ነጋሪ 19
ይጫኑ

1

ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም ዋጋ 15 ብር



2

3 2 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ



3

5 4 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11 +251-11-56-39-31

+251-11-56-52-21

ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09 enanegari@gmail.comበኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት

ማውጫ

መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች

ዋና አዘጋጅ አብዱራህማን ናስር

ም/ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሰናይ

ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ

አዘጋጅ አየለ ያረጋል

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com

ፎቶግራፍ በሀይሉ አስፋው

እርምት ባለሙያ ትዝታ ሁሴን

እነሆ!

ኢትዮጵያ ሁሌም አሸናፊ ናት። በዘመናት ውስጥ በአሸናፊነት ደምቃ ወጥታለች።

ኢትዮጵያዊያን በአንድነታቸው ፀንተው፤ በህብር ተመው አሸንፈዋል። የትናንትናው ትውልድ የአሸናፊነት ችቦን ለዛሬው አስረክቧል። የዛሬ ትውልድም በጋለ መንፈስና ንቃት በጠንካራ ክንዱ ታሪኩን ደግሟል። በደም የተጻፈው ታሪክ ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ የአሸናፊ ምድር መሆኗን አሳይቷል። ለዚህም ነው “የአሸናፊዎች ምድር - ኢትዮጵያ” የሚለውን ሀሳብ የመረጥነው። በዚህ ርዕስ ስር ዘመናትን መሻገር አላስፈለገንም። አሸናፊነት በቅርባችን ተመዝግቧል። እርሱን አይተናል።

ለውጥ ለማምጣት የተደረገውና ወጣቶች ከአሸባሪው ህወሃት ጋር ያደረጉት ትንቅንቅ በአሸናፊነት መወጣትን፣ “ከእኔ በላይ ማንም ሊኖር አይችልም” ያለውን የትዕቢት ሃይል በሀሳብ ልዕልና ድል መንሳትን በማንጸባረቅ ብቻ የአሸናፊነት ጥበብን ማሳያ አድርገነዋል። ቀጣይ የአሸናፊነት ክንድ በመልሶ ግንባታ፣ ህዝብን መልሶ በማቋቋምና ማህበረሰባዊ መዋቅር በማጠናከር መገለጥና ለውጡን ማስቀጠል ነው።

ነጋሪ እነሆ! ካለችው ጽሁፎች መካከል ቀጣዩ የዓለም ታላቅ ተግዳሮት የሆነውን የመረጃ መረብ (ሳይበር) ጥቃትን የዳሰሰው ይገኝበታል። ጽሁፉ ከመረጃ መረብ ጥቃት ለመዳንና ከአደጋ ራስን ለመከላከል ዝግጁ የመሆን ጉዳይ ለነገ መተው እንደሌለበት አመላክቷል። ጥቃቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳደረውን ስጋት፣ እያስከተለ ያለውን ጉዳት መረጃ በማጣቀስ እንዲቀርብ ተደርጓል። በዚህ ዘመን የመረጃ መረብ ጥቃት እጅግ አሳሳቢ ለምን ሆነ? የዓለም ህዝቦችን፣ ተቋማትን በምን ያህል ደረጃ ጉዳት ያደርስባቸዋል? የሚለውን ጥያቄ በማንሳት “የዓለማችን ቀጣይ የሃያላን የጦር አውድማ” በሚል ርዕስ ሥር ምላሽ ፈልገንበታል።

ሌላው ርዕሰ ጉዳይ ኪነት ናት። ኢትዮጵያዊያን በዘመናት ውስጥ ኪነትን ለጥበብ ብቻ አልተጠቀሙም። የህዝባቸውን ወኔ በመቀስቀስ ጠላታቸውን ድል ለመንሳት ዋነኛ መሳሪያ አድርገዋታል። የታሪክ ድርሳናት ሲፈተሹ ጠላት ድል ሲነሳ የጥበብ ሰዎች ከፊትና ከኋላ ይገኛሉ። “ኪነት በዘመናት ውስጥ ምን ሰራች?” ለሚለው ጥያቄያችን መልስ ፈልገንበታል። በኢትዮጵያ ምድር ያረፈን ጠላት ድል ለመንሳትና አሳፍሮ ለመመለስ ማንም ወደ ኋላ እንደማይል መዘከሪያም ነው ኪነት። “ኪነት በዘመናት መካከል” በሚል ጠበብት፣ የኪነት ባለሙያ ከዳር እስከ ዳር በመዝለቅ ታላቅ ነገር መስራታቸውን ለማሳየት ርዕሰ ጉዳዩን መርጠነዋል።

በዚህ ዕትም እንደተለመደው ከኢዜአ ጋር በትብብር የሚያዘጋጁ ተቋማትም ሀሳባቸውን አጋርተዋል። በግብርናው ዘርፍ ያልተጠቀምንበትን አቅም የምንገለገልበትን መስመር አሳይተውናል። የወጣቶች መደራጀት ዋና ጉዳይ መሆኑንም አመላክተውናል። መልካም ነጥቦች ተነስተዋል።

እነሆ! ነጋሪ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመያዝ ወደ እናንተ እጅ ደርሳለች።

መልዕክት

የዓለማችን ቀጣይ የጦር አውድማ! 6

የአፍሪካ ቀንድና የኃያላኑ ፍትጊያ 39

ለምግብ ዋስትና የኢንቨስትመንት አማራጮቻችን

44

ኪነት በዘመናት መካከል!

53

አገር አቀፍ የወጣቶች ምክር ቤት መቋቋም

63

ወባን ታሪክ ለማድረግ… 66

ጨቅላ ሕፃናት ለመታደግ 70

የብልጽግናችን አስኳል

13

የአሸናፊዎች ምድር - ኢትዮጵያ! 28

የሀሰት ትርክት ቸርቻሪዎች

21



4

7 6 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ፣ ዛሬና ነገ…

በአለምሸት ተሾመ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ

ግንኙነት ዳይሬክተር

በኢትዮጵያ አንጋፋ ከሆኑት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በ509 ከ.ሜ. ርቀት በሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች መካከል ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያን ትምህርት በተለይ የግብርናን ዘርፍ ለማዘመን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በነበራቸው ፍላጎት በ1942 የዛሬው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው “የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የእርሻና መካኒክ ጥበባት ኮሌጅ”ን ለማቋቋም መሠረት የሆነው ሀሳብ በንጉሰ ነግስቱ ቀረበ፡፡ በወቅቱ ንጉሱ የኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሄነሪ ቤኔትን ባገኙበት አጋጣሚ ከአሜሪካ መንግስት ጋር በነበራቸው “ፖይንት ፎር” የተባለ የትብብር ስምምነት መሰረት የምርምርና የቴክኒክ ድጋፍ እንዲደረግላቸውና የትምህርት ተቋሙም እንዲቋቋም ጥያቄ አቀረቡ፡፡

በኢትዮጵያና አሜሪካ መንግስት በሚያዝያ 1944 ዓ.ም. የትብብር ሰነድ ተፈረመ። በዚሁ መሠረት የአገራችንን ፍላጎት የሚያጠና የግብርና ባለሙያዎች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የግብርና ቴክኒክን የሚያስተምር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመስከረም 1945 (አሁን የጅማ ዩኒቨርስቲ) በጅማ እንዲመሰረት ተደረገ። ይህትምህርት ቤት በተግባር የተደገፈ የግብርና ትምህርት በመስጠት ለኮሌጅ የማዘጋጀት ዓላማ አንግቦ ነበር የተመሰረተው። በየካቲት 1945 ዓ.ም. ደግሞ የግብርና ኮሌጁ የሚቋቋምበት ቦታ ሐረማያ እንዲሆን ንጉሰ ነገስቱ ቦታውን መርጠው አሳወቁ፡፡ በ1946 ዓ.ም ንጉሱ በመረጡት ቦታ ላይ የኮሌጁ ህንፃ ግንባታ ሥራ ተጀመረ፡፡ የኮሌጁን ህንፃዎች ዲዛይን የኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አርክቴክቸሮች የግንባታ ስራውን ደግሞ አዲስ አበባ የነበረ ጣሊያናዊ የኮንስትራክሽን ድርጅት በመስራት ግንባታውን በ1948 ዓ.ም አጠናቆ የመጀመሪያዎቹን 11 ተማሪዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀበል ትምህርት መስጠት መጀመሩን የታሪክ ድርሳናት ያሰፈሩት ነጥብ

የመረጃ መረብ



5

9 8 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ነው፡፡ በቀጣዩም ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርቶችን በኮሌጁ ግቢና በአካባቢው አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ማስተማር ተጀመረ፡፡ ይህም ተግባር ተኮር ትምህርት በተለያዩ መንገዶች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ የዩኒቨርሲቲውን ምስረታ አስመልክቶ ሲናገሩ “በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግስት መካከል በነበረው ትብብር በኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መሪነት እንደ አንድ የግብርና ኮሌጅ ነው የተቋቋመው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ 11 (አስራ አንድ) ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ስራ የጀመረው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የግብርና ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን በሀገራችን የነበሩትን የግብርና ምርምሮችና የግብርና ኤክስቴንሽን ስራዎች የግብርና ሚኒስቴር ተቋቁሞ በተለይ የግብርና ኤክስቴንሽን ስራን ከመጀመሩም በፊት የግብርና ቴክኖሎጂን በኤክስቴንሽን ለማህበረሰቡ በማስተዋወቅና እንዲጠቀሙት በማድረግ ለዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገሪቷ የሚፈለገውን የዕድገት ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባትም ከግብርናው በተጨማሪ በተለያዩ መስኮች የሚያስተምሩ ኮሌጆችን በማቋቋም ከማስተማርም ባሻገር የምርምር ሥራዎችን ዘርፍ አስፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡” በማለት ነው የገለጹት።ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተቋቋመበት

የመጀመሪዎቹ ዓመታት የምርምር ሥራዎችን ለማከናወን እንዲቻል “የደብረዘይት የግብርና የምርምር ማዕከል”ን በማቋቋም የምርምር ስራዎችን በማከናወን ለአገር እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

የቀድሞው “የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት የእርሻና ሜካኒክ ጥበባት ኮሌጅ” ወይም የአሁኑ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ1952 ዓ.ም. የእንሰሳትና የዕፅዋት ሳይንስ ትምህርቶችን፣የግብርና ኢንጅነሪንግ ደግሞ በ1953 ዓ.ም. ፣ የግብርና ምጣኔ ሀብትን በ1954 ዓ.ም. ፣ በ1955 ዓ.ም. ደግሞ “ሆም ኢኮኖሚክስ” የሚባሉትን ትምህርት ክፍሎች በመክፈት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ትምህርትን በማስተዋወቅ በርካታ ባለሙያዎችን እያስተማረ ማስመረቁን ቀጠለ፡፡ ኮሌጁ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያዊ ኢትዮጵያዊ ዲን ኮሌጁን እንዲመራ እስከተመደበበት 1959 ዓ.ም. ድረስ በኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ድጋፍና አስተዳደር ስር ይተዳደር ነበር፡፡ አብዛኛዎቹም መምህራን የኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሲሆኑ፤ ኢትዮጵያዊያንን በሂደት በማስተማሩ ዘርፍ እንዲገቡ በማድረግ ከኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ስር ሙሉ ለሙሉ ወጥቷል፡፡ ከኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር የነበረውን ውል ሲጠናቀቅም “ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” ይባል የነበረው የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ራሱን የቻለ ቻርተርድ ኮሌጅ በመሆን እስከ 1978 ዓ.ም. ቆይቷል፡፡ በኋላም ራሱን ችሎ የአለማያ

ግብርና ዩኒቨርሲቲ ተባለ፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአገራችን ውስጥ በትምህርት ዘርፍ ያለው አስተዋፅዖ እጅግ በጣም ሰፊ መሆኑን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ ይናገራሉ “ቀደም ሲል በአገራችን የነበሩት አዲስ አበባና አስመራ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ነበሩ፡፡ ሐረማያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ለረጅም ጊዜ በኮሌጅነት ቆይቶ ወደ ዩኒቨርሲቲነት አድጓል፡፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአገራችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ ያለው አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ከመነሻው ጀምሮ በአገራችን ትምህርት ታሪክ ውስጥ በርካታ ምሁራንን በማፍራት አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡ በብዙዎቹ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩና ዩኒቨርሲቲዎቹንም የሚመሩ የዩኒቨርሲቲያችን ተመራቂዎች ናቸው፡፡ ለግብርናው ዘርፍ ዕድገት ጉልህ አስተዋፅዖ የሚያበረክቱ ብቃት ያላቸው ምሁራንን በማፈራት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚ ነው፡ ፡ በአገራችንና በዓለም ዙሪያ ታዋቂና ተሰሚነት ያላቸው የግብርና ሳይንስ ምሁራን እንደ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ ፣ ዶክተር አዛገ ተገኝ ፣ ዶክተር ሰገነት ቀለሙና ሌሎችንም ዩኒቨርሲቲያችን አፍርቷል፡፡ ለተለያዩ የምርምርና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ብቁ የሰው ሀይል በማፍራት ለአገራችን ባለውለታ ነው፡፡’’

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚሰጡት ትምህርት ዘርፎችን በማስፋፋት በመምህራን ትምህርት፣ በቴክኖሎጂ፣

በጤናና ኅብረተሰብ ሳይንስ ትምህርት የሚሰጠውን የትምህርት ዓይነቶች በመክፈቱ በ1988 ዓ.ም. ከግብርና ዩኒቨርሲቲነት ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲነት አድጓል፡፡ በ1998 ዓ.ም ደግሞ ስያሜውን ከዓለማያ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቀይሯል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለይ ለምስራቁ የአገራችን ክፍል “እናት ዩኒቨርሲቲ ነው” ማለት ይቻላል፡፡ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር እንዲጨምር በተፈለገበት ወቅት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይህንን ተልዕኮ ወስዶ ሶስት (3) ኮሌጆቹን አሳድጎ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆኑ አብቅቷል፡ ፡ ድሬዳዋ ፣ ኦዳ ጅግጅጋና ቡልቱም ዩኒቨርሲቲዎች ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወጥተው ራሳቸውን የቻሉ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡

ባለፉት 65 ዓመታት ኢትዮጵያ በግብርና እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የሚያስፈልጓትን የሰው ሀይል አብቅቶ ወደስራ በማስገባት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ በመጀመሪያ ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ (በፒ.ኤች.ዲ) ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ለአገሪቷ ሁለንተናዊ እድገት የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አድርጓል፡፡ ከኢትዮጵያም አልፎ በአፍሪካ አገሮችና በአጠቃላይ በዓለም ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚጥሩ በርካታ ተመራማሪዎችን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አፍርቷል፡፡ በማፍራትም ላይ ይገኛል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 10 ዓመታት ከ2000 በላይ የምርምርና ጥናት ውጤቶችን አሳትሞ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ አድርጓል፡፡ እኤአ የ2021 ብቻ ብንወስድ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 408 ምርምሮችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት ባላቸው የምርምር ጆርናሎች ላይ አሳትሞ እውቀቱ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ አድርጓል፡ ፡ ከዚያ በተጨማሪ በተለይ በግብርናው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ተጠቃሚዎች ጋር በማድረስ እንዲሁም ሌላ ቦታ የበለፀጉ ቴክኖሎጂዎችን አምጥቶ ከአካባቢው ጋር በማላመድ አርሶና አርብቶ አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

የዛሬ አርባ ዓመት አካባቢ በአገራችን የተሻሻለ አንድም የበቆሎ ዝርያ ባለመኖሩ በወቅቱ የበቆሎ ምርጥ ዘርን ከውጪ አገር ማምጣት ግዴታ ነበር፡፡ ይህን ችግር ለማስቀረትም የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በወቅቱ ባካሄዱት ምርምር ለአገራችን መሬትና አየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ የበቆሎ ዝርያዎችን በምርምር በማውጣት ለአርሶ አደሮች እንዲደርስና ምርታማ እንዲሆኑ በማገዝ ለአገራችን የግብርና ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል፡፡

‹‹ጥሩ ምርት የሚሰጥ በሽታን መቋቋም የሚችል በገበያ ተፈላጊ የሆነ ምርጥ ዘር አምርቶ ለተጠቃሚው በማደረስ በኩል ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ቀጥሎ ሐረማያ ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ያለ ዩኒቨርሲቲ ነው፡ ፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ጠንካራ የሶስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ፕሮግራም አለውና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እዚህ መጥተው ተምረው በማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲያቸው የሚመለሱ ዶክተሮች በተማሩበት ዘርፍ ምርምሮችንም በማካሄድ አገልግሎት እየሰጡ ለሀገር ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እያደረጉ ነው››ሲሉ ዶክተር ተስፋዬ ያስረዳሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ስራዎችን ከአገር በቀልና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑን የሚናገሩት የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ‹‹በአሁኑ ወቅት ውጤታማ ምርምሮችን ለብቻ መስራት አስቸጋሪ ስለሆነ ቴክኖሎጂን፣ ልምድንና ሀብትን በአገር ውስጥና በውጪ አገሮች ከሚገኙ ተመሳሳይ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትብብራዊ አሰራሮችን በመፍጠር ውጤታማ ስራዎችን ሰርተናል፡፡ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ከፈጠራቸው አጋርነቶች መካከል ከፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ጋር የዶሮ ዘረመል ማሻሻያ ስራን ፣ ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር ደግሞ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ሞት መንስኤ የመለየትና የመከላከል የጥናት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ በግብርና ደግሞ ከአሜሪካው ካንሳስ ዩኒቨርሲቲ ጋር ማሽላ ላይ ምርምሮች እየሰራን እንገኛለን፡፡ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድርም ለአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ የግብርና ቴክኖሎጂና የአካባቢ ጥበቃ

ዘመናዊ የግብርና አሰራርን ለማስተዋወቅ የተቋቋመው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አድማሱን በማስፋት በአሁኑ ወቅት የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ ኮምፒውቲንግና ኢንፎርማቲክስ ፣ ትምህርትና ስነ-ባህሪ ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ስነቀመር ፣ የጤናና ህክምና ሳይንስ ፣ የህግ ፣ የኅብረተሰብና ስነ-ሰብ ፣ የእንሰሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጆች ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩትና የስፖርት አካዳሚ በመክፈት በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ለአገራችን የሚያስፈልጉ ባለሙያዎችን ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ አስተምሮ በማስመረቅ የአገራችንን የሰው ሀይል ፍላጎት ለሟሟላት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በተከታታይና በርቀት እንዲሁም በክረምት መርሀ ግብሮች የሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ዓይነት 218 ደርሷል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የድህረ ምረቃ መርሀ ግብሮችን በማስፋፋትና የቅድመ ምረቃ መርሀ ግብሮችን በመቀነስ ዩኒቨርሲቲው ሙሉ ለሙሉ የምርምርና ድህረ ምረቃ ዩኒቨርሲቲ እንዲሆን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ የግብርና ምርምር እና የግብርና ኤክስቴንሽን ስርዓት የተጀመረው ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን መረጃ አጣቅሰው የሚናገሩት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ተስፋዬ ለማ፤ የአሁኑ “የደብረዘይት የግብርና ማዕከል”ን አቋቁሞ ግብርናውን ለማዘመንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅ ስራን ሲያከናውን ነበር፡፡ የደብረዘይት ምርምር ማዕከል ራሱን እንዲችል ከተደረገም በኋላ ዩኒቨርሲቲው ሐረርጌ ውስጥ ስምንት የምርምር ጣቢያዎችን በማቋቋም፣ በአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላትና በአርሶ አደሩም ማሳ ላይ ምርምሮችን በማካሄድና ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከግብርናው ባሻገር ሁሉም ኮሌጆች በየዘርፋቸው የምርምር ስራዎችን እንዲሰሩና በአገራችን ያሉ ችግሮች እንዲቃለሉ የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ እየተደረገ ሲሆን፤ ከግብርና ቀጥሎ በአሁኑ ወቅት ጠንካራ የምርምር ስራዎችን በሚያካሂደው የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆኑ የኅብረተሰብ ጤና ክትትል መረጃዎች የሚደራጁበት የጤና ዲሞግራፊ ማዕከል ፣ የእናቶችና የህፃናት ሞት ምክንያትን የሚያጠናና ቅድመ መከላከል ላይ እገዛ የሚያደርጉ ስራዎችን ታዋቂ ከሆኑ ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋማት ጋር በመቀናጀት ምርምሮች እየተሰሩ መሆኑን ዶክተር ተስፋዬ ይገልፃሉ፡፡ “እነዚህ የምርምር ስራዎች ለጤና ፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ውጤቶችን እያፈለቀ ይገኛሉ” ብለዋል፡፡



6

11 10 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ሳይንስ ትምህርት የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል “African Center of Excellency for climate smart Agri- culture and biodiversity conservation” በመሆን ተማሪዎችን ከኢትዮጵያና ሌሎች ስምንት የአፍሪካ አገሮች እየተመለመሉ ለማስተርስና ዶክትሬት ዲግሪ ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት አህጉራችንን ተጠቃሚ እያደረግን እንገኛለን” ብለዋል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲቋቋም በኢትዮጵያና አሜሪካ መንግስታት መካከል በነበረ ትብብር በኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መሪነት ስራ እንደጀመረ ይታወቃል፡፡ ይህ ሂደት ለዩኒቨርሲቲያችን የአጋርነት ትስስሮችን ፈጥሮ መስራትን ያለማመደ አጋጣሚ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ ይናገራሉ፡፡ አሁን የምርምርና የድህረ ምረቃ ዩኒቨርሲቲ ተብለን በተልዕኮ ስለተለየን ይህን ተልዕኮ ለመወጣት ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን በመፍጠር የአጋርነት ትስስር ላይ አቅደን እየሰራን ነው፡፡ እስከዛሬ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተፈጠሩልን የአጋርነት ትስስሮች ጥሩ ተሞክሮ ያገኘንባቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- በህፃናት ጤናና ሞት ክትትል ፕሮጀክት “Champs project” ከኢሞሪ ዩኒቨርሲቲና ከለንደን ስኩል ኦፍ ትሮፒካል ሜዲሲን ጋር እየሰራን ነው፡፡ በተመሳሳይ ከፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ ጋር የህፃናት ጤናና ዕድገት ከአመጋገብ ጋር ያለውን ቁርኝት አብረን እያጠናን ነው፡፡ የምርምር ውጤቶቹም የማህበረሰቡን ህይወት እንዲያሻሻል እገዛ እያደረጉ በመሆኑ ይህንን ተሞክሮ በማስፋት የዩኒቨርሲቲችንን ተልዕኮ ለማሳካት ትብብሮችን በመፍጠር ያለንን ጥሩ ተሞክሮ አጠናክረን እንቀጥልበታለን ሲሉ ዶክተር ጀማል ተናግረዋል፡፡

በስልጠና፣ በቁሳቁስና በመፃሀፍት ድጋፍ፣ በመሰረት ልማት ማስፋፋት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ለመቀነስ በሚያስችሉ ተግባራት፣ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች መንገዶች ፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ስራዎችንም በማከናወን የአካባቢውን ህዝብ ችግር ለማቃለል እየሰራ ይገኛል፡፡ “በአካባቢ ጥበቃ ስራም የሐረማያ ሀይቅ ተፋሰስን በማልማት የጠፋው ሀይቅ እንዲመለስ ያስቻሉ ስራዎችን በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተባበር ያለፉትን ዘጠኝ ዓመታት በመስራት ያገኘውን ውጤት ከሀይቁ ተፋሰስ ክልል በመውጣት ደንገጎ አካባቢም ከኖርዌይ መንግስት ከፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር አስር ሚልዮን ብር የተመደበለት ፕሮጀክት አስጀምረን ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያየን ነው” የሚሉት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይስሀቅ ዩሱፍ

ስራችንን አግባብነት ያለው፣ በተጨባጭ የከተማም ሆነ የገጠር ነዋሪ ማህበረሰባችንን ህይወት ሊለውጥ የሚችል፣ በተለይም በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በግብርና በማዕድን… አደራጅተን እንሄድበታለን፤ ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገንን ቤተሙከራዎችን በማዘመን ፣ የሰው ሀይልን በማጠናከር ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን እንዲጠቀሙ ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅማችንን በማጠናከር በሰፊው ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን” ብለዋል የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ተስፋዬ ለማ፡፡ የንግድ ስራ ሀሳብ ማበልፀጊያ ማዕከልን “Incubation center” ማጠናከር፣ ኢንተርፕራይዙን በማጠናከር በተለይ ለህብረተሰቡ አንድ አስተዋፅኦ ያለው የእርሻ ውጤቶችን እንዲቀርብ ማድረግ፤ ለዚህ ደግሞ የሚታዩ “እጥረቶች ለማስወገድ በቴክኖሎጂ ተደግፎ ምርት እንዲጨምርና ህብረተሰቡ ፍላጎቱን የምናሟላበት መንገድ እያሰብን ነው” የሚሉት ዶክተር ይስሀቅ፤ ከሌላው ጊዜ ለየት ባለመልኩ በአካባቢው ላይ ገፅታን የመፍጠር እርምጃ እንደሚወሰድ ነው የገለጹት። ለዚህ አንዱ ማሳያ “የባቴ አካባቢ አለመቀየር ሐረማያ ዩኒቨርሲቲን ሲያስወቅስ የከረመ ጉዳይ በመሆኑ አካባቢውን ለመቀየር

የሚያስችሉ ዕቅዶችን አዘጋጅተን ወደስራ ገብተናል” ሲሉ አብራርተዋል፡፡

“በቀጣዩ 10 ዓመታት ከአፍሪካ አስር ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ለመሆን ስትራቴጂክ ጎላችን አስቀምጠን እየሰራን ነው” ያሉት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ፤ ይህ ሲደረግ የመማር ማስተማሩ ሂደት ጥራትን ያማከለ፣ የማህበረሰብ ኑሮን ሊያሻሽልና ችግር ፈቺ ምርምሮችን መስራትንም ያቀፈ መሆኑን ነው የተናገሩት። የማህበረሰብ አገልግሎት ስራችን ማህበረሰቡን ሊያሻግር የሚችል በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት፣ ከኢንዱስትሪውም ጋር ትርጉም ያለው ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ትስስርም ይፈጠራል፡፡

“እየሰራን ያለነው ዩኒቨርሲቲያችንን ትራንስፎርም በማድረግ የሀገራችንን እድገት ለማሳካት የበኩላችንን አስተዋፅዖ ለማበርከት እንሰራለን” ሲሉ ነው የዩኒቨርሲቲውን ቀጣይ ዕቅድ ያመላከቱት።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በቀጣዮቹ ዓመታት ሊያከናውናቸው

ያቀዳቸውን ጉዳዮች ለመፈፀም ሰላም ወሳኝ መሆኑን የሚናገሩት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጄይላን ወሊዪ፤ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ፣ አገልግሎት ሰጪ ክፍሎችም በመርህ ላይ ተመስርተው ቀልጣፋ ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ፣ ከሀብትና ከጊዜ ብክነት የፀዳ አገልግሎት እንዲሰጡና የቅሬታ ምንጮች እንዲደርቁ የሚስችል ዕቅድ መዘጋጀቱን ነው ያስታወቁት፡፡

እንደፕሮፌሰር ጄይላን ገላጸ፤ ቅሬታን የማድረቅ ዕቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ በየጊዜው ራሱን እያበቃ ወደተሻለ ደረጃ የሚያሳድግ የሰው ኃይል መገንባት ታሳቢ ተደርጓል። ነባር መምህራንና ሰራተኞች ከወጣቶቹ/ አዲሶቹ ጋር አንድ ላይ በማያያዝ ነባሩ አዲሱን እየገራና እየደገፈ ወደሚፈለገው የብቃት ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የስራ አካባቢን በመፍጠር የታለሙ ዕቅዶችን ለማሳካት በቁርጠኝነት ይሰራል።

ናቸው፡፡

ስራ ፈጠራን ለማበረታታትና የምርምር ውጤቶች የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ ለማድረግ የንግድ ሀሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል በማቋቋም ስራ እንዲጀምር ተደርጓል፡፡ በተለይም ወጣቱ የስራ ፈጠራ ሀሳቦቹን እንዲያቀርብ በማድረግ በውድድር የሚመረጡት ሀሳቦች ወደ ተግባር እንዲለወጡ የሀሳቡ ባለቤቶች በማዕከሉ ውስጥ ገብተው ስልጠናዎችን እንዲያገኙና ሀሳባቸውንም ወደ ተግባር እንዲለውጡት ለማስቻል የስራ ማስጀመሪያ ገንዘብ በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ዶክተር ይስሀቅ ያስረዳሉ፡ ፡ በቀጣይም የስራ ፈጠራ ሀሳብ ማበልፀጊ ማዕከላችንን በማጠናከር ከምንሰጠው ስልጠናና የስራ ማስጀመሪያ በጀት በተጨማሪ ከአበዳሪ ተቋማት ጋር ወጣቶቹን በማስተሳሰር የወጣቶችን ስራ አጥነት ለመቀነስና ሰርተው ራሳቸውን ፣ ቤተሰባቸውንና አገራቸውን መጥቀም እንዲችሉ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪዎቹ ጋር እንደሚሰራም ዶክተር ይስሀቅ ተናግረዋል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና

ስርፀት እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ባከናወናቸው ተግባራት የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ዓመታትም አሻሽሎ ውጤታማ ለመሆን መሪ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

በትምህርት ዘርፍ መምህራንን የማብቃት ፣ በቂ መምህራንን የመቅጠር ፣ የማሰልጠን ፣ የማብቃት መምህራንን ወደ ከፍተኛ ዲግሪ በተለይም ወደ ሦስተኛ ዲግሪ የማሳደግ ስራ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሲሟሉና በተጨማሪ ደግሞ የትምህርት ግብዓቶች እንደ ላቦራቶሪ የመሰሉ ትኩረት አድርገን እየሰራንበት ነው፡፡ እነዚህ ሲሟሉ በንድፈ ሀሳብ የሚሰጠው ትምህርት ዘመኑ በሚፈቅደው ልክ በተግባርም እንዲደገፍ በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ ይናገራሉ:: “ስለዚህ እነዚህ ለትምህርት ጥራት ግብዓት የሆኑ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንሰራለን” ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ከዚህ በፊት ከሚሰራው በተለየ መልኩ “የምርምር



7

13 12 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ማህበራዊ

ጭንቅ አቅላዮች በፍቅርተ ባልቻ

ጭንቅ አቅላዮች

ቤተልሄም ባህሩ (ኢዜአ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ)

ምትክ የለሽ መሆኗ የታመነ የልጅ ደስታ እናት አንድ ህፃን ከማህፀን ጀምሮ እስከ ውልደቱ ከተወለደም አንስቶ በመላ ህይወት ዘመኑ ለእድገትና ስኬቱ የተቻላትን ሳትሰስት ትለግሳለች። ልጇ የህይወትን ውጣውረድ አሸንፎ እንዲጓዝ ከምታጋፈጠው ፈተና ባሻገር እናት ልጅን ፀንሳ እስከምትወልድበት እለት ድረስ የተለያዩ ህመሞች ባስ ሲልም ከእርግዝናና ወሊድ ጋር ለተያያዘ ሞት ልትዳረግ ትችላለች። አንዲት እናት ወደዚህ ምድር ሊመጣ የወደደ ልጇን በምጥ ለመውለድ ስታስብ የሚገጥማት ስቃይና ጭንቅ በቃል የማይገለፅ ቢሆንም ልጇን ስታቀፍ በርካታ አጥንቶች ሲሰባበሩ ከሚሰማ ህመም ጋር አቻ ነው የተባለለትን ምጥ ረስታና ረትታ በሀሴት ትፈካለች ለዛም ነው በሀገራችን ምጡን ርሺው ልጁን አንሺው የሚባለው። ምጧንና ጭንቋን የሚያግዛት ባይኖርም አይዞሽ ባይ አጠገብ ሲኖር ድጋፍና ብርታት ለማግኘት ይረዳታል የሞራል ስንቅም ይሆናታል። ወይዘሮ መዓዛ ሙላቱ ሁለተኛ ልጇን ለመውለድ ለሊት 9ሰዓት ወደቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ መጥታ ሊነጋጋ ሲል በሆስፒታሉ ባለሙያዎች እርዳታ ባለቤቷ ከጎኗ ሆኖ እያበረታት መውለዷን ትናገራለች። በሆስፒታሉ የተደረገላት እንክብካቤ ምጧን ያስረሳ ጭንቀቷንም ያቀለላት መሆኑን የነገረችን ወይዘሮ መአዛ አገልግሎት አሰጣጡ ከከዚህ ቀደሙ የላቀ መሆኑን ገልፃለች።የዛሬ ሶስት አመት የመጀመሪያ ልጇን በዚሁ ሆስፒታል በኦፕሬሽን ስትወልድ በአልጋ እጦት ለእንግልት ተዳርጋ እንደነበርም ታወሳለች። ባለቤቷ አቶ ማርቆስ ፖሊስ በበኩሉ በሆስፒታሉ



8

15 14 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ያሉ ባለሙያዎች በጥሩ እንክብካቤ ሚስቴ በሰላም እንድትገላገል ረድተዋታል ያለ ሲሆን አገልግሎት አሰጣጡ ከዚህ በፊት ከነበረው በብዙ መሻሻሉንና ስራዎቹን በቴክኖሎጂ የተደገፉ ማድረጉን ይገልጻል። በሆስፒታሉ የተጀመረው ሚስት በምታምጥበት ወቅት የቅርብ ሰው እንዲገባ የማድረግ አሰራር ይበል የሚያሰኝ መሆኑንና በምጧ ሰዓት አብሯት መሆኑ ከመውለዷ በፊት ጭንቋን ከወለደች በኃላም ደስታዋን እንዲጋራ ማስቻሉን ተናግሯል። በሆስፒታሉ እያገለገሉ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ከፈጣሪ በታች የሰው ህይወት የሚያስቀጥሉ በመሆናቸው ይህን ስራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበትም ጠይቋል።

እናት በሰላም በምጥም ሆነ በኦፕሬሽን ተገላግላ የአብራኳን ክፋይ አቅፋ ለመሳም እንድትበቃ የህክምና ባለሙያዎች አበርክቶ ወሳኝ ነው። ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸውን ነብሰጡር እናቶች ተቀብሎ እናትም ልጅም ደህንነታቸው ተጠብቆ ጤንነታቸው ተረጋግጦ እንዲወልዱ ማስቻል ጤና ባለሙያዎችን የሚፈትን ተግባር ቢሆንም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህፀንና ፅንስ ባለሙያዎች ይህን ተግባር ለማሳካት እየሰሩ ይገኛሉ። ከ7አስርት አመታት በላይ የዘለቀ አገልግሎትን እየሰጠ ባለው ሆስፒታል እንደ አንድ ክንፍ ሆኖ እየሰራ የሚገኘው የማህፀንና ፅንስ ክፍሉ እናቶችን በምጥና ኦፕሬሽን ከማዋለድ በተጨማሪ ሌሎች ተግባራትን በማከናወን የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እየተጋ ይገኛል ።በሆስፒታሉ በወር 900 እናቶች የወሊድ አገልግሎት እያገኙ ሲሆን ከእነዚህ እናቶች መካከል 45 በመቶው በኦፕሬሽን የሚወልዱ ናቸው። በሆስፒታሉ ክትትል የሚደረግላቸው አብዛኛዎቹ እናቶች ተጓዳኝ የሆነ የጤና ችግር ያለባቸው አሊያም እርግዝናው በራሱ ችግር ያለበት ነው።

በኢትዮጵያ በ 2000ዓ.ም ከ100,000 እናቶች 871 የነበረው የሞት መጠን በ2017ዓ.ም ወደ 401 ማለትም በየዓመቱ ወደ 12,000 የእናቶች ሞት መቀነስ የተቻለ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። ከዚህም ውስጥ ቀጥተኛ የወሊድ ችግሮች 85% የሚሆኑት የሞት መንስኤዎች መሆናቸውን የሚጠቅሰው የሚኒስቴሩ መረጃ ከእናቶች ሞት ቀጥተኛ መንስኤዎች መካከል ፅንስ ከማስወረድ ጋር ተዛማጅ ሞቶች እየቀነሱ መሆኑንና ከውሊድ በፊት እና በኋላ ደም መፍሰስ ለአብዛኛው ሞት መንስኤ እንደሆነ ያትታል። ሚኒስቴሩ ከአጋር አካላትና ማህበረሰቡ ጋር ባከናወናቸው ተግባራት አማካይነት ብሎም የተካነ የወሊድ የአገልግሎት አሰጣጥ በ2000 ከነበረበት 8በመቶ በ2016 ወደ 49በመቶ ማሳደግ መቻሉ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ማስቻሉንም መረጃው ይገለፃል።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህፀንና ፅንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ድልአየሁ በቀለ እንዳሉት ቅድመ ወሊድ ፣ የማዋለድና የድህረ ወሊድ የእናቶች ክትትል ማድረግ የክፍሉ የዕለትተዕለት

ስራ ነው። የፅንስ መውረድ ለገጠማቸው እናቶች ከውርጃ በኃላ የሚሰጡ ህክምናዎችን መስጠት፣ የአገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መሰረት የፅንስ ማቋረጥ፣ ከማህጸን ጋር የተገናኙ ህመሞች ህክምና፣ የመካንነት ህክምና፣ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በሆስፒታሉ እየተሰጠ እንደሚገኝም ዶክተር ድልአየሁ ገልፀዋል። ነብሰጡር ሆነው አሊያም ከማህጸን ጋር የተያያዘ ህክምናን እየተከታተሉ በፅኑ የታመሙ እናቶች ክትትልና የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ሀይ ዲፔንደንሲ ዩኒት የሚባል ክፍል በሆስፒታሉ ይገኛል ብለዋል።

የነባሩ ሆስፒታል ህንፃ የኮቪድ ህክምና ማዕከል በመሆን ሲያገለግል በመቆየቱ ለእናቶችና ህፃናት ብቻ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ታሰቦ የተገነባው ባለ8ወለል ህንፃ የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠበት ነው። ነባሩ ህንፃ በቅርቡ ወደመደበኛ ስራው ሊመለስ መሆኑን ተከትሎም የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታሉ በወራት ጊዜ ውስጥ የታለመለትን አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ይህም ሆስፒታሉን ከጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልና በቅርቡ አገልግሎት መስጠት ከጀመረው አበበች ጎበና ሆስፒታል ቀጥሎ በአገሪቱ ሶስተኛ የእናቶችና ህፃናት ህክምናን የሚሰጥ የመንግስት ተቋም ያደርገዋል።

በሆስፒታሉ ከሚወልዱ እናቶች 40 በመቶው ሆስፒታሉ ትስስር ካለው 16ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም 60 በመቶው ከአጎራባች የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚመጡ ናቸው። አብዛኞቹ በሆስፒታሉ የሚወልዱ እናቶች ተጓዳኝ ችግር ያለባቸውና በኦፕሬሽን የሚወልዱ በመሆናቸው ከወለዱ በኃላ የተወሰኑ ቀናት ክትትል ያስፈልጋቸዋል።ሆኖም የማዋለጃ ክፍሉ ካሉት 20 የማይሞሉ አልጋዎች ለክፍሉ ስራ ፈተና ሆኗል።ተመላላሽ ህክምና መስጫ ክፍል የማዋለጃ ቦታ በማዘጋጀት በእቅድ በኦፕሬሽን የሚወልዱ እናቶች በተመላላሽ እንዲታዩ ተደርጎ በጠዋት መጥተው ኦፕሬሽን ክፍል እንዲወልዱ በማድረግ ለችግሩ መፍትሄ እየተሰጠ ነው። በተጨማሪም ከሆስፒታሉ ማኔጅመንት ጋር በመነጋገር የእናቶች ማቆያ ህንፃ እየተሰራ ሲሆን በእናቶች ሆስፒታል አገልግሎት እየሰጡ ያሉት የውስጥ ደዌና የቀዶ ህክምና ዲፓርትመንቶች ወደነባሩ ህንፃ መሸጋገርም ለአልጋ ችግሩ መላ መሆኑን ዶክተር ድልአየሁ ተናግረዋል። ትስስር ያላቸውን ጤናጣቢያዎች አቅም በመገንባት ሪፈር የሚያደርጉት እናቶች ቁጥር በተወሰነ መልኩ ማስቀረት የአልጋ ችግር መፍቻ መፍትሄ ተደርጎ በሆስፒታሉ እየተሰራበት ያለ ተግባር ነው። የኮልፌ ጤና ጣቢያ ከአራት አመት በፊት በሆስፒታሉ የሰመመን ሰጪዎችና ህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም የግብአት ድጋፍ ተደርጎለት በኦፕሬሽን ማዋለድ ጀምሯል።ባለፉት ሁለት አመታትም በርካታ እናቶች በሪፈር ወደሆስፒታሉ የሚመጡበት የቡራዩ ሀኒዴማ እንዲሁም ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያዎች በኦፕሬሽን የማዋለድ አገልግሎት እንዲጀመሩ ድጋፍ መደረጉን ነው ዶክተር ድልአየሁ የገለፁት። እነዚህ ጤና ጣቢያዎች በኦፕሬሽን ማዋለድ

ለቅድመ ወሊድ የሚመጡ እናቶች የህክምና ቀጠሯቸው ቀን በሰዓት የመከፋፈል ስርዓት በመከተል በሆስፒታሉ ይስተዋል የነበረውን መጨናነቅ መቀነስ ብሎም እናቶች በጥበቃ ከሚያጠፉት ጊዜና ይገጥማቸው የነበረውንም እንግልት መታደጉንም ዶክተር ድልአየሁ ተናግረዋል።

ልዩ እገዛ ለሚፈልጉ ጨቅላ ህፃናት ድጋፍ የሚያደርጉ ኒዎናታል አድቫንስድ ላይፍ ሰፖርት ባለሙያዎችን በኮሌጁ በተቀረጸ ስርዓተ ትምህርት በማሰልጠንና ስራ በማስጀመር የጨቅላ ህፃናት የሙቀት ክፍል መጨናነቅንና የህፃናቱን ህመምና ሞት መቀነስ ተችሏል።

ትምህርት

ሆስፒታሉ ህክምናን ከመስጠት በተጨማሪ በተለያዩ ዘርፎች የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት ከጀመረም ከ10 አመት በላይ አስቆጥሯል። የማህፀንና ፅንስ ክፍሉም ከቅድመ መደበኛ እስከ ፌሎውሺፕ ድረስ የተለያዩ ትምህርት መስኮችን ቀርፆ እያስተማረ ይገኛል። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህፀንና ፅንስ ህክምና ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ና የማህፀን ካንሰር ሰብስፔሻሊስት ዶክተር ታደሰ ኡርጌ እንደነገሩን ከቅድመ ምረቃ እስከ ድህረ ምረቃ በሪዝደንሲና ሰብ ስፔሻሊቲ መርሃግብር በሆስፒታሉ ትምህርት እየተሰጠ ነው። የመደበኛ የህክምና የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች እንደሌሎች ትምህርት ክፍሎች ወደማህፀንና ፅንስ ክፍል መጥተው እየተማሩ መሆኑንና በድህረ ምረቃ የማህፀንና ፅንስ የህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን እያስተማሩ መሆኑንም ገልፀዋል። በድህረ ምረቃ መርሃግብሩ ተማሪዎች ለ4አመት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በየአመቱ በአማካኝ 25 የማህፀንና ፅንስ ህክምና ስፔሻሊስቶች ይመረቃሉ።በሰብስፔሻሊስት አራት መርሃግብሮች ማለትም ማተርናል ፌታልሜድስን፣ጋይኒኮሎጂክ ኦንኮሎጂ፣ ሪፕሮዳክቲቭ ኢንዶክሮሎጂ ና ፈርቲሊቲ እንዲሁም ሪፕሮዳክቲቭ ኸልዝና ፋሚሊ ፕላኒንግ ትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ነው። በ7 ሬዚደንቶች በፈረንጆች 2013 የድህረ

ምረቃ ትምህርት መስጠት የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ መርሃግብሮች ከ80 እስከ 100 ተማሪዎች ትምርህታቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ከአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከደቡብ ሱዳንና ሩዋንዳ የመጡ ተማሪዎች በትምህርት ክፍሉ እውቀትን እየገበዩ ነው።

የህክምና አገልግሎት የሚፈልገውን የሰው ኃይል አቅምና ጥራት ለማሳደግ ትምህርት ክፍሉ ከኮሌጁ ጋር በመሆን መርሃግብሮችን ቀርፆ በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ ድጋፍ ነበር ትምህርት መስጠት የጀመረው።በውጭ ዩኒቨርስቲ

ድጋፍ የተጀመረው ትምህርት ለፍሬ በቅቶ የፈጠረው አቅም ቀድሞ ያልነበሩ የህክምና አገልግሎቶች በሆስፒታሉ ለመጀመር አስችሏል። በዚህም የካንሰር ህክምና፣ የመካንነት ህክምና እንዲሁም ሌሎች ህክምናዎች በሆስፒታሉ ሊጀመር ችሏል።

ጣምራ ስራ

ሆስፒታሉ አገልግሎቱን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል ከጤና ሚኒስቴርና ከተለያዩ አጋሮች ጋር በትብብር ይሰራል። ከተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ትምህርትና ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች በመስጠት ላይም ይገኛል። ሆስፒታሉ የቅዱስ ጳውሎስ የስነተዋልዶ ጤና ምርምር ማዕከል ከተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በስነተዋልዶ ጤና ላይ ይሰራል። የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋዬ ሁሪሳ ማዕከሉ የሆስፒታሉን የቤተሰብ እቅድ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥና የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ህክምናን የመሳሰሉ የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ከመደገፍ ባለፈ በተለይ በስነተዋልዶ ጤና ላይ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮችን እያገዘ ነው ብለዋል። ጥናትና ምርምሮችን በገንዘብ እንዲሁም በማዕከሉ ባለሙያዎች እየደገፈ መሆኑንም ያነሳሉ። የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት ሌላው ማዕከሉ ድጋፍ የሚያደርግበት ዘርፍ ሲሆን በዚህም ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ ፌሎውሺፕ ድረስ ያሉ

ተማሪዎች በተለይ በስነተዋልዶ ጤና ላይ የተሻለ እውቀት ይዘው እንዲመረቁ ለማድረግ እገዛ እያደረገ መሆኑን አመላክተዋል። በስነተዋልዶ ጤና ከምስራቅ አፍሪካና ከሰሀራ በታች ካሉ አገራት በብቸኝነት እየተሰጠ ያለውን የሁለት አመት የፌሎውሺፕ መርሃግብር ማዕከሉ እያገዘ መሆኑን ጠቁመው መርሃግብሩን እየተከታተሉ ያሉ ፌሎዎች አንዱን አመት ከኢትዮጵያ ውጪ በአለም ጤና ድርጅት በመገኘት የተለያዩ አገራትን ልምድ ቀስመው ለአገር አሰተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀውልናል።በትብብር የተሰሩ ተግባራት ውጤት እያስገኙ ሲሆን በዚህም የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በፊት በወር ከነበረበት 2እና 3 አሁን ከ150 በላይ መሆኑን እንዲሁም የጥናትና ምርምር ቁጥር በአመት ከነበረው 2ና 3 አሁን ወደ20 ከፍ ማለቱን ዶክተር ተስፋዬ ተናግረዋል። ሆስፒታሉን በስነተዋልዶ ጤና የልህቀት ማዕከል ለማድረግ የጥናት ቤተሙከራዎችን፣ የኦፕሬሽን ክፍሎችን፣ ዲጂታል ቤተመጻሕፍትና የስብሰባ ማዕከላት ያካተተ ባለአራት ወለል ህንፃ እየተገነባ ሲሆን የህንፃው

ግንባታ ቀሪ ስራ ከስድስት ወር እስከ አንድ አመት ጊዜ ይወስዳል ብለዋል። የህንፃው መጠናቅ የተቋማቱን ትብብር የሚያልቅ ከሆስፒታሉ ጋር በትስስር የሚሰሩ ጤና ጣቢያዎች ባለሙያዎችን አቅም በመገንባት ታካሚዎች በአቅራቢያቸው ጥራቱን የጠበቀ ግልጋሎት እንዲያገኙና የሆስፒታሉ ጫናን ለመቀነስ እንደሚያስችል ታምኖበታል። ማዕከሉ በቀጣይም ለሆስፒታሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን።

የማህፀንና ፅንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶክተር ድልአየሁ በቀለም ሆስፒታሉ በስነተዋልዶና እናቶች ጤና ዙሪያ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ያልተቆጠበ ጥረት ያስቀጥላል ብለዋል ።

በመጀመራቸው የሆስፒታሉን ጫና ለመቀነስ እያገዙ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በእነዚህ ጤና ጣቢያዎች ላይ ዳሰሳ ጥናት ተካሂዶ የድርጊት መርሃግብር ተዘጋጅቶ የስልጠና እንዲሁም የግብአት ክፍተታቸው ተለይቶ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀውልናል።

የቡራዩ ሀኒዲማ ጤና ጣቢያ ዳይሬክተር ዱጋሳ አበበ እንዳሉን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተደረገለት ድጋፍ በግንቦት ወር 2013ዓ.ም በኦፕሬሽን እናቶችን የማዋለድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት በየወሩ 200 በላይ እናቶች ከጤና ጣቢያው ወደሆስፒታሉ ይላኩ እንደነበር ጠቅሰው አሁን ቁጥሩን ወደ55 መቀነስ መቻሉን ነግረውናል። በየቀኑ በጤና ጣቢያው ከ15 እስከ 20 እናቶች እየወለዱ ሲሆን ከእነሱም መካከል ከ3እስከ 4 በኦፕሬሽን የሚወልዱ ናቸው እስካሁን ባለውም 492 እናቶች በጤና ጣቢያው በኦፕሬሽን ወልደዋል። በጤና ጣቢያው በኦፕሬሽን ማዋለድ አገልግሎት መጀመር በአቅራቢያቸው አገልግሎቱን በማጣት ረጅም ርቀት ለመጓዝ የሚገደዱ ባስ ሲልም በመንገድ ላይ በሚፈሳቸው ደም የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር እንዲቀንስ አድርጓል። እየተደረገላቸው ባለው ድጋፍ ምስጋናን የቸሩት ዳይሬክተሩ በቀጣይ በተለይ ባለሙያዎችን በማሰልጠንና ተጨማሪ ግብአቶችን በማሟላት አገልግሎቱን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት።

ሆስፒታሉ ከአዲስአበባ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን ራስ ደስታና ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታሎች የማዋለድ አገልግሎት እንዲጀምሩ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የወላድ እናቶች ቁጥር ሲበራከት ወደእነዚህ ሆስፒታሎች እንደሚላኩም ዶክተር ድልአየሁ ገልፀዋል።

ልዩ አገልግሎቶች

በሆስፒታሉ በሌሎች ጤና ተቋማት የሌሉ በርካታ የማህፀንና ፅንስ ህክምና አገልግሎቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። የፅንስ ችግሮችን በማህፀን ውስጥ በመለየት አንዳንድ ህክምናዎችን መስጠት መጀመሩ አገሪቱ ውስጥ እንደአዲስ ከተጀመሩ አገልግሎቶች አንዱ መሆኑን ዶክተር ድልአየሁ ይናገራሉ። ህክምናው ከእናትና አባት ደም ያለመመሳሰል ጋር ተያይዞ የሚከሰት የፅንስ ደም ማነስ (በተለምዶ ሾተላይ እየተባለ የሚጠራውን ማለት ነው) ማህፀን ውስጥ እንያለ ፅንሱ ደም እየተሰጠው ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ምንም ሳይጎዳ ማቆየት የሚቻልበት አገልግሎት ነው። ከዚህም ሌላ ሌበር አካምፓንየን የተሰኘ እናቶች በምጥ በሚወልዱበት ጊዜ አብሯቸው የመረጡት ሰው እንዲገባ በማድረግ የእናቶቹን ጭንቅ እንዲጋሩ ማድረግም በሆስፒታሉ የሚሰጥ ልዩ አገልግሎት ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶች አገልግሎት ያገኙበት የመካንነት ህክምናን በመንግሥት ሆስፒታል ደረጃ በብቸኝነት እየሰጠ ያለውም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ነው።



9

17 16 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ዓለም አቀፍ

ከሳዑዲ ዓረቢያ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን

በሰዎች መነገድ እና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር በማሻገር ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ችግር አገራት እየተጠቁ ነው። ኢትዮጵያም የዚህ ዓለምአቀፋዊ ወንጀል ሰለባ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ነች። በአገራችን የሕገወጥ ፍልሰት ችግር ሥር የሰደደ በመሆኑ በርካቶች ኢትዮጵያዊያን እየተሰደዱ ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል።

ዜጎች በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሀሰት ማማለያ ተታለው ያላቸውን ጥሪት ሸጠውና ተበድረው፤ ሕይወታቸውንም ለከፋ አደጋ አጋልጠው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያና ሌሎች የባሕረ ሰላጤ አገራት የተሻለ ኑሮና ሥራ ፍለጋ እየፈለሱ ነው።

ኢትዮጵያዊያኑ በሕጋዊ መንገድ በሃይማኖታዊ ጉዞ (ሐጅ፣ ዑምራ)፣ በጉብኝት ቪዛ እና በሥራ ኮንትራት ውል ወደ አገራቱ ከገቡ በኋላ ለተሻለ ኑሮና ሥራ ፍለጋ ሕገወጥ ከሚሆኑበት መንገድ አንዱ ሲሆን ሌላውና አስከፊው ደግሞ በሕገወጥ መንገድ ድንበር በሟቋረጥ ወደ አገራቱ የሚገቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በሕገወጥ መንገድ ለመሸጋገር በሚደረገው የጉዞ ሂደት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ዜጎች ለስቃይ፣ ለእንግልት፣ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለወሲብ ጥቃት፣ ለእስራት፣ ለአሸባሪና ታጣቂ ቡድኖች ጥቃትና መጠቀሚያነት ይጋለጣሉ።

ከዚህም ባሻገር ዜጎች ለተለያዩ የአካል ክፍል መሰረቅ፣ ለዘላቂ አካል ጉዳትና ለሞት እየተዳረጉ ነው። ይህንን ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናትና ሴቶች በብዛት መሰደድ እና የዚህ ገፈት ቀማሽ መሆናቸው ነው፡፡

መንግሥት በሰዎች የመነገድ እና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከል፣ የወንጀሉ ሰለባ የሆኑ



10

19 18 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ዜጎችን መብት ለማስከበርና ተጋላጮችን ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል። ከዚህ ባሻገር ወንጀሎቹን ለመግታት የሚያስችል የሕግ ሥርዓት የዘረጋ ቢሆንም እስካሁን የሚጠበቀውን ያህል ውጤት ማምጣት አልተቻለም፡፡

ሕገወጥ ድርጊቶቹም ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደዱ መልካቸውን በመቀያየርም እየተባባሱ በመምጣታቸው ዜጎችን ለአስከፊ የሠብዓዊ መብት ጥሰት እና እንግልት እየዳረጉ ነው። ይህ ሕገወጥ ድርጊቶቹን በዘላቂነት ለመፍታት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደራጁ ድንበር ዘለል ወንጀሎችን ለመከላከል የተደረገውን ሥምምነት ፈራሚ አገር ናት፡፡ ይህን ሥምምነት ተከትሎ ለወጡት የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በተለይም የሴቶችና የሕፃናት ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን ፕሮቶኮል እንዲሁም ወንጀል ፈጻሚዎችን ለመቅጣት በወጣው ፕሮቶኮል መሠረት በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን በየብስ፣ በባሕር እና በአየር የማስወጣትና የማስገባት ተግባራትን ለመከላከል የወጣውን ፕሮቶኮል አጽድቃለች ፡፡

ከሕገ መንግሥቱና ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ጋር ተጣጥሞ የተሟላ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉም በሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ዓ.ም ወጥቷል፡፡

ባለፉት ዓመታት ሕግ በማስከበር ረገድ በርካታ ተግባራት ቢከናወኑም ችግሩን ከሥር መሠረቱ ለመፍታት ባለመቻሉ በዜጎች ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት እንዲበራከት

ዕድል ከፍቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መረብና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የገቡ ኢትዮጵያዊያን በገፍ እየታፈሱ ደረጃቸውን ባልጠበቁ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት በብዛት ታስረው በእንግልት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሕጋዊ መንገድ ለረጅም ዓመታት የኖሩና የመኖሪያ ፍቃድ ባለማሳደሳቸው ብቻ የሚታሰሩ መኖራቸው ጉዳዩን እጅግ ውስብስብ አድርጎታል። እንዲሁም አልፎ አልፎ ሕጋዊ የሆኑትንም የማፈስና የማንገላታት ሁኔታ ከዕለት ዕለት እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል።

በአሁናዊ መረጃ በሳዑዲ ዓረቢያ ቁጥራቸው ወደ 750 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል። ከእነዚህ መካከል 300 ሺህ የሚሆኑት በሕጋዊ መንገድ ወደ አገሪቷ የገቡ ናቸው። የተቀሩት 450 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በሕገወጥ መንገድ የአገሪቷን ድንበር አቋርጠው የገቡ እንደሆኑ ከሚሲዮኖች የተገኙ ሪፖርቶች ያመላክታሉ።

በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ጂዳ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ በጂዳና በሪያድ የማቆያ ጣቢያዎች ከ102 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ በጂዳና በሪያድ የማቆያ ማዕከላት በተጣበበና መሠረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉላቸው ቦታዎች በብዛት በመታሰራቸው ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ሆነዋል። ከዚህም በተጨማሪ የምግብና አልባሳት እጥረቶች እንዲሁም ለሌሎች ፈርጀ

ብዙ ችግሮች ተጋላጭ እንደሆኑም ይገለጻል፡፡ ከ400 እስከ 500 ኢትዮጵያዊያን በተለይም ልጅ የያዙ እናቶች ታጉረው እንዲታሰሩ በመደረጋቸው ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ተጋልጠዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑ በሳዑዲ ዓረቢያ ማቆያ ቦታዎች እየደረሰባቸው ያለውን የመብት ጥሰት በመቃወም ሰፊ የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻዎች ተካሂደዋል።

መንግሥት እየተከተለ ካለው የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በኢትዮጵያዊያኑ ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ጥሰት ለማስቆም፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ የሳዑዲ ዓረቢያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይቶችን በማድረግ በርካታ ዜጎችን ወደ አገር ቤት መመለስ ተችሏል።

በቀጣይም ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸውና በማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ ከሳዑዲ ዓረቢያ ባለሥልጣናት ጋር ምክክር ተካሂዷል። በዚህም ከ102 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ራሱን የቻለ ዕቅድ በማዘጋጀት ተመላሾችን ለመቀበል ወደ ተግባር ተሸጋግሯል። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም ብሔራዊ ዕቅዱን ካስኬድ በማድረግ ከክልሎች ጋር በብሔራዊ ደረጃ በመወያየት ሙሉ በሙሉ ወደ ተግባር ገብቷል፡፡ እያንዳንዱ ዘርፍም ሚናውን በበቂ መጠን እንዲወጣ ተደርጓል። በተለይም ለተመላሾች ማረፊያ የሚሆኑ ሰባት መቀበያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ተመላሾች ወደየአካባቢያቸው ከመሄዳቸው

በፊት ማረፊያ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በዚህ ሂደት የተመላሾች ንብረት በባለቤቶቹ እጅ ሳይገባ መጥፋትና ኢትዮጵያ ሲገቡም ጭምር የአብዛኞቹ ተመላሾች ዕቃዎች መጥፋት ካጋጠሙ ተግዳሮቶች መካከል ይጠቀሳል።

ከስደት ተመላሾችን ወደየአካባቢያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ከተመላሾቹ የሚበዙት በእጃቸው ምንም ገንዘብና ንብረት የሌላቸው በመሆናቸው ባዶ እጅ ለመመለስ ፍላጎት እያሳደሩ አይደለም፡፡ እዚሁ ያገኘነውን እየሰራን ገቢ ለማገኘት እንጥራለን በማለት ወደ ቀያቸው ላለመመለስ የሚያንገራግሩ፣ ከተመላሾቹ መካከል እናትና አባት ሲታሰሩ ከልጆቻቸው ጋር የተለያዩበት ሁኔታ በመፈጠሩ ልጆቻቸው የት እንዳሉ መረጃ ለማግኘት የተቸገሩም ይገኛሉ።

ከተመላሾቹ አብዛኞቹን ወደየመጡበት ክልል መመለስ ተችሏል። ይሁንና የግጭት ሥጋት ካለባቸው አካበቢዎች የመጡ በመሆናቸው ለመመለስ ስጋት አድሮባቸዋል፡፡ ወደ ትግራይ ክልል የሚመለሱ ዜጎች እንዲሁም በአማራ በአፋር ክልሎች ጦርነት ከተካሄደባቸው ቦታዎች የመጡ ዜጎች ባለባቸው ሥነ ልቦናዊ ጫና ምክንያት ለመመለስ ሥጋት ያደረባቸው መሆኑም ሌላው ተግዳሮት ነው።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም በቂ ባለሙያዎችን በማደራጀት በጎ ፍቃደኞችን መልምሎ በሁሉም ማዕከላትና ኤርፖርት በማሰማራት የድጋፍ አግልግሎት እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል። ተመላሾችን በመቀበልና መረጃዎቻቸውን በማደራጀት እንዲሁም የዕለት ድጋፍ ለሕፃናት አልሚ ምግቦችና የንጽሕና መጠበቂያ

መገልገያዎችን እንዲደረሳቸው ድጋፍ ከሚሰጡ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።

ከስደት ተመላሾች ወደ ማዕከል ከገቡ በኋላ ባለሞያ ተመድቦ የማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ድጋፍ በየጊዜው እንዲያገኙ በማድረግ ወደ መኖሪያ ቀያቸው በመሄድ ከማኅበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ለማስቻል የክልል ግብረ ኃይል እንዲቋቋም በማድረግ በተለይም የመልሶ ማቀላቀሉ ሥራ እንዲከናወን እያደረገ ነው።

ከስደት ተመላሾቹ ወደ አካባቢያቸው ከተመለሱ በኋላ ስለተደረገላቸው ድጋፍና ወደ ገቢ ማስገኛ ሥራ ተሰማርተው ያመጡትን ለውጥ በተመለከተ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ክትትል በማድረግ ተመልሰው እንዳይሰደዱ በየወቅቱ የግንዛቤ ሥራዎችንም ይሰራል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀልን የሚከላከል የሥራ ሂደት እንዲደራጅ በማድረግ የተሟላ የሰው ኃይል መድቦ ሥራው በተቀናጀ መልኩ እንዲከናወን፤ ለተመላሾች በዋናነት የሴቶችና የሕፃናት አልባሳት በማዘጋጀት እንዲደርሳቸው በማድረግ እንዲሁም ለማቆያ ማዕከላት የተለያዩ ፍራሾችና ብርድ ልብሶችን ተደራሽ አድርጓል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ለተመላሾች በተሟላ ሁኔታ ድጋፍ እንዲደርስ እያደረገም ይገኛል።

ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሽ ዜጎች መካከል ያሉ አጥፊዎችን በምርመራ ለመለየት የሚያስችል የምርመራ ቡድን ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫ መስጠቱን ያስታወቀው ፍትሕ

ሚኒስቴር ደግሞ በሰው በመነገድና ሰዎችን ድንበር በማሻገር ወንጀሎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመላሾች መካከል የሚኖሩ አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብና የወንጀል ተሳትፎ ያላቸውን ግለሰቦች ከመለየት አንጻር ልዩ የምርመራ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ሥራ አንዲገባ አድርጓል።

አጥፊዎችን ለመለየት የምርመራ ዕቅዱ በፍትሕ ሚኒስቴር ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል߹ ከፌዴራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ለተውጣጡ ባለሙያዎች ቀርቧል። የምርመራ ቡድኑ በንዑስና በቴክኒክ ቡድን ተከፋፍሎ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ አንዲገባ አቅጣጫ በመስጠት የጋራ መግባባት ላይም ተደርሷል ።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን መወጣትና ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ፤ የወንጀሉ ተጠቂ ቤተሰቦች ወይም ማኅበረሰቡ አዘዋዋሪዎችን ለሕግ አስከባሪ አካላት መጠቆም ተገቢ እንደሆነ ፍትሕ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባዘጋጀው ውይይት ተነስቷል።

ኅብረተሰቡ አታላዮች ዓረብ አገር ሆነው የተመቻቸው በማስመሰል ብልጭልጭና ቅንጡ የሚመስሉ ቁሶችን ተደግፈው የተነሱ ፎቶግራፎችን በመላክ የሕገወጥ ደላሎችን ሥራ ከሚያቀላጥፉ ራሱንና ቤተሰቡን መጠበቅና መጠንቀቅ አለበት።

መንግሥትም በአገር ውስጥ ሰርቶ መለወጥን ማሳመንና ከስደት ለተመለሱት በመልካም ሁኔታ አቀባበል በማድረግ፣ የሥራ ዕድል በማመቻቸት ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የክህሎት ሥልጠናዎችን መስጠት ይጠበቅበታል።

ወጣቱም ራሱን ለመለወጥ ከአገር ውጭ ለመሥራት መሄድ አስፈላጊ ከሆነ ለውጭ የሥራ ዕድል በቂ ሥልጠና በመውሰድ ሕጋዊውን መንገድ መከተል እንጂ ሕይወትን ቁማር አስይዞ ያልፍልኛል ማለት ሞኝነት ነው፤ እየሞቱ መለወጥ የሌለ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

ከመጋቢት 21 ቀን 2014 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2014/ በየዕለቱ ከሦስት እስከ አራት በሚደርሱ በረራዎች ቁጥራቸው ከ26 ሺህ 868 በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ አገር ቤት ተመልሰዋል። እንደ አውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር ከ2018 እስከ 2022 ባሉት ዓመታትም 305 ሺህ 116 ወንዶችና 83 ሺህ 976 ሴቶች በድምሩ 367 ሺህ 772 ከስደት ተመላሾች ወደ አገራቸው መግባታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።



11

21 20 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ማንነታችን የሚያፈርሱ የኪነ- ህንጻ ግንባታዎች

ዐብይጉዳይ

አዲስ አበባችን በየጊዜው ወደ ላይ አንጋጠው የሚመለከቷቸው አዳዲስ ህንጻዎች “የሚበቅሉባት” ከተማ ሆናለች፡ ፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመሀል የከተማዋ አካባቢዎች የሚገነቡ ህንጻዎች በግዝፈትም በርዝመትም በውበትም የተመልካችን ቀልብ በ ቀላሉ ይስባሉ፡፡ የብዙዎቹ ገጽታም በበለጸጉ አገሮች የምናያቸውን የረቀቀ ቴክኖሎጂ ውጤቶች የተገለጸባቸው ሆኖ እናስተውላለን።

አሁን አሁን ደግሞ በጌጣ ጌጦችና በመ ብራት ቀለማት መልካቸውን የሚቀያይሩ ህንጻዎችን መመልከት እየተለመደ ነው፡፡ ቀን ላይ ሙሉ ነጭ ሆኖ የተመለከትነው ህንጻ ምሽቱን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ አሊያም ሐምራዊ ቀለም ከተዋቡ አምፑሎች በሚፈልቅ ብርሃን ተጠለቅልቆና መልኩን ቀይሮ መመልከት ተለምዷል።

ይኼማ ውጭ አገር ያለው የሚመስለው የሚያስብሉን ውጪያዊም ሆነ ውስጣዊ ገጽታን የተላበሱም ብዙ ናቸው፡፡

የህንጻዎቿን ብዛትና ብልጭልጭ ውበት በመመልከት ብቻ፤ ‹ዋው! አዲስ አበባ ታምራለች! በጣም አድጋለች!› ሲል በአድናቆት የሚናገር ሰውም እንዲሁ በርካታ ነው፡፡

ነገር ግን የከተማዋን ኪነ ህንጻ በአስተውሎት መመልከት የቻለ አገር ወዳድ ዜጋ ‹ይህ የእኛ ነው ወይስ የሌላ?› በሚል ጽኑ ስጋት ያድርበታል፡፡ በህንጻዎቹ ግንባታ የተነሳ እየፈረሱ ያሉ አገራዊ እሴቶች መኖራቸውን ይገነዘባል፡፡



12

23 22 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባና በሌሎችም የአገራችን ከተሞች ኪነ ህንጻ ላይ የእኛ ያልሆኑ ፍልስፍናዎች፣ ዓለማዊ እሳቤዎች፣ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤ ተምሳሌት የሆኑ የህንጻ ንድፎችና አሰራሮችን መመልከት የተለመደ ሆኗል፡ ፡ ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ማንነታችንን በገዛ ፈቃዳችን እንዲሸረሸር ነጻ ፈቃዳችንን እንደሰጠን ሊቆጠር ይችላል፡ ፡ በኪነ ህንጻው ቅኝ ተገዝተን እንዳንቀር የምንገኝበትን መንገድ በማስተዋል መመርመር ይኖርብናል፡፡

ከህንጻም በላይ

ኪነ-ህንጻ ከሰው ልጆች ተፈጥሮ ጋር አብሮ እያደገ የመጣ ዘርፍ ነው፡፡ የሰው ልጆች በዘመናት መካከል እንደ ቅርስ ይዘውልን የቆዩት ጥበብ ነው፡፡ በጽሑፍ የቀሩ… በዜማ የቀሩ… ቅርሶች እንዳሉ ሁሉ፤ ከምንም በላይ ግን ጎልቶ የቀረው የሰው ልጆች የጥበብ ማሳያ አንዱ ኪነ-ህንጻ ነው፡ ፡

ኪነ-ህንጻ የህንጻ ጥበብ ማለት ነው፡፡ ሳይንሱ እንደሚለው አንድን አካባቢ ለሰው ልጆች የተመቸ ለማድረግ መስራት ማለት ነው፡፡ አካባቢያችንን ማሳመር ማለት ነው፡፡ ለአንድ ለታለመለት አገልግሎት የሚገነባ ህንጻ የአካባቢውን ማህበረሰብ ማንነነትና ስነ-ልቦና የመግለጽና የማነጽ ኃይል እንዳለውም ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡ ኪነ-ህንጻ ከሰው ልጅ አስተሳሰብ የተቀዱ ሐሳቦች የሚንጸባረቁበት፤ መልሶ ደግሞ የሰዎችን አስተሳሰብን የማነጽና ስነ-ልቦናን የመገንባት (በበጎም ይሁን አፍራሽ በሆነ መልኩ) አቅም ያለው ጥበብ ነው፡፡

“ከፍ ባለ የጥራት ደረጃ” መሰራቱ የኪነ-ህንጻ አንደኛው

መገለጫ ነው፡፡ ህንጻው ሁሌም ባየነው ቁጥር የምናደንቀው… የምንገረምበት… ደግመን እንድንጎበኘው በሚያደርግ የጥራት ደረጃ መሰራቱ የኪነ-ህንጻ መለያ ባህሪው ነው፡፡

በዘመናዊው ኪነ-ህንጻ ደግሞ “እጅግ ከፍ ያለ ሐሳብ” የኪነ-ህንጻ ዋንኛ መገለጫው ነው፡፡ እንዲኖረውም ይጠበቃል፡፡ “የሰው ልጅ ነፍሱ ስትወጣ ‹አስክሬን› እንደሚባል ሁሉ፤ ሐሳብ የሌለው ህንጻም ‹የኪነ-ህንጻ አስክሬን› ልንለው እንችላለን” በማለት ጣሪያና ግድግዳ የተሰራለት ሁሉ ኪነ-ህንጻ እንደማይባል ሙያተኞቹ ይገልጻሉ፡፡ ሐሳቦቹ የህዝቦች ታሪክ፣ ባህልና ማንነት እንዲሁም አካባቢያዊ ሁኔታዎችን የሚያስረዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

እነዚህን ባህሪዎቹን መነሻ አድርገን የዘመናችን ኪነ-ህንጻን በብዙ ጥያቄዎች ታጅበን እንመልከተው፡፡ እንደ ሌላው የጥበብ ዘርፍ ሁሉ የአገርና ህዝብ መገለጫዎችን አጉልቶ ለማሳየት የሚሞክር ነው? ህንጻዎቻችን ላይ ታሪኮቻችን ተጽፈዋል? በአለም ላይ ልዩ ያደረጉን መገለጫዎቻችን ይታያሉ? የገጠሙን ፈተናዎችና ያገኘናቸው ድሎችስ ተገልጸዋል? የትኞቹ ህንጻዎች ናቸው “የኢትዮጵያ” የሚያሰኛቸው የግንባታ መልኮች ያሏቸው? የቀደመው ድንቅ የህንጻ ግንባታ ታሪካችን ጥበብ ዛሬ ላይ የት ደርሷል ማለት እንችላለን?

ጥያቄዎቹ “ጥናት ማድረግ ይፈልጋል” የሚል ምላሽ የምንሰጥባቸው አይደሉም፡፡ እውነቱ በአካል ቆሞ ሁላችንም ይታያልና! ብዙዎቹ የከተሞቻችን ኪነ- ህንጻዎች ከእኛነታችን የራቀ ማንነት ለብሰው ይታያሉ፡

፡ የሚነግሩን ታሪክ የእኛን አይደለም፡፡ አካባቢያቸውን የዘነጉ ባህር ማዶን አሻግረው የሚያሳዩን ናቸው፡፡ “የእኛ ነው” ብለን እንድንሳሳለት የሚያደርግ “አንዳች ነገር ያለው በዚህ ዘመን አናገኝም” ብለን መደምደም እስክንችል ድረስ ባዳነት እንዲሰማን ያደረጉ ናቸው፡፡

እኛን የማይመስሉ መልኮች

ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የግንባታ ንድፍ ፍልስፍናን ያዳበረች አገር ናት፡፡ ህዝቦቿ ከጥንት ጀምሮ አገር በቀል በሆኑ የግንባታ ቁሶች የመኖሪያ እና የእምነት ቤቶችን በመገንባት ይታወቃሉ፡፡ ትናንሽ ድንጋዮችን በመረብረብ በጭቃና በኖራ ቤቶችን ከመስራት ባሻገር ከአንድ ወጥ ትልቅ ድንጋይ በመፈልፈል ቤተ-እምነቶችን በመስራትና ረጃጅም ሐውልቶችን በመቅረጽ ህዝቦቿ የረቀቀ ክህሎትን ለዓለም አሳይተዋል፡፡ በአክሱማውያን ዘመን ከፍ ብሎ የተገለጠው ይህን የማነጽ ጥበብ፤ በእነ ቅዱስ ላሊበላ ዘመን ደግሞ እጅጉን ጥልቅ ፍልስፍናን ይዞ… አዲስ የኪነ- ህንጻ እሳቤን ጭምር ለዓለም አስተዋውቆ… ብዙ ዘመናትን ተሻግሮ ቆይቷል፡፡ የጎንደር ድንቅ የኪነ ህንጻ ታሪክም በእነ ፋሲል ቤተ መንግስት እና ግንብ ላይ ተከትቦ አሁን ድረስ ይነበባል፡፡

ዘመናዊው የኪነ-ህንጻ ታሪካችንን ግን የቀደመውን የከፍታ ታሪክ ይዞ በፍጥነትና በጥራት መጓዝ አልቻለም፡ ፡ ለምን?

“ዘመናዊው ኪነ-ህንጻ በቀላሉ ብዙ ነገሮችን ለመስራት የሚችልበትን ብዙ እድሎች የማግኘቱን ያህል፤ ብዙ ፈተናዎችም ደግሞ ያሉበት ነው” ሲል የኪነ-ህንጻ

ባለሙያው በእምነት ደምሴ የግል እይታውን ይገልጻል፡ ፡ ወደ ኋላ ቀርተናል ብሎ ባያምንም፤ የሚገባን ደረጃ ላይ አለመድረሳችንን ግን ያውቃል፡፡

የኪነ-ህንጻ ባለሙያው በእምነት በከተማችን የተለያዩ የህንጻ ፕሮጀክቶች ላይ የተሳተፈና በከተሞች ኪነ-ህንጻ ላይ ትኩረት ያደረጉ ስራዎችን በሚሰራው ኧርባን ሴንተር (‹ከቤት እስከ ከተማ› የተሰኘው በኪነ-ህንጻና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከሚሰራው የራዲዮ ፕሮግራም የተወለደ ተቋም ነው) ውስጥ ስፔስ ማናጀር ነው፡፡ መሐል አዲስ አበባ እስጢፋኖስ አካባቢ የህንጻ ክዳናቸው የጎጆ ቤት አይነት ቅርጽ ባላቸው ቢሮዎች ውስጥ ነው የሚሰራው፡፡ ቢሮዎቹ በግራና በቀኙ ወደ ላይ ገዝፈው በሚታዩ ህንጻዎች መካከል በቁመት አጥረው ቢገኙም፤ የገጠር ጎጆ ቤቶች ዓይነት ቅርጽን የለበሰው የጣሪያ ክዳናቸው ውበት ግን ማንም ሰው በቀላሉና በግልጽ እንዲያያቸው የማድረግ ኃይልን አጎናጽፏቸዋል፡፡ የጎጆ ቤቶች ዓይነት ክዳን በህንጻዎቹ ላይ ስንመለከት ባለንበት ቆም የሚያደርግ ልዩ ስሜት ይፈጠርብናል፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራሱን የሚመስል፣ የሚያውቀውን ባህልና እምነት የሚያንጸባርቁ ነገሮችን ማየት ደስ የሚል ስሜት እንደሚፈጥርለት የሚነገረው ሐሳብ በእርግጥም እውነት ነው ለካ!

እንዲህ ዓይነት ስሜት የሚፈጥሩ የህዝቦች መገለጫዎችን የያዙ ኪነ-ህንጻዎችን በከተሞቻችን በዝተው ማየት ያልቻልነው ለምንድን ነው?

ለዚህ መዋጮ ያደረጉ ብዙ መሆናቸውን በእምነት ይገልጻል፡፡ በቂ የግንባታ ቦታ አለመኖር፣ የግንባታ እቃዎች ከውጭ ሀገር የሚመጡ መሆናቸውና የአሰሪዎች (ደምበኞች) የሙያተኞችን ነጻነትን መንፈጋቸው በዋናነት ይጠቅሳል፡፡

እነዚህ ችግሮች እያሉም ቢሆን ሙያተኛው ሊወስድ የሚገባውን ወቀሳ መሸሽ አያስፈልግም፡፡ የሙያተኛው ስንፍና ወይም ክህሎት የለሽነት ኪነ-ህንጻው አገርኛ መልክም ሆነ አንዳች ድንቅ ውበትና ጥበብ እንዳይታይበት ለማድረጉ ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

“ከውበትም ከጥበብ በፊት አንድ ኪነ-ህንጻ ግምት ውስጥ የሚያስገባው ህንጻው የሚሰጠውን አገልግሎት ነው” ሲል በእምነት ይሞግታል፡፡ ህንጻው ሊሰጠው የሚፈልገውን አገልግሎት በብቃት መስጠት የሚችልበት ነገር ነው ቅድሚያ የሚታየው፡፡ “ውበትና ሌሎች ነገሮች ቀጥሎ የሚታዩ ናቸው” ይላል፡፡

እዚህ ላይ በኪነ-ህንጻ ስራዎቿ ተሸላሚ የሆነችው አንጋፋዋ አሜሪካዊ የኪነ-ህንጻ ባለሙያና መምህርት ማርታ ቶርኔ፤ ምርጥ ኪነ-ህንጻ ሊፈጥርብን የሚገባውን ስሜት በተመለከተ የተናገረችውን ሐሳብ ማንሳቱ አስፈላጊ ነው፡፡



13

25 24 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

“ምርጥ ኪነ-ህንጻ ከሚሰጠው

አገልግሎትም… ከጥራትም…

በላይ ነው፡፡ ህንጻውን

የሚጠቀምበትና የሚኖርበትን

ህዝብ ልብ የምር የሚነካ አንዳች

ነገር ሲኖረው ነው፡፡ ልክ እንደራሳችን

በጣም እንድንጠነቀቅለትና

እንድናስብለት የሚያደርግ አይነት

ስሜትን የመፍጠር ኃይል ያለው

ነው” ኢትዮጵያ የቅዱስ ላልይበላ ድንቅና ምትሀታዊ የሚባል ጥልቅ የግንባታ ንድፍና ክህሎት የታየባቸው የውቅር አብያተ ክርስትያናት መገኛ ናት፡፡ ከዓለም በልዩነት እንድትጠቀስ ያደረጓት የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትን በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና የሳይንስ ተቋም (ዩኔስኮ) ተመዝግበዋል።

ሌላው የጎንደር ከተማ ጥንታዊ የኢትዮጵያ የኪነ-ህንጻ ጥበብ መገለጫዎችን ከያዙ ቀደምት ከተሞቻችን መካከል አንዷ ናት፡፡ በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተ መንግስትና ግንብ እስከነ ውበቱ የዓለምን ህዝብ እያስደመመ የሚገኝ ነው። ነገር ግን አሁን በአካባቢው የሚገነቡ ዘመናዊ ህንጻዎች ደግሞ የቀደመውን የኪነ-ህንጻ ታሪኳን የበረዙ ግድፈቶች ይታዩባቸዋል፡፡ ከባዕድ አገር የተቀዱ የሕንጻ ንድፎችና አሰራሮች በብዙ ህንጻዎቿ ላይ ይታያሉ፡፡ ከተማይቱ ልዩ ያደረጋት ማንነቷን ትታ የውጪውን ዓለም ከፈለገች፤ የዓለም ቱሪስት ወዲህ ምን ያመጣዋል?

“ቱሪስቶችን ለማስተናገድ ብዙ ጉድለቶች ስላሉብን ይህን ዓይነት ህንጻ እንገነባለን ብለው የሚመጡትን ሁሉ እሺ እያልን መቀበላችን ለዚህ ሁሉ መዘበራረቅ ዳርጎናል” የሚሉት የጎንደር ከተማ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡

የከተማይቱ ዘመናዊ ኪነ-ህንጻ አዲስ አበባ ላይ ከሚታየው የተለየ እንዳልሆነ በመግለጽ፤ “የእኛን የማይመስሉ… ጎንደር ጎንደር የማይሸቱ… ኢትዮጵያን የማያሳዩ…. ከማንነታችን የራቁ ሐሳቦችን የያዙ ኪነ-ህንጻዎች መሰራታቸው ሊያሳስበን ይገባል” ብለው ያምናሉ፡፡ ጎንደር የቀደመው የኪነ-ህንጻ መገለጫዎቿ በዚህ ዘመን ከፍ ብለው አለመገኘታቸው ያስቆጫቸዋል፡፡

በእርግጥ የፋሲል ግንብን የሚገልጹ አንዳንድ

ተምሳሌታዊ ምልክቶች በማኖር የሚገነቡ ጥቂት ሆቴሎች አሉ፡፡ “ይኼ መልካም ቢኾንም በቂ አይደለም” ይላሉ፡፡

ይህንን አቋራጭ መንገድ ደግሞ እንደ አንጋፋው የኪነ- ህንጻ ባለሞያና መምህር ፋሲል ጊዮርጊስ ያሉት ፈጽሞ አይስማሙበትም፡፡ “አንዲት ፈረንጅ የኢትዮጵያን ባህላዊ የጆሮ ጌጥ ብታደርግ ወዲያውኑ ‹ለኢትዮጵያ ፍቅር አላት› እንጂ፤ ‹ይቺ ሴት ኢትዮጵያዊ ናት› ልንል አንችልም” ሲሉ ይተቻሉ፡፡ ህንጻውን ታሪካዊና ጥንታዊ ለማስመሰል መስኮቱን ወይም በሩን አሊያም ሌላውን ነገር ከላሊበላ ወይም ከጎንደር የህንጻ አሰራር ስልት ወስዶ ለጥፎ ሌላውን ነገር ባለበት እየሰሩ የማምታታት ነገር በዚህ ዘመን ኪነ-ህንጻ ስራዎች ላይ መታየቱን ታዝበዋል፡፡ ይህ ህመም ራስን አጥብቆ በመመልከትና በመመርመር በጊዜ ሊታከም እንደሚገባም ይመክራሉ፡፡

ወደ ምስራቁ የሐገራችን ክፍል ስንጓዝ …. ጥንታዊውን የጀጎል ግንብ በዩኔስኮ ቅርስነት ያስመዘገበችው የሐረር ከተማን እናገኛለን፡፡ በድንጋይና በጭቃ ብቻ የተገነባው የጀጎል ግንብ መለያዋ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አምስቱ በሮች ተብለው የሚታወቁት የግንብ በሮች፤ በትልቁ የሐረር መስፍን በር እና በብዙ የመንግስት ተቋማት ህንጻዎች የላይኛው ክፍል አናት ላይ የ‹ሀ› ፊደል ቅርጽ ያላቸው ምልክቶች ይታዩባቸዋል፡፡ ይህ አሁንም ድረስ እየታየ የቀጠለ የኪነ-ህንጻ መልኳ ነው፡ ፡ መሰል ምልክት ያላቸው ኪነ- ህንጻዎችን በማየት ብቻ ከተማዋ ሐረር መሆኗን በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡ ይህ የኾነው በአጋጣሚም ይሁን ታስቦበት፤ በተሻለ መልኩ እንዲቀጥል በበጎ ምሳሌነት የሚጠቀስ ነው፡፡

አርክቴክት ህሊና አየናቸው ከጓደኞቿ ጋር በከፈቱት ድርጅት ውስጥ በከተሞች ኪነ-ህንጻ ላይ በመስራት ከአስር ዓመት በላይ የቆየ ልምድ ያላት ባለሙያ ናት፡፡

“ባህልም ውበትም አንጻራዊ ነው፡፡ በማን ሚዛን ተለክቶ ነው ሁላችንንም የሚያስማማ መልክ ማግኘት የምንችለው?” ስትልም ትጠይቃለች፡፡ “አንዱ የወደደውን ሌላው ላይፈልገው ቢችል በመጥፎነት መፈረጅ የለበትም” ስትልም ዘመናዊው ኪነ-ህንጻ ላይ የሚሰጠውን መደምደሚያ ትተቻለች፡፡ ሁሉም ዘመን የራሱ የሆነ ጥሩም መጥፎም መልክ እንዳለው በመጥቀስ፤ የዚህ ዘመን ኪነ-ህንጻንም በዚህ አግባብ እንድንመለከተው ትጠይቃለች፡፡

“እኛ ኢትዮጵያን የዓለም አካል ነን፡፡ በእለት ተእለት ኑሯችን ላይ ዓለምአቀፋዊ ተጽዕኖዎች እንደሚንጸባረቁ ሁሉ ላይ በኪነ-ህንጻም ላይ ይህ ቢታይ የሚወገዝ መሆን የለበትም” የሚል አቋም አላት፡፡ የአፍሪካ መዲና የሆነች ከተማ ላይ አፍሪካዊና ዓለምአቀፋዊ መልኮችም በኪነ-ህንጻ ላይ መታየት አለባቸው፡፡ “በራሳችንን ነገር ብቻ መታጠርም አይኖርብንም” ስትልም ዘመናዊው የአገራችን ኪነ-ህንጻ የውጭ አገር ተጽዕኖዎች የበዛበት

ነው የሚለውን ትችት አጥብቃ ትቃወማለች፡፡ በመሰረቱ ከዓለም ጋር ያለን ትስስር በማንሳት “ለኪነ ሕንጻዎቹ እኛነት አለመላበስ” ምላሽ ቢሰጥም በራሱስ የእኛ እምነት፣ አብሮነት፣ ፍልስፍናና ማህበረሰባዊ እሴቶች ለምን ጎልተው አልታዩም? ላለመታየታቸው ምክንያቱ በርግጥ ዘመኑን በወጀ መንፈስ የአሁኑን እይታ መውደድ ነውን? የሚል ጥያቄ መጋበዙ አየቀርም።

የባለሙያዎች ፈጠራ ክህሎት ማነስና የተሰራ ንድፍን በቀላሉ የመኮረጅ ተግባር የአገራችን ዘመናዊ ኪነ ህንጻ ወደፊት እንዳይራመድም፤ ሀገርኛ መልክ እንዳይኖረውም ማድረጉ ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ ይኼ የፈጠራ ክህሎት አለመኖር ጊዜ ወስዶ የማሰላሰልና በጥናትና ምርምር አለመስራትም የሚመጣ ነው፡፡

‹በቂ ጊዜ አለማግኘት› ሙያተኞቹ የሚገልጹት አንደኛው ችግራቸው ነው፡፡

“የእኛ ችግር አንድም በቂ ጊዜ የማይሰጠን መሆኑ ነው፡ ፡ ለንድፍ ስራ የሁለትና ሶስት ወራት ነው የሚሰጠው፡ ፡ ግንባታው ስምንት ዓመት ሊቆይ ይችላል” የሚለው በእምነት፤ የህንጻ ንድፋቸው በጥድፊያ በመሰራታቸው የተነሳ ግንባታቸው እንደገና ፈርሶ እንዲሰሩ የሆኑ ህንጻዎች መኖራቸውንም ይጠቅሳል፡፡

እንደ ጥሩ ማሳያ…

ዘመናዊው ኪነ-ህንጻ ብዙ ጉድለቶች የሚታዩበት ዘርፍ ቢሆንም ሊደነቁ የሚገባቸው ጥቂት ማሳያዎችን አልጠፋበትም፡፡

ህንጻዎቹ ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር ቅድሚያ በመስጠት በተደጋጋሚ ሲናገር የሚደመጠው አርክቴክት በእምነት፤ በግሉ በጥሩ ማሳያነት እንድንመለከታቸው የሚጋብዛቸውን ኪነ-ህንጻዎችን ይጠቁማል፡፡ “የኮሪያ ሆስፒታል በትክክል ለህክምና ተገቢ የሆነ ንድፍ የተገለጸበት ነው” ይላል፡፡ ፍሬንድሺፕ ህንጻ ከኮሪደሮቹ ስፋት የተለያየ ንግድ ስራ ከተዘጋጁ ክፍሎቹ ድንቅ ነው፡ ፡ ጥላ ህንጻ… ሞሞና ሆቴል… ማራኪ የኪነ-ህንጻ ንድፍ የተገለጸባቸው መሆናቸውንም መስክሯል፡፡

ምንም እንኳን ጊዜያዊ ቢሆንም፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓለ ሲመት መስቀል አደባባይ ላይ የተገነባው መድረክ ከሚኮራባቸው ድንቅ የኪነ-ህንጻ ማሳያዎች አንዱ ነው፡፡

የሰዎች ግንዛቤ ሲያድግ፣ ሙያተኞች በቂ ጊዜና ነጻነት ሲያገኙ፣ በቂ የግንባታ ቦታ ሲኖርና ግብዓቶችንም እንደልብ በቀላሉ ማግኘት ሲቻል፣ እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ አጋዥ ህጎች ተግባራዊ ሲኾኑ፤ ዘመናዊው ኪነ- ህንጻ የራሱን አሻራ የሚያኖርባቸውን ስራዎችን መስራት እንደሚቻልም ያምናል፡፡

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ከምትጠቁማቸው ድንቅ የኪነ-ህንጻ ማሳያዎች መካከል ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ በብዙ

ችግሮች ውስጥ የተወለደውና በጭቃ የተገነባው ዞማ ቤተ-መዘክር አንደኛው ነው፡፡ በአዲስ አበባ መካኒሳ አቦ ዙሪያ አካባቢ የሚገኘው ይህ ቤተ-መዘክር፤ ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶች፣ የግንባታ ጥበብ፣ አኗኗርን፣ ባህልን በአጠቃላይ ‹የእኛ› የምንለውን ስሜትን የሚፈጥሩ ብዙ መገለጫዎች አሉት፡፡

ቤተ-መዘክሩ በውስጡ ቤተ-መጽሐፍና የስዕል ማሳያን ጨምሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተገነቡ ከአስር በላይ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን፤ ሁሉም ክፍሎች እንደ መጽሐፍ ተገልጠው የሚነበቡ ታሪኮችን በውጪያዊ ገጽታ ንድፋቸው ላይ ተጽፎባቸዋል፡፡ የሚያመራምሩን… እንደገና እንድንጎበኛቸው የሚያስገድዱን… ጥልቅ ሐሳቦች ተስሎባቸዋል፡፡ መነሻውና መድረሻውን ለማወቅ የሚያጓጓ ጥምዝምዝ የሰው ልጅ የእጅ ጣት አሻራ በሚያስገርም ጥበብ በውጪ የግድግዳው ክፍል ላይ በጭቃ ተገንብቶ እናያለን፡፡ የሁሉም ክፍሎች ግንባታዎች አገር በቀል በሆኑ ቁሶች የተሰሩ ናቸው፡፡ ግቢውም አካባቢውን በማይረብሹ የተፈጥሮ ተክሎችና ትናንሽ ድንጋዮች ርብራብ ውበቱን ሰርቶ እናያለን፡፡ የቤተ- መዘክሩ መስራቾች አርቲስት መስከረም አሰግድና ኤልያስ ስሜ የሙያም የዜግነትም ኃላፊነታቸውን በመወጣታቸው

ክብር ይገባቸዋል፡፡

የቀደመውን ጥበብ መመርመር

አንድ የሚያስማማን ነጥብ የአገራችን ዘመናዊው ኪነ ህንጻ የሚገባው የእድገት ደረጃ ላይ አለመሆኑና ኢትዮጵያዊ መልኮች የደበዘዘበት መሆኑ ነው፡፡ ይህንን እውነት በዝምታ መመልከታችን ከቀጠለ በገዛ ምድራችን ላይ የባዕድ አገሮችን ባህልና እሴቶችን ተቀብለን እየገነባን የራሳችንን የሚያኮራ ማንነታችንን እንድንዘነጋ እንሆናለን፡ ፡

ይህ ስጋት አብዝቶ ያስጨነቃቸው አካላት ከአንድ ዓመት በፊት አዳማ ላይ ተሰብስበው መክረው ነበር፡፡ “በኢትዮጵያ የሚገነቡ ህንጻዎች የማህበረሰቡን ማንነትና ባህል እንዲገልጹ ያስፈልጋል” የሚል የጋራ አቋም በመያዝ ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ቢዘገይም መልካም የሚባል ውሳኔ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት በፊርማ የጸደቁ ስምምነቶች ድንቅ ክህሎትን ለሚጠይቅ የጥበብ ዘርፍ ያሰቡትን ለውጥ የማስገኘት አቅም ይኖራቸው ከሆነ በቀጣይ ዓመታት የምንመለከተው ይሆናል፡፡

“መጀመሪያ የእኛን ኃላፊነት መወጣት አለብን” የሚል አቋም ያላቸው የጎንደር ባህልና ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኜ፤ “በቂ የግንባታ ቦታ፣ የጥሬ እቃዎች አቅርቦት ማሟላት ከቻልን ሌሎቹን በዚህ መልኩ መስራት አለባችሁ የሚል አስገዳጅ መስፈርት ሁሉ ልናወጣ እንችላለን፡፡ ባለሀብቶች በኪነ-ህንጻ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖቸው የማድረጉ ስራ በተጠና ሁኔታ አቅጣጫ ዘርግተን ልንሰራበት እንደሚገባ ተረድተናል” በማለትም ሲሉ በመንግስት በኩል ሊቀድም የሚገባውን የመፍትሔ እርምጃ አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ የቀደመ የኪነ-ህንጻ አሰራር ጠንቅቀው የሚያውቁና እጅጉን የሚያከብሩት ደግሞ የጥንቱን የራስን መንገድ መመርመር ትክክለኛውን መፍትሔ እንደሚሰጥ ያምናሉ፡፡ ምክንያቱም እዚያ ውስጥ ልብን በሚነካና በሚያሳምን መልኩ ፍጹም ጥበብን፣ ከፍ ባለ የጥራት ደረጃ መስራትን፣ ጥልቅ ሐሳብን የመግለጽ ብቃትን፣ አገር በቀል የግንባታ ግብዓቶችን መጠቀም መቻልን፣ ለራስ ማንነት አብዝቶ ክብር መስጠትን በትክክል ማየትና መማር ይቻላልና!



14

27 26 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

አሳሳቢው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ

ዐብይጉዳይ

በአሁኑ ወቅት ምድራችን ላይ ከተንሰራፋው ትልልቅ ስጋቶች ውስጥ ከኒውክለር ቀጥሎ በሁለተኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጧል፤ የአየር ንብረት ለውጥ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ በቁልፍ ችግርነት የሚጠቀስ ዋና ዋና ጉዳይ ነው፡፡ በምድራችን የከባቢ አየር ውስጥ የሙቀት አማቂ ጋዞች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እያደገ እንደመጣ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

የሰው ልጅ የእለት ተእለት ኑሮውን ለመግፋት በሚያደርጋቸው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የሚከሰተው የተፈጥሮ ሃብትን አላግባብ በሽሚያ መልክ የመጠቀም ተግባር ለዚህ የሙቀት አማቂ ጋዞች መጨመር እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

በዚህም ምክንያት የአየር ንብረት ለውጡ ለሰው ልጆች እና ህይወት ላላቸው ፍጡራን በሙሉአጥፊ ውጤት እያስከተለ ነው። ይህን ሁኔታ ለመቀልበስ በከባቢ አየር ውስጥ የሙቀት አማቂ ጋዞች ክምችትም መቀነስ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ሆኗል።

የአየር ንብረት ለውጥ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ በሆነ መልኩ የሚከሰት ነው። በመሰረቱ ተፈጥሮ ራሷን የማሰተካከልና ሚዛኗን የመጠበቅ ተፈጥሯዊ ጸጋ አላት። አሁን ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ያለው ከሰው ልጆች የዕለት ተእለት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የሚለቀቀው የሙቀት አማቂ ጋዝ ልቀት መጨመር ነው፡፡

በዚሁ የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚከሰት የውቅያኖስ መጠን መጨመር እና የድርቅ መከሰት የሰው ልጆችን ህይወት



15

29 28 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ፈተና ውስጥ ከማስገባት እስከ በርካታ የምድሪቱ ፍጡራን ነፍስ መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

የአየር ንብረት ተፅዕኖዎች አገሮች ለሚያደርጉት የዘላቂ ልማት ከፍተኛ ማነቆ እንደሆነም ይገለፃል፡፡ ይህ ደግሞ የአፍሪካ የአገሮችን በተለይ የሰብ ሰሃራን አፍሪካ አገሮችን በእጅጉ ተጎጂ ያደርጋቸዋል፡፡

በዚህ ጽሁፍ የአየር ንብረት ለውጥ በአገሮች ላይ እያደረሰ ያለው ጫና መሰረታዊ ባህርያት አገራችን የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን ተጽእኖ ለመቋቋም በማከናወን ላይ ያለችው ተግባር እንዳስሳለን፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ

የአየር ንብረት ለውጥ ማለት በየዓመቱ አንድን አካባቢ የአየር ፀባይ አማካይ ልኬት የሚያሳይ መሆኑን ጽንሰ ሃሳባዊ ትርጓሜው ያስረዳል።

የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን ለማሟላት ሲል ነዳጅን፣ የድንጋይ ከሰልን፣ ፋብሪካን፣ ማጓጓዣን እና ሌሎች ጋዝ አመንጪ ጭሶችን ይጠቀማል። እነዚህ ኃይል አምንጪ ንጥረ ነገሮችን የሚለቁት “ግሪን ሃውስ ጋዝ” አብዛኛው ክፍሉ በካርቦን ዳይኦክሳይድ የተሸፈነ ጭስ ነው። ይህ ጋዝም ከፀሃይ የሚመጣውን ሙቀት አምቆ በመያዝ ለምድር ሙቀት መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሚና ይጫወታል።

በዚህ ወቅትም ዓለማችን በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከነበረችበት የሙቀት መጠን በአንድ ነጥብ ሁለቱ ዲግሪ ሴልሺዩስ የጨመረ ሲሆን፤ ወደ አየር ንብረት ለውጥ የሚለቀቀው የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠንም 50 በመቶ መጨመሩ ጥናቶች ያሳያሉ። በአየር ንብረት ለውጥ ላይ

እርምጃ መውሰድ ካልተቻለም በተያዘው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ወደ ሁለት ዲግሪ ሴልሺዩሽ ከፍ ሊል እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ።

የሳይንስና ደን ኢኮሎጂ ባለሙያ እና በአካባቢና አየር ንብረት ኮሚሽን የሬድ ፕላስ አስተባባሪ ዶክተር ይተብቱ ሞገስ እንደሚሉት፤ የአየር ንብረት ለውጥ ከነበረው መጨመር ወይም መቀነስ ዥዋዥዌ እንደመጫዎት ሊሆን ይችላል።

የአየር ንብረት ለውጥ ለረጅም ጊዜ የተመዘገበ ወይም በቋሚነት የታየ የአየር ንብረት ኩነቶች የለውጥ ሂደት የሚያመለክት ተግባር ነው። ይህ ክስተት ወይም ውጤት የሚሸፍነው ሰፊ የሆነ የመልከዓ ምድር ሽፋንን የሚያካልል በመሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ መስተጋብር ይባላል፡፡

በሌላ በኩል የአየር ንብረት ተለዋዋጭነት በአንድ አካባቢ በተወሰነ ጊዜ የሚታይ ከአማካኝ የአየር ንብረት የመለወጥ ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን፤ ይህ እንደ አየር ንብረት ለውጥ ለረጅም ጊዜና በሰፊ መልከአምድራዊ አካባቢ የሚከሰት ሳይሆን ለአጭር ጊዜ በውስን አካባቢ የሚከሰት ለውጥ ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ እና መዘዙ

በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምድራችን የሙቀት መጠን በከፍተኛ መጠን እንደሚጨምሩ የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የባህር ወለል የሚጨምርና ከዋና ዋና አሳሳቢ በመጠኑም ይሁን በዓይነቱ አደገኛ የሆነ ጉዳት የማድረስ አቅም ያለው የዓለማችን ክስተት እንደሚሆን መረጃዎች ያሳያሉ።

የአየር ንብረት ለውጥ ከሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች

መካከል የዝናብ መጠንና ስርጭት መዋዠቅ ነው። በዚህም በአንድ አንድ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ በጎርፍ መጥለቅለቅን የሚያስከትል ሲሆን፤ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በድርቅ መመታትን እንዲከሰት ያደርጋል የምል ስጋት ፈጥሯል፡፡

በአየር ፀባይ መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር ከፍተኛ የሆነወበቅ፣ ከመጠን ያለፈ ድርቅና ጎርፍ የሰውን ልጅ በሰላም ተረጋግቶ የኖር ህልውናውን ይፈታተኑታል፤ አሁን እየተከሰተ ያለው ይሄው ነው።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የሙቀት መጠን የተፈጥሮ ሃብትን በማጎሳቆል ወደ በርሃማነት እንዲቀየሩ እያደረገ ነው። በሌላ በኩልም የተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚያገኙት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝንብ ጋር ተያይዞ ለከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በመጋለጥ ላይ ይገኛሉ። አሜሪካ፣ ቻይና፣ ቤልጂየም፣ ፊሊፒንስ፣ ኔዘርላንድስ እና ሌሎች አገሮች ለከባድ የአውሎ ንፋስና የጎርፍ አደጋ መጋለጣቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።

በዚሁ መዘዝም የምጣኔ ሃብታቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመፋለም የሚያስችል ሃብት ስለሌላቸው እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ተጽዕኖውን ለመቋቋም ሲቸገሩ ይስተዋላል። የአየር ንብረት እየተቀየረ መመጣት ለሙቀት መጠን መጨመር እና ለሰደድ እሳት መነሳት ለውጥ ተጋላጭ በመሆን የምድራችን ግንባር ቀደሙ ክፍል ነው።

እንደ ሳይቤሪያ ያሉ ግግር በረዷማ አካባቢዎችም በመቅለጥ ታምቀው ለቆዩ ግሪን ሃውስ ጋዞችን መለቀቅ ምክንያት በመሆን ለአየር ንብረት መወሳሰብ አሉታዊ ሚና አላቸው። በዚሁ ተጽዕኖ ስር እየወደቁ የሚገኙት

የምድር ፍጥረታትም የሚፈልጉትን ምግብ ለመመገብና ውሃ ለመጠጣት በመቸገር ህይወታቸው አደጋ ውስጥ በመውደቅ ላይ ይገኛሉ።

የሳይንስና ደን ኢኮሎጂ ባለሙያው ይተብቱ ሞገስ (ዶክተር) “የአየር ንብረት ለውጥ በረጅም ዓመታት በ10 ሺዎችና በመቶዎች ዓመታት ሲታይ ከፍ ዝቅ ሊል ይችላል። ያሁኑ ባለፉት 250 ዓመታቶች የማይጠበቅ፣ በተፈጥሮ ሂደት ሊሆን የማይችል ለውጥ እየታየ ነው።” ብለዋል።

ኢንዱስትሪያል ሪቮሉሽን ያመጣው እና የዘመናችን አኗኗር የድንጋይ ከሰልና ነዳጅ በማቃጠል የሚለቀቀው ሙቀታማ ጋዝ እንዲሁም የደን ጭፍጨፋ ያስከተለው በረሃማነት ተባብሮ በከባቢ አየር ላይ ለውጥ እንዲከሰት አድርጓል። በከባቢ አየር ላይ የተፈጠረው ካርቦን ዳይኦክሳይድ የመሳሰሉት ሙቀታማ ጋዞች በከፍተኛ ሁኔታ በመከማቸታቸው ምድራችን ከፀሐይ ጋር ያላት መስተጋብር እንዲዛባ ማድረጉ ነው የሚገለጸው። “የደን መመናመን ለአየር ንብረት ለውጥ ዋና ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳልም” ይላሉ ይተብቱ ሞገስ (ዶክተር)፡፡

የዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኃን ቢቢሲ “የሙቀት መጠን በአንድ ነጥብ አምስት ዲግሪ ሴልሺየስ መቆየት ካልቻለ የአውሮፓ ክፍለ አህጉር በጎርፍ መጥለቅለቅ ሊጠቃ ይችላል” የሚል ሐተታ አስነብበዋል፡፡ ተቋሙ አክሎውም በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ደግሞ ከፍተኛ የሙቀት መጠን በማስተናገድ የእርሻ ቦታዎች ወደ በርሃማነት ይቀየራሉ፤ በውቅያኖስ መጠን መጨመር ሳቢያ በፓስፊክ ክፍል ያሉ ደሴቶች ሊዋጡ እንደሚችሉ የቢቢሲ ሐተታ ያጠናክራል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የአፍሪካ አገሮች በሚያስተናግዱት ድርቅ ሳቢያ ዜጎቻቸውን ለመመገብ በማይችሉበት ሁኔታ የምግብ እጥረት ይከሰታል። ምዕራባዊው የአሜሪካ ክፍልም በካባድ ድርቅ የሚጠቃ ሲሆን፤ ቀሪው ደግሞ በነጎድጓዳማ ዝናብ ሊጥለቀለቅ ይችላል። የፕላኔቷ አነስተኛ ክፍለ አህጉር አውስትራሊያም በከባድ ድርቅና ሙቀት ልትጋለጥ ትችል እንደምትችል ቢቢሲ ባስነበበው ቅድመ ትንበያ ተቀምጧል።

የአየር ንብረት ለውጥ በህይወት የመኖር መሰረት የሆነውን የስርዓተ ምህዳር መናጋት በማስከተል ለከፍተኛ ስነ- ህይወታዊ ውድመት እና ለአንዳንዶቹ ዝርያዎች መጥፋት ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግብርናው ዘርፍ የምርትና ምርታማነት መስተጓጎል እንዲደርስ በተለያየ መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

የዓለም መንግስታት ጥረት

በኢንዱስትሪ ያደጉት እና በማደግ ላይ ያሉት አገሮች መካከል ያለው ፉክክር ለበርካታ ዓመታት የበካይ እና ሙቀት አማቂ ጋዞች ቅነሳ በታሰበለት መንገድ ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

በዓለማችን በካይ አየር በመልቀቅ ቻይና እና አሜሪካ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ በጠቅላላው ከሚለቀቀው በካይ አየር 40 በመቶው የሚሆነው ከቻይና እና አሜሪካ የሚወጣ ነው። ህንድ፣ ሩሲያ፣ ጃፓን፣ ብራዚል፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራን፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በካይ አየር ከሚለቁ የመጀመሪያዎቹ 10 በካይ አገሮች ዝርዝር ውስጥ ይገኙበታል።

በሌላ በኩል 54ቱ የአፍሪቃ አገሮች ለከባቢ አየር ብከላው በጥቅሉ ያላቸው አስተዋጽኦ ከስምንት በመቶ እንደማይበልጥ ነው የሚነገረው። ሆኖም ግን የመዘዙ ከፍተኛ ተጠቂዎች መሆናቸው በተግባር እየታየ ነው።

የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተው በሙቀት መጨመሩ ምክንያት አፍሪቃ ውስጥ ያሉ ግግር በረዶዎች እንደሚቀልጡ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል። ለማሳያም 5 ሺ 200 ሜትር ከፍታ ያለው የኬንያ ተራራ ላይ የሚገኘው ግግር በረዶ እስከ ጎርጎሪዮሳዊው 2040 ድረስ እንደሚጠፋ አመላክቷል።

በጎርጎሪዮሳዊው 2009 ዓ.ም በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አገሮች በአየር ንብረት ለውጥ መዘዝ የተጋለጡ ድሀ አገሮች ለውጡን ተላምደውና የሚያደርሰውን ጥፋት ተከላክለው ለመኖር እንዲችሉ በየዓመቱ የ100 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ገንዘቡንም እስከ እኤአ 2020 ድረስ ለማሰባሰብ ነበር የታሰበው። ሆኖም እስከ እኤአ 2019 ድረስ የተሰባሰበው 80 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ከዚህ ገንዘብ 43 በመቶው ለእስያ አገሮች የሚሰጥ ሲሆን፤ ለአፍሪቃ 26 በመቶው፣ 17 በመቶ ደግሞ ለላቲን አሜሪካ አገሮች የሚሰጥ ነው፡፡

ሆኖም የታሰበው ገንዘብ ሊሟላ የሚችለው በ2023 ሲሆን፤ የተገባው ቃል መዘግየት በአፍሪቃ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ በአንድ ወገን ድርቅ በሌላው በኩል ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝን ጨምሮ የተለያየ የተፈጥሮ ቁጣ ለሚፈራረቅባት አፍሪቃ ሊደረግ የሚገባው ድጋፍ ከተጠቀሰው የገንዘብ መጠንም ከፍ ሊል እንደሚገባ የሚከራከሩ ወገኖች አሉ።

በቅርቡ የወጣ መረጃ እንደሚያሳው የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ድርቅ አፍሪቃ ውስጥ ከጎርጎሪዮሳዊው 1970 ዓ.ም ጀምሮ ከ700 ሺ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከ400 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በአህጉሪቷ በድህነት ሕይወቱን ይገፋል። የአየር ንብረት ለውጥ በተፋጠን መጠን ደግሞ ይኽ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ነው የዓለም ሜትሪዎሎጂ ድርጅት ያመለከተው።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 በፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የዓለማችን የሙቀት መጠን አንድ ነጥብ አምስት ሴልሺዩስ በላይ ከፍ እንዳይል ማድረግ የሚያስችል ስምምነት አገሮች ተፈራርመዋል። መሰረታዊ ጉዳይ ተባብረው መስራትን ታሳቢ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ በግላሰጎ የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ከ200 በላይ የሚሆኑ አገሮች ስምምነቱን ፈርመውታል። በዚሁ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት በተደረገው ስምምነት ላይ ከሚደርስባቸው ተጽዕኖ አኳያ ታዳጊ አገሮችን አላስደሰተም።

ብዙዎች በፕላኔቷ ላይ እያደረሰ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ በመጣው አየር ንበረት ለውጥን ለመቋቋም እምነት የጣሉበት ስምምነት የግላስጎ የአየር ንብረት ለውጥ (Glasgow Climate Impact) የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል።

በጉባዔው (ኮፕ-26) ሲሳተፉ በነበሩ ከ200 በላይ አገሮች መካከል የአየር ንብረት ተጽዕኖን ለመቋቋም ያስችላል በተባለው የስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ ሲሆን፤ በሚቀጥለው 2023 የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔን የተባበሩት አረብ ኤሚሪቶች እንድታሰተናግድ መመረጧ ይታወቃል።

እ.አ.አ 2015ቱን በፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ጨምሮ ቀደም ብለው ተካሂደው የተደረሱ ስምምነቶች እና የተገቡ ቃል ኪዳኖች አተገባበር ዙሪያ ክርክር እና ምክክር ያደረጉት የግላስኮው ጉባዓይተኞች የዓለምን አማካይ የሙቀት መጠን በአንድ ነጥብ አምስት ዲግሪ ሴልሺየስ እንዳይበልጥ ለማድረግ ነው።

የግላግስጎው ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚረዳ አዲስ ዓለም አቀፍ ስምምነት የተደረገበት ሲሆን፤ ከዚህም አደገኛ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚረዳ ስምምነት አንዱ ነው፡፡ ጉባኤው የአየር ፀባይ ስምምነት የከሰል ምርትን ለመቀነስ የተደረገ በዓይነቱ የመጀመሪያው ስምምነት የተደረገበትም ነበር፡፡

ስምምነቱ ጎጂ ጋዞችን መልቀቅ በፍጥነት እንዲቆምና በማደግ ላይ ለሚገኙ አገሮች የአየር ጸባይ ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችላቸው ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የከሰል አጠቃቀምን በመቀነስ ረገድ መሻሻል ቢታይም እኤአ 2019፣ 37 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ኤሌክትሪክ ከዚሁ ኃይል ምንጭ ይገኛል።

በዚህ ጉባኤ ፖላንድ፣ ቬትናም እና ቺሊን ጨምሮ ዋና ዋና የከሰል ተጠቃሚዎች በኮፕ 26 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደ ከሰል፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ የኃይል ምንጮችን ላለመጠቀም ቃል ገብተዋል። በሌላ በኩል እንደ አውስትራሊያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና አሜሪካ ያሉ አንዳንድ በከሰል ላይ ጥገኛ የሆኑ ቀዳሚ አገሮች ግን ቃል ከመግባት ተቆጥበዋል።

ስምምነቱን ከ40 በላይ አገሮች ፈርመዋል። ፖላንድ፣ ቬትናም እና ቺሊ ለመጀመሪያ ጊዜ የድንጋይ ከሰል ኃይል ላለመገንባት እና በዘርፉ መዋለ ንዋይ ላለማፍሰስ ከተስማሙ 18 አገሮች መካከል ናቸው።

ይህ ጉባኤ ለየት የሚያደርገው በዓለማችን ከፍተኛውን



16

31 30 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት የሚያደርጉት አሜሪካ እና ቻይና በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በአየር ጸባይ ለውጥ ዙሪያ ተባብረው ለመስራት ከስምምነት የደረሱበት ጉባኤ ነው፡፡

ስምምነቱም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በሚከሰት የሙቀት መጠንና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች እየተፈተነች የምትገኘውን “ምድርን ለመታደግ ያስችላል” የሚል ተስፋ ጭሯል። ምንም እንኳን የበለጸጉ አገሮች በኢንዳስትሪዎቻቸው አማካኝነት የሚለቁትን በካይ ጋዝ መቀነስ፣ የአረንጓዴ ልማትን ለማጠናከር በተግባር የተደገፈ ስራ የሚጠይቅ ቢሆንም። ተመራማሪዎች ግን አገሮች የገቡትን ቃል ለመፈጸም ቸልተኝነት ባሳዩ ቁጥር ከባድና ተደጋጋሚ ጎርፎች፣ በረሃማነት እንዲሁም “ያልተለመደ ቅዝቃዜ እየጨመረ ይሄዳል” ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው፡፡

ኢትዮጵያ እና የአየር ንብረት ለውጥ

የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ጫና ምክንያት የችግሩ ሰላባ ከሆኑት አገሮች አንድዋ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ባስከተለው ተጽፅኖ በተከታታይ በድርቅና ጎርፍ በከፍተኛ ሁኔታ ስትጠቃ ቆይታለች፡፡ ዘመን እየቀያየረ የሚከሰተው ከአየር ንብረት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ችግር ዛሬም ድረስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በድርቅና በጎርፍ እንዲጠቁ ምክንያት ሆኗል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም ችግር ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ያላአደጉ አገሮች የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡ አየር ንብረት ለውጡ በድርቅ ሳቢያ የግብርና ምርታማነት ቅናሽ እንዲያሳይ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን መነሻ በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ በምርትና ምርታማነት ሂደት ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት የተለያዩ ጥረቶች ስታደርግ ቆይታለች፡፡

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የጋዝ ልቀትን የመቀነስ፣ ከፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጭ ቴክኖሎጂዎችን በአማራጭነት የመጠቀም፣ የተፈጥሮ ሀብቷን በተገቢው የመገልገል፣ የተፋሰስ ልማትን የማስፋፋትና፣ የደን ልማትን በስፋት የማካሄድ ስትራቴጂዎችን ነድፋ ተግባራዊ እያደረገች ነው፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ በዓለማችን እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ፣ ለኦዞን መሳሳትና በዓለም ላይ እየደረሱ ላሉ ተግዳሮቶችም መንስዔ ሲሆን ታይቷል፡፡ የዘርፉ ምሁራን እንደሚሉት ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች በዋና ምክንያትነት የሚጠቀሱት ወደከባቢ አየር የሚለቀቁ የበካይ ጋዞች ልቀት መጨመርና የደን ሀብት እየተመናመነ መምጣት ነው፡፡

ታዲያ ችግሮቹን ለመፍታት የበካይ ጋዝ ልቀትን መቀነስና የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን መከተል እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤን ማጎልበትና በደን ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት የግድ ይሆናል።

በተለይም በግብርና ምርታማነት ላይ መሠረቱን ለጣለ ምጣኔ ሀብት የአየር ንብረት ለውጥ ምን ያህል ተፅዕኖ እንዳለው መረዳት ቀላል ነው።

የአየር ንብረት ለውጥ በግብርና ምርታማነት ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ ቀድማ የተገነዘበች ኢትዮጵያም የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን እየተከተለች ትገኛለች፡፡ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂን በመጠቀም በአካባቢ ጥበቃ ላይ በማከናወን ላይ ያለችውን ተግባር እንደ ማሳያ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በስፋት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ ልማት አሻራ ዓለምን እየፈተነ የሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር በኩል በጉልህ አግዞታል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ተተክለዋል። በዚህም ተመናምኖ የቆየውን የአገሪቷን አረንጓዴ ሽፋን በመጠኑም መመለስ ተችሏል። በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች ሲያድጉ ለአረጓዴ ሽፋኑ ከማደግ ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ ከመቋቋም አኳያ የሚኖራቸው ሚና የላቀ ነው፡፡

ደኖችና የአየር ንብረት ለውጥ በመግታት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የደን ልማት በዓለማአቀፍ ደረጃ 17 በመቶ ያህል የሚሆን የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀት የሚፈጥር ሲሆን፤ ከኢንዱስትሪ እና ከኃይል አቅርቦት ቀጥሎ ሦስተኛው ከሰዎች ተግባራት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የልቀት መንስኤነው፡፡ በደን የሚደረገው የልቀት መጠን አሜሪካን ወይም ቻይና ከሚያደርሱት ዓመታዊ የልቀት መጠን ጋር ተመጣጣኝ ነው፡፡

የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ተቀብላ እየተገበረች ያለችው ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት አረንጓዴ ልማት ላይ በሰጠችው ትኩረት የደን ሽፋኗን ማሳደግ ችላለች።

ኢትዮጵያም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችላትን ዕቅድ ካስተዋወቀች ወዲህ በዓለም መድረክ ተጠቃሽ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር እንድትሆን እንዳስቻላት የሚናገሩት የሳይንስና ደን ኢኮሎጂ ባለሙያው ይተብቱ ሞገስ (ዶክተር) “ከሁሉም አገሮች ቀድማ ከፍተኛ የልቀት መጠን ለመቀነስ ለተባበሩት መንግስታት ሀሳብ ያቀረበች እና ለኮንቬንሽኑ ተግባራዊነት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለች አገር ነች” ብለዋል፡፡

ዶክተር ይተብቱ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያ በተለይ በደን ልማት እና ጥበቃው ላይ ሰፊ ስራ እንደምታከናውን ለድርጅቱ ባቀረበችው ሰነድ ላይ ተገልጿል። በደን እየተሸፈኑ የሚገኙ ይዞታዎችን ኢትዮጵያዊያን የማገዶና የወደፊት የእርሻ መሬት እንደማይችሉ መገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። “የደን ተቋማትን ማጠናከር እንዳለባቸው በመጠቆም የአየር ንብረት ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ዘርፍ መፍጠር ይገባል” ይላሉ።

በሌላ በኩል ደኖች ባላቸው የበካይ ጋዝ ልቀትን የማመቅ

አቅም በርካታ የደን ሀብት ያላቸው አገሮች ከካርበን ንግድ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ። የካርበን ንግድ በኪዮቶ ፕሮቶኮል መሠረት ከፍተኛ የጋዝ ልቀት መጠን ያላቸው ያደጉ አገሮች ዝቅተኛ ልቀት ላላቸው እንዲሁም ደኖችን በአግባቡ ለሚጠብቁ አገሮች ክፍያ የሚፈጽሙበት አሠራር ነው።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የድርሻዋን በመወጣት የደን ልማቱን በማጠናከር ከልማት ተጠቃሚነቷ በተጨማሪ ከካርበን ንግድ በሠፊው ልትጠቀም የምትችልበት አቅም አላት፡፡ ይተብቱ ሞገስ (ዶክተር) “የደን ሽፋኗን በመጨመርና ደኖችን በማልማት ከካርበን ንግድ የውጭ ምንዛሪን ማግኘት ይቻላል።” ሲሉ ነው የሚያስረዱት።

የተራቆቱና አካባቢዎችን መልሶ በማልማት እና የደን ጭፍጨፋን በመከላከል በደን ልማት አማካኝነት ከከባቢ አየር ለሚመጡት ካርቦን የገንዘብ ምንጭ ለማስፋት ቀጣይ አማራጭ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ ይህ በማድረግም እንደ አውሮፓ ካርበን ንግድ ድርጅት መረጃ የበካይ ጋዝ የሚለቁ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቆጣጠር ለሚችሉ ጥቅጥቅ ደኖች ክፍያ የሚፈጽሙበት አሠራር ተዘርግቷል።

“የኢትዮጵያውያን ብልጽግና የሚረጋገጠው የደን ልማት በሚሰራ ስራ ነው” የሚሉት ይተብቱ፤(ዶክተር) ደን የሽፍታ መደበቂያ ሳይሆን የብልጽግና እና የዘላቂ ልማት ዋስትናችን የሚል አስተሳሰብ መፍጠር አስለፈላጊ መሆኑን ነው አጽንኦት የሚሰጡት። የደን ልማት ኢትዮጵያን ከድህነት የማውጣት ትልቅ አቅም እንዳለው የሚናገሩት ይተብቱ(ዶክተር)፤ ከካርበን ንግድ በሬድ ፕላስ ፕሮግራም ባለፉት አምስት ስድስት ዓመታት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳገኘች ይናገራሉ፡ ፡ ሆኖም ከዚህ ዘርፍ በቀጣይነት ለመጠቀም “ራሱን ችሎ ዘርፉን የሚመራ ተቋም አለመኖሩ ትልቅ ፈተና ነው” ብለዋል፡፡

ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ መፍትሄዎች የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለማቃለል ያላቸው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም፤ በብሄራዊና ዓለም አቀፍ ፖሊሲዎች ላይ ትኩረትን አላገኘም፣ በአግባቡ አልተተገበረም ከዚህ በተጨማሪ ለትግበራውም በቂ ፋይናንስ አልተመደበለትም። ሆኖም ኢትዮጵያ ተፈጥሮን መሰረት ላደረጉ መፍትሄዎች ያላትን ቁርጠኝነት የአንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን ይፋ በማድረግ አሳይታለች።

በዚህ ፕሮግራም ከ20 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በአራት ዓመታት ውስጥ ለመትከል አቅዳ ስትሰራ ቆይታለች። ፕሮግራሙን በተሳካ ሁኔታ መተግበር የመሬት መራቆትን በመቀነስ የህብረተሰቡን የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ችሎታውን ለማሳደግ፣ የተራቆቱ መሬቶች ወደነበሩበት ሁኔታ ለመመለስ፣ የተፋሰስ ሀይድሮሎጂንና የአፈር ለምነትን በመጨመር የስርዐተ ምህዳሩን ጤና ለማረጋገጥ እና የማህበረሰቡን የኑሮ ዘዴ ለማሻሻል ይረዳል።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮንና እርሱን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎች አካባቢ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለማቃለል ላላቸው ሚና ከፍተኛ ዕውቅና ሰጥታለች፡፡ የኢትዮጵያ የአካባቢ ፖሊሲ ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎች ውስብስብ የአካባቢ ችግሮችን እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለማቃለል ለሚኖራቸው አስፈላጊነት አፅንዖት ይሰጣል፡፡

በተመሳሳይ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂን መሰረት አድርገው የተሰሩት የኢትዮጵያ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ለውጥ ዕቅድ (NDC) እና አገራዊ የማጣጣሚያ ዕቅድ (NAP) ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ መፍትሄዎች ለአየር ንብረት ማጣጣሚያነት ያላቸውን ከፍተኛ ጠቀሜታ ላይ ትኩረት ሰጥቷል፡፡

እነዚህ ተግባራት የደን ጥምር እርሻን ከማስፋትና ዘላቂ ደን ልማት በተራቆቱ ስፍራዎች ላይ ከማካሄድ እስከ የስርዐተ- ምህዳርን ጤናን በስርዐተ-ምህዳራዊ የአስተራረስ ዘዴ ማሻሻል ድረስ ያካትታል። ከዚህ በተጨማሪም የአፈር መሸርሸርን የሚከላከሉ፣ የውሀን መጠን የሚጠብቁና የዕፅዋትን ሽፋን የሚጨምሩ የዘላቂ የመሬት አጠቃቀም ተግባራትን ሲያጠቃልል በተጨማሪም የስርዐተ-ምህዳር፣ የማህበረሰቡንና የመሰረተ ልማቱን አየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም ችሎታ ስርዐተ-ምህዳራዊ በሆነ መንገድ መጠበቅን ይመለከታል።

በተመሳሳይም በአገራዊ የማጣጣሚያ ዘዴ ስር የተለዩት ተግባራት ተፈጥሮን መሠረት ያደረጉ የአየር ንብረት ማጣጣሚያዎችን አካተዋል። ይህም የግብርና ምርትን ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆነ ትግበራ መንገድ በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ መሬትንና የውሀ ተፋሰስን በመጠበቅ ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ማጠናከር፣ ብዝሀ-ህይወትን በመጠበቅ የስርዐተ-ምህዳር አልበገሬነት ማረጋገጥን ከአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ማጠቃለያ

በሰው ምክንያት የተፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ ለሰው ልጅ ትልቅ ፈተና ከሆነ ከራርሟል፡፡ የችግሩ መንስኤ የሰው ልጅ አኗኗር በተፈጥሮ ሀብት ላይ የተመሰረተ እና በተለያዩ ምክንያቶች በተፈጥሮ ሀብት ላይ የደረሱ ውድመቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በቀጣይ በሰው እና በንብረት ላይ ሊፈጠር የሚችለው ከአየር ንብረት ለውጥ የሚመነጭ ችግርን ለመቋቋም ተፈጥሮ ሃብት ላይ የደረሰ ጉዳት ማከም ግድ ሚል ሲሆን፤ ይህን ለማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ ታቅዶ እየተሰራ የሚገኘው አገር አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላን ስኬታማ ለማድረግ አጠናክሮ መቀጠል ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው፡፡



17

33 32 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

የአፍሪካ ጉዳይ

የአንድ አገር ኢኮኖሚ “ጤነኛ ነው” የሚባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ሲጠጣም ነው፡፡ ፍላጎቱ በዝቶ አቅርቦቱ ካነሰ ወይም አቅርቦቱ እያለ ከዋጋ አኳያ ተደራሽ ካልሆነ፤ እንዲሁም አቅርቦቱ እያለ በቂ ፈላጊ ከሌለው ኢኮኖሚው ተፈጥሮአዊ ዑደቱን ጠብቆ በአግባቡ እየሄደ እንዳልሆነ ያመላክታል፡፡

ሰዎች ተሰባስበው በአንድ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ድረስ የመንግስታት አንዱና ዋናው ሃላፊነት የሚያስተዳድሯቸውን ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስጠበቅ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ መንግስታት የተለያዩ ህጎችን የማውጣት፣ ልማትን የሚያፋጥኑ ፖሊሲዎችን ቀርፆ ተግባራዊ የማድረግ፣ የምርት እጥረት በሚስተዋልበት አጋጣሚ ሁሉ ጣልቃ በመግባት ምርትን ወይም አስፈላጊውን ቁስ በተቻለ መጠን በማቅረብና አገልግሎቶችን በመስጠት የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ጣልቃ ሲገባ ይስተዋላል።

ኢኮኖሚ አገር እንደአገር፣ መንግስት እንደመንግስት እንዲቀጥል ያለው ሚና የጎላ ከመሆኑ አኳያ ስልጣን ላይ ባለ መንግስት ቅሬታ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢኮኖሚው በተስተካከለ መንገድ እንዳይጓዝ የማድረግ ስራ የሚያከናውኑበት ወቅት በርካታ ነው። በተለይም ከውስጥም ከውጪም ያሉ የመንግስት ተቃዋሚዎች ኢኮኖሚውን በመረበሽና የተፈለገውን ውጤት እንዳያመጣ በማድረግ መንግስትን ተቀባይነት ለማሳጣት እንደ አንድ የፖለቲካ መታገያ ስልት እነደሚጠቀሙበት መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሌላም በኩል ገንዘብ መሰብሰብ እና የግል ሀብትና ንብረት ማካበትን ዓላማ ያደረጉ በየደረጃው የሚገኙ ትርፍ የማይበቃቸው ነጋዴዎች ኢኮኖሚው ጤነኛ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉ ተግባራትን ሲያከናውኑ ማየት ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተለመደ

አገራዊ ኢኮኖሚ ከተግዳሮት ባሻገር

የሰነቀው ተስፋ



18

35 34 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

መጥቷል።የዚህ ዓይነቱ ተግበር በባለሙያዎቹ የኢኮኖሚ አሻጥር /economic sabotage/ በመባል እንደሚጠራ የፍትሕ ሚኒስቴር ”የኢኮኖሚ አሻጥር ምንነት እና ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ህጋዊ አንድምታዎቹ” በሚል ርዕስ ካስነበበው ጽሁፍ መረዳት ይቻላል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ መጥቷል። የዚህ ዓይነቱ ተግባር መስፋፋትና መጨመር የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ስለ ኢኮኖሚ አሻጥር ምንነት እና በአገራችን ያለው ገጽታ እንዲሁም አሻጥሩ በማክሸፍ “የተረጋጋ ኢኮኖሚ ስርዓት ለመፍጠር ያስችላል” ተብሎ ወደ ስራ የገባው አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ በተመለከተ እንዳስሳለን፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር እና የማሰፈጸሚያ ስልቶቻቸው

ዳንኤል ፕሮቶር የተባሉ ኢኮኖሚስት የኢኮኖሚ አሻጥር የአንድ አገር አጠቃላይ ኢኮኖሚ እንዳያድግ፣ ውጤታማ እንዳይሆን፣ አቅም እንዲያንሰው እና ኢኮኖሚው የሚመራበት ሥርዓቱ እንዲረበሽ በማድረግ በመንግስት ላይ ተጽእኖ የመፍጠሪያ ስልት እንደሆነ ያትታል።

በአገሮች ታሪክ የሚሳሳቡና የሚገፋፉ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ይኖራሉ። ቡድኖቹ ማሕበረ ፖለቲካዊ ልዩነት መሰረት የበላይነትን ለማግኘት ይንቀሳቀሳሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ድጋፍ ማሰባሰብ የግድ ስለሚሆን ድጋፉን ለማግኘት አንዱ ቡድን ሌላው ላይ ጫና መፍጠሩም የማይቀር ነው። ለዚህ ደግሞ የፖለቲካና የምጣኔ ሀብት ተዋናዮች ተሳትፎ በብርቱ ስለሚሻ ድጋፍ ማሰባሰቢያና ድጋፍ ማሳጫ መንገድ አሻጥር (sabotage) ተድርጎ ሊወሰድ ይችላል።

የኢኮኖሚ አሻጥር በአገሮች ላይ ከሚያጋጥሙ ክስተቶች እንደ አደገኛ ሁኔታ የሚወሰድ ነው። ሁኔታው ሰላማዊ የአገሮች ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን መረበሽና ማወክ ነው። በአመዛኙ የሚደረገውም መንግስታት ላይ ጫና ለማሳረፍ ነው።

ዋና ዓላማው ሕዝብ መንግስት ላይ ተስፋ እንዲያጣ፣ በቁጣ እንዲነሳ ማድረግ ሲሆን፤ ከሚፈጸምባቸው መንገዶች አንዱ የሸቀጦች ዋጋ በድንገት እንዲያሻቅብ ማድረግ ነው። ይህ እንደ ቀዳሚ ሊሆን ይችላል እንጂ አፈጻጸሙ እንደ አገሮቹ ሁኔታ፣ እንደ ዘመኑ የሚወሰን ይሆናል። በአብዛኛው ለኢኮኖሚ አሻጥሩ ሰለባ ከሚሆኑ ሸቀጦች መካከል ነዳጅ፣ ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ይጠቀሳሉ።

የኢኮኖሚ አሻጥር ተለዋዋጭ መልኮች አሉት። አንደኛው በቂ የሸቀጥ አቅርቦት በገበያ ላይ ባለበት ወቅት ሆን ተብሎ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ምርቱን ከገበያ በመሰብሰብ የማከማቸት ተግባር በመፈጸም እጥረት ማስከተል ይሆናል።ሁለተኛው በቂ ሸቀጥ ገበያ ላይ ሳይኖር ሲቀር፤ አሁንም እነዚሁ ቡድኖች ሆን ብለው ኢኮኖሚያዊ

መስተጓጎሎችን ለመፍጠር ምርቱን በፍጥነት ከገበያ ላይ በመሰብሰብ ማጥፋት ነው።

የኢኮኖሚ አሻጥረኞች ትኩረት አድርገው የሚነሱት ገበያውን ነው። ዋናው ተግባራቸው በማንኛውም መንገድ በገበያው ላይ የአቅርቦት እጥረት ተፈጥሮ ፍላጎት እንዲንር ማድረግ፣ የህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ማዳከም ወይም ከሚፈለገው በላይ አቅርቦት የገበያው ሥርዓት ሚዛኑን እንዲስት መስራት ነው።

ይህ ኩነት ገበያው ላይ እንዲገለፅ ከጀርባ ዓይነተ ብዙ አሻጥሮች ይሰራሉ፡፡ ገበያ በአግባቡ ካልተመራ የአንድን አገርን ኢኮኖሚ ለመጉዳት እና መንግስትን ለማዳከም መሳሪያ ሆነውም ያገለግላሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኢኮኖሚ አሻጥሩን ከውጭ ምዕራባውያን በወኪሎቻቸው አማካኝነት የየአገሮቹን መንግስታት ለማንበርከክ ይጠቀሙበታል። በአገሮች ላይ በተለይ በሶስተኛ ዓለም አገሮች ላይ የፖሊሲ ጫና ለመፍጠር፣ ፍላጎታቸውን የሚያስፈጽሙ መንግስታትን ለማግኘት ጥቅም ላይ ያውሉታል። እነዚሁ አካላት፣

የሚሳተፉባቸው የንግድ ሰንሰለቶችን በማደናቀፍ፣ ቀረጥ በመጫንና በመጨመር አሻጥሩን የሚቀላቀሉበት ጊዜ አጋጥሞ ያውቃል፤ የተለመደም ነው።

አንደኛው የኢኮኖሚ አሻጥር መስፈፀሚያ ስልት እቃዎች ከተመረቱበት ዓላማ ውጪ ምክንያታዊ ከሆነ ጊዜ በላይ ይዞ የማቆየት ተግባር ወይም ምርቶችን ማከማቸት ነው፡፡ ምርቶችን ማከማቸት ለተለያየ ዓላማ ሊፈፀም ይችላል፡፡ የመጀመሪያው ዋጋ በመጨመር የተሻለ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ሲሆን፤ ሌላው እና ውስን የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦች ተናበው የሚሰሩት ሰው ሰራሽ የእቃዎች እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዲሳድር ማድረጊያ ስልት ነው። ይህም ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲያጉረመርም፣ ሰላም እንዲጠፋና አመጽ እንዲነሳ ከዚያም አልፎ የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ ዓላማን ይዞ የሚፈፀም ነው፡፡

በተለይ የውጪ አገር ገንዘቦችን ከባንኮች ቁጥጥር ውጪ በማድረግ የፋይናንስ ስርዓቱን መረበሽ (ጥቁር ገበያ)

የሌላኛው የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፈጸም የሚረዳ ዘዴ ነው፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አብዛኛው የፍጆታ እቃዎች ከውጪ በሚያስገቡ እና የወጪ ንግድ ሚዛናቸው ያልተመጣጠነ በሆነ አገሮች የውጪ ምንዛሪ ያለው ሚና እጅጉን የጎላ ነው፡፡ ይህን ሚናውን በመሰናከልና የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በገበያው ላይ ጫና የመፍጠር ተግባር መፈጸም ከኢኮኖሚ አሻጥሩ አንዱ ተደረጎ ይወሰዳል።

መንግስት የህብረተሰቡን ፍላጎት ከመድሃኒት ጀምሮ እስከ አልባሳት እና ጥቃቅን እቃዎች ጭምር አብዛኛውን የሚያሟላው ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ሲሆን፤ እነዚህ ምርቶች የሚገዙት ደግሞ በውጪ ምንዛሪ ነው፡፡

በአንድ አገር ውስጥ ህገወጥ የገንዘበ ዝውውርና የጥቁር ገበያ መስፋፋት መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን የውጪ ምንዛሪ እንዳያገኝ ያለውንም በአግባቡ እንዳይጠቀም ያደርገዋል። በተለይ ህጋዊ ነጋዴዎች ከባንኮች ማግኘት የሚገባቸውን የውጪ ምንዛሪ ያሳጣቸዋል።

ቀስ በቀስ ህጋዊ ነጋዴዎችም የውጪ ምንዛሪ ፍለጋ ጥቁር ገበያውን ይቀላቀላሉ። ለአብነት የጥቁር ገበያ የዶላር ዋጋ

ከባንኮች ይልቅ ከፍተኛ በመሆኑ በውጪ ምንዛሪው የሚመጣው እቃ ዋጋም በዚያው ልክ ከፍ ይላል ወይም ከውጪ የሚገቡ እቃዎች እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል። በአገር ውስጥ የሚመረቱት ደግሞ ዋጋቸው ይጨምራል። ሁኔታው ከሰፋና ከተደጋገመ ሁሉን አቀፍ የዋጋ ግሽበት በማስከተል አጠቃላይ ኢኮኖሚውን ሊገዳደር ይችላል፡፡

የአገልግሎት ወይም የምርት ሂደት ማቋረጥም የኢኮኖሚ አሻጥረኞች ዓላማቸው ለማስፈጸም የሚጠቀሙበት አንዱ ዘዴ ነው፡፡ አንዳንድ የምርት ወይም የአገልግሎት ዓይነቶች በባህሪያቸው በሚወስዱት ካፒታል፣ በሚጠቀሙት የተማረ የሰው ሀይል የተነሳ በውስን ሰዎች የሚሰሩበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡

የእነዚህ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት ባለቤቶች ለግል ወይም ፖለቲካዊ ዓላማቸው መሳካት ሲሉ ምርቶቹን እና አገልግሎቶቹን በማቋረጥ የእቃዎች እና አገልግሎቶች እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንዲከሰት የሚያደርጉበትም ሁኔታ ይስተዋላል፡፡

የተለያዩ እቃዎች መንግስት ያስቀመጠው የቁጥጥር

ስርዓትን ሳያልፉ እና ተገቢው ቀረጥና ታክስ ሳይከፈልባቸው በድብቅ ወደአገር ውስጥ ማስገባት እንደ ኢኮኖሚ አሻጥር ማስፈጸሚያ ስልት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ይህ ተግባር የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ያሉት ሲሆን፤ የመጀመሪያው መንግስት በቀረጥና ታክስ መልክ ሊያገኝ የሚገባውን ገንዘብ እንዳያገኝ ያደርጋል። በመቀጠል የእቃዎች ዋጋ እንዲረክስ በማድረግ ህጋዊ ነጋዴዎች ከገበያ ያስወጣል። አለፍ ሲልም ጥራታቸውን ያልጠበቁ እቃዎች፣ መንግስት የማያውቃቸው ገንዘቦች፣ ጦር መሳሪያዎች እና የመሳሰሉት ወደአገር ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ለማስከተል ለሚፈልጉ ሃይሎች ጉልበት ይሰጣቸዋል።

ሕገወጥ ሃዋላ ሌላኛው የኢኮኖሚ አሻጥር ማስፈጸምያ ስልት ነው፡፡ ወደ አንድ አገር የሚገባ ወይም ከአንድ አገር የሚወጣ ገንዘብ በተዘረጋ የፋይናንስ ስርዓት ውስጥ ማለፍ እና ፈቃድ በተሰጣቸው ፋይናንሻል ተቋማት አማካኝነት ማለፍ ይኖርበታል፡፡

ይህ ካልሆነ በዚህ ገንዘብ የመላክ እና የመቀበል ሂደት አገሪቷ ማግኘት የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ እንዳታገኝ ያደርጋል፡፡ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራት በህገወጥ አስተላላፊዎች አማካኝነት ፈቃድ ከተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ ሲደረግ የአገሪቷን ኢኮኖሚ የማዳከም እና በመንግስት ላይ ጫና የመፍጠር ውጤት ያለው ተግባር ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ “ህገወጥ የሆነ የከበሩ ማዕድናት ንግድ እና ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርም የኢኮኖሚ አሻጥረኞች ለሚፈልጉት ድብቅ ዓላማ ለማሳካት ይጠቀሙበታል” ሲል ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘው ጽሁፍ ያትታል፡፡

የኢኮኖሚ አሻጥር እና በተለያዩ አገሮች ለማሳያ

የኢኮኖሚ አሻጥር በተለያዩ አገሮች ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፤ ዚምባብዌን እንደ ማሳያ ብንመከለት በአንድ ወቅት ደቡብ አፍሪካ በዚምባብዌ ውስጥ ያላትን የትራንስፖርት ተሳትፎ በማወክ የዚምባብዌን ኢኮኖሚ እንዳቃወሰች በታሪክ ተሰንዷል።

የቀድሞዋ ሮዴሺያ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴዋ በደቡብ አፍሪካ ላይ የተንጠለጠለ ነበር። ዚምባብዌ ሸቀጦቿ ለደቡብ አፍሪካ ገበያ ነበር የሚቀርቡት። ይህ ብቻ ሳይሆን ለገቢ እቃዎችም የደቡብ አፍሪካ ወደቦችን ትጠቀማለች። ለዚህ አገልግሎት አገሪቷ ወድ ዋጋም ትከፍል ነበር ። 90 በመቶ የዚምባብዌ ንግድ መተላለፊያው ጉዞውን የሚያደርገው በደቡብ አፍሪካ በኩል ነበር።

ይህ ሆኖ በደቡብ አፍሪካ በኩል በተከሰተ ችግር በዚምባብዌ የኑሮ ውድነት በድንገት ሰማይ ነካ። ሕዝቡ መሰረታዊ ፍጆታዎችን ማግኘት እያቃተው ሲሔድ መንግስት ላይ ጫናውን በረታ።



19

37 36 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ዚምባብዌ ሌሎች ጎረቤት አገሮችን ጭምር ለምርት መተላለፊያነት ለመጠቀም አስባ ሊሳካላት አልቻለም። በነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ጫና ውስጥ የገባው የዚምባብዌ ኢኮኖሚ በስተመጨረሻ ለአሻጥር ተጋለጠ።

በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው አሉታዊነቱ ብቻ ሳይሆን ቁጭት በመፍጠር አዎንታዊ ሚናም አለው። በዚህ ክስተት ዚምባብዌ ከጥገኝነት ወጥታ ራሷን ለማቻል እንድተንቀሳቀስ እድል አግኝታለች። በኢኮኖሚም በፖለቲካም ዘርፍ። በአሉታዊ ጎኑ መንግስትን ረፍት ከመንሳት ባለፈ የዜጎችን እለታዊ እንቅስቃሴ አቃውሷል፤ ጊዜያዊ መንገላታትን ፈጥሮ፤ በመንግስት ላይ ቅሬታን አስነስቷል። ሆኖም ለዚምባብዌ እድትልወጥ ዕድል ሰጥቷተል። ይህኛው ውጫዊ ጫና ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።

ከአስር ዓመት በፊት የባህረ ሰላጤው አገሮች ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ በጸደይ አብዮት ምክንያት ከፍተኛ መቃወስ አጋጥሞት ነበር። የእነዚሁ አገሮች መሪዎች ዴሞክራሲ ጠል መሆናቸውን መነሻ አድረገው በጀመሩ አመጾች ምጣኔ ሀብቱ ለአሻጥር ተጋልጦ ነበር። በነበረው አመጽ ምክንያት የስራ መቀዛቀዝ የተሰተዋለ ሲሆን፤ ሰራተኞቹም የአመጹ ዋና ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ለምሳሌ በኦማን በነበረው ሕዝባዊ አመጽ የነዳጅ ምርት መቀነስ ታይቶ ነበር። ኦማናውያን የተሽከርካሪዎች ጉዞ አግደዋል። ዋና ዋና መተላለፊያ መንገዶችን ዘግተው ከፍተኛ መስተጓጎል ፈጥረዋል። በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ወደ ሰፋፊ የግንባታ ስፍራዎች ባለመሔዳቸው የግንባታ ስራ

ተቋርጧል።

በባህሬንም የነበረው አመፅ በከፍተኛ አሻጥር ታጅቦ አገሪቷን አመሰቃቅሏት እንደነበረ ተመልክቷል። በጥቅሉ በባህረ ሰላጤው አገሮች የነበረው አሻጥር አምራች ኢንዳስትሪዎችን፣ ሰፋፊ ግንባታዎችንና የቱሪዝም ዘርፉን አቃውሷል። አጋጥሞ የነበረው የኢኮኖሚ መቃወስም አገሮቹ ለከፍተኛ ክስረት ዳርጓል።

ይህ ማለት አሻጥር አመጽን ሽፋን አድርጎ የሚፈጸም መሆኑን ነው። እንዲህ ዓይነት አካሄዶች ዋና ግባቸው በስልጣን ላይ ያለውን የፖለቲካ ድርጅት ወይም መንግስት ማደከም፣ ከሥልጣን ማውረድና በሌላ መተካት ነው። አሁንም ዋና ዋና አሻጥረኞች ከኋላ ሆነው ፍላጎታቸውን ያስፈጽማሉ።

ለዓመታት በፖለቲካዊ ቀውስ ስትናጥ በኖረችው ቬንዙዌላ ውስጥም የኢኮኖሚ አሻጥር ሲፈጸም መቆዬቱ ተሰንዷል። እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር መስከረም 2013 ዓ.ም በአገሪቷ ከፍተኛ የኤሌክትርክ ኃይል አገልግሎት መቋረጥ አጋጠመ። የኃይል መቋረጡ በኤሌክትርክ አማካኝነት ስራቸውን የሚያቀላጥፉ ግለሰቦችና ድርጅቶች፣ መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ጭምር አሰናክሏል። ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ በቀጥታ የተቋዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በፈጠሩት የፖለቲካ አሻጥር የኃይል መቋረጡ እንዳጋጠመ ይፋ አደረጉ። በተጨማሪም የዶላር ምንዛሬ መንግስት ከሚመነዝረው በስድስት እጥፍ በጥቁር ገበያ ይመነዘር ጀመረ። አሻጥሩ አጠቃላይ የአገሪቷን ማክሮ ኢኮኖሚ ስርዓት አቃወሰ።

የኢኮኖሚ አሻጥር በአገር ውስጥ ያለን መንግስት ከመጫን ባለፈ አንድ አገር የሌላኛውን አገር መንግስት በማጥቃት እጅ ለመጠምዘዝ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡

በተለይም ኃያላን አገሮች ከእነሱ ጥቅም ተቃራኒ ሆኖ በሚቆም መንግስት ላይ የመጀመሪያው የሚወስዱት እርምጃ በኢኮኖሚ አሻጥር መንግስቱን ማዳከም ሲሆን፤ አሻጥር የሚፈፀምበት መንግስት አሻጥሩን መቋቋም ሲያቅተው ታዛዥ መንግስት ሆኖ ይቀጥላል አልያም በህዝባዊ አመፅ እንዲወገድ ይደረጋል፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ስውር እጆች

ከአራት አመት በፊት በኢትዮጵያ በተካሄደ ህዝባዊ ንቅናቄ ለውጥ ተከስቷለ። አዲስ መንግስት ተመስርቷል። አዲሱ የለውጥ መንግስት በትረ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ማግስት ጀምሮ በአገሪቱ በርካታ እረምጃዎች መውሰዱ ይታወቃል። የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራትን በአጭርና በመካከለኛ የጊዜ ገደብ ለመመለስ የሚያስችሉትን ተግባራት በማከናወን የለውጡን ቀጣይነት እውን አድርጓል። መንግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የወሰዳቸው እርምጃዎችና የተመዘገቡት ውጤቶች እነደተጠበቁ ሆኖ በተለያየ መልኩ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲከሰት መቆየቱ የአደበባይ ምሥጢር ነው። መንግስት ባካሄዳቸው ግምገማዎቸም የኢኮኖሚ አሻጥሮች መኖራቸውን አረጋግጣል።

ከእነዚህ መካከል አንዱ የንግድ እቃዎችን በማጓጓዝ ሂደት ተደጋጋሚ መስተጓጎሎች መፍጠር ተጠቃሽ

ነው። ይህም በተወሰነ መልኩም ቢሆን ኢኮኖሚውን ረብሾታል። በተመሳሳይ የዶላር ጥቁር ገበያ ዋጋም ከፖለቲካ ንፋስ ጋር አብሮ የሚነፍስ መሆኑም ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ድንገተኛ ሰማይ ጠቀስ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት ያደረጉ ከመጠን ያለፉ ክምችቶችም ተገኝተዋል። ከዚህ በዘለለም የኤሌትሪክ ሃይልና የቴሌኮም መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ ድርጊቶች ችግሩን አሳሳቢ ማድረጋቸው እሙን ነው።

ባለፈው አንድ ዓመት የኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ የሕልውናና የሕግ ማስከበር ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ። ይህን ወቅት እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀሙ የሽብር ቡድኑ ቅጥረኞችና ከእርሱ ጋር ትስሰር ያላቸው የኢኮኖሚውን ሥርዓት የመረበሽ ሙከራ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሌሎች ነገሮች እንዳሉ ቢሆኑም እንኳን በቅርብ ወራት ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዲከሰት የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ አስተዋጽኦ አላቸው። የማዕከላዊ ስታስቲከስ ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ባለፉት ወራት ብቻ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ እስክ 42 በመቶ ድረስ ጭማሪ አሳይቷል። ሁኔታው ዝቅተኛ ተገቢ መጠን ያላቸውን ዜጎች ብቻ ሳይሆን መላውን ሕዝብ እየጎዳው መሆኑን ያመላክታል። የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ መምጣቱ አሳሳቢ ሆናል።

በርግጥ አሁን ለተፈጠረው አገራዊ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ውስጣዊና ውጫዊ ምክንያቶች መኖራቸወን ማስተዋል ይቻላል። የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የፈጠረው ዓለምአቀፍ ተጽእኖ አንደኛው ጉዳይ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በዩክሬንና በሩሲያ መካከል የተከሰተወ ጦርነት ሌላው ተጠቃሽ ነው። በዚህ ላይ የአገር ውስጡ የኢኮኖሚ አሻጥር ሲጨመር ችግሩን ከሚገባ በላይ አሳሳቢና ውስብሰብ ማድረጉ አውነት ነው።

የፕላንና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም ከዘመን መጽሄት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ “ከዋጋ ግሽበቱ ጋር ተያይዞ የመጣው የኑሮ ውድነት ዜጎቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያማረረ እና እያስጨነቀ ያለ መሆኑ እውነት ነው” በማለት ገልጸውታል። እንደውም መንግስት የአገር በቀል የኢኮኖሚ መሻሻያ ተግባራዊ ባይደረግ ኖሮ ችግሩ ከዚህም ይከፋ እነደነበር ነው ያመለከቱት።

የኢኮኖሚው አሻጥር በግልጽ እንደሚታየው በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ስራዎችን ለማስተጓጎል አሻጥረኞች በተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች ከፍተኛ የብረት ክምችት አስቀምጠው መገሸታቸውን በአብነት ማንሳት ይቻላል። በመሰረታዊ ፍጆታም ላይ አሻጥረኞቹና ሕግ ወጥ ደላሎች በጋራ ሆነው ኢኮኖሚውን በመረበሻቸው የአንድ ኪሎ ግራም ሽንኩርት ዋጋ እስከ 50 ብር ደርሶ እንደነበር ይጠቀሳል።

ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን መንግስታት በተለያዩ ጫና ውስጥ በገቡ ጊዜ አጋጥሞ ያውቃል። የኢትዮጵያ መንግስት ዋና ትኩረቱ የሕልውና ጦርነት ላይ መሆኑን

በመመልከት በርካታ ራስ ወዳዶች ኢኮኖሚያዊ አሻጥር ውስጥ እንደሚሳተፉ ተገማች ጉዳይ ነው። ለዚህ የመንግስት ብርቱ ክንድም አስፈላጊ ነው።

አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ስርዓት እንደ መገንቢያ

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢኮኖሚ እድገትን በቀጣይነት ለማረጋገጥ እና ለተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል በመስከረም 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ቀርጾ በሥራ ላይ አውሏል።

ዕቅዱ ኢትዮጵያ በቀጣይ አስር ዓመታት ውስጥ ግብርና መር ከሆነ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ፣ ዝቅተኛ ገቢ ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እንድትሸጋገር ያለመ ነው። በአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ምሶሶዎች የኢኮኖሚ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት፣ ጥራት ያለው ዕድገትና የጋራ ብልጽግና፣ ዘላቂ የልማት ፋይናንስ፣ የግሉ ዘርፍ እድገት መሪነት፣ የሴቶች ተሳተፎ እና ማሀበራዊ አካታችነት፣ ዘላቂ ሰላም እና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትብብር፣ የፍትህ ተደራሽነትና የህዝብ አገልግሎት፣ የሥርዓታት ለውጥ፣ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ፣ የቴክኖሎጂ አቅምና ዲጂታል ኢኮኖሚን የትኩረት መስኮቹ አድርጓል።

በማክሮ ኢኮኖሚ፣ በመዋቅር እና በዘርፎች አኳያ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ አተኩሯል። የልማት ዕቅዱ አግባብነት ያላቸውን ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች በመተግበር ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና አገራዊ አቅምን ለማጠናከር ይረዳል።

የገንዘብ ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ሲናገሩ “የማሻሻያ ፕሮግራሞቹ ያስፈለጉት (macro fi- nancial stability) ወይም የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ መገንባት ሆኖ ኢኮኖሚው በቀጣይነት እያደገ የሚመጣ፣ ሸማቹ፣ ኢንቨስተሩ፣ ሕዝቡም የሚተማመንበት ጠንካራ የፋይናንስ ስርዓት እንዲሁም በቅርብ ዓመታት ያጋጠሙ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የዋጋ ግሽበት፣ የእዳ ጫና፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረት፣ የንግድ ሚዛን መዛባትን ማስተካከልን ማዕከል ያደረገ የኢኮኖሚ እቅድ ነው” ይላሉ።

እንደዶክተር እዮብ ገለጻ፤ ለልማት ዕቅዱ መሳካትና እውን መሆን የፋይናንስ ስርዓቱን በማዘመን ረገድም ባንኮች በርካታ ማሻሻያ ስራዎች ይሰራሉም።

‘’እስካሁንም ብሔራዊ ባንክ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። የአቅም ግንባታ ስራዎችና የፋይናንስ ስርዓቱን የማዘመን፣ የገንዘብ ፖሊሲን የማዘመን ስራ ተሰርቷል። በዚሁ መሰረት የውስጥ ሚዛኑን ለማስጠበቅ የገቢ ማሰባሰብ ስራ በሰፊው ተሰርቷል።

አሁንም ቢሆን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ አኳያ

ብዙ መዛባት አለ። ይህ ደግሞ ገቢ ከአገራዊ ምርት ጋር ካለው ድርሻ ጋር ሚዛን ለማስጠበቅ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርጓል። የቁርጥ ግብር አሰራሮችን ለማስተካከል፣ ከክልሎች ጋር በመነጋገር ስራዎች ተሰርተዋል’’ ነው ያሉት።

ከዚህም አልፎ “የኤክሳይስ (የቅንጦት እቃዎች) ታክስ ማሻሻያ መደረጉን፣ የጉምሩክና የገቢዎች የውስጥ አሰራር እንዲዘምን ማድረግ፤ የብሔራዊ ባንክና የገንዘብ ሚኒስቴር አሰራርም ተሳስሯል” በማለት ነው ለአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተደረገ መሆናቸውንነው የገለጹት ዶክተር እዮብ።

ይህ ብቻ ሳይሆን ‘የገንዘብ ፖሊሲው የዋጋ ግሽበት እንዳያስከትል ክትትል እየተደረገ ወደ ካፒታል ገበያ የመሔድና የብር marginal productivity ውጤታማ ሆኖ “ገንዘብ ስራ ላይ ማዋል የሚያስችል የዘመነ የፋይናንስ ስርዓት ያስፈልጋል’ በሚለው እሳቤ መሰረት መሻሻያዎች እየተሰሩ ነው” ብለዋል።

እንደዶክተር እዮብ ገለጻ፤ በቁንጽል መልኩ ለተወሰኑ አካላት ሲሸጥ የነበረው የግምጃ ቤት ሰነድ ክፍት ተደርጓል። የእዳ ጫናውን ለመቀነስ የመንግስት ኢንቨስትመንት ውጤታማና በተመረጡ ዘርፎች ላይ እንዲሆኑ የብድር አለቃቅ ሥርዓቱ በሳይንሳዊ መንገድ እንዲመራ ስራዎች ተጀምሯል።

“ድርጅቶቹ በተለያየ መልኩ ወደ ውድድር ስራ መቀላቀል እንዲችሉም ይደረጋል” ይላሉ ሚኒስትር ደኤታው። ሁኔታው ሁሉን ዓቀፍ መሆን ስላለበት የሎጂስቲክስ ስርዓቱን ማሳለጥም ግድ የሚል ነው። አንዱ የንግድ ሚዛን መዛባቱ መንስኤ “የሎጂስቲክስ ችግር መሆኑም ታውቋል” ብለዋል።

እንድ ዶክተር እዮብ ገለጻ፤ ትልቅ ሀብት ያላት አገር ራሷን መመገብ አለመቻሏ ትልቅ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት መኖሩን የሚያረጋግጥ ነው። ችግሩን ለማስተካከል በዋናነት በዘርፍ በዘርፉ ስራዎችን ማቀላጠፍ አንድና ዋነኛው መንገድ ነው። በዚህም በቀዳሚነት በግብርና ዘርፍ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት አበረታች እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።

የግብርናውን ዘርፍ ማሻሻል የሚችሉ አቅርቦቶች የማሟላት ስራ እየተሰራ ይገኛል። ኮምባይነሮች፣ ትራክተሮች፣ ሌሎች ግብርናውን የሚደግፉ መሳሪያዎች ያለ ቀረጥ ወደ አገር ወስጥ እንዲገቡ ማድረግማ ሌላው መንገድ ነው። ‘የኢትዮጵያ ማሳዎች የትራክተር ጩኽት የሚሰማባቸው መሆን አለባቸው’ ይላሉ ዶክተር እዮብ።

ሌላው የግብርና ፋይናንስ ስራን ማቀለጠፍ ሲሆን፤ ይህ አነስተኛ ገበሬዎችን መደገፍና ለወጪ ንግድ የታሰቡ የግብርና ምርቶችን በስፋት ለማምረትም ይረዳል ባይ ናቸው። “ከግብርናው ዘርፍ ባለፈ አምራች ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን ዘርፍ፣ ቱሪዝም ዘርፍ፣ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዋናና



20

39 38 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ቁልፍ ተብለው የተለዩ ናቸው” ይላሉ ሚኒስትር ደኤታው ዶክተር እዮብ። እነዚህን ዘርፎች የማነቃነቅና የመነቃቃት ስራ መስራትም አስፈላጊ ነው።

የአገር በቀል የኢኮኖሚው ማሻሻያ መደረጎ በግብርናው ዘርፍ ውጤት ለማስገኘት ችሏል። ይህ የዓለምን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ግብርናውን ዘርፍ በመለወጥ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ እንደሚቻል ታምኖ መታቀዱ ውጤት አሳይቷል።

በላፉት ሶስት ዓመታት ለግብርናው ልዩ ትኩረት በመሰጠቱ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ ግብዓቶች አቀርቦት ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መንገድ የሚያገኝበት ሁኔታ ተመቻችቶለታል። የግብርና ማዘመኛ ቴክኖሎጂዎችና በርካታ የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መደረጉ ነው የሚወሳው።

ከዚህ ቀደም ያልነበረ የበጋ ስንዴ ምርት በስፋት መስራት መጀመሩ ግብርናው ወደፊት ለማስፈንጠር የሚችለውን አቅጣጫ፣ ከኢንዱስትሪው ጋር መመጋገብ የሚችልበትም መስመር መያዙን ነው መረጃዎቸ የሚያረጋግጡት።

በማዕድን ዘርፍ አነስተኛ ማዕድን አውጪዎችን በማደረጀት በዘመናዊ መልኩ ወደ ምርት እንዲገቡ የማድረጉ ስራ በስትራቴጂ ተደግፎ ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል። ዘርፉ ውስጥ የነበሩ ችግሮችን መፍታትም ተችሏል።

በቱሪዝም ዘርፍም ቢሆን የግል ዘርፉን በስፋት የማሳተፍ ስራ፣ ማበረታቸዎችን እንደ አሰፍላጊነቱ ማቅረብ የግድ

ከሚሰሩ ስራዎች መካከል መሆናቸውን ተመልክቷል። ያለውን የቱሪዝም ሀብት በአግባቡ መለየትና ማልማትም ሌላው ስራ ነው።

በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክም ስራዎችን በቴክኖሎጂ የማስደገፉ ስራ ቁልፍ ተግባር እንደሆነ አመላክተዋል።

ለዚህ ደግሞ “የዲጂታል ስራዎችን ማቀላጠፍ፣ ኢትዮጵያን ‘ዲጂታል ሀብ’ የማድረግ ስራ ይከወናል” ብለዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን የ’ቴክኖሎጂ ኢንተርፕረነርሺፕ’ ማቀላጠፍ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የወጪ ንግድ ማከናወን ስራዎች በስፋት የሚካሄድበት ይሆናል እንደ ሚኒስትር ደኤታው ገለጻ።

በጥቅሉ አገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተቀናጀ መልኩ የሚተገበር የልማት እቅድ ነው። በመንግስት በኩል የሚወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች በአንድነትና ጎን ለጎን በማስኬድ የሚተገበሩ ናቸው። በዚህም ማክሮ ኢኮኖሚ ማሸሻያ፣ መዋቅራዊ ማሻሻያ፣ የዘርፍ ማሻሻያ ተያይዘውና ተናበው እንዲሄዱ ማስቻል አንዱ የችግር መፍቻ መንገድና የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻው ስኬት መሆኑን ነው ዶክተር እዮብ የሚያረጋግጡት።

ማሻሻያውና የአሰር ዓመቱ የልማት እቅድ ትስስር

የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው የአስር ዓመቱ የልማት እቅድ ራዕይ ዋና መሰረት ነው። ዋና ዋና ግቦቹም ሰፊ የስራ እድል መፍጠር፣ የዋጋ ግሽበት ማስተካከልና መቆጣጠር፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ (ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ማምረት)፣ የማክሮ

ኢኮኖሚ መዛባት ምክንያቶች መለዬትና ማስተካከልና መሰል ጉዳዮች ናቸው።

‘ኢትዮጵያ - አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት’ የማድረግ ራዕይ ሰንቆ የተዘጋጀውና ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበር የልማት እቅድ ኢትዮጵያ በተሻለ መልኩ ወደ ልማት ጎዳና የማስፈጠር ውጥን ነው።

‘’የልማት ዕቅዱ ለአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ ቀጣይ የስትራቴጂክ አቅጣጫዎችንና ዓላማዎችን በማስቀመጥ፣ አገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትንና ልማትን በረጅም ጊዜ ዕቅድ በመምራት፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የማምጣት ዓላማን ለማሳካት ብሎም ሀላፊነትንና ተጠያቂነትን በግልፅ በማስቀመጥ፣ ውጤታማና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልና የጋራ ብልጽግናን ለማስፈን ያስችላል’’።

በኢትዮጵያ ባለፈ ዓመታትበልማት ዕቅድ ትግበራ ወቅት በጉልህ የታዩ ችግሮችን በመለየትና በተለያዩ መልኮች የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተቀረጸው እቅድ እስካሁን ባለው ውጤት መልካም ሰኬቶችን አስመዝግቧል።

የውሀ ሀብት በሚገኝባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ምርጥ ዘር በመዝራትና የድግግሞሹን ብዛት በመጨመር የተሻለ ጥራትና ብዛት ያለው የስንዴ ምርት ማግኘት መቻሉ ለስኬቱ እንደአብነት መጥቀስ ይቻላል። በተጨማሪም በአገር ደረጃ በመካሄድ ላለው መስኖ ስንዴ ልማት ባለሙያዎችን በመመደብ የማሽኖች አጠቃቀም እና አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ቴክኒካል ድጋፍ

ማድረግ መቻሉ የጥንካሬ ምንጭ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በቅርቡ ያወጣው አንድ ጽሁፍ ያትታል።

ከጽሁፉ መረዳት እንደሚቻለው፤ የውሀ ሀብት በሚገኝባቸው አካባቢዎችም የመስኖ አውታሮች ግንባታ ተስፋፍቷል። የበጋ መስኖ ስንዴ ከመዝራት እስከ ምርት አሰባሰብ በተቀናጀ እና ብክነት በሌለበት ሁኔታ ተከናወኗል። አርሶ አደሮች በኩታ-ገጠም ተቀናጅተው የሚሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የበጋ ስንዴ ልማት እንደ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የፌዴራል ግብርና ተቋማት መሥሪያ ቤቶች፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ፣ ዩኒቨርሲቲዎችና በየደረጃው ያሉ የፌደራል እና የክልሎች የምርምር ተቋማት በጋራ የሚሰሩት መሆኑ የቅንጅት አሠራርን ለማጎልበትም ያግዛል፡፡

ምርት ወደ ገበያ በቀላሉ ለመቅረብ እንዲችልና የአርሶ አደሮችም ሆነ የሸማቾች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የገበያ ትስስርን ለማሳለጥ አምራቾች፣ ክልሎችና የህብረት ሥራ ማህበራት ትስስር ተፈጥሯል። በአገር ደረጃ የሚስተዋለውን የስንዴ እጥረት ለማቃለል በሁለት ዙር በመስኖ ስንዴ ልማት በአምስት ክልሎች (በአማራ፣ ደቡብ፣ አሮሚያ፣ ሲዳማና አፋር ክልሎች) 400 ሺህ ሄ/ር ለማልማት ሥራዎች ተከናውኗል። አመርቂ ውጤትም ተመዝግባል።

እስካሁን የተገኘው ውጤት አርሶ አደሩም ከባለሙያዎች ከሚያገኘው ግንዛቤ ብቻ ሳይሆን በሂደቱ ካካበተው ልምድ በመነሳት በቀጣይ ዓመታት ተጠናክሮ እንዲሰራ

መነቃቃት ሆኖታል። ከበጋ መስኖ ስንዴ እና አትክልት ምርት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም የሚደረጉ ጥረቶች፣ የቆላ ግብርና ያስገኟቸው ውጤቶች በትክክለኛው ጎዳና መጓዝ መጀመራችንን የሚያሳዩ መሆናቸው ነው በቅርብ ጊዜ የተደረገ ግምገማ የሚያመለክው።

የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ በኃይል፣ በትራንስፖርትና መገናኛ፣ በመስኖ የተፈጠሩት አቅሞች፣ ሊለማ የሚችል ከፍተኛ የሆነ የመስኖ አቅም፤ ሰብዓዊ ካፒታል፤ ዝቅተኛ የቴክኖሎጂና የምርታማነት ደረጃዎች እና ያልለሙ ዘርፎች እንደ አዲስ የዕድገት ምንጭ አቅሞች ለልማት ዕቅዱ እንደመነሻ መወሰዳቸው ለውጤታማነት ፈር ቀዳጅ ነው።

ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ አሁን ካጋጠሟት ችግሮች ትወጣ ዘንድ የመንግስት ውጥኖች ሊሳኩ ግድ ይላሉ። ከነዚህ መካከል ዋናው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጅምር ያሳየው ውጤት ነው። የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት ካለት የሰው ሀብት ጋር አጣምራ ጥቅም ላይ እንድታውል ትልቅ እድል እየፈጠረ እንደሚገኝ አመላካቾች አሉ። ይህኛው መንገድ ‘በራስ መንገድ ራስን መለወጥ’ የሚያስችል ነው። ለስኬቱም መንግስት የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውን የሚቀላጥፉ ተግባራትና የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገ አካሄድ እንዲኖር የሚተጋው።

አገር በቀል ኢኮኖሚው ይሳካ ዘንድ በአስር ዓመቱ ፍኖተ

ብልጽግና ይደገፋል። የአስር ዓመቱ የልማት እቅድ እንደ ውጥኑ ሁሉ ኢትዮጵያን አፍሪካዊ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እቅድና የሚጠበቅ ውጤት ተዘርዝሮ ተቀምጧል። እቅዱ ሁሉን አቀፍና አካታች ከመሆኑ ባለፈ ቀጣናዊ ሁኔታዎችን ቀጣይ የሚያገጥሙ ክስተቶች ጭምር በዝርዝር የታዩበት መሆኑ በተለዋዋጭ አገራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ሁኔታዎች ውስጥ እቅዱን ተፈጻሚ ማድረግ ያስችላል።

የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውም ይሁን የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለስኬት ይበቃ ዘንድ ሕገ ወጥነትና አሻጥር መወገድ ይጠበቅባቸዋል። በተለይ ደግሞ ኢኮኖሚን ማዕከል ያደረጉ አሻጥሮች ጉዳታቸው የትዬ ለሌ ከመሆናቸው አኳያ ተጋላጭነትን የሚቀንሱ አሰራሮች በስፋት ሊተገብሩ ይገባል። ሁሉም በላድርሻ አካላት አጠቃላይ ኢኮኖሚው ችገር ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ የኤኮኖሚ አሻጥረን መታገል ይጠበቅባቸዋል። ማህበረሰቡን ማንቃትና ኤኮኖሚ አሻጥረን እንዲያጋልጡ ማድረግ፣ አጥፊው ተጠያቂ እንዲሆን መስራት መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

ኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጽሙትን በሕግም ይሁን በሌሎች መንገዶች ተጠያቂ በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚውን ጤንነት ማስጠበቅ ይገባል። ይህም የኢትዮጵያውያንን ሁለንተናዊ የህይወት ፈተናዎች መቀልበስ ያስችላል። ለዚህም ሕዝባዊ ተባባሪነት አስፈላጊነት ጉዳይ ነው።



21

41 40 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

የአፍሪካ ጉዳይ

ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን …

በሶማሌ ክልል ቆራሄ ዞን ቀብሪደሃር በምትባል ከተማ 1981 ዓ.ም ነው የተወለድኩት። እስከ ሦስተኛ ክፍል ድረስ እዚያው ትምህርቴን ስከታተል ቆየሁ። ከሦስተኛ ክፍል በኋላ ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ሶዲንሶዶ ወረዳ አጨበር ወደ ምትባል የአባቴ ቤተሰቦች የሚኖሩበት ከተማ እንድሄድ ተደረገ። ጠዋት ትምህርት ቤት አሳልፋለሁ። ከሰዓት በኋላ እቤት ውስጥ ስራ ይጠብቀኛል።

በአብዛኛውን ጊዜ የማነበው ግን ከብቶችን ለግጦሽ አሰማርቼ ነው። ማታ ላይ በኩራዝ አጠናለሁ፤ ካልሆነም ሌሊት ማልጄ ተነስቼ ለማጥናት እና የቤት ስራ ለመስራት እሞክር ነበር። እስከ ስምንተኛ ክፍል ለመማር ብዙ መስዋዕትነት ከፍዬ በ1996 ዓ.ም ሚኒስትሪ ተፈተንኩ። በምኖርበት አካባቢ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አልነበረም፤ ትምህርት ቤት ወዳለበት ሄጄ ትምህርቴን ለመቀጠል ጥያቄ አቀረብኩ።

የቤተሰብ ምላሽ ትምህርት አቋርጬ ሙሉ በሙሉ ወደ ግብርና ስራው እንድገባ የሚገፋፋ ሆነ። በዚህ ምክንያት አለመግባባት ተፈጠረ እና በ2000 ዓ.ም እናት እና አባቴ ወደ ሚኖሩበት አካባቢ ለመሄድ ወሰንኩ። እዛም አልጋ በአልጋ የሆነ ሕይወት አልገጠመኝም። የአባቴ ዘመዶች ለወላጆቼ “ይህ ልጅ ወደ ከተማ መሄድ የፈለገው ቤተሰብ ለመርዳት

በፍቅርተ ባልቻ

የችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ …



22

43 42 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ፍቃደኛ ስላልሆነ ነው” ብለው ነግረዋቸው ስለነበር የእኔን ፍላጎት የሚረዳኝ ሰው አላገኘሁም።

የተለያዩ ሙያዎችን በመሰልጠን እራሴን ማስተዳደር ጀመርኩ። የውበት ስራ፣ የጉልበት ስራ ከሰዓት በመስራት ትምህርቴን ቀን ቀን እየተማርኩ በመቀጠል 10ኛ ክፍል ገባሁ። ቤተሰብ ለመለወጥ ያለኝን ጉጉት ከተመለከቱ እና በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጧቸው አቋማቸውን ለመቀየር ተገደደዱ። ይህ ተከትሎም ከሀሳብ ባሻገር በተወሰነ መልኩ በገንዘብ እና በቁሳቁስ ያግዙኝ ጀመር።

የማጠናከሪያ ትምህርት በመከታተል፣ የቋንቋ ትምህርት በመማር ክህሎቴን ለማሳደግ መትጋቱን ተያያዝኩት። በዚህ ሁኔታ፣ በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፌ የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ብጥርም ወደ መሰናዶ የሚያስገባኝ ነጥብ አልመጣልኝም። ያለኝ አማራጭ ቴክኒክና ሙያ መግባት ነበርና የሐረር ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተቀላቀልኩ። በ2006 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ትምህርቴን አጠናቀኩ።

በዚህ ወቅት በተወለድኩባት ቀብሪደሃር ከተማ አዲስ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ተከፍቶ ነበር። ይህም

በ2007 ዓ.ም በተመረኩበት ሙያ በመምህርነት ለመቀጠር መልካም አጋጣሚ ፈጠረልኝ። ተደራራቢ ስራዎችን፣ ኃላፊነቶችን በመቀበል ስንቀሳቀስ ስለነበር “የዓመቱ ምርጥ” በሚል ለመሸለም በቃሁ። በ2008 ዓ.ም የትምህርት ዕድል አገኘሁ፤ በ2013 ዓ.ም በዲግሪ ተመረኩኝ። ኤረር ዞን ፊቅ ከተማ ተመደብኩኝ። በ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ዲግሪ electrical communication and development የትምህርት ዕድል አግኝቼ በመማር ላይ እገኛለሁ በማለት ታሪኩን ያካፈለን ተስፋሁን መንግሥቱ ነው።

ተስፋሁን እነዚህን ሁሉ ውጣ ውረዶች አልፎ በቴክኒክና ሙያ ዲፕሎማ፣ በመቀጠል ዲግሪ፣ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ዲግሪ እየተማረ ነው። ተስፋሁን እዚህ ደረጃ የደረሰው ብዙ መሰናክሎችን ተጋፍጦ ነው። ንባብ እና እውቀት ለሕይወት ብርሃን ፈንጣቂ መሆናቸውን በማመኑ ነው ከላይ የተመለከተውን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለው። ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ ተስፋሁንም እሳቱን ተቋቁሞ ወርቅነቱን አስመስክሯል። የተስፋሁን ታሪክ እና የሕይወት ገጠመኝ ለአሁኑ ትውልድ ፈርጀ ብዙ ትምህርት ይሰጣል።

ለምን? ... እንዴት እናነባለን?

‘ንባብ’ በድምጽ ውክልና የተጻፈን ወይም የታተመን ነገር ትርጉም የመስጠት ሂደት ነው። በተለይ የጽሑፍ (የምልክት) ቋንቋ ውስጥ ከአራቱ የቋንቋው ክፍሎች ማለትም ከማዳመጥ፣ ከመናገር፣ ከማንበብና ከመጻፍ መካከል አንደኛው የሆነው የንባብ ክሂል ነው።

ፈለገ ጥበብ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሚዘጋጀው ዓመታዊ መጽሔት ቅጽ 1 ቁጥር 21/2013 ዕትሙ ስለንባብ እንዲህ ሲል አስፍሯል፤ “ንባብ ውስብስብ የቋንቋ ክፍሎችን ትርጉም የምንሰጥበት አንድ የቋንቋ ሂደት አካል ነው። ንባብ አንድን ቋንቋ የምንለምድበት ተግባቦትም የምንፈጥርበት መረጃዎችንና ሀሳቦችንም የምንለዋወጥበት አንዱ ክሂል ነው። ድምጽን በማውጣት እና በዓይን በመከተል ብቻ ንባብ ሊከወን ይችላል።”

ንባብ በጸሐፊውና በአንባቢው መካከል የሚደረግ ግንኙነት ነው። የንባቡ መቀጠል፣ አለመቀጠልና የንባብ ችሎታ የአንባቢው የቀደመ እውቀት፣ ልምድ፣ አመለካከት እና ሊነበብ በታቀደው ጽሑፍ የተጻፈበት ቋንቋ ባለቤት ማሕበራዊና ባህላዊ ደረጃ ይወሰናል። በገረፍታ (Skim- ming)፣ በአሰሳ (Scanning)፣ በጥልቅ (Intensive) ወይም በስፋት (Extensive) ለማንበብ ይቻላል። የንባብ

ስልቶቹን ለመምረጥ የሚወስነው አንባቢው የሚያነብበት ዓላማ እና ሁኔታ ነው።

ማንበብ ግንኙነትን ቋንቋን ያሻሽላል፣ የማስተዋል አቅምን ይጨምራል። አንባቢ አእምሮው ምሉዕ ነው፤ ሁሌም በሀሳብ ላይ ነው፤ ሙግቱም ሆነ ጨዋታው ከእውቀት ማዕድ የሚጨለፍ ነው። በአገራችን በንግግሮቻቸው፣ ጨዋታቸው፣ በጸሐፊነታቸው፣ ወዘተ … የታወቁት ግለሰቦች ከመጽሐፍት ዓለም፣ ከመጽሐፍት መንደር የሰነበቱ እና እዛው የሚኖሩ ናቸው። “የሚያነብ ሰው የሚናገረው አያጣም።” የሚባለው ለዚህ ሳይሆን ይቀራል?

መምህር መክብብ ገ/ማሪያም በአዲስ አበባ ባህል፣ ቱሪዝም እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ከፍተኛ የቅርስ ጥናት ባለሙያ ነው። በስነ መለኮት፣ በህግ ትምህርቶች ተመርቋል። ስለንባብ ልምዱ ስንጠይቀው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ወደ ዩኒቨርሲቲ እስከገባበት ወቅት ድረስ የነበረው የንባብ ልምድ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልነበር ነው ያወጋን።

መምህር ወደ ኋላ ተመልሶ ሁኔታውን ሲያስታውስ “በተለይ ስነ መለኮት በማጠናበት ወቅት ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በተያያዘ ብዙ መጻህፍትን አንብቤያለሁ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስሰራም

ትልልቅ የኢትዮጵያ የብራና መጽሐፍት፣ በአረበኛ ያሉትን ጭምር (አረበኛ ቋንቋ ተምሬ) አንብቤያለሁ። ዋናው ወደ ንባብ እንድሳብ እና አብዛኛውን ጊዜዬን ንባብ ላይ እንዳሳልፍ ያደረጉኝ የምስራቸው ጥናት እና ምርምሮች ናቸው። ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናትና ምርምሮች፣ የብራና ላይ ጽሑፎች የንባብ ልማዴን እንዳሳድግ ገፋፍተውኛል። በመደበኛ ትምህርት ያገኘሁት እንዳለ ሆኖ በንባብ ያገኘሁት እጅግ በጣም ትልቅ እና የተለየ ቦታ የምሰጠው ነው።” ብሏል። መምህር መክብብ እንደሚያምነው፣ ሰው ሙሉ የሚሆነው በማንበብ እንጂ በመማር ብቻ አይደለም። “ለእኔ አንባቢነት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉልኝ አብያተ መጻህፍት ናቸው” ሲል ነው የሚመሰክረው።

የባለታሪካችን ተስፋሁን ትምህርት እና ንባብን እንድትወድ ያደረገህ ምንድን ነው? በሚል ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ “በአደኩበት አጨበር አካባቢ ያለው ማኀበረሰብ ለትምህርት እና ለተማረ ሰው አክብሮት አለው። በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ አልፈው እና ዕድል አግኝተው ትምህርት የሚማሩ የአካባቢው ተወላጆች የተሻለ ውጤት፣ አምጥተው የተሻለ ደረጃ ሲደርሱ ሳይ እኔም በትምህርት እና በንባብ እንድማረክ አድርጎኛል።” የሚል ነበር፤ ተስፋሁን አንባቢ በመሆኑ በርካታ ቋንቋዎችን እንዲለምድ፣ የተለያዩ ክህሎቶችንም እንዲያዳብር መንገድ እንደከፈተለት ነው የንባብን ትሩፋት አስመልክቶ የሚናገረው።

መምህር መክብብም በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ ሀሳብ ነው የሰነዘረው። ለማንበብ ካለው ጉጉት የተነሳ ከአማርኛ እና እንግሊዝኛ በተጨማሪ የግዕዝ፣ አረበኛ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎችን ተምሯል። በእነዚህ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሐፍትንም ማንበቡን ነው የሚናገረው። እስከ አሁን ድረስም ከአንድ ሺህ በላይ መጽሐፍት ማንበቡን አውግቶናል። ግዕዝ የኦርቶዶክስ፣ አረበኛ የእስልምና ሃይማኖቶች ተከታይ እየመሰለን ቋንቋዎቹን አለመልመዳችን ተገቢ አለመሆኑን ነው አጽንኦት ሰጥቶ የገለጸው። ለዚህም በምክንያትነት የሚያቀርበው የኢትዮጵያ፣ የቤተ መንግስቱና የገዳማቱ ታሪክ በእነዚህ ቋንቋዎች በተዘጋጁ መጽሐፍት ውስጥ ተሰድረው የሚገኙ መሆናቸው ነው።

መጽሐፍቱን ማንበቤ የአገሬን ታሪክ እንዳውቅ፣ አገሬን እንድወድ፣ ለአገሬ እንድቆረቆር አድርጎኛል የሚለው መምህር መክብብ፤ በተጨማሪም “አንባቢ በመሆኔ ሀሳብ አዘል ንግግር እንዳደርግ፣ የቋንቋ ችሎታዬን እንዳሳድግ፣ ጽሑፍ እንድጽፍ ጠቅሞኛል፤ እንቅስቃሴያችንን በሙሉ ከመጽሐፍ ጋር ማስተሳሰር ስንችል ነው ሙሉ ሰው የምንሆነው” ሲልም ምክሩን ለግሷል።

አንዳንድ ጠቢባን ሲናገሩ፤ በዓለማችን ላይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩን ንባብን ሳይሆን ማንበብ እንደምንችል ነው። ስለዚህ ከዩኒቨርሲቲ መመረቅ ብቻውን ሙሉ ሰው አያደርግም። “የተሟላ ሰብዕና የሚሰጠው ንባብ ነው” ሲሉ ይደመጣል። ታዲያ በዚህ

አባባል እንድንረጋጋ የሚያደርገን “ኢትዮጵያዊ የንባብ ጀግና ጳውሎስ ኞኞ ነው” ያለው የአሃዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ፣ የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ዋና ጸሀፊ ጥበቡ በለጠ ነው።

ጳውሎስ ኞኞ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣ የታሪክ ፀሐፊ፣ ዲስኩር አዋቂ እና የብዙ ችሎታዎች መገለጫ ነው። ጳውሎስ የቀለም ትምህርቱን እስከ አራተኛ ክፍል ብቻ ነው የተማረው። ጳውሎስ ኞኞ በንባብ ብቻ የታላላቅ ሰዎች ሸንጐ ላይ መቀመጥ የቻለ ከኢትዮጵያ ውስጥ ቦግ ያለ የዕውቀት ብርሃን ነበር። ጳውሎስ አዘውትሮ በማንበቡ ብቻ ምርጥ የታሪክ ፀሐፊ የሆነ፣ ምርጥ ጋዜጠኛ የነበረ እና የተዋጣለት ደራሲ ጭምር ሆኖ ያለፈ በትውልዶች ታሪክ ውስጥ ሁሌም ስሙ የሚጠራ ባለዝና ነው።

“መፃሕፍት በዓለም ላይ ሁሉ መግባትና መውጣት እንድንችል የሚያደርጉን ቪዛ ያላቸው ፓስፖርቶች ናቸው። የየአገሩን ወግና ልማድ፣ ታሪክና ፍልስፍና፣ የሕዝቦችን አስተሳሰብና ባህሪ ወዘተ እንደልባችን እንድናይ እንድናውቅ የሚያደርጉን ከልካይ የሌለባቸው ዘላለማዊ ሀብቶቻችን ናቸው።” ሲል ስለመጻሕፍት ታላቅነት የገለጸው ጥበቡ በለጠ ነው።

መፃሕፍት የትውልድ ድልድይ ሆነው ሩቁን ከቅርቡ ብሎም ከመጪው የሰው ዘር ጋር የሚያገናኙ ናቸው። ያልኖርንባቸውን ዘመናት እያሳዩን የሚያስተምሩን፣ ከብዙ ልሂቃን፣ ጠቢባን፣ ፈላስፋዎች፣ ደራሲያን፣ ሳይንቲስቶች ጋር ጓደኛ የሚያደርጉን ልዩ ገፀ-በረከቶች ናቸው። መፃሕፍትን ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል፤ የተሟላ ሰብዕና ይሰጣል የሚባለውም ለዚህ ነው። ከምሁራን አደባባይ እና ሸንጐ ላይ አስቀምጠው የዚህችን ዓለም ምስጢር ወለል አድርገው ያሳዩናል።

አንድ ሰው ባለማንበቡ ምን ያጣል? ያላነበበ ምን ይሆናል? ባለማንበቤ ምን እሆናለሁ ብለው ዛሬም የሚጠይቁ አሉ። ታላቁ ደራሲ ቻርልስ ዲከንስ “ባላነብ ኖሮ አልባሌ ሰው ሆኜ እቀር ነበር። በማንበቤ ስሜቴን ገዛሁ፤ አስተዋይ እና አመዛዝኜ የምሰራ ሰው ሆኛለሁ።” ነው ያለው። ጳውሎስ ኞኞ “እውቀቴን ሁሉ ያገኘሁት በማንበብ ነው። ማንበብ አዋቂ ብቻ ሳይሆን ሙሉ ሰው ያደርጋል።” በማለት ነው የንባብን ጥቅም የገለጸው።

ያልኖርነውን ትላንት ዛሬ ላይ መኖር እንድንችል፣ ካልኖርንበት ዘመን እንኳን ጓደኞች እንዲኖሩን፤ የነርሱንም ያህል ዘመኑን የኖርነው ያህል እንዲሰማንም ያስችላል - ማንበብ።

ንባብ በዘመናት መነጽር

አገራችን ከዓለም የቀደመ ስልጣኔ ባለቤት ናት። የበርካታ ብርቅዬ ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኙ ቅርሶችም መገኛ ናት። አያት፣ ቅድመ አያቶቻንን ይህን ገናና ታሪክ ሰርተው ማለፍ የቻሉት ምጥቁ አእምሮ ስላላቸው መሆኑ አይታበልም። ተፈጥሮ ያደለቻቸውን ጸጋ በንባብ እና ሌሎችንም ስልቶች ተጠቅመው ክህሎታቸውን አሳድገው በእነሱ ዘመን



23

45 44 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

አገራችን ከዓለም ቀድማ እንድትገኝ አስችለዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም። የነገሮች ሁሉ መሰረት የሆነው የንባብ ባህል በኢትዮጵያ የቀደመው እና የአሁኑ ትውልድ ያለው ገጽታ ምን ይመስል ይሆን?

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ማንበብ እና መጻፍ የሚችለው ሰው ቁጥሩ አነስተኛ ነበር። ቁጥራቸው ቢያንስም በጣም የሚደነቁ መጻህፍት ይታተሙ ነበር። የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ፕሬዚዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ እንደሚገልጹት ፍቅር እስከ መቃብር የተጻፈው በንጉሱ ዘመን ነው፤ በወቅቱ ማንበብ እና መጻፍ የሚችሉት ሰዎች በጣም ያነቡ ነበር።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት እንደሚያስረዱት በደርግ ዘመን አንባቢው ትውልድ ጣራ የነካበት፣ ከፍተኛ የሆነ ፉክክር የነበረበት መጽሀፍትም (እንደአሁኑ ሁለት እና ሶስት ሺህ ሳይሆን) በትንሹ ከ30 እስከ 40 ሺህ ቅጂ የሚታተምበት ነበር። “ክርክርም የሚካሄደው በንባብ ላይ ተመስርቶ መሆኑን ከዚህ በመነሳት በደርግ ዘመን የተሻለ የመጽሀፍት ሽያጭ፣ የመጽሐፍት አንባቢ ትውልድ ነበር ብሎ መግለጽ ይቻላል” ይላሉ ደራሲ አበረ።

የ1960ዎቹ ትውልድ አንባቢ እንደነበር ይገለጻል። ለዚህም አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ ፖለቲካው የሚዘወረው በወጣቱ ኃይል መሆኑ፣ ወጣቱ ለአገሩ የሚሰጠው ክብር፣ ማህበረሰቡ ለተማረ የሰው ኃይል የሚሰጠው ቦታ ይጠቀሳሉ።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ 110 ሚሊየን ህዝብ፣ የግል ትምህርት ተቋማትን ሳይጨምር 50 የመንግስት

ዩኒቨርሲቲዎች አሉ። በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለውን የሰው ኃይል ብዛት ስንመለከተው በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ማንበብ እና መጻፍ እንደሚችል ያስረዳናል። ሆኖም “በገበያ ላይ ያሉት መጽሀፍት የህትመት ብዛት ከ3 እስከ 5 ሺህ ቅጂ አይዘልም” ያሉት ደራሲ አበረ ናቸው። ይህም “የንባብ ባህላችን ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ፣ ምን ያህል የንባብ ድህነት እንደገጠመን ማሳያ ነው” ይሉናል የደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት። በራሱ ጥናት የሚጠይቅ ቢሆንም የንባብ ልማዳችን በትውልድ ተከፋፍሎ ሲታይ “አሁን ላይ የቁልቁለት መንገድ እየሄደ ነው” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተው ነው የገለጹት ደራሲ አበረ።

መምህር መክብብ የቀድሞው ትውልድ አንባቢ እንደነበር ያምናል። የአሁኑ ትውልድ አነበበ ከተባለ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑትን ጽሑፎች ነው እንጂ “ጥንታዊ የሆኑትን ዞር ብሎ አይመለከትም” ሲል ያለውን ምልከታ ጠቅሷል። ኢትዮጵያ ያለችው በግእዝ እና በአረበኛ በተጻፉት የብራ መጽሐፎች ውስጥ ቢሆንም፤ አንባቢ ግን አለመኖሩን የሚገልጸው መምህር መክብብ የሚያነብ ከተገኘም ከትምህርት እንዲሁም ከጥናት እና ምርምር ጋር የተያያዘ ስራ ለመስራት ነው። እነርሱም ቢሆን ከተመረቁ በኋላ መረጃዎቹንም ሆነ ቤተ መጻህፍቱን መለስ ብለው እንደማይመለከቷቸው ነው የገለጸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ አለማንበብ ብዙ ነገር እየጎዳን ነው። ባለማንበባችን ዓለምን የምናይበት ማንጸሪያ የለንም። ራሳችንን ከሌላው ጋር አስተያይተን እኛ የቱጋ እንደምንገኝ ማወቅ እየቻልን አይደለም። በዚህም የተነሳ መንገዳችን

ጉዟችን ወደየት እንደሆነ መለየትም አንችልም፣ ባለማንበባችን ራዕይ (vision) እናጣለን ያለው ጥበቡ በለጠ ነው።

ከ17 ዓመታት በፊት ጎዳና ላይ መጽሐፍትን ዘርግቶ በመሸጥ ስራውን የጀመረው የጃፋር መጻህፍት መደብር ባለቤት ጃፋር ሺፋ አሁን በአዲስ አበባ አምስት የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮችን ከፍቶ ሕይወቱን እየመራ ይገኛል። በቀጣይም በክልሎች ላይ ቅርንጫፎችን የመክፈት ዕቅድ እንዳለው ነው የሚናገረው። ጃፋር የንባብ ልማዱን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ በሰጠበት ወቅት መንገድ ዳር ላይ በሚሸጥበት ወቅት በርካታ መጽሐፍትን በተለይም ልብወለድ አቀራረብ ያላቸውን ያነብ እንደነበር ነው የገለጸው።

ጃፋር አሁን ያለውን የመጽሐፍት ህትመት ብዛት እና የተጠቃሚዎችን ፍላጎት አስመልክቶ ያለውን አስተያየት የገለጸው፤ አንድ እና ሁለት ሺህ ቅጂ አሳትሞ የማያልቅለት የመኖሩን ያህል 15 እና 16 ሺህ ቅጂ አሳትሞ ደግሞ የሚያልቁ መጽሐፍት አሉ በማለት ነው። ጃፋር እንደሚገልጸው፤ በገበያው ላይ ቀዝቀዝ ያለው የግጥም መጽሀፍት ሽያጭ ነው። አክሎም እየተሸጡ እንደሆነ የምገልጻቸው መጻህፍት ብዛት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ጋር አይነጻጸርም። የኢትዮጵያዊያን የማንበብ ልማድ የዳበረ ላለመሆኑ ምስክርነቱን ሰጥቷል።

የኑሮ ውድነቱ ሰው በብዙ ችግር ውስጥ እንዲያልፍ እያስገደደ በመሆኑ መጽሐፍትን ደፍሮ እየገዛ ያለው የማንበብ ሱስ ያለበት ሰው እንደሆነ የሚያስረዳው የጃፋር መጻህፍት መደብር ባለቤት ነው። “ከኑሮ ውድነቱ አኳያ

10 ሺህ መጻህፍት መሸጣቸው ጥሩ ነው ያሰኛል” ሲልም አክሏል። ገንዘብ እያጠራቸው ልምዴን እንዳልተው እያሉ አንድ ብቻ መጽሐፍ ገዝተው የሚሄዱ ደንበኞች እንዳሉትም፣ በፊት አምስት መጽሀፍ ይገዙ የነበሩ አሁን ቢበዛ ሁለት መጽሀፍትን መግዛት እንደጀመሩ ሳይጠቅስ አላለፈም።

ማህበረሰቡ ለመጽሀፍ ገንዘብ ማውጣት ላይ ያለው ልምድ ምንድን ነው? ቤተሰብ ለልጆች መጻህፍት በመግዛት ረገድ ያለው ልማድ ምን ይመስላል? ወላጆች ልጆችን ይዘው ይመጡና ልጆቹ “ይህን፣ ይሄን፣ ግዙልኝ?” እያሉ በጉጉት ሲጠይቁ ቤተሰብ “ተው የመጣህበትን ብቻ ይዘህ

ሂድ” ሲሏቸው እመለከታለሁ ያለን ጃፋር ቁጥራቸው አነስተኛም ቢሆን ልጆች የሚፈልጉት እንዲወስዱ የሚያደርጉ ወላጆች እንዳሉ ያስረዳል።

የአቅም ማነስ ሊሆን ስለሚችል ዝም ብሎ በደፈናው መወንጀል እንደሚከብድ የጠቀሰው ጃፋር፤ “ሁላችንንም የሚያስማማን ነጥብ የልጆችን የንባብ ፍላጎት ላለመጉዳት መጠንቀቅ ያስፈልጋል የሚለው ነው” ሲል በጉዳዩ ላይ ያለውን አስተያየት ገልጿል።

“ልጆችንም ሆነ ወላጆችን በደፈናው መወንጀል ሳይሆን እንዴት ለሚለው ጥያቄ መፍትሔ ማመላከት ነው

የሚያስፈልገው” ሲል ይመክራል። በልደት በዓል ላይ ኬክ እና የመሳሰለውን ስጦታ ይዞ ከመሄድ ይልቅ መጽሐፍትን ብንወስድላቸው የንባብ ልማዳቸውን እንዲያዳብሩ መንገድ የሚያበጅ አንደኛው አማራጭ መሆኑን እንደማሳያ አቅርቧል።

ትምህርት እና ንባብ

ስለትምህርት ሲወሳ ንባብ አብሮ መነሳቱ አይቀሬ ነው። ተማሪን ከንባብ ነጥሎ መግለጽ የሚታሰብ አይሆንም። ቀደም ሲል እንደተመላከተው የአሁኑ ትውልድ አንባቢ ላለመሆኑ በርካቶች ስምምነታቸውን የሚቸሩት ሀሳብ

አዕምሯችን በቀን ከ50 ሺህ በላይ ሀሳቦችን እንደሚያፈልቅ ጥናቶች ያመላክታሉ። ከሀሳቦቹ 95 በመቶው በየቀኑ የሚደጋገሙ እና ያሉንን ልማዳዊ አመለካከቶች የሚያመላክቱ ናቸው። ይህም የሚያስረዳን ሀሳቦች በሃሳብነት እዚያው እንደማይቀሩ ነው። ይልቁንም ቀስ በቀስ ለአንድ ተግባር እንድንዘጋጅ ነው የሚያደርጉን።

“አንድ ሀሳብ ተግባርን ሲወልድ፣ ተግባሩ ደግም ሌላ ሀሳብን ይወልዳል፤ ይህ ዑደት ዕድሜ ልካችንን እንደተከተለን ይኖራል።” ይሉናል ዶ/ር ኢዮብ ማሞ በ2009 ዓ.ም እይታ ‘በአመለካከታችን በሕይወታችን ላይ ያለው ወሳኝነት’ በሚል ርዕስ ለንባብ ባዋሉት መጽሀፋቸው።

እንደዶ/ር ኢዮብ ገለጻ የምናስባቸው ሀሳቦች ፈጠኑም ዘገዩም ወደ ተግባር መለወጣቸው አይቀርም፤ ተግባር

ካለ ደግሞ ውጤት አለ። ሀሳብ ወደ ተግባርና ውጤት፣ ከውጤት አለፍ ስንል ሀሳባችንና አመለካከታችን ወደ አንድ ተጨባጭ እውነታ መምጣታቸው እንደማይቀርም ጽፈዋል። ይህ አገላለጽ የሁሉም ነገር መነሻው ሀሳብ ነው ወደ ሚል ድምዳሜ ያመራናል። (አንባቢያን የራሳቸውን አመክንዮ በማረቅብ ሀሳቡን ሊሞግቱ ይችላሉ።)

ከላይ የተመላከተውን ነጥብ የሚያጠናክርልን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አፍላቂነት በመዲናችን አዲስ አበባ ግንባታው የተከናወነው የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ነው። ታህሳስ 23 ቀን 2014 ዓ.ም የቤተመጻሕፍቱ ግንባታ ተጠናቆ የምርቃት ስነ ስርዓቱ መከናወኑ ይታወሳል።

በዕለቱም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ንግግር አጽንኦት ሰጥተው ከጠቀሷቸው ነጥቦች ውስጥ የጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀሳብ አፍላቂነት፣ ሀሳቡን

የአብሪ ኮከቦች ማዕከል

በፍቅርተ ባልቻ ወደ ተግባር ለመለወጥ ያሳዩትን የመሪነት ሚና እና እገዛ ይገኝበታል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት እና ድጋፍ ማስመረቅ ችለናል ሲሉም ተደምጠዋል ከንቲባዋ።

እንደከንቲባዋ ገለጻ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በተግባር እንዲታይ እና ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ሌት ተቀን ሲደግፉ ነበር። ከተማዋ እጅግ ውብ እንድትሆን የመሪነት ሚናቸውን እየተወጡ ለመሆኑም እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ይህም “አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ እናደርጋታለን ብለን የገባነውን ቃል ለመፈጸማችን አንዱ ማሳያ ነው” ብለዋል።

አዲስ አበባ የአገራችን ዋና ከተማ፤ የአፍሪካ መዲና፣ የእውቀት እና የቴክኖሎጂን እምብርት፣ የማህበራዊ መስተጋብር፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማዕከል እንደመሆኗ የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ ሰው ተኮር ልማት ያስፈልጋል። ለዚህም የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ፕሮጀክት መጠናቀቅ የሚኖረው አስተዋጽኦ ደማቅ ነው።

የአእምሮ ልማቱን ስራ ውጤታማ ለማድረግ በር ከፋች ነው።

ፈርቀዳጅ ለሆነው ለዚህ ቤተ መጻህፍት ግንባታ አድናቆታቸውን የገለጹ በርካታ ናቸው። ቤተ መጻህፍቱ ግንባታው ዘመናዊ፣ ግዙና እጅግ ውብ ከመሆኑ የተነሳ አካባቢው ልዩ መስህብ እንዲኖረው አድርጓል።

የአብርሆት ገጾች

አብርሆት በ19 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ የሚያምር የኪነ ህንጻ ጥበብ ያረፈበት ቤተ መጻህፍት ነው። በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙት የመጀመሪያዎቹ 10 ቤተ መጻህፍት ተርታ ተመድቧል። ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።

ከ400 ሺ በላይ መጽሀፍትን፣ ከ240 ሺ በላይ ወረቀት አልባ መጽሐፍት፤ 360 ሺ አገራዊ ጥናታዊ ጽሑፎችን፣

120 ሺ ጥናታዊ ህትመቶችን ማግኘት ያስችላል። 1.5 ኪ.ሜ የሚረዝም የመጽሐፍ መደርደሪያ አለው። በአንድ ጊዜ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎች ቁጭ ብለው ሊያነቡ ይችላሉ።

ስምንት የመጽሀፍት እና ተጓዳኝ ቁሳቁስ መሸጫ ሱቆችን በውስጡ ይዟል። በአንድ ጊዜ 115 ተሽከርካሪዎችን ማስቆም የሚችል ዘመናዊ ተሽከርካሪ ማቆሚያ አለው። ለእናቶች እና ህጻናት የሚያገለግል የማንበቢያ ስፍራም አለው። ማየት ለተሳናቸው የብሬል መጻህፍት ተዘጋጅቷል። ዘመናዊ ካፍቴሪያ እና መሰብሰቢያ አዳራሽ በውስጡ ይገኛል።

በዓለማችን ላይ ካሉት 190 በላይ አገሮች የራሳቸው ፊደል ያላቸው 18ቱ ብቻ ናቸው። በአፍሪካ የራሷ ፊደል ያላት ብቸኛው አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ከ18ቱ አንዱ ያደረገን የአባቶቻችን ድንቅ የእውቀት ውጤት የሆነው ይህን ጥበብ ለልጆቻችን ለማሸጋገር ብሎም ከ18ቱ አገሮች መካከል መሆናችንን ለማሳየት ፊደላቱ በህንጻው ዲዛይን



24

47 46 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ነው። ትውልዱ አንባቢ እንዳይሆን ያደረጉት ምክንያቶች የትኞቹ ይሆኑ?

እንደደራሲ አበረ ገለጻ፤ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲመራት የነበረው ሕወሃት በስርዓተ ትምህርቱ እና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ዘምቶ ነበር። ይህን ያደረገውም “ኢትዮጵያ ለመበታተን እንዲመቸው ነው” ይላሉ። ይህም የሁለተኛም፣ የሦስተኛም ዲግሪ ይዘው አስተካክለው መጻፍ የማይችሉ ዜጎች እንዲፈጠሩ ማድረጉንም ያብራራሉ። የአገር እና የቤተሰብ ፍቅር ጠፍቶ ፍቅረ ነዋይ ያደረበት፤ ስለመንደር፣ ስለቀበሌ፣ ስለጎራ የሚያቀነቅን ትውልድ እንዲፈጠር በመሰረታዊ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ስርዓተ ትምህርቱ እንደሆነም ያስረዳሉ።

ሌላኛው መንስኤ የሃይማኖት ተቋማት እና አባቶች ከመገሰጽ ይልቅ በጉዳዮቹ ውስጥ ራሳቸው ተዋናይ መሆናቸው ነው። በትውልዱ ዘንድ የስነምግባር መጓደል ስለመኖሩ በበርካታ አጸያፊ ድርጊቶች እየተንጸባረቀ ነው። ስለሆነም አገራችን ከአሁኑ የከፋ ችግር ውስጥ እንዳትወድቅ ስርዓተ ትምህርቱን ማስተካከል እና ግብረገብነትን መቅረጽ ላይ ጠንክረን መስራት እንደሚኖርብን ደራሲው ይመክራሉ።

የዚህ ጽሁፍ ባለታሪክ ተማሪ እና መምህሩ ተስፋሁን እርሱ ያሳለፈው ውጣ ውረድ እና አሁን ካለው ትውልድ ፍላጎት እና ዝግጁነት ጋር ሲነጻጸር ለየቅል መሆኑን ነው የሚናገረው። ሁኔታውንም ሲያብራራ፤ “ወጣቱ ትውልድ በሚፈትን ነገር ውስጥ የመግባት፣ ገብቶም የማለፍ አቅሙም ፍላጎቱም የለውም። ለምን ቢባል ትውልዱ አቋራጭ መንገድ ይፈልጋል። ሁለተኛ ቀላል

ሕይወት መኖር ይሻል። እኔ መምህር እንደመሆኔ ተማሪዎቼ በአካባቢያቸው ያለውን ችግር እንዲታዘቡ፣ እንዲመረምሩ እገፋፋቸዋለሁ። የሚማሩበትንም ዓላማ ያልተረዱ ምንም የማይጨበጥ ዓለም ውስጥ ያሉም አሉ። ሌላው ቀርቶ ተምራችሁ ስትወጡ ምን ለመሆን ትፈልጋላችሁ ሲባሉ የሚሰጡት ምላሽ ለየቅል ነው። በአንድ ወቅት በዚህ ጉዳይ ተማሪዎችን እያወያየሁ ሳለሁ ኤሌትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ሙያ (Electrical Electron- ics) እየተማረ ገንዘብ ያዥ (ካሸሪ) መሆን ነው የምፈልገው ያለኝ ተማሪ ሁሌም ትውስ ይለኛል።” ብሏል።

ተስፋሁን የአሁኑ ትውልድ ላይ ያለው አስተያየት በተለይ በትምህርት ዓለም ላይ ያሉት ቀለል ባለመንገድ መማር ሳይለፉ፣ ሳይደክሙ፣ ብዙ ሳያነቡ ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ነው የሚፈልጉት የሚል ነው። የትውልዱ የንባብ ልማድ እንዲዳብር፣ በስነ ምግባር የታነጸ እንዲሆን መሰረት የሚጣለው በህጻናት ላይ የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ሲቻል ስለመሆኑ መምህራኑ እየገለጹ ነው።

ወ/ሮ አልማዝ አለማየሁ በአዲስ አበባ በመጀመሪያ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ (ለአስራ አምስት ዓመታት) በቋንቋ መምህርነት እየሰሩ ይገኛሉ። መምህር አልማዝ ከተመክሯቸው በመነሳት “ተማሪዎች የንባብ ልማድ አላቸው” ብሎ ለመግለጽ እንደሚያስቸግር፣ አብዛኞቹ የንባብ ፍላጎት እንደሌላቸው ነው የነገሩን።

አማርኛ ቋንቋን ለመማርም ሆነ ለማንበብ “እናውቀዋለን” የሚል አመለካከት በተማሪዎች ዘንድ መኖሩ ክሂላቸውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ማነቆ እንደሆነ መምህሯ

ያስረዳሉ። የተለያዩ መጽሐፍትን ይዞ ክፍል ውስጥ በመግባት ተማሪዎችን ለማበረታታት እየሰሩ እንደሆነ የቋንቋ መምህሯ ይገልጻሉ። መጽሐፍቱን ፍቃደኛ የሆኑትን ተማሪዎች እንዲያነቡ የሚጋብዙ መሆኑን በዚህም ወቅት የቃላት ግድፈት፣ የፊደል ግድፈት፣ መንተባተብ፣ ዐረፍተ ነገሩን ሙሉ በሙሉ ያለማንበብ ሁኔታ እንደሚያጋጥማቸው አልሸሸጉም።

ሰኔ 2001 ዓ.ም በየካቲት 12 የመሰናዶ ትምህርት ቤት ‘የተማሪዎች ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድ’ አስመልክቶ በአቤል ገ/ኪዳን ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ክፍለ ትምህርት ለዲግሪ ማሟያ የተሰራው ጥናት ውጤት የተማሪዎች ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎች የማንበብ ልምድ ዝቅተኛ እንደሆነ አመላክቷል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው

ተማሪዎች ስለ ንባብ ያላቸው ግንዛቤ እጅግ ዝቅተኛ መሆን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ጫና፣ የትምህርት ቤቶች ንባብን ለማስለመድ ኃላፊነታቸውን በሚገባ አለመወጣት ናቸው።

የተማሪዎችን የንባብ ልምድ በማዳበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ አካላት ቤተሰብ፣

የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ የሚጠበቀውን ያህል ተጽእኖ መፍጠር እንዳልቻሉ ጥናቱ ጠቁሞ በተለይ በትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎች አንጻር ያላቸው አስተዋጽኦ ዝቅተኛ እንደሆነ ተረጋግጧል።

ወደፊት ትምህርት ነክ ያልሆኑ ጽሁፎችን የማንበብ ልምድ ለማዳበር ቢሰሩ ያሏቸውን አጥኚው እነሆ ብለዋል። የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ውስጥ ለንባብ መደበኛ የሆነ ክፍለ ጊዜ በመስጠት ተማሪዎች የተለያዩ ዓይነት ጽሁፎችን እንዲያነቡ ቢደረግ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማከናወን እንዲሁም ሳቢነት ያላቸውን ጽሁፎች በመማሪያ መጻህፍት ውስጥ ማካተት በጥናቱ ውስጥ እንደመፍትሔ ከተመላከቱ ሀሳቦች መካከል ናቸው።

በቅርቡ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መከናወኑ ይታወሳል። የፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን ተከትሎ የሥርዓተ ትምህርት ለውጥ በማድረግ፣ የማስተማሪያ መጽሐፎች ተዘጋጅተው ወደ ሙከራ ትግበራ ተገብቷል። ይህም በትውልዱ የንባብ ልማድ ላይ የሚያመጣውንም ለውጥ በቀጣይ የምንመለከተው ይሆናል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን

ቴክኖሎጂው ከውጪው ዓለም ጋር ለመገናኘት ቀላል መንገድ አበጅቷል። መረጃን በፍጥነት በመለዋወጥ ረገድም ጥሩ አማራጭ ነው። መጽሐፍትን ገበያ ወጥተን መግዛት ሳይጠበቅብን ካለንበት ለማግኘት አስችሎናል።

ላይ እንዲካተት መደረጉ በምርቃቱ ወቅት ተጠቅሷል። አብርሆት ኢትዮጵያን ለተቀረው ዓለም የሚያስተዋወቅ የጥበብ ማዕከል ነው።

እውቀት የተጠሙ ጥበብን የሚቀዱበት፤ የአእምሮ ሰላም፣ ጤና እና እረፍት የሚሸመትበት፤ ተስፋን፣ ብርሃንና ጮራን የፈነጠቀ ታላቅ ፕሮጀክት እንደሆነ ተነግሮለታል - አብርሆት።

… ምን አሉ?

የአብርሆት ቤተ መጻህፍት መጠናቀቅን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ምስጋና እና አድናቆታቸውን እየገለጹ የበኩላቸውን እገዛም እያደረጉ ነው። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡትን መካከል የ’ቡክ ኮርነር’ መጽሐፍ መደብር ሥራ አስኪያጅ ተስፋዬ ኩምሳ እና ተማሪ ቤዛ ታዬ ይገኙበታል። በቤተ መጽሐፍቱ መከፈት ብቻ ሳይሆን ባለው መስህብ፣ ጥራት እና ደረጃ መደነቃቸውን መጽሀፍትን ለመለገስ መነሳሳታቸውንም ነግረውናል።

“መጻሕፍት ቤት እንደሚከፈት እየጠበቅን ነበር። በዚህ ደረጃ እና ጥራት እንደሚሆን ግን አልገመትንም።

አድናቆታችንን ጭምር በመጥቀስ 500 መጽሐፍትን ለግሰናል።” ሲሉም ስራ አስኪያጁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። አክለውም ያነበቡ ሰዎች የሚሉት አያጡም፤ የሚጽፉትም እነሱ ናቸው፣ ስለሆነም “መጽሀፍት ላይ መሰራቱን ወደነዋል” ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ እንደሚገልጹት ለአብርሆት የሚደረገው ድጋፍ ሁለት ዓይነት ጠቀሜታ አለው።በአንድ በኩል የሚለግሱት ሰዎች መስጠትን እንዲለማመዱ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በቤተ መጻህፍቱ ውስጥ የራሳቸው መጽሐፍ እንዳለ እንዲሰማቸው ያደርጋል።

የ’ቡክ ኮርነር’ መጽሐፍ መደብር ሥራ አስኪያጅ “የመጽሐፍትን ጥቅም ያወቀ ሰው ነው በመጽሀፍት ህትመት እና ሽያጭ ስራ የሚገባው” ይላሉ። ህብረተሰብ መለወጥ የሚችለው በእውቀት ስለመሆኑ፣ የእውቀት ማስተላለፊያ እና የመጀመሪያው መንገድ ደግሞ ንባብ ስለመሆኑ፣ የንባብ ማዕከላትም ቤተ መጻህፍት እንደሆኑ ያስረዳሉ።

የ11ኛ ክፍል ተማሪዋ ቤዛ ታዬ በበኩሏ 950 መጽሐፎችን

ለግሳለች። ሁሉም የአባቷ መጽሐፎች እንደሆኑ እና በቤት ውስጥ ተቀምጠው እየተነበቡ እንዳልሆነ ነግራናለች። “አብርሆት ብዙ ሰዎች የሚያነቡበት ትልቅ ቤተ መጻህፍት ስለሆነ ለመስጠት ወሰንኩ” ብላለች። ትውልዱ አንባቢ እንዲሆን፣ ሲያነብ ደግሞ እንዲያመዛዝን ያስችለዋል ስትል ፋይዳውን የምትጠቁመው።

ቤተ መጻህፍት የህዝብ እንደመሆናቸው ህዝብ ሲጠቀም አንባቢ ትውልድ ይፈጠራል፤ አንባቢ ትውልድ ደግሞ ነገሮችን ያመዛዝናል፣ ስሜታዊ አይሆንም። “አብርሆት ወደ ክልልም መስፋፋት አለበት፣ በገጠራማ አገሪቷ ክፍሎች ያሉት የንባብ ልማድ የላቸውም፣ እነሱም በንባብ ሊያድጉ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል።” የተማሪ ቤዛ አስተያየት ነው።

ደራስያን መጽሐፎቻቸው ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችላቸው ማዕከል ነው - አብርሆት። አጋጣሚው በመጠቀም የራሳችን ታሪክ ጽፈን፣ የቀደመውንም ጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር ይኖርብናል። ደራስያን፣ ተቋማት፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ቤተ መጻህፍቱን የተሟላ በማድረግ

ረገድ የበኩላቸውን ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል።

አብርሆት አንባቢ ትውልድ ለማፍራት ያለው ፋይዳ ትልቅ ነው። በተለያዩ ቦታዎች ጊዜያቸውን ከሚያባክኑ እንዲያነቡ ያነሳሳል። የሚፈልጉትን እያንዳንዱን መጽሐፍ ገዝቶ ለማንበብ ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። መጽሐፍት በዚህ ደረጃ እንዲሰባሰቡ ከተደረገ በርካታ ሰዎች ወደ ንባብ እንዲመለሱ ያነሳሳል። አቶ ተስፋዬ የአንባቢው ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ እንደሆነም የዓይን እማኝነታቸውን ገልጸዋል።

የብርሃን ዘመን

አብርሆት (Enlightenment) እራሳችንን ከገባንበት ድቀት እና ባዶነት ነጻ ማውጣት ማለት እንደሆነ (ethio- headline.com) ድረገጽ ላይ ሰፍሮ እናገኛለን። አብርሆት የአስተሳሰብ አብዮት እንደሆነም መረጃው ጠቁሟል። የሥነ ልቦና ሳይንስ አጥኝዎች አብርሆትን (self ac- tualization)፣ (Enlightenment) የሚለውን ደግሞ “ንቃት” ብለው ይተረጉሙታል። አንዳንድ የሥነ መለኮት

አጥኚዎች በበኩላቸው አብርሆትን (Illumination) ሲሉት ለትክክለኛ መረዳት መለኮታዊ ብርሃንን የማግኘት ትርጉም እንደሚሰጡትም ድረ ገጹ አስነብቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ “እውቀት ከድንቁርና ቀንበር ነጻ የሚያወጣ መንገድ ነው። ድንቁርና ለእኛ ጨለማ ነው። ጨለማ ያስፈራል፤ ይጠላል። በጨለማ ውስጥ ያለ ማህበረሰብ የላቀ ነገር ማሰብ አይችልም። ከጨለማ የሚያወጣን ብርሃናማ የሚያደርገን እውቀት ነው። እውቀት ለማግኘት እንደአብርሆት ዓይነት ቤተ መጻህፍት በእጅጉ ያስፈልጋሉ።” ብለው ነበር።

ያለማወቅን ጨለማ ለመግፈፍ የሚረዳ አሻራ በአብርሆት ፕሮጀክት ተቀምጧል። “የበርካታ ትውልድ ብርሃን የሆነውን ቤተ መጻህፍት ሰርተን ለአገልግሎት አብቅተናል። ለማወቅ መጠየቅ፣ ለመጠየቅ ማንበብ ያስፈልጋል። ከእነዚህ ስንነጠል ድንቁርና እና ድህነት እኛ ላይ ይሰለጥናሉ። በዚህ ቤተ መጻህፍት በርካታ አብሪ ኮከቦች እንደሚፈጠሩ እናምናለን። ወላጆች ልጆቻችሁን ላኩ፣ እናንተም ኑ፣ መምህራን እና

ምሁራን መብራትነታችሁ እንዳይደበዝዝ ከዚህ ተገኙ፤ ተመራማሪዎች አሻራችሁን አሳርፉ።” ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ናቸው።

የነገ አገር ተረካቢዎች ለማፍራት፣ እውቀትን አላምጦ ለመዋጥ ቤተመጻህፍት ትልቅ ሚና አላቸው። “አገርን አሳድጋለሁ፤ ህዝብን አሰለጥናለሁ” ከተባለ ዋናው መሳሪያ ንባብ እና ንባብ ብቻ ነው። የመለወጫ መንገዳችን እውቀት ነው። ለእውቀት ደግሞ መጻህፍት ትልቅ አበርክቶ አላቸው። ሰው እራሱንም ሀገሩንም የሚለውጠው በንባብ እና በእውቀት መንገድ ነው።

ህጻን ተወልዶ ለማደግ የተፈጥሮ ሂደትን የግድ ይጠብቃል። በተመሳሳይ ትውልድን በእውቀት የታነጸ፣ እና አንባቢ ለማድረግም በአንድ ጀንበር የሚሆን አይደለም። በትምህርት እና በእውቀት ላይ የሚሰራን ስራ ውጤት በማግስቱ ማየት አይቻልም። ለውጡን ለማየት ዓመታትን መጠበቅ ይጠይቃል። ስለሆነም የአብርሆትን ፍሬ ከዓመታት በኋላ እንደምንቋደስ ልበ ሙሉ ነን።



25

49 48 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጂ መጽሐፍቱን ስንፈልግ በስስ ቅጂ (soft copy) አልያም በድምጽ ተቀናብረው (au- dio) በቀላሉ እጃችን ላይ እንድናገኛቸው ቀላል መንገድ አበጅቶልናል። በአንደኛው የዓለም ክፍል የታተመን መጽሐፍ ለማግኘት የሚጠይቀን ከድረገጾች ላይ ማውረድ ብቻ ነው።

በተንቀሳቃሽ ስልካችን አማካኝነት እነዚህን የስስ ቅጂ እና በድምጽ የተቀናበሩ መጻህፍት ለመጠቀም በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ ለማንበብ እና ለማዳመጥ ዝግጁ መሆን ነው የሚጠይቀን። አገራችን ላይ ወዳለው ነባራዊ ሁኔታ መለስ ብለን ብንመለከት የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን ቡራቡሬ ቀለም ይዞ ነው የምናገኘው።

በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወሩት አጫጭር መረጃዎች ሲሆኑ፤ መጽሐፍትን አንብቦ ለመረዳት ደግሞ ትዕግስት እና ጊዜ መጠየቁ አይቀሬ ነው። በመጽሐፍቱ የተወከሉት ገጸ ባህሪይ ምን መልዕክት ያስተላልፋሉ? ምን እያሉ ነው ያሉት? በአጭሩ የመጽሐፍቱን እማሬ እና ፍካሬ ለመስጠት ጊዜም ይፈልጋል። ማህበራዊ ሚዲያ ለዚህ አይጋብዝም። በሌላ በኩል መደበኛው የመገናኛ ብዙሃን ግራ ቀኝ አይቶ በማስረጃ የተደገፉ ስራዎችን ተንትኖ ያቀርባል። መደበኛው መገናኛ ብዙሃን እና ማህበራዊው ሚዲያ የተለያየ ባህሪይ ነው ያላቸው።

“ማህበራዊ ሚዲያውን መከታተል በራሱ ንባብ ነው” የሚሉ የመኖራቸውን ያህል ቴክኖሎጂው አንባቢ ትውልድ እንዳይፈጠር እያደረገ ለመሆኑ የሚሞግቱ በርካታ ሰዎች ናቸው። ትውልዱ “ከመጽሐፍት እንዲራራቅ አድርጓል” በሚል በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ነጥቦች አንዱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን ነው። (አንባብያን ከራሳቸው ተመክሮ በመነሳት ወይም አካባቢያቸውን በመቃኘት የራሳቸው ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።)

አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ደበበ እሸቱ “የቴክኖሎጂ መስፋፋት ዘመናዊ አኗኗርን ገቢራዊ ለማድረግ ቢያግዝም የንባብ ባህልን በማጎልበት ረገድ ግን እራሱን የቻለ አሉታዊ

ተጽእኖ አሳድሯል” ይላሉ። በተለይ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ መረጃዎች ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ማድረጉንም ይናገራሉ። ይህም በመረጃ የበለጸገና ስለአገሩ ሙሉ እይታ ያለው ትውልድ በመገንባቱ ስራ ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር ነው ያብራሩት። በንባብ ባህል የተቃኘ ትውልድ መፍጠር የአገር ግንባታ አንደኛው መሰረት እንደሆነ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያዊያንን የማይመጥኑ በስነምግባር የዘቀጡ በተለይ ከዝሙት ጋር የተያያዙ መረጃዎች የሚተላለፉበት እየሆነ ነው” ሲል በምሬት የገለጸው መምህር መክብብ፤ የአገራችንን ባህል እና እሴት የማይወክሉ መልዕክቶችን ማየት እየተለመደ መምጣቱን ነው የሚናገረው። በተዘዋዋሪ “በመረጃዎቹ ቅኝ እየተገዛን ነው” ሲልም መዘዙን ሳያመላክት አላለፈም።

መገናኛ ብዙሃንም የሚሰሩት ዜና፣ መጣጥፍ እና ፕሮግራም የሰውን ጆሮ ሰቅዞ ይዞ እንዲከታተለው የሚያደርግ አይደለም። ሁሉንም የሚገልጽ ባይሆንም የማህበራዊ ሚዲያውን እንቶ ፈንቶ ወደ መደበኛው መገናኛ ብዙሃን አምጥቶ መጫንና በእርሱ ተጽዕኖ ስር ሲወድቁ ይስተዋላል። ይህም የሚሆነው “በንባብ ካለመብሰል ነው” የሚሉት የደራስያን ማህበር ፕሬዝዳንት አበረ ናቸው።

ከዚህ ቀደሙ በተሻለ አሁን ለማንበብ ምቹ ሁኔታ ቢኖርም ፊልም፣ ቲቪ፣ ኳስ፣ መጠጥ ቤቶች፣ ማህበራዊ ሚዲያው የትውልዱ ማደንዘዣዎች እንደሆኑ እየተስተዋለ ነው። በስልኮቻችን አማካኝነት ጌሞችን በመጫወት፣ ቪዲዮዎችን በመመልከት፣ ማህበራዊ ሚዲያው በሚያራግባቸው ጉዳዮች ላይ በመጠመድ ጊዜያችንን ማባከን ጀመርን ሰነባብተናል።

የቴክኖሎጂውን ተጽዕኖ እንዴት ነው መቋቋም የምንችለው? ለመልካም ነገር እንዴት እናውለው? በምን መንገድ እንደጠቀምበት? የሚለው የሁላችንንም ትኩረት የሚሻ ነጥብ ነው።

“ክብሯን አስጠብቃ የቆየችውን አገራችን የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ውስጥ እንዳለች ነው የሚሰማኝ” ያለው መምህር መክብብ፤ ለዚህ ምክንያቱ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እና በቴክኖሎጂው አማካኝነት ወረራ መካሄዱን ይጠቅሳል። በጣም ከባድ ጊዜ ላይ እንዳለን፣ በዚሁ ከቀጠለ በቀጣይ ይቺን አገር “ማን ነው የሚመራት?” ሲል ይጠይቃል። የባህልና ቱሪዝም ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድርጅቶች ስራዬ ብለው በዚህ ጉዳይ ላይ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። የትውልዱ መነጠቅ ሊያንገበግባቸው እንደሚገባም ነው አጽንኦት የሰጠው።

ከቤት ስራዎቻችን አንዱ

ዛሬ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ያለውን የማንበብ ባህል ማየት ጠቀሚ ነው። ዛሬ በሕይወት ላለነው ኢትዮጵያውያን የጋራ መኖርያ ቤቶች እየተገነቡልን ነው፤ ሪል ስቴቶችም እና ። እነዚህ ቤቶች መኝታ ክፍል፣ እንግዳ መቀበያ ሳሎን፣ ኪችን እና መፀዳጃ ቤት ሲኖራቸው የመጽሐፍት ቤት ግን የላቸውም።

መፃሕፍት ውስጥ ብዙ ሰዎች አሉ። ታላላቅ ምሁራን፣ ነገስታት፣ ሕዝቦች፣ ማኅበረሰቦች ወዘተ … ውስጣቸው ይርመሰመሳሉ። አገራት በመፅሐፍት ውስጥ ይገነባሉ፣ ጦርነቶች ይካሄዳሉ፣ አሸናፊና ተሸናፊዎች ታሪክ ይጽፋሉ። መፅሐፍት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ያለባቸው የሕይወት ድርሳን ናቸው። ስለዚህ ለመፃሕፍትም የክብር ቤት፣ አንዲት ክፍል ያስፈልጋቸዋል። “የመፃሕፍት ቤት የሌለው ሕንፃ መስኮት እንደሌለው ቤት ጨለማ ነው” ይባላል።

“በየአካባቢው ቦታ ሊመቻችላቸው ይገባል፤ ሰው ተምሮ ከተመረቀ በኋላ ቤተ መጽሐፍቱን ዞር ብሎ አያያቸውም፤ አካባቢያቸው ላይ የንባብ ባህል እንዲያድግ አይሰራም። ኮንደሚኒየም እና ሪልእስቴቶች አካባቢ ቤተ መጽሀፍት ሲዘጋጁ አይታይም። ሁሉም ተቋማት ርብርብ አድርገው ወደ ንባብ እንድንመለስ ማድረግ የሚቻለው እዚህ ላይ ትኩረት ካደረግን ነው።” ሲል ስጋቱን እና ከንባብ ጋር

ተያይዞ የሚስተዋለውን ክፍተት ያመላከተው መምህር መክብብ ነው።

የብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንደሚገልጸው፤ በተለይ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሉባቸው አካባቢዎች በጋራ የሚገለገሉባቸው ቤተ መጻህፍት እንዲኖሩ ጥረት እያደረገ ነው። በእነዚህ አካባቢዎች ተቋሙ ሄዶ ቤተ መጻሕፍትን በመክፈት፣ የተከፈቱትን በማደራጀት፣ እየተጀመሩ ያሉትን በማጠናከር፤ የአካባቢው ማሕበረሰብ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ተጠቃሚዎች በራሳቸው የቤተ መጻህፍት ባለሙያ ቀጥረው የማንበቢያ ስፍራ እንዲያገኙ ለማስቻል እየተንቀሳቀሱ ናቸው።

በዚህ መልኩ ድጋፍ ተደርጎላቸው የቤተ መጻህፍት ካደራጁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል በጎተራ፣ በቱሉ ዲምቱ፣ በንፋስ ስልክ፣ ጀሞ ቁጥር 1 እና 2 ይጠቀሳሉ። ተቋሙ በሌሎች አካባቢዎች ያሉትም ይህን ተመክሮ ወደ ራሳቸው ወስደው ተግባራዊ ቢያደርጉ “ትውልዱን ወደ ንባብ መመለስ ብሎም በአልባሌ ቦታዎች ጊዜው እንዳያባክን ይታደገዋል” ሲል አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ደራስያን ማሕበር በበኩሉ በንባብ ላይ አብዮት እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳለው ነው የሚገልጸው። የማህበሩ ፕሬዝዳንት ማህበሩ ይህን አቋም እንዲይዝ ያስገደደውን ምክንያት ያብራሩት “ችግሮቻችን በሙሉ የሚመነጩት ከእውቀት ማጠር ነው ብለን እናምናለን። እገሌን ግደለው ሲባል ለምን የማይል፣ የማይጠይቅ ትውልድ ነው አሁን እያየን ያለነው። በባንክ ብድር የሚሰሩ ፋብሪካዎች በደቂቃ ውስጥ ሲቃጠሉ እያየን ነው። ድርጊቱም ፋብሪካዎቹ ያላቸውን ፋይዳ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው። በጥቅሉ ሮቦት ያልሆነ፣ ለምን ብሎ የሚይጠይቅ፣ በምክንያት የሚያምን ትውልድ እንዲመጣ እንፈልጋለን። ይህ እውን የሚሆነው ደግሞ ትውልዱ እውቀት እንዲኖረው፣ አንባቢ፣ ጠያቂ እንዲሆን መስራት ሲቻል ነው።” በማለት ነው።

ያላነበበ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ፣ ፓይለት፣ ሀኪም፣ የግብርና ባለሙያ፣ ሳይንቲስት በተሰማራበት የሙያ መስክ ውጤታማ ሊሆን አይችልም። “ስለዚህ ንባብ የሁሉ ነገር መድሃኒት ስለሆነ በአግባቡ እና በልኩ እንድንወስደው እንፈልጋለን፤ በመላው ኢትዮጵያ አብያተ መጻህፍት እንዲገነቡ፣ አንባቢ ትውልድ እንዲፈጠር ጥረት እያደረግን ነው” ብሏል ማህበሩ። ከንጉሱ በኋላ ትልቅ ቤተ መጻህፍት በመገንባት ረገድ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሁለተኛው መሪ ናቸው፤ ለትውልዱ ባለውለታ ናቸውና ሊመሰገኑ ይገባል” ሲሉ ያላቸውን አስተያየት የሰነዘሩት ደራሲ አበረ ናቸው።

አዲስ አበባን የሚያህል የአፍሪካ መዲና በሆነች ከተማ ላይ አንድ ለናቱ የሚባለው የብሔራዊ ቤተ መዛግብት ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ነው የነበረው። ንባብ ላይ ብዙም ስላልተሰራ ወጣቱም ትልልቁም አንባቢ ስላልሆነ ያንን ለማስፋት አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ተከፍቷል።

ቤተ መጻህፍቱ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ በተለያዩ አካላት የመጽሐፍት ድጋፍ እየተደረገ ነው። ደራሲ አበረ አንድ አብርሆት በቂ እንዳልሆነ፣ በርካታ አብርሆቶች ሊኖሩ እንደሚገባ እና እንደአሁኑ ተግተን ከሰራን ትውልዱን ወደ አንባቢነት መመለስ እንደማያዳግት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ትውልዱን እንዴት እንታደገው?

ንባብ የሰው ልጅ በእርጅና ዘመኑ ሊያጋጥመው ከሚችል የአንጎል ጉዳት በብዙ ሊያድነው እንደሚችል መጽሃፍት ያስረዳሉ። የሰዎች የማስታወስ አቅም ይጨምራል፤ አንጎሉ እንዲነቃቃ ያደርጋል፤ ለተማሪዎችና እና ለአንባቢዎች እውቀትን ለመቅሰም፣ የስሌት ብቃታቸው እንዲጨምር ያደርጋል።

እውቀት ከመጨመር ባሻገር የሰው ልጅ የአስተሳሰብ ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት እንዲሻሻል ያግዛል፤ የሰው ልጅ ከጭንቀት መንፈስ እንዲወጣ ያደርጋል፤ ማህደረ ትውስታ እንዲሻሻል ይረዳል፤ የመጻፍ ችሎታን ይጨምራል፤ የአስተሳሰብ አድማስን ያሰፋል። ስለሆነም ንባብ የእውቀትን፣ ግንዛቤን፣ ቅልጥፍናንና ተነሳሽነትን የሚያካትት ዘርፈ ብዙ ሂደት ነው።

የዓለም የሥልጣኔ አውራ ከነበሩት አገራት መካከል አንዷ የነበረችው አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ የሥልጣኔ ውራ ሆናለች። የዚህ ምክንያቱ ሌላ አይደለም። የዕውቀት ማነስ፣ ያለማንበብ ችግር የፈጠረብን አበሳ ነው። ሌላው ዓለም የበለጠን በማንበቡ ነው።

አገር በችግር ውስጥ የምትወድቀው የዜጋው የማንበብ ክሂል እየቀነሰ በሚሄድበት ወቅት ነው። አሁን አገሪቷ ላይ አስፈሪ የሆኑ ድርጊቶች እየተከሰቱ ያሉት የንባብ ባሕላችን የኋልዮሽ ስለተጓዘ ነው።

መንግሥትም፣ ሕዝቡም፣ ቤተሰብም ከሕፃናት ጀምሮ ንባብ ላይ የሚሰራ ከሆነ ክፍተቶች አይፈጠሩም። ያነበበ ሰው አገሩን ይወዳል፣ አገሩን ይጠብቃል አገሩንም ያሳድጋል። ስናነብ እንለወጣለን የማናነብ ከሆነ መለወጥ የሚባል ነገር አይኖርም የምንናፍቀው አገር አይኖረንም። በማንበብ ብዙ ነገሮችን የምንቀይርበትን አቅም መፍጠር እንችላለን። ስለሆነም የንባብ ባህልን ከፍ ለማድረግ ወይም የአገሪቷን ዕድገት ለማፋጠን አንባቢ ትውልድ መፍጠር ይጠይቀናል።

ምርምር የተደረገባቸው በርካታ መጽሀፍት በአገራችን አሉ። በአንጻሩ የግዕዝ እና የአረበኛ ቋንቋ ምሁራን ግን የሉንም። ተተኪው ትውልድ እነዚህን መጽሐፍት እየመረመረ ወደ ነበርንበት ከፍታ እንዲመልሰን አገር በቀል እውቀት ያላቸው ሰዎች ማፍራት ይጠይቀናል። ታሪክን ጠብቀው እያስተዋወቁ እንዲቆዩ መደረግ አለበት፤ የመጽሀፍት ክምችት ባለባቸው አካባቢዎች ላይ በተለየ ትኩረት መሰራት ይኖርበታል።

“እሳት ቢነሳ መጀመሪያ ለማጥፋት የምንሞክረው የራሳችንን ነው፤ በተመሳሳይ አንድ ሰው እራሱን ካላተረፈ

ማንንም ተጠያቂ ሊያደርግ አይችልም። ለስኬቱም ሆነ ለውድቀቱ ቀዳሚው ተጠያቂ እራሱ ግለሰቡ ነው። በመቀጠል ቤተሰቡ፣ ማህበረሰቡ፣ ተቋማት፣ መንግስት ትውልዱን ለመቅረጽ መስራት ይጠይቃቸዋል።” ሲል አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ኃላፊነቱ የሚወድቀው አንድ አካል ላይ ብቻ አለመሆኑን ያመላከተው ተማሪ እና መምህሩ ተስፋሁን ነው።

“ተማሪዎች ተምረን ምንም አናገኝም፣ እቤት ከመቀመጥ ብለን ነው ትምህርት ቤት የምንመጣው የሚሉ በርካታ ናቸው። ዓላማ ይዘው የሚማሩት ውስን ተማሪዎች ናቸው።” ሲሉ ተማሪዎች የማያነቡበትን ምክንያት ያስረዳሉ። በአገሪቱ ለትምህርት እና ለተማረ ሰው ክብር እና ቦታ ቢሰጠው ንባብ ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልም የሚመክሩት መምህራኑ ናቸው።

ለንባብ ባህል መጎልበት የንባብ ማዕከላት መስፋፋት ከፍተኛ ሚና አለው። አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር በየክልሉ በየአካባቢው አብያተ መጻሕፍት መገንባት አለባቸው። ቤተመጽሀፍትን በመገንባት ረገድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ያለው ጅማሮ ወደ ሌሎችም እንዲሰፋ ቢሰራ መልካም ነው። ቤተ መጻሕፍቱ ስለተከፈተ እና መጻሕፍት ስለተሟሉ ብቻ አንባቢ ትውልድን መፍጠር የመቀስቀስና ሁሉም ወላጅ ልጆቹን እንዲልክ እንዲያነቡ ማድረግ ይጠበቅበታል።

ጸሐፊያንም ለትውልዱ የሚጠቅመውን ለይተው ቢጽፉ መልካም ነው። አብዛኛው ሰላማዊ ሆኖ ለአገሩ እንዲቆም ሳይሆን አገሩን እንዲጠላ፣ እንዲጠራጠር፣ ተሰዶ ወደ ሌላ አገር እንዲሄዱ የሚያነሳሱ ናቸው። ደራስያን በቀልድ እያዋዙ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ መጽሐፍትን ቢያዘጋጁ ይመከራል። ታዳጊዎችን ታሳቢ በማድረግ በዕድሜያቸው በሚመጥን አቀራረብ መጽሐፍት ተዘጋጅተው ቢታተሙ መልካም ነው።

የሃይማኖት አባቶች፣ ባህል ላይ የሚሰሩ አካላት፣ ፖለቲከኞች ትውልዱ ከሌለ ማንን ሊመሩ ነው። ትውልዱን ተነጥቀናል፤ ስነ ልቦናቸው ተወስዷል፤ ለውጥ ለማምጣት መንቀሳቀስ ይኖርብናል። መምህራንም በዚህ ዙሪያ ምን ሰራችሁ ሊባሉ ይገባል። የንባብ፣ የክርክር ውድድሮች በየትምህርት ቤቱ ማካሄድ ይጠይቃቸዋል።

በአጭሩ ንባብ የሁሉም ነገር መሰረት፣ የችግሮቻችን ሁሉ መፍቻ ቁልፍ ነው። ማንቸስተር፣ አርሴናል … እያሉ የሬድዮ ጣቢያዎች ሰፋፊ የአየር ሰዓት ወስደው እንደሚያቀርቡት ሁሉ መገናኛ ብዙሃን በንባብ የመጠቀ አእምሮ ያላቸውን ሰዎች በማቅረብ በማነጋገር የንባብ ውጤት ምን እንደሚመስል ማሳየት ይኖርባቸዋል። መገናኛ ብዙሃንም ሆነ ማህበረሰቡ እንዲሁም መንግስት ለንባብ እና ለተማረ ሰው ክብርና ቦታ ከሰጡ ትውልዱን ወደ ንባብ ለመመለስ አያዳግተንም።



26

51 50 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

የአፍሪካ ጉዳይ

ዓለም በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት እየተፈተነች ትገኛለች፡፡ በዓለማችን ብሎም በአገራችን በተለያዩ ምክንያቶች በሰዎች ላይ የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች እና የህይወት እልፈቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

እንደ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በየዓመቱ አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች በድንገተኛ አደጋ ምክንያት ይሞታሉ። ይህም ከአጠቃላይ የሞት መጠን ውስጥ 10 ከመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን፤ በወባ፣ በሳንባ ነቀርሳ እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተደምሮ ከሚሞቱት ሰዎች ጋር ሲነጻጸር የ32 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ድንገተኛ የጤና እክሎች ፈጣንና ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ወሳኝ ቢሆንም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ አገሮች ቀላል አይደለም፡፡ በዚህም ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ከድንገተኛ አደጋዎች ጋር ተያይዞ ከሚከሰተው ሞት 54 በመቶው ቀድሞ መከላከል በሚችሉ ምክንያቶች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ ለተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጋላጭ ከሚባሉ አገሮች ተርታ የምትመደብ ሲሆን፤ በከተሞችና በኢንዲስትሪዎች መስፋፋት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችና በከፍተኛ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የኑሮ ዘይቤ መለወጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መበራከት ለአደጋዎቹ መጨመር እንደ ምክንያት ተደርጎ ይነሳሉ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እ.አ.አ በ2018 ያወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ብቻ 29 ሺ 386 ሰዎች መሞታቸው እና ይህም ከአገሪቷ አጠቅላይ የሞት መጠን 4 ነጥብ 81 ድርሻ እንዳለው ያሳያል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የአደጋዎች አዙሪት

ድንገተኛ አደጋ መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓት ለመፍጠር



27

53 52 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

መጋለጧ በቤተሰብ፣ በመሰረተ ልማት እና በጤና ስርዓቱ አቅም ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ ከድንገተኛ አደጋዎች ጋር ተያይዞ እየደረሳበት ያለው ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ለመቀነስ ጠንካራ የድንገተኛ ሕክምና ስርዓት መፍጠር እና ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ፣ አደጋና ጽኑ ህክምና የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ አውጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የድንገተኛ አደጋና ፅኑ ህክምና የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ፣ የጤና ሚኒስቴር በመተግበር ላይ ባለው ሁለተኛው የአምስት ዓመት የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ለተካተቱት የጤናው ምላሽ ስርዓት ማሻሻል፣ ከድንገተኛ ጤና አደጋዎች ኅብረተሰቡን መከላከል፣ በቤተሰብ ጤና አስተዋፅኦ ማድረግ እንዲሁም የጤና ሽፋንን ለሁሉም ለማዳረስ ሥራዎችን ለማስፈጸም አገራዊ የሚያስቀምጥ ነው፡፡ ይህ አገራዊ የአምስት ዓመት የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከአገሪቷ የአስር ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ጋር የተናበበ ሲሆን፤ በዋናነት ለጤናው ዘርፍ የተለዩ ግቦችን በማስቀመጥ ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር ይገልጻል፡፡

በዚህ ጽሁፍ በአገራችን ወቅቱን እና ጥራቱን የጠበቀ የድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ያለበት ደረጃ እና በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የስራ እንቅስቃሴ እንዳስሳለን፡፡

የክፍሉ መቋቋም

የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሥሩ አምስት ኬዝቲሞች የያዘ ሲሆን፤ ዜጎች ወቅታዊና ያልተቆራረጠ፣ ጥራቱን የጠበቀ የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህሙማን እንክብካቤ እንዲያገኙ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የስራ ክፍል (ዳይሬክቶሬት) ነው፡፡

ድንገተኛና ጽኑ ሕክምና እንደ አገር ብቻ ሳይሆን እንደ ዓለምም አዲስ አገልግሎት ቢሆንም ይህንን ክብደቱን በማየት ጤና ሚኒስቴር ላይ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ተቋቁሞ ሰፊ ስራ ሲያከናውን ቆይቷል። የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከማኅበረሰብ ጀምሮ እስከ ጽኑ ሕክምና ድረስ ድንገተኛ አደጋ ሲደርስ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ለመደገፍ እና ለማሻሻል የተቋቋመ የስራ ክፍል እንደሆነ የሚናገሩት የክፍሉ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ቤተልሔም ወርቄ ናቸው፡፡ ክፍሉ ድንገተኛ አደጋ መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓት በመፍጠር ዜጎችን ከድንገተኛ የጤና አደጋ መጠበቅና ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ተደራሽ የማድረግ ተልዕኮ አለው፡፡

ህብረተሰቡ ድንገተኛ ህመሞችና ስለሚደረገው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ በተመለከተ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስቻል እና ጤና ባልሙያ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ድንገተኛ አደጋ ሲገጥመው አደጋው ለደረሰበት ሰው ሊያደርጋቸው የሚችሉ ቅድመ ሕክምናዎችን ማሰልጠን በስራ ክፍሉ አማካኝነት የሚከናወኑ ተግባራት እንደሆኑ ኃላፊዋ ይናገራሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከአቅም ያለፈ ድንገተኛ አደጋ በሚያግጥምበት ጊዜ ጉዳት የደረሰበት ሰው እርዳታ ማግኘት ወደሚችልበት ተቋም ማድረስ የሚችልበት መንገድ የግንዛቤ መስጫበጫ ስራዎችን መስራት እና የማኅበረሰቡን ተሳትፎን ማነቀሳቀስ ለስራ ክፍሉ የተሰጡ ተልዕኮዎች ናቸው፡፡

የተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት የማኅበረሰቡ ጥሪዎች የሚስተናገዱበት ስርዓት፣ የአምቡላንስ አገልግሎት መከታተል እንዲሁም “የቅድመ ጤና ተቋም አገልግሎት መስጠት በዚህ ክፍል ክትትልና ድጋፍ ይደረግላቸዋል” የሚሉት ዶ/ር ቤተልሔም፤ ዳይሬክቶሬቱ ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ሪፈራል እና ተርሸሪ ሆስፒታል ድረስ የሚሰጠውን የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት “የመደገፍ፣ ጥራት የማሻሻል፣ ተደራሽነትን የማስፋት ስራዎች የሚከናወንበት ነው” ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከድንገተኛ እና ሌሎችም ቦታዎች ወደ ጽኑ ሕክምና ደረጃ የሚደርሱ ታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት (ICU) አገልግሎትን እንዲሁ ተደራሽነትና ጥራት ማሻሻል ላይ ይህ ዳይሬክቶሬቱ ሰፊ ስራዎች ይሰራል። የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአደጋ ሕክምና፣ የቃጠሎና የመመረዝ ሕክምና አገልግሎቶች ላይም እንዲሁ ተደራሽነትና ጥራት ማሻሻል ላይም ዳይሬክቶሬቱ በስፋት እየሰራ እንደሆነም ምክትል ዳይሬክተሯ ይናገራሉ፡፡

ዓበይት ክንውኖች

የስራ ክፍሉ ከተቋቋመበት 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን በርካታ ስራዎች ያከናወነ ሲሆን፤ የቅድመ ጤና ተቋም ግብዓቶችን በማዘጋጀት እና ለማኅበረሰቡ የመጀመሪያ እርዳታ ስልጠና መስጠት ላይ ሰፋፊ ስራዎች ሰርተዋል።

ድንገተኛ አደጋ ሲደርስ የሰዎች ህይወት የሚያልፈው ወይም ከፍተኛ ጉዳት የሚደርሰው በአደጋው ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን ስለመጀመርያ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ እውቀት ያላቸው ሰዎች በወቅቱ ተገኝተው ተገቢውን የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ማድረግ ባለመቻላቸው ጭምር ነው፡፡ ብዙዎች ጉዳቶች የመጀመርያ ሕክምና እርዳታና እንክብካቤ ወዲያውኑ በመስጠት ሊደርስ ከሚችል ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት መከላከል ይቻላል፡ ፡

ይህን ታሳቢ በማድረግ የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በድንገተኛ ሕመምና አደጋ ምክንያት በሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ከፍተኛ

የአካል ጉዳት እና ሞትን ለመቀነስ ብሎም ለመከላከል ማህበረሰቡ ስለመጀመርያ ህክምና እርዳታ አሰጣጥ በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖሮው የሚስችል ስልጠናዎች ሲሰጥ መቆየቱንም ዶ/ር ቤተልሔም ይናገራሉ፡፡

የስራ ክፍሉ በመላው አገሪቷ የአምቡላንስ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በሰራው ስራ እስከ አሁን 4 ሺ 300 የሚሆኑ አምቡላንሶች ተገዝተው ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል። በእነዚህ አምቡላንስ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን በመስጠት በከፍተኛ ቁጥር ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል።

የአምቡላንስ የጥሪ ማዕከላት በዋና ዋና ከተሞች ላይ ለማቋቋም ጥረት ሲደረግ መቆየቱን የሚናገሩት ዶ/ር ቤተልሔም፤ እስከ አሁን በአዲስ አበባ፣ ጅማ፣ ሃዋሳ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር የአምቡላንስ ጥሪ ማዕከላት ማስጀመር ተችሏል፡፡ እነዚህ የጥሪ ማዕከሎች ማህበረሰቡን አራት ዲጂት ባላቸው ስልኮች ደውሎ ፈጣን የአምቡላንስ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችሉ ናቸው።

የሪፈራል የህሙማን ቅብብሎሽ አገልግሎት ለማሻሻል የላይዘን ኦፊሰሮችን በማሰልጠን በሆስፒታሎች ውስጥ የላይዘን ቢሮዎች እንዲኖሩ በማድረግ የህሙማን ቅብብሎሽ የተሳለጠ እንዲሆንም ሲሰራ ቆይተዋል፡፡ በሁሉም ጤና ተቋማት ላይዘን ኦፊሰሮችን በማሰልጠን ታካሚ ከአንድ ጤና ተቋም ወደ ሌላ ጤና ተቋም ከመላኩ በፊት በውስጥ መነጋገር የሚችሉበት እንዲሁም የሚሰጡት አገልግሎት ማወቅ የሚችሉበት ታካሚዎች ያለእንግልት አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓት ተፋጥሯል፡ ፡ በአገሪቷ የሚገኙ “ሁሉም የጤና ተቋማት በኢንተርኔት በመገናኘት የህሙማን ቅብብሎሹ የተሳለጠ እንዲሆን እየተሰራ ነው” የሚሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ፣ በዋና ዋና ከተሞች ላይ ፓይለት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ነው ያረጋገጡት።

በጤና ተቋሞች ላይ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግና ጥራቱን ለማሻሻል “የቴክኒካል ድጋፎች፣ ሙያዊ ድጋፍ ይደረጋል” የሚሉት ዶ/ር ቤተልሔም፤ የጤና ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት አጫጭር ስልጠናዎች ለመስጠት የስልጠና ግብዓቶች በማዘጋጀት የባለሙያን አቅም ለመገንባት ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል።

በዓለም ጤና ድርጅት መሰረታዊ የድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ ስልጠና (WHO Basic Emergency Care) አማካኝነት ኢትዮጵያ ከሌሎች አፍሪካ አገሮች በበለጠ በጤና ጣቢያ ደረጃ ለሚሰሩ በርካታ ባለሙያዎች በሁሉም ክልሎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተችሏል።

በአገሪቷ ከአምስት ዓመት በፊት የጽኑ ሕክምና አገልግሎት የነበረው ተደራሽነት በጣም ዝቅተኛ እንደነበር የሚያስታውሱት ዶ/ር ቤተልሔም፤ በአሁኑ ወቅት ከ30 በላይ አዳዲስ የጽኑ ሕክምና አገልግሎት መስጫ

ክፍል ማቋቋም ተችሏል። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በመላው አገሪቷ 73 የሚሆኑ የጽኑ ሕክምና አገልግሎት ክፍሎች ወደ ስራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፤ የሚሰጡት አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን የተለያየ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ “የአደጋ ሕክምና ወይም የትሮማና ኢንጁሪ ሕክምና አገልግሎትን ለማሻሻል ባለፉት አምስት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በአለርት እና አቤት ሆስፒታል ሁለት አዲስ የትሮማ ማዕከሎች መክፈት” ብለዋል ሃላፊዋ፡፡

በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የመመረዝ ሕክምና ማዕከል እና የጥሪ ማዕከል ለማቋቋም ብዙ ስራዎች የተሰራ ሲሆን፤ በአሁን ሰዓት መልሶ መቋቋም ላይ ቢሆንም፤ የመመረዝ ሕክምና መስጫ ማዕከል በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። የኢንፎርሜሽን ማዕከል አገልግሎት ማቋረጥ ቢኖርም መልሶ በማቋቋም ከማኅበረሰብም ከጤና ባለሙያዎችም ጥሪዎችን በመቀበል በመመረዝ ዙሪያ ላይ መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ባለፈው አምስት ዓመት እየተሰራ ቆይቷል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዋና ዋና ከተሞች የድንገተኛ እና የጽኑ ህመምተኛ እንክብካቤ ማሻሻያ ፕሮግራም (Ma- jor cities emergency and critical care improve- ment program - MECIP) በሚል ፕሮግራም ቀርጾ በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ ያለውን የድንገተኛና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ለማሻሻል ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡ ፡ ፕሮግራሙ

“ከ2012 ጀምሮ በሐረር፣ ሀዋሳ፣ ባህርዳር፣ ጅማ፣ መቀሌንም ጨምሮ ሲተገበሩ ቆይተዋል” የሚሉት ዶ/ር ቤተልሔም፤ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ስምንት የሚሆኑ ተጨማሪ ከተሞችን በመጨመር እየተሰራበት መሆኑን ነው አጽንኦት የሰጡት። ፕሮግራሙ በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የድንገተኛ አደጋዎችና ድንገተኛ ክስተቶች ለመቀነስ ያስችላል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድንገተኛ አደጋዎች ሲደርሱ የሚሰጡ ምላሾች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች ሲደርሱ ጤና ተቋማት እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው እና አደጋዎች ከመድረሳቸው በፊት ቀድመው ምን ዓይነት ዝግጁነት ማድረግ አለባቸው በሚል ስልጠና በመስጠት ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራ ተሰርቷል። “ለተቋማቱ የአደጋ ዝግጁነት እቅድ እንዲሁም የምላሽ ዝግጁነት እንዲኖራቸው ሙያዊ ድጋፍ ተደርጓልም” ብለዋል ዶ/ር ቤተልሔም።

በዚህ ፕሮግራም ባለፉት ዓመታት ብዙ ውጤቶች ተገኝተዋል የሚሉት ሃላፊዋ፤ ለጥሪ ማዕከላት መስፋፋት የአምቡላንስ አገልግሎት መሳለጥ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ተቋሞች ላይ የሚሰጠው አገልግሎት የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አብርክተዋለል ባይ ናቸው፡፡

ቀጣይ ጉዞ..

የጤና ሚኒስቴር ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም በሚተገበረው የሁለተኛው የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ካስቀመጣቸው ግቦች መካከል የድንገተኛ አደጋዎች እና የጽኑ ህክምና አገልግሎት ተደራሽት እና ጥራት በማሻሻል ማህበረሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎችና ችግሮች መጠበቅ የሚል ይገኝበታል፡፡

በእቅዱ ላይ በተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች፣ ግጭቶች፣ በተደጋጋሚ የሚከሰቱና ያልተጠበቁ የበሽታዎች ክስተትና ወረርሽኝ፣ በመንገድ ትራፊክ አደጋዎች፣ ድንገተኛ የሆኑ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና በአዳዲስ የጤና ስጋቶች ምክንያት የሚከሰቱ የማህበረሰብ እና የህክምና ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት የህዝቡን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ እንደሚሰራ ተነስተዋል፡፡

በተጨማሪም ድንበር ተሻጋሪ የጤና ችግሮችን በመከላከል የህዝቡን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ ያቀደ ነው። የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና አደጋዎች አገልግሎት በዋናነት የሚያተኩረው በቅድመ ዝግጁነት፣ በመከላከል፣ በልየታ፣ በድንገተኛ አደጋዎች አስተዳደር እና የማገገም ስራዎች ላይ ነው።

የህክምና ድንገተኛ አደጋዎች በአፋጣኝ ህክምና አገልግሎት ካልተሰጠ ሞት ወይም ዘላቂ ጉዳት የሚያስከትል ማንኛውም የጤና እክልን ያካትታል። እነዚህ የድንገተኛ የጤና እክሎች ተላላፊ በሆኑና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እንዲሁም አፋጣኝ ህክምና በሚያስፈልገው የአካል ጉዳት አደጋ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ። ስለዚህ የድንገተኛ፣ የትራውማ እና የጽኑ ህክምና መስጫ ማዕከላት ማቋቋም እና ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል።

የማህበረሰብ እና የህክምና ድንገተኛ የጤና ችግሮችን ለመከላከል የዝግጁነት፣ የመከላከል፣ የአስቀድሞ ልየታ እና ምላሽ አቅምን እና ግብዓት ማሟላት የሚጠይቅ ነው። በተጨማሪም ድህረ ድንገተኛ አደጋዎች ዳሰሳ ማድረግ፣ የተከናወኑ ተግባራትንና እና ተሞክሮዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ አሰፍላጊ እንደሆነም በእቅዱ ሰነድ ተብራርቷል፡፡

ከሁለተኛው የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በመነሳት 10 ስትራቴጂካዊ ግቦች ያሉት የድንገተኛ፣ አደጋና ጽኑ ህክምና የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ማሕበረሰቡ በዘርፉ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የሚያሳድግበትን መንገድ፣ የድንገተኛ፣ የአደጋና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞችና የአገልግሎት ሰጪ ማዕከላት አቅም የሚገነባበትን አግባብ እንዲሁም የመድኃኒትና የህክምና ቀሳቁስ አቅርቦት የሚሻሻልበትን አሠራር ለመዘርጋት አቅጣጫ የሚጠቁም እንደሆነም በሰነዱ ተመላክቷል፡፡

የእቅዱ ተግባራዊነት ከማኅበረሰብ ጀምሮ የቅድመ ጤና ተቋም የተቀናጀ የማኅበረሰብ ጤና እና የአንቡላንስ ስምሪት ሥርዓትን መገንባት፣ በጤና ተቋማት ቀልጣፋና

ጥራቱን የጠበቀ ህይወት አድን ህክምና መስጠት፣ የህሙማንን ቅብብሎሽ በማሳለጥ አላስፈላጊ መዘግየቶችን መቀነስ፣ ለማንኛውም የጤና እክሎች መልስ መስጠት የሚያስችል አቅምን በየደረጃው መፍጠርና መረጃን ለውሳኔ በመጠቀም ላይ የሚያጠነጥን፣ የላቀ ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያስችላል ተብለዋል፡፡

ይህንን የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ በአግባቡ ተግብሮ ለኅብረተሰቡ በሁሉም ደረጃ የተቀናጀ፤ የተናበበ፤ ወቅቱን እና ጥራቱን የጠበቀ የድንገተኛና ጽኑ ህክምና አገልግሎት ለማቅረብና አግባብነት ያለው የጤና ሥርዓትን በመዘርጋት በድንገተኛ አደጋ እና ጽኑ ህመም የሚከሰቱ ህመሞችን፣ የአካል መጉደልን እና ሞቶችን በመቀነስ ጤነኛና አምራች ዜጋን ለመፍጠር ያስችላል፡፡

የዘርፉ ተግዳሮትና ምላሽ

የዝግጅት ስራ በጤና ተቋማት አነስተኛ መሆን በድንገተኛ እና ጽኑ ህክምና የሰለጠኑ ባለሙያዎች እጥረት፤ ለአስቸኳይ የጤና ክብካቤ አገልግሎቶች የሚውል ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት አለመጠናከር በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳረቶች ናቸው፡፡

የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ህክምና አገልግሎት መዋቅር በሁሉም ክልሎች እስከ ወረዳ ድረስ ባለመኖሩ ስራዎችን እስከታች ድረስ ወርዶ ለመስራት ሰፊ ተግዳሮት እንደነበር የሚያነሱት ሃላፊዋ በክልሎች ከሚኒስቴሩ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ አደረጃጀት ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ “የድንገተኛና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት እስከ ታችኛው የማህበረሰቡ ክፍል ድረስ ለማውረድ ይሰራልም” ብለዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የጤና ክብካቤ አገልግሎቶች የሚውል ዘላቂነት ያለው የፋይናንስ ስርዓት አለመኖር እንደ Major cities emergency and critical care improvement program (MECIP) ያሉት አዳዲስ ኢኒሺየቲቭ ተግባራዊ ለማድረግ የፋይናንስ ስርዓቱ ክፍተት እንዳለበት የሚናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ፤ አገልግሎቱን በተሻለ መልክ ለመስጠት በፋይናንስ ስርዓቱ ያሉት ማነቆዎች ለመፍታት የሚያስችል ጥናት ይካሄዳል፡ ፡

የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱ ለማሳካት በዘርፉ ያለው የሰው ኃይል በቁጥርም በጥራት ለማሳደግ በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ አደጋና ጽኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራበት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ዶ/ር ቤተልሔም አስረድቷል፡፡

በመጨረሻም በአገር አቀፍ ደረጃ የድንገተኛ አደጋ መቋቋም የሚችል የጤና ስርዓት በመፍጠር ዜጎችን ከድንገተኛ የጤና አደጋ ለመጠበቅ የአንድ ዘርፍ ሃላፊነት ተግባር ብቻ ሳይሆን፤ የሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርና የተባበረ ክንድ ያስፈልጋል፡፡



28

55 54 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

የአፍሪካ ጉዳይ

ኢትዮጵያ ባለፉት መቶ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ከጦርነት ስጋትና ጦርነት ወጥታ የምታውቅባቸው ዓመታት ደርዘን አይሞሉም። በተለይ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ፣ ረሃብና ስደት እጅግ የከፋና አገሪታብ በብዙ ዓመታት ወደ ኋላ የጎተተ ነው። አገሪቷ በየአxስር ዓመቱ እየተፈራረቀ የሚመጣውን ድርቅና የሚያስከትለውን የሰው ህይወት ሕልፈት ፣የከብቶች ሞት ከዚያም አልፎ ወልለደው ከብደው ከኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለው፣ ወደ ውጭ ተሰደው ሕዝቦቿ ከስቃይ ስቃይ እያለፉ ነገን በተስፋ ሲጠብቁ የጦርነት ነገሪት ይጎሰማል።

ተፈጥሮ የነጠቀቻቸውን ሰላም በሰው ሰራሽ መንገድም እያጡ መጥተዋል። የጦርነት ነገሪት ይጎሰማል። ከውጭ ወራሪ እስከ እርስ በርስ ጦርነት ይካሄዳል። በውጤቱ አገርና ህዝብ እየተጎዳ መጥቷል። ዜጎች ተፈናቅለዋል። ህጻናት ያለወላጅ ቀርተዋል። ወጣቶች ህልማቸው ተጨናግፏል። አዛውንቶች ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት አጥተው፤ በወጣትነታቸው ዘመን ያገለገሏት አገር በእስተርጅና ውለታቸውን ከመመለስ ይልቅ በጥፋት ውስጥ እንዲያልፉ ተገደዱ። ዛሬም በተመሰሳይ መልኩ ሰላምና ደህንነቷ የሚነጥቁ በርካታ አሜካላዎች አጋጥመዋታል። ከዓመት በፊት የተጀመረው ጦርነትና ያስከተለው ሰቆቃ፣ በየአካባቢው በጽንፈኞችና አክራሪዎች የሚነሳው ግጭት አገሪታን ሰላም አሳጥታቷል።

ኢትዮጵያዊያን ድህነትን የሚያክል ታላቅ ጠላታቸው ላይ አተኩረው እንዳይንቀሳቀሱ እግር ከወርች ስሯቸዋል። ሰላምና ደህንነታችን እውን መሆኛው ጊዜ መጣ ሲባል ድንገት የሚያከስም የጦርነት ሰቆቃ ይለሰማል። ለምን? እንዴትስ ይህ ሊሆን ቻለ? ዘላቂ መፍትሄውስ ምንድን ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ምላሽ የሚሹ ናቸው።

ሰላምን ፍላጋ - ኢትዮጵያ



29

57 56 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ሰላም

“አገራችን ሰው ሞተ ይባላል። በምን ስንል? በዘር በሃይማኖት፣ በማንነት ይባላል። ሰው ባልተፈጠረበት ሃይማኖት፣ ዘር፣ ማንነት መገደል የለበትም። ስለዚህ ትልልቅ ሰዎች ሰውን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በማንነት አትግደሉ፤ እባካችሁ፤ እባካችሁ።” የሚል ንግግር የሰማሁት ምናልባት አስር ዓመት ከሚሆነው ሕጻን አንደበት ነው። የሕጻኑ ሀሳብ የሰው ልብ በሁለት ነገሮች እንደከፈል ያደርጋል። ሕጻኑ ሀሳቡን የገለጸበት መንገድ ብስለቱን ያሳያል። አሁን በአገርና መንግስት ግንባታ ላይ እየተሳተፈ ላለው ትውልድ ግን ያነሳው ጥያቄ ቀለል ተደርጎ የሚታይ አይደለም።

የሕጻኑ ሀሳብ በአንድ በኩል የአገራችን ሰላምና ደህንነት ማጣት ጥልቀቱ ምን ያህል እየዘለቀ መምጣቱን ያሳያል። በአገሪቷ ላይ የተንሰራፋው የሰላም እጦት ከሁለትና ሶስት ትውልድ አልፎ በጣም ለጋ አእምሮ ላላቸው ሕጻናት ላይ እያሳደረ ያለው ጫና ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፤ በትውልድ መካከል የጥላቻና ፍርሃት ዘር እየተዘራ መሆኑን ያመላክታል። ሕጻኑ እያወጋን ያለው ጉዳይ የችግሩን ስፋት ብቻ ሳይሆን አሁን ያለወና መጪው ትውልድ እየተገነባበት ያለው ስነ ልቦና አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን ያረጋግጣል።

በሌላ በኩል ግን የሕጻኑ ንግግር አዲስ ተስፋን ያመላክታል። በዘር፣ በሃይማኖትና ማንነት መከፋፈል ላይ ያልተመሰረተ ትውልድ በመገንባት በኩል እጆቻችንን ዘርግተን በጥንካሬ ብንሰራ ተስፋ መኖሩን ያሳያል። በዘር፣ በሃይማኖትና በማንነት መገዳደል እርባና ቢስ ዘመኑን የማይዋጅ ድርጊት መሆኑን ከህጻንነታቸው እየተገነዘቡ የመጡ የ21ኛ ክፍለ ዘመን እንቦቀቅላዎች መኖራቸው ተስፋ ያጭራል። ይህ ግን እንዲቀጥል ለማድረግ ለአእምራቸው ስለምናቀርበው እውነት መጠንቀቅ ተገቢ መሆኑን ያመላክታል።

የአሁኑ አያያዛችን የዚህን ዘመን ትውልድ ሰብዕና ለመወሰን የሚያስችል ማንነት እንዳለው መረዳት ተገቢ ነው። ህጻኑ ስጋቱን አሳየን። “ትላልቅ ሰዎች እባካችሁ አትግደሉ” ሲል በተማጽንኦው ውስጥ ተስፋውን አሳይቶናል። ለሰላም ያለውን ናፍቆት ገልጾልናል።

አዲሱ ትውልድ መጪውን ዘመን ለመለወጥ የሚያስችለው አቅም ለመገንባት ለእነርሱ የምናስተምራቸው “ሰላም ያስፈልጋል። ስለሰላም ኑሩ” የሚል ሳይሆን ሌላ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ የሚቸል እውነት መስተማር እንዳለብንም ያመላክታል።

ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው መንገዶች ዳገት ቁልቁለት የበዛባቸው፣ ጭንቅና መከራ ያልተለያ ቸው ናቸው። የአንድ ክፍለዘመን ታሪክን ብንመለከት የሚያረጋግጥልን ይሄው ነው። አገራችን በ188 ዓ.ም አደዋ፣ በ1928 ማይጨው፣ በ1970 ጅግጅጋ፣ በ1990 ባድመ ጦርነቶችን አካሂዳለች። በጀግንነት ድል ብታስመዘግበም ለጆቻን

ገብራለች፤ ለጥሪት ሊሆናት የሚችለውን ሀብታነ አጣለች። ዜጎች ከጦርነት በኋላ በሚከሰት ስነ ልቦናዊ አሉታዊ ጫና ውስጥ እንዲገቡ ሆነዋል። የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት በራሱ ወገኖች ተከድቶ ወደ መንግስት ወደ ህግ ማስከበር የተሰማራበት የ2013 ዓ.ም ጦርነትም ሌላው የታሪክ ምዕራፍ ነው።

በእነዚህ መካከልም በ1953 ዓ.ም ተሞክሮ የከሸፈው መፈንቅ ለመንግስት፣ በ1966 ዓ.ም የተካሄደው የመፈንቅ ለመንግስት እና ያስከተለው አብዮት የአገሪቱን መሰረታዊ የታሪክ አቅጣጫ ያሰቀየረና ዛሬ ለተደረሰበት አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ገጽታዎቸ መሰረት የጣለ ጊዜ ነበር። ከዚህ በኋላ የተከሰተው የ1977 ዓ.ም የመፈነቀ ለመንግስት ሙከራና መክሸፍ በአገሪቷ ላይ ያስከተለው ሚዛን መዛባት ነው።

የ1983 ዓ.ም የለውጥ ሂደት ለአገሪቷ መጻኢ እድል መልካም አጋጣሚዎቸን ይዞ መጥቶ ነበር። በወቅቱ የኢህአዴግ የመሰረተው የሽግግር መንግስትም ሀገመንግስት ሲጸድቅ የህዝቦችን ሰሜት አርገቦ አድነታቸወን ሊያጠናክር በሚቸል አግባብ መጠቀም የሚያስቸሉ ስራዎች የከናወኑ ነበር። እነዚህን አድሎች በአግባቡ ከመጠቀመ ይለቅ የዴሞክራሲ ሥረዓትን ገፎ፣ መልካም አሰተዳደረን አጥፈቶና የሰብዓዊ መብት ጥሰተን አስፋፍቶ ዓመታትን ቆይታል። በዚህ ወቅት ውስጥም የተለያዩ ትርክቶችን በማስፋፋት አገር ወደ ገደል አፋፍ ላይ አደረሰ፤ የህዝቦችን አንድነት አደጋላይ ጣለ።

የትናንትናዎቹ የፈጠሩት ታሪክ ዛሬ ላይ ላለነው ሰላምና ደህንነታችንን ያሳጣን ከሆነ፤ እኛ እምንሰራው ደግሞ ለነገዎቹ ሰላምና ደህንነታቸውን የሚመልስ መሆን አለበት። ለዚህ ደግሞ ለሰላምና ደህንነታችን ማጣት መንስኤ ምንድን ነው? የሚለውን መፈተሽ ይገባል። በመሰረታዊ ነገር መሰረቶቹ በርካታ ቢሆኑም ጎልቶ የታየው ችግሮቹን መመልከት ያስፈልጋል። ግን ሰላም የምንለው ሀሳብ ምን ያመላክተናል? የጋራ መሰረታዊ ግብዓት አለን ወይ? ለሚለው ጥያቄ ቅድሚያ እንስጠው።

“ሰላም” ስንል በርካታ ትርጓሜዎች ይሰጠዋል። አንዱና በቀላሉ ተደርጎ የሚታየው “ከሁነት ነጻ መሆን፤ መረጋጋት” የሚለው ነው። ሌሎቹ በሰዎች ግንኙነት መካከል የተረጋጋ መስተጋብር መኖር፣ የተለያዩ ማህበረሰባዊ መዋቅሮች ያለምንም እንከን መስራት፣ ልዩነትን ተረድቶና አድንቆ ያለምንም ሁከት በመልካም ተረጋግቶ መኖር፣ የመከባበር ባህል የዳበረበት፣ እርስ በርስ እውቅና ተሰጣጥቶ አንዱ ለሌላው መኖር የበኩሉን የሚያደርግበት፣ በስምምነትና በመተባበር አብሮ በመኖር የሚፈጠረው ጥልቅ ግንኙነት ሳይታወክና ሳይረበሽ በሰላም መኖርን ያመላክታል።

ሰላም ከጎረቤትም ሆነ ከሌሎች ጋር ጦርነት ያለመክፈተን ወይም ጦርነት አቁሞ በጸጥታ መኖርን ያሳያል። አጠቃላይ ማህበረሰባዊ እሴቶች፣ ተግባቦቶች፣ መዋቅራዊ አደረጃጀቶች የማያናጉ አነስተኛ ግጭቶች ቢኖሩም ከአጠቃላይ የሰላም መደፍረስ ጋር ሊታዩ አይችሉም።

አሁን በአገራችን የሚስተዋለው የሰላም አጦት አጠቃላይ ማህበረሰባዊ መዋቅሩን እያናጋ መጥቷል። ተባብረውና ተሳስበው የኖሩትን ህዝቦች ቅራኔ ውስጥ የከተተ፣ የሃይማኖት ልዩነት ቢኖራቸውም ተፋቅረው የኖሩ ህዝቦችን የረበሸ፣ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጭካኔ የተስተዋለበት ወቅት መሆኑ ተስተውላል። ይህ መሰረታዊ የሰላም ማጣት ለምን ተከሰተ?

አሁን በአገራችን የተከሰተው ሰላምና ደህንንት እጦት መሰረቱ አሁን አይደለም። ለዘመናት ተከማችቶ የቆየ መሰረታዊ ችግር ያለበት ጉዳይ ነው። ዛሬ ላይ ውጤቱ እጅግ ገዝፎና ከብዶ ቢታይም ዘሩ የተዘራበት ዘመን ሩቅ ነበር። ዛሬ ትናንት የተዘራውን ፍሬ እየተቋደስን መሆኑን ያመላክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ እንደሚሉት ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ሲነሳ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። “አንደኛው ማንኛውም ግጭት፣ ማንኛውም ጠብ ከህብረተሰቡ የሚወጡ መነሻቸው መዋቅራዊ ነው።” በማለት ይገልጹታል።

በየትኛውም አካባቢ ለግጭቶች መነሻ ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ህብረተሰቡን ሊገፉፉና ወደ ግጭት ሊያደርሱ የሚቸሉ ምክንያቶች በአግባቡ እየታዩ፣ እየተፈተሹና ቅድሚያ የሚሰጣቸወን ቅድሚያ በመስጠት መፍተሄ ካልተፈለገ ለሰላም እጦት እንደዋነኛ መሳሪ ይሆናሉ።

“ሁለተኛው መሰረታዊ ጉዳይ የግጭት መንስኤ፣ የሰላም አጦት አባባሽ ጉዳዮች ሊከሰቱ ይችላሉ። ዋናው ችግር ካለ ቀላል የሚመሰሉ ነገሮች ሁሉ በርካታ አደጋዎች ሊያስከትሉ ይችላሉ።” በማለት ዶክተር ቀነዓ ይናገራሉ።

ዛሬ በአገራችን ማንኛውም ጉዳይ ለጸብ መነሻ ምክንያት ሆኖ በርካታ ሰዎቸ ለህልፈተ ህይወት ይዳረጋሉ። ንብረቶች ይወድማሉ። በአገራቸን ለዓመታት መፍትሄ ሳይሰጣቸወ የቆዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ላይ ሌላ በመጨመር እየገዘፈ መምጣቱን ማስተዋል ይቻላል። ሰላምን እያቃወሰ፣ ማህበረሰባዊ መዋቅርን እያናጋ የመጣው ፈታኝ ሁኔታን በጥንካሬ መታገል ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል።

ዛሬ ሁላችንም ሰላምን በየመንገዳችን እንፈልጋላን። ግን ሰላም ተናግታል። ለምን?

የትርክት አባዜ

አገራችን በተለይ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የመጣችባቸው መንገዶች እጅግ እንቅፋት የተሞሉባቸው ናቸው። በጦርነት፣ በረሃብ፣ በስደት ለዓለም ህዝብ የተገለጠችባቸው መሆኑን ድርሳናት ያሳዩናል። በዚህ ዘመን ውስጥ የከፋውና አገራችንን ወደ ቁልቁለት ጉዞ እየወሰዳት ያለው ጉዳይ ግን ጽንፈኝነትና አክራሪነት

ናቸው። ለእነዚህ መነሻቸው “የእኔ ብቻ ትክክል ነው፤ እኔ ብቻ ትልቅ ነኝ” ከሚል አስተምሮና የሚመነጭ መሆኑን ማጤን ይቻላል። የዚህ ዓይነቱ አመለካከተ ደግሞ ማህበረሰቡ ለዘመናት በጋራ ይዞት የቆየውን መልካም አሴቶች የሚያስጥልና “አኛ ብቻ” በሚል ሌላውን የሚሳንስ አለፎመ የሚያጠፋ ነው።

ማህበረሰቡ በሃይማኖት፣ በማንነት፣ በብሄር የነበረውን አመለካከት በመቀየር የመጠፋፋት ሰብዕና እያላበሰ የሚመጣ ነው። ታሪክን የሚጠፋ ታላቅ ሴራ ነው። “በአገራችን ትልቁ የሚታየው የነበረው ጥንካሬ በብሄርና በሃይማኖት አካባቢ የሚታየው ነበር። ዛሬ . . . ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልግ በዋናው ምንጭ ላይ ነው ያተኮረው።” በማለት ነው ዶክተር ቀነዓ የጽንፈኝነቱና አከራሪነቱ ዋናው ዒላማ ምን እንደሆነ የገለጹት።

ለዚህ ደግሞ ለዓመታት እየተፈጠረ የተዘራው ትርክት ማጤን ግድ ይላል። በአስደናቂ መልኩ በጋራ ክነድ በተመዘገቡ ታሪኮች እንኳን መግባባት እስከሚሳነን ድረስ በትርክት እርስ በርስ እንድንፋጅ ሆነናል።

ለምንድን ይህ ሆነ? ብለን ስንጠይቅ እ.ኤ.አ. በ1975 በስደት ወደ ፈረንሳይ የሄደው ቼክ ጸሃፊ ሲሆን በ1981 በዜግነት የፈረንሣይ ዜጋ የሆነው ደራሲ ሚላን ኩንደር ያለው ሀሳብ መልስ ሆኖ ይገኛል። ደራሲ ሚላን እንደሚገልጽልን አንድን ህዝብ ለማጥፋት ከታሰበ የማስታወስ ችሎታውን ማጥፋት ይገባል።

የህዝቡን “መጽሃፎቹን፣ ባህሉን፣ ታሪኩን ማጥፋት። ከዚያም አንድ ሰው አዲስ መጽሐፍ እንዲጽፍ፣ አዲስ ባህል እንዲሠራ፣ አዲስ ታሪክ እንዲፈጥር ማድረግ። ብዙም ሳይቆይ ያ ሕዝብ ምን እንደሆነና ምን እንደነበረ መርሳት ይጀምራል” (Destroy its books, its cul- ture, its history. Then have somebody write new books, manufacture a new culture, invent a new history. Before long that nation will begin to for- get what it is and what it was...) በማለት የገለጸው በአገራችን ላይ ለሃምሳ ዓመታት መፈጸሙን መዘንጋት ይቻላል። መጽሀፎቻችንን ማጥፋት ባየቻል የማያነብ ትውልድ ተፈጥራል። ከእራሱ ታሪክ ይልቅ የአውሮፓና የአሜሪካንን ታሪክ ሲያሳድድ እንዲቆይ ተደርጓል። ለዘመናት የገነባነውንና የሰራነውን የጋራ ታሪክ ረስተን፣ አንድነታችንን አጥተን፣ አብረን ኖረን ዛሬ የማንተዋወቅ ዓይነት እስከመሆን ደርሰናል።

“ሕዘብን የሚያስተሳስረው ታሪክ ነው። ታሪክ የሌለው ህዝብ አንድነቱን ያጣል” የሚለውን የታሪክ ፕሮፌሰር ኖሃ ሃራሬ ሃሳብ ከሚላን ኩድር ሀሳብ ጋር አሰናስነን ከተመለከት ነው ኢትዮጵያ የምትባለው የረጅም ዘመናት ባለታሪክ አገር ለማጥፋት ለተሸረበ ሴራ ሰለባ መሆኗን መገንዘበ አያቅትም።

ለዚህም ነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ማዕከል አስተባበሪ ሚኒስትር አቶ አብርሃም አለህኝ “እዚህ አገር የተለያዩ

ትርክቶች አሉ። በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ውስጥ ብዙ ትርክቶች አሉ። እርስ በርስ እንዳንግባባ፣ እንዳንዋደድ፣ እንዳንፋቀር ዘላቂ ትልምና ግብ ታሳቢ እንዳናደርግ፣ በአጠቃላይ መስተጋብር ላይ እንቅፋት የሆኑ ስሁት ትርክቶች አሉ። እነዚህን ስሁት ትርክቶች ወደ አዲስ ትርክት መቀየር አለብን” በማለት የገለጹት ሀሳብ ቆም ብሎን ራሳችንን እንድንጠይቅ የሚያስገድደን።

የስህተት ትርክት ለምንድን እንዲገባ ተፈለገ? የሚለው ሀሳብ ብዙዎችን የሚያወያይ ጉዳይ ነው። የታሪክ ምሁሩ ታዬ ቦጋለ “መራራ እውነት” በሚለው መጽሀፋቸው “በታሪክ ዙሪያ ከ1970ዎቹ ጀምረው የተዘጋጁ ሰነዶች በሴራ ፖለቲካ እግር ተወርች ተቀፍድደዋል። ከታሪክ አልፋና ኦሜጋ ርቀዋል። ከመዳረሻ ግቡ በአያሌው አፈንግጠዋል” በማለት ታየኢትዮጰያ ታሪክ በሴራ ፖለቲካ እጅ ውስጥ መውደቁን ያረጋግጣሉ። ለዚህም ነው ትርክት እየበዛ የመጣው። ግን ትርክት በራሱ ምንድን ነው? በታሪክና በትርክት መካከል ምንድን ልዩነት አለው? የሚሉ ነገሮችን ማየት “ውሃን ከምንጩ፤ ነገርን ከስሩ” እንዲሉ ይሆናል።

ታሪክ በዘመናት፣ በዓመታት ውስጥ የተፈጸሙ ነገሮችን በሰነድ፣ በማስረጃ አሰደግፎ የሚቀርብ እውነታን የሚገልጽ ነው። በተለያዩ አካዳማዊ መስፈርቶች ሲመዘን ተጨባጭነቱ የሚረጋገጥ ነው። ተጨማሪ ማስረጃዎች በማግኘት የሚዳብር፣ ትውልድ ያለፉ ጉዳዮችን እንዲያጠና ለማስቻል የሚረዳ አቅም ነው።

ትርክት ግን ይለያል። አንድ ፍላጎት ባለውና ግብ ባስቀመጠ ቡድን የሚዘጋጅ ልቦለዳዊ ነው። በማስረጃ ማስደገፍ አይቻልም። በፈጠራ የተሞላ ነው። አንዳንዴ የግለሰቦችን ስብዕና መሰረት አድርጎ ለማግዘፍ፣ ለማንቋሸሽ፣ የሚተረክ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ የቡድን ፍላጎትን ለመጫን፣ እነደሂትለር ልዩ ዘርነን ለማለትና ለማረጋገጥ የሚፈጠር፣ ማስረጃ የማይገኝለት ልቦለዳዊ ጉዳይ ነው።

ትርክት ከሰሜት ጋር ተቀላቅሎ ስለሚነገር ሰዎችን በቀላሉ ይማርካል። በሃሳቡ ተጽእኖ ለመፈጠር ያስችላል። ሰዎች በምንባቸው ለፈጠሩትና በሌሎች ሰዎች አእምሮ ላይ በሳሉት ምስል እውነታን በማጥፈት አዲስ ታሪክ ይመሰርታሉ። የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ነው ኢትዮጵያን የገጠማት።

የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ጥላቻ፣ ቂም በቀል፣ መከፋፈል የሚያሰርጽ ትርክት ተተክሏል። ትርክቱ ወንድማማቾችንና እህትማማቾችን “አንተ ትብስ” የሚለውን እሴታቸውን አጥፍቶ ቂምና ጥላቻን ዘርቷል። ይህ ደግሞ ለአገር ፋይዳ የለውም።

ለአንድ ቡድን ወይም ግለሰብ ፍላጎት ማስጠበቂያ ሲባል የተዘራው ትርክት የዛሬ የታሪክ ስብራት ሆኖ እየተስተዋለ ነው። ባለፉት ዓመታት በተለያየ መንገድ ተሰንደው

ሲሰራጩ የቆዩት ትርክቶች ዛሬ ላይ ጦር አማዘው እያጋደሉ ናቸው።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን በፈጠራ ሙያ ራሳቸውን አብቅተው ስማቸውንና አገራቸውን ማስጠራት የሚጠበቅባቸው ወጣቶች በሃሰተኛ ትርክቶች ሳቢያ ለንትርክ፣ ለጸብ፣ ለሁከትና ለግጭት ከመዳረግ አልፈው ጦር ሰብቀው መወጋት ጀመረዋል። በአንድነት፣ ተፈቃቅሮ፣ አብሮ የኖረን ህዝብ ተያይቶ እንደማይተዋወቅ የማድረግ ስራዎች ተከናውነዋል። በዚህም ዜጎች ተሰቃይተዋል፤ ከኖሩበት ቀዬ በግፍ ተፈናቅለዋል። ተሰደዋል። ሕጻናትና አረጋዊያን ተበትነዋል። በአጠቃላይ በትርክት ስሀተት፣ አንዱ ሌላውን ተከባብሮ መቀበል ባለመቻል አገራችን ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች።

ስለዚህ ምን ይደረግ ጥያቄ ሆኖ ይገዝፋል። እነዚህን ትርክቶች እንዴት ይነቀሉ? ትርክቶቹን ለመንቀል የጋራ መግባባትስ አያስፈልገንም? የችግሮቻችን ምንጭ ለማጥፋት ምንድን ማድረግ እንችላለን?

የፈታኙን ምዕራፍ ማለፊያ መንገዶች

በአገራችን ፈታኝ ምዕራፎች ከፊታችን ተደቅነዋል። ህዝቦቻችን መካከል የቆየውን መልካምና ጠንካራ እሴት መልሶ ለማምጣትና ከዘመኑ ጋር በዋጀ መልኩ ለመቀጠል መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። አሁን ያለንበት ዘመን እጅግ አሳሳቢ ቢሆንም ብዙዎች “ኢትዮጵያ ጠላቶቿ እንደሚመኙት ሳይሆን እያሸነፈች ትመጣለች” እንደሚሉት በአስተማመኝነት ለማሸነፍ ዛሬ የሚከናወኑ ተግባራት ወሳኝ ጉዳዮ ናቸው።

ትርክትን ማስተካከል

“ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር በታሪክ ላይ የተፈጠረውን ተቃርኖ ማረቅ ያስፈልጋል” በማለት የታሪክ ኤምሬተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ የገለጹት ሀሳብ ሁሉንም ያመላከታል።

በኢትዮጰያ ውስጥ ታሪክ መጻፍ ከተጀመረ ስድሳ ዓመታትን ያሰቆጠረ ቢሆንም የትርክትን ያህል ተጽእኖ መፈጠር ተሰኖታል። በእውነትና በማስረጃ ላይ መሰረት ያደረገ ታሪክ መጻፉ እየተስፋፋ የመጣውን ትርከት ለመቀነሰ አቅም እንዳጠረው ብዙዎቸ ይናገራሉ።

የኢትዮጵያነ ትክክለኛ ታሪክ ለመገንዘብ በእቅውነትና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ሰነዶቸን መግኘት አስፈላጊነተ አያጠራጥርም። እስከ ዛሬ ያለው ታሪክን እያጠፉና በተለያዩ ቡድኖቸ ፈላጎት ላይ መሰረተ ያደረጉ ትርክቶች ትውልድ በተገቢው መንገድ አገሪቷን እንዳያውቅ አድረጋታል። የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም “በኢትዮጵያ ታሪክ በትርክት እየተተካ ዜጎች የአገራቸውነ ታሪክ በትክክል እንዳይረዱ አድርጋል” በማለት ሀሳቡን ያጠናክሩታል።

እንደሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ ገለጻ የተዛባ የታሪክ አረዳድና ታሪክን በትርክት መቀየር ለአገራዊ ውድቀት መነሻ ሆኗል።



30

59 58 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም

ይህን ለመቀየር በመሰረታዊ ደረጃ ሁለቱን ነገሮች መፍታት ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት ብዙዎች የሚስማሙበት ነጥብ “በኢትዮጵያ የተንሰራፋው ትርክት” መፍትሄ ማግኘት አለበት። ለዓመታት የተዘራውን የመከፋፈል፣ የቂምና የጥላቻ ትርክትን በአዲስ እውነተኛ የመቀየር፣ የተዛባን የታሪክ አረዳድ የማስተካከል ተግባር የሁሉም የቤት ስራ ሆኗል።

ሰላም በጠፋና ጭንቅ በመጣ ቁጠር ሕጻናት “ሰው ለምን ይገደላል?” በማለት ለሚያነሱት ጥያቄያቸው ትርክት ላይ መሰረት ያደረገ ምላሽ በመስጠት የጥፋት መሳሪያዎች አድርገን ማሳደግ አይገባንም። ስለዚህ “ስሁት ትርክቶች ወደ አዲስ ትርክት መቀየረ አለብን” በማለት የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባት ማዐከል አሰተባበሪ ሚኒስትር አቶ አብርሃም ያነሱት ሀሳብ የትርክት ለውጥ አሰፈላጊነትን ያጸናል።

በመሰረቱ በ21ኛው ክፍለዘመን በትርክና በታሪክ አረዳድ መንስኤነት ለጭቅጭቅና ጥፋት መጋበዝ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ማህበረሰቡ በእየለት ጉዳዩ ሊያከናውናቸወ ሊተገብራቸው የሚገቡ ማህበረሰባዊ ለውጦችን የሚያፋጥኑ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም እዚህ ላይ በመከፋፈል ለጠላት ሴራ ራስን አሳልፎ መስጠት መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። በዚህ ሁኔታ ምን ያህል እርቀት ይኬዳል? ምላሽ ይፈልጋል።

ለዘመናት እየተሰናሰነ የተነገረ ታሪክ በአንድ ጀንበር ወይም በዘመቻ የሚጠፋ ጉዳይ አይደለም። መጸሀፍት ተጽፈው፣ ተራኪ ተዘጋጅቶና አዳዲስ ነገሮች ተፈጥሮ የተተረከን፣ በትውለዱ አእምሮ ውስጥ ዘልቆ የገባን ጉዳይ በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻል፤ በአዲስ ታሪክም በመቀየር ውጤት ማስመዝገብ ፈታኝ ነው። ይህም ሆኖ ታሪክ ለአገረ መንግስት ግንባታ የሚኖረው ፋይዳ ታላቅ በመሆኑ ያሉትን ችግሮች በመፍታት ኢትዮጵያን የሚወክል ታሪክ መጻፍ አስፋለጊነት ጊዜው የጠየቀው ጉዳይ ነው።

የታሪክ አረዳድን ለማሰተካከል፣ የተዛባን ታሪክ ለማስተካከል፣ ትረክቶቸን በአዲስ ለመቀየር ማህበረሰባዊ ቁርጠኝነት ይፈልጋል። አገራዊ አንድነትን ለማምጣት የሁሉም ፍላጎት መኖር ይገባዋል። ለዚህ መወያየት፣

መግባባትና ለሚደረስበት መደምደሚያ ወሳኝ ምላሽ መሰጠት መፍትሄ ይሆናል።

“በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ መምከርና ጥልቅ ውይይት አድርጎ መግባባት ላይ” መደረስ እንዳለበት ነው የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አጽንኦት የሰጡት። በዚህ ሀሳብ የታሪክ ምሁራን ይስማማሉ።

“አንዱን ብሄር እንደባዕድ የማየት ትርክት መንቀል፤ ጠንካራ እሴት ማጽደቅ ይጠበቃል።” ያሉት ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ፤ በአሁኑ ወቅት የጥላቻ ትርክት መንቀል መጀመሩን ነው ያበሰሩት። መንግስት ህብረ ብሄራዊ አንደነትን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክሩ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ይህም ሆኖ በቀኑ ፈተናው ቀላል አየደለም። ዜጎች ችግሮች ያጋጥማቸዋል።

አገራዊ ምክክር እንደተስፋ

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች፤ እያለፈችም ነው። በለውጥ ሂደት ውስጥ ከሚያጋጥም ለውጥን በጽናት ከሚገዳደር ሃይል ባለፈ ለጦርነት፣ ለሰዎች መሞት፣ ለስደትና በከፍተኛ ደረጃ ንብረት መውደም ምክንያት የሆነ ችግር ተፈጥሯል። ሰላም ጠፍቷል። ሰዎች ወጥተው መግባት ስጋት እስከሚሳናቸው ድረስ ችግሮች ተፈጥረዋል።

በኢትዮጵያ የተካሄደው ለውጥ ዴሞክራሲን እንዲሰፍን፣ የህዝቦችን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር በህዝባዊ አመጽ የመጣ ነው። ከዚህ ለውጥ ህዝቡ ዴሞክራሲን፣ ሰብዓዊ መብትን፣ መልካም አስተዳደርን ይጠብቃል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቹ በአግባቡ እንዲመለሱ ይናፍቃል።

የህዝባዊ ለውጡ ዋና ማጠንጠኛ ህዝቡ በኢህአዴግ የአገዛዝ ሥርዓት ያጣውን እንዲያገኝ፣ ጠንካራ አገረ መንግስት እንዲገነባ፣ በወረቀት ላይ ሰፍረው የቆዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መብቶቹ እንዲረጋገጡ ለማድረግ ነበር። ለውጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካም ውጤት ያስመዘግባል ተብሎ ቢጠበቅም፤ “በለውጡ ደስተኛ ያልሆኑና የተለያዩ ፍላጎቶች ያሏቸው የውስጥና የውጭ ሃይሎች ለውጡን ለመቀልበስ በቅንጅት

በርካታ አፍራሽ ተልዕኮችን እየፈጸሙ ይገኛሉ” በሚል የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የሰፈረው ሃሳብ ውጤቱን በግልጽ ያመለክታል።

በአገራችን በብርካታ ጉዳዩች በሀሳብ አለመስማማት መኖሩም ይስተዋላል። ለዓመታት እርስ በርስ ያጋደለ በፖለቲካ አመለካከት፣ በአገረ መንስት ግንባታ በህዘቦች ጥያቄ ላይ በምሁራን መካከል ያለው የሀሳብ ልዩነት ነው። ይህን የሀሳብ ልዩነት አውርዶ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የመወያየት ባህል ያለመዳበሩ ዛሬ እየደረሰ ላለው ጥፋት ሌላው መንስኤ ነው። በታሪክ አረዳድ፣ በተዛባ ታሪክ ላይ መንጠልጠልና ትርክቶችን ተቀብሎ መጓዝ አገሪቷንና ህዝቦቿን ብዙ አክፍሏል።

በአገራችን ምሁራን መካከል በብዙ ጉዳዮች መግባባት አልተፈጠረም። ከዚህ ቀደም “አሸናፊ” እና “አቸናፊ” በሚሉ ቃላት ውስጥ ባለ ፊደልና እስን ተከትሎ በሚመጣ ሀሳብ ምክንያት የሰው ህይወት እስከሚጠፋ ድረስ ያለመግባባት ልምምድ ያደረገ ምሁራዊ ምልከታ ዛሬ ድረስ ዘልቆ የህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ አድርጓል። ጽንፈኝነትና አክራሪነት እንዲስፋፋ መንገድ ከፍቷል።

“በልሂቃን መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ፤ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደቱን እጅግ ፈታኝ አድርጎታል። ይህ ቅራኔ እና መዘዙ ከልሂቃን አልፎ በማህበረሰቡ ውስጥ እየሰረጸ ከፍተኛ ምስቅልቅል ማስከተሉ እሙን ነው” በማለት ከላይ የጠቀስነው ሰነድ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ያሳያል።

ይህ ወደ ማህበረሰቡ የዘለቀው ችግር ሰላምን አደፍርሷል፤ ህዝቡ በቂም፣ ጥላቻና መከፋፈል ውስጥ ሆኖ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲያይ ከማድረግ ያለፈ በድርጊት የተገለጸ ጥፋት ተከስቷል።በየአካባቢው ጽንፈኝነት መንገድ አግኝቷል፤ አክራሪነት ተመችቶታል። በዚህም ሰዎች ሞተዋል፤ ተፈናቅለዋል፣ ተሰደዋል። ወልደው ከብደው ድረው በደስታ በኖሩበት አካባቢ ተዋርደው፣ አንገታቸውን ደፍተው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ተሰደዋል። ድርጊት በአንድት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ያነጠጣጠረ እኩይ ድርጊት ነው።

“ጽንፈኝነት የሚባለው ጉዳይ ፖለቲካዊ ቃል ሳይሆን በዋናው በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ጉዳይ ነው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልግ በዋና ምንጩ ላይ ነው ያተኮረው”በማለት ዶክተር ቀናዓ ይገልጻሉ። ዛሬ በኢትዮጵያ በጽንፈኝነትና በአክራሪነት በተግባር እየተገለጹ የመጡት ችግሮች በምስራቅ አፍሪካ የነጻነት ታሪክ ያላትን፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ሀብቷ የብዙዎችን ትኩረት የምትስብን ታላቅ አገር አፍርሶ ትናንሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ያመለክታል።

በአንድ ወቅት አንድ የምዕራቡ ዓለም ፕሮፌሰር በአንድ ቪድዮ ላይ “ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ምስራቅ አፍሪካ

ከድህነት መውጣት የለባትም” ሲል የተሰማው ንግግር እውን እንዲሆን መንገድ ከፋች ድርጊት እየተፈጸመ መምጣቱን ያመላክታል። ታዲያ ምን ይደረግ?

ዶክተር ቀናዓ “የኢትዮጵያ ጥንካሬ ምንጭ መመለስ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ የጥንካሬ ምንጭ አንድነት፣ መተባበር፣ ኢትዮጵያዊነት መመለስ ያስፈልጋል” በማለት የቀድሞውን የህዝቡን አንድነት እንዲመጣ የመስራት አስፈላጊነትን አጽንኦት ይሰጡታል። ይህ አንድነት እንዴት እናምጣው?

ለዚህ ጉዳይ “አገራዊ ምክክሩ ትልቅ እድል ነው፤ ጠቅላላ ኢትዮጵያዊ መወያየት አለበት” በማለት የአገራዊ ምክክር ማካሄድ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ዋነኛ እርምጃ መሆኑን ያሳያሉ። ብሄራዊ ምክክር ከተደረገ ቀድሞ የነበረውን አንድነት ለማምጣት ያስችላል። ለሰላም መንስኤ የሆኑትን መዋቅራዊ ችግሮችን የመፍታትና እርሱ እንዲባባስ የሚያደርጉ አቀጣጣይ ምክንያቶችን የመግታት አቅምም ይፈጠራል።

መንግስት “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች መድሃኒቱ የዜጎች ቁጭ ብሎ መወያየት ነው” በማለት እንደሚያምን ዶክተር ቢቂላ የተናገሩት በቅርቡ የተቋቋመው ኮሚሽን መንግስትም ተስፋ እንደጣለበት ያመላክታል። ኢትዮጵያዊያን ቁጭ ብለው ከተመካከሩ የችግሮቻቸውን መንስኤዎች የመፈተሽ፣ መፍትሄያቸውንም በጋራ የመተለምና የመተግበር እድላቸው ይሰፋል።መነሻቸው አገር ስለሚሆንም በፖለቲካ፣ በአመለካከት ልዩነት ድንበር አይሆንባቸውም። ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክር ማድረግ በምሁራን፣ በህዝቡ መካከል መግባባት የመፍጠር አቅም ይኖረዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶክተር ንጉሱ ለገሰ በቅርቡ “የዘመናት ቁስላችንን ሽረን ወደ ፊት መመልከት እንችል ዘንድ ተመካክረን አንድ ነገር ላይ መድረስ አለብን” ብለዋል። ሁሉም ተስፋ የሚያደርገው አካታች አገራዊ ምክክር ተደርጎ የችግሮቹ ሰበዞች ተነጥለው ይወጣሉ የሚል ነው። ችግሮቹን በመለየት የሚቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎች፣ ምክረ ሀሳቦች የአገሪቷን መጻኢ እድል እንደሚወስን ይታመናል።

በህዳር 2015 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የአገራዊ ምክክር አጀንዳ ኢትዮጵያን ከጥፋት ይታደጋት ይሆን? ሁሉም በቅን ልቦና አገራዊ አንድነትን ጠብቆ ለመሄድ፣ በሀሰት ትርክት የገነባውን የባቢሎን ግንብ አፍርሶ ሰላምን ለማስፈንና ይቅርታን ለማወጅ ምን ያህሉ ዝግጁ ይሆናል? ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት ጊዜውን መጠበቅ ግድ ይላል። ነገር ግን ብሄራዊ ምክክር ማለት ምንድን ነው? ምንስ እንዲያመጣ ታስቦ ይዘጋጃል? ለሚሉት ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት አመላካች ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል።

አገራዊ ምክክር ለምን?

አገራዊ ምክክር በተለያዩ ጊዜያት እያደጉና ስር እየሰደዱ የመጡ ግጭቶችን ለመፍታት፣ አለመግባባቶችን ለማረቅ ያስችላል ተብሎ የሚታመንበትና ተግባራዊ የሚሆን የግጭት መፍቻ አንድ ስለት ነው። በኢተዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ማድረገ አሰፈላጊነት አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታና አሳሳቢ ጉዳይ አኳያ ተመራጭ ዘዴ መሆኑን ነው የሚገለጸው። ሰዎች ምክክር ለምን ተባለ? ውይይት ወየም ድርድር የሚለው የተመረጠ አይሆንም እነዴ የሚሉ ጥያቄዎች ያነሳሉ።

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማብራሪያ ላይ እንደገለጸው፤ውይይትም ሆነ ድርድር የሚሉትን ቃላት መጠቀም አላስፈለገም። ውይይት ሃሳብ መለዋወጥን እና ማንሸራሸርን የሚያመለክት የመስተጋብር ውጤት ነው። ድርድርም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች አሊያም ቡድኖች በሰጥቶ መቀበል መርህ የሚሰሩበት በመሆኑ ነው።

በአገራዊ ምክክሩ ሂደት የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሄ በመፈለግ፣ በመፍተሄዎቹ ላይ በመግባባት አገራዊ አንድነት እና ህበረታችን ማጠናከርን መነሻ ያደረገ በመሆኑ “ምክክር” የሚለውን ሀሳብ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። አገራዊ ምክክር ሲካሄድ አንድ ወጥ ሀሳብ እና አንድ ወገን ብቻውን የሚመክርበት አይደለም።

በምክክሩ ወቅት በየአጀንዳው የተለያዩ ሀሳቦች፣ ጥቅሞች፣ ፍላጎቶችና መብቶች ተወክለው ምክክር ይደረግበታል። ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ልዩነትን በሚያሳይ መልኩ ሁሉም ያላቸውን ሀሳብ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንደሚያመጡ ተስፋ ይደረጋል። ጥልቅትና አግባብነት ባላቸው አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ስለሚሰጠውና ተገቢ የሆነ አቀጣጫ ስለሚቀመጥለት ወጤቱ መለካም እነደሚሆን ቷስፋ ይደረጋል። በዚህም ለአገሪቱ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦች ይገኛሉ፤ ሁሉም በጋራ ለመፍትሄያቸው ይረባረባል።

በሕዝብ ጥቆማ የተመረጡ 11 አባላትን ያቀፈው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዋጅ የተቋቋመውና የኢትዮጵያ ህዝብ ያካሂደዋል ተብሎ የሚጠበቀው አገራዊ ምክክር “ጉዳዮች ከታች ወደ ላይ አካታችና አሳታፊ በማድረግ አገራዊ መግባባት እውን እንዲሆን ማስቻል ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

የአገራዊ ምክክር ሰላምን ለማስፈንና ግጭትን ለማስወገድ፣ በተለየም በለውጥ የተጀመሩተን የፖለቲካና ዴሞክራሲ ሽግግሮችን ለማሳለጥ ይረዳል። በተለይም በአገር ውስጥ ያጋጠሙተን ልዩነቶች በማጥበብ፣ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማሻሻልና መተማመን ለመፍጠር እነደሚያስችል እምነት ተጥሎበታል። ይህም ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ጽንፈኝነትንና አክራሪነትን ለማስወገድ አንድ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል።

ምክክሩ ከሌሎች ጊዜ የሚለይ መሆኑም እመርታን

ያሳያል። “የተለመደ ልሂቃን ውይይት ሳይሆን ከታችኛው ህብረተሰብ ጀምሮ ሁሉን አሳታፊና ሀሳብ የሚንሸራሸርበት፣ በግልፀኝነትና ተጠያቂነት መርሆች የሚመራ ነው” በማለት የገለከጹት ፕሮፌሰር መስፍን ከታች ወደ ላይ በመምጣት መፍትሄው ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ያደርጋል።

በዚህ በኩል የምሁራን ተመሳሳይ አቋም ያሳያሉ። ፖለቲከኛው ሌንጮ ለታ ከኢፕድ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ብሄራዊ ምክክሩ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና መግባባትን በመፍጠር ሰላምን ያሰፍናል። የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት ያስችላል።

እንደአቶ ሌንጮ ገለጻ፤ ሂደቱ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና መግባባትን በማጠናከር ሰላም ለማስፈን የጎላ ሚና ይኖረዋል፤ በግጭት አካባቢዎች ሰላም በማውረድ፣ ሰላም በሰፈነባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከሁሉም አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመሥራት ይረዳል።

ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ለመወጣትም ሆነ ዘላቂ ሰላም ለማሰፈን በራሳ መንገድ ችግሮቿነ የመፈታት አቅም አላት። ምሁራን፣ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና መገናኛ ብዙሃን በእውነተኛ መሰረት ላይ በመቆም ለአገሪቷ መጻኢ እድል ጠንክረው መስራት አለባቸው።

ህዝቡ ከላይ እስከታች በመንቀሳቀስ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውይይት እንዲያካሂድ ማድረግ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። በመሰረቱ አገራዊ ሰላምና መረጋጋት ለምክክሩ ሂደት ትግበራ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያዊያን በምክክሩ አሸናፊ ሆነው ለመውጣትና ስኬታማ ለመሆን ሁሉም የድርሻውን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል። በኢትዮጵያ ምድር ስር ሰላምና ደህንንት እውን እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች መረባረብ ይኖርባቸዋል። ዚህም በየአካባቢው የሚስተዋሉ ግጭቶች መቆም ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። ግጭቶችን መቀልበስ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።ህዝቡ፣ የጸጥታ ሃይሉ በየአካባቢው የሚስተዋሉ ግጭቶችን እንዲቆም በማድረግ መጪውን ዘመን መልካም ማደረግ ተገቢ ነው። በዚህም ዶክተር ቀናዓ “የኢትዮጵያን የጥንካሬ ምንጭ መመለስ ያስፈልጋል” ያሉትን ሀሳብ አጽንኦት መስጠት ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ነን።



31

61 60 ነጋሪ 5ኛ ዓመት ቁጥር 19 ታህሳሥ 2014 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም