ነጋሪ መጽሔት 14ኛ ዕትም
ይጫኑ

1

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም ዋጋ 15 ብር



2

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ



3



4

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11 +251-11-56-39-31

+251-11-56-52-21

ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09 enanegari@gmail.comበኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ

በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት

ማውጫ

መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች

68

34

40

በሕግ ከመግዛት ወደ

በሕግ መተዳደር

የሙላት ጉዞ መካንነትን የሚያመክነው

ማዕከል የሽግግሩ

ምሰሶዎች



5

ዋና አዘጋጅ ገዛኸኝ ዳንጉል

ምክትል ዋና አዘጋጅ ፍጹምእሸት ሺመልስ

ከፍተኛ አዘጋጆች ፍቅርተ ባልቻ ታዬ ለማ

አዘጋጆች መንገሻ ገ/ሚካኤል ብርሀኑ ተሰማ አዲሱ ረታ አንዱንሰው ሺፈራው

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com

እርምት ባለሙያ ትዝታ ሁሴን

በቅድሚያ እጅ ነስተን እንኳን 2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አልን፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የከፍታ፣ የደስታና የሀሴት ዘመን ይሆንላችሁ ዘንድም ተመኘን። ውድ አንባቢያን ይህ አዲስ ዓመት የሰነቅናቸውን አበይት ጉዳዮች የምናሳካበት ይሁንልን።

አዲሱ ዓመት አንድም ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በህብረት እየተከላከልን፤ ሀገራችንን ከቫይረሱ ነፃ የምናደርግበት ነው። ሁለትም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የምንጀምርበትና የህዳሴያችንን የምስራች ፍሬ የምንቋደስበት ነው። በሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት 14 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለመያዝ የያዝነውን ውጥን በስኬት የምንደመድምበት ዓመትም ይሆናል።

በሌላ መልኩ በክረምቱ ወራት ባኖርነው የአረንጓዴ ልማት አሻራችን የተከልናቸውን ችግኞች እየተንከባከብን አጽድቀን የምናለማበት ነው። ዓመቱ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ተግተን እየሰራን አዳዲስ ውጤቶችን እየደመርን የኢትዮጵያን ከፍተና ብልፅግና እውን እያደረግን የልዕልና ጉዟችንን ወደፊት እያስፈነጠርን የምንገሰግስበት የብሩህ ተስፋ ዘመን እንደሚሆን እምነታችን የጸና ነው።

ነጋሪያችን በዚህ እትሟ ሕዝቦች በጋራ ማንነትና ባህል አማካኝነት ያዳብሯቸውና ከፍ ያለ ዋጋ የሰጧቸውና የማንነታቸው መገለጫ የሆኑ ዕሴቶች ለምን የኋልዮሽ ጉዞ ጀመሩ ስትል ጠይቃለች። የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪዎችንና የጥናት ውጤቶቻቸውን ዋቢ አድርጋም ሰፊና ጥልቅ መረጃዎችን ይዛ ቀርባለች።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተጽዕኖ በትሩን ካሳረፈባቸው ዘርፎች መካከል የትምህርት ዘርፍ አንዱ መሆኑን፤ በወረርሽኙ ሳቢያ የትምህርት ተቋማት በራቸው ተከርችሞ በዓለም ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ዕውቀት በሚቀስሙበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ለመቀመጥ መገደዳቸውንም በጥልቀት ዳሳለች።

የኢትዮጵያውያን ቀለም፣ ባህል፣ ታሪክ፣ እሴት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ ፍልስፍና፣ መስተጋብር ወዘተ… ተዋዝተው የሚቀርቡባትና የሚገለጡባት ኪነ-ጥበብ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ታውኳ በመቆዘም ላይ እንደሆነች፤ ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ስርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር የዘርፉ ባለሙያዎችን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አባላት ያሉት ሀገር አቀፍ የሚዲያና ኪነ-ጥበባት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑንም ተመልክታለች።

ነጋሪያችን በዐብይ ጉዳይዋ ታላቁ ህዳሴ ግድባችን ይህ ትውልድ በአብሮነት አሻራውን ያኖረበት፣ ዘመን ተሻጋሪ ድሎችን እያስመዘገበ ያለበት፤ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን የልማት፣ የዕድገት፣ የብልፅግና፣ የከፍታና የልዕልና መሰረት እና የኃይል ሙሌትና የብሩህ ብርሃን ተስፋ ነፀብራቅ መሆኑን በስፋት ዳሳ እኖሆ ብላለች።

በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን፣ በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የሕግ ልዕልና ወሳኝ መሆኑንም ተንትናለች። የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ነፃነት ምንነት፤ የነፃነት ማሳያዎች ምን እንደሆኑና ማንኛውም ሰው ነፃ እና ገለልተኛ በሆነ ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ ፍትሃዊ በሆነ አግባብ የመሰማት መብት እንዳለው በርካታ የሕግ ሰነዶችን ፈትሻለች።

በኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም የተከናወኑ አበይት ጉዳዮችን በአጭሩ ዳሳ ከ2013 ዓ.ም ተስፋ ጋር አዋዝታ፣ የኢትዮጵያን የብልፅግና ፍኖተ ካርታ የአስር ዓመት ውጥን አመላካቾችን በጥጎሽ መረጃ ይዛ ቀርባለች። በጤናው ዘርፍም የበርካቶችን ዐይናቸውን በዐይናቸው የማየት ህልም አጨናግፎ፤ ትዳር አፍርሶ፤ ለሥነ-ልቦና ስብራት ስለሚዳርገው መካንነት፣ መንስኤውና መፍትሄው መረጃዎችን ዳሳና ተንትና የዘርፉን ባለሙያዎች አነጋግራ አቅርባለች። ዝለቁ!

መልእክት

ፎቶግራፍ ሙሉቀን ገረመው በሀይሉ አስፋው ገብረመድን እንግዳ ወርቅነህ ረጋሳ

የዘመቻው

ከዋክብት

የዕሴቶቻችን የኋልዮሽ ጉዞ

6

12

22

28

50

ኢትዮጵያ አምናና ለከርሞው

የፍትህ ስርአቱ በህግ መነጽር

መካንነትን የሚያመክነው

ማዕከል



6

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

የዘመቻው ከዋክብት

ማህበረሰብ



7

በፍቅርተ ባልቻ

የትውልድ ዘመኑ 1978 ዓ.ም፣ ዕድገቱም አዲስ አበባ አውቶቡስ ተራ ነው። የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ መቐለ ዩኒቨርሲቲ አምርቶ በ1998 ዓ.ም በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል። በተመረቀበት የሙያ ዘርፍ ተሰማርቶ ራሱን መቻል ሲጀምር ሌላ የህይወት ጥሪ በጆሮው ያቃጭል ጀመር፤ ጥሪውን በጥሞና ሲያደምጥ፤ ጥሪው የጥበብ ማዕድ መሆኗን ተገነዘበ። መደበኛ ስራውን እየከወነ በተጓዳኝ በ2001 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማታው የትምህርት መርሃ ግብር ቴአትር ማጥናት በመጀመር ለጥሪው ምላሽ ሰጠ። ለህይወት መስመሩ መቀየር ምክንያት የሆነውን የቴአትር ጥበብ ትምህርቱን በብርቱ ትጋት ተያያዘው። በርትቶ የተጋ የድካሙን ፍሬ ይቋደሳልና ከሶስት ዓመት በኋላ በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ ህልሙን አሳካ። የቴአትር ጥበብ ፍላጎቱን ያዳበረው ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው። አጫጭር ልብወለድ እና ግጥሞችን መጻፍ ይሞካክር ነበር። በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ በቴአትር እና ስነጽሑፍ ክበብ ይሳተፍ ነበር።

የመጀመሪያ ስራው የሆነውን ´ብር አምባር´ የተሰኘውን ቴአትር እነሆ ብሏል። ቴአትሩ ለመድረክ የበቃው ግንቦት 2004 ዓ.ም ሲሆን፤ ተወዳጅነትን በማትረፉ ለሁለት ዓመት ከሰባት ወር ያህል ታይቷል። ሌላኛው በታህሳስ 2010 ዓ.ም ለመድረክ የበቃውና በተመልካቹ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘው ‘ከመጋረጃ ጀርባ’ የተሰኘው ቴአትር ነው። ‘ከመጋረጃ ጀርባ’ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት የሰንበት ቴአትር ሆኖ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ትዕይንቱ እስከ ተቋረጠበት መጋቢት 2012 ዓ.ም ድረስ ተመልካቹ ከአዳራሹ አቅም በላይ እየሆነ እስኪመለስ ድረስ ሲታይ ነበር። ከእነዚህም ባሻገር በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ “ወይ አዲስ አበባ” በተሰኘው የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ “የሁለት ኮንደሚኒዬሞች ወግ” የተሰኘ ስራው ቀርቧል። አልፎ አልፎም በጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ መጣጥፎችን ለአንባቢያን ያቀርባል-ወጣቱ የቴአትር ደራሲና ባለሙያ ቶፊቅ ኑሪ።

አርቲስቱ እስከ 2010 ዓ.ም ድረስ ቀን በሙያው እየሰራ፣ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ማታ ማታ የሥነ-ጽሑፍና ቴአትር ማዕድን ለተማሪዎች ሲያቋድስ ነበር። በኋላ ለቴአትር እና ሥነ-ጽሑፍ ሙሉ ትኩረቱን በመስጠት የሙሉ ጊዜ የቴአትር ባለሙያ



8

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ለመሆን ይወስናል-አርቲስት ቶፊቅ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በአቢሲኒያ የኪነ-ጥበብ እና ሞዴሊንግ ኮሌጅ ስለቴአትር አጻጻፍ፣ ትወና እና ዳይሬክቲንግ በማስተማር የቀረውን ሙሉ ጊዜውን በቴአትር ዝግጅት ለማዋል ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ ተግባር ለመቀየር ጊዜ አልፈጀበትም። ይሁንና ውሳኔውን የሚፈታተን ጥቁር እንግዳ በሩን እያንኳኳ። የእንግዳውን ድንገተኛ ክስተት ተከትሎ በሙያው ለመቀጠል፣ አልያም ወደ ሌላ ስራ ለመሰማራት ከራሱ ጋር ሙግት ገጥሟል። ሙግቱ ለምን ይሆን?

አይነኬው የጥበብ ፋይዳ ጥበብ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ እሳቤ እና የአኗኗር ዘይቤ ነጸብራቅ ናት። ኪነ-ጥበብ ማህበረሰቡ የተሰራበትን ባህል ታጎላለች፤ መልሳም አዎንታዊ አልያም አሉታዊ ተጽዕኖዋን በተደራሲያኑ ላይ ታሳርፋለች። አድማጭ፤ ተመልካች በቴአትር፣ በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በሥነ-ስዕል፣ በቅርፃ ቅርፅ፣ በሥነ-ፅሑፍ በመሳሰሉት የጥበብ ስራዎች አማካኝነት ትናንትን የኋልዮሽ ይቃኛል፣ ዛሬን ይመረምራል፣ ነገን አሻግሮ ይመለከታል።

ኢትዮጵያውያን ያለንን የራሳችን የሆነውን ቀለም፣ ባህል፣ እሴት፣ አስተሳሰብ፣ አመለካከት፣ ፍልስፍና፣ መስተጋብር ወዘተ… በጥበባቱ ተዋዝተው ሲቀርቡ የሚፈጥሩትን ደስታና ሀሴት ለማጣጣም ብዙ መልፋት ሳያስፈልግ በአንድ የጥበብ ማዕድ ላይ መታደም ብቻ በቂ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።ኪነ-ጥበብ የአንድ ማህበረሰብ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ሁሉ ትዳስሳለች፤ ማንነትንና የሀገርን ኃብት ትገልጣለች። በኪነ-ጥበብ አማካኝነት እነዚህ ሁሉ ማንነቶችና የሀገር ኃብቶች ይንጸባረቃሉ። ጥበብ ከፍ ያለ የማስተማር፣ የማዝናናት አቅም አላት፤ በሚሰሩ የልማትና የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር በመሳሰሉት ስራዎች ላይ ቁልፍ ሚናዋን ተጫውታለች፤ ባለሙያዎቹም ግንባር ቀደም ሆነው ሰርተዋል።

“ኪነ-ጥበብ ችግርን ለመቋቋም፣ የህብረተሰቡን ደስታም ደስታ ለማድረግ አቅም አላት። ጠላት ሀገርን በወረረበት ወቅት ከመሳሪያው በላይ አቅም የሆኑት የጥበብ ሰዎች ናቸው። መሳሪያ ለመተኮስ፣ ወኔ ለማግኘት፣ ሮጦ ጠላት ጋ ለመድረስ መጀመሪያ አእምሮን መገንባት፣ እራስን ማሳመን ያስፈልጋል። እልህና ቁጭት እንዲፈጠር የሚያስችሉ የጥበብ ስራዎችን እየሰሩ በሀገር ፍቅር ስሜት ጠላትን እንዲከላከሉ እንዲያሸንፉ የሚያስችሉ ሥራዎች ተሰርተዋል። ህብረተሰቡ ለሀገሩ ዘብ እንዲቆም ያስቻሉት፣ የአእምሮ ስንቅ የሆኑት የጥበብ ስራዎች ናቸው።‘’ ሲሉ የጥበብን ጠቀሜታ ያብራሩት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ተክሉ ናቸው። በጥበብ ውጤቶች የሀገር ገፅታ ይገነባል፣ ማህበረሰቡ ይተዋወቃል፤ ይህ የጥበብ ባህርይ ፋይዳዋን ከፍ እንደሚያደርገው ነው ሲሉም ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ‘’ኪነ-ጥበብ የአንድ ሕዝብ የስሜት የሰላ ጫፍ ናት’’ ሲል የኪነ-ጥበብን ከፍታ ያሳየበትን ሃሳብ ያጠናክራሉ።

እንደ አርቲስት ማስረሻ ገብረማሪያም ገለጻ አድማጭ ተመልካችን በማዝናናትና በማስተማር ባህልን፣ ቋንቋን

ከማሳደግና ከማስተዋወቅ አንጻር የጥበብ ማህበራዊ ጥቅም ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም። በሙያው የተሰማሩ ተቋማትና ባለሙያዎች በአንድ በኩል ግብር ከፋይ መሆናቸው በሌላ በኩል ስራዎቻቸው የገቢ ምንጭ በመሆናቸው ጥበብ ለሀገር ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት የድርሻዋን እየተወጣች ነው።

ዘርፉ እጅግ በጣም በርካታ የስራ ዕድል መፍጠሩን፣ ለባለሙያዎቹም በገቢ ምንጭነት እያገለገለ እንደሚገኝ፣ በሚገኘው ገቢም እራሳቸውንና ቤተሰባቸውንም ጭምር እያስተዳደሩበት መሆኑን አቶ ተፈሪ ይገልጻሉ። ጥበብ እያስተማረች በማዝናናት የማህበረሰቡን አስተሳሰብ የመቅረጽ አቅሟ ጎልቶ የሚጠቀስና አይነኬው ትሩፋቷም ነው ይላሉ።

እንደ አቶ ተፈሪ ማብራሪያ ኪነ-ጥበብ የምታድግበት ትልቁ መንገድ ትምህርትና ስልጠና በመሆኑ በሁሉም የትምህርት እርከኖች ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆ ማበልጸግ ያስፈልጋል። የባህል ዘርፉ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና እንዲካተት ተደርጓል። ከ60 ለሚልቁ ሙያዎች ደረጃ ተቀርጾላቸዋል። ከደረጃ አንድ እስከ አራት ስልጠና የሚሰጥበት አሰራር ተዘርግቷል። ባለሙያዎች በማህበር ተደራጅተው ስለሙያቸውና ስለመብታቸው የሚመክሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ባህላዊ መገለጫዎቻችን እንዲተዋወቁና የኪነ-ጥበብ ስራዎች እንዲስፋፉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በዚህም በዘርፉ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ቁጥር አድጓል። ሀገራችንን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ በሚያግዙ ዝግጅቶች የሚሳተፉ ማህበራትና ባለሙያዎችም አሉ።

በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ቀደም ብሎ በነበሩት ጊዜያት ከጸጥታና አለመረጋጋት ስጋት ጋር በተያያዘ በቴአትር ቤቶች የተመልካች ቁጥር ቀንሶ ነበር። ከለውጡ በኋላ ግን በማህበራዊ ሚዲያዎች ጭምር እንደ ፊልሞችና ድራማዎች የመሳሰሉ የኪነ-ጥበብ ስራዎች መቅረብ ጀምረው እንደነበር ነው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ አርቲስት አብዱልከሪም ጀማል የሚገልጸው። ምንም እንኳን ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም፤ የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከመከሰቱ ቀደም ብሎ ባሉት ጊዜያት በኢንዱስትሪው ከፍተኛ መነቃቃትና ዕድገት እንደነበር አርቲስት ማስረሻ ይገልጻል። አዲስ ባለሙያዎች የተሳተፉበትና የተዋወቁበት እንዲሁም አዳዲስ ስራዎች እየቀረቡ የነበረበት ወቅት በመሆኑ የአድማጭ ተመልካቹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን በአብነት ይጠቅሳል።

የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኃብታሙ ተክሉ በበኩላቸው በዘንድሮው የመጀመሪያው ግማሽ የበጀት ዓመት መደበኛ ትርኢቶችን ከተመለከቱ 15 ሺህ ታዳሚዎች 114 ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን ይገልጻሉ። በቅርቡ 85ኛ ዓመቱን ያከበረው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከማክሰኞ እስከ እሁድ አጠቃላይ ስምንት ቴአትሮችን ለተመልካች እያቀረበ ነበር። የተመልካቹ ቁጥር ከፍና ዝቅ የሚልባቸው ጊዜያት ቢኖሩም በአንድ ቴአትር በአማካኝ እስከ 300 ተመልካች ይታደም ነበር። ይህ ትዕይንት በኮቪድ-19 ምክንያት ባይቋረጥ ኖሮ በቴአትር ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት ቴአትሮችን ለመመልከት ከሚታደሙ ከ14 ሺህ በላይ ተመልካቾች

ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ይገኝ ነበር። በዚህም መንግሥት ከዘርፉ የሚያገኘው ገቢ እንደተጠበቀ ሆኖ የዘርፉ ባለሙያዎች በሚያገኙት ገቢ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጉ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጣ ሸቀጥና ሌሎች ግብዓቶችን ለማሟላት ወደገበያ ሲወጡ ገንዘቡ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳም የዚያኑ ያህል ይሆን እንደነበር ነው አርቲስት አብዱልከሪም የሚገልጸው።

አርቲስት ቶፊቅ በበኩሉ በተለይ ‘’ከመጋረጃ ጀርባ’’ የተሰኘውን ቴአትር በ2012 ዓ.ም በመጀመሪያው ግማሽ የበጀት ዓመት በርካታ ተመልካች ስለነበረው ከትዕይንቱ ጥሩ ገቢ ያገኝ እንደነበርና ይህም በማስተማርም ከሚያገኘው ቋሚ ገቢ ጋር በቂ በመሆኑ ደስ ብሎት ይሰራ እንደነበር ይገልጻል።

ጥቁሩ እንግዳ በቻይና እ.ኤ.አ በታህሳስ 2019 መጨረሻ እንደተከሰተ የተነገረለት የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የጋረጠው ፈተና የዓለምን መልክ ቀይሯል። የአያሌ የዓለም ሕዝቦችን በሕይወት የመኖር ተስፋ አጨልሟል። በርካቶች ከሥራ ገበታቸው አፈናቅሎ የዕለት ጉርሳቸውን እስከማጣት ደርሰው አደባባይ ወጥተዋል። በቢሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቤት እንዲቀመጡ አድርጓል። በተለይ የበለፀጉ ሀገሮች ወርሽኙን በቸልታ በመመልከታቸው ውድ ዋጋ አስከፍሏቸዋል። ወረርሽኙ ምንም እንኳን የተወሰነ ጊዜ ቢወስድበትም ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገሮችን በር ከማንኳኳት አልቦዘነም። በኢትዮጵያ በመጋቢት መጀመሪያው ሳምንት ላይ የኮሮና ቫይረስ የመከሰቱ ዜና መሰማቱን ተከትሎ መንግሥት የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ቀይሶ ተግባራዊ አድርጓል፤ እያደረገም ነው።

እንደ ሌሎቹ የዓለም ሀገሮች ሁሉ ኮቪድ-19 በሀገራችንም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ራሱን የቻለ ተፅዕኖ አሳድሯል። በወረርሽኙ ከተጎዱ የስራ መስኮች መካከል ኪነ-ጥበብ አንዷ ናት። ኪነ-ጥበብ በወረርሽኙ ታውካ በመቆዘም ላይ ነች ቢባል ማጋነን አይሆንም። እንደ ፊልምና ቴአትር የመሳሰሉት የኪነ-ጥበብ ስራዎች በአብዛኛው በቡድን የሚሰሩ ከመሆናቸው ጋር ይያያዛል። እነዚህ ሥራዎች በቡድን የሚሰሩ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ልምምድ ማድረግን የሚጠይቁና ከተጠናቀቁም በኋላ ለመመልከት የታዳሚዎቻቸውን አንድላይ መሰባሰብን የሚፈልጉ ናቸው። ኮቪድ-19 ይህን ባለመፍቀዱ ምክንያት የመዝናኛ ኢንዱስትሪው መቀዛቀዙን ያስረዳል አርቲስት ማስረሻ። አዳዲስ የጥበብ ውጤቶችን አዘጋጅቶ ለአድማጭ ተመልካች ለማድረስ አዳጋች በመሆኑ ወረርሽኙ በሙያው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።

የወረርሽኙን ስርጭት መከላከያ ስልቶች መካከል አንድላይ አለመሰባሰብንና ርቀትን መጠበቅን ይጠቀሳሉ። እነዚህ የኪነ-ጥበብ ውጤቶች ደግሞ በቡድን መስራትንና ተሰባስቦ መመልከትን ይጠይቃሉ። በዚህ ምክንያት የቴአትር ጥበብን ለታዳሚያን ማቅረብ እንዳልተቻለ ነው አርቲስቱ የሚገልጸው። አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ እንዳለው በኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚያስችል



9

ደረጃ የኪነ-ጥበብ ስራዎች እየተከወኑ አይደለም። በዚህም ምክንያት ስራም ገቢም ባለመኖሩ ባለሙያዎች ችግር ውስጥ ናቸው።

“ኮቪድ 19 ከጎዳቸው ዘርፎች መካከል ኪነ-ጥበብ ቀዳሚ ናት። በሙያው ተሰማርተው ይተዳደሩ ከነበሩትና በቀጥታ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ከሆኑት መካከል ደግሞ እኔ አንዱ ነኝ፤ ወረርሽኙ በሀገራችን ከተከሰተበት ወቅት እንስቶ ወጪ እንጂ ምንም አይነት ገቢ የለኝም” ይላል አርቲስት ቶፊቅ። ከቤት ኪራይ ወጪ በተጨማሪ የምግብና መሰል መሰረታዊ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስችል ገቢ እንደሌለው በመግለጽ የችግሩን አሳሳቢነት ያስረዳል።

በሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት በህብረ ዝማሬ፣ በባህላዊ እና በዘመናዊ ውዝዋዜ እንዲሁም በድምጽ የጥበብ ስራዎችን የሚያቀርቡ 120 ያህል ሕፃናት አሉ። ከመካከላቸው የኪነ- ጥበብ ውጤቶችን በመድረክ አቅርበው በሚያገኙት ገቢ የሚማሩና ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱ ነበሩ። እነዚህ ሕፃናት አሁን በችግር ውስጥ መሆናቸውን የቴአትር ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ኃብታሙ ያስረዳሉ።

“የቴአትር ቤቶች ባለሙያዎች የሚከፈላቸው ደመወዝ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር አይመጣጠንም፤ እስካሁን ሲደጎሙ የነበረው በመደበኛነት ከሚሰሯቸው ስራዎች ውጪ ሰርተው በሚያገኙት ክፍያ ነው። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ግን ምንም እንቅስቃሴ ባለመኖሩ ለጉዳት ተዳርገዋል። አንዳንዶቹ ወደ አደባባይ የወጡና ከልመና ባልተናነስ ሁኔታ ውስጥ የወደቁም አሉ።” ሲሉ የችግሩን ስፋት አመላክተዋል።

“በኮቪድ-19 ምክንያት ጉዳት ከደረሰባቸው መስኮች ኪነ-ጥበብ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ወረርሽኙ በሙያውም፤ በባለሙያውም ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድሯል። ባለሙያዎቹም ያለስራ ተቀምጠዋል፤ ሙያውም ባለበት ቆሟል፤ ምክንያቱም ሙያ የሚያድገው ሲሰራበት ነው። የፊልምም የቴአትርም ስራዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቆመዋል። በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በልምምድ ላይ የነበሩ ሦስት አዲስ ቴአትሮች ልምምዳቸው ተቋርጧል።” ይላል የቴአትር ቤቱ ስራ አስኪያጅ አርቲስት አብዱልከሪም።

አንድ ቴአትር ሲቀርብ በስራው የሚሳተፉት ባለሙያዎች የማበረታቻ ክፍያ የሚያገኙበት አሰራር አለ። በቴአትር ቤቱ በየሳምንቱ ይቀርቡ በነበሩት ስምንት ቴአትሮች ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ባለሙያዎች መካከል 100 ያህሉ ቋሚ ሠራተኞች አይደሉም። በኮቪድ-19 ምክንያት ስራ ሲቆም እነዚህ ባለሙያዎች በመድረክ ሲሳተፉ ያገኙት የነበረው የማበረታቻ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ነው የሚለው አርቲስቱ።

አርቲስት ማስረሻ እንዳለው አብዛኞቹ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ቋሚ ሠራተኞች አይደሉም። በመንግሥት በቋሚነት ተቀጥረው የሚሰሩት በጣም ውስን ናቸው። በኪራይ ቤት እየኖሩ በምሽት ጭፈራ ቤቶች ይሰሩ የነበሩ ሙዚቀኞች፣ ተወዛዋዦች ወዘተ… ችግር ላይ ወድቀዋል። አርቲስት ደሳለኝ በበኩሉ ለሀገር ብዙ ሲሰሩ የኖሩ አርቲስቶች ባለፉት ስድስት ወራት ሥራም ሆነ ምንም ገቢ ስላልነበራቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸው መታወቅ እንዳለበት ነው የገለጸው። መንግሥት ለመድረክ ከበቁት ቴአትሮቹ ከፍተኛ

ገቢ እንዳገኘና ለሙያው ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጾ፤ ይህንን ውጤት ለማግኘት ሚና የነበራቸው ባለሙያዎች ለችግር ሲጋለጡ ዞር ብሎ የሚያያቸው አካል ከሌለ ተገቢ አይደለም።” ሲል ቅሬታው የገለጸው ደግሞ አርቲስት ቶፊቅ ነው።

መፍትሔው ምን ይሆን? የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል። ከዚህ አንጻር በመንግሥት የተወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ነው። መልዕክቶችን ለማስተላለፍ በዋናነት የተመረጠችው ደግሞ ኪነ-ጥበብ ናት ነው ያሉት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ተክሉ። እሳቸው እንዳሉት ወረርሽኙ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ስርጭቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከሚኒስቴር መ/ቤቱ፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከመገናኛ ብዙኃን፣ ከኪነ-ጥበብ ማህበራትና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጡ አባላት ያሉት ሀገር አቀፍ የሚዲያና ኪነ-ጥበባት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

“በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አርቲስቶቻችን ከፊት ተሰልፈው በዘመቻው ተሳትፈዋል። በወረርሽኙ ላይ ለመስራት ጥሪ ስናቀርብ ሁሉም ማህበራት ተሰባስበዋል። ከወቅቱ ጋር የሚሄዱ የኪነ-ጥበብ ስራዎቻቸውን ሰርተው እነሆ ብለዋል። በየጎዳናው በመውጣት ወገን ስማ በማለት ቀስቅሰዋል፣ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ከ100 በላይ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ለህብረተሰቡ ቀርበዋል” ሲሉ ነው አቶ ተፈሪ በግብረ-ኃይሉ የአርቲስቶችን አስተዋጽኦ

የገለጹት። በግብረ-ኃይሉ እስካሁን ባለው ሂደት አርቲስቶች ያከናወኗቸው ተግባራት የኪነ-ጥበብ ማህበራት በጋራ ቢሰሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ትምህርት የተገኘበትን መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ሲሉም ያክላሉ።

የግብረ ኃይሉ አባል አርቲስት ደሳለኝ እንዳለው በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጭምር እየሰሩ ያሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል። የግብረ ኃይሉ አባላት ተቀናጅተው የሰሩት ስራ ወራሪ ሲመጣ ሀገር ለማስከበር እንደተደረገ ዘመቻ የሚቆጠር፤ በጣም ደስ የሚል ነው። በቀረቡት የኪነ-ጥበብ ውጤቶች ስለቫይረሱ ባህርይ፣ ስለመተላለፊያ መንገዶቹ፣ ስለመከላከያ ዘዴዎቹና ስለሚያስከትለው ጉዳት ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲጨብጥ የተሰራው ስራ ውጤታማ ነው። የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት በራሱ ተነሳሽነት ስፖቶች፣ የሙዚቃ ክሊፖች፣ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የሕፃናት ህብረ ዝማሬ ማዘጋጀቱን ከቴአትር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትም በወረርሽኙ ምክንያት በመድረክ የሚቀርቡ ስራዎች ቢቋረጥም መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ወረርሽኙ የሚያስከትለውን ችግር ሕዝቡ ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት የሚያስተላልፉ ስፖቶችን፣ የሬዲዮ ድራማዎችንና ህብረ ዝማሬዎችን አዘጋጅቶ እያቀረበ መሆኑን ነው አርቲስት አብዱልከሪም የሚገልጸው።

እንደ ቴአትር ቤቱ ስራ አስኪያጅ አርቲስት አብዱልከሪም ገለጻ ባለሙያው እራሱን ከቫይረሱ እንዲጠብቅ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከማቅረብ ባሻገር፤ በኮቪድ-19 ሳቢያ ገቢያቸው ተቋርጦ ለችግር የተጋለጡ ባለሙያዎች ለማህበረሰቡ የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል ዙሪያ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ በሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች

የቴአትር ቤቶች ባለሙያዎች የሚከፈላቸው ደመወዝ ከሚሰጡት አገልግሎት ጋር አይመጣጠንም፤

እስካሁን ሲደጎሙ የነበረው በመደበኛነት ከሚሰሯቸው ስራዎች ውጪ ሰርተው በሚያገኙት ክፍያ ነው። ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ግን ምንም እንቅስቃሴ

ባለመኖሩ ለጉዳት ተዳርገዋል። ወደ አደባባይ የወጡና ከልመና ባልተናነስ

ሁኔታ ውስጥ የወደቁም አሉ።

የቴአትር ደራሲና ባለሙያ ቶፊቅ ኑሪ



10

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

እንዲሳተፉ እየተደረገ ነው።

“ወረርሽኙ ከተከሰተ ከወራት በኋላ አርቲስቱ መተዳደሪያው የሆነውን ስራ በማጣቱ ለችግር ተጋልጧል፤ መታከሚያ እስከማጣት የደረሱም አሉ። ቋሚ ባልሆኑ ስራዎች ተሰማርተው የነበሩትንና አሁን ለጉዳት የተጋለጡትን ባለሙያዎች መለየት አዳጋች ሆኖ ነበር። አሁን ግን በአዲስ አበባ ደረጃ በጣም የከፋ ችግር ውስጥ ያሉ 70 ያህል አርቲስቶች በሙያ ማህበራቸው አማካኝነት ተለይተዋል። እነዚህን አርቲስቶች ለመርዳት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ አሰራር እንዲኖር ግብረ ኃይሉ እየሰራ ነው።” በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኩል አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው እየተለዩ የዕለት ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው። በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ አስር ያህል ባለሙያዎች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓልም ይላሉ አቶ ተፈሪ ።

በተለይ የዘመኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤት በሆነው ዲጂታላይዜሽን፣ ማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎች የቴክኖሎጂ አማራጮችን የኪነ-ጥበብ ሥራዎች የሚቀርቡበትና ገቢ የሚገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር በስትራቴጂው ተመላክቶ ፕሮጀክት እየተቀረጸ መሆኑንም ጠቁመዋል። አቶ ተፈሪ እንዳሉት የማገገሚያ ስትራቴጂው ባለሙያው ለምግብና ለሌሎች መሰረታዊ ፍጆታዎች የሚውል ዕርዳታ እንዲደረግለት ሳይሆን፤ ሰርቶ እራሱን የሚችልበትና ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት ሁኔታ መፍጠር በሚያስችሉ አማራጮች ላይ ያተኮረ ነው። ስትራቴጂውን ወደ ተግባር ለማሸጋገር በትኩረት እየተሰራ ነው።

በአንጻሩ የዘርፉ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች በበኩላቸው በሙያው ላይ የሚደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ እንደሆነ ከመስማት ባለፈ በተጨባጭ የታየ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ተፈሪ ለዚህ ቅሬታ የሰጡት ምላሽ “ስትራቴጂው በወጣለት የጊዜ መርሃ ግብር መሰረት ተግባራዊ አልሆነም፤ የሚያጋጥሙ ችግሮች እንቅፋት ሆነዋል። ጥረቱ ስላለ ግን መተግበር አልተጀመረም ማለት አይቻልም።” የሚል ነው።

የግብረ-ኃይሉ አባልና በማገገሚያ ስትራቴጂው ዝግጅት ወቅት ተሳትፎ እንደነበረው የሚገልጸው አርቲስት ደሳለኝ “በችግር ላይ የወደቁትን ሙያተኞችና ሙያውን ለመደገፍ እየተሰራ ያለው ስራ ከችግሩ ስፋት አንጻር በቂ አይደለም።

በኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ላይ ከደረሰው ችግር አንጻር ´ከምንም ይሻላል´ እንደሚባለው እንደመፍትሔ ይወሰዳል እንጂ ችግር ይፈታል ብዬ አላምንም” ነው ያለው። “ከኮሮና ቫይረስ መከሰት በኋላ አዲስ ቴአትር ለተመልካች ለማቅረብ ድርሰት (ስክሪፕት) እያዘጋጀሁ ነው። በተጨማሪም ቀደም ሲል ሲታይ የነበረውን `ብር አምባር´ ቴአትር ወደ መድረክ የመመለስ ዕቅድ አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ያለው ሁኔታ ሙሉ ጊዜዬን ኪነ-ጥበብ ላይ ለማዋል መወሰኔ ትክክል እንዳልነበር እንዲሰማኝ ስላደረገኝ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ትክክል መሆን አለመሆኔን መፈተሽ ይኖርብኛል፣ ውሳኔዬን መከለስ ጀምሬያለሁኝ።” በሚል የወደፊት ዕቅዱን ይገልጻል አርቲስት ቶፊቅ።

አርቲስት ቶፊቅ ውሳኔውን ለመከለስ ያስገደደውን ምክንያት ሲገልጽ “መንግሥት የጥበብ ሙያንና ሙያተኞችን ሲፈልግ ይጠቀምበታል፤ በእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች ምክንያት ባለሙያው ሲጎዳ ፊት ለፊት አይታይም። መንግሥት ሙያውንና ሙያተኞችን ሌላውን ማህበረሰብ ለማገዝ እንደመሳሪያ ይጠቀምበታል እንጂ ባለሙያዎች ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ገቢያቸው ሲቋረጥ መፍትሔ እየሰጣቸው አይደለም።” በማለት ነው። የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ችግር ለመፍታት እየተከናወኑ ካሉት ስራዎች መካከል የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትና የሚደገፉበት አሰራር ማበጀት ይገኝበታል።ይህን አሰራር ወደ ተግባር ለማሸጋገር ሚኒስቴር መ/ቤቱን ጨምሮ ከስራ ዕድል ፈጠራ ኤጀንሲ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እየተመከረ ነው።

“የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮችን በመጠቀም በሚገኘው ገንዘብ አርቲስቱ ሰርቶ አቅም እንዲፈጥር እስከታች ድረስ ተወርዶ የሚሰራበት ማዕቀፍ በስትራቴጂው ተመላክቷል። ዋና አቅም የሚሆነው በመንግሥት በኩል የሚመቻቸው የፋይናንስ አቅርቦት ነው። ገንዘቡ መልሶ ገቢ ማመንጨት በሚያስችል መልኩ ዘርፉን መደገፍ ያስፈልጋል። ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ ወደ ውጤት የማይቀየርበት ምንም ምክንያት የለም።” ሲሉ አቶ ተፈሪ ይገልጻሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተወያዩበት ወቅት በመዲናዋ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እየተሰሩ ያሉት የቤተ-መንግሥት፣

የእንጦጦ፣ የሸገር ፕሮጀክቶች ወደፊት ከኮቪድ-19 በኋላ በሚኖረው ጊዜ ስፍራዎቹን ለሚጎበኙ ቱሪስቶች የጥበብ ስራዎችን ለማቅረብ እና እንደ ፊልም የመሳሰሉ የጥበብ ስራዎች ቀረጻ ለማከናወን ተስማሚ በመሆናቸው ለመስኩ ዕድገት የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ጠቅላይ ያስረዱበት አግባብ ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ነው።

በቴክኖሎጂ አማካኝነት ሰው ቤቱ ሆኖ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን እንዲመለከት ማድረግ አንዱ አማራጭ ቢሆንም ሰው ሙሉ በመሉ ወደዚህ ከዞረ ከኮሮና ቫይረስ ክስተት በኋላ እንደ ቴአትር የመሳሰሉ በመድረክ የሚቀርቡ ዝግጅቶች ላይ ላይታደምና ተመልካች ተመልሶ ላይመጣ ስለሚችል ጥቅምና ጉዳቱን ከወዲሁ ማጤን ይገባል ይላል አርቲስት ቶፊቅ። ይህን ሃሳብ የሚጋራው አርቲስት ማስረሻ እንደሚለው ቴአትር ለካሜራ ሲተወንና ለተመልካች ሲተወን በጣም ትልቅ ልዩነት አለው። ወረርሽኙን በመግታት ነገሮችን ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ማድረግ ዘላቂ መፍትሔ በመሆኑ ባለሙያው የሚተላለፉ መልዕክቶችን በመተግበር ላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ያስገነዝባል። አርቲስት ቶፊቅን የመሳሰሉ ጥበብን ወደው በችግር ውስጥ ሆነው በሙያው እየሰሩ ያሉ አርቲስቶችን በዚህ ወቅት አለንላችሁ ሳንላቸው ቀርተን ፊታቸውን ቢያዞሩ ጉዳቱ የሚያርፈው በኪነ-ጥበብ፣ በባለሙያዎች፣ በሕዝብ በአጠቃላይ በሀገር ላይ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለሆነም ተቋማትና ህብረተሰቡ ከኪነ-ጥበብ ውጤቶች ፊትና ጀርባ ያሉ ባለሙያዎችን የኑሮ ሁኔታ ማጤንና መደገፍ ይጠበቅባቸዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች የዘመቻው ከዋክብት ሆነው ህብረተሰቡ ራሱን ከቫይረስ እንዲጠብቅ እየተጉ ያሉ ባለሙያዎችን ከተጋረጠባቸው ችግር መታደግ ያስፈልጋል። ስትራቴጂውን በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ የማድረጉ ሥራ የሁሉንም ቅንጅታዊ አሰራር ይጠይቃል። ስለሆነም “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲል ብሂሉ የኪነ-ጥበብ ማህበራት የጋራ ፎረም መመስረትና ባለሙያዎች ደግሞ ተቀናጅተው መስራት አለባቸዋል። እንዲሁም ህብረተሰቡ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ ተረድተው ለስትራቴጂው ተግባራዊነት እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰሩ ይገባል።

የገቢ ማሰባሰቢያ አማራጮችን በመጠቀም በሚገኘው ገንዘብ አርቲስቱ ሰርቶ አቅም እንዲፈጥር እስከታች ድረስ ተወርዶ የሚሰራበት

ማዕቀፍ በስትራቴጂው ተመላክቷል። ዋና አቅም የሚሆነው በመንግሥት በኩል የሚመቻቸው የፋይናንስ አቅርቦት ነው። ገንዘቡ

መልሶ ገቢ ማመንጨት በሚያስችል መልኩ ዘርፉን መደገፍ ያስፈልጋል። ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ ወደ ውጤት የማይቀየርበት ምንም ምክንያት የለም።



11



12

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ማህበረሰብ



13

የዕሴቶቻችን የኋልዮሽ ጉዞ

በፍቅርተ ባልቻ

በምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ስርዎ መንግሥት መስርተው የአፍሪካን ቀንድና ደቡባዊውን የአረብ ክፍል የራሳቸው ግዛት (empire) አድርገዋል። የዓባይ ሸለቆን የሥልጣኔ መሰረታቸው አድርገው አክሱምን፣ ኑቢያንና ፑንትን የመሳሰሉ ኃያላን መንግሥታትን መስርተው በመልክዓ ምድራዊ አሰፋፈር ሲታይ ቀጠናውን ለብዙ ዘመናት ያስተዳደሩ ሕዝቦች እንደነበሩ በታሪክ ይነገርላቸዋል።

ከጥንታዊ መንግሥታት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትና ጠንካራ ወታደራዊ አቅም የነበረው መንግሥት የመሰረቱ፣ ሉዓላዊነታቸውን አስጠብቀው የኖሩ ስመ ገናና ነበሩ። የተለያዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ቢሆኑም እርስ በርስ ተከባብረው በሰላም አብረው የኖሩና የሚኖሩ ሕዝቦችን የሚወክል ስያሜ እንደሆነ በታሪክ ድርሳናት ሰፍሯል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊና የመንፈሳዊ ትምህርት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል እንዳሉት እነሆሜር፣ ሄሮዶተስ፣ አሌክሳንደር…ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመት አስቀድሞ የብሉይ ኪዳንን ቅዱስ መጽሐፍን ወደ ግሪክ ቋንቋ ተርጉመዋል። መልካቸው ጠየም አልያም ጠቆር ያለ የመሰላቸውን ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ፣ የደቡብና ደቡባዊ ምዕራብ አካባቢ ሕንዶችን ጨምሮ ያሉ ሕዝቦችን ኢትዮጵያ በሚል ስም እንደጠሯቸው ይናገራሉ።

በአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ መምህር መክብብ ገብረማሪያም በበኩላቸው በግሪክና በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ስማቸው ሲጠራ አስቀድሞ ድቅን የሚለው ሰው የማይበድሉ፤ እርስ በርስ ተዋደው፤ ተቀላቅለው በሰላም የሚኖሩ የፍትሕ ሀገር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚለው ነው ይላሉ። ጥንታዊት ኢትዮጵያ ቀደምት የሰው ዘር መገኛ፣ ግዛቷም እስከ ግብፅ፣ የመንና ሕንድ ውቅያኖስ፣ ድረስ እንደነበርም የታሪክ መጽሐፍትን



14

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

በማጣቀስ ያስረዳሉ።

አረቦች ኢትዮጵያን “አልሐበሻ” ብለው ይጠሯት እንደነበር መስከረም 2007 ዓ.ም ለንባብ የበቃው “ባሕል ወ ቱሪዝም” የተሰኘችው መጽሔት አትቷል። ቃሉም “ሐበሺ” ከሚለው የአረብኛ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ቅይጥ ወይም የተደበላለቀ ማለት ነው። አረቦች ቃሉን ብዙ ሕዝቦች በአንድነት ተዋህደው ይኖራሉ የሚለውን ለማመልከት እንደተጠቀሙበትም አመላክቷል። ኢትዮጵያ በዓለም ሥልጣኔ ገናና ከነበሩት ሮም፣ ፋርስና ከሕንድ ጋር ተደጋግማ የምትጠቀስ ሀገር እንደነበረችም አስነብቧል።

እንደ “ባሕል ወ ቱሪዝም” መጽሔት መረጃ ኢትዮጵያ የሚለው የግሪክ ስም ከ1 ሺህ 500 ዓ.ዓ እስከ 63 ዓ.ም ድረስ በአስራ ሦስት ደራስያን በተጻፉ 15 መጽሐፎች ውስጥ 40 ጊዜ ተጠቅሷል። የአይሁዳውያኑ የብሉይ ኪዳን ቅዱስ መጽሐፍ ከ280-150 ዓ.ዓ ድረስ በግብፅ እስክንድርያ ከአይሁዳውያኑ ዕብራይስጥ ቋንቋ ወደ ግሪክ ቋንቋ በተተረጎመ ጊዜ ኩሽ የተሰኘው የሕዝብና የሀገር ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ተካቷል። በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደግሞ በአክሱም መጽሐፍ ቅዱስ ከግሪክ ቋንቋ ወደ ግዕዝ ቋንቋ በተተረጎመ ጊዜም ኢትዮጵያ ተብሎ ተጽፏል።

አረቦች ሐበሻ ብለው ለሚጠሩት ጥንታዊ የአፍሪካ ጥቁር ሕዝብና ሀገር ኢትዮጵያ በሚል የተሰጠው የግሪኮች መጠሪያ በአፄ አምደ ፅዮን ዘመነ መንግሥት በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መታወቁን እንዲሁም ሐበሻ እና ኢትዮጵያ ነባር የጥቁር አፍሪካ ሕዝቦች የወል መጠሪያ ሆነው ለረጅም ዘመን ማገልገላቸውን መጽሔቱ የታሪክ ድርሳናትን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል።

ቀደምት ፈርጦቻችን … በርካቶች የሰዎችን ማንነትን አንድ እንደሆነ ከመረዳት በሚመነጭ መልኩ ሃሳብ ሲሰነዘሩ ይደመጣሉ። ሃሳቦቹ የእኔ የሚሏቸውን በማቅረብና ሌላውን በማግለል በድርጊትም ጭምር ይገለጻሉ። የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪዎች ግን በዚህ ሀሳብና ድርጊት አይስማሙም። ለዚህ እንደምክንያት የሚጠቅሱት አንድ ሰው አንድ ማንነት ብቻ ሳይሆን ድርብርብ ማንነቶችን አቅፎ መያዙ ነው። የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ገብሬ ኢንቲሶ እንዳሉት በፆታው፣ በጎሳው፣ በብሄሩ፣ በሃይማኖቱ፣ በአካባቢውና በሀገሩ የሚያገኘውን ድርብርብ ማንነቶች በአንድ ሰው ማንነት ውስጥ የምናገኘው። ለዚህ ነው ስለማንነት ስናወራ ስለየትኛው ማንነት ነው በሚል እየነጠልን መግለጽ የሚጠበቅብን ነው ይላሉ።

መታሰቢያ መላከ ሕይወት “አቃፊ ማንነት” በሚል ርዕስ በ2012 ዓ.ም ባሳተሙት መጽሐፋቸው ባሕላዊ ማንነት

አንድ ሰው ወይም ቡድን ከቤተሰብ፣ ከአካባቢው አብሮ ከሚኖረው ማህበረሰብ እንደሚወርስ፣ ኢትዮጵያውያንም የበርካታ ማንነቶች (የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ ወዘተ …) ባለቤት መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ሕዝቦች በጋራ ማንነትና ባህል አማካኝነት ያዳብሯቸውና ከፍ ያለ ዋጋ የሰጧቸው ልማዶች የማህረሰብ ዕሴቶች (values) ይሆናሉ። የኢትዮጵያውያን ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዕሴቶች የሚመነጩት ከአኗኗር ዘይቤያቸው ነው። ማህበረሰቡ ተስማምቶ ሲያዳብራቸው ልማዶቹን መገለጫው ያደርጋቸዋል።

ሰዎች በራሳቸው ላይ እንዳይሆኑ ወይም እንዲደረጉ የማይፈልጓቸው በሌሎች ላይ እንዳያደርሱ፤ የመልካም እንጂ የእኩይ ተግባራትና ባህርያት ተገዥ እንዳይሆኑ የሚመራ፤ ማህበራዊ ህጋቸውን የሚቀርጹበትና ትውልድን የሚያንጹበት በጥቅሉ ሰው መሆናቸው የሚጠይቃቸውን ስብዕና አሟልተው ማህበራዊ ጉድኝታቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስችላቸውን ዕሴታቸው ከግብረገብነት ፍልስፍና ጋር በማስተሳሰር የገለጹት የአቶ ወንድወሰን ሽመልስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ሰኔ 2010 ዓ.ም “የሰብዓዊነት መንጠፍ ኪናዊ ፈርጆችና ረቦች “ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ነው።

ዕሴቶቹንም ማህበረሰቡ ከሚከተላቸው ሃይማኖቶች፣ ረጅም ጊዜ ባስቆጠረው የእርስ በርስ ትስስርና አንድነት እንዲሁም ከጎረቤቶቻቸውና በአካባቢያቸው ካሉ ሕዝቦች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የጎለበቱ በሚል መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል በሦስት ከፍለዋቸዋል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በ2006 ዓ.ም “የሰላም ዕሴት ግንባታ” በሚል ርዕስ ባሰናዳው መጽሐፍ ሰላማዊነት፣ አብሮነት፣ መከባበር፣ እውነተኝነት፣ ፍትሃዊነት፣ ይቅርታ፣ ሩህሩህነት፣ መልካም ምሳሌነትና በጎነት የሃይማኖቶች መሰረታዊ የጋራ ዕሴቶች መሆናቸውን ያስረዳል።

እንደ መምህር ዳንኤል ገለጻ ጥንታዊ ኢትዮጵያውያን ጠቢቦችና ዕውቀት ፈላጊዎች እንደነበሩ ምስክር የሚሆኑ በርካታ የታሪክ ድርሳኖች አሉ። ቀድሞ የክርስትና ሃይማኖትን ከመቀበል ጀምሮ ዕሴቶቹን የህብረተሰቡ አድርጎ ለማቆየትና መገለጫችን እንዲሆን እናት አባቶቻችን ብዙ ሰርተዋል። ንግሥተ ሳባ (ማክዳ) ጥበብን ፍለጋ ጠቢቡ ሰለሞን ዘንድ ሄዳ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን የብሉይ ኪዳን ቅዱስ መጽሐፍ ሥርዓት ወደ ሀገራችን ይዛ መምጣቷንም በአብነት ያነሳሉ። ሀገራችን የራሷን ፊደል ቀርፃ፣ የራሷን ድርሰት፣ የግጥም፣ የንባብ፣ የቅኔ ባሕልን አዳብራለች። በስነ-ሥዕልም፣ በግብረ ሕንጻም፣ በዜማም በማንራጎር፣ ከመሸለል አልፎ የዜማ ድርሰት፣ በምልክት ማዜም፣ እያሸበሸቡ ምስጋና የማቅረብ ባሕላዊ ዕሴት አለን። ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ጥበብ ጠብቀው ከሌላው ጥበብ ተምረው ሀገራቸውን የጠቢባን ሀገር አድርገው አቆይተዋል።

ኅብረተሰቡ በጋራ ሆኖ አዳብሯቸው ጎልተው እና ደምቀው ከሚታዩት ኢትዮጵያዊ ዕሴቶች መካከል በጋራ ተዋግቶ ጠላትን ድል የማድረግ ልማድ አንዱ ነው። ይህ ዝም ብሎ በአንድ ጊዜ የመጣ አይደለም። ትልቅነቱን የመጠበቅ በመሪው ተማምኖ በጋራ የመዝመት፣ ነፃነቱን የመጠበቅ የዳበረ ባሕል ስላለው ነው። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዓድዋ ሲዘምቱ ሕዝቡ አብሮ ተዋግቶ ቅኝ ገዢዎችን ድል ማድረግ እንደሚቻል ለዓለም ሕዝብ አስተምሯል። ይህ ኢትዮጵያውያን የመተባበራችን ውጤት ነው። ድሉም የሁሉም ሕዝብ ነው። ጥቃትን ያለመቀበል፣ የጀግንነት፣ ክብርን የመጠበቅ ወርቃማ ዕሴቶች ናቸው ይላሉ መምህር ዳንኤል።

የቅርስ ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ መምህር መክብብ በመምህር ዳንኤል ሃሳብ ይስማማሉ። ኢትዮጵያ ለዚህ የደረሰችው ችግሮቿን በራሷ እየፈታች፣ የውጭ ወራሪ ኃሎችን ጥቃት እየመከተችና እየተከላከለች ሉዓላዊነቷን ጠብቃ ነው። ጠላትን ድል በመንሳት አሸንፋ ስሟ ተከብሮ እንዲኖር ያስቻሏትን የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርሶች ትውልዱ ሊያውቃቸው እንደሚገባ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰሩና አንድ ያደረጉ የጋራ ጀግኖች አሉ። ጠላትን በጋራ ተፋልመውና ተዋግተው ድል ያደረጉ ጀግኖች የሁሉም ናቸው።

“አለመግባባት ሲፈጠርና ችግር ሲያጋጥም ቁጭ ብሎ መምከር የተለመደ ባህላችን ነው። ሰው እሳት ሲሆን፤ ውሃ መሆን ነው ይባላል፤ ሁለቱም ወገኖች ይወቀሱና እንዲስማሙ ይደረጋል። በሽምግልና ውስጥ ብዙ ጥበቦች አሉ። በመወያየትና በመከራከር ወደ መግባባት የሚደረሰው የመተማመን መንፈስ ስለሚያድግ ነው። በውስጡ መተባበር፣ መከባበር፣ መደማመጥ አለ።” ይላሉ መምህር ዳንኤል።

የሀገር ሽማግሌዎችንና የሃይማኖት አባቶችን ማክበር፤ ተግሳጻቸውን መፍራት፤ ምርቃታቸውን መቀበል የኢትዮጵያውያን ባሕል ነው። በአማራ-ሸንጎ፣ በትግራይ- ባይቶ፣ በኦሮሞ-ሱባና ጉሚ፣ በከፊቾ-የሚክሪቾ፣ በጉራጌ- የሰመኙት፣ እና ሎሎችም መጠሪያዎች ይሰጣቸው እንጂ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የባህላዊ አስተዳደሮች እንደነበሩ መምህር መክብብ ያስረዳሉ። በእነዚህ ሥርዓቶች አማካኝነት በዳይና ተበዳይ በሽማግሌዎች ፊት ቀርበው እንዲስማሙ ይደረጋል።

በግለሰቦች መካከል ግጭት ሲነሳ ገለልተኛ ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተው በመሸምገል መፍትሄ እንደሚያፈላልጉ፤ ሥርዓቱም ማደራደር፣ ፍርድ መስጠት፣ ካሳ ማስከፈልና ማስታረቅን ያካትት እንደነበር የነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) በ2008 ዓ.ም “የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ” በሚል ርዕስ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ያስረዳል።

እርጥብና ለምለም ሳር ይዞ ፈጣሪን መለመንና ማመስገን፣



15

የተጣላን ማስታረቅና መመረቅ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። በሃድያ እና በጉራጌ ማህበረሰብም ዘንድ የተለመደ ባህል ነው። በተለያዩ አጋጣሚዎች በሰዎች መካከል አሁን አለመግባባት ሲያጋጥም አባቶች ተሰባስበው እርጥብ ሳር ይዘው ይማልዳሉ፤ ያስማማሉ፣ ያስታርቃሉ። ከሀገር ሽማግሌዎችና አባቶች ቃል የሚያፈነገጥ ስለሌለም አለመግባባቱ ረግቦ እርቀ ሰላም ወርዶ ሰላማዊ ህይወት ይቀጥላል።

ኢትዮጵያውያን ለሰው ልጆች ያላቸው ክብርና ፍቅር በዘመናት ሁሉ ተገልጿል። ጽድቅ፣ እውነተኛነት፣ መስዋዕትነት፣ ፍትሕ፣ ያላቸውን በፍቅር ማካፈል፣ መዋደድ ባህላቸው አድርገዋል። የእንግዳ ተቀባይነት ባህላቸው ሳይነሳ የሚታለፍ አይደለም። በተለይ በገጠር እንግዳ ሲመጣ አልጋ ለቆ፣ እግር አጥቦ፣ ቤት ያፈራውን አቋድሶ ማስተናገድ የቆየ ባሕላችን ነው። “በአንተ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌላው ሰው ላይ አታድርግ፣ ለአንተ እንዲደረግ የምትፈልገውን ለሌላው አድርግ” የሚለው ብሂል የማህበረሰቡን አስተሳሰብና ሥነልቦና የሚገልጽ ነው።

እንደ መምህር ዳንኤል ገለጻ ከውጪ ሀገር የመጡ መነኮሳትና የእምነት አባቶች እንግዳ ተቀባይ በሆኑት ኢትዮጵያውያን ልዩነት ሳይደረግባቸው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው፣ ገዳማትን ጨምረው የእምነት ተቋማትን መስርተው ተከታይ አፍርተው ኖረዋል፤ እየኖሩም ነው። የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ፍትሕ ወደ አለባት ሀገር ሂዱ ተብለው ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ጊዜ አረቦች ስለሆናችሁ ቋንቋችሁን ቀይሩ፣ ሃይማኖታችሁን ለውጡ አልተባሉም። የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑት የፖርቹጋል ወታደሮችም ምንም ጫና ሳይደረግባቸው በነፃነት በኢትዮጵያ ኖረዋል።

ነቢዩ መሐመድ ተከታዮቻቸውን አላህ ብርታቱን እስኪሰጠን ድረስ ወደ ሐበሻ ሀገር ሄዳችሁ እዚያ ቆዩ፤ ንጉሱም ፍርድና ፍትሕ አዋቂና አስተዋይ ስለሆነ በእርሱ ዘንድ ማንም አይበደልምና አትስጉ ብለው እንደነበር “ባሕል ወ ቱሪዝም” መጽሔት አስነብቧል።

ሌላው በኢትዮጵያውያን ዘንድ በስፋት ጎልቶ የሚጠቀሰው እንደ ደቦ/ጂጊ ያለው በህብረት የመስራት ባህላዊ እሴት ነው። በገጠር አርሶ አደሩ ማህበረሰብ የግብርና ሥራውን የሚያከናውነው በህብረት ነው። ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) “የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ” በሚለው መጽሐፋቸው እንዳሉት አንድ ሰው ብቻውን አርሶ አዝመራውን ለመሰብሰብ ስለሚቸገር የግብርና ሥራውን የሚያከናውነው እንደ ደቦና ጂጊ በመሳሰሉት ማህበራዊ መሰረቶቹ ተሰባስቦ በጋራ ነው። መኖሪያ ቤት ሲሰራም እንዲሁ ምሰሶ የሚያቆመው በአንድነት ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ መከናወን ያለበትና በቤተሰብ አቅም ሊሸፈን የማይችል ሥራ ሲኖር ማህበረሰቡ ይሳተፋል። በሀዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ የማህበረሰቡ ማህበራዊና ምጣኔ

ሀብታዊ መስተጋብር ጠንካር እንደሆነ በመጽሐፉ ተብራርቶ ተጠቅሷል።

ኢትዮጵያውያን በተለይም የገጠሩ ማህበረሰብ አባላት በጉዞ ላይ እንዳሉ በመንገድ የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ሰው አወቁትም፤ አላወቁትም ከአንገታቸው ዝቅ ብለው በአክብሮት እጅ ነስተው ሰላምታ ሳይለዋወጡ አይተላለፉም። ይህ ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሀገር ባህልና ወግ ነው። የኢትዮጵያውያን ማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት የሚጀምረው ከሰላምታ ነው። ሰውን በማክበር የሚገኝ ምርቃት በረከት ነው ተብሎም ይታመናል። ኢትዮጵያውያን የእርስ በርስ መከባበር ባህላዊ እሴት የሚጀምረው ከቤተሰብ ነው። ልጆች ቤተሰቦቻቸውን፣ አዛውንቶችን ያከብራሉ። ታናሽ ታላቅን፣ጎረቤት ጎረቤቱን ያከብራል። ይህ ሲሆን፤ አንዱ ለሌላው ያስባል፣ ማህበራዊ ትስስራቸውን ይጎለብታል፤ ውጤቱ ደግሞ መተሳሰብን ይፈጥራል፤ መተሳሰብ ሲኖር በጋራ መሰልጠን ማደግ ይቻላል። ኃብታሙ ደሃውን የበታች አድርጎ አያየውም፣ የኃብታሙ ማግኘት ለደሃው ጥቅም ስለሚሆን ደሃው የጎረቤቱ ኃብት አያስፈራውም።

የደስታና የሀዘን ሥነ ሥርዓቶችም የራሳቸው መልክና ቀለም ያላቸው ልዩ ኢትዮጵያዊ መገለጫ ዕሴቶቻችን ናቸው። በገጠርም ሆነ በከተሞች ልጅ ሲወለድ የአካባቢው ማህበረሰብ ተባብሮ እመጫቷን ይንከባከባል። በአራስ ጥሪ ወገቧ ይጠንክር እየተባለ ለተወለደው ሕፃንም ለእናትም ይሰጣል። ማህበረሰቡ ልጆችን የራሱ ልጅ አድጎ ስለሚያይ ሁሉንም ልጄ ብሎ ነው የሚጠራው። አድገው ለወግ ማዕረግ ሲበቁም በጋራ ሰርጎ፤ ድሮ ኩሎ ጎጀ ቀልሶ የሚያወጣቸው በህብረት ነው።

የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ገብሬ እንደሚሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትስስር በብዙ መልኩ ይንጸባረቃል። በጋብቻ፣ በጉርብትና፣ በዕቁብ፣ በዕድር፣ በንግድ፣ በማህበር፣ በሰንበቴ በመሳሰሉት ማህበራዊ መስተጋብሮቻቸው ሁሉ ይገለጻል። የሌላውን ልጅ እንደራሱ አድርጎ በጉዲፈቻ ወስዶ በማሳደግ፣ የክርስትናና የጡት ልጅ በማድረግ፣ እንዲሁም በሞጋፈቻ ጭምር ላይለያይ ተሰናስሎ የተጋመደ ነው።

የቅርስ ጥናት ባለሙያው መምህር መክብብ እንዳሉት የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫ ፈርጥ የሆኑትን ባህላዊ ዕሴቶችን ኅብረተሰቡ ጠብቆ ያቆያቸው በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ስላስቻሉት፣ ነፃነቱን ስላጎናጸፉት፣ በዜግነቱ እንዲኮራ ስላላደረጉት ነው። ችግር እንኳን ቢኖር መፍትሔ የሚሰጥ አካል በመኖሩ ባህላዊ ዕሴቶቹን የራሴ ናቸው ብሎ በእምነት ስለተቀበላቸው ነው። ከማህበረሰቡ ባህልና ወግ በሚያፈነግጡት ላይ ኅብረተሰቡ የሚወስዳቸው ከማንኛውም ማህበራዊ መስተጋብር እስከ ማግለል

የሚደርሱ እርምጃዎች ባህላዊ ዕሴቶቹ እንዲጠበቁ የራሳቸው አበርክቶኦ አላቸው።

ጥቁር ነጥብ ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገሩ ዛሬ ላይ ያደረሱን እነዚህ የማንነታችን መገለጫ የሆኑት ወርቃማ ፈርጦቻችን አሁን ላይ እንቅፋት እየገጠማቸው ነው። በተለይ ሀገርን መውደድ፤ እርስ በርስ መከባበር፤ የእናቶችን፣ የአባቶችንና የታላቅን ምክር የመስማት ባህላችን እየተሸረሸረ ነው። ከኢትዮጵያውያን ወግና ባህል ውጭ ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት፣ ወልደው ከከበሩበት፣ ክፉና ደጉን ካዩበት ቀዬ ሲፈናቀሉ፤ የህይወትና የአካል ጉዳት ሲደርስ፣ ሀብት ንብረት ሲወድም እየተስተዋለ ነው። ተቻችሎና ተከባብሮ በሰላም አብሮ የመኖር፣ የመተማመን፣ የመተዛዘንና የአብሮነት ባህሎቻችን እየደበዘዙ መጥተዋል። ከመረዳዳት ይልቅ መጎዳዳት፣ ከመደማመጥ ይልቅ መነቃቀፍ፣ ከመደጋገፍ ይልቅ መጠላለፍ፣ ከመተማመን ይልቅ መጠራጠር፣ ራስን ከመሆን ይልቅ መስሎ ማደር፣ ከእውነት ይልቅ አባይነት ባህርይው አድርጎታል ሲሉ አቶ ወንድወሰን በጥናታዊ ጽሁፋቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ ከእኛነት ይልቅ እኔነት፣ ተካፍሎ ከመብላት ይልቅ መናጠቅ፣ በእጅጉ እየተስተዋለ ነው። የመተሳሰብና መደጋገፍ ባህለዊ ዕሴቶች እየተጣሱ ነው። ለሀገርና ለወገን በፍቅር የሚከፈል ዋጋ እየቀነሰ ዓላማ ቢስነት የነገሰበት ጊዜ ላይ ተደርሷል። ሰው ከራሱም ከማህበራዊና ግብረ ገባዊ እሴቶቹ ተቀያይሞ እየተኳረፈ ነው። ሰብዓዊነቱም እየነጠፈ ነው። በጨዋነቱ የሚታወቀውን ኢትዮጵያዊ ጨካኝ እንዲሆን ያስገደዱት ምክንያቶች ምን ይሆኑ?

መምህር ዳንኤል እንደሚሉት መልካም ዕሴቶቻችን በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ በትምህርትና በሌሎች ተቋማት አለመሰራቱ አንዱ ምክንያት ነው። ከኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ፣ ማህበራዊ መዋቅርና የአኗኗር ዘይቤ ጋር የማይሄዱ ከውጭ እያመጡ በኅብረተሰቡ ላይ መጫን ሌላው ነው። ይህ ድርጊት ከመቶ ዓመት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል። ምንም እንኳን በጥናት ማረጋገጥን ቢጠይቅም፤ በታሪክ ሲወራረሱ የመጡ እንደ ሶሻሊዝምና ኮሙዩኒዝም ያሉት የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለሞች ተፅዕኖ እነዚህ ኅብረተሰቡ ለዘመናት ያዳበራቸው ባህላዊ ዕሴቶቹ እንዲሸረሸሩ ካደረጉት ውስጥ ይጠቀሳሉ።

እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችን በዓለማችን ባሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦች (የሶሻሊዝምና ኮሙዩኒዝም) ከተበረዘው ማንነት ጋር የማይቀላቀሉ ናቸው። ይሁን እንጂ አስተሳሰቦቹ በተፈጠሩበት ዓለም (በራሺያና ምስራቅ አውሮፓ) ያልተወሰዱ መገለጫዎች ነባር ዕሴቶቻችንን



16

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ከመሸርሸር አልፎም ለበርካታ ጥፋቶች ምክንያት እንደሆኑም ተያይዞ ይነሳል።

መምህር ዳንኤል እንደሚሉት ለችግሮቻችን እልባት በመስጠት የሚታወቀው የሽምግልና ሥርዓታችን መልኩን ቀይሮ ለይስሙላ እየተደረገ ነው። “ሽምግልና ለማታለል፣ ለንግድ፣ ለራስ ጥቅም እየዋለ ነው። በጣም እየጠፋ ያለው ባሕላችንም ይህ ነው። `ሁሉንም አሸማጋዮች ባይገልጽም´ እኛ አለን መከታ እንሆናለን እናንተ በርቱ የሚባልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።” የችግሮቹ መወሳሰብ የሽምግልናውን ጥበብ አኮስምነው፣ እንዴት አድርገን እንደምንፈታቸው ፈታኝ እየሆነ በግልፅ መወያየት ተስኖን ሀገርን እያወከ ነው። በተደጋጋሚ የሚነሳው ሁሉም ሰው ተናጋሪ፣ የእኔ ብቻ ትክክል ስለሆነ ይሰማ ባይ እየሆነ ነው። በየጋዜጣው ሲነበብ ፀሐፊው እራሱን የሚያቀርበው ሁሉን አዋቂ አድርጎ ነውም ይላሉ።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰውን ጎድቶ ለችግር መዳረግ ቀርቶ መንገደኛው ሳያልፍ ሰላም ሳይሉ በመንገድ አቋርጦ መሄድ ነውር ነው። አሁን ከተሸረሸሩት ባህላዊ እሴቶቻችን አንዱ የሰላምታ አሰጣጣችን ነው። ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ በ´ፍቅር እስከ መቃብር` መጽሐፋቸው ገጸ ባህሪይ በዛብህ አማካኝነት የገለጹት ይህንን ነው። በዛብህ አዲስ አበባ ሲመጣ በለመደው ባሕል መሰረት ሰላምታ ሲያቀርብ በአጸፋው `የት ታውቀኛለህ?´ የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው፤ ይህን የጻፉት ባሕሉ መሸርሸሩን ለማሳየት መሆኑ ግልጽ ነው።

መምህር መክብብ ዕሴቶቻችን እንዲደበዝዙ በመንስኤነት የሚጠቀሱትን ዕሴቶቻንን ኋላ ቀር አድርጎ በመመልከት ወደ ጎን መተዋቸውና ለትውልዱም በዚህ መልኩ መነገሩ ዋናው ነው። ሌላው ተተኪው ትውልድ እንዲያውቃቸው፣ እንዲጠብቃቸውና እንዲንከባከባቸው አለመሰራቱ ነው። ዘመናዊውን የፖለቲካ አስተዳደር ከባሕላዊ ጋር አጣጥሞ አለመሄድና በዘመናዊነት መስፋፋት ሰበብ ትውልዱ ባሕሉን

እንዲቀበል አለመደረጉም ተያይዞ የሚነሳ ጉዳይ ነው። ነፃነትና ዴሞክራሲ በሚል ሽፋን ለአባቶች ቦታ ያለመስጠት፣ ትውልዱም በመቃወም ብቻ መፍትሔ የሚያገኝ እየመሰለው መምጣቱ፤ ለሃይማኖት አባቶችና ተቋማት ይሰጠው የነበረው ክብር ገሸሽ መደረጉን ከምክንያቶቹ መካከል ናቸው ይላሉ።

ባሕላዊ ዕሴቶች እንዲሸረሸሩ መንስኤ ከሆኑት ውስጥ የት እንደተማሩ የማይታወቁ ሰባኪያን መበራከት፣ የአስተምህሮ ችግር እንዳለ የሚያሳይ መሆኑ፣ ሃይማኖትን ለፖለቲካ መሸጋገሪያ አድርገው መጠቀም የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው የሚሉት ይጠቀሳሉ ያሉት በፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የሰላምና እርቅ ዘርፍ ኃላፊ እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ ሼህ መሐመድ ሲራጅ ዑመር ናቸው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በ2006 ዓ.ም “የሰላም ዕሴት ግንባታ” በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፉ “በሀገራችን ብዙ የእምነት ዓይነቶች እና የሃይማኖት ተቋማት አሉ፤ የየራሳቸው አስተምህሮ ጠብቀው በመከባበር ኖረዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አንዱ የሌላውን እምነትና አስተምህሮ በማጥላላት ተከታዮችን ለመውሰድ በሚያደርገው ጥረት ምክንያት መልካም የነበረው የመከባበር ባሕል የሚሸረሽሩና ሰላማዊ ግንኙነቱን የሚያውኩ ጭላንጭሎች ይታያሉ። … እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ በሃይማኖት ስም የራሳቸውን አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት እንጂ ተከባብሮ የኖረው ሕዝብ እምነትና ከሃይማኖቶቹ አስተምህሮ የሚመነጭ አይደለም።”ሲል አስረድቷል።

“አቃፊ ማንነት” በሚል ርዕስ በመታሰቢያ መላከ ሕይወት የተዘጋጀው መጽሐፍ በአንድ ዴሞክራሲን ዓላማ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሀገር የዜጎችን የአስተሳሰብ መብት ማክበር ግዴታ ቢሆንም ሕዝብን የሚያስተዳድር ግለሰብ ግን አስተሳሰቡን አጥርቶ፣ ማንነቱ በማያሻማ መልኩ አውቆ መገኘት አለበት የሚል ሀሳብ አስፍሯል።መጽሐፉ አያይዞም

ኢትዮጵያዊያን ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የማንነት ውዥንብር ውስጥ ገብተን ስንቸገር መቆየታችንንም ይጠቅሳል። አንዳንዶች ይህ መሬት የዚህ ብሔር ነው፤ ያኛው ደግሞ የዛኛው ነው፤ ሲሉ እየተደመጡ ነው። ይህ አስደንጋጭ ነው። መሬት ፍጡራን ሁሉ በጋራ እንዲጠቀሙባት የተሰጠች ናት ሲሉ መታሰቢያ መላከ ሕይወት በመጽሐፋቸው ያስረዳሉ።

መልካሙ ተሾመ በ2010 ዓ.ም “የአማራ ብሔርተኝነት” በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፍ “ብሔርተኝነት ወደ ገነት የሚወስድ ወይም ከገነት የሚያሰድድ መሆኑ የሚወሰነው በአያያዙ ነው። በህሊናችን ውስጥ አሉታዊ ምስል እንዲኖረው ወይም ቀለሙ እንዲጠይም የተደረገው በአያያዝ ጉድለት ነው። ከአያያዝ ይቀደዳል፤ ከአነጋገር ይፈረዳል የሚሉት ኢትዮጵያውያንም ብሔርተኝነትን በአግባቡ መያዝ ባለመቻላቸው የተነሳ ብዙ ፍዳ ከፍለዋል።” በማለት ብሔርተኝነትን በአግባቡ መያዝ እንደሚገባ አብራርተዋል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በበኩሉ የችግሩ ዋነኛ መንስኤ ስር የሰደደ ድህነት እንደሆነ ነው የሚገልጸው። ኅብረተሰቡ የማንነቱ መገለጫ የሆኑትን ባህላዊ ዕሴቶች ጠብቆ ለተተኪው ትውልድ ለማሸጋገር እያደረገው ባለው ጥረት ላይ ድህነት ራሱን የቻለ ተጽዕኖ ያሳደረበት ነው። ከዚህም ባሻገር በሀገር ባህልና ወግ መሰረት እንግዳ ተቀብሎ ማስተናገድ እንደአላዋቂነት የሚቆጠርበት ዝንባሌ መፈጠሩ እና በመገናኛ ብዙሃን የሚተላለፉ መረጃዎችም እንዲሁ ድርሻ አላቸው ይላል።

ከዘመናት በፊት የተፈጸሙ ስህተቶችን ለምን እንደግማቸዋለን? ሲሉ የሚጠይቁት ሼህ መሐመድ አሁን የምንሰማቸውና የምናያቸው ነገሮች የሚያሳዝኑ፣ ልብ የሚሰብሩ፣ የሚያስጨንቁና እንቅልፍ የሚነሱ ድርጊቶች ናቸው ይላሉ። ሰው በሀገሩ የመኖር ተፈጥሯዊም ህጋዊም መብት አለው። ወንድም ወንድሙ ላይ ተነስቶ ለህይወትና ለአካል ጉዳት እንዲዳረግ ማድረግ፤ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬ

የማይሻረው የማይለወጠው የሰው ልጅ መገለጫ ሰው መሆኑ ብቻ ነው። አሁን

የምንጋጭባቸው ማንነቶችና ምክንያቶች የኢትዮጵያውያን መግለጫዎች አይደሉም።

ኢትዮጵያውያን ማንኛውንም ወደ ሀገራቸውም ሆነ ወደ ቤታቸው የመጣን ሰው

ብሔሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ጠይቀው አይደለም በእንግድነት ተቀብለው የሚያስተናግዱት

ሰውነቱን ተቀብለው እንጂ።

የሰላም ተምሳሌቶቹ የጋሞ አባቶች



17

ማፈናቀል፤ ሀብት ንብረት ማውደም በየትኛውም አግባብ ተቀባይነት የለውም። ከኢትዮጵያውያን ባህልና ወግ ውጭ የሆኑ አስነዋሪ ድርጊቶች ስለሆኑ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲል ብሂሉ በጊዜ ሊታረሙ ይገባል ነው ያሉት።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪው አይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) የሀገራችን ታሪክ በአግባቡ ተሰንዶ አለመያዙ ትውልዱ ስለማንነቱ በቂ ዕውቀት እንዲያገኝ እንዳላስቻለው ይገልጻሉ። የሀገራችን ታሪክ በቤተ- መንግሥትና በሃይማኖት ተቋማት አካባቢ ያተኮረ በመሆኑ የአብዛኛውን ማህበረሰብ ታሪክና ባህል አያመለክትም። ትውልዱ ታሪኩን እንደተመቸው መጻፍ በመጀመሩ ምክንያት ታሪክ የስልጣን መወጣጫ መብት ማስከበሪያ እየሆነ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ገብሬ የዶክተር አይረዲንን ሃሳብ ይጋራሉ።

ወጣቶች በርካታ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች አሏቸው። ይህን ክፍተት ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል የሚፈልጉ አካላት ወጣቶቹን ወደማይሆን አቅጣጫ እንዲሄዱ ያደርጓቸዋል። በዚህም የተወሰኑ ወጣቶች ጥያቄያቸውን በህጋዊ መንገድ አቅርበው ተገቢውን ምላሽ ከማግኘት ይልቅ በኃይል ለማስፈጸም ሲንቀሳቀሱ የጥፋትና የጉዳት ሰለባ ሲሆኑ እየተስተዋለ ነው። የነገዋን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ ወጣቶችን በመልካም ስነምግባርና በሁለገብ ዕውቀት የታነጹ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስፊያ ስራዎች ከታች ጀምሮ መሰራት ይገባል። በሀገራችን የተፈጸሙ እኩይ ድርጊቶችን ቀደም ሲል በነበሩን ድርብርብ ማንነቶችና ዕሴቶች አማካኝነት ተሻግረናቸዋል የሚሉት አይረዲን (ዶ/ር)፤ እነዚህ ክስተቶች ቆም ብለን ራሳችንን መለስ ብለን እንድናይ የሚያግዝ የማስጠንቀቂያ ደውል መሆናቸው ጠቅሰዋል።

መምህር ዳንኤል እንደሚሉት የማይሻረው የማይለወጠው የሰው ልጅ መገለጫ ሰው መሆኑ ብቻ ነው። አሁን የምንጋጭባቸው ማንነቶችና ምክንያቶች የኢትዮጵያውያን መግለጫዎች አይደሉም። ኢትዮጵያውያን ማንኛውንም ወደ ሀገራቸውም ሆነ ወደ ቤታቸው የመጣን ሰው ብሔሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ጠይቀው አይደለም በእንግድነት ተቀብለው የሚያስተናግዱት ሰውነቱን ተቀብለው እንጂ።

መልካምነት ከሌላው መጠበቅ ሳይሆን፤ ሁሉም ከእራሱ ነው የሚጀምረው ሰናይ ተግባር ነው የሚሉት ሼህ መሐመድ ሲራጅ ናቸው። ለእኩይ ተግባር ከመተባበር ይልቅ ድርጊቶቹ እንዳይፈጸሙ ማድረግ፤ ተፈጽመው ሲገኙ እንዳይደገሙ ማውገዝ ይገባል። የሰውን ልጅ መብት ማክበር የሁሉም ግዴታ ነው። የልጆቻቸው አዕምሮ በመጥፎ ነገር ሲበረዝ፤ ሰላም ሲደፈርስ፣ አብሮነታችን ሲሸረሸር እያዩና እየሰሙ በዝምታ የሚያልፉ ወገኖች ትውልድ ገዳይ ሀገራቸውን አፍራሽ እንደሆኑ ነው የሚገልጹት ሼህ መሐመድ።

የመታሰቢያ መላከ ሕይወት በ”በማንነት ማዕቀፍ” መጽሐፋቸው እንዳስረዱት አንድ ሀገር የምትበለጽገው በእያንዳንዱ ዜጋ ላይ በሚደረግ መሰረታዊ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ሲደረግ ብቻ ነው። ስለሆነም ለጉዳዩ ትረኩረት መስጠት ይገባል። ሰለሞን ሥዩም 2010 ዓ.ም “የኦሮሞ ጉዳይ እና ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ባሳተሙት

መጽሐፋቸው ሰው ምን ቢዘምን ለባሕልና ለማንነቱ ያለው ቀናኢነት ይጨምር እንደሆነ እንጂ አይቀንስም ነው ያሉት።

“ኢትዮጵያ ወደ ከፍታ እንድትወጣ የምናስችላት መሰላሎቿ እኛ ነን። መሰላል በተለያዩ እንጨቶች እንደሚሰራው እኛም በመፈቃቀድ መስተጋብር፣ በአንድነት ሆነን ነው ኢትዮጵያን ከፍ የምናደርጋት። ቀስተደመና የሁሉም ቀለማት መስተጋብር ውጤት እንደሆነው እኛም አንድ ሆነን መሰላሉን በመገንባት ወደ ከፍታ እንውጣ።” የሚሉት ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት መምህሩ ዑስታዝ ያሲን ኑሩ ናቸው።

የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪው አይረዲን (ዶ/ር) እንደሚሉት አሁን ከብዙ ጥፋት የታደጉንን ዕሴቶች ካልተንከባከብናቸው የማይጠፉበት ምክንያት የለም። ብዝሃነታችንን ከአንድነታችን ጋር ሚዛናዊ አድርገን ለማስቀጠል የሚያስችሉን ተቋማት ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤቶች መፈተሸ ይገባል ይላሉ። ፕሮፌሰር ገብሬ በበኩላቸው የታሪክ ምሁራን ትክክለኛውን ታሪክ በጋራ በመምከር ለይተው ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ቢሰሩ፤ ቀደም ሲል የተሰሩትንም ስህተቶች ማረም ቢችሉ ጠቃሚ መሆኑን አመላክተዋል።

ሲጠቃለል የኢትዮጵያውያን ሥልጣኔና ዕውቀት ፈላጊነት እንዲሁም ለሰው ልጆች ያላቸው ክብር በዘመናት ተገልጠዋል። የቀደሙ አባቶቻችን ለሀገራቸው ዘብ ቆመው ሉዓላዊነቷን አስከብረውና አስጠብቀው ለዓለም ተምሳሌት ሆነዋል። እርስ በርስ በመረዳዳት ችግሮቻቸውን በጋራ አልፈዋል። በደስታቸው ስቀው፤ በሀዘናቸው አብረው አልቅሰዋል። የትላንት ኢትዮጵያውያንን ወርቃማ ዕሴቶች ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሰርተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያነቷ ፀንታ እንድትቆም መሰረት ጥለዋል። ይሁን እንጂ አሁን አሁን የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶች መደብዘዝ ጀምረዋል። ስለሆነም ከአዙሪቱ ለመውጣት ምን ይደረግ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው።

ባሕላዊ ዕሴቶች በማህበረሰብ ውስጥ በመከበራቸው የራሱን ነፃነትና የሌላውን ሰው ክብርና መብት ጠንቅቆ እንዲያውቅ ከማስቻል ባሻገር ትውልዱ በበጎ ሥነምግባር የተቀረፀና የታነፀ እንዲሆን የማድረግ አቅም አላቸው። ባሕላዊ ዕሴቶች አስተዋይነትና ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው፣ የተረጋጋ የአኗኗር ሥልትን የሚከተሉ፣ አርቆ አሳቢና ከግላዊ ጥቅም ይልቅ ለማህበረሰቡ የሚያስቡ ግለሰቦች እንዲበዙ ምክንያት ይሆናሉ። የዚህ ትሩፋት ተቋዳሽ የምንሆነውም በተተኪው ትውልድ ላይ ብዙ ስንሰራ ብቻ ነው።

ጠንካራ ስብዕና ያለውን ትውልድ ለማፍራት ከቤተሰብ ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁ፣ የቀደሙትን ዕሴቶቻችንን የሚያደምቁ ባሕሎቻችንን ለማሳወቅና ለማስረፅ የሚረዱ ስራዎችን ማከናወን ይገባል። የማህበረሰቡ ዕሴቶች እየተጎዱ ሲመጡ እርስ በርስ ያለው መተማመን ይጠፋል። በሰላም ወጥቶ ለመግባት፣ ወልዶ ለማሳደግ፤ ነግዶ ለማትረፍ ሰርቶ ለማደግ የሚደረገው ጥረት አስቸጋሪ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትን የሚያንጸባርቁ ዕሴቶቻችንን

የሚያደምቁ ባሕሎቻችን ማሳወቅና ማስረፅ ወሳኝ ነው። ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና፣ ትውልዱን በባሕሉና በማንነቱ የታነፀ ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንዲኖረው፤ በእራስ ጥረት ሰርቶ በማግኘት የሚያምን እንዲሆን ከታች ጀምሮ መስራትን የግድ ይላል።

ስለሆነም ወጣቱ ትውልድ ሁለገብ ዕውቀትና ብስለት እንዲኖረው የሚያስችሉ መሰረታዊ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ እንዲሁም የክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠናዎችን እንዲያገኝ መስራት የማህበረሰብ ጥናት ተመራማሪዎች ምክረ ሀሳብ ነው። ወጣቱ ወደ መደበኛ ስራ ከመግባቱ አስቀድሞ በሙያው ለማህበረሰቡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጥ ቢደረግ በአንድ በኩል የስራ አካባቢን ይላመዳል፣ በሌላ በኩል ባህሉን፣ የማህበራዊ ዕሴቶቹን፣ ወግና ሥርዓቱን አውቆ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዴት እንደሚወጣ በተግባር የተፈተነ ልምድ እንዲያገኝ ያስችለዋል። ስለዚህ ተተኪውን ትውልድ ሰርቶ በማግኘት እንዲያምን በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባርም ጭምር ማለማመድን ይጠይቃል። ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማትም የተሟላ ስብዕና እና የራስ መተማመን ያለው፣ በምክንያትና በውይይት የሚያምን ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ከአፀደ ሕፃናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ያሉት የትምህርት ተቋማት የማህበረሰቡን ዕሴቶችን ለማጎልበት ምን እየሰሩ እንደሆነ ቆም ብለው እራሳቸውን በመጠየቅና የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

ነብዩ መሐመድ ተከታዮቻቸውን “አላህ ብርታቱን እስኪሰጠን ድረስ ወደ ሐበሻ ሀገር ሄዳችሁ እዚያ ቆዩ፤ ንጉሱም ፍርድና ፍትሕ አዋቂና አስተዋይ ስለሆነ በእርሱ ዘንድ ማንም አይበደልምና አትስጉ” ብለው ነው ወደ ኢትዮጵያ የላኳቸው። እርግጥ ነው ነብዩ መሐመድ እንዳሉት ኢትዮጵያ ማንኛውም ሰላማዊ ሰብዓዊ ፍጡር ከየትኛውም ሀገር ይምጣ በቋንቋ፣ በዘሩ፣ በእምነቱ/በሃይማኖቱ፣ በቆዳው ቀለም ወዘተ. ልዩነት ሳይደረግበት በሰላም የሚኖርባት ሀገር ነች። ከመንግሥትም ብዝሃነትን ከኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ጋር አዋህዶና አስማምቶ ለመጓዝ የሚያስችል ስልት መከተል ይጠበቃል። ባሕላዊ ዕሴቶቻችንን ከዘመናዊው አስተዳደር ጋር ተጣጥመው ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትን አሰራርም ማበጀት ለዕሴቶቹ ቀጣይነት ራሱን የቻለ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ስለሆነም ባሕላዊ ዕሴቶቻችንን በዚሁ አግባር የሚተገበሩበትን አሰራር ማበጀት የግድ ይላል። ኅብረተሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ያቆያቸውን የማንነቱ መገለጫ የሆኑ ባህላዊ ዕሴቶችን በሀገሪቱ ሥርዓት ትምህርት አካትቶ ትውልዱን ተግቶ ማስተማር ያስፈልጋል። ወጣቶች የሀገራቸውን ባህል፣ ወግና ሥርዓት እንዲሁም የማንነታቸው መገለጫ የሆኑትን ባህላዊ ዕሴቶቻቸውን አውቀው በአግባቡ እንዲጠቀሙባቸውና ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዲችሉ በመገናኛ ብዙሃንም ጭምር እንዲሰራ ትኩረት ማድረግ ይገባል። እነዚህ ዘመናትን ያሻገሩን ባህላዊ ዕሴቶቻችን ተጠብቀው ዘመን ተሻጋሪ ይሆኑ ዘንድ መንግሥት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት በአጠቃላይ የሁሉም ዜጋ የቤት ስራ ነው።



18

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

2012 በወፍ በረር



19

በመስከረም 2012 ዓ.ም • በአዲስ አበባና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ነበሩ የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

• በአዲስ አበባ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማሩ ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ 1 ሺ 440 የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት መልሰው ተገንብተዋል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2019 የሰላም የኖቤል ሽልማት አሸነፉ።

• በታላቁ ቤተ መንግሥት የተገነባው የአንድነት ፓርክ የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቆ ለህዝብ ክፍት ሆኗል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩቬሪ ሙሶቬኒ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፣ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ታድመዋል።

• በአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት “ሸገርን የማስዋብ” ፕሮጀክት ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

ጥቅምት 2012 ዓ.ም • የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር አሰባሰቡን ዘመናዊ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክስ የግብር አከፋፈል ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል።

• በጣና ሀይቅ ዳርቻ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የመገጭ ሰራባ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ተመርቋል።

• በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ይማሩ ለነበሩ 300ሺ ያህል

በአንዱንሰው ሺፈራው



20

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል። ፕሮግራሙ ለ10 ሺ እናቶች የሥራ እድል ፈጥሯል።

• ኢትዮጵያ የኒውክለር ኃይልን በጤናው ዘርፍ ለካንሰር ሕክምና እና ለኃይል ልማት ለማዋል ከሩሲያ ጋር በኒውክለር ቴክኖሎጂ አብረው ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሙያዊ ስነ-ምግባርን ተከትለው የማይሠሩ መገናኛ ብዙሃንን አስጠንቅቀዋል። አብዛኛዎቹ ነፃ ለመሆን ባቀረቡት ጥያቄ ልክ ነፃ ሆነው እየሠሩ እንዳልሆነ አስረድተዋል። ለኢትዮጵያ ሠላምና ዴሞክራሲ ከመስራት ይልቅ የዘር፣ የሃይማኖት እና የገንዘብ ነጋዴዎች በመሆን እየቀለዱና የሆነ አካልን ወክያለሁ ብለው በሚነግዱ ሰዎች እጅ መውደቃቸውን ተናግረዋል። “ለነዚህ ነጋዴዎች ሕዝቡ ዓይንና ጆሮ ባለመስጠት ሊቀጣቸው ይገባል” ሲሉም መክረዋል። የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም ሕጉን መሠረት በማድረግ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

• በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “መደመር” የተሰኘው መፅሐፍ በሚሊኒየም አዳራሽ ተመርቋል።

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤሌክትሮኒክስ ቪዛ 200 ሺህ መንገደኞችን አስተናግዷል።

• የዓለም ሜቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፍቶ ስራውን በይፋ ጀምሯል። የጽህፈት ቤቱ መከፈት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ እያደገ የመጣውን የአየር ሁኔታ ጠባይ መረጃና ፍላጎት ለማርካትና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።

ህዳር 2012 ዓ.ም • የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዓለም ዓቀፍ ነፃና ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠና ፌዴሬሽን የሚሰጠውን የፌሞዛ የ2019 ሽልማት አሸነፈ። ፌሞዛ በአባል ሀገሮች ውስጥ የሚገኙና ወደ ለውጥ እየመጡ ያሉ ሀገሮችን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማሳደግ የሚሰራ ድርጅት ነው።

• የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳኡዲ አረቢያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት በሳኡዲ እስር ቤቶች ከ5 እስከ 8 ዓመት ተፈርዶባቸው የነበሩ 840 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ታህሳስ 2012 ዓ.ም • የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ደርጅት /ዩኔስኮ/ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ተመዝግቧል።

• የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኖቤል ሽልማት በብሔራዊ ሙዚዬም በክብር ተቀምጧል። በኖቤል ኮሚቴ የተበረከተላቸው አንደኛው ሜዳልያና የምስክር ወረቀት ምስለ ቅርፅ በሰላም ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀምጧል።

• የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፎርብስ መጽሔት ባወጣው የዓመቱ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

• ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የመሬት መመልከቻ ‘ETRSS-1’ የተሰኘችውን ሳተላይት ወደ ህዋ አምጥቃለች።

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ዓመታት በፊት አቋርጦት የነበረውን የግሪክ አቴንስ በረራ አገልግሎት ጀመረ።

• የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለውህዱ ብልጽግና ፓርቲ ህጋዊ ዕውቅና ሰጥቷል።

• የ11ኛ ክፍል ተማሪ ወጣት አጃዬ ማጆር በአንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችልና 4 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላት ተሽከርካሪ ሰርቷል።

ጥር 2012 ዓ.ም • የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ‘ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት’ ነው ተብሎ መታወጁን አስታውቀዋል።

• የኤርትራ ልዑክ ቡድን አባላት የጥምቀት በዓልን ጎንደር አከበሩ።

• በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ ድርድር ተካሂዷል።

• የግብርና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።

• የጤና ሚኒስቴር ከ700 በላይ አምቡላንሶችን ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ሰጥቷል።

• 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የገናሌ ዳዋ 3 የኤልክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመርቋል።

• የተሻሻለው ኢንቨስትመንት አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

• በምስራቅ ሸዋ ዞን በ125 ሚሊዮን ብር የተገነቡ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ሥራ ጀምረዋል።

የካቲት 2012 ዓ.ም • ከኢትዮጵያ ተሰርቆ ወደ ኔዘርላንድስ ተወስዶ የነበረው ዘውድ ተመልሷል።

• በ100 ሚሊዮን ብር የተገነባው የወረታ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

• የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨትን ለመከላከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

መጋቢት 2012 ዓ.ም • የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ 80 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሲያደርግ የነበረውን በረራ አቋርጧል።

• ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በ2013 ዓ.ም ወደ ቅድመ ኃይል ማመንጨት ስራ እንዲጀምር በከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

• የበረሃ አንበጣ መንጋ በኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰብል ምርት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

• በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ትላልቅ ስብሰባዎችና የስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይካሄዱ ተወስኗል።

• በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

• የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ሁሉም የሀገሪቱ ድንበሮች ለሰዎች ዝውውር ዝግ ተደርገዋል።

• ኢትዮጵያ ለኮሮና ቫይረስ አስፈላጊውን እገዛና የሕክምና

አገልግሎት የሚሰጥበት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ዝግጁ አድርጋለች።

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአምስት ቀናት ውስጥ ለ39 የአፍሪካ ሀገሮች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውል የሕክምና ቁሳቁሶችን አቅርቧል።

• የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በማረሚያ ቤቶች ለመከላከል ከ4 ሺህ በላይ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚለቀቁ አስታውቋል።

• የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ወስኗል።

• ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በተቋቋመ አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከሀገር ውስጥ 150 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማግኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሚያዝያ 2012 ዓ.ም • የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም በ3ኛው ሩብ የበጀት ዓመት ከ183 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል።

• የግብርና ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ በቀጣዩ ዓመት 40 ሚሊዮን ኩንታል የምርት ቅናሽ እንደሚያጋጥማት አስታውቋል።

• የመቂ-ዝዋይ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ደ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።

• ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ የሕክምና መሣሪያዎች ማከፋፈያ ማዕከል ሆና መመረጧን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

• የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለችግር እንዳይዳረጉ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

• የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት የተነሳ የተቀዛቀዘው የቱሪዝም ዘርፍ ፈጥኖ እንዲያንሰራራ የማገገሚያ ስትራቴጂያዊ ሰነድ ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ግንቦት 2012 ዓ.ም • ከኮቪድ-19 ጋር ተያይዞ የወጪና ገቢ ምርቶች እንዳይቀዛቀዙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በልማት ባንክ በኩል 2 ቢሊዮን ብር ለጥቃቅንና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት እንዲደርስ አድርጓል።

• ሁለተኛው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ባለስልጣናት በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ በታቦር ተራራ በይፋ ተጀምሯል።

• የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሁለት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመግታት የሚያግዙ የሞባይል መተግበሪያዎችን አዘጋጅቷል።

• የትምህርት ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ሳቢያ የተቋረጠው የትምህርት ዘመን በምን መልኩ መቀጠል እንዳለበት የሚያጠና ቡድን ተደራጅቶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።

• በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል’ ተገነባ።



21

• የታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀጣይ ውሃ የመሙላት ወሳኝ የግንባታ ምዕራፍ በመልካም ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልጸዋል።

ሰኔ 2012 ዓ.ም • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገዶች አሁንም ቀዳሚ መሆኑ አፍሪካ ሎጂስቲክስ ዶት ኮም ገልጿል።

• ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ በአምስት ዓመት ማዘግየት ኢትዮጵያን 41 ነጥብ 7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያሳጣት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ግብረ ኃይል አስታውቋል።

• በአዲስ አበባ ከተማ በ 5 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ወጪ የከተማ አውቶቡስ ፍጥነት መንገድ ግንባታ ተጀምሯል።

• የታዋቂው የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በታዋቂው ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።

• አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ኮሪ ቡከር እና ሴናተር ክርስቶፎር ኩንስ የተባሉ ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮች ለሀገሪቱ ግምጃ ቤት በላኩት ደብዳቤ ጥሪ አቅርበዋል።

• የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚተኛበት ስፍራ ደን ምንጣሮ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

• የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ዳቦ ማምረት ጀምሯል።

• የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሶስት አዳዲስ የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ተሰጥቷል። ፈቃዱን ያገኙት የኢትዮ ዋርካ መልቲ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን፣ የትርታ ትሬዲንግ እና የአዲስ ኦንላይን የሚዲያና የግብይት ስራዎች ኃላፊነታቸው የተወሰኑ የግል ማህበራት ናቸው።

• የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) መቀመጫቸውን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን አክሽፏል።

• በኢትዮጵያ ከማለዳው 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃዎች ጀምሮ ቀለበታማ የፀሃይ ግርዶሽ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ላልይበላን ጨምሮ በሞጣ፣ ደብረታቦር፣ አላማጣ፣ ጋይንት እና ሌሎች አካባቢዎችም ታይቷል። በተለይ በላልይበላ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ ፀሐይ እሳታማ ቀለበት ሰርታ ታይታለች።

• የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባካሄዱት የጋራ ስብሰባ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲራዘም ወስኗል።

ሐምሌ 2012 ዓ.ም • ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል።

• በአዲስ አበባ ከተማ በህዳሴው ግድብ ዋንጫ ከ80 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ቦንድ ተሸጧል።

• በኢትዮጵያ በ2012/13 የመኸር እርሻ ከ12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ ከ375 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየተሰራ ነው።

ነሐሴ 2012 ዓ.ም • ከመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገኘ ከ110 ነጥብ 67 ሚሊዮን ብር ለትምህርት ቤቶች ማሰሪያ እንዲውል ለቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ተበርክቷል።

• ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የወጭ ንግድ 164 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ “ገበታ ለሀገር” የተሰኘና በአማራ ክልል ጣና ሐይቅ ምዕራባዊ ዳርቻ ጎርጎራ፣

በአሮሚያ ክልል ወንጪ ሐይቅ እና በደቡብ ክልል ኮይሻ አካባቢዎችን ማልማት የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይፋ አደረጉ።

• በትግራይ ክልል ይደረጋል የተባለው ምርጫ እንዳልተደረገ የሚቆጠር፣ የማይጸናና ተፈፃሚነት የሌለው መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ገልጿል።

• በኢትዮጵያ ሁለት አለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የኦፕሬተርነት ፈቃድ ወስደው እንዲሰሩ መንግሥት ወስኗል።

• በኢትዮጵያ ከባንክ ውጭ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቀመጥ መከልከሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።

• የኮቪድ-19ን የምርመራ መጠን ከፍ ለማድረግ እና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የሚያስችል ብሔራዊ መረጃን ለማግኘት ሀገር አቀፍ ዘመቻ ተካሂዷል።

• ዓለማችን በቀጣይ ሊከሰት ለሚችል ወረርሽኝ ራሷን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳስበዋል።

ጳጉሜን 2012 ዓ.ም • የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፈው በጀት ዓመት 165 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ምርት ወደ ውጭ ልኳል።

• ኢትዮጵያ በ2012 በጀት አመት በብድር እና በእርዳታ 106 ነጥብ 875 ቢሊየን ብር ማግኘቷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

• ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደህንነት ከግብፅና ሱዳን ግድቦች የተሻለ መሆኑን የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ ገልጸዋል፡፡

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት ከሚወክሉ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።

መልስ ያገኘው የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ



22

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ኢትዮጵያ አምናና ለከርሞው



23

ያሳለፍነው 2012 ዓ.ም ታሪክ ሆኖ ላይመለስ ሄዷል። የጀመርነው ዓመትም ከ365 ቀናት በኋላ ይህንኑ ይጋራና ያልፋል። ዘመን ዘመንን እየተካ፤ ዛሬ ትናንት፤ ነገ ደግሞ ዛሬ እየሆነ እዚህ ደርሰናል። በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ታሪክ መስራት በመልካምነቱ፤ መጥፎ ሥራ ደግሞ በአስከፊነቱ የሚጠቀሰው በዚሁ ለሁላችንም እኩል በተሰጠው ጊዜ ባስመዘገብነው ውጤት ነው።

ኢትዮጵያም የታሪክ ውጣ ውረድን አልፋ በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ ደርሳለች። ባጠናቀቅነው ዓመት በተከናወኑ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ዓበይት ክንውኖቿን ከአዲሱ ዓመት ተስፋዋቿና ሊያጋጥሟት ከሚችሉት ችግሮች ጋር በማስተያየት መቃኘት ደግሞ ካለፈው ተምሮ ነገን በተሻለ ለመገንባት ይረዳልና እነሆ ብለናል።

አገሪቱ የተጠናቀቀውን ዓመት ያሳለፈችው ለፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮቿ መፍትሄ በማፈላለግ ነበር። ኢትዮጵያዊነትን ያስቀደመ ዓመት ሆኖም አልፏል። ዘመኑ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ እውን ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት የተከናወኑበት ነው። ከሁሉም በላይ ሕዝብና መንግሥትን ብቻ ሳይሆን፤ ዓለምን ያስደመሙ ጉዳዮች በታሪክ ተመዝግበውበታል። ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገ ኹነት ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን የኖቤል ሰላም ሽልማት ባለቤት መሆናቸው የዓመቱ ጉልህ ጉዳይ ነበር፡፡

የኖርዌይ የኖቤል የሠላም ሽልማት ኮሚቴ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዶ/ር በተለይም ኤርትራ ጋር የነበረው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ላደረጉት ጥረት ይህን ከፍተኛ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸው፣ በባዕድ አገር ለቆዩት እና እንደ አሸባሪ ይቆጠሩ ለነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እውቅናን በመስጠት ወደ አገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ

ኢትዮጵያ አምናና ለከርሞው

በብርሃኑ ተሰማ



24

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

መንገድ እንዲገቡ ማድረጋቸው፣ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ስርዓት ለማሻሻል ጥረት ማድረጋቸው እና ሌሎችንም በርካታ የለውጥ እርምጃዎችን መውሰዳቸው የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። ሽልማቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆኑበት፣ አገሪቱን በዓለም አቀፍ መድረክ ስሟንና ክብሯን ከፍ እንዲል ያደረገ፣ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አንገታቸውን ቀና አድርገው በዓለም አደባባይ እንዲሄዱ ያደረገ ነው።

ሲዳማ 10ኛ ክልል ሆኖ የወጣበት ሕዝበ ውሳኔ የተካሄደውም በዚህ ዓመት ነበር። ሲነሱ የነበሩና ለዓመታት ሲንከባለሉ የቆዩ የአደረጃጀት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የጀመሩትም በዚሁ ዓመት ነበር፡፡ በክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ለረዥም ዓመታት የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በኃይል ታፍኖ የቆየ ቢሆንም የህዝቡ ጥያቄ ከቀደመው ጊዜ በተለየ ሁኔታ

ገፍቶ በመምጣቱ ክልሉን በሚመለከት አዳዲስ ጥናቶች እና ዉሳኔዎች ማስተላለፍ ግድ ሆኗል፡፡ በዚህም የሲዳማ ብሔር በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በህዝበ ውሳኔ ሪፈረንደም እልባት አግኝቷል፡፡

መንግሥት የሕዝብ ጥያቄዎችን አገራዊ አንድነት ተጠብቆ፤ ማንነትና ኢትዮጵያዊነት ባስከበረ መልኩ ለመፈጸም እንደሚሰራ ደጋግሞ የገለጸበት ዓመትም ነበር። ጥያቄዎቹ ሲመለሱ ግን ደረጃ በደረጃ በጥናት ላይ ተመስርቶ እንጂ፤ በግርግር ሊሆን እንደማይገባው ተሰምሮበታል። በዚህ ላይ የዚህችን አገር የወደፊት አከላለል ለመወሰን የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን ተቋቁሞ እየሰራ ነው። ኢትዮጵያን የሕዝቦቿን አንድነትና ማንነት አጣጥማና አክብራ እንደምትቀጥል መጠራጠር ጊዜውን አለማወቅ እንደሆነ አጽንኦት የተሰጠበት ዓመትም ነበር።

በአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አምስት ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል የተያዘው ዕቅድ በስኬት

የተጠናቀቀው በክረምቱ አጋማሽ ላይ ነበር። በመጪው ዓመት በጎረቤት አገሮች ጭምር ከ6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል መታቀዱን ዶ/ር ዐቢይ ባህር ዳር ላይ በተከናወነ የዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ላይ አስታውቀዋል። አረንጓዴ ልማትን በማስፋፋት የአየር ንብረት ለውጥን በክፍለ አህጉር ደረጃ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ይረዳል።

ሌላኛው የዓመቱ ትልቅ ክስተት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያስደነገጠውና በታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመው ግድያ ነው፡፡ ታዋቂው የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ምሽት ነበር አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትቶ ሕይወቱ ያለፈው። አርቲስት ሃጫሉ በተለይም ለለውጡ ቁልፍ ሚና በነበረው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ወቅት እጅግ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱ አይዘነጋም። የሙዚቃ ስራዎቹም ቋንቋውን ማድመጥ በማይችሉ የሕብረተሰብ

በ2022 በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና

የአገልግሎት ዘርፎች የሰው ኃይል ሥምሪት ስብጥር 42 በመቶ፣ 19 በመቶ እና 39 በመቶ እንዲሆን

ለማድረግ ታቅዷል።

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም. ባሉት አስር

ዓመታት በአማካይ በ10 ነጥብ 2 በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል።

4 ሚሊዮን410 ሺ 400 ቤቶችን በመገንባት በከተሞች የቤት አቅርቦት አሁን ካለበት 64 በመቶ ወደ 84 በመቶ

እንዲያድግ ይደረጋል።

የሀገሪቱን ታክስ የመሰብሰብ አቅም ከሀገራዊ ምርት በመቶኛ በ2011 ከተመዘገበው የ10 በመቶ ምጣኔ በ2022 ወደ 18 ነጥብ 7

በመቶ ለማድረስ ታቅዷል።

ከፍኖተ ብልጽግና የአሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ (2013 – 2022) በጥቂቱ



25

ክፍሎች ዘንድ ጭምር ተወዳጅነትን ያተረፉ ነበሩ። በአገሪቱ ተቀስቅሶ ከነበረው የመንግሥት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት ያወጣው ‘ማላን ጂራ’ የተሰኘው ነጠላ ሙዚቃው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከማትረፍ አልፎ የእንቅስቃሴው መነቃቂያ ሆኖ እንደነበር ብዙዎች ያወሳሉ። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመቃብር በላይ ህያው ታሪክ አስቀርተው ካለፉ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን አንዱ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡

የአርቲስት ሃጫሉ ሞት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ሰዎች አደባባይ ወጥተው ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡ ፡ ይህን ተከትሎ የተፈጠረው መሪር ሀዘን ግን ያለፈው ዓመት አከናንቦን ካለፋቸው መሪር ክስተቶች ጉልሁ ነበር፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች በሚዘገንን አኳኋን ተገድለዋል፡ ፡ አያሌ ሀብት ንብረት ወድሟል፡፡ ከዚህ ባለፈ የለውጡን ሂደት ወደ ራሳቸው መንገድ ለመውሰድ በሞከሩ ጽንፈኞችና

አክራሪ ብሄርተኞች እንዲሁም እምነትን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች የተጎዳንበትም ነበር ያለፈው ዓመት፡፡ ብዝኃነት መለያው የሆነውን ሕዝብ ለማለያየት የተደረገው ጥረት ባይሳካም በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አስከትሏል። መንግሥት የሕግ የበላይነትን የማስከበርና የማረጋገጥ ተግባሩን ያጠናከረበትና በወሰደው እርምጃም ሰላምና መረጋጋትን ከሞላ ጎደል ለመመለስ የቻለበት ዓመትም ነበር።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት ውጥን የፈጠረው ደስታ ተራ ደስታ አልነበረም፤ ዓመቱ የሚታወስበት ትልቅ ኹነት እንጂ። 2012 ዓ.ም የኢትዮጵያውያንን በዓባይ ላይ ያላቸውን የዘመናት ቁጭትና የባለቤትነት ጥያቄ የመለሰ፣ የአሸናፊነትና የወደፊት ዕድገት ተስፋም የተንጸባረቀበት ደስታ የታየበት ዓመት ነበር። ግድቡ 4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ አጠራቅሟል። ግድቡ ለመጀመሪያ ዙር የታቀደለትን

ውሃ መያዝ የቻለ ሲሆን በሚቀጥሉት ከአራት እስከ ስድስት ዓመታት በግድቡ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ይይዛል፡፡ ሙሉ በሙሉ ግንባታው ሲጠናቀቅና ስራ ሲጀምር በአፍሪካ ትልቁ ኤሌክትሪክ የኃይል ማመንጫ ግድብ ይሆናል።

የግድቡ ውሃ ሙሌት አንድ ነባራዊ ሃቅ ይቀይራል። ይህም ከዚህ በኋላ የሚኖረው ድርድር ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት የተካሄደውን ዓይነት አይሆንም። ኢትዮጵያ በዓባይ ላይ ያላትን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በውሃው ሙሌት ተረጋግጧል። በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርቶ የሚደረገው ግንኙነት ግን ይቀጥላል። የማይገታውን የወንዙን ፍሰት ለዘመናት ያስተሳሰራቸው ሕዝቦችን ግንኙነት የመጀመሪያውም ሆነም የመጨረሻው የውሃ ሙሌት አያቋርጠውም። የዓለም አገሮችን እየተፈታተነ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሌላው የ2012 ትልቁ ዓለም አቀፍ ክስተት ነው፡፡ ታህሳስ ወር ላይ በቻይና ሁቤ

የመካከለኛና ሰፋፊ የመስኖ አውታሮች ግንባታን ከ490 ሺ ሄክታር ወደ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር ለማሳደግ ተወጥኗል።

መልሶ በማልማትና የማሻሻያ ልማት በማካሄድ ከደረጃ በታች የሆኑ

ሰፈሮችን አሁን ካሉበት 74 በመቶ ወደ 10 በመቶ መቀነስ ለማሳደግ

ታቅዷል።

በአምራች ኢንዱሰትሪው የፋብሪካዎችን በሙሉ

የማምረት አቅም አሁን ካለበት 50 በመቶ ወደ 80 በመቶ ከፍ

ለማድረግ ተወጥኗል።

የከተማ ሥራ አጥነት ምጣኔን ከ9 በመቶ በታች ለማድረስ

ታቅዷል። ለዚህም በአማካይ በየዓመቱ ለ1 ነጥብ 36 ሚሊዮን ዜጎች ሥራ መፍጠር ያስፈልጋል።

ከፍኖተ ብልጽግና የአሥር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ (2013 – 2022) በጥቂቱ



26

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ግዛት ውሃን ከተማ ነበር የዚህ አስከፊ ወረርሽኝ የመከሰቱ ዜና የተሰማው። የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ ሪፖርት ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ስምንት ወራትን ያስቆጠረው የኮሮና ወረርሽኝ በፍጥነት በርካታ አገራትን በማዳረስ ከጤና ችግርነት አልፎ የኢኮኖሚ ቀውስ ማስከተሉን ተያይዞታል። ቫይረሱ ዓለምን ማስጨነቁን፣ ለብዙዎች የጤና እክል ምክንያት መሆኑንና የብዙዎችን ህይወት መቅጠፉንም ቀጥሏል።

መጋቢት 4 ቀን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ የተረጋገጠውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ለአምስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ሆኗል። የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በርካታ እርምጃዎች የተወሰዱ ሲሆን፤ የትምህርት ተቋማት መዘጋት በጉልህ ይጠቀሳል፡፡ ትምህርትን በኢንተርኔት፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ለመስጠት ጥረት የተደረገ ቢሆንም፤ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ፣ መቆራረጥና አልፎ አልፎም መዘጋት ችግሮች ብሎም በቤት ውስጥ ትምህርትን የመከታተል ልምድ አናሳነት ጋር ተዳምሮ የተሟላ ትምህርት ለመስጠት የተቸገርንበትን ዓመት አሳልፈናል።

ሌላው ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የሚነሳው በአዲስ አበባና በክልል ታላላቅ ከተሞች ለይቶ ማቆሚያዎችና ማገገሚያ ማዕከላትን ለማቋቋም የተወሰደው ፈጣን እርምጃ ነበር። የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውንና ሕዝቡን ከዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ለመታደግ የነበራቸው የመንፈስ ዝግጅትም ጥሩ ነበር። ሆኖም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እና የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ኅብረተሰቡ ለበሽታው ያለው ተጋላጭነት በመዘናጋትና በቸልተኝነት የተዋጠ መስሏል። መንግሥት 17 ሚሊዮን ዜጎችን ለመመርመር ያስተላለፈው ውሳኔና አተገባበሩም የባህርይ ለውጥ እንደሚያመጣና የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ እንደሚያስችል ይታመናል። ኮሮናን የምንቆጣጠረው እንጂ፤ የሚቆጣጠረን እንደማይሆን እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ተስፋ የሚሰጡ ናቸው።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙዎች በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውን 6ኛውን አገራዊ ምርጫ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዛወር ማድረጉ ሌላው የዓመቱ ትልቅ ክስተት ሆኖ አልፏል። ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ ምክንያት ለነሐሴ ታቅዶ የነበረውን ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፋለች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ካሳወቀ በኋላ መንግሥት አማራጮችን አቅርቧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መበተን፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ ሕገ-መንግሥቱን ማሻሻል፣ የሕገ-መንግሥት ትርጓሜ መጠየቅ የሚሉ አራት አማራጮችን አቅርቦ ከሚመለከታቸው አካላት መክሮበታል። በመጨረሻም ሕገ- መንግስታዊ ትርጓሜ መጠየቅ የሚለው አማራጭ የውሳኔ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡

በዚህም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

በሰጠው ውሳኔ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሕዝብ ጤና ስጋት ሆኖ ባለበት ሁኔታ ምርጫውን ማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የፌዴራልና ክልል ምክር ቤቶች የስልጣን ዘመን እንዲቀጥል እንዲሁም አጠቃላይ ምርጫው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ወረርሽኙ የሕዝብ ጤና ስጋት አለመሆኑን ካረጋገጡበት ጊዜ ጀምሮ ከዘጠኝ ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ እንዲካሄድ ወስኗል፡፡

የኮሮና ቫይረስ የአቅርቦት፣ የፍላጎትና፣ የፋይናንስ ቀውስ በማስከተል በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ያሳደረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል ባይሆንም በሌላ በኩል ወረርሽኙ የራሱ የሆነ መልካም እድልም ይዞ መጥተዋል፡ ፡ በዓመቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ ከወጪ ንግድ የሚገኘው ገቢ ከአምስት ዓመታት በኋላ 3 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል። የአገሪቱ ዓመታዊ ጥቅል ምርት 3 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ዓቢይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ይፋ አድርገዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት አገራዊ ጥቅል ምርቱ 2 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ነበር። ለግል ዘርፍ የሚመደበውም ብድር ከ90 ቢሊዮን ብር ወደ 160 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ገልጸዋል።

የፋይናንስ ተቋማት በተለይ ባንኮች በተቀማጭ፤ በቁጠባና በብድር የሚሰጡት አገልግሎት ዕድገት ማስመዝገብ ቀጥሏል። ዓለም በኮሮና ወረርሽኝ ቤቱን በዘጋበት ዓመት በእንቅስቃሴ ውስጥ መቆየት በራሱ ትልቅ ነገር ነውና። በዓመቱ ውስጥ 12 ያህል ባንኮች በምስረታ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የተወሰኑት በአገሪቱ የመጀመሪያ የሚሆነው እስላማዊ ባንኮች ናቸው። ንግድ ባንኮች በየራሳቸው የሚከፍቷቸው የሸሪዓን ሕግ የሚከተሉ ቅርንጫፎችና መስኮቶች እንደተጠበቁ ሆነው ማለት ነው። የአገሪቱ ባንኮች 87 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ሲያደርጉ፣ የሰጡት ብድር 221 ቢሊዮን ደርሷል። እንዲሁም ከሰጡት ብድር ውስጥ 138 ቢሊዮን ብር ብድር ተመልሶላቸዋል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ብልጫ የተመዘገበበት ዘመን እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የባንኮች የተበላሸ ብድር መቀነስም ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ያበረከተው አስተዋጽኦ የጎላ ነበር። በመንግሥታዊዎቹ ሁለት ባንኮች ብድር አመላለስ የነበረው ችግር እየተስተካከለ መጥቷል። በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበላሸ ብድር ወደ ሁለት በመቶ ወርዷል። በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያልተመለሰ ብድር 34 ከመቶ ነው። ከ2011 ተመሳሳይ ወቅት የ13 በመቶ ቅናሽ እንዳሳየ አስረድተዋል።

ከቡና የወጪ ንግድ 667 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ይህም ከዕቅዱ 16 በመቶ ብልጫ አለው። ከአበባ የተገኘው 440 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ዕድገት የተመዘገበበት ነበር ይላሉ ዶክተር ዐቢይ በሪፖርታቸው። በማዕድን ዘርፍ ከወርቅ የተገኘው 800 ኪሎ ግራም ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ሆኗል። ይህም 27 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለውና ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ የተመዘገበ የተሻለ ውጤት እንደሆነ አስታውቀዋል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ ዕድገት የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከወጭ ምርቶች የተሻለ ገቢ እንዲገኝ መልካም አጋጣሚ የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል።

መንግሥት ባንኮች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ እንዲገዙ ከተቀመጫቸው 27 በመቶ የሚይዝበትን አሰራር ማስቀረቱ በተሻለ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ አስችሏቸዋል ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ። ውዝፍ ግብር ለነበረባቸው ነጋዴዎች 78 ሚሊዮን ብር ዕዳ መሰረዙንም አስታውቀዋል። ኮሮናን እየተከላከሉ ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ የተደረገው ጥረት በግብርናው ዘርፍ ያልታረሰ መሬት ጭምር ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ በምግብ ራስን የመቻል እንቅስቃሴን በሚደግፍ መልኩ እንዲከናወን ተደርጓል። የምሥራቅ አፍሪካ ስጋት የነበረው የበረሃ አንበጣን ወረርሽኝ በመከላከል ረገድ 95 በመቶ ውጤታማ መሆን የተቻለበት ዘመንም ነበር።

ከዚሁ ከኮቪድ 19 ጋር የሚያያዘው ሌላው ጉዳይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የ’’ማዕድ ማጋራት’’ መርሐ ግብር ነው፡፡ ወገን ወገኑን የሚደግፍበት ቅን ልብ እንዳለው አስመስክሯል። የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህላችን ዛሬም እንዳለ አሳይቶናል። በወረርሽኙ ኑሯቸው ለተናጋ ወገኖች ከምግብ እስከ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ተለግሷል። በተጨማሪም በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎች፣ ማህበራትና ተቋማት ለጤና ተቋማት ሳይቀር ድጋፍ አድርገዋል። በጎደለ ሞልተዋል። ባነሰ ጨምረዋል። በተለይ በአሜሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለራሳቸው ሥራ አጥተውና ለወረርሽኙ ተጋልጠው ባለበት ወገንን ለመርዳት ያሳዩት ተነሳሽነት የሚያስደንቅ ነበር።

2013 ዓ.ም ምን ይዞልን ይመጣል?

አዲሱ ዓመት ተስፋዎችን ይዞ መጥቷል። በሂደት ችግሮች ሊያጋጥሙን ይችላሉ። ሁሉንም አጣጥመን መሄድ የሕይወት ግዴታ ነው፡፡ ዘመንን ጥሩም መጥፎም የምናደርገው እኛው ነን። እርግጥ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ነገሮች የሚለውጡት ነገር ይኖራል። ኢትዮጵያውያን በዜግነታቸው የሚኮሩባት፣ ዜጋዋ በመሆናቸው የማያፍሩባት አገር ለመመስረት የተጀመረው ጥረት አንድ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በማንነትና በእምነት ልዩነት የሚጠቁበት ሁኔታ እንዳይከሰት ለመፍጠርም ያለሰለሰ ጥረት ይደረጋል። በ2013 ዓ.ም መንግስት የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት እና ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ብዙዎች ይስማማሉ። በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲታነፅ የመንግሥት አመራሮችም ሆኑ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ከብሔር ተኮር አጀንዳዎች ይልቅ ብሔራዊ መግባባትን በሚፈጥሩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ



27

ማተኮር ግድ ይላቸዋል፡፡ የተለየ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነቶቻቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር በጋራ በመምከር መስራት ይጠበቅባቸዋል።

በአዲሱ ዓመት ከመንግስት ከሚጠበቁት ዋና ዋና ተግባራት መካከል የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በበለጠ ጠንክሮ መስራት ነው፡፡ አሁን በአገሪቱ አንድ አንድ አከባቢዎች የሚስተዋሉ የስርዓት አልበኝነት እንቅስቃሴዎች በማስወገድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሶ የሚሰራበት፣ በሰላም የሚኖርበትና ሃብት የሚያፈራበት ሕገመንግስታዊ መብቱ መከበር አለበት። በአገርና በክልል ደረጃ ባለፈው ዓመት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስተጓጎሉ በኋላ የሚካሄደው ምርጫ ነጻ፤ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ብሎም ተዓማኒነት ያለው ሆኖ የሕዝብ ድምዕ የሚሰማባቸው ምክር ቤቶች ይሆናሉ። መቼም ምሉዕ በኩለሄ የሆነ ነገር ስለሌለ ቅሬታዎች ባይቀርም።

በአዲሱ ዓመት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ኤሌክትሪክ በማመንጨት ብሥራት ያሰሙናል። የግደቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትም በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል። አሁንም በግብጽ በኩል እየተደረገ ያለውን የሀገራችንን ጥቅምና ሉዓላዊነትን በነካ መልኩ በዓባይ ውሃ ተጠቃሚ የመሆን ሀሳብ በአግባቡ በመረዳት በመንግስት በኩል እየተወሰዱ ያሉ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን በትክክል ተገንዝቦ የሀገርን ጥቅም በማስቀደም መደገፍ ያስፈልጋል፡፡ መላው የሀገራችን ዜጎች በተለያዩ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎች ሳይሸበሩ መንግስት ይህን የባንዲራ ፕሮጀክታችንን ለመጨረስ ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር በሚደረገው ድርድር የሀገራችንን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ካልሆነ ምንም አይነት ስምምነት እንደማያደርግ በመረዳት የጀመርነውን ይህን ታሪካዊ ግድብ አጠናቀን ለትውልድ ለማስተላለፍ በአንድ ዓላማ ልንረባረብ ይገባል፡፡

ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበረው የፍኖተ ብልጽግና የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ትግበራው ይጀመራል። ዕቅዱ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ የሕዝቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተዘጋጀ ነው። ዕቅዱ አገሪቱ በ2011 ያፀደቀችውን ‘’ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ’’ መነሻ ያደርጋል። አጀንዳው ‘’የኢትዮጵያን የልማት እምቅ ኃይል ማበልጸግን’’ ዓላማው ያደረገ መርሃ ግብር ነው። በፕላንና ልማት ኮሚሽን አማካይነት የሚተገበረው መርሃ ግብር በዋነኝነት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ለማሻሻል የተሰናዳ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩ ባለፉት ዓመታት የተገኘውን ስኬት ላይ በመመስረት ይተገበራል። በዚህም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትን ለማስተካከልና መዋቅራዊ ማነቆዎችን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል።

አዳዲስ ዕድሎችንና የዕድገት ምንጮችን ለመፍጠር

መደላድል ለመፍጠር፤ ስኬቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የፖሊሲና ተቋማዊ ማዕቀፎችን ደረጃ ለማሻሻል የሚሰራበት ዓመት እንደሚሆንም ይጠበቃል። ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችሉ ቀልጣፋና ግልጽነት የተላበሱ መንግሥታዊ ተቋሞች መኖር አስፈላጊ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ተቀምጧል። መርሃ ግብሩ ሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ ማክሮ-ኢኮኖሚያዊ፣ መዋቅራዊና ሴክቶራል ማሻሻያዎችን እንደሚያካትት የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል። የመርሃ ግብሩ ዓበይት ግብ ዘላቂ የኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ማረጋገጥ፣ ሰፊ የሥራ ዕድሎችን መፍጠርና ድህነትን መቀነስ ናቸው፡፡

ኢንቨስትመንት ከአገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት ድርሻ እንዲያድግና ኢኮኖሚው የሚያጋጥሙትን ውጫዊ ተጽዕኖዎችን በሚቋቋም መልኩ መገንባትን ዓላማው ያደርጋል፡፡ መርሃ ግብሩን ለማሳካትም የአገር ውስጥ ቁጠባን ለማሻሻል ጥረት የሚደረግ ሲሆን፣ የውጭ ፋይናንስን በሚመለከት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመሸጥ ገቢ ለማግኘት ይታሰባል፡፡

የአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ከኮቪድ-19 በኋላ ተስፋ እንዳለው ዓለም አቀፍ የቱሪዝምና የአስጎብኚ ድርጅቶች መረጃዎች ከወዲሁ እየገለጹ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሪፖርታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ስራቸው እየተከናወኑና በመጠናቀቅ ላይ ባሉት የአንድነት፣ የእንጦጦና የሸገር የወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ዘርፉን እንዲያድግና የአገሪቱን የቱሪስት መስህብነት እንዲጨምር ያደርጋሉ ብለዋል። ክልሎች ለቱሪዝም የሚሆኑ ሀብቶቻቸውን ለይተው ለዘርፉ ዕድገት ብቻ ድርሻቸውን መጫወት እንደሚችሉ ኮንታን፤ ዘጌንና አፋርን በመጥቀስ እንዲያለማቸውም ጠይቀዋል። ’’ገበታ ለሀገር’’ የተሰኘ መርሃ ግብር ይፋ አድርገው ሀብት ማሰባሰብ ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ሞዴል ሆና መገኘቷን የምታጠናክርበት ዓመት እንዲሆንም ሰፊ ርብርብ ያሻል። በሂደትም ወደ ፖለቲካ መስተጋብርነት የሚቀይሩ ተግባራት በአዲሱ ዓመት እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል። በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሚካሄደው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሎም በማደግ ላይ የሚገኙ አገሮች ‘’ድምፅ’’ መሆኗን ትቀጥላለች። በተለይም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አየደረሰ ካለው የጤናና የኢኮኖሚ ጉዳት ለመታደግ አበዳሪ ድርጅቶችና ለጋሽ አገሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ ትጠይቃለች።

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የተዘገ ይከፈታሉ። ትምህርት ቤቶች። የወረርሽኙን መከላከያ መንገዶች በአግባቡ በመተግበር የትምህርት ስርአቱ ይከናወናል። ኮቪድን ከመከላለል ጎን ለጎን የጤና ስርአቱን የማዘመን አሰራርም በተሻለ ትኩረት እንደሚከናወን ይጠበቃል፡፡ ወረርሽኙ ፈተናችን ሆኖ በዚህኛው ዓመት በተወሰነ ጊዜም ይቀጥላል።

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያበቃበት ትክክለኛ ጊዜ ስለማይታወቅ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ሚያሳድረው ተፅዕኖ መፈጠሩ አይቀርም። በ2013 በኢኮኖሚው ዘርፍ ከሚጠበቁት ችግሮች መካከል የገቢና ወጪ ንግድ ሚዛን ያለመስተካከል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ አለመሟላትና የመንግሥት ተበዳሪነት መቀጠል መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም ከውጭ መንግሥታት የሚገኘው ድጋፍና ብድር ኮሮናን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች መቀነስና ክልሎች የቱሪዝም ሀብታቸውን ለማልማት የአቅምና የትኩረት ማነስም የሚጠበቁ ችግሮች ናቸው፡፡ በአቅም ማነስ ወይም በሀብት እጥረት ምክንያት ዕቅዶች ላይሳኩ ይችላሉ። የውጭ ምንዛሪ እጥረት በዘርፉ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ጫና ማሳደሩ አይቀርም። በተለይ በካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም።

በፖለቲካው ዘርፍም በዓመቱ አገራዊ አንድነትን የሚፈታተኑ ችግሮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። የሕግ የበላይነት በማስከበር ረገድ ያለው ግንዛቤ በሚጠበቀው ደረጃ አለመድረስ ችግር ሆኖ ሊቀጥል ይችላል። በአጠቃላይ ግን አንዱን ዘመን አጠናቀን ወደ ሌላው ተሸጋግረናል። በዕድሜያችን አንድ ዓመት እንጨምራለን። በዚያው ልክ አገርም ወደፊት እንድትራመድ በሚያልፈው ዕድሜያችን ጠቃሚ ሥራዎችን ማከናወን ይጠበቅብናል። እናም አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ ተቀብለን የተሻለች አገር ለመገንባት መነሳት ይጠበቅብናል። ዜጎች ደህንነታቸው ተረጋግጦ በሰላም ወጥተው መግባት ብሎም በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት ይፈልጋሉ። አገሪቱ ለአንዱ ተብላ የተፈጠረች ሳትሆን፤ የሁሉም እንደሆነችም ያምናሉ። ሕዝብ ሕይወቱን በሥራ በመቀየር ለልማትና ለዕድገት ለመትጋት ይፈልጋል። ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ተከብረውለትና ግዴታዎቹን እየተወጣ መኖርም ፍላጎቱ ነው። አገሩ በሁለንተናዊ መልኮቿ ወደፊት እንድትራመድ በመትጋት የተሻለ ኢትዮጵያን ለመፍጠርም ጥረቱን ይቀጥላል። ለሁሉም በምትበቃው አገርና በዘመነ ሉላዊነት ዘረኝነትን ማስተናገድን አይሻም።

ስለሆነም አዲሱን ዘመን የምትቀላቀለው ኢትዮጵያ ብዝኃነትን ያስጠበቀችና ያከበረች፤ ሕዝቦቿ የሚዋደዱና የሚከባበሩባት ሆና እንድትቀጥል በመስራት ነው። በማንነት፣ በባህል፣ በፆታ ልዩነት የማይደረግባት ለሁሉም የተመቸች አገር መገንባት ያሻል። የዴሞክራሲ ሥርዓት አብቦና ለምልሞ ፍሬ የሚያፈራባት ኢትዮጵያ እንድትኖረን ጠንክሮ መሰራት ያስፈልጋል። ለዚህም የንግግር፤ የውይይትና የክርክር ባህልን ማሳደግ ይገባል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ፤ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ መድረኮች ‘’ድምፅ’’ ሆና ትቀጥላለች። አኩሪ የሆነውን የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል በማጠናከር የተቸገሩትን መርዳት፣ የወደቁትን ማንሳት፣ የተፈናቀሉትን ማቋቋም፣ የተሰደዱትን በራሳቸው ቤት እንዳሉ አድርጎ መንከባከብን እንደ ባህል ማስቀጠል ከሁላችንም ይጠበቅብናል።



28

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ፖለቲካ

የፍትህ ስርአቱ በህግ መነጽርል



29

የኢትዮጵያ የፍትሕ ታሪክ ረጅም ዘመናትን ቢያስቆጥርም የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችልና የዜጐችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚያስከብር ነፃ የዳኝነት አካል እንዳልነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በኢትዮጵያ በ1923 ዓ.ም የወጣው የመጀመሪያው ሕገ¬-መንግሥት ስራ ላይ ከመዋሉ አስቀድሞ እንደ ሕገ-መንግሥትና ሕግ ሲያገለግሉ የነበሩ የተለያዩ የሕግ ሰነዶች እንደነበሯትም እንዲሁ። ከሰነዶቹ መካከል ፍትሐ ነገሥት እና ክብረ ነገሥት በመባል የሚታወቁት ተጠቃሽ ናቸው። እነዚህ ሰነዶች ቢኖሩም ሃይማኖታዊ ይዘት የነበራቸውና በቤተ መንግሥት አካባቢ የተወሰኑ በመሆናቸው እንደ ሕግ በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ ሆነዋል ለማለት ግን አያስደፍርም።

በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ሁለት ሕገ-መንግሥቶች ወጥተው ስራ ላይ መዋላቸውን ታሪክ ያስረዳል። የመጀመሪያው በ1923 ዓ.ም የወጣው ሕገ-መንግሥት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በ1948 ዓ.ም እንደገና የተሻሻለው ነው። መጀመሪያ የተደነገገው ሕገ መንግሥት ንጉሡ የማይከሰሱ በእግዚአብሔር የተመረጡ ልዩ ፍጡር መሆናቸውን በግልፅ የደነገገ በመሆኑ የሕግ የበላይነትን የተቀበለና ለዳኝነት አካሉ ነፃነት የሰጠ አልነበረም። ሁለቱም ሕገ መንግሥቶች ስለዳኝነት ሥራ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ቢኖሯቸውም፤ ዳኞች የሚሾሙት በአካባቢ ገዢዎችና በንጉሠ ነገሥቱ አጽዳቂነት እንደሆነ በግልፅ አስቀምጠዋል። በመሆኑም ንጉሡ ባሻቸው ጊዜ ዳኞችን ከሥራቸው ለማንሳትም ሆነ ለመሻር ሙሉ ሥልጣን ስለነበራቸው የሕግ ማዕቀፉ ዳኞች ነፃ ሆነው ውሣኔ የሚሰጡበት ሁኔታ አልፈጠረም። ንጉሡ በቀጥታ ፍርድ የሚሰጡበት የመጨረሻ ይግባኝ ሰሚ የዙፋን ችሎት በሚል ይታወቅ የነበረውን ከፍተኛ የዳኝነት አካል ይመሩም ነበር። ይህም በሕግ አውጪው፣ ተርጓሚውና አስፈጻሚው መካከል ግልፅ የሥልጣን ክፍፍል እንዳልነበር አስረጂ ነው። ስለሆነም በዘመኑ የዳኞችንና የፍትሕ አካላትን ነፃነት ማንሳት አይታሰብም።

በወታደራዊው የደርግ አስተዳደር ዘመንም የፍርድ ቤቶች እና የዳኝነት ሥልጣን በጊዜ ቀመር የተገደበ እንደነበር መረጃዎች

በፍቅርተ ባልቻ



30

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ያመለክታሉ። ለዚህ በ1980 ዓ.ም የወጣው ሕገ መንግሥት አብነት ነው። ይህ ሕገ መንግሥት የዳኞችን የአገልግሎት ዘመን እንደ ሕዝብ እንደራሴዎች የገደበ፣ ዳኞችን የሥራ ዋስትና ያሳጣና ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ ሁሉንም የመንግሥት አካላት የመቆጣጠር ሥልጣን ለሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሰጠ በመሆኑ ነፃ የዳኝነት አካል ለማቋቋም አልፈቀደም።

በሀገሪቱ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገ ከአራት ዓመት በኋላ በ1987 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት ተከትሎ የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 መሰረት የፌዴራል መንግሥት መዋቅሩን መነሻ በማድረግ በፌዴራልና በክልል ደረጃ ፍርድ ቤቶች እና የዳኝነት አካላት እንዲቋቋሙ ተደርጓል። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) የዳኝነት ስልጣን በፌዴራል መንግሥቱ እና በክልሎች የተከፋፈለ መሆኑን በግልፅ አስቀምጧል። ይህ አዋጅ ይሄንኑ ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ስልጣን መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ የታወጀ ነው።

የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ነፃነት ከሕግ አንጻር

የፍትሕ አካላትን በተለይም የፍርድ ቤቶችንና የዳኞችን ነፃነት አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ መመዘኛ ማግኘት ቢያስቸግርም ከሞላ ጎደል ግን አብዛኞቹ ሀገሮች የሚስማሙባቸው ሰነዶች አሉ። በመንግሥታቱ ድርጅት፣ በአፍሪካ፣ በአውሮፓና በእስያ የተለያዩ ሰነዶች ስለፍትህ አካላት ገለልተኝነት፣ ስለዳኞች ነፃነት፣ ከሰብዓዊ መብቶች ጋር የተያያዙ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተውና ድንጋጌዎች ወጥተው በስራ ላይ ውለዋል። በዚህ ረገድ የአፍሪካ ቻርተር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ ተጠቃሾች ናቸው።

በተለይ ዴሞክራሲን፣ ምርጫዎችን እና አስተዳደርን የተመለከተው የአፍሪካ ቻርተር (African charter on De- mocracy, Elections and Governance) በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ ጥር 2007 ዓ.ም የታተመው የአፍሪካ ቻርተር ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ የፍትሕ አካላትና ባለሙያዎች ነፃነት በሕገ-መንግሥት፣ ዋስትና እንዲኖረውና ከተጽዕኖ ነፃ መሆን እንደሚገባው በአንቀጽ 2 በግልፅ ደንግጓል። ከዚህም ባሻገር የፍትሕ አካላት ሥራቸውን የግልጽነትና የተጠያቂነት አሠራር መርህን ዘርግተው ማከናወን እንደሚጠበቅባቸውም አመልክቷል። ይህም የዳኞች ምርጫና ሹመት ሂደት በሕግ አግባብ ብቻ እንዲፈጸም ስለሚያደርግ ነፃነታቸውን ለማስጠበቅ እንደሚያስችልም ያስረዳል።

ዘርን፣ ፆታን፣ ቀለምን፣ ሃይማኖትን፣ ኃብትን መሰረት አድርጎ የዳኞች ምርጫና ሹመት ማከናወን እንደማይገባ ኦክስፎርድ ኮንስቲቱዩሽናል ለው ኢንሳይክሎፒዲያ እ.ኤ.አ መጋቢት 2019 “Independence of the Judiciary” በሚል ርዕስ ያቀረበው ጽሑፍ ያስረዳል። መረጃው አያይዞም ዳኞችና ፍርድ ቤቶች ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ ለማስቻል የተቋማቱን ፋይናንስ ነፃነት የሚያረጋግጥ ሕግ ማበጀት እና መተግበር በተለይም ዳኞች በሚወስኑት ውሳኔ ምክንያት የስራ ዋስትና እንዳያጡ የሚረዳ አሰራር መዘርጋቱን አስነብቧል።

በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 79 የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ መሆኑንና ነፃ የዳኝነት አካል መቋቋሙን ተደንግጎ እናገኛለን። በሀገራችን የሕግ ተርጓሚ የሆነው የፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሚባሉ ሦስት እርከኖች እንዲደራጁ መደረጉን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መረጃ ያስረዳል። በተመሳሳይ ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮችም በተለያዩ እርከኖች እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ድረስ እንዲደራጁ ተደርጓል።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 ንዑስ አንቀፅ (1) ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ የማግኘት መብት እንዳለው፤ በአንቀጽ 78 ንዑስ አንቀፅ (1) ደግሞ ነፃ የዳኝነት አካል መቋቋሙን፣ የፌዴራል ፍርድ ቤት ከፍተኛው የዳኝነት አካልም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሆነ በግልፅ ተደንግጓል።

እንዲሁም በአንቀጽ 79 ንዑስ አንቀፅ (1) በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የዳኝነት ስልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ እንደሆነና በንዑስ አንቀጽ (2) በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካልና ባለስልጣን ተጽዕኖ ነፃ መሆናቸውን ሲደነግግ፤ በንዑስ አንቀጽ (3) ደግሞ ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነፃነት እንደሚያከናውኑና ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ እንደማይመሩ በግልጽ አስቀምጧል።

በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እንደሚያስወስንና ሲፈቀድም በጀቱን እንደሚያስተዳድርም አስቀምጧል።

የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ነፃነት ምን እንደሆነ፤ የነፃነት ማሳያዎች ምን እንደሆኑና ማንኛውም ሰው ነፃ እና ገለልተኛ በሆነ ፍርድ ቤት ፊት ቀርቦ ፍትሃዊ በሆነ አግባብ የመሰማት መብት እንዳለው በርካታ የሕግ ሰነዶች ያስረዳሉ። በዓለም አቀፍ መርህ መሰረት ዳኞች በሕግ እየተመሩ ነፃ ሆነው የመስራት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም “International Principles on the Independence and Accountability of Judges, Lawyers and Prosecutors” እና “international commission of Jurists” በሚሉ ርዕሶች የተሰናዱት የሕግ ድንጋጌዎች በስፋት አብራርተዋል።

የዳኝነት ነፃነት ትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ላይ ጥላቻና ፍራቻ፣ ስሜትና ግፊት ቦታ እንዳይኖራቸው ዳኞች ጉዳዮችን በሕግ አግባብ መርምረው በሕጉ መሠረት ውሳኔ እንዲሰጡ ማስቻሉን አቢሲኒያ ሎው ድረ ገፅ “ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ወይም ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ቀዳሚ ነገሮች” በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ መስከረም 2014 ያሰናዳው ጽሁፍ ያስረዳል።

የዳኝነት ነፃነት ጽንሰ ሀሳብን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ንዋይ እንዲህ ያስረዳሉ። የዳኝነት ሥርዓቱ ከማንኛውም አካል ጣልቃ ገብነትና ተጽዕኖ ነፃ ሆኖ የጉዳዮችን ፍሬ ነገርና ማስረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ብቻ ሊሰጥ እንደሚገባ የሚያስረዳ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ፅንሰ ሃሳቡን

ተቋማዊ እና ግለሰባዊ የዳኝነት ነፃነት በሚል በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል ሲሉም ያክላሉ።

እንደ እሳቸው ማብራሪያ ተቋማዊ የዳኝነት ነፃነት (Institu- tional Judicial Independence) ለማስጠበቅ ነፃነቱን በሕግ ማሳወቅ ወይም ማወጅ፣ ነፃ የሆኑ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ ማድረግ እና በጀታቸውን በራሳቸው ማስተዳደር የሚችሉበት አሰራር መፍጠር፣ የዳኞችን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ የመሳሰሉትን ጉዳዮች እንዲፈጸሙ ግድ ይላል።

ግለሰባዊ ነፃነት የዳኝነት ነፃነት ሌላው ገጽታ ነው። ዳኞች በግለሰባዊ ህይወታቸው ቁጥብ ሊሆኑ እንደሚገባ፣ በፖለቲካዊ ጉዳዮች መሳተፍም ሆነ አስተያየት መስጠት እንደሌለባቸው፣ ማህበራዊ ግንኙነታቸውም የተገደበ መሆን እንዳለበት ይህን ማድረግ ካልቻሉ በሚመለከቷቸው ጉዳዮች ገለልተኛ ለመሆን እንደሚቸገሩ ያስረዳሉ።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ነፃነቱ የዳኝነት አካሉ በሥልጣን ክፍፍሉ መሰረት ራሱን ችሎ በሕገ- መንግሥቱና በአዋጅ ተቋቁሟል። የዳኝነት አካሉ በተከራካሪ ወገኖች የሚነሱ ክርክሮችን መርምሮ በሕጉ መሠረት ውሣኔ የመስጠት ተግባሩን በአግባቡ ለማከናወን የሚያስፈልገውን በጀት በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረብ መቻሉ እና ውስጣዊ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን እራሱ እንደሚወስን ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ማግኘቱ ለፍትሕ አካላት ለተሰጠው ነፃነት ማሳያ እንደሆነና የዳኞች ሙያዊ ነፃነት አንድ ዳኛ የቀረበለትን ጉዳይ ሕግንና ሕግን ብቻ መሠረት አድርጐ እንዲወስን ከውስጥና ከውጭ ከሚደርስበት ማንኛውም ተጽዕኖ ነፃ ሆኖ እንዲሰራ ማስቻል ነው።

በራውል ዋለንበርግ የሰብዓዊ መብት እና የጦርነት ሰብዓዊነት ሕግ ኢንስቲትዩት እና የሄይግ የሕግ ዓለም አቀፋዊነት ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው የሕግ ሰነድ የዳኝነት አካላት ከውጪ ተጽዕኖ ነፃ መሆንን ሲያብራራ፤ “የዳኝነት አካላት ከውጪ ተጽዕኖ ነፃ መሆን አለባቸው። በሕግና በሕጉ ብቻ ውሳኔ መስጠት አለባቸው። ውሳኔያቸው ከመንግሥት ተጽዕኖ ነፃ መሆን አለበት። ነፃነት በዳኞች አሿሿም፣ በስራ ባሕርይ፣ በስራ ዋስትና እና በደመወዝ አከፋፈል ሥርዓቶችና ሕጎች ከመንግሥት ተጽዕኖ ነፃ በሆነ መንገድ መረጋገጥ እና መጎልበት አለበት። ነፃነታቸው ዳኛው ወይም ዳኛዋ ለየትኛውም ወገን አለማዳላታቸውን ያካትታል። ዳኛው የሚያዳላ መሆኑን ተከራካሪ ወገኖች ከጠረጠሩ ሊሟገቱት መብቱ ሊኖራቸው ይገባል። ዳኛው ጉዳዩን እንዳያይ ማስነሳት ይችላል። ዳኞች ከተከራካሪ ወገኞች ከአንደኛው ጋር የዝምድና ወይም ሌላ ዓይነት ትስስር ካላቸው ከጉዳዩ ለመነሳት መብት ሊሰጣቸው ይገባል።” ብሏል።

የዳኝነት ስልጣን ትልቅ ነው፣ ምክንያቱም ሰውን ለማሰር ትዕዛዝ የሚሰጡት ዳኞች ብቻ ናቸው፣ ይህንን ስልጣን ደግሞ በአግባቡ ካልተጠቀሙበት አንዱን ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት የሚውልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። በመንግሥት በኩል ጣልቃ ገብነት ሲኖር አልያም ዳኞች የተሰጣቸውን ነፃነት ከደንበኞች ጋር ባላቸው ዝምድናና ትውውቅ ሳይፈጽሙ ሲቀሩ እንደሚጣስ የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

የፍርድ ቤቶች እና የዳኝት ስራ በርካታ ኃላፊነት እና ተቃራኒ



31

ፍላጎቶች ያሉበት በመሆኑ ማመዛዘን እንደሚጠይቅ፤ ዳኞች በሚሰጡት ውሳኔ ተቃራኒ ፍላጎቶች ካላቸው ወገኖች ተጽዕኖ ነፃ ሆነው መስራት እንደሚጠበቅባቸው፣ ከሌሎች ተጽዕኖ ብቻ ሳይሆን ከራሳቸው ስሜትም ጭምር ገለልተኛ የመሆን ፈታኝ ኃላፊነት እንዳለባቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ ያስገነዝባሉ።

እንደ ክብርት ፕሬዝዳንቷ ማብራሪያ የሕግ ባለሙያዎች የዳኝነት ነፃነት የኅሊና እና የሕግ ገደብ እንዳለው ከሕገ መንግሥቱ ጀምሮ በሌሎች የሕግ ማዕቀፎች ውስጥ የሚታይ ነው። ዳኞች ፍትሕ የመስጠት ተግባራቸውን የሚያከናውኑት በዋነኛነት በሕግና በሕግ ላይ ተመስርተው በመሆኑ ሕግን አክብረው፤ እንዲያስከብሩ ሁኔታው ያስገድዳቸዋል።

ፍርዱ በግፊት ወይም በስሜት፤ በጥላቻ ወይም በፍራቻ የተሰጠ ሆኖ በይግባኝ ሳይታረም ከጸና በሁለት በኩል ለነቀፋ የተጋለጠ ይሆናል። ይኸውም በአንድ በኩል ተጽዕኖው ከውስጥም ይምጣ ከውጪ በራሱ ሕገ ወጥ መሆኑ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ፍርዱ ወይም ውሳኔው በሕግ መሠረት ያልተሰጠ በመሆኑ ከራሱ አልፎ ሥርዓቱን ጭምር ለሥጋትና ለሐሜት በመዳረግ አመኔታውን ስለሚያሳጣው ነው። ይህ የዳኝነት ነፃነት የጥበቃ አድማስ ዳኚውንም ተዳኚውንም እንደሚያካት ያመለክታል። ሁለቱም ካልተጠበቁ ለአደጋ የሚጋለጠው ዳኛው የሚተረጉመው፣ ተከራካሪው የሚማጸነው ሕግ ነው። ሕግ ሥርዓት ስለሆነ ለሥጋት ከተጋለጠ አመኔታ ስለሚያጣ ነጸብራቁ ከዚያ አልፎ ህብረተሰቡን የሚያውክ ይሆናል።

ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ወይም ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ቀዳሚ ነገሮች መካከል የሚሰየመው ችሎት ከሚካሔደው ሙግት ወይም ክርክር ጋር የተገናኘ ሰፊ ዕውቀትና ልምድ ያላቸውና ስለጉዳዮቹ ማብራሪያ እና አስተያየት መስጠት የሚችሉ ዳኞች መሆን እንዳለባቸው ጠቅሶ በቁንጽል አመለካከት ወይም እውቀት የተሰጠ ውሳኔ በይግባኝ ተመዝኖ የሚለወጥ ወይም የሚሻሻል ቢሆን የዳኝነት ሥርዓቱን የሚያጠናክር እንጂ የሚያስነቅፍ እንደማይሆን አቢሲኒያ ሎው ድረ ገፅ “ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት ወይም ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ቀዳሚ ነገሮች” በሚል ርዕስ ያሰናደው ጽሁፍ ያስረዳል።

ስለሆነም የዳኝነት ነፃነት ከተወሰነ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሳይሆን ሰፋ ብሎ ከህብረተሰቡ የፍትሕ አስተዳደር ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ከላይ ከተጠቀሱት ፍሬ ሃሳቦች መረዳት ይቻላል።

ህጎቹ በገቢር … ግልፅ የሥልጣን ክፍፍል ባላቸው ዴሞክራሲያዊ ሀገሮች ነፃነቱ የተጠበቀ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራር መርህን የተላበሰ የዳኝነት አካል መኖር የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ወሳኝ ነው። ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትም ሆነ የተረጋጋ ሠላም የሰፈነባትን ሀገር እውን የማድረግ ራዕይ ማሳካት የሚቻለው ከማንኛውም ተጽዕኖና ጫና ነፃ የሆነ፣ ሕግና ፍሬ ነገር ላይ ብቻ ተመስርቶ አለመግባባቶችን መመርመር፣ መወሰንና ውሣኔውን ማስፈፀም የሚችል ጠንካራ ፍርድ ቤት ሲኖር ነው።

በሀገራችን ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች በመከተል ባለፉት

ዓመታት የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እና አደረጃጀቶች ተዘርግተው ሥራ ላይ እንዲውሉ በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቶች ከተጣለባቸው ትልቅ ኃላፊነት አንጻር የሚጠበቅባቸውን ያህል እንዳይጓዙ ያደረጓቸው ውስጣዊ ችግሮች እና ውጫዊ ማነቆዎች አልታጡም።

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሕጋዊ ዕውቅና ያገኘ፣ ከሦስቱ የመንግሥት አካላት በተለየ መልኩ የተደራጀና አባላቱንም ከተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማትና የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው። የዳኝነት አካል ነፃነት መገለጫ የዳኞች የዲሲፕሊን፣ የዕድገት፣ የሹመት፣ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲሁም የዕጩ ዳኞች ምልመላ ጉዳዮች ነፃና ገለልተኛ አካል በሆነው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የሚወሰን እንደሆነ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ-ገፅ አስነብቧል። ሆኖም የዳኞች ሹመት እና ምልመላ ሲደረግ ሕገ መንግሥቱን የተቀበለ የሚል መስፈርት በማዘጋጀት በዚህ ሰበብ ለፖለቲካ የተጠጉ (ቅርበት) ያላቸው ሰዎች እየተሾሙ መሆናቸውን የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሙሉጌታ ዮሐንስ ይገልጻሉ።

እንዲሁም አቶ ኃይሉ ታደሰ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድረ ምረቃ ትምህርት “የኢትዮጵያ ፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ” በሚል ርዕስ የሰሩት ጥናት በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የዳኞች ነፃነት ቢደነገግም ሹመታቸው ለአስፈጻሚው አካል ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ በኋላ ወደ ምክር ቤቶች ቀርቦ እንዲጸድቅ የሚደረግ መሆኑ፣ በተቋም ደረጃ ፍርድ ቤቶች ያላቸው ነፃነት በሕጉ በሰፈረው አግባብ የተጠበቀ እንዳልሆነ አረጋግጠው፣ ይህ መስተካከል እንደሚገባው ምክር ሀሳብ አስቀምጠዋል።

የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጠንካራ ሆኖ የፍትሕ አካሉን እንዲደግፍ በተለይ ከጉባኤው አባላት አብዛኞቹ ዳኞች እንዲሆኑ ስልጣኑም እንዲሰፋ የሚያስችሉ ነጥቦች በሚሻሻለው አዋጅ እንዲካተት መደረጉን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ይገልጻሉ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ጉባኤው ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ለሁለት ጊዜ ብቻ እንደተሰበሰበ ገልጸው፤ አሁን ግን ማስተካከያ ተደርጎ በየስድስት ወሩ መገናኘት እንደጀመረ፤ ይህም ፍርድ ቤቶች ላይ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ፣ አጀንዳዎቻቸው ላይም በነፃነት እየተወያዩ መሆኑን ያስረዳሉ።

ክብርት ፕሬዝዳንቷ አምና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የሦስት ዓመት የማሻሻያ ፕሮጀክት ዕቅድ ማስተዋወቂያና ትግበራ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ፍርድ ቤቶችን ለማዘመን እየተሰራ ነው ብለው ነበር። የማሻሻያ ፕሮጀክቱ የፍርድ ቤቶች እንዲሁም የዳኞች ነጻነት፣ ገለልተኝነት እና ተጠያቂነት፤ የፍርድ ቤቶች አገልግሎት ውጤታማነትና ቀልጣፋነት፤ የአገልግሎት ተደራሽነት ላይ ያተኮረ መሆኑን አብራርተው፤ ወንጀል እንዲቀንስ ግንዛቤ ለመፍጠር ካልተሰራ በፍርድ ቤቶች ላይ ብቻ በሚደረገው ማሻሻያ ለውጥ እንደማይመጣም እንዲሁ ገልጸው ነበር። የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌዴራል ጠቅላይ፣ የፌዴራል ከፍተኛ እና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ በቅርቡ በተካሄደው ውይይት ላይ እንዳሉት “እኛ ኢትዮጵያውያን የበሰለ ዳኝነትና የበሰለ ተቋም ያስፈልጉናል።” የበሰለ ዳኝነት ወይም ተቋም

ሲባል ሕግን ማዕከል አድርጎ የሚሠራ፣ ከየትኛውም አቅጣጫ ለሚመጣ ግፊት እጅ የማይሰጥ ዳኛና ተቋም ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ሁለቱም እጅግ በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ያስፈልጓታል።

እንደ ፕሬዝዳንቷ ማብራሪያ በዳኞች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥረው መንግሥት ወይም አስፈጻሚው አካል ብቻ አይደሉም። ተፅዕኖ ከመገናኛ ብዙኃን፣ ከሕዝቡና ከራሱ ከዳኛውም ይፈጠራል። ነገር ግን አንድ ዳኛ እነዚህን ተፅዕኖዎች ተቋቁሞና ተጨባጭ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሕግንና ህሊናውን ብቻ መሰረት አድርጎ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይታመናል። ዳኞች በችሎት የሚሰጡት ውሳኔ ከሳሽና ተከሳሽን እኩል አያስደስትም። የተወሰነለት በውሳኔው ሲደሰት የተወሰነበት ደግሞ ቅር መሰኘቱ አይቀርም። በውሳኔው ያልተደሰተው አካል “ፍርድ ቤቶች ነፃ አይደሉም” ሊል ይችላል። በዚህ ረገድ ማድረግ የሚቻለው ብቸኛው አማራጭ ሕዝቡን በማስተማር የሕግ ግንዛቤውን ማሳደግ ብቻ ነው።

የሕግ አማካሪና ጠበቃው አቶ ሙሉጌታ እየተደረጉ ባሉ ማሻሻያዎች የተገኙ ውጤቶች ይኖሩ ይሆን በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “የፍርድ ሂደቱ እየሄደ ያለው አስቀድሞ በነበረበት አሰራር ነው። የዳኞች ሹም ሽር በተደረገ ሰሞን ረጅም ጊዜ ይሰጥ የነበረው ቀጠሮ አጭር የማድረግ ሁኔታ ቢታይም ለተወሰነ ጊዜ ከቆየ በኋላ ወደ ነበረበት ይመለሳል፤ በእኔ እይታ በፍርድ ሥርዓቱ ላይ የተሻሻለና በተጨባጭ መሬት ላይ ወርዶ የህብረተሰቡን ችግር መፍታት አስችሏል የሚባል እንዳልሆነ ሂደቱም ምልልሱም አሰልቺ ነው።” በማለት ያትታሉ። እንዲሁም “ለውጥ አላየንም በነበረው ነው እየቀጠለ ያለው፤ በተለይ በወንጀል ጉዳዮች ላይ ያለው አመለካከት አልተቀየረም” በማለት በሃሳቡ የሚስማሙት ሌላው የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ አቶ ዮሴፍ ኪሮስ ናቸው።

ከሦስቱ የመንግሥት አካላት አስፈጻሚው እንደ ሽብርተኝነት፣ ሙስና እና የወንጀል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በግልፅ የማይታዩ ቢሆንም፤ ጣልቃ የመግባት ፍላጎቶች ግን ይስተዋላሉ፣ ነገር ግን የሚከሰተው በጥቂት ጉዳዮች ላይ ነው፤ በማለት እያጋጠማቸው ያለውን ችግር የገለጹት አቶ ዮሴፍ ኪሮስ የድርጊቱን አሳሳቢ እና አደገኝነት በመግለጽ የመንግሥት ባለስልጣናት (በግለሰብ ደረጃ) ለሚያውቋቸው ሰዎችና ድርጅቶች በፍትሃብሔር ጉዳዮች ጭምር ጣልቃ የሚገቡበት ሁኔታ እንደሚስተዋል ይጠቅሳሉ። ይህም በእነዚህ ጉዳዮች ለተከሰሱ ሰዎች ጥብቅና የመቆም ፍላጎት እንዳይኖራቸው ማድረጉን የጥብቅና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ይህንን አስመልክቶ ብዙ ጠበቆች በወንጀል፣ በሙስናና በሽብር ጉዳዮች ጥብቅና የማይቆሙት ለምን እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባዩ አቶ ተስፋዬ “ዳኞች ካለማንም ጣልቃ ገብነት በሽብርም በወንጀልም ችሎቶች በነፃነት እየሰሩ እንደሆነ ነው መረጃ ያለኝ፤ ምናልባት ጠበቆች የተከሳሾችን ጉዳይ ይዘው እንዳይሄዱ በራሳቸው ወይም በሌላ አካል ተጽዕኖ ስር በመሆን ጉዳዮችን ላይዙ ይችሉ ይሆናል። ከፍርድ ቤቶች አንጻር ግን ዳኞች ከማንም ተጽዕኖ ነፃ ሆነው ደንበኞችን እንዲያስተናግዱ የራስ መተማመን (confi- dence building) እንዲኖራቸው የሚያስችል ስራ ሰርተናል፤



32

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ጠበቆች በእነዚህ ጉዳዮች እንዳይሰሩ ተጽዕኖ ያሳደሩባቸው እነማን እንደሆኑ ለምን ጉዳዮቹን እንዳልያዙ ምክንያቶቹን በደንብ ማጥናት ይፈልጋል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ዳኞች ጉዳዮቻቸውን በገለልተኝነት እያዩላቸው እንዳልሆነ ሲሰማቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደመፍትሔ የተቀመጡ አሰራሮች እንዳሉ የሕግ አማካሪና ጠበቃው አቶ መሉጌታ ዮሐንስ ያስረዳሉ። ይህም ምክንያቶቹን ጠቅሰን አቤቱታ እናቀርብና ዳኞቹ በራሳቸው እንዲያስተካክሉ አልያም መዝገቡ ሌሎች ዳኞች እንዲከታተሉ ለማድረግ ነው። በዚህም መልኩ ታይቶ በሚወሰነው ውሳኔ ያልተደሰተ አካል ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳለውም ይገልጻሉ። እንደባለሙያዎቹ ገለጻ ከሆነ ጣልቃ ገብነቱ የሚከሰተው የፍርድ ሂደቱ በተገቢው ሁኔታ ሲከናወን ቆይቶ ውሳኔ ደረጃ ላይ ሲደረስ ስለሆነ ዳኞች ገለልተኛ ሆነው ጉዳዩን አላዩልንም የሚል አቤቱታ አስቀድሞ ለማቅረብ ያስቸግራል።

በሕግ ማዕቀፎቹ የተጠቀሱትን የፍርድ ቤቶች እና የዳኞች ነፃነት ማስፈጸም ላይ ብዙ ችግሮች እንደነበሩ በተለያዩ መድረኮች ከሚነሱ ሃሳቦች ማየት ችለናል፣ የተለያዩ ሰዎች በጉዳዮች ጣልቃ የመግባት ፍላጎቶች እንደነበሩ ዳኞች ያነሳሉ በማለት የነበረውን ክፍተት የገለጹት አቶ ተስፋዬ ንዋይ ናቸው። የፍርድ ቤቶች ትልቁ ኃብታቸው ነፃነታቸው ቢሆንም የዳኝነትን ነፃነት በአግባቡ ባለመተግበር በተጽዕኖ ስር የሚገቡ የተወሰኑ ዳኞች እንዳሉ፣ ነፃ ሆኖ ሚዛኑን ጠብቆ በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ለመተግበር እጥረቶች እንደነበሩ አሁንም በገለልተኝነት ውሳኔዎችን መስጠት ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ እንዳልተቀረፉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ ይገልጻሉ።

እንደ የሕግ አማካሪውና ጠበቃው አቶ ዮሴፍ ኪሮስ እምነት አሁን ላይ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው “እውነት ትፍረደኝ” የሚለው አመለካከት ተሸርሽሮ በምትኩ በመተዋወቅ ጉዳይ ማስፈጸም ልማድ ሆኗል። ቀደም ባሉት ጊዜያት ሰዎች ሲጣሉ በሕግ አምላክ ከተባለ ጸቡ ቀዝቀዝ ይል እንደነበር ሲገለጽ ሰምተንም፣ አጋጥሞንም ይሆናል። የሕግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ሰው ፍርድ ቤት የሚያስኬድ ጉዳይ ሲገጥመው መጀመሪያ የሚያደርገው የሚያውቀውን ሰው መፈለግ ነው፣ እኛም ጋ ሲመጡ ዳኞቹን ታውቋቸዋላችሁ? የሚል ጥያቄ ያቀርቡልናል፣ ይህም የሚያሳየው በዳኝነቱ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው ነው ሲሉም ያክላሉ።

ተገልጋዮች በፍርድ ቤቶች ላይ እምነት እንዳይኖራቸው ከሚያደርጓቸው በርካታ ምክንያቶች መካከል የምልልሱ አሰልቺነት፣ የአሰራር ግልጽ አለመሆን፣ በመተዋወቅ ጉዳይ ማስፈጸም፣ አድሎ፣ ሙስና፣ አጠቃላይ የፍርድ ቤት ሂደቱን ካለመገንዘብ ወዘተ … የሚመነጩ መሆናቸውን የዓለም ባንክ “Uses and Users of Justice in Africa the case of Ethi-

opia’s Federal Courts” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተገልጋዮችን አስመልክቶ ያካሄደው ጥናት ያስረዳል።

ሰዎች ስለፍርድ ቤቶች አሰራር ያላቸው ግንዛቤ አነስተኛ ሲሆን፤ እምነቱም የዛኑ ያህል የተሸረሸረ ይሆናል። በሌላ በኩል ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት ስለማያድን በዚህም ረገድ ለውጥ ለማምጣት አሰራሮችን ግልጽ ማድረግ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ማንቃት ያስፈልጋል። ተገልጋዮች አሰራሮቹን አለማወቃቸው ላልተገባ ድርጊትና ለብልሹ አሰራር ሊያጋልጣቸውም ይችላል።

አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በፍርድ ቤቶች የፍርድ ሂደት ላይ የግንዛቤ እጥረት እንዳለው ያረጋገጠ ሲሆን፤ ይህም ወደ ፍርድ ቤቶች የመሄድ ፍላጎቱን እንደሚቀንስ የዓለም ባንክ ጥናት አረጋግጧል። አያይዞም ተገልጋዩ ግንዛቤ ከሌለው ምን ማድረግ እንዳለበትና እንደሌለበት ስለማያውቅ ለጭንቀት፣ ለስነልቦና እና መሰል ችግሮች እንደሚዳረግ ጠቅሷል።

በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ላይ የአንድ አሰሪና ሰራተኛ ክርክር በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ማለቅ እንዳለበት ተደንግጓል። ነገር ግን በተጨባጭ ከአንድ ቀጠሮ ሌላ ቀጠሮ ለመስጠት የሁለት ወር ጊዜ እየወሰደ ነው። ይህም በሕጉ ላይ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ አለመተግበሩን ያሳያል። በሌሎች ጉዳዮች ላይ በዚህ ወቅት ይጠናቀቁ የሚል መመዘኛዎች ባይቀመጡም እስከ አምስት እና ስድስት ዓመታት እልባት ያላገኙ ክርክሮች መኖራቸውን፣ ሂደቱ አሰልቺ እና ውጣውረድ የበዛበትም እንደሆነ የሕግ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ለዚህም አንድ ማሳያ የሚሆን ጉዳይ እንመልከት።

በግል ድርጅትና በግለሰብ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት አምርቷል። ከሳሽ እና ተከሳሾች ላቀረቡት ጉዳይ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተሰጥቶበታል። አንደኛው ወገን ያቀረበው አቤቱታ በዝምታ በመታለፉ ተቀባይነት እንዳላገኘ ያሳየናል በሚል፣ አቤቱታውን ለመመልከት ስልጣን ወደተሰጠው ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማቅረብ ተገደዋል። አቤቱታው በፍርድ ቤቱ መታየት እንደሚችልም አዎንታዊ ምላሽ ያገኛል። ጉዳዩ መታየት ጀምሮ በርካታ ምልልሶች ከተደረጉ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ ያላገኘ ጉዳይ በመሆኑ እዚህ መቅረብ የለበትም በሚል ለአቤቱታ አቅራቢዎች ውሳኔ ሳይሰጣቸው ፋይላቸው ተዘግቷል።

የዚህ የፍርድ ሂደት (በተለያዩ ደረጃዎች ሲታይ) አራት ዓመታትን እንደፈጀ፣ ያቀረብነውም አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ መታየት ከጀመረ በኋላ የመጨረሻ ውሳኔ አላገኘም ተብሎ መመለሱ ለእኛ በዳኞች መካከል የአቅም ክፍተት መኖሩን፣ እርስ በርሳቸውም እንደማይናበቡ ያስረዳናል፤ ይህም በተገልጋዮች ዘንድ የሚፈጥረው ተጽዕኖ ከፍተኛ ነው፣ በፍርድ ሂደቱ ላይ እምነት ማጣትን፣ አለፍ ሲልም ተስፋ መቁረጥ እያስከተለ መሆኑን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የባለጉዳዮች

ጠበቃ ይገልጻሉ።

የአራት ዓመታት ምልልስ አሰልቺ መሆን፣ ደንበኞች በስራ ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ የሚሻማ በመሆኑ በግል ገቢ እና በሀገር ዕድገት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው እርግጥ ነው። ወደ ፍርድ ቤቶች የሚደረገው ምልልስ ስነልቦናዊ ጫና እንደሚያሳድርም አይታበልም። ውሳኔውም በፍርድ ቤቶች ላለው የአሰራር ክፍተት ማሳያ ሲሆን ተገልጋዮችም አቤቱታቸውን በታችኛው ፍርድ ቤት እንደገና መልሶ የማቅረብ መብታቸውን ያሳጣ መሆኑን ነው እኚሁ የባለጉዳዮች ጠበቃ የሚያስረዱት።

እንደዚህ ዓይነት በአቅም ማነስ እና በአሰራር ክፍተት ምክንያት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ባለሙያዎችም፣ ተገልጋዮችም በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዳይኖራቸውና ተስፋ እንዲቆርጡም መንስኤ እንደሆኑ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ።

ለውጥ የምናመጣው በወንጀልና በፍትሕ አስተዳደር ላይ ባለው ሂደት ማለትም ክስ ከተመሰረተበት ጀምሮ እስከሚወሰንበት ያለውን አሳማኝ ስናደርግ ነው። ይህንን በሕግ አምላክ የሚባልበትን ዘመን የምንመልሰው ለሕግ፣ ለፍትሕ ጥብቅና የሚቆሙ የሕግ ባለሙያዎችን ወደ ዳኝነት ስራ እንዲገቡ ማድረግ ስንችል ነው። አድገዋል በልጽገዋል የሚባሉ የዓለማችን ሀገሮችም እዚህ ደረጃ የደረሱት በዚህ መንገድ እንደሆነ የመስኩ ባለሙያዎች በአጽንኦት የሚሰጡት አስተያየት ነው።

ተደጋጋሚና የተራዘሙ ቀጠሮዎችን መስጠት ላይ፣ ግልጽ ችሎት ማስቻል ላይ፣ ዳኞች ለደንበኞች የሚገባቸውን ክብርና ትህትና ሰጥቶ ማስተናገድ ላይ ችግሮች መኖራቸውን እያስተዋልን ነው፤ ይህንንም ለማስተካከል ከዳኞች ጋር እየተነጋገርን ነው የሚል ምላሽ የሰጡት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ናቸው። መፍትሄውም የሚሰሩትንና የማይሰሩትን ለመለየት የሚረዳ ዝርዝር መመሪያ ለመተግበር በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ በዝግጅት ላይ ያለው የዳኞች አስተዳደር ረቂቅ መመሪያ ተግባራዊ ሲሆን በፍርድ ሂደት ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን በጊዜ ገደብ እንዲቀመጥ፣ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የማይወስኑ ከሆነ ምክንያቱን እንዲያስረዱ ያስገድዳቸዋል። መመሪያው ደንበኛው አንድን ጉዳይ ሲያቀርብ በምን ያህል ጊዜ እንደሚያልቅ እንዲያውቅ፣ ዳኞች ስራቸውን በተወሰነ ጊዜ አቅደው ማከናወን እንዲችሉ፤ በዚህም ተደጋጋሚ ቀጠሮዎችን በመቀነስ የቀጠሮ አሰጣጡን ጥብቅ ለማድረግ እንደሚያስችል ተስፋ ተጥሎበታል።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ በበኩላቸው የፍትሕ ሥርዓቱ ሁለቱን ተከራካሪ ወገኖች በእኩል የማይመለከት ከሆነ ፍትሕ አይገኝም፣ ህዝቡ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት ካላሳደረ መንግሥትንም አያምንም ይላሉ። በአንድ ሀገር የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ወሳኞቹ ፍርድ



33

ቤቶች እንደሆኑ ጠቅሰው፤ ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ማገልገል ሳይሆን የሰዎችን መብቶች ለማስከበር የሚሰሩ ተቋማት መሆን እንዳለባቸው ይገልጻሉ።

ተቋማዊ አቅም ለመፍጠር በርካታ ህጎችን የማሻሻል ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር፣ በፍርድ ቤቶች በግል ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንዳልነበራቸው እና ወደ ፊትም እንደማይኖራቸው ጠቅሰው የሀገረ መንግሥት ግንባታችን ጠንካራ እንዲሆን ከሕግ ጋር መለማመድ ያሉብንን ጉዳዮች ማየት ብንችል፣ ጠበቆችና አቃቤ ህጎችም ማሸነፍን ብቻ ሳይሆን መሸነፍንም በመለማመድ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን አሜን ብለው መቀበል እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሕግ ባለሙያዎች ጋር ባካሄዱት የውይይት መድረክ ላይ ገልጸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ሕግን ወደ ራስ አጋድሎ ለራስ በሚጠቅም ሁኔታ ብቻ መመልከት ተገቢ እንዳልሆነ በመጥቀስ ዜጎች መብታቸውን በሚጠይቁበት ልክ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ያስገነዝባሉ።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ እንዳሉት አሁን እየተሰራበት ያለው የስነምግባር ደንብ ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር ብዙ ማስተካከያ ይፈልጋል። ዳኞች ላይ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ውሳኔ ድረስ የሚታወቅ መሆን አለበት፤ ዳኞች የመከላከል መብታቸውን የጠበቀ መሆን አለበት። እየተዘጋጀ ያለው የስነምግባር መመሪያ ዓላማም ስነምግባራቸውን የጠበቁ በስራው ላይ እንዲቆዩ፣ ችግር ያለባቸው ደግሞ ከሙያው የሚወጡበትን ሁኔታ መፍጠር ነው።

የዳኝነት ነፃነት ማሳያዎች አንዱ የበጀት አመዳደብ ሂደቱ ነው። በሕገ መንግሥቱ ፍርድ ቤቶች የሚያስፈልጋቸውን በጀት አዘጋጅተው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በኩል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያቀርቡ ቢደነገግም ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤቱ የበጀት ፍላጎቱን አዘጋጅቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ አንድ እምርታ ነው።

በችግር ምክንያት ሰው ወደ አልባሌ ድርጊት እና ወደ ሙስና ሊገባ ይችላል። ለኅሊናቸው ያደሩ ዳኞች በቂ ገንዘብ የማያገኙ ከሆነ ስራ እየለቀቁ ወደ ጥብቅና እና ሌሎች ስራዎች እንዲገቡ ይገደዳሉ። ይህ ደግሞ በዳኝነት ስራው ላይ የራሱ አሉታዊ ተጽፅኖ ይኖረዋል። ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት መንግሥት በቅርቡ ለዳኞች የደሞዝ ማሻሻያ አድርጓል። የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለማቃለል ከ200 በላይ የአፓርታማ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው። ከቤቶቹ መካከል 80 ያህሉ በሐምሌ 2012 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ተመርቀዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለዳኞች ምቹ መኖሪያ ቤት መገንባቱ የዳኝነት ሥርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ

እንዲሆንና ዳኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እየተደረገ ላለው ጥረት ስኬት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

አፍሪካን ጨምሮ የዓለም ሀገሮች ፍርድ ቤቶችን ከሚገዳደሩ ፈታኝ ጉዳዮች መካከል ትልቁን ስፍራ የሚይዘው ምርጫ ነው። ምርጫ ብዙ ትኩረት ከመሳቡ ባሻገር በበርካታ አካላት ላይ አዎንታዊ አልያም አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል። የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ተከትሎ የሚፈጠሩ ውዝግቦችና ፍርድ ቤቶች ለውዝግቦቹ የሚሰጡት ውሳኔ የብዙዎችን ቀልብ ይስባል። እ.አ.አ. በ2017 በኬንያ የተካሄደውን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት በፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል። የዚህ ዓይነት ውሳኔ በአፍሪካ አህጉር የመጀመሪያው እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የደህንነት ጥናቶች ተቋም (Institutes for security studies /ISS) የማላዊ፣ የኬንያ እና የጊኒቢሳው ፍርድ ቤቶች በምርጫ ወቅት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሷል። እነዚህ ውሳኔዎች የአፍሪካ ፍርድ ቤቶች እየተጠናከሩ፣ ነፃነታቸው እየተጠበቀ እና በህዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት እና አመኔታ እያደገ ለመምጣቱ አስረጂዎች ናቸው።

በአሜሪካ ወደ መንበረ ስልጣን ለመምጣት የሚደረጉ ፉክክሮች ብቻ በቂ እንዳይደሉ ይልቁንም የጠቅላይ ፍርድ ቤት (Su- preme Court) ውሳኔ ወሳኝ መሆኑን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎችንና የፍርድ ቤቱን ውሳኔዎች በማጣቀስ የገለጹት በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ፕሮፌሰር ሪቻርድ አል ሀሰን ናቸው። በሀገራችን ለሚካሄደው ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ በፍርድ ቤቶች በኩል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ክብርት ወይዘሮ መዓዛ በሀገራችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመከሰቱና ምርጫው ከመራዘሙ በፊት ገልጸው ነበር።

የሕግ የበላይነት እና ነፃ ዳኝነት የሕግ የበላይነት እንዲኖር ወሳኙ ወገናዊ ሳይሆኑ አለመግባባቶችን በነፃነት በመፍታት ሕግን ለማስከበር ብቁ የሆኑ ፍርድ ቤቶች መኖር ነው። ባለስልጣናትም ሆኑ ዜጎች ሕጉን እንዲያከብሩ ከተፈለገ ሕጉ እንዴት መተርጎም እንዳለበት እና ከእውነታው ጋር ተገናዝቦ እንዴት በሥራ ላይ መዋል እንዳለበት ማወቅ አለባቸው። ይህም በአንድ ጉዳይ ውስጥ ያሉትን ግጭቶችን ከመፍታት አልፎ ባለስልጣናት እና ዜጎች ሕጉን እንዲረዱትና እንዲታዘዙት ያስችላቸዋል።

የዳኞችን ነፃነት ወይም ከአድልዎ ነፃ መሆንን በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈታተኑ ነገሮች አንዱ ሙስና በመሆኑ ለዳኞች በቂ ደመወዝ እና የስራ ዋስትና ማመቻቸት አስፈላጊ ነው። ዳኞች የሙያውን ሥነምግባር እና ክብር የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው። ሁሉም ወገኞች ክርክርን፡ ግጭትን በመፍታት በኩል ጥሩ የሙያ ስነምግባርና ባሕርይ ሊያሳዩ ይገባል።

ዳኞች በግል ሕይወታቸው ነፃነታቸውንና ከአድልዎ ነፃ መሆናቸውን ለሚፈታተኑ የውጭ ግፊቶች ራሳቸውን ማጋለጥ የለባቸውም። ዳኞች ሕጋዊ ቢሆኑም ነገር ግን ተጽዕኖ ውስጥ ሊከቷቸው በሚችሉ ድርጊቶች ውስጥ ከመሳተፍ መጠንቀቅ አለባቸው። ዳኞች ልምድን፣ ጥበብን ከእውቀት ጋር አጣምረው አገልግሎት ሲሰጡ ፍትሕን ማረጋገጥ ይችላሉ።

ፓለቲከኞች በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይን በተመለከተ የሚፈልጉትን ውጤት የሚያንጸባርቅ አስተያየት መስጠት የለባቸውም። ፓለቲከኞች አንዳንድ የፍርድ ውጤቶች በትክክል አልተወሰኑም ከማለት ወይም ስለዝርዝር ጉዳዮች ከመተቸት መቆጠብ አለባቸው። የራውል ዋለንበርግ የሰብዓዊ መብትና የጦርነት ሰብዓዊነት ሕግ ኢንስቲትዩት እና የሄይግ የሕግ ዓለም አቀፋዊነት ኢንስቲትዩት የሕግ የበላይነት አስመልክቶ ለፖለቲከኞች የተዘጋጀው መመርያ ፖለቲከኞች ስለዳኞች አቀጣጠር ሂደትና መስፈርቶች በሚናገሩበት ጊዜ መጠንቀቅ እንዳለባቸው ይመክራል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕ ሥርዓቱ በትክክለኛ መንገድ እየሰራ መሆኑን ለማረጋገጥ የሕግ አስፈፃሚውንና ፍርድ ቤቶችን መከታተል አለበት። ምክር ቤቱ ፍርዶች በትክክለኛው ጊዜ ሊሰጡ የማይችሉበት አሰራር በፍትሕ ሥርዓቱ መዘርጋቱን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።

ፍርድ ቤቶች ለማንኛውም ዜጋ ክፍት መሆን አለባቸው። በሕግ የበላይነት በሚመራ ህብረተሰብ ውስጥ የፍትሕ ተደራሽነት ወሳኝ ነው። ‘የዘገየ ፍትሕ እንደተነፈገ ይቆጠራል’ የሚለው የሀገራችን ብሂል የፍርድ ቤት ክርክሮች ረጅም ጊዜ ሳይወስዱ ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ ውሳኔ ሊያገኙ እንደሚገባ የሚገልጽ ነው።

ተከራካሪ ወገኖች ከፈለጉ በውክልና መከራከር፣ ክርክራቸውን ለማቅረብ በቂ የዝግጅት ጊዜ ማግኘት፣ ሌላው ወገን ላቀረበው ክርክር መልስ መስጠት፣ ጉዳያቸው በበላይ የሕግ አካል በይግባኝ እንዲታይ መደረግ አለበት። ዳኞች ከፍትሕ ፈላጊው ህብረተሰብ ጋር በቀጥታ በየቀኑ የሚገናኙ መሆኑም ስራቸውን ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለማከናወን በሕግና በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ወይም ፍርድ ሊሰጡ ይገባል። ሙያን ማክበር እውነት ላልተገባ ጥቅም አሳልፎ አለመስጠት፣ በዘመድ አዝማድ አለመወሰን ለእውነት ጥብቅና መቆም ሲቻል ኅሊና ትረካለች።

ከምንም በላይ ሙስናን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል የፍትሕ ተቋማትን ማጠናከር፣ አሰራሮችን ግልጽ ማድረግ እንደመፍትሔ የሚወሰድ ቢሆንም ዋናው ግን የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት መሆኑን ሁሉም ሊያጤነው የሚገባ አብይ ጉዳይ ነው።



34

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

በሕግ ከመግዛት ወደ

በሕግ መተዳደር



35

በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገታችን እንዲፋጠንና በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ አንድ ፓለቲካል ኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲገነባ የሕግ የበላይነት ወሳኝ እንደሆነ በኢፌዴሪ ሕገ- መንግሥት መግቢያ ላይ ሰፍሯል፡፡ ከዚህ ቁልፍ የሕገ መንግሥት ምሰሶ የምንረዳው ነገር ቢኖር የሕግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት ሀገር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና መልካም አስተዳደር ይኖራል ብሎ ማሰብ አዳጋች መሆኑን ነው። የሕግ የበላይነት ሰላምና ዘለቄታ ያለው ልማት ለማረጋገጥም ዋስትና ነው። የዚህ ፅሁፍ ዋና ዓላማም ከመንግሥት ቀዳሚ ኃላፊነትና ግዴታዎች አንዱ እና ዋነኛ የሆነው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መቃኘት ነው።

ሕግ እና የሕግ የበላይነት ሕግ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር የመንግሥትና የዜጎች ግንኙነት የሚመሰረትበት ማህበራዊ ውል ሲሆን ዜጎች በአጠቃላይ ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መብታቸውን ለማስከበር ከመንግስት ጋር የሚፈጽሙት ውል ነው፡፡ በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅ እና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ የሕግ የበላይነት በቀላል መንገድ ሲገለፅ ‘’ከተራ ዜጋ ጀምሮ ሀገሪቱን እስከሚመሯት ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ፕሬዚዳንት ድረስ ያሉ ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ሲሆኑና ተጠያቂነታቸውም በዚያው ልክ ሲረጋገጥ የሕግ የበላይነት ሰፈነ ይባላል’’ ይላሉ። ሰዎች መብታቸውን የሚያገኙትም ሆነ የሚያጡት በሕግ ሲሆንና ያለ ልዩነት ሁሉንም የሚገዛው ሕግ የበላይ ሆኖ ሰዎች ደግሞ ከሕግ በታችና ለሕግ ተገዥ ሲሆኑ የሕግ የበላይነት ተረጋገጠ ይባላል፡፡

የሕግ የበላይነት በተለያየ መልኩ የሚገለፅ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰጠው ትርጓሜ ግን ብዙዎችን ያስማማል። የሕግ የበላይነት የአስተዳደር መርህ ሲሆን ሁሉም ሰው እንዲሁም የመንግሥትና የግል ተቋማት በግልፅ በፀደቀ፣ ያለአድሎ በእኩል

በመንገሻ ገ/ሚካኤል



36

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

በሚፈፀም፣ በገለልተኛ ፍርድ ቤት በሚተረጎም እና ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች የቃል ኪዳን ሰነዶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በሕግ ተጠያቂ መሆንን የሚያመለክት ነው። ይህም ሲባል ተጠያቂነትን፣ ፍትህን፣ ርትዕን፣ ተገማችነትን፣ የስልጣን ክፍፍልን፣ ውሳኔ ሰጪነትና ተሳታፊነትን፣ ዘፈቀዳዊ አሰራርን ማስወገድን እና የሕግና የሥነ ስርዓት ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ሂደትና ጥረት የሚጨምር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለህግ የበላይነት ከሰጠው ትርጓሜ መረዳት ይቻላል፡፡

የሕግ የበላይነት ብዙዎችን ያስማሙና እንደ ዓለም አቀፍ ዕሴቶች የሚወሰዱ አራት አላባውያን አሉት፡፡ አንደኛው ተጠያቂነትን የተመለከተ ሲሆን በመንግሥትም ይሁን በግል ችሎታ በማናቸውም ጉዳይ ላይ ተዋናይ የሆኑ ሰዎች ላይ በሕግ ተጠያቂነት መኖርን ይመለከታል፡፡ ሁለተኛው ፍትሐዊ ሕጎችን የሚመለከት ነው፡፡ ይህም ሕጎች ግልጽ፣ ለሕዝብ ይፋ የሆኑ፣ በፍጥነት የማይለዋወጡ፣ ትክክለኛና ፍትሐዊ፣ በሁሉም ላይ በወጥነት ሥራ ላይ የሚውሉ፣ መሠረታዊ መብቶችን የሚያስከብሩ መሆናቸው የሚለካበት ነው፡፡ ግልጽ መንግሥት መኖር ሶስተኛው የሕግ የበላይነት አለባውያን ነው። ሕጎች የሚወጡበት፣ የሚተዳደሩበትና ተግባራዊ የሚደረጉበት ሁኔታ ተደራሽ፣ ፍትሐዊና ውጤታማነት መሆኑን ይመለከታል። ተደራሽ፣ ገለልተኛ እና አለመግባባትን የሚፈታበት ዘዴ መኖር አራተኛው የሕግ የበላይነት አለባውያን መገለጫ ነው። ፍትሕን የሚሰጡ አካላት ብቃትና በጎ ሥነ-ምግባር ያላቸው፣ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ፣ የማህበረሰቡ ማህበራዊ ስሪት ነጸብራቅ የሆኑ እንዲሁም ተደራሽና በበቂ ቁሳቁስና ሀብት የተደራጁ መሆናቸውን ለመለካት የተመረጠ መሥፈርት ነው፡፡

መንግሥት ሕግና ስርዓትን ለማስፈን ሕግ ያወጣል፤ ያወጣውንም ሕግ በፍርድ ኃይል እንዲሁም እንደ ሕግ አስፈጻሚነቱ ኃይልን በብቸኝነት የመጠቀም ስልጣኑን ተጠቅሞ ያስከብራል። ይህ ሂደት በተለምዶ የሕግ የበላይነት ማስከበር በመባል የሚታወቀው ነው። መንግሥት የሕግ የበላይነት የሚያስከብርበት አግባብ እንደ መንግሥት ባህርይ እና እንደሚከተለው የፖለቲካ ሁኔታ ይለያያል። መንግሥት የሕግ የበላይነትን የሚያስከብርበት አግባብ እና ስርዓት በሕግ ከመግዛት እና በሕግ መተዳደር የፖለቲካ ሁኔታ አንጻር ይቃኛል፡፡ በሀገራችንም ብዙዎች የሚስማሙበት ከለውጡ ትሩፋቶች መካከል የሀገሪቱ መንግሥት በሕግ ከመግዛት ወደ በሕግ መተዳደር ተሸጋግሯል የሚል ነው፡፡ ለመሆኑ በሕግ መግዛት እና በሕግ መተዳደር ያላቸው ልዩነት ምንድነው? የሚለውን ሃሳብ ለመገንዘብ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚዘጋጀው የአዲስ ወግ መድረክ ላይ ለሁለቱም ሀሳቦች የተሰጠውን ትርጉም መመልከት አስፈላጊ ነው፡

በሕግ መግዛት እና በሕግ መተዳደር

የሕግ የበላይነትን ከማስከበር አኳያ የመንግሥት አንደኛው ኃላፊነት ለሕጎች ራሱን ተገዥ ማድረግ ነው። የመንግሥት ሥልጣን መገደብ ወይም መወሰን አለበት የሚለው የሕግ የበላይነት አንድ መለኪያ መስፈርትም ነው፡፡ ዋና ዓላማውም

መንግሥት በዘፈቀደ ያለገደብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ የሚፈነጭ ከሆነ የዜጎችን መብት በመጨፍለቅ ጨቋኝና አምባገነን ይሆናል ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ መንግሥት መጠቀም ያለበት የስልጣን መጠን የሃገርን እና የዜጎችን ሰላም፣ ደህንነት እና መብት አክብሮ ለማስከበር በሚያስችል መልኩ ብቻ በመሆኑ ስልጣኑ በዚህ ልክ መገደብ አለበት ከሚል አስተሳሰብ የሚመነጭ ነው፡፡

አምባገነን መንግሥት ወይም ጨቋኝ ስርዓት በነገሰበት ሀገር የሕግ እና የፍትህ ተቋማት ተፈጥሮአዊ ተግባራቸው የሆነውን ሕግና ስርዓት የማስፈን ስራቸውን በአግባቡ አያከናውኑም። ይልቁንም ዜጎችን አፍኖ እና ጨቁኖ ለመግዛትና የገዥዎችን ጥቅም እና ፍላጎት በተለይ ስልጣንን ለማስጠበቅ መሳሪያ ይሆናሉ። ይህ አይነቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ ወይም ስርዓት በሕግ መግዛት የሚባለው ነው፡፡ በሕግ የመግዛት የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ የሕግ የበላይነት ማስከበር ማለት የገዥዎችን ፍላጎትና፣ ጥቅም እና ሥልጣን ፍጹም በሆነ አኳኋን ሊረጋገጥበት የሚችል ሕግና ስርዓት ማስፈን ነው፡፡ ለዚህም ሲባል የገዥዎችን ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብሩ፤ በአንጻሩ የዜጎችን መብት፣ ነጻነት እና ጥቅም የሚደፈጥጡ ሕጎች እንዲወጡ እና እንዲተገበሩ ይደረጋል፡፡ የዳኝነት አካሉ የዜጎች መብት፣ ነጻነት እና ጥቅም የሚጥሱ ሕጎችን በሕግ የበላይነት ማስከበር ሽፋን በተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡ የሕግ አስፈጻሚው አካልም ሕግና ስርዓት በማስፈን ሽፋን የዜጎችን በህይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብት፣ የመንቀሳቀስ ነጻነት እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን በሚጥስ አኳኋን የመንግስትን በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም ስልጣን በማጉላት አፋኝ፣ ጨቋኝና ኢፍትሃዊ የሆኑ ሕጎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ያደርጋል፡፡

በሌላ በኩል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና መንግስት ባለበት ሀገር የሕግና የፍትህ ተቋማት መሰረታዊ ዓላማ እና ተግባር የዜጎችን ነጻነት፣ መብት፣ እኩልነት በሚያከብር እንዲሁም የጋራ ጥቅም፣ ማሕበራዊ ፍትህ፣ ብልጽግና እና ደህንነትን በሚያረጋገጥ መልኩ ሕግና ስርዓትን ማስፈን ነው። በሕግ የመተዳደር የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ማስከበር ማለት ገዥና ተገዥ በማይኖርበት አኳኋን መንግሥትም ሆነ ዜጎች፣ ኃይለኛውም ሆነ ደካማው በሕግ ፊት እኩል በሚታዩበት እና በሚዳኙበት አግባብ የዜጎችን ጥቅምና ፍላጎት ለማስጠበቅ የወጡ ሕጎችን የዜጎችን መሰረታዊ ነጻነቶችና መብቶች ባከበረ መንገድ በመተግበር ማህበራዊ ፍትህን፣ ብልጽግናን፣ ሰብአዊ ደህንነትን እና ሰላምን ማረጋገጥ የሚችል ሕግ እና ስርዓትን በመዘርጋትና የመንግሥትን በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም ስልጣን በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋል ጭምር ማስፈን ነው። ለዚህም ሲባል የሚወጡ ሕጎች የዜጎችን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስጠብቁ እና መሰረታዊ መብቶቻቸውን እና ነፃነታቸውን የሚያከበሩ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ የዳኝነት አካሉ ተፈጥሮአዊ ነፃነቱን በመጠበቅና በገለልተኛነት የዜጎችን መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በሚያከብር መልኩ ሕጎችን ይተረጉማል፣ ይተገብራል፡፡ የሕግ አስፈፃሚው አካልም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መሰረታዊ ነፃነቶችን በማይጥስ መልኩ የመንግሥትን በብቸኝነት ኃይል የመጠቀም ስልጣን ስራ ላይ በማዋል ጭምር፤ ሕጎች በሁሉም ዘንድ እኩል እንዲከበሩና

እንዲተገበሩ ያደርጋል፡፡

የሕግ የበላይነት እና የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ

ኢትዮጵያ በለውጥ ጎዳና መጓዝ ከጀመረች እንሆ ከሁለት ዓመታት በላይ ሆኗታል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በፖለቲካ ተሳትፏቸው የተነሳ ታስረው የነበሩ ዜጎችን ከእስር መፍታት፣ ተሰደው የነበሩ እንዲሁም በነፍጥ ትግል የጀመሩ አካላት በነፃነት ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ፣ የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች የሚገድቡ የጸረ ሽብር፣ የመገናኛ ብዙኃንና መሰል አፋኝ የሆኑ አዋጆችንና ሕጎችን ማሻሻል፣ የዳኝነት አካሉን ጨምሮ የፍትህ ተቋማት በነፃነት እና በገለልተኛነት እንዲሰሩና የህዝብ አመኔታ እና ቅቡልነትን ሊያገኙ በሚችሉበት መልኩ መሰረታዊ ለውጥና ማሻሻያ ማድረግ የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በአገሪቱ በእነዚህ ሁለት ዓመታት በርካታ አዎንታዊ ተግባራት መከናወናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በአንጻሩ የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማስከበር ረገድ ጉድለት ተስተውሏል። በሀገራችን ያለው አሁናዊ ሁኔታ ሲታይ በየጊዜው በሚቀሰቀሱ ግጭቶችና ሁከቶች በርካቶች ውድ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ለአካል ጉዳት እና እንግልትም ተዳርገዋል፡፡ በብዙ ሥፍራዎች ከፍተኛ የሆነ የሀገር ሀብት ወድሟል፡፡ በዚህም በአንዳንድ አካባቢዎች የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴዎች ተዳክመዋል። በየአካባቢው በሚነሱ ብሄር እና እምነትን መሰረት ያደረጉ በሚመስሉ ግጭቶች ምክንያት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው የመስራትና ሀብትና ንብረት የማፍራት መብታቸው እየተሸራረፈ መጥቷል፡፡ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ስርዓት አልበኝነት ተደጋግሞ ተስተውሏል። በዚህም የተነሳ በአንድ በኩል መንግሥት የሕግ የበላይነት በማስከበር ሕግና ስርዓትን ማስፈን ተስኖታል የሚል አስተያየት የሚሰነዘር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ የሽግግር ወቅት የሚጠበቅ ክስተት መሆኑን ብዙዎች ያወሳሉ፡፡

የአንድ ሀገር የፀጥታ ኃይል ትልቁ ኃላፊነት ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት መከላከል ነው፡፡ ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ወንጀለኞችን ፍርድ ቤት አቅርቦ ማስፈረድ እና ቅጣት ማስቀጣት ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ የፀጥታ ኃይል ኃላፊነት ነው። የሀገር ደህንነት እና ሰላም የሚረጋገጠው ግን በዋናነት ወንጀሎችን በማሳደድ ሳይሆን ወንጀልን ከመፈጸሙ በፊት በመከላከል ነው። የአንድን መንግሥት የጸጥታ አካል ጠንካራነት የሚለካውም የታቀዱ የወንጀል ድርጊቶችን ቀድሞ በመከላከልና በማክሸፍ ረገድ ባስመዘገበው ውጤት ነው። አሁን አሁን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እዚህም እዚያም የሚስተዋሉ ግጭቶችን በማረጋጋት ተጠምደዋል የሚሉት አቶ ብሩክ አሰፋ የተባሉ አስተያየት ሰጪ መንግሥት ወንጀልን ቀድሞ የመከላከል ሥራ መሥራት እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ እንደሚሉት በአንድ ሀገር የሕግ የበላይነትን አክብረው የሚንቀሳቀሱና ሌሎችም ሕግን



37

አክብረው ስራቸውን እንዲያከናውኑ የሚሹ ዜጎች እንዳሉ ሁሉ በአንጻሩ ደግሞ የዕለት ገቢያቸውን በወንጀል ስራዎች ላይ ያደረጉ ዜጎችም የሚኖሩበት አጋጣሚ አለ፡፡

ወንጀለኞች ችግር ከመፍጠራቸው እና የሚፈልጉትን ዓላማ ከማሳካታቸው በፊት ለመከላከል የመንግሥት እና የህዝብ መተባበር በጣም አስፈላጊ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የፀጥታ ኃይላችን ግን በርካታ ወንጀሎች ከመከሰታቸው በፊት ማምከን ችሏል ይላሉ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ። አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የወንጀል ድርጊቶችም የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን በመጠቆም። የሀገሪቱን ሰላም በአስተማማኝ መልኩ ሊያረጋግጥ የሚችል የተሟላ አደረጃጀትና በቂ አቅም ያለው የጸጥታ ሃይል መፈጠሩን የሚናገሩት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ የሀገሪቱ ሁኔታ ከጸጥታው ኃይል አቅም በላይ ሆኗል በሚል አንዳንዶች የሚያሰራጩት መረጃም ከእውነት የራቀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ መንግሥት ለትንሹም ለትልቁም ኃይል ከመጠቀም ይልቅ ህብረተሰቡን በማስተማር ወንጀልን መከላከል ላይ ያተኮሩ ስራዎችን እየሰራ ነው። ይህም የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ምህዳር ለማስፋት ትልቅ ፋይዳ አለው ይላሉ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም አሁን ላይ በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ግጭቶች ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ከአንድነት ይልቅ ልዩነቶች እንዲጎሉ በመደረጋቸው ምክንያት የተፈጠሩ ናቸው የሚል አስተያየት አላቸው፡፡ አቶ የሱፍ ከለውጡ በፊት የነበረው መንግሥት ራሱ ያወጣውን ሕግ የማያከብር እና ሕግን የስልጣን ማራዘሚያ ስልት አድርጎ የሚጠቀም እንደነበር በማስታወስ ከሁለት ዓመታት ወዲህ ደግሞ መንግሥት በተለያዩ ቡድኖች ወንጀሎች ሲፈጸሙ በዝምታ ሲያልፍ ይስተዋላል ብለዋል፡፡ በዚህም ዜጎች ወጥቶ ለመግባት እየተሳቀቁ፤ የደቦ ፍርድ በየአካባቢው እየተስተዋለ፤ ሰዎች ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ገደቦችን ተላልፈው ወንጀል ሲፈጸሙ በርካታ ጥፋቶችም ሲደርሱ ነበር። መንግሥት ከዋና ዋና ተልዕኮዎቹ መካከከል ዋነኛው ሕግን አክብሮ ማስከበር እንደሆነ መዘንጋት የለበትም ይላሉ፡፡

በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የህግ ጥናት ማርቀቅ እና ማስረፅ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ እንደሚሉት ደግሞ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ከተከናወኑ ዓበይት ጉዳዮች መካከል የሀገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ ‘’ከበሕግ መግዛት ወደ በህግ መተዳደር’’ የሚያሻገሩ እርምጃዎች በዋነኛነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ለአብነትም የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች የሚገድቡ ሕጎች መሻሻላቸውንና የዳኝነት አካሉን ጨምሮ የፍትህ ተቋማት በነፃነት እና በገለልተኛነት ኃላፊነት እና ግዴታቸውን መወጣት ይችሉ ዘንድ መሰረታዊ ለውጥና ማሻሻያ መደረጉን ያነሳሉ፡፡ ወንጀለኛን ብሄር እና ሃይማኖት ነጥሎ ማየት ላይ ክፍተት መኖሩን የሚናገሩት አቶ እንዳልካቸው ወንጀለኛ ብሔርም ሃይማኖትም የለውም ይላሉ። ምክንያቱም ማንኛውም ብሄር ሆነ ሃይማኖት ሌላውን ማጥቃትም ሆነ ወንጀል መስራትን አይቀበልም፡፡

ስለዚህ ከየትኛውም ብሄር ሆነ ሃይማኖት ተነስተው ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ያን ብሄር ወይም ሃይማኖት ይወክላሉ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ግለሰቦች ባጠፉት ጥፋት ሕዝብ እንዳለ የመውቀስና የመፈረጅ ዝንባሌ መስተካከል አለበት ይላሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች በሰሩት ወንጀል በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በብሄራቸው እና በሃይማኖታቸው ምክንያት ተጠያቂ እንደሆኑ ለማስመሰል ጥረት ማድረግም ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ሰዎች ወንጀል ሰርተው ሲያበቁ ብሄርና ሃይማኖታቸውን መሸሸጊያ ዋሻ አድርገው ለመጠቀም በር ይከፍትላቸዋልና። ነገር ግን ሰዎች በዚህ መንገድ መሸሸግ እንደማያዋጣቸው መረዳት ይኖርባቸዋል። ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ እንደሚሉት የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ወንጀል ሰርቶ ተደብቆ ሊቀር አይችልም፡፡ ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር ለማዋል የህብረተሰቡ ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ ወንጀላቸውን በብሄርና በሃይማኖታቸው ለመሸፈን የሚሹ አካላትን አሳልፎ መስጠት አለበት ይላሉ።

በማህበራዊ የትስስር ገጾች የሚሰራጩ የሃሰት እና የጥላቻ ንግግሮች አሁን አሁን በሀገሪቱ ለሚከሰቱት ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች በተለይም ብሄርን እና እምነትን መሰረት አድርገው የሚሰራጩ የጥላቻ ቅስቀሳዎች መቻቻል እና መከባበር መገለጫቸው የሆነ ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው በመሸርሸር ትልቅ ፈተና ሆናባቸዋል፡፡

ሰዎች በትክክል ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዳይለማመዱና ስርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን ማህበራዊ ሚዲያ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው የሚሉት አቶ ብሩክ በተለይም በርካታ ተከታዮች ያሏቸው አክቲቪስቶች የማህበራዊ ሚዲያውም ሆነ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን አውታሮችን በመጠቀም የሚያስተላልፉት መልዕክት በተከታዮቻቸው በኩል አመፅ እንዲቀሰቀስና የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸር በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ እየተወጡ ነው፡፡

እንደ ሀገር ማህበራዊ ሚዲያ የመጠቀም ባህላችን እና ያለን ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ ዘርፉ ከጥቅሙ ይልቅ እያስከተለ ያለው ጉዳት የላቀ መሆኑን ነው ብዙዎች የሚናገሩት፡፡ ስለሆነም ይላሉ አቶ ብሩክ በቅርቡ የወጣው ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር አዋጅ መሰረት በማድረግ አፍራሽ ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች እንዲሁም በሀገሪቱ ሰላም ላይ አደጋ የሚጥሉና ግጭት የሚቀሰቅሱ አክቲቪስቶች በሕግ አግባብ መጠየቅ አለባቸው፡፡

በጥላቻ ንግግር ህጉ መሰረት የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሚፈጸሙ ህዝብን በህዝብ ላይ የማነሳሳት፣ ሰዎችን የማጥላላት፣ የሰውን ስም የማጥፋት፣ ማህበረሰብን፣ የሃይማኖት ተከታዮችን ወይም በአንድ ብሄረሰብ ስር የሚካተቱ ማህበረሰቦች የሚያሳንስና የሚያኮስስ ድርጊትና ጽሁፍ የሚያሰራጩ አካላትን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ነው። በሌላ በኩል መንግሥት ማህበረሰብ እንዲነቃ በማድረግ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎች እራሱን

እንዲያርቅ ትክክለኛ መረጃዎችን የማድረስ ኃላፊነት አለበት፡

የሕግ የበላይነት ማስከበር እና የመንግስት ሆደ ሰፊነት

ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለይም ከውጭ ፖለቲከኞች ከገቡ በኋላ ሀገር ውስጥ ያሉ ሕጎችን አክብሮ የመንቀሳቀስ ግዴታና ኃላፊነትን ዘንግተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶች ሲሳተፉ መንግስት ችግሩን በጊዜ ከማረም ይልቅ መታገስን ወይም በመንግስት ቋንቋ ሆደ ሰፊነት የሚል አካሄድ መርጧል፡፡ ለዚህ እንደ ምክንያት የሚያቀርበው ደግሞ የአገሪቱ ህዝብ ቀደም ሲል በሀገሪቱ በነበረው የአፈና ስርዓት በእጅጉ ተማሯል፤ ስለሆነም ሁሉም የመሰለውን ሃሳብ እንዲያቀርብ በመፍቀድ የሀገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት አስፈላጊ በመሆኑ ነው። ሆኖም የታሰበው ቀርቶ ያልታሰበው ሆነ እና ሰዎች በሕግ የሚያስቀጡ የጥላቻ ንግግሮችን፣ ስድቦችን ያለሃላፊነት ተናግረው ዝም የሚባሉበት ሁኔታ ሲፈጠር በአገሪቱ ስርአት አልበኝነት እንዲስተዋል አድርጓል፡፡ የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት መጠበቅ እና አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ተገቢውን ፍርድ እንዲያገኙ ማድረግ እና ሆደ ሰፊነት የሚያገናኛቸው ነገር እንደሌለ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም በፊት ባሳለፍነው ታሪክ እንደነበረው ህግ ማስከበር ማለት የዜጎችን መብት መጣስ፣ መብቶችን መገደብ ማለት እንዳልሆነ መገንዘብ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

አገርን ለማፍረስ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ፣ ዜጎች እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉና ንብረታቸው እየወደመ የመንግስት ከልክ ያለፈ ሆደ-ሰፊነት ተገቢ እንዳልሆነ እና መንግስት ሁሉንም አጥፊዎችን ለህግ ማቅረብና የህብረተሰቡን ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ይኖርበታል የሚል ደግሞ አቶ ብሩክ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል መንግስት የፖለቲካ ምህዳርን ለማስፋት ሲባል የህግ የበላነይትን ከማስከበር ይልቅ መታገስን መምረጡ አቅም እንደሌለው ተደርጎ ተወስዷል፡፡

መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ በአንድ በኩል መንግስት ሃይል አልተጠቀመም፣ የህግ የበላይነትን አላስከበረም እንዲያውም የተልፈሰፈ ነው የሚል አስተሳሰብ አለ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ከሚገባው አቅም በላይ ሃይል እየተጠቀመ ነው የሚል አስተያየት ይሰነዘራል፡፡ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ ሁለቱም አስተሳሰቦች ምክንያታዊ እንዳልሆኑ ይናገራሉ፡፡ መንግስት መታገስን የመረጠው ዜጎች መንግስትን በመቃወምም ሆነ በመደገፍ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ለመጠቀም ዕድል ይሰጣል በሚል ነው፡፡አንድ አንድ ቦታዎች የሰዎች ህይወት እና ንብረት አደጋ ላይ ሲወድቅና መንግስት ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ ሲጀምር ከመጠን በላይ ሃይል እየተጠቀመ ነው የሚሉ አስተሳሰቦችም ብቅ ብቅ ይላሉ። ሆኖም መንግስት አሁን ባለው ግምገማ እንኳን ከመጠን በላይ ሃይል ሊጠቀም ችግሩን የሚመጥን ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅሟል ለማለት እንኳን አያስደፍርም። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ የፖሊስ የሃይል አጠቃቀም መመሪያ ተዘጋጅቶ ለሰራዊቱ ስልጠና የተሰጠበት ሁኔታ አለ፤



38

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ይህ የተደረገበት ምክንያት እንደዚህ ዓይነት ወቀሳዎች እንዳይፈጠሩ ነው፡፡ መንግስት ህግ በሚያስከብርበት ጊዜ ሃይል የመጠቀም መብት በህግ የተሰጠው ቢሆንም ከሚገባው በላይ በመጠቀም የዜጎችን መብት እንዳይጥስ መመሪያ ተዘጋጅቶ ውይይት ተደርጎበታል ብለዋል ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ፡፡

አቶ እንዳልካቸው ወቅቱ የሽግግር ጊዜ በመሆኑ የመንግስት ሆደ ሰፊነት የሚበረታታ ቢሆንም ህግ የማስከበር ጉዳይ ለድርድር መቅረብ ያለበት ጉዳይ አይደለም ይላሉ። ሰዎች መንግስት መፍጠር ያስፈለጋቸው የመጀመሪያው ምክንያት ጸጥታንና ህግን ለማስከበርና ጉልበተኞችንና ወንጀለኞችን ሥርዓት ለማስያዝ ሲሉ ነው። ስለሆነም መንግስት ይህን በህዝብ የተጣለበትን ሃላፊነት አለመወጣት ከሆደ ሰፊነት ጋር ማገናኘት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ነገር ግን እንደ ከዚህ ቀደም ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች በውይይት ከመፍታት ይልቅ በህግ ሽፋን ከመንግስት የተለየ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች እና ቡድኖች ላይ የእስርና የአፈና ድርጊት ማካሂድም ተገቢ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደቱን ለማጨናገፍ የሚፈልጉ ሃይሎች በሚያቀናብሩት ሴራ እና የብሔር ማንነትን መሰረት ባደረጉ ግጭቶች የተነሳ ዜጎች ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጡበት እንዲሁም ቤት ንብረታቸውን ትተው የተፈናቀሉበት ሁኔታዎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተከስተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ እንኳን የተወዳጁ ዘፋኝ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የበርካቶች ህይወት አልፏል፤ ንብረት ወድሟል እንዲሁም በርካቶች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ይህን ተከትሎም መንግስት የወሰዳቸው የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራዎች በአንድ በኩል መንግስት ህግ ለማስከበር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው የሚል አስተያየት እየተሰጠ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በህግ ሽፋን ተቃዋሚዎችን ለማዳከም እየተጠቀመበት ነው የሚል ትችት እየቀረበ ይገኛል።

የፖለቲካ ድርጅት አባል በመሆኑ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው የለም ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ እንደዛ ቢሆን ኑሮ በአገሪቱ ከመቶ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ እነዚህ ሁሉ ይታሰሩ ነበር ማለት ብለዋል፡፡ ማንኛወም ሰው በህግ እየተጠየቀ ያለው በተጠረጠረበት ወይም በፈጸመው ወንጀል ነው፡፡ ወንጀለኛ ነው ወንጀለኛ አይደለም የሚለው የሚረጋግጠው ደግሞ በፖሊስ እና አቃቢ ህግ ሲሆን ፍርዱ የሚሰጠው ደግሞ ፍርድ ቤት ነው፡፡ የፀጥታ ሃይሉ በተለየ መልኩ ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት መስራት ሳይሆን በህገ መንግስቱ በተቀመጠለት ተልዕኮ መሰረት የህግ የበላይነትን ማስፈን ነው፡፡ የፀጥታ ሃይሉ የተቋቋመበት ዓላማ ወይም ጥብቅናው ለአገሪቱ ህዝቦች እና ደህንነት እንዲሁም ለህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መጠበቅ ነው፡፡

የሕግ በላይነት እና የፍትህና የጸጥታ ተቋማት

ነጻ የሆኑ የፍትህና የጽጥታ ተቋማት የሕግ በላይነት መሰረታዊ ገፅታና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መኖር ቁልፍ መሳሪያ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው የህግ በላይነት ለማረጋገጥ መንግሥት በመጀመርያ እነዚህ ተቋማት ከፖለቲካ መሣሪያነት ነፃ እንዲወጡ የማድረግ ኃላፊነት አለበት የሚባለው ይላሉ አቶ

እንዳልካቸው፡፡ ከለውጡ በፊት መንግስት ከሚያስተቸው ዋነኛው ጉዳይ አንዱ የህግ አስፈጻሚ እና የፀጥታ አካላትም ህግ እና ስርዓት በማስፈን ሰበብ የመንግስትን በብቸኝነት ሀይል የመጠቀም ስልጣን በመጠቀም በተለይም መንግስትን የሚቃወሙ እና የሚተቹ ዜጎችን ህይወት፣ የአካል ደህንነት እንዲሁም የመንቀሳቀስነጻነት ላይ ጉዳት የሚያደረሱ ተግባራትን ያለምንም ተጠያቂነት የሚፈጽሙበት ሁኔታ ስለነበር ነው፡፡ በዚያን ወቅት የዜጎችን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን በተለይም ሀሳብን የመግለፅ፣ የመሰብሰብ እንዲሁም የመደራጀት መብት የሚገድቡ ህጎች ወጥተው በመተግበራቸው የዜጎች የዴሞክራሲ ተሳትፎ የቀጨጨበት እንዲሁም በአጠቃላይ የፖለቲካ ምህዳሩ በከፋ ሁኔታ የጠበባትና የሀሳብ ብዝሃነት የማይስተናገድበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡

የዳኝነት አካሉን ጨምሮ የፍትህ ተቋማት በነጻነትና በገለልተኛነት የዜጎችን ፍላጎት እና ጥቅም በሚያስከብር ሁኔታ ግዴታቸውን መወጣት ሲገባቸው መሰረተ ቢስ ክሶችን ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በማዘጋጀት እና በመዳኘት የዜጎችን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን በማፈን ረገድ ተባባሪ እንደነበሩም ይነገራል፡፡ አቶ የሱፍ እንደሚሉት ምንም እንኳን ካለፈው ስርዓት ጋር ሲነጻጸር በዚህ ሁለት ዓመታት የዳኝነት እና የጸጥታው መዋቅሩ ገለልተኝነት የተሻለ ተደርጎ የሚወሰድ ቢሆንም አሁንም የእነዚህ ተቋማት ግንባታ ላይ መስራት ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ በተለይም በፀጥታው መዋቅሩ ውስጥ ከተጣለበቸው ሃላፊነት ውጭ በተለያ የወንጀል ድርጊቶች የሚሳተፉ እንዲሁም ለወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ አባላት እንዳሉ የሚናገሩት አቶ የሱፍ መንግስት የህግ የበላይነት ማስከበር ከራሱ መዋቅር መጀመር አለበት ይላሉ።

የመንግስት የጸጥታ አካላት ጸጥታ ሲደፈርስ ማስቆም እየቻሉ በዝምታ ሲመለከቱ የመንግስትነትን ግዴታና ኃላፊነት አለመወጣት ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ማለት የጸጥታ ተቋማት ጸጥታ ሲደፈርስ ዝም ብለው ከተመለከቱ ስራን ባግባቡ ባለመስራት ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ አብዛኛው የጸጥታው መዋቅር አባላት በረደኝ ፣ ራበኝ ሳይሉ የአገሪቱን ሰላም ተገቶ በመጠበቅ ላይ ናቸው ይላሉ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ አፍራሽ ለሆኑ ሃይሎች ወግነው ሌላ ወንጀል ሲፈጽሙ የሚውሉ የጸጥታ አባላት አሉ፡፡ በወንጀል ድርጊቶች በቀጥታ የተሳተፉ እና ሃላፊነታቸው በአግባቡ ያልተወጡ የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሆነ የሚናገሩት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፈንታ ይህ ማለት ግን በግለሰቦች የሚሰሩ ወንጀሎች እንጂ ተቋምን የሚወክሉ አይደሉም ብለዋል፡፡ ማንኛውም ሰው ከህግ በታች በመሆኑ የፖሊስ ወይም የመከላከያ አባል በመሆኑ ወንጀል ሰርቶ ከተጠያቂነት የሚድን የለም ብለዋል፡፡

መንግስት በተለያ ጊዜያት በህግ አስፈጻሚው በኩልም በተለይም የፀጥታ እና የፍትህ አካላቱ የህዝብን አመኔታ እና ቅቡልነትን በሚፈጥር እና የዜጎችን መሰረታዊ መብቶች በሚያከበር አኳኋን ህግና ስርዓትን የማስከበር ግዳጃቸውና ተልዕኳቸውን በውጤታማነት ማከናወን የሚያስችል ብቃትና ዲሲፕሊን እንዲሁም ተቋማዊ አቅም እንዲኖራቸው ለማድረግ መሰረታዊ ማሻሻያ እያደረገ እንደሆነ ሲገልጽ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም የተቋማት ግንባት በአንድ ጀምበር የሚጠናቀቅ አለመሆኑንም መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ማጠቃለያ ኢትዮጵያውያን ዘመናዊ የሕግ አሠራርና ስርዓት ባልነበረበት ዘመን ሳይቀር ባልተጻፈ ሕግ እየተዳደረ የሕግ የበላይነትን አክብሮ ሲኖር የነበረ ህዝብ ነው፡፡ የሕግ የበላይነትን ማክበር እየተሸረሸሩ ከመጡት የኢትዮጵያውያን መልካም የሆኑ የጋራ እሴቶቻችን አንዱ ሲሆን ለዚህ ማሳያም በሕግ ዓምላክ የሚለው ሀረግ ያለውን ሃይል መረዳት ብቻ በቂ ነው፡፡ ከዚህ ዓረፍተ ነገር የምንረዳው ህግ በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያውያን እንደ ፈጣሪያቸው አልፋና ኦሜጋ እንደነበር ነው፡፡ አሁንም ይህን መልካም እሴት እንዲጎለብት በማድረግ ለሃገር ህልውና፤ ለግላችንም ህይወትና ኑሮ አለኝታችን ግለሰብ ወይንም ቡድን ሳይሆን ህግ ማክበር ላይ የተንጠለጠለ መሆን አለበት።

አገራችን ጠንከራ አገር ሆና ፀንታ መቆም የምትችለው ማንኛውም ሰው ከሕግ በታች ሲሆን ነው፡፡ ሕግ የሁሉም መሰረትና ዋስትና ሲሆን ነው አገር የምታድገውና የምትበለጽገው ሰላምና ዴሞክራሲ የሚኖረው። መልማት የሚቻለው ለሕግ የበላይነት የሚገዛ ሥርዓት ሲኖር ነው፡ ፡ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር የሚናፍቀው በሰላም፣ በነፃነት፣ በእኩልነትና በፍትሐዊነት የሚኖርበት ሥርዓት ነው፡ ፡ ሰላምን ማስፈን እና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ለነገ የማይባል ተግባር ነው፡፡ ሰላም በታጣበት ሰብዓዊ መብት አይከበርም፡፡ ለሰብዓዊ መብት መከበር ሰላም ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ሰላም ሳይኖር ልማት የመኖሩ ነገር የሚታሰብ አይደለም፡፡

በአገሪቱ የፍትህ ስርአት በአስተማማኝ መልኩ እንዲሰፍን፤ የጉልበተኞች የበላይነት እንዳይነግስና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከተፈለገ በተለይ ህዝብና መንግስት፤ የሀይማኖት አባቶች፤ ያገር ሽማግሌዎች፤ ወጣቱ ሁሉ በቅንጅት፣ በመናበብና በመግባባት እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰሩ ይገባል። በተለይም አሁን ያለንበት ወቅትም ይህንን የግድ ይላል። መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በአጠቃላይ ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚሰሩ አካላት ሁሉ የሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ጉዳይ የሚያገባቸውና በቀጥታ የሚመለከታቸው በመሆኑ በጋራ በመስራት የህግ የበላይነት እንዲሰፍንና የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች ሁሉ በእኩል እንዲከበሩ በጋራ ሊጥሩ ይገባል። የሕግ የበላይነት ይከበር ብሎ ማውራት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ከራሱ ጀምሮ ሕግን ማክበር መለማመድ መቻል አለበት፡፡ በአንድ ሃገር ውስጥ የህግ የበላይነት መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡

የህግ የበላይነት በጊዜ ሂደት የሚገነባ እና የጋራ ባሕል መገለጫ የሚሆን እና መንግስት እና ዜጎች ሕጎች የእሴቶቻቸው መገለጫ እና ጥቅማቸውን ለማስከበር የወጡ መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ህጎች በማክበርም ሆነ በማስከበር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡ ወጣቱም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚሰፍነው በዴሞክራሲያዊ ዓምዶች ላይ ነው እንጂ፣ በአመፅና በግርግር አለመሆኑን መገንዘብ አለበት፡፡ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ከጠባብ ፖለቲካዊና ቡድናዊ ትስስር በላይ ሕዝብና አገርን ማስቀደም አለባቸው፡፡ የግል ፍላጎትን በሃይል ለማስፈጸም ከማሰብ ይልቅ በሰጥቶ መቀበል መርህ ልዩነትን እያቻቻሉ ለሐሳብ የበላይነት ልዕልና በመገዛት የሕዝብን ልብ ማማለል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡



39

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2013 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ ይላል።

አስተዳደሩ በርካታ እድለኞችን ወደ ሚሊየነርነት የቀየረ ሲሆን ከመስከረም 01/ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር ፣ በ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ሌሎች በርካታ ዕጣዎችን የሚያሸልመው ልዩ ዕድል ሎተሪን ገበያ ላይ በማዋል በማሳደግ እድለኞችን ለመሸለም ተዘጋጅቷል።



40

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ወቅታዊ

የሙላት ጉዞ



41

እንንደርደር ! ትውልዴ ተስፋ አለው። አዎ፤ የእኔ ትውልድ በተስፋ የተሞላ ነው። ኢትዮጵያም ተስፋ አላት፤ ያውም አድማስ ተሻጋሪ። አገሬ ከፊት ለፊቷ አንጸባራቂ ድሎች ይጠብቋታል። የድል ችቦዎች ደምቀው ያበራሉ። በሚገባ ተስፋዋ የለመለመ ነው። ዓባይ በመከራ የጨለመ ፊቷን ብርሃን ያላብሳል። እርግጥ ነው ዓባይ ብርሃን ይፈነጥቃል። የሕዳሴ ግድብ - የእኔ ትውልድ ተስፋ። ይህ ተስፋ የከበበንን ጭጋግ የሚገፍ፣ ጠባሳችንን የሚሽር፣ ከህመማችንም የሚፈውስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በብዙ ችግር ውስጥ ያለፈች ዜጎቿም ከአፍ እስከ ገደፉ የሞላ የስቃይና የሰቆቃ ጽዋ ሲጎነጩ የኖሩባት አገር ናት። ከእዚያኛው አጽናፍ ግን የተስፋ ብርሃን ፈንጥቋል። ዓባይ ደማችን፤ አጥንታችን፤ ተስፋችን።

ሽሮ ሜዳ - እንጦጦ: የሰቆቃ ማሳያ የአዲስ አበባ ራስ፤ የጉለሌ ትራስ እንጦጦ መልከ ብዙ ነው። ገሚሱ አዲስ አበባን ማያ፤ መመልከቻ ነው ይሉታል። ከፊሉ እንጦጦ የሸገር እስትንፋስ ‘ኦክሲጂን’ ነው ይሉታል። ለምዕተ ዓመት አዲስ አበቤን ቁልቁል ሲመለከት የኖረው ችምችም ያለው ጫካ ግን በውስጡ መከራና ስቃይን ሲታዘብ ኖሯል። እናቶች ከዱርና ከሰው ጅብ ጋር ተናንቀው ሕይወትን ሲያስቀጥሉ ታዝቧል። በዚህ ጫካ ውስጥ ‘’ማገዶ ለቀማ’’ ይሉት ወገብ አጉባጩ፣ ተስፋ አጨላሚው የሕይወት መንገድ አለ።

መልከ ብዙውን ችምችም ያለውን የእንጦጦ ተራራ እየወጣን ነው። ዘንድሮ እግር በዝቶበታል፤ ውበትም ጨምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጠንሳሽነት የተጀመረው የእንጦጦ ፓርክ ስራው እየተገባደደ ነው። እኛም ይህንኑ ፓርክ ለመጎብኘት ነበር ወደ ስፍራው ያቀናነው። አቀበቱን እንደጀመርን በግምት ከሁለት ሜትር የሚልቅ ማገዶ የተሸከሙ እናቶች አልፍ አልፍ ብለው

በአዲሱ ረታ



42

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ይታያሉ። እኔ እንደው አቅልዬ ‘ማገዶ የተሸከሙ’ አልኩ እንጂ ነገሩ እንዲህ አይደለም። እነዚህ እናቶች የተሸከሙት ስቃይና ሰቆቃ ነው። ሲሰበስቡት በመከራ፣ ሲሸከሙት ክብደቱ፤ ሲጠቀሙት ጉዳቱ - ማገዶ።

ወደ አንድ እናት ጠጋ ብለን ማውጋት ጀመርን። ምስላቸውን በፎቶ መያዝ እንደምንፈልግ፣ ድምጻቸውንም እንደምንቀዳ ነገርናቸው። ፎቶ መነሳቱን አልፈለጉም ‘’ልጆች አሉኝ’’ ላያስደስታቸው ይችላል አሉን። ድምጻቸውን ብንቀዳ ግን ችግር እንደሌላው ነገሩን። እውነተኛ ስማቸውንም እንደማንጠቀም አረጋገጥንላቸው። እኛም ለዚህ ጽሁፍ ሲባል ወይዘሮ ክብነሽ ሰዲቃ የሚል ስም እንደምንሰጣቸውና ታሪካቸውን እንዲያጋሩን ጠይቀናቸው፤ ተስማማን።

እንጦጦ ለሽሮ ሜዳ ነዋሪዋ ለወይዘሮ ክብነሽ እንደ አብዛኛው አዲስ አበቤ የሚመለከቱት ደን አይደለም የሕይወታቸው ሁሉ ነገር እንጂ። እሳቸው ለ15 ዓመታት ገደማ ከዚህ ጫካ ውስጥ እንጭት ለቅመው የቤተሰባቸውን ሕይወት አስቀጥለዋል። የሶስት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮዋ ሸክማቸው እጅግ የከበደ ነበር። ሽቅብ ለመውረድ ይታገላሉ። በጀርባቸው ያዘሉት የማገዶ ጭነት ቁልቁል ይገፈትራቸዋል። መኪና ሲመጣ ያንኑ ሸክም ይዘው ለማሳለፍ ይታገላሉ። ክፍት መንገድ ሲያገኙ የያዙትን ምርኩዝ ዱላ ተደግፈው በፍጥነት ይጓዛሉ። ድግግሞሽ ነው ማኪና ሲመጣ ማሳለፍ፣ ክፍት መንገድ ሲገኝ በፍጥነት መጓዝ፣ ትንሽ እረፍት መውስድ። የህይወት ድግግሞሽ። ብርድና ቁር ሳይበግራቸው ከንጋቱ 11

ሰዓት የጀመሩት ትንቅንቅ ከረፋዱ 5 ሰዓት እስከ ቀትር ባለው ይጠናቀቃል።

ሕይወት ለእርሳቸው ቀላል አለመሆኑን ገጽታቸው ይመሰክራል። ቀዳዳ የበዛበት ቀሚሳቸው ጉስቁልናቸውን አጋልጦቶታል። ከላይ የለበሱት ልባሽ ጨርቅም ቢቸግር ነው። አዲስ አበባ ያሉም አይመስልም። ‘’በጣም ካባድ ነው፤ ሌላ ስራ የለም፤ እኔ ይህንን ነው የምችለው’’ አሉን ሸክማቸውን አቀበቱ ላይ አስደግፈው። እረፍት መውሰጃ መንገድ መሆኑ ነው። ‘’ይህንን እሸጣለው፤ ግማሹን ደግሞ እጠቀማለሁ፤ ከዚያ ለቤት የሚያስፈልገንን እንገዛበታለን። ልጆችም እንዲሁ ነው ያሳደግኩት’’ አሉን። ሽሮ ሜዳ በተለይ ወደ እንጦጦ ተራራ ተጠግተው ያሉ መንደሮች በተለምዶ በጨረቃ የተሰሩ ደሳሳ ጎጆዎች የሚበዙበት ሲሆን መሰረተ ልማትም የላቸውም - ማብራትን ጨምሮ። ወይዘሮዋ በነዚህ ዓመታት ውስጥ እንጦጦ ጫካ ውስጥ ይህ ነው ብለው ባይገልጹም ከባድ ነገሮች እንደገጠማቸው ተናግረዋል። እሙን ነው በየቀኑ ይህን ስራ ሲሰሩ ከባድ ነገር ይገጥማቸዋል።

ልንሰናበት በመሆኑ የሸክማቸውን ክብደት እናውቅ ዘንድ ተሸክመን እንሞክረው ብለን ጀመርን። በጣም ከባድ ነው። ሁለት ሆነን ከብዶናል። አይደለም ተሸክሞ መንቀሳቀስ፤ ከመሬት ማንሳት ከብዶናል። እሳቸው ግን የኖሩበት ስለሆነ በብልሃት ተሸከሙት። ምንም ሸክሙ ቢከብድም የሕይወት መንገዳቸው ነውና በእኛ ሁኔታ ፈገግ ብለው ቁልቁለቱን ተያያዙት። እንግዲህ የኤሌክትሪክ ኃይል አስፈላጊነት እዚሁ

ቀዳዳ የበዛበት

ቀሚሳቸው ጉስቁልናቸውን

አጋልጦቶታል። ከላይ

የለበሱት ልባሽ ጨርቅም

ቢቸግር ነው። አዲስ አበባ

ያሉም አይመስልም። ‘’በጣም

ካባድ ነው፤ ሌላ ስራ የለም፤

እኔ ይህንን ነው የምችለው’’ አሉን ሸክማቸውን አቀበቱ

ላይ አስደግፈው። እረፍት

መውሰጃ መንገድ

መሆኑ ነው። ‘’ይህንን

እሸጣለው፤ ግማሹን

ደግሞ እጠቀማለሁ፤ ከዚያ

ለቤት የሚያስፈልገንን

እንገዛበታለን። ልጆችም

እንዲሁ ነው ያሳደግኩት’’ አሉን።



43

አዲስ አበባ ራስጌ ምን ያህል እንደሆነ መገመት ነው። ልክ እንደ ወይዘሮ ክብነሽ ሁሉ አያሌ የኢትዮጵያ እናቶች ጀርባቸውን ማገዶ አጉብጦ ጤናቸውን እያጎደለ ዘመናትን አልፈዋል። የተሻለ ኑሮ መምራት ብርቅም ሩቅም ሆኖባቸዋል። ለዚህ ነው ዓባይ ደማችን፤ አጥንታችን የሚሆነው። ዓባይ የሸክማችን ማቅለያ፤ የጎበጠውን ማቅኛ ወንዝ።

ኢትዮጵያን የተመለከቱ የቅርብ ዓመታት አሀዛዊ መረጃዎች የሚያሳዩት አዳጊ ምጣኔ ሃብት ያላት አገር መሆኗን ነው። በተለይ የመሰረተ ልማት ዝርጋታው በተሻለ መልኩ ማደጉን የዓለም የገንዘብ ተቋም በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ባወጣው ሪፖርት መስክሯል። ይህም ሆኖ የአህጉሪቷ ሁለተኛ የብዙ ህዝብ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ዛሬም ፈተናዎች የተጋረጡባት አገር ናት። አጠቃላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ 60 ሚሊዮን ያህሉ ዘመናዊ ኃይል አይጠቀምም። ልብ በሉ እንግዲህ የ110 ሚሊዮን ሕዝብ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ምን አይነት ችግር ውስጥ እንዳለች። ከ70 በመቶ በላይ ህዝቧ የገጠር ነዋሪ ነው። የዕለት እንጀራውንና መተዳደሪያን ከግብርና ነው የሚያገኘው። ኤሌክትሪክ ደግሞ ብርቅና ቅንጦት ነው፤ እንኳን ለገጠሩ ለከተሜውም።

ኢትዮጵያ በቂ ኃይል ባለማምረቷ ምን አጣች? ጥቂት መዳሰስ ይኖርብናል። የአንድ አገር ምጣኔ ኃብት አንቀሳቃሽ ሞተር ኤሌክትሪክ ኃይል ወይም በጥቀሉ በቂ ኃይል መኖር ነው። በዚህ ረድፍ ከትንንሽ ንግድ አንቀሳቃሹ እስከ ቱጃሩ እየተፈተነ መሆኑ እሙን ነው። ትንሽ መንደር ውስጥ ተበድሮ/ራ፤ ቤት

ተከራይቶ/ታ ጸጉር ቤት የከፈተ/ች አንድ/አንዲት ወጣት የኃይል አቅርቦት ማነስ ኑሮውን/ዋን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎታል። በሳምንት ሁለት ወይ ሶስት ቀን መብራት የለም። ይህ ደግሞ ሰርቶ መለወጥንና የራስን ላብ መብላትን አዳጋች አድርጎታል።

በተመሳሳይ ከፍተኛ ንዋይ መድቦ ለሌሎች ስራ ፈጥሮ፤ የአገሪቷን የወጪ ንግድ ለማገዝ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ትልቅ ፋብሪካ የከፈተ ባለሃብትም የኃይል ችግር ተሰቃይ ነው። በተቋረጠ ወይም በተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ምክንያት ወይ ከአቅም በታች ያመርታል ባስ ሲልም በውጪ ምንዛሪ የተገዙ ማሽነሪዎች ይነዱበታል። ይህ ሲሆን ባለኃብቱ እንዴት ሻል ያለ ደመወዝ ይክፈል፤ እንዴት ግብርና ታክስ ይክፈል። የኃይል እጥረት ሕልም አጨላሚነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ይህ እንግዲህ የዛሬይቷ ኢትዮጵያ እውነታ ነው በጥቂቱ ሲገለጽ።

የአገሪቷ እውነታ እንደነ ወይዘሮ ክብነሽ ያሉ ከነጭራሹ ኃይል ከማያገኙ እስከ ከተሜው እየፈተነ ነው። ዘመናዊ ኃይል አቅርቦት የሕዝብ ጤናም ጭምር ነው። በኤሌክትሪክ እጦት ምክንያት በርካቶች ጤናቸው ይቃወሳል። የጤና ፖሊሲና የምርምር ስርዓት ጥምረት ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር ተባብሮ የዛሬ ሶስት ዓመት አንድ ጥናት ይፋ አድርጎ ነበር። ጥናቱ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያንን በመግደል አንደኛ የሆነው በሽታ የመተንፈሻ አካላት መጎዳት ነው። በገደምዳሜም ቢሆን ማገዶ ተጠቃሚ እናቶች ለዚህ በሽታ ሰለባ መሆናቸው



44

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

አይቀሬ ነው ይላል ጥናቱ። የመተንፈሻ አካላት መጎዳት ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች ምክንያት መሆኑ ሲታሰብ ደግሞ ችግሩን ያጎላዋል ብሏል ጥናቱ።

የፓወር አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ ሌላው ቢቀር አገሪቷ የጤና ተቋማትን የኃይል ተደራሽ ማድረግ አለባት ይላል። የድርጅቱ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ወደ 200 የሚጠጉ የጤና ተቋማት ይገኛሉ። ራቅ ያሉትን ለጊዜው ብንተወው እንኳን እነዚህ ከዋና ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ተቋማት አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት የላቸውም። ይህም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ተቋማቱ በኮምፒውተር የታገዘ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት እንዳይሰጡ ከማድረግ ባለፈ በቀዶ ህክምና ወቅት ደግሞ የኃይል ችግር ምን ያህል እንደሚፈትናቸው መገመቱ ቀላል ነው። ስለዚህ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ለኢትዮጵያ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው። ዓባይ የሕልውናችን ምሶሶ ነው።

ታዲያ የአፍሪካ የውኃ ማማ ተብላ የምትሞካሸው ኢትዮጵያ ለምን እንዲህ ሆነች። እውን የውኃ ማማ ናት? የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያን ኃይል የማመንጨት አቅምን እንዲህ ያብራራሉ። የኢትዮጵያ የኃይድሮ ፓወር አለኝታ ወደ 160 ሺህ 170 ጊጋ ዋት አወር በዓመት ነው በማለት ይጀምራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ወደ 299 ሊለሙ የሚችሉ ቦታዎች አሉ። እስካሁን ደግሞ ወደ 10 በመቶ ብቻ ነው ማልማት የተቻለው። በጥቅሉ አሁን ኢትዮጵያ ማምረት የቻለችው ኃይል 4 ሺህ 400 ሜጋ ዋት ነው። ይህ አሃዝ እስከ 2035 ድረስ ወደ 37 ሺህ ሜጋ ዋት እንዲያድግ ይሰራልም ይላሉ ሚኒስትሩ።

እስኪ የዓባይን አቅም ለብቻው እንመልከት። ያው ስለ ውኃ ኃይል አይደል የምናወራው። ኢንጂነር ስለሺ ዓባይ ከጣና ተነስቶ እስከ ድምበር ድረስ ዋና ዋና የኃይድሮ ኃይል ጣቢያዎች አሉት ብለዋል። መንደያ፣ መቢል፣ ከራ ዶቢ፣ ቢሺሎና ሌሎች ገባሮች ላይ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎች መኖራቸውንም ነው የጠቆሙት። ስራዎቹ ከኤሌክትሪክ ኃይል በተጨማሪ በመስኖ በኩል ሊሰሩ የሚችሉ መሆናቸውንም አመላክተዋል። የጣና በለስ ተፋሰሶች እንዲሁም የፊንጫ ኃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ቀድሞ መሰራቱን አስታውሰዋል። ወደ ፊት ወንዙን ማልማት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በዓባይ ወንዝ ሸለቆና በገባሮች ላይ መስራት የሚያስችል አቅም እንዳለ አረጋግጠዋል። ዓባይን ብቻ መውሰድ ቢቻል እንኳን እውነትም ኢትዮጵያ የውኃ ሃብታም ናት የሚያስብል በረከት አለው። ምንም እንኳን የውኃ ማማ የሆነችው አገራችን በረከቶቿን በተለያየ ምክንያት መጠቀም ሳትችል ዘመናት ቢነጉዱም።

ዓባይ ማነው? በጨረፍታ የዓባይ ወንዝ ምንጭ ከሰከላ ወረዳ ግሽ ከሚባል ተራራ ስር ረግረጋማ ከሆነ ቦታ በምንጭ መልክ በመፈንዳት እንደሚጀምር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። የዓባይ ወንዝ ከመነሻው በምንጭ መልክ እየተንቆረቆረ ወደ ምስራቅ በመፍሰስ ዳሞቴ የሚባል ወንዝን በመጨመር የግሽ ዓባይ ከተማን በመዞር ግራ እና ቀኝ ሸለቆዎችን በመፍጠር

ከምስራቅ ወደ ሰሜን ምዕራብ በመዞር ከተማዋን አቋርጦ ከወጣ በኋላ ሌሎች ገባር ወንዞችንም በመጨመር ጣና ሃይቅ ይቀላቀላል። መረጃዎች እንደሚያመላክቱት የዓባይ ወንዝ ገነትን ያጠጡ ከነበሩ አራት ወንዞች ውስጥ አንዱ ግዮን እንደሆነ ይህም የዓባይ ወንዝ ቀደምት መጠሪያው መሆኑን ይጠቅሳሉ።

ይህንኑ ገናና ወንዝ በተመለከተ የተለያዩ ድርሳናት በተለያየ መልኩ ገልጸውታል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንዙን በአመዛኙ ዓባይ ብሎ ይጠራዋል። ዓባይ ማለት ደግሞ ታላቅ ማለት ነው የሚሉ አሉ። ዓባይ ከወንዞች ሁሉ ታላቁ ነው እንደስሙ። አገራትን አቋርጦ ሜድትራኒያን ይቀላቀላል። ስሙ ዓባይ ብቻ ሳይሆን ግዮንም ነው ብለው የሚከራከሩም አሉ። እነዚህኞቹ ኃይማኖታዊ ድርሳናትን ይጠቅሳሉ።

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በ1929 ዓ.ም ባሳተሙት መፅሐፍ ‘’ከአፍሪካ ወንዞች ተለይተው፣ ነጭ ኒል (nile)፣ ጥቁር ኒል (nile) የሚመስሉ፤ በኦሪትም ግዮንና ኤፌሶን የሚባሉ ነጭ ዓባይና ጥቁር ዓባይ ናቸው ይባላል። እነዚህም ኹለቱ ወንድማማች ወንዞች ከየምንጮቻቸው በኃይል ተነስተው፣ ግርማቸውን ለብሰው፣ ተሰልፈው፣ በየፊታቸው ያለውን ሐይቅ እንደመርከብ ሠንጥቀው አልፈው ሠራዊታቸውን ከፊትና ከኋላ አስከትለው እንደ ኹለት ንጉሥ ካርቱም ላይ ሲገናኙ ሁለትነታቸው ይቀርና፣ አንድ ወንዝ ብቻ ይሆናሉ፤ ከካርቱም ደግሞ እስካትባራ ወርደው ከተከዜ ጋር ይገጥማሉ። ከዚያ በኋላ ግን የሌላ ወንዝ ውኃ ሳይጨምሩ ባንድነት መላ ምድረ ግብፅን ከላይ እስከታች አጠጥተው አጥግበው አርክተው፣ አልፈው ተርፈው ወደ ሰሜን ጎርፈው ሜዲትራኒ ከሚባለው ከታላቁ ባሕር ይገባሉ’’ ሲሉ አቅርበውታል።

ይህ ገናና ወንዝ የሆነው ዓባይ ለኢትዮጵያ ጉልበት እንዲሆን በተለያየ ጊዜ ቢታሰብም በኢትዮጵያ አቅመ ቢስነት በተግባር የታየ ነገር አለመኖሩን መመስከር ይቻላል። ወንዙ በቅኝ ገዢዎች አማካይነት በተለያየ ጊዜ የኢትዮጵያን እጅ የሚጠመዝዙ ስምምነቶች ተፈርመውበታል። የሆነው ሆኖ ዓባይን የመገደብ ሀሳብ መጀመሪያ የተጠነሰሰው በንጉሱ ጊዜ ነው የሚሉ አሉ። ግን ንጉሱ የተለያዩ ጫናዎች እንደሚገጥማቸው ስለሰጉ ብዙም አልሄዱበትም። በደርግ መንግሥት ወቅትም እንዲሁ ጣና በለስ አካባቢ የተወሰኑ ሙከራዎች ተደርገው ነበር። በመጨረሻም የወቅቱ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ወንዙን የመገደብ እንቅስቃሴ በተግባር ጀመረው። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግዙፉ የዓባይ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም በይፋ እንዲጀመር አድርገዋል። በዚህም አቶ መለስ ዜናዊ ትልቁን በረዶ ሰብረዋል።

ዓባይ የማንስ ነው? ከሕግ አንጻር

ዓባይ ወይም ናይል የዓለም ረዥሙ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ ሆኖ 11 ተፋሰስ አገራትን የሚያቋርጥ ነው። የወንዙ የላይኛው ተፋሰስ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳና

ኬንያ ናቸው። መሀል ላይ ይገኛሉ የሚባሉት የተፋሰስ አገራት ደቡብ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ሩዋንዳና ብሩንዲ ሲሆኑ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ደግሞ ሱዳን እና ግብጽ ናቸው። የናይል ገባር ወንዞች ነጭ ናይል፣ ሰማያዊ ናይል እና አትባራ ወንዞች ናቸው። ነጭ ዓባይ ከታንዛንያ፣ ኡጋንዳና ኬንያ ድንበሮች አካባቢ ከሚገኘው ከቪክቶርያ ሀይቅ ተነስቶ ወደ ናይል ወንዝ የሚቀላቀል ሆኖ 15 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርጋል ሲል ያብራራል አቶ ገብረእግዚአብሄር ወልደገብርኤል በአቢሲኒያ ብሎግ ላይ ያወጡት ጽሁፍ።

ሰማያዊ ናይል (ብሉ ናይል) ደግሞ ከጣና ሀይቅ የሚነሳና 70 በመቶ አካባቢ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን አትባራ የተባለው ወንዝ ደግሞ በተከዜና በሰቲት ወንዝ ገባርነት ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ ተነስቶ በሱዳን በኩል አድርጎ ናይልን የሚቀላቀልና 15 በመቶ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነው። ሰማያዊ ናይል (ጥቁር ዓባይና አትባራ) ከኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ተነስተው ካርቱምን አቋርጠው ግብፅ የሚገቡና 85 በመቶ የናይል የውሀ ይዘት የሚሸፍኑ ናቸው። በአጠቃላይ ሰማያዊና ነጭ ናይል በደቡባዊ የሱዳን ክፍል በሚገኘው ካርቱም አካባቢ ይገናኙና ተያይዘው ወደ ግብፅ ሲና በረሀ በመክነፍ ሜዲትራንያን ባህርን ይቀላቀላሉ ሲል ማብራሪያውን ይቀጥላል።

እንግዲህ ዓባይ መነሻውን ኢትዮጵያ ያደረገ ወንዝ ነው። የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባልደረባው አቶ ገብረእግዚያብሔር እንደሚሉት በወንዙ ላይ በርካታ ውሎች ተከናውነዋል። በናይል ላይ የተከናወኑ ውሎችና ስምምነቶች በዋነኛነት በቅኝ ገዢዎች የተከናወኑ ሲሆን ግብጽን ማዕከል ያደረጉና ሌሎች ተፋሰስ አገራትን የሚያገሉ ብሎም ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው በማለት የክርክር ሃሳባቸውን ይጀምራሉ።

የናይል ወንዝ የቅኝ ገዢዎች ቀልብና ፍላጎት መሳብ የጀመረው ከ19ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነው። በሚያስገርም ሁኔታ እንግሊዝ የናይል ወንዝን አጠቃቀምና አጠባበቅን በማስመልከት ስምንት ስምምነቶችን ተፈራርማለች። እንግሊዝ ለምን ይህን ያህል ስምምነት በናይል ወንዝ ላይ መዋዋል አስፈለጋት የሚለውን ጥያቄ ስናይ እንግሊዝ የግብፅ ቅኝ ገዥ ስለነበረች በአንድም በሌላ መንገድ የራሷን ጥቅም እያስከበረች ነበር። ሌሎች የቅኝ ገዥ አገራትም በናይል ወንዝ ዙርያ ሲያከናውኗቸው የነበሩት ስምምነቶች የራሳቸውን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማጎልበት እንደነበር ግልጽ ነው። ይሁንና የእነዚህ ስምምነቶች ትሩፋቶች የግብፅን ብሔራዊ ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩና የሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም ታሳቢ ያላደረጉ ነበሩ እንደ አቶ ገብረእግዚያብሔር።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1891 እስከ 1959 ዓ.ም ድረስ በናይል ወንዝና ገባሮቹ ላይ የተከናወኑ ስምምነቶችንም እንደሚከተለው ያቀርቧቸዋል። ኢትዮጵያን የማይመለከቱ ወደ ስምንት ስምምነቶች መፈረማቸውን የታሪክ ድርሳናትን አጣቅሰው ያቀርባሉ። እነዚህም የ1891 እና 1901 የጣልያንና የእንግሊዝ ስምምነት፣ የ1902 የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ስምምነት፣ የ1906 የቤልጂየም እና የእንግሊዝ ስምምነት፣ የ1906 የእንግሊዝ፣ የጣልያንና የፈረንሳይ ስምምነት፣ የ1925 የእንግሊዝና የጣልያን ስምምነት፣ የ1929 የእንግሊዝ እና



45

የግብፅ ስምምነት፣ የ1952 የእንግሊዝና የግብፅ ስምምነት፣ የ1959 የግብጽና የሱዳን ስምምነትን ይጠቀሳሉ።

የመጀመሪያው የግብፅን ጥቅም ላለመንካት ሲባል ጣልያን በአትባራ ወይም ተከዜ ወንዝ ላይ ግድብ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር የተዋዋለችበት ነው። በውሉ እንደሰፈረው ጣልያን የናይል ገባር ወንዝ የሆነውና ከአዲሲቷ የቅኝ ተገዥ ኤርትራ ግዛት ላይ የሚነሳው አትባራ ወንዝ ላይ የመስኖ ወይም የውኃውን ፍሰት የሚቀንስ ማንኛውም አይነት ስራ እንደማትሰራ ከእንግሊዝ ጋር ውል ማድረጓን ያሳያል።

የግንቦት 09 ቀን 1906 እ.ኤ.አ ስምምነት ደግሞ በቤልጂየም (ኮንጎን በመወከል) እና በእንግሊዝ መካከል የተከናወነ ሆኖ በዚሁ ስምምነት በአንቀፅ 3 ላይ በግልፅ እንደተመለከተው የኮንጎ መንግስት ከሰምሊኪ ወይም ከልሳንጎ ወንዝ ወደ አልበርት ሀይቅ የሚወርደውን ውሀ ከሱዳን መንግስት ጋር አስቀድሞ ሳይስማማ የውሀውን ይዘት የሚቀንስ ስራ እንዳይሰራ ወይም ውሀውን የሚቀንስ ስራ ለመስራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጥ በዚህ ውል አድርገዋል የሚል ነበር።

ሌላው በተመሳሳይ ዓመት (1906 እ.ኤ.አ) በእንግሊዝ፣ ጣልያንና ፈረንሳይ መካከል በሎንደን የተከናወነው የሶስትዮሽ ስምምነት (Tripartite Agreement) አንቀፅ 4(a) ላይ እንደተመለከተው ፍፁም ግዛታዊ አንድነት ላይ በመመስረት የኢትዮጵያ መብትን ገታ በማድረግ በአንድ በኩል፤ ጣልያን በሶማሊያና በኤርትራ ላይ ያላትን የቆየ ጥቅምን በማስጠበቅ በሌላ በኩል፤ የእንግሊዝና የግብጽን ጥቅም በናይል ወንዝ ለማረጋገጥ ሶስቱም ሀገራት የተስማሙበት ነው።

በ1919 እ.ኤ.አ እንግሊዝ በጣና ሀይቅ ላይ ግድብ እንድትሰራ የኢትዮጵያን ይሁንታ እንድታገኝ ጣልያን ድጋፏን የምትሰጥ መሆኗን የሚገልፅ የስምምነት ማዕቀፍ በእንግሊዝና በጣልያን መካከል ተከናወነ። ይህን ስምምነት ተከትሎ በ1925 እ.ኤ.አ ግብፅና ሱዳን በነጭና ሰማያዊ ናይል (ጥቁር አባይ) እንዲሁም በሌሎች የናይል ገባር ወንዞች ላይ የውሀ ስራዎችን ለመስራት ቅድሚያ መብት እንዳላቸውና ሌሎች ሀገራት የወንዙን የውሀ ይዘት የሚቀንስ ማንኛውም አይነት ስራ እንደማይሰሩ በመግለፅ ጣልያንና እንግሊዝ የማስታወሻ ልውውጥ አደረጉ።

የተፈጥሮአዊና ታሪካዊ መብቶች ቅኝት

ግብጽ የናይል ወንዝን ከአምስት ሺህ በላይ ዓመታት በቀደምትነት ስትጠቀምበት እንደቆየች የታሪክ ድርሳናት ያብራራሉ። ኑሮዋ፣ ድህነቷ፣ ጉሮሮዋ የህዝቧ ህልውና መሰረት ያደረገው በናይል ወንዝ ላይ ነው። ሄሮዶቱስ የተባለ ግሪካዊ የጥንት ፀሃፊ ‘’ግብፅ የናይል ስጦታ ነች’’ ብሎ ነበር፤ ግብፅም ይህን ትለዋለች። ይህ ማለት ግን ናይል የግብፅ “የግል ስጦታ” ነው ማለት ባለመሆኑ ናይል የአስራ አንድ ተፋሰስ ሀገራት “የጋራ ስጦታ” መሆኑን ማመን ያስፈልጋል ሲሉ ይከራከራሉ።

ለዚህም እንደምክንያት የሚያቀርቡት ድንበር ተሻጋሪ በሆኑ ወንዞች ላይ እያደጉና የዓለም አቀፍ ልማዳዊ ሕግ መገለጫ እየሆኑ የመጡትን ሁለት መሰረታዊ መርሆዎች ነው። በአንድ

በኩል ፍትሀዊና ምክንያታዊ የመጠቀም መብት በሌላ በኩል ደግሞ መሰረታዊ ጉዳት ያለማድረስ ግዴታ ናቸው። እነዚህ መርሆዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለመጓጓዣነት የማያገለግሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ለማስተዳደር ባወጣው ዓለም አቀፍ ስምምነት (1997) በአንቀጽ 5 እና 7 ላይ እንደቅደም ተከተላቸው ተደንግገዋል። ዝቅ ብለን እንደምናየው እነዚህ መርሆዎች የዓለም አቀፍ ልማዳዊ ሕግ ተብለው የሚወሰዱ ናቸው።’’

በመሆኑም ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ የተፈፀሙ ስምምነቶችና ውሎች የላይኞቹን የዓባይ ተፋሰስ አገራት ሙሉ በሙሉ ያገለሉና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ታሳቢ ያላደረጉ በመሆናቸው አልቀበላቸውም በማለት በግልጽ ስትቃወም ቆይታለች። ታንዛንያና ኬንያም እነዚህ ስምምነቶች ተቀባይነት እንደሌላቸው ከቅኝ ገዥ ሀገራት ነፃነታቸውን በተጎናፀፉበት ማግስት ጀምሮው በመሪዎቻቸው በኩል አሳውጀዋል። የታንዛንያው መሪ ጁሊየስ ኔረሬ ማንኛውም አይነት የቅኝ ገዢዎች ስምምነቶች በታንዛንያ ላይ ተፈፃሚነት እንደሌላቸው በግልጽ አውጀዋል። ”ኔረሬ ቀኖና” እየተባለም ይታወቃል። ይሁንና በስምምነቶቹ ላይ አስተያየታቸውን ሳይሰጡ እስከ አሁን ዝምታን የመረጡ የላዕላይ ተፋስስ ሀገራትም አሉ። ለምሳሌ ሩዋንዳና ኡጋንዳ። እነዚህ ሀገራት በናይል ወንዝ ላይ ጠንካራ አቋም ማራመድ ያልቻሉበት ምክንያት ከናይል ወንዝ በላይ ሌሎች ጂኦግራፊያዊና ፖለቲካዊ ብልጫ ባላቸው የተፈጥሮ ኃብት የተከበቡ ከመሆኑ በላይ ግዙፍ ፕሮጀክት ለመስራት የሚያስችል አቅምም ያላሳደጉ በመሆናቸው ነው ይላሉ አቶ ገብረእግዚያብሔር።

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ሙሉ ሕጋዊ መብት ያላት አገር ናት። ይህን ደግሞ ዓለም ዓቀፍ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ልማትና ፖሊሲዎችም የሚያረጋግጡት ነው። በኢትዮጵያ በኩል ይህን አስረግጦ መናገር ግድ ነው ይላሉ። ኢትዮጵያም መቼም ቢሆን በውኃው የመጠቀም መብቷን ከማንም ጠይቃ ማግኘት አያሻትም፤ በእጇ ያለ በመሆኑ። ‘’ከዓለም አቀፍ ሕግ አኳያ ሲታይም መሰረታዊ የሆነ መብታችን ነው። በሉዓላዊ ግዛታችን ውስጥ የሌሎች ተፋሰስ አገራት መብትና ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማያደርስ አግባብ በውኃ ሀብታችን መጠቀም እንችላለን። ስለዚህ ሃብትን የማልማት ብሔራዊ አቅምን እያዳበሩ ልማትን መቀጠል ነው የኢትዮጵያ አቋም መሆን ያለበት’’ በማለት ይመክራሉ የሕግ ምሁሩ።

ግድቡ እና እኛ መጀመሪያ እንደታሰበው ኢትዮጵያ 6 ሺህ 450 ሜጋ ዋት ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ከሚያመነጨው የህዳሴ ግድብ በፈረንጆቹ 2017 ላይ መጠቀም ከመቻልም በላይ ለኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲና ታንዛኒያ ኤሌክትርክ በመሸጥ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ትችላለች ተብሎ ነበር። በወቅቱ የነበሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ግድቡ መቶ በመቶ የኢትዮጵያዊያን የሆነ፣ በኢትዮጵያዊያን ሀብትና እውቀት ብቻ ያለ ምንም ማቋረጥ 24 ሰዓታት የሚገነባ ታላቅ የአገርና የህዝብ ቅርስ ነው ሲሉ ደጋግመው ተደምጠዋል። ይሁን እንጂ እንደተባለው አለመሆኑን ያረጋገጡ መረጃዎች ደግሞ

ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ

የተፈፀሙ ስምምነቶችና

ውሎች የላይኞቹን የዓባይ

ተፋሰስ አገራት ሙሉ በሙሉ

ያገለሉና የኢትዮጵያን ብሄራዊ

ጥቅም ታሳቢ ያላደረጉ

በመሆናቸው አልቀበላቸውም

በማለት በግልጽ ስትቃወም

ቆይታለች።



46

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ባለፉት ሁለት ዓመታት ለህዝብ ይፋ ተደርገዋል።

ግድቡ የቡድኖች እጅ የረዘመበትና ግለሰቦች በስሙ የነገዱበት የተቀራመቱት መሆኑም ተመልክቷል። በወቅቱ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው የኢፌዴሪ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እንዲሰራው ቢደረግም ስራው ላይ ከፍተኛ ክፍተት በመፈጠሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለውጦች ተደርጓል። በዚሁ ምክንያት የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ የተቀመጠው አምስት ዓመትም ካለፈ ቆይቷል። የግድቡ ግንባታ ሂደት ሲቃኝም የውቅቱ ሹማምንቶች እንደሚሉት አፈጻጸሙ አንዳንዴ እጅግ ከፍ ሲል ሌላ ጊዜ ደግሞ ሲውርድ ቆይቷል። በርከት ያሉ ባዶ ተስፋ ያነገቡ መግለጫዎች ግን አልተቋረጡም ነበር። በወቅቱ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ‘’ነገሮች በተሻለ መልኩ እየሄዱ ነው፤ በግድቡ ግንባታ ላይ ምንም የሚለወጥ ነገር የለም’’ የሚሉ መግለጫዎችን ደጋግመው ሲሰጡ ነበር። በስተኋላ ግን እሳቸው እንዳሉት ሳይሆን የግድቡ አጠቃላይ ሁኔታ መስመር ስቶ መቆየቱ ተገልጧል።

ይህ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን አቅም ብቻ የሚገነባው ግድቡ ሕዝቡንም ተስፋ እያስቆረጠ መጥቶ ነበር። ይህ ደግሞ የገቢ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕም አሳድሮ ነበር። በአንድንድ አካላት ዘንድ የግድቡ ግንባታ መቆሙ እንደ ትልቅ ዜና ሲስተገባም ነበር። ከቆይታ በኃላ ግን እውነት እራሷን እየገለጠች፤ ግድቡም ራሱን እየገለጠ ሄደ። በመጨረሻም ትልቅ ስኬት ሆነ። የፍጻሜው መጀመሪያ ተበሰረ፤ ሀይቅም መሆን ጀመረ።

ሁለቱ የለውጥ ዓመታት ጉዞና ውጤቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ባለፈው ሰኔ ወር ለሕዝብ

እንደራሴዎች ስለ ግድቡ ይህን ብለው ነበር። ‘’ግድቡ ስድስት ዓመት ነው የዘገየው። የሕዳሴ ፕሮጀክት ስምንት ኮንትራት፣ ስድስት ኮንትራክተሮች ይሰሩታል። ከነዚህ ስራዎች ውስጥ አንዱ በብቃት ማነስ ወይም በሌላ ምክንያት ቢያዘገየው የአምስቱ ኮንትራክተሮች ስራቸውን መስራት ሕዳሴን ሙሉ አያደርገውም። ስድስቱንም እኩል በእያንዳንዷ ቀን መከታተል፣ አንዱ ለአንደኛው እንቅፋት አለመሆኑን ማረጋገጥ ተሰናስሎ በፕሮጀክቱ ላይ ያለንን ትልቁን መሻት የሚያሳካ መሆኑን ማረጋገጥ ይፈልጋል’’። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት ሁለት ዓመታትም የለውጡ መንግስት ይህንኑ ተግባር በአግባቡ ሲመራ ነበር ብለዋል። ‘’እንደውም ለውጡ ለሕዳሴ ነው የመጣው’’ በማለት ነበር አሁናዊውን ሁኔታ የገለጹት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘’ሕዳሴ አፉን የከፈተ ጅብ ነው። በየወሩ ዩሮ ካላጎረሱት አይነቃነቅም። ለዚህ የሚገኝ ብድር የለም፣ እርዳታ የለም። ኢትዮጵያ ከምታገኘው አጠቃላይ ሀብት ቅድሚያ ሰጥታ ይህን ፕሮጀክት ማጉረስ ካልቻለች በገንዘብ ምክንያት ብቻ የምንፈልገውን ፕሮጀክት በፈለግነው ጊዜ ላይ ማሳካት አይቻልም’’ ሲሉ ነበር ያስረዱት። ይህም ሆኖ የለውጡ መንግስት ግምገማን ጠቅሰው ግድቡ ከተጀመረ ጀምሮ እንደዚህኛው ዓመት የዲፕሎማሲ ትግል ገጥሞት አያውቅም ብለዋል። የተፋሰሱን አገራት ወክለው ድርድሩን የሚያካሄዱት ሰዎች ምን እየተሰራ እንደሆነ ስለሚያውቁ፤ ስራው ሲሰራ ድርድሩ ይበረታል ስራው ሲቀዛቀዝ ድርድሩ ይላላል በማለት አጋጥሞ የነበረውን የዲፕሎማሲ ፈተና ተንትነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዘንድሮ በግድቡ ዙሪያ በዲፕሎማሲ፣ በገንዘብ፣ በቴክኒክና በሌሎችም ጉዳዮች ጥሩ ስራዎች ተሰርተዋል ባይ ናቸው። ‘’ከለውጡ በኋላ ሕዳሴ እንዴት ከሞት እንዳገገመ በገሃድ ማየት ይቻላል። ፕሮጀክቱ ከጥፋት ነው የዳነው። እንዲያውም ለውጡ የመጣው ለሕዳሴ ነው።’’ በማለት ለውጡ ለግድቡ ምን ያህል እንደፈየደ አቅርበዋል ለሕዝብ እንደራሴዎቹ። ለዚህ ደግሞ ምስክርነት መስጠት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ለሕዝቡ ቃል በገቡት መሰረት ግድቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ውኃ ይዟል፤ ሐይቅም ፈጥሯል።

ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሐሳብ ያጠናክራሉ። የግድቡን ወቅታዊ ሁኔታ ሲያብራሩም ግንባታው በተሻለ መልኩ ቀጥሏል ብለዋል። የግድቡ ግንባታ 645 ሜትር ላይ ሲጠናቀቅ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይይዛል። 632 ሜትር ላይ ሲሆን ደግሞ 60 ነጥብ 6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይይዛል። 625 ሜትር ላይ 49 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር እንደሚይዝም አብራርተዋል። ሂደቱ እንዲሁ ቀጥሎ ቀጣይ ዓመት አቅሙ እየጨመረ የሚሄድ ይሆናል ብለዋል። የግድቡ ውኃ የመያዝ አቅም ከ625 እስከ 645 ሜትር መካከል ይሆናል። አምስት ለግድቡ ኃይል ማመንጨት የሚያስፈልጉ የብረት ገጠማ ስራዎች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል። ድርቅ በሚሆንበት ጊዜም ቢሆን የታችኛው ተፋሰስ አገሮችን በማይጎዳ መልኩ ፍሰቱ ይሳለጣል። ይህንንም በዝርዝር ሲገልጹ ‘’ድርቅ በሚሆንበት ጊዜ ከ49 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የድርቁ ከባድነት ታይቶ በማከማቻው (ሪዜርቫዬር) ካለው እየተወሰደ ኃይል የማመንጨት ስራው ይቀጥላል። ለእኛም ለታችኛው ተፋሰስ አገራትም በዚያው ልክ እንለቅላቸዋለን ማለት ነው’’ ብለዋል።

ኢንጅነር ስለሺ ዝርዝር ነገሮችን ባብራሩበት ወቅት አሁንም ግድቡ 590 ሜትር ድረስ ከተገነባ በኋላ ውኃው በ13ቱም የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች ውስጥ ያልፋል። ከዚህ ቀጥሎ ግንባታውን 608 ሜትር ማድረስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 618 ማድረስ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ። በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ 625 ሜትር ማድረስ መሆኑን ገልጸው ይህ የሚከናወነው ከ2014 እስከ 2016 ዓ.ም እንደሆነም አብራርተዋል። በዚህ ከቀጠለ 2016 ላይ ግድቡን ሙሉ መሙላት ይቻላል ባይ ናቸው። ይህ ከሆነ በኃላ ደግሞ ከዚህ ክረምት ጀምሮ የሁለት ተርባይኖች ውኃ ማስተላለፊያ ‘’ፔንስቶከሮች’’ ስራ ማጠናቀቅ አንዱ ነው። የሁለቱ ተርባይኖችና የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ስራዎችን ማጠናቀቅ ቀጣይ ስራ ነውም ብለዋል።



47

እነዚህ ስራዎች ተሰርተው ካለቁ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራ ላይ ይደረሳል ብለዋል። በዚሁ መሰረት አሁን ባለው እቅድ የማመንጨት ሙከራ የሚደረገው ቀጣይ ዓመት መጋቢትና ሚያዚያ ወር ላይ ይሆናል እንደሚኒስትሩ ገለጻ። ኃይል ማመንጨቱን ደግሞ ሰኔ ወር አካባቢ ለማሳካት እየተሰራ ነው ያለው ሲሉም ጠቅሰዋል። በበጋው ወራት ደግሞ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል የ11 የውኃ ማስተላለፊያ ‘ፔንስቶኮች’ ስራ ማከናወን አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። ግድቡን 590 ሜትር ማድረስና የ11 ተርባይኖች ተከላ ማድረግና የሁለተኛ ዓመት ውኃ ሙሌት የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ማጠናቀቀም ከሚሰሩ ስራዎች መካከል እንደሆነ ገልጸዋል።

ከሁለት ዓመት በኋላ በ2014 ላይ ደግሞ እነዚህ 11 ተርባይኖች ኤሌክትሪክ ማመንጨት እንዲያስችሉም ስራዎች ተሰናስለው ይሰራሉ። በ2015 የግድቡን ግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ነው። በዚህ ጊዜ አስፈላጊውን የውኃ መጠን ይዞ መገኘትም ግዴታ መሆኑን ጠቁመዋል። እንደ አጋጣሚ ሆኖ ግድቡ የማይሞላ ከሆነ 2016 ላይ ግድቡን የመሙላት ስራ እንዲቀጥል ይደረጋል። በዚሁ ዓመት የኃይል ማመንጭት ስራውን መቀጠልና ከግድቡ ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ስራዎችም በአግባቡ ይቀጥላሉ ብለዋል። እንግዲህ ዓባይ ያኔ እውነትም ወደ ውስጥ ይፈሳል። ፍጻሜውም እውን ይሆናል። ያኔ የኢትዮጵያ ተስፋ ይለመልማል። እነ ወይዘሮ ክብነሽና ሌሎች ሀይል ብርቁ ኢትዮጵያውያን ፊታቸው ይበራል። ኢትዮጵያዊነታቸውን ይበልጥ ይወዳሉ፤ በራሳቸውም ይተማመናሉ። ምክንያቱም ‘’አድዋ’’ን በደማቸው የጻፉ አያቶች ያላቸው ሕዝቦች ናቸውና።

ማን ምን ሲያደርግ ቆየ ለትውስታ ያህል አንዳንዱን እንጠቃቅስ። ያኔ ወረሃ መጋቢት 2003 ዓ.ም የአገሬውን ሕዝብ ልብ ያሞቀ፣ ያነቃቃ ዜና ተሰማ። ለዘመናት ሲዜምለት፣ ሲዘፈንለት የቆየው ዓባይ ኢትዮጵያዊነቱን ሊያረጋግጥ ነው። በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡም መልካም ምላሽ አግኝቷል። ‘’ግድቡን እንሰራዋለን እኛም የምንፈልገው ይህን ነበር’’ ብለው ለመንግስታቸው ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ግድቡም ከተጀመረ ‘’እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን’’ መፈክር ሆነ። ቀጠለ ‘’እንደ አጋመስነው እንጨርሰዋለን’’ የአገሬው መፈክር ሆነ። ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከደሃው እስከ ሃብታሙ በአቅሙ ለግድቡ ድጋፉን አደረገ።

ተማሪዎች ለሻይ የሚሰጣቸውን ሳንቲም ቆጥበው ቦንድ ገዙበት። ግድቡ የወደፊት ሕይወታቸውን አድማቂና ቀያሪ ነውና። አሻራቸውን አሳረፉ። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁርሳቸውን ለግድቡ ሰጡ። ‘’አይ ከቁርሳችን የሚበልጥ የለም’’ አላሉም። ምክንያቱም ዓባይ ነውና ነገሩ። የጉልበት ሰራተኛው በወዙ በላቡ ያገኛትን ሳንቲም አልሰሰተም። በሚችለው ሁሉ ግድቡን አግዟል። የመንግስት ሰራተኛው ‘’ደመወዜ ትንሽ ነው’’ ለራሴም አይበቃኝም አላለም። በወር ደመወዙ ቦንድ ገዛ፤ ዓባይ ሕይወት ቀያሪ ነውና።

እስከዚህ ዓመት ድረስ በዚህ መልኩ ሕዝቡ 13 ቢሊዮን ብር አስተዋጽዕኦ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግድቡ ጎን ነው። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሚና ቀላል አልነበረም። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዘጠኝ ዓመታቱ ጉዞ የሁሉም ድርሻ የነበረበት በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል። የምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በገመገሙበት ወቅት አቶ ደመቀ ‘’በሁሉም ማዕዘናት የሚገኙ ዜጎች፣ ገንዘባቸውን፣ ምክራቸውን፣ ባለቤትነታቸውን እያረጋገጡ ነው የመጡት’’ በማለት አሞካሽተዋል። በግድቡ ግንባታ ሂደት ሊታወሱ የሚገቡ ወሳኝ ምዕራፎች የታለፉት ሕዝቡ ከዳር እስከ ዳር በመሳተፉ ነው ብለዋል። ለሺህ ዓመታት በከንቱ ሲፈስ የነበረው የዓባይ ወንዝ ወደ ልማት እየተቀየረ መሆኑንም ያብራራሉ። አጠቃላይ ሂደቱ ‘’ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በእውነት መንገድ መብታቸውን ለመጠቀም በጽናት የቆሙበት፣ መሰረት የጣሉበት ትልቅ የትውልድ አሻራና ሁላችንም የምንኮራበት ነው’’ ሲሉ ገልጸውታል።

ድርድር: አህጉር አቋራጩ የጽናት ጉዞ

ከግድቡ ግንባታ መጀመር በኋላ የተጀመረው የሶስቱ አገራት (የኢትዮጵያ፣ የግብጽና ሱዳን) ድርድር ዛሬም ድረስ ቀጥሏል። ይህ የድርድር ጉዞ ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ አንስቶ የነበረ ነው ማለት ነው። ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ እንደጀመረች የታችኛው ተፋሰስ አገራት የሆኑት ግብጽና ሱዳን ግንባታው እንደሚያሳስባቸው ገልጸው ነበር ወደ ድርድሩ የተገባው። ኢትዮጵያም ግድቡ ማንንም ለመጉዳት አለመሆኑን ለማስረዳት ድርድሩን መቀበሏን በወቅቱ የነበሩት የመንግስት ኃላፊዎች ደጋግመው የገለጹት ነው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባለፈው ግንቦት ወር ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ‘’የታችኞቹ ተፋሰስ አገራት እውነታውን እንዲያውቁት ነው ድርድሩ ያስፈለገው። በዚህም ግልፅነት የሚጎላቸው ነገሮች ካሉ እነሱን ለማጥራት እንዲሁም የሚያስፈልግ ጥንቃቄም ካለ ለዚህ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ነው። ኢትዮጵያ በአግባቡ አቅዳ ግድቡን እንደመጀመሯ ውይይቱን ያልሸሸችው’’ ብለዋል።

ግብጽና ሱዳን ግድቡ ከጥራቱ አንጻር በአካባቢ ላይ ተፅዕኖ ይኑረው አይኑረው የሚለውን እንዲያውቁትና የግድቡን ደህንነት በተመለከተም ግልጽነት እንዲፈጠር ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ሙያተኞች እንዲገመግሙትም ተደርጓል ይላሉ። በዚህም የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የእንግሊዝ ሙያተኞች የተሳተፉ ሲሆን ከአፍሪካ ደግሞ የደቡብ አፍሪካ፣ የግብፅ፣ የሱዳን እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እንዲገመግሙት ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደነበረችም ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ነገሮች በእንዲህ መልኩ ቀጥለው በተለያዩ ዙሮች በተለያዩ አካላት ድርድሮች ሲካሄዱ መቆየታቸውን

ያስታውሳሉ። አገራቱ የሚያካሂዱት ድርድር አንዳንድ ጊዜ ወጥነት ባለው መልኩ የሚሄድ ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ሲቋረጥም ቆይቷል። ይህ ሂደትም እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም ድረስ ሲከናወን መቆየቱንም ጠቁመዋል። በመጨረሻም ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ይፈረም ሲባል የግብጽ ተደራዳሪዎች ‘ለመመካከር ጊዜ ያስፈልገናል’ በማለት ሰነዱ ሳይፈረም ቀረ። ድርድሩ በዚሁ ምክንያት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ቀጥሎም በሱዳን የተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ተከተለ ይላሉ አቶ ገዱ።

ቀጥሎም የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በድርድሩ እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረበ። ኢትዮጵያም የሶስተኛ ወገን ጥሪው እስካሁን አገራቱ የደረሱበትን ውጤቶች የሚጎዳ መሆኑን መግለጿንም አንስተዋል። ሁኔታው በሱዳን በኩልም ተቀባይነት እንዳላገኘ ነው ያብራሩት ሚኒስትሩ። ነገሮች በእንዲህ እያሉ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2019 ዓ.ም የአሜሪካ መንግስት ድርድሩን ማገዝ እንደሚፈልግ ገለጸ። ኢትዮጵያም ግብዣውን ተቀብላ ወደዚያው አመራች። በዚህ ውስጥ የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ እያገዙ ተደራዳሪ አገራት ጠለቅ ያለ ውይይት አካሂደው ብዙ ልዩነቶችን ማጥበብ ተችሎም ነብር ብለዋል።

ሆኖም የኋላ ኋላ የአሜሪካ መንግስት ጫና በርትቶ አገራቱ ከስምምነት ያልደረሱባቸው ጉዳዮች ጭምር እያሉ ስምምነት እንዲፈራረሙ ተባለ። አቶ ገዱ እንደሚሉት መጀመሪያ አካባቢ አሜሪካ በታዛቢነት ብትሳተፍም ድርድሩ ቶሎ እንዲቋጭ ፍላጎት አሳየች ይላሉ። ቀጥሎም ኢትዮጵያ በአሜሪካው ድርድር ላይ እንደማትካፈል ገለጸች። በወቅቱ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እንዲህ ይነባበል። ‘’የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በታዛቢነት በሚገኙበት የካቲት 17 እና 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከሱዳን እና ግብጽ ጋር ሊካሄድ በታቀደው ቀጣይ የሦስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ አትገኝም። በዋሺንግተን ከተማ ለሁለት ቀናት ሊካሄድ ታስቦ በነበረው የሦስትዮሽ የድርድር መድረክ ላይ ኢትዮጵያ የማትሳተፈው፤ ተደራዳሪ ቡድኑ በአገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ውይይት ባለመጠናቀቁ በተጠቀሰው ጊዜ በአሜሪካ በመገኘት ውይይቱን ማድረግ እንዳልተቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ የትሬዠሪ ቢሮ አሳውቄያለው’’ ይላል።

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ድርድሩ ወደ አፍሪካ ሕብረት የመጣው። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ስሪል ራማፎሳ ናቸው ድርድሩን የሚመሩት። የአፍሪካ ሕብረት ጽህፈት ቤት ተወካዮችን ጨምሮ የሌሎች አገራት ሙያተኞች ድርድሩን እየታዘቡም ቆይቷል። ድርድሩ ወደ አፍሪካ መድረክ መመለሱ ለኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑንም የመሰከሩ አካላት ነበሩ። ሆኖም ይህኛው ድርድር እንዲሁ መቋጫ ሳያገኝ ወጣ ገባ እየለ ቀጥሏል። በዚህኛው ድርድር አገራቱ በመሪዎቻቸው አማካኝነትም እየተደራደሩ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከዚህ



48

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

በኋላ ያለውን የሶስቱን አገራት የድርድር አቅጣጫ ሲያብራሩ በቀጣይ መግባባት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ድርድር ይቀጥላል ይላሉ። በተለይ የወደፊት የውኃ አጠቃቀም ላይ፣ የልዩነት ወይም የጠብ መፍቻ መንገዶች ላይ፣ የሙሌትና የኦፕሬሽን እና ደንቦች ማሻሻያ ላይ ውይይት የሚቀጥል ነው የሚሆነው። በቴክኒክ ጉዳዮች ደግሞ የተራዘመ የድርቅ ዓመታት ጉዳይ፣ በየቀኑ የሚለቀቅ የውሃ መጠን ልዩነቶችና ጥቅል የኦፕሬሽን ሁኔታዎች ላይም ውይይት ይደረጋል።

በቅርቡ በተካሄዱት ድርድሮች በመሪዎች ደረጃ መግባባት የተደረሰበትን ጉዳይም አብራርተዋል። የሁሉም ደረጃ ውሃ ሙሌት ጉዳይ ላይ በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስምምነት እንዲደረስ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነትና የወደፊት የውሃ አጠቃቀምን ጨምሮ በወደፊት ድርድሮች እንዲቋጩ በመሪዎች ደረጃ መወሰኑንም አብራርተዋል። በተለይ የወደፊት የውሃ አጠቃቀም ጉዳይ በሙሉ መወሰን ያለበት በኢትዮጵያ በኩል መሆን እንዳለበት ጽኑ አቋም አለ ብለዋል።

ኢትዮጵያን ወክለው በድርድሩ ውስጥ ለዓመታት የቆዩት ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው የእስካሁኑ ድርድር ፍሬያማ መሆኑን ያብራራሉ። ዓለም ላይ ከ8 ሺህ በላይ ትላልቅ ግድቦች አሉ፤ እንደ ግድብ ከታየ የህዳሴ ግድብን ከሌላው የሚለየው ነገር የለም በማለት ይጀምራሉ። የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ግን በስምምነት የሚወሰነ ነው የሚሆነው። ይህ ደግሞ እስካሁን ዓለም ላይ ያለ ተሞክሮ ነው። ግብጽና ሱዳን ግን ላለፉት መቶ ዓመታት የዓባይን ውኃ ለብቻቸው ሲጠቀሙት ቆይቷል። ሁለቱ አገሮች ተስማምተው 55 ነጥብ 5 ቢሊዬን ሜትር ኪዩብ የወንዙን ዓመታዊ የውኃ ፍሰት ግብጽ እንድትጠቀም፣ 18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ደግሞ ሱዳን እንድትጠቀም አድርገው፤ ዘጠኙን የተፋሰሱን አገራት ዜሮ ላይ ያስቀመጡበትም ነው። ግድቡን ዓለም አቀፍ አጀንዳ ያደረገውም ይኸው የተዘባ የውኃ አጠቃቀም ስምምነት ነው ይላሉ ኢንጂነር ጌዲዮን።

ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሃዊነቱን ወደ ፍትሃዊነት ለመቀየር ለዓመታት ስትታገል ነው የቆየቸው። ይኸው ጉዳይ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ለዓለም ሲገለጽ ነው የቆየው። ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ ህጎች መሰረት ጎረቤቶቿን እንደማትጎዳና ፍትሃዊነትን ይዛ እየሰራች መሆኑን ሳትታክት ስትገልጽ ቆይታለች። ሲደረግ የነበረው ድርድርም የኢትዮጵያ መብት ሳይሸራረፍ እንዲተገበርና የትኛውም ተጽዕኖ እንዳይበግረው አስተዋጽኦ ነበረው። በዚሁ መልክ የግድቡ ግንባታም ድርድሩም ጎን ለጎን ሲራመድ ነበር። ፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነት ነው የኢትዮጵያ መርህ።

ይህ ሆኖ ሳለ ግብጾች በተለያዩ ጊዜ አወናባጅ አጀንዳዎችን እያነሳች የማወናበድ ስራ ስትሰራ ቆይታለች። አንዱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2015 ዓ.ም የተፈረመውን የመርህ ስምምነት በተሳሳተ መንገድ መጥቀስ ነው። እነርሱ ይህን ስምምነት ቢያነሱትም በሰነዱ ላይ ግን የኢትዮጵያን ፍትሃዊ አጠቃቀም አሳልፎ የሚሰጥ አንድም አንቀጽ አልተካተተበትም

እንደ ኢንጂነሩ ገለጻ። የኢትዮጵያም የመደራደር አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መብትንና ጥቅምን የማስከበር አቅም አድጎ እዚህ መድረሱን ያረጋግጣሉ። ሆኖም በሱዳን በኩል የአቋም መለዋወጦች ተደጋግመው ታይተዋል። ይህም መጥፎ ሊባል የሚችል አለመሆኑን የሚገልጹት ኢንጂነር ጌዲዮን የሱዳን ‘’ወጣ ገባ’’ ከብሔራዊ ጥቅማቸው አንጻር እንደሆነ ይታመናል ይላሉ። ምናልባት የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ተጽዕኖም ሊኖር ይችላል የሚል ግምታቸውን ይሰነዝራሉ። ይህም ሆኖ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ ነገር አይኖርም በማለት ያረጋግጣሉ።

ግብጾች ዛሬም ቢሆን ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ውኃውን ዘግታ እንደምታስቀረው አድርገው ነው ለፖለቲካ ፍጆታ እየተጠቀሙ ያሉት ይላሉ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ። ይህን የተሳሳተ መንገድ እየተከተሉ በድርድሩም ኢትዮጵያን ተጠያቂ ለማድረግ ይሞክራሉ። ግብጾቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ለዘመናት የተካኑ መሆናቸውን የሚጠቅሱት አቶ ገዱ ለዚህ የተዘጋጁ መገናኛ ብዙሃን አላቸው፣ የምርምር ተቋማት አላቸው፣ በዓለም ዙሪያ ብዙ ምሁራን አላቸው፣ የግብጽ ዲፕሎማሲም ከሞላ ጎደል የተመሰረተው በዓባይ ጉዳይ ላይ ነው። የግብጽን የበላይነት ማሳያ አድርገው የሚጠቀሙት ናይል የሚሉትን የዓባይ ወንዝ በመቆጣጠር ነው።

ኢትዮጵያ ግን የያዘቸውን ፍትሃዊ አቋም ለማስረዳት እንዳልቦዘነች ያብራራሉ። ኢትዮጵያ ግድቡን የምትሰራው ከድህነት ለመውጣት፣ በጨለማ ውስጥ ያለውን ሕዝብ ወደ ብርሃን ለማምጣት ነው። ይህንኑ እውነታ ለዓለም ሕብረተሰብ ማስረዳቷን ትቀጥላለች። የአገራትን ልምድ የሚጠቅሱት አቶ ገዱ ‘’በብዙ አገሮች የሚፈሩት የላይኞቹ ተፋሰስ አገራት ናቸው። የእኛ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ይሔ ልምዱ በዓልም ላይ የለም። ኢትዮጵያ አሁን የምትሰራውም ይህንን እውነታ የሚገለብጥ ነው።’’ የግብጽን ኢፍትሃዊ አካሄድ የማጋለጡ ስራም የሚቀጥል ይሆናል። ለዚህ ደግሞ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ የውጪ ጉዳይ መዋቅሩን በሳተፈ መልኩ የኢትዮጵያ አቋም ይንጸባረቃል። እስካሁንም በአፍሪካ ላይ በተሰራው ስራ የኢትዮጵያን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ ማስረዳት ተችሏል እንደ ሚኒስትሩ ሃሳብ። ኢንጂነር ስለሺ ደግሞ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ ከሚደረገው ድርድር ባሻገር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ማጠናከሩም መልካም ነው ብለዋል። በተለይ ደግሞ ከሱዳን ሕዝብ ጋር የነበረውን ቅርበት ተጠቅሞ የፐብሊክ ዲፕሎማሲውን ማበርታት ያስፈልጋል። ግድቡ ለሱዳን ሕዝብ ግልጽ ጥቅም እንዳለው በአግባብ የማስረዳት ስራም እንዲሁ ይጠናከራል።

የመጨረሻው ትንቅንቅ የሶስቱ አገራት ድርድር እየከረረ መምጣቱን ተከትሎ የሕዳሴ ግድብ በሕዝቡ ዘንድ የውዝግብ ምንጭም ሆኖ ነበር ማለት ይቻላል። ከውስጥም ከውጭም ያሉ የተለያዩ ቡድኖች ግድቡ አደጋ ላይ መሆኑን ጎላ ባለ ድምጽ ሲያስተጋቡ ነበር። እንደው የተወሰነውን ለማሳየት ያህል ‘’ግድቡ ተሽጧል’’ የሚል አሉባልታ ነበር። ምንጩ በግልጽ ባይታወቅም ገሚሱ

ለግብጽ ተሽጧል ይላል የቀረው ለአሜሪካ ይላል። ይህ ነገር እየጎላ የመጣው ደግሞ ተደራዳሪዎቹ ወደ ዋሺንግተን ካቀኑ በኋላ ነበር። ‘’የኢትዮጵያ ሕዝብ ከስሯል’’ የግድቡ ነገር ያለቀለት ጉዳይ ነው፤ ግንባታውም ተቋርጧል የሚሉም ነበሩ።

ይህ ነገር ትልቅ አጀንዳ ሆኖ የህዝብ እንደራሴዎች ጭምር ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋቸው ነበር። ‘’አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች አዲሱ አመራር የሕዳሴውን ግድብ ለውጪ ኃይሎች እንደመደራደሪያ አቅርቦታል፤ የአሜሪካ ድርድርም ቢሆን በቸልተኝነት የተገባበትና የሕዳሴውን ግድብ በገንዘብ ለመቀየር የተሸረበ ሴራ ነው። አሁን ከድርድር ወጣን የተባለውም የሕዝቡን አዝማሚያ ለማየት ነው ይላሉ። የመንግሥት ግልጽ አቋም ምንድነው?’’ ተብለው ተጠይቀው ነበር። እሳቸውም ሲመልሱ ‘’የግድቡ ብልሽት የጀመረው እነ ‘ሜቴክ’ ስራው ሲሰጣቸው ነው። መጀመሪያ የለውጡ አመረር ችግሩን የመለየት ስራ ነው የሰራው። ከዚያ ጠንካራ ውሳኔ ነው የወሰነው። አጠቃላይ የአመራር ለውጥ ተደረገ፤ የኮንትራት ለውጦችም ተካሄዱ። ከዚያ በኋላ በየሳምንት ሳይቆራረጥ ሪፖርት ይቀርብልኛል። በሳምንት ሁለት ጊዜ ቦርዱ ጉዳዩን ይመለከታል። የፕሮጀክቱ ማናጀር ለስራ አስፈጻሚው በየቀኑ ሪፖርት ያቀርባሉ። በቅርብ ክትትልና አመራር ነው ስራ እየተመራ ያለው።’’ በማለት ነበር ያብራሩት።

‘’እንደዚህ ዓመት ዲፕሎማሲው ፈታኝ ሆኖ አያውቅም። ምክንያቱም ስራ ስለተሰራ። ድርድር የሚያካሂዱ ሰዎች ምን እየሰራን እንዳለ በደንብ ያውቃሉ። ስንሰራ ዲፕሎማሲው ይጠብቃል፣ ስንቀልድ ደግሞ ይቀላል። በዲፕሎማሲ፣ በገንዘብ፣ በውኃ ሙሌት፣ በቴክኒክ በሌሎችም ነገሮች ሙሉ አድርገን ፕሮጀክቱን ካልመራን ሕዳሴ ግድብ ፈተና ውስጥ ይገባል። የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው ከዜሮ ነው የጀመረው። የበፊቱ እንዳለ ተነስቶ እንደ አዲስ ነው የተሰራው። የኢትዮጵያን የማደግና የመለወጥ ጉዞ የሚያስቆም ሀይል የለም’’ በማለት ይደመድማሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ። ሁሉም አልፎ ግድቡ ወኃ መያዝ ጀምሯል። ይህ እንዳይሳካ ግን ብዙ ጥረት ተደርጓል። ግብጽና ሱዳን ድርድሩ ተካሂዶ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ በፊት ኢትዮጵያ ግድቡን በውሃ የመሙላት ሥራ እንዳትጀምር መወትወታቸውን ቀጠሉ። ኢትዮጵያም በሁለት ሳምንት ውስጥ ወኃ መያዝ እንደምትጀምር ይፋ አደረገች። ጉዳዩ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ድረስም ሄዶ አጀንዳ ሆነ። ኢትዮጵያም በበኩሏ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ምንም አይነት የደኅንነት ስጋት በሱዳንና በግብጽ ላይ እንደማያስከትል እየታወቀ ለምክር ቤቱ መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን አስረዳች። የኢትዮጵያ መንግስትም ቃሉን ጠበቀ፤ አባይም ወደ አገሩ አዘነበለ።

ደብዛዛው ፌሽታ: ሙያ በልብ ልዩ ቀን ነበር። ሀምሌ 12 ጠዋት። ሁሉም ሰው ማልዶ ወደ ስራ ሲሄድ ልቡ በሐሴት ተሞልቶ ያወጋል። ግድቡ ሞልቶ



49

እየፈሰሰ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዘመናት ቁጭቱ መቋጫ አግኘቷል። ደስታ በአገሩ ላይ ሰፈነ መገናኛ ብዙሃን የደስታ መግለጫዎችን ሲያስተላልፉ ዋሉ። ብዙዎች ይህን ድል እንዲህ አይነት የደሰታ አገላለጽ አይመጥነውም አሉ። ይህ በአንድነት በአደባባይ የሚገለጽ ደስታ ነው አሉ። ግን አልሆነም ኮቪድ - 19 ጭራቁ የዓለም ስጋት አለ። ደስታ አጨላሚው በሽታ። ደብዛዛው ፌሽታ ግን ቀጥሎ ነበር። ሁሉም በየቤቱ፤ በየጓዳው ደስታውን ገለጸ። ግድቡን ለዚህ ያበቁትንም አካላት አመሰገነ። ‘’ሙያ በልብ ነው’’ አለ አገሬው።

ይህ አይበቃም ደስታችንን ባለንበት ሆነን መግለጽ አለብን የሚል ቡድን እንደገና እንቅስቃሴ ጀመረ። በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ደስታቸውን ይገልጻሉ ተባለ። ‘’ድምጻችንን ለግድባችን’’ በሚል መሪ ሀሳብ የደስታ መግለጫ ተዘጋጀ። ይህ በመጠኑ ደብዘዝ ያለ ቢመስልም ኢትዮጵያውያኖች ባሉበት ሆነው ድብልቅልቅ አድርገው ደስታቸውን ገልጸዋል። እንደውም በአንድንድ ቦታዎች ሕዝቡ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ለበሽታ ሊጋለጥ በሚችልበት መልኩ ነበር ሲደሰት የነበረው። በጥቅሉ ዘንድሮ ዓባይ ኢትዮጵያን አስደስቷል።

የፍጻሜው ትሩፋቶች እንግዲህ እዚህ ደርሰናል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እስካሁን 120 ቢሊዮን ብር ወጪ ተድርጎበታል። የግድቡ አጠቃላይ የግንባታ አፈጻጸምም 75 በመቶ ደርሷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ነሀሴ 14 ቀን 2012 ከህዳሴው ግድብ የቦርድ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ይህ የግድቡ አሁናዊ አሀዝ የተገለጸው። የአሌክትሮ ሜካኒካል ስራው 46 ነጥብ 5 በመቶ፤ የሲቪል ስራው ደግሞ 88 ነጥብ 8 በመቶ ደርሷል። ከወጪም አኳያ ለግድቡ በኮንትራት ደረጃ የተያዘው አጠቃላይ በጀት 78 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ ለግድቡ ግንባታ 120 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉንና ግድቡን ለማጠናቀቅም 160 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ የግድቡ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ገልጸዋል።

በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድቡ በመጪው ዓመት አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ሁሉ ተደርጎለት ነሀሴ 2013 ላይ 18 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በመያዝ ለህዝቡ ይበሰራል ብለዋል። ከመስከረም እስከ ነሀሴ 2013 የሚሰሩ ስራዎች ለግድቡ ግንባታ ስኬታማነት ወሳኝ መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ አግባብ መስራት ከተቻለ “በ2015 ዓ.ም የግደቡን የምረቃ ሪባን እንቆርጣለን” ብለዋል።

ግድቡ የሚፈጥረው ሃይቅ ምን ይጠቅማል የሚለውን ጥያቄ ሚኒስትሩ ሰፋ አድርገው ያብራራሉ። አንደኛው የቱሪዝም አገልግሎት ነው። የአሳ ሃብት ልማት፣ ግብርናና አነስተኛ የመስኖ ልማት፣ የውሃ ትራንስፖርት፣ የውሃ ሃብት ልማትና

የመዝናኛ ጥቅሞች እንዲሁም ለትምህርትና ለምርምር ስራዎች ትልቅ ጠቀሜታ አለው ይላሉ። ግድቡ የሚፈጥረው ኃይቅ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውም ሚኒስትሩ ይገልጻሉ። በዚህም ወደ 78 ደሴቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። የደሴቶቹ መጠንም ከአምስት ሔክታር በላይ የሚሆን ነው። ይህ ደግሞ ቱሪዝም ለማስፋት ትልቅ ዕድል ነው። የውኃ ትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዲጠነክር ተደርጎ ትልልቅ ሆቴሎች፣ ሪዞርቶች ይገነባሉ። ይህ ደግሞ ለአደን፣ ለአሳ ማጥመድና ሌሎች የሰውን ልጅ ቀልብ የሚስቡ ነገሮችን ለመስራት ያስችላል።

ጎብኚዎች ግድቡን፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጡንና ደኖችን መጎብኘት የሚችሉበት ሁኔታን ማመቻቸት እንደሚቻልም ግምታቸውን ሰንዝረዋል። በጥቅሉ ተወዳጅና የሚመረጥ የጉብኝት ቦታ መሆን ይችላል ባይ ናቸው ሚኒስትሩ። ቱሪስቶች ሱዳንን ጨምሮ ከሌሎች ጎረቤት አገራት እንዲመጡ የሚያደርግ ለአገር ውስጥ ጎብኚም መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው። ምክንያቱ ደግሞ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ትልቁ የአፍሪካ የልማት ፕሮጀክት ነው።

ሌላው ጥቅሙ ዚዮሎጂካል ጋርደንና ቦታኒካል ፓርክ መገንባት የሚያስችል መሆኑ ነው። ፏፏቴዎች፣ የውኃ ስፖርቶች ማካሄጃ፣ ወፎች መመልከቻ ስፍራዎችን ጨምሮ በግድቡ ዳርዳርም በርካታ ስራዎችን መስራት ይቻላል ይላሉ ሚኒስትሩ። ሪዘርቫይሩ ዙሪያ ዛፎችን በመትከል እንዲሁም ሳር እንዲበቅል በማድረግ እዚያው ከብት ማርቢያ ስፍራ መፍጠርም ይቻላል። ይህን ተከትሎም ስፍራውን የልማት ኮሪደር ለማድረግም ታልሟል ነው ያሉት። አነስተኛ የመስኖ ግብርና ስራዎችን በማከናወንም እስከ 10 ሺህ ሔክታር መሬት ማልማት ይቻላል። የአዞ እርባታን በማቋቋምም ለኢንዱስትሪ መስፋፋት፣ ለስራ እድል ፈጠራና ለተያያዥ የአገሪቷ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ ስፍራ ማድረግ ይቻላል።

ግድቡ ከገቢ አንጻር በርካታ ትሩፋቶች ይዞ የሚመጣ ነው። አንደኛው የውጪ ምንዛሪ ማግኛ መንገድ ነው። አንዱና ዋና መንገድ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ሲሆን ሌላኛው መንገድ ደግሞ ከጎብኚዎች የሚገኝ ገቢ ነው። ይህም ሰላማዊ ቀጠናን ለመመስረት የሚረዳና ለቀጣናዊ ትስስርም ያለው ፋይዳ ቀላል አለመሆኑን ነው ኢንጂነር ስለሺ የሚያብራሩት። በኤሌክትሪክ አቅርቦት አንጻር ዓባይ ትልቁን ሚና ይጫወታል። እነ ወይዘሮ ክብነሽን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወጣሉ። ሕይወታቸው ይሻሻላል፤ ተስፋም ይፈነጥቃል። ኃይል የስራ ዕድል ነው፣ ኃይል የእድገትና የልማት ምንጭ ነው ይህም በዓባይ ይሳካል።

በአጠቃላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን መልከ ብዙ ነው። ይህ ፕሮጀክት የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የማህበራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ተጽዕኖ ትርጉሞች ያሉት ነው። ግድቡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሁሉም አሻራ ያረፈበት ግድብ ነው። የአንድነት፣ የመተባበርና የአብሮነት ማሳያና መገላጫ የልማት ፕሮጀክት ነው። አለፍ ሲልም ለቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም

ዓቀፋዊ ተሰሚነትና ተቀባይነት አጉሊ ተግባር ነው። ግድቡ የአገሪቷ የሉአላዊነትና የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድበት ጊዜም አለ። አቶ ገዱ ግድቡ ኃይል ከማመንጨነትና ድህነት ከመቀነሻነትም በላይ ነው ይላሉ። ግድቡ የጂፖሎቲካል ነባራዊ ሁኔታውን ወደ ፍትሃዊነት አቅጣጫ እንዲያመራ ለማድረግ ትልቅ ጥቅም ያለው ፕሮጀክት መሆኑንም ይገልጻሉ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይህ ፕሮጀክት የአገራዊ መግባባት አንዱ ማሳያ ነው ይሉታል። በዚህ መልክ ሲታይ ብርቅዬና እንቁ ፕሮጀክት መሆኑን ሁሉም ሊረዳው ይገባል ብለዋል። ‘’ኢትዮጵያውያን በጽናት ቆመን ኢፍትሃዊነትን የተቃወምንበትና ለዓለም ያሳየንበት የልማት ስራም ነው’’ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በመጨረሻም አርቲስት ስለሺ ደምሴን (ጋሽ አበራ ሞላን) እናስታውስ። አንድ ልብ የሚያቆ ዜማ አለው አርቲስቱ። ዓባይ የእኛ አልፋና ኦሜጋ ነው።

….ዓባይ ዓባይ ዓባይ

አባቱ ደጀን፣ እናቱ ጣና

የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና

የአፍሪካ ልጆች መጡ እንደገና …

ዓባይ የኢትዮጵያ ልጆች ዳግም እንዲነሱ ምክንያት ይሆናል። ተስፋን ያለመልማል። አዎ የኢትዮጵያ ልጆች እንደገና ይመጣሉ። የአድዋዎች አንበሶቹ ዛሬም ድል እያደረጉ ነው። ዛሬም ቃላቸውን ይጠብቃሉ። ይፈጽማሉ ይተገብራሉ። የአፍሪካ ልጆች ይነሳሉ። ዓባይ ለአህጉሪቷ አርዓያ የሚሆን የልማት ፕሮጀክት ነው። ማንም አልሞከረውምና። ኢትዮጵያ ሞከረች እያሳየችም ነው።

ዓባይ ለወይዘሮ ክብነሽና ለመሰሎቻቸው እንደገና መጥቷል፡ ፡ እነርሱም ወደእርሱ እየቀረቡ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም የነዚህ እናቶች ወገብ መጉበጥ ሊያበቃ ይገባል፡፡ ዓባይ የከፍታችንን ብርሀን ሲያጎናጽፈን በጭስ የተጨናበሰውና የሚያነባው ዐይናቸው ይታበሳል፡፡ ለጨለማ ህይወታቸውም ጎህ ይቀድለታል፡፡ ከጉባ ተራሮች መሀል ከህዳሴው መንደር የሚመነጨው ኀይል የኑሯቸው ጉልበት ይሆናል፡፡ የኑሮ ዘይቤአቸውም ማገዶ ከመልቀምና ከመቸርቸር ተላቆ በኤሌክትሪክ ኀይል የታገዘ ስራ ወደ መስራት ይለወጣል፡፡

በአጠቃላይ ግን ዓባይ የዚህ ትውልድ አብሪ ኮከብ ነው። የትውልዱ የድል ችቦ ከፍ ብሎ የሚውለበለብበት ፕሮጀክት ነው። ዓባይ የዘመኑ ትውልድ ተስፋ ነው። የይቻላል መንፈስን ያስመሰከረ የልማት ውጤት። ዓባይ ይገደባል፤ የጎበጠው የኢትዮጵያ እናቶች ወገብ ይቀናል። ከብርሃኑም ተቋዳሽ ይሆናሉ። ኢትዮጵያም ታድጋለች ትመነደጋለች፤ ከፍታዋም ይረጋገጣል። ይህ ደግሞ በወዛችን፣ በደማችን፣ በአጥንታችን ይሳካል። ለዚህ ነው ዓባይ ደማችንና አጥንታችን ነው የምንለው። ፍጻሜውን ለማየት ያብቃን።



50

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

መካንነትን የሚያመክነው

ማዕከል

ማህበረሰብ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና በኢዜአ ትብብር የተዘጋጀ



51

በርካቶችን ለስነ-ልቦና ስብራት ዳርጓል፤ የብዙዎችን ትዳር አፍርሷል፤ ዐይናቸውን በዐይናቸው የማየት ህልማቸውን አጨናግፏል፤… የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ “ጥንዶች በተከታታይ ለ12 ወራት ወይንም ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ምንም አይነት የእርግዝና መከላከያ ሳይወስዱ በሳምንት ሦስት ቀንና ከዚያን በላይ ወሲባዊ ግንኙነት ፈጽመው ነገር ግን መፀነስ አለመቻል ነው” ይለዋል፤ መካንነትን። ነገር ግን የሴቷ ዕድሜ 35 እና ከዚያ በላይ ከሆነ መካን ለመባል የሚያስፈልግበት ጊዜ እስከ ስድስት ወር እንደሆነም መረጃዎች ያመለክታሉ።

የግብረ ስጋ ግንኙነት በአግባቡ ከሚፈፅሙ ጥንዶች ውስጥ ከ80 እስከ 90 ከመቶ የሚሆኑት የመውለድ አሊያም ዘራቸውን የመተካት ዕድል አላቸው። ይሁንና በተለያዩ ምክንያቶች በአማካይ 15 በመቶ የሚሆኑ ጥንዶች ለመካንነት ይጋለጣሉ። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመካንነት ሕክምናና የስነተዋልዶ ጤና ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቶማስ መኩሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና ጥናት አለመኖሩን ጠቅሰው የዓለም ጤና ድርጅት ግን በኢትዮጵያ ከ15 እስከ 20 በመቶ ጥንዶች መካንነት እንደሚያጋጥማቸው በጥናት ይፋ ማድረጉን ይናገራሉ።

መካንነት በወንዱ አልያም ደግሞ በሴቷ መውለድ አለመቻል ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ ደግሞ ሁለቱም በተመሳሳይ ይህ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል። አንዳንድ መረጃዎች 20 ከመቶ መካንነት በወንዶች፣ 38 ከመቶ በሴቶች፣ 27 ከመቶ በወንዶችና ሴቶች ተመሳሳይ ችግር እንደሚያጋጥምና ቀሪው 15 ከመቶ የመካንነት ችግር ደግሞ በውል የማይታወቅ ይልቅም በሕክምና ተቋማት በሚደረግ ምርመራ የሚታወቅ መሆኑን ይጠቁማሉ።

ሌሎች ደግሞ በወንድና በሴት የመከሰት እድሉን እኩል ያደርጉታል። ለአብነትም የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል

በፍጹምእሸት ሺመልሽ



52

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

(CDC) መረጃ እንደሚያመለክተው አንድ ሶስተኛ ለሚሆነው የመካንነት ችግር ምክንያቱ ወንዶች ሲሆኑ በተመሳሳይ አንድ ሶስተኛ ለሚሆነው ልጅ ያለመውለድ ችግር ምክንያቱ ሴቶች ይሆናሉ። አንድ ሶስተኛ የሚሆነው የመካንነት ችግር ደግሞ የሁለቱም ችግር ነው ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። በሃገራችን መካንነት 40 በመቶ በሴቶች፣ 40 በመቶ በወንዶች እንዲሁም 20 በመቶ በሁለቱም ላይ እንደሚከሰት ዶክተር ቶማስ ይናገራሉ።

ልጅ የመውለድ እድል ለወንዱም ሆነ ለሴትዋ እንደ እድሜያቸው ሁኔታው ይወሰናል። በእርግጥ እድሜ በተለይም በሴቶች በኩል ልጅ ላለመውለድ ከወንዶች በበለጠ ምክንያት መሆኑ እርግጥ ነው። በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ልጅ የመውለድ ተፈጥሯዊ ብቃታቸው በሀያዎቹ እድሜያቸው ከነበረው በግማሽ ያህል ይቀንሳል። ሴቶች እድሜያቸው 35 ሲደርስ የማርገዝ እድላቸው በፍጥነት እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን የወንዶች የማስረገዝ ብቃት ግን እየቀነሰ የሚሄድ ቢሆንም በዝግታ ነው ይላሉ የዘርፉ ምሁራን።

አጋላጭ ምክንያቶችና ምልክቶች

በወንድ፡- እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሴቶች መካንነት እንጂ የወንዶች መካንነት ያለ የማይመስላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በተለያዩ አገሮች መኖራቸውን ጥናቶች ያረጋግጣሉ። በተለይም የወንዶች የበላይነት ጎልቶ በሚታይባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ሴቶች መካን ናቸው ተብለው ወደ ሐኪም ቀርበው የተለያየ የጤና ምርመራ ሲያደርጉ ወንዶቹ ግን ያሉበትን የጤና ሁኔታ ለማወቅ እንኳን የሕክምና ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አይሆኑም።

ወንዶች መካን የሚሆኑባቸው ምክንያቶች በርካታ ቢሆኑም የወንድ ዘር አለመስራት እና የወንድ ዘር አለማመንጨት በአበይትነት ይጠቀሳሉ። የመካንነት ችግር ካለባቸው ወንዶች ወደ 15 በመቶ የሚሆኑት የዘር ፍሬ ጭራሹኑ የሌላቸው መሆናቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ። የወንድ የዘር ፍሬ አለመስራት ደግሞ testes የተሰኘ በብልት አካባቢ የሚገኝ የስነተዋልዶ አካል ስራውን በአግባቡ መስራት ሲያቅተው የሚፈጠር ነው። ይህ አካል ሁለት ተግባራት አሉት። አንደኛው የወንድ ዘር ፍሬ ማምረት ሲሆን ሁለተኛው ተግባሩ ደግሞ ቴስቴስትሮን የተባለውን ሆርሞን ማምረት ነው። አንድ ወንድ ይህ የሰውነት ክፍሉ በትክክል ካልሰራ የሴቷን እንቁላል መስበርና ልጅ እንዲረገዝ ማስቻል እንደሚያቅተው ዶክተር ቶማስ ይናገራሉ።

ሌላው በወንድ ላይ የሚከሰተው የመካንነት ችግር ከሆርሞን መዛባት፣ ተፈጥሮው ማቆም እንዲሁም ከዘር ፍሬ ማስተላለፊያ መዘጋት ጋር የተገናኘ ነው። የስኳር በሽታ፣ የአባላዘር በሽታ፣ ካንሰር፣ ኤች አይቪ ኤድስ፣ ቲቢ፣ እንዲሁም በባክቴሪያ የሚመጡ ኢንፌክሽኖች የዘር ማስተላለፍያ ችግር እንዲያጋጥም ሊያደርጉ ይችላሉ። ከአኗኗር ዘይቤ ጋር በተያያዘም አልኮል አብዝቶ መጠጣት፣ ሲጋራ ማጤስ እና አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶክተር ቶማስ ያስረዳሉ።

ከትክክለኛው መጠን ያነሰ የዘር ፍሬ የሚያመርቱ ወንዶችም ለመካንነት ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ። የተለያዩ የጤና እና ተፈጥሯዊ እክሎች የወንዶች የዘር ፍሬ በትክክለኛው መንገድና መጠን እንዳይመረት ሊያደርጉ ይችላሉ። ለአብነትም testicle የተባለው የዘር ፍሬና ሆርሞን አምራች የሰውነት ክፍል መጎዳት እንዲሁም የChromosome መዛባት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው። የደም መልስ ቧንቧዎች መስፋትም የወንድ ዘር ፍሬ ማመንጫ አካባቢ ሙቀት በመፍጠር ትክክለኛ የሆነ የወንድ የዘር ፍሬ ወይም ስፐርም አፈጣጠር ሂደት እንዳይኖር ያደርጋል።

የዕድሜ መግፋትም የዘር ፍሬ ጥራትና መጠንን ስለሚቀንስ ለመካንነት ሊዳርግ ይችላል። ይህ የሚሆነው የወንዱ ዘር ወይም ስፐርም እንቁላል የመስበርና ልጅ እንዲረገዝ የማስቻል አቅም ስለሚዳከም ነው።

ስፐርም ከተመረተ በኋላ ወደ ሴቷ እንቁላል በመጓዝ ልጅ እንዲመረት የሚያደርገው በተለምዶው የትራንስፖርት መስመር ወይንም መጓጓዣው ሲዘጋም መካንነት ይፈጠራል። ይህ መስመር ማለትም የዘር ማስተላለፊያ ቱቦው በአባላዘርና ባልሆነ ኢንፌክሽን ወይንም ቀደም ብሎ ባጋጠሙ በሽታዎች ምክንያት ሊዘጋ ይችላል። በተፈጥሮ ምክንያት ቱቦው እስከ ጭራሹም ላይፈጠር የሚችልበት እድል እንዳለም የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በተፈጥሮ የዘር ፍሬ ወደ ብልት አለመውረድ (በሆድና በብልት መሀል መቅረት) ሌላው ለመካንነት ሊዳርግ የሚችል ችግር ነው።

በሴት፡- ሴቶች የሚወለዱት በሕይወት ዘመናቸው የሚጠቀሙባቸውን እና እያደርም የማይተኳቸውን እንቁላሎች ይዘው ነው። አንዲት ሴት ከ1 እስከ 2 ሚሊዮን እንቁላሎችን ይዛ እንደምትወለድ ይታመናል። የሴቷ እድሜ እየጨመረ ሲሄድ የእንቁላል ቁጥር እየቀነሰ ይሄዳል። ይህም ማለት ሴቶች እድሜያቸው በጨመረ ቁጥር ልጅ የማፍራት እድላቸው እየቀነሰ ይሄዳል ማለት ነው። የወር

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመካንነት ሕክምናና የስነተዋልዶ ጤና ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቶማስ መኩሪያ



53

አበባ ሲቋረጥ ደግሞ እስከጭራሽ ስለ እርግዝና ማሰብም ይቀራል።

ተፈጥሯዊ የሆነው የሴት ልጅ ዕድሜ ትልቅ ተፅዕኖ አለው። በተለይ እድሜዋ ወደ 30ዎቹ አጋማሽና 40ዎቹ የደረሰ ሴት ልጅ ወልዳ የመሳም ዕድሏ ይመናመናል። አንዲት ጤነኛ ሴት በ20ዎቹ ዕድሜ ወይም የ30ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የማርገዝ ዕድሏ በየወሩ ከ25 እስከ 30 በመቶ ሲሆን በ 40 ዎቹ ውስጥ ያለች ሴት ግን የማርገዝ ዕድሏ 10 በመቶ ወይም ከዚያ ያነሰ እንደሚሆን የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ።

ከእድሜ መግፋት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው እድሜዋ ለአቅመ ሔዋን የደረሰ ሴት በወር ውስጥ አንዴም እንቁላል (የሴት ዘር) ካልለቀቀችም የማርገዝ ችግር ያጋጥማታል። ይህም የእንቁላል ከማህጸን አለመውጣት ችግር ሊባል ይችላል። ይህን ችግር ሊያመጡ ከሚችሉ ምክንያቶች መካከል የእንቅርት ህመም፣ የሆርሞን ችግሮች እና PCOS የሚባል የማህጸን በሽታ ተጠቃሾች መሆናቸውን ዶክተር ቶማስ ያስረዳሉ።

የማህጸን ቱቦ መዘጋት ሌላው ለመካንነት ሊዳርግ የሚችል ችግር ነው። እንቁላል ከኦቫሪ በቱቦ አድርጎ ከወንድ የዘር ፍሬ ጋር ቱቦው ላይ ከተገናኘ በኋላ ወደ ማህጸን ይጣበቃል። ነገር ግን የወንድ ዘርና እንቁላል የሚገናኙበት የማህጸን ቱቦ (Fal- lopian Tube) መዘጋት ወይም መጎዳት መካንነት ወይም ከማህጸን ውጭ እርግዝናን ሊያስከትል ይችላል ።

በእንቁላሎቹ ላይ ተፈጥሯዊ ችግር ካለም መካንነት ሊገጥም ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ እንቁላል ከእንቁላል የማጠራቀሚያ ወደ ማህጸን እንዲመጣ እንዲሁም ከወንድ የዘር ፍሬ ጋር ተጣምሮ በማህጸን እንዲቀበር የሚያደርጉ ሆርሞኖች ችግሮች ካጋጠማቸውም መካንነት ይከሰታል። ችግሮቹም የማህጸን እጢ፣ ካንሰር፣ በተደጋጋሚ እንዲሁም በህክምና ተቋም በተገቢው መንገድ ያልተደረገ ውርጃ፣ ከእንቁላል ማጠራቀሚያ ወደ ማህጸን የሚወስደው ቱቦ መጎዳት የመሳሰሉት ናቸው።

ከዚህም በተጨማሪ የአኗኗር ሁኔታ እንዲሁም ከመጠን በላይ ውፍረት መጨመር እና መቀነስ የመካንነት ችግር ሊያመጣ ይችላል። ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል አብዝቶ መጠጣትና ዕጽ መጠቀም ተፅዕኗቸው እየጎላ ነው።

ለወንድም ለሴትም አጋለጭ ምክንያቶች ተብለው የሚጠቀሱ ችግሮች ሳይገኙም መካንነት ሊከሰት ይችላል። ይህም ከአጠቃላይ መካንነት 20 በመቶ ሊደርስ እንደሚችል ዶክተር ቶማስ ይናገራሉ። ዶክተሩ “አጋላጭ ምክንያቶች አልተገኙም ማለት ግን ችግር አለመኖሩን ሳይሆን ችግሮቹ አለመታወቃቸውን ወይም እንዳልተደረሰባቸው ነው የሚያመለክተው” ይላሉ።

የመካንነት ችግሩ በየትኛውም ምክንያት ይከሰት የሚያሳድረው ተጽዕኖ ግን ቀላል አይደለም። የስነልቦና ባለሙያዎች እንደሚሉት ልጅ መውለድ ያልቻሉ ጥንዶች ለተለያዩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ቀውሶች ይዳረጋሉ። ጭንቀት፣ ደስታ ማጣትና ድብርት ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ ራስን መቆጣጠር አለመቻል፣ የወሲብ ፍላጎት መቀነስ፣ የበታችነት

ስሜት፣ ማህበራዊ ጉዳዮችን መሸሽ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ቁጡ መሆን ከሚያጋጥማቸው ቀውሶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

መካንነት ትልቅ ማህራዊ ጫናም አለው። ልጅ አለመውለድ እንደ ሐጢአተኛነት ወይንም የሚያስኮንን ድርጊት ተደርጎ ስለሚወሰድ መጥፎ ስሜትን ይፈጥራል። በትዳር አጋር ተቀባይነትን ስለሚያሳጣ የትዳርን ሕይወት ጣዕምና ለዛ ያሳጣዋል። በሕይወት ውስጥ ሊሳተፉበት የሚገባን ተግባር ይቀንሳል። ለራስ ያለ አመለካከትን ዝቅ ያደርጋል። በትዳር ጸንቶ ለመኖር እንቅፋት ይሆናል። ፍቅርን ይቀንሳል። መተሳሰብ፣ መከባበርና ኃላፊነትን በጋር መወጣት እንዳይኖር ያደርጋል።

መካንነት ያጋጠማቸው ሰዎች በሳይንሱ ከስነ ተዋልዶ አካላት አሰራር ጋር የተያያዙትን ችግሮች ከጽንስና ማህጸን ስፔሻሊስት ሐኪሞች ወይንም ከመካንነት ሕክምና ስፔሻሊስቶች ጋር በቅርብ በመመካከር መፍታት ይቻላል። ከዚህ ባለፈም የስነልቦና ባለሙያዎች የመንፈስ ህክምናን በማድረግ ከጭንቀትና ድብርት ስለሚገላግሉ ወደ እነርሱ ማቅናትም ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል።

የመካንነት ሕክምና ብዙ ጊዜ ጥንዶች ልጅ ማግኘት ካልቻሉ ችግሩ ከሴትዋ ይሆናል የሚል ግምት በመያዝ ወንዶቹ ሐኪም ዘንድ አይቀርቡም። የመካንነት ሕክምና ግን መጀመሪያ ጥንዶቹ መካንነትን ለማረጋገጥ በጋራ ሐኪም ጋር ሲቀርቡ የሚጀመር ነው። ባልና ሚስት ወይም ጥንዶች በአንድ ዓመት ውስጥ ተገቢውን የግብረ ስጋ ግንኙነት እየፈፀሙ እርግዝና ካልተፈጠረ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ መመርመር ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም የሴቷ ዕድሜ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነ አንድ ዓመት ሳይጠብቁ ከስድስት ወር በኋላ ሄደው መመርመር አለባቸው። ይህም ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የማርገዝ ዕድል እየቀነሰ ስለመሄድና ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ባለመሆኑ በወቅቱ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።

ለመካንነት መፍትሄ ለመስጠት በመጀመሪያ ደረጃ መካንነትን ያስከተለው ችግር ምንድን ነው ብሎ መለየት ያሻል። ይህን ለመለየት ደግሞ የጥንዶቹን ዝርዝር ታሪክ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህን በተሳካ ሁኔታ ማከናወን የሚቻለው ደግሞ ጥንዶቹ አብረው ወደ ህክምና ማዕከል ሲያመሩ ነው። ከዚያ በኋላ ችግሩን በሕክምና የመለየት ስራ ይከናወናል። ችግሩ በሕክምና ከተለየ በኋላም የተለያዩ ሕክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ በተለያዩ ምክንያቶች በቂ የወንድ ዘር (ስፐርም) ለሌላቸው ወንዶች ወይንም አነስተኛ ዘር ያላቸው ወንዶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ዘራቸውን በመውሰድ ወደ ሴቷ ማህጸን እንዲገባና ከሴቷ እንቁላል ጋር እንዲዋሃድ ብሎም እርግዝና እንዲፈጠር ማድረግ ይቻላል። እንደ ችግሮቹ ዓይነትም ሌሎች መፍትሄዎች ይኖራሉ።

ሴቶችን በተመለከተም ለአብነት የዘር መተላለፊያ ቱቦ ከተዘጋ፣ የማህጸን ህመም አልያም ደግሞ ሌሎች ኢንፌክሽኖች የተከሰቱ እንደሆነ በሕክምና በመታገዝ እርግዝና እንዲፈጠር ማድረግ ይቻላል። የተለያዩ ሆርሞኖች መዛባትና የዘር እንቁላል ችግሮችንም በሐኪም የታዘዘ መድኃኒት በመውሰድ

ማስተካከል ይቻላል። ከዚህ ባለፈ እንደ IVF፣ ICSI፣ PGD፣ እንቁላል ወይም የወንድ ዘር መለገስ ያሉ ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ለመካንነት በህክምና መፍትሄ መስጠት ይቻላል።

አንድ ለእናቱ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከመካንነት ሕክምና እና ከሥነ ተዋልዶ ጤና ጋር ለተያያዙ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ማዕከል አቋቁሞ መስራት ከጀመረ ገና ዓመት ከመንፈቅ አልተሻገረም። ይህ እንደ IVF እና ICSI ያሉ ዘመናዊ የመካንነት ሕክምናዎችን በመስጠት አንድ ለእናቱ የሆነው የመካንነት ሕክምና እና የስነ ተዋልዶ ጤና ማዕከል በፈተናዎች ተከቦም ቢሆን ከእድሜው በላይ እየሰራ እንደሆነ የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ቶማስ ይናገራሉ።

ከ60 ሺህ በላይ ጥንዶች የመካንነት ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን የሚገልጹት ዶክተር ቶማስ ከእነዚህ መካከል 1 ሺ 400ዎቹ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመካንነት ሕክምና ለማግኘት መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። ማዕከሉ ለ280 ጥንዶች ይህን በቴክኖሎጂ የታገዘ የIVF ሕክምና መስጠት የቻለ ሲሆን 117 ወይም 42 በመቶ እርግዝና መፈጠሩን ዶክተሩ አስረድተዋል። የIVF ሕክምና የሴቷን እንቁላል እና የወንዱን ዘር ወይም ስፐርም በዘመናዊ መንገድ በመሰብሰብ ላቦራቶሪ ውስጥ እንዲዋሀዱ በማድረግ ጽንስ በመፍጠር ጽንሱን በተገቢው ቀን ወደ ሴቷ ማህጸን እንዲቀመጥ የማድረግ ሂደት ነው። ዶክተር ቶማስ IVF ከተሰራላቸው መካከል ከ30 እስከ 50 በመቶ እርግዝና ከተፈጠረ መልካም የሚባል መሆኑን አስታውሰው ከዚህ አኳያ የማዕከሉ አፈጻጸም ይበል የሚያሰኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሕክምናው የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ባስተማራቸው ሰባት የሕክምና ባለሙያዎች ይሰጣል። የIVF ሕክምና የሚከናወነው ከ 8 እስከ 10 የሚሆኑ እንቁላሎች እንዲያድጉ የሚያደርግ መድኃኒት በመርፌ መልክ በመስጠት ሲሆን እንቁላል የሚያድግበት ቤት (Follicle) ተገቢው መጠን ላይ መድረሱ በአልትራሳውንድ ክትትል ሲረጋገጥ HCG የሚባል መድኃኒት ይሰጣል ይህ መድኃኒት ከተሰጠ ከ 35 እስከ 36 ሰዓት በኋላ ቀላል የሰመመን ማደንዘዣ እና አልትራሳውንድ በመጠቀም እንቁላሎቹ በዕለቱ ወይም ቀደም ብሎ ከተዘጋጁ የወንድ ዘሮች/sperm cells/ ጋር ላቦራቶሪ ውስጥ በዚያኑ ቀን እንዲዋሀዱ ይደረጋል።

ላቦራቶሪ ውስጥ ጽንስ የመፍጠሩ ሂደት በባለሙያ /Em- bryologist/ በከፍተኛ ጥንቃቄ ከ3 እስከ 5 ቀናት ክትትል ከተደረገለት በኋላ ጥራት ያላቸው ሁለት ጽንሶች ለዚህ በተዘጋጀ መሳሪያ አማካኝነት ማህጸን ውስጥ እንዲቀመጡ እንደሚደረግ ዶክተር ቶማስ ያስረዳሉ። ይህ አይነቱ እርግዝና ከተፈጥሯዊው እርግዝና ጋር የሚያመሳስሉትም የሚያለያዩትም ነገሮች አሉ። የእርግዝናው ወራት፣ በምጥ አልያም በቀዶ ሕክምና ሊወለድ መቻሉ ከተፈጥሮው የእርግዝና ሂደት ጋር ያመሳስለዋል።



54

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

የሴቷ እንቁላል ከወንዱ የዘር ፈሳሽ ጋር የሚገናኝበት ሂደት በቤተ ሙከራ መከናወኑ፣ ጽንሱ ማህጸን በሚመስል ‘’ኢንኩቤተር’’ ለአምስት ቀናት እንዲቆይ መደረጉ፣ ከተፈጥሯዊው በበለጠ አደጋዎች ሊኖሩት መቻሉ፣ በተፈጥሯዊ እርግዝና ወቅት ከሚወሰዱ መድኃኒቶች በተጨማሪ ሌሎች መድኃኒቶች ማስፈለጋቸውን ወዘተ ልዩ ያደርጉታል።

ሌላው ማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎት የICSI ሕክምና ነው። ይህ መካንነት ሕክምና Intra Cytoplasmic Sperm Injection የሚባል ሲሆን በላቦራቶሪ ውስጥ የወንድ ዘርን በቀጥታ የተዘጋጀው እንቁላል ሴል ውስጥ ማስገባት ነው። በዚህ መልክ የተፈጠረው ጽንስም ጊዜውን ጠብቆ ማህጸን ውስጥ እንዲቀመጥ ይደረጋል። ይህ ሕክምና በIVF ወቅትም አንዳንዴ አገልግሎት ላይ ሊውል እንደሚችል ዶክተር ቶማስ ያስረዳሉ።

ከ IVF እና ICSI ሕክምና በተጨማሪ የእንቁላል ወይም የዘር ፈሳሽ ልገሳ (Egg or Sperm donation) ሕክምናም አለ። ይህ ሕክምና በኢትዮጵያ ባይሰጥም በሌሎች አገሮች ይተገበራል። ሕክምናው ሀገር ውስጥ የማይሰጥበት ዋነኛ ምክንያት የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ እንደሆነ ዶክተር ቶማስ ይናገራሉ። የሕግ ማዕቀፍ አዘጋጅቶ ሕክምናውን መስጠት የሚቻልበትን አውድ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን በማከል። እርሳቸው እንደሚሉት ሕክምናውን የሚፈልጉ ሰዎች በሀገር ውስጥ በብዛት አሉ። በተለይ ያለ እድሜ የእንቁላል ማነስ ሲያጋጥም ይህ ሕክምና ፍቱን ነው ይላሉ።

ሕክምናው የሚሰጠው ከጥንዶቹ ውጭ ከሌላ ሴት እንቁላል አልያም ከሌላ ወንድ የዘር ፈሳሽ ወስዶ ልጅ እንዲፈጠር ከተደረገ በኋላ እንደገና ወደ ማህጸን መመለስ ነው። የእናት ማህጸን ጽንስ መያዝ አልችል ሲልም የማህጸን ኪራይ ይኖራል። በነዚህ መንገዶች የሚወሰደው ህጻን የሴቷ ወይም የወንዱ ባዮሎጂካል ልጅ ስለሚሆን ልጅ በማጣት ሊበተን የነበረን ትዳርም ከመፍረስ የማዳን አቅም አለው። ዶክተር ቶማስ እንደሚሉት በእንቁላል ወይም በዘር ፈሳሽ ልገሳ በሚደረግ ሕክምና ሊያጋጥም የሚችለው የዘር ፈሳሽ ለጋሹ አካል ልጁ የእኔ ነው ብሎ ሊመጣ መቻሉ ነው። ለዚህ መድኃኒቱ ልግስናው ለማን እንደሚሄድ ማሳወቅን በሕግ መከልከል ነው።

ሌላው ልጅ ለመውለድ እንዲቻል እንቁላልን ወይንም የዘር ፍሬን በላቦራቶሪ ማስቀመጥ እና ልጅ መውለድ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ መጠቀም እንዲችሉ የማድረጊያ ዘዴ ነው። ለምሳሌም ሰዎች በተለያዩ ሕመሞች ከተያዙ ወይንም የጤና መዛባት ከገጠማቸው እና ወደፊት ልጅ የመውለድ እድላቸውን የሚያሰናክል ከሆነ በጊዜ እርምጃ እንዲወስዱና ልጅ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ይህንን የሳይንስ ውጤት ሊጠቀሙ የሚችሉ ሰዎች ለመርዛማ ንጥረ ነገሮች ተጋላጭ በሆነ ቦታ የሚሰሩ ከሆነ፤ በካንሰር ሕመም ከተያዙ፣ በአለርጂክ ሕመም የሚሰቃዩ ከሆነ፤ ልጅ የመውለድን እድል በሚያጨናግፉና በቤተሰብ በሚወረሱ ሕመሞች ከተጠቁ፤ ወዘተ የመካንነት ችግር አለም አቀፍ ችግር በመሆኑ ይህንን ለመፍታት የሚያስችሉ ሳይንሳዊ አገልግሎቶች በአገራችንም በስፋት ቢገኙ ብዙዎች መካንነት አያሳስባቸውም እንደ

CDC መረጃ።

የማዕከሉ ፈተናዎች ልጅ መውለድና ቤተሰብ መመሰረት በአብዛኛው ማኅበረሰብ ዘንድ የሕይወት ግብ ተደርጎ ይወሰዳል። መካንነት በዚህ ‘’ የሕይወት ግብ’’ ላይ ትልቅ ስነ ልቦናዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ያስከትላል። ማዕከሉ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በሚሰጣቸው ሕክምናዎች መፍትሄ ያገኙ ጥንዶች ሲደሰቱ ከመመልከት በላይ እርካታ እንደሌለ የሚናገሩት ዶክተር ቶማስ ባለው የባለሙያ እጥረት እና ተቋማዊ አቅም ውስንነት የተነሳ አያሌ ጥንዶች ሕክምናውን አለማግኘታቸውን ሲያስቡ ግን ደስታቸው ይደበዝዛል።

በተለይ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ከ 60 ሺ የሚልቁ ጥንዶች አገልግሎት ፈልገው ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውን እና በዓመት ከመንፈቅ ውስጥ የታዩ ጥንዶች 6ሺ ገደማ መሆናቸውን ሲያስታውሱ የተሰራው ስራ እንደ አንድ ጀማሪ ማዕከል መልካም መሆኑን ቢረዱም ወረፋ በመጠበቅ ላይ ያሉ ከ 50 ሺ በላይ ጥንዶች መኖራቸው በእጅጉ ያሳስባቸዋል። በተለይ የIVF ሕክምና በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመካንነት ሕክምና እና የስነ ተዋልዶ ጤና ማዕከል እና በአንድ የግል ተቋም ብቻ የሚሰጥ መሆኑ ችግሩን ሰፊ አድርጎታል።

ሌላው እንደ ችግር የሚነሳው ጉዳይ እንደ IVF ያሉ የማዕከሉ አገልግሎቶች መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት እርዳታ መከናወናቸው ነው። ልገሳ ደግሞ ሁልጊዜ የሚቀጥል አይሆንም። በዚህ ላይ የአገልግሎቱ ውድነት ሲታሰብ የገንዘብ ጉዳይ ትልቁ ፈተና መሆኑን መረዳት አያዳግትም። ዶክተር ቶማስ እንደሚሉት ውጭ አገር ሄዶ IVF ለማሰራት ከ5 ሺ እስከ 10 ሺ ዶላር (ከ175 ሺ እስከ 350 ሺ ብር) ያስወጣል። አገልግሎቱን ከማዕከሉ እያገኙ ያሉ ሰዎች እየከፈሉ ያሉት ለመድኃኒቱ ብቻ ሲሆን ሌላው ወጪ እተሸፈነ ያለው በእርዳታ ነው። ነገር ግን ይህ እርዳታ እንደማይቀጥልና መንግሥትም ይህን ወጪ የመሸፈን አቅም እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል።

ስለዚህ ይህን ችግር መቅረፍ የሚቻለው ማዕከሉ የራሱን አቅም እንዲያደረጅ በማገዝ መሆን ይኖርበታል። ማዕከሉ ችግሩን ለማቃለል ውጭ አገር ሄደው አገልግሎቱን የማግኘት አቅም ያላቸው ሰዎች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እዚሁ አገር ውስጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ በማድረግ ከነርሱ በሚገኘው ገንዘብ ደግሞ አቅም የሌላቸውን በመደጎም ባነሰ ክፍያ እንዲስተናገዱ የማስቻል ስራ እየሰራ መሆኑን ዶክተር ቶማስ ያስረዳሉ።

ሌላው ችግር አገልግሎቱን የሚፈልጉ ሰዎችና የማዕከሉ አቅም አለመመጣጠን ነው። ተመዝግበው ሕክምና የሚጠባበቁ ከ 50 ሺ በላይ ጥንዶች አሉ። ማዕከሉ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ስፔሻሊስቶች ናቸው ያሉት። በዚያ ላይ የሕክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ችግር ይፈታተነዋል። ቅርንጫፍ የሕክምና ማዕከላትን መክፈትም ደግሞ የራሱ ሌላ ፈተና አለበት። የተገልጋዬች ፍላጎትና የማዕከሉ አቅርቦት አለመጣጣሙን ተከትሎም በርካታ ጥንዶች ‘’ቀጠሮዬ ረዘመ’’ የሚል ቅሬታ

እንደሚያቀርቡ ዶክተር ቶማስ አልሸሸጉም። ይሁን እንጂ አገልግሎቱን የሚሹ ሰዎች ሁኔታውን መረዳትና ወረፋቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው ሳይናገሩ ማለፍም አልወደዱም።

እንደ መውጫ ማዕከሉ ሁለት ዓመት እንኳን ያልሞላው ጀማሪ መሆኑን ልብ ይሏል። ይሁን እንጂ ጥቂት ለማይባሉ ሰዎች የህይወት ዘመን መሻታቸው የሆነውን ዘር የመተካት ፍላጎት ማሳካት ችሏል። በዚህም ሊበረታታ ይገባል። ታድያ ወልዶ የመሳም ተስፋቸው ያከተመ የመሰላቸውን ሰዎች ተስፋ እየቀጠለ በደስታ የሚሞላውን ይህን ማዕከል በሁለንተናዊ አቅሙ እንዲጠናከር ማድረግ ልዩ ትኩረት ያሻዋል።

ማዕከሉ የባለሙያዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ ነው። አራት ስፔሻሊስቶችን አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን በቅርቡ የሚመረቁ ተጨማሪ ሶስት ባለሙያዎች መኖራቸውንም ዶክተር ቶማስ ነግረውናል። ነገር ግን ይህ በቂ አለመሆኑ የሚታበል አይደለም። የተሻለ ውጤታማ ስራ ለመስራት የባለሙያዎችን ጫና ማቃለል ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግሥትን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻዎች ትምህርትና ስልጠናው ይጠናከር ዘንድ መደገፍ ይጠበቅባቸዋል።

ማዕከሉ አገልግሎቱን በስፋት ማድረስ የሚችለው በተለያዩ አካባቢዎች ቅርንጫፍ ማዕከላት ሲኖሩት በመሆኑ በተለይ ባለሀብቱ በዚህ ረገድ ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። መንግሥትም በዚህ ላይ በትኩረት ቢሳተፍ ህዝብንና አገርን ይጠቅማል። ኢትዮጵያ የመካንነት ሕክምናን በሀገር ውስጥ ብታስፋፋ በሚሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ማዳን ይቻላልና።

ሀገር ውስጥ የሌሉ የመካንነት ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ተደራሽ ማድረግና ለአፈጻጸማቸው የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ሌላው አስፈላጊ ነገር ነው። እነዚህን ሕክምናዎች መስጠት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ አለመኖር ሰዎችን ውጭ አገር ሄደው ከመታከም እስካላዳናቸው ድረስ አገልግሎቱን በአገር ውስጥ መስጠት የሚቻልበትን ስርዓት ዘርግቶ የውጭ ምንዛሬ ማዳን የተሻለ አማራጭ ነው። ዶክተር ቶማስ የእንቁላል ወይም የወንድ ዘር ፈሳሽ ልገሳ ሕክምና ለማግኘት ወደ ተለያዩ አገሮች በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን በዓመት 11 ነጥብ 5 ሚሊዮን የውጭ ምንዛሪ አገሪቷ እንደምታጣ የንግድ ባንክን መረጃ ጠቅሰው ያስረዳሉ።

በአጠቃላይ ማዕከሉን በመደገፍ የራሱ የገቢ ምንጭ እንዲኖረውና አገልግሎቱን በስፋት እንዲያዳርስ ማድረግ ያሻል። እዚህ ጋር ግን አንድ ልብ መባል ያለበት ነገር አለ። ሁሉም የመካንነት ሕክምና አማራጮች ተከናውነውም ወልዶ ለመሳም የመታደል አጋጣሚ ላይሳካ ይችላል። ነገር ግን ወልዶ መሳም ባይቻልም ደስተኛ ሆኖ መኖር የሚቻልባቸው አማራጮች መኖራቸው መዘንጋት የለበትም። የመጀመሪያው በማደጎ ወይም በጉዲፈቻ ልጅ በማሳደግ የወላጅነትን ወይም የአሳዳጊነትን ወግ መጎናጸፍ ነው። ይህ ካልሆነ ደግሞ ልጅ ሳይኖርም ደስተኛ የትዳር ህይወት መምራት እንደሚቻል መረዳትና ለዚህም ራስን ማሳመን ወሳኝነት አለው።



55



56

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ጥረታቸውን

አናደብዝዘው

ወቅታዊ



57

ያለንበት ወቅት የአገራችን የጤና ባለሙያዎች ለራሳቸው ህይወት ሳይሰስቱ የወገኖቻቸውን ህይወት ለመታደግ እየፈጸሙ ያለው ተጋድሎ ከፍ ብሎ የታየበት ነው። ወቅቱ የሰው ልጅ ትክክለኛ ማንነት የታየበት ነው የሚባለውም ለዚህ ነው። ብዙዎች የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ከተነገረበት ቀን አንስቶ በዜጎች ጤና ላይ እያሳደረ ያለውንና ወደ ፊትም የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት እና የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት የተለያዩ እርምጃዎች ሲወሰዱ ቆይተዋል። የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት የጤና ሴክተሩ እና የህክምና ባለሙያዎች ድርሻ የላቀ ነው። ወረርሽኙ በየሃገራቱ በተስፋፋት በዚህ ወቅት የህክምና ባለሙያዎች ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው የሌሎችን ሕይወት ለማትረፍ እየሠሩ ነው።

የሀገራችን የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመከላከያ ቁሳቁስ በበቂ መጠን ባልነበረባቸው የመጀመሪያዎቹ ወራት ጭምር ሀገራቸው የጣለችባቸውን ግዴታ ለመወጣት ራሳቸውን ለበሽታው ተጋላጭ በማድረግ የወገኖቻቸውን ሕይወት ለመታደግ ከፊት ሆነው ተፋልመዋል። ቤተሰቦቻቸው በነርሱ ምክንያት ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ እያወቁም የተቻላቸውን ጥንቃቄ እያደረጉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን በማስቀደም ግዴታቸውን ተወጥተዋል እየተወጡም ይገኛሉ።

የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጭንቀትና ስነ ልቦናዊ ጫና በመቋቋም በመደበኛ የስራ ሰዓት ሳይገደቡ ተጨማሪ የስራ ሰዓት ጭምር በስራ ቦታ በማሳለፍ ሙያዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው። ከትዳር አጋራቸው፣ ከልጆቻቸው፣

በጤና ሚኒስቴርና በኢዜአ ትብብር የተዘጋጀ

ጥረታቸውን

አናደብዝዘው



58

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

ከቤተሰቦቻቸውና ከኑሯቸው ተለይተው በተመደቡበት የጤና ተቋም በኮሮና ቫይረስ የተጎዱ ወገኖቻቸውን ሕይወት ለማትረፍ ቀን ከሌት ይተጋሉ እንቅልፍ አጥተው፣ የምግብ ሰዓታቸው አልፎ፣ ፊታቸው በጭምብል ሰምበር ተጠብሶ፣ ግንባራቸውን በህሙማን ላይ ሳያጠቁሩ ሕይወትን ከሞት ለመታደግ ሲሯሯጡ ማየት የተለመደ ነው። ከዚህ አልፎ ህሙማንን ለማዳን ብለው ሲተጉ እነርሱም በቫይረሱ ተይዘው ባከሙበት አልጋ ላይ ህመምተኛ ሆነው የተኙና ከቤታቸው ሕይወት ለማዳን ብለው እንደወጡ በዚያው የቀሩ ባለሙያዎችም አሉ።

የእነዚህን የጤና ባለሙያዎችና አጠቃላይ የጤና ዘርፉን ጥረት የተመለከተው የበጎ ሰው ሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴ የሕክምና ባለሙያዎችንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን የዓመቱ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ አድርጎቸዋል። ሽልማቱ የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን ከተከሰተ ጀምሮ ሕይወታቸወንና ኑሮአቸውን መስዋት አድርገው የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ከፊት ተሰልፈው ሕብረተሰባቸውን እያገለገሉ ስለሚገኙ የተበረከተላቸው መሆኑም በስነስርአቱ ላይ በጉልህ ተጠቅሷል። ደግሞም ይገባቸዋል። የሽልማት ስነ ስርዓቱ አዘጋጅ ኮሚቴ “ሀገራችሁ ኢትዮጵያ የጣለችባችሁን ትልቅ መስዋትነት የሚጠይቀውን ይህን ግዳጅ በመወጣት ላይ የምትገኙ እናንተ የዘመኑ አርበኞች ለሰጣችሁንና ለምትሰጡን ፍቅርና ሙያዊ አገልግሎት ሁሉ አድናቆታችን ምስጋናና ከበሬታችን ይድረሳችሁ። ይህ ምስጋናችን ኮቪድን ሲከላከሉ ሕይወታቸውን የገበሩትን የሙያ አጋሮቻችሁን ሁሉ ያጠቃልላል” በማለት የ2012 የበጎ ሰው ልዩ ሽልማትም ይህንን ውለታቸውን ለማስታወስ የተሰጠ መሆኑን የሽልማቱ አዘጋጆች ተናግረዋል።

በሽልማት ስነ ስርዓቱ የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከፊት ለፊት ተጋፍጠው በርካታ ስራ ሲሰሩ የቆዩና እስካሁንም እያገለገሉ ያሉ የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። ወቅቱ ከጤና ባለሙዎች በተጨማሪ በርካቶች ይህን ሀገራዊ ፈተና ለማለፍ የተነሱበትና የግልም ሆነ የመንግስት አካላትም በአንድነት የተረባረቡበትና ትልቅ ስራ የተሰራበት ወቅት ነውም ብለዋል። ዶክተር ሊያ አክለውም እንደ ሀገር በጋራ ከቆምን ከባድ ፈተናዎችን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ወደ ተሻለ ነገር ማሻገር እንደምንችልም የተማርንበት ወቅት ነው ብለዋል።

በዚህ ፈታኝ ወቅት በማህበረሰቡ መካከል እየተመለከትን የምንገኘው የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ ባህል ተስፋ የሚያጭር ተግባር ነው። በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎች የምግብ እጥረት እንዳያጋጥማቸው የተደረገው የመረዳዳት ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው። ይህንን

የህብረተሰቡን የመረዳዳት ባህል በተቀናጀ መልኩ ለመምራት እንዲያስችል የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ መደረጉም የሚታወስ ነው። ይህን አገራዊ ጥሪ ተከትሎም የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት በገንዘብም ሆነ በዓይነት ድጋፋቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሰማርተው ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ ግለሰቦች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባስከተለው መጠነ ሰፊ ችግር ሥራቸውን ትተው በቤት ለማዋል መገደዳቸው ይታወሳል። ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ዜጎች በሃገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ታቅፈው እየተደገፉ ይገኛሉ። በሌላ በኩል ቤታቸውንና ሆቴሎቻቸውን ሳይቀር ለለይቶ ሕክምና መከታተያነት በነጻ ያበረከቱ ሰዎች ቁጥርም ቀላል አልነበረም።

የ2012 የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚ የሆኑት አቶ ካሊድ ናስር ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። በሀገራችን ኮቪድ-19 በተከሰተ ጊዜ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ወራት የነበረው መደናገጥ ብዙዎች ቤት እንዲቆዩ አስገድዷቸው ነበር። ችግሩ አፍጥጦ ከመጣባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ደግሞ የኔ የሚሉት መጠለያ ማረፊያ የሌላቸው ወገኖቻችን ብዙ ነበሩ ብርድና ፀሀዩን ተቋቁመው ጎዳና ላይ መኖሩን ቢቀበሉት እንኳን ለወትሮው ተሯሩጠው ለመስራት የነበራቸው ተስፋ ላይ ውሃ የቸለሰ ወረርሽኝ ሲከሰት ሁሉ ነገር ጨላልሞባቸው ነበር። ይሄኔ ነበር በጎ አድራጊው አቶ ካሊድ ናስር የቀን ስራ እየሰሩ በጎዳና ላይ የሚኖሩ ወገኖቻቸውን ለመርዳት ተነሳስተው መኖሪያ ቤታቸውን ለዚህ በጎ ተግባር ለማዋል የወሰኑት። ግቢያቸውን ለሴቶችና ለወንዶች ማቆያና ማረፊያ እንዲሆን አድርገው ያሳናዱት አቶ ካሊድ በዚህም ጊዜ 100 የሚደርሱ መቆያ የሌላቸው ወገኖቻችንን በዚህ ማረፊያ እያኖሩ ይገኛሉ።

እራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እውቅና መስጠት ባለሙያዎቹ ይበልጥ ለማገልገል ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው አያጠራጥርም። በተመሳሳይ በወረርሽኙ ምክንያት በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን ኢኮኖሚዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ካላቸው አካፍለው ወገኖቻቸውን በመርዳት ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን የተወጡ በጎ አድራጊ ሰዎችን በርቱ ማለትና እውቅና መስጠትም ተገቢ ነው።

የጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ዘርፍ አመራሮችና በጎ አድራጊ ሰዎች ከምንም በላይ የሚያስደስታቸው ነገር ቢኖር አሁን ወገናቸው ከዚህ አደገኛ ወረርሽኝ ተርፎ የነገን ብሩህ ተሰፋ ማየት ነው። ለዚህ ደግሞ ከህብረተሰቡ የሚጠበቀው ቀዳሚ ተግባር የህክምና ባለሙያዎች የሚነገሩትን የጥንቃቄ መመሪያ መተግበር ነው። ይህ

ማለት አካላዊ ርቀትን ቢያንስ በሁለት የአዋቂ እርምጃ መጠበቅ፤ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፤ አፍና አፍንጫን መሸፈን፤ ሲያስሉና ሲያስነጥሱ ፊትን ዞሮ በክንድ ማፈን የሚሉ ቀላል መመሪያዎችን ማክበር ነው።

አሁን አሁን ግን ይህንን የጥንቃቄ መልዕክት ጥቂቶች ተግባራዊ ቢያደርጉም በብዙዎች ዘንድ ግን መዘናጋቱና ቸልተኝነቱ እጅግ ጎልቶ በመታየት ላይ ይገኛል። ውሃና አስፈላጊ የጽዳት ዕቃዎች ተሟልተው ላለመታጠብ የሚደረግ ግብግብ፣ አካላዊ ርቀትን ሳይጠብቁ መጓዝና ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታዎች መገኘት አሁንም በስፋት የሚታዩና ተፈላጊው የባህሪ ለውጥ ያልመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው። ይህ ደግሞ እራስን፣ ቤተሰብን፣ አገርንና ወገንን ለከፍተኛ አደጋ የሚያጋልጥ አደገኛ ድርጊት ከመሆኑም በላይ የእነዚህን ጤና ባለሙያዎች ልፋት ከንቱ ማድረግም ጭምር ነው፡።

ከቻይና በመነሳት መላውን ዓለም ያዳረሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የመቶ ሺዎችን ህይወት እየቀጠፈ ልጓም ሳይገኝለት በፍጥነት መስፋፋቱንና በርካቶችን መቅሰፉን ተያይዞታል። ከተከሰተ ድፍን ዘጠኝ ወራት የሞላው የኮሮና ወረርሽኝ እስከ አሁን በመላው ዓለም ከ23 ሚሊየን በላይ ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን የሟቾችም ብዛት ከ883 ሺህ 590 ማለፉን ጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው መረጃ ያሳያል።

በኢትዮጵያም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 58 ሺህ 672 የደረሰ ሲሆን እስከ አሁን ከ1 ሚሊዮን 44 ሺህ በላይ የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑንም ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል። ወረርሽኙ በዓለም ኢኮኖሚም ሆነ በአገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድቀት እያስከተለ እንደሆነም የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ። በአገራችን የቫይረሱ ስርጭት ዕለት ዕለት ጨምሮ በአንድ ቀን ብቻ ከ1 ሺ 500 በላይ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የምናስመዘግብበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

በሌሎች አገሮች ያየነው አይነት አስደንጋጭና አሰቃቂ ችግር በሀገራችን ህዝብ ላይ እንዳይደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እርግጥ በየደረጃው ያለው የመንግስትና የጤናው ዘርፍ የተናበበ አመራርና አሰራር ሊመሰገን የሚገባው ነው። ነገር ግን ይህ ሰፊ ልፋት በመልካም ውጤት እንዲታጀብ ማድረግ የሚቻለው እያንዳንዱ ሰው ለራሱና ለሌሎች መጠንቀቅ ሲችል ነው። ስለሆነም ዛሬ የሚጠበቅብን ተግባር ከመቼውም ጊዜ በላቀ የባህሪ ለውጥ ማምጣትና አስፈላጊዎቹን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር ራስን፣ ቤተሰብን፣ ወገንንና አገርን ከዚህ ክፉ ወርርሽኝ መጠበቅ ነው። ይህን ማድረግ ስንችል የባለውለታዎቻችንን መስዋእትነትና ጥረት ፍሬያማ እናደርገዋለን።



59



60

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

የእውቀት ጠላት

ማህበረሰብ



61

የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈ የዓለማችን ኢኮኖሚ ፖለቲካና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የፈጠረ ተህዋስያን ነው፡- ኮቪድ-19፡፡ ቫይረሱ ዛሬም ጉልበቱን እያፈረጠመ የዓለም ስጋትነቱን እያጠናከረ ይገኛል፡፡ ከቻይናዋ ዉሃን ከተማ የተነሳው ኮቪድ-19 (ኮሮና) ዓለምን ከጫፍ ጫፍ አካሎ ከ800 ሺ በላይ ህይወት በመቅጠፍ አረጋውያንን ያለ ጧሪ፣ ህጻናትን ያለአሳዳጊ ያስቀረ፣ ልጅ እናት አባቱን እንዳይቀብር ወዳጅ ዘመዱን እንዳይሰናበት ያደረገ የዘመኑ መቅሰፍት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ኮሮና ስጋትነቱ ተወግዶ ዓለም ሙሉ በሙሉ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴዋ የምትመለሰው መቼ ነው ለሚለው ጥያቄ እርግጠኛ መልስ መስጠት የሚችል አካልም አልተገኘም፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) የተጽዕኖ በትሩን ካሳረፈባቸው ዘርፎች መካከል የትምህርት ዘርፍ በዋነኝነት ይጠቀሳል፡ ፡ በዚህም በዓለማችን የሚገኙ በርካታ ሀገሮች ሳይወዱ በግድ ትምህርት ቤቶች በሮቻቸውን እንዲዘጉ ተማሪዎችም ወደ ቤት እንዲሸኙ አድርገዋል፡፡ ህጻናት የሚቦርቁባቸው፣ ታዳጊዎች እውቀት የሚጨብጡባቸው፣ ዜጎች የሚቀረጹባቸው፣ የአንድን ሀገር ልማትና እድገት ከማረጋገጥ አልፎ ዓለምን የሚቀይሩ ትልልቅ ሀሳቦች የሚፈልቁባቸው የትምህርት ተቋማት ለወራት ተከርችመው ቆይተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምሕርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) መረጃ እንደሚያመለክተው ኮሮና ትምህርት ላይ ባሳደረው ተጽዕኖ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ተማሪዎች እውቀት በሚቀስሙበት ወቅት ቤታቸው ለመቀመጥ ተገደዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) መረጃ እንደሚያመለክተው በመጋቢት ወር ብቻ ከዘጠና በመቶ በላይ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ በዓለም ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ሲባል ትምህርታቸውን አቋርጠዋል፡፡ እንደመረጃው ከሆነ 188 ሀገሮች ከመዋለ ህጻናት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ያሉ የእውቀት

የእውቀት ጠላት

በታዬ ለማ



62

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

መገብያ ተቋሞቻቸውን ዘግተዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት /UNESCO/ መረጃ እንደሚያሳየው ኮቪድ- 19 መጀመሪያ በዓለም ላይ ሲከሰት በቻይና ያሉ ተማሪዎች ብቻ ነበሩ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ የተደረጉት፡፡ በወቅቱ ከትምህርት ገበታቸው የራቁት 900ሺ ተማሪዎች ብቻ ነበሩ፡፡ ይህም የዓለምን 0 ነጥብ 1 በመቶ ተማሪዎች እንደ ማለት መሆኑን የሚያመለክተው መረጃው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን በሽታው በመስፋፋቱ በርካታ ሀገሮች ትምህርት ቤቶቻቸውን ለመዝጋት መገደዳቸውን መረጃው ያትታል፡፡

ይህ ቁጥር በአንድ ወር ውስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይቶ በዓለም ላይ የሚገኙ 486 ሚሊዮን ተማሪዎች በኮቪድ- 19 ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገድደዋል፡፡ ይህም የዓለምን 28 በመቶ ተማሪዎች የሚሸፍን ሲሆን፤ በዚህም 53 ሀገሮች በችግሩ ተጠቂ መሆናቸው ያመለክታል። በመጋቢት ወር ግን የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በመስፋፋቱ 771 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ በመገደዳቸው የመቶኛ ድርሻው ወደ 44 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

ኮሮና እየተባባሰ አድማሱን በሁሉም ሀገሮች በማስፋት የመማር ማስተማር ሂደት ላይ እንቅፋት መሆኑን ቀጥሎ በሚያዝያ ወር 194 ሀገሮች ትምህርት ቤቶቻቸውን መዝጋታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት ዓለም ላይ የሚገኙ 92 በመቶ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው የዓለም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት እንዲርቁ ግድ ሆኗል ማለት ነው፡፡ አብዛኛው ሀገሮች ትምህርት ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ የዘጉ ሲሆን ጥቂት ሀገሮች ብቻ በአንዳንድ ቦታዎች ትምህርት ቤታቸውን አለመዝጋታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የትምህርት ቤቶችን መዘጋት ተከትሎ ታዲያ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ሆኗል፡፡

ኮሮና ባደረሰው ተፅዕኖ ሳቢያ ትምህርት ቤቶቻቸው ሙሉ ለሙሉ ያሳሰባቸው ሀገሮች የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን ወስደዋል፤ እየወሰዱም ይገኛሉ፡፡ ተማሪዎች ቤታቸው ሆነው በተለያየ መንገድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረግ በብዙ ሀገሮች በቀዳሚነት የተወሰደ አማራጭ ነው፡፡ ሀገሮቹ ተማሪዎች ባሉበት ሆነው ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ ስትራቴጂ ቀርጸው በተለያዩ ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ትምህርት እንዲቀጥል ሲያደርጉ ጊዜ አልወሰደባቸውም። ምንም እንኳን ውጤታማነቱ ከሀገር ሀገር የተለያየ ቢሆንም፡፡ በቴክኖሎጂ የተደገፈው የቤት ውስጥ ትምህርት በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ባለው የቴክኖሎጂ እጥረትና ተያያዥ ጉዳዮች ምክንያት ብዙም ውጤታማ እንዳይደለ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ያመለክታል።

“Impact of Coronavirus Pandemic on Educa-

tion” በሚል ርዕስ በሪሰርች ጌት የተሰራው ጥናት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳረፉን ያትታል። ምንም እንኳን ትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂ በመጠቀም ትምህርትን ለማስቀጠል ቢሞክሩም ኦንላይን ትምህርት ብዙም ውጤታማ መሆን አለመቻሉን ይገልጻል። የቴክኖሎጂው መሰረተ ልማት ደካማ መሆን፣ የኔትወርክ መቆራረጥ፣ የኃይል አቅርቦት ችግር፣ በቂ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አለመኖር፣ እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕውቀት አናሳ መሆን የሚሉት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።

ሁለት መቶ የሚጠጉ ተማሪዎች፣ መምህራንና ፖሊሲ አውጭዎች የተሳተፉበት ይህ ጥናት ኮቪድ-19 የመማር ማስተማር እንቅስቃሴን በጅጉ ማዛባቱን፣ የትምህርት ተደራሽነት እንዲቀንስ ማድረጉን፣ በተለይ በትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ የምርምር ስራዎች እንዲዳከሙ ምክንያት መሆኑን በመጥቀስ ቫይረሱ በትምህርት ዘርፍ ያደረሰው ተጽዕኖ የጎላ መሆኑን አትቷል፡፡ በተጨማሪም ልዩ ፍላጎት ያላቸውና ድጋፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ላይ ጫና ማሳደሩንም ጥናቱ ጠቁሟል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ዳይሬክተር ጀኔራል አውድሪ አዞላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱ የተማሪዎችን የመማር መብት አሳጥቷል ይላሉ። ትምህርት ቤቶች በድንገት መዘጋታቸው በተማሪዎች፣ በመምህራን፣ በተማሪዎች ወላጆችና በመላው ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ችግር ማስከተሉ እሙን ነው። ዳይሬክተር ጄኔራሉ በተለይ በተማሪዎች ውጤታማነት ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ኮሮና ቫይረስና ትምህርት ቤቶቻችን

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ኮሮና መገኘቱንና እየተስፋፋ መሄዱን ተከትሎ ከመጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ የትምህርት ዘርፍ ብዙ ህብረተሰብ የሚሳተፍበት በመሆኑ ለበሽታው በከፍተኛ መስፋፋት ምክንያት እንደሚሆን በመንግሥት በመታመኑ ከመዋዕለ ህጻናት እስከ ዩንቨርስቲ ድረስ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ተደርጓል። ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች እና 600ሺ የሚሆኑ መምህራን በትምህርት ገበታ እንዳይገኙ ሆነዋል ይላል የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ።

መንግሥት ትምህርት እንዲቋረጥ ማድረጉ በሽታውን ለመከላከል ትልቅ ድርሻ እንዳለው የብዙዎች እምነት ቢሆንም የትምህርት ቤቶች መዘጋት መደናገጥን መፍጠሩ አልቀረም፡፡ በመንግሥት ትምህርት ቤት ሁለት ልጆቻቸውን እንደሚያስተምሩ የሚናገሩት የአዲስ አበባ ነዋሪዋ ወይዘሮ አበበች አየለ ትምህርት መቋረጡን ሲሰሙ

ተጨንቀው እንደነበር በማስታወስ “ዕውቀት በመጨበጫ ጊዜያቸው ልጆቼ ቤት መቀመጣቸው ስነ ልቦናዊ ጫና ያስከትልባቸው ይሆን፤ ወደ መጥፎ ነገርስ ያመሩብኝ ይሆን’’ የሚል ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ያስታውሳሉ።

በተመሳሳይ ሁለት ልጆችን በመንግሥት ትምህርት ቤት የሚስተምሩት አቶ ሀብቴ ዘነበ በበኩላቸው መንግሥት የደንብ ልብስ (uniform) ሰጥቶ፣ ደብተር ገዝቶ፣ ምግብ እየመገበ ልጆች ጥሩ ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ እንደነበር በማስታወስ ’’ትምህርት መቋረጡ ግን ወላጆችንም ሆነ ተማሪዎችን ችግር ውስጥ የከተተ ነው’’ ይላሉ። ተማሪዎችን ከእውቀት ገበታ ከማራቅ ባለፈ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው እንዳይረጋጉና እንዲጨነቁ ማድረጉን ይጠቁማሉ።

ይሁን እንጂ መንግሥት እንደሌሎች ሀገሮች ሁሉ ተማሪዎች ባሉበት ሁኔታ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ ሲሰራ ቆይቷል፤ በመስራት ላይም ይገኛል። ተማሪዎች በተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በተለይ በገጠር የሚኖሩ ተማሪዎች ቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ትምህርት እንዲከታተሉ ማድረግ የሚያስችለውን ዕቅድ በመንደፍ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል። የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሐረገወይን ማሞ በድንገት የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በመላ ሀገሪቱ በተለይ በትምህርቱ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ መንግሥት ትምህርት በቴሌቪዥንና በሬዲዮ እንዲሁም በሌሎች ዲጂታል መንገዶች በፍጥነት እንዲጀመር በማድረጉ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ያነሳሉ።

ተማሪዎች ቤታቸው ሆነው እውቀት እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር በሀገር አቀፍ ደረጃ ትምህርት በቴሌቪዥን እንዲሁም ከክልል የመገናኛ ብዙሀን ጋር በመተባበር በኤፍኤም ሬዲዮ ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርት መሰራጨቱን ይናገራሉ። ከዚህ ባለፈ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸው በቴሌግራም ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የማድረግ ስራ መከናወናቸውን ይጠቁማሉ፡

Keeping children learning during Covid-19 የሚለው የዘሪሁን ሰውነት ጽሁፍ እንደሚያሳየው በሀገር አቀፍ ደረጃ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የርቀት ትምህርትን ለማካሄድና ትምህርቱንም ለማሳደግ ችግሮች ቢኖሩም ትምህርት ሚኒስቴርና ክልሎች በሬዲዮና በቴሌቪዥን ትምህርት እንዲቀጥል ማድረጋቸው በመልካምነት ሊወሰድ ይገባል። ይህ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ የትምህርት ፕሮግራም 5 ነጥብ 1 ሚሊዮን የግልና የመንግሥት ት/ቤቶች ተማሪዎችን ዓላማ ያደረገ መሆኑም ይጠቀሳል ።

በኢትዮጵያ ትምህርት በቴሌቪዥንና ሬዲዮ መጀመሩ ብዙዎችን እሰየው ያሰኘ ቢሆንም በርካታ ተማሪዎች ጋር የመድረሱ ጉዳይ የብዙ ትምህርት ባለሙያዎች ጥያቄ እንደነበር የዘሪሁን ሰውነት ጽሁፍ ያትታል። አብዛኛው



63

የገጠር ነዋሪ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የሌለው መሆኑን ተከትሎ ይህ ፕሮግራም ለምን ያህሉ ይደርሳል የሚለውን በመገመት አብዛኛው ተማሪ ኮሮናን ተከትሎ ከትምህርት ውጭ ሆኗል ሲሉ ምሁራን ሀሳባቸውን ያነሳሉ። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዮሐንስ በንቲ ምን ያህል የሀገሪቱ ነዋሪ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ አለው የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው የሚሉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ መብራት መቆራረጥ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ትምህርትን ለሁሉም ተማሪዎች ለማዳረስ እንቅፋት እንደሆነ ይናገራሉ።

በቴክኖሎጂም በተለይ በኢንተርኔት የሚተላለፈው ፕሮግራም ውጤታማነቱ አጠያያቂ ነው። ምን ያህል ተማሪ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው የሚል ጥያቄ ሲነሳ “ጥቂት’’ የሚል መልስ ይጠበቃል። በመሆኑም በቴክኖሎጂው ለማስተማር የተደረገው ጥረት ከዚህ አንጻር ብዙዎች ጋ ደርሷል ማለት አይቻልም ባይ ናቸው። ልጆች ቤት ሲውሉ ቁጭ ብለው ትምህርታቸውን በቴሌቪዥን ይከታተላሉ ወይ፤ እንዲከታተሉስ በማድረግ በኩል የሚቆጣጠር ወላጅ ምን ያህል ነው የሚለው በራሱ የትምህርት ተደራሽነቱ ላይ ችግር ፈጥሯል ሲሉ ሀሳባቸውን ይገልጻሉ።

የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሐረገወይን የኤሌክትሮኒክስ ትምህርቱ በማይደርስላቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ዝም ብለው እንዲቀመጡ አለመደረጉን ይናገራሉ። ተማሪዎች በእጃቸው ላይ ያለውን መማርያ መጻህፍት እንዲያነቡ የማድረግ ስራ መሰራቱን በመጠቆም። ከትምህርት ውጭ እንደሆኑ እንዳይሰማቸው ለማድረግ በአካባቢያቸው ያሉ መምህራን እንዲደግፏቸውና የተማሪዎች ሥነልቦና እንዳይጎዳ ከትምህርት ውጭ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የተለያዩ ምሁራን በመጋበዝ ድጋፍ መደረጉን ያመለክታሉ።

ቴክኖሎጂ በመጠቀም እየተሰጠ ያለው የርቀት ትምህርት ለተማሪዎች በቀጥታ የሚደርስ ቢሆንም ከገጽ ለገጽ ትምህርት ጋር ሲወዳደር ለተማሪዎች በቂ እውቀት ከመስጠት አንጻር ዝቅተኛ እንደሆነ የትምህርት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የገጽ ለገጽ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን በቀጥታ የሚገናኙበት መሆኑ ትምህርት በተሻለ ሁኔታ እንዲከናወን የማስቻል አቅም አለው። ተማሪዎች በምን ያህል ትምህርቱን እንደተገነዘቡ የማወቅ እድል የሚያስችል በመሆኑ መምህራን ተማሪዎቻቸውን በተሻለ እንዲደግፉ እድል ይሰጣል። በቴሌቪዥንና በሬዲዮ የሚሰጠው ትምህርት በአንጻሩ ይህን እድል እንደማይሰጥ የትምህርት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ደበበ ገብረጻድቅ መምህራን ተማሪዎቻቸውን በቀጥታ አለማግኝታቸው በቴሌግራም፣ በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ ትምህርት መገናኘታቸው ትምህርቱ በተፈለገው ደረጃ እንዳይሄድ ማድረጉን ይናገራሉ። ይህ በመሆኑም ተማሪዎች እንደከዚህ ቀደሙ በቂ የሆነ እውቀት እንዳያገኙ ምክንያት መሆኑን ያብራራሉ። የአቶ ደበበን ሃሳብ የሚያጠናክሩት

የኢትዮጵያ የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ “የርቀት ትምህርት ፈታኝ ነው’’ ይላሉ፡ ፡ ተማሪዎች ምን ያህል እንደተገነዘቡ ለማወቅ፣ የቤት ስራ በመስጠት የመገምገም ሁኔታ አለመኖሩ አስቸጋሪ ያደርገዋል ይላሉ።

የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ኤርሚያስ ሰለሞንም ይህንኑ ሀሳብ ይጋራል። ትምህርት በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንደሚከታተል በመጥቀስ ይህ አይነቱ የትምህርት አሰጣጥ እንደ ትምህርት ቤት ባይሆንም የተሻለ ዕውቀት እንዳገኘበት ያስረዳል። ከሚሰጠው የቴሌቪዥን ፕሮግራም በተጨማሪ ከትምህርት ቤት በቴሌግራም የሚላኩለት መረጃዎች ትምህርቱን በመከታተል ላይ መሆኑን ያስረዳል። ይህም ከቤተሰቦቹ ድጋፍ ጋር ተደምሮ መጨበጥ ያለበትን ያህል እውቀት ማግኘት እንዳስቻለው ይጠቁማል። በቴሌቪዥንም ሆነ በኢንተርኔት ትምህርት አለመከታተላቸውን ጊዜውን ዝም ብለው በመቀመጥ ማሳለፋቸውን የሚናገሩ ተማሪዎችም ጥቂት አይደሉም። የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሰለሞን ታዬ ትምህርት ከተዘጋ ጀምሮ ምንም አይነት ጥናትም ሆነ የማንበብ ነገር ሞክሮ እንደማያውቅ ያወሳል። ወላጆቹ የዕለት ጉርስ ለማግኘት የሚሯሯጡ መሆኑን ተከትሎ ስለ ትምህርቱም ጠይቀውት እንደማያወቁና አብዛኛውን ጊዜውን ከጓደኞቹ ጋር በእንቶ ፈንቶ ለማሳለፍ መገደዱን ያወሳል፡፡

የቴሌቪዥን ችግር ትምህርቷን በቴሌቪዥን ለመከታተል እንዳላስቻላት የምትናገረው የ11ኛ ክፍል ተማሪዋ ሰላም አስፋው ቤተሰቦቿም የእርሷን ትምህርት ጉዳይ ብዙም ትኩረት ሰጥተው እንደማይደግፏትና እንደማይከታተሏት በመጥቀስ ብዙውን ጊዜዋን ከትምህርት ውጭ ለማሳለፍ መገደዷን ታስረዳለች። “ነገ ትልቅ ደረጃ ለመድረስ ፍላጎት አለኝ’’ የምትለው ተማሪዋ ይህ በሽታ ጠፍቶ ወደ ትምህርት ለመመለስ ያላትን ጉጉትም ገልጻለች።

ወላጆች የልጆቻቸውን ትምህርት መከታተል ለልጆቻቸው ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና እንዳለው እሙን ነው፡፡ በተለይ ተማሪዎች ከመምህራን ጋር በቀጥታ በማይገናኙበት በዚህ ወቅት የወላጅ ክትትል ትልቅ ድርሻ እንዳለው አቶ ደበበ ይናገራሉ። “ያለ ወላጆች ክትትል የርቀት ትምህርት ውጤታማነቱ አጠያያቂ ነው’’ የሚሉት ዶክተር ዮሐንስ ደግሞ በዚህ ረገድ ያለንበት ደረጃ ብዙ የሚቀረው እንደሆነ ይናገራሉ።

በእኛ ሀገር ሁኔታ ሲታይ ወላጅ በደህናው ጊዜ እንኳን ልጁን በትምህርት በኩል ሲያግዝ ብዙም አይስተዋልም። መምህራን ስለ ልጆቻቸው ለመወያየት ወላጅን በሚጠሩበት ወቀት እንኳን ትኩረት ሰጥቶ የሚገኝ ወላጅ በጣም ጥቂት እንደሆነ ዶክተር ዮሐንስ በንቲ ይናገራሉ። ቴሌቪዥንና ሬዲዮ በቤት ውስጥ አለመኖር ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ቢያደርጋቸው እንኳን በእጃቸው ያለውን የትምህርት መሳሪያ በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ በኩል የበርካታ የብዙሀን ወላጆች ድጋፍና ክትትል ደካማ

እንደሆነ በማከል።

ወይዘሮ ዓለም አዲስ ልጆቻቸውን በትምህርት ለመከታተል ቢሞክሩም ብዙም እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡ ፡ ምንም እንኳን ኃላፊነት እንዳለባቸው ቢያውቁም በስራና በኑሮ ምክንያት ጊዜ ስለሌላቸው ልጆቻቸውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተከታተላችሁ ወይ ምንስ ዕውቀት አገኛችሁ ለማለት መቸገራቸውን ይጠቅሳሉ። ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንዲከታተሉ መናገር ብቻ በቂ እንዳልሆነና መከታተል የወላጅ ኃላፊነት እንደሆነ ቢያምኑም ብዙ ወላጆች ቤት ተቀምጠውም ይህን ያደርጋሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ይናገራሉ። በዚያው ልክ ግን ይህን የሚያደርጉ በርካታ ወላጆች መኖራቸው መዘንጋት እንደሌለበት በማንሳት።

ኮሮና ልጆቻቸውንም ሆነ እሳቸውን ቤት እንዲቀመጡ እንዳደረጋቸው ይህም ልጆቻቸው በዲጂታል የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባ መከታተላቸውን ለማረጋገጥና የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለማድረግ እድል እንደሰጣቸው የሚናገሩት ሌላው ወላጅ አቶ ተስፋዬ ዘላለም ይህ ወቅት ወላጅ ከልጆቹ ጋር በደንብ የሚተዋወቅበትና ከትምህርት ውጭ ልጆች ብዙ እውቀት የሚጨብጡበት ወቅት መሆኑን ያብራራሉ። ይህን መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ በመጠቆም ወላጆች በምንም ሁኔታ ቢሆን ለልጆቻቸው ትምህርት ጊዜያቸውንም አጣበው ቢሆን ተገቢውን እገዛ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ ሀሳባቸውን ያጋራሉ።

የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት በቴሌቪዥንም ሆነ በሬዲዮ ፕሮግራም እንዲካተት እንዳልተደረገ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በእድሜያቸው ልክ የተዘጋጀላቸው ነገር ባለመኖሩ የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች ዝም ብለው ለመቀመጥ እንደተገደዱ ይነገራል፡፡ በዚህም የተነሳ ለእድሜያቸው የማይመጥኑ እና ከባህላቸው ያፈነገጡ ፊልሞችን እንዲመለከቱ እያደረጋቸው መሆኑን የሚገልጹ ወላጆች ጥቂቶች አይደሉም :: የመዋዕለ ህጻናት ተማሪ ልጅ እንዳላቸው የሚናገሩት ወይዘሮ ገነት ዓለሙ የቴሌቪዥንም ሆነ የሬዲዮ ትምህርት ለህጻናት እየተሰጠ ባለመሆኑ ሕፃናት መሰረት በሚይዙበት ወቅት ከእውቀት እየራቁ ነው ይላሉ። የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረገወይን ማሞ በበኩላቸው ህጻናት በዚህ ወቅት ትምህርት ማግኘት ያለባቸው በመደበኛ መልክ ሳይሆን ቤታቸው ሆነው በጨዋታ መልክ እንዲማሩ እንዲነቃቁ ማድረግ የተሻለ መንገድ መሆኑን ይገልጻሉ።

በዚህ ወቅት ከምንም በላይ አካባቢያቸውን እንዲለዩና እንዲያውቁ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚጠቁሙት ወይዘሮ ሐረገወይን ከዚህ አኳያ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ጋር በመተባበር በስፋት እየተሰራ እንደሆነ ያስረዳሉ። ይህም ቢሆን ወላጆች ልጆቻቸውን በመምራትና በመከታተል ኃላፊነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በዚሁ አግባብ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አመልክተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ



64

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

እና የባህል ድርጅት/UNESCO/ የትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል አስናቀ በዚህ ሰዓት ልጆች ከአካዳሚ ትምህርት ባለፈ ባህልን፣ ወግና ሥርዓትን፣ አኗኗርን፣ ሙያን ወዘተ ከወላጆቻቸው መማር እንዳለባቸው ይጠቁማሉ። ይህ ወቅት አስቸጋሪ በመሆኑ ተማሪዎች ድብርት ውስጥ እንዳይገቡ መከታተልና መርዳት የግድ ነው ይላሉ። ወላጆች ልጆቻቸውን አድምጠው መረዳትና ማገዝ እንደሚገባቸው በማስታወስ። ችግሩን በጋራ ኃላፊነት ልንሸጋገረው እንደሚገባ አስረድተዋል።

የኮሮና ወረርሽኝ በመማር ማስተማሩ ላይ ካሳደረው ተጽዕኖ በተጨማሪ በተማሪዎች ላይ የተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ማድረሱን መረጃዎችም ያመለክታሉ። በተለይ የተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም መቋረጡ፣ የህጻናት ጥቃት መጨመሩና ያለ አቻ ጋብቻ መበራከቱ ከተጽዕኖዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ለአብነት ያህል በአዲስ አበባ ከ300 ሺ በላይ ህጻናት ትምህርት ከመቋረጡ በፊት በትምህርት ቤታቸው ምግብ እየተመገቡ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ሁኔታ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ታዲያ ይህ ምገባ መቋረጡ በቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተሰጠ ያለውን ትምህርት በአግባቡ እንዳይከታተሉ ሊያደርጋቸው ይችላል።

ከዚህም በተጨማሪ ኮሮና ለሴት ተማሪዎች ትልቅ ፈተና ይዞ መምጣቱ ይታወቃል። ሴቶች ህጻናት ትምህርት በማቋረጣቸው እንደማንኛውም ተማሪ ዕውቀት ከማጣታቸው በተጨማሪ ትምህርት አቋርጠው ቤት በመቀመጣቸው በገዛ ቤተሰባቸው ሳይቀር ለጥቃት እየተዳረጉ እንዲሁም ትምህርት አቋርጠዋል በሚል ሰበብ ለጋብቻ እየተጠየቁ እንደሆነ መረጃዎች ያመለከታሉ። ዶክተር ዮሐንስ ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ ሴቶች ለጋብቻ እየተጠየቁ ያለበት ሁኔታ መበራከቱን በማስረዳት ጫናው ሴቶች ላይ መበርታቱንም ይናገራሉ። በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች በብዛት ይታይ የነበረው ያለ ዕድሜ ጋብቻ መቀነሱ በተለያዩ ጊዜዎች ሲገለፅ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ኮሮና ቫይረስ ያለዕድሜ ጋብቻን እንዲያንሰራራ

አድርጎታል እየተባለ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ ቀደም ያለዕድሜ ጋብቻ ሊፈጸም ሲል ተማሪዎች በሚስጥር ለትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ የሚያሳውቁበት አሠራር በመቋረጡ ነው፡፡ ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ መግባቱ ተገልጾ ትምህርት ከተቋረጠ በኋላ ታዳጊዎች ለጋብቻ እየታጩ መሆኑን አስመልክቶ የአማራ ክልል ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ባወጣው መረጃ በክልሉ 243 የልጅነት ጋብቻዎች ተፈጽመዋል፡፡ ከመጋቢት እስከ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ 1 ሺ 279 ያህል ታዳጊ ሴቶች የታጩ ሲሆን ከእነዚህ የ534 ጋብቻ መቋረጡን አስታውቀዋል፡፡

በአፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ለተማሪዎች ትምህርት በመስጠት ላይ ያለው መምህር ዳንኤል ጌጥዬ የገጽ ለገጽ ትምህርት ተማሪዎች በቂ እውቀት የሚያገኙበት አስተማሪውም ተማሪዎችን በትክክል አቅማቸውን የሚለኩበት መሆኑን በማመልከት የርቀት ትምህርቱ አስተማሪው ተማሪውን በትክክል ለመከታተል የማይችልበት ሊመዝንም የማይመችበት ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ያወሳል። ተማሪዎች በቴሌቪዥን ትምህርቱን ከተከታተሉ በቂ እውቀት የሚያገኙ ቢሆንም በአግባቡ እንዲከታተሉ በማድረግ በኩል ግን የቤተሰብ ሚና የላቀ ነው ይላል።

የቴሌቪዥን ትምህርት በተለይ በከተማ የተሻለ ውጤት እንደሚኖረው ይታመናል። የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነትም ይህንኑ ያረጋግጣሉ። እርሳቸው እንደሚሉት በቴሌቪዥን የተሰራጨውን የትምህርት ፕሮግራም በርካታ ተማሪዎች ተከታትለውታል። የከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎች ትምህርቱን እንዲከታተሉ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የጥያቄ ውድድር በማካሄድ የሽልማት ፕሮግራም በማዘጋጀት ተማሪዎችን ለማነቃቃት የሄደበት ርቀት ውጤት እንዳስመዘገበ ያስረዳሉ። በአፍሪ ሄልዚ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተማሪዎች በአጭር የጽሁፍ መልዕክት በየትምህርት አይነቱ የሚጠየቁትን ጥያቄ እንዲመልሱ እየተደረገ የተለያየ የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል። በውድድሩ

አሸናፊ ለሚሆኑት የላፕቶፕ ሽልማት መበርከቱን አቶ አበበ ገልጸዋል። ልጆቻቸውን ለደገፉ ወላጆችም የዘመናዊ ቴሌቪዥን ሽልማት መበርከቱ ጥሩ መነቃቃት መፍጠሩን በመጠቆም በቀጣይም ይህ አካሄድ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በአጠቃላይ ትምህርት በኮሮና ምክንያት ከፍተኛ ቀውስ የተፈጠረበት ዘርፍ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ኮቪድ ዝግጅት ሳይደረግበት ቴክኖሎጂን በተጣጣመ መንገድ ማቆራኘት ሳይቻል የመጣ በሽታ በመሆኑ በመማር ማስተማሩ ላይ ትልቅ ችግር ፈጥሯል። ለወደፊት በትምህርት አሰራር ላይም ትልቅ የቤት ስራ ይዞ የመጣ ነው፤ ኮቪድ-19።

ቀጣይ ትምህርት እንዴት ይቀጥል?

ተማሪዎች እንዴትና መቼ ወደ መደበኛ ትምህርታቸው የሚመለሱት የሚለው የሁሉም ጥያቄ ነው። አዲስ የትምህርት ዘመን የሚጀመርበት የመስከረም ወር መምጣቱን ተከትሎ ደግሞ ጥያቄው እየበረታ ይገኛል። በሽታው ከኢትዮጵያ ካልጠፋ የተማሪዎች እጣ ፈንታ ምንድነው የሚለው ወላጅንም ሆነ ተማሪውን እያስጨነቀ ይገኛል። መንግሥትም በቀጣይ ዓመት ትምህርት እንዴት ይጀመር ፤ ተማሪዎች እንዴት ወደ ትምህርት ይመለሱ የሚለውን በትኩረት እየሰራበት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል። በሽታው ሙሉ ለሙሉ ከሀገሪቱ ካልጠፋም እንደ ሌሎች ሀገሮች ትምህርትን በተለያየ መንገድና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ጠቁመዋል። የሌሎች ሀገሮችን ተሞክሮ በመቅሰምና የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብን በማየት ትምህርት ቤቶችን በቀጣይ ለመክፈት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ያብራራሉ።

በአሁኑ ወቅት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ደረጃ ስርጭቱ እየጨመረ ቢሆንም በሽታው ቀንሷል የሚሉ ሀገሮች ትምህርት ቤቶቻቸውን በመክፈት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ



65

ሀገሮችም ትምህርት ቤትን በተለያየ መንገድ ለመክፈት በሂደት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ትምህርት ቤት ሲከፈት መሟላት ያለባቸውን መሰረታዊ ነገሮች በማለት ካስቀመጣቸው መስፈርቶች መካከል በዋነኝነት ትምህርት ቤት በሚከፈትበት ቦታ በኮቪድ-19 ያለው ተጠቂነትና አከባቢው ከቫይረሱ ምን ያክል የጸዳ እንደሆነ ታሳቢ መደረግ እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት ተቋማቱ ኮቪድ- 19ን ለመከላከል ያላቸው አቅምና ዝግጁነት ታሳቢ መድረግ እንደሚገባው ምክረ ሀሳብ ያስቀምጣል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶችን የመክፈት እና ያለመክፈት ጉዳይ ከበሽታው ስርጭት መቀነስ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ በመጥቀስ ቀጣይ የትምህርት አቅጣጫን በተመለከተ ከጤና ሚኒስቴር በሚገኝ ምክረ ሀሳብ ታሳቢ በማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተናግረዋል። ብዙ ሀገሮች የበሽታው የስርጭት መጠን ሲቀንስ ትምህርት ቤቶች እንደከፈቱ የሚታይ ሲሆን በኢትዮጵያም የበሽታው መጠን መቀነስ ለትምህርት ቤቶች መከፈት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ ቀነሰ ብለው ትምህርት የጀመሩ ሀገሮች ትምህርት ከፍተው ተማሪዎቻቸውን ቢልኩም ኮሮና ዳግም አገርሽቶ በርካታ ሀገሮች ደግመው ትምህርት ሲዘጉ ታይተዋል።

ደቡብ አፍሪካ እና ደቡብ ኮርያን የመሳሰሉ ሀገሮች ትምህርት ቤቶቻውን ከፍተው ዳግም ለመዝጋት ሲገደዱ ተስተውለዋል፡፡ ትምህርት ቤትን ለመክፈት ቅድመ ጥንቃቄዎች የሚያስፈልጉ ሲሆን፤ በተለይ በአንድ ክፍል ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የተማሪዎች ቁጥር ታሳቢ መደረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ ያስረዳሉ። ሌሎች ሀገሮች ትምህርት ቤት ሲከፍቱ ያደረጉት ነገር የተማሪዎች ቁጥርን መቀነስና በአንድ ክፍል ውስጥ ጥቂት ተማሪዎች እንዲገኙ በማድረግ ነው። ይህ በኛ አገር ተግባራዊ ለማድረግ በጣም

አስቸጋሪ እንደሚሆን መረጃዎች ያሳያሉ። ምክንያቱም ባደጉት ሀገሮች አንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር ከኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር የሚመጣን አይደለም። በዚህ መንገድ ትምህርት ቤቶችን መክፈት አስቸጋሪ እንደሆነ የሚያምነው የትምህርት ሚኒስተር ችግሩን በመገንዘብ በቀጣይ ከትምህርት ቤቶች በተጨማሪ ሌሎች የተለያዩ የግል ቤቶችን ሳይቀር በመጠቀም የተማሪዎችን ጥግግት በመቀነሰ ትምህርት ለማስጀመር ማቀዱን ያመለክታል።

በሌሎች ሀገሮች የኮሮናን ስርጭት ለመቀነስ ትምህርትን በፈረቃ በማድረግ ትምህርት የጀመሩ ሀገሮች እንደለ መረጃዎች ያመለክታሉ።ኢትዮጵያም ከእነዚህ ሀገሮች መማር እንደምትችል የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በአርግጥ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በኢትዮጵያም በፈረቃ ታሳቢ ያደረገ የጠዋትና ማታ ትምህርትን የማድረግ እድሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያሳያል። እንደ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ገለጻ ትምህርት ቤት ሲከፈት በሽታውን ለመከላከል ይቻል ዘንድ መከላከያው ላይ ትኩረት መደረግ አለበት።

ትምህርት ቤት ሲከፈት የሙቀት መጠን መለካት፤ የእጅ ንጽህና መስጫ፣ ማስክ መሸፈን የመሳሰሉ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮሮና ለመከላከል ከሚሰሩት የምርምር ስራ በተጨማሪ ወቅት የለይቶ ማቆያ ሆነው በሽታውን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ከፍተኛውን ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተገኘ መረጃ ያሳያል፡፡ እነዚህን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስከፈት ታዲያ ተቋማቱን ከቫይረሱ ንጹ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ ቅድሚያ መሰራት እንዳለበት የትምህርት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ትምህርት ለመጀመር እንደዚህ ቀደሙ ቀላል እንደማይሆን ይገመታል፡፡ በተለይ በሽታው

ሙሉ ለሙሉ ካልጠፋ ቀላል እንደማይሆን የትምህርት ባለሙያዎች አሳብ ነው። ወረርሽኙ ቀንሶ ትምህርት ለማስጀመር ከተፈለገ ከፍተኛ በጀት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ዩሀንስ በንቲ ይናገራሉ። በተለይ በሽታው ንጽህና የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ውሃ እንዲኖራቸው ማድረግ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

ከዚህም በተጨማሪ የበሽታወን መከላከያ መሳሪያዎች በየትምህርት ቤቱ በከፍተኛ ሁኔታ ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር መንግስት ከፍተኛ በጀት መመደብ እንዳለበት ያመለክታሉ።ታዲያ በጀትን በተመለከተ ተጨማሪ በጀት እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስተርም እምነት ሲሆን በአጠቃላይ ለዋና ዋና ተግባራት ምን ያህል በጀት እንደሚያስፈልጉ ለይቻለው ይላል። በአብዛኛው በመደበኛ በጀትና አደረጃጀት ስራዎች የሚሰራ ቢሆንም ተጨማሪ በጀት እንደሚፈለግ ታሳቢ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

በአጠቃላይ ኮሮና በቀጣይ ዓመት ስርጭቱን ቀንሶ ትምህርት እንዲጀምር ተማሪዎች በትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርታቸውን እንዲማሩ የሁሉም ፍላጎት ነው። ለዚህ ግን ዋነኛው እንደ ጤና ሚኒስተር መረጃ የኮሮና ሥርጭት መቀነስ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው። ታዲያ ትምህርት እንዲቀጥል ወላጅ ልጁ ቤት መቀመጡ እንዳስጨነቀው ሁሉ ጥንቃቄውን በማጠናከር በሽታው እንዲቀንስ የበኩሉን ሚና በመጫወት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። ይህ ግን የወላጅ ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የሁሉም የማህበረሰብ ስለሆነ የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት በጋራ መረባረብ አለብን። ያኔ ልጆች ታዳጊዎች እንደ ከዚህ ቀደሞ ወደ ትምህርት ቤት ልከን እንደ ልባቸው እንዲቦርቁ እውቀት እንዲጨብጡ ማድረግ ይቻላል። ወላጅም ከጭንቀቱ ይገላገላል ሀገርም የነገ ሀገር ተረካቢዎችን ታገኛለች።



66

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

የሽግግሩ ምሰሶዎች

ኢኮኖሚ



67

በፍቅርተ ባልቻ እና በአንዱንሰው ሺፈራው

የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ለአገልግሎት የማዋል እንቅስቃሴ በተለያዩ የዕድገት ምዕራፎች (generations) ውስጥ አልፏል። በዓለማችን የመጀመሪያውን ኢንዱስትሪ ፓርክ እ.ኤ.አ በ1896 የገነባችው ብሪታንያ ነበረች። በሌላዋ አውሮፓዊት ሀገር ጀርመን ታሪኩ የጀመረው እ.ኤ.አ በ1963 ነው። የዕድገት ምዕራፉ ወደ የእስያ አህጉር ተሸጋግሯል። በዚህም የእስያ ሀገሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮች አማካኝነት ፈጣንና ተከታታይነት ያለው ዕድገት ማስመዝገብ ችለዋል።

የኮሪያው የኢንዱስትሪ መንደር እ.ኤ.አ. በ1970 ሲመሰረት ዓላማ አድርጎ የተነሳው የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ የአምራች (manufacturing) መስኩን እንቅስቃሴ ማገዝ ነበር። ማሌዥያ የመጀመሪያ የኢንዱስትሪ መንደሯን የከፈተችው እ.ኤ.አ በ1972 ሲሆን፤ በኢንዱስትሪ መንደሯ የተሰባሰቡ የአምራች ኩባኒያዎች አሃዝም በ1995 ከአራት መቶ በላይ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሞሪሺየስ ደግሞ እ.ኤ.አ ከ1980ዎቹ መገባደጃ እስከ 90ዎቹ አጋማሽ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 600 የሚጠጉ ኩባንያዎች ወደ ስራ ገብተዋል። በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ ተጀምሮ በ1970 የኢንዱስትሪ መንደሮች መስፋፋታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገሮች እስከ 1990ዎቹ ድረስ የኢንዱስትሪ መንደሮችን መመስረት አልጀመሩም። ከአፍሪካ ላይቤሪያ እ.ኤ.አ በ1970፣ ሴኔጋል በ1974 የኢንዱስትሪ መንደሮችን ለማቋቋም ዕቅዶቻቸውን ይፋ አድርገው ወደ እንቅስቃሴ ከገቡት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

ቻይና ዝግ የነበረውን ፖሊሲዋን በመለወጥ ኢኮኖሚዋ ገበያ ተኮር እንዲሆን ማሻሻያ ማድረጓን ተከትሎ በልማት ቀጠናዎች አማካኝነት የውጭ ባለሃብቶችንና ቴክኖሎጂን ለማስገባት፣ የውጭ ንግድን ለማስፋፋት፣ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ስትራቴጂ ነድፋ ተግብራለች። ባለሃብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ በተዘጋጁት አበረታች ህጎችና ግልፅ አሰራሮች



68

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም

የተደገፈው ስትራቴጂ በኢኮኖሚያዋ ላይ አመርቂ ውጤት ማስገኘት የቻለው ፈጥኖ ነው። ከሀገሪቱ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 60 በመቶ ያህሉ እ.ኤ.አ በ1981 የተገኘው በተመረጡት የልማት ቀጠናዎች ሲሆን፤ ከአራት ዓመት በኋላ ወደ 1 ነጥብ 17 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አድጓል። የስትራቴጂውን ውጤታማነት ያረጋገጡት ቻይናውያን የልማት ቀጠናዎችን በመላው ሀገሪቱ ማስፋፋታቸው አሁን ለደረሱበት ዕድገት መሰረት ሆኗቸዋል። ቻይና የኢንዱስትሪ መንደሮችን በሀገር ውስጥ ለማስፋፋት ከምታደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎች ሀገሮች ጋር በጋራ እየሰራች ነው።

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማቋቋም ለምን?

በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት የተጀመረው በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት ነው። በደርግ ወቅትም በተወሰነ ደረጃ የነበረ ቢሆንም፤ ተገቢ ፖሊሲ፣ ልዩ ትኩረትና ክትትል ባለመኖሩ ሳቢያ የሀገር ውስጥ ባለሃብት እንቅስቃሴም ሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሊያድግ አልቻለም።

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 43 የሀገሪቱ ዜጎች ኑሯቸውን የማሻሻልና ዕድገት የማግኘት መብት እንዳላቸው፤ የልማት እንቅስቃሴዎች ዋና ዓላማ የዜጎችን ዕድገትና መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል። ይህን ህግጋት መሰረት በማድረግ በሀገሪቱ ከ1984 ዓ.ም በኋላ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ። የመጀመሪያው የኢንቨስትመንት አዋጅ በ1984 ዓ.ም ወጥቶ ስራ ላይ ዋለ። ይህን ተከትሎ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው፤ በመንግሥት ልዩ ድጋፍ ተደርጎላቸው በተለያዩ የልማት መስኮች መሰማራት ጀመሩ። የኢንዱስትሪ ዞኖችንና መንደሮችን አቋቁመው ወደ ስራ ከገቡት መካከል ኢስተርን ኢንዱስትሪያል ዞን (ዱከም)፣ ኢትዮ-ቱርክ አይዜድ (ሰንዳፋ)፣ አይካ አዲስ፣ ሁጂአን፣ ጆርጅ ሹ የኢንዱስትሪ ዞኖች ተጠቃሾች ናቸው።

መንግሥት መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ሥርዓት ለመሸጋገር ብርቱ ጥረት እያደረገ ነው። ምጣኔ ሀብታዊ ሽግግሩ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ የሚያስችል፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋመት ጋር ትስስር የሚፈጥር፣ የግብርና ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት የሚጠቀምና እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ገቢን የሚያስገኝ ነው።በመሆኑም የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በአዋጅ የተቋቋመ። የኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት፣ በማስተዳደርና በሊዝ በማከራየት ወይም ለተወሰኑ ዓመታት በሽያጭ ማስተላለፍ የሀገሪቱን ዕድገት ማፋጠን ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያዩ ሀገሮች የተለያየ ስያሜ ቢኖረውም ፅንሰ ሀሳቡ ግን ተመሳሳይ ነው። የኢንዱስትሪ

ፓርክ በተመረጠና ለኢንዱስትሪ ልማት ምቹ እንደሆነ ታስቦ በተከለለ አካባቢ ኢንዱስትሪዎች የሚቋቋሙበትና ለዘርፉ ማደግና መጎልበት ድጋፍ የሚሰጥበት አሰራር ነው። በኢንዱስትሪ ፓርኮች አዋጅ ቁጥር 886/2007 እንደተደነገገው የኢንዱስትሪ ፓርክ እንደ መንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል፣ ውሃና ስልክ የመሳሰሉ የመሰረተ ልማት አውታሮችና የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች የተሟሉለትና ልዩ የማበረታቻ ድጋፍ እየተደረገለት ኢንዱስትሪዎችን ለማልማት በተመረጡ የልማት ኮሪደሮች የሚቋቋም ነው። እንዲሁም ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናን፣ የቴክኖሎጂ ፓርክን፣ የወጭ ንግድን፣ የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያን (agro processing)፣ ነፃ የንግድ ቀጠናዎችን አካቶ የያዘ ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሏቸው።ከጠቀሜታዎቻቸው መካከል ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር በማሰባሰብ ምርታማነትን ማሳደግ፣ ለባለሀብቶች ፈጣን አገልግሎት መስጠት፣ የአካባቢ ብክለትን ማስወገድ፣ ሰፊ የስራ ዕድል መፍጠር፣ ከተሞችን በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር በመፍጠር የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ተጠቃሾች ናቸው። የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ የወጭ ንግድን በማበረታት በገቢ ምርቶችን መተካትና ማህበራዊ ዕድገት የፓርኮቹ ትሩፋቶች ናቸው። እንዲሁም ፈጠራን ለማስፋፋት፣ በተመሳሳይ የስራ መስኮች የተሰማሩ ተቋማት መካከል ጤናማ የውድድር ባህል እንዲኖርና የመማር ማስተማር ሂደቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማቆራኘት ያላቸው ፋይዳ የላቀ ነው።

ኢንዱስትሪዎች በአንድ አካባቢ ተሰባስበው መገንባታቸው የአንዳቸው ምርት ለሌላው በግብዓትነት ስለሚያገለግል እርስ በርስ በመቀባበል እሴት ጨምረው ለገበያ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል።የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ተጠቅመው ተረፈ ምርቶችንና ፍሳሾችን መልሰው ጥቅም ላይ ስለሚያውሉ የአካባቢና የአየር ብክለትን ለመከላከል ብሎም የውሃ እጥረት ለማስወገድ ያግዛል። በአጠቃላይ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባሻገር የማህበረሰብ ዕድገት፣ የከተሞች መስፋፋትና ልማት የሚታይበት ዘርፍ በመሆኑ በመጀመሪያውና በሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ትኩረት አግኝቷል።

የለውጥ እርሾ … የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተለያየ ስያሜ እየተሰጣቸው በተለያዩ ሀገሮች የተስፋፉት እ.ኤ.አ በ1970ዎቹ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ዘርፉን ለማልማት ወደ እንቅስቃሴ የተገባው ከሃምሳ ዓመት በላይ ዘግይቶ ነው። ኢትዮጵያን በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ ማድረግ የሚያስችሉ፣ ራዕይ የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ዕቅዶች ተነድፈዋል። ቅድሚያ የተሰጣቸውም የግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ (agro processing)፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የኬሜካልና የመድሐኒት፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ መስኮች ናቸው። መንግሥት የዘርፉ ዕድገት ለማሳለጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባት የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ በማመን ወደ ተግባር መግባቱን ተከትሎ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሀገሪቱ እየተስፋፉ ነው።

በመንግሥትና በባለሃብቶች ትብብር በሀገሪቱ 30 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ታቅዶ የአስራ ሁለቱ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ትግበራ መሸጋገራቸውን የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ ይገልጻሉ። መንግሥት በተመረጡ የልማት ኮሪደሮች የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባትና የመሰረተ ልማት አውታሮችን በማሟላት፤ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሳተፉ፣ ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡና የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ ግልፅ የሆነ አሰራር ዘርግቶ ተገቢውን ድጋፍ እያደረገና እያበረታታ ነው።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረቻ ሼዶችን ገንብቶ የውጭና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሳተፉም እየሰራም ነው። በፓርኮቹ የተገነቡ ሼዶች 11ሺህ፣ 5ሺህ 500 እና 3ሺ ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ናቸው። 3ሺ ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ታስበው የተገነቡ ናቸው። የፓርኮቹ መገንባት በሀገሪቱ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚሳተፉ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን ጭምር በመሳብ የውጭ ባላሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲመጣ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል። በዘርፉ የተሰማሩ የእስያ፣ የአውሮፓና የአሜሪካ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን ለዓለም ገበያ እያቀረቡ የሀገራችንን በማስተዋወቅ መልካም ገጽታዋን በመገንባት ረገድ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።

የፓርኮቹ ተግዳሮቶች አንድ የኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት ከተማ ከመገንባት አይተናነስም። የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገነቡት የሕዝብ ብዛትን፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን፣ የአካባቢን መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥን፣ በተለይም የባቡር መስመርንና የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎት አቅርቦትን መሰረት አድርገው ነው። ስለዚህ ከፍተኛ መዋለ ንዋይን ይጠይቃሉ። ይህን ቅድመ ሁኔታ በተጨባጭ አሟልቶ ፓርኮቹን የማልማቱ ሥራ ግን ቀላል አይደለም። የመሰረተ ልማት በበቂ ደረጃ አለመሟላት፣ አስተማማኝ ገበያ አለመኖር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ የቋንቋና የባህል ልዩነት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዕድገት የሚጎትቱ አበይት ተግዳሮቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያመላክታሉ።

“ኢንዱስትሪ ፓርኮች በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተሰናዳው ሰነድ ዘርፉ ለኢትዮጵያ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙት እንደሆነ ያብራራል። በዘርፉ የዳበረ ልምድ አለመኖሩ፣ የመሰረተ ልማት በተለይም የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝ አለመሆን፣ ጉዳዩ በሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ቀልጣፋ አለመሆንና ለልማቱ የሚውል በቂ የገንዘብ አቅም አለመፈጠሩ የዘርፉ አበይት ማነቆዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ምርምር ኢንስቲትዩት ጥናት እንዳረጋገጠው ለፋብሪካዎቹ መረጃ ሳይደርሳቸው ተደጋጋሚ የሚከሰተው የኃይል መቆራረጥ በአንድ በኩል በርካታ ስራ ላይ መዋል ያለባቸው ሰዓቶች እያባከነ፣ በሌላ በኩል በውድ



69

ዋጋ ከውጪ በሚገቡ ማሽኖች ላይ ጭምር ጉዳት እያደረሰ በመሆኑን ነው።

ለጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪው በግብዓትነት የሚያገለግሉ ከ50 እስከ 60 በመቶ ጥሬ ዕቃዎች ከውጭ ሀገር እንደሚመጡ የዓለም ባንክ መረጃ ያመለክታል። ለፋብሪካዎች በቂ ግብዓት በተፈለገው ጊዜ እየቀረበ እንዳልሆነ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ይገልጻሉ። የዚህ ተግዳሮት መንስኤም ከውጭ ከሚገባው ጋር እኩል ጥራት ያለው ተወዳዳሪ የሆነ ግብዓት በሀገር ውስጥ እያለ የመጠቀም ዝንባሌ አለመኖሩ ነው ሲሉም ያክላሉ።

በርካታ ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለውጭ ገበያ እንዳያቀርቡ በገበያው ሰንሰለት ላይ በርካታ ደላሎች መኖራቸው የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው። ዘርፉ የሚጠይቀው መዋለ ንዋይ ከፍተኛ ከመሆኑና ውጤቱም ፈጥኖ የሚታይ ካለመሆኑ ጋር በተያያዘ በዘርፉ የሚሳተፉ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ቁጥር አነስተኛ እንደሆነም ይጠቅሳሉ።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች ቁጥር በየጊዜው እያደገ ቢመጣም ከክፍያና ከሰራተኛ አያያዝ ጋር የሚያያዙ ችግሮች እንዳሉ ይነሳል። በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሰሩ ሰራተኞች ክፍያ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ መሆኑን ሴንትራል ኦፍ ኒውዮርክ ዩንቨርስቲ እ.ኤ.አ በ2019 ያወጣው መረጃ ጠቁሟል። የዓለም ባንክ መረጃም በኢትዮጵያ ያለው ክፍያ በቻይና እና በሕንድ ካለው ዝቅተኛ ክፍያ በታች መሆኑን ያመለክታል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማልማት፣ የማስተዳደርና ምርቶቻቸውን ለገበያ እስኪያቀርቡ ድረስ ያለው ሂደት የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ ነው። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን 55 ያህል ባለድርሻ አካላት ለይቶ አብሮ ለመስራት ጥረት እያደረገ ቢሆንም፤ ወደ ስራ አስገብቶ ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነበት ነው የሚገልጸው።

መሰናክሎቹን ለመሻገር ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶች ተቋዳሽ ለመሆን ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ ምርትን ለገበያ እስከ ማቅረብ ያለውን ውጣ ውረድ ለመሻገር የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎችን መተግበር ይጠይቃል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች የመሰረተ ልማት አውታሮችን ማሟላት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። በተለይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግርን ለማስወገድ ፓርኮቹ ከዋና የኃይል ማመንጫዎች ጋራ እንዲገናኙ ማድረግ ይገባል። እንዲሁም ከፀሐይ ብርሃን የሚገኝ ኃይልን (solar energy) እንዲጠቀሙ መደገፍና ማበረታታት ያስፈልጋል። ለኢንዱስትሪዎች የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችን ከውጭ ሀገር ከማስመጣት ይልቅ የሀገር ውስጥ ግብዓቶችን እንዲጠቀሙ አቅራቢ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ማገዝ ይገባል። የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሳተፉ በቅንጅት መስራት፣ መደገፍና ማበረታታት የግድ ይላል።

ባለሃብቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ሠራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ተከራይተው ሥራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ በመቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል።

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ ለሰራተኞቹ የመኖሪያ ቤት አገልግሎት በማቅረቡ የሰራተኞችን ፍልሰት በ85 በመቶ መቀነስ ችሏል። በአዳማና ድሬድዋም ባለሃብቶች መኖሪያ ቤት ገንብተዋል።ይህን ጥረት በሁሉም አካባቢ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማግኘት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር አስተሳስሮ መስራት ያስፈልጋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር በማድረግ ዜጎች ከአካባቢያቸው ሳይርቁ የስራ ዕድል እንዲያገኙ ባለሃብቶች፣ የፖርኮቹ አመራሮች ከአካባቢው የመንግሥት መዋቅር ጋር በቅንጅት በመስራት የዘርፉን መሰናክሎች ማለፍ የግድ ይላል።

እንደማጠቃለያ በዓለማችን ቻይናን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ስኬታማ መሆን የቻሉት ሀገሮች የፓርኮቻቸውን ልማት ከአጠቃላይ ሀገራዊ ዕድገታቸው ስትራቴጂ ጋር አቆራኝተው መስራት በመቻላቸው ነው።ሀገራዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተለየ ተቋማዊ አደረጃጀትን ይጠይቃል። የቻይናም ተሞክሮ የሚያሳየው ይሄንኑ እውነታ ነው። ስለሆነም ሀገራዊ ስትራቴጂውን ግልፅ ማድረግና የጋር መግባባት መፍጠር ይገባል። ሌላው ከዓለም ሀገሮች በተለይም ከቻይና የሚወሰደው መሰረታዊ ተሞክሮ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ስኬታማ ለማድረግ በፓለቲካና በመንግሥት አመራሮች ዘንድ ቁርጠኛ አቋም መያዙን ነው። የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማልማት ሂደት እያንዳንዱ የኢንዱስትሪ ፓርክ ከሌላው የሚለይበትን መሰረታዊ ባህርይ ተረድቶ ከመነሻው ጀምሮ ግልፅ የሆኑ ስትራቴጂዎችን መከተል እንደሚገባ ነው።ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለይቶና የመከላከያ ስልቶችን ቀይሶ መስራት እንደሚገባ ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያና ከሲንጋፖር መማር ይቻላል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ባለሃብቶች የአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ምልልሶችን መቀነስ መቻላቸው፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመሩባቸው ግልፅ ስትራቴጂዎች ነድፈው በቅንጅት መስራታቸው፣ የመንግሥት ማበረታቻ ማግኘታቸው፣ ከፖለቲካ ተጽዕኖ ነፃ መሆናቸው፣ ምርታማነትን የሚያሳድጉ አሰራሮችን መተግበራቸው ወዘተ. በዓለም ላይ ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለውጤት ካበቋቸው ጉዳዮች መካከል በጉልህ የሚነሱ እንደሆኑ “የኢንዱስትሪ ፓርኮች መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች” በሚል ርዕስ የተካሄደው ጥናት ውጤት አመልክቷል። የጥናቱ ግኝት የሚያስረዳው ተቋማዊ አሰራርን በማሻሻል፣ አላስፈላጊ ምልልሶችን በማስወገድ፣ ባንኮችን በማዘመንና የሁሉንም አቅም በማጠናከር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እንደሚገባ ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማልማትና የማሳደግ ሥራ የሁሉንም ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር እያደረገች ላለችው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት ዋነኞቹ ምሰሶዎች የኢንዱስትሪ ፓርኮች ናቸው። ስለሆነም የነገዋን ኢትዮጵያ የተሻለች በማድረጉ ሂደት ሁላችንም በባለቤትነት ስሜት ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን ይጠበቅብናል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮችን

በማልማት ሂደት እያንዳንዱ

የኢንዱስትሪ ፓርክ ከሌላው

የሚለይበትን መሰረታዊ

ባህርይ ተረድቶ ከመነሻው

ጀምሮ ግልፅ የሆኑ

ስትራቴጂዎችን መከተል

ይገባል። ሊያጋጥሙ

የሚችሉ ችግሮችን

አስቀድሞ ለይቶና

የመከላከያ ስልቶችን ቀይሶ

መስራት እንደሚገባም

ከቻይና፣ ከደቡብ ኮሪያና

ከሲንጋፖር መማር ይቻላል።



70

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም



71



72

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 14 መስከረም 2013 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም