጃ ሊኖር ቢችልም፤ ሕገ መንግሥታዊነት ግን ያለ ሕገ መንግሥት የሚታሰብ አይሆንም። በጥቅሉ ሕገ መንግሥታዊነት ሕገ መንግሥቱን ተግባራዊ ማድረግ ነው።

ከዚህ መሰረታዊ ሀሳብም በመነሳት የሕገ መንግሥታዊነትን አስፈላጊነት ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች በማንሳት መመልከት ይቻላል።

በሕገ መንግሥታዊነት ሕዝቡ በሕገ መንግሥቱ ላይ ያለውን እምነት (trust) ያዳብራል

እምነት ሲባል ሰዎች በሕገ መንግሥቱ ተማምነው እና ሕገ መንግሥቱን ዋስትና አድርገው በሥርዓቱ ውስጥ የሚኖሩበት ተስፋ ነው። ሕገ መንግሥቱንም የሚያከብሩት “ሌሎችም እንደ እኔ ሕገ መንግሥቱን ያከብሩታል፣ አናከብርም ቢሉ እንኳን መንግሥት ይሄን እምነቴን ያስከብርልኛል ብለው ስለሚያምኑ ነው። በሚታወቅ ሕግና ሥርዓት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ እንደማንኛውም ዜጋ ነጻነቴና መብቴ ይከበርልኛል። በሰላም አብሮ ለመኖር ያስችለኛል። እኩል የመልማት ዕድል ይፈጥርልኛል። መንግሥትን ተጠያቂ ማድረግ ያስችለኛል። ለአገሬ የበኩሌን አስተዋጽኦ እንዳደርግ ዕድል ይፈጥርልኛል።” በሚል እምነት ነው። ከዚህም የተነሳ በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡት ሕጎች ተግባራዊነት ላይ ያላቸውን አመኔታ በሕገ መንግሥቱ ላይ ለሚኖራቸው አመለካከት ገላጭ ነው። ሕገ መንግሥታዊነት

እምነት ሲባል ሰዎች በሕገ መንግሥቱ ተማምነው እና ሕገ መንግሥቱን ዋስትና አድርገው በሥርዓቱ ውስጥ የሚኖሩበት ተስፋ ነው። ሕገ መንግሥቱንም የሚያከብሩት ሌሎችም እንደ እኔ ሕገ መንግሥቱን ያከብሩታል፣ አናከብርም ቢሉ እንኳን መንግሥት ይሄን እምነቴን ያስከብርልኛል ብለው ስለሚያምኑ ነው።



16

መስፈን ዜጎች በአገራቸው ሕገ መንግሥት ላይ አመኔታ እንዲኖራቸው ከማድረጉም በላይ የሕገ መንግሥቱ ቅቡልነት እያደገ እንዲሄድ ያደርጋል።

የመንግሥትን ሥልጣን መገደብ (Limiting government power)

ሌላው የሕገ መንግሥታዊነት ዋነኛ ግብ እና ዓላማ፤ መንግሥት በሕግ በተሰጠው ማዕቀፍ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ እና ከተሰጠው የሥልጣን ገደብ ውጭ ዝንፍ እንዳይል የመገደቢያ መሳሪያ ሆኖ ማገልገሉ ነው። ይህም የሉዓላዊነት ሥልጣን ባለቤት የሆነው ሕዝብ የጋራ ጉዳዮቹን ለማስፈጸም አስፈላጊ የሆኑ ስልጣኖችን ብቻ በሕገ መንግሥት መሰረት ለመንግሥት አሳልፎ የሚሰጥበት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት የተሰጡትን ስልጣኖች ብቻ ሕገ መንግሥቱን መሰረት አድርጎ እንዲተገብር የመገደብ አስፈላጊነት የሚያሳይ እሳቤ ነው። በፌዴራል ሥርዓት ቢያንስ ሁለት መንግሥታት ስለሚኖሩ እያንዳንዳቸው በሕገመንግሥታዊው የሥልጣን ክፍፍሉ በተሰጣቸው ሥልጣን እና ኃላፊነት እንዲገደብ ያስችላል። በተለይ በሥርዓቱ ውሳኔ የሚሰጥባቸው በርካታ የሥልጣን ማዕከሎች ስላሉ በየደረጃው የመንግሥት ሥልጣን የሚገደብበት ሁኔታ መፍጠር የሚያስችልም ነው።

የዴሞክራሲ ሥርዓትን ማጎልበት (Strengthning of the democratic system)

የዴሞክራሲ ሥርዓት መሰረቱ የሕዝብ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭነት ነው። በዚህ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕገ መንግሥት እና እርሱ ባስቀመጠው አግባብ በሕዝቡ ይሁንታ አግኝቶ በየጊዜው ለሚመረጥ አስተዳደር ሥልጣን ይሰጣሉ። በመሰረቱ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ ተወስነው በተሰጡት ሥልጣን ልክ እየተንቀሳቀሰ ለማኅበረሰቡ የገባውን ቃል ይፈጽማል። መንግሥት መልካም ሲፈጽም የሚበረታታበት ሳይፈጽም ሲቀር ተጠያቂ የሚደረግበት ሥርዓት ለማዳበርም መሰረቱ ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት ነው። ስለዚህ ያለ ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግስታዊነት የዴሞክራሲያዊ ሂደትን መለማመድም ሆነ ማጎልበት የሚታሰብ አይሆንም። በመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥት ዴሞክራሲን ሕጋዊ ቅርጽ የሚያስይዝ፣ ሂደቱን የሚወስን እና የሥርዓቱ ግንባታ ዋናው መሰረት ነው። ሕገ መንግሥታዊነት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በሕገመንግሥቱ የተቀመጡ ዓላማዎች፣ መርሆዎች፣ እሴቶች፣ መብትና ነጻነቶች፣ አሰራር ሥርዓቶች፣ አደረጃጀቶች እና ተቋማት በተግባር የሚገለጹበት ሂደት ነው።

ለአገር ሰላም፣ ለሕግ የበላይነት እውን መሆን፣ እና ለመብቶች መከበር

የሰው ልጆች በጋራ መኖር የግድ የሚላቸው ፍጡራን ናቸው። ማንኛውም ሕግ አስፈላጊነቱ የሰው ልጆች ሕግ አልባ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊኖራቸው ከሚችለው ነጻነት እና መብት በአንጻራዊ መልኩ የተሻለ ነጻነት እና መብት ማስከበር መሆኑን ከአዎንታዊ የሕግ ጽንሰ ሃሳብ መረዳት ይቻላል። የሕግ የበላይነት ሕግ ማክበርን እና ሕግ ማሻሻልን ጨምሮ ማንኛውንም ተግባር ሕግን ተከትሎ ማከናወን የሚጠይቅ ነው።

ሕገመንግሥት የሕዝቦች ሉዓላዊነት መገለጫ የሆነ የበላይ ሕግ ነው። ስለሆነም እንደ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በሰላም ለመኖር እና ለመብቶች እና ነጻነቶች መከበር አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ባልተከበረበት እና ሕገ መንግሥታዊነት ተግባራዊ ባለሆነበት ሁኔታ ስለሰላም፤ የሕግ የበላይነት እና ስለ መብቶች መከበር ማሰብ አዳጋች ነው። ስለሆነም ሁሉም ዜጎች፣ የመንግሥት አካላት እና ተቋማት የሕዝቦች ሉዓላዊነት መገለጫና ከሁሉም ሕጎች የበላይ የሆነውን ሕገ መንግሥት እና በሕገመመንግሥቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ መርሆች መብቶችና ነጻነቶች ማክበርና ማስከበር ለአገር ሰላም፣ ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ እና ለመብቶች መከበር አስፈላጊ መሆናቸውን መረዳት ይገባል። ሁሉንም ጉዳይ ሕግና ሕግን ብቻ መሰረት አድርጎ በመንቀሳቀስ ለመፈጸም እና ለመለወጥ ቢፈለግ እንኳ “በሕግ በተቀመጠው አግባብ መለወጥ ይቻላል” የሚል እምነት መያዝ ይጠይቃል። ለሰላም፣ የሕግ የበላይነት እና ለመብቶች መከበር የሕገ መንግሥታዊነት መዳበር አንዱ አስፈላጊ መሰረት ተደርጎ ይወሰዳል።

በፌዴራል ሥርዓት በሁለቱ መንግሥታት በሚኖር ግንኙነት፣ መንግሥታት ከማኅበረሰቡ ጋር በሚያደርጉት ግንኙነት፣ ሕገመንግሥታዊ ድንጋጌዎችን በሌሎች ሕጎችና ፖሊሲዎች ተደግፈው ወደ ተግባር ለማዋል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ የሕግ የበላይነት መጠበቅና ማክበር አንዱ መሰረታዊ የሕገ መንግሥታዊነት መገለጫ ነው።

ሕገ መንግሥት፣ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና ሕገመንግሥታዊነት የማይነጣጠሉ ናቸው። በዚህም ፌዴራላዊ ሥርዓት ያለ ሕገ መንግሥት አይታሰብም፤ ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ሆነ ሕገመንግሥቱ ያለ ሕገ መንግሥታዊነት ፋይዳ ቢስ የሚሆኑበት ሁኔታ ሰፊ ነው።

ሆኖም ሕገ መንግሥት በራሱ ብቻውን

ፌዴሬሽኖችን ሊሰራ ወይም ሊያፈርስ አይችልም። የፌዴሬሽኖች ቀጣይነት በፌዴራል ሥርዓቱ ሂደት ላይ በሚኖር አስተሳሰብና በአጠቃላይ በፖለቲካ ባህል ላይ የተጣበቀ ነው። ምንም ቢሆን ሕገ መንግሥት የማይንቀሳቀስ ድርቅ ያለ ሊሆን አይቻልም። በመሰረቱ መደበኛ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ባይኖሩም እንኳ በሕገ መንግሥት ትርጉም፣ በፖለቲካው በኩል በሚኖሩ መግባባቶች ሕገ መንግሥቱ በሂደት በተግባር እየተለወጠ ሊሄድ ይችላል። ሕገ መንግሥቱ የሚያቋቁማቸው መርሆዎች፣ ተቋማትና ሂደቶች የፌዴራል ሥርዓቱ ላይ የራሳቸው ተጽዕኖ እየፈጠሩ መሄዳቸውም የማይቀር ነው።

ማጠቃለያ

በዚህ አጭር ጽሑፍ ፌዴራላዊ ሥርዓት ከሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊነት ጋር ያለውን ትስስር ለማየት ተችሏል። ፌዴራላዊ ሥርዓት በባህሪው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነው። ሥርዓቱ ደግሞ ያለ ሕገ መንግሥታዊነት ቀጣይነቱና የተረጋጋ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። ለዚህ ምክንያቱ ሕገ መንግሥትን መሰረት አድርገው የተፈጠሩ ሁለት መንግሥታት በሕገመንግሥቱ የተሰጣቸውን የሥልጣን ገደብ አክብረው፤ የጋራ ጉዳዮቻቸውን በትብብርና በተቀናጀ መልኩ መተግበር ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ ሕገመንግሥቱን ወደ መጣስ ስለሚያመሩ ፌዴራል ሥርዓቱ ሊቀጥል የማይችልበት እድል ሰፊ ነው። በፌዴራል ሥርዓት የሕገ መንግሥታዊነት አለመረጋገጥ በሌሎች ስርዓቶች ከሚያስከትለው የሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች አለመከበር፣ የግልጽነትና ተጠያቂነት መጓደል፣ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓት ወደ አምባገነናዊ ሥርዓት መጓዝ፣ የፍትሕ እና እኩልነት መዛባት በተጨማሪ የሥርዓት መፍረስ ያስከትላል። ሕገ መንግሥታዊነት ካልተከበረ በፌዴራል ሥርዓት የሚተዳደሩ መንግሥታት አብረው የመቀጠል እድላቸው አናሳ ነው። ሕገመንግሥት፤ ፌዴራላዊ ሥርዓት እና ሕገ መንግሥታዊነት የማይነጣጠሉ እና ፌዴራላዊ ሥርዓት ያለ ሕገ መንግሥት የማይታሰብ ሲሆን፤ ፌዴራላዊ ሥርዓቱም ሆነ ሕገ መንግሥቱ ያለ ሕገ መንግሥታዊነት ፋይዳ ቢስ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሰፋ ያለ ነው።

በመሆኑም ሕገ መንግሥቱን ማክበር እና ማስከበር የሚችል ሕገ መንግሥታዊነትን የተላበሰ ማኅበረሰብ መገንባት የፌዴራል ሥርዓት ለሚከተሉ አገሮች ለነገ የማይባል ቁልፍ ተግባር ነው። ለተግባራዊነቱም ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ የድርሻችንን መወጣት ይጠበቅብናል።



17



18

መገናኛ ብዙሃን ለአገር ግንባታ

ፖለቲካ



19

“ብሔራዊ ጥቅም ምንድን ነው?” ጥያቄው ከመድረክ ሲወረወር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጥነው የስራ ባልደረቦች ተያየን። የጥያቄው አውድ ከውጭ ግንኙነት አኳያ እንዳልተነሳ ግልጽ ነው። ከጥያቄው ባሻገር እያንዳንዱ ሰው “የአንድን አገር ብሔራዊ ጥቅም” ለማስጠበቅ ከየት ይጀምራል? የሚለውን ሀሳብ እንድንመረምር ይጋብዛል።

ከአገር ውስጥ አውድ አኳያ ስለ ብሔራዊ ጥቅም ስናወራ ኃላፊነቱ ማን ላይ ይወድቃል? የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ ጉዳይ ይሆናል። ብሔራዊ ጥቅም ‘national interest’ የሚሉ የእንግሊዝኛ ቃላትን ወክለው የቆሙ ናቸው። ቃሉን በመተርጎም ደረጃ የአንድን አገር ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እሳቤዎችና እሴቶች ግምት ውስጥ የሚከት፤ ጠንከር ያለ ሀሳብ የያዘም ነው።

ሰዎች ስለ ብሔራዊ ጥቅም ሲጠየቁ ቀድሞ ወደ አዕምሯቸው የሚመጣው ከደህንነትና ከሉዓላዊነት፣ ከአገሮች ጋር ባሉ ግንኙነቶች ውስጥ የአገራቸውን ተጠቃሚነት ታሳቢ የሚያደርጉ ጉዳዮች ይሆናል። የአንድ አገር የውጭ ግንኙነት ቅኝቱ ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው። ከሌሎች አገሮች ጋር የሚኖር መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና የተለያዩ ስምምነቶች መነሻቸው ብሔራዊ ጥቅም

መገናኛ ብዙሃን ለአገር ግንባታ

ሰላምነህ እውነቱ



20

መሆኑ እሙን ነው። ሳሙኤል ሀንቲንግተን (Samuel Huntington) “ብሔራዊ ጥቅም ሁሉንም ሰው ወይም ብዙ ዜጎችን የሚመለከት የሕዝብ ጥቅም ነው። ለወሳኝ አገራዊ ጥቅም ደማቸውን ለማፍሰስ እና ሐብታቸውን ለመከስከስ ፈቃደኞች የሆኑበት ጥቅም ነው። ብሔራዊ ጥቅም አብዛኛውን ጊዜ ደህንነትን ከንብረት ጋር በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሞራል እና የስነ-ምግባር ጉዳዮችን ያጣምራል” በማለት ይገልጸዋል። ይህን ስናስተውል ብሔራዊ ጥቅምን ለማብራራት እጅግ ውስብስብ ነጥቦችን ማንሳት ሊኖርብን ይችላል። ስለዚህ ከላይ እንደዋዛ የተሰነዘረው ጥያቄ ሰፊ የሀሳብ ባሕር ውስጥ የሚከት መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።

የአንድን አገር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና የደህንነት ጥያቄ ለመመለስ ከሚደረጉት ተግባራት አኳያ ሲታይ ብሔራዊ ጥቅም መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ጥያቄውን በቀጥታ ለመመለስ መሞከር ቀላል እንዳልሆነ ይገነዘባል።

ከመድረክ ስለተሰነዘረ ብቻ “ብሔራዊ ጥቅም ማለት….” በሚል ወደ ዝርዝር ጉዳይ ለመግባት መሞከር የመላሹ ስብዕና፣ አገራዊ ምልከታ፣ ፖለቲካዊ አቋምና ሌሎች ጉዳዮችን ምላሹን ሊወስኑት ይችላሉ። በአንድ አገር ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ዜጎች አስተዋጽኦ አላቸው ወይ? የሚል ሌላ ጥያቄ ይነሳል። በማንኛውም የሕይወት መስመር ውስጥ ዜጎች የሚያከናውኑት ተግባር ለብሔራዊ ጥቅማቸው የጀርባ እጥንት መሆኑን መረዳት ዋነኛ ጉዳይ ነው። ዜጎች የሚያከናውኑት ተግባር የአገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ ፖለቲካዊ መረጋጋት ለመፍጠር ማኅበራዊ ንቃተ ህሊናን የሚያልቅ ነው። ይህ በራሱ ከሌላው አገር ጋር በሚደረግ ግንኙነት ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚያስችል ትልቅ ድርሻ አለው። አንድን አገር በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን ተሰሚነትና ተጽዕኖን በማየት ጥንካሬውን መግለጽ እንደሚቻለው ሁሉ፤ በአገር ውስጥ ያለውን የዜጎች ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ እንቅስቃሴ በመመልከትም

አዝማሚያውን ማወቅ ይቻላል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ስለ ብሔራዊ ጥቅም የሀንስ ሞገርታውን ብያኔ በመጥቀሰ “የአንድ አገር የውጭ ፖሊሲ የሚበየነው ከሕዝብ ጥቅም አኳያ ነው። ብሔራዊ ጥቅም የአንድን አገር የውጭ ፖሊሲ ይቀርጻል። ከግለሰብ እስከ ዓለም አቀፍ ደረጃ በተዋረድ ሊሄድ ይችላል” በሚል አስቀምጠውታል።

በዚህ ዘመን የአንድ አገር ጥንካሬ መለኪያው በውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት በዜጎች ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖና ውጤት ነው። የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ መዋቅር፣ ፖለቲካዊ መረጋጋትና ሠላም ከፊት ሊቀድሙ የሚችሉ መሰረታዊ ነጥቦች ናቸው። ዜጎች በተናበበና በአንድነት እጅ ለእጅ ተሳስረው ከሰሩ አገራቸውን በኢኮኖሚ ጠንካራ የማድረግ፣ ሕዝባቸውን በዕውቀት የመገንባት፣ በቴክኖሎጂ የመራቀቅ አቅም ይኖራቸዋል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራቸውን ተቀባይነት ያሳድጋል።

ኢኮኖሚው ያደገና የፖለቲካ መረጋጋት ያለው አገር በወታደራዊ አቅሙም የተሻለ የመሆን ዕድሉ የላቀ ነው። በዚህም በዓለም ዘንድ የሚኖረው ተሰሚነት ከፍተኛ ይሆናል።

አንድ አገር በትክክለኛ ፖሊሲ ከተመራና ‘ከውስጥ ወደ ውጭ” የማየት አቅሙን ካጠናከረ፣ ዜጎች በአገራቸው ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ካደረጉ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰሚነት አቅማቸው ይጨምራል። ስለዚህ “ብሔራዊ ጥቅም የአንተ፣ የአንቺ፣ የሁላችንም ጥቅም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል” በማለት አምባሳደር መለሰ ያነሱት ሀሳብ የሚያጸናው ይህን ነጥብ ነው። በተጨማሪም ዜጎች በተሰለፉበት መስክ የሚያከናውኑት ተግባር ድምር ውጤቱ ለብሔራዊ ጥቅም መሰረት መሆኑንም ያንጸባርቃል።

ዛሬ ጠንካራ አገሮች ብልጽግናን ያረጋገጡ ናቸው። እነዚህ አገሮች በዓለምአቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ራሳቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ያሳደጉ፣ ለፈጠራና ክህሎት ዕድል የፈጠሩና ለብልጽግናቸው ዋና መሳሪያ ያደረጉ መሆኑን የታሪከ ድርሳናት የሚያረጋግጡት ጉዳይ ነው። ሌላው የጋራ እሴታቸውን በማበልጸግ አገራቸውን ቀዳሚ ያደረጉ፣ ሠላምን በተግባር ያረጋገጡና የሚያቀነቅኑ፣ ደህንነትን እውን የሚያደርጉና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚያግዳቸው ነገር አልታየም።

በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ “ብሔራረዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ ኃይል ያስፈልጋል። ኃይል ደግሞ በሁለት መልኩ ይከፈላል። እነዚህም ገር ኃይል (soft power) እና ድድር ኃይል (hard power) የሚሏቸው ናቸው” በማለት አምባሳደር መለሰ ይገልጻሉ። በሁለቱም የተዋጣለት ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የውስጥ ጥንካሬ አጠያያቂ አይደለም። የዜጎች ክህሎት፣ በሚሰማሩበት መስክ በብቃት መወዳደርና የፈጠራ ልቀትን መጥቀስ ይቻላል።

“በዲፕሎማሲው ዓለም ምን ይዘህ ትሄዳለህ?” የሚለው ጉዳይ ዋና ጥያቄ እንደሚሆን ነው አምባሳደር መለሰ የሚናገሩት። ለማንኛውም አገር አምባሳደር መሰረታዊ ጉዳይ የአገር ውስጥ ጥንካሬ፣ የኦኮኖሚውን አቅም፣ የፖለቲካው ሁኔታ፣ ዴሞክራሲያዊ መስተጋብርና የማኅበረሰቡን ዘመናትን የተሻገረ እሴት ጉልበት እንደሚሆነው ይታመናል። ለአንድ ዲፕሎማት “ገር እና ድድር” ኃይልን መጠቀም የሚያስችል አቅም ከውስጥ የሚያገኘው አንጡራ ሐብቱ አድርገን መውሰድ እንችላለን።

አገሮቸ ከሌሎች አገሮች ጋር ብሔራዊ ጥቅማቸውን ለማስከበር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የውስጥ ጥንካሬያቸው ዋነኛ መሳሪያ ነው። አገሮቹ የሚከተሉት ፖለቲካዊ ሥርዓት የተረጋጋና ሠላማዊ መሆን፣ በኢኮኖሚ መፈርጠም፣ የሕዝቦች አንድነትና ማኅበራዊ መዋቅር መጠንከር ከፍተኛ ጉልበት ይሰጠዋል።



21

ይህን ጠንካራ ሁኔታ ለመግለጽ ከገር ኃይል መካከል የመገናኛ ብዙኃንን ጉልበት መጠቀም ተጠቃሽ ነው። በዓለም ላይ ያለን ስፍራ በትክክለኛና ተገቢ በሆነ መንገድ ለማግኘት፣ ዓለምአቀፍ ተጽዕኖ ለማምጣትና ለዘመናት የዘለቀን ጠንካራ እሴት ለማስተዋወቅ፣ የተፈጥሮ ሐብትን ለማሳየት፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርስን ለማስቃኘት የመገናኛ ብዙኃን እንደሚያስፈልጉ ሁሉ በዓለም ሥርዓት ውስጥ ተገቢውን ስፍራ ለማግኘትና ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን በጠንካራ ይዘት መከሰት የግድ ይላል።

አምባሳደር መለስ፤ “የመገናኛ ብዙኃን አጀንዳ ይቀርጻሉ፤ የተቀረፀ አጀንዳን ያሰርጻሉ። አገሮች እንዲቀጥሉ፣ እንዲደግፉትም ይሰራሉ” በማለት ነው የገለጿቸው።

ሠላም ግንባታ

“ሠላም ምንድን ነው?” በሚል ለሚነሳው ጥያቄ ሰዎች ያሉበትን ሁኔታ በመመልከት በአንጻራዊነት ትርጉሙን እንደሚሰጡ ይታወቃል። አንድ የቃላት ትርጉም የሚሰጥ ድረ ገጽ “ሠላም ግጭት ወይም ጦርነት የሌለበት፣ ሁሉም ነገር ጥንቃቄ ባለበት ሁኔታ ተሰናስኖ የሚሄድበት ከጭንቀት ነጻ የሆነ፣ መረጋጋትና ደህንነት የሚሰማበት ነው” ሲል ይተረጉመዋል። አር.ጄ. ሩሜል የተባሉ ጸሀፊ ደግሞ “ሠላም

ምን ጊዜም ቢሆን ከሰው ልጅ ከፍተኛ እሴቶች መካከል ነው - ለአንዳንዶች ከሁሉም የላቀ” በማለት ይገልጹታል።

ይህ ሀሳብ ሲተነተን ሠላም የሚወሰነው በግለሰቦች ወይም በኅብረተሰብ የሞራል ልህቀትና መርህን መሰረት ያደረገ መስተጋብር መፍጠር ይሆናል። የሰው ልጅ ከጎረቤቱ፣ ከማኅበረሰቡና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር ከቻለ ሠላም እውን ይሆናል ማለት ነው። ስምምነቱ በሁሉም መስክ ተጣጥሞ፣ ሥርዓት፣ ሚዛናዊነት እና ፍትህ መፍጠር ይኖርበታል። ሰዎች ከራሳቸው፣ በዙሪያቸው ካሉ ሰዎችና ከተፈጥሮ ከባቢያቸው ሠላም መፍጠራቸው ለራሳቸው ዕድገትና ለውጥ መንስኤ ይሆናል። ይህም ሠላምን በእጅጉ እያጎለበተው፣ እያሳደገው፣ ይመጣል። የአንድ አገር ማኅበረሰብ ውስጣዊና ውጫዊ ተጣጥሞ ካለው ሠላም እውን ይሆናል። ይህ “ሠላም ሁሉን አቀፍ ነው” ማለት ይሆናል። ይህም ሠላም ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን በሂደት የሚገነባ መሆኑንም ያሳያል፤ ያረጋግጣል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ስለ ሠላም ግንባታ ሲናገሩ “የተረጋጋ ማኅበረሰብ መፍጠር ነው፤ ዴሞክራሲ መገንባት፣ በየትኛውም ፈተና



22

ውስጥ አብሮ መቆም፣ አብሮ ማለፍ” ነው ይላሉ። በሕዝቦች ዘንድ ተጣጥሞ ፈጥሮ፣ ሚዛናዊነትን ለማረጋገጥም ሆነ ፍትህን ለማስፈን ሠላም ዋና ማጠንጠኛው ነው። የሰው ልጆች አካባቢያዊ ሁኔታ ያለመስተካከል፣ ሁከትና ብጥብጥ መስፈን፣ ሞትና መጎዳት መስፋፋት የሚያመጡት ሥነ ልቦናዊ አለመረጋጋት በማኅበረሰብ ግንባታ ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተጽዕኖ ግልጽ ነው።

ይህ ደግሞ በሚገነባ አገርና ሊረጋገጥ በሚታሰብ ብሔራዊ ጥቅም ላይ የራሱ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ስለዚህ ነው ሠላምን መገናኛ ብዙኃን ሊያበስሩት፣ ስለ እርሱም ሊዘምሩለት የሚገባ ጉዳይ የሆነው።

መገናኛ ብዙኃን

በዓለም ላይ የመገናኛ ብዙኃን መረጃን በማድረስ በኩል ከመቼውም ጊዜ ፈጣን፣ ፍሰቱ የማያቋርጥ አድርገውታል። መረጃን በሚፈልጉት ዓይነትና ቅርጽ በማሰራጨት በዓለም ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ እየወሰዱም ነው። በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምዕራብና በምሥራቅ እየተንቀሳቀሱ የሚያሰራጩት መረጃ ዓለም የአሁኑን ቅርጽ እንዲይዝ የራሱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ይህም ሆኖ ለዓለም የሚያሳዩት ከራሳቸው አተያይ እንጂ ያለውን እውነታ አይደለም። ይህ ማለት ደግሞ ሕዝብ የሚያነበው፣ የሚያየውና

የሚሰማው የመገናኛ ብዙኃኑ ከቆሙለት “እውነት” አኳያ የፈቀዱለትን እንጂ በራሱ ክስተቱን ላይሆን ይችላል።

“በየቀኑ ማለት ይቻላል ዘግናኝ ወንጀሎችን ያሳያሉ፤ ነገር ግን አንዳንዶቹ በጣም አስጸያፊ፣ አስፈሪ እና ጥላቻ የተሞላባቸው ናቸው። ከዚህም የተነሳ ሌላውን ሁሉ ይደብቃሉ።” ታዋቂው ተማራማሪ፣ ፈላስፋ፣ የፖለቲካ አንቂ፣ ደራሲና መምህር ኖማ ቾምስኪ (Noam Chomsky) “ዓለምን የሚመራት ማነው?” በሚለው መጽሀፍ ላይ ያሰፈሩት ሀሳብ የሚገልጸው በርካታ ነጥብ አለ። መገናኛ ብዙኃን ዓለም ሁከት የበዛባት፣ የጭንቅ፣ የመከራ፣ የግጭት አካባቢ መሆኗን የሚገልጹ፤ ተስፋ ያጣች አስመስለው የሚስሉ ሌላውን መልካም እውነታ የሚደብቁ መሆናቸውን ያሳያል። በዚህም የዓለምን ገጽታ በሚፈልጉት መልኩ ማዕቀፍ ሰጥተውት ያሳያሉ። ይህ ነው በዓለም ላይ ተጽዕኖ የሚያደርሰው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ እንደሚሉት፤ በዓለም ላይ ካሉ ስምንት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል መገናኛ ብዙኃን ተጠቃሽ ነው።

“ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹም” ይላሉ ረዳት ፐሮፌሰር ምህረቱ ሀሳባቸውን በእጽንኦት ሲገልጹ፤ “መንግስት፣ ቢዝነስ፣ ትምህርት፣ ሃይማኖት፣



23

መገናኛ ብዙኃን፣ ስፖርት፣ ሥነ ጥበብ፣ የጤና ጉዳይ ናቸው። ከነዚህ መካከል መገናኛ ብዙኃን አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።”

ይህ የሚያመለክተው መገናኛ ብዙኃን በዓለም ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ምን ያህል ከባድ መሆኑን ነው። ጥያቄው የሚነሳው ይህን ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይል እንዴት እንጠቀምበታለን? የሚለው ላይ ነው።

“መገናኛ ብዙኃን ለሕዝብ መልዕክት እና ምልከታን ለማስተላለፍ የሚያገለግሉ ዘዬዎች ናቸው። ግለሰቦችን ከሰፊው የኅብረተሰብ ተቋማዊ መዋቅር ጋር እንዲዋሃዱ ለማድረግ እሴት፣ እምነት እና የስነ-ምግባር መርሆዎችን የሚያስተዋውቁ፣ የሚያስተምሩና የሚያዝናኑ ናቸው” በማለት ታዋቂው ተማራማሪ፣ ፈላስፋ፣ የፖለቲካ አንቂ ደራሲና መምህር ኖማ ቾምስኪ በአንድ ወቅት የገለጹትን ሀሳብ እዚህ ላይ ማንሳቱ መልካም ነው። የዚህ ዓይነቱ ኃላፊነት የተጣለባቸውና የግለሰብን አመለካከት የመቅረጽ አቅም ያላቸው መገናኛ ብዙኃንን እንዴት እየተጠቀምንባቸው ነው? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት “መገናኛ ብዙኃንና ብሔራዊ ጥቅም” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ባካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የተጠቆመው ሀሳብ “በሠላም፣ በዲፕሎማሲና በአገር ግንባታ ላይ የሚኖረው ሚና ቀላል ባለመሆኑ በአግባቡ መጠቀም” አስፈላጊነቱን ነው የሚያጸናው።

በፓናል ውይይቱ ወቅት “ለዓለምአቀፍ ግንኙነት መረጃ ትልቁ መሳሪያ ነው። የተሻለ መረጃ እና መረጃውን በተገቢው መንገድ፣ ቦታና ጊዜ መጠቀሙ ብሔራዊ ጥቅምን ያረጋግጣል” ያሉት አምባሳደር መለሰ፤ የመገናኛ ብዙኃን የአገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸውን ነው ያመላከቱት።

መገናኛ ብዙኃን ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም እንዳለባቸው መገነዘብ ይገባል። የማንኛውም አገር መገናኛ ብዙኃን ቅድሚያ የሚሰጡት ለብሔራዊ ጥቅማቸው ነው። አገራቸው በዓለም አቀፍ

ደረጃ የሚኖረውን ስፍራ በማሰብ የፖለቲካም ሆነ የባህል ተጽዕኖ ለመፍጠር ይሰራሉ። ይህንን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንም በሚገባ ተረድተው ሊሰሩበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። እያንዳንዱን ዝግጅት ዓላማ ኖሮት አጀንዳ ተቀርጾለት ሊሰሩበት የሚገባ፣ የማኅበረሰቡን ብዝኃ ባሕላዊ ሐብት በማስተዋወቅ በተቀረው ዓለም የተቀባይነት ድርሻን ከፍ የማድረግ አስፈላጊነትን መገንዘብ ይገባል።

በአገር ውስጥም የማሳወቅ፣ የማስተማርና የማዝናናት ተልዕኮውን የማኅበረሰቡን አስተሳሰብ በመቅረጽ፣ የአዕምሮ ልማት ላይ በማተኮር የመስራትን ጉዳይ ከብሔራዊ ጥቅም ጋር አስተሳስሮ ማየት ያስፈልጋል።

“የመገናኛ ብዙኃን የአገራቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በጥፍራቸውና በጥርሳቸው ይሰራሉ” በማለት አምባሳደር መለስ የተናገሩት ጠንካራ ሀሳብ የጉዳዩን ጥልቀት የሚገልጽ ነው። በአገር ደረጃ የተገኙ መረጃዎች ሲሚዘገቡ፣ ለአገርና ለሕዝብ ትርፍ የሌላቸው መረጃዎች የሚሰራጩበት ሁኔታ መኖር የለበትም።

መገናኛ ብዙኃን የኅብረተሰቡን መሰረታዊ ጉዳዮች በማንሳት፣ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማመላከት ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብርበትን ጥበብ ሊያስታጥቁት ግድ ይላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “የመደመር ትውልድ” በሚለው መጽሀፋቸው “ሚዲያ በአዎንታዊ ሚናው የማኅበረሰብ ክፍተቶችን ነቅሶ በማውጣት እንዲታረም የሚያደረግ ነው።” ሲሉ የገለጹት ሃሳብ የመገናኛ ብዙኃንን ሚናን ያሳያል።

የአሀዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ስራ ስኪያጅ ጥበቡ በለጠ “ዴሞክራሲና መገናኛ ብዙኃን” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ሃሳብ ሲገልጹ “መገናኛ ብዙኃን ከኃላፊነት ጋር ለአገር ግንባታ ያላቸው ሚና፣ የሰው ልጅ አዕምሮ፣ እንቅስቃሴ ኢኮኖሚውን ማንነቱን ሁሉ የሚሳበው በአብዛኛው በመገናኛ ብዙኃን ነው። ስለዚህ መገናኛ ብዙኃን ጠንካራ ናቸው ማለት …. ትልቁ

ጉዳያቸው ለአዕምሯዊ ልማት ይሆናል” በማለት ያብራሩት ሀሳብ የመገናኛ ብዙኃንን በአግባቡ በመጠቀም የሰውን ልጅ ወደ መልካም አቅጣጫ፣ ወደ ለውጥ መምራት ይኖርባቸዋል ማለት ነው።

መገናኛ ብዙኃን አጀንዳ በመቅረጽና መልዕክቶችን በአስፈላጊው መንገድ በማስተላለፍ የሕዝብን ተሰሚነት ከፍ የማድረግ ድርሻቸውን የመወጣት ጉዳይ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም። በአሁኑ ጊዜ የማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋትና የመረጃ ፍሰት እጅግ ፈጣንና በብዛት መፍሰስ ማኅበረሰቡ ትክክለኛውን መረጃ በትክከለኛው ወቅት እንዳያገኝ እያደረጉት ይገኛል። መንግስትና ትላልቅ ኩባንያዎች የመረጃ የበላይነታቸውን ያጡበት ጊዜ ላይ መገኘታችን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባና ከወዲሁ ተገዳዳሪ አቅጣጫ ልንከተልበት የሚያስፈልግ መሰረታዊ ነጥብ ነው።

ማጠቃለያ

የአገር ልማትና ዕድገት ለማኅበረሰብ አጠቃላይ ለውጥ ከፍተኛ ሚና አለው። ዜጎች በኢኮኖሚ ሲጠነክሩ፣ በትምህርት ሲጎለብቱና ማኅበራዊ ንቃተ ህሊናቸው ሲያድግ የአገር ልማት የበለጠ እያደገና እየጎለበተ ይመጣል። በዚህ ደግሞ በአካባቢያቸው፣ በጎረቤታቸው፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ። በድድርም ይሁን በገር ኃይል የሚያሳድሩት አዎንታዊ ተጽዕኖ አገሮች በዓለም አቀፍ መድረክ የሚገባቸውን ስፍራ እንዲያገኙ ያስችላል።

ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሀፊ ሄነሪ ኪሲንገር “ኢኮኖሚ አንዱ አገሮችን ማንበርከኪያ መሳሪያ ነው” ያሉትን እውነታ መገዳደርና ማሸነፍ የሚችሉበት አቅም ይኖራቸዋል።

ይህን ሲያደርጉ የበለጠ ብሔራዊ ጥቅማቸውን ያስከብራሉ። ሠላማቸውን ከመቼውም በላይ ያጎለብታሉ። ለዚህ መሳለጥ የመገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን አይተኬ ሚና ይጫወታሉ። ችግሮችን ከመፈተሽና መፍትሄዎችን ከመጠቆም ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ አገር የሚኖራትን ገጽታና ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም በግልጽ ያሳያሉ።



24

ሥነ ጥበብ

ሣይንስን ከጥበብ ያቆራኘ ሙዚየም



25

ሣይንስን ከጥበብ ያቆራኘ ሙዚየም

እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ኅዳር 2013 ኩዌት ያስተናገደችውን ሦስተኛው የአፍሪካ- ዓረብ አገሮች የመሪዎች ጉባዔ በአገሪቷ አሚር ሼህ ናዋፍ አል-አህመድ አል-ጃብር አል-ሳባህ ጋባዥነት የመዘገብ ማለፊያ ዕድል አግኝቼያለሁ። በኩዌት የአንድ ወር ቆይታ ማድረግም ችያለሁ። ከጉባዔው መጀመር ቀደም ብዬ ወደዚያው አቅንቼ ስለነበረ ከታላቁ የቡርጋን ነዳጅ ማውጫ እስከ የኩዌት የሳይንስ ማዕከልን (The Scientific Center of Kuwait-TSCK) የመጎብኘት ዕድል ገጥሞኛል።

“TSCK” በሚል ምህፃር የሚጠራው የኩዌት የሣይንስ ማዕከል የኩዌታዊያን የባሕል ስኬት እና የትምህርት ነጸብራቅ ስለመሆኑ በአገሬው በስፋት ይነገርለታል። ማዕከሉ በሣይንሳዊ የግኝት ስብስቦች የበለፀገ ሲሆን፤ የእስልምናን ጥበብና ባህል የሚያንፀባርቅ አስደናቂ የኪነ-ህንፃ ንድፍ አለው። ኩዌታዊያንም በእጅጉ የሚኮሩበት ዘመናዊ እና ውብ የሣይንስ ሙዚየም ነው። የማዕከሉ ግድግዳዎች የአገሪቷን ታሪክ የሚያሳዩ ምስሎችን ይዘዋል። ዋናው ሕንፃ ሦስት ዋና ዋና መስህቦችን ያቀፈ ሲሆን፤ የውኃ ውስጥ እንስሳት እና ዕፅዋት ማያ (Aquarium)፣ የግኝት ቦታ (Discovery Place) እና የምስለ ከፍታ (Image Maximum-IMAX) ቴአትርን አካቷል።

የምስለ ከፍታ (IMAX) ሰፊ የማያ-ገጽ (Screen) ሲኒማቶግራፊ ዘዴ ሲሆን፤ ከመደበኛው 35

በጌታቸው ያለው



26

ሚሊሜትር ፊልም በአሥር እጥፍ ያህል የሚበልጥ ምስል ማውጣት የሚችል ነው። እንዲያውም ከማያ ገጽ በላይ እንደሆነ ይነገርለታል። ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ካሜራዎች፣ የፊልም ፕሮጀክተሮች እና ቴአትሮችን ያካተተ የሲኒማቶግራፊ ሥርዓት ነው።

ለጉባዔው የተጋበዝነው የተለያዩ አገሮች ጋዜጠኞች የሣይንስ ማዕከሉን በጎበኘንበት ወቅት የተሰማንን ስሜት እንድናጋራቸው የኩዌት መገናኛ ብዙሃን ጠየቁን። ከናይጄሪያ፣

ከደቡብ አፍሪካ… እያሉ ከኢትዮጵያ ሲሉ እኔ ላይ ደረሱ።

በዕውነት ለመናገር የሣይንስ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ ታግዞ የተገነባ ድንቅ ሙዚየም ነው። አሸዋማ እና በረሃማዋ ኩዌት ለም አፈር ከአውስትራሊያ እና ኢንዶኔዥያ ሳይቀር በማስመጣት የሣይንስ ማዕከሉን አድምቃዋለች። በተለይ የፋርስ ባሕርን የወከለው አኳሪየም (Aquarium) በርግጥም ውብና ቀልብ የሚሰብ ድንቅ ገጽታ አለው። በተመለከትኩት ሁሉ መደነቄን የተሰማኝን

ሳልሰስት ለኩዌት ጋዜጠኞች ገለጽኩላቸው።

ለአንድ ጥያቄያቸው ከእኔ ያገኙት ምላሽ ግን ቃለ-መጠይቁን አቋረጠው። ‘የኩዌትን ባለ ሦስት ወርድ ማሳያ (3D Display) እንዴት አገኘኸው?’ ሲሉ በኩራት ጠየቁኝ። ምላሼን ከመስጠት ይልቅ ፈገግ አልኩኝ። ጠያቂዎቼ መልሴን በጉጉት ጠበቁ። ቀለል አድርጌ “እኛ አገር ባለ ሰባት ወርድ ማሳያ (7D Display) መጠቀም ከጀመርን ሰነባብተናል እኮ” ስል ፈርጠም ብዬ መለስኩላቸው። ‘እየነገርከን ያለኸው ስለ



27

ኢትዮጵያ ነው?’ ሲሉ ጠየቁኝ። “አዎን” ስል በተራዬ በኩራት መለስኩላቸው። በቃ ከዚህ በላይ ቃለ ምልልሱን መቀጠል አልፈለጉም። እንደ መበሳጨት እያደረጋቸው እርስ በእርሳቸው በዓረብኛ በአግራሞት እየተነጋገሩ ትተውኝ ሄዱ።

ለአፍታ ከኩራት ስሜቴ ጋር ብቆይም ውስጤን ግን ቁጭት ሰቅዞ ያዘው። ኢትዮጵያ የኩዌትን ያህል ድንቅ የሣይንስ ማዕከል ባይኖራት እንኳ ሱዳን በካርቱም የገነባችው የሣይንስ ሙዚየም ዓይነት የሌላት መሆኗ በውስጤ ተቆጨሁ። “ምናለ መንግሥት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ቢሰጥ?” ስልም ተመኘሁ። መሰንበት ደግ ነው እንዲሉ ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት በቁጭት ያብከነከነኝ እና የተመኘሁትን የሣይንስ ሙዚየም በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ጠንሳሽነት በመገንባት ለሕዝቧ ገጸ-በረከት አቀረበች። ውስጤን ሲያምሰው የነበረው የቁጭት ስሜት ተገፈፈ። በአገሬም ኮራሁ።

የሣይንስ ሙዚየም ምንድን ነው?

የሣይንስ ሙዚየም በዋናነት “ለሣይንስ የተሰጠ ሙዚየም ነው” ሲል ኒው ወርልድ ኢንሳክሎፒዲያ (New World Encyclopedia) ይገልጸዋል። የሥነ-ጥበብ ሙዚየሞች የጥበብ ሥራዎችን በመመልከት የጎብኚዎችን የሥነ-ውበት እሴቶችና ልምዶችን ለማሳደግ የተነደፉ ናቸው። የሣይንስ ሙዚየሞች ደግሞ ለሣይንሳዊ ግኝቶች እና ለቴክኖሎጂ ፈጠራ ወሳኝ የሆኑ የጎብኝዎችን አስደናቂ ስሜት እና የማወቅ ጉጉት ለመሳብ የሚገነቡ ናቸው።

በተመክሮ አሊያም ከነገሮች ጋር በሚኖር መስተጋብር ጎብኚዎች ማየት፣ መስማት፣ መንካት አንዳንዴም የነገሮችን ለውጥ ማሽተት ይችላሉ። ይህ ብቻ አይደለም የሣይንስ ሙዚየም ሳይንቲስቶች እና የፈጠራ ባለሙያዎች ያጋጠሟቸውን ልምድ ለጎብኚዎች ለማጋራት ይሞክራሉ። ብዙውን ጊዜ የሣይንስን እርካታ

ከፍ ለማድረግ የቅርብ ጊዜውን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ናቸው።

በአንፃሩ ቆየት ያሉ የሣይንስ ሙዚየሞች ከተፈጥሮ ታሪክ፣ ከቀደምት ፍጥረታት አወቃቀርና ባህሪይ ጥናት (Palaeontology) ፣ ከሥነ-ምድር፣ ከኢንዱስትሪ እና ከኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች… ወዘተ ጋር በተያያዘ የቋሚ ቁሳቁስ ማሳያዎች ብቻ ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ይስተዋላል።

ሙዚየሞችን በማደራጀት እና በማስተዳደር ሣይንስ (Museology) ውስጥ ያሉ የዘመኑ አዝማሚያዎች ደግሞ የርዕሰ-ጉዳዩን ወሰን ይበልጥ በማስፋት በርካታ መስተጋብራዊ ትዕይንቶች እንዲካተቱ አድርገዋል። በዚህም የዘመናዊ ሣይንስ ሙዚየሞች ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሳቸውን በማስፋትና ትኩረታቸውን ይበልጥ ቴክኖሎጂ ላይ በማድረግ ‘የሣይንስ ማዕከሎች’ ወይም ‘የግኝት ማዕከላት’ እየተባሉ እንዲጠሩ ሆኗል።

የሣይንስ ሙዚየም ፋይዳ

“ሣይንስ የሕይወት መንገድ ነው” ሲሉ ብዙ የመስኩ ሊቃውንት ይገልጹታል። ሣይንስ እይታ ነው፤ ሣይንስ ከግራ መጋባት ወደ ትክክለኛ፤ ከግምታዊ አስተማማኝ በሆነ መንገድ ወደ መረዳት የሚወስድ የለውጥ ሂደት እንደሆነም ይገልፃሉ። በዘመናት እና በትውልድ ቅብብሎሽ የሚፈጠሩና ጥቅም ላይ የሚውሉ የሣይንስ የፈጠራ ውጤቶች ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ የሙዚየሞች ፋይዳ በቀላሉ የሚታይ እንዳልሆነም ያስረዳሉ።

የሣይንስ ሙዚየሞች ሣይንሳዊ ቅርሶችን እና መረጃዎችን የሚሰበስቡ እና ለሕዝብ የሚያቀርቡ ተቋማት ስለሆኑ ከጥንት ቅሪተ አካላት እስከ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚደርሱ ቅርሶችን ለትውልድ እንዲተላለፉ በማድረግ



28

በኩል ፋይዳቸው የላቀ ነው።

የሣይንስ ሙዚየሞች ለሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ጠቃሚ የታሪክ ምንጮች ናቸው። ሣይንሳዊ መነሻዎችን ለማሳየት አስፈላጊ ታሪካዊ ነገሮች ተሰብስበው እንዲቀመጡ የሚደረግባቸው ማዕከላት ናቸው። ከመጀመሪያው ግኝት “Eu- reka” እስከ ዛሬው የተራቀቁ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ድረስ ምርምርን በማስተዋወቅ ወሳኝ ድርሻ አላቸው።

የሣይንስ ሙዚየሞች መሳጭ ትዕይንቶች የሚመለከቱባቸው እና ስለ ሣይንሳዊ ጽንሰ- ሃሳቦች የሚማሩባቸው ቦታዎች ብቻ አይደሉም። የማወቅ ጉጉትን የሚያነሳሱ፣ ፍለጋንና ፈጠራን እንዲሁም ትምህርትን የሚያበረታቱ ተቋማት ጭምር ናቸው።

የሣይንስ ሙዚየሞች ባህላዊ፣ ታሪካዊ ወይንም ሣይንሳዊ ፋይዳ ያላቸውን አጠቃላይ የሕዝብ ቁሶች የሚጠብቁ፣ የሚሰበስቡ እና ተደራሽ የሚያደርጉ የሕዝብ ተቋማት እንደሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም በሣይንስ ታሪክ፣ በታዋቂ ሳይንቲስቶች እና በወቅታዊ ሣይንሳዊ ምርምር ላይ ዓውደ ርዕዮች ያዘጋጃሉ። የሣይንስ ሙዚየሞች በተለምዶ ለህፃናት እና ለአዋቂዎች ትምህርታዊ መርሃግብሮችን የሚሰጡ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ የምርምር ተቋማትን ያካትታሉ።

የሣይንስ ማዕከላት እና የዘመናዊ ሙዚየሞች ዓላማ እንደየአገራቱ ፍላጎት የተለያየ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም ሣይንስን ተደራሽ የሚያደርጉና የግኝቱን እርካታ የሚያበረታቱ ስፍራዎች መሆናቸው ዓላማቸውን አንድና ተመሳሳይ ያደርገዋል።

የሣይንስ ሙዚየሞች ተልዕኮ ስለ ሣይንስ እና በኅብረተሰብ ውስጥም ስላለው ሚና ማስተማር ነው። በተጨማሪም የሣይንስ ሙዚየሞች በተለምዶ የተለያዩ መስተጋብራዊ ትዕይንቶችን አሊያም ዓውደ ርዕዮችን እና ትምህርታዊ መርሃ ግብሮችን ያቀርባሉ።

በአጭሩ የሣይንስ ሙዚየሞች የትምህርት ማዕከል ናቸው። በሁሉም የዕድሜ ክልልና የትምህርት ደረጃ ለሚገኙ ሰዎች ሣይንሳዊ ዕውቀትን ለማሳደግ የሚረዱ በርካታ የትምህርት ቁሳቁስ ስብስብ የያዙ ግዙፍ ማዕከላት ናቸው።

በአሜሪካ በሚገኘው የመሀመድ ዓሊ የባህል

ሙዚየም የሕዝብ ግንኙነት እና የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጄኒ “ሙዚየም የቅርስ ቦታ ብቻ ሳይሆን የሃሳብ ቦታ ጭምር ነው” ስትል አስፈላጊነቱን ትገልጻለች።

የሣይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት በብዙ መልኩ የሰው ልጆችን ሕይወት መቀየር ብቻ ሳይሆን ምቹና ቀላል አድርጎታል። የትምህርት የመጨረሻ ግቡም ይኸው ነው። ሕይወትን ምቹ እና ቀላል ማድረግ።

ሣይንስና ቴክኖሎጂ ሰዎች በቀላሉ እንዲገናኙ ከማድረግ ጀምሮ ግዙፍ መረጃን እስከ ማከማቸት እንዲሁም አይቻሉም የሚባሉ ነገሮችን ያስቻለ የሰው ልጅ ድንቅ ብቃት የታየበት አቅም ነው። ቴክኖሎጂ ዘመናዊ ሕይወትን ቀላል ያደረገባቸው መንገዶችም እጅግ ብዙ ናቸው።

በዚህ ረገድ በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል። ከሞባይል ስልክ እስከ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ፣ ከህክምና እስከ የደህንነት መጠበቂያ እና ውሂብ (data) መላክና ማከማቸት ያሉ ቴክኖሎጂዎች፣

ከገንዘብ አልባ እስከ ኦንላይን ግብይት፣ ከትምህርት እስከ መዝናኛ …ወዘተ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ሕይወትን ፈጣንና ቀላል እንድትሆን ማድረግ ችለዋል።

ቴክኖሎጂ ሰዎች ከአልጋቸው ሳይነሱ በምቾት እንዲሰሩ በማድረግ ክፍተቱን በብቃት ሞልቷል። የእነዚህ ሁሉ የግኝት ማዕከል ደግሞ የሣይንስ ሙዚየሞች መሆናቸው ፋይዳቸው እንዲጎላ አድርጎታል።

የኢትዮጵያ የሣይንስ ሙዚየም

የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቷን የዲጂታል መሰረተ ልማት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ዘመናዊ የሣይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብቶ አበርክቷል።

ሙዚየሙ ጊዜው የሚጠይቀውን የሣይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሃሳቦች እንዲዳብሩበት ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እንዲመጥን ተደርጎ የተገነባ ነው። የሙዚየሙ መገንባት በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ የቴክኖሎጂ



29

ሚናን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያራምድ እንደሆነም ታምኖበታል።

የጉልላት ቅርጽ ያለውና በጠፈር አምሳል የተገነባው ይህ የሣይንስ ሙዚየም በአፍሪካ በዓይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነ ተነግሮለታል። ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገትና ልማትን የሚያግዙ አዳዲስ ሣይንሳዊ ግኝቶች የሚጸነሱበትና የሚወለዱበት ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ሻገር ሲልም ለመጪው ትውልድ የሚተላለፉ ቴክኖሎጂዎች ነባርም ሆኑ አዳዲስ የምርምር ውጤቶች ማዕከል እና ማከማቻ ሆኖ እንደሚያገለግል ተነግሯል። የሣይንስ ሙዚየሙ የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት ወሳኝ ክፍል።

በሙዚየሙ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከሁለት ዓመት በፊት ተግባራዊ መሆን የጀመረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ

ስትራቴጂ አገሪቷ ለሣይንስና ቴክኖሎጂ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ነው ያመለከቱት። ግንባታው “ኢትዮጵያ ለሣይንስና ቴክኖሎጂ ያላትን ትኩረት የሚያሳይ ነው” ሲሉ የሙዚየሙን አስፈላጊነት አጉልተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ኢንስቲትዩት (Artificial Inteligence Insti- tute) የአገሪቷን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጥረቶች ለማገዝ ከሚሰሩ መንግሥታዊ ተቋማት አንዱ መሆኑን በማውሳት፤ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ያለውን ተስፋ ሰጪ ብቃት አድንቀዋል።

ሙዚየሙ ወጣቶች ስለፈጠራ እንዲያስቡ እንደሚያነሳሳ እና የፈጠራ ሃሳቦች ማፍለቂያ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ እምነት አሳድረውበታል።

በሙዚየሙ ምረቃ ላይ የታደሙት የመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ፔድሮ ኢትዮጵያ የገነባችውን የሣይንስ ሙዚየም “ድንቅ” ሲሉ አሞካሽተውታል።

በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የሚደገፉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ የሽግግር ፕሮጀክቶችን በማሳደግ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እውን ለማድረግ ብሎም አህጉራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማስቀጠል መሰል ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጣቸው በመስኩ የኢትዮጵያ ጅማሮ ላቅ ያለ ዋጋ እንዳለው መገንዘብ ይቻላል።

ለመሆኑ ይህ የመጪው ትውልድ የፈጠራ ሃሳቦች ማፍለቂያ እና የችግር ፈቺ ምርምሮች ማዕከል ‘የኢትዮጵያ የጥበብ እና የሣይንስ ሙዚየም’ ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታ ምን ይመስላል? የሚለውን ይህ ጽሁፍ በወፍ በረር ያስቃኛል።

የሙዚየሙ ውጫዊ ገጽታ በከፊል

የኢትዮጵያ የጥበብና የሣይንስ ሙዚየም ብሔራዊ ቤተ-መንግሥትን ተንተርሶ ከሸራተን አዲስ ጀርባ የተገነባ ነው። ግዙፉ ሙዚየም በአፍሪካ ታላላቅ ከሚባሉ የሣይንስ ሙዚየሞች ተጠቃሽ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ክብ ቅርጽ ያለውና 14 ሺህ 864 ካሬ ሜትር ስፋት የሚሸፍነው እንዲሁም 10 ሜትር ያህል



30

ከፍታ ያለው ይኸው ሙዚየም ቋሚ ዕድገትን እንዲሁም የሰውን ልጅ ምጡቅነት ለማሳየት በሚያስችል መልኩ ተነድፎ የተገነባ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ በቀጣይ የቴክኖሎጂ ዕድገት ለማምጣት ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ ውብ ኪነ-ሕንፃ ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ሙዚየሙ በሰባት ሄክታር መሬት ላይ የተንጣለለ ሲሆን፤ ይህም አሥር ያህል የእግር ኳስ ሜዳዎችን የሚሸፍን ነው። የሙዚየሙ 80 በመቶ ያህሉ በአረንጓዴ ተክሎች እንዲሸፈን ተደርጓል። ይህም የአየር ንብረት ለውጥን ከመቀነስ እሳቤ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ መገንባቱን ያሳያል።

የሙዚየሙ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታ እና የእግረኛ መንገዶች ከሌሎቹ በቅርቡ ከተገነቡት ውብ የመዲናይቱ መናፈሻዎች /ፓርኮች/ ጋር በማራኪ ሁኔታ እንዲስማሙ ሆነው የተገነቡ ናቸው። በዚህ ድንቅ ሙዚየም ፓርኮች ውስጥ ከአራት ሺ በላይ አገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና በህብረ ቀለማት ያሸበረቁ አበቦች መገኘታቸው ደግሞ ፈረንጆቹ “The Cherry on the Cake” እንደሚሉት ዓይነት ተጨማሪ ጌጥ ሆነውታል።

የዋናው ሕንፃ ጣሪያ የአረንጓዴ ሽፋን ሥፍራ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚረዱ የፀሐይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎችን (So- lar Panels) የያዘ ነው። በተጨማሪም የውኃ ግድቦችን አካቷል። ከብክለት የፀዳ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያገኘው ሙዚየሙ ተፈጥሯዊ የኃይል ማስተላለፊያዎችና ኃይል ቆጣቢዎችን ይጠቀማል።

ማንም ሰው ዘና ብሎ የሚመገብበት ካፌ በሙዚየሙ ሰገነት ላይ ይገኛል፤ በዚህ ጉልላት (Planetarium) የከተማዋን ውብ ገጽታ ከማየት ባለፈ ከዋክብትንና ሌሎች የህዋ ምስሎችን በጨረፍታ መመልከት የሚያስችል ነው። በአጭሩ የተፈጥሮን ድንቅ ችሮታና ውብት ለመመልከት “ተመራጭ የሙዚየሙ ክፍል ነው” ማለት ይቻላል።

ሙዚየሙ ከላይ ሆነው አዲስ አበባን የሚታዘቡ የሚመስሉ ሁለት ግዙፍ ህንፃዎች ያሉት ሲሆን፤ የከተማዋን ትዕይንት ለመመልከት ምቹ ሥፍራዎች ናቸው። የአትክልት ስፍራው ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ምቹ የመመገብያ ላውንጆች ይገኛሉ። ይህም እንግዶች እየተመገቡ የሙዚየሙን ውብ ገጽታ እንዲቃኙ ያስችላቸዋል። በአጭሩ ያማረው የሙዚየሙ የውጭ ገጽታና ኪነ-ህንፃው ለመዲናይቱ አዲስ

አበባ ተጨማሪ ድምቀት ሆኗታል።

የሙዚየሙ ውስጣዊ ገጽታ በከፊል

የሙዚየሙ አቀማመጥ ሁለት ዋና ዋና ሕንፃዎችን የያዘ ሲሆን፤ በውስጡ በርካታ መስተጋብራዊ ማሳያዎችን ያካተተ ነው። ወደ ቅጥር ግቢው ከተገባ በኋላ ወደ ሙዚየሙ ውስጥ የሚያዘልቀው በር በልዩ ንድፍ የተሰራና የተለየ ድባብ የሚፈጥር ሆኖ እናገኘዋለን። ወደ ውስጥ ሲገባ ደግሞ ሰፊ ክፍልና የጉልላት ቅርጽ ባለው ከፍ ያለ ጣሪያ ተውቦ የተገነባ ማራኪ ኪነ-ህንፃ ነው። ዞር ዞር ብሎ ለሚመለከተው በርግጥም “አገር ውስጥ ነኝ ያለሁት” የሚያስብል ድንቅ ኪነ-ውበት የተላበሰ ነው።

ክፍሉ በተለያዩ መስኮች የአገር ውስጥ ፈጠራዎችን የሚያጎሉ የማኑፋክቸሪንግ፣ የሮቦቲክስ፣ የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ የጤና አጠባበቅ እና የሳይበር ደህንነትን በውስጡ አቅፏል። በዚሁ የሙዚየሙ የመጀመሪያ ክፍል የሰው ልጆችን የኑሮ ዑደት (Human Progress) ከአመጋገብ ሥርዓት እስከ መድኃኒት ቅመማና ግኝት ያለውን የሰውን ልጅ ኑዋሬ የየዘመናት ዕድገትና መሻሻሎችን ያሳያል።

ሌላው ነገረ-ሥርዓት (Room of Systems) በሚል የተሰየመው የሙዚየሙ ክፍል የመረጃና ከቦታ ቦታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሚታዩበት ሲሆን፤ በጥልቀት የሚመራመሩበት ነው። በዚህ ክፍል በተለየ መልኩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሰው ልጆች ሕይወት ላይ ያላቸው ተጽዕኖ በሰፊው የሚታይበት ነው።

በዚህ ክፍል ኢትዮጵያዊ ባህልን ከሚያንጸባርቁ አሃዛዊ መጫወቻዎች (Digital Games) አንስቶ ያለማንም አጋዥነት በርቀት (Reom- te) የመስተንግዶ ትዕዛዝ ማድረግና መጠቀም የሚያስችለውን ‘ስማርት ሆም’ የያዘ ድንቅ የቴክኖሎጂ ማዕከል ነው።

በሙዚየሙ መሀከለኛው ክፍል 14 ሺህ ካሬ ሜትር ያህል ስፋት ያላቸውና ከድምጽ ብክለት የተጠበቁ ቋሚ እና ጊዜያዊ የዓውደ ርዕይ ክፍሎች ይገኛሉ። የክፍሎቹ ድባብ ጎብኚዎች ፍጹም የጸጥታ ስሜት እንዲሰማቸው እና በትይዕንቱ እንዲመሰጡ ያደርጋል።

የመረጃ እና ተንቀሳቃሽ ሥርዓተ ክፍል ሌላው የሙዚየሙ የውስጥ ገጽታ ነው። ይህ ክፍል መስተጋብራዊ ቴክኖሎጂዎች በሰው ልጅ ዕድገት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ

የሚያብራሩና ልዩ እይታን ለማቅረብ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ስብስቦችን የያዙ የተለያዩ ክፍሎችን ያካተተ ነው። በተጨማሪም ሥነ- ምኅዳር (Mobility Ecosystem) በሰዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እና ተጽዕኖውን ለመሻገር የሚጠቅሙ ቴክኖሎጂዎች የሚንጸባረቅበት ክፍል ነው።

የጉልላት ቅርጽ ያለው (Planetarium) የሙዚየሙ ሰገነት ሌላው የሙዚየሙ የውስጥ ክፍል አካል ሲሆን፤ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሥነ-ፈለጋዊ፣ ሥነ-ምድራዊ፣ ሥነ-ሕይወታዊ ትዕይንቶችን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመመርመር የሚያስችል ነው።

በአንድ ጊዜ እስከ 200 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል እና 25 ሜትር ርዝማኔ እንዲሁም ከሰባት ካሬ ሜትር የሚበልጥ ስፋት ያለው “ሲኒማ” የሙዚየሙ ድንቅ የውስጥ ገጽታ ነው። ይህ ክፍል (Room of Exploration) ከደቂቅ እስከ ህልቆ-መሳፍርት ያሉ ቁስ አካላትን ለማጥናት የሚረዳ ብቻ ሳይሆን ጎብኚዎችን ከምድር ወደ አጽናፈ ሰማይ እንዲጓዙ የሚያደርግ ነው - በምናብ።

በሙዚየሙ መሃል ክፍል የሚገኘው ዘመናዊ አምፊ ቴአትር ዓለም አቀፍ ዓውደ ርዕዮች እና የመድረክ ትዕይንቶችን የማስተናገድ ብቃት እንዲኖረው ተደርጎ ተገንብቷል። ሙዚየሙ ለተማሪዎች እና ለተመራማሪዎች የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ቤተ ሙከራዎች፣ ቢሮዎች እንዲሁም የባለ ልዩ ማዕረግ (VIP) ማስተናገጃ ላውንጅ አካቷል።

ለእንግዶችና ለሰራተኞች ከሚሰጠው የካፌና የሱቆች አገልግሎት ባለፈ ልዩ ልዩ የውስጥ እና የውጭ መስተንግዶ አገልግሎትም በሙዚየሙ ይሰጣል። ዘመናዊ የሣይንስ፣ ጥንታዊ እና የዘመኑ የጥበብ ስራዎችን ጨምሮ መረጃ ሰጪ፣ አነቃቂ እና አዝናኝ የሆኑ በርካታ ትዕይንቶችን እንዲሁም የሣይንስና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚገለገሉበት የድምፅ ስቱዲዮዎችን ያካተተ ነው።

አዳዲስ ክስተቶችን ለመከታተል አሊያም ከሥራ መልስ ዘና ማለት ቢያስፈልግ በሙዚየሙ የሚገኙ የዓውደ ርዕይ ሥፈራዎችና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የመዝናኛ ስፍራዎቹ ተመራጭ ናቸው።

በጥቅሉ የኢትዮጵያ የሥነ-ጥበብ እና የሣይንስ ሙዚየም የትናንቱን፣ የዛሬውን እና የነገውን



31

ኢትዮጵያዊነት በአንድ ጣሪያ ሥር ሣይንሳዊና ኪናዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ እጹብ ድንቅ ማዕከል ነው።

ግንባታው 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ የሆነበት ይህ ግዙፍ እና ድንቅ ሙዚየም ለወጣቶች ወርክሾፕ አማራጮችን እየሰጠ ይገኛል።

የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ሙዚየሞች

ዘመናዊ የሣይንስ ሙዚየሞች የተፈጥሮ ድንቃ ድንቆችን በማስቃኘት ጎብኚዎች የራሳቸውን የማወቅ ጉጉት ወደ ዕውነታና ፈጠራ እንዲለውጡ የሚያበረታቱ ማዕከላት ናቸው። ዓላማቸውም ሰዎች ስለ ሣይንስ እና የሣይንስ ታሪክ የሚማሩበትን ቦታ መስጠት እንደሆነ ይታመናል።

የሣይንስ ሙዚየሞች ስለ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ለመማር ዓይነተኛ አማራጮች ጭምር ናቸው። የሚያቀርቧቸው ትዕይንቶች አስደሳች እና መስተጋብራዊ በመሆናቸው ሰዎች ዕውቀታቸውን ለማዳበር ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ።

‘በሚሄዱበት አገር ሁሉ ሙዚየም መጎብኘት ግዴታ ነው’ የሚል የተለመደ አባባል አለ። እናም በጎብኚዎች የማይታለፉ ከሚባሉ ከዓለማችን 10 ድንቅና የተለዩ ሙዚየሞች መካከል ሁለቱን ለቅምሻ ጀባ ብያለሁ።

በሜክሲኮ የሚገኘው የካንኩን የባሕር ውስጥ ሙዚየም (Cancun Underwater Muse- um of Art) ወይም በአገሬው አጠራር ሙሴዮ

ሱባኩዋቲኮ ዴ አርቴ (MUSA) በዓለም ላይ ትልቁ የውኃ ውስጥ ሙዚየም በመሆን የሚያስከነዳው አልተገኘም።

በካንኩን እና ኢስላ ሙጄረስ ደሴቶች መካከል የሚገኘው ይህ የውኃ ውስጥ ገነት በዓመት ወደ 750 ሺህ የሚጠጉ ቱሪስቶች ይጎበኙታል።

ሌላው የዓለማችን ድንቅ ሙዚየም የአሜሪካው ዓለም አቀፍ የስለላ ሙዚየም (The Interna- tional Spy Museum) ነው። እ.አ.አ በ2002 በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ፔን ኳርተር ውስጥ የተከፈተ ሲሆን፤ በ2019 ኤል-ኤንፋንት ፕላዛ ወዳለው አዲስ የዓውደ ርዕይ ህንፃ እንዲዛወር ተደርጓል።

ይህ ሙዚየም ለሕዝብ እይታ የበቁ በርካታ ዓለም አቀፍ የስለላ ቁሳቁስ ስብስብ የያዘ ነው። በተለይ የመስኩ ስኬቶች እና ውድቀቶች፣ ተግዳሮቶቹን እና ውዝግቦችን በማሰስ በተደበቀው የእውቀት ዓለም የምስጢርነት መጋረጃን ገላልጦ የሚያሳይ ነው።

የዓለም አቀፉ የስለላ ሙዚየም ጎብኚዎች የስለላን ዓለም አሳታፊ በሆነ መልኩ እንዲመለከቱት ያደርጋል። ብዙውን ጊዜ በምስጢር የተሞሉ ርዕሶችን ይጠቀማል። ሙዚየሙ የማሰብ ችሎታ በታሪክ ውስጥ የተጫወተውን ጠቃሚ ሚና እና አሁናዊ አጠቃቀሙን ሰዎች እንዲረዱ ለማድረግ ያለመ ነው። ተልዕኮው ዓውደ ርዕዮች እና ሌሎች የመማሪያ ልምዶችን መፍጠር ሲሆን፤ ይህም በስለላ እና በዕውቀት ጥላ ዓለም ላይ ብርሃን የሚፈነጥቅ፣ እያንዳንዳችን በዙሪያችን ካለው ውስብስብ ዓለም ጋር በወሳኝነት መስተጋብር እንዲኖረን ማስተማር ነው።

ሙዚየሙ በስብስቡ ከያዛቸውና ለሕዝብ እይታ ከበቁ አስደናቂ ቅርሶች መካከል በዘመነ ቀዝቃዛው ጦርነት በቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት የስለላ ቡድን (KJB) ሴት ሰላዮች ጥቅም ላይ የዋለውና “ሞትን መሳሚያ” Kiss of Death የተባለው የረቀቀ የሊፕስቲክ ሽጉጥ ይጠቀሳል።

የስለላ ሙዚየሙ በትይዕንቱ ‘ኦፕሬሽን ስፓይ’ የተሰኘ መስተጋብራዊ ትዕይንትን ጨምሮ በተለያዩ ዘውጎች የተከፈለ ሲሆን፤ ጎብኚዎችም የምስጢር የስለላ ወኪሎችን ሚና በመውሰድ በአንድ ሠዓት ውስጥ በስለላ ሚና እንዲሳተፉ ዕድል ይፈጥራል።

ይህ ሙዚየም ምስጢራዊነት በዜጎች ነፃነት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ፣ የቴክኖሎጂ ሚና በስለላ ስራ ላይ ስለሚኖረው ለውጥ እና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ሌሎች ጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮችን ለመዳሰስ ተጨባጭ እና ፖለቲካዊ መድረክ ሆኖ ያገለግላል።

ታላላቅ ተመራማሪዎች ሲመክሩ “ለሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ያለው ሰው በዓለም ላይ ካሉት በርካታ የሣይንስ ሙዚየሞች አንዱን መጎብኘት ይኖርበታል” ይላሉ። ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ የሚመጣ ማንኛውም ጎብኚ ደግሞ የሣይንስ ዝንባሌ ኖረውም አልኖረውም የኢትዮጵያን የጥበብና የሣይንስ ማዕከል መጎብኘት ግድ ይለዋል። ምክንያቱም ሣይንስን ከጥበብ ያቆራኘ ድንቅ ኢትዮጵያዊም አፍሪካዊም ሙዚየም ነውና።



32

ኢኮኖሚ

…የዳቦ ቅርጫት



33

በዓለም ንግድ ከተጀመረ ብዙ ዘመናት ተቆጥረዋል። የንግድ ሂደቱ ይከናወን የነበረው አሁን እንዳለው በዘመናዊ መንገድ አይደለም። ይልቁንም አንዱን ምርት በሌላ በመለዋወጥ፤ አሞሌ ጨውን እና የተለያዩ እቃዎችን እንደ ምርት መለዋወጫነት በመጠቀም፣ ከዛም ገንዘብ እና ሳንቲም በማተም በገንዘቡ አማካኝነት አንዱ ያለውን ለሌላው መለዋወጥ ተጀመረ። ንግድ ሲጀመር በብዛት ለገበያ ይቀርቡ እና ይሸመቱ የነበረው የግብርና ውጤቶች ናቸው። ከሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ባለው ጊዜ የምግብ እና የግብርና ውጤቶች ላይ የሚካሄደው ንግድ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። የግብርና ውጤቶች የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ አገሮችም ቁጥር በዛው ልክ እየጨመረ ነው። ይህ እድገት እንዲመጣ ካስቻሉት ምክንያቶች ውስጥ ሉላዊነት (globalization) ይጠቀሳል። ሉላዊነት የዓለም አገሮች እርስ በእርሳቸው የሚያደርጉትን ግንኙነት እና መስተጋብር ወደ ላቀ ደረጃ አድርሶታል። ከሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አንስቶ በምግብ እና የግብርና ውጤቶች ላይ የሚካሄደው ንግድ እየተስፋፋ መምጣት ዓለም እንድትቆራኝ አድርጓል።

…የዳቦ ቅርጫት በፍቅርተ ባልቻ



34

እ.ኤ.አ ከ1995 ዓ.ም በኋላ ባለው ዘመናዊ ኢኮኖሚ በርካቶቹ አገሮች ወጪ ንግድ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ ስለመምጣቱ Food and Agriculture Organization of the United Nations (The State of Ag- ricultural Commodity Markets) በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ 2022 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ሰነድ አስነብቧል። ሂደቱ ቀላል የሚሆነው በተለይ ያደገ ኢኮኖሚ ላላቸው አገሮች እንደሆነ በሰነዱ ተመላክቷል። አያይዞም በአንጻራዊ ተጠቃሚነት (compara- tive advantage) እና ምርታማነት ላይ ያደጉት እና በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ሰፊ ልዩነት መኖሩን ጽፏል። ቴክኖሎጂ ሦስት አራተኛውን ምርት ለማሳደግ አስተዋጽኦ እንዳለው ይኸው ሰነድ ጠቅሶ የግብርና ውጤቶች ምርታማነት ላይ ባደጉት እና በማደግ ላይ ባሉት አገሮች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ ነው ያመላከተው። የኢትዮጵያ አቅም እና የጀመረችው አዲስ መንገድ እ.ኤ.አ. በ2050 ዓ.ም የዓለም ሕዝብ ብዛት 10 ቢሊዮን እንደሚደርስ እየተነገረ ሲሆን፤ እድገቱ በ2013 ከነበረው የግብርና ውጤቶች ፍላጎት አኳያ 50 በመቶ ጭማሪ እንዲያመጣ የሚያስገድድ መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያመላክቱት። በአደጉት አገሮች ከግብርና ምርቶች መካከል ስጋ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ በብዛት የሚጠቀሙ ሲሆን፤ በማደግ ላይ ያሉ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በተቃራኒው ሰብሎችን በስፋት ይመገባሉ። የሕዝብ ብዛት መጨመር እና የኢኮኖሚ እድገት በኢኮኖሚው ላይ መዋቅራዊ ለውጥ ያስከትላሉ። ዝቅተኛ ገቢ ወይም ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባላቸው አገሮች ግብይት ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው እና እያንዳንዱ ቤተሰብ ለምግብ ከሚያወጣው ወጪ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል እህል ነው። በኢትዮጵያ ከሚታረሰው መሬት ውስጥ 75 በመቶው ያህሉ እህል እንደሚዘራበት የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት መረጃ ያሳያል። የአፍሪካን ቀጣይ እጣ ፈንታ የሰመረ ለማድረግ ቁልፉ ያለው በግብርና ላይ ነው። በዓለም መታረስ ከሚችል መሬት ውስጥ አብዛኛው በአህጉሪቷ ይገኛል። ከሃምሳ በመቶው በላይ የሚሆነው ሕዝብ በግብርና መስክ የተሰማራ ከመሆኑም በላይ ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው አጠቃላይ ምርት (Gross Domestic Product) ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ሆኖም አፍሪካ የምታመርተው ዝቅተኛ እና እሴት ያልታከለበት

ነው። ”መስኩ መዋቅራዊ ለውጥ (struc- tural transformation) ማድረግ እንዲችል መስራት ይጠይቃል።” በሚል የስንዴ ምርትና ገበያ በኢትዮጵያ (Wheat production and marketing in Ethiopia) በሚል ርዕስ 17 Jun 2020 በCogent Food & Agriculture ጆርናል ላይ የታተመ ጥናት ያመለክታል። አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች ስንዴን የሚያመርቱት ለራሳቸው ፍጆታ ለማዋል አልያም ለመሸጥ ነው። የምርቱ እና የሽያጩ መጠን ከአገር አገር የተለያየ ነው። ኢትዮጵያ ለስንዴ ከምታውለው የእርሻ መሬት ስፋት እና የምርት መጠን አኳያ በአፍሪካ የምትጠቀስ መሆኗን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ገልጿል። ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች በስንዴ አምራችነቷ ቀዳሚ ናት። ለስንዴ ልማት የዋለው መሬት ከጤፍ፣ በቆሎ እና ማሽላ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ Cogent Food & Agriculture ጆርናል አገልግሎቱን ዋቢ በማድረግ ጠቅሷል። “ጤፍ ከጠቅላላው የእህል ምርቶች ከፍተኛውን የሚታረስ መሬት የሚሸፍን ሲሆን፤ ከጠቅላላው የታረሰ መሬት 29 ነጥብ 5 በመቶ፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የእህል ምርት 19 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻን ይጋራል። ለበቆሎ ምርት የዋለው እርሻ መሬት በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን፤ ከጠቅላላው እርሻ መሬትም 20 ነጥብ 8 በመቶ ሽፋን አለው። የበቆሎ ምርት የአገራችንን ጠቅላላ እህል ምርት ሲሶውን የሚጋራ በመሆኑ በሕብረተሰቡ የምግብ አቅርቦት ላይ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው። ማሽላ የእርሻ መሬትን 18 ነጥብ 5 በመቶ የሚጋራ ሲሆን፤ ከጠቅላላው የሰብል ምርት 19 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ አለው። ባለፉት ዓመታትም በማሽላ የተሸፈነው መሬት በየዓመቱ በ1 ነጥብ 71 በመቶ ሲያድግ ምርቱ በ3 ነጥብ 11 በመቶ እንዲሁም ምርታማነቱ በ1 ነጥብ 37 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ገብስ ከሚታረሰው መሬት 9 ነጥብ 3 በመቶ እንዲሁም ከጠቅላላ እህል ምርት 7 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ አለው። በገብስ የሚሸፈነው መሬት በየዓመቱ በ0 ነጥብ 57 በመቶ ምርት በ2 ነጥብ 19 በመቶ እንዲሁም ምርታማነቱ በ1 ነጥብ 62 በመቶ በማደግ ላይ ነው።” ሲል የሚያብራራው የግብርና እና የገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ ተግዳሮቶቹ፣ አበረታች ሁኔታዎች እና አስፈላጊ የማሻሻያ እርምጃዎችን አስመልክቶ እ.ኤ.አ 2020 ዓ.ም በዶ/ር ጌታቸው ዲሪባ የተዘጋጀው ሰነድ ነው። ይኸው ሰነድ ባለፉት 38 ዓመታት ከ1972 እስከ 2010 የታረሰ መሬት ሽፋን፣ ጠቅላላ ምርትና የምርት መጠን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተመላክቷል። በአገራችን



35



36

ያለውን የስንዴ ምርት ፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው የጠቅላላውን የአገር ውስጥ እህል ምርት ዘጠኝ በመቶ ድርሻ ያለው ስንዴ ከውጭ በየዓመቱ ማስገባት ግዴታ ስለመሆኑም ዶ/ር ጌታቸው በጥናታቸው ያመላከቱት ነጥብ ነው። ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው። Cogent Food & Agriculture ጆርናል ላይ የታተመው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው በአጠቃላይ ግብርና በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ድርሻ (GDP) 40 በመቶ ነው። የወጪ ንግዱን 80 በመቶ ሲይዝ፣ በአገሪቱ በስራ ላይ ካለው የሰው ኃብት ውስጥ 75 በመቶው የተሰማራው በግብርና መስክ ነው። በአገራችን 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን የስንዴ አምራች አርሶ አደሮች መኖራቸውን ከእነዚህም ውስጥ 78 በመቶው በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እንደሚገኙ የዓለም ባንክ መረጃ ያስረዳል። ሰፋፊ (large-scale commercial) እርሻዎች ላይ የተሰማሩት አምስት በመቶው ብቻ ሲሆኑ፤ የተቀሩት በአነስተኛ ማሳ (Small-scale) በሆነ ደረጃ የሚሰሩ መሆናቸውን ሰነዶች ያመላክታሉ። ከላይ በተጠቀሰው ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት እንደሚያሳየው፤ በኢትዮጵያ አንድ ቤተሰብ ለምግብ ከሚያወጣው ወጪ ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነውን እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ገብስ ያሉትን ለመግዛት ያውላል፤ በአገሪቱ

ከሚታረሰው መሬት ውስጥ ሦስት አራተኛው በእነዚህ ሰብል እህሎች የሚሸፈን ነው። ኢትዮጵያ ለግብርና ስራዎች ተስማሚ የሆነ መሬት፣ የአየር ንብረት የታደለች አገር ናት። ከሕዝቧም መካከል አብዛኛው ወጣት ኃይል ነው። ሆኖም ይህን ተፈጥሮ የቸራትን ጸጋዋን እና የሰው ሀብቷን አስተባብራ በመስራት የፈረጠመ ኢኮኖሚ ለመገንባት አልሆነላትም። በዚህ ረገድ ለውጥ ማምጣት ይቻል ዘንድ አገሪቷ ያላትን ይህን አቅም በተደራጀ መልኩ በመጠቀም ፈርጀ ብዙ ጥቅም ለማግኘት በመንግሥት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል። በ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅዱ (2013 - 2022) የአምራች ዘርፎች የልማት ግቦችና ስትራቴጂዎች ተጠቅሰዋል። አዝዕርት፣ የእንስሳት ሀብት፣ ደን፣ የዓሣ ሀብት ትኩረት የሚደረግባቸው እንደሆኑም ተመላክቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት፣ ለሌሎች ዘመናዊ ዘርፎች በቂ ግብዓት ማቅረብ፣ ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ የሥራ ዕድል መፍጠር ከግብርናው ዘርፍ ይጠበቃል። የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ግብርና ቁልፍ ዘርፍ ነው። ይህም በመሆኑ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ነው። ወደ ውጭ በመላክ ለአገራችን የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ የግብርና ምርቶች ውስጥ

ቡና፣ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ይገኙበታል። ባለፉት አራት ዓመታት ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርትን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትኩረት አድርጋ ስትሠራ መቆየቷን የግብርና ሚኒስቴር ጠቅሷል። አገሪቱ ከአራት ዓመታት ወዲህ ልዩ ትኩረት ሰጥታ የሰራችበት የስንዴ ልማት ስራ አዲስ መንገድ ያበጀ ነው። … ለምን ወደ ውጭ ይላካል? አገሮች በተፈጥሮ የተቸሩትን ወይም እሴት የጨመሩባቸውን ምርቶች ወደተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይልካሉ። አገሮች ያላቸው የምርት መጠን ‘ምን ያህል ሲሆን ወደ ወጪ ንግድ (export) መግባት አለባቸው‘ የሚለው ግልጽ የሆነ መስመር የለውም። አገሮች ምርቶቻቸውን ለምን ወደ ውጭ ይልካሉ? ይህን በማድረጋቸው የሚያገኙትስ ጥቅም ምን ይሆን? የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የሚሰጡት ምላሽ “ከሌሎች አኳያ በአነስተኛ ዋጋ ማምረት የሚችሉትን ወደ ውጭ አገሮች በመላክ በአንጻሩ በውድ ዋጋ የሚያመርቱትን ከውጭ ማስገባት ተጠቃሚ ያደርጋል” የሚል ነው። ይህም ‘com- parative advantage’ ነው የሚሰኘው። ይህ አተያይ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉት አገሮች ያላቸውን አንጻራዊ ጥቅም በደንብ እንዲያጤኑ ይረዳል። የዓለም አገሮች ለሕዝቡ ፍጆታም ሆነ ለተለያዩ



37

ኢንዱስትሪዎች የሚውሉ ግብዓቶችን ሁሉ በአገር ውስጥ ምርት ማሟላት ስለማይችሉ የመግዛት እና የመሸጥ ሂደት ውስጥ ይገባሉ። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች በቂ ምርት ለማምረት የሚያስችላቸውን ግብዓት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ሲሉ ምርቶቻቸውን ሽጠው በጣም መሠረታዊ የሆኑትን እቃዎች ያስመጣሉ፤ ይህ አሰራር የተለመደ ነው። በመሰረታዊነት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን መድሃኒት፣ የደህንነት፣ የትምህርት፣ የአፈር ማዳበሪያ እና ሌሎች ግብዓቶችን የግድ ከውጭ አገሮች ማስመጣት ይኖርባቸዋል። ግብዓቶቹን ከውጭ የሚያስመጡት ደግሞ በዶላር ስለሆነ ዶላሩን የሚያገኙበትን መንገድ ማበጀት ይጠይቃቸዋል። የዶላር ፍላጎታቸውን ለማሟላት ያላቸው አንደኛውና ዋነኛው አማራጭ በአገር ውስጥ ያለውን ምርት ወደ ውጭ መላክ (export) ነው። የዓለም አገሮች የውጭ ምንዛሪ የሚያገኙበትን ስልት መቀየሳቸው ለኢኮኖሚያዊ ዕድገታቸው አዎንታዊ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ለዛም ነው “አገሮች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚልኩት የተትረፈረፈ ምርት ሲኖራቸው ብቻ አይደለም።” የሚባለው። “ሲተርፍ ወደ ውጭ አገሮች ይላካል” የሚል አተያይ አለመኖሩንም ነው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የሚገልጹት። አገሮች የሚያስፈልጓቸውን መሰረታዊ ግብዓቶች የሚገዙበትን የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ሲሉ ወደ ንግድ ሊገቡ ይችላሉ። አገራቱ የተገኘውን

ምንዛሪ ‘ለምን ዓላማ እና ተግባር አዋሉት?’ የሚለው ዋናው ጉዳይ ነው። እሴት በሚጨምሩ እና ለኢኮኖሚው እድገት አስተዋጽኦ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ እንዲውል መስራት ጠቃሚ ነው። አገሮች ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የሚልኩበት ሌላኛው ምክንያት ከዓለም አገሮች ጋር የፖለቲካ ትስስር ለመፍጠር ነው። ከዚህም የምንረዳው ወጪ ንግድ ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔም ጭምር እንደሆነ ነው። ለዚህ አንድ ማሳያ ብንመለከት ሩስያ እና ዩክሬይን ለዓለም አገሮች የግብርና ምርትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚያቀርቡ አገሮች መካከል ናቸው። ሩስያ ከዓለም አገሮች ጋር ጥብቅ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ነበራት። ሩስያ ከዩክሬይን ጋር ግጭት ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ምዕራባዊያኑ በርካታ ማዕቀቦችን ሲጥሉባት ተመልክተናል። ሩስያም በአጸፋው ከጎኔ ላልቆሙ አገሮች ‘ምርቶቼን አልክም‘ ማለቷ የዓለምን ኢኮኖሚ በእጅጉ ፈትኖታል። ስለሆነም ይህ የሩስያ አቋም ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሩስያ 32 ነጥብ 9 ሚሊዮን ቶን ስንዴ በማቅረብ ከዓለም አንደኛ ስትሆን፣ ከዓለም ገበያ 18 በመቶውን ድርሻ ይዛለች። ዩክሬይን በበኩሏ 20 ሚሊዮን ቶን ስንዴ በማቅረብ ከዓለም ገበያ 10 በመቶውን ድርሻ ትሸፍናለች። ወደ ተለያዩ የዓለም አገሮች ስንዴ፣ ገብስ እና ሌሎች የቅባት እህሎች ምርቶችን በመላክ በዓለም ገበያ ውስጥ 64 በመቶውን የያዙት ሁለቱ አገሮች ናቸው። በማደግ ላይ ላሉ በርካታ አገሮች ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡም መረጃዎቹ ያሳያሉ። ከእነዚህ ውስጥ አፍሪካ አንዷ ስትሆን፣ ኢትዮጵያም በርካታ መጠን ያለውን ስንዴ እና የአፈር ማዳበሪያ ታስገባለች። ኢትዮጵያ ስንዴን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ስታወጣ መቆየቷን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ይህን ወጪ ለማስቀረት እና በምግብ ራስን ለመቻል መንግሥት የተለያዩ አማራጮችን በማስቀመጥ ወደ እንቅስቃሴ ገብቷል። እንደመፍትሔ ከተቀመጡት እና ወደ ተግባር ከተለወጡት ውስጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማቱ ይጠቀሳል። በአፋር የተጀመረው የመስኖ ስንዴ ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ተስፋፍቷል። ስራውም፣ ምርታማነቱም በየዓመቱ እድገት እየታየበት መሆኑን መንግሥት እየገለጸ ነው። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ “ኢትዮጵያ ስንዴን ለማምረት የሚያስችል መሬት፣ ውሃ፣ የሰው ኃይል፣ እውቀት አላት። ስለዚህ ስንዴን

ወደ ውጭ መላካችን ከዚህ አኳያ ቢታይ መልካም ነው።” ብለዋል። የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው፤ ኢኮኖሚ በጣም ተለዋዋጭ (daynamic) እንደሆነ ጠቅሰው “የተመረተው ሁሉ ለአገር ውስጥ ፍጆታ መዋል የለበትም” ይላሉ። አያይዘውም ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ባለመረዳት የሚነሱ ሀሳቦች መኖራቸውን ያነሳሉ። “ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አልፋ የዓለም የዳቦ ቅርጫት መሆን የምትችል አገር ነች።” ሲሉ አጽንኦት የሚሰጡት። “በአቅማችን ብቻ እንደግ ካልን እንዳንሞት እንዳንሽር ሆነን መኖር እንችላለን። ኢኮኖሚያችን ትራንስፎርም በማድረግ ወደ ዘመናዊ መዋቅር ለማምጣት የውጭ ምንዛሪ ግድ ይለናል። ዛሬ ሁሉንም በልቶ ጨርሶ ማደር ወይስ ዛሬን ተቸግረን የውጭ ምንዛሪ አምጥተን ፋብሪካዎችን ገንብተን፣ እውቀት ወስደን ለልጆቻችን ጠንካራ ኢኮኖሚ እናስረክባለን የሚለው ነው ጥያቄ መሆን ያለበት።” ሲሉ ምርትን ወደ ውጭ መላክ ያለውን ፋይዳ ያስረዱት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ናቸው። መንግሥት የመጀመሪያ ምርጫው በአገር ውስጥ የተትረፈረፈ ምርት ኖሮ ዜጎች ማግኘት እንዲችሉ መስራት መሆኑን ሚኒስትሯ አመላክተዋል። “ምርቶቻችንን ወደ ውጭ መላካችን ለአገራችን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ወሳኝ ነው።” ሲሉ ፋይዳውን አብራርተዋል። ስለሆነም ምርት ወደ ውጭ የሚላከው “ከእኛ የተረፈውን ነው” የሚል ብቻ መሆን የለበትም። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ነዳጅ፣ የአፈር ማዳበሪያ፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ የትምህርት ቁሳቁሶች፣ መድሃኒት ይሸምታል። ስለዚህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በጣም መሰረታዊ የሆኑትን ግብዓቶች ለመግዛት የውጭ ምንዛሪ ያስፈልገዋል። ብስራት … የግብርና ሚኒስቴር ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት (Import substitution)፣ ለማስተዋወቅ (promotion)፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ዓይነት ለመጨመር (ex- port diversification) እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ሰብሎች በሚል ለይቶ በልዩ ትኩረት ለመስራት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ከአገራችን የሰብል ምርቶች ውስጥ አምስቱ (ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ ጤፍ፣ በቆሎ) 75 በመቶውን ይሸፍናሉ። ከእነዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ለመላክ



38

ያቀደችው ስንዴን ነው። የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር መለስ መኮንን እንደሚሉት፤ የስንዴ ልማቱ በሁለት ወቅቶች የሚከናወን ነው። የመኸሩ በመደበኛ የክረምት ወቅት የሚሰራው ሲሆን፤ የበጋው በመስኖ አማካኝነት የሚከናወን ነው። “የስንዴ ልማቱ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት በማድረግ ይጠይቃል። ማሳ ልየታ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት (ለባለሙያውም፣ ለአመራሩም፣ አርሶ አደሩም) ሰፊ ውይይቶች በየጊዜው ይካሄዳሉ። ግብዓቶችን በተለይም ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር እንዲቀርብ ክትትል እና ድጋፍ ይደረጋል። የመስኖ ግብዓቶች እና መሰረት ልማቶችን የማሟላት እና የመጠገን ተግባራት ይከናወናሉ።” ሲሉ ለስንዴ ልማቱ የተሰጠውን ልዩ ትኩረት እንዲሁም የሚደረገውን ክትትል እና እገዛ ያብራሩት ዶ/ር መለስ ናቸው። ስንዴን ወደ ውጭ ለመላክ እያንዳንዱ ክልል በእቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል። ኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ፤ የምርት ቦታዎችን በማስፋት፤ አገራዊ የስንዴ ምርት ፍላጎቷን ለማሳካት መቻሏም እየተነገረ ነው። ይህን አስመልክቶ ሚኒስትር ዲኤታው ሲገልጹ ”ስንዴን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ሰብሎች ስናለማ የመጀመሪያው ትኩረታችን ለአገር ውስጥ ፍጆታ ማዋል ነው። ከዛ አልፍ ሲል ለውጭ ገበያ ቀርበው ለአገር የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እንዲሆኑ ጭምር ታስቦ ነው የሚሰራው። ስለዚህ በተለይ ስንዴን በሚመለከት ዋና ዓላማችን አድርገን ስንሰራ የነበረው ‘ከውጭ የምናስገባውን ስንዴ ማስቀረት አለብን’ በሚል ነው። በአገር ውስጥ ምርት መተካት አለብን የሚል ዓላማ ይዘን ላለፉት አራት ዓመታት ሰርተናል። አሁን እሱን ማሳካት ችለናል።“ ነው ያሉት። ስንዴን ወጪ ንግድ በሚመለከት የግብርና ትልቁ ድርሻ ከግብዓት አቅርቦት፣ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ ምርትን ሰብስቦ ወደ ጎተራ እስከሚገባበት ድረስ ያለው ነው። በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት፣ እንዲሁም በሌሎች ዓለም አቀፍ ጫናዎች፣ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ በመሳሰሉት ችግሮች ምክንያት እንደአጠቃላይ በዓለም ላይ የስንዴ እጥረት ተከስቷል። ስለዚህ ይህን ዓለም አቀፍ ችግር እንደ አንድ መልካም አጋጣሚ መጠቀም ተገቢ ነው። የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ስንዴ ከውጭ የሚያስገቡ ናቸው። ለእነዚህ አገሮች በዋናነት የስንዴ ምርት ያቀርቡ የነበሩት ሩሲያና ዩክሬን ነበሩ። ምርቱ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮችን (በተለይ ጎረቤት አገሮችን) ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳንና ጅቡቲን ለገበያ መዳረሻነት ታሳቢ መደረጉን

የግብርና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወሳል። የወጪ ንግዱን ምርቶች በዓይነት፣ በመጠን፣ በጥራትና በገቢ የማሳደግ ኃላፊነት እና ስልጣን የተሰጠው የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ”ወደ ውጭ ገበያ የሚላከው የስንዴ ምርት ከአገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈ ነው“ ሲል መግለጹ አይዘነጋም። ሚኒስትሩ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ እንደሚሉት፤ ከዚህ እውነታ በተጻረረ ወደ ውጭ ገበያ መቅረቡ “የአገር ውስጥ ገበያ እንዳይረጋጋ ያደርጋል” በሚል እየቀረበ ያለው አስተያየት ተገቢ አይደለም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ በተሰራው አበረታች ተግባር እንዲህ ያለ ለውጥ በመገኘቱ ሁሉንም የሚያኮራ ስለመሆኑ አንስተዋል። የአገሪቷ ኢኮኖሚ እንዳይታመም እና የተስተካከለ የኢኮኖሚ ፍሰት እንዲኖር “የወጪ ንግድ መርህን መከተል አማራጭ የለውም። ይህንን መርህ ለመተግበር በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው” ብለዋል። ቀደም ሲል የዘንድሮውን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ባስጀመሩበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ገፅታዋን የሚለውጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ እንደምትገባ መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህም

መሰረት ኢትዮጵያ ስንዴን ወደ ውጭ የመላክ ተግባርን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በይፋ አስጀምራለች። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት የአገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዳላት ማረጋገጡን የብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ (የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም) ይፋ አድርጓል። የኮሚቴው አስተባባሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት በተረጅነት መቆየቷን ጠቅሰው፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ታሪኳን የሚቀይር የስንዴ ልማት ውስጥ መግባቷን ገልጸዋል። የኤክስፖርት ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው የአገራዊ የነፍስ ወከፍ ፍጆታና የአገሪቷን አጠቃላይ የምርት ሚዛን በማጥናት ከፍጆታ የሚተርፍ 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ወደ ውጭ መላክ እንደሚቻል ማረጋገጫ ሰጥቷል። ”ስንዴን ከእንግዲህ በኋላ ከውጭ አታስገባም የሚለው ራዕይ ለብዙዎች በቀላሉ የሚቀበሉት እና የሚዋጥላቸው አልሆነም፤ ደግሞ ኢትዮጵያ ከልመና ወጥታ አርሳ እራሷን አብልታ፣ ከዚህ አልፋ ለሌሎች አገሮች መሸጥ ይቻላታል የሚለው በሕዝባችን ብቻ ሳይሆን በርካታ አመራሮች ይህን ሀሳብ ተጋርተው ለመስራት



39

ተቸግረው ነበር።“ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጪ ንግዱ በተበሰረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። ”በእርሻ የማናውቀው ሶማሌ ክልል ሳይቀር ለማመን በሚቸግር ደረጃ በዘመናዊ መንገድ በማምረት ለመብላት ብቻ ሳይሆን ለመሸጥ የሚያበቃ ምርት ማየት እንድንችል አድርገዋል። ባሌ ላይ ያየነው የስንዴ ወጪ ንግድ ለኢትዮጵያ ማድረግ ከሚገባን ትንሹ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማ እና መሻት ያለባትን ከፍተኛ እዳ ማቃለል ነው።“ በማለት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጎረቤት አገሮች የሚሸጥ መሆኑንም አንስተዋል። የወጪ ንግዱን በማሳለጥ የኢትዮጵያን እዳ እናቃልላለን ሲሉም ፋይዳውን ጠቅሰዋል። የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፤ በስንዴ ልማት በቁጭትና ቁርጠኝነት በመስራት ኢትዮጵያን ከስንዴ ተመጽዋችነት ወደ ለውጭ ገበያ አቅራቢነት ማሸጋገር መቻሉን አንስተዋል።”የስንዴ ልማት ኢትዮጵያን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ትልቅ የስኬት መንገድ ነው።“ ሲሉ ነው የገለጹት። የስንዴ ወጪ ንግድ መጀመሩ ለሎጂስቲክስ የሚውለውን የውጭ ምንዛሪ ከማስቀረቱ ባሻገር ተጨማሪ ገቢ በማስገኘት ኢኮኖሚውን ያነቃቃል። ስንዴን በስፋት ማምረት ይቻላል የሚለው የአመራሩ ቁጭትና እንዲሁም በእውቀት ላይ የተመሰረተ የምርምር ተቋማትና የዘርፉ ባለሙያዎች ተነሳሽነት በአንድ ላይ የታየበት ኹነት ነው። ባለፉት የለውጥ ዓመታት በስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት የአመራሩን፣ የምርምር ተቋማትና የአምራቹን ቁጭትና ቁርጠኝነት ያሳየ ነው። ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በስንዴ ላይ ውጤት ስታስመዘግብ ከአመራሩና የዘርፉ ባለሙያዎች ባሻገር የአርሶ አደሩ ተሳትፎ የጎላ ነበር። የስንዴን ምርት ከአገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለው ስንዴን በእርዳታ እንጂ በሰብል ደረጃ አይቶት የማያውቀው ከፊል አርሶ አደር በፍላጎት መስራት በመቻሉ መሆኑን ነው የግብርና ሚኒስትሩ የሚናገሩት። ስለሆነም መንግሥት ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በአገር ውስጥ ምርት መተካቱ ይበል የሚያሰኝ ነው። የአገሪቷን ኢኮኖሚ ወደ ከፍታ ለመውሰድ በስንዴ ላይ የተገኘው ስኬት እና ልምድ ወደ ሌሎች ምርቶችም በማስፋት መስራት ይጠይቃል።

ማጠቃለያ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት እያደገ ቢመጣም ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አኳያ ሲታይ ዝቅተኛ ነው። “በአገር ውስጥ ያለው ፍላጎት መጨመር፣ ጠንካራ እና ተነሳሽነት ያላቸው አርሶ አደሮች መኖራቸው፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም መፈለጋቸው፣ ምርቱ ለተለያየ ጥቅም መዋሉ (diverse use value of wheat)፣ ለመስኖ የሚሆን ወንዝ መኖሩ፣ የፓስታ እና የመኮረኒ ፋብሪካዎች መቋቋም ስንዴን ለማምረት እና ለገበያ ለማቅረብ የሚያበረታቱ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው።” በማለት ነው ቀደም ሲል የጠቀስነው ጥናት ያብራራው። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በአገሪቷ በአርሶ አደሩ አማካኝነት በአነስተኛ መጠን ባለው ይዞታ (small-scale) የሚመረተው ስንዴ በሰፋፊ እርሻዎች (large-scale) ከሚመረተው መጠን በላይ እንደሆነ በጽሑፉ ተመላክቷል። ይህም በምርት እና ምርታማነት፣ በጥራት እና በዓለም አቀፍ የስንዴ ገበያ ላይ ኢትዮጵያ ለሚኖራት ተሳትፎ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው። ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ግብርና ወሳኝ እንደመሆኑ ዘመናዊ አሰራሮች በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል። በአርሶ እና አርብቶ አደሩ የሚከናወነውን የእርሻ ስራ ወደ ሰፋፊ (invest- ment large-scale Commercial) መለወጥ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ያስችላል። የዋጋ አለመረጋጋትን (unpredictabili- ty) ለመግታት ግልጽ የሆነ የፖሊሲ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና መረጃን ግልጽ ማድረግ (trans- parent information)፣ የግብርና ምርቶች ግብይት የሚከናወንበት የገበያ መረጃ ስርዓት ማበጀት፣ የህብረት ስራ ማህበራትን አቅም ማሻሻል፣ ከእቅድ ጀምሮ ተቀናጅቶ መስራት በስንዴ የገበያ እሴት ሰንሰለትን ለማሻሻል የሚረዱ ስልቶች መሆናቸውን የዓለም ባንክ ይመክራል። ከስንዴ ጋር በተያያዘ የሚከናወኑትን ተግባራት ስኬታማ ለማድረግ አንደኛ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ተከታታይነት ባለው መልኩ ማከናወን ይጠይቃል። አርሶ አደሩ ባለው አነስተኛ መሬት ላይ የተሻለ ምርት ማግኘት የሚችልበትን ስልት ማስገንዘብ እና ለተግባራዊነቱም እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ተስማሚ የሆነ ፖሊሲ በመንደፍ በሰፋፊ እርሻዎች ላይ የሚያመርቱ ኢንቨስተሮችን ወደ መስኩ እንዲገቡ ማበረታታት ይገባል። ይህም በአፍሪካ ብሎም በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የስንዴ

ምርት ለማቅረብ ጠቃሚ ነው። ምርቱን ከገበያው ጋር ለማገናኘት እና የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር የሚረዱ እንደመንገድ እና ቴሌኮሚኒኬሽን ያሉ መሰረተ ልማቶችን ማሟላትም ለስራው ስኬታማነት ወሳኝ ነው። ምርት እና ምርታማነትን በመጨመር ለአገር ውስጥ ገበያም ሆነ ለውጭ ለማቅረብ የሚከናወነው ተግባር ለማንም የሚተው እና የተወሰነ ሰው ወይም ተቋም ድርሻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው። ”አገር እንወዳለን፣ ለአገራችን እንሰራለን እስካልን ድረስ ባለን አቅም፣ በሀሳባችን፣ በአቅማችን፣ በእውቀታችን ማገዝ አለብን።“ የሚለው መልዕክት ዶ/ር መለስ መኮንን ነው። በየደረጃው ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር፣ ባለሙያ እና አርሶ አደር በስንዴ ራስን የመቻልና በገቢው ፈጥኖ ለመለወጥ ያለው ፍላጎት ወሳኝ ነው። ስለሆነም ስራውን ከሉዓላዊነት ጋር በማያያዝ ለስኬታማነቱ መትጋት ያስፈልጋል። የስንዴ ወጪ ንግድ ለማስቀጠል እና በመስኩ በሚሰራው ስራ ስኬታማ ለመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው የስንዴ ምርት ለገበያ ለማቅረብ መንቀሳቀስ ይጠይቃል። ለዚህም እንዲረዳ “ስንዴ ጥራቱን ጠብቋል” የሚባለው ምን ሲያሟላ እንደሆነ በመተንተን የጥራት ደረጃ (Quality Stan- dard) ለማውጣት ብሎም ከምርት ስብሰባ እስከ ማሸጊያ እና ማጓጓዣ ያሉትን ሂደቶች በምን መልኩ ማከናወን እንደሚባ ግልጽ የሆነ አሰራር እና የሕግ ማዕቀፍ ማበጀቱ ጠቃሚ ነው። የገበያው እሴት ሰንሰለት በምን መንገድ እየተመራ እንደሆነ እና ምን መልክ ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶ መንቀሳቀስ የመንግሥት የቤት ስራ ነው። ኢትዮጵያ አንጻራዊ ተጠቃሚ የምትሆንበትን ምርት በአገር ውስጥ ማምረት፣ በተመሳሳይ አንጻራዊ ተጠቃሚ የማትሆንባቸውን ከሌሎች አገሮች ነው መግዛት ያለባት። ስለሆነም ኢትዮጵያ ”በአገር ውስጥ ለማምረት የምታወጣው ዋጋ ከውጭ አገር ከምታመጣበት የበለጠ ከሆነ ከውጭ ነው ማስመጣት ያለባት“ የሚል አቅጣጫ አስቀምጦ ወደ ስራ መለወጥ ያስፈልጋል። ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ገንዘብ ለትምህርት፣ ለመሰረተ ልማት ስለመዋሉ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ጊዜ ሳይሰጡ የእርምት እርምጃ መውሰዱ የአገሪቷን ኢኮኖሚ በቀናው ጎዳና እንዲጓዝ ለማስቻል ወሳኝ ነው።



40

ወርቃማ ዕድል ወደ አዲስ ከፍታ

ፖለቲካ



41

ወርቃማ ዕድል ወደ አዲስ ከፍታ

ቁምልኝ አያሌው

“አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ እናደርጋታለን” በሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገለጹት ሃሳብ አዲስ አበባን የሚመጥን አደረጃጀት፣ የአሰራር ዘዬ እና የማኅበረሰብ ንቃት ተግባቦት የመፍጠር ራዕይ መኖሩን ያመላክታል።

መዲናዋ የአፍሪካዊያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሕዝቦች መናሪያ ነች። ይህቺን መዲና የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ የማድረግ ጽኑ ፍላጎት ስለመኖሩ ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ የተደረጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚያረጋግጡት እውነታ ነው። የከተማዋ አስተዳደርም ዕድሜ ጠገብ መንደሮችን መልሶ ለማልማት የጀመራቸው ተግባራት መጪውን ዘመን ያንጸባርቃሉ። ቀደም ባሉት ዓመታት ታጥረው ያለስራ የቆዩ ስፍራዎችን ወደ ልማት ለማስገባት እርምጃ መውሰድ ከጀመረም ሰነባብቷል። ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የተጀመሩ ተግባራት መልካም ውጤት እየታየባቸው ነው። እነዚህ ተግባራት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት መኖሩን ከማረጋገጥ ባሻገር አዲስ አበባ ስሟን ልትመስል የምትችልበት ወቅት ሩቅ ያለመሆኑን ያንጸባርቃሉ።



42

ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በከንቲባ ስትተዳደር የቆየችው አዲስ አበባ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዲፕሎማሲያዊ መዲና ናት። ብዝኃነትን በመላበስ ኢትዮጵያን ትወክላለች። ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ ትናንት የሚዘከርባት፣ ዛሬ ላይ ነገ የሚገነባባትና የመጪው ዘመን ዕጣ ፈንታ የሚወሰንባትም ናት። በመሆኑም ከተማዋ አገርን፣ አህጉርንና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብን የሚመጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመራ አገልግሎት ማቅረብ ይጠበቅባታል።

የዲፕሎማሲ ማኅበረሰቡን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በማከናወንና ዘመናዊነት የተላበሱ የአሰራር ሂደቶችን በመከተል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በተግባር ማረጋገጥ የከተማዋ የዕለት ተዕለት ተግባር ነው። ለዚህ ነው “የበርካታ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መናኸሪያ የሆነችውን አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ከፍታ አስጠብቆ ለማስቀጠል ምን መደረግ ይኖርበታል?” የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ግድ የሚለው።

በቅርቡ “አዲስ አበባን በአዲስ የዲፕሎማሲ ከፍታ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አማካኝነት መዲናዋ ላይ ተመክሯል። የከተማዋ ዕድገት ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታዋ ለዜጎቿ ብቻ ሳይሆን ለዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ ያለው አንድምታ ማጠንጠኛ ሃሳብ ሆነዋል። የመዲናዋን የዲፕሎማሲ፣ የመሰረተ ልማትና የለውጥ ስራዎች እና ቀጣይ አቅጣጫ የሚያመላክቱ የመነሻ ሃሳቦች ተዘክረዋል።

በዚሁ ጊዜ ነው “አዲስ አበባ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘችውን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ዕድል በማጎልበትና በማጽናት ለተሻለ ለውጥ ትተጋለች” በማለት ከተማዋ ለለውጥ እየሰራች መሆኑን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ ያሳወቁት።

ለዚህም “መዲናዋንም የአፍሪካ የብልጽግና ተምሣሌት ሆና ማየት” የሚል ራዕይ በመሰነቅ የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ፣ የአረንጓዴ አሻራና የመዝናኛ ስፋራ ልማትን ጨምሮ የቴክኖሎጂና የ“ስማርት ሲቲ” ግንባታ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት የመዲናዋን ነዋሪዎች የኑሮ ሁኔታ ያሻሻሉ በርካታ ግዙፍና ሰው ተኮር የልማት ተግባራት ተከናውነዋል።

አዲስ አበባን በለውጥ አስተሳሰብ ወደ አዲስ መለወጥ ለነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል። ዓለም

አቀፍ ደረጃን በተላበሰ መልኩ መታደሷና ዘመነኛ መሆኗ የኢትዮጵያ ኩራት፤ የአፍሪካ መከታነቷን ያረጋግጣል።

በዚሁ የምክክር መርሃ ግብር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተወካያቸው በአምባሳደር እሸቴ ጥላሁን በኩል ያስተላለፉት መልዕክት፤ አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እና መዲና ሆና ትቀጥል ዘንድ “ተከታታይ የአመራር ትውልዶች ጥበብ የተሞላበት የዲፕሎማሲ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል” በማለት መዲናዋ ለዲፕሎማሲ ከፍታ በትውልድ ቅብብሎሽ መስራቷን ያረጋግጣል።

በተከታታይ ዘመናት የኢትዮጵያ መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባዎችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊት ከተማ ሆና እንድትቀጥል ያደረጉ ተግባራትን ሲከውኑ መቆየታቸው እሙን ነው። ለአብነት ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተለያይቶ ከቆየ ከሶስት ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ግፊቶች የነበሩ ቢሆንም በተከናወነው ዲፕሎማሲያዊ ስራ የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ እንዲካሄድ ወስነው ጉባዔው ተካሂዷል። ይህ የአገራችንን የዲፕሎማሲ ከፍታ ከማሳየቱ ባሻገር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮቸ ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም፣

ለአፍሪካ ኅብረት እውን መሆን ያበረከተችውን አስተዋጽኦ እና የአፍሪካ ጉዳዮች በአፍሪካ እንዲታዩ ላላት የጸና መርህ ከፍ ያለ ዋጋ መሰጠቷን እንደሚያሳይ በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የገለጹበት መንገድ መዲናዋ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያላትን ፖለቲካዊ አቋም ያንጸባርቃል።

በኢትዮጵያ በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የውስጥ ጸጥታ ጉዳዮችንና አንዳንድ ችግሮችን እንደ ምክንያት በመጠቀም ተገዳዳሪ ኃይል ለመሆን የሚሹ እንዳሉ ባለፉት ዓመታት በግልጽ ማየት ተችሏል። የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ለራሳቸው ለመውሰድ የሚሞክሩም ብዙዎች ናቸው። ለዚህም ነው ከተማዋ ወቅቱን የሚዋጅ ዝግጅት ማድረግና መስራት የሚጠበቅባት። በተለይም አዲስ አበባን በጸጥታ፣ በመሰረተ ልማት፣ በአገልግሎት፣ በእንግዳ ተቀባይነት፣ በዘመናዊ አሰራር እና ሌሎች መስተንግዶዎች ተወዳዳሪነት በማሳደግ ተመራጭነቷን በማስቀጠል “የማይቋረጥና ኀብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ የሚጠይቅ ጉዳይ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ ያነሱትን ሃሳብ አጽንኦት ሰጥቶ መተግበር



43

ይገባል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የአመራር ለውጥ ቢኖርም አዲስ አበባ የአፍሪካ ከተማ ሆና እንድትቀጥል የማድረግን ተግባር ለአፍታም አይዘነጉትም። “አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና፣ የበርካታ ሚሲዮኖች መገኛ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች መቀመጫ ሆና እንድትቀጥል ድጋፍ አድርገዋል” ብለዋል።

አዲስ አበባን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተለያዩ ተግዳሮቶች ገጥመዋታል። በተለይም የአህጉሪቷ ዋና መዲና የማድረግ ጉዳይ፣ የተቀናቃኝ መብዛትና አፍራሽ ዘመቻ መካሄድ ፈተና ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። የአፍሪካም ሆነ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ መናኸሪያነቷን ለመገዳደርና ወደ ራሳቸው ለመውሰድ የሚያስቡ አገሮች የተለያዩ ተግባራት ያከናውናሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን በማጤን “ለአፍሪካ አገራት ሚሲዮኖች በነፃ የኤምባሲ መገንቢያ መሬት በመስጠት መልክ እየያዘ እንዲመጣ እያደረገ ይገኛል” በማለት ችግሩን ለመፍታት የተሄደበትን ርቀት ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ያመላከቱት። የከተማዋ አስተዳደር ለዲፕሎማቲክ ተቋማት

ግንባታ የሚውል መሬት እያመቻቸ ይገኛል። በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች መንገዶች በአፍሪካ አገራት ተሰይመዋል። የኤርፖርት ጉምሩክና የቪዛ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ እየተደረገ ይገኛል። ይህ ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ ለማምጣትና ኢትዮጵያ ከሌላው ዓለም የምትፈልገውን ግንኙነት ፍሬያማ ለማድረግ የሚበጅ ነው።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባን ውበት የሚያጎሉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። እስከ አሁን የዘለቀችበትን ከፍታና ዝናዋን ሳትለቅ፤ ታሪኳን አስጠብቃና ተመራጭነቷን ጠብቃ እንድትቀጥል የተለያዩ የልማት ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰፋፊ የመዳረሻ ስፍራዎች መገንባት ለከተማዋ ልዩ ሀብት መሆናቸው አይካድም። “ለአገልግሎት ክፍት የሆኑት የወዳጅነት፣ የአንድነት፣ የእንጦጦ ፓርኮች እና መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶች የመዲናዋን ጥራትና ውበት በማስጠበቅ ከፍተኛ ግምት ይሰጣቸዋል” በማለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በማረጋገጥ በሁሉም የገቢ ደረጃ ለሚገኙ ዜጎች ምቹና የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር የበጎ ፈቃደኞችን እውቀት፣ ጉልበት፣ ፈጠራ እና ሌሎች አቅሞች በማቀናጀት ዘመናዊ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ እና መሰል ፕሮጀክቶችም ተጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል።

የከተማዋን ዘመናዊነት ማረጋገጥ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ትስስር ማቀላጠፍ አስፈላጊ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራትን ስፍራ አስጠብቆ ለማስቀጠል በቴክኖሎጂ መዘመንና የአከታተም የአሠራር ይትባሃል እንደ ዋና ጉዳይ መያዝ አስፈላጊነትም አጠያያቂ አይደለም።

“የከተማዋን ዘመናዊነት በማሳደግ ቀጣይነት ያለውና ዘመኑን የሚዋጁ የአሰራር ማሻሻያዎችን መከተል ካልተቻለ የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ማስቀጠል አዳጋች ይሆናል።” በማለት ነው የገለጹት።

የአፍሪካ ከተሞች የኮንፈረንስ ቱሪዝምን መነሻ በማድረግ ተወዳዳሪነታቸውን በማጎልበት የሚሰጧቸውን መብትና ጥቅም በማሳደግ ተመራጭነትን መፍጠር ያስፈልጋል።



44

ከተማዋ ባለፉት ዓመታት የውስጥ ለውጥ ስታካሄድ መቆየቷ እውን ነው። ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ተወስነዋል። ውጤትም ተመዝግቧል። ለከተማዋ ዘመናዊነት እንደሚበጁ የታመነባቸው መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ ነው። ለዜጎችም ሆነ ለዲፕሎማቶችና ለውጭ አገር ሰዎች ምቹ ለማድረግ፣ የዘመናዊነት ገጽታ እንድትላበስ በባለሐብቶች እና በመንግሥት የሚከናወኑ ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል።

ከተማዋን ለማዘመን የሚከናወኑ ተግባራት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎቸን በማጤን መሆኑን የማረጋገጥ ጉዳይ የከተማዋ አስተዳደር ይሆናል። ዕድገቷን ሁሉን አቀፍ አድርጎ መስራት በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ማዕከልነት ይዛ የቆየችውን ስፍራ አስጠብቆ የመጓዝ አንድምታ ይኖረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደ አዲስ አበባ ዓይነት ያሉ ግዙፍ የዲፕሎማሲ ማዕከል ከተሞችም በውስጣቸው ታሪክ፣ ባሕል፣ አካባቢያዊነትን በጉያቸው አቅፈው ይዘዋል። አዲስ አበባም በውስጧ የያዘቻቸውን መነሻ መሰረቶች ታሳቢ በማድረግ “የዲፕሎማሲ ከተማነቷ ጸንቶ እንዲቀጥል ውብና ማራኪ እንድትሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል” ብለዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ በአካባቢዋ ካሉ ትንንሽ መንደሮችና ነዋሪዎች ጋር በመጣጣም ዕድገትና ተመራጭነቷን እንድታስቀጥል መስራት ያስፈልጋል። አዲስ አበባ ብቻዋን ደሴት ሆና ልትቀጥል፣ ልትኖርና ልትቆይ አይቻላትም። ከሌሎች ጋር ተጣጥሞ በመኖር ዕድገቷን ማስቀጠል ግድ ይላል።

ከተሞች ብዝኃነትን የሚያስተናግዱ ናቸው። ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ ዜጎች የሚኖሩበት፤ አገር አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ባህሪ ያለው መስተጋብር ሰፊና ብዝኃ ተሳትፎና አተያይ የሚገኝበት ነው። የሃይማኖት፣ የባህል፣ የማንነት፣ የቋንቋ ብዝኃነት መገለጫዎች የሚስተዋሉት በከተማ ውስጥ ነው። “አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ጅግጅጋን ጨምሮ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ብዙ ዓይነት የኅብረተሰብ ክፍሎችን አቅፈው በመያዝ የብዝኃ ማንነት መገለጫ ናቸው” የሚለው የዲያቆን ዳንኤል ገለጻም የሚያንጸባርቀው ይህንኑ እውነት ነው።

ዓለም አቀፋዊ ባህሪን በጉልህ ማንጸባረቅ የሚጠበቅባት አዲስ አበባ፤ አህጉራዊ ስሜትን ማሳየት ግድ ይላታል። ይህም ሆኖ ግን አገራዊ ማንነትን ሊያንጸባርቁ የሚችሉ፣ ብዝኃነትን ማጉላት የሚችሉ ባህሪያቷን ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሳየት እንደሚኖርባት የአደባባይ ምስጢር ነው። ዜጎች በአብሮ መኖር ያዳበሯቸው የከተሜነት ባህሪያትና የፈጠሯቸው የመስተጋብር ሥርዓቶች ለአንድነታቸው ማሰሪያ ድር ሊሆን ይገባል።

“መዲናዋን ከዓለም አቀፍ ከተሜነት ጋር ትጣጣማለች ወይ?” ሲሉ የጠየቁት ዲያቆን ዳንኤል፤ “አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ፣ ዋና ከተማችን ለሚሏት፣ ኢትዮጵያዊያን፣ የዲፕሎማሲ ከተማችን ለሚሉ፣ አፍሪካዊያን፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከልና መቀመጫ ናት፣ ልናርፍባት፣ ልንኖርባት፣ ልንሰራባት፣ በልማት መስክ ልንሰማራባት ይገባል’ ለሚሉ ዓለም አቀፋዊያን ዜጎች ሁሉ ምቹ መሆን ይኖርባታል” ብለዋል።

ለዚህም በመዲናዋ የአሰራር ህጎችን፣ የከተማ ማስተር ፕላኖችን፣ መሰረተ ልማቶችን፣ አስተሳሰቦችንና ሌሎች የልማት ስራዎች አካባቢያዊ፣ አገራዊና ዓለም አቀፋዊነትን ባሰናሰለ መልኩ አጣጥሞ መዝለቅ ይገባል። መዲናዋን በሚመለከት የሚወጡ ጽሁፎች፣ ስያሜዎች፣ የሚካሄዱ ክዋኔዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን የዘገባና የመርሃ ግብር ሽፋን ስራዎች በከተማዋ የሚኖሩ የውጭ አገራት ዜጎችን ጭምር ታሳቢ ያደረጉ መሆን ይኖርባቸዋል።

ከተማዋ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለማካሄድ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት ይኖርባታል። የሆቴሎች ብዛት እና የአገልግሎት ጥራት፣ የዘመናዊ ትራንስፖርት አቅርቦት፣ ብቃትና ክህሎት የተላበሰ አስተናጋጅ ከተማዋ ለምታደርገው ለውጥ አስፈላጊ ስለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም። የኮንፈረንስና የጤና ቱሪዝም ማካሄድ ለሚያስችሉ የለውጥ ስራዎች ትኩረት መስጠትም አስፈላጊ ነው።

አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስፖርታዊ፣ ትላልቅ ኮንቬንሽን እና ኤግዚቢሽን ስራዎችን ማከናወን የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር አስፈላጊነትን ትኩረት ሰጥተውታል። “ሰፊ ቁጥር ማስተናገድ የሚችል የትራንስፖርት ሥርዓት ማዘመን፣ ሠላም፣ ጸጥታና ደህንነት በማስጠበቅ መዲናዋን ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ የልማት ስራ ማከናወን



45

ሌላኛው ወሳኝ ጉዳይ ነው” ሲሉ ነው ያብራሩት።

ዜጎች ለአገራቸውም ሆነ ለከተማቸው አምባሳደሮች ናቸው። በሚሰጧቸው ቀልጣፋ አገልግሎቶች እንግዶችን በትህትና ተቀብለው ማስተናገዳቸው ባሕላቸውን ታሪካዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶቻቸውን ለማስተዋወቅ የሚያስችላቸው አንድ ጉዳይ ነው።

የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትሩ ዲያቆን ዳንኤል ለአብነት የታክሲ አሽከርካሪዎችን በማንሳት “የኢትዮጵያ ታክሲ ሾፌሮች በዓለም ላይ የዲፕሎማቲክ ማዕከል የሆነች ከተማ ዓለም አቀፍ አሽከርካሪዎቸ መሆናቸውን በኩራት መናገር ካልቻሉ ቀሪ ስራ እንዳለ ታሳቢ መደረግ ይኖርበታል” ነው ያሉት።

የአዲስ አበባን ዓለም አቀፋዊነት ታሳቢ በማድረግ በአኗኗር፣ በአሰራር ሥርዓት፣ በሆቴል፣ መስተንግዶ፣ በዘመናዊ ቢሮክራሲ ሊገለጽ የሚችል ትርጉም ያለው ስራ መስራት ያስፈልጋል። “በመዲናዋ በዓረብኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በስፓኒሽ እና በሌሎች ዓለም

አቀፍ ቋንቋዎች አገልግሎት ለሚሹ ዜጎች ምላሽ መስጠት የሚችሉ የሰለጠኑ ጉዳይ ፈፃሚዎች ሊኖሩ ይገባል” ብለዋል።

የተለያዩ አገሮች ኤምባሲዎች፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ማድረጋቸውን ያለቀለት ጉዳይ አድርጎ መውሰድ እንደማይገባም ነው ያመለከቱት። የዲፕሎማሲ ማዕከልነትን እንደ ላሊበላ፣ አክሱም፣ ጀጎል ግንብ፣ ጅማ ቤተ መንግስትና ሌሎች ቅርሶች ከአገር የማይወጣ የኢትዮጵያ ብቻ ሆኖ የሚቀር አድርጎ ማሰብ ተገቢነት የለውም።

“የመዲናዋን የኢትዮጵያዊያንና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት በመንከባከብ፣ የተሻለ ስራ በመስራት በታሪክ አጋጣሚ የተገኘው ወርቃማ ዕድል ሊታጣ እንደሚችል ታሳቢ አድርጎ መስራት ያስፈልጋል” በማለት የከተማዋ አስተዳደርና ነዋሪዎቿ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው ነው የተናገሩት።

የዓለም ተወዳዳሪነት እያደገ መምጣቱ የዜጎች

እና የተቋማትን የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት በመወጣት ተወዳዳሪነትን ማጎልበት የሚያስችል ውጤታማ ስራ ማከናወን ይጠይቃል። “አዲስ አበባ ያላትን የታሪካዊነትና የተወዳዳሪነት ዕድሎች በመጠቀም ለዲፕሎማሲ ከፍታዋ ዕድገት ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል” የሚሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እድሪስ ናቸው።

የከተማ ዲፕሎማሲ ከቀደምቶቹ ተጨባጫዊነት /Realism/ እና ሃሳባዊነት /Idealism/ እሳቤዎች ወደ ተግባራዊነት /Pragmatisim/ እሳቤ ሽግግር እያደረገ መምጣቱን ዓለም አቀፍ ዝንባሌ መኖሩን ዶክተር መሀመድ አንስተዋል። መንግስታትም ከተሞቻቸው ያላቸውን ዕድል ታሳቢ በማድረግ የዲፕሎማሲ ማዕከል እንዲሆኑላቸው ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል ውጤታማ ስራ ሲያከናውኑ እንደሚስተዋል በመጥቀስ።

ከተሞች በሁሉም ዓይነት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ጉዳዮች ላይ አይተኬ ሚና ይጫወታሉ። ብዙዎቹ



46

የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች የከተሞች ግንኙነቶች በሚባል ደረጃ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ሚና አላቸው። “ከተሞች በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚጫወቱት ሚናም እጅግ ሙያዊ እየሆነ መጥቷል። ሙያዊ ተወዳዳሪነትም ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ ነው” ሲሉ ነው ያብራሩት።

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የማስዋብና መዲናዋን የማደስ ተግባራትም እንደሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ከተሞች ሁሉ ማደግ የሚጠበቅበት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ከተሞች ትልቁን የኢኮኖሚ ሥርዓት በማንቀሳቀስ የከተሜነት ዕድገትና ለውጥ እያሳዩ መጥተዋል።

እንደ ዶክተር መሀመድ ገለጻ፤ እ.አ.አ በ2050 ሰባ ከመቶ የሚሆነው የዓለም ማኅበረሰብ “ከተማ ላይ ይኖራል” ተብሎ ይጠበቃል። በአህጉረ አፍሪካም እ.አ.አ በ2030 ከ760 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በከተማ ውስጥ እንደሚኖር ነው የተተነበየው። በአህጉሪቷ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የሚኖርባቸው ትላልቅ ከተሞች እየተፈጠሩ ይሄዳሉ።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናም ተመሳሳይነት ያለው የከተሜነት ዕድገትና ፍላጎት እየጨመረ መጥቷል። የአህጉሪቷን ቀጣይ ዕጣ ፋንታ የመወሰን አቅም ያላቸው ከተሞች እየተፈጠሩም ይመጣሉ። የአፍሪካ ሕብረት በ2016 አጀንዳ “የምንመኛት አፍሪካ” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ

የአህጉሪቷ ከተሞችና ሌሎች የሕዝብ መኖሪያ ስፍራዎች የኢኮኖሚ መናኸሪያ በማድረግ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች ያላቸው እንዲሆኑ መስራት ተቀዳሚ ራዕዩ አድርጓል። ይህ ራዕይ አዲስ አበባንም ይመለከታል። ለዚህ ደግሞ ጠንካራ ዝግጅት ያስፈልጋል። “ከተሞችን ኅብረቱ ባስቀመጠው ራዕይ መነሻነት ገንብቶ ማሳየት ይጠይቃል” በማለት ነው ሃባቸውን ያጋሩት።

የከተሞች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና ቁርኝት ከደህንነት፣ ከኢኮኖሚ፣ ከባህል፣ ከተቋማት ግንባታና ከውክልና አኳያ የሚታይ ነው። ይህ ከተነሳ ኢትዮጵያ ምን ያህል ትርጉም ያለው ክስተቶችን በስኬት አስተናገደች? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው።

እ.አ.አ በ2019 የፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ የዓለምን ቅርጽ መቀየር የቻሉ ከ400 በላይ መድረኮችን ማስተናገዷን አብነት ጠቅሰዋል። የበርካታ አገራት መሪዎችና ሌሎች የስራ ኃላፊዎችን አስተናግዳለች፤ በዚህም ስኬታማ ሆናለች።

ከዚህ አኳያ “አዲስ አበባ ምን ያህል አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮችን በማስተናገድ ተጠቃሚ ሆነች?” የሚለውን ጥያቄ አንስቶ መገምገም እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት። በእህትማማችነት ስምምነት ከ22 በላይ ከተሞች ጋር ፊርማ አላት። “ኢትዮጵያ ካላት ባህልና መስተንግዶ አኳያም ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ

ሁነቶችን ማስተናገድ የሚችሉ መዲናዋን የማስዋብና ትላልቅ የልማት ስራዎች አዲስ አበባን ሳቢ የማድረግ ዕድል አለን”።

በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተቀየረ የመጣውን የዲፕሎማሲ መስመር ለአዲሱ ትውልድ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የአሰራር ሥርዓት መቀየስ አስፈላጊነት አፅንኦት የሰጡት ጉዳይ ነው። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ የአፍሪካ አገሮች ከቅኝ ግዛት እንዲወጡ የከፈለችው መስዋዕትነት ከፍተኛ ነው። በተለይም የነፃነት ታጋዮችን በማሰልጠን እና የስነ ልቦና እና ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ ብዙ ከፍላለች። ይህን ትውልዱ ማወቅ እና መገንዘብ ይኖርበታል።

ዶክተሩ “የአህጉሪቷን ቀጣይ ትውልድ የማስተማር ኃላፊነት በብቃት መወጣት እየጨመረ የመጣውን የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት ጭምር ማስተናገድ የሚቻልበትን መርህ መከተል ያስፈልጋል” በማለት ነው ቀጣይ አቅጣጫ ምን መሆን እንዳለበት ያስረዱት።

አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ምልክትና መገለጫ ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ አቅምን ወደ ኢኮኖሚ፣ ባሕላዊና ማኅበራዊ ግንኙነት መቀየር ያስፈልጋል። የአዲስ አበባን ተመራጭነት በማስቀጠል የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ያለውን ጥቅምና ጫና ታሳቢ ያደረገ የልማት ስራ ማከናወን ጊዜው የሚጠይቀው መሰረታዊ ጉዳይ ነው።



47

እንደ ዶክተር መሀመድ ገለጻ፤ ከውጭ የሚመጡ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት የተሻለ ትምህርት ቤት፣ የገበያ ማዕከላት፣ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ የመዝናኛ ቦታዎችና ሁነቶች ያስፈልጓቸዋል። ምቹ የጤና፣ የባንክ አገልግሎቶች የሚሰጡ ተቋማትን ማስፋፋትም ይጠይቃል።

በአዲስ አበባ የሚሰጡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን የተሳለጡና ዘመነኛ በማድረግ የዓለም አቀፍ ማዕከልነቷን አስጠብቆ ማስቀጠል ይገባል። የሆቴል፣ የመዝናኛ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮች ማሟላት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ ሆኖ የሚታይ አይደለም።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር የሕንፃ ግንባታና የከተማ ፕላን ኢንስቲትዩት መምህሩ ዶክተር ዘገየ ቸርነት እንደሚሉት፤ ከተሞች የሰው ልጆች ውስብስብ የእጅ ስራ ውጤት ናቸው። ከተማ እንደ ቁስ ሳይሆን እንደ ህዋስ የሚታይ ውስብስብ ጉዳዮችን በውስጡ የያዘ ነው። “ከተሞች ይወለዳሉ፣ ዕድል ከተሰጣቸውም ያድጋሉ፣ ይፋፋሉ ይቆያሉ ብዙ ሺህ ዘመናትን ያሳልፋሉ”።

እንደ ዶክተር ዘገየ ገለጻ፤ አዲስ አበባ ተጠንስሳ፤ ተወልዳ እያደገች የምትገኝ ጎረምሳ ከተማ ናት። መዲናዋ ያሳለፈቻቸው የ140 ዓመት ዕድሜ ጊዜያትም በከተማ ዕድሜ ስሌት ሲለካም

ወጣትነትን ነው የሚያንጸባርቀው። ይህም በከተማ ዕድሜ ስሌት ሲታይ ገና የልጅነት ዕድሜ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ያረጋግጣል።

ከሰው ልጆች አጠቃላይ የሥልጣኔ ጉዞ አኳያ ከተሞች መካከለኛ ቦታን ይወስዳሉ። የሰው ልጆችን ስልጣኔ ከከተማ ውጭ ማየት አይቻልም። የሰው ልጅ አብሮ እንዲኖር የተፈጠረ ነው። ለዚህም “የሰው ልጅ ከተሞችን ለአብሮነት መድረኩ ሲል በጋራ ሆኖ በጋራ ለመኖር የፈጠራቸው ናቸው” ሲሉ ነው የገለጹት። አብሮነት እና በጋራ መኖርም ስልጣኔ እንዲወለድ ያደረጉ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መነሻነት መዲናዋ በርካታ ብዝኃ ማንነቶችን አቅፋ በመያዝ የአብሮነትና በጋራ የመኖር መገለጫ ሆናለች።

ከተሞች ውስብስብ የግንኙነት መረብን የተላበሱ የጋራ መድረኮች ናቸው። የሰው ልጆች የሚኖሩባቸው የተለያዩ መስተጋብሮች ሚዛናቸውን በማስጠበቅ በመሞከር የሚንሳቀሱባቸው መድረኮች ናቸው። “ውስብስብ የሰው ልጆች የእጅ ስራ ውጤቶች ያሰኛቸዋል” ብለዋል። የአብሮነትና መስተጋብር ጠንካራ በመሆኑ ከተሞች የባህል፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የኃይማኖት እና የእውቀት መሰረቶችና ምንጮች ሆነው ይገኛሉ። ከተሞች ሰውንና ተፈጥሮን የሚያቆራኙ መረቦችም ናቸው።

አሁን ያለው የሰው ልጆች የስልጣኔ እምብርት ከተሞቹ ናቸው። የሰው ልጆች የወደፊት የአብሮነት ጉዞ መገለጫ ከተሞቹ ናቸው። ከተማ ስለሆነ ብቻ በልዩ ተዓምር የተስፋ ምድር ሊሆን አይችልም። የከተማን ዕድገትና ልማት በሃሳብ በመደገፍ መድረስ ከሚገባቸው የዕድገት ደረጃ እንዲደርሱ አበክሮ መስራት አስፈላጊ ነው። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሰው ልጅ የወደፊት ተስፋ የሚወሰነው በተሻለ የከተሞች አወቃቀር ሥርዓት ነው።

ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፈጣን የከተሜነት መስፋፋት የሕዝብ ቁጥር ዕድገት እየጨመረ እንዲመጣ አድርጎታል። እ.አ.አ. በ2050 የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በ100 ሚሊዮን ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። እዚህ ላይ አሁን ያለው የገጠር ሥርዓት እየጨመረ የሚሄደውን “የሕዝብ ቁጥር ማስተናገድ ይችላል ወይ?” የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ይሻል። “በሚቀጥሉት 25 ዓመታት የኢትዮጵያ ከተሞች ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የማስተናገድ ኃላፊነት አለባቸው። ለዚህም በየዓመቱ አዲስ አበባን የሚያክል ከተማ መገንባት ይጠበቅብናል” በማለት ቀጣዩ የከተሜነት ዘመን ተስፋና ተግዳሮት ይዞ እንደሚመጣ አመላካች ሀሳብ አቅርበዋል ዶክተር ዘገየ።

መዲናዋ አዲስ አበባም እየጨመረ የመጣውን የሕዝብ ቁጥርና የከተሜነት ፍላጎት እንድትሸከም መጠበቅ አስቸጋሪ መሆኑን ያመላከቱት። “ኢትዮጵያ ዝቅተኛ የከተማ ምጣኔ ያላት፤ ከፍተኛ የመከተም ሂደት የሚታይባት፤ በልዩ ሁኔታም ዝቅተኛ የከተሜነት ተሞክሮ ያላት አገር ናት” በማለት ነው የገለጹት። በተጨማሪም ብቁ የሆነ የሃሳብ፣ የፖሊሲ ዝግጅት፣ የጥናትና ምርምር ዝግጅት ማነስ ደካማ አገራዊ የከተሜነት ዝግጅት የሚስተዋልባት አገር አድርጓታል።

ዶክተር ዘገየ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ በከተማ ግንባታ ታሪክ መሰረታዊ ችግር ያጋጠሟቸውን አገራት ውጣ ውረድ ላለመድገም በፍጥነት እየከተመ የሚሄድና እየጨመረ የመጣን የሕዝብ ቁጥር ታሳቢ የሚያደርግ ዝግጅት ያስፈልጋታል። አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች እየታጨቀ የመጣውን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ታሳቢ ያደረገ የከተማ ግንባታና ልማት ስራን ይጠይቃል።

አዲስ አበባ ዋና ከተማ በመሆኗ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ በመጣው የከተሜነት ፍላጎት የስበት



48

ማዕከል ትሆናለች። ይህን ታሳቢ በማድረግ “መዲናዋ ከውስጥ ያለውን የፍላጎት ውጥረት ምላሽ ለመስጠት ራሷን እንደገና እንድታይ ይጠበቅባታል” ብለዋል።

መዲናዋም የፖለቲካ መድረክ እና አገሪቷ የኢኮኖሚ እምብርት ናት። ከተማዋ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ የባህል እና የእውቀት ማዕከልነት የሰጣትን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ዕድገቷን የሚያሳልጡ ስራዎችን መስራት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው።

እንደ ዶክተር ዘገየ ገለጻ፤ ጥሩ ከተማ ለሕዝብ ተጠቃሚነት ይተጋል። በአብሮነት መጠቀሚያና የጋራ ስፍራዎች ልማት ላይ ያተኩራል። የጋራ መጠቀሚያ ስፍራዎች ልማትና ሁኔታም የከተማ ጤንነትን ያመላክታል። “ከተሞችን ማስተዋወቅ የሚቻለው በህንፃ ግንባታ ብቻ ሳይሆን በሕዝብ የጋራ መጠቀሚያ መድረኮቻቸው ጭምር ነው”።

ከውሃና ከኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት በማይተናነስ መልኩ መንገዶች፣ የሰፈር ክፍት ቦታዎች፣ አደባባዮች እና መዝናኛ ፓርኮች የአብሮነት ሳሎን ቤቶች ናቸው። መልካም ከተማ ተወዳዳሪ፣ አዲስ ግኝት ፈጣሪ፣ ከከተሞች ጋር በትብብር የሚሰሩ ናቸው። አዲስ አበባም ባሕርዳርን ጨምሮ ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ጋር በትብብር መስራት ይጠበቅባታል።

ከተሞች ውስጥ የሚታጨቅን ሰፊ የሕዝብ ቁጥርና ኢንዱስትሪ ታሳቢ ያደረገ ጤናማና ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ ከተማ መፍጠር ትኩረት ይሻል። የተሻለ የከተማ ዲዛይንና መዋቅር በመዘርጋት ለሕዝቦቻቸው ምቹና ቆንጆ መሆን ይጠበቅባቸዋል። “አዲስ አበባ” የሚለውን ሃሳብም በመዋቅር እና ቅርጽ በህንፃዎች መዋቅርና አደባባዮች ሳቢና ማራኪነት ሊገለጽ በሚችል መልኩ ማልማት ያስፈልጋል። መልካም ከተሞች መልካም አስተዳደር አላቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፤ ኢትዮጵያ የተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብና የዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች መቀመጫ መሆኗን ያበቃለትና የላቀ ጉዳይ አድርጎ መውሰድ አይገባም።

የአዲስ አበባን የፖለቲካ ከፍታ ለማስቀጠል ኒው ዮርክም ሆነ ጄኔቭ፣ ብራስልስና አዲስ አበባ ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተመሳሳይ ባህሪ ስላላቸው ከፍታውን የሚመጥን ስራ ማከናወን ያስፈልጋል። እነዚህ ዓይነት ተቋማትና ድርጅቶች የተመቻቸ ሁኔታና የተረጋጋ የስራ አካባቢን የሚፈልጉ ናቸው። ይህን ማድረግ ያልቻለ ከተማ

“አንዴ ያገኘውን ዕድል አዝልቆ ያቆየዋል ማለት አይደለም” ሲሉ የጉዳዩን ትልቅነት አጉልተዋል።

ከዚህ ቀደም ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መናኸሪያ የነበሩ ነገር ግን አጋጣሚውን በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው ዕድሉን ያጡ መኖራቸውን አመላክተዋል። እንደ እነ ቪየና እና ለንደን ያሉ ከተሞች የነበራቸውን ከፍታ በእነ ዱባይና ሆንግኮንግ እየተነጠቁ መምጣታቸውን የጠቀሱት አምባሳደር መለስ፤ አዲስ አበባም መሰል ዕጣ ፋንታ ሊገጥማት እንደማይችል ዋስትና አለመኖሩን ነው ያሳሰቡት። በአፍሪካ እንደ ሩዋንዳዋ መዲና ኪጋሊ ዓይነት ከተሞች ወደ ትልቅ የኮንፈረንስ ቱሪዝምና የሳይንስ ማዕከልነት እየተቀየሩ መምጣታቸውን አብነት በመጥቀስ። እናም የተሻለ የከተማ ግንባታን በማሳለጥ አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን አስጠብቃ እንድትቀጥል ቀጣይነት ያለው ስራ ማከናወን ያስፈልጋል።

አምባሳደሩ፤ የአዲስ አበባን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ለማጽናትም ተቋማት፣ የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ያለባቸውን ድርብ ኃላፊነት በሚገባ መወጣት ይጠበቅባቸዋል። የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫውን አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ እንዲያደርግ በቀደምት መሪዎች ብርቱ ትግል ተደርጓል። በአሁኑ ወቅት የዲፕሎማሲ ማዕከልነትን ለመፎካከር ተቀናቃኝ እየበዛ መጥቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኒውዮርክ መኖር፤ የአውሮፓ ኅብረት ብራስልስ መኖር ለአሜሪካና ቤልጂየም ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ሁሉ “የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ አዲስ አበባ መሆኑ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕድል ነው። ሕብረቱ ለኢትዮጵያ የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ አስጠብቆ መጓዝ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

በመዲናዋ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ የተሻለ የቴሌኮሙዩኒኬሽን፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ የባንክ፣ የኤርፖርትና ጉምሩክ፣ ትምህርት ቤትና ጤና ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማቶችን ማሟላትም ይጠይቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም በተቻለው ሁሉ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ፣ የውጭ ተቋማትና ድርጅቶች ምቹነት እንዲሰማቸው ከሚመለከታቸው ተቋማትና አካላት ጋር በትብብር ይሰራል።

አዲስ አበባ የዲፕሎማቲክ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ሚና አላቸው። መዲናዋም በርካታ ቁጥር ያላቸው

የአገር ውስጥና የውጭ አገራት የመገናኛ አውታሮች ይኖራሉ። መገናኛ ብዙኃኑም ስለ ከተማዋ ታሪክ፣ አመሰራረት፣ ማንነትና የወደፊት ምኞትና መሻት አውቀውና ተገንዝበው መስራት ይኖርባቸዋል የሚሉት ደግሞ የአሃዱ ራዲዮና ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ናቸው።

አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን ይዛ እንድትቀጥል መገናኛ ብዙኃን ቅርጽ ይዘው መስራት ይኖርባቸዋል። የመዲናዋ የኋላ ታሪክ በአፍሪካዊያን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ ይፈጥራልና።

የአዲስ አበባን የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ለማሳየት “ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊያን ያበረከተቻቸውን አስተዋጽኦ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ሙያዊ ክህሎትን መሰረት ያደረገ የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ ያስፈልጋል” ይላል ጋዜጠኛ ጥበቡ። በመዲናዋ ከአፍሪካ ኅብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች በተጨማሪ ትላልቅ ዓለም አቀፍ የመገናኛ አውታሮች ዋና መቀመጫ እንድትሆን መስራትም ያስፈልጋል።

የባሕር-ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ፤ “የፌዴራል መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ሌሎች ግዙፍና ትላልቅ ከተሞች እንዲፈጠሩ ድጋፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል” የሚል አስተያየት አላቸው።

እንደ ባሕርዳር፣ ሐዋሳ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችን ትስስር በማጎልበት የዋና ከተማ አማራጭ ዕድል መፍጠር ያስፈልጋል። ደቡብ አፍሪካ እንደ ጆሀንስበርግ፣ ፕሪቶሪያ እና ኬፕታውን ያሉ ከተሞቿ ለሶስቱ የመንግስት አካላት ማዕከል ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። በኢትዮጵያም ይህን ልምድ በመውሰድ ከተሞች ተያይዘው እንዲያድጉ ማድረግ ተገቢ ነው።

አዲስ አበባ ከተማም እናት ከተማም ሆና በማገልገል ሌሎች የአገሪቷ ከተሞች ዕድገት እንዲያመጡ መስራት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። መዲናዋ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ማዕከል መሆኗ የሁሉም ዓይነት ትኩሳት መነሻ እንድትሆን እያደረጋት ይገኛል። አሁን ላይ አዲስ አበባ መጨነቅ የሚኖርባት “ከሌሎች ታላላቅ ዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር እንዴት ልወዳደር?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ነው።



49



50

መጪውን ዘመን በጥበብ ለመራመድ

መንገድ የቀየሰ - ዩኒቨርሲቲ

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልገሎት ትብብር የተዘጋጀ

ማህበራዊ



51

መጪውን ዘመን በጥበብ ለመራመድ

መንገድ የቀየሰ - ዩኒቨርሲቲ

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ንድፈ ሀሳብን ከተግባር አጣምሮ ትምህርት መስጠት ከጀመረ ግማሽ ክፍለ ዘመን አሳልፏል። ተማሪዎች በግብርና፣ በጤና፣ በቴክኖሎጂ ፣ በተፈጥሮ ሳይንስና በሌሎች ዘርፎች ላይ እውቀት የሚቀስሙት መጽሐፍ ላይ ከሰፈረ ንድፈ ሀሳብ ብቻ አይደለም፤ ከነባራዊው ዓለም ጋር በተሳሰረና በገቢር በተገለጠ መንገድ እንጂ።

ዩኒቨርስቲው በ11 ተማሪዎች የመማር ማስተማር ከጀመረበት፣ የምርምር እና የማኅበረሰብ አገልግሎትን ካከለበት ከ1946 ዓ.ም አንስቶ በርካታ ምሁራንን አፍርቷል። ከአገራቸው አልፈው በዓለምአቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸራቸውን ተመራማሪዎች ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው።

በተለይ በግብርና ዙሪያ የተለያዩ ምርምሮችን በማካሄድ ያገኘው ውጤትና ተሞክሮ ዩኒቨርሲቲውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደሪ ለመሆን የሚያስችሉት የመሰረት ድንጋዮች ናቸው። ለረጅም ዓመታት የሰጠው የማኅበረሰብ አገልግሎትም በአገር ደረጃ ቀዳሚና የማይተካ ሚናውን መጫወቱን ከመመስከር አልፎ መልካም ስሙን ከፍ የሚያደርግ አንጡራ ሀብቱ ነው።

በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቷ ተስፋፍቶ የበርካታ አርሶአደሮችን ህይወት የቀየረው የግብርና ኤክስቴሽን ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ በኩልም ግንባር ቀደምነቱን ይዟል። ተመራማሪዎቹ የአርሶ አደሩን ማሳ በማሳያነት በመጠቀም የተሻሻሉና ምርታማነታቸው አስተማማኝ የሆኑ የሰብል፣ የእንስሳትና

ጌታቸው ሠናይ



52

የአትክልት ዝርያዎችን በማግኘት ስኬታማ ስራ አከናውነዋል።

በግብርና፣ በእንስሳት ሀብትና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተመራቂ ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን በምርምር የተገኙ ውጤቶች ወደ ተግባር እንዲተረጎሙ፣ ተጠቃሚው ዘንድ በመድረስ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል። ለዚህ መነሻው የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ራዕይና የአገር የማደግና መበልጸግ ፍላጎት ናቸው።

በሐረማያ አካባቢና በዙሪያው የሚገኙ አርሶአደሮች ተጠቃሚ ሊሆኑባቸው የሚችሉ መስኮች በርካታ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ሕይወታቸውን ለማቅለል የሚያስችሉ የተለያዩ አገልግሎት ይሰጣቸዋል፤ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ያስተዋውቃቸዋል። የተሻለ የምርት ውጤት እንዲያገኙ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል። የተሻሻሉ የከብት ዝርያዎች፣ የዶሮ ዓይነቶች በማቅረብ፣ ምርጥ ዘር በመስጠት የተሻለ ውጤት እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ ዩኒቨርሲቲው አገሪቷ የምታካሂደውን የቴክኖሎጂ ሽግግር ከጅምሩም አግዟል። በግብርና ኤክስቴንሽን የጀመረው እንቅስቃሴ እያደገና እየሰፋ መጥቶ በዓይነትም በስፋትም ከፍ ብሏል። ጤናን ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ማከናወኑን ቀጥሏል ይላሉ።

ዩኒቨርሲቲው የምርምር ተግባራቱን የሚያከናውነው በለያቸው የትኩረት መስኮች ነው። ምርትና ምርታማነት ፣ የአካባቢና ተፈጥሮ ጥበቃ ፣ ጤና ከትኩረት መስኮች ውስጥ ይጠቀሳሉ። እነዚህ የትኩረት መስኮች በየጊዜው ይከለሳሉ። ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ይቀያየራሉ። ከዚህ አኳያ በየዓመቱ የምርምር ፍላጎቶች ይሰበሰባሉ። ከአካባቢው ማኅበረሰብ በተሰበሰበው ሀሳብ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጠው ችግር ይለያል። ተመራማሪዎች የምርምር ንድፈ ሀሳብ አስገብተውና በሂደት ተፈትሾ አብላጫ ያገኘው ስራውን ይጀምራል።

“በዚህ ሂደት ጥሩ ውጤቶችን እያገኘን ነው። በጣም የተዋጣለት ነው ባንልም የስንዴ፣ ኦቾሎኒ፣ ቦሎቄ፣ በቆሎ፣ ማሽላ የመሳሰሉትን ዝርያዎችን ያበረከተ ነው።” ያሉት ዶክተር ጀማል፤ የተገኙ መልካም ውጤቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በተቀናጀ መልኩ ለመስራት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው አጽንኦት የሰጡት።

ለአብነት በግብርና ማሰልጠኛ ዘርፍ ባለንበት አካባቢ ሰርቶ ማሳያዎች አሉ። ከ11 በላይ የምርምር ጣቢያዎች ይገኛሉ። አርሶአደሩ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳር ጋር የተቀራረበ ኢኮሎጂ ውስጥ ነው የሚገኘው። አዲስ ቴክኖሎጂ ሲገኝ ወደ አርሶአደሩ ማሳ በማቅረብ ሰርቶ ማሳያዎች ላይ ይታያል። ቴክኖሎጂዎች ወደ ግብርና ቢሮዎች በማስተላለፍ ወደ አርሶ አደሩ እንዲደርሱ ይደረጋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከስንዴ ምርት ጋር ተያይዞ አንድ የሚጨበጥ ተግባር ማከናወኑ እዚህ ላይ በአብነት መጥቀስ ይቻላል። የአካባቢውን አርሶአደር አስተባብሮ የዘር ብዜት ላይ መስራቱና ውጤት ማስመዝገቡ የተግባር ማሳያ ነው። አርሶአደሮች የመስኖ ስንዴ ዘር እንዲያመርቱ ተመራማሪዎች የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ስራቸውን እያከናወኑም ይገኛሉ።

“ይህ በዘላቂነት እንዲቀጥል ምን ተግዳሮቶች ሊኖሩ ይችላሉ? መስኖ በተደጋጋሚ የምንጠቀም ከሆነ የአፈር ጨዋማነት ሊመጣ ይችላል። የዛሬ ሦስትና አራት ዓመት ተግዳሮት እንዳይሆንና አስቀድሞ በመለየት ችግሩን ለመቋቋም እንዲችል ምን መሰራት

አለበት? የሚለውን ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት በምርምር እየሞከርን ነው” በማለት ዶክተር ጀማል ይናገራሉ።

ዩኒቨርሰቲው በአገር አቀፍ ደረጃ የተማረና ብቃት ያለው የሰው ኃይልን በተለያዩ ዘርፎች አሰልጥኖ በማውጣት የአገሪቷን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችለውን እቅስቃሴ እያካሄደ ይገኛል። “በአካባቢውም አርሶአደሩ ጋር ሰርቶ ማሳያዎች ነበሩ፤ የአገሪቷም የለውጥና እድገት ፍላጎት አለ። በዓለም ዙሪያም የተለያዩ ሳይንሶች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ስለዚህ የአገሪቷ የእድገት ፍላጎት ስላለና ነባራዊ ሁኔታዎች እየተለወጡ ስለሆነ ከግብርና በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች ትምህርት መስጠት ጀምሯል። በዚያም ልክ ምርምሮችን እያካሄደ ነው” በማለት ነው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል የገለጹት።

በአሁን ወቅት ዩኒቨርሲቲው ዘጠኝ ኮሌጆች አሉት። አንድ የቴክኖሎጂ ተቋምና አንድ የስፖርት አካዳሚ እንዲሁም ብዙ ማዕከላት አቋቁሞ እየሰራ ነው። የሰላምና ልማት፣ በአየር ንብረት ለውጥና ባዮዳይቨርሲቲ ጥበቃ ላይ አተኩሮ የሚሰራ የአፍሪካ የልህቀት ማዕከላት ተጠቃሽ ናቸው። ከግብርና፣ ጤና፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ሕግ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ፣ ማኅበራዊ ሳይንስ፣

ዶክተር ጀማል ዩሱፍ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት



53

በትምህርትና ስነባህሪ ፣ የኮምፒውቲንግና ኢንፎርማቲክስ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ አስተምሮ በማስመረቅ ተወዳዳሪ እጩዎችን ለእውቀት ገበያው ያቀብላል።

ዩኒቨርሲቲው በአገር ደረጃ እያከናወነ ያለው ተግባር መነሻ ሆኖት ነው መንግሥት ባካሄደው ልየታ ከምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሊሆን የቻለው።

“ግብርናን ጨምሮ በጤና፣ በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምርምር እናደርጋለን። ከዚህ በፊት ሲሰራባቸው የነበሩ የተለያዩ መስኮችን አናካትትም ማለት አይደለም። ነገር ግን በተልዕኮ ከተለዩ የትኩረት አቅጣጫዎች አኳያ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን። ግብርና፣ ጤና፣ ማኅበረሰብ ሳይንስ፣ ኢንጅነሪንግ በዚያ ዙሪያ የድህረ ምረቃና የምርምር ስራዎችን እናከናውናለን” በማለት ነው ዶክተር ጀማል ያብራሩት።

ምርምርና ስርጸትን መሰረት ያደረገው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ለቀጣይ የማስፈንጠሪያ አቅም አድርጎ “ምን ሊሰራ አስቧል?” የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ይሆናል። በአገር ደረጃ ለተመዘገቡ ውጤቶች የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ሲጫወት

የቆየው ዩኒቨርሲቲ በዘመኑ ከፍታ ምን ላይ ለመድረስ አቅዷል። በአገር ውስጥ እና በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳድሮ በልህቀት ማዕከልነት ለመገስገስ ምን አስቧል?

“በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ አሥር ከሚባሉት መካከል ለመሆን ራዕይ ሰንቀናል።” በማለት ዶክተር ጀማል የገለጹት ሀሳብ ዩኒቨርሲቲው የምስራቅ ኮኮብ ለመሆን ራዕይ ሰንቆ እየተጓዘ መሆኑን ያረጋግጣል። ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው በዓመታት ውስጥ ያካበተው ልምድ፣ አካባቢያዊ ሁኔታ፣ ብቁ የሰው ኃይል፣ የምርምር ተግባራት ምሰሶዎች ናቸው።

“ይህን ስናደርግ አገሪቷ የምትፈልገው የሰው ኃይል ታሳቢ በማድረግ በ’የትኛው ዙሪያ ብናተኩር ይሻላል?’ የሚለውን እንደ አንድ ትኩረት ለይተናል። ለአብነት መንግሥት ለግብርና ትኩረት ሰጥቶ ልዩ ልዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ አኳያ ግብርናን ከማዘመንም አልፎ በአገር ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በተጨማሪ ለወጪ ንግድ እየታሰበ ነው። በዚህ ዙሪያ እኛም ድጋፍ እያደረግን ነው።” በማለት ነው የገለጹት።



54

ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ አኳያ በርካታ ያልተነኩ የቱሪስት መስህቦች እንዳሉት እሙን ነው። የሐረር ጀጎል ፣ የቁንዱዱ ጋራ የዱር ፈረስ ፣ የባቢሌ ድንጋዮች፣ የልጅ እያሱ እስር ቤት የነበረው ጋራ ሙለታ፣ ቁልቢ ገብርኤል ፣ ከ100 ዓመት በላይ እድሜ ያለው መስጅድ የቱሪስት መስህቦች ይሆናሉ። ለዩኒቨርሲቲውም ልዩ አቅም ናቸው። ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው በምርምር ተፈጥሯዊ ምስጢራቸውን እየፈታና አቅሙን እያጎለበተ የራዕዩ ማስፈጸሚያ ጉልበት ይሆናሉ። በአገር አቀፍ ደረጃም እጅግ ጠንካራ አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም ይኖራቸዋል።

“ድንበር ተሻጋሪ ወይም ዓለምአቀፍ ሁኔታውንም ስንመለከት የእኛ አካባቢ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ።” ይላሉ ዶክተር ጀማል፤ የጎረቤት አገሮች ዩኒቨርሲቲዎች አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም ነው የሚናገሩት። ለአብነት በሶማሌላንድ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ላይ መስራት መፈለጋቸው ነው የሚገለጸው። በዚህ በኩል በጤና ዙሪያ እና በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የተጀመሩ መርሃ ግብሮች ስኬታማ እየሆኑ መጥተዋል። ይህ ለአገር መልካም ስምና ዝና የሚያመጣ ፣ በትምሀርት ዘርፍ አምባሳደር መሆኑን የሚያመላክት ነው።

“ይህ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ 10 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል እንሆናለን ያልነው እንደሚሳካ ማሳያ ማድረግ ይችላል” በማለት ዶክተር ጀማል ይናገራሉ። እነዚህ እንደማሳያ ቢወሰዱም በተለያዩ ዘርፎች የሚካሄዱ ምርምሮች በአካባቢው ሆነ በዙሪያው ላሉ አጎራባቾች የሚሰጠው አዎንታዊ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

ለአብነት በጤናው ዙሪያ “የጨቅላ ሕፃናቶች ሞት ምክንያት ምንድን ነው?” በሚል ርዕስ የሚያጠና በቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የሚካሄድ ፕሮጀክት አለ። በፕሮጀክቱ የጨቅላ ህጻናትን ሞት ምክንያት ይጠናል። ተመራማሪዎቹ ‘ኒዩላር ዲፌክት’ (neural de- fect) ችግር መሆኑን ደርሰውበታል። ይህን የ’ኒዩራል ዲፌክት’ መቀነስ የሚቻልበትን የመፍትሄ ሀሳብ ጭምር ይዞ ነው ምርምሩ የመጣው። ይህም ዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰቡን ችግር በመፈተሽና በማጥናት መፍትሔ የማመንጨት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ያሳያል። ከዚህ ባሻገርም የጤና ዩኒቨርሲቲው የሕክምና አገልግሎት በመስጠት

ውጤታማ ስራ እያከናወነ ይገኛል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ ሺ በላይ አልጋ ያለው ሆስፒታል እያስገነባ ነው። አሁን ግንባታው ወደመጠናቀቂያው ተቃርቧል። ስለዚህ ከግብርና ቀጥሎ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ ተግባራትን ያከናውናል። በአሁኑ ወቅት በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች በምርምር በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። ይህም ለዩኒቨርሲቲው ልዩ አቅም ሆኖታል፤ ተማሪዎቹ ንድፈ ሀሳብ ከተግባር የሚቀስሙበት ክፍል ነው። የሕክምና ኮሌጁ አልቆ በሚፈለገው ደረጃ ቁሳቁስ ከተሟላለት ከማስተማርም አልፎ በምስራቁ የአገሪቷ ክፍል የጤና ቱሪዝም ለማስፋፋት ያስችላል።

“የምስራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን እየሰራን ነው። ልምድ ካላቸው የውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋርም ተመክሮ ለመቅሰም እየተነጋገርን ነው። ዩናይትድ ስቴት ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ፍሎሪዳ፤ በጤና ቱሪዝም ትታወቃለች። እነሱም ፍላጎት አሳይተዋል” በማለት ያስረዳሉ።

በዚህ ደረጃ አቅሙን እየገነባ የመጣው ዩኒቨርሲቲ ለራስ ገዝ ጉዞ ምን እቅድ ይዟል? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አስፈላጊነቱ አያከራክርም።

ለዚህስ ዋነኛ ተግዳሮቱ ምን ሊሆን ይችላል? ሌላው መነሳት ያለበት ነጥብ ነው።

ዶክተር ጀማል እንደሚሉት፤ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ለመሆን ሲፈልጉት የቆዩት ጉዳይ ነው። በልዩ ልዩ መንገድ ራሳቸውን ችለው የሚወጡበትን ሁኔታ ለመንግሥት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። በአሁኑ ወቅት ጥያቄያቸው ምላሽ እያገኘ መምጣቱ ብዙዎችን አስደስቷል።

“ዩኒቨርሲቲዎች የራሳቸውን ዓለምአቀፍ እሴትና ልዩ እውቀትን ብቻ ማዕከል አድርጎ በሁሉም አቅጣጫ በነፃነት እንዲሰሩ ይጠበቃል። ራስ ገዝ ሲኮን አብዛኛውን በጀት ራስ ማመንጨት መቻል ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ለራስ አገዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።” በማለት ነው ዶክተር ጀማል ያብራሩት። ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት አሰጣጡን በንድፈ ሀሳብና በተግባር አጣምሮ የመስጠትና ጥራቱን የማስጠበቅ ጥረት መስፈንጠሪያ ሊሆነው እንደሚችል ያምናል። ራስ ገዝ መሆን መልካም አጋጣሚዎችንና ተግዳሮቶችን ይዞ መምጣቱ እውን ነው።

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትን ማስጠበቅ ወደ ራስ አገዝነት ለሚያደርጉት



55

ሽግግር እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ አለው። ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጡት የንድፈ ሃሳብና ተግባር ትምህርት ጥራት ምርጫቸውን ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። የትምህርት ቤቱ መስተንግዶ፣ የተማሪዎች ማደሪያ፣ የመመገቢያና የካፍቴሪያው ብቃት መመዘኛ ሆነው መቅረባቸው አይቀሬ ነው። ለዚህ ቀድሞ መዘጋጀትና ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት አስፈላጊነቱ አያጠያይቅም።

“መንግሥት ራሳቸው ከፍለው መማር ለማይችሉት የተወሰኑ ተማሪዎች በጀት ሊመድብ ይችላል። ነገር ግን በራሱ ወጪ የሚማረውን መሳብ መቻል ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ ዘመኑን የዋጀ፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትና አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል። ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ተማሪው በራስ መተማመን፣ ‘ስራ ልፈጥር እችላለሁ’ በሚል ዲግሪውን መውሰድ መቻል አለበት” በማለት ነው የሚያብራሩት ዶክተር ጀማል።

እንደዶክተር ጀማል ገለጻ አሁን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የታሰበው ጉዳይ ዓለምአቀፍ እሴቶችን ጠብቀው ለመጓዝ ቁልፍ ጉዳይ ነው። እንደሐረማያ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የቤተ ሙከራ መሰረታዊ ቁሳቁሶች ማሟላት ሊጠይቅ፣

የመሰረተ ልማት እድሳት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ይህም ቢሆን ግን ራስ አገዝ መሆን በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆንን አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ይሆናል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ግብርናው ላይ ለመስራት የሚያስችሉት ከአሥር በላይ የምርምር ማዕከላት አሉት። በግቢው ውስጥ ሰፋፊ የምርምር ስፍራዎች ይገኛሉ። ከመጀመሪያው ሲቋቋም ጀምሮ የሰራበትና የዳበረ ልምድና ያካበተበት ዘርፍ ነው። በዚህም ለዘርፉ እድገት የሚበጁ ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን ሲፈጥር ቆይቷል፤ አሁንም ለመፍጠር የሚያስችለው ስራ እያከናወነ ይገኛል። ይህም የግብርናን እድገት የሚያግዙ በሰብልና እንስሳት ሀብት ላይ አቅም የሚጨምሩ ውጤቶችን ማግኘት ያስችሉታል።

ለዓመታት ያካበተውን ተሞክሮ በማስፋት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በምስራቅ አፍሪካ ተጠቃሽ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ እውን ለማድረግ መሰረት መጣሉን ያመላክታል። ይህ ደግሞ ከሌሎች አካባቢ ተማሪዎችን የመሳብ ስራ አቅም ይፈጥራል።

በአሁኑ ወቀት ዩኒቨርሲቲዎች የፋይናንስ አቅማቸውን የሚያጎለብትና ዓመታዊ በጀታቸውን የሚደጉም አሰራር ለመከተል ስለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል። በተለይም የምርምር ስራዎችን ለማከናወን፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን መጪውን ዘመን ለመዋጀት ማቀድ ዓብይ ጉዳይ ነው። የዚህ ዓይነቱ ተግባር የአገርን ጥቅም ለማስጠበቅ ከመስራትና ውጤታማ ከመሆን ባሻገር በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነትን፣ በአገር ደረጃና በዓለምአቀፍ ነባራዊ ሁኔታ ተወደዳሪነትን ሊፈጥርላቸው ይችላል።

ከዚህ መሰረታዊ ምልከታ በመነሳት ነው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የራሱ የሆነ ኢንተርፕራይዝ ለማቋቋም ወስኖ ወደ ተግባር የገባው። ኢንተርፕራይዙ በቦርድ የሚተዳደርና ለማኅበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ተመጣጣኝ ገቢ ለማስገባት የሚችል ተደርጎ የሚሰራ ይሆናል።

“የእኛ ኢንተርፕራይዝ የሚያከናውነው ዩኒቨርሲቲው ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ልክ አበጅተንለት ያንን እያስኬደ ትርፋማ በሆነ መልኩ ኢንቨስት ማድረግ አለበት ብለን ወስነን መመሪያ አዘጋጅተናል።



56

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ አጽድቆልናል።” በማለት ይገልጻሉ ዶክተር ጀማል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ኢንተርፕራይዙ የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ደግሞ ተገቢውን አገልግሎት ሰጥቶ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል አደረጃጀት ይከተላል።

በአብነት የጠቀሱት ዩኒቨርሲቲው ለተሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥገና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ማሽነሪዎች መኖራቸውን ነው። ይህ ደግሞ በአካባቢው የሚታየውን የተሽከርካሪዎች ጥገና ችግር ይፈታል። በአሁኑ ወቅት ለከባድ ጥገና ወደ ማዕከል ጉዞ ይደረጋል፤ በቀጣይ የዚህ ዓይነቱ ጉዞ ይቀራል የሚል እምነት ተጥሏል።

“ይህ ደግሞ ተማሪው የተቀናጀ ትምህርት ይቀስምበታል። በተግባር ይማርበታል። የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ለተግባር ተኮር ትምህርት እድል ይሰጣል። ማኅበረሰቡም በአነስተኛ ክፍያ የሚፈልገውን አገልግሎት በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል። ለእኛም ትልቅ ገቢ የሚያስገኝ ይሆናል።” በማለት ያብራራሉ።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በእድገት ለመለወጥ ውስጡን ብቻ ሳይሆን ውጩን ለማየት

ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ቀደም ብሎ ዩኒቨርሲቲው የሚገኝበት አካባቢ “ምን መምሰል ይኖርበታል?” በሚል አስጠንቶ ዲዛይን አሰርቷል። አካባቢው ያለውን ለመለወጥ ሲነሳ የክልሉ መንግሥት ከተማዋን በአዲስ መልክ ለመስራት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ መልካም አጋጣሚ ሆነ።

“ዘመናዊ የሆነ ከተማ በሐረማያ ዙሪያ ሊቆረቆር ነው። አወዳይ አካባቢ ኤርፖርት ሊቋቋም በጀት ተፈቅዶ እየተሄደበት ነው። በእዚህ ወቅት የኢንቨስትመንት አጋጣሚዎች ይኖራሉ። ለምሳሌ እንግዳ ማረፊያ፣ አፓርትመንት፣ ለወጣቱ መዝናኛ ማዕከል፣ ስፖርት ማዘውተሪያ ለእኛም ገቢ ለእነሱም አገልግሎት የምንሰጥበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእኛ ስፖርት አካዳሚ ትልቅ ስቴዲየም አለው። ለወጣቱ ጥሩ አጋጣሚን ፈጥሮ እንደገቢ ማመንጫም እንጠቀመዋለን።” ይላሉ።

መንግሥት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከፍተኛ በጀት ይመድባል። ነገር ግን ተቋማቱ የፋይናንስ ፍላጎታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሟላት እንዲችሉ የራሳቸው ገቢ ማስገኛ መንገድ መፍጠር አለባቸው። ከድጋፍ ሰጪዎች፣ ከተለያዩ ተቋማት ገንዘብ የሚያገኙበትን መንገድ ማሰብም ይጠበቃል። የራሳቸውን ገቢ ማግኘት ሲጀምሩ

ትምህርትን በተግባር ከማስደገፊያ አንዱ የዶሮ እርባታ ተጠቃሽ ነው፤



57

መንግሥት ድጋፉን ያቋርጣል ማለት አይደለም።

“ዩኒቨርሲቲዎች በራሳቸው ገቢ ማመንጨቱ ላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል። በሌላው ዓለም አንዳንድ ትላልቅ ኩባንያዎች ምርምር እንድትሰራላቸው ይፈልጋሉ። ሀብት ይዘው ነው የሚመጡት። አንዳንዶቹ ስማቸው ለማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እንዲተከልላቸው ይፈልጋሉ። ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት ነው። ትላልቅ ቤተ ሙከራዎች በስማቸው እንዲገነባ ይፈልጋሉ። ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ የማስተማሪያ ማዕከል ይሆናል። የደቡብ አፍሪካን ልምድ ካየን አገር አቀፍ የምርምር ፈንድ የሚባሉ አለ። በዚህ ዓይነት መንገድ መጠቀም ይችላል። ፈንዱን ለማግኘት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ውድድር ክፍት ይሆናል። መንግሥት ለዚያ ትልቅ ገንዘብ ይመድባል። ውድድሩ ጥራትን ያመጣል። ዩኒቨርሲቲዎች ይወዳደራሉ። በዚያ መሰረት ሀብቱን ወደ ዩኒቨርሲቲው ያመጣሉ። ዩኒቨርሲቲው የተቀመጠለት ተልዕኮ ዓላማ ሊያሳካ በሚችል መልኩ በራሳቸው አውድ ውድድር ይፈጥራል። ተማሪውንም ወደ ውድድር ያስገባል በሚፈለገው ደረጃና ጥራት እንዲሰራ መንግሥት ይፈልጋል፤ ይደጋገፋል ማለት ነው” በማለት ነው የገለጹት።

ዩኒቨርሲቲ ‘ራስ ገዝ ነህ’ ተብሎ እንደ ንግድ ማዕከል አይተውም። መንግስት ድጋፉን ይቀጥላል። ዩኒቨርሲቲዎችም የትምህርት ጥራትን እያስጠበቁ ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ፣ በምርምርና ስርጸት እየተሳተፉ የፋይናንስ አቅማቸውን ያጎለብታሉ። ለዚህ ደግሞ የባለሀብቶች ወደ ዩኒቨርሲቲ መምጣት አስፈላጊነት አያጠያይቅም። ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ “ርዕስ ሰጥተው በዚህ ላይ ተመራመሩልኝ የሚሉ ባለሀብቶች አሉ?” የሚለው ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይነሳል። ይህ ደግሞ የአገራችን ባለሀብቶች ስራቸውን ውጤታማ ለማድረግ ምርምርና ጥናትን መሰረት ያደርጋሉ ወይ? የሚለው ሀሳብ እንዲነሳ ያደርጋል። እውነቱ ግን ኢንዱስትሪዎቻችን የዚህ ዓይነቱ ልምምድ በብዛት የሌላቸው መሆኑ ነው።

“ባህሉን መቀየር ያለብን እኛው ነን። አሁን ባለሀብቶ በፍላጎት እየመጡ ነው” በማለት ነው አብነት በመጥቀስ የገለጹት።

በአሁኑ ወቅት አንድ ባለሀብት ዳቦ ለማምረት “የስንዴ ግብዓት ቸገረኝ ለምን ራሴ አላመርትም?” በሚል ዩኒቨርሲቲውን ጠየቁ። የአፈር ናሙና፣ የሚትዎሮሎጂ ዳታ ተወስዶ እየተጠና ነው። በአካባቢው የከርሰምድር የውሃ ክምችት አለ ወይ? የሚለው እየተፈተሸ

ነው። የአፈሩ ሁኔታ ጥናት እየተደረገበት ነው። በአጠቃላይ ተቋሙ ያመረተውን ምርት ወደ ፋብሪካው የሚወስድበት፤ ተረፈ ምርቱን ለእንስሳት መኖ የሚሆንበትን መንገድ በጥናት በተደገፈ መልኩ ምላሽ እየተሰጠው ነው።

በአንድ ወቅት መንግሥትም የስኳር ፋብሪካ ሲታሰብ ሥርዓተ ትምህርት ቅረጹልን ተብለን ተቀርጾ የተወሰኑ ተማሪዎች አስመርቋል።

ከግሉ ዘርፍ ዲቦራ ፋውንዴሽን ተምሳሌት የሚሆኑ ስራዎችን እየሰራ ነው። ‘ዳውን ሲንድረም’ ያለባቸው ሕፃናቶችን ማስተማር፣ በሕክምና አገልግሎት ዙሪያ በአገር ደረጃ በዚህ ጎልቶ የወጣ የለም። የዚህ ሥርዓተ ትምህርት ፍላጎት ከፋውንዴሽኑ ነው የመጣው። ሥርዓተ ትምህርት ጸድቆ ሰው በማስተርስ ደረጃ እስከሚሰለጥን ጊዜ ስለሚያስጠብቅ ፍላጎቱ የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ስለሆነ “የአጭር ጊዜ ስልጠና አዘጋጁልን” በማለታቸው ውይይት እየተካሄደ ነው።

“ያለንበት ወቅት ዓለም አቀፍ ውድድር ያለበት ነው። ጥራት ያለው ነገር አምርቶ ወደ ውጭ ለመላክ ደረጃውን መጠበቅ ግድ ይላል። ማን እንዳመረተው ይጠየቃል። ስለዚህ የግሉ ባለሀብት ሳይፈልግ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ይመጣል” ብለዋል።

የግሉ ዘርፍ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የማይመጣበት አንዱ ተግዳሮት “ተማሪ ይፈራል፤ የሚፈለገው ክህሎት አለው ወይ? ማሽን ይሰብርብኛል ብሎ ይፈራል። ስለዚህ ይህ ፍራቻ መቆም አለበት። ዩኒቨርሲቲዎች ማስተካከል ያለብንን ነገር ማስተካከል አለብን። ተግባር ተኮር ትምህርት ሰጥተን ቢያንስ መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸው አድርገን ነው ወደ ኢንዱስትሪው መላክ ያለብን። በዚህ በኩል ብዙ መስራት ይጠበቅብናል” በማለት ያብራራሉ።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለባለሀብቱ ክፍት ነው። የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር የሚባል ዳይሬክቶሬት አለ። እነርሱ ዋናው ስራቸው ዩኒቨርሲቲዎችን ከባለሀብቱ ማስተሳሰር ነው። “ባለሀብቱ የግድ መምጣት የለበትም እኛም ባለሀብቶችን መፈለጉ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ሆኗል” በማለት ዶክተር ጀማል ያነሱት ሀሳብ የዩኒቨርሲቲዎችና ኢንዱስትሪዎች ትስስር አስፈላጊነት ብቻ ባለሀብቱ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ስራ እንዲያከናውን የማሳመን ተግባር ዩኒቨርሲቲዎች እንዲከተሉ የማድረግን አስፈላጊነት አመላካች ነው።



58

ዋናው መድኃኒት ቤት

በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ

ማህበራዊ



59

ዋናው መድኃኒት ቤት

የሰው፣ የእንስሣት እና የዕፅዋት መድኃኒቶችን እና የሕክምና መሣሪያዎችን በማምረት፣ ከውጭ አገሮች በመግዛት ሲያከፋፍል ሁለት አስርት ዓመታትን ዘለቀ፤ ቀጠለና የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አስመጪና ጅምላ አከፋፋይ ድርጅት ሆነ፤ ጥቂት ዓመታት አለፉና ወደ አክሲዮን ማኅበርነት ተቀይሮ ለትርፍ የሚንቀሣቀስ ድርጅት በመሆን ሥራውን ማካሄድ ጀመረ፡፡ የአክሲዮን ማኅበሩ በርካታ ውጣ ውረዶችን እያሳለፈ ሥራውን ማከናወን የእለት ተዕለት ተግባር አደረጎ ቆየ። ሆኖም በተበታተነ ግዥ ይፈፀም የነበረውን የመድኃኒት አቅርቦት ከልማት ጋር አብሮ የሚሄድ አደረጃጀት አለመፍጠሩ ስለታየ ሰብሰብ ያለ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ ግዥ መፈጸም እንዲያስችል በአዋጅ ቁጥር 553/1999 ዓ.ም ተቋቁሞ በወርሃ ታህሣስ 2ዐዐዐ ዓ.ም ወደታለመለት ተግባር ተሰማራ፡፡

የ76 ዓመቱ የዕድሜ ባለጸጋ “ዋናው መድኃኒት ቤት” በሚል ስያሜ ከተመሰረተበት ከ1939 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ስያሜዎች እየወጡለት ዓመታትን ዘልቋል። በ1968 ዓ.ም የኢትዮጵያ

የሺመቤት ደመቀ



60

የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ድርጅት /ኢፋርሚኮር/፣ በ1986 ዓ.ም የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አስመጪና ጅምላ አከፋፋይ ድርጅት /ፋርሚድ/፣ በ1994 ዓ.ም ፋርሚድ እንደገና ተዋቅሮ አክሲዮን ማኅበር፣ በ1999 ዓ.ም በአዋጅ ሲቋቋም የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በሚሰኙ ስያሜዎች የሚያቀርባቸውን መድኃኒቶች በዓይነትና በመጠን በማሳደግ ፈዋሽነታቸውን እና ደህንነታቸውን መጠበቅ የሚያስችሉ የስርጭትና የክምችት አውታሮችን በመዘርጋት ከአንድ ሺህ አይነቶች በላይ ያሏቸውን መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች በአገሪቷ ለሚገኙ የጤና ተቋማት የማቅረብ ተልዕኮውን ሲወጣ ቆይቷል።

መጠሪያውን እየቀያየረ እስካሁን የዘለቀው እና አሁን የሚጠራበትን ስያሜ በ2014 ዓ.ም ያገኘው “የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት” የሚሰኘው መንግሥታዊ ተቋም ነው።

አንጋፋው ተቋም በ2023 ዓ.ም በአፍሪካ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ እና ብቁ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ያለው ድርጅት የመሆን ራዕይ፤ የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ሥርዓቱን በማዘመን ጥራታቸውን የጠበቁ መሰረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ቀጣይነት ባለው መልኩ ለደንበኞቹ በማቅረብ የማኅበረሰቡን ጤና የማሻሻል ተልዕኮ ሰንቋል።

ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጤና ተቋማት አገልግሎት የሚሠጠው ይህ ተቋም በአሁኑ ወቅት ለ987 ሆስፒታሎች፣ ለ5 ሺህ 117 ጤና ጣቢያዎች፣ ለ1 ሺህ 397 ክሊኒኮች፣ ለ1 ሺህ 161 መድኃኒት ቤቶች፣ ለ2 ሺህ 175 መድኃኒት መደብሮች እና ለ103 የገጠር መድኃኒት መደብሮች አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ከ304 በላይ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያ ግብዓቶች አቅራቢዎች ጋር ውል በመፈጸም አገልግሎት ይሰጣል። ከእነዚህ መካከል ስምንቱ የአገር ውስጥ የመድኃኒት፣ የሪኤጀንት እና የሕክምና መርጃ መሣሪያ አምራቾች ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ ከተለያዩ አገሮች መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን የሚያቀርቡ ተቋማት ናቸው፡፡

“ማገልገል ክብር ነው” የሚለውን መርህ የሚከተለው ተቋሙ ደንበኛ ተኮር መሆን፣ ታማኝነት፣ ግልፀኝነት፣ ተጠያቂነት፣ የቡድን መንፈስ፣ አለማዳላት እና ሕግ ማክበርን እሴቶቹ አድርጓል።

ዓላማዬ የመንግስት ጤና ተቋማት ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ እንዲቀርቡ ማስቻል፤ የመድኃኒት አቅርቦቱን በማጠናከርና ዘለቄታዊነቱን በማረጋገጥ የጤና አገልግሎትን ለማስፋፋትና ለማጠናከር በሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ የራሴን አስተዋፅኦ ማበርከት፤ የተቋሙ መደበኛ ተገላባጭ ፈንድ /Revolving drug fund – RDF/ ወጪውን እንዲሸፍን ከተደረገ በኋላ ተመልሶ በማዟዟር ራሱን በማሳደግ የተገለፁትን ዓላማዎች እውን ማድረግ መሆኑን የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።

በዚሁ መሰረት አገልግሎቱ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የያዘችውን ጤናማና አምራች ዜጋ የማየት ራዕይ ማሳካትና መምራት የሚያስችሉ የልማት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶችን ነድፎ በመተግበር ሰፊ መሰረት ያለው፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ልማትን የማፋጠንና ድህነትን የማስወገድ ዓላማ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

ጤና ከሁሉም የአገሪቷ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ዕድገትና የኅብረተሰብ ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ከሆኑ ማኅበራዊ የልማት ዘርፎች በሁለተኛው አገራዊ የ10 ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል አንዱ ነው። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትም የኅብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል የሚያግዙ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎችን ማቅረብ ያስችል ዘንድ የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደሩን በማዘመንና በማጠናከር ሥራዎችን ለማከናወን እቅድ ይዞ ይተገብራል። በተለይ በ2015 በጀት ዓመት ለጤና አገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ጥራታቸው፣ ፈዋሽነታቸውና ደህንነታቸው የተረጋገጡ መሰረታዊ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎችን በበቂ መጠን፣ በተመጣጣኝ ዋጋና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማቅረብ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን በየደረጃው በመገምገም ጠንካራ

እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም መፍትሄዎች ተለይተው ለ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ግብዓት ሆነው ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ለመከወን በያዘው ዕቅድ መሰረት የጤና ተቋማትን ፍላጎት ለማሟላት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 33,701,057,064.56 ብር ዋጋ ያላቸው የመድኃኒት፣ የኬሚካልና የሪኤጀንቶች፣ የሕክምና መገልገያዎችና መሳሪያዎች በአጠቃላይ ግዥና በእርዳታ ወደ መጋዘን አስገብቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ በመደበኛ በጀት የ8,247,824,391.64 ብር፣ በጤና መርሃግብር የ3,697,810,908.38 ብር በአገልግሎቱ ተገዝተው ወደ መጋዘን የገቡ ሲሆን፤ ከመደበኛ በጀት ግዥ ውስጥ የ3,278,947,091.64 ብር የግዥ ሂደቱን ጨርሶ በመጓጓዝ ሂደት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ የ21,755,421,764.54 ብር የጤና ግብዓቶች ወደ መጋዘን እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በመደበኛ እና በጤና መርሃግብሩ በድምሩ 22,157,252,761.62 ብር ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶች፣ ሪኤጀንቶች፣ የሕክምና መገልገያዎችና መሳሪያዎች ለጤና ተቋማት ተሰራጭተዋል፡፡ የሕይወት አድንና የመሰረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት አፈፃፀም በመደበኛ 83.4% ሲሆን፤ በጤና መርሃግብር 93.5% ነው፡፡ የዘጠኝ ወራት የበጀት አጠቃቀሙም 98.3% ነው፡፡

በተመሳሳይ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመግታት እና ለመቆጣጠር የ2,524,597,833.22 ብር፤ እንዲሁም በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ጦርነት ሊደርስ የሚችለውን የማኅበረሰቡን የጤና ጉዳትና ድንገተኛ በሽታዎች ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የ478,527,113.04 ብር ዋጋ ያላቸው የጤና ግብዓቶች ስርጭት የተካሄደ ሲሆን በግሎባል ፈንድ በኩል ተገዝተው ከገቡ 19 ነጥብ 7 ሚሊዮን አጎበሮች 2,225,706,743.70 ብር ዋጋ ያላቸው በቁጥር 17,526,630 አጎበሮች፤ በ10 ክልሎች (በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በደቡብ ምዕራብ፤ በድቡብ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል፣ በአፋርና በሶማሌ) ስር ለሚገኙ ወረዳዎች ከቅርንጫፎች እና ከዋናው መስሪያ ቤት ተሰራጭተዋል።



61

• በመድኃኒት ፈንድ በመጠቀም በአገሪቷ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ላይ ያተኮሩ ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶች በበቂ መጠን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመንግስት የጤና ተቋማት ማቅረብ የሚያስችል ቀልጣፋና ብቃት ያለው የግዥና የሥርጭት ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይተገብራል፤ • ዘመናዊ የክምችት አስተዳደር ማስፈን የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ተመጣጣኝ እና ተገቢ የመድኃኒት ክምችትና ያልተቋረጠ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋል፤ • የክምችትና የሥርጭት አውታሮችን ፍትኃዊና ውጤታማ በሆነ መልኩ ያስፋፋል፣ ያጠናክራል፤ • አግባብ ባለው አካል ደህንነታቸው፣ ፈዋሽነታቸውና ጥራታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችን ለመንግሥት የጤና ተቋማት ያቀርባል፣ አግባብ ሆኖ ሲገኝ በበቂ መጠን ሊቀርቡ ያልቻሉ የተመረጡ መድኃኒቶችን ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ላልሆኑና ለግል የጤና ተቋማት ያቀርባል፤ • የማጓጓዣ ሥርዓትን በማመቻቸት መድኃኒቶችን በቀጥታ ለወረዳዎች፣ ለሆስፒታሎች እና እንደ አመቺነቱ ለጤና ጣቢያዎች ያደርሳል፤ • በዘርፉ ከሚዘረጋው ሥርዓት ጋር የሚጣጣም ዘመናዊ የሎጂስቲክስ መረጃ ልውውጥ ሥርዓት ይዘረጋል፤ • የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ፤ የግዥ፣ የስርጭት፣ የማከማቸትና የማጓጓዝ ዕቅድ በማዘጋጀት ይተገብራል፣ አፈፃፀሙንም ይገመግማል፤ • በሚያከናውናቸው የስራ ዘርፎች ላይ ሙያዊ የምክር አገልግሎትና ስልጠና ይሠጣል፤ • አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አማካሪ ኮሚቴዎችን ያቋቁማል፣ ሥራቸውን ይመራል፣ ያስተባብራል፤ • ለሚሰጠው አገልግሎት ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ክፍያ ያስከፍላል፤ የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሣል፣ ይከሠሣል፤ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

የአገልግሎቱ ሥልጣንና ተግባር፡-



62

በጤና ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ

የጤናን ጉዳይ - በወፍ በረር

ማህበራዊ



63

ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተዘጋጀው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ / ዕትዕ II ከ2008-2012/ በቀረጸችው የጤና ዘርፍ የልማት መርኃ ግብር ለኅብረተሰቡ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ በርካታ አዎንታዊ ውጤቶችና ስኬቶችን በማስመዝገብ ፈጽማለች። የሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እና የቀጣይ አስር ዓመት አመላካች መነሻ ሰነድ ዝግጅት የመጀመሪያው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ

አፈፃፀም፣ ባለፉት አራት ዓመታት የተሰሩ አገር አቀፍ ጥናቶችን ማለትም የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ዳሰሳ ጥናት፣ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ፣ የብሔራዊ የጤና ወጪ ስሌት፣ የሥነ-ሕዝብ እና የጤና ዳሰሳ ጥናት፣ የተለያዩ በፕሮግራም ዘርፍ የተሰሩ ጥናቶችን እና የዘላቂ የልማት ግቦችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

ይህ የትግበራ ወቅት በርካቶች ዜጎቿ ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉባቸው ግጭቶች የተከሰቱበት መሆኑ በጤና ሥርዓቱ ላይ ተጨማሪ ጫና መፍጠሩ አይዘነጋም። ዓለም

መንገሻ ገብረሚካኤል



64

አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 በአገሪቷ የለውጥ እንቅስቃሴዎች እና በአንጻራዊነት በጠንካራ የኢኮኖሚ ዕድገቷ ላይ ግልጽ ስጋት ደቅኖ ከማለፉ ባሻገር በአገሪቷ ሰፊና ከባድ ተጽዕኖዎችን ያሳደረበትም ነው። ይሁንና እነዚህና ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም አገሪቷ የሕዝቦቿን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለመለወጥ የሚደረገውን ጥረት ለማስቀጠል አድናቆት የተቸረው አፈጻጸም ማስመዝገብ ችላለች። የመጀመሪያው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የሁለተኛው ዘመን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (ዕ.ት.ዕ II) አካል እና በአገሪቷ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤን በማጠናከር እ.አ.አ በ2035 ዓ.ም ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ላይ ለመድረስ የተዘጋጀው ዕቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው።

ዕቅዱን በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ተቀርጸው የተተገበሩት አራት የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች የወረዳ ትራንስፎርሜሽን፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ፣ የመረጃ አብዮት መፍጠር እንዲሁም ተንከባካቢ፣ አክባሪ እና ሩህሩህ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት ናቸው፡፡ በእነዚህ ተደጋጋፊ አጀንዳዎች ትግበራ የጤና ሥርዓቱን ወሳኝ ማነቆዎች መፍታት የሚችል አቅም ተፈጥሯል።

የመጀመሪያው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ዓመታዊ የአፈፃፀም ግምገማዎች እና መደበኛ የጤና መረጃ ሥርዓቱን ጨምሮ የዕቅድ ዘመኑ የግማሽ ዘመን ዳሰሳ፣ የዘርፉና የአጋሮች የጋራ ግምገማ ሪፖርት እና የተለያዩ የሥነ-ሕዝብ እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን በማካሄድ ጥልቅ ግምገማ ተካሂዷል።

የጥናቶቹ አና የዳሰሳዎቹ ውጤት በጥቅሉ ሲታይ አገሪቷ ከላይ የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የዕቅዱን ግቦች ማሳካት መቻሏን ያሳያሉ። እነዚህ ውጤቶች የተገኙት በዋነኛነት ትልቅ ፋይዳ የሚያስገኙ ተግባራት በተለይም እንደ ጤና ኤክስቴንሽን መርኃ ግብር የመሳሰሉ ማኅበረሰብን መሰረት ያደረጉ መርኃ ግብሮች በመተግበራቸው ነው። በተጨማሪም ጤናን የሚወስኑ ማኅበራዊ ጉዳዮችን ለመመለስ ዘርፉ የዘርፈ-ብዙ ትብብርን አስፈላጊነት በትጋት ሲሟገት/ሲያስተዋውቅ ቆይቷል። ሆኖም ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት በመስኩ ለማስመዝገብ ከታለመው ግብ ከመድረስ አኳያ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራስፎርሜሽን ዕቅድ የቀጣይ አምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ሲሆን፤ ከሐምሌ 2012 እስከ ሰኔ 2017 በጀት ዓመት (እ.ኤ.አ ሐምሌ 2020–ሰኔ 2025) መካከል ያለውን ጊዜ ይሸፍናል።

በዚህ የዕቅድ ዘመን የማይበገር፣ ዘላቂ፣ ጥራትና ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በመጀመሪያው የጤና ዘርፍ ትራስፎርሜሽን ዕቅድ የተገኙ ስኬቶችን መሰረት በማድረግ እና ውጤቶችን በማዳበር ይሰራል። በመሆኑም በመጀመሪያው የጤና ዘርፍ ትራስፎርሜሽን ዕቅድ ወቅት የነበሩ ተጨባጭ የትግበራ ሁኔታዎች ላይ ጥልቅ ትንተና በማካሄድ እና እንደ ግብዓት በመጠቀም ሁለተኛው ዕቅድ ተዘጋጅቷል።

የአገሪቷ የረጅም ጊዜ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስትራቴጂና የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችና አገሪቷ ለዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት እንዲሁም ወቅታዊና ተለዋዋጭ ጤናን የሚወስኑ ማኅበራዊ ጉዳዮች በዕቅድ ዝግጅቱ ወቅት ታሳቢ ተደርገዋል።

ይህ በሰባት ምዕራፎች የተደራጀው የሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሰነድ በየምዕራፎቹ በቅደም ተከተል መግቢያ፤ አገራዊ ገጽታ፤ የሁኔታዎች ትንተና፤ የዕቅዱ ዓላማዎች፣ ግቦችና ስትራቴጂክ አቅጣጫዎች፤ የሃብት

ትመናና የፋይናንስ ክፍተት ትንተና፤ የዕቅድ አተገባበር ስልት እና የክትትልና ግምገማ ዕቅድ በሚሉ ርዕሶች ተሰንዷል።

በዚህ ጽሁፍ የዚሁ የሁለተኛው የጤና ዘርፍ የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ዓላማ፣ ዒላማና የትኩረት አቅጣጫዎችን በወፍ በረር ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡

የሁለተኛው የጤና ዘርፍ የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ዓላማ፣

ዒላማና የትኩረት አቅጣጫዎች

ዓላማ የሁለተኛው የጤና ዘርፍ የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ዓላማ የኅብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ማሻሻል ነው፡፡ ይህ ዓላማ ትኩረት የሚያደርገው የዜጎችን ረዥምና ጤናማ ሕይወት ማረጋገጥን ነው። ይህም የሚሆነው የእናቶችና ህጻናት ጤናን ጨምሮ ያለ ዕድሜ ሞት ምክንያት የሚሆኑ ጠንቆችን እንዲሁም ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤን ወይንም አደጋዎችን በመቀነስ፤ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽነትን በማሳደግ፤ በጤና ላይ ተጽዕኖ ለሚያሳድሩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ምላሽ በመስጠት ነው። ይህ ሲጠቃለል ሁሉም ዜጎች ጥራት ያለው ረዥም ዕድሜ እንዲኖራቸው ማድረግን የሚይዝ ነው።



65

በተጨማሪም ይህ ዓላማ ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች ጾታ፣ ዕድሜ፣ የመኖሪያ ቦታ፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የኢኮኖሚ፣ የትምህርት ሁኔታዎችን እና ሌሎች የፍትሐዊነት መስፈርቶችን አካታች ሆኖ የዜጎችን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ነው። እዚህ ላይ የማኅበረሰቡን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል የተቀረጹትን አራት ምሰሶዎች ይጠቅሷል።

• ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን የሚደረገውን ሂደት ማፋጠን

• ማኅበረሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎች መጠበቅ

• የወረዳ ትራንስፎርሜሽን

• የጤና ሥርዓት ምላሽ ሰጪነትን ማሻሻል

ወደ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን የሚደረገውን ሂደት ማፋጠን፡-

ይህ ዓላማ ውጤታማ የሆነ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሽፋን ለሁሉም ማዳረስን እና በገንዘብ እጦት ምክንያት ኅብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ሳያገኝ እንዳይቀር የሚደረገውን ትግበራ ማፋጠን ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው። ከጤናው ዘርፍ እና ከምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ ጋር የተናበበ በማድረግ ይህ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በ2030 ውጤታማ የሆነ የጤና አገልግሎት ሽፋንን በማሳደግ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት

ሽፋንን ለማሳካት አልሟል።

ይህም ዓላማ የሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ሽፋንን ሦስት ክፍሎች መሟላታቸውን የሚያረጋገጥ ነው።

ማኅበረሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎችና ችግሮች መጠበቅ፡-

በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች፣ በግጭቶች፣ በተደጋጋሚ በሚከሰቱ እና ባልተጠበቁ የበሽታዎች ክስተትና ወረርሽኝ፣ በመንገድ ትራፊክ አደጋዎች፣ ድንገተኛ በሆኑ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና በአዳዲስ የጤና ስጋቶች ምክንያት የሚከሰቱ የማኅበረሰብና የሕክምና ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት የሕዝቡን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ ያለመ ነው። በተጨማሪም ድንበር ተሻጋሪ የጤና ችግሮችን በመከላከል የሕዝቡን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ ያቀደ ዓላማ ነው።

የማኅበረሰብ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች አገልግሎት በዋናነት የሚያተኩረው በቅድመ ዝግጁነት፣ በመከላከል፣ በልየታ፣ በድንገተኛ አደጋዎች አስተዳደር እና የማገገም ስራዎች ላይ ነው። የሕክምና ድንገተኛ አደጋዎች አፋጣኝ የሕክምና አገልግሎት ካልተሰጠ ሞት ወይም ዘላቂ ጉዳት የሚያስከትል ማንኛውም የጤና እክልን ያካትታል። እነዚህ የድንገተኛ የጤና እክሎች ተላላፊ በሆኑና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች

እንዲሁም አፋጣኝ ሕክምና በሚያስፈልገው የአካል ጉዳት አደጋ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ። ስለዚህ የድንገተኛ፣ “የትራውማ” እና የጽኑ ሕክምና መስጫ ማዕከላትን ማቋቋምና ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል። የማኅበረሰብ እና የሕክምና ድንገተኛ የጤና ችግሮችን ለመከላከል የዝግጁነት፣ የመከላከል፣ የአስቀድሞ ልየታ እና ምላሽ አቅም እና ግብዓት ማሟላት የሚጠይቅ ነው። በተጨማሪም የድህረ ድንገተኛ አደጋዎች ዳሰሳ ማድረግ፣ የተከናወኑ ተግባራትንና ተሞክሮዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ ያሻል፡፡

የወረዳ ትራንስፎርሜሽን፡-

የግለሰብ፣ የቤተሰብ እና የማኅበረሰብ ጤንነት እና ደህንነትን ለማሳደግ የሚጫወተውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት የወረዳ ትራንስፎርሜሽን የሁለተኛው የጤና ዘርፍ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንዱ አካል ተደርጎ ተወስዷል። በቤተሰብ ሁሉን አቀፍ እና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የቤተሰቦቻቸውን ችግሮች በመፍታት እና የኅብረተሰቡን እምቅ አቅም በመጠቀም ላይ እንደ አንድ የስበት ማዕከል ተደርገው ይወሰዳሉ። ስለሆነም የተለወጡ ቤተሰቦች ድህነትን እና ረሃብን ለመግታት እና ጤና እና ጤናማነትን ለማጎልበት እንዲሁም ለአገሪቷ እድገት እና የልማት ስኬቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።



66

በወረዳ ውስጥ የቤተሰብ መለወጥ የአካባቢ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች የልማት ግቦች ስኬቶች እንዲሻሻሉ እና የተለወጠ ወረዳ እንዲፈጠር ያስችላሉ። በዚህ መልኩ ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ሁሉን አቀፍ የሆነ አጠቃላይ የልማት አካሄድ የጤናን ማኅበራዊ ችግሮች በመፍታት የተሻለ ጤና እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያስችላል። የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት የኅብረተሰቡ ተሳትፎ፣ አካታችነት፣ አቅም ማጎልበት እና ባለቤትነትን ማረጋገጥ ይጠይቃል። የልማት እና ጤናን ሁኔታ የሚወስኑ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም ሁለገብ የትብብር ጥረት ይጠይቃል።

የጤናው ዘርፍ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚፈልጉ ስራዎችን ከሌሎች ዘርፎች ጋር በጋራ በመሆን የወረዳ ለውጥ እንዲመጣ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል። የዚህ ዓላማ ስኬት የሚለካው በሁለት መመዘኛዎች ላይ ተመስርቶ ይሆናል። እነዚህም በዘርፈ ብዙ ምላሽ አማካኝነት የሚመጣ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን እና የጤናው ዘርፍ ላይ ብቻ ያተኮረ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን ስለመኖሩ መመዘን የሚያስችሉ መለኪያዎችን በመጠቀም ይሆናል።

የጤና ሥርዓት ምላሽ ሰጪነትን ማሻሻል፡-

የጤና ሥርዓት ምላሽ ሰጪነት የጤና አገልግሎቶች የግለሰብና የማኅበረሰብ የአገልግሎቶች ፍላጎት እንዲሁም ከአገልግሎቶቹ የሚጠብቁትን በመለየትና በመዘጋጀት እንደየፍላጎታቸው ምላሽ መስጠትን ያካትታል። ይህ ማለት በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የግለሰቦችን ብሎም የማኅበረሰብን ምርጫ፣ ፍላጎት እና እሴቶችን ማክበርና ምላሽ መስጠትን ያጠቃልላል።

የጤና ሥርዓት ምላሽ አሰጣጥ ማለት ለአገልግሎት ፍላጎት ምላሽ መስጠት ብቻ ሳይሆን ጤና ነክ ላልሆኑ ማኅህበራዊ ጉዳዮች የጤና አገልግሎት ሥርዓቱ ምላሽ የሚሰጥበትን መንገድ፣ ማኅበረሰቡ ከጤና ባለሙያው የሚጠብቀውን አገልግሎት አሰጣጥና እንክብካቤ ማግኘት አለማግኘቱን የሚያሳይ ነው።

የጤና ሥርዓት ምላሽ ሰጪነት ክብርን፣ ግላዊነትን፣ አለማዳላትን፣ ውሳኔ የመስጠትን፣ የመረጃ ምስጢራዊነትን፣ ግልጽ የሆነ ተግባቦትን፣ የጤና አገልግሎት ሰጪ ባለሙያ ምርጫን፣ ያልተራዘመ የቆይታ ጊዜን፣ የታካሚን ድምጽና እሴቶችን፣ የዋጋ ተመጣጣኝነት ያለው አግልግሎት የማግኘት መብት እና

በቀላሉ መጠቀምን ያካትታል። የዚህ ዓላማ ውጤት ለማኀበረሰቡ እርካታን እና እምነትን በመጨመር አጠቃላይ የአገልግሎት ተጠቃሚነት እንዲጨምር በጎ ጎኑን ለሌላ በማስተላለፍ የራስን አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡

የሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዒላማዎች

ሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራስፎርሜሽን ዕቅድ ዓላማዎቹን እና አፈፃፀሙን ለመለካት ዒላማዎችን አስቀምጧል። ዒላማዎቹ የተቀመጡት “ዋን ሄልዝ” መሣሪያን በመጠቀም ሲሆን የአፈጻጸም መነሻ፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎች እንዲሁም ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁ ሃብቶችን ከግምት በማስገባት ነው።

አገልግሎትን ከመጠቀም አኳያ የተወሰኑ ዒላማዎችን ማለትም በባለሙያ የታገዘ የወሊድ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ወደ 76 በመቶ፣ አራተኛውን የቅድመ ወሊድ ክትትል ሽፋን ወደ 81 በመቶ፣ የጸረ አምስት /ፔንታቫለንት ሶስት ክትባት ሽፋንን ወደ 90 በመቶ፣ የቲቢ ልየታ መጠን ወደ 81 በመቶ፣ የጸረ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መድኃኒት ሽፋን ወደ 90 በመቶ ማሳደግ የሚሉ ይገኙበታል፡፡

የትኩረት አቅጣጫዎቹ

ስትራቴጂክ ዕቅዱ 14 የትኩረት አቅጣጫዎች ያሉት ሲሆን፤ የትኩረት አቅጣጫዎቹ መግለጫዎችና ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡-

• የተሟላ የጤና አግልግሎት ጥራትና ፍትሐዊ ተደራሽነትን ማሻሻል

• የድንገተኛ ጤና አደጋዎችና ጉዳቶች አገልግሎትን ማሻሻል

• የማኅበረሰቡን ተሳትፎ/አካታችነትና ባለቤትነት ማሻሻል

• የመድኃኒትና ሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦትን ማሳደግና አግባባዊ አጠቃቀምን ማረጋገጥ

• የቁጥጥር ሥርዓትን ማሻሻል

• የሰው ኃይል ልማት እና አስተዳደርን ማሻሻል

• በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት እና ፈጠራ ማሻሻል

• የጤና የፋይናንስ ሥርዓትን ማሻሻል

• አመራር እና መልካም አስተዳደርን ማጠናከር

• የጤና መሰረተ ልማትን ማሻሻል

• የጤና ዲጂታል ቴክኖሎጂን ማሻሻል

• የባህላዊ ሕክምናን ማሻሻል

• ጤና በሁሉም ዘርፍ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካተቱን ማረጋገጥ እና

• የግሉ ዘርፍ በጤና መስክ ያለውን ተሳትፎ/ አካታችነት ማሳደግ ናቸው።

የትኩረት መስኮች/ የትራንስፎሜሽን አጀንዳዎች፡-

በነባራዊ ሁኔታ ትንተና ወቅት ከተለዩ ዋና ዋና ችግሮች በመነሳት ከ14ቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ዘርፉ ቁልፍ የትኩረት መስኮችን/ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለይቷል። እነዚህም የጤና ሥርዓቱን መሰረት የሚችሉ ዘርፉ መዋዕለ ነዋይ የሚያወጣባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ፤ በአግባቡ ከተተገበሩ የጤና ሥርዓቱን በመለወጥና ብቃት ያለው የጤና አገልግሎት በመስጠት በጎ የጤና ውጤት ለሁሉም ማምጣት ያስችላሉ። በዚህ መሰረትም የሁለተኛው የጤና ዘርፍ ትራስፎርሜሽን ዕቅድ የትኩረት መስኮች የሚከተሉት ይሆናሉ።

የጤና አገልግሎት ፍትሃዊነትና ጥራት፡-

ይህ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ የሚያመለክተው ጥራት ያለው /አስተማማኝ፣ ሰው-ተኮር እና ወጪ ቆጣቢ/ ፍትሃዊና ወቅታዊ የጤና ክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማቅረብን ማረጋገጥ ነው። ይህ ማለት ጥራት ያለው ክብካቤ እንደ ዕድሜ፣ ጾታ፣ ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ወይም የመኖሪያ ቦታ፣ የአካል ውሱንነት ሁኔታ ባሉ ግላዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ሳይለያዩ የላቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም መድረሱን ማረጋገጥ ነው።

የጤና ክብካቤ ጥራትን በማሻሻል የማኅበረሰብ ጥራት ያለው አገልግሎት ፍላጎት እና የሚሰጠውን ክብካቤ ጥራት ለማሳካት መጠነ ሰፊ መፍትሔዎች ያስፈጋሉ። ጥራት ያለው የአገልግሎት ፍላጎትን ለመመለስ በእስካሁን ሂደት ውስን ዘዴዎች ስራ ላይ ውለዋል። ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ጠብቀው የሚመጡ ተገልጋዮች ጥራት ያለው አገልግሎት ይጠይቃሉ፤እንዲሁም ይጠብቃሉ። የተወሰኑ ተግባራት የተጠቀሱ ቢሆንም፤ በርካታ ፈጠራ የታከለባቸው ዘዴዎች ያስፈልጋሉ።

የተቋማትን የተጠያቂነት አሰራር በመዘርጋት



67

ዝቅተኛ ጥራት ያለውን አገልግሎት ማረምና ለተገልጋዩ የሚሰጠውን አገልግሎት የጥራት ደረጃ በግልጽ ማሳወቅ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ጥራት ባለው የአገልግሎት አሰጣጥ በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት በዕቅዱ ወቅት ትኩረት ይሰጠዋል። ፍትሃዊነትን በተመለከተ፤ ፍትሃዊነት ያለበትን ሁኔታ በሁሉም ደረጃ መደበኛ ክትትል ይካሄዳል። እንዲሁም ተስማሚ የሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴዎችን መልሶ መቀየስ፣ የማትጊያ ማዕቀፎችና ሌሎች ዘዴዎችን በመንደፍ ይተገበራል።

የመረጃ አብዮት፡-

የመረጃ አብዮት ዋነኛ ግብ በጤና ሥርዓቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃ በማመንጨት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ እና ወደ ተሻለ አፈፃፀም የሚያመራ የዳበረ አቅም ያለው የጤና ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል ነው። የመረጃ አብዮት አጀንዳ የጥሬ መረጃ እና የመረጃ አስተዳደር ቴክኒክን ማዘመን ላይ ያተኮረ ብቻ ሳይሆን ለመረጃ አጠቃቀም የተሰጠ ግምት እና ልማድ ላይ መሰረታዊ የባህልና የአመለካከት ለውጥ ማምጣትም ነው። በዕቅዱ በሦስት የመረጃ አብዮት ምሰሶዎች ላይ ማለትም የከፍተኛ ጥራት ያለው መረጃን የመጠቀም ባህልን መለወጥ፣ የጤና መረጃ ሥርዓትን ማዘመንና የመረጃ ሥርዓት አስተዳደርን ለማሻሻል ጥረቶች ይደረጋሉ።

የተነቃቃ፣ ብቁ እና ሩህሩህ የጤና የሰው ኃይል፡-

ይህ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በበቂ ቁጥር፣ የሙያ ስብጥርና ጥራት ያለው የተነቃቃ፣ ብቁና ሩህሩህ የጤና የሰው ኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ የተቀረጸ ነው። የተነቃቃ፣ ብቃት ያለው እና ሩህሩህ የጤና የሰው ኃይል ማፍራት በርካታ እርስ በእርስ የተቆራኙ ጉዳዮች ማለትም በአግባቡ ቁጥጥር የሚደረግበትና ጥራት ያለው የቅድመ ስራ ትምህርት፣ የስራ ላይ ስልጠናዎች እና ቀጣይነት ያለው የሙያ ማሻሻያ ዕድሎችን በማመቻቸት ብቃት ያለው ባለሙያ እና አመራር በበቂ ቁጥር መፍጠር፤ ጠንካራ የሰው ኃይል አስተዳደር ፖሊሲና ደንብ በመተግበር ተገቢ የሆነ ምልመላ፣ መረጣ፣ ገለጻ እና ምደባ ሂደት፣ አስቻይ የስራ ከባቢ ግልጽ ከሆነ ሚና እና ኃላፊነት ጋር፣ ፍትሃዊ የክፍያ ጥቅል እና የአፈጻጸም ድጋፍ /ድጋፋዊ ጉብኝት እና ወቅታዊ

ግብረ-መልስ/ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል።

የጤና ፋይናንስ፡-

የጤና ፋይናንስ ትራንስፎርሜሽን ማለት ሀብትን በበቂ እና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ለማሰባሰብና የሀብት አጠቃቀምን ለማሳደግ የጤና ሥርዓት የፋይናንስና አስተዳደር ሥርዓትን ማሻሻል/ ሪፎርም ማድረግ ነው። የጤና አገልግሎት ለማግኘት ከግለሰቦች ኪስ የሚወጣው ገንዘብ ከፍተኛ መሆን፣ የኑሮ ቀውስ የሚያስከትል የጤና አገልግሎት ወጪ፣ ወጪ ቆጣቢ የሃብት ምደባና አጠቃቀም አለመኖር በጤናው ዘርፍ ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን የሚደረገውን ጉዞ የሚያደናቅፉ ናቸው።

እነዚህን ፈተናዎች ለመፍታትና የጤና ስኬቶችን ለማሻሻል የጤና ክብካቤ ፋይናንስ ዘላቂነትን

ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። ይህንን ለማሳካትም ከአገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች በቂ ሃብት ማሰባሰብ፣ የሃብት ምደባና ቅድሚያ አሰጣጥ ሥርዓትን ማሻሻል/ሪፎርም ማድረግ፣ የጤና መድን ሥርዓትን የሚፈለገው ደረጃ ላይ ማድረስ፣ የግልና የመንግስት ዘርፍ አጋርነትን ማጠናከር፣ የወጪ ማስመለስ ዘዴዎችን ማሻሻል፣ አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ፋይናንስ መተግበር፣ ወጪ ቆጣቢ የሃብትና አቅም አጠቃቀም ስልቶችን መንደፍና መተግበር ትኩረት የሚሰጣቸው ይሆናሉ።

አመራር፡-

የአመራር ትራንስፎርሜሽን አገራዊ ስትራቴጂክ ግቦችን ለማሳካት በሁሉም የጤና ሥርዓት ደረጃዎች የአመራር እና የአስተዳደር ሥርዓትን ማጎልበት ነው። በአመራር አባላቱ በኩል የሚታዩት የተጠያቂነት እጦት፣ የግልጸኝነት መጓደል፣ የጋራ ራዕይ ያለመያዝ፣ መረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ያለመስጠት፣ ቁጥጥርና ቅንጅት ያለመኖር የዘርፉ የአመራርና አስተዳደር ተግዳሮቶች ናቸው። የአመራር ጥበብ በጤና ሥርዓት አፈጻጸም ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ቁልፍ ምሰሶ ነው።

ዕቅድን ወደ ውጤት መለወጥ የሚቻለው በሁሉም የጤና ሥርዓት ደረጃ በአግባቡ የሚሰራ የአመራር አባል ሲኖር ነው። በመሆኑም በሁሉም ደረጃ አመራርን ትራንስፎርም ለማድረግ በዕቅዱ መሰረት የጤና ሥርዓትን መልሶ መቀየስና ማዋቀር፣ የተጠያቂነት ዘዴዎችን ተቋማዊ ማድረግ፣ የሕክምና አስተዳደርን ማጠናከር፣ የቁጥጥር ሥርዓቱ ራሱን እንዲችል ማድረግ፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና አጋርነት ማጠናከር፣ በሁሉም ደረጃ የመሪነት አቅምን ማጎልበት እና ‘ጤና’ በሁሉም ዘርፍ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች መካተቱን ማረጋገጥ የሚሉት ቁልፍ ተግባራት ይከወናሉ።



68

ሙሉ ማዕድ!

በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ



69

በፍቅርተ ባልቻ

አገራችን ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብቷ ከአፍሪካ አንደኛ፣ ከዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያስረዳሉ። በተያያዘም ግብርና የኢኮኖሚውን 40 በመቶ (GDP) ሲይዝ፣ ወደ ውጪ ከሚላከው ምርት 80 በመቶው ድርሻ አለው። ከአገሪቱ የሰው ኃይል ውስጥ 75 በመቶው በዚሁ መስክ የተሰማራ ነው። የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት “current situation of the livestock in Ethiopia” በሚል ርዕስ ይፋ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው 71 ሚሊዮን የቀንድ ከብቶች፣ 43 ሚሊዮን በጎች፣ 54 ሚሊዮን ፍየሎች፣ 57 ሚሊዮን ዶሮዎች፣ 13 ነጥብ 33 ሚሊዮን የጋማ ከብቶች እንዲሁም 7 ሚሊዮን የንብ መንጋዎች በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ጥናቱ አያይዞ እንደገለጸው ወደ ውጪ ከሚላኩት ምርቶች ውስጥ ከ16 እስከ 19 በመቶውን የሚሸፍነው የእንስሳት ሀብቷ ነው። በግብርና ከተሰማራው የሰው ኃይል ውስጥ 30 በመቶ ከእንስሳት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ስራዎች የተሰማራ ነው።



70

ስለሆነም የእንስሳት ሀብቱ እንደወተት፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር ያሉትን ምግቦች ለማግኘት እንጠቀምበታለን። እያንዳንዱ አባ ወራ እነዚህን የእንስሳት ተዋጽኦ የሆኑ ምግቦችን በመጠቀም ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉትን ንጥረ ምግቦች (ገንቢ እና ኃይል ሰጪ) ማግኘት ይችላል። የእንስሳቱን እና የእንስሳቱን ተዋጽኦ ለማሳደግ በአገሪቱ እምቅ አቅም አለ። በተያያዘ የሚነሳው በዓይነትም በቁጥርም በርካታ እንስሳት መኖራቸው፣ በአየር ንብረት እና መልክአምድራዊ አቀማመጥ የታደለች አገር መሆኗ ነው። በእንስሳት ሀብቱ ላይ ያለው ምርት እና ምርታማነት ዝቅተኛ ለመሆኑ በምክንያትነት ከሚነሱት ነጥቦች ውስጥ መስኩ በባህላዊ መንገድ የሚመራ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የማይጠቀም መሆኑ ይገኝበታል። ስለሆነም በአገሪቱ ያለው የእንስሳት ሀብትን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ለመሆን፣ ጥሪት እና ሀብት ለማፍራት አላስቻለም። መንግሥት ይህን በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት በመጠቀም የትሩፋቱ ተቋዳሽ መሆን ይቻል ዘንድ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ እቅዶች እያዘጋጀ ወደ ትግበራ ይገባል። በያዝነው በጀት ዓመትም ”የሌማት ትሩፋት“ የሚል ስያሜ የተሰጠውን አገር አቀፍ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ መርሃ ግብር ምንድን ነው? ዓላማው እና ከመርሃ ግብሩ የሚጠበቁ ውጤቶችስ የትኞቹ ናቸው? የሚል እና ሌሎች ተያያዥ ነጥቦችን በማንሳት ከግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ጋር ቆይታ በማድረግ የነበረንን እንደሚከተለው አጠናቅረነዋል፤ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ ተመኘን። ዝለቁ!

ነጋሪ፡- በቅድሚያ ለጊዜዎ ከልብ እናመሰግናለን!

ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፡- መረጃ እንድሰጥ ስለጋበዛችሁኝ እኔም አመሰግናለሁ!

ነጋሪ፡- የሌማት ትሩፋት ምንድን ነው?

አጀማመሩስ ምን ይመስላል? ዓላማውስ እንዴት ይገለጻል?

ዶ/ር ፍቅሩ፡- ሰው በቤቱ ገበታ ላይ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉ ንጥረ ምግቦችን ማግኘት ይኖርበታል። በተለይ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የፕሮቲን (protein) ይዘት ያላቸው ገንቢ ምግቦች በየቤቱ ገበታ ላይ ማቅረብ የተለመደ አይደለም፤ ከቀረበም በበዓላት እና ዝግጅቶች በሚኖሩበት ወቅት ነው። ለዛም ነው በእያንዳንዱ ቤተሰብ ቤት በሚቀርበው ገበታ ላይ በተለይ የፕሮቲን ይዘት ያላቸውን ምግቦች ለማቅረብ እንዲቻል የሌማት ትሩፋት የተሰኘ መርሃ ግብር ይፋ የተደረገው። እያንዳንዱ አርሶ እና አርብቶ አደር የራሱን ፍላጎት ያሟላል፣ ያተርፋል፣ የተረፈውን ለገበያ እንዲያቀርብ ማድረግ እንዲቻል በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ይሰራል። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተገኙበት ነው የተበሰረው። የሌማት ትሩፋት በእንስሳት ሀብት ላይ በተለይም በወተት ልማት፣ በዶሮ እንቁላል እና ስጋ፣ በማር እና በዓሣ ምርት ላይ አትኩሯል። በመደበኛ ስራ የምናመርተውን ካለን ሕዝብ ብዛት እና ጸጋ ጋር ስናስተያየው በቂ አይደለም። ስለሆነም በአጭር ጊዜ ውስጥ በሕዝብ ንቅናቄ፣ ቆራጥ አመራር ሰጪነት እና በጥሩ ክትትል እንዲሰራ ታቅዶ ነው የሌማት ትሩፋት ማስጀመሪያ ሥነ- ሥርዓት የተካሄደው። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተከታታይ ለአራት ዓመታት ሰርተን የምናሳካቸውን ስራዎች ለይቶ አስቀምጧል። ከተለዩት ተግባራት ውስጥ አሁን ላይ 7.1 ቢሊዮን ሊትር በዓመት የሚመረተውን የወተት መጠን ወደ 11.7 ቢሊዮን ሊትር ማድረስ አንዱ ነው። በዓመት 3.2 ቢሊዮን እንቁላል እያመረትን ሲሆን ይህን ቁጥር በአራት ዓመት ውስጥ ወደ 9.2 ቢሊዮን ማሳደግ ሌላው የሌማት ትሩፋቱ መርሃ ግብር ውጥን ነው። የዶሮ ስጋን ከ90 ሺ ቶን ወደ 240 ሺህ ቶን ለማሳደግም

በእቅዱ ተይዟል። በሌላ በኩል የማር ምርትን ከ147 ሺህ ቶን ወደ 296ሺህ ቶን፣ የዓሣ ምርትን ከ38 ሺህ ቶን ወደ 215 ሺህ ቶን ማድረስንም መርሃ ግብሩ አካቷል። አንድ ሰው በዓመት ውስጥ 200 ሊትር ወተት መጠጣት እንዳለበት ዓለም የጤና ድርጅት ይመክራል፤ ኢትዮጵያ 66 ሊትር ላይ ነች። ይህን ቁጥር በእጥፍ ብናሳድገው እንኳን የዓለም የጤና ድርጅት ያስቀመጠው ቁጥር ላይ ለመድረስ ይቀረናል። በሌማት ትሩፋቱም የወተት ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን ስራውን ከአራት ዓመትም በኋላ አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠይቀናል። ስለሆነም አሁን ላይ ማስጀመሩ፣ ወደ ስራ ማስገባቱ እና የአመለካከት ለውጥ ማምጣቱ ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን በሚል ታሳቢ ነው በዚህ ወቅት ይፈጸማል በሚል በእቅዱ የተያዘው እንጂ ከዛ በኋላ ስራውን እንተወዋለን ማለት አይደለም። ከዛም በኋላ በመደበኛ እቅዶቻችን ውስጥ ተካቶ ቀጣይነት ያለው ተግባር ይከናወናል። ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ወተትን በእጥፍ፣ እንቁላልን ሦስት እጥፍ፣ ስጋን በሦስት እጥፍ፣ ዓሣን ሶስት እጥፍ፣ ማርን በእጥፍ ለማሳደግ ነው ግብ የተጣለው። ይህን ውጥን ለማሳካትም የምንጠቀማቸው ስልቶች አሉ። በምን ሁኔታ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችልም ተለይቷል። ሰነዶች ተዘጋጅተዋል፣ ክልሎች በየትኞቹ ስራዎች ላይ ቢሰማሩ ውጤታማ ይሆናሉ የሚለውም ካላቸው እምቅ አቅም አንጻር ተለይቷል። ወደራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ቀይረው ወደ ስራ ገብተዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ የእንስሳት ሀብት እና ጸጋ ያላት አገር ሆና ሳለ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ከውጪ ታስገባለች። ይህም የአቅርቦት እጥረት እንዳለን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ ወተትን ብንወስድ የወተት ዱቄት ከውጪ ይገባል። ይህን በብዛት የምንጠቀመው በከተሜው አካባቢ ነው። ወደ ገጠሩ ስንወስደው ደግሞ ውስንነት አለ። ይህም



71

የሚያሳየው በቂ የሆነ አቅርቦት አለመኖሩን ነው። ወደ ውጪ መላክ ሲገባን በእንስሳት ተዋጽኦ በኩል ትልቅ እጥረት ነው ያለብን። የሌማት ትሩፋት የመጀመሪያ ዓላማው በምግብ እና በሥነምግብ ራስን መቻል ነው። ሌማቱ ሙሉ ሆነ ማለት በምግብ ራሳችንን ቻልን የሚለውን ነው የሚገልጸው። ከውጪ የምናስገባቸውን የእንስሳት ተዋጽኦዎች በአገር ውስጥ ምርት እንተካለን። ምርቱ ሲትረፈረፍ ወይም የአገር ውስጥ ፍጆታን ስናሟላ ወደ ሌሎች አገራት እንልካለን። በዚህ ሂደት በእንስሳት ሀብት ላይ ተሰማርቶ ያለውን ሰው ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን።

ነጋሪ፡- በሌማት ትሩፋቱ መርሃ ግብር እንደ አገር ምን ምን ስራዎች እየተከናወኑ ነው?

ዶ/ር ፍቅሩ፡- ኢትዮጵያ ሰፊ የእንስሳት ሃብት ቢኖራትም ምርት እና ምርታማነቱ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ ያንን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች (interven- tion) መስራት ይጠይቀናል። ለምሳሌ ከአገረሰብ ከብቶች (ከአንድ ላም) በቀን 1.5 ሊትር ወተት ነው የምናገኘው፤ የተሻሻለ ዝርያ የምንላቸው በአማካኝ እስከ 15 ሊትር ወተት ይሰጡናል፣ ስለሆነም ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ዝርያቸውን ማሻሻል ትልቁ እና ሰፊው ስራ ነው። በእንስሳቱ ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው ዝርያቸውን በማሻሻል ነው። ከዚህ አንጻር በክልሎች መነቃቃት ተፈጥሮ እንደየአካባቢው አቅም (Potential) በየክልሉ የማዳቀል ተግባር በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። የአገረሰብ ዝርያዎችን ከውጪ ከገቡ እና ከተሻሻሉ ዝርያዎች ጋር ማዳቀል፤ ይህም በሁሉም ክልል ላይ በስፋት እየተሰራ ያለ ነው። በተለይ ለወተት ላሞች እርባታ ምቹ በሆኑ ክልሎች በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው። የኮርማ ፍላጎት እንዲኖራቸው መርፌ ተወግተው ፍላጎታቸው ሲመጣ እንዲዳቀሉ ይደረጋል። በተጨማሪም የወተት ላሞች ቁጥር ለማሳደግ የሚፈለገው ወንዱ ጥጃ ሳይሆን ሴቶቹ ናቸው። ለዛ ጾታቸው የተለየ አባላዘር ከውጪ አስገብተናል፤

ይህ የኮርማ አባላዘር 90 በመቶው ጊደር የሚሆንበት ቴክኖሎጂ ነው። ይህን አስገብተን በክልሎች አከፋፍለናል። አምና 10 ሺህ ነው ለክልሎች የሰጠነው። በተመሳሳይ ዘንድሮም 10 ሺህ ገዝተናል፣ ከዚህ ውስጥ 7500 ተሰራጭቷል። የማዳቀል ስራውን እያከናወኑ ይገኛሉ። ይህ ዛሬ ዘርተን ነገ ውጤቱን የምናይበት ሳይሆን ከሁለት እና ሦስት ዓመታት በኋላ ትልቅ ለውጥ የምናገኝበት እና ወደ ውጤት የሚለወጥ ይሆናል። የእንስሳቱን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ ሌላው የቤት ስራ (intervention) የሚሆነው በአርብቶ አደሩ እጅ ያሉትን የተሻሻሉ የአገረሰብ ላሞችን የአመጋገብ ሥርዓት እንዲያሻሽሉ ማድረግ ነው። ዘንድሮ ለሁሉም ክልል ስልጠናዎችን ሰጥተናል። ዘንድሮ በበጋው ወቅት ትልቁ የእንስሳት መኖ የሰብል ተረፈ ምርት ነው። ምክንያቱም የግጦሽ ቦታ እያነሰ በሄደ ቁጥር የሰብል ምርቱ ይሰፋል፤ የሰብል ተረፈ ምርቱ ደግሞ የእንስሳት መኖ የሚሆንበት ሁኔታ ይፈጠራል። ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ የተሻሻለ የመኖ ዘር እንዲያገኙ ተደርጓል። እዚህም ላይ ከሁሉም ክልል የተውጣጡ ባለሙያዎች አሰልጥነን፣ የሰለጠኑት ባለሙያዎች ደግሞ አርሶ እና አርብቶ አደር አካባቢ ገብተው የተግባር ስልጠና ሰጥተዋል። ከዚህ ጎን ለጎን የሚከናወነው ሌላው ተግባር የእንስሳትን ጤንነት አጠባበቅ ማሻሻል ነው። በእንስሳትም ጤና በኩል ያደረግነው ድጋፍ የሚወለዱ ጥጆች ማደግ አለባቸው፣ የጥጆችን ሞት መቀነስ አለብን የሚል ፓኬጅ አዘጋጅተን የልማት ትሩፋቱን ለመደገፍ በተለይ ወተት የማምረት አቅም (dairy potential) ላላቸው ክልሎች በቀጥታ በግብርና ሚኒስቴር እንዲሰጣቸው ተደርጓል ። ዶሮም ጋር ስንሄድ በተመሳሳይ ዝርያ ካላሻሻልን ለውጥ ማምጣት አንችልም። አንዷ የአገረ ሰብ ዶሮ 40 እንቁላል ነው በዓመት የምትጥለው፣ የተሻሻለችው ደግሞ በዓመት 300 እንቁላል ትጥላለች። ስለዚህ በመስኩ የተሰማሩ አካላት የተሻሻሉ ዘመናዊ ዝርያ ይዘው ማልማት ያለባቸው የሚለውን አቅጣጫ ይዘን እየሰራን ነው። ይህን

የተሻሻለ ዝርያ የምንላቸው በአማካኝ እስከ 15 ሊትር ወተት ይሰጡናል፣ ስለሆነም

ምርታማነታቸውን ለማሳደግ ዝርያቸውን

ማሻሻል ትልቁ እና ሰፊው ስራ ነው።

በእንስሳቱ ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት

የሚቻለው ዝርያቸውን በማሻሻል ነው።



72

ውጤት ለማምጣት ግን ብዙ ስራዎችን ማከናወን ይጠይቃል። የተሻለ መኖ መመገብ፣ ተስማሚ የሆነ መኖሪያ ቤት እና ሌሎች ግብዓቶችን ማሟላት ያስፈልጋል። አንድ አርሶ እና አርብቶ አደር 25 ዘመናዊ እና 5 ባህላዊ ዶሮ ቢይዝ 30 ዶሮ እንዲኖረው ነው እንደአቅጣጫ አስቀምጠን እየሰራንበት ያለው። በዚህም አርሶ እና አርብቶ አደሩ በየቤቱ በአማካኝ 24 እንቁላል በቀን ያገኛል ማለት ነው። ይህን በራሱ ለቤቱ ይጠቀማል ከዛ የሚተርፈውን ደግሞ ለገበያ ያቀርባል፤ ገንዘቡን ለሚፈልገው ነገር ሊያውለው ይችላል። በባህላዊው ከአንድ ቀፎ በዓመት 10 ኪሎ ግራም ማር ነው የሚቆርጠው። ዘመናዊውን ቀፎ በመጠቀም እስከ 30 ኪሎ ግራም ማር በአንድ ጊዜ ይቆረጣል፤ የንብ ቀሰም የሚሆኑ ተክሎችን/ እጽዋት ከተተከሉ፣ በዓመት እስከ 3 ጊዜ የመቁረጥ እድል ይኖራል። ኦሮሚያ ክልል በጅማ ከተማ ከሁለት ዓመት በፊት የንብ ቀፎዎችን በማሰራጨት ተጀምሯል። ኦሮሚያ 100 ሺህ ቀፎ አሰራጭቷል። ይህን ተሞክሮ ወደ ሌሎች ክልሎች ማስፋፋት ያስፈልጋል። እንደየአጀማመራቸው የዘመናዊ ቀፎ ስርጭት እየተካሄደ ነው። በሌማት ትሩፋቱ መርሃ ግብር ላይ ዘግይቶም (ወደ ኋላ ላይ) የዓሣን ስራ ይዘናል። በተያያዘም የተቀመጠው አቅጣጫ ወንዞች እና አጠቃላይ የውሃ አካላትን በተገቢው መጠቀም እንደሚገባ ነው። ዓሣዎቹ በራሳቸው ሲራቡ መጠቀም ብቻ ሳይሆን በውሃ አካላቱ ላይ (በሐይቆች እና በወንዞች) የዓሣ ጫጩት በመጨመር እና አስፈላጊ ሲሆን ምግብ በመስጠት ምርት እና ምርታማነትን ማሳደጉ ወሳኝ ነው። ሰው በየቦታው በገንዳ አማካኝነት ዓሣ ማርባት እንዲጀምር እና መጀመሪያ ለራሱ ቤተሰብ እንዲመግብ፣ የሚተርፈውን ደግሞ ለገበያ እንዲያቀርብ ይጠበቃል። ለዚሁ ስራ የሚውሉ እና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። በተያያዘ የዓሣ ጫጩት ማሰራጫ መኪኖች ለክልሎች እየሰጠን ነው።

ነጋሪ፡- ከሌማት ትሩፋት ጋር በተያያዘ በልዩ ሁኔታ ተግባራዊ የተደረጉ አሰራሮች እንዲሁም የክትትል እና ድጋፍ አግባቦች ካሉ ቢገልጹልን?

ዶ/ር ፍቅሩ፡- የወተት፣ የዶሮ፣ የማር፣ የዓሣ ስራው ስኬታማ እንዲሆን በአደረጃጀት መታገዝ ይኖርበታል። አደረጃጀቱ ስራውን ለመከታተል፣ ለመደገፍ፣ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሟላት፣ የገበያ ትስስር የመፍጠር ሰፊ ፋይዳ አለው። ስለሆነም ቴክኖሎጂ እና ግብዓት ለማቅረብም መደራጀታቸው ይጠቅማል፤ ምርቱን ወደ ገበያ ለማቅረብም የመንደር አደረጃጀቱ ወሳኝ ነው።

የበቆሎ፣ የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ (ክላስተር) የምንለውን ወደ እንስሳት ሀብት ዘርፍ ስናመጣው የመንደር አደረጃጀት እንዲሆን ነው ያደረግነው። በዚህም መሰረት የወተት፣ የማር፣ የዓሣ የመሳሰለው መንደር ይኖረናል ማለት ነው። ስንት መንደር ያስፈልጋል? የትኛው ብዙ መንደር አለው? የምን መንደር ነው የሚደራጀው? የሚለው እንደክልሉ ሁኔታ የተለያየ ነው የሚሆነው። መንደሮቹ ስለሚታወቁ ወተት የሚመረትበት ቦታ በቀጥታ የሚያስፈልጉትን ቴክኖሎጂዎች እና ግብዓቶች ይዘን እንሄዳለን። የሚመረትበትን ቦታ ካወቅነው ምርቱን ሳይበላሽ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለገበያ ለማቅረብ ቀላል ይሆናል። ጎን ለጎን የሌማት

ትሩፋት ዓላማውን እና ጥቅሙን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እስከታች ባለው አደረጃጀት እየተሰራ ነው። ሴቶች ብቻ የተደራጁበት የዓሣ ማምረት፣ የዶሮ እርባታ ስራ አለ። ዜጎች ተደራጅተው የራሳቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ያለው። እኛም እነሱን ለማገዝ፣ ለማሳደግ እየሰራን ነው። አቅማቸው እና ካፒታላቸው እያደገ በሄደ ቁጥር ወደ ህብረት ስራ ማህበር የሚያድጉበትን አሰራር ነው እየዘረጋን ያለነው። የሌማት ትሩፋቱን ለመተግበር ከሙያዊ እገዛው ባሻገር የአሰራር ሁኔታውም በትክክል መታየት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል። የሌማት ትሩፋትን እንተገብራለን ስንል ብቻ አይደለም የቃኘነው። የሌማት ትሩፋት መክፈቻ በተከናወነበት ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየክልሉ ያለውን የሌማት ትሩፋትን ስራ የሚከታተሉ፣ የሚደግፉ ሻምፒየንስ/አምባሳደር ተብለው

ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ



73

የተመደቡ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች አሉ። እነዚህ አምባሳደሮች ከክልል ፕሬዝዳንቶች ጋር አብሮ ለመስራት ቃል ገብተዋል። ሌላው የሌማት ትሩፋትን ስኬታማ ለማድረግ የተበጀው አሰራር የፌዴራል አስተባባሪ እና የፌዴራል ቴክኒክ ኮሚቴዎችን አዋቅሮ ወደ ስራ ማስገባት ነው። የአስተባባሪ ኮሚቴውን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ቴክኒክ ኮሜቴውን ደግሞ እንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ሚኒስትር ዲኤታ እንዲመሩት ተደርጓል። የቴክኒክ ኮሚቴው በቨርቹዋል በየሁለት ሳምንቱ እየተገናኘ ይወያያል። በውይይቱም አፈጻጸሙ ምን እንደሚመስል፣ ያጋጠሙ ችግሮች ይቀርባሉ። በቴክኒክ ኮሚቴው መፈታት ያልቻለውን ችግር ለአስተባባሪ ኮሜቴ ሪፖርት ያደርጋል። የአስተባባሪ ኮሚቴው ከሻምፒዮኖቹ ጋር በየ3 ወሩ ተገናኝተው ይወያያሉ። ስራው የደረሰበትን ደረጃ ይገመግማሉ፣ ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ ያበጃሉ። በፌዴራል ደረጃ ያለው አስተባባሪ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አደረጃጀት ክልሎች አላቸው። በዞን፣ በወረዳ፣ ቀበሌ ድረስ አደረጃጀቱ ተዋቅሮ እየተሰራበት ነው። ስለሆነም በዚህ መልኩ ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል። በቅርቡም የአንድ ቀን ጫጩቶችን ከውጪ ለማስመጣት የውጪ ምንዛሪ እጥረት አጋጥሞ በዚህ አደረጃጀት አማካኝነት ገንዘብ ማግኘት ተችሏል። ከታች ያለው እንቅፋት፣ የገጠማቸው ችግር ምን እንደሆነ እናያለን፣ ከላይ ያሉት አመራሮች ደግሞ በዚህ መልኩ ምላሽ እየሰጡ ነው።

ነጋሪ፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ይፋ መሆንን ተከትሎ የአርሶ አደሩ ምላሽ እና አቀባበል ምን ይመስላል? የባለድርሻ እና አጋር አካላትን ተሳትፎስ እንዴት ይገልጹታል?

ዶ/ር ፍቅሩ፡- የማደራጀት፣ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በሁሉም ክልል በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው። እንስሳቶችን ለማርባት፣ ማርም ለማምረት ጥሩ መልክአ ምድር፣ ተስማሚ የአየር ንብረት አለን። የደን ሽፋኑም ጥሩ ነው። እንስሳቱም በቁጥር ብዙ ናቸው። በአፍሪካ ደረጃ ብዙ የንብ መንጋ ያላት አገር ናት። እንደዚህ ሆኖ ሳለ ወደ ማዕዳችን ስንመጣ በየጊዜው እጥረቱ እየከፋ ነው። የወተት፣ የእንቁላል፣ የማር፣ የዓሣ እጥረት እየገጠመ ነው። እየቻልን፣ ተፈጥሮም ጸጋ ቸራን እኛ አልሰራንበትም። ‘ለውጥ ማምጣት ይቻላል’ የሚውለውን ነገር ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ ስናስጨብጣቸው ትልቅ ፍላጎት እና መነሳሳት መጥቷል፤ ፋይዳውንም ተረድተውታል። በሌማት ትሩፋት በተሰሩት ስራዎች የመጣው ትልቁ ለውጥ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉትን ዘዴዎች

ለመጠቀም ፍላጎት መፈጠሩ ነው። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ ዝርያ አሻሽሉልን በሚል እየቀረበ ያለው ጥያቄ ነው፤ ይህ ከዚህ ቀደም የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ ፍላጎቱ በብዙ እጥፍ ጨምሯል። ‘አሁን ገብቶናል ግን ግብዓቶቹ ምንድን ናቸው? አምጡ‘ እያሉን ነው። አሁን ክልሎች 300 ሺህ እና ከዚያ በላይ ለማዳቀል አቅደው እየሰሩ ነው። ለምሳሌ ኦሮሚያ 500 ሺህ እንስሳት አዳቅላለሁ ብሎ አቅዷል። ለዚህም የሚረዳ አባላዘር፣ ፍሳሽ ናይትሮጂን ማቅረብ፣ ጾታው የተለየ ጊደሮች ብቻ የሚወለዱበት አባላዘር ማቅረብ ያስፈልጋል። ሌሎች የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎችም ፍላጎት አድጓል። ጫጩት አምጡልን እያሉ ነው። ይህም በሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴ የመጣ ለውጥ ነው። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን በአባወራ እና እማወራ ደረጃ ብቻ አይደለም ማሳካት የሚቻለው፤ የግል ባለሀብት በስፋት መሳተፍ አለበት። ለምሳሌ ከውጪ የሚገቡትን ነገሮች የሚያስገቡት ባለኃብቶች ናቸው። ለእነሱም በዛው ልክ ግንዛቤ ተፈጥሯል። የገበያ ፍላጎትም ስላለባቸው በየጊዜው ግብዓቶቹን ከውጪ ለማስገባት ያለው ጥረት ከፍተኛ እየሆነ ነው የመጣው። ከዛ አልፎ ተርፎ ደግሞ የመንግሥት ተቋማት ማባዣ ማዕከላት አሉ። ለእነሱም እንደዚሁ ግንዛቤ ተፈጥሮ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው። የተለያዩ የግል፣ የመንግሥት ተቋማት እና ተባባሪ ድርጅቶች ስራውን የመደገፍ ፍላጎት አላቸው። ለሌማት ትሩፋት የሚያስፈልጉ በተለይ የማዳቀል ስራ የአንድ ቀን ጫጩት፣ ዘመናዊ ቀፎ፣ የዓሣ ጫጩት ማከፋፈል ተጀምሯል። ከእሱ ጎን ለጎን የመኖ እና የእንስሳት ጤና ማስጠበቅ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያለው። ስለሆነም በየክልሉ የማዳቀሉ ስራ በስፋት እየተከናወነ ነው፤ እኛም የቻልነውን ግብዓት እያቀረብን ነው። ለማዳቀል የሚያገለግሉ አባላዘርን ጨምሮ፣ በዶሮ በኩል የአንድ ቀን ጫጩት እና የቄብ ስርጭት ነው። በመንግሥት የማባዣ ማዕከላትም፣ በግለሰቦች እና በካንፓኒዎችም እነዚህ ጫጩቶች እየተራቡ በየመንደሩ በየቀበሌው፣ በየክልሉ እየተሰራጩ ነው።

ነጋሪ፡- የእንስሳትን ተዋጽኦዎች ሳይበላሹ ወደ ከተሞች እና ወደ ተጠቃሚዎች ዘንድ ለማድረስ እና ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ምን እየተሰራ ነው?

ዶ/ር ፍቅሩ፡- በመንደር ስናደራጅ አንደኛው ጥቅሙ የገበያ ትስስር መፍጠር ነው። አንድ ሰው ለብቻው 20 ሊትር ወተት ትርፍ ቢያመርት ለዚች ተብሎ ገበያ ለማቅረብ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን

ማመቻቸት አስቸጋሪ ነው። 10 አርሶ እና አርብቶ አደር እያንዳንዳቸው ሃያ ሃያ ሊትር ቢያመርት 200 ሊትር ይሆናል። ይህን ለገበያ ወይም ለፋብሪካዎች ለማቅረብ አዳጋች አይሆንም። ተጨማሪ መንደሮችን እያደራጀን ስለሆነ ምርቱን ከገበያ ጋር ከማስተሳሰር ጋር በተያያዘ ያሉብንን እና ወደፊት ሊገጥሙን የሚችሉ ማነቆዎችን ከወዲሁ ማጤን ይጠይቃል። ምክንያቱም የገበያ ችግር አርሶ እና አርብቶ አደሩን ከጎተተው የስራ ሞራሉ ይነካል፤ ወደ ኋላ ይመለሳል፤ መስራት እንደሚችል እያወቀ ምርቱን ሸጦ ራሱን ካልደገፈ ስራውን ሊተወው ይችላል። ስለሆነም በተያያዘ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች እና አሰራሮች ከወዲሁ ማስተካከሉ ወሳኝ ነው። የእንስሳት ተዋጽኦዎች በፍጥነት ተጠቃሚዎች ዘንድ ካልደረሱ የመበላሸት እድላቸው ሰፊ ነው። ስለሆነም ማቀዝቀዣ እና ማጓጓዣ መኪኖችን ለማሟላት ጎን ለጎን መስራት ይጠይቃል። በቅርቡም ሰባት የወተት መኪኖችን (ቦቴዎች) ግዥ ፈጽመናል። እነዚህ መኪኖች ወተቶቹን ወደ ተጠቃሚዎች እና ድርጅቶች ለማድረስ የሚኖራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። ከዚህ ቀደም ስንጠቀምባቸው የነበሩትንም አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል። የወተት ማሰባሰቢያ ማዕከላትንም ማብዛት በጣም አስፈላጊ ነው። በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት ትልልቅ ግቦችን ይዞ ወደ ትግበራ የገባ መርሃ ግብር እንደመሆኑ እነዚህን ግቦች ማሳካት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይፈልጋል። እንስሳትን በማርባት የሚኖሩ አርብቶ አደሮች፣ ስራውን የሚደግፉ የግብርና ባለሙያዎች፣ የግል ባለሀብቱ፣ የመንግሥት መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራርን ሁለገብ ድጋፍ የሚጠይቅ መርሃ ግብር ነው። በሚዲያ በኩል ያሉትም ባለሙያዎች ግንዛቤ በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። የምርቱን ከገበያ (ተጠቃሚውን እና አምራቹን) ለማገናኘት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል። ተረባርበን ከሰራን በቅድሚያ የምንወቀስበትን መቀንጨር ታሪክ እናደርጋለን። ሰፊ መሬት ምቹ መልክዓምድር ይዘን እንስሳት እና የእንስሳት ተዋጽኦዎችን ከውጪ ማስገባት ትልቅ የታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገን ነው። ይህንንም ከማስቆም አልፎ ተርፎ ወደ ውጪ ልከን አገራችን ከእንስሳቱ እና የእንስሳት ተዋጽኦ ወጪ ንግድ የመጥቀም ውሳኔው በእጃችን ላይ ነው። ይህን መርሃ ግብር ስኬታማ ለማድረግ ሁላችንም የሙያ ኃላፊነታችን፣ የአመራር ሰጪነት እና የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አደራ እላለሁ።

ነጋሪ፡- ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን!

ዶ/ር ፍቅሩ፡- እኔም አመሰግናለሁ።



74

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና በኢዜአ ትብብር የተዘጋጀ

የዓይን ብርሃን

ታዳጊው - የትምህርት ክፍል



75

በመንገሻ ገብረሚካኤል

ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በዘርፉ ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት አበርክቷል። በሆስፒታሉ ውስጥ እያከናወነ ካለው አገልግሎት በተጨማሪ በዘመቻ መልክ የዓይን ቅድመ ምርመራ፣ የዓይን ሞራ ግርዶሽ እና የዓይን ቆብ መገልበጥ ቀዶ ሕክምና በማድረግ ቀደም ሲል በወራቤ እና በሰቆጣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፍቼ እና በአፋር ክልል ለሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት አገልግሎቱን እያበረከተ ይገኛል - የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዓይን ትምህርት ክፍል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የዓይን ትምህርት ክፍል ከአጋር ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች መምህራን መሠረታዊ የዓይን ልኬት ሥልጠና በመስጠት የዓይን ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች ቅድመ ልየታ እንዲያከናውኑ በማድረግ በዓይን ባለሙያዎች የታገዘ የመነጸር ልኬት እና ሕክምና እየሰጠ ይገኛል። በዓይን ሕክምና ትምህርት ሥልጠና በመስጠት የዓይን ስፔሻሊስት ሐኪሞችን አስመርቋል። በዚህም በአገሪቷ ያለውን የዓይን ሕክምና ባለሙያ እጥረት በመቀነስና ዓይነስውርነትን በማስወገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል። የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከዓይን ሕክምና ጋር ተያይዞ ምን እየሰራ ነው?

የዓይን ብርሃን

ታዳጊው - የትምህርት ክፍል



76

ምን ዓይነት ተግዳሮቶችስ እየገጠሙት ነው? የዚህ ጽሑፍ ዐበይት ማጠንጠኛ ነጥቦች ናቸው። ለዚህም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የዓይን ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር አዱኛ ልሳነወርቅ የሰጡንን መረጃ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ጥቂት ስለ የዓይን ጤና ችግር ዓይናችን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ከሚገኙ ነገሮች በብርሃን ሞገድ አማካኝነት መረጃ በመቀበልና ለአንጎላችን በማድረስ ምስል እንድንመለከት ያደርጋል። ከ85-90 በመቶ የሚሆነውን መረጃ ለአንጎል በማድረስ ዓይናችን እጅግ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል ። ዓይናችን ለእኛ የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ የተራቀቀ ተፈጥሯዊ ሥራ ስለሚያከናውን ራሱን ከአደጋና ከሽታዎች መታደግ የሚያስችሉ የተለያዩ መከላከያ ዘዴዎች አሉት። ይሁን እንጂ እነዚህ መከላከያ ዘዴዎች እንከን የለሽ ባለመሆናቸው ዓይናችን በተለያዩ በሽታዎች ይጠቃል። ድንገተኛ አደጋዎችም ይደርሱበታል። የዕይታ መቀነስ ወይም ዓይነ ስውርነት ከሚያመጡ የዓይን የጤና ችግሮች ዋናዎቹ ስንመለከት፦ በመነጽር ሊስተካከል የሚችል የዕይታ ችግር (Refractive error) ይህ የዕይታ ችግር በአገራችን ከፍተኛ የዕይታ መቀነስ በማምጣት ከሞራ ግርዶሽ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በ1998 ዓ.ም የተካሄደ የእይታ መቀነስና ዓይነ ስውርነት መንስኤ አሰሳዊ ጥናት ያመለክታል። በትምህርት ላይ ያሉ ልጆች ለዚህ ችግር ከፍተኛ ተጋላጭ ሲሆኑ፤ ችግሩም የመማር ችሎታቸውን ከመቀነስ በተጨማሪ በአካላዊና አእምሮአዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። የሚከሰተው የእይታ ችግር ደረጃውና ዓይነቱ የሚለያይ ሲሆን፤ በዋናነት የዓይን ቅርጽና መጠን እንዲሁም የዓይን የብርሃን አቅጣጫ የማስቀየር ኃይል ናቸው። በአጠቃላይ አራት ዓይነት በመነጽር ሊስተካከሉ የሚችሉ የእይታ ችግሮች አሉ። እነዚህም በቅርብ የማየት ችግር (Hyperopia) ፣ በርቀት የማየት ችግር (Myopia) ፣ አጠቃላይ እይታ ብዥብዥታ (Astigmatism) እና በእድሜ መግፋት ምክንያት የሚመጣ በቅርብ የማየት ችግር (Presbyopia) ናቸው። በቅርብ የማየት ችግር (Hyperopia) መጠኑ ትንሽና አጭር የሆነ ዓይን ሲኖረን ወይም የዓይናችን የብርሃን አቅጣጫ የማስቀየር ኃይል አነስተኛ ሲሆን ነው። ምልክቶችም የቅርብ እይታ

መደብዘዝ፣ የዓይን ድካም ስሜት፣ በዓይን ዙሪያ ህመም መሰማት፣ የዓይን መቅላትና ማቃጠል፣ የራስ ህመም፣ የዓይን መንሸዋረር ናቸው። በርቀት የማየት ችግር (Myopia) በመባል የሚታወቀው የእይታ ችግር መጠኑ ትልቅ የሆነ ዓይን ሲኖር ወይም የዓይን የብርሃን አቅጣጫ የማስቀየር ኃይል ከፍተኛ ሲሆን ነው። የርቀት እይታ መደብዘዝ የችግሩ ምልክት ሲሆን፤ ይህ ችግር በዘር ሊተላለፍ ይችላል። ከፍተኛ የሆነ በርቀት የማየት ችግር ያለባቸው ሰዎች ለብርሃን መቀበያ የዓይን ክፍል (ረቲና) መላቀቅ የተጋለጡ ስለሆነ መደበኛ የዓይን ምርመራ ማድረግና የብርሃን መቀበያ መላቀቅ ምልክቶችን (የብርሃን ብልጭልጭታ፣ ጥቃቅን እና ጥቋቁር የሸረሪት ድር የሚመስሉ ነገሮች ማየት፣ የእይታ አድማስ ከፊል ግርዶሽ ወዘተ) ማወቅና ምልክቶች ሲታዩ ወዲያውኑ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ በዓይን ሐኪሞች መታየት ያስፈልጋል ። አጠቃላይ እይታ ብዥብዥታ በቅርብ ወይም በርቀት የማየት ችግር ጋር በጥምረት ሊከሰት ይችላል ። በእድሜ መግፋት ምክንያት የሚመጣ በቅርብ የማየት ችግር (Presbyopia) እድሜ እየጨመረ ሲሄድ (በተለይም ከ40 ዓመት ጀምሮ) የተፈጥሮ ሌንስ እየጠነከረና ቅርጹንም የመቀያየር ችሎታው እየቀነሰ ስለሚሄድ በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ ነገሮችን ለማየት ወይም ለማንበብ፣ ክር በመርፌ ቀዳዳ ለማስገባትና ለመስፋት፣ የሞባይል ቁጥሮችን ለማየት ወዘተ ለማየት ሲሞከር አስቸጋሪ ይሆናል። እነዚህ የእይታ ችግሮች በባለሙያ በሚደረግ የዓይን ምርመራ የችግሩን ዓይነት፣ መጠንና ያስከተሉትን ተያያዥ ችግር ማወቅና ማረጋገጥ የሚቻል ሲሆን፤ በወቅቱ አስፈላጊውን የዓይን ሕክምና መካሄድ የተስተካከለና የጠራ እይታ እንዲኖር ማድረግ ያስችላል። በብዛትና በዋናነት የሚደረገው ሕክምና መነጽር ወይም ተለጣፊ ሌንስ ማድረግ ነው። መነጽር ማድረግ ለማይፈልጉ ሰዎች ቀላልና ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና አማራጮች አሉ። ለምሳሌ በጨረር የዓይን መስታወት ቅርጽ መቀየር፣ ዓይን ውስጥ ሰው ሰራሽ ሌንስ ማስገባት፣ የተፈጥሮ ሌንስን ማውጣት ይገኙበታል። የዓይን ሞራ (Cataracts) በአገራችን ለዓይነ ስውርነት ከሚዳርጉ ሕመሞች መካከል የሞራ ግርዶሽ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል። ለሞራ መከሰት አያሌ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን፤ ዋና ዋና የእድሜ መግፋት (እርጅና

)፣ በሌንስ ላይ የሚደርስ አካላዊ ጉዳት፣ የስኳር ህመምና ሌሎች መሠል የጤና ችግሮች፣ ለሕክምና የሚወሰዱ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ በሌሎች የዓይን ህመሞች እንዲሁም ተፈጥሮአዊ በሆኑ የዓይንና ሌሎች አጠቃላይ የጤና ችግሮች፣ በተለይም ገና በተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ልጆች ላይ የሚከሰት የሞራ ችግር ናቸው። ሂደታዊ የእይታ መቀነስ፣ በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ ለማንበብ መቸገር፣ የቀለማት ድምቀት መቀነስ፣ በብርሃን ነጸብራቅ መቸገር እና አንድ ነገር ሁለት ሆኖ የመታየት ችግር ደግሞ የዓይን ሞራ ምልክቶች ናቸው። ለሞራ ግርዶሽ የሚደረገው ሕክምና በዋናነት የሞራ ቀዶ ሕክምና ነዉ። የሚደረገው ቀዶ ሕክምና ሞራ ያለበትን የተፈጥሮ ሌንስ በማውጣት በሰው ሰራሽ ሌንስ መተካት ነው። የዓይን ማዝ (Trachoma) የዓይን ማዝ Chlamydia trachomatis በሚባል በዓይን በማይታይ ረቂቅ በሽታ አምጭ ተህዋስያን አማካኝነት የሚመጣ ተላላፊ የዓይን ቆብ ምርቀዛ ነው። የግልና የአከባቢ ንጽሕናን ባለመጠበቅ ምክንያት ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ በንክኪ እንዲሁም በዝንብ አማካይነት ይተላለፋል። ይህ ዓይነት የዓይን ህመም ያለበት ሰው የመቆርቆር ስሜት፣ የማቃጠል ስሜት፣ የዓይን መቅላት፣ የእንባ መፍሰስ፣ ብርሃን ማየት መፍራት እና የዓይናር መያዝ የመሳሰሉት ምልክቶች ይታዩበታል። የዓይን ማዝ በሽታ ዓይነ ቆብን በተደጋጋሚ ሲያጠቃ እንዲሁም የዓይን ቆብ ምርቀዛ ለረጅም ጊዜ ሲቆይ የዓይን ቆብ የውስጥ ክፍል ጠባሳ እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህ ጠባሳ እየበዛ ሲሄድም የላይኛው ዓይነ ቆብ ወደ ውስጥ እንዲገለበጥ በማድረግ የዓይን ሽፋሽፍት



77

የዓይን መስታወትን እንዲወጋና እንዲፈገፍግ በማድረግ ተደጋጋሚ የዓይን መስታወት ብግነት እና ከፍተኛ የሆነ የዓይን ህመምና የመቆርቆር ስሜት ያስከትላል። በመጨረሻም በዓይን መስታወት ላይ ጠባሳ በመፍጠር ለዓይነ ስውርነት ይዳርጋል። የዓይን ማዝ በሽታን ለመከላከልና ብሎም ለመታከም የማመንን (SAFE) ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም የዓይነ ቆብ መቀልበስን በቀዶ ሕክምና ማስተካከል (S-Surgery)፣ ጸረ-ባክቴሪያ የዓይን መድኃኒት ሳያቋርጡ መጠቀም (A-Antibi- otics)፣ የፊት ንጽሕናን መጠበቅ (F-Facial cleanliness) እንዲሁም የግልና የአካባቢ ንጽሕና መጠበቅ (E-Environmental hy- giene and sanitation ) ዋነኛቹ የመከለከያ መንገዶች ናቸው። የዓይን ግፊት ህመም (Glaucoma) ግላኮማ ዓይናችን በብርሃን አማካኝነት የሚቀበለውን መረጃ ለአንጎላችን የሚያደርሰውን የእይታ ነርቭ በማጥቃት ለዓይነ ስውርነት የሚዳርግ የዓይን ጤና ችግር ነው። በዓይን ሞራ እንዲሁም በዓይን ማዝ የሚመጣን ዓይነ ስውርነት በቀዶ ሕክምና ሰዎች ችግሩ ከመከሰቱ በፊት ወደ ነበራቸው እይታ ወይም ተቀራራቢ የእይታ መጠን መመለስ ሲቻል በግላኮማ ምክንያት የመጣን የእይታ መቀነስ (ዓይነ ስውርነት) ግን መመለስ አይቻልም። ስለዚህ የሕክምናው ዋና ዓላማ ህመሙ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስና የጉዳቱ መጠን እየከፋ እንዳይሄድ ማድረግ ነው። የበሽታው ምልክት እንደ ግላኮማው ዓይነት የሚለያይ ሲሆን፤ በአብዛኛው የሚከሰተው

(Open Angle) ግላኮማ የእይታ ነርቭ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀስ በቀስ በመሆኑ ህመሙ ሲጀምር ምንም ዓይነት ምልክት አያሳይም፤ በሂደትም የእይታ አድማስ መጥበብ፣ የርቀት እና የቅርብ እይታ መቀነስ ናቸው። ለግላኮማ ህመም የሚደረጉ ዋና ዋና የሕክምና አይነቶች ስንመለከት የመድኃኒት ሕክምና፣ የብርሃን ጨረር ሕክምና፣ የዓይን ግፊት ቀዶ -ሕክምና የመሳሰሉት አማራጮች እናገኛለን። በስኳር ህመም ምክንያት የሚመጣ የዓይን ብርሃን ተቀባይ ክፍል (ረቲና) ጤና መታወክ (diabetic retinopathy) የስኳር ህመም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ በሚገኙ የደም ስሮች፣ ነርቮች እና ፈሳሽ አመንጭ የተፈጥሮ እጢዎች ላይ ጉዳት ከማድረሱም በላይ አጠቃላይ በሽታ የመቋቋም አቅምን ያዳክማል። ዓይናችንም የራሱ የሆኑ የደም ስሮች፣ ነርቮች፣ ፈሳሽ አመንጭ የተፈጥሮ ዕጢዎች፣ በሽታ ለመቋቋም የሚረዱ ህዋሳትና ሌሎች ተፈጥሯዊ የበሽታ መከላከያ መሣሪያዎች አሉት። የስኳር ህመም በእነዚህ ለዓይን ህልውና አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ጉዳት በማድረስ በዓይን ላይ የተለያዩ ችግሮች እንዲከሰቱ ያደርጋል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱና በከፍተኛ ሁኔታ የእይታ መቀነስና ዓይነ ስውርነት እያስከተለ ያለው በስኳር ህመም ምክንያት የሚመጣ የዓይን ብርሃን ተቀባይ ክፍል (ረቲና) የጤና መታወክ (diabetic reti- nopathy) ነው። የስኳር ህመም የቆይታ ጊዜ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የረቲና ጤና መታወክ የመከሰት እድሉ እየጨመረ ይሄዳል ። የመከሰት ምጣኔው እንደ ስኳር ህመሙ ዓይነት ይለያያል። ዓይናችን የሚያስልገውን ምግብ፣ ንጥረ ነገርና ኦክስጅን የሚያቀርብለት ደም ቅዳ እንዲሁም አገልግሎት ላይ የዋለና የተቃጠለውን ተረፈ ምግብና ንጥረ ነገር የሚያስወግድበት ደም መልስ አለው። የስኳር ህመም በረቲና የደም ስሮች ላይ ጉዳት በማድረስ ደም እንዲፈስና ረቲናው ውሃ መሠል ፈሳሽ እንዲቋጥር በማድረግ እብጠት ያስከትላል። የደም መፍሰሱ እንዲሁም የረቲና እብጠት ከፍተኛ ከሆነ ወይም ዋና የማያ ክፍል የሆነውን ሠገነተ እይታ(ማኩላ) ጉዳት ከደረሰበት የእይታችን መጠንና ጥራት ይቀንሳል። በረቲና የደም ስሮች ላይ የደረሰው ጉዳት እየጨመረ ከሄደና ዋና የችግሩ መንስኤ የሆኑትን የጤና እክሎች ማከምና መቆጣጠር ካልተቻለ ለዓይናችን የሚደርሰው የደምና ኦክስጅን መጠን በከፍተኛ ደረጃ ስለሚቀንስ ረቲና

ተገቢውንና የሚጠበቅበትን ሥራ ለማከናወን የማይችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። ረቲና ሥራውን በጥራትና በተፈለገው መጠን ለማከናወን ከፍተኛ የሆነ የኦክስጅን መጠን ስለሚፈልግ የከፋ የኦክስጅንና ሌሎች ንጥረ ነገሮች እጥረት ሲከሰት ችግሩን ለማቃለልና እይታችንን ለመታደግ ዓይናችን የራሱን እርምጃ ይወስዳል። የሚፈለገውን የኦክስጅን መጠን በበቂ ሁኔታ ለማግኘት እንዲችል አዳዲስ የደም ስሮች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። እነዚህ የተፈጠሩት አዳዲስ የደም ስሮች ግድግዳ ጥንካሬና ጥራት የጎደለው በመሆኑ ደምና ሌላ ፈሳሽ በቀላሉ ሾልኮ እየወጣ በረቲና ላይ የተከሰተው የመድማትና የማበጥ ችግር እንዲባባስ በማድረግ እይታ በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጋል። ከዚህም በተጨማሪ አዳዲስ የተፈጠሩት የደም ስሮች በቀላሉ ስለሚጨማደዱ ረቲናን ከመደበኛ ቦታው እንዲላቀቅ ያደርጋሉ። በስኳር ህመም ምክንያት የሚመጣ የዓይን ብርሃን ተቀባይ ክፍል (ረቲና) ጤና መታወክ (diabetic retinopathy) ሕክምናው ጥብቅ የስኳር መጠን ቁጥጥርና ክትትል፣ የብርሃን ጨረር (የሌዘር ) ሕክምና፣ ዓይን ውስጥ የሚሰጥ የመርፌ ሕክምና (Avastine,Lucen- tis ,Eylea ,...)፣ የረቲና ቀዶ ሕክምና፣ የሰገነተ እይታ መጃጀት (Macular degeneration) ናቸው። የሠገነተ እይታ መጃጀት በእድሜ መጨመር ወይም በሌላ የዓይን ጤና መታወክ ምክንያት የሚመጣ የማዕከላዊ ረቲና ክፍል የመጃጀት ችግር ሲሆን፤ በተለያዩ ምክንያቶች የሚመጣ የዓይን መስታወት ጠባሳ (corneal opacity) እና በሕፃናት ላይ ዓይነ ስውርነት የሚያስከትሉ የተለያዩ ችግሮች የዓይን ጤና እክሎች ናቸው። የኮሌጁ የዓይን ትምህርት ክፍል የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዓይን ትምህርት ክፍል አጠቃላይ የዓይን ሕክምና፣ የትምህርት እና የምርምር አገልግሎቶችን ይሰጣል። የዓይን ሕክምና አገልግሎት የዓይን ሕክምና ክፍሉ ለድንገተኛ ህሙማን እና በሪፈራል ለሚመጡ ተመላላሽ ታካሚዎች አገልግሎቱን ይሰጣል። በውስጡም የተለያዩ ንዑሳን ክፍሎች አሉት። የመነጽር ልኬት እና ተያያዥ ምርመራዎች



78

ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ በመነጽር የሚስተካከል የእይታ ችግር ያላቸው ህሙማን የሚመረመሩበት እና የሚታከሙበት ክፍል ሲሆን፤ በተጨማሪም የተለያዩ አጋዥ ምርመራዎች በክፍሉ የሚገኙ ባለሙያዎች Optometrists እና Residents አማካኝነት ይከናወንበታል። ድንገተኛ እና ሌሎች አዳዲስ የዓይን ህሙማን መመርመሪያ ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ ድንገተኛ የዓይን ችግር ያጋጠማቸው ህሙማን የመጀመሪያ ምርመራ የሚያደርጉበት ክፍል ሲሆን፤ በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ በሪፈራል የሚመጡ አዳዲስ ህሙማን የሚመረመሩበት እና የሚታከሙበት ክፍል ነው። ነባር ተመላላሽ የዓይን ህሙማን መመርመሪያ ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ ነባር ተመላላሽ የዓይን ህሙማን የሚታከሙበት እና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። በክፍሉ የሚገኙ ባለሙያዎች፦ ጠቅላላ የዓይን ሐኪሞች፣ ረዚደንቶች፣ ኦፕቶሜትሪስቶችና ነርሶች ናቸው። የሕፃናት የዓይን ህሙማን ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ የተለያየ የዓይን ችግር ያለባቸው ሕፃናት (ከጨቅላ ሕፃናት ጀምሮ) የሚመረመሩበት፣ የሚታከሙበትና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መንሸዋረር ያጋጠማቸው አዋቂ ህሙማን የሚመረመሩበት፣ የሚታከሙበትና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። በዚህ ክፍል የሚሰጡ የሕክምና ዓይነቶች ስንመለከት የመነጽር ሕክምና፣ የመድኃኒት ሕክምና፣ የተንሸዋረረ ዓይን ማስተካከያ ቀዶ ሕክምና (ለሕፃናት እና ለአዋቂዎች)፣ የሕፃናት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና፣ በሕፃናት ላይ የሚከሰት የረቲና ካንሰር ሕክምና ናቸው። በክፍሉ የሚገኙ ባለሙያዎች፦ የሕፃናትና የዓይን መንሸዋረር ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ የሕፃናት ኦፕቶሜትሪስቶች፣ ረዚደንቶች እና ነርሶች ኣማካኝነት ሕክምናው ይስጣል። የግላኮማ ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ የግላኮማ ህሙማን የሚመረመሩበት፣ የሚታከሙበት እና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። የመድኃኒት ሕክምና፣ የብርሃን ጨረር (የሌዘር) ሕክምና፣ የግላኮማ ቀዶ ሕክምና በክፍሉ የሚሰጡ የሕክምና አይነቶች ናቸው። የረቲና ክፍል ፡- በዚህ ክፍል ውስጥ የረቲና ጤና መታወክ ያለባቸው ህሙማን ምርመራ፣

ሕክምናና ክትትል የሚያደርጉበት ነው። በዚህ ክፍል የሚሰጡ የሕክምና ዓይነቶች የብርሃን ጨረር (የሌዘር) ሕክምና፣ ዓይን ውስጥ የሚሰጥ የመርፌ ሕክምና፣ (Avastine,Lucentis,Ey- lea,steroids...) የረቲና ቀዶ ሕክምና ናቸው። በዚህ ክፍል ይሰጥ የነበረው የመርፌ ሕክምናና የረቲና ቀዶ ሕክምና በግብዓት እጥረት ምክንያት አገልግሎቱ ተቋርጧል። የኮርኒያ ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ የዓይን መስታወት እና ሌሎች ተያያዥ የዓይን የጤና ችግር ያለባቸው ህሙማን የሚመረመሩበት፣ የሚታከሙበት እና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። የመድኃኒት ሕክምና፣ የመነፅር ሕክምና፣ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና፣ የዓይን መስታወት ንቅለ-ተከላ፣ ሌሎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎቶች በዚህ ክፍል የሚሰጡ የሕክምና ዓይነቶች ናቸው። የኦኪዩሎፕላስቲ ክፍል፡- በዚህ ክፍል ውስጥ የተለያዩ የውጫዊው የዓይን ክፍል የጤና ችግር ያለባቸው ህሙማን የሚመረመሩበት፣ የሚታከሙበት እና ክትትል የሚያደርጉበት ክፍል ነው። የመድኃኒት ሕክምና፣ የእንባ ማስወገጃ ቱቦ ቀዶ ሕክምና የተለያዩ የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምና፣ ሰው ሰራሽ የዓይን ኳስ ተከላ እና ሌሎችም በኦኪዩሎፕላስቲ ክፍል የሚሰጡ የሕክምና ዓይነቶች ናቸው። የዓይን ክፍሉ የተለያዩ የቀዶ ሕክምና የሚሰራባቸው መለስተኛና ዋና የቀዶ ሕክምና ክፍሎች አሉት። ሆኖም ይህ ዋና የቀዶ ሕክምና ክፍል የሚገኘው ተመላላሽ ሕክምና ከሚሰጥበት ከሆስፒታል አጥር ውጭ እና እሩቅ በመሆኑ ታካሚዎችም ሆነ ሠራተኞች ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረጉ ይገኛሉ። የትምህርት አገልግሎት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዓይን ትምህርት ክፍል ከመስከረም 2008 ዓ.ም ጀምሮ የዓይን ሕክምና ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ይገኛል። የመጀመሪያ ዙር ስድስት ሰልጣኞችን መስከረም 2012 ዓ.ም ያስመረቀ ሲሆን፤ እስከአሁን ድረስ 20 የዓይን ሐኪሞችን በማስመረቅ በአገራችን ያለውን የዓይን ሐኪሞች እጥረት በማቃለል የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በሥልጠና ላይ የሚገኙ ጠቅላላ ሰልጣኞች ቁጥር 35 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ መምህራን የፌሎውሽፕ ሥልጠና ያገኙ ሲሆን፤ አሁንም በሥልጠና ላይ የሚገኙ አሉ። የዓይን ክፍሉ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የምርምር

አገልግሎት ሲሆን፤ ሰልጣኝ ተማሪዎች ከመምህራን ጋር በትብብር ለመመረቂያ የሚረዳቸውን የምርምር ሥራ ይሰራሉ። መምህራንም በየተመረቁበት የሙያ መስክ የተለያዩ ችግር ፈች የሆኑ የምርምር ስራዎች እያበረከቱ ይገኛሉ። ክፍሉ ያሉበት ፈተናዎች የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዓይን ትምህርት ክፍል ከሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች የተለያዪ የዓይን ሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች መበላሸት (OCT machine ,HVF machine ,VR machine,Pha- co machine,Cryo Machine, Laser Indi- rect ophthalmoscope)፣ በተለያዩ የዓይን ሕክምና መሳሪያዎች ጥገና ላይ በቂ ክህሎት ያለው ባለሙያ (Ophthalmic Biomedical Engineer) አለመኖር፣ የዓይን መመርመሪያ መሳሪያዎች እጥረት (VOLK)፣ ለተለያዩ የረቲና ጤና መታወክ የሚያገለግሉ በመርፌ የሚሰጡ መድኃኒቶች አለመኖር (Avastine, Lucen- tis,Eylea)፣ ለተለያዩ የዓይን ቀዶ ሕክምና የሚያገለግሉ ግብዓቶች በተደጋጋሚ እጥረት መከሰት፣ የተመላላሽ ሕክምና እና የኦፕሬሽን ክፍል መራራቅ፣ እንዲሁም አጠቃላይ አገልግሎት መስጫ ቦታ ጥበት ተጠቃሽ ናቸው። በዚህም የሕክምና ክፍሉ የተበላሹ የዓይን ሕክምና መስጫ መሳሪያዎች ጥገና እንዲደረግላቸው በሙያው ብቁ ሥልጠና ያለው Ophthalmic Biomedical Engineerእንዲመደብላቸው ጠይቀዋል። በተጨማሪም እጥረት ያለባቸው መሳሪያዎች፣ መድኃኒቶች እና ግብዓቶች ግዥ እንዲፈፀም እንዲሁም ሁሉም የአገልግሎት ዓይነቶች በተመሳሳይ ቦታ እንዲሰጥ በቂ ቦታ እንዲመቻችላቸው ነው የጠየቁት። የክፍሉ ቀጣይ እቅድ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አጥቢያ በሚገኙ የተመረጡ ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት ማስጀመር ቀዳሚው የሕክምና ክፍሉ እቅድ ነው። በዘመቻ የሚሰጠውን የሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ከዚህ ቀደም ከሚሰጥባቸው አካባቢዎች በተጨማሪ ለሌሎችም ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዓይን ሕክምና ትምህርት ሥልጠና የምንቀበላቸውን ሐኪሞች ቁጥር በአንጻራዊ ማሻሻል እንዲሁም በተወሰኑ የዓይን ድህረ ምረቃ እስፔሻሊቲ (ፌሎውሽፕ) ሥልጠና ማስጀመር ክፍሉ በቀጣይ ለማከናወን በእቅድ ያስቀመጣቸው ተግባራት ናቸው።



79



80




የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም