ነጋሪ 22

1

ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 22 ኅዳር 2015 ዓ.ም ዋጋ 15 ብር

ሰላም ለኢትዮጵያ



2

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ



3



4

ማውጫ

ሰላም - ለኢትዮጵያ

14

የኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት - ማዕድን

6

በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት

መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች


አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ

ስልክ ቁጥር

+251-11-55-00-11

+251-11-56-39-31

+251-11-56-52-21

ፋክስ ቁጥር

+251-11-55-16-09

enanegari@gmail.com

14

22

ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ተግባር



5

ዋና አዘጋጅ አብዱራህማን ናስር

ም/ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ሰናይ የሺመቤት ደመቀ

ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ

አዘጋጅ አየለ ያረጋል መንገሻ ገ/ሚካኤል

አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com

ፎቶግራፍ በወርቅነህ ረጋሳ

እርምት ባለሙያ ትዝታ ሁሴን

መልዕክት

28

የሥነ-ጽሑፍ ሚና ለአገር እና ለሕዝብ ፅናት

34

የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ጉዞ

40

አፍሪካ ቀንድ እና ኢትዮጵያ

46

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ፖሊሲ

54

የወርቃማው ዘመን ፈርጦች

62

“ትንኝ ለመራባት . . .

66

“የሕሙማን እፎይታ” - ማንዚሎፋሻ ሰርጀሪ እና የጥርስ

ሕክምና

እነሆ!

ሰላም የብዙ ነገሮች መሰረት ነው። ሰላም የአብሮ መኖር ማጠንጠኛው እሴትም ነው። ሰላም ካለ የፈጉበት

ለመድረስ፣ ራዕይን እውን ለማድረግ ይቻላል። በአገር ላይ ሰላም መስፈን ሩቅ ለመጓዝ መሰረቱ ነው። ለዚህም ነው

ኢትዮጰያዊያን ሰላምን አጥብቀው የሚሹት።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የሰላም እጦት አጋጥሟታል። በዚህም ዜጎች ውድ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ከቤት

ንብረተታቸው ተፈናቅለዋል፤ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ለአብነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜኑ

የአገራችን ክፍል የተቀሰቀሰው ጦርነት ብንመለከት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ያስከተለው

ጉዳት ከባድ ነበር። ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና አገራዊ አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ እርምጃዎችን መውሰድ

የግድ ይላል። ሰሞኑን በፌዴራል መንግስትና በህዋሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት ለሰላም ወዳድ

ሃይሎች ታላቅ ብስራት የሆነውም ለዚህ ነው። ነጋሪ መጽሔታችን የሰላም ስምምነቱ አንድምታዎች ምንድን ናቸው?

በአገራችን የተፈጠሩ የሰላም እጦት ችግሮች እንዴትና ለምን ሊያጋጥሙ ቻሉ? ዘላቂ መፍትሄውስ ምንድን ነው?

በሚሉት መሠረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥልቅ ዳሰሳ ይዛለች።

ኢትዮጵያ በማዕድን ሀብት ከሚታወቁ አገሮች መካከል ትጠቀሳለች። ይሁን እንጂ ይህንን ሀብት በማልማት

ዘርፉ ሊያስገኘው የሚችለውን ጥቅም በማግኘት በኩል በሚፈለገው ደረጃ ሳትጠቀምበት ቆይታለች። ከቅርብ

ዓመታት ወዲህ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። የማዕድንና ነዳጅ ዘርፉን ለማልማትም የተለያዩ እንቅስቃሴዎች

እየተካሄዱ ነው። ለመሆኑ በአገራችን የሚገኙ የማዕድናት ዓይነት እና የነዳጅ ሀብት መጠን እንዴት ይገለጻል?

እነዚህን ሀብቶች በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ከማዋል አኳያ የነበሩ ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? አሁን የተጀመሩ

እንቅስቃሴዎችስ ምን ያህል ውጤት ያስገኛሉ? ነጋሪ ምላሽ አላት።

ፈጠራ አዳዲስ ሃሳቦችን በማመንጨት እና ወደ ምርት ወይም አገልግሎት በመለወጥ ለገበያ በማቅረብ ለተጠቃሚው

የማድረስ ችሎታ ነው። ብዙዎቹ የበለጸጉ የዓለማችን አገሮች ለኢኮኖሚ ዕድገታቸው መሠረት የሆነው የፈጠራ

ሀሳብ ነው። በኢትዮጵያ ለአዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች የተሰጠው ትኩረት እስከምን ድረስ ነው? የመንግስትና የአጋር

አካላት እንቅስቃሴ እንዴት ይመዘናል? በአገር በቀል ኢኮኖሚው የተቀመጡ ዋና ዋና ምሰሶዎች ምንድን ናቸው?

የሚሉ ጉዳዮች በስፋት ተተንትነዋል።

የአገራችን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ታሪክ ከአሁኑ ዘመን ጋር በማነፃፀር ታስቃኘናለች። “ዕድገት አሳይቷል ወይስ ወደ

ኋላ ቀርቷል?” የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ በማንሳት የዘርፉን ባለሙያዎች አናግራለች። እነርሱም የየራሳቸውን

እምነትና ምላሽ ሰጥተዋል፤ ነጋሪ መጽሄታችን አስተናግዳዋለች።



6

የኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት - ማዕድን

ኢኮኖሚ



7

በጥሩወርቅ አያሌው

ዳራ

ማዕድን ከአላቂ ሐብቶች አንዱ ቢሆንም ቀጣይነት ያለው የምጣኔ ሀብት ዕድገት መሰረት በመጣል የማይተካ ሚና ካላቸው ዘርፎች መካከል ተጠቃሽ ነው። በብልጽግና ማማ ላይ የሚገኙ አገሮች የማዕድን ሀብታቸውን በአግባቡ በመጠቀም በዓለም ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን ሲያሳዩበትም ይስተዋላል። ኢትዮጵያም በማዕድን ሐብታቸው ከሚታወቁ አገሮች መካከል ትጠቀሳለች። ከኮፐር፣ ከወርቅ፣ ከታንታለም፣ ከፖታሽ፣ ከብረትና ከድንጋይ ከሰል

ማዕድናት ዋነኛ ዓለም አቀፍ አቅራቢዎች አንዷ የመሆን አቅም እንዳላት በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጥናቶች ያመላክታሉ። ይሁን እንጂ ይህንን ሀብት ማልማት የሚያስችል አሰራርና ፖሊሲ በመቅረጽ ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ባለሃብቶችን በመሳብ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት ዘርፉ ሊያስገኘው የሚችለውን የውጭ ምንዛሬ ከመጠቀም አኳያ እንደ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿ ሁሉ በሚፈለገው ደረጃ ሳትጠቀምበት ቆይታለች።

የኢትዮጵያ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት - ማዕድን



8

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች እምቅ የማዕድን ሀብት እንደሚገኝ መረጃዎች እና የማዕድን መልክዓ ምድር ጥናት አረጋግጠዋል። ከሰፊው የኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት የኢንዱስትሪ፣ የድንጋይ ከሰልና የብረት ማዕድናት ተጠቃሾች ናቸው። ከማዕድን ሀብቶቿ መካከል የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ወርቅ የአንበሳውን ድርሻ ቢይዝም ጂም ስቶን እና ኦፓል የተሰኙት ማዕድናትም የወጪ ንግድ መጠን ድርሻቸው ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ ማዕድናቱ ላይ እሴት ጨምሮ መላክ የሚያስችል ኢንዱስትሪ ባለመኖሩ አብዛኞቹ የሚላኩት እሴት ሳይጨመርባቸው በመሆኑ የሚያስገኙትን ገቢ መጠን ይቀንሰዋል።

ለማዕድን ልማት ኢንቨስትመንት ምቹ የአየር ንብረት የሚገኝባት ኢትዮጵያ የማዕድን ልማቱ በቀዳሚነት የተያዘው በአነስተኛ አምራቾች፣ እውቀት መር ባልሆነ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ባልተደገፈ መንገድ እየተከናወነ ይገኛል።

የማዕድን ልማት ኢንቨስትመንት ማስፋፋትና ዕድገት

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የማዕድን ሐብቷን በጥልቀት የመጠቀም ዕቅድና ትግበራ ውስጥ ገብታለች። ከላይ የተዘረዘሩትን የማዕድን ሐብቶች ለመጠቀም በአገር በቀል ምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ላይ ተመስርቶ መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ለማሻገር ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ ውሰጥ የተለየ ትኩረት በመስጠት በብዝሃ ዘርፍ የምጣኔ ሃብት ዕድገት እና የሥራ ዕድል ምንጮች ተደርገው ከተዘረዘሩት ዋና ዋና የትኩረት ዘርፎች መካከል የማዕድን ልማት ዘርፍ አንዱ ነው። ለዚህም ፈጣን፣ ዘላቂና መሠረተ ሰፊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የኢኮኖሚያዊ ብዝሃነት (Economic Diversification) ዕሳቤ እንደ ስትራቴጂ ይተገበራል።

ኢትዮጵያ እምቅ የማዕድን ሃብቷ ለአገር ብልጽግና የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በዘርፉ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የፖሊሲና የአሰራር ማሻያዎችን እያደረገች ትገኛለች። የሥነ-ምህዳር መረጃን ማሰባሰብና ለባለሃብቶች ማስተዋወቅ በ10 ዓመቱ ዕቅድ የተለየ ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል ይጠቀሳል።

የማዕድን እና ነዳጅ ዘርፍ ልማት ዕቅድ ዋና ዓላማ የማዕድን እና ነዳጅ ሐብቶችን ለይቶ በማወቅ፣ በማልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጡን ማፋጠንና አገራዊ ሃብትን ማሳደግ እንዲሁም ዘርፉ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትና አገር ውስጥ ገቢ የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማጉላት፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማስፋት፣ ለማኑፋክቸሪንግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማቅረብ፣

የዘርፉን ምርቶች እሴት እንዲጨምሩ በማድረግና የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ፋይዳውን ማሳደግ ነው። ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ለያዘችው የምጣኔ ሃብት መዋቅራዊ ሽግግር ዕቅድና የመካከለኛ ገቢ አገር የመሆን ትልም መሳካት ወሳኝ እንደሆኑ የታመነባቸውን የማኑፋክቸሪንግና የግብርና ዝመና ስትራቴጂዎች ከማፋጠን አኳያ ከማዕድን ዘርፍ ልማት ከፍተኛ ሚና እንደሚጠበቅ ዕቅዱ ያመላክታል።

ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ልማትን በስፋት ለመጠቀም በመንደርደር ላይ ያለች አገር እንደመሆኗ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግና በዘርፍ ያለውን እምነት ለመጨመር በመሰረተ ልማትና ዘርፉን የሚደግፉ አሰራሮችን በመዘርጋት በኩል ከመንግስት በርካታ ስራዎች እንደሚጠበቁ አስቀምጧል።

የማዕድን ዘርፍ ልማት በኢትዮጵያ ትርጉም ባለው ደረጃ ዘመናዊ የማዕድን ልማት የሚታየው በወርቅ ማዕድን መሆኑን በማስቀመጥ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የገቢ ምንጭ በመሆን። በገንዘብ ተቋማት እንደ ሀብት መያዣነት ከመቆጠር። እንዲሁም በአገር ደረጃ እንደ አንድ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ጎልቶ ከመውጣት አኳያ ብዙ ርቀት አለመሄዱን የልማት ዕቅዱ አስፍሯል። በሌላ በኩል የጨው ምርት ጥራትና መጠንን በመጨመር ከውጭ የሚገባውን የጨው ምርት በ2022 በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ግብ ተጥሏል።

ኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፉን ጨምሮ ሰፊ ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖራትም አልምቶ ከመጠቀም አኳያ ብዙ ርቀት አልተጓዘችም። በተለይም በማዕድን ዘርፍ ያላትን ሀብት አልምቶ ከመጠቀም አኳያ ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው። ይህም ከበለጸጉ አገሮች አኳያ በልማት ወደኋላ የመቅረቷ አንዱ ምክንያትም፣ መገለጫም ነው። ለዚህም በዋነኝነት በዘርፉ ያለው ኢንቨስትመንት በመጠን፣ በዓይነትና በጥራት ዝቅተኛ መሆን። በአገሪቷ የማዕድን አለኝታ ሽፋን መረጃ በዝርዝር እና በጥራት በበቂ ደረጃ አለመኖር፣ መረጃው በሚገኝበት ጊዜም መረጃ ከማቅረብ፣ የተቀላጠፈና ፈጣን የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ከማስፈን፣ ከማስተዋወቅና አቅም ያላቸውን ባለሀብቶች ከመሳብ ጀምሮ ዘርፉን የማስተዳደር አቅም ውስንነት። በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅም ደካማ መሆን፣ የዘርፉን ልማት ከሌሎች ዘርፎች ልማት ነጥሎ የማየት ችግር ወይም በተገቢው ደረጃ ግምት ውስጥ አለማስገባት፣ የሥልቶች ግልጽና ወጥ አለመሆን፣ ከማኅበረሰብ እስከ ፖሊሲ አውጪ ባሉ ተቋማት ስለ ማዕድን ሀብትና በዘርፉ ስለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የተያዙ ገንቢ ያልሆኑ ግንዛቤዎችና አመለካከቶች፣ የፌዴራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት የማዕድን አስተዳደር የዘርፉን ሕጎች ለመተግበር የአቅም ውስንነት መኖር ተጠቃሽ ተግዳሮቶች መሆናቸውን በአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ተዘርዝሯል።

በመሆኑም የልማት ዕቅዱ ተግባራዊ በሚደረግበት ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም እነዚህን ችግሮች በማቃለል የማዕድን ዘርፍ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ በአጽንኦት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ ነዳጅን ጨምሮ ከማዕድን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ምርቶች ከውጭ ለማስገባት በዓመት ከስምንት ቢሊዮን ዶላር በላይ ታወጣለች። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከምታወጣባቸው መካከል አንዱ የሆነውን ማዳበሪያ የተፈጥሮ ጋዝ ላይ መሰረት በማድረግ በአገር ውስጥ ለማምረትና በአጠቃላይ በማዕድን ዘርፍ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተለያዩ ተባራት እየተከናወኑ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ገልጸዋል። በተለይም መንግስትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያስወጡ ያሉና በአገር ውስጥ ከማዕድን መመረት የሚችሉ ምርቶች ላይ ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል በአገር ውስጥ ለማምረት በትኩረት እየተሰራ ነው።

መንግስት በቀጣዮቹ ዓመታት ከውጭ የሚገቡትን ማዳበሪያ፣ ከሰል፣ ብረት እና የውሃ ማከሚያ ክሎሪን በአገር ውስጥ ለመተካት ቁርጠኛ አቋም ይዟል። በዓመት 300 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የድንጋይ ከሰል ወደ አገር ውስጥ ይገባል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በዓመት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰል ከውጭ ከሚገባው በተሻለ ጥራት ማምረት የሚችል ፋብሪካ በቤኒሻልጉል ጉሙዝ ክልል ተተክሏል። በተጨማሪም በጅማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። በዚህም በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ከውጭ የሚገባውን የድንጋ ከሰል ለማስቀረት እና ወደ ውጪም ለመላክ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ ያብራሩት። መንግስት በእያንዳንዱ ዓመት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን የተጣራ የድንጋይ ከሰል ይፈልጋል። በቀጣዮቹ 10 ዓመታትም ከ7 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን በላይ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት የድንጋይ ከሰል ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ለሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን በቀጣይ የሚቋቋሙ የብረት፣ የወረቀትና የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎችን ታሳቢ በማድረግ እየተሰራ ነው።

ለማዳበሪያ ምርት 98 በመቶ በግብዓትነት ከሚያገለግለው የተፈጥሮ ጋዝ፣ በኢትዮጵያ ፍለጋው ከተጠናቀቀው የተፈጥሮ ጋዝ ማዳበሪያን በቀጣይ ሶስትና አምስት ዓመታት ማምረት የመጀመር ዕቅድ አለ። መንግስት በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያላቸውን ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች እየጋበዘ ይገኛል የአቡዳቢ፣ የአሜሪካ እና የቱርክ ኩባንያዎች ከተጋበዙት መካከል ተጠቃሾች ናቸው። የተወሰኑት ተፈልጎ የተገኘውን የማልማት ስራ የሚጀምሩ ሌሎች ደግሞ ፍለጋ ላይ የሚሰማሩ ይሆናሉ።

በተለያዩ አካባቢዎች በተደረገ ጥናት የብረት ፋብሪካዎችን ለመገንባት ቦታዎችን መለየት ተችሏል። 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ቶን የብረት ክምችት ያለባቸው አምስት ቦታዎችን እንዲሁም በዘርፉ ተሰማርተው ማምረት የሚችሉ



9

ኩባንያዎችን የመለየቱ ስራም እየተከናወነ ይገኛል። ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚያስፈልገውን 10 ሚሊዮን ቶን ብረት በአገር ውስጥ ለመሸፈን ከወዲሁ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

ከውጭ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡትን የግንባታ ዕቃዎች በአገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ትኩረት ተሰጥቷል። የአገሪቷን የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እየመራ የሚገኘው የግንባታው ዘርፍ እስከ 70 በመቶ የሚደርሰው ግብዓት በማዕድናት ላይ እሴት ተጨምሮባቸው ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ናቸው። የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ይህንን ክፍተት የመሙላትና የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ማስቀረት አንዱ ትኩረት ነው። ከውጭ የሚገባውን የሴራሚክ ምርት ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት እና በአገር ውስጥ ለመተካት በባለሀብቶች ሁለት ፋበሪካዎች እየተገነቡ ይገኛል።

በልማት ዕቅዱ የተያዘው አቅጣጫ የማዕድን ዘርፉን መዋቅራዊ ሽግግር በማፋጠን አጠቃላይ አቅም መፍጠር ሲሆን፤ በተለይም የዘርፎችን ትስስር ማጠናከር፣ የማኑፋክቸሪንግና የግብርና ዝመናን ለማፋጠን ከውጭ የሚገቡ የግብርናና የማኑፋክቸሪንግ ግብዓቶችን በመተካት ማዕድናትን በግብዓትነት መጠቀም፣ ተጨማሪ እሴት በዘርፉ በመፍጠር ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽኦ ማድረግ፣ ለዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ አጋዥ ዘርፍ እንዲሆን በማድረግ የማኅበረሰብ የሀብትና የልማት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ እና ተወዳዳሪ የማዕድን ኢንዱስትሪ በመፍጠር መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት

ትኩረት ይሰጠዋል። ለዚህም የቀጣይ አስር ዓመታት የማዕድን እና ነዳጅ ልማት የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይተዋል።

የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የአገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ

የውጭ ምንዛሪ ግኝትና የአገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ በ2012 በጀት ዓመት 160 የደረሰውን የዘርፉን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ብዛት በ2022 ወደ 660 ለማሳደግ ዕቅድ ተይዟል። ለዚህም የወጪ ንግድ ማዕድናት (ወርቅ፣ ጌጣጌጥና የከበሩ ማዕድናት፣ ዕብነበረድ፣ ፖታሽ፣ ታንታለምና ሌሎችም)፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ምርቶች ለዓለም ገበያና ለአገር ውስጥ ፍጆታ በዓይነት፣ በብዛትና በጥራት የሚቀርቡ ሲሆን ለዚህም የቤተ ሙከራ፣ የቤተ መሳሪያና የመረጃ ማሰራጨት አገልግሎቶች ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ይደረጋሉ።

በማዕድናት እና ነዳጅ ምርምርና ልማት ጥናት ወቅት ባለሀብቱ የሚያወጣቸው ወጪዎች አግባብነት ያላቸውና የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘቡ እንዲሆኑ በማድረግ አገራዊ የሀብት ብክነትን የመቀነስ፣ የገቢ ምንጮችን አሟጦ የመጠቀም፣ እሴት የመጨመርና የማጣሪያ ወጪዎችን ለመቀነስ አገራዊ አቅም የማሳደግ። ምርትና ምርታማነትን የማጎልበት እንዲሁም በዘርፉ የልማት ሥራዎች የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ግልፅ አሠራር የመከተል ሥራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል።

ዕቅዱ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ የዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ድርሻ መሻሻል እያሳየ ይገኛል። ለአብነትም በ2014 ከግብርና ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ካስገኙ ዘርፎች መካከል ማዕድን አንዱ ነው።

ሚኒስትር ታከለ እንዳብራሩት ኢትዮጵያ ካላት ሀብት አኳያ አሁን እየተገኘ ያለው ገቢ ከሚጠበቀው ጋር ሲነጻጸር እምብዛም አይደለም። ያም ሆኖ የተደረጉ የፖሊሲና የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች ለግኝቱ መጨመር በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። የወርቅን ባሕላዊ አመራረት ወደ ኩባንያ መቀየር የመንግስት ትኩረት ነው።

በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው በባሕላዊ መንገድ እየተከናወነ ያለውን የማዕድን ዘርፍ ልማት ማዘመን ትኩረት ተሰጥቶታል። የባሕላዊና አነስተኛ የማዕድናት አምራቾች እንዲደራጁ ድጋፍ በማድረግ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግና የማዕድናት ምርትና የምርት ውጤቶች ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት እንዲጠናከር እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አንስተዋል፣ ለዚህም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ተኩል ወደ ምርት የሚገቡ ፈቃድ የተሰጣቸው ግዙፍ ኩባንያዎች ይገኛሉ።

የወጪ ንግድ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሊትየምና ታንታለም ላይ እየተሰራ ይገኛል። በጌጣጌጥ ማዕድናት ላይም አበረታች ለውጥ እየመጣ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል። በተመሳሳይ እምነበረድ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። የተደረጉ የፖሊሲ



10

ማሻሻያዎች፣ የተደራጀው ተቋማዊ አቅምና የሰው ኃይል ተደምሮ በቀጣዮቹ ሦስትና አራት ዓመታት ዘርፉ ከግብርና እኩል የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምንጭ የመሆን አቅም እንዳለው አረጋግጠዋል። ላለፉት ዓመታት ዘርፉን እየተፈታተነ የቆየውን አሁን ደግሞ በሊትየምና በወርቅ ላይ የሚስተዋለውን የኮንትሮባንድ ንግድ ለማስቀረትና ሕጋዊ አሰራር ለመዘርጋት ከብሔራዊ ባንክና ከክልል ቢሮዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የዘርፉን ኢንቨስትመንት ማስፋትና ማጎልበት

በዘርፉ ኢንቨስትመንት ለመሳብ መሰረተ ልማት በማመቻቸት፣ ፖሊሲና አሰራሮችን በማሻሻል ሰፊ ልምድ ያላቸው ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ከአገር በቀል ባለሃብቶችና ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጋር በሽርክና እንዲሰሩ የማስማማት። በማዕድን ሥራዎች ፖሊሲ የተለዩ የማዕድን መስኮች ላይ የምርምርና ሥርፀት ሥራዎችን የማካሄድ። ፕሮጀክቶችን በተገቢው የጊዜ ሰሌዳ እንዲከናወኑና ምርታማነታቸው እንዲጨምር የማድረግ፣ የባዮፊውል ቴክኖሎጂን የማስፋፋት፣ የግሉ ዘርፍ ደፍሮ የማይገባባቸውን መስኮች በመለየት በመንግሥት መሪነት የግሉን ዘርፍ በማበረታታት ኢንቨስትመንት የማመቻቸት። ለግሉ ዘርፍ በጥናት ላይ የተመሠረተ የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ነው። በዚህም በ2012 በጀት ዓመት 50 የደረሰውን የአገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ብዛት በ2022 በጀት ዓመት ወደ 1 ሺህ 50 ለማሳደግ። በዘርፉ

በአገልግሎት መስክ የሚሰማሩ ኢንቨስትመንቶችን ብዛት በ2012 ከነበረበት 1 ሺህ 700። በ2022 በጀት ዓመት ወደ 6 ሺህ 700 የማሳደግ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ ነው።

የአገር በቀል አነስተኛና መካከለኛ ባለሀብቶች በብዛት እንዲፈጠሩ በማድረግ ከከፍተኛ ደረጃ ባለፈቃዶች ጋር በትስስር እንዲሰሩ የማድረግ እና ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ሥራዎች የሚሰሩ ይሆናል። በኩባንያዎችና በባሕላዊ አምራቾች በ2012 በጀት ዓመት የነበረውን 3 ነጥብ 2 ቶን የወርቅ ምርት በ2022 በጀት ዓመት ወደ 137 ቶን ለማድረስም ዕቅድ ተይዟል። ከማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ የሚጠበቀው ከአገራዊ ፍጆታና ፍላጎት አኳያ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው መልማት ያለባቸውን የዘርፉን የሀብት ክምችት ለይቶ የቅድመ አዋጭነት ጥናት በማካሄድ ለመንግሥትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮች በስፋት እንዲቀርቡ ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ መሰረት እየተሰራ ነው። ከሥነ-ምድር መረጃ ጋር በተያያዘ የማዕድናት ክምችት ሀብት ማደራጀት በ2022 በጀት ዓመት ወደ 40 በመቶ በማሳደግ /ይህ አሃዝ በ2012 በጀት ዓመት 10 በመቶ ነበር/ ለኮንስትራክሽን፣ ለኬሚካል፣ ለፔትሮኬሚካል፣ ለኃይል ማመንጫና ሌሎች ተዛማጅ ምርቶች ግብዓት የሚሆን የአለኝታ ክምችት ቦታዎችን በመለየትና በማጥናት ለሚመለከታቸው አካላት ለማቅረብ በ2012 1ሺህ 600 የነበሩትን ጥናቶች በ2022 በጀት ዓመት ወደ 6 ሺህ ለማድረስ ግብ ተይዟል።

እሴት የሚጨምሩ የማኑፋክቸሪንግ ሥራዎችን

ማስፋፋት

እምቅ ክምችት እንዳላቸው የተረጋገጡ ማዕድናትና የተፈጥሮ ጋዝ እሴት ተጨምሮ ለገበያ ማቅረብ እንዲቻል የኢንዱስትሪ ግብዓት ማዕድናትን በተገቢው ዓይነት፣ መጠንና ጥራት እንዲቀርብ ማድረግና ለአገር ውስጥ ፍጆታ ወይም ወደ ውጭ ተልከው ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ የማዕድን የማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች እንዲቋቋሙ የቅድመ አዋጭነት ጥናት በማድረግ ለግሉም ይሁን ለመንግስት የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲቀርቡ ይደረጋል። የማዕድንና ነዳጅ ምርት አቅራቢ ባለሀብቶች በግላቸው ወይም ከሌላ ባለሀብትና በመንግስትና በግል አጋርነት በማስተሳሰር የምርት አቅርቦት እሴት ሰንሰለት እንዲጎለብት በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም የማሳደግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል።

በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚመረቱ የዘርፉ ምርቶች ተገቢው እሴት ተጨምሮባቸው ለገበያ እንዲቀርቡ ቴክኖሎጂ የማላመድ፣ የእሴት ማበልጸጊያ ማዕከላትን የማቋቋምና ሌሎች የድጋፍ ሥራዎች በስፋት እየተሰሩ ነው።

የሥራ ዕድል ፈጠራ በርካታ የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብለው ከሚገመቱ መስኮች መካከል አንዱ የማዕድን ዘርፍ ነው። በአሁኑ



11

ወቅት በተለየዩ አካባቢዎች በባሕላዊ መንገድ ዘርፉን በገቢ ምንጭነት የሚጠቀሙ ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ ነው። መንግስት በቀጣይ አስር ዓመታት በዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራን በተመለከተ በ2012 በጀት ዓመት 200 ሺህ የነበረውን የሥራ ዕድል በ2022 ወደ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። ዘርፉ እውቀት መርና ዘመናዊ አሰራርን እንዲከተል ለሥራ ፈላጊ ዜጎች በማዕድንና ነዳጅ እንዲሁም የነዳጅ ተቋማት ጥናት፣ ልማትና የምር እንዲሁም የግብይት ሥራዎች ላይ የሥራ ዕድል። ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና ለባሕላዊ የዘርፉ አልሚዎች የሥነ-ምድር መረጃ ተደራሽ የማድረግና በዘርፉ ሥራዎች ዙሪያ የቴክኒክ ሥልጠናዎችን ለመስጠት ከተመረጡ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ለማዕድን ዘርፍ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆን የሰው ኃይል አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር እየሰራ ይገኛል።

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ “የዘርፉን የልማት ዕቅድ እውን ለማድረግ ተቋማዊ ግንባታ፣ ፖሊሲ መቅረጽ፣ የሰው ኃይል ስልጠና እና መረጃ ማደራጀት ላይ ጠንካራ ስራዎች ተከናውነዋል።” ብለለዋል።

የማዕድንና ፔትሮሊየም የፖሊሲዎችና የሕግ ማዕቀፎች ጥናትን መሠረት በማድረግ ተዘጋጅቷል። ዘመናዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ሥርዓት በመዘርጋት፣ የካዳስተር ሥርዓት በመተግበር፣ የፔትሮሊየም ዳታ ቤዝን በማዘመን፣ ዘመናዊ የጂኦ ሳይንስ ኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሥርዓት በመገንባት፣ የኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት አሰጣጥ በመጀመር እንዲሁም የማዕድን

ስኮር ካርድ እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት እንዲኖር በማድረግ፣ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በመገንባትና አደረጃጀቱን በማዘመን እንዲሁም የነዳጅ ጥራት መፈተሻ ላቦራቶሪ እንዲቋቋም በማድረግ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ይደረጋል።

የማዕድን ኢንቨስትመንት ሥራ ከአካባቢ ብክለት የፀዳ እንዲሆን ለማድረግ የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክቶችን ተከትሎ በመስራት፣ በሚለማው ማዕድን አካባቢ የሚገኘውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም በየክልሉ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይን ቅርንጫፍ በማቋቋም የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል። የቤተ-ሙከራ፣ የመሳሪያና ጥናት ማዕከላት በዘመናዊ መልክ ይደራጃሉ። ከከፍተኛ ትምህርትና ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በመተባበር ለዘርፉ ጥናት፣ ልማትና ዕድገት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ባለሙያዎችን የማፍራት እንዲሁም ብቁና በቂ ባለሙያዎችን በዘርፉ ማቆየት የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋ እየተሰራ ነው። የወርቅ ማጣሪያ መሣሪያና ደረጃ ማስጠበቂያ፣ የሳተላይት ምስል መቀበያና መተንተኛ፣ የጂኦ-ሳይንስ ዳታ መተንተኛና ማሰራጫ ሶፍትዌር ፕሮግራም፣ የድሮን፣ የማዕድን ኢንተለጀንስ ትግበራ፣ የማምረቻና የማበልጸጊያ ማዕከላትም ይገነባሉ።

ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሃብት በተደራጀ መልኩ ከማወቅ አኳያ ክፍተት እንደነበር በመጠጥቀስ አገራዊ ምጣኔ ሀብት ላይ የማዕድን ዘርፍ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ስለ መሆኑ ሚኒስትሩ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በአግባቡ ጥቅም ላይ ላለመዋላቸው አስፈላጊ ተቋማትን አለመገንባት፣

የፖሊሲና መመሪያ አለመኖርን እንደ ክፍተት አንስተዋል። ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ አሰራሮችና መመሪያዎችን ለመዘርጋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትም ዘርዝረዋል።

ማዕድን በሚወጣባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የማድረግ ጉዳይ በአዋጅ መመለሱን ገልጸዋል። ቀደም ሲል ኩባንያዎች ከሚያመርቱት ማዕድን የፌዴራል መንግስት አምስት በመቶ ነጻ ድርሻ ሲኖረው ክልሎች ምንም ዓይነት ድርሻ አልነበራቸውም አሁን በተዘረጋው አሰራር ግን ክልሎች ሁለት በመቶ ድርሻ እንዲኖራቸው ተደርጓል። ይህም በተደጋሚ ሲነሳ የነበረውን የተጠቃሚነት ጥያቄ በመመለስ ሐብቱን በጋራ አልምቶ ለመጠቀም ያግዛል።

መረጃን ከማደራጀት አኳያ ሊቲየም፣ ወርቅ፣ ብረትና ሌሎች የተወሰኑ ማዕድናት መገኛ ቦታዎች የሚታወቅ ቢሆንም ካለው ሀብት አኳያ በርካታ ስራዎች እንደሚጠይቁ በመጠቆም በተያዘው 2015 ዓ.ም “ኤር ቦርን ጂኦ-ፊዚክስ” የተሰኘ በንግድ አውሮፕላን የሚታገዝ ሙሉውን የኢትዮጵያን መሬት መረጃ በመሰብሰብ ማዕድን ያለባቸውን ቦታዎች የሚለይ የ200 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ተግባራዊ እንሚያደርግ ነው ሚኒስትሩ ታከለ የጠቆሙት።

የተጠቀሱትን ተግባራት በማከናወን ማዕድን በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የራሱን አሻራ የማስቀመጥ ጉልህ ሚና ይኖረዋል። በተፈጥሮ ሀብት የታደለች ብቻም ሳይሆን ሐብቷን በመጠቀም ዘላቂ ልማት በማረጋገጥ የተሻለች ኢትዮጵያን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ መስራት የሚገባበት ጊዜ አሁን ነው።



12

የኢትዮጵያ የማዕድን አይነቶች

ወርቅ በማዕድን ዘርፍ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ወርቅ እንደ ንጉስ የሚታይ ማዕድን ነው። በኢትዮጵያ የወርቅ ታሪክ ምዕት ዓመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ ይነገራል። ለዚህ በአብነት የሚጠቀሰወ የአሶሳ ወርቅ ማዕድን በዓለም ረዥም ዕድሜ ካላቸው ማዕድናት መካከል ይጠቀሳል። በአሁኑ ወቅት የወርቅ ማዕድን ስራ በለገደንቢ እና ሳካሮ አካባቢዎች በሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እየተከናወነ የሚገኘውን መጥቀስ ይቻላል።

በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ልማት ትርጉም ባለው ደረጃ ዘመናዊ የማዕድን ልማት የሚታየው በወርቅ ማዕድን ሲሆን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የገቢ ምንጭ በመሆን፣ በገንዘብ ተቋማት እንደ ሀብት መያዣያነት በመቁጠር ሲያገለግል የቆየ ቢሆንም በአገር ደረጃ እንደ አንድ ተወዳዳሪ ኢንደስትሪ ጎልቶ ከመውጣት አኳያ ብዙ ርቀት ሳይሄድ ቆይቷል።

የማዕድን ኢንቨስትመንት ከሚወስደው የፍለጋ ጊዜ አኳያ ውጤቱ በአጭር ጊዜ የሚታይ አይደለም። አንድ ኩባንያ የወርቅ ክምችት ለማግኘት በአማካኝ 10 ዓመታትን በፍለጋ ሊያጠፋይችላል። ተመሳሳይ ሌሎች ማዕድናትን ለመፈለግም በርካታ ዓመታትን ሊወስድ ይችላል። በመሆኑም በማዕድን ፍለጋ የሚባክነውን ጊዜ ለማስቀረትና በዘርፉ የሚሰማሩ ባለለሃብቶች በቀላሉ ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ለማድረግ መንግስት በአገሪቷ የሚገኙ ሃብቶችን በዘመናዊ መንገድ ለይቶ የማደራጀት ስራ እያከናወነ ይገኛል። የተቋማት ግንባታ፣ አሰራር መዘርጋትና ያለውን ሃብት በማወቅ በፍትሃዊነት ለመጠቀም እየተሰራ ነው።

ፕላቲነም ፕላቲነም ወይንም ብራማ የማይዝግ ለጌጣጌጥ እና ኢንዱስትሪ የሚያገለግል ብረት በመባል የሚታወቀው የማዕድን ዓይነት ላይ የተደረጉ ጥቂት ጥናቶች ዘርፉ አቅም እንዳለው ያመላከቱ ሲሆን፤ ያለውን ትክክለኛ ሃብት ለማወቅ ሰፊ ጥናት ማካሄድ ተገቢ ነው። በኢትዮጵያ የተላያዩ አካባቢዎችና “ማዕድኑ አለ” ተብሎ በሚገመትባቸው አካባቢዎች ጥናቱ በሰፊው ይካሄወዳል።

ኦፓል የኦፓል ማዕድን የተገኘው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን ቀመር በ1994 እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዓለም ገበያ ላይ ያለው ተጽዕኖና ተቀባይነት እያደገ መጥቷል። የኦፓል ማዕድን በኢትጵያም ወሎ አካባቢ በተለያዩ ቀለማትና ቅርጽ በብዛት እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። በተጨማሪም በአዘዞ አካካቢ ሸዋ ኦፓል በመባል የሚታወቅ የኦፓል ዓይነት መገኘቱ ይነገራል።

ኦፓል በተለያየ መንገድ ለጌጣጌጥነት ያለውን ተፈላጊነት በመጠቀም በዘርፉ የተሰማራ ኩባንያም ሆነ የጌጣጌጥ ፋብሪካ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የለም። ኢንዱስትሪው ገና ጨቅላ ደረጃ ላይ መሆኑ ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት ካሳነሱት ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል።ኢትዮጵያ ያላትን የኦፓል ማዕድን በአግባቡ መጠቀም ከቻለች ለመቶ ዓመታት በአውስትራሊያ የበላይነት ተይዞ የነበረውን የኦፓል ገበያ መቆጣጠር እንደምትችል ጥናቶች ይጠቁማሉ።

የከበረ ድንጋይ በኢትዮጵያ የከበረ ድንጋይ ማዕድን ገና በጅምር ላያ ሲሆን፤ በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ለማልማት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ ነው። የማዕድን ሐብቱ በደቡብ ክልል ሻኪሶ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። የከበረ ድንጋይ በተፈጥሮ የሚገኝና ለማጽዳት ተጨማሪ ዘይት የማያስፈልገው በመሆኑ አሰራሩን ዘመነኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በተሻለ ደረጃ ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል።

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች አንዱ የከበሩና በከፊል የከበሩ ማዕድናት የሚገኙበት ናቸው። በ2012 በጀት ዓመት 30 የነበረውን እሴት የሚጨምሩ የማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች ቁጥር በ2022 በጀት ዓመት ወደ 130፣ እንዲሁም በዚሁ ወቅት የኮንስትራክሽን ግብዓት ማኑፋክቸሪንግ ብዛት ከ1 ሺ



13

500 ወደ 6 ሺ 500፣ ለኬሚካልና ፔትሮኬሚካል ምርት የሚረዱ ማዕድናትን የሚያመርቱ የማኑፋክቸሪንግ ተቋማትን ብዛት ከ100 ወደ 1 ሺህ 100 ለማሳደግ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ግብ ተቀምጧል።

የተፈጥሮ ጋዝ በኢትዮጵያ የነዳጅ ማዕድናት ታሪክ ከምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በመጠንም በዓይነትም ይህ ነው የሚባል የተጠናከረና በጥናት ላይ የተመሰረተ መረጃ ባይቀርብም እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ1860 የነዳጅ ዘይት መገኘቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ይህንኑ የአገሪቷን ሀብት አስመልክቶ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ሲያብራሩ ኢትዮጵያ ከኦጋዴን ቤዚን ተነስቶ ስምጥ ሸለቆን፣ አባይ ቤዚን እና ጋምቤላን ይዞ የሚገኝ የተፈጥሮ ጋዝ አላት፣ ይሁን እንጂ የተፈጥሮ ጋዝ ተቆፍሮ የሚወጣ እንደ ምንጭ የሚያገለግል ሲሆን፤ ሙሉ ለሙሉ ያለው ሃብት ግን ተፈልጎ በጥናት አልታወቀም።

አንድ አገር የተፈጥሮ ጋዝ ቢኖረውም ለመነሻ የሚሆን ያለውን መጠን የሚየሳይ በጥናት የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ከሌለ ባለሃብቶች የተፈጥሮ ጋዝ አለ ስለተባለ ብቻ አይመጡም። ምን ያህል የተፈጥሮ ጋዝ አለ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን

ለመሳብና ሐብቱን ለኃይል፣ ለማዳበሪያና ለሌሎችም ለመጠቀም አዳጋች ሆኖ ቆይቷል። በመሆኑም በቁጥር ደረጃ ምን ያህል የተፈጥሮ ጋዝ እንዳለ ለማጥናት በዓለም አቀፍ ደረጃ በታወቁት የአሜሪካ ኩባንያዎች አማካኝነት በኦጋዴን ቤዚን በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ከ50 የማይበልጡ ጉድጓዶችን በመቆፈር በተደረገ ጥናት በትንሹ “7 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ፊት” መኖሩን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ለመንግስት አስረክቧል። ይህ ምስክር ወረቀት ይነሱ የነበሩ በርካታ ጥያቄዎችን በመመለስ ኩባንያዎች ፍላጎት እንዲያሳዩ ምክንያት ሆኗል እንደ ሚኒስትር ታከለ ኡማ ገለጻ።

የምስክር ወረቀቱ በተፈጥሮ ጋዝ የታወቁና ጋዙን የሚያበለጽጉ ወይንም የሚያመርቱ ኩባንያዎች እንደ ዋስትና ይጠቀሙበታል። መንግስትም አልሚዎችን በመሳብም የተፈጥሮ ጋዝን ወደ ማልማት እየሄደ ይገኛል። በቀጣይም በኦጋዴን ቤዚን እና ሌሎች የተፈጥሮ ጋዝ እንደሚገኝባቸው በሚታመኑ ቦታዎች ላይ ጥናቱ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።

የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጥሮ ጋዝን ለማዳበሪያ፣ ለኃይል እና ለፊውል እንዲሁም ጋዙን በመሸጥ ለገቢ ምንጭነት ይጠቀምበታል። ፍለጋው የተጠናቀቀውን የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ማልማት ለመግባት መንግስት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ለአብነትም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ማዳበሪያ ማምረት ይጀመራል።

መዳብ የመዳብ ማዕድን ክምችት በደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማ ክልል እንዳለ ይገመታል። መተመሳሳይ በትግራይ ክልልም እንዳለ መረጃዎች ያመላክታሉ። በዘርፉ አዳዲስ ኩባንያዎች ገብተው ቢሰሩ ኢትዮጵያን ብሎም ራሳቸውን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ከላይ ለማሳያነት የተዘረዘሩት ማዕድናት ኢትዮጵያ ከዘርፉ በስራ ዕድል፣ በውጭ ምንዛሪና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ተጠቃሚ ልትሆን እንደምትችል አመላካች ናቸው።



14

ሰላም - ለኢትዮጵያ

ዐብይ ርዕስ



15

ሰላም - ለኢትዮጵያ በሰላምነህ እውነቱ



16

ሰላም- ለኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያን ሰላምን አጥብቀው ይሻሉ። ለእርሱም ታማኝ ስለመሆናቸው ለዘመናት በቃል ሳይሆን በተግባር አረጋግጠዋል፤ እያረጋገጡም ይገኛሉ። በሃይል እየተገፉ ስለሰላም ሲሉ ይታገሳሉ፤ እየተጎዱም ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት በቻሉት መንገድ ሁሉ እጃቸውን ይዘረጋሉ። በርግጥ ስለሰላም ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ቢቆዩም ከሚያሰምሩት ቀይ መስመር የሚያልፍን ሊታገሱት አይችሉም። በደምና በአጥንታቸው ሰላማቸውን ለማሰጠበቅ ወደኋላ አይሉም። ይህን ለማድረግም የትኛውም ሃይል አያግዳቸውም። ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ድንቅ ታሪካቸው ነው። በሃይላቸው ሰላማቸውን ያረጋግጣሉ። ይህም ቢሆን ለሰላም እድል ካገኙ ወደ ኋላ የማለት ፍላጎት የላቸውም። ግማሽ መንገድ ተጉዘው ሰላምን ይፈልጋሉ፤ ለሰላም ይቆማሉ። በፌዴራል መንግስትና በህወሃት መካከል የተደረሰው ስምምነትም ለሰላም የሚሰጡትን ዋጋ ያሳያል።

በፌዴራል መንግስትና በህዋሃት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ ሰላም ወዳድ ሃይሎችን አስደስቷል። ኢትዮጵያውያን የጥይት ጩኸት የማይሰሙበት፣ ዜጎች መላ ሃይላቸውን አስተባብረው የመጨረሻ ጠላታቸው ድህነትን ለማጥፋት የሚተጉበት ወቅት እንዲመጣ የሰላም ስምምነት ፋይዳው ከፍ ያለ ነው። ለዚህም ነው ብዙዎች በደስታ ሃሴት ያደረጉት።

የዛሬ ሁለት ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ብዙ ዋጋ አስከፍሏል። ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል፤ ዜጎች ተሰደዋል፣ ለስነ ልቦና ስቃይ ተዳርገዋል። የሁለት ዓመታት ግጭት ያስከተለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮት ከባድ ነበር። የስቃይ ምሽት፣ የጨለማ መንገድ ነበር። ነገር ግን በተከሰተው ግጭት ከፍተኛ ዋጋ ቢከፈልም፤ ከሁሉም በላይ ሰላምን አስቀድሞ ቀጣዩን ማስተካከል የበለጠ ዋጋ አለው። ኢትዮጵያዊያን ይህን ወስነዋል። ከሁሉም በላይ ሰላም፣ ከሁሉም በላይ ባወጡት የህጉች ሁሉ ህግ ለ“ህገ መንግስት መገዛት” በሚል አቋማቸውን በፊርማቸው አረጋግጠዋል። ‘ችግራችንን በውይይት፣ በድርድር ፈተን ሰላማችንን አረጋግጠን በመጪው ዘመን ቀዳሚ እሴታችንን እውን እናደርጋለን’ በሚል መንገድ ጀምረዋል።

የሰላም ስምምነቱ የአገሪቷን ህገ መንግስት ያከበረና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የጠበቀ መሆኑን የተረዱ ሁሉ ደስታቸውን በተለያዩ መልኮች አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያዊያን ችግሮቻቸውና ግጭታቸው ከአንድነታቸው፣ ከተግባቦታቸው በላይ እንደማይሆን በተግባር የሚያረጋግጡበት፣ ለወዳጆቻቸው የምስራች ያሳዩበት፣ ለጠላቶቻቸው ቁርጡን ያሳወቁበት ነው። በተለይም ግጭቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እየተባባሰ በመሄድ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ በተለያዩ መንገዶች ለጣሩ አንዳንድ አገሮች “ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ታሪክ የሚሰሩ ናቸው” የሚለውን ሀሳብ በደማቅ የጻፈ ስምምነት ነው።

ከስምምነቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “ኢትዮጵያን ማፍረስ የማይታሰብ ነው” በማለት የገለጹት ሀሳብ የኢትዮጵያዊያንን ጠንካራ እሴት ያመለክታል። ኢትዮጵያዊያን ችግሮችን ሁሉ አሸንፈው በድል እንደሚወጡ ያሳያል። በአድዋ የተመዘገበው ታሪክ ለዚህ ምስክር ነው። የአሁኑ ስምምነትም የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛትን የሚያረጋግጥ፣ አንድነቷን የሚያስጠብቅ የህገ መንግስቱ ድንጋጌ የሚያረጋግጥ መሆኑን ነው አጽንኦት የተሰጠው።

የሰላም ስምምነቱ አንድምታ በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚንስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት “በመንግስት በኩል የተያዘው ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን ማክበር ነው። ኢትዮጵያ የምትጸናው ህገ መንግስቷ ላይ ስትቆም ነው። ለሁላችን የሚሆን መደላድል በጋራ የፈጠርንበት ህገ መንግስት ይዘን፣ ህግና ስርዓት የማክበር ጉዳይ ማረጋገጥ ነበር። ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይ ነበር። በዚህ ስምምነት እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ተሟልተዋል። አንድ መከላከያ እንደሚኖር፣ በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ መረጋገጥ እዳለበት ተማምነናል” ያሉት ሀሳብ የኢትዮጵያዊያንን አቋም በግልጽ ያመለከተና እውነታውን ያሳየ ነው።

በአንድ አገር ውስጥ አንድ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነ ህገ መንግስት ይኖራል፤ የህገ መንግስት ስርዓቱ በእርሱ ይመራል። ይህ ደግሞ ለአንድ አገር ሰላምና ደህንነት እውን መሆን፣ ለመረጋጋት እና ለህዝቦች ልዕልና ከፍተኛ ድርሻ አለው። ይህን የሚያስከብር ስምምነት መፈጸሙ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ክስተት ሆኗል። በተለያየ መልኩ አገሪቷን ሊደፍሩ ለሚሞክሩ ሃይሎችም የማስጠንቀቂያ ደወል ነው።

ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጉዳዮች መጋጨታቸው ያልተለመደ አይደለም። የታሪክ ድርሳናት ሲፈተሹ የሚያረጋግጡት ምንም ያህል ቢጋጩም ችግሮቻቸው ፈትተው አድነታቸውን አስጠብቀው ወደፊት መጓዛቸው የስኬታቸው ምስጢር መሆኑን ነው።

ኢትዮጵያዊያን የውስጥ ጉዳያቸውን በራሳቸው እየፈቱ የውጭ ወራሪ ሃይሎችን ድል እየነሱ መጥተዋል። ይህ ታሪካቸው አሁንም እየደመቀ የሚሄድ የታላቅ ገድል አካል ነው። በአድዋ ድል የተበሰረው በኢትዮጵያዊያን መካከል የውስጥ ችግሮች ሳይኖሯቸው ቀርቶ ሳይሆን ያጋጠማቸውን ተግዳሮት ሁሉ በራሳቸው መንገድ መፍታት በመቻላቸውና ለፓን አፍሪካ አስተሳሰብ በመገዛታቸው ነው።

በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ እንዳለ ንጉሴ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እንደሚሉት፤ ኢትዮጵያዊያን ለሉዓላዊነታቸው ቀናዒ ናቸው። በሉዓላዊነታቸው አይደራደሩም። በሌላው አገር ጉዳይም ጣልቃ አይገቡም። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ስትሰራ ያጋጠሙ ወሳኝ የሆኑ ችግሮች አሉ። እነዚህን ችግሮችን ፈታለች። በድልም ተወጥታለች። አሁን የሆነውም ይሄው ነው።

በዘመናት ውስጥ ኢትዮጵያዊያን በደም ባጥንታቸው ራሷን ከፍ የማድረግ ስራ አከናውነዋል። የግዛት አንድነታቸውንና ሉዓላዊነታቸውን ጠብቀዋል። የውስጥ ችግሮቻቸውን ፈተው ወደ ሰላም በመምጣት ትልቁን ምስል የማየት እሴታቸውን ይጠቀሙበታል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በግጭቱ ሳቢያ ያልተጎዳ ክፍል የለም። ዜጎች ተሰደዋል፣ ሞተዋል፣ ቆስለዋል፤ ንብረት ወድሟል፤ ሀብት ከስሯል። ይህም ቢሆን ዛሬ ላይ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዚህ ጉዳይ “የአሸነፈ የተሸነፈ የሚል የለውም። የተጎዳችው ኢትዮጵያችን ነች። የተጎዳነው ሁላችንም ነበርን። ለሁላችን ጥቅም የጋራ ኢትዮጵያችንን ከፍ የሚያደርግ ሀሳብ ያለው ነው” በማለት ስምምነቱ የኢትዮጵያን ከፍታ እንደሚያመጣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ያነሱትን ሀሳብ እዚህ ላይ መጥቀሱ ተገቢ ነው።

የሰላም ውይይቱ በስኬት በመጠናቀቁ “ያሸነፈችው



17

ምክክር - ሰላምን ፍለጋ መንደርደሪያ

ኢትዮጵያ ባለፉት መቶ ዓመታት ውስጥ ከጦርነትና ጦርነት ስጋት ወጥታ የምታውቅባቸው ዓመታት ሁለት ደርዘን አይሞሉም። በተለይ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ፣ ረሃብና ስደት እጅግ የከፋና አገሪቷን ለበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የጎተተ ነው።

አገሪቷ በየአስር ዓመቱ እየተፈራረቀ የሚመጣው ድርቅና የሚያስከትለው የሰው ህይወት ማለፍ፣ የከብቶች መሞት አጠቃላይ ሕዝቡን ለከፋ ችግር ዳርገውታል። ከዚያም አልፎ ወልደው ከብደው ከኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል፤ ወደ ውጭ አገር ተሰደዋል። ይህን ሲያልፉት ሌላ ዙር ይጠብቃቸዋል። በዚህም ሕዝቦቿ ከስቃይ ወደ ስቃይ እየተሸጋገሩ ነገን በተስፋ እየጠበቁ እያለ የጦርነት ነጋሪት ይጎሰማል። እናም በጦርነት ውስጥ እንዲያልፉ ይገደዳሉ።

በኢትዮጵያ ምድር ከውጭ ወራሪ ጋር ጦርነት ተካሂዷል፤ በእርስ በርስ ግጭት ብዙዎች ወድቀዋል። በውጤቱ አገርና ህዝብ ተጎድቷል። ዜጎች ተፈናቅለዋል። ህጻናት ያለወላጅ ቀርተዋል። ወጣቶች ህልማቸው ተጨናግፏል። አዛውንቶች ጥረው ግረው ያፈሩትን ሀብት አጥተው፤ በወጣትነታቸው ዘመን ያገለገሏት አገራቸውን በስተርጅና ውለታቸውን ከመመለስ ይልቅ በስቃይ ውስጥ እንዲያልፉ ተገደዋል።

ኢትዮጵያውያን ድህነትን የሚያክል ታላቅ ጠላታቸውን ላይ አተኩረው እንዳይንቀሳቀሱ በጦርነትና በሽብር ናፋቂዎች እግር ከወርች ታስረዋል። ብልጽግና ላይ ትኩረት አድርገው እንዳይሰሩ በመኖርና ባለመኖር ሃሳብ እንዲናጡ ጠላቶቻቸው እየሰሩባቸው ይገኛል። ሰላምና ደህንነታችን እውን መሆኛው ጊዜ መጣ ሲባል ድንገት የሚያከስም የጦርነት ሰቆቃ ይሰማል። ለምን? እንዴትስ ይህ ሊሆን ቻለ? ዘላቂ መፍትሄውስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሹ ናቸው።

ሰላም “በአገራችን ሰው ሞተ ይባላል። በምን? ስንል በዘር በሃይማኖት፣ በማንነት ይባላል። ሰው ፈልጎ ባልተፈጠረበት ሃይማኖት፣ ዘር እና ማንነት ምክንያት የግድያ ሰለባ መሆን የለበትም። ስለዚህ ትልልቅ ሰዎች ሰውን በዘር፣ በሃይማኖት፣ በማንነት አትግደሉ፤ እባካችሁ፤ እባካችሁ።” የሚል ንግግር የሰማሁት ምናልባት አስር ዓመት ከሚሆነው ሕጻን አንደበት ነው። የሕጻኑ ሀሳብ የሰው ልብ በሁለት ነገሮች እንዲከፈል ያደርጋል። ሕጻኑ ሀሳቡን የገለጸበት መንገድ ብስለቱን ያሳያል። አሁን በአገር መንግስት ግንባታ ላይ እየተሳተፈ ላለው ትውልድ ግን ያነሳው ጥያቄ ቀለል ተደርጎ የሚታይ አይደለም።

የሕጻኑ ሀሳብ በአንድ በኩል የአገራችን ሰላምና ደህንነት ማጣት ጥልቀቱ ምን ያህል እየዘለቀ መምጣቱን ያሳያል።

ኢትዮጵያ” በማለት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀሳቡን ያጠናክሩታል። የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ድል መሆኑን ያረጋግጣል።

ለዚህም ነው የሰላም ስምምነቱን ከተበሰረ በኋላ ብዙዎች ደስታቸውን የገለጹት፤ ለተፈጻሚነቱም የበኩላቸውን ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ያስታወቁት። የጉዳዩ ባለቤቶች ኢትዮጵያዊያን የሰላም ስምምነቱን “የምስራች ድምጽ” ብለውታል።

የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያበስራል። የፓን አፍሪካ መርህ የተከተለች አገር መሆኗን በተግባር ያረጋገጠችበት መንገድ ነው። በተለይ ለቅኝ ግዛት ሀሳብ የማትበገር መሆኗን በኒዎ ኮሎኒያሊዝም አስተሳሰብ ለተተበተቡት ምዕራባዊያን በትክክለኛው ሰዓት ትክክለኛውን መልዕክት አስተላልፋለች።

“የራሴን ፕሮጀክት በራሴ እሰራለሁ ብላ ኒዮኮሎኒያሊዝም እንደሚሸነፍ ፍንጭ ያሳየችበት ነው። የአፍሪካ ችግር በአፍሪካዊያን መፈታት እንዳለበት በተግባር ያሳየችበት ታላቅ ፕሮጀክት ነው።” በማለት ነው መምህር እንዳለ የገለጹት። ኢትዮጵያ አፍሪካዊያን የራሳቸውን ችግር ለመፍታት “ብቃትም፣ ፍላጎቱም አላቸው” የሚለውን እምነቷን ያንጸባረቀችበትና ዳግም ትክክለኛ ተግባር የፈጸመችበት ጉዳይ ነው።

እንደመምህር እንዳለ ገለጻ፤ በዓለም ላይ ምዕራባዊያን ፈተነዋል የሚሉትና በምሳሌነት ሊጠቅሱት የሚችሉት መፍትሄ ያገኘ ግጭት የለም።

ስምምነቱ በራሱ ጊዜ ተግባራዊ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊያን ሙሉ ለሙሉ ሰላም ፈጥረው ወደ ልማት ፊታቸውን ለማዞር የሚችሉበት ጊዜ ቅርብ ነው። በድህነት ባርነት ውስጥ እየኖሩና የሌሎችን ድጋፍ እየጠበቁ ሰላማቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ያረጋገጣሉ ማለት ዘበት ነው። ስለሆነም ይህን አሁን የተደረገውን የሰላም ስምምነት በአግባቡ በመጠቀም መላ ሃይልን ወደ ልማት ማዞር ግድ ይላል።

በአገሪቷ ላይ የተንሰራፋው የሰላም እጦት ከሁለትና ሶስት ትውልድ አልፎ በጣም ለጋ አእምሮ ባላቸው ሕጻናት ላይ እያሳደረ ያለው ጫና ከፍተኛ መሆኑንም ያንጸባርቃል፤ በትውልድ መካከል የጥላቻና ፍርሃት ዘር እየተዘራ መሆኑንም ያመላክታል። ሕጻኑ እያወጋን ያለው ጉዳይ የችግሩን ስፋት ብቻ ሳይሆን አሁን ያለውና መጪው ትውልድ የሚገነባበት ስነ ልቦና አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለዚሀ ከወዲሁ ጥንቃቄ ወስደን በልዩነት ውስጥ ብዝሃነት ውበት መሆኑን የማስረጽ አስፈላጊነትን አጽንኦት የሚሰጠን ነጥብ መምዘዝ እንችላለን።

በሌላ በኩል ግን የሕጻኑ ንግግር አዲስ ተስፋን ያመላክታል። በዘር፣ በሃይማኖትና ማንነት መከፋፈል ላይ ያልተመሰረተ ትውልድ በመገንባት በኩል እጆቻችንን ዘርግተን በጥንካሬ ብንሰራ ተስፋ መኖሩን ያሳያል። በዘር፣ በሃይማኖትና በማንነት መገዳደል እርባና ቢስና ዘመኑን የማይዋጅ ድርጊት መሆኑን ከህጻንነታቸው እየተገነዘቡ የመጡ የ21ኛ ክፍለ ዘመን እንቦቀቅላዎች መኖራቸው ተስፋ ያጭራል። በአንድ ወቅት ለአርቲስቶች ሽልማት በሰጡበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ሲናገሩ “ዕድሜያቸው ከአስር ዓመት በታች የሆነ ትውልድ ‘ኢትዮጵያ’ እያሉ ናቸው” ያሉትን ሀሳብ ያጸናል።

የአሁኑ አካሄዳችንና አሰራራችን የዚህን ዘመን ትውልድ ስብዕና ለመቅረጽና አቅጣጫውን ለመወሰን የሚያስችል መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው። ህጻኑ ስጋቱን አሳየን። “ትላልቅ ሰዎች እባካችሁ አትግደሉ” ሲል በተማጽንኦው ውስጥ ተስፋውን አሳይቶናል። ለሰላም ያለውን ናፍቆት ገልጾልናል። ከሁሉም በላይ ሰው እንደሚበልጥ፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እንደሚገዝፍ በድምጹ ውስጥ አሳውቆናል።

አዲሱ ትውልድ መጪውን ዘመን ለመለወጥ የሚያስችለው አቅም ለመገንባት ለእነርሱ የምናስተምራቸው “ሰላም ያስፈልጋል፤ ስለሰላም ኑሩ” የሚል ብቻ ሳይሆን ለዚህ ችግር የዳረገንን መሰረታዊ እውነት በማስተማር ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመናት ያለፈችባቸው መንገዶች ዳገት ቁልቁለት የበዛባቸው፣ ጭንቅና መከራ ያልተለያቸው ናቸው። የአንድ ክፍለዘመን ታሪክን እንኳን ብንመለከት የሚያረጋግጥልን ይሄው ነው። አገራችን በ1888 ዓ.ም በአድዋ፣ በ1928 ዓ.ም ማይጨው፣ በ1970 ዓ.ም ጅግጅጋ፣ በ1990 ዓ.ም ባድመ ላይ ጦርነቶችን አካሂዳለች። በእነዚህ ጦርነቶች በጀግንነት ድል ብታስመዘግብም ውድ ልጆቿን ገብራለች፤ ለጥሪት ሊሆናት የሚችለውን ሀብቷን አጥታለች። ዜጎች ከጦርነት በኋላ በሚከሰት የስነ ልቦና መቃወስ አሉታዊ ጫና ውስጥ እንዲገቡ ተገደዋል።

በእነዚህ መካከልም በ1953 ዓ.ም ተሞክሮ የከሸፈው መፈንቅ ለመንግስት፣ በ1966 ዓ.ም የተካሄደው የመፈንቅ ለመንግስት እና ያስከተለው አብዮት የአገሪቷን መሰረታዊ የታሪክ አቅጣጫ ያሰቀየረና ዛሬ ለተደረሰበት አዎንታዊም



18

ሆነ አሉታዊ ገጽታዎቸ መሰረት የጣለ ነበር። ከዚህ በኋላ የተከሰተው የ1981 ዓ.ም የመፈንቅ ለመንግስት ሙከራ መክሸፍ በአገሪቷ ላይ ያስከተለው የሃይል ሚዛን መዛባት ተጠቃሽ ነው። በርካታ ጄኔራሎችን አጥታለች።

የ1983 ዓ.ም የለውጥ ሂደት ለአገሪቷ መጻኢ ዕድል መልካም አጋጣሚዎችን ይዞ መጥቶ ነበር። በወቅቱ ኢህአዴግ በመሰረተው የሽግግር መንግስት፣ ህገ መንግስት ሲጸድቅ “የህዝቦችን ስሜት አርግቦ አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ፣ ብዝሃነትንና ልዩነትን አጣጥመው ለመሄድ የሚያስችሉ ስራዎች ይከናወናሉ” የሚል ተስፋ ተሰንቆ ነበር። ሆኖም ኢህአዴግ በሥልጣን ዘመኑ እነዚህን እድሎች በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ በሂደት የዴሞክራሲ ሥርዓትን ገፎ፣ መልካም አስተዳደርን አጥፍቶና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አስፋፍቶ ቆይቷል። በእነዚህ የስልጣን ዓመታት የተለያዩ ትርክቶችን በማስፋፋት አገሪቷን ወደ ገደል አፋፍ ላይ አደረሰ፤ የህዝቦችን አንድነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አደረገ። በተለይ ዜጎች እርስ በርሳቸው እንዳይደጋገፉ በተደራጀና በተጠና መንገድ የሀሰት ትርክቶች ተፈጥረው በተለያዩ መንገዶች ተሰራጭተዋል፤ እየተሰራጩም ናቸው።

በየጊዜው የተፈጠሩ ትርክቶች ተዋደውና ተፋቅረው ሲኖሩ የቆዩትን የአገራችንን ህዝቦች ሰላምና ደህንነት አሳጥቷል። ትናንት የተፈጠሩት ትርክቶች በህዝቦች አንድነት ላይ አደጋ የደቀኑ ናቸው። ዛሬ እኛ የምንገነባው እውነት የህዝቦችን ሰላም የሚያረጋግጥ፣ አንድነትን የሚመልስና ለነገዎቹ ተስፋ የሚሰጥ መሆን አለበት። ለዚህ ደግሞ ለሰላምና ደህንነታችን እጦት መንስኤ የሆነው “ምንድን ነው?” የሚለውን መፈተሽ ይገባል። መሰረቶቹ በርካታ ቢሆኑም ጎልተው የሚታዩ ችግሮችን

ለይቶ መመልከት ያስፈልጋል። ግን ሰላም የምንለው ሀሳብ ምን ያመላክተናል? የጋራ መሰረታዊ ግብዓት አለን ወይ? ለሚለው ጥያቄ ቅድሚያ እንስጠው።

“ሰላም” ስንል በርካታ ትርጓሜዎች ይሰጠዋል። አንዱና በቀላሉ የሚታየው “ከሁከት ነጻ መሆን፤ መረጋጋት” የሚለው ነው። ሌሎቹ በሰዎች የዕለት ተዕለት ግንኙነት መካከል የተረጋጋ መስተጋብር መኖር፣ የተለያዩ ማህበረሰባዊ መዋቅሮች ያለምንም እንከን መስራት፣ ልዩነትን ተረድቶና አድንቆ ያለምንም ሁከት ተረጋግቶ መኖር፣ የመከባበር ባህል የዳበረበት፣ እርስ በርስ እውቅና ተሰጣጥቶ አንዱ ለሌላው መኖር የበኩሉን የሚያደርግበት፣ በስምምነትና በመተባበር አብሮ በመኖር የሚፈጠረው ጥልቅ ግንኙነት ሳይታወክና ሳይረበሽ በሰላም መኖርን ያመላክታል።

ሰላም ከጎረቤትም ሆነ ከሌሎች ጋር ጦርነት ያለመክፈትን ወይም ጦርነት አቁሞ በጸጥታ መኖርን ያሳያል። በአጠቃላይ ማህበረሰባዊ እሴቶች፣ ተግባቦቶች፣ መዋቅራዊ አደረጃጀቶች የማያናጉ አነስተኛ ግጭቶች ቢኖሩም ከአጠቃላይ የሰላም መደፍረስ ጋር ሊታዩ አይችሉም።

አሁን በአገራችን የሚስተዋለው የሰላም አጦት አጠቃላይ ማህበረሰባዊ መዋቅሩን እያናጋ የመምጣት ሁኔታ ይታይበታል። ተባብረውና ተሳስበው የኖሩትን ህዝቦች ቅራኔ ውስጥ የከተተ፣ የሃይማኖት ልዩነት ቢኖራቸውም ተፋቅረው የኖሩ ህዝቦችን የረበሸ፣ አንዱ ሌላውን ከመጠበቅና ከመንከባከብ ይልቅ ማሳደድን ሲመርጥ ተስተውሏል። ይህ መሰረታዊ የሰላም ማጣት ለምን ተከሰተ?

በአገራችን የተከሰተው የሰላምና ደህንንት እጦት መሰረቱ አሁን አይደለም። ለዘመናት ተከማችቶ የቆየ መሰረታዊ ችግር ያለበት ጉዳይ ነው። ዛሬ ላይ ውጤቱ እጅግ ገዝፎና ከብዶ ቢታይም ዘሩ የተዘራበት ዘመን ሩቅ ነበር። በ1983 ዓ.ም የመጣው ለውጥ ችግሩን ከመፍታትና ወደ ዘላቂ መፍትሄ ከመውሰድ ይልቅ መዋቅራዊ በሆነ መንገድ ልዩነቱን አራግቦታል። ዛሬ ትናንት የተዘራውንና ሆን ተብሎ እንዲያድግ የተደረገውን የጥፋት ፍሬ “እየተቋደስን” መሆኑን ያመላክታል።

ሰላምና ጸጥታ ሲነሳ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው። አንደኛው ማንኛውም ግጭት፣ ማንኛውም ጠብ ከህብረተሰቡ የሚወጡ መነሻቸው መዋቅራዊ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልጹት እውነት ነው።

በየትኛውም አካባቢ ለግጭቶች መነሻ ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ህብረተሰቡን ሊገፋፉና ወደ ግጭት ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች በአግባቡ እየታዩ፣ እየተፈተሹና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቅድሚያ በመስጠት መፍትሄ ካልተፈለገ ለሰላም እጦት እንደዋነኛ መሳሪ መሆናቸው እውነት ነው።

የዘርፉ ባለሙያዎቸ እንደሚተነትኑት፤ ሁለተኛው መሰረታዊ ጉዳይ የግጭት መንስኤ፣ የሰላም እጦት አባባሽ ጉዳዮች ሊከሰቱ ይችላሉ። ዋናው ችግር ካለ ቀላል የሚመስሉ ነገሮች ሁሉ በርካታ አደጋዎች ማስከተል የሚችሉ ናቸው።

ዛሬ በአገራችን ማንኛውም ጉዳይ ለጸብ መነሻ ምክንያት ሆኖ ሰዎች ለህልፈተ ህይወት ይዳረጋሉ። ንብረቶች



19

ይወድማሉ። በአገራችን ለዓመታት መፍትሄ ሳይሰጣቸው የቆዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ላይ ሌላ ሸክም በመጨመር እየገዘፈ መምጣቱን ማስተዋል ይቻላል። ሰላምን እያቃወሰ፣ ማህበረሰባዊ መዋቅርን እያናጋ የመጣው ፈታኝ ሁኔታን በጥንካሬ መታገል ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ከሆነ ሰንብቷል።

ዛሬ ሁላችንም ሰላምን በየመንገዳችን እንፈልጋለን። ግን ሰላም ተናግቷል። ለምን?

የትርክት አባዜ አገራችን በተለይ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት የመጣችባቸው መንገዶች እጅግ እንቅፋት የተሞሉባቸው ናቸው። በጦርነት፣ በረሃብ፣ በስደት የተጋለጠችባቸው መሆኑን ድርሳናት ያሳዩናል። በዚህ ዘመን ውስጥ የከፋውና አገራችንን ወደ ቁልቁለት ጉዞ እየወሰዳት ያለው ጉዳይ ግን ጽንፈኝነትና አክራሪነት ናቸው። ለእነዚህ መነሻቸው “የእኔ ብቻ ትክክል ነው፤ እኔ ብቻ ትልቅ ነኝ” ከሚል አስተምሮ የሚመነጭ መሆኑን ማጤን ይቻላል። የዚህ ዓይነቱ አመለካከት ደግሞ ማህበረሰቡ ለዘመናት በጋራ ይዞት የቆያቸውን መልካም እሴቶች የሚያስጥልና “እኔ ብቻ” በሚል ሌላውን የሚያሳንስ፤ አልፎም የሚያጠፋ ትርክት እየተፈጠረ በመዘራቱ ነው።

ማህበረሰቡ በሃይማኖት፣ በማንነት፣ በብሄር የነበረውን አመለካከት በመቀየር የመጠፋፋት ስብዕና እያላበሰ እንዲመጣ በውስጥም በውጭም ሃይሎች ለዓመታት ተሰርቷል፤ እየተሰራ ነው። ይህ ታሪክን የሚያጠፋ ታላቅ ሴራ ነው።

ለዚህ ደግሞ ለዓመታት እየተፈጠረ የተዘራው ትርክት

ማጤን ግድ ይላል። በአስደናቂ መልኩ በጋራ ክንድ በተመዘገቡ ታሪኮች እንኳን መግባባት እስከሚሳነን ድረስ በትርክት እርስ በርስ እንድንጋጭና በጠላትነት እንድንተያይ እየሆነ መምጣቱን ማስተዋል ይቻላል።

ለምንድን ይህ ሆነ? ብለን ስንጠይቅ እ.ኤ.አ. በ1975 በስደት ወደ ፈረንሳይ የሄደው ደራሲ ሚላን ኩንደር ያለው ሀሳብ መልስ ሆኖ ይገኛል። ደራሲ ሚላን እንደሚገልጽልን፤ አንድን ህዝብ ለማጥፋት ከታሰበ የማስታወስ ችሎታውን ማጥፋት ይገባል።

የህዝቡን “መጽሃፎቹን፣ ባህሉን፣ ታሪኩን ማጥፋት። ከዚያም አንድ ሰው አዲስ መጽሐፍ እንዲጽፍ፣ አዲስ ባህል እንዲሠራ፣ አዲስ ታሪክ እንዲፈጥር ማድረግ። ብዙም ሳይቆይ ያ ሕዝብ ምን እንደሆነና ምን እንደነበረ መርሳት ይጀምራል” (Destroy its books, its cul- ture, its history. Then have somebody write new books, manufacture a new culture, invent a new history. Before long that nation will be- gin to forget what it is and what it was...) በማለት የገለጸው በአገራችን ላይ በተለይ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት መፈጸሙን ማስታወስ ይቻላል።

መጽሓፎችን ማጥፋት ባይችሉ የማያነብ ትውልድ በመፍጠር ታሪኩን እንዳይረዳና ለትርክት እንዲጋለጥ ተደርጓል። የተማረውም ኢትዮጵያ ታላቅ ታሪክ ያላት አገር መሆኗን ለማወቅ ከመሻት ይልቅ የአውሮፓና የአሜሪካንን ጠንቅቆ እንዲያውቅና እነርሱን እንዲናፍቅ ነው የተደረገው። እርስ በርሱ እንዳይተማመን የሚያደርግ ስራም ተሰርቷል። ለዘመናት የገነባነውንና የሰራነውን የጋራ ታሪክ ረስተን፣ አንድነታችንን አጥተን፣ አብረን

ኖረን ዛሬ የማንተዋወቅ ዓይነት እስከመሆን እንድንደርስ የሚያደርግ የልዩነት ዘር ተዘርቷል።

“ሕዘብን የሚያስተሳስረው ታሪክ ነው። ታሪክ የሌለው ህዝብ አንድነቱን ያጣል” የሚለውን የታሪክ ፕሮፌሰር ኖሃ ሃራሬ ሃሳብ ከሚላን ኩድር ሀሳብ ጋር አሰናስነን ከተመለከትነው ኢትዮጵያ የምትባለው የረጅም ዘመናት ባለታሪክና ታላቅ አገር ለማጥፋት ታሪኳን የማያውቅ ትውልድ እንዲያድግና ለተሸረበ ሴራ ሰለባ እንዲሆን መደረጉን መገንዘበ አያቅትም።

በታሪካችን ውሰጥ የስህተት ትርክት ለምንድን እንዲገባ ተፈለገ? የሚለው ሀሳብ ብዙዎችን የሚያወያይ ጉዳይ ነው። የታሪክ ምሁሩ ታዬ ቦጋለ “መራራ እውነት” በሚለው መጽሓፋቸው “በታሪክ ዙሪያ ከ1970ዎቹ ጀምረው የተዘጋጁ ሰነዶች በሴራ ፖለቲካ እግር ተወርች ተቀፍድደዋል። ከታሪክ አልፋና ኦሜጋ ርቀዋል። ከመዳረሻ ግቡ በአያሌው አፈንግጠዋል” በማለት የኢትዮጵያ ታሪክ በሴራ ፖለቲካ እጅ ውስጥ መውደቁን ያረጋግጣሉ። ለዚህም ነው ትርክት እየበዛ የመጣው። ግን ትርክት በራሱ ምንድን ነው? በታሪክና በትርክት መካከል ምንድን ልዩነት አለው? የሚሉ ነገሮችን ማየት “ውሃን ከምንጩ፤ ነገርን ከስሩ” እንዲሉ ይሆናል።

ታሪክ በዘመናት፣ በዓመታት ውስጥ የተፈጸሙ ነገሮችን በሰነድ፣ በማስረጃ አስደግፎ የሚቀርብ እውነታን የሚገልጽ ነው። በተለያዩ አካዳማዊ መስፈርቶች ሲመዘን እውነትነቱና ተጨባጭነቱ የሚረጋገጥ ነው። ተጨማሪ ማስረጃዎች በማግኘት የሚዳብር፣ ትውልድ ያለፉ ጉዳዮችን እንዲያጠና ለማስቻል የሚረዳ አቅም አለው። ትውልድ ከትናንት ታሪኩ የሚጠቅመውን በመውሰድ፣ ስህተቱን በማረም አዲስ ታሪክ በመስራት በወርቅ ቀለም ለማጻፍ የሚጥርበት ነው።

ትርክት ግን ይለያል። አንድ ፍላጎት ባለውና ግብ ባስቀመጠ ቡድን ወይም ግለሰብ የሚዘጋጅ ልቦለዳዊ ነው። በማስረጃ ማስደገፍ አይቻልም። በፈጠራና በስሜት የተሞላ ነው። አንዳንዴ የግለሰቦችን ስብዕና መሰረት አድርጎ ለማግዘፍ፣ ለማንቋሸሽ፣ የሚተረክ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴ የቡድን ፍላጎትን ለመጫን፣ እንደሂትለር “ልዩ ዘር ነን” ብሎ ለመስበክና ለማረጋገጥ የሚፈጠር፣ ማስረጃ የማይገኝለት ልብ ወለዳዊ ጉዳይ መሆኑን ሰነዶች ያረጋግጣሉ።

ትርክት ከስሜት ጋር ተቀላቅሎ ስለሚነገር ሰዎችን በቀላሉ ይማርካል። በሃሳቡ ተጽእኖ ለመፈጠር ያስችላል። ሰዎች በምናባቸው ለፈጠሩትና በሌሎች ሰዎች አእምሮ ላይ በሳሉት ምስል እውነታን በማጥፋት “አዲስ ታሪክ” ሆኖ ይተረካል። የዚህ ዓይነቱ አካሄድ ነው ኢትዮጵያን የገጠማት።

በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ጥላቻ፣ ቂም በቀል፣ መከፋፈል የሚያሰርጽ ትርክት ተተክሏል። ትርክቱ ወንድማማቾችንና እህትማማቾችን “አንተ ትብስ” የሚለውን እሴታቸውን አጥፍቶ ቂምና ጥላቻን ዘርቷል። ይህ ደግሞ ለአገር ፋይዳ የለውም።

“አዲሱ ትውልድ መጪውን ዘመን ለመለወጥ የሚያስችለው አቅም ለመገንባት ለእነርሱ የምናስተምራቸው “ሰላም ያስፈልጋል፤ ስለሰላም ኑሩ” የሚል ብቻ ሳይሆን ለዚህ ችግር የዳረገንን መሰረታዊ እውነት በማስተማር ነው። ”



20

ለአንድ ቡድን ወይም ቡድኖች ፍላጎት ማስጠበቂያ ሲባል የተዘራው ትርክት የዛሬ የታሪክ ስብራት ሆኖ እየተስተዋለ ነው። ባለፉት ዓመታት በተለያየ መንገድ ተሰንደው ሲሰራጩ የቆዩት ትርክቶች ዛሬ ላይ ለዜጎች ህልፈት መንስኤ እየሆኑ ናቸው። ጠንካራ አንድነት እንዲኖረን ከማረግ ይልቅ ልዩነት እንዲሰፋ መንገድ ከፍተዋል።

በ21ኛው ክፍለ ዘመን በፈጠራ ሙያ ራሳቸውን አብቅተው ስማቸውንና አገራቸውን ማስጠራት የሚጠበቅባቸው ወጣቶች በሃሰተኛ ትርክቶች ሳቢያ ለንትርክ፣ ለጸብ፣ ለሁከትና ለግጭት ከመዳረግ አልፈው የሰዎችን በሰላም መኖር መብት በመግፈፍ አንዱ ሊላውን ማሳደድ ጀምሯል። በአንድነት፣ ተፈቃቅሮ፣ አብሮ የኖረን ህዝብ ተያይቶ እንደማይተዋወቅ የማድረግ ስራዎች ተከናውነዋል፤ እየተከናወኑ ናቸው። በዚህም ዜጎች ተሰቃይተዋል፤ ከኖሩበት ቀዬ በግፍ ተፈናቅለዋል፤ ተሰደዋል። ሕጻናትና አረጋዊያን ተበትነዋል። በአጠቃላይ በስህተት ትርክት፣ አንዱ ሌላውን አክብሮ መቀበል ባለመቻል አገራችን ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች።

ስለዚህ ምን ይደረግ ጥያቄ ሆኖ ይገዝፋል። እነዚህን ትርክቶች እንዴት ይነቀሉ? ትርክቶቹን ለመንቀል የጋራ መግባባትስ አያስፈልገንም? የችግሮቻችን ምንጭ ለማጥፋት ምንድን ማድረግ እንችላለን?

የፈታኙን ምዕራፍ ማለፊያ መንገዶች

በአገራችን ፈታኝ ምዕራፎች ከፊታችን ተደቅነዋል። በህዝቦቻችን መካከል የቆየውን መልካምና ጠንካራ እሴት መልሶ ለማምጣትና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመቀጠል መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች በርካታ ናቸው። አሁን ያለንበት ዘመን እጅግ አሳሳቢ ቢሆንም “ኢትዮጵያ ጠላቶቿ እንደሚመኙት ሳይሆን እያሸነፈች ትመጣለች” የሚለውን ለማጽናትና በአስተማማኝነት ለማሸነፍ ዛሬ የሚከናወኑ ተግባራት ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው።

ትርክትን ማስተካከል “ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር በታሪክ ላይ የተፈጠረውን ተቃርኖ ማረቅ ያስፈልጋል” በማለት የታሪክ ኤምሬተስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ የገለጹት ሀሳብ ሚዛን የሚደፋና በትርክት ብዛት የተሰበረውን ታሪክ መጠገኛ መንገዱን ያሳየ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ታሪክ መጻፍ ከተጀመረ ስድሳ ዓመታትን ያሰቆጠረ ቢሆንም የትርክትን ያህል ተጽእኖ መፈጠር ተስኖታል። በእውነትና በማስረጃ ላይ መሰረት ያደረገ ታሪክ በተለያየ መልኩ እየተስፋፋ የመጣውን ትርክት ለመቀነሰ አቅም እንዳጠረው ብዙዎች ይናገራሉ።

የኢትዮጵያን ትክክለኛ ታሪክ ለመገንዘብ በእውነትና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ሰነዶችን ማግኘት አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም። እስከ ዛሬ ያለው ታሪክን እያጠፉና በተለያዩ ቡድኖች ፍላጎት ላይ መሰረት ያደረጉ ትርክቶች

ትውልድ በተገቢው መንገድ አገሪቷን እንዳያውቅ አድርጎታል።

በአሁኑ ወቅት ብዙዎች የሚስማሙበት ነጥብ “በኢትዮጵያ የተንሰራፋው ትርክት” መፍትሄ ማግኘት አለበት። ለዓመታት የተዘራውን የመከፋፈል፣ የቂምና የጥላቻ ትርክትን በአዲስ እውነተኛ የመቀየር፣ የተዛባን የታሪክ አረዳድ የማስተካከል ተግባር የሁሉም የቤት ስራ ሆኗል። በተለይ ጸሀፊያንና የታሪክ ተመራማሪዎች የዝሆኑን ያህል የገዘፈ ሃላፊነት አለባቸው። የመገናኛ ብዙሃን እውነቱን እየፈተሹና እያቀረቡ፣ ሀሰቱን በማስረጃ እያጋለጡ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ሰላም በጠፋና ጭንቅ በመጣ ቁጥር ሕጻናት “ሰው ለምን ይገደላል?” በማለት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ትርክት ላይ መሰረት ያደረገ ምላሽ በመስጠት የጥፋት መሳሪያዎች አድርገን ማሳደግ አይገባንም።

በመሰረቱ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በትርክትና በታሪክ አረዳድ መንስኤነት ለጭቅጭቅና ጥፋት መጋበዝ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ማህበረሰቡ በየእለት ጉዳዩ ሊተገብራቸው የሚገቡ ማህበረሰባዊ ለውጦችን የሚያፋጥኑ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩትም እዚህ ላይ መከፋፈል ለጠላት ሴራ ራስን አሳልፎ መስጠት መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። በዚህ ሁኔታ ምን ያህል እርቀት ይኬዳል? የሚለው ምላሽ ይፈልጋል።

ለዘመናት እየተሰናሰነ የተነገረ ታሪክ በአንድ ጀንበር ወይም በዘመቻ የሚጠፋ ጉዳይ አይደለም። መጸሀፍት ተጽፈው፣ ተራኪ ተዘጋጅቶና አዳዲስ ነገሮች ተፈጥሮ የተተረከን፣ በትውልዱ አእምሮ ውስጥ ዘልቆ የገባን ጉዳይ በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻልም፤ በአዲስ ታሪክም በመቀየር ውጤት ማስመዝገብ ፈታኝ ነው። ይህም ሆኖ ታሪክ ለአገረ መንግስት ግንባታ የሚኖረው ፋይዳ ታላቅ በመሆኑ ያሉትን ችግሮች በመፍታት ኢትዮጵያን የሚወክል ታሪክ መጻፍ አስፈለጊነት ጊዜው የጠየቀው ጉዳይ ነው።

የታሪክ አረዳድን ለማስተካከል፣ የተዛባን ታሪክ ለማስተካከልና ትርክቶችን በአዲስ ለመቀየር ማህበረሰባዊ ቁርጠኝነት ይፈልጋል። አገራዊ አንድነትን ለማምጣት የሁሉም ፍላጎት መኖር ይገባዋል። ለዚህ መወያየት፣ መግባባትና ለሚደረስበት መደምደሚያ ወሳኝ ምላሽ መስጠት መፍትሄ ይሆናል።

አገራዊ ምክክር እንደተስፋ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት በርካታ ፈተናዎችን አልፋለች፤ እያለፈችም ነው። በለውጥ ሂደት ውስጥ ከሚያጋጥም ለውጥን በጽናት ከሚገዳደር ሃይል ባለፈ ለጦርነት፣ ለሰዎች መሞት፣ ለስደትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆኑ ችግሮች ተፈጥረዋል። ሰላም ጠፍቷል።

በኢትዮጵያ የተካሄደው ለውጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ የህዝቦች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር በህዝባዊ አመጽ የመጣ ነው። ከዚህ ለውጥ ህዝቡ ዴሞክራሲን፣ የሰብዓዊ

መብት መከበርን፣ መልካም አስተዳደርን ይጠብቃል። ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቹ በአግባቡ እንዲመለሱ ይናፍቃል።

የህዝባዊ ለውጡ ዋና ማጠንጠኛ ህዝቡ በኢህአዴግ የአገዛዝ ሥርዓት ያጣውን እንዲያገኝ፣ ጠንካራ አገረ መንግስት እንዲገነባ፣ በወረቀት ላይ ሰፍረው የቆዩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መብቶቹ እንዲረጋገጡ ለማድረግ ነበር። ለውጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ መልካም ውጤት ያስመዘግባል ተብሎ ቢጠበቅም፤ “በለውጡ ደስተኛ ያልሆኑና የተለያዩ ፍላጎቶች ያሏቸው የውስጥና የውጭ ሃይሎች ለውጡን ለመቀልበስ በቅንጅት በርካታ አፍራሽ ተልዕኮችን እየፈጸሙ ይገኛሉ” በሚል የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ የሰፈረው ሃሳብ ሁኔታውን በግልጽ ያመለክታል።

በአገራችን በበርካታ ጉዳዩች በሀሳብ አለመስማማት መኖሩም ይስተዋላል። ለዓመታት እርስ በርስ ያጋደለ በፖለቲካ አመለካከት፣ በአገረ መንግስት ግንባታ በህዝቦች ጥያቄ ላይ በምሁራን መካከል ያለው የሀሳብ ልዩነት ነው። ይህን የሀሳብ ልዩነት አውርዶ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ የመወያየትና የመመካከር ባህል ያለመዳበሩ ዛሬ እየደረሰ ላለው ጥፋት ሌላው መንስኤ ነው። በታሪክ አረዳድ፣ በተዛባ ታሪክ ላይ መንጠልጠልና ትርክቶችን ተቀብሎ መጓዝ አገሪቷንና ህዝቦቿን ዋጋ አስከፍሏል።

በአገራችን ምሁራን መካከል በብዙ ጉዳዮች መግባባት አልተፈጠረም። ከዚህ ቀደም “አሸናፊ” እና “አቸናፊ” በሚሉ ቃላት ውስጥ ባለ ፊደልና እርሱን ተከትሎ በሚመጣ ርዕዮተ ዓለም ምልከታ ምክንያት የሰው ህይወት እስከሚጠፋ ድረስ ያለመግባባት ልምምድ ያደረገ ምሁራዊ ሀሳብ ዛሬ ድረስ ዘልቆ የህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ አድርጓል። ጽንፈኝነትና አክራሪነት እንዲስፋፋ መንገድ ከፍቷል። የ“እኔ ብቻ ትክክል ነው። እኛ ብቻ ታላቅ ነን” የሚል አስተሳሰበ እንዲሰርጽ አድርጓል።

“በልሂቃን መካከል በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመኖሩ፤ በመካከላቸው ያለው አለመተማመን እና ጥርጣሬ የዴሞክራሲ ሽግግር ሂደቱን እጅግ ፈታኝ አድርጎታል። ይህ ቅራኔ እና መዘዙ ከልሂቃን አልፎ በማህበረሰቡ ውስጥ እየሰረጸ ከፍተኛ ምስቅልቅል ማስከተሉ እሙን ነው” በማለት ከላይ የጠቀስነው ሰነድ የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ያሳያል።

ይህ ወደ ማህበረሰቡ የዘለቀው ችግር ሰላምን አደፍርሷል፤ ህዝቡ በቂም፣ ጥላቻና መከፋፈል ውስጥ ሆኖ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲያይ ከማድረግ ያለፈ በድርጊት የተገለጸ ጥፋት ተከስቷል። በየአካባቢው ጽንፈኝነት መንገድ አግኝቷል፤ አክራሪነት ተመችቶታል። በዚህም ሰዎች ሞተዋል፤ ተፈናቅለዋል፣ ተሰደዋል። ወልደው ከብደው ድረው በደስታ በኖሩበት አካባቢ ተዋርደው፣ አንገታቸውን ደፍተው ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ተሰደዋል። ድርጊቱ በአንድነት፣ በወንድማማችነትና በእህትማማችነት ላይ ያነጣጠረ እኩይ ተግባር ነው።



21

ዛሬ በኢትዮጵያ በጽንፈኝነትና በአክራሪነት በተግባር እየተገለጹ የመጡት ችግሮች በምስራቅ አፍሪካ የነጻነት ታሪክ ያላትን፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ሀብቷ የብዙዎችን ትኩረት የምትስብን ታላቅ አገር አፍርሶ ትናንሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ሴራ እየተሰራ መሆኑን ማስተዋል ተገቢ ነው።

በአንድ ወቅት አንድ የምዕራቡ ዓለም ፕሮፌሰር በአንድ ቪድዮ ላይ “ማንኛውም ዋጋ ተከፍሎ ምስራቅ አፍሪካ ከድህነት መውጣት የለባትም” ሲል የተሰማው ንግግር እውን እንዲሆን መንገድ ከፋች ድርጊት እየተፈጸመ ስለመሆኑ ፍንጭ መስጠቱን ያጤነዋል። ታዲያ ምን ይደረግ?

ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ጥንካሬ መመለስ ይኖርበታል። የኢትዮጵያ የጥንካሬ ምንጭ ደግሞ አንድነት፣ መተባበር፣ ኢትዮጵያዊነትን ነው። ይህ አንድነት እንዴት እናምጣው?

ለዚህ ጉዳይ “አገራዊ ምክክሩ ትልቅ እድል ነው፤ ጠቅላላ ኢትዮጵያዊ መወያየት አለበት” በማለት የአገራዊ ምክክር ማካሄድ ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ዋነኛ እርምጃ መሆኑን ብዙዎች እየመሰከሩ ነው። የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሃት በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት ማድረጋቸው፣ ዘላቂ ተኩስ አቁም መፍጠራቸው፣ ህወሃት ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን እንደሚያከብር በፊርማው ማረጋገጡ በቀጣይ ለሚካሄደው አገራዊ ምክክር ከፍተኛ ትርጉም አለው። የቆሰለውን ለመፈወስ ታላቅ ነው።

አገራዊ ምክክር ከተደረገ ቀድሞ የነበረውን አንድነት ለማምጣት ያስችላል። ለሰላም እጦት መንስኤ የሆኑትን መዋቅራዊ ችግሮችን የመፍታትና እንዲባባስ የሚያደርጉ አቀጣጣይ ምክንያቶችን የመግታት አቅምም ይፈጠራል።

መንግስት “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች መድሃኒቱ የዜጎች ቁጭ ብሎ መወያየት ነው” በማለት ያምናል። ለዚህ ሀሳቡ ማጠንከሪያ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም ማደረጉ ትልቅ ትርጉም አለው። ኢትዮጵያውያን ቁጭ ብለው ከተመካከሩ የችግሮቻቸውን መንስኤዎች የመፈተሽ፣ መፍትሄያቸውንም በጋራ የመተለምና የመተግበር እድላቸው ይሰፋል። የፖለቲካ፣ የአመለካከት ልዩነት ድንበር አይሆንባቸውም። ሁሉን አካታች አገራዊ ምክክር ማድረግ በምሁራን፣ በህዝቡ መካከል መግባባት የመፍጠር አቅም ይኖረዋል።

በህዳር 2015 ዓ.ም ለማካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት የአገራዊ ምክክር አጀንዳ ኢትዮጵያን ከጥፋት ይታደጋት ይሆን? ሁሉም በቅን ልቦና አገራዊ አንድነትን ጠብቆ ለመሄድ፣ በሀሰት ትርክት የተገነባውን የባቢሎን ግንብ አፍርሶ ሰላምን ለማስፈን ምን ያህሉ ዝግጁ ይሆናል? ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ መስጠት የዜጎች በተግባር የሚገለጥ የቤት ስራ ነው። አገራዊ ምክክር ማለት ምንድን ነው? ምንስ እንዲያመጣ ታስቦ ይዘጋጃል? ለሚሉት ሀሳቦች አመላካች ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል።

አገራዊ ምክክር ለምን? አገራዊ ምክክር በተለያዩ ጊዜያት እያደጉና ስር እየሰደዱ የመጡ ግጭቶችን ለመፍታት፣ አለመግባባቶችን ለማረቅ ያስችላል ተብሎ የሚታመንበትና ተግባራዊ የሚሆን የግጭት መፍቻ አንድ ስልት ነው። በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምክክር ማድረግ አስፈላጊነት አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታና አሳሳቢ ጉዳይ አኳያ ተመራጭ ዘዴ ነው። ሰዎች ምክክር ለምን ተባለ? ውይይት ወይም ድርድር የሚለው የተመረጠ አይሆንም እንዴ? የሚሉ ጥያቄዎች ያነሳሉ።

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 ማብራሪያ ላይ እንደተገለጸው፤ ውይይትም ሆነ ድርድር የሚሉትን ቃላት መጠቀም አላስፈለገም። ውይይት ሃሳብ መለዋወጥን እና ማንሸራሸርን የሚያመለክት የመስተጋብር ውጤት ነው። ድርድርም ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች አሊያም ቡድኖች በሰጥቶ መቀበል መርህ የሚሰሩበት ነው።

በአገራዊ ምክክሩ ሂደት የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሄ በመፈለግ፣ በመፍትሄዎቹ ላይ በመግባባት አገራዊ አንድነት እና ህብረታችን ማጠናከርን መነሻ ያደረገ በመሆኑ “ምክክር” የሚለውን ሀሳብ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። አገራዊ ምክክር ሲካሄድ አንድ ወጥ ሀሳብ እና አንድ ወገን ብቻውን የሚመክርበት አይደለም። ልሂቃንንና አብዛኛውን ማህበረሰብ አካቶ የጋራ መፍትሄ የሚፈለግበት መንገድ ነው።

በምክክሩ ወቅት በየአጀንዳው የተለያዩ ሀሳቦች፣ ጥቅሞች፣ ፍላጎቶችና መብቶች ተወክለው ምክክር ይደረግበታል። ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ልዩነትን በሚያሳይ መልኩ ሁሉም ያላቸውን ሀሳብ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንደሚያመጡ ተስፋ ይደረጋል። ጥልቀትና አግባብነት ባላቸው አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ስለሚሰጠውና ተገቢ የሆነ አቅጣጫ ስለሚቀመጥለት ወጤቱ መልካም እንደሚሆን ተስፋ ይደረጋል። በዚህም ለአገሪቷ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦች ይገኛሉ፤ ሁሉም በጋራ ለመፍትሄያቸው ይረባረባል።

በሕዝብ ጥቆማ የተመረጡ 11 አባላትን ያቀፈው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በአዋጅ የተቋቋመውና የኢትዮጵያ ህዝብ ያካሂደዋል ተብሎ የሚጠበቀው አገራዊ ምክክር “ጉዳዮችን ከታች ወደ ላይ አካታችና አሳታፊ በማድረግ አገራዊ መግባባት እውን እንዲሆን ማስቻል ነው” ሲሉ ነው የገለጹት።

የአገራዊ ምክክር ሰላምን ለማስፈንና ግጭትን ለማስወገድ፣ በለውጥ የተጀመሩትን የፖለቲካና ዴሞክራሲ ሽግግሮችን ለማሳለጥ ይረዳል። በተለይም በአገር ውስጥ ያጋጠሙትን ልዩነቶች በማጥበብ፣ የእርስ በርስ ግንኙነትን ለማሻሻልና መተማመን ለመፍጠር እንደሚያስችል እምነት ተጥሎበታል። መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች ምሁራንና ህዝቡ ለአገራዊ አንድነት ገንቢ የሆነ አቋም እንዲይዙ የማድረግ ግብ ሰንቋል። ይህም ዘላቂ ሰላምና

ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ጽንፈኝነትንና አክራሪነትን ለማስወገድ አንድ መፍትሄ ተደርጎ ይወሰዳል።

ምክክሩ ከሌሎች ጊዜ የሚለይ መሆኑም እመርታን ያሳያል። “የተለመደ ልሂቃን ውይይት ሳይሆን ከታችኛው ህብረተሰብ ጀምሮ ሁሉን አሳታፊና ሀሳብ የሚንሸራሸርበት፣ በግልፀኝነትና ተጠያቂነት መርሆች የሚመራ ነው” በማለት ፕሮፌሰር መስፍን የገለጹት ሀሳብ በምክክሩ ከታች ወደ ላይ የሚደረግና ሁሉን አቀፍ መፍትሄ የሚያስገኝ እንደሆነ ያመለክታል።

በዚህ በኩል ምሁራን ተመሳሳይ አቋም ያሳያሉ። ፖለቲከኛው ሌንጮ ለታ እንደሚገልጹት፤ አገራዊ ምክክሩ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና መግባባትን በመፍጠር ሰላምን ያሰፍናል። የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመገንባት ያስችላል።

እንደአቶ ሌንጮ ገለጻ፤ ሂደቱ በሕዝቦች መካከል መተማመን እና መግባባትን በማጠናከር ሰላም ለማስፈን የጎላ ሚና ይኖረዋል። በግጭት አካባቢዎች ሰላም በማውረድ፣ ሰላም በሰፈነባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከሁሉም አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመሥራት ይረዳል።

ማጠቃለያ ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ችግር ለመወጣትም ሆነ ዘላቂ ሰላም ለማሰፈን በራሷ መንገድ ችግሮቿን የመፍታት አቅም አላት። ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና መገናኛ ብዙሃን በእውነተኛ መሰረት ላይ በመቆም ለአገሪቷ መጻኢ እድል ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

ህዝቡ ከላይ እስከታች በመንቀሳቀስ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምክክር እንዲያካሂድ ማድረግ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። በአገራዊ ምክክሩ አገራዊ መግባባትን ለማምጣት፣ የአገረ መንግስቱን ቅቡልነት ለማሳደግ የሚረዱ ምክረ ሀሳቦች ይገኛሉ ተብሎ ይታመናል። በሚካሄደው ምክክር ምክረ ሀሳቦቹ የአብዛኛው ዜጋ ድጋፍ ያላቸው፣ ተፈጻሚ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የሚገለጸው። በመሰረቱ አገራዊ ሰላምና መረጋጋት ለምክክሩ ሂደት ትግበራ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያውያን በምክክሩ አሸናፊ ሆነው ለመውጣትና ስኬታማ ለመሆን ሁሉም የድርሻውን በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል።

በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሰላምና ደህንነት እውን እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች መረባረብ ይኖርባቸዋል። ለዚህም በየአካባቢው የሚስተዋሉ ግጭቶች መቆም ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። ግጭቶችን መቀልበስ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

ህዝቡ፣ የጸጥታ ሃይሉ በየአካባቢው የሚስተዋሉ ግጭቶችን እንዲቆም በማድረግ መጪውን ዘመን መልካም ማደረግ ተገቢ ነው።



22

ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 22 ኅዳር 2015 ዓ.ምበግብርና ሚኒስቴር እና በኢዜአ ትብብር የተዘጋጀ

ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ተግባር

ግብርና



23

በፍቅርተ ባልቻ

በዓለማችን ላይ ከተደቀኑ ስጋቶች አንዱ የአየር ንብረት ለውጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም አገራት መሪዎች መነጋገሪያ ከሆነ ውሎ አድሯል። የአገራት መሪዎች በስብሰባዎቻቸው አንደኛው አጀንዳ እያደረጉ ቢመክሩበትም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲገባ ግን ወገቤን የሚሉ አገራት በርክተዋል።

የአየር ንብረት ለውጥን ስጋት እየጨመሩ ያሉ እንቅስቃሴዎች ከዘመናዊነት ጋር በጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። በርካታ ፋብሪካዎች ሲገነቡ የፋብሪካዎቹ ጭስ፣ ተረፈ ምርት የአየር ንብረቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ፋብሪካዎቹ በግብዓትነት የሚጠቀሟቸው ቁሳቁሶች ደግሞ ከእፅዋት የሚገኙ እንደመሆናቸው የእፅዋት፣ የዛፎች፣ ዝርያዎች፣ ወዘተ … እንዲመናመኑ የዓለማችን የደን ሽፋን እንዲቀንስ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።

ስለሆነም እነዚህ እና መሰል ድርጊቶች በቀጥታ በአየር ንብረቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ከዚህ አንጻር የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑት እና በቀጥታ የጥቅሙ ተቋዳሽ ያልሆኑት በማደግ ላይ ያሉ አገራት መሆናቸው እርግጥ ነው። የኢትዮጵያ መሪዎች በዓለም መድረኮች ላይ አገራችንን ከዛም አልፎ አፍሪካን ወክለው የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ አጀንዳዎችን በማንሳት ሲሞግቱ፣ ሲከራከሩ ይታያል፣ ይደመጣል።

ኢትዮጵያ በዓለም አገራት ላይ ጫና ለማሳደር የምታደርገው ጥረት እና እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ በአገር ውስጥ ያለውን አቅም አሟጦ በመጠቀም አረንጓዴ ልማቱን ለማፋጠን ብዙ እየተሰራ ነው። በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት በመለስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተገኘው ውጤት ‘በአንድነት ከቆምን’ ምን ዓይነት አቅም እንዳለን አስተማሪ የሆነ መልዕክት ያስተላለፈ ነው።

ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበስ ተግባር



24

ነጋሪ በዚህ ዕትሟ የግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ታደሰን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተገኙ መልካም አፈጻጸሞች እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ቆይታ አድርጋ እንደሚከተለው አሰናድታዋለች። ዝለቁ!

ነጋሪ፡- በቅድሚያ ለጊዜዎ ከልብ እናመሰግናለን!

አቶ ተፈራ ታደሰ፡- መረጃ እንድሰጥ ስለጋበዛችሁኝ እኔም አመሰግናለሁ!

ነጋሪ፡- የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር (ፕሮግራም) አፈጻጸም ስኬት ከዓላማው ጋር ሲነጻጸር እንዴት ይገልጹታል?

አቶ ተፈራ፡- ኢትዮጵያ በመሬት መደህየትና መቆርቆዝ የተጠቃች አገር ናት። ይህም የእፅዋት ሽፋን መራቆትን እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የአፈር መከላት፣ የደረቃማና ለምርት ምቹ ያልሆኑ ቦታዎች መስፋፋትን ያካተተ ነው። ይህንን ለመቀልበስ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ የቆየ ቢሆንም የተቀናጀና ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ሳይሆን እዚህም እዚያም የተበጣጠሱ እንቅስቃሴዎች ናቸው የነበሩት።

የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ መርሃ ግብር ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ሲተገበር ነበር። ይህን ተከትሎ በተለያዩ ተቋማት ተበጣጥሰው ሲከናወኑ የነበሩትን ሰብሰብ አድርጎ በተማከለ አግባብ ከላይ እስከታች በተናበበ መንገድ እንዲተገበር ተደርጓል።

ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበናል። 20 ቢሊዮን ችግኞችን ነበር ለመትከል የታሰበው። ይሁንና በነበረው ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ይህንን በማስፈጸም ሂደት ውስጥ ባሉ ተዋንያን ተሳትፎ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ ወደ 25 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን መትከል ተችሏል።

አብዛኛው (90 በመቶ በሚጠጋው) ሕብረተሰብ ዘንድ ያለው ግንዛቤ ጥሩ ነው። በከተማም በገጠርም ሳይወሰን፣ የአንድ ተቋም ስራ ነው ተብሎ ሳይተው ሲሰራ ነበር። ሁሉም የተሳተፉበት መንግሥታዊ መዋቅር፣ ፖለቲካ አመራሩ፣ የከተማውና የገጠሩ ሕብረተሰብ ተሳትፎና እንቅስቃሴ አንዱ መልካም አፈጻጸም እንደሆነ መግለጽ ይቻላል።

ነጋሪ፡- በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተመዘገቡ ስኬቶች ምንድናቸው?

አቶ ተፈራ፡- ስኬቶችን በየፈርጁ ማየት አስፈላጊ ነው። ስለሆነም ስኬቶቹን በተለያዩ ዘርፎች ከፋፍሎ መግለጽ ይቻላል። ማንኛውም እፅዋት ደን ሊሆን አይችልም። ለደን ሊውሉ የሚችሉ የእፅዋት ዓይነቶች አሉ። እነዚህም የዛፍነት ባሕሪይ ያላቸውና ከሁለት ሜትር በላይ ሊያድጉ የሚችሉ ናቸው። ማንኛውም የእንጨትነት ባሕሪይ

ያለው ዛፍ ለደንነት ብቻ ሊውል አይችልም። ምክንያቱም መተከል ያለበት ቢያንስ ከግማሽ ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ ነው። ወደ 500 ካሬ ሜትር ላይ የተተከለ የዛፍነት ባሕሪይ ያላቸው የእፅዋት ዓይነቶች (የአገር በቀልም የውጭ አገርም) የተተከሉበት ስፋራን ነው ደን የምንለው።

የአረንጓዴ አሻራ ስራው ለኢትዮጵያ የደን ሽፋን መጠን መጨመር አስተዋጽኦ አለው። አንደኛ የሰው ሰራሽ ደኖችን እየፈጠርን ስንሄድ በተፈጥሮ ደኖች ላይ የነበረውን ተጽዕኖ ይቀንሳል። ምክንያቱም ሕብረተሰቡ የራቁ የተፈጥሮ ደኖች ጋር ከመሄድ በአካባቢው አልምቶ ለማንኛውም ነገር መጠቀም የሚችል ከሆነ ወደተፈጥሮዎቹ ደኖች አያመራም።

ሁለተኛው የተፈጥሮ ደንን ለማስፋት እንዲሁም በሳሱ የተፈጥሮ ደኖች መካከል የሚተከል ስለሆነ የደን ሽፋንን ለውጥ እንዲያመጣ አድርጓል። ይህንንም በተለያየ መልኩ የተጠኑ ጥናቶች እያረጋገጡ ነው።

ቀርከሀ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ሊሰጡ ከሚችሉ የእጽዋት ዓይነቶች እና በአጭር ጊዜ ሊደርስ የሚችል ነው። ከቀርከሀ ጋር ያለው ልማት አንደኛው የአረንጓዴ አሻራ

ችግኝ ተከላ እንቅስቃሴ አካል ነው። እንቅስቃሴው (ሁለቱንም አይነቶች) በደጋ የሚበቅለውም፣ ውስጡ ክፍት የሆነና በቆላማ አካባቢ የሚበቅለውን ውስጠ ድፍን ወይም ሽመል ተብሎ የሚጠራውን ቀርከሀ ያካተተ ነው።

ፍራፍሬ ስንተክል በአንድ በኩል በተራቆቱ አካባቢዎች አረንጓዴነትን ለማስፋት ይረዳል በሌላ በኩል ወደ ኪስ ሊገባ፣ የሕብረተሰቡን ኑሮ ሊያሻሽሉ እና ለአገርም የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ። ስለሆነም ፍራፍሬዎችን መትከል ያለው ፋይዳ ፈርጀ ብዙ ነው። የስራ ዕድል መፍጠራቸው፣ በሕብረተሰቡ እና በባለድርሻ አካላት ዘንድ የተፈጠረው ግንዛቤ የመልካም አፈጻጸሙ አካል እንደሆኑ ማንሳት ይቻላል።

ነጋሪ፡- የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ ምን ይመስላል?

አቶ ተፈራ፡- በሂደቱ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ መልካም አጋጣሚዎች አሉ። ዘር ከመሰብሰብ ጀምሮ ችግኝ በማፍላት ሂደት ውስጥ የሚመጡ ስራዎች አሉ። ምንም እንኳን ቁጥራቸው በርካታ ባይሆንም ዘር ሰብስበው የሚሸጡ ወጣቶች አሉ። በጣም ሰፊ ቁጥር

የግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈራ ታደሰ



25

ያለውን የስራ ዕድል የሚፈጥረው ግን በችግኝ ጣቢያ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው የጉልበት ስራ ነው። ለምሳሌ አንድ የአገር በቀል ችግኝ ለማፍላት ወደ አስራ ሁለት ወራት ይፈጃል። ስለሆነም በእነዚህ ወራት ውስጥ ስራ ፈላጊ ተቀጥሮ ይሰራል ማለት ነው።

ወጣቶች በራሳቸው እንዲሁም ከላይ እስከታች ባለው የመንግሥት መዋቅር የቴክኒክ ድጋፍ በማግኘት እየሰሩ ነው። ቢሾፍቱን፣ ሞጆን፣ ሲዳማ፣ ወዘተ … ውስጥ በተለያየ ቦታ ብንሄድ እያንዳንዱ ግለሰብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን እያፈሉ የሚሸጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የሚፈሉት አብዛኛዎቹ ችግኞች ደግሞ ፍራፍሬ ናቸው።

ፍራፍሬ ማፍላቱ በጣም ጥብቅ ክትትል ይፈልጋል። አንዳንዶቹ መዳቀል ስላለባቸው ፈልተው የማይተከሉ አሉ። ለምሳሌ እንደአቮካዶ፣ ማንጎ ያሉት መዳቀል ይኖርባቸዋል። ማዳቀል ራሱን የቻለ ሳይንስ እና እውቀት ነው። ይህ ሳይንስ ድሮ በተማረው ሕብረተሰብ ዘንድ ብቻ ነበር። ይህንን ትምህርት በሚያስተምሩ ኮሌጆች ውስጥ አልፈው የሚመጡ ልጆች ብቻ ነበር የሚያውቁት። ዛሬ ግን ወጣቱ ይህንን ማድረግ ይችላል። ሞጆ የተደራጁ ወጣቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ የሚያፈሉት ራሳቸው ናቸው። ይህ እውቀት ከየት መጣ? በነበረው

ፍላጎትና መነሳሳት ሕብረተሰቡ ወደዚያ እንዲዞር አድርጎታል።

ከጥበቃ ጋር ተያይዞም የስራ ዕድል ተፈጥሯል። በተለይ በወል ሜዳ፣ ማሳ መሬት ላይ የሚተከሉ ችግኞች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል። ሕብረተሰቡ ወይም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በዚህ ደረጃ አደራጅተው እንዲጠብቁ በማድረግ የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ከለሙ ተፋሰሶች ጋር ተያይዞ በበጋ የምንሰራው ስራና በክረምት የምንሰራው ስራ ተቀናጅቶ ስለሚሄድ በለሙ ተፋሰሶች ላይ ወጣቶች ንብ በማነብ፣ ከብት በማድለብ እንዲደራጁና እንዲጠቀሙ ማድረግ መቻሉ አንደኛው ስኬት ነው።

ነጋሪ፡- የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ለማዘመን ወይም ከቴክኖሎጂ አንፃር ምን ታስቧል?

አቶ ተፈራ፡- አገሪቷ ውስጥ ስንት ችግኝ ጣቢያዎች አሉ? የት ነው የሚገኙት? የማናቸው? የፕሮጀክት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የግለሰብ የሚለውን ለይተን ለማወቅ ጥረት አድርገናል። በመንግሥት ስር ያሉት ስንት ችግኝ ጣቢያዎች ናቸው? ስፋታቸው ስንት ነው? የሚገኙበት ሥነ ምህዳር ምንድን ነው? የሚለውን

ለመለየት ተሰርቷል።

የተከላ ቦታ የት ነው የሚገኘው በየትኛው ቀበሌ በየትኛው ወረዳ፣ ዞን፣ ክልል ውስጥ ነው ይህንን እኔ ፌደራል ላይ ተቀምጬ ማየት ማወቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ ተሰርቷል። የተከላ ቦታም ሆነ የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች በየትኛው ቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን፣ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ቦታዎቹ ድረስ መሄድ ሳይጠበቅብን ባለንበት ሆነን ማወቅ እንችላለን።

ለዚህም መልስ ሊሰጠን የሚችል በቴክኖሎጂ የታገዘ መረጃ ተደራጅቷል። ማንኛውም ሰው የጂኦግራፊክ መገኛ መረጃ በመውሰድ እና ከጎግል ኧርዝ (google earth) ጋር አያይዞ ማየት እንዲችል ተደርጓል።ካርታ በእጃችን ስላለ ቦታዎቹን ለማየት ጎግል ማድረግ ብቻ ነው የሚጠይቀን ይህ አንድ ትልቅ እድገት እና ለውጥ ነው። የችግኝ ጣቢያዎችን ቁጥር በዚያ ደረጃ ሪፈረንስ ለማድረግ የተኬደበትን ጥረት ለየት ያለ ነው ብለን መውሰድ እንችላለን። በየትኛውም ቦታ ያለ ሰው፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተቀምጦ ማየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን መሰረት አድርገን የሰራነውን ስራ እንደ ስኬት ነው የምንወስደው።

ነጋሪ፡- የተተከሉት የፍራፍሬ ተክሎች የሚገኙበት ሁኔታ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸው ምንድን ነው?

አቶ ተፈራ፡- ትኩረት በሚፈልጉ ችግኞች ቁጥር ላይ የመጣው ለውጥ ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይላል የአገራችን ሰው እና ለምሳሌ ፍራፍሬን፣ መኖን፣ ቀርከሀን ስንወስድ በአንድ ድንጋይ ሁለትና ሶስት አራት ወፎችን እንደመምታ ነው። ፍራፍሬን ብቻ ነጥለን ብናይ መጀመሪያ ከነበረው 4ኛ ዓመት ላይ የመጣው ለውጥ የተሻለ ነው።

ከነበረን ክንውን ፍራፍሬን ብቻ ነጥለን ብናይ በ2011 ስንተክል ከነበረው 2012 የሚበልጥበት፣ ከ2012 ደግሞ 2013፣ ከ2013 ደግሞ የ2014 ተከላ በርካታ የፍራፍሬ ችግኞችን እንድንተክል ያደረገ ነው። ወደ ፍራፍሬ የማድላቱ ስራ በአንድ ጊዜ ብዙ ጥቅም የሚሰጠን ስለሆነ ከስኬት ማየት እንችላለን። በ2011 የተተከሉት ምንም እንኳን በመጠን ከ2014 ያነሰ ቢሆንም የምስራች ፍሬ ሰጥተውናል። ምሳሌ ቢሾፍቱ ላይ የተተከሉ አቮካዶ ፍራፍሬዎች የመጀመሪያ የምስራች አብሳሪዎች ሆነዋል።

ችግኝ ማፍላትና መትከሉ እንደዚህ እያደገ የመጣበት ነገር ከሕብረተሰቡ ጋር ፍላጎቱ መጨመሩ ነው። አንደኛ ከገበያ ጋር ለማስተሳሰር የተደረገውና ከኤክስፖርት ጋር ተያይዞ የመጣው ለውጥ ነው። ፍሬውን በመብላት ሥርዓተ ምግባችንን እናሻሽላለን ፍሬውን በመሸጥ ለአገር ተጨማሪ ኃብት በማምጣት ረገድ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ነጋሪ፡- ዛፍን ተክሎና ተንከባክቦ ለማሳደግ

ችግኝ ማፍላትና መትከሉ እንደዚህ እያደገ የመጣበት ነገር ከሕብረተሰቡ ጋር ፍላጎቱ መጨመሩ ነው። አንደኛ ከገበያ ጋር ለማስተሳሰር የተደረገውና ከኤክስፖርት ጋር ተያይዞ የመጣው ለውጥ ነው።



26

በሕብረተሰቡ ዘንድ የዳበረ ተሳትፎና ልምድ ምን መልክ አለው? የጽድቀታቸው ሁኔታስ ምን ይመስላል?

አቶ ተፈራ፡- በድህረ ተከላ የመጣው ለውጥ አንደኛው የስኬት ማሳያ ነው። በርካታ ችግኞች እንዲጸድቁ ተደርጓል። ባለፉት አራት ዓመታት ከተተከሉት ችግኞች ከሰማንያ በመቶ ያላነሱት ጸድቀዋል። የዓለም አቀፉ መስፈርት ከተተከሉት ችግኞች ከሰባ አምስት በመቶው በላይ ከጸደቁ ጥሩ አፈጻጸም ስለመሆኑ ይጠቅሳል። እኛ ከዚህ ትንሽ ፈቀቅ ብለን ወደ ሰማንያ በመቶ የሚጠጋው ችግኝ እንዲጸድቁ ማድረግ ችለናል። አሁን የተተከሉን ችግኞች ብቻ በዚህ ደረጃ ይዘን ከቀጠልን ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት እና አስር ዓመታት ውስጥ የአየር ሁኔታዋ የተስተካከለ፣ አረንጓዴነት በስፋት የሚታይባት አገር ትሆናለች።

ሌላው እንደስኬት መታየት ያለበት ሕብረተሰቡ ላይ የመጣው የግንዛቤ ለውጥ ነው። የሕብረተሰቡን ተሳትፎ እኛ የሰው ቀን እያልን ነው የምንገልጸው፤ የሰው ቀን ማለት አንድ ሰው ስንት ቀን፣ ስንት ጉልበት ሰጠ ማለት ነው። ይህም የተሳተፈውን ሰው ብዛት ሳይሆን የሚነግረን (አንድ ሰው በተደጋጋሚ ስራ ላይ ተሰማርቶ ሊሆን ስለሚችል) ምን ያህል የሰው ጉልበት ተጠቅመናል የሚለውን ያሳየናል። በዚህም መሰረት በ2014 ዓ.ም ወደ ሰላሳ ሦስት ሚሊዮን ሰው ቀን ወጥቶ ስራ ሰርቷል። ከደን ልማት ስራው ጋር፣ እፅዋትን በቤት ውስጥም ከግቢ ውጪም በመትከል ረገድ በሕብረተሰቡ ዘንድ ለውጥ መጥቷል።

ድሮ የአንድ ተቋም ስራ ነው ተብሎ ይወሰድ ነበር። አሁን ሁሉም ይመለከተኛል የሚለውን ግንዛቤ ማዳበር መቻሉ ትልቅ ለውጥ ነው። ይህ በሚቀጥሉት ዓመታት ለሚካሄደው ስራ ትልቅ ጉልበት እና አቅም የሚሆን ነው።

ነጋሪ፡- የለሙትን አካባቢዎች ለከብቶች ግጦሽነት መጠቀም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ይህን ለመከላከል ምን ዓይነት ጥንቃቄ እየተደረገ ነው?

አቶ ተፈራ፡- ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በእንስሳት ኃብት የተሻለ ቁጥር ካላቸው የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በቀዳሚነት ተርታ ትመደባለች። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ መሬቱ እየተራቆተ፣ ግጦሽ እየጠፋ ይሄዳል። ይህንን ለመደገፍና ለማገዝ ከመኖ ጋር የተያያዙ ስራዎች መሰራት አለባቸው።

የለሙ ተፋሰሶች እና ችግኝ የተተከለባቸው አካባቢዎቸ ከሚጎዱባቸው አንዱ ግጦሽ ነው። ይህንን እንዲያግዝ የመኖ ልማት ታስቦ እየተሰራ ነው። ለመኖነት ሊውሉ የሚችሉ የእንጨትነት ባህሪይ ያላቸው (ከሳር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን በሙሉ አይጨምርም) እፅዋቶች ለምተው ሲተከሉ ለመኖነት ይውላሉ።

ከመኖነትም ባሻገር የአረንጓዴነት ሽፋንን ይጨምራሉ፣ የአፈርን መሸርሸር ለመከላከል የሚሰሩ እርከኖችን ለማጠናከር ያግዛሉ። በተጨማሪም አካባቢን ከቆላማነት የመከላከል ሂደት ውስጥ ጠቀሜታቸው የጎላ ነው። አካባቢዎቹም አረንጓዴነት እና ውበትን የተላበሱ እንዲሆኑ ያደርጋሉ።

ነጋሪ፡- በድህረ ተከላ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምን ምን ናቸው?

አቶ ተፈራ፡- የድህረ ተከላ እንክብካቤ ብለን የምንጠራው በውስጡ ብዙ ስራዎችን ያካተተ ነው። ጥበቃ፣ አረም፣ ኩትኳቶ፣ ውሃ ማጠጣት የድህረ ተከላ ወቅት የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው። ከድህረ ተከላ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ እና ከተከሉት ችግኞች በርካቶቹ እንዲጸድቁላቸው በማድረጋቸው የተሸለሙ ድርጅቶች አሉ፤ እኛ ትኩረት የምናደርገው ግን በስራው በስፋት እየተሳተፈ ያለው እና ሰፊውን ሕብረተሰብ በሚወክለው አርሶ አደር ዘንድ ያለው እንቅስቃሴ ላይ ነው። በአርሶ አደር ደረጃ ምርጥ የሚባሉ አሉ።

በቢሊዮን የሚቆጠረው ችግኝ ያረፈው በአርሶ አደሩ እጅ ነው። አርሶ አደሩ የሚሰራው ስራ ምንድነው የሚመስለው የሚለውን ስናይ የመጀመሪያው ነገር የጥበቃ ነው። በተለይም ከተፋሰስ ተጠቃሚዎች እና ከደን ተጠቃሚዎች ማህበር ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ስራዎች አሉ። ችግኝ በተተከለባቸው አካባቢዎች ከብቶች እንዲሰማሩ አይፈቀድም ይልቁንም ሳሩን አጭዶ ከብቶች መመገብ አለ። ጥበቃ ከሚካሄድባቸው ቦታዎች ውስጥ ባሌን፣ ሰሜን አቸፈርን፣ አርሲ፣ ወላይታ አካባቢዎችን መጥቀስ እንችላለን።

ነጋሪ፡- በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ምን ምን ናቸው?

አቶ ተፈራ፡- በርካታ የተሻሻሉ ነገሮች ቢኖሩም መቶ በመቶ እንከን አልባ ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም፤



27

የኢትዮጵያ መሪዎች በዓለም መድረኮች ላይ አገራችንን ከዚያም አልፎ አፍሪካን ወክለው የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከቱ አጀንዳዎችን በማንሳት ሲሞግቱ፣ ሲከራከሩ ይታያል፣ ይደመጣል።

ክፍተቶች አሉ። በተከላ ጊዜ የሚታዩ የቴክኒክ ክፍተቶች አሉ። አንዳንዱ የአፈሩን ኳስ ወደ ታች ትቶ ከላይ ያለችውን እፅዋቷን ብቻ ይዞ ይታያል፤ ይህም ችግኞች እንዲነቃቀሉ ያደርጋል።

አንዳንድ ጊዜ ከነ ላስቲካቸው ሲተከሉም ያጋጥማል። ሌላ ጊዜ ደግሞ የተቆፈረው ጉድጓድና የችግኙ አፈር ተመጣጥኖ የማይተከልበት ሁኔታ አለ። አንዳንዴ ጉድጓዱ ወደ ውስጥ ይጠልቅና ችግኙ ወደ ውስጥ ይቀበራል። አንዳንዴ ጉድጓዱ ያንስና ችግኙ ወደ ላይ ይወጣል።

የወጣው ሕብረተሰብ በሙሉ በሚፈለገው ልክ ከተከላ ጋር የተያያዘውን ስራ ጉልበቱ ሳይባክን ከማሰራት አንጻር የሚስተዋሉ የተወሰኑ ክፍተቶች አጋጥመዋል። በጣም ውስን በሆኑ አካባቢዎች ላይ ለሥነ ምህዳሩ የማይመጥኑ ችግኞች የመትከል ሁኔታዎችን አይተናል እነዚህ ሂደቶች እንዲስተካከሉ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ከድህረ ተከላ እንክብካቤ አንጻርም በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶች አሉ።

ነጋሪ፡- በቀጣይ በሚከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከማስቀጠል እና የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክቦ ለውጤት ከማብቃት አኳያ የተቀመጡ አቅጣጫዎች የትኞቹ ናቸው?

አቶ ተፈራ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የቀጣይ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ትኩረት የሚያደርግባቸው መሰረታዊ ስራዎችን የተመለከተ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል። አገር በቀል ችግኞች ላይ ማተኮር አንደኛው ነው። ተከላን ከማሰባችን በፊት

የት ነው መትከል ያለብን የሚለውን ማጤን አለብን። ቦታ መለየት ብቁ ቦታ መኖሩን እርግጠኛ መሆን ይህን መሰረት አድርጎ ችግኞችን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። መተከል ያለበት ችግኝ ከሥነ ምህዳር አንጻር ለዚያ አካባቢ የሚመጥን፣ ለአቅመ ተከላ የደረሰ፣ ያልቀጨጨ እጅግም ያልገዘፈ ችግኝ መተከል እንዳለበት ተቀምጧል።

የድህረ ተከላ ስራው ወሳኝ ነው። የአረም፣ ኩትኳቶ፣ ከጥበቃ ጋር የተያያዘው ስራ ላይ በትኩረት መሰራት አለበት። ችግኝ የተተከለባቸው አካባቢዎችን በመጠበቅ ለግጦሽ እንዳይጋለጡ ለማድረግ እንዲሁም እሳት አደጋን እና ሌሎች መሰል ችግሮችን ለመከላከል እየተሰራ ነው።

የቱ ጋር እንደምንተክል፣ ስፋቱ ምንድነው የሚመስለው፣ ባለቤትነቱ የማነው የሚለውን ሊገልጽ በሚችል መልኩና ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ላይ ሆኖ መረጃውን ማየት እንዲችል ይሰራል። በአጠቃላይ ከዝግጅት እስከ ተከላ ድረስ ጥራትን መሰረት አድርጎ እንዲሰራ ነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ የተሰጠው።

ተከላ የአንድ ወገን አይደለም አረንጓዴ አሻራ ያሳየን ይህን ነው። ሁሉም ጉልበቱን ሰጥቶ ስራውን ሲሰራ ነበር። በተከላ ወቅት ሕብረተሰቡ የሚያሳየውን ትጋት በድህረ ተከላ ስራ ላይም በዚህ ደረጃ መውጣትና ማገዝ አለበት። ችግኝ እንክብካቤ ይፈልጋል፤ ይህንን ማድረግ ከቻልን የምንፈልገውን ዓላማ እናሳካለን።

ነጋሪ፡- ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን!

አቶ ተፈራ፡- እኔም አመሰግናለሁ!



28

የሥነ-ጽሑፍ ሚና ለአገር እና ለሕዝብ ፅናት

ሥነ ጥበብ



29

ቦታው አዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ነው፡፡ ዓመታዊው “ንባብ ለሕይወት” የመጽሐፍት አውደ ርዕይ ክዋኔን ያስተናግድ ይዟል - ማዕከሉ፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች በዓይነትም በብዛትም፤ በተለያዩ ቋንቋዎችም ጭምር ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ሸማችም እንደ ምርጫው ይገበያል፡፡

ከገበያው መሐል ቆየት ያሉ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎችን እና የታሪክ መጽሐፎችን እየሸመተ ያገኘሁት ወጣት እውነትም መላኩ፤ አዳዲስ መጽሐፎችን እየዘለለ ወደ ኋለኛው ዘመን የመጓዙ ምክንያት አስገርሞኛል፡፡ የዚህ ዘመን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ምርጫው ውስጥ ያለመሆናቸውን ምክንያት እንዲነግረኝ ጠየቅኩት፡፡

“የአሁኑ ዘመን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች የቀድሞዎቹን ያህል ረብ ያለው ነገር የሚሰጡኝ አይደሉም፡፡ በማኀበራዊ ሚዲያዎች የተጮኸላቸውን ያህል ከፍ ያለ ነገር ይዘው አይገኙም” ይላል፡፡ ከእርሱ ከግል ፍላጎቱ ባሻገር ለብዙኀኑ ማኅበረሰብ እና ለአገርም ጭምር ሊሰጡ የሚችሉት አንዳች ፋይዳ የሌላቸው ናቸው፡፡

“የቀደሙቱ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ዘመናቸውን ከመግለጽ ባሻገር ብዙዎቹ መጪውን ጊዜም በመተንበይ ሕዝብና አገርን ወደፊት ለማራመድ ይሞክሩ ነበር፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ዛሬ ላይ ስናነባቸው ትርጉም የሚሰጡን አሉ” በማለት የበዓሉ ግርማን ኦሮማይ እና የብርሃኑ ዘሪሁን ማዕበልን ለአብነት ይጠቅሳል፡፡

የአሁን ዘመን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ግን የተባለውንና የምናውቀውን ነገር እንደ በቀቀን ከማስተጋባትና የጸሐፊዎቹን ውስን የሆነ የግል ስሜትና ህልም ከመግለጽ ባለፈ “ለአገርና ለማኅበረሰብ ታላቅነት ግድ ኖሯቸው የሚገኙ አለመሆናቸውን ታዝቤያለሁ” ይላል፡፡

በቆንጂት ተሾመ

የሥነ-ጽሑፍ ሚና ለአገር እና ለሕዝብ ፅናት



30

ሥነ-ጽሑፍ በዚህ ዘመን ላይ ዕድለኛ ናት እላለሁ፡፡ ይኼ ትውልድም ዕድለኛ ነው እላለሁ፡፡ ምክንያቱም አሁን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች የተሻለ የህትመት ብርሃንን ማየት የሚችሉበት ዘመን ነው፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች የሳንሱር መሰናክል ሳይገጥማቸው በቀላሉና በፍጥነት አንባቢያን ጋር መድረስም ይችላሉና!

ግን ደግሞ ሥነ-ጽሑፍ የህትመት ብርሃንን ለመመልከት ከፍ ያለ ዕድል ያገኘችበት ዘመን ቢሆንም፤ ሚናዋ እና ፋይዳዋ ዝቅ ብሎ የተገኘበትም ነው፡፡ ጸሐፍት ምናባቸውንና እሳቤያቸውን ሊያሰፉ የሚችሉበት ዘመን ላይ ተገኝተን ጥበባዊ ውበትን እና ጥራትም የተላበሱ ስራዎች ነጥረው አለመውጣታቸው ያስገርማል፡፡ አገር ተሻግረው ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለመድረስና ተጽዕኖ ለመፍጠር አለመቻላቸው ‘ምነዋ?’ ያሰኛል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን አገር በፈተናዎች እንዳትናጥ፤ ሕዝቦቿም በድንቁርናና በረሃብ እንዲሁም በስደት እንዳይቸገሩ የሚያስችሉ ኅብረተሰብ አናጺ፤ የተሻለ ስልጣኔ ፈጣሪ እና ለውጥ አመላካች የሥነ- ጽሑፍ ስራዎች አለመኖራቸው ያሳዝናል፡፡

በእኔ ዘመን ሥነ-ጽሑፍ የመሪነት ሚናዋን እና ኅብረተሰብን በተሻለ አስተሳሰብ የማነጽ ጉልበቷን አጥታ የሌሎች ታዛዥ እና ተከታይ መሆኗን እታዘባለሁ፡፡ የተባለውን ማስተጋባት ወይም የምናውቀውን ችግር አጉልቶ በመንቀስ አንዳንዴም አጋኖ በማቅረብ ኪናዊ ጉልበትን ያጡ ስራዎች በእርግጥ በዝተዋል፡፡ ይኼ ደግሞ የደካማ ሥነ-ጽሑፍ መገለጫ ነው፡፡

አሁን እንደ ኢትዮጵያ ያለች አገርና ሕዝቧ የሥነ-ጽሑፍን ታላቅ ጥበባዊ ኃይል ይፈልጋሉ፡፡ ሕዝብን የሚያነቁ፤ አገርን የሚያጸኑ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች በብዛት ሊኖሩ ይገባል፡፡

“መጀመሪያ ሥነ-ጽሑፍ ራሷ መች ጸንታ ቆመችና ነው አገር ለማጽናት፣ ሕዝብን ለማበርታት የምትችለው?” ሲል ሐሳቡን በጥያቄ የሚገልጸው በሥነ-ጽሑፍ ስሙ ቡርሀን አዲስ ተብሎ የሚታወቀው ደራሲና ሐያሲ መሐመድ አሊ ነው፡፡

“እውነት እንነጋገር ከተባለም በዚህ ዘመን ሥነ-ጽሑፍ የማታስፈልግ እስክትመስል ድረስ ዋጋዋ ተዘንግቷል” ሲልም በቁጭት ይናገራል፡፡ ወረቀትና እስክሪብቶ የጨበጠ ሁሉ ጸሐፊ የሆነ እስኪመስል ድረስ ብዙ መጽሐፎች የታተሙ ቢሆንም፤ ሥነ-ጽሑፋዊ ፋይዳቸው ሲመዘን ግን ብዙ እንዳልሆነ ታዝቧል፡፡

በእርግጥም በዚህ ዘመን ሥነ-ጽሑፍ የገዥነቷ ኃይል . . . የማራኪነቷ ባህሪይ . . . እጅጉን አንሶ ተገኝቷል፡፡

ቡርሀን እንዲህም ያስባል፡፡ “ምንም እንኳን የሥነ-ጽሑፍ ውጤቶች በዓይነትም ሆነ በብዛት ዛሬ ላይ ከቀደመው ዘመን ቢልቁም፤ አንድ ደረጃውን የጠበቀ የሥነ-ጽሑፍ ውበትና ጥበብ የተገለጸበት ስራ ቢታተም ሁሉንም በልጦ ሊወጣና ሊያንጸባርቅ ይችል ነበር፡፡”

የቀደመው ዘመን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች የሆኑት እነ ፍቅር እስከ መቃብር… እነ ሰመመን… በዚህ ዘመንም እንደገና እየታተሙ መገኘታቸው፤ አንድም ይኼ ዘመን የሥነ- ጽሑፍ ኃይል አውጥቶ ባለማሳየቱ እንደሆነ ይስማማል፡፡

“የመሲኆች መንደር”፣ “የነብያት ታሪክ”፣ “ኢትዮጵያኖች ሶሐቦችና ሌሎችም አጫጭር ታሪኮች” እና “የዘር ካርድ” የተሰኙትን ጨምሮ ሌሎችም መጽሐፎችን ለንባብ ያበቃው ደራሲውና አሰላሳዩ ቡርሀን አዲስ፤ በእነ ሐዲስ ዓለምአየሁ እና በዓሉ ግርማ ዘመን የወጡ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎችን የሚልቁና ዘመን የሚሻገሩ ስራዎች በዚህ ዘመን ያለመኖራቸው ምክንያት በጥልቀት ሊፈተሽ እንደሚገባ ይመክራል፡፡

ከዚህ ዘመን ደራስያን የሚሰለፈው ደራሲ ተስፋዬ አለነ ግን ከቡርሀን በተቃራኒ ይኼ ዘመንም ድንቅ ጸሐፍትን ያየንበት፤ ድንቅ ስራዎችም የወጡበት መሆኑን ነው የሚረዳው፡፡ እንዲህም ይላል “እኔ በበኩሌ ይህ ትውልድም የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑ ነው የሚገባኝ፡፡ ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ እያልኩ ዘመኔን የምረግም አይደለሁም፡፡ ሁሉም ዘመን የራሱ የሆነ ጥሩም ድክመትም አለው”

“የመንጌ ውሽሚት”፣ “እንክልካይ” እና “የሚስት ምርቃት” በተሰኙት መጻሕፎቹ የሚታወቀው ወጣቱ ደራሲ ተስፋዬ፤ በዚህ ዘመንም እንደ በዕውቀቱ ስዩም ስራዎች ኤፍሬም

እንዳለ፤ የ”እያዩ ፈንገስ” ቴአትር ጸሐፊው በረከት በላይነህ ዓይነት ሳተና የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች መኖራቸውን አንዘንጋ ይላል፡፡

በእርግጥ አዳም ረታስ?! አለማየሁ ገላጋይስ!?

ብዙ ጸሐፍት አሉ፡፡ ብዙ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ታትመዋል፡፡ ግን ደግሞ ይኼ ዘመን የቀደመውን ያህል ወይም በበለጠ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ ስራዎችን ለማበርከት ስለምን ተሳነው?

የምግብ አዘገጃጀት፣ የውበት መጠበቂያ መንገዶች፣ ስለ ጦር ሜዳ ውሎዎች፣ የፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የእስር ቤትና የስደት ውሎዎችን የሚተርኩት ሁሉ ከሥነ-ጽሑፍ እንደማይመደቡ ቡርሀን ይናገራል፡፡ ለእርሱ የሥነ-ጸሑፍ ስራዎች ማለት ፈጠራዊ የጥበብ ስራዎች (Creative works) የተገለጸባቸው ብቻ ናቸው፡፡

አበረ አዳሙም “የታተመ ጽሑፍ ሁሉ… አሰሱም ገሰሱም… ሥነ-ጽሑፍ ሊባል አይችልም፡፡ የሥነ-ጽሑፍን ደረጃ የጠበቀ . . . የሥነ-ጽሑፍን መስፈርቶች በትክክል የሚያሟላውን ስራ ነጥለን እንለይ ብንል ጥቂቱ ነው ሚዛን የሚደፋው” በማለት ሀሳቡን ያጠናክረዋል። ።

ዮሐንስ አድማሱ እንደሚለው ሥነ-ጽሑፍ የሰው ሐሳብና

ኢትዮጵያዊነት መስፈርቱ፤ ነጻነት ነው ለአንድ ዜጋ፣

መንፈሳዊ ነው እሴቱ፤ የማይዳሽቅ ለስጋ፣

የማይገብር ለጠመንጃ፣ የማይተመን በዋጋ፣

መንፈሱን ቆርሶ ለመሸጥ ሳይኾን፤ እንደባንዳ መንጋ፡፡

ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን



31

ስሜት በኪነት ኃይል ግዘፍ ነስቶ፤ አካል ገዝቶ የሚታይበት ጥበብ ነው፡፡ ዓላማው ማስደሰት ነው፡፡ ይህንን ዓላማ የሚፈጽመው ደግሞ ሁሉን አቀፍ የሕይወት ሒስ በማቅረብ ነው፡፡ ዓላማውን ለመፈጸም ጥራትና ወጥነት እንዲኖረው ያስፈልጋል፡፡

“ሥነ-ጽሑፍን ሥነ-ጽሑፍ የሚያሰኘው የደራሲው የኪነት ኃይሉ፤ የማስተዋልና የማንጠር ስጦታው፣ ያስተዋለውንና ያነጠረውን ከሰው ልጅ እውነታ ጋራ በቋንቋ ኃይል አገናዝቦና አዋህዶ እነሆኝ ብሎ ሚያቀርብበት ልዩ ችሎታው ነው” ይላል።

ይህንን ድንቅ ትርጓሜ ይዘን የሥነ-ጽሑፍ ስራዎችን በተለይ በዘመናት ውስጥ የነበራቸውን መልክና አበርክቷቸውን እንመለከታለን፡፡

ሥነ-ጽሑፍ በዘመናት ውስጥ የ14ኛው ክፍለ ዘመን በተለይ የአማርኛ ቋንቋ ሥነ-ጽሑፍ ውልደት እንደነበር ይታመናል፡፡ በወቅቱ ለንጉሥ አምደ ጽዮን የተጻፉ የውዳሴ ግጥሞች የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሥነ-ጽሑፍ ውጤት ተብለው ይጠቀሳሉ፡፡ የግጥሞቹ ይዘትና ዓላማ ንጉሡን ማወደስና ማጀገን ላይ እንዲሁም የመሪነት ብቃትና አገርን ከጠላት የመጠበቅ ብቃት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን በአገር ግንባታ፣ ሕዝቦችን

በአንድነት በማስተሳሰርና ለስራ በማነቃቃት ረገድ ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ደራሲና ሐያሲ ደረጀ ገብሬ ይገልጻል፡፡

ግጥሙ ከግዕዙ ወደ አማርኛው ቋንቋ የተደረገን የሽግግር ሙከራ ሲያመለክት የአማርኛን ጽሑፋዊ ሥነ-ጽሑፍ መፈጠርን ያበሰረ እንደነበርም ይታመናል፡፡ አማርኛ ቋንቋ ሥነ-ጽሑፍ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከፍ ብሎ ለ200 ዓመታት ዘጭ ብሎ መቆየቱን ከዚያም በአጼ ቴዎድሮስ ጊዜ ልሳነ-ንጉሥ ሆኖ መቆየቱንም ይመሰክራል፡፡

የደብተራ ዘነብ “መጽሐፈ ስጋዊ ወ መንፈስ” መጽሐፍ አጫጭር መልዕክቶችና ሐሳቦችን የያዘ ቢሆንም፤ አገር ሕዝብ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሥነ-ምግባር፣ ስለ አገር መከላከያ አስፈላጊነት፣ ስለ ፍትህና ነጻ መንፈስ የሚያትቱ ናቸው፡፡

ፈላስፋው ዘርአያዕቆብ ዘመኑን የቀደመ እሳቤና ጥልቅ ፍልስፍና የነበረው ይህንንም በጽሑፍ በማስፈር ከሚጠቀሱ የኋለኛው ዘመን አሳቢዎች ቀዳሚው ነው፡፡ ዘርአያዕቆብ አገርና ሕዝብ በስልጣኔ እና በበለጸገ መንገድ የሚጓዙበትን፣ ከሌላው ዓለም አገሮች ጋር መፎካከርና መብለጥ የሚችሉበትን መንገዶች የሚያሳዩ ሐሳቦቹን ጽፏል፡፡ በእርግጥ ይኼ ሰው ኢትዮጵያዊ ነው ያሰኙትን

ሐሳቦች ለአገሩና ለሕዝቡ እነኾ ብሎ በጽሑፍ መስጠት የቻለ አሳቢ ነው፡፡

19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ግን ተክለሐዋርያት ተክለማርያም እና አፈወርቅ ገብረእየሱስ የተባሉት ጸሐፍት ለአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ ማንሰራራት ትልቅ ድርሻ የነበራቸውን ስራዎች አምርተዋል፡፡ በተለይም ከኢጣሊያ ወረራ በፊት የጻፉት እንደሆነ የሚነገረውና ከወረራው በኋላ ለእይታ የበቃው “አፋጀሽኝ” የተሰኘው ቴአትር የትንቢት ያህል ዘመንን ቀድሞ በመመልከት የአገሪቷን ሁኔታ ያሳየ ነበር ተብሎለታል፡፡

የእርሳቸው ጽሑፎች ሐይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ቢያተኩሩም የዘመኑን እሳቤና ፍልስፍና የሚያሳዩ ነጸብራቆች ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ተጠቃሽ የሆነው “የጉለሌው ሰካራም” አጭር ልብ ወለድ የሞራል ጉዳይ ላይ ያተኮረ፣ ማኅበረሰብን ለአንድ ዓላማ የሚያሰልፍ፣ የአገርና የነጻነት፤ የፍትህ ትርጉም እንዲገባው የሚያደርግ ነው፡፡

በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት እስከ አብዮቱ መባቻና ማግስት ድረስ ባሉት ዘመናትም ወርቃማ የሚባሉ የድርሰት ስራዎች ቀርበዋል፡፡ ብዙዎቹም ሕዝብ እና አገርን በመልካም ስብዕና ማነጽን ዓላማ ያደረጉ ነበሩ፡፡

ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው አርሙኝ፣ ዓለም ወረተኛ፣ ጣይቱ ብጡል፣ አልሞትም ብዬ አልዋሽም፣ ጊዜና ሰው፣ የሕልም ሩጫ የተሰኙ ስራዎችን አቅርበዋል፡ ፡ ቴክኒኩን ትተን (ሥነ-ጽሑፍ በየዘመኑ የተለያየ ቴክኒክ የሚንጸባረቅበት የጥበብ ዘርፍ ስለሆነ) እነዚህ አይነት ስራዎች የያዙትን ጭብጥ ብንመለከት የአገር ፍቅርን የሚሰብኩ፣ ስለ ሕዝቦች አንድነት የሚናገሩ፣ አገርን ከጠላት ስለ መጠበቅ የሚመክሩ ናቸው፡፡

የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደሥላሴ “ወዳጄ ልቤ” የተሰኘው ዘመን አይሽሬ መጽሐፍ ክርስቲያናዊ እና ሥነ-ምግባራዊ ምናባዊ ጉዞን የሚመለክት ነው፡፡ ጥበባዊነቱ አንድም በአዲስ የአጻጻፍ መንገድ መጻፉ፤ በሌላ በኩልም ለመልካም ስብዕና የሚሞርዱ ረቂቅ ሐሳቦችን ማንጸባረቁ ዛሬም ድረስ ከፍ ብሎ የሚገለጽ የሥነ-ጽሑፍ ስራ አድርጎታል፡፡

በዚያው ዘመን ከበደ ሚካኤል ለአገር ስልጣኔ ይጠቅም ዘንድ “ጃፓን እንደምን ሰለጠነች?” ን ጨምሮ ልጆችና ታዳጊዎች በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው የአገራቸውን ታሪክ አውቀውና አገራቸውን ወደው እንዲያድጉ “ታሪክና ምሳሌ” የተሰኙ መጽሐፎችን አቅርበዋል፡፡

የታሪክና ማኅበራዊ ነክ ስራዎች ደራሲና ጸሐፊ ተክለጻድቅ



32

መኩሪያም ለትውልድ የሚጠቅሙ የስነ-ጽሑፍ ስራዎችን አሳትመዋል፡፡

ወልደጊዮርጊስ ወልደዮሐንስ “የአባቶች ምክር”፣ “ብልጽግና በግብርና” እና “ስነ-ምግባር” የተሰኙ የሥነ- ግጥም ስራዎችንና መጣጥፎች በማበርከት ለትውልድ መልካም ስብዕና የብዕራቸውን ቀለም አቅርበዋል፡፡

ሐዲስ አለማየሁ ዛሬም ድረስ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ የገዘፈ ሚና በመጫወት የሚጠቀሰውን “ፍቅር እስከ መቃብር” ልብ ወለድን ጨምሮ አይረሴ ስራዎችን አበርክተዋል፡፡

ፍቅር እስከ መቃብር በእርግጥ የበዛብህን እና የሰብለ ወንጌልን የፍቅር ታሪክ የሚያሳይ ልብወለድ መጽሐፍ ብቻ አይደለም፡፡ በዘመኑ የነበረውን የማይገባ የመደብ ልዩነት፣ ኢ-ፍትሃዊ አስተዳደር እና ለውጥ አስፈላጊነትን ያሳያል፡፡ አገርና ሕዝብ የሚገባቸውን ዘመናዊ አኗኗር የሚጠቁምም ነው፡፡ ሕዝብን የሚያነቃ፣ ለተሻለ ለውጥ የሚያነሳሳና የመንግስትንም ኋላቀር አስተዳደር የሚነቅፍ ነው፡፡

የዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስ”ም ተመሳሳይ መልዕክት የሚያስተላልፍና የለውጥ ዓላማን ያነገበ እንደሆነ ደረጀ በላይነህ ይናገራል፡፡ “ የፊውዳል ሥርዓትን ይኮንናል፡፡ የአንባቢውን አዕምሮ የሚያሰላ፣ የሚያመራምርና የሚጠይቅ እንዲሆን የሚገፋፋ፣ ሕዝብ አገር በእኩልነት የምንኖርባት ናት? ብሎ እንዲጠይቅ የሚያደርግ… የገዥውን እና የታችኛውን መደብ ሰፊ ልዩነት የሚያሳይ ነው”

የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ “የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰው በደርጉ ጊዜ ይመስለኛል” የሚለው ደረጀ፤ የብርሃኑ ዘሪሁንን ማዕበል፤ የአብዮት ዋዜማ፣ መባቻ እና ማግስት የተሰኙ ድርሰቶችን ለማሳያነት ይጠቅሳል፡፡ ከሁሉም ግን “ማዕበል” ዛሬም ድረስ የአገራችን ችግር ሆኖ ለቀጠለው ውዝግብ እውነታውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይና ትክክለኛ ምላሽ የሚሰጥም መሆኑን ነው ያመለከተው፡፡ ስለ ወሎ ድርቅ… ስለ ገበሬዎች መፈናቀል… የመሳሰሉ ችግሮችን መንስኤ የሚያሳይ መሆኑን በመግለጽ አሁን በድጋሚ መነበብ ያለበት ድርሰት እንደሆነ ይመክራል፡፡

በግጥም የሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ እነ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን፣ ሰለሞን ደሬሳ፣ ሰይፉ መታፈሪያ ፍሬው፣ ገብረክርስቶስ ደስታ እና ደበበ ሰይፉ ዘመን የሥነ-ጽሑፍ ታላቅ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የታየባቸው ስራዎችን በማበርከት ይወሳሉ፡፡

“የአክሱም ጫፍ አቁማዳ” የተሰኘው የደበበ ሰይፉ ግጥም፤ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ እስከ ጫፍ የማንለያይባቸው የተጋመድንባቸው ህያው እውነቶችን ያሳያል፡፡

የጸጋዬ ገብረመድህን ብዙዎቹ ግጥሞች ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ሕዝቦችን ልዩና ድንቅ

ባህልና እሴት ከፍ አድርገው የሚገልጹ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የሚያጸኑ ሐሳቦችን የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡ “ኢትዮጵያዊነት” በተሰኘው ግጥሙ ውስጥም ጸጋዬ የኢትዮጵያዊነትን ልክ ለመግለጽ ሞክሯል፡፡ ከግጥሙ ጥቂት ስንኞችን ብንመዝ ዛሬ ላይም ትርጉም የሚሰጥ ነው፡፡

ኢትዮጵያዊነት መስፈርቱ፤ ነጻነት ነው

ለአንድ ዜጋ፣

መንፈሳዊ ነው እሴቱ፤ የማይዳሽቅ ለስጋ፣

የማይገብር ለጠመንጃ፣ የማይተመን በዋጋ፣

መንፈሱን ቆርሶ ለመሸጥ ሳይኾን፤ እንደባንዳ መንጋ፡፡

የኢትዮጵያዊነት ፈተና ለመሆን የሚሞክረው ጎሰኝነት የሚያንገዳግድ ጤናማ ያልሆነ መንገድ መሆኑን፣ ኢትዮጵያዊነት ትክክለኛው መፍትሔነቱን ለማስረዳት ተግቷል፡፡

ይኼ በቁም ተደናብሮ፤ በመገነጣጠል ሮሮ፣

ጤና እንደሌለው አዕምሮ፣ በጎሰኝነት ተሳክሮ፣

ወደ ሲኦል መሽቀዳደም፤ በዘር ጥላቻ ታውሮ፣

ኢትዮጵያዊነት አይደለም!..

በእርግጥ ብሔርተኞች ወይም ጎሰኞች በየዘመኑ እየተነሱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጠልሸት ቢሞክሩም በስተመጨረሻ ግን ኢትዮጵያ አሸንፋ ማብራቷ እንደማይቀር ነው የጻፈው፡፡ ይህ ዛሬም ከፍ ብሎ ለዚህ ትውልድ ልናስተጋባው የሚገባ ሐቅ ነው፡፡

በነቀዝተኞች ብትደቅም፤ በዘረኞች ብትዳሽቅም፣

በጎሰኞች ብትቆሽሽም፤ በመናፍቃን ብታድፍም፣

ኢትዮጵያ የፀሐይ ምኩራብ፤ የአዲስ ትውልድ ብሩህ ሕልም፣

አውዳሚዎቿን አውድማ፤ ትነሳለች እንጂ አትሞትም!

… ኢትዮጵያ የካም ግንድ እናት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ገዳም፣

ያጠፋትን እያጠፋች፤ ታበራለች እንጂ አትጠፋም!

በሕዝቦች መካከል ያለው ልዩነት ጎልቶ እንዲታይ በተደረገባቸው ባለፉት ከሰላሳ የሚልቁ ዓመታት እንኳ

ሥነ-ጽሑፍ አብዛኛውን ጊዜ አንድነትን የሚሹ፣ የሕዝብን ልዩነት እንደማይጠቅም የሚገልጹ ስራዎች በብዛት ማስተዋሉን ደረጀ በላይነህ ይናገራል፡፡ “ሥነ-ጽሑፍ ጊዜውን ይመስላል” ይለናል፡፡

አሁን በህልውና ዘመቻ ላይ እንኳ ሥነ-ጽሑፍ ሕዝብን ከዳር እስከ ዳር ለአንድ ዓላማ በማሰለፍ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቷንም ይገልጻል፡፡ ደረጀ ሥነ-ጽሑፍ ሁሌም ቢሆን ለአገርና ለሕዝብ ወገንተኛነቷን ማሳየቷን ነው የሚረዳው፡ ፡ በአጠቃላይም ሥነ-ጽሑፍ መጠኑ እንደየዘመኑ እሳቤና ፍልስፍና የተለያየ ቢሆንም ለአገርና ለሕዝብ የማገልገል ሚናዋን ሳትሰስት መስጠቷን ያምናል፡፡

ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር ሱራፌል ወንድሙ ደግሞ ከዚህ በተቃራኒው ሥነ-ጽሑፍ ለአገርና ለሕዝብ የሚገባትን ግልጋሎት እንዳልሰጠችና የሚጠበቅባትን የመሪነት ሚና እንዳልተወጣች ነው የሚገልጸው፡፡ ይልቁንም ለገዥ መንግስታት እና ለመሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ርዕዮተ ዓለም ተገዥ ሆና ማገልገሏን ነው የተመለከተው፡፡ ለማሳያነትም የአብዮቱ ማግስት የቴአትር ድርሰቶችን ይጠቅሳል፡፡ ብዙዎቹም የመንግስትን የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ሕዝብ ላይ ለመጫን ተብሎ ይሰሩ እንደነበር ይገልጻል፡፡

“በኢትዮጵያ ቴአትር ከ”እናት አለም ጠኑ” ቀጥሎ የነበሩ ቴአትሮች አብዮታዊውን ለውጥ የሚያወድሱና ሕዝብን የሚቀሰቅሱ ወይም የፊውዳሉን ሥርዓት መበስበስ የሚያመለክቱ ነበሩ፡፡ የጸጋዬ ገብረመድህን “አጽማነ ፈለጉ” (1966) የተስፋዬ ገሰሰ “ትግላችን” (1969) የመንግስቱ ለማ ትርጉም “ጠያቂ” (1969) የጸጋዬ ገብረመድህን “የአቡጊዳ ቀይሶ” (1969) የአያልነህ ሙላት “ሻጥር በየፈርጁ” (1970) እና “በቀይ ካባ ስውር ደባ” (1970) ናቸው፡፡”

በእርግጥ እነዚህ የድህረ አብዮቱ ቴአትሮች የገዥው መንግስት ርዕዮተ ዓለም ማንጸባረቂያ ወይም የቅሰቀሳ ዓላማን ያነገቡ የመሆናቸው ምክንያት በጸሐፍቱ በጎ ፈቃድ የተሰሩ ናቸው ወይ ብለን እንድንጠይቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም ዘመኑ ከመንግስት ፈቃድ ውጭ የሆኑ ጥበባዊ ስራዎች በሳንሱር የሚመቱበት ነበርና! ዶ/ር ሱራፌልም ይመልሳል፡፡

“በእርግጥ ቴአትር ቤቶች ሁሉ አብዮቱን የሚደግፉ ስራዎችን ብቻ እንዲያስተናግዱ የሚያስገድድ ደብዳቤ ይደርሳቸው ነበር፡፡ ግን ደግሞ እንደ መንግስቱ ለማ ያሉ ጸሐፊዎች “ለአረንጓዴው ምርት ዘመቻ አረንጓዴ ቴአትር አንጽፍም” ሲሉ አቋም ይዘው ተገኝተው ነበር”

በፈቃደኝነትም ይሁን በግዳጅ የተሰሩ የወቅቱ የቴአትር ስራዎች ላይ በስፋት የታየው “ጥልቅ የሥነ-ጽሑፍ ውጤት ሳይሆን የቅስቀሳ ስራ ነበር” ሲል ይደመድማል፡፡ “ይኼ ደግሞ የሥነ-ጽሑፍን ወይም የኪነ-ጥበብን የመሪነት ኃይል ለመጠቀም ካለመድፈር ወይም ዋጋ ለመክፈል



33

ካለመዘጋጀት የሚመጣ ነው”

ይህ የእኔ ዘመን ታዲያ እንደቀደመው የግዳጅ ትዕዛዝ ሳይደርሰው ጥልቀት ያለው የሥነ-ጽሑፍ ስራዎችን አለማምረቱ ለምን ይሆን?

የሂስ አብዮት ለሥነ-ጽሑፍ ዕድገት ብዙዎች ሥነ-ጽሑፍ የሚገባትን ሚና መጫወት እንድትችል ከተፈለገ የሂስ ባሕል ስር መያዝ እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ በእርግጥ የሂስ ባሕላችን የዳበረ አለመሆኑ እሙን ነው፡፡ በአብዛኛው ስለ ሂስ ያለው ግንዛቤ የተንሻፈፈ ነው፡፡ ሂስ አንድን ጸሐፊ ወይንም ጽሑፍ ለመጣል ወይም ከፍ ለማድረግ የሚጠቀሙበት መሳሪያ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡ ይህ አስተሳሰብ መስተካከል ይኖርበታል፡፡

ደራሲና ገጣሚ አበረ አዳሙ ስለ ሒሂ አስፈላጊነት ሲናገር፤ አስቀድሞ የአያልነህ ሙላትን ገለጻ በመዋስ የሂስን ትርጓሜ እንድንረዳው ይሻል፡፡ “ሂስ ወይም ሃያሲ ማለት ወተት ውስጥ የተጨመረን መርዝ ለይቶ እንደማውጣት ያህል ረቂቅ ጥበብ ነው።”

አበረ እንዲህ ሲልም ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡

“ሂስ አንድን የሥነ-ጽሑፍ ስራ ውበቱ ከምን አንጻር እንደሆነ ይፈትሻል፡፡ የቋንቋውን ጥልቀት፣ የሤራውን ውስብስብነት፣ ወኪል ባለታሪኮቹ የተገነቡበትን ስብዕና እና ተልዕኳቸውን ይመዝናል፡፡ ሥነ-ጽሑፉ ምን ዓላማ ይዞ እንደተነሳ ከመግለጽ ባሻገር ጭብጡ የጽሑፉን ዓላማ ማሳካት የሚችል ስለመሆኑ ይመረምራል፡፡”

የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ አገርና ሕዝብን ወደፊት በማራመድና በማበልጸግ ሒደት ውስጥ ድርሻውን እንዲወጣ፤ ደግሞም የላቀ ጥበባዊ ፋይዳው ከአገር አልፎ ዓለም አቀፋዊ እንዲሆን ጠንካራ የሂስ ባሕል ሊኖረን እንደሚገባ ያስማማናል፡፡

ሂስ ከጥንትም ጀምሮ በቅኔ ቤት የተለመደ ነው፡፡ የቅኔ ተማሪ በጥበቡ የሚያብበውና ከፍ ያለ ችሎታን የሚጎናጸፈው በሂስ ጥበብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተማሪውን ቅኔ ተማሪዎችና መምህሩ ጭምር አብጠርጥረው ይተቻሉ፡ ፡ ተማሪዎችም የመምህራኑን ቅኔ ይተቻሉ፡፡ ይህ መንገድ የነጠረ ቅኔ እንዲወጣ እንደሚያደረግ ያውቃሉና ቅሬታ የሚሰማው ወገን የለም፡፡ ይሄ ባሕል በሥነ-ጽሑፍ ስራዎቻችን ሂስ ላይም መለመድ አለበት፡፡ ሂስ ቢለመድ ጥራት ያላቸው ስራዎች ነጥረው ሊወጡ ይችላሉ፡፡

ደራሲና ተዋናይ እንዲሁም ገጣሚ ስዩም ተፈራ በቅርቡ “ድኆች” የተሰኘ የቴአትር ድርሰቱን በመጽሐፍ አቅርቧል፡ ፡ ድርሰቱ ከሃምሳ ዓመት በፊት የተጻፈ ቢሆንም የዚህ ዘመን ነጸብራቅ ነው፡፡ ግን ይህን ሁሉ ዓመት ለመቆየቱና በወቅቱ ለመድረክ ወይም ለህትመት ያለመብቃቱን

ምክንያት ሲናገር “መጀመሪያ ለኅብረተሰቡ የሚመጥን ስራ መሆኑ ላይ እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡ የሚረባ ነገር ነው ወይ? አዲስ ነገር አለው ወይ? ጥበብ አልጎደለውም ወይ? ለሚሉ ጥያቄዎች ልብ የሚሞላ ምላሽ ሳላገኝ በመቅረቴ ነው” ይላል፡፡

እርሱና መሰል የሙያ ጓደኞቹ በዘመናቸው አንድን የሥነ- ጽሑፍ ስራ ለአንባቢ ከማብቃታቸው በፊት እርስ በእርስ እየተቀባበሉ በማንበብ ጥሩና ጎዶሎውን የመለየት ልምድ ነበራቸው፡፡ እነ ስብሀት ገብረእግዚአብሔር ጭምር ያሉበት የንባብ ቡድን እንደነበራቸው በማስታወስ፤ “ጽሑፎቻችን ከመታተማቸው በፊት ነበር የምንተቻቸው፡ ፡ ይኼን የምናደርገው ደግሞ የማይረባና ትርጉም የሌለው ስራ ለአንባቢ ላለመስጠት ከመጠንቀቅ የመነጨ ነው” ይላል-ደራሲ ተዋናይና ገጣሚ ስዩም ተፈራ፡፡

አሁን አሁን ብዙ የሥነ-ጽሑፍ ውጤቶች ለህትመት መብቃታቸው መልካም ቢሆንም፤ የሂስ መድረኮች አለመኖራቸው የሥነ-ጽሑፍን እድገት ያቀጭጫል የሚል እምነት አለው፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ስራዎች ለህትመት ከመብቃታቸው በፊት መፈተሽ፤ ለህትመት ከዋሉም በኋላ በባለሙያ ሂስ ሊሰጥባቸው እንደሚገባ በአጽንኦት ይናገራል፡፡

አሁን ግን ጥያቄው ለመሆኑ የሂስ ባለሙያዎች አሉን ወይ? የሚለው ነው፡፡ አበረ አዳሙ “አሉ” ወይም “ፈጽሞ የሉም” ብሎ መደምደሚያ ለመስጠት ጥናት ይፈልጋል” ሲል ምላሹን ቢሰጥም፤ የዳበረ የሂስ ባሕል እንደሌለን ግን በእርግጠኝነት ይናገራል፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ዕድገት እንዲመጣ ከተፈለገ “የሂስ አብዮት ሊፈጠር ይገባል” የሚል እምነት አለው፡፡ አብዮቱን ለማቀጣጠል ግን ሂስን የተረዱ ትክክለኛ የሂስ ባለሙያዎች ሊኖሩ ይገባል፡፡

“ሒስ ለሥነ-ጽሑፍ ሕይወት መጠበቂያ ዓይነተኛ ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ ሂስ ጉድለትንም ጥራትንም መግለጫ ጥበብ ነው፡፡ ማስተማሪያም ነው፡፡ እንደ ስድብ እንደ ነውር መቆጠር የለበትም፡፡ በሂስ መስታወት ስጋውን የማይከላ ሥነ-ጽሑፍም ሆነ ደራሲ ከበድን አንድ ነው፡፡ ተገቢ ቦታውም ቤተ-መዘክር ነው” ሲል ዮሐንስ አድማሱ ከሃያ ዓመታት በፊት ጽፎ ነበር፡፡ በወቅቱ የሥነ-ጽሑፍ ጥራት ዝቅ ያለበት አንደኛው ምክንያትም በሂስ እና ሃያሲ እጦት እንደሆነ ነበር የገለጸው፡፡ ይህ በዚህ ዘመንም ቢሆን ተገልጦ የሚታይ እውነታ ነው፡፡

የዚህ ዘመን ደራሲው ቡርሀን አዲስ በበኩሉ “ሂስ አለ ብዬ አላምንም” ይላል፡፡ ግን ደግሞ ሥነ-ጽሑፋችን እንዲያድግና ሚናው እንዲጎለብት የሂስ ባህል ልንፈጥር እንደሚገባ ይስማማል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከደራሲያንና ከሃያሲያን ባሻገር የመገናኛ ብዙሃንን ጉልህ ሚና ያስታውሳል፡፡ “የመገናኛ ብዙሃን የሂስ መድረኮች ከአዳራሽ እንዲወጡና ወደ ሰፊው ኅብረተሰብ እንዲደርሱ በማድረግ ሊሰሩ ይገባል።”

የደራስያን ማኅበሩ የቤት ስራ የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍ ዕድገት የማሳካት ዓላማን ያነገበው የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር ሃያሲያን የማፍራት ኃላፊነት አለበት፡፡ ይሁንና መጽሐፍ ያሳተመ ሁሉ በደራሲነት በሚጠራበት ዘመን ላይ ሃያሲያን በብዛትም በጥራትም እንዲኖሩ ወይም የሂስ ባሕል እንዲለመድ በማድረግ ረገድ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት አልተወጣም፡ ፡ ይህንን የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አበረ አዳሙም የሚስማማበት ሐቅ ነው፡፡

“እውነት ነው የሂስ ባሕል እንዲዳብር ጥቂት ሞከርን እንጂ ብዙ አልገፋንበትም፡፡ ቀደም ሲል አንድ ጊዜ አንድ መጽሐፍ ላይ ሂስ በማዘጋጀት ሂስን ለማሳየት ሞክረን ነበር፡ ፡ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ብንፈልግም አጋዦች ባለማግኘታችን ገፍተን አልሔድንበትም፡፡ የስብሰባ አዳራሾችን ለማግኘት፣ እንግዶች ለመጥራትና ለማስተናገድ የሚያስፈልገው የገንዘብ ወጪ ፈተና ሆኖብናል፡፡”

ከማኅበሩ አባላት በየወሩ ከሚሰበሰብ 15 ብር የሠራተኛ ደመወዝ ከመሸፈን ያለፈ ምንም የሚጠቅም ገቢ እንደሌለው በመጥቀስ፤ ገንዘብ ዋንኛ ችግር መሆኑን ነው የደራስያን ማኅበሩ መሪ አበረ አዳሙ የሚገልጸው፡፡ የደጋፊ አካላት እገዛ ካልተደረገ ማኅበሩ ለሥነ-ጽሑፍ ዕድገት ሊሰራቸው የሚገቡ ስራዎችን በተገቢው ሁኔታ ለመከወን አዳጋች እንደሆነባውቸውም ጭምር፡፡

በስማቸውም ሆነ በስራቸው ገንዘብ ሊያስገኙ የሚችሉ አባላትን በውስጡ የያዘው የደራስያን ማኅበሩ ግለሰቦች ታዳሚዎችን በክፍያ በማስተናገድ የጥበብ ድግሶችን በሚያሰናዱበትና በሚያተርፉበት ዘመን የተሻለ ገቢ እና የገቢ ምንጭ መንገዶችን ለመፍጠር መስራት ይጠበቅታል፡ ፡ ከዚህ ቀደም ወደተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጉዞ ሲያደርግ ከፍተኛ የሚባል የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ የቻለበት ልምድ ላለው ለዚህ ማኅበር በጠባብ አዳራሽ የሂስ መድረኮችን ለማዘጋጀት የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ይቸገራል ብሎ ማመን ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ይከብዳል፡፡

በሌላ በኩል አሁን አሁን በአዲስ አበባ እየተለመደ ያለው በመጽሐፎች ላይ በመደበኛነት ውይይቶችን የማድረግ ልምድ ወደ ሂስ ባሕል ቢለወጥ መልካም ነው፡፡ በግርድፉ የሚሰሩ የመጽሐፍ ዳሰሳዎችም ወደ ጠንካራ የሂስ መንገዶች መለወጥ አለባቸው፡፡

አንባቢውም አዳዲስ መጽሐፍትን በማስተዋወቅ በተለያየ መንገድ የሚሳተፍበትን የማሻሻጥ ተግባሩን፤ አንብቦ በመመዘን ሐሳቡን ወደ መግለጽ ቢለወጥ ለሥነ-ጽሑፍ ዕድገት የበኩሉን ውለታ እንደዋለ ይቆጠራል፡፡



34

የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ጉዞ

የሃረማያ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ



35

የዩኒቨርሲቲው የልህቀት ጉዞ

ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ 509 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዘን ያገኘነው ቅጥር ግቢ ዓይንን ይማርካል፤ ነፋሻማ አየሩ መንፈስን ያድሳል። በአረንጓዴ በተሸፈነው ምድር ላይ የታነጹት ሕንጻዎች ለግቢው ውበት ሆነዋል። በዚህ ውበት ውስጥ ለስለስ ብሎ የሚነፍሰው ንፋስ የጥሞና ጊዜ ለመውሰድ ይጋብዛል። በጸጥታ ውስጥ ራስን መፈለጊያ፣ መመራመሪያ አዲስ ነገር ማንጸሪያ ሆኖ ይታያል። መንፈስን ያነቃቃል - ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ።

በዩኒቨርሲቲው ግቢ ስንዘዋወር የተመለከትነው የአትክልት፣ የሰብል እና የእንስሳት ምርጥ ዘር ለማግኘትና ለአርሶ አደሩ የተሻለ ዝርያ ለማቅረብ እየተከናወኑ ያሉ በርካታ የምርምር ስራዎች መኖራቸውን ነው። በቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ኃይለሥላሴ ለግብርና ኮሌጅ ማቋቋሚያ የተመረጠውና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተቀበላቸው 11 ተማሪዎች ትምህርት መስጠት የጀመረው የዚያን ጊዘው “የግብርና ኮሌጅ” የአሁኑ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለምርምር ምቹ ስለመሆኑ ዓይን አይቶ ልብ ይመሰክራል።

ለተማሪዎቹ ንድፈ ሃሳብን ከተግባር አጣምሮ ትምህርት የሚሰጠው ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ላለበት ደረጃ ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን፣ የስም ለውጦችን አድርጓል። ይህም ሆኖ በቅጥር ግቢውና በአካባቢው አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በማስተማር “ሀ” ያለውን ተግባር አሳድጎ ዛሬ ወደ ልህቀት ማዕከልነተ በግስጋሴ ላይ ይገኛል።

ጌታቸው ሠናይ



36

የአገሪቷን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን፣ በምርምርና ስርጸት ከፍ ለማድረግ ታልሞ የተቋቋመው የመጀመሪያው የግብርና ኮሌጅ ለዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት በአገር ደረጃ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የታሪክ ድርሳናት ምስክሩ ናቸው። የያኔው ኮሌጅ በተቋቋመበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የ “ደብረ ዘይት ግብርና የምርምር ማዕከል”ን በማቋቋም የምርምር ስራዎችን ማከናወኑን አብነት መጥቀስ ይቻላል።

በኢትዮጵያና በአሜሪካ መንግስታት መካከል በነበረ ትብብር በኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መሪነት የተለያዩ የትምህርት ክፍሎችን በመክፈት የግብርና ልሂቃንን በማፍራት ዘርፉ በበቁ ምሁራን እንዲመራ የራሱን አዎንታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል። የእንስሳት እና የእፅዋት ሳይንስ፣ የግብርና ኢንጂነሪንግ፣ የግብርና ምጣኔ ሀብት እንዲሁም ሆም-ኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍሎች በማስተማርና በማስመረቅ ግብርናው ላይ የራሱን አሻራ አኑሯል፤ እያኖረም ቀጥሏል።

በአሁኑ ወቅት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለምርምር የትምህርት ተቋምነት ከተለዩት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው። ዩኒቨርሲቲው ለዓመታት ያካበተው ልምድ፣ አሁን ያለው አቋምና ብቃት ለዚህ ደረጃ እንዳበቃው ግልጽ ነው።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንግሥቱ ኡርጌ እንደሚሉት፤

በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ልየታ ዩኒቨርሲቲው የምርምር ስራዎች ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ተመርጧል።

በአገራችን የሚገኙት 45 ዩኒቨርሲቲዎች በሦስት ተለይተዋል። ይህ ልየታ ዩኒቨርሲቲዎቹ በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ዕድል የከፈተ ነው። ለመማር ማስተማር ተግባራት፣ የምርምርና የማኅበረሰብ ለውጥ ስራዎችን ለማሳለጥም ሰፊ ዕድል ይሰጣል።

እንደ ፕሮፌሰር መንግስቱ ገለጻ፤ በምርምር ከተለዩት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አንደኛው ነው። የልየታው መሰረታዊ መስፈርት የዩኒቨርሲቲዎች ዕድሜ፣ በዕድሜያቸው ያከናወኗቸው የምርምር፣ የመማር ማስተማር ስራዎች፣ ያስመረቋቸው ተማሪዎች ቁጥር፣ ያወጧቸው ሳይንሳዊ ጽሑፎች ከግምት ውስጥ ተካተዋል።

ለአብነት ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 10 ዓመታት ከሁለት ሺህ በላይ የምርምርና ጥናት ውጤቶችን በማሳተም ለተደራሲያን እንዲደርስ አድርጓል። እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ2021 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ በሆኑ የምርምር ጆርናሎች ላይ ከ400 በላይ የምርመር ስራዎቹ ታትመው ለንባብ በቅተዋል። የእነዚህ የምርምር ውጤቶቹ ለንባብ መብቃት ዩኒቨርሲቲውን በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር አድርገውታል።

“ስምንቱም ዩኒቨርሲቲዎች አሁን መቶ በመቶ የምርምር ዩኒቨርሲቲ የሚያሰኝ አቅም አላቸው ማለት አይደለም። ግን መሰረቱን ጥለዋል በአጭር ጊዜ ውስጥ መሆን የሚያስፈልጋቸውን መስፈርት ያሟላሉ በሚል ይህ የምርምር ተቋምነት ስም ተሰጥቶናል” በማለት ነው ፕሮፌሰር መንግሥቱ የገለጹት።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለዓመታት ያካበተው ልምድ ለምርምር ከሚሰጠው ትኩረት አኳያ አገሪቷ እደርስበታለሁ በማለት ለሰነቀችው የብልጽግና መዳረሻ ዋነኛ ተዋናይ መሆኑ አይቀሬ ነው። በተለይም በእንስሳት ሐብትና ተዋጽኦ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በሠብል ዓይነትና በምርት ሰጪነት ሰፊ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ምርጥ ዘር በማውጣት የአገሪቷን አርሶ እና አርብቶ አደሮች ጥያቄ ለመመለስ የጀመረውን ጉዞ በላቀ የምርምር ጥበብ ምላሽ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የኒቨርሲቲው የረጅም ዘመን የካበተ ልምድ እና ታታሪ መምህራንና ሠራተኞቹ የልህቀት ተምሣሌት ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ የሚያጋጥሙትን መሰናክሎችና ተግዳሮቶች በስኬት እንደሚወጣ መተማመኛ አቅም ይሆኑታል።

በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የልየታ መስክ ዩኒቨርሲቲዎቹ መስራት ያለባቸውን ሁሉ እንዲያከናውኑ አቅጣጫ ተቀምጧል። ከዚህ በመነሳት ሐረማያ



37

ዩኒቨርሲቲ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት የት መድረስ እንዳለበት የሚያሳይ ዕቅድ አዘጋጅቷል።

“ይህ ዓመት የዝግጅት ጊዜ ነው። መሰራት ያለባቸውን ኮሚቴ አቋቁመን አስጠንተን ዩኒቨርሲቲያችን ምን ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት አለበት? በምን ወደኋላ ቀርተናል? በምን ቀድመናል፤ በቀደምናቸው እንዴት እየተጠናከርን እንሄዳለን? ወደኋላ በቀረንባቸው እንዴት መፍጠን እንችላለን? የሚሉትን ምላሽ የሚሰጥ ስራ ተሰርቷል። በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ጥናት እያስጠናን እየሰራን ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር መንግስቱ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መሰረት ያደረገው የግብርናው ዘርፍ ለዓመታት በውጣ ውረድ ውስጥ ያለፈ በመሆኑ በሚፈለገው መጠን ለመለወጥና ለማደግ ባይታደልም በውስጡ ለታዩት ለውጦች ግን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ገናና የሆኑ ምሁራንን በማፍራት ግንባር ቀደም መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ታሪክ ይመሰክራል።

ዩኒቨርሲቲው የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የኮምፒውቲንግና ኢንፎርማቲክስ፣ ጤናና ሕክምና ሳይንስ፣ የሕግ፣ የኅብረተሰብና ሥነ- ሰብ፣ የእንስሳት ሕክምና ሳይንስ ኮሌጆች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትና የስፖርት አካዳሚ በመክፈት

በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ በማስተማር ለምረቃ በማብቃት ላይ ይገኛል። በዚህም ብቁ ምሁራን በማፍራት የበኩሉን አሻራ በማሳረፍ እየገሰገሰ ነው። በአሁኑ ወቅት በምርምር ዩኒቨርሲቲነት ሲመረጥ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው።

አንደኛው የመማር ማስተማር ነው። የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ዓመትና ከሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ትምህርትን እየቀነሱ የድህረ ምረቃ እና የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርቶችን መስጠት ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም ሶስተኛ ዲግሪያቸውን የጨረሱ ከየትኛውም ዓለም የሚመጡ ተማሪዎች ምርምር የሚሰሩባቸው አካሄዶች ተግባራዊ ይሆናሉ። ይሄ ዲግሪ አይደለም ግን ከዶክትሬት ከፍ ያለ “ፖስት-ዶክተሬት ተሳትፎ እውቅና” ይሰጣል። እነዚህ ዩኒቨርሲቲውን በምርምርና በማስተማርም እንዲልቅ የሚያደርጉ በመሆናቸው በእነዚህ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ነው የተመለከተው። “የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብሮችን እየቀነስን እንሄዳለን የሁለተኛ ዲግሪ፣ የሶስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮችና ሌሎች ተጓዳኝ ፖስት-ዶክትሬት ተሳትፎ እያሳደግን እንሄዳለን” በማለት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ፕሮፌሰር መንግስቱ የገለጹት።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በርቀትና በክረምት 228 የሚደርሱ መርሃ ግብሮች ይሰጣል።

አሁን ከደረሰበት ደረጃ አኳያ ለምርምርና ለድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትኩረት እንደሚሰጥ ነው መረጃዎቹ የሚያረጋግጡት።

ለዚህም ዩኒቨርሲቲው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ አዘጋጅቶ በስራ እየተረጎመ ይገኛል። ይህን ተግባራዊ የሚያደርገው ዩኒቨርሲቲው ትኩረት የሚያደርግባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች ምንድን ናቸው?

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንደ ምርምር ዩኒቨርሲቲነቱ በሰው ኃይል ረገድ ከአምስት እስከ አስር ዓመት ባሉ ጊዜያት ውስጥ ሃምሳ በመቶዎቹ የሶስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ያላቸው፣ ሃምሳ በመቶ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ መምህራንን መፍጠር እንዳለበት ያምናል።

“አሁን ባለንበት ደረጃ ከሃምሳ በመቶ የራቅን ነን። አሁን ያለው የመምህራን ጥምርታ በዲግሪ ደረጃ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የያዙ መምህራን ከ15 በመቶ አይበልጡም። ሁለተኛ ዲግሪ የያዙት ወደ 60 በመቶ ሲሆኑ፤ የተቀሩት የመጀመሪያ ዲግሪ የያዙ ወጣቶች ናቸው። ይህን ሚዛን ማስጠበቅ አለብን። እዚህ ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል። የሰው አቅምን የማሳደግ ስራም እንሰራለን” ብለዋል።

እንደ ፕሮፌሰር መንግስቱ ገለጻ፤ የምርምር ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ላይ ነው ትኩረት አድርጎ



38

የሚሰራው፤ ትምህርቱም ጥናት ተኮር ነው። የምርምር አቅምን ማሳደግ ሁለተኛው የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል ማለት ነው። በሰው ኃይል የሶስተኛ ዲግሪ ያላቸው ብዛት ይጨምራል። የምርምር አቅምም ያድጋል።

“የቤተ ሙከራ ግብዓት ያስፈልጋል። ቤተ ሙከራዎቻችን እስካሁን ለምንሰራቸው ስራዎች ጥሩ ናቸው። ወደ ምርምር ዩኒቨርሲቲነት ስንሸጋገር አሁን ያለው የቤተ ሙከራ አቅም በጣም ማደግ አለበት፤ እጅግ በጣም የዘመነ መሆን አለበት፤ ቤተ ሙከራዎቻችንን ለይተን አንዳንዶቹን የዘመነ ቤተ-ሙከራ የማድረግ ስራዎችን ጀምረናል፤ እየሰራን ነው። በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት አድርገን እንሰራለን። ብቃት ያላቸው ችግር ፈቺ ምርምሮች ላይ አትኩረን እንሰራለን። የተለያዩ ምርምሮችን የሚያካሂዱ ተማሪዎችን ነው የምንቀበለው። ችሎታቸው ከፍ ያለ ተማሪዎች ስለሆኑ የሚመጡት የተሻለ የምርምር ስራ ያከናውናሉ ብለን እንገምታለን። ለዚህም ግብዓት የሚሆን በቂ የቤተ-ሙከራ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ይጠይቃል። ለአብነት ኢንተርኔትን የመሳሰሉ፣ ቤተ ሙከራዎችን፣ የማስተማር ዘዴዎቻችንን የማዘመን በዚህ ውስጥ የሚጠቃለሉ ይሆናል” በማለት ፕሮፌሰር መንግስቱ የገለጹት ሃሳብ ዩኒቨርሲቲው ከፊቱ የሚጠብቁትን ተግባራት በብቃት ለመወጣት የሚያስችሉትን በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ መሆኑን ያመላክታል።

በዓለማችን ላይ አሁን ያለው ተሞክሮ በግልጽ የሚያሳየው ሰው ባለበት አካባቢ ሆኖ መማር እንዲችል ዕድል መስጠትን ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የመማር ማስተማርን ሂደት በድረ-ገጽ የመስጠት አዝማሚያ እየተስተዋለ መጥቷል። በሌላ በኩል ይህ አዲስ ሃሳብና ዕድል ቢሆንም ወጣት ተመራማሪዎች በተመራማሪነት ለመብቃት ገጽ-ለገጽ መማር እንዳለባቸው ይመከራል። ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይህን ሃሳብ እንዴት ያየዋል? የሚለውን ጥያቄ አነሳን።

“በእርግጥ ባሉበት ሆኖ መማር የገጽ-ለገጽ ትምህርትን አይተካም። ግን በዩኒቨርሲቲው አንድ የትምህርት መስጫ መንገድ (ሞዳሊቲ) ይሆናል። ይህ መንገድ (ሞዳሊቲ) የሚፈጥረው ዕድል ለምሣሌ በአካል ተገኝተው መማር ለማይችሉና በስራ ላይ ለሚገኙ ሰዎች ለምሣሌ በግል ስራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች ዕድል የሚሰጥ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ለአራት ዓመታት ፊት ለፊት ተቀምጠው መማር የማይፈልጉ ሰዎች አጋጣሚውን ይጠቀማሉ። ቀደም ሲል እንደዚህ ዓይነቱ አሰራር አይፈቀድም ነበር አሁን ግን ክፍት ነው። ይህ አቅም ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ማስተማር እንዲችሉ ዕድሉ ተከፍቷል። መስፈርቶቹ ከተሟሉ አቅም ብቻ ነው የሚጠይቀው ትምህርቱን ኦንላይን ማስተማር

ይቻላል” ሲሉ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይህን ዕድል ሊከፍት እንደሚችል ነው ፕሮፌሰር መንግስቱ የጠቆሙት።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይህን አጋጣሚ ለመጠቀም መወሰኑን በተግባር እያረጋገጠ ነው። ለዚህም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማሟላት ላይ ይገኛል። ትምህርቱ በዲጂታል መሰረተ ልማት በኩል የሚሰጥ በመሆኑ የማስተማሪያ ቤተ-ሙከራ ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ትምህርቱን ለመስጠት በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣን ሕግ መነሻ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሕግ ማዕቀፎች እንዲኖሩት ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑም ነው።

“ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እንደዚህ ዓይነት የትምህርት አሰጣጥ ሞዳሊቲ ውስጥ ቢገባ ምን አይነት መርሆዎችን መከተል አለበት? በሚል የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖረው የአተገባበር መመሪያ እያዘጋጀን ነው። በሚቀጥሉት ዓመታት የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍነት ላይ በደንብ መስራት አለባቸው የሚል አቅጣጫም አለ። በተለይም የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም አቀፋዊነት ላይ ማለት የሰዎችን ተዟዙሮ መስራት (የሂዩማን ሞቢሊቲ)፣ የመምህራን፣ የተማሪዎች ልውውጥ ወደ ውጭ የሚሄዱበት የውጭ ተማሪዎች ወደ እኛ የሚመጡበት፤ ሌሎች በምርምርና በትምህርት ትብብር የምንፈጥርበት ሁኔታ ማለት ነው። እነዚህ ላይም በትኩረት እየሰራን ነው” ብለዋል።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ አመሰራረቱ በአሜሪካው ኦክሎሀማ ስቴት ዩኒቨርሲቲ መሪነት በመሆኑ ከሌሎች ጋር በአጋርነት መስራት አዲስ ጉዳይ አይሆንበትም። የምርምርና የድህረ ምረቃ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ደግሞ ከዓለም አቀፍ የኒቨርሲቲዎች፣ ከምርምር ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን የበለጠ አመቺ ይሆንለታል።

ይህ ተቋም የምርምር የኒቨርሲቲ እንዲሆን ከተለዩት መካከል መሆኑ በመሰረታዊነት ትኩረት የሚያደርግባቸውን አቅጣጫዎች እንዲመርጥ፤ ግብርናን ለማዘመን መቋቋሙና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአገር ደረጃ ከፍተኛ ልምድ ማካበቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በቀላሉ እንዲለይ እንደሚያስችለው እሙን ነው። ዩኒቨርሲቲው ትኩረቱን በምን ላይ ያደርጋል? ሌላው ጥያቄ ሆኖ ይነሳል።

ፕሮፌሰር መንግስቱ ለዚህ የሰጡት ምላሽ “የምርምር ዩኒቨርሲቲ ተብለን ከተሰየምን በኋላ በአራት ነገሮች ላይ ነው ትኩረት አድርገን የምንሰራው። አንደኛው ግብርና ነው። የተቋቋመውም እንደ ግብርና ኮሌጅ ነው።

ከየትኛውም ዩኒቨርሲቲ ጋር ሲወዳደር ግብርና ላይ ላቅ ያለ ልምድና አስተዋጽኦ አለው። የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ሲለዩ እኛ በመጀመሪያ የተለየነው በግብርና ነው። ስራችንም በዚያ ላይ ስለነበር በአንደኛ ደረጃ በግብርና ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን” የሚል ነው።

በግብርና ውስጥ እንስሳት እርባታ፣ እፅዋት፣ የግብርና ምጣኔ ኃብት (አግሪካልቸር ኢኮኖሚክስ)፣ የተፈጥሮ ሐብት ሌሎችም በርካታ የትምህርት መስኮች አሉ። ግብርናን በማዘመን ከፍ ያሉ ምርምሮችን መስራት፣ ስመ-ጥር ምሁራንን ማፍራትም በዩኒቨርሲቲው የኃላፊነት ጫንቃ ላይ ይወድቃሉ።

“ቀጣዩ በማኅበረሰብ እና ሠብዓዊነት ላይ አተኩረን የምንሰራው ነው። በሦስተኛ ደረጃ ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጃችን በዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ ከተመሰረተ 26ኛ ዓመቱ ነው። በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለ ነው። ልየታችንም የሚያሳየው ያንን ነው። ጤናና ሕክምና ዘርፍ ላይ በማስተማርም በምርምርም ትኩረት አድርገን ነው የምንሰራው። አራተኛው ደረጃ በሳይንስ ላይ ነው ማቴማቲክስ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ መሰረታዊ ሳይንስ የሚባሉት ላይ ትኩረት አድርገን እንሰራለን። ወደፊት ዩኒቨርሲቲው ሲያቅድም ግብዓቶችንም ሲያሟላ እነዚህን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ነው” ሲሉም ያብራራሉ።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያሳድረውን በጎ ተጽዕኖ ይበልጥ በማስፋት ከጎረቤት አገራትም ጋር መስራት ጀምሯል። በሶማሌ፣ በጅቡቲና በሶማሌ ላንድ ስራዎች መጀመራቸው በቀጣይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ምስራቅ አፍሪካ ላይ መስራቱ ከአገራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትብብር በመፍጠር የትምህርት መስኮችን የማስፋት ፍላጎቱን ያሳያል። ይህን በተግባር ጀምሮታል። ሶማሌላንድ ውስጥ ከሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የተወሰኑ የትምህርት መርሃ ግብሮችን በማስተማር ላይ ይገኛል። “ወደፊት የኦንላይን ትምህርት ግብዓቶችን አሟልተን ዝግጁ ስንሆን መምህራን የግድ ሶማሌላንድ መሄድ ሳይጠበቅባቸው እዚሁ ሆነው ያስተምራሉ። በዚህም በምስራቅ አፍሪካ የራሱን አሻራ መጣል ጀምሯል ማለት ነው” ብለዋል-ፕሮፌሰር መንግስቱ።

በቀጣይ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የሚያደርገው ጉዞ እውን እንደሚሆን እስካሁን የሄደባቸው ርቀቶች፣ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች የፈታባቸው መንገዶች አብይ ምስክር ይሆኑለታል። በምርምር ዩኒቨርሲቲነት ሲመረጥም በእነዚህ የስኬት ጉዞዎቹ ታሳቢነት ነው። ይህም ሆኖ ግን መጪው ዘመን ቀላል የሚባል አይሆንም። በአገር አቀፍና



39

በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝናን ካተረፉ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚጠብቀው ውድድር ቀላል አይሆንም። ውድድሩ አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚደረግ በመሆኑ በልህቀት ለመውጣት የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ብዙ መስራት ግድ ይለዋል።

“እስከ አሁን ጥሩ እየሄድን ነው የሚል እምነት አለኝ። በተለይ በድህረ ምረቃው በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ የልየታ ተልዕኳችንን ተከትሎ እስካሁን ያለንበት ሁኔታ ጥሩ ነው። ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተፈጥሯዊ ውድድር መምጣት አለበት። የተሻለ ተማሪ ለመውሰድ ውድድር እናደርጋለን፣ የተሻለ በጀት ከመንግሥት ለማግኘት፣ የተሻለ ዓለምአቀፍ ትብብር ለማድረግ ውድድር እናደርጋለን።” ይላሉ ፕሮፌሰሩ። ዩኒቨርሲቲው በአዎንታዊ ውድድር ላይ የተመሰረተ ስራ በመከወን ውጤታማ ለመሆን ይተጋል።

በሌላው ዓለም የሚካሄዱ ምርምሮችን የሚያሳልጠው ባለሐብቱ ነው። ትላልቅ ኩባንያዎች ችግራቸው እንዲለይ፣ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው፣ ከአገራቸው አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ለመፍጠር የምርምር ተቋማትን በር ያንኳኳሉ። በገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ። የተገኙ ውጤቶችን በብዛትና በጥራት በማምረት ለአገራቸውም ሆነ ለዓለም ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

በዚህ ደረጃ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ከታላላቅ ኩባንያዎችና ከባለሐብቶች ጋር ተቀራርበው በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይችላሉ። በአገር ደረጃ የዚህ ዓይነቱ ሃሳብ ብዙም አላደገም። ዩኒቨርሲቲዎችና ኩባንያዎች ከተባበሩ በጥናትና ምርምር የታገዘ እንቅስቃሴ በማድረግ ውጤታማ ስራ ለማከናወን የሚችሉበት ዕድል አለ። ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ደረጃ ምን ያህል ርቀት ሄዷል? ምንስ አግኝቷል? ለወደፊቱስ ምን አስቧል?

“እንደ አገራችን ይህ እሳቤ መምጣት አለበት። የአገራችን ኩባንያዎች መጀመሪያ የራሳቸውን አቅም መገንባት አለባቸው። ምርምር የሚሰራው በመቶና በሁለት መቶ ሺህ ብር አይደለም። በሚሊዮን ብሮች ሊፈልግ ይችላል። አቅም ያለው በራስ መተማመኑ ያደገ ኩባንያ መምጣት አለበት። አሁን የሉም ማለት አይደለም። ትንሽ ፈንድ በመስጠት አብረናቸው የምንሰራ ኩባንያዎች አሉ። ብዙ ባይባልም በጣም ጥቂት ምርጥ ዘር ምርት ላይ አብረናቸው የምንሰራ ኩባንያዎች አሉ። በጣም ትንንሾች ናቸው። ግን አቅሙ ትልቅ ነው” በማለት ይገልጻሉ ፕሮፌሰር መንግስቱ።

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምሩ ዘርፍ በአገር ደረጃ እያስመዘገባቸው የሚገኙትን ውጤቶች ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የራሱን ጥረት ያደርጋል። ለአገራችን ባለሐብቶችና ኩባንያዎችም ዘርፉን በማሳደግ በኩል አሻራቸውን ለማኖር የሚያስችለው ዕድል ክፍት መሆኑን ከፕሮፌሰር መንግስቱ ንግግር መረዳት ይቻላል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መንግሥቱ ኡርጌ



40

የአፍሪካ ቀንድ እና ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ቀንድ



41

በአየለ ያረጋል

በታሪካዊ፣ ባሕላዊና ተፈጥሯዊ ክስተቶች የደመቀ ነው። በተመሳሳይ በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች መልኩ የጎደፈ ነው። ጉራማይሌው ክፍለ አህጉር-አፍሪካ ቀንድ። ቀንዱ የጥንት ሰብዓ ዘሮች ቅሪት መገኛ፤ በብዝኃ ባህል፣ ኃይማኖት፣ ማንነት የተቆራኙ ማኅበረሰቦች ባለቤት ነው። በጥንተ ስልጣኔው ከሮማዊያን ስልጣኔ ጋር ይጣቀሳል። ይህ መንደር በሰው ልጆች የጭቆና፣ የቅኝ ግዛትና

ባርነት ሁነቶች ታሪክ አብይ ጎዳና ነበር። የባሕር ማዶ ተጓዦች፣ ወራሪያን፣ ነጋድራሶች፣ ሳይንቲስቶች መንደሩን እየታከኩ ሾልከዋል። በሁለቱ የዓለም ጦርነቶች የአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ስትራቴጂካል ስፍራ ነበር።

ምሥራቅና ምዕራብ ክፍላተ ዓለምን በማቆራኘቱ የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ መዘውር ነው። ከስዊዝ ቦይ መከፈት በኋላ የአውሮፓ፣ የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ የሶስትዮሽ ማቆራኛ አንጓ ነው። የሜዲቴራኒያን ባሕርና የሕንድ ውቅያኖስ ማዕዶት ወይም መሿለኪያ የሆነችው ባብ-ኤል መንደብ የባሕር ወሽመጥን ከጉያው ወሽቋል። ባብ - ኤል - መንደብ ደግሞ ከጅቡቲ፣ ከኤርትራና ከየመን የምትዋሰን የዓለም የንግድ ፍሰት መሿለኪያ በር ነው።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በየዓመቱ 30 ሺህ መርከቦች ይርመሰመሱበታል፤ ሦስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በርሜል

የአፍሪካ ቀንድ እና ኢትዮጵያ



42

ነዳጅ በየቀኑ ያልፍበታል፤ በቀን አንድ ቢሊዮን ዶላር የንግድ እንቅስቃሴን ያስተናግዳል። በዚህም ከእስያ 59 በመቶ፣ ከአውሮፓ 21 በመቶ፣ ከአፍሪካ ደግሞ 16 በመቶ የንግድ ግብይቶች መተላለፊያ መስመር ነው። ምስጢሩ ደግሞ ቀይ ባሕርንና የኤደን ባህረ ሰላጤን የሚያስተሳስረው መወሸቁ ነው። እናም ዓለም ዘወትር የሚገበያይበት የምንጊዜም ብቸኛ የንግድ አውታር ሆኗል።

መንደሩ የመላ አፍሪካዊያን አገሮች የጋርዮሽ ጉባዔ መምከሪያ ነው። ከሁሉም በላይ አፍሪካዊያን ከዘመናት ቅኝ ግዛት፣ ባርነት፣ ኢ-ርቱዕ ንግድ ልውውጥ ትግልና መስዋዕትነት በኋላ የአንድነታቸው፣ የወደፊት አብሮነት ተስፋቸው፣ የሰላምና ደኅንነት ደጀንነት የመሰረቱት ተቋም (የዛሬው የአፍሪካ ሕብረት) ደጅ ነው - ለቅኝ ግዛት ቀንበር ባልተንበረከከችው ኢትዮጵያ። ቀንዱ የራሳቸው ልዩ አዎንታዊና አሉታዊ መልኮች ያላቸው አገሮችን ያቀፈ ቀጣና ነው።

ከጥቃቅን እስከ ግዙፋን ብርቅዬ የዱር እንስሳት አምባ ነው። የዓለማችን ወንዞች አለቃ የሆነው ዓባይ/ ናይልን ያመነጨ፣ የዓለማችንን ሁለተኛውን ጥልቅ ሐይቅ ታንጋኒካን ያፈለቀ፣ የአፍሪካን ሠማይ ጠቀስ ተራራ ኪሊማንጃሮን የገተረ፣ የታላቁን ስምጥ ሸለቆ ተፈጥሯዊ ገፀ በረከቶች የተቸረ… መልከ ብዙ ፀጋዎችን ያቀፈ አካባቢ ነው። ይህም ሆኖ የአፍሪካ ቀንድ ሥነ-ምህዳራዊ ክሽፈትም ሌላው መገለጫው ነው። በድርቅ፣ በረሃብና በቸነፈር የተጎሳቆለ፣ በድህነትና ስደተኝነት ስሙ የገነነ ቀጣናም ነው። ተደጋጋሚ ድርቅና አካባቢያዊ መራቆት ሰለባ ሆነናል። ይህም ለሕዝቦች መፈናቀልና ፍልሰት ዳርጓል። አካባቢያዊ ሥነ-ምህዳር አለመጠበቅ ውስጣዊ የሕዝብ ፍልሰቱን አንሮታል። ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ጥሪዎች ማዕከል ነው። በከፍተኛ ውስጠ ፍልሰት እና ስደት የሰዎች ዝውውር የሚካሄድበት በመሆኑ ‘የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ ጥናት የስደት ታሪክ ነው’ አሰኝቶታል። እናም ተደጋጋሚ ድርቅ፣ ተለዋዋጭ ዝናብ፣ ግጭት፣ አቅመ ቢስ ተቋማት፣ መሃይምነትና ስራ አጥ ወጣት የበረከተበት፣ ድህነት፣ ደካማ ኢኮኖሚ … መገለጫው የሆነ ቀጣና ነው። ለዚህም ለውስጥና ለውጭ ዓለም ዐብይ ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።

በጥቅሉ የአፍሪካ ቀንድ የዘመኑ ትርምስምስ ቀጣና ነው፤ የግርግር መንደር ነው። ስያሜው እንደተዋጊ ቀንዳም በሬ ከግብሩ የተሰጠው ይመስል አካባቢው የውጊያ ቀጣና ነው። የግጭት፣ የብጥብጥና የሠብዓዊ ቀውስ ማዕከል ነው። ዘመዱም ባዕዱም ቀጣናውን በመቆጣጠር ምኞትን ለማርካት ሩጫ ከጀመረ ውሎ አድሯል። ስፍራው የዓለም የዓይን ብሌን ነውና!

የኃያላኑ ርኩቻ፣ የቀንዱ አገሮች ሽኩቻ እና የችግሩ መፍቻ

ዓለም ላይ ምሉዕ በኩልሄ ተፈጥሯዊ ጸጋ የተቸረ ምድር ባለመኖሩ አገሮች ፀጋን ተጋርተው፤ ምርትን ተገበያይተው፣ የጎደለን ተሞላልተው፣ ተጠቃቅሞ የማደግን፣ የሕዝቦችን ኑሮ ማረጋገጥ የዲፕሎማሲ መርህ ተደርጎ ይወሰዳል። ዳሩ ጥቂቶች ኃያላን አዛዥ ናዛዥ ብዙኀኑ ደግሞ ምንዝር በሆኑባት ዓለም ይህ መርህ ተጥሷል። በታሪክ አጋጣሚ የአገሮች የኃይል ሚዛን በመዛባቱ የኃያላኑ ቡድን የዲፕሎማሲን መርህ ጥሶ ጣልቃ ገብነትና ጫና መፍጠርን መለያው አድርጓል። የአፍሪካ ቀንድ ደግሞ ለዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናል። በኃያላኑና በቀንዱ አገሮች መካከል ያለው ዲፕሎማሲ አንዱ በስመ-አጋዥ፤ ሌላው በእርጥባን ሸክም ተንፏቃቂ የአራጣ አበዳሪና ተበዳሪ ግንኙነት ሆኗል። አበዳሪው እየከበረ፤ ተበዳሪው እየቆረቆዘ የሚድህበት የተቃርኖ መንገድ። ይህም እርጥባን ተጠቅሞ አገሮችን አንገቱ ላይ ገመድ እንደተጠለቀለት ውሻ በራስ ርምጃ የማንቀሳቀስ የቅኝ ገዥዎች ገመድ ነው። በእርዳታ ሰበብ እንዳሻው ማሾር፣ አልሾርም ካለም የማሰሪያ ገመዱን ተጠቅሞ ማሽመድመድ፣ የአገሮች መንግሥታትን ማፈራረስ፣ አፈንጋጭ የሚሏቸውን መሪዎች ማስወገድ ገሃዳዊ ስልት ነው። እናም አፍሪካ ቀንድ ያላባራ ግጭት ይዘንባል፤ መንግሥታት በየወቅቱ በኃይል ይፈናቀላሉ። የቀጣናው አገሮች የዕጅ አዙርና የውክልና ጦርነት ሜዳ ሆነዋል።

ቀንዱ በስትራቴጂካዊ አቀማመጡ ተመራጭነቱ የሁሉም የጥቅም ማዕከል ሆኗል። ኃያላን አገሮች ለቀጣናው ባላቸው ፍላጎት ባለፉት አስር ዓመታት የባሕር ላይ ውንብድናን መከላከል በሚል አጀንዳ ከየፊናው ተጠራርተው ባሕር ኃይላቸውን በቀጣናው አስፍረዋል። በርግጥም ቀጣናው ላይ ማንዣበቡ የቅርብ ጊዜ ታሪክ ብቻ አይደለም። ዕድሜ ለሶማሊያ የባሕር ወንበዴዎች ይሁንና “ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል” እንዲሉ ውንብድናን በመከላከል ሰበብ የጅቡቲ ወደብ በኃያላኑ የጦር መርከቦች ተጥለቀለቀች። ዛሬ ላይ ከሰባት በላይ አገሮች የጦር ሰፈሮችን በቀጣናው ገንብተዋል። ሁሉም ዓለም አቀፍ የጦር ኃይሎች በአፍሪካ ቀንድ ዳርቻ ለመስፈር አሰፍስፈዋል፤ ከባሕር ወደ የብስ እሽቅድምድም። በአሜሪካ የተጀመረው ከባሕር ወደ የብስ የተደረገው እሽቅድምድም ሁሉንም ኃያላን አስከትሏል። በተለይም ቻይና በአካባቢውና በአፍሪካ ውስጥ ያላት ጥልቅ እንቅስቃሴ ለአሜሪካና ተከታዮቿ የምዕራብ አገሮች እንቅልፍ ከነሳ ውሎ አድሯል።

ቀድሞውኑ በኢኮኖሚ ብቻ እንጂ በውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ የማትገባው ቻይና ከቀጣናው እንድትወጣ በምዕራባዊያን ኢ - ቀጥተኛ ግፊቶች ቢኖሩም በተቃራኒው መሰረቷን እያሰፋች መጥታለች። ባሳለፍነው ወርኅ የካቲትም

በቀጣናው ልዩ መልዕክተኛ መሾሟ፣ በቅርቡም የቻይና- ምስራቅ አፍሪካ ጉባዔ መጀመሯ፣ በአገሮች መካከል ያሉ የሰላም ችግሮችን ለመሸምገል እና ለማደራደር ዝግጁ መሆኗን ስትገልጽ መደመጧም በርግጥም ቻይና በቀጣናው ያላትን ተጽዕኖ እያጎላች መምጣቷን፤ የቀድሞ ምጣኔ ሀብታዊ ፍላጎቷ ወደ ፖለቲካዊ መልኮች እየተለወጠ መምጣቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

በቅርቡ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና ልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደበት ወቅት የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግ አገራቸው ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸው ነበር። በቀጣናው ሰላም፣ ልማትና መልካም አስተዳደር እንዲዘረጋ፣ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ፣ በቴክኖሎጂና ምርምር፣ በፕሮጀክቶች ፋይናንስ ድጋፍ እና በድህነት ቅነሳ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም እንዲሁ። ቻይና በኢኮኖሚ ረገድ ዘላቂነት ያለው ቀጣናዊ ትስስርን ማጎልበት፣ ሽብርተኝነትን መከላከልና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲዘረጉና የቀጣናው አገሮች በወጪ ንግዳቸው የነጻ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደምታደርግ ነው ያመለከቱት። ይህ የቻይና እና የቀንዱ አገሮች ሁለንተናዊ ግንኙነት በጎ ሚና ቢኖረውም በእያንዳንዱ አገር የውስጥ ጉዳይ ገብተው መፈትፈት ለለመዱት አንዳንድ ምዕራባዊያን አገሮች ግን ምቾት የሚነሳ ጉዳይ ነው።

ከጅቡቲ ባሻገር በአልሸባብ የምትታመሰው ሶማሊያ እና በኤርትራ የባሕር ዳርቻዎች የጦር ሰፈር መገንባት የሚሹ ኃይሎችም አልጠፉም። የዓረቡ ዓለም አገሮች ወደ ቀጣናው ያደረጉት ትኩረትና እንቅስቃሴ ሌላው ብዙ መልኮች ያሉት የቀንዱ ገጽታ ነው። የየመንን ጦርነት ምክንያት በማድረግ ወደ ሽኩቻ የገቡት የባህረ ሰላጤው አገሮች ከየመን ተሻግረው ወደ አፍሪካ ቀንድ የጦር ሰፈር መገንባት ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ ለሁሉም አካል የጥቅም ማዕከል ሆኗልና መልኩ ኢ-ተገማች እና ተለዋዋጭ ነው። የብዙ ወገኖች እጆች ስለሚያተራምሱት ከአፍጋኒስታንና ከመካከለኛው ምሥራቅ ቀጥሎ ሶስተኛው መረጋጋት የተሳነው ቀጣና ሆኗል። የበዮች አለመስማማትና የቀዬው ትርምስ ደግሞ ለቀንዱ አገሮች በየጊዜው በአይገመቴ ሁነቶች እየታጀበ ለስጋት ተዳርጓል። ይህ የኃያላኑ ርኩቻና ፍጥጫ ለቀንዱ አገሮች ከተስፋ ይልቅ ለዘላቂ ሕልውና ችግር ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል። ቀንዱ በዓለም ላይ ከሚገኙ ቁልፍ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ወይም ጂኦ-ፖለቲካል አካባቢዎች አንዱ ቢሆንም፤ የቀንዱ አገሮች እርስ በርስ እየተናኮሩ፣ መንግሥታትም ቀስ በቀስ እየከሸፉ



43

መጥተዋል። የቀንዱ አገሮች ያላባራ መልከ ብዙ ግጭትና ጦርነት ቁልፍ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል።

የቀንዱን መልከ ብዙ ችግሮች ለማቃለል የቀንዱ አገሮች ትብብር አይነተኛ መፍትሔ ነው። ቀንዱ በተፈጥሮ የመክበር ጸጋዎች ቢቸረውም ዕድሉን አልተጠቀመም፤ እንዳይጠቀምም ሳንካዎች በርክተዋል። እናም ሰላምና ጸጥታን እንዲሁም ልማትና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ያሻዋል። ለዚህ ደግሞ የልማት ተግዳሮቶችን በጋራ መጋፈጥ ይፈልጋል።

የቀንዱ አገሮች ቀዳሚ ፈተና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በየዓመቱ ሚሊዮኖችን እየፈተነ ያለው ድርቅና ጎርፍ ነው። የሥነ ምህዳራዊ ክሽፈት ለተደጋጋሚ ድርቅና አካባቢያዊ መራቆት ሰለባ አድርጎታል። በአፍሪካ ቀንድ የድርቅ ተጋላጭ ማኅበረሰብ ቁጥር አሻቅቧል። እ.ኤ.አ 2011 በቀጣናው 16 ሚሊዮን ዜጎች ለከፋ ጉዳት ተዳርገው ነበር። እ.ኤ.አ ታህሳስ 2021 ይፋ በሆነ መረጃ በሶማሊያ ብቻ አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎች በድርቅ ተጠቅተው ነበር። ቀደም ብሎም እ.ኤ.አ 2011 በሶማሊያ በተከሰተው ረሃብ ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል። በወቅቱም ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶማሊያዊያን ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ገጥሟቸዋል። ባሳለፍነው ዓመት በኢትዮጵያ ከ40 ዓመታት ወዲህ እጅግ አስከፊ የተባለ ድርቅ ተከስቶ ነበር። ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ ሶማሌ ክልልን የነካካው አስከፊ ድርቅ በሚሊዮን የሚቀጠሩ የቁም እንስሳትን ገድሏል፤ ሚሊዮኖችን ለረሃብ ዳርጓል። ኬኒያ እና ሱዳን በከፍተኛ ጎርፍ ተመተው የድረሱልኝ ጥሪ ማሰማታቸውም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

የሰሃራ በረሃማነት መስፋፋትና የሥነ ምህዳር ክሽፈት ሌላው ፈተና ነው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና የሰሃራ በረሃ እየሰፋ የሳህል አገሮችን አዳርሶ ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ስጋት መደቀኑን ያነሳሉ። የአየር ንብረት መዛባትን መቀነስ እንጂ ሙሉ በሙሉ ማስቆም እንደማይቻል ነው ያመለከቱት። በዚህም የውሃ እጥረትን ጨምሮ መልከ-ብዙ ጉዳቶች ሊከተሉ እንደሚችሉ ይገልጻሉ። ኢትዮጵያ እንደ ቀጣናው አባል ፈተናዎችና ስጋቶች እንዳሉባት በመረዳት በውሃ አጠቃቀም፣ በግብርና እና መሰል ከአየር ንብረት መዛባት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ “መቋቋም የሚያስችሉ ሥራዎች ማከናወን ይጠይቃል” ብለዋል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ በአየር ንብረት ለውጥ የሚጠበቅበትን እየሰራ እንዳልሆነ ይተቻሉ። በዚህም በርካታ የምርምር ተቋማትን በማቋቋም በጉዳዩ ላይ በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ ነው የሚገልጹት። የቀጣናው ጥናትና ምርምር ተቋማትም ቢሆኑ “በአፍሪካ ቀንድ እየተስፋፋ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ መዛባት መቋቋም የሚያስችሉ የመፍትሔ አማራጮችን ማፍለቅ ይጠበቅባቸዋል ነው” ያሉት። በዚህም እንደ ቀንዱ አገሮች የምርምር ተቋም የበኩሉን ሚና እየተወጣ መሆኑን ነው የገለጹት።

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ድንበር ታሻጋሪ በመሆኑ የአገሮችን ቅንጅታዊና የተናበበ ስራ እንደሚጠይቅ ፕሮፌሰር ጣሰው ያነሳሉ። ለአብነትም ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን ጨምሮ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ለዓባይ ወንዝ ዘላቂ ፍሰት ዋስትና ስለሚሰጥ ለታችኛው ተፋሰስ አገሮች

ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ያወሳሉ። በመሆኑም ኢትዮጵያ ለዓባይ ወንዝ ዘላቂ ፍሰት የምታካሂደውን የአካባቢ ጥበቃ ስራ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች በወጪ መጋራት ጭምር ሊደግፉ እንደሚገባ ይሞግታሉ።

በቅርቡ በተካሄደው የቻይና-ምስራቅ አፍሪካ የሰላምና የልማት ጉባዔ ላይ የታደሙት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንደገለጹት፤ በውጭ ጣልቃ ገብነት፣ ግጭት፣ ድርቅና የዓለም አቀፍ ሁነቶች ሳቢያ የቀጣናው ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች መዳረጉን የሚያመላክት ነበር። “የቀጣናው አገሮች የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በመፍታት የቀጣናውን መጻኢ መዳረሻ መወሰን ይገባናል” በማለት የቀጣናው አገሮች በውጭ ኃይሎች ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ለችግሮቻቸው በጋራ ሊመክሩ እና የመፍትሔ አካል መሆን እንደሚገባቸው ነው የተናገሩት።

እንደ እርሳቸው ገላጻ፤ የቀጣናውን መዳረሻ መወሰን በአገሮቹ እጅ ላይ የወደቀ ነው። ለተፈጻሚነቱ ቁርጠኛ ሆኖ መስራት እንደሚገባና የአካባቢው ሕዝቦች በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በባህል የሚጋሯቸውን እሴቶች በመጠቀም በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ስትራቴጂካዊ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ማጠናከር ያስፈልጋል።

ኢጋድና አፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ አገሮችን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን መጋፈጥ የሚቻለው ጠንካራ የጋራ ተቋማት በመመስረት መሆኑ እሙን ነው። ምስራቅ አፍሪካ በተለይ



44

የአፍሪካ ቀንድ ተደጋጋሚ ድርቅ እና ጦርነት ያልተለየው ክፍለ አህጉር ነውና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ሕብረት ለጉዳዩ መፍትሔ የቀጣናው ዓይነተኛ ባለቤት መሆናቸው ይታወቃል። ነገር ግን “ተቋማት ከሚጠበቅባቸው አኳያ ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣት አልቻሉም” በሚል የሰላ ትችት ይቀርብባቸዋል።

ኢጋድ ድርቅን በጋራ መከላከል እና የጋራ ስትራቴጂ እየነደፉ ለልማት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የተቋቋመ ድርጅት ነው። እ.ኤ.አ 1986 የምስራቅ አፍሪካ የልማት እና የድርቅ መከላከል በይነ ድርጅት ሆኖ መቀመጫውን ጅቡቲ አድርጎ ነበር የተመሰረተው። በ1996 (ከ10 ዓመታት በኋላ) የዛሬውን ስያሜ ይዞ ተቋቋመ። ትኩረቱ ድርቅ ብቻ ሳይሆን በክፍለ አህጉሩ ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት ላይ አተኮረ። ዛሬ ላይ ከ300 ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ (የአፍሪካን ሕዝብ ብዛት 20 ከመቶ በላይ) ያላቸው ስምንት አባል አገሮችን አቅፏል።

ኢጋድ ከተመሰረተ ሶስት አስርት ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም በቀንዱ አገሮች ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት ረገድ ምን ተጨባጭ ለውጥ አመጣ የሚለው ለብዙዎች አጠያያቂ ሆኗል። በሌላ ጎኑ “የኢጋድ ሚና ባይታከልበት ኖሮ የቀንዱ ችግር ከዚህም በላይ ይወሳሰብ ነበር” የሚሉ ወገኖችም አልጠፉም። በአኗኗር ዘይቤና የምጣኔ ሀብት መሰረታቸው ተመሳስሎሽ ያላቸውን የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ወደ ብልፅግና

የማሻገር ህልም ቢሰንቅም በአገሮቹ መካከል ግጭት እና የፖለቲካ ዥዋዥዌ እንጂ ቀጣናዊ ትብብር እምብዛም አልዳበረም። ኢጋድ ለቀይ ባሕር እና ለኤደን ባሕረ ሰላጤ ልዩ ትኩረት ሳይሰጥ በውስጥ ጉዳዩ ላይ ብቻ ማተኮሩም፤ ቀጣናው በኃያላን ሽኩቻ እንዲታመስ አድርጓል ተብሎም ይተቻል።

የኢጋድ አባል አገሮች ለጋራ ችግሮቻቸው የጋራ የድርጊት መርሐ ግብር ቀርጸው እንዲራመዱ ማስቻል የባለስልጣኑ ኃላፊነት ነው። በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋለው የኃያላን አገሮች እሽቅድምድም መልክ እንዲይዝ አገሮቹን ወክሎ የመንቀሳቀስ፣ ቀንዱ የጋረጠበትን የሥነ ምህዳር መቃወስ የማስተካከልና በድርቅና ታያያዥ ችግሮች የምግብ ዋስትና ችግር ላለበት ቀጣና የመፍትሔ አማራጭ እንዲፈልቅ የማድረግ ስራ ይጠይቀዋል። በአገሮቹ መካከል የሚስተዋል የጥርጣሬ ፖለቲካ፣ የእጅ አዙር ጦርነቶች እና ግጭቶች መንስኤዎች፣ የድንበር ላይ ግጭቶች፣ የባሕር ዳርቻዎች ይገባኛል ፍላጎቶች እና ርኩቻዎች ለኢጋድ የቤት ስራዎች ናቸው።

በኬኒያ ናይሮቢ የተካሄደው 39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ በቀጣናው ሰላምና ደኅንነት፣ ኢኮኖሚያዊ ትብብር፣ ድርቅ፣ ጦርነት፣ አካባቢያዊና አገራዊ ፖለቲካዊ ለውጦች፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ላይ ያተኮረ ነበር። በጉባዔው ማጠቃለያ በወጣው የጋራ የአቋም መግለጫ በኢጋድ አባል አገሮችና በቀጣናው ላይ ተፅዕኖ እየፈጠሩ የሚገኙ ውስጣዊና ውጫዊ

የፖለቲካና የደኅንነት ችግርችንም በጋራ መቋቋምና ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ስራ መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥቷል። የሶማሊያን ምርጫና ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር አድንቋል፤ በሱዳን፣ በሰሜን ኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን የሰላም ችግሮች በሠላማዊ አማራጭ እንዲፈቱ ኢጋድ ሚናውን እንደሚወጣ ገልጿል።

በድርቅና በተፈጥሮ አደጋዎች ለወደቀው የምግብ ዋስትና ችግር ዘላቂ መፍትሔዎችን በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶታል። ዓለም አቀፍ አጋሮችና የረድኤት ተቋማት ሠብዓዊ ድጋፋቸውን አጠናክርው እንዲቀጥሉ በመሪዎች ጉባኤ ጥሪ ቀርቧል። በኢጋድ መሪዎች መግለጫ ግን እንደወትሮው ሰላምንና ልማትን ከመመኘት በቀር ምኞትን እንዴት ማሳካት እና የቀንዱን ፈተናዎች እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ግልጽ ነገር አልተንጸባረቀም።

ሌላው የአፍሪካዊያን ተቋም በዚሁ ቀጣና በአዲስ አበባ የሚገኘው የአፍሪካ ሕብረት ነው። መላ አፍሪካዊያንን በአባልነት ያቀፈው ይህ ተቋም ግን በአህጉሪቷ ብልጽግና ከማረጋገጥና ሰላምና ጸጥታን ከማስፈን አኳያ አቅመ ቢስ እንደሆነ ይተቻል። ኃያላን መንግሥታት የአፍሪካን ሰላምና ጸጥታ በራሳቸው ሃዲድ ለማሾር ተግባራቸውን በብርቱ ቀጥለውበታል። የአፍሪካ ደኅንነት ሁኔታ በፍጥነት ተለዋዋጭ ቢሆንም ሕብረቱ በየወቅቱ በሚፈነዱ አህጉራዊ የደኅንነት ስጋት በሚፈጥሩ አዳዲስ ኃይላት ተጽዕኖ ፀጥታውን የመቆጣጠር ተስፋው እየተሟጠጠ መጥቷል። በአንድ ወቅት ለ‘ኒው አፍሪካን’



45

መጽሔት ዕይታቸውን የለገሱት ኢትዮጵያዊው ፕሮፈሰር መድህኔ ታደሰ (በሕብረቱ የቀድሞ የደኅንነት አማካሪ) ከምዕራባዊያኑ ይልቅ ሕብረቱ ቀይ ባሕር በጦር ሰፈሮች ሲጥለቀለቅ ፓሊሲ አለማውጣቱና በጉዳዩ ላይም አንዲትም ቀን ተሰብስቦ ባለመምከሩ ተችተው ነበር። የሰላጤው አገሮች ቀይ ባሕርን ሲቀራመቱት ትንፍሽ አለማለቱ አሳሳቢ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

እናም ሕብረቱ “አህጉራዊ ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ ትልሙን ስቷል” ሲሉ ተችተዋል። ይልቁንም ከሕብረቱ አፍንጫ ስር የደኅንነት ችግሮች ሲቀያየሩ መስተዋሉን ነው ያመለከቱት። ቀጣናዊ የጸጥታ ጉዳዮች አፀፋ የሚሰጥ ተጠባባቂ የሰላም አስከባሪ ኃይልም እንደተዳከመ ይገልጻሉ። በሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ መሪነት ሕብረቱ በፋይናንስ ራሱን ችሎ እንዲቆም የማድረግ ዕቅድ ለአፍሪካ መልካም ጅምር ቢሆንም፤ ጠንካራ አህጉራዊ አመራር ባለመሰጠቱ ግቡን አልመታም። የወቅቱ ዓለም አቀፋዊ የደኅንነት አደረጃጀት ለአፍሪካ ስጋት ተደርጎ መወሰድ እንዳለበት፤ የአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት አጀንዳ ባለቤት የመሆን ጉዳይ መሪዎች ሊያስቡበት እንደሚገባ መክረዋል። በአህጉሪቷ የግጭት መንስኤዎችን የሚያጠኑ ጠንካራ ተቋማት እንደሚያስፈልጉም እንዲሁ። ከአፍሪካ አገሮች መሪዎች በማኅበረሰባቸው ውስጥ የፖለቲካን መነጣጠል የማጥበብ፣ አካታች ፖለቲካዊ ሂደትን የመዘርጋትና የዴሞከራሲ ምህዳርን የማስፋት ስራ ይጠበቃል። እነዚህ አህጉራዊ ፖለቲካዊ ቁልፍ ጉዳዮች

እልባት ካልተበጀላቸው እ.አ.አ የ2063ን አህጉራዊ መዋቅራዊ ሽግግር አጀንዳ ማሳካት ከባድ ነው። በወቅቱ ነባራዊ ሁናቴ የአፍሪካ ሕብረት ጸጥታና ደህንነቱን በበላይነት የመቆጣጠር ተስፋው አጠራጣሪ ሆኗል።

አጀንዳ 2063 ሠላማዊት፣ የበለጸገችና ያደገች አፍሪካን ለመገንባት ሃሳብ የሰነቀ ግብ ነው። ይህን አህጉራዊ ግብ ማሳካት የሚቻለው ታዲያ ሁሉም አገር በየቤቱ ያለውን አካባቢ ሰላም ሲያረጋግጥ እንደሆነ ባለሙያዎች ያምናሉ። ካልሆነ ግን አንዱ ደፍርሶ የሌላው ጎረቤት አገር ሰላምና ፀጥታ አይረጋገጥም። ለአህጉራዊ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ዋስትና ግጭቶች ባሉበት አካባቢ የሰላም ተጠባባቂ ኃይል ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያ፣ ቀንዱ እና የይሁንታ ጥቁምታዎች

ከአፍሪካ ቀንድ አገሮች መካከል በተለይ ኢትዮጵያ ላይ ልዩ ትኩረት ይደረጋል። በቀጣናው ያሰፈሰፉ ኃያላንም ሆኑ ኃያላኑን በትሮይ ፈረስነት የሚያገለግሉ መንግሥታት “ለየራሳቸው ጥቅም” ሲሉ ኢትዮጵያን ይነክሳሉ። ይህም የዛሬና የወደፊት ስጋት ሳይሆን የትናንትናም ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ በተለይም በአንዳንድ ምዕራባዊያን ዘንድ የተቄመባት አገር ናትና።

ኢትዮጵያ ከዓለም ኃያላን ጥርስ ውስጥ የገባች

በዲፕሎማሲው መስክ የምዕራቡ ዓለም እንዳሻው ለማድረግ የሚሻት አገር ነች። በርጥባን ከሚሞከር ዲፕሎማሲያዊ ጫና ባሻገር ኢትዮጵያ ላይ የሚፈጠረው ጫና እና የጣልቃገብነት ግብግብ አንድምታ መልከ ብዙ ነው።

ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በዲፕሎማሲው መስክ ኢትዮጵያን ያገለገሉት አንጋፋው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በአንድ ወቅት ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምዕራባዊያን በየዘመኑ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና አመክንዮ በዋናነት ከአድዋ ድል ጋር አያይዘውታል። ይኸውም እ.ኤ.አ 1884 የበርሊን አፍሪካን የመቀራመት ጉባዔ በኋላ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛትን ድል አድርጋ የአፍሪካዊያን የነጻነት ትዕምርት መሆኗ በክፉ ዓይናቸው እንዲመለከቷት ሰበብ መሆኑ ነው። ድሕረ አድዋ ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት ሆና መቀጠሏ፤ የጥቁር አፍሪካዊያን ታሪክና ስልጣኔ ቅርስ መሆኗም ለነጮች መጥፎ ስሜት እንዲያድርባቸው አድርጓል ባይ ናቸው። በዚህም “ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ደካማ በመሆኗ ከምዕራባዊያን ጋር ግንኙነት ቢኖራትም ዳሩ ችግር በገጠማት ወቅት አንድም ጊዜ ከጎኗ አልተሰለፉም፤ በተቃራኒዋ ቆመዋል እንጂ” ይላሉ አምባሳደር ጥሩነህ። ለአብነትም የ1928ቱን የፋሺስት ኢጣሊያ የግፍ ወረራ የመንግሥታቱ ማኅበር ማስቆም አለመቻሉ፣ የራሷ ጦር መሳሪያ ከምታመርተው ኢጣሊያ እኩል ኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ብሎም በኢትዮ-ጅቡቲ



46

የባቡር መንገድ መሳሪያ እንዳታጓጉዝ መከልከላቸውን ይጠቅሳሉ። በሶማሊያ ወረራ ወቅትም ለኢትዮጵያ ወዳጅ አገር የምትባለዋ አሜሪካ የግፍ ወረራ ሲፈጸምባት ክፍያ የፈጸመችበትን የጦር መሳሪያ ከመከልከል ባለፈ ከታሪካዊ ጠላቶች በመወገን ኢትዮጵያን መክዳቷን ያወሳሉ። በሌላ በኩል “የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እና ለቀይ ባሕር ስትራቴጂክ ስፍራ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ለምዕራባዊያን ስጋት ትሆናለች በሚል እንድትዳከምና እንድትፈራርስ የምን ጊዜም ፍላጎታቸው ነው” ይላሉ። እነዚህ ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ጊዜ ሁሉ ወደ ገደል ሲገፏት የነበሩ ምዕራባዊያን ዛሬም በገጠማት የሕልውና አደጋ አሜሪካን ጨምሮ ከአሸባሪው ቡድን ጋር መወገናቸው ህወሓትን ወደውት ሳይሆን ኢትዮጵያን ለመበታተን ሊጠቀሙበት ስለፈለጉ እንደሆነ ይገልጻሉ።

ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካ፣ ከሜዲትራኒያን፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከደቡብ እስያ ጋር ባላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተሻለ የንግድ፣ የምጣኔ ሃብታዊ፣ የባህላዊና ዲፕሎማሲያዊ ትስስር የጀመረችው ከጥንት የግብጽ ስልጣኔ በፊት እንደሆነ ይነገራል። እስልምናና የአይሁድ እምነትን የተቀበለች አፍሪካዊት አገር ብቻ ሳትሆን፣ የነብዩ መሃመድ ተከታዮችንም ያስተናገደች የመጀመሪያዊቷ ሙስሊሞች የተጠለሉባት አፍሪካዊት አገረ ሰላም ነች።

በቀጣናው የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶች፣ የሽብርተኛ ድርጅቶች እንቅስቃሴዎች፣ የአገራቱ ተለዋዋጭ አሰላለፎችና ተቃርኖ መልካቸውን መለዋወጥ ለኢትዮጵያ ትልቅ አንድምታ አለው። የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አደም ካሚል (ረዳት ፕሮፌሰር) ምዕራባዊያንና የዓረቡ ዓለም በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ዘመን ተሻጋሪ ምክንያቶች የየራሳቸው መንስኤ እንዳላቸው ይገልጻሉ። ግብጽ በተለይም የዓረቡን ዓለም በዓባይ ፖለቲካ ጉዳይ ከጥንት እስክ ዛሬ በሀሰተኛ ትርክት በማሳመን አትዮጵያን ለማዳከም ያልፈነቀለቸው ድንጋይ እንደሌለ ለአብነት ያነሳሉ። የዓባይ ፖለቲካ ዛሬም ዋነኛ የጠላት አጀንዳ እንደሆነ ገልጸው፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ለማስተጓጎል ብሎም የወደፊት በዓባይ ወንዝ ላይ አሳሪ ውሎችን ለማስቀመጥ በየጊዜው ያልተቋረጡ አጀንዳዎችን እንደምታመጣ ያነሳሉ። አሁን ላይ የግብጽና መሰሎቿ አጀንዳ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ውላቸው አስረው መያዝ እንዳልቻሉ ሲረዱ፤ ሁነኛ አጀንዳቸው ውስጣዊ ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር፣ ክልሎችን ገነጣጥሎ ወደ ጎረቤት አገሮች የመለጠፍ አጀንዳ በምሁራን በኩል እያስተጋቡ እንደሆነ ይገልጻሉ። ከሰሞኑም ዶክተር አልፋቂህ የተባለ ግብጻዊ ምሁር የግድቡን ሙሌት ማስቆም ስላልቻልን ትግራይ ወደ ኤርትራ፣ ቢኒሻንጉል ጉሙዝን ወደ ሱዳን፣ ጋምቤላን ወደ ደቡበ ሱዳን፣ አፋርን ወደ ጅቡቲ፣ ሶማሌን ወደ ሶማሊያ በመገንጠል ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕቅዱን ካርታ አዘጋጀቶ ሲናገር እንደነበር ያስታውሳሉ። በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ

ልዩነት አጥር ሳይበጅ ጠንካራ አንድነት መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም በብልሃት ነገሮችን በማከናወን አገር ማዳን ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ይገልጻሉ።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ኢትዮጵያ በእስልምናው ዓለም ትልቅ ከበሬታ አላት፣ በአፍሪካ አገሮች ዘንድም በነጻነት ቀንዲልነቷ ከፊት የምትቀድም አገር ነች። ይህን አጋጣሚ በዲፕሎማሲው መስክ መጠቀም ይገባል። ኢትዮጵያ አካባቢያዊና አህጉራዊ ትስስርና የጋራ ጥቅም እውን መሆን ላይ ያተኮረ ዲፕሎማሲ ሊኖራት ይገባል። ከጎረቤቶቿም ሆነ ከአጠቃላይ ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ጋር ግንኙነቷን ማጠናከር ያሻታል። ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያና ኬንያ ጋር ያለውን ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነት ማጠናከር፣ ከዓባይ ወንዝ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ጋርም ሰላም፣ ዕድገትና ብልጽግናን ባረጋገጠ መልኩ እንዲመራ ይመከራል።

በሌላ በኩል “በአንዳንድ ጎረቤት አገሮች በኩል ያለው ግንኙነትም ሊጤን ይገባል” ይላሉ የታሪክ ምሁሩ። ለአብነትም ሱዳንን ያነሳሉ። በየጊዜው የሚመጡ መሪዎች ከሱዳን ሕዝብ ፍላጎት ውጭ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽሙት ደባ በኢትዮጵያ በኩል በጥልቅ ሊታሰብበት እንሚገባ ነው አጽንኦት የሚሰጡት። ኢትዮጵያና ሱዳን እንደ ሕዝብ በመልክ፣ በቋንቋ፣ በባህል ተመሳስሎሽ ያላቸው፣ ከ1 ሺ 600 በላይ ኪሎ ሜትር ድንበር የሚጋሩ እንደሆኑ ይገልጻሉ።

በታሪክ አጋጣሚ ግን ሱዳን በርካታ ደባዎች መፈጸሟን ያነሳሉ። ፈላሻዎችን ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ማድረጓ፣ የግብጹ መሩ ሆስኒ ሙባረክ ግድያ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲደረግ ማሴሯ፣ በዘመነ ደርግ በቀይ ሽብር መዘዝ ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ኤጀንሲዎችን በማቋቋም ወደ ሰላጤው አገሮችና ወደ አውሮፓ መሸኘቷ፣ የአሸባሪውን ህወሓት ቡድን ከምስረታው ጀምሮ በማስታጠቅ ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት እንድትታመስ ትልቅ ሚና መጫወቷን፤ ኤርትራ እንድትገነጠል በማሴር ይወቅሷታል። ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ሰሜን ዕዝ በአሸባሪው ህወሓት ሲጠቃ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ መውረሩን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ውስጥ ትንሽ ቀዳዳ በተፈጠረ ልክ ሱዳን እንጨት ስትቆሰቁስ መክረሟን ነው ያስረዱት። በአጠቃላይ ሲታይ ኢትዮጵያ ለሱዳን ትልቅ ውለታ ብትውልላትም በአንጻሩ “በየጊዜው ሱዳንን የገዙ መሪዎች የፈጸሟቸው ደባዎች ሲታዩ የሁለትዮሽ ግንኙነት ጉዳይ በጥልቅ ሊታሰብበት የሚገባ ነው” ብለዋል። ኢትዮጵያ ግን ሱዳን ችግር በገጠማት ቁጥር ለሰላሟ መትጋቷን ከሶስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የሱዳንን ችግር በሰላም አሸማግላ ከብተና እንደታደገቻት ያወሳሉ።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን (የዛሬውን የአፍሪካ ሕብረት) ደግሳ መስርታለች፤ በራሷ ከተማ ጎጆ አውጥታለች። አፍሪካዊያንን በፓን አፍሪካዊነት መንፈስ በማሰባሰብ ከባርነት ቀንበር ነጻ እንዲወጡ የመሪነት

ሚናዋን ተወጥታለች። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት /ኢጋድ/ እንዲመሰረት ሚናዋ ጉልህ ነው። ሁልጊዜም ከሩቅም ከቅርብም ወረራና ሴራ ብታስተናግድም ኢትዮጵያ ቀድሞውኑም ከጎረቤቶቿ ጋር በቅርበት እና በእኩል ተጠቃሚነት ለመስራት ለፍታለች። ኢትዮጵያ ይህን የቀደመ አገሮችን የማስተባበር፣ ተቋማትን የመገንባትና ተጽዕኖዋን የማጎልበት ሚናዋን ልትወጣ ይገባል።

ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ መቆየቷ ብቻ ሳይሆን፤ ለሕዝቦች ነጻነት፣ ሰላምና መረጋጋት በበርካታ አገሮች የተጫወተችው ሚናም ለአፍሪካ ሕብረትና ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ማዕከል መሆን አስችሏታል። ከፖለቲካ ማዕከላዊነቷ ባሻገር የገጠሟትን ውስጣዊ የህልውና ፈተናዎች ተቋቁማ የኢንቨስትመንት መዳረሻነቷን ማረጋገጥ ይገባታል።

ኢትዮጵያ የባሕረ ሰላጤው ወይም ሌሎች የዓረብ ሊግ አገሮችን የማይተኙላት ታሪካዊ ጠላቶች አድርጋ ባትመለከትም ተለዋዋጭ ክስተቶችን እንደ አመጣጣቸው በመገምገም ነባራዊውን ሁኔታ ያገናዘበ ስልት ወይም ስትራቴጂያዊ እርምጃ በመውሰድ ብሔራዊ ጥቅሟን የማስጠበቅ ፖሊሲ መከተል እንደሚገባት ምሁራን ይናገራሉ። እንደ ሌሎች አገሮች በቦታው በመገኘት አልያም በሌላ መልኩ ስትራቴጂካዊ ስልቶችን ቀይሶ በርካታ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባትም እንዲሁ።

በዲፕሎማሲ ቋንቋ ዘላቂ ወዳጅና ጠላት የለም። የዲፕሎማሲ መርህ ብሔራዊ ጥቅም ነው፤ የሉዓላዊነት ክብር ነው። አምባሳደር ጥሩነህ “ምዕራባዊያኑ ከትናንት እስከ ዛሬ ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲሰሩ እንደቆዩት ሁሉ ነገም ምቹ ጊዜ እየጠበቁ ኢትዮጵያን ለመበታተን ከመሞከር አይቦዝኑም” ይላሉ። ለዚህ መፍትሔው ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል የመገንባት፣ ውስጣዊ አገራዊ ስሜት የመፍጠር እና የኢኮኖሚ አቅምን የማጠናከር እርምጃዎችን መውሰድ እንደሆነ ይመክራሉ። በኢኮኖሚ ረገድም ቢያንስ የምግብ ፍጆታን በአገር ውስጥ ምርት መሸፈን እንዲሁም የግብርና መሳሪያዎች ከሺህ ዘመናት በፊት ከነበረው ኋላቀር አሰራር መላቀቅ አለባቸው። የኢኮኖሚ ጥገኝነት እያለ የፖለቲካ ነጻነትን ማረጋገጥ ስለማይቻል ከግብርና ግብዓቶች ግዥ እና ከልመና መውጣት ያሻል።

የኢትዮጵያን ሕልውና እንደ እስካሁኑ ጠብቆ ለማቆየት “ብሔራዊ ስሜትና ውስጣዊ አንድነትን የሚያጠናክር የትውልድ ግንባታ ያስፈልጋል” ነው ያሉት። ኢትዮጵያን ከድህነት ማውጣት ላይ በማተኮር ዲፕሎማሲያችን የትኛው አገር የተሻለ ጥቅም ይሰጠኛል በሚለው መታየት ይኖርበታልም ነው የሚሉት። የኢትዮጵያ ሕዝብ በየዘመናቱ የተፈተነ በመጥፎ ጊዜ አንድ ሆኖ የተሻገረ፣ ፋሺዝምን ያለፈ ጠንካራ ሕዝብ በመሆኑ አሁንም በድል ይወጣዋል።



47

የ20 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 በወጣው እንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊዮን ብር ዕድለኛው ማቲዎስ ግርማ በአ.አ ን/ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ ሲሆን፤ በሞባይል ጥገና ሥራ የተሰማራ የ40 ዓመት ዕድለኛ በአገኘው ገንዘብ በትላልቅ ኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።



48

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ግስጋሴ

ዓለምአቀፍ



49

“ዲፕሎማሲ” በአገሮች መካከል የሚኖር ግንኙነትን በተገቢው ሁኔታና መልኩ ለማሳለጥ የሚያስችል ተግባር ነው። በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውም አገሮች አንዳቸው የሌላውን ጥቅም ሳይነኩ ወይም ሳይጎዱ የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም የስከብራሉ።

በአገሮች መካከል የሚካሄደው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በሶስት ይከፈላል። እነሱም የፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና የዜግነት ወይም የሕዝብ ዲፕሎማሲ ናቸው።

የፖለቲካ ዲፕሎማሲ በአገሮች መካከል በፖለቲካ፣ በጸጥታ የመሳሰሉ ጉዳዮች ዙርያ የሚደረግ ግንኙነት ነው። የዜግነት ዲፕሎማሲ ደግሞ በሁለቱ አገሮች ሕዝቦች መካከል መልካም የሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር፣ እንዲሁም ዜጎች በአገራቸውም ሆነ በውጭ አገር ሆነው የአገራቸውን መልካም ገጽታና ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰሩት ስራ ነው።

በዘካርያስ ወልደማርያም



50

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ምንድን ነው?

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ማለት ከሶስቱ የዲፕሎማሲ ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በዓይነቱ ሰፋ ያለ እና በአጠቃላይ የዲፕሎማሲ ስራ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊፈጥር የሚችል ዘርፍ ነው። ከዲፕሎማሲ ታሪካዊ አመጣጥ አኳያ ሲታይም የሁሉም ዓይነት ዲፕሎማሲዎች መነሻው የኢኮኖሚ ወይም የንግድ ዲፕሎማሲ እንደሆነ ድርሳናት ያመለክታሉ።

በጠባብ መልኩ ሲታይ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የወጪ ንግድ ማስተዋወቅ እና የውስጥ ኢንቨስትመንትን የማበረታታት ተግባር ሊሆን ይችላል። ይህ አንዳንዴ የንግድ ዲፕሎማሲ በመባል ይታወቃል። ሰፋ ባለ መልኩ ሲታይ ደግሞ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የመንግሥትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያራምድ ወይም የአገሪቷን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በማስፈጸም ብሔራዊ ጥቅምን ለማሳካት የሚደረግ ማንኛውም ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።

ከክርስቶስ ልደት በፊት አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ በጥንታዊት ግሪክ የነበሩ የከተማ መንግሥታት የውጭ ጠላቶቻቸውን ጥቃት ለመቋቋም የመሰረቱት የ “ዴሊያን ሊግ” ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው በመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ላይ ነበር። ከዚያም በአስራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ሥር በሰደደውና በውጭ ዜጎች ተወካይነት ሲካሄድ የነበረው ዲፕሎማሲ ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያለው ነበር።

እንደውም እንደዚህ ዓይነት ተልዕኮዎች በመካከለኛው ዘመን መገባደጃ ላይ በሜዲትራኒያን ባሕር እና በአጎራባች ባሕሮች ዙሪያ ከተመሰረቱት የአውሮፓ ቆንስላዎች የተገኙ ሲሆን፤ እነዚህ ቆንስላዎች መነሻቸው ዓለምአቀፍ ንግድ ነው። ከሩቅ አገሮች የሚመጡ የጭነት መርከቦች ወደቦች ላይ ሲደርሱ አለመግባባቶች እና ችግሮች በግልጽ ይከሰቱ ነበር። በሩቅ አገሮች መካከል የንግድ ልውውጥ እንዲስፋፋ ከተፈለገ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሥልጣንና ችሎታ ያለው የወደብ ነጋዴዎች የተወሰነ ተወካይ መኖር ነበረበት። ይህም በሂደት ወደ ቆንስላ አሰራር አመራ።

ቆንስላዎቹ በመጀመሪያ የመንግሥት አገልጋዮች አልነበሩም። ቆንስላዎቹ ከነጋዴዎች ጋር በመስማማት ከግል ንግዳቸው ከሚያገኙት ገቢ አነስተኛ ቀረጥ በየአካባቢዎቻቸው በሚዘዋወሩ ሸቀጦች ላይ እንዲጥሉ ተስማሙ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ዘመናዊው የኤምባሲ አሰራር በሂደት እያደገ የመጣው፡፡ የዲፕሎማሲ ስራ የተጀመረው በንግድ ምክንያት ነው የሚባለውም ለዚያህ ነው።

በዘመናዊው የአውሮፓ ታሪክ ዘመን ከ1500 ገደማ ጀምሮ

እስከ አንደኛው የዓለም ጦርነት ድረስ የተካሄደው ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ እንቅስቃሴ የአብዛኞቹን የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ሥራ ተቆጣጥሮት ነበር። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን ለመምራት የቋሚ ውክልና አቅም በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን ሆኖ ስለነበር ነው።

በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ምንም እንኳን የቆንስላ አገልግሎት ከዲፕሎማቲክ አገልግሎት የተለየ ቢሆንም ቀስ በቀስ ተሻሽሎ፡ በተሻለ የተደራጁ እና በሙያ የተካኑ፣ ደመወዝ የሚከፈላቸው ከፍተኛ የቆንስላ መኮንኖች መተግበር ጀመረ።

የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች ራሳቸው ነጋዴዎቻቸውን እና የባንክ ሰራተኞቻቸውን አዳዲስ ገበያዎችን እና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያዎችን በመደገፍ ረገድ የበለጠ ተሳትፎ ነበራቸው።

በሒደትም በኤምባሲዎች ውስጥ የንግድ አታሼዎች ተቀጥረው የነጋዴዎቻቸውን የዕለት ተዕለት ንግድ በማስተዋወቅ ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን እንዲሁም የተግባር ውልን በመቅረጽ ረገድ አስተዋጽኦ ማድረግ ጀመሩ። በዋናነት ዓላማቸውም የወጪ ንግድን ማስተዋወቅ ነበር።

በአሁኑ ወቅትም በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ንግድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን ማስፈጸሚያ ሆኖ የሚያገለግል እና የንግድ ጉዳይም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስር የተጠቃለለበት ሁኔታ እንዳለ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ሺበሺ ቤተ ማርያም ይገለጻሉ። “በአብዛኛው የለሙ አገሮች ወጪ እና ገቢ ንግድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ኢኮኖሚ ወይም ንግድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ሆኖ ይገኛል” በማለት ነው ያብራራሉ፡፡

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዓበይት ሚናዎች

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ በጣም ሰፊ አድማስ ሊኖረው የሚችል ቢሆንም፤ ዋና ዋና የሚባሉትን ጠቀሜታዎች በሁለት ዓበይት ዘርፎች ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት እንዲሁም አገራዊ ደኅንነትን ማስጠበቅ ናቸው። በዚህም በመልማት ላይ የሚገኙ አገሮች ለልማታቸው የሚያስፈልጋቸውን የገበያ እድል፣ የፋይናንስ፣ የቴክኒክና የሰው ኃይል ድጋፍና ትብብር የሚያገኙበትን መንገድ ሲያፈላልጉ የለሙት አገሮች ደግሞ የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን እና በእርሱም የደረሱበትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት አስጠብቀው የሚቀጥሉበትን ተግባር ለመፈጸም ደፋ ቀና የሚሉበት ነው።

ሀ. ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት

በአሁኑ ወቅት አገሮች የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ከሚተገብሩባቸው በርካታ ምክንያቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ ለወጪ ምርቶቻቸው ገበያን ለማፈላለግ እና ለኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማቶቻቸው የሚያግዙ እርዳታና ባለአነስተኛ ወለድ ብድሮችን ለማግኘት መሆኑን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የዓለምአቀፍ ሕግ መምህርና የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ዮሀናን ዮካሞ ያስረዳሉ።

ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሕዝቧን ለመመገብ፣ የስራ እድልን ለማስፋት፣ ለግብርና፣ ቱሪዝም እና ኢንዱስትሪ ምርቶቿ የገበያ እድልን ለመፍጠር የሚያስችል በመሆኑ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ተግባራቷን ማጠናከር ያስፈልጋታል።

መንግሥት በስካሁኑ ጥረቱ እያደገ የሚሄድ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማስመዝገብ እንደቻለ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በተለያዩ የዓለም አገሮች በተከናወኑና የአገሪቷን የኢንቨስትመንት አማራጭ እድሎች የማስተዋወቅ ተግባር አማካኝነት የዓለምአቀፉ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ አሶሴሽን (WAIPA) እንዲሁም የዓለምባንክ ግሩፕ በጥምረት የሚያዘጋጁትን ዓለምአቀፋዊው የ‘Strengthening IPA Advocacy Ser- vices’ Gold award 2021.ተሸላሚ መሆን መቻሏ ነው፡፡

እንደ ኮሚሽኑ መረጃ በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 307 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፡፡ ይህም የዕቅዱን 64 ነጥብ 4 በመቶ ሲሆን፤ አፈጻጸሙ ዝቅ ሊል የቻለው በአገራችን በነበረው አለመረጋጋት በተፈጠሩ ጫናዎች እና የኮቪድ-19 ስርጭት ናቸው።

የወጪ ንግድን በተመለከተ በ2014 በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የአልባሳት፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምርት የወጪ ንግድ 310 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 202 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙም 65 በመቶ ነው፡፡ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 13 ነጥብ 7 በመቶ ወይም የ24 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ አለው፡፡

ለግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶቿ ሰፊ የውጭ ገበያን ከመፍጠር አኳያ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አገሪቷ ስኬቶችን እያሳየች ትገኛለች። ለምሳሌ በያዝነው ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲሆን፤ ይህም በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ነው።

የአገሪቷን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከማሳደግ እና የወጪ ንግድን መዳረሻን ከማስፋፋት አኳያ በአገራችን ዓይነተኛ ሚና እየተጫወቱ ከሚገኙት መካከል የንግድ ምክር ቤቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ ንግድ ምክር



51

ቤቶች መካከል አንዱና ትልቁ የአዲስ አበባ ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ነው፡፡

ምክር ቤቱም የስራ ግንኙነቶቹን የሚያከናውነው በንግድ አሳላጮችና ኤጀንቶች አማካኝነት መሆኑን ዋና ጸሐፊው አቶ ሺበሺ ይናገራሉ። በዚህ መሰረት በአዲስ አበባ ብቻ በየዓመቱ አራት ትላልቅ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶችን የሚያካሂድ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ 40 የሚደርሱ ከውጭ የሚመጡ እና ወደ ውጭ የሚሄዱ የንግድ ግንኙነቶችን ይፈጥራል፡፡

“ይህ ለአገር ገጽታ ግንባታ ለወጪ እና ገቢ ንግድ ሊሆን የሚችል ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው” ይላሉ።

የዳያስፖራውን አቅም መጠቀም በመልማት ላይ የሚገኙ በርካታ አገሮች በለሙት አገሮች ከሚገኙ ዜጎቻቸው ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ፣ የእውቀትና ክህሎት፣ እንዲሁም ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን ያገኛሉ፡፡ በተለይም በነዚህ በለሙት አገሮች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ቁጥር ያላቸው አገሮች ይህን ተጠቃሚነታቸውን ሊያሳድግ የሚችል አሰራር ዘርግተው ከተንቀሳቀሱ ተጠቃሚነታቸውም በዚያው ልክ ሊጨምር እንደሚችል እሙን ነው፡፡

በዚህ ረገድ ሕንድ፣ ቻይና፣ ግብጽ እና ናይጄርያ በከፍተኛ ተጠቃሚነታቸው ሊጠቀሱ የሚችሉ አገሮች ናቸው፡ ፡ ኢትዮጵያም በተለያዩ የበለጸጉ አገሮች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አላት፡፡ የዳያስፖራውን አቅም ለመጠቀም የተቀናጀ ጥረት እያደረገች ግን ሁለት አስርት ዓመታት ያልሞላ ጊዜ አሳልፋለች፡፡

ይሁን እንጂ አገሪቷ የዳያስፖራ ፖሊሲ አውጥታ መንቀሳቀስ የጀመረችው በ2012 እንደ ሆነ የኢትየጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን ግርማ ይገልጻሉ፡፡

“ፖሊሲው ከመውጣቱ በፊት በነበሩት 10 ዓመታት የዳያስፖራው ጉዳይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር በሚገኝ ዳይሬክቶሬት ደረጃ ይመራ ነበር፡፡ ባለፉት አራት ዓመታት ግን ራሱን የቻለ ተቋም ተቋቁሞለት እየሰራ ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ከተቋቋመና የዳያስፖራ ፖሊሲ ወጥቶ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በአገሪቷ የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን አቶ ወንደሰን ይናገራሉ፡፡

ለምሳሌም በዳያስፖራው በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት የተላከ የዶላር መጠን በ2013 ዓ.ም ከነበረው 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር፤ በ2014 ዓ.ም ወደ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር አድጓል፡፡ በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ያስመዘገቡት

ካፒታልም በ2013 ዓ.ም ከነበረበት 37 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በ2014 ዓ.ም ወደ 99 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር አድጓል፡ ፡ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ የተሰበሰበ ድጋፍ በ2013 ዓ.ም 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፤ በ2014 ዓ.ም ደግሞ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ነበር። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ወረርሽኝ ለመከላከል ከኢትዮጵያዊያንና ትውልድ-ኢትዮጵያዊያን የተሰበሰበ ሀብት በገንዘብና በዓይነት በ2012 ዓ.ም 305 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ በ2014 ዓ.ም 282 ነጥብ 8 ሚሊዮን እንዲሁም በ2014 ዓ.ም 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ ለሰብዓዊ ድጋፍና ለበጎ ሥራዎች የተሰበሰበ ሀብት በገንዘብና በዓይነት በ2013 ዓ.ም ከ704 ሚሊዮን ብር በላይ፣ በ2014 ዓ.ም ደግሞ ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በአገር ውስጥ የዳያስፖራ አካውንት ለመክፈት በተሰጣቸው እድል አማካኝነት አካውንቶችን የከፈቱ ሲሆን በእዉቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሸግግርም በርካታ አስተዋጽኦዎችን አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና ለወጪ ምርቶቿ ገበያን በማፈላለግ ረገድ እስከአሁን ያሳየችው እመርታ የማይናቅ ቢሆንም፤ ከአገሪቷ ተመጣጣኝ አቋም ያላቸው አገሮች ከደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ግን ከእስካሁኑ የበለጠ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ስራዎችን መስራት እንዳለባት አቶ ሺበሺ ይናገራሉ፡፡

በተለይም የአገሪቷ የንግድ ማህበረሰብ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በሚካሄዱ የንግድ ትርኢቶች እና ኤግዚቢሽኖች የሚያደርገው ተሳትፎ የአገርን ገጽታ በመገንባት ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው መንግሥት ለንግዱ ማኅበረሰብ የውጭ አገሮች የንግድ ትርኢትና ኤግዚቢሽኖች ተሳትፎ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡

የኢትዮጵያን የቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት በማሳደግ ረገድ መንግሥት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ በማቋቋም ያደረገው ጥረት ባለፉት ዓመታት በታየው የኢንቨስትመንት ፍሰት እድገት አኳያ መገመት ይቻላል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተንሰራፍቶ የነበረው የኮሮና ቫይረስ፣ በአገራችንም ከተከሰተው የሰላም እጦት ጋር ተያይዞ በዘርፉ የተመዘገበውን ውጤት አበረታች አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የአገሪቷን የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከማሳደግ አኳያ የኤክስፖርት ፕሮሞሽን ኤጀንሲን አቋቁሞ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ አቶ ሺበሺ ይናገራሉ፡ ፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት በዓለምአቀፍ በአህጉር አቀፍ ደረጃ እንደ የዓለም ንግድ ድርጅት እና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና የመሳሰሉ እድሎች የመጡበት ጊዜ በመሆኑ

በብቃት መሳተፍ እንደሚገባ ነው አጽንኦት የሰጡት።

በወጪ ንግድ ዘርፍ ኢትዮጵያን ውጤታማ ሊያደርጓት የሚችሉ በርካታ የአገር ውስጥ ብራንድ ሊሆኑ የሚችሉ ምርቶችን የታደለች አገር እንደሆነች ዋና ጸሐፊው ያብራራሉ፡፡ ይህ ግን እውን የሚሆነው የወጪ ንግዱን የማስተዋወቅ ስራ በኃላፊነት ተሸክሞ የሚሰራ ኤጀንሲ ሲኖር ነው፡፡

“ኢትዮጵያ በአገር በቀል ምርቶቿ ለምሳሌ ቡና፣ ማር .. ወ.ዘ.ተ የምትታወቅ ናት፡፡ ይህ የኤክስፖርት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የኢትዮጵያን ብራንድ ተሸክሞ የኢትዮጵያን ገጽታ ለውጭ ነጋዴዎች ያስተዋውቃል፡፡” ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የአገሪቷን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት አናሳ እንደሆነና ዘርፉ ብዙ ሊሰራበት የሚገባ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

“የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው አንዱና አንኳር ስራ ቱሪዝምን ለመሳብ ሕዝብ ለሕዝብ የሚኖረውን ግንኙነት ለማሳለጥ ቱሪዝም ወደ ውስጥም ወደውጭም ለመሳብ ባሉን ባሕላዊ ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች ላይ የተመሰረተ አድርጎ መስራት ነው፡፡ ለዚህም ሰፋ ያለ የፖሊሲ ምህዳር መቅረጽ ያፈልጋል፡፡”

በዚህ በኩል በአሁኑ ወቅት መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከፍተኛ ጉልበት ይሆናሉ።

ለ. ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ በታሪካዊ አመጣጡ እንደታየው የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዋነኛ ዓላማው ንግድን ማሳለጥ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ማስተዋወቅ ቢሆንም፤ በዘመናችን ግን ከዚህም ያለፈ እና ከአገር ደኅንነት ጋር የተያያዘ ከፍተኛ ኃላፊነትን የሚሸከም ተግባር ሆኗል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን እና ብሔራዊ ደኅንነትን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። “የኢኮኖሚ ደኅንነት የአገር ደኅንነት ነው፣ ብሔራዊ ደኅንነት ደግሞ የኢኮኖሚ ደኅንነት ነው” ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እጅግ ውስብስብ እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን እና ደኅንነትን ከማስከበር አኳያ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል። የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ከፍተኛ አንገብጋቢነት ለመረዳትም የዓለማችን ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች ብሎም በዓለም ፖለቲካ ላይ ሁሌም ተፎካካሪ የሆኑትን የአሜሪካና ቻይናን ሽኩቻ ማየት ይቻላል።

ሁለቱ አገሮች በተለይ እየተራኮቱባቸው የሚገኙት ዋና ዋና መስኮች ውስጥ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የበላይነት፣ በአምስተኛው ትውልድ የቴሌኮሙዩኒኬሽንና ሞባይል ቴክኖሎጂ ቀዳሚነት ይይዛል። የዶላር ዓለም



52

አቀፍ መገበያያነትን ማስቀጠል፣ በዓለም የንግድ ድርጅት ውስጥ ቻይና የያዘችውን የታዳጊ አገርነት ደረጃ እንድታጣ ማድረግ ይገኙበታል።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የበላይነት

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ያላሰለሰ የአሰራር ቅልጥፍናን የሚያሰፍን ቴክኖሎጂ በመሆኑ አዳዲስ ኢኮኖሚያዊ አሸናፊዎችን እና ተሸናፊዎችን ይፈጥራል። የደኅንነት እድሎችን እና አደጋዎችንም ይዞ ይመጣል። በመሆኑም የቴክኖሎጂውን አጠቃቀም ደኅንነት አጠባበቅ እና ሥነ ምግባርን በተመለከተ አገራዊ ስጋት ይፈጥራል። በመሆኑም የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች የሥራ ምትክን እና እኩልነትን በሚቀንሱበት ጊዜ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተጎላበተውን ኢኮኖሚያዊ ዕድል ከፍ ማድረግ አለባቸው። ዓለም አቀፍ ደንቦችን ማቋቋም፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በጦርነት እና በክትትል አጠቃቀም ላይ የሕዝብ ስጋቶችን መፍታት እና የዩኤስ-ቻይናን ለአለም አቀፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አመራር ውድድር ማሰስ አለባቸው ።

አምስተኛው ትውልድ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ

አምስተኛው ትውልድ (5G) ሽቦ አልባ የቴሌኮሙዩኒኬሽን አውታሮች የመተላለፊያ ይዘትን፣ አቅምን እና የሞባይል

ግንኙነቶችን አስተማማኝነት ይጨምራሉ። ይህ የቅርብ ጊዜ ዝግመተ ለውጥ ለብዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወሳኝ ድጋፍ ይሰጣል። እነዚህ ኔትወርኮች ለአሜሪካ ሰፊ ሀብት እና ማኅበራዊ ጥቅሞችን የማፍራት አቅም አላቸው። ነገር ግን “የተወሰኑ ስጋቶችንም ይፈጥራሉ” ሲሉ በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ምክር ይለግሳሉ።

የአቅርቦት ሰንሰለት ውህደት እና የቴክኖሎጂ ፈተናዎች እነዚህን አደጋዎች ያጎላሉ። የአሜሪካ ኩባንያዎች የአምስተኛው ትውልድ አካላትን ማምረትና መቆጣጠራቸውን ቀጥለዋል። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ ለቴሌኮሙዩኒኬሽን ስርዓቶች በውጭ አቅራቢዎች ላይ ብቻ ትተማመናለች። እርስ በርስ የተሳሰሩ እና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱ የአሜሪካ መሠረተ ልማቶች በብዙ ቁጥር የአካል፣ ሥነ ልቦናዊ ወይም የገንዘብ ጉዳት ለሚያስከትሉ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭነቱ ይጨምራል። ሁዋዌ እና ዜድቲኢ የተባሉ ሁለት የቻይና ኩባንያዎች አምስተኛው ትውልድ (5G) ገበያ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። ይህ ደግሞ አሜሪካ ዘወትር ተቀናቃኟ የሆነችውን ቻይናን በስጋት እንድታያት አድርጓል።

የአሜሪካ ዶላር የበላይነትን መጠበቅ

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ አሜሪካ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ዘዋሪ ሆናለች። ዓለም የአሜሪካን ዶላር (USD) እና በዶላር የሚደገፉ ንብረቶችን እንደ ተጨባጭ መጠባበቂያ ገንዘብ ይጠቀማል።

በመሆኑም የአሜሪካ የፋይናንስ ስርዓት ለዓለም አቀፍ ንግድ ዋና ማዕከል ነው።

ይህ አቋም አሜሪካ ቢያንስ በሶስት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ልዩ ኃይል እና ኃላፊነት ይሰጣታል። አንደኛ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ቅንጅት ውስጥ የመሪነት ቦታ፣ ለምሳሌ በ G7/G20 መንግሥታት መካከል፤ ሁለተኛ በዶላር ላይ በተመሰረተ ዓለም አቀፍ ንግድ ላይ የተሰማራ ማንኛውም መንግሥት እና ማዕቀብ እና ተጽዕኖ የማድረግ ችሎታ፤ ሦስተኛ ከዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውሶች የተጠበቀ ኢኮኖሚ እንዲኖራት ያደርጋል።

የዓለም ንግድ ድርጅትን ማሻሻያ ማድረግ

እ.ኤ.አ. በ1995 የተመሰረተው የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) “ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር አልሞ የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። አራት ዋና ዋና ተግባራትን ለማገልገል የተነደፈ ነበር። ዓለም አቀፍ የንግድ ሕጎች ሥርዓትን ማስያዝ፣ የንግድ ስምምነቶችን ለመደራደር እንደ መድረክ መስራት፣ በአባላቱ መካከል የንግድ አለመግባባቶችን መፍታት እና በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን ፍላጎት መደገፍ።

ከነዚህ አራት ተግባራት መካከል በተለይ ለታዳጊ አገሮች ፍላጎቶች የሚደረገው ድጋፍ “ቻይና አላግባብ ትጠቀማለች” በማለት ያደጉት አገሮች ይህንን ተጠቃሚነቷን ለማስቀረት ደፋ ቀና በማለት ላይ ናቸው።



53

ቻይና በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ሁለተኛው ግዙፉ ኢኮኖሚ ባለቤት ብትሆንም ከዚህ በፊት ተሰጥቷት የነበረው የታዳጊ አገርነትን ደረጃ ለመተው ፈቃደኛ አለመሆኗ በለሙት አገሮች ጫንቃ የአለም ንግድ ድርጅት የፈጠራቸውን እድሎች ትጠቀማለች በሚል ነው አገሮቹ ቻይናን ከዚህ ምድብ እንድትወጣ አለበለዚያም ድርጅቱ መመዘኛዎቹ ላይ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚወተውቱት። ይህንንም ዘመቻ አሜሪካ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ተግባሯ በፊታውራሪነት መምራት እንዳለባት ይመክራሉ።

የስደተኞችን ፍልሰት መግታት የበለጸጉ አገሮች በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸው ትኩረት ከሚሰጡት ዘርፍ አንዱ ከፍተኛ የሆነውን የስደተኞች ፍልሰት መከላከል ነው። በዚህም ስደተኞች ለሚመነጩባቸው አገሮች የኢኮኖሚ ድጋፍ በማድረግ የስደተኞችን ቁጥር መቀነስ እና በራሳቸውም ላይ የሚደርሰውን የኢኮኖሚ መቃወስ ለመግታት ያለመ ነው።

በእርዳታ እና በስደት መካከል ያለው ግንኙነት የተወሳሰበ ነው። በርዕሰ-ጉዳዩ ላይ ሰፊ የሆነ የኢኮኖሚ ጥናት እንደሚያሳየው በአጠቃላይ የልማት ዕርዳታ በስደት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ቤተሰቦች ከድህነት ወደ መካከለኛ ገቢ ደረጃ ሲሸጋገሩ፣ ፍልሰት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይሄዳል። ስለዚህ፣ በተለይ ለሥራ ፈጠራ ወይም ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ ያነጣጠረ አነስተኛ መጠን ያለው እርዳታ ስደትን ሊጨምር ይችላል። ለዓለማችን በጣም ድሃ አገሮች ግን እዚህ ደረጃ ላይ

መድረስ አሥርት ዓመታትን ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ የትኛውም ተጨባጭ የእርዳታ መጠን ስደትን ለመቀነስ በቂ የኢኮኖሚ እድሎችን በማሻሻል ላይ ብዙ ተጽዕኖ አይኖረውም።

በ2018 በሞሮ ላናቲ እና በሬይነር ቲኤሌ የተደረገ ጥናትን ጨምሮ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የኢኮኖሚ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የልማት ዕርዳታ ስደትን በመቀነስ ላይ ተጽዕኖ እንዳለው ነገር ግን አግባብ ባላቸው ዘርፎች ላይ ያነጣጠረ መሆን እንዳለበት ያመለክታል። በተለይም የኢኮኖሚ ድጋፍ ውጤታማ የሚሆነው የግዳጅ ስደት መንስኤዎችን በማነጣጠር እንደ ትምህርት ወይም የጤና አጠባበቅ ያሉ የሕዝብ አገልግሎቶችን ማሻሻል ላይ በማተኮር ሲሆን ይህም በትውልድ አገሮች ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚጎድላቸው ወይም የማይገኙ ናቸው። ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ምንም እንኳን በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ የሚደረገው ዕርዳታ በስደት ቁጥር ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመያዝ አስቸጋሪ ቢሆንም የልማት ዕርዳታ የግዳጅ ስደትን በመቀነሱ ረገድ ፖለቲካዊ መረጋጋትን፣ የሕግ የበላይነትን እና የዴሞክራሲ እና የጸጥታ ተቋማትን ለማጠናከር ዒላማ ማድረግ እንዳለበት ይታመናል። በተጨማሪም እርዳታው የሚታይ ተጽዕኖ እንዲኖረውና ከተቀባዩ አገር ጥቅል አገራዊ ምርት ጋር የተመጣጠነ መሆን እንዳለበት ጥናቶች ይመክራሉ።

ስትራቴጂክ የጤና ዲፕሎማሲ ያደጉ አገሮች ለታዳጊ ወይም ደሀ አገሮች የሚያደርጉት ስትራቴጂካዊ የጤና ዲፕሎማሲ ጤናን፣ ብልጽግናን እና

መረጋጋትን በማምጣት ብሔራዊ ደኅንነትን ለማምጣት የሚያልም ቁልፍ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ተግባር ነው። ይህም እ.ኤ.አ በ2015 ሁሉም የተባበሩት መንግሥታት አባል አገሮች ባጸደቁት በ2030 የዘላቂ ልማት አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ነው።

በዚህም መሰረት ያደጉ አገሮች በመልማት ላይ ላሉ አገሮች ኤች አይ ቪ፣ ቲቢ፣ ወባ ለሕፃናት እና ለእናቶች ሞት፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እንደ የአየር ብክለት እና ትምባሆ፣ የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኮቪድ-19፣ ወይም አዲስ ኮሮና ቫይረስ መስፋፋት እና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ካለው አስደንጋጭ ተጽዕኖ ጋር በጤና እና በኢኮኖሚ መካከል ያለው ትስስር በጣም ግልፅ ሆኗል።

የኢኮኖሚዲፕሎማሲ ተግዳሮቶችን መቋቋም

አገራችን በመልማት ላይ ካሉ አገሮች አንዷ በመሆኗ ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን መሳብና ለምርቶቿም መዳረሻ በመፈለግ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እንዳለባት እሙን ነው፡፡

ይሁን እንጂ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በሚደረገው ጥረት የአገርን ብሔራዊ ጥቅም እና ደኅንነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ከሚችሉ ነገሮች መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ አቶ ሱራፌል ጌታሁን ይናገራሉ፡፡



54

“አንዳንድ ኩባንያዎች በኢንቨስትመንት ስም የሚገቡት የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ አማጽያንን ለመደገፍ ወይም በኢንቨስትመንት ስም ተጽዕኖ ለመፍጠር ነው፡፡” በማለት ነው የገለጹት።

እንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች በተለያዩ የአፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ አገሮች ማጋጠማቸውን አቶ ሱራፌል በዋቢነት አንስተዋል። ይህን ለመከላከል ዲፕሎማቶች ለውጭ ኩባንያዎች ፍቃድ ከመስጠታቸው በፊት የኩባንያዎችን የጀርባ ታሪክና ዝርዝር መረጃ በአግባቡ ማጥናት ይጠበቃል።

ስልታዊ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለአገራዊ ደኅንነትና ጥቅም

ከታዳጊ ወይም በመልማት ላይ ከሚገኙ አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች። እንደአገር በመልማት ላይ ከሚገኙ አገሮች ትመደብ እንጂ ካላት ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እንዲሁም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አንጻር ጠንካራ የሚባል የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ማራመድ የግድ ይላታል።

እርዳታና የተለያዩ ዘላቂነት የሌላቸው ድጋፎች ለጊዜው አቅምን ለመገንባት ያግዙ ይሆናል እንጂ ለአንዲት አገር መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደማያስችል በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የዓለምአቀፍ ሕግ መምህርና የሕዝብ ዲፕሎማሲ ማዕከል ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ዮሀናን ይናገራሉ። በመሆኑም አገሪቷ ልማቷን ለማረጋገጥ ብሎም አገራዊ ደኅንነትን እና ብሔራዊ ጥቅሟን በዘላቂነት ለማስከበር በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መስክ የሰጥቶ መቀበል ግንኙነትን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑንም ነው ያስረዱት።

አገሪቷ አሁን ካለችበት የዕድገት ደረጃ እና ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳትም የደኅንነት እና የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከምስራቅ እስያ አገሮች ስኬታማ የእድገት ጉዞ ትምህርትን የመውሰድ ፍላጎት እንዳለ ያትታል፣ እንደ አቶ ዮሃናን ገለጻ።

ባለንበት የሉላዊነት ዘመን (ግሎባላይዜሽን) የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ዘመኑ ያስገኛቸውን የነጻ ንግድ ትስስር፣ የኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እድሎችን በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም እንዲሁም የግሎባላይዜሽንን ተግዳሮቶች ለመቋቋም የሚያግዝ መሆኑን አቶ ዮሃናን ይገልጻሉ።

እንደአገር ብሔራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን ከማስከበር አኳያ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መሰራት ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራትም የአገሪቷን በምግብ ምርት ራስን

መቻል ብሎም የወጪ ንግድ ማሳደግ፣ የአገሪቷን የማእድን ሀብቶች በተገቢው ሁኔታ በጥቅም ላይ ማዋል ይገኙበታል።

ከላይ አንዳንድ አገሮች አገራዊ ጥቅማቸውንና ደኅንነታቸውን ከማጠናከር አኳያ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራቸው ትኩረት ከሰጧቸው እንቅስቃሴዎች በመነሳት አገራችንም በእርዳታና የቴክኒክ ድጋፍ ላይ ከመመርኮዝ ይልቅ በኢኮኖሚ ራሷን በመቻል ከራሷ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ የጀመረቻቸውን ጥረቶች አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት መገመት ይቻላል።

በምግብ ምርት ራስን መቻል ይህ የማንኛውም የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት ሲሆን፤ በዚህ ረገድ ራሳቸውን ያልቻሉ አገሮች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለተለያዩ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ሲጋለጡ ይስተዋላል። በተለይም የሩስያና ዩክሬን ግጭት ከተፈጠረ በኋላ በእነዚህ አገሮች የስንዴ አቅርቦት ላይ የተማመኑ ለችግር መጋለጣቸው ተስተውሏል።

አገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስንዴ ምርት ራሷን ለመቻል ብሎም ወደውጭ እስከመላክ ድረስ ለመድረስ ጥረት አድርጋ አመርቂ ውጤት አግኝታለች። ይህም የሆነው ስንዴን በመስኖ እርሻ እንዲሁም በቆላማ አካባቢዎች ማምረት የሚያስችል አሰራርን በተሳካ ሁኔታ በመተግበር ነው።

ይህ ምርታማነት ቀጣይነት እንዲኖረውና እያደገ እንደሄድ ለማድረግ ደግሞ ማዳበርያን በአገር ውስጥ ማምረት መቻል ወሳኝ ነው። ምክንያቱም ከፍተኛ ምርት ለማምረት የሚያስችል ማደበርያን ሁሌም ከውጭ ማስመጣቱ አዋጭ ካለመሆኑ በተጨማሪ አገሪቷን አሁንም ከውጭ በሚመጡ ወሳኝ ምርቶች ጥገኛ እንድትሆን ያደርጋል። ስለሆነም በቀጣይ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ተግባራት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

የመድኃኒት ምርት ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች ግብዓት አቅርቦት በመጠቀም የአፍሪካ የመድኃኒትና ሕክምና መገልገያዎች ምርት ማዕከል የመሆን ግብ እንዳላት በአገሪቷ የኢንዱስትሪ ልማት መርሃ ግብር ላይ ተቀምጧል። ለዚህም ግብ መሳካት በማልማት ላይ ካሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ለመድኃኒት አምራች የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች ከፍተኛ ቦታ በመስጠት በርካታ የሕንድና መካከለኛው አገሮች ገብተው በመስራት ላይ ይገኛሉ።

ይህም አገሪቷ አንገብጋቢ በሆነው የመድኃኒትና ሕክምና መገልገያዎች ምርት ጥገኛ እንዳትሆን ከማገዙ በተጨማሪም ከተለያዩ አገሮች ጋር አቅሟ በፈቀደ መጠን የጤና ዲፕሎማሲን ተግባራዊ በማድረግ ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር እንድትችል ሊያግዝ ይችላል።

የአረንጓዴ አሻራ ልማት ባለፉት አራት ዓመታት አገሪቷ በሰፊው እያካሄደች ያለችው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ዘመቻ ከራሷ አልፎ ዓለምአቀፍ እውቅና እንድታገኝ አስችሏል። ልማቱ የአገሪቷን የአየር ንብረት ደኅንነት ከመጠበቅ እና ለምግብነት የሚውሉ ተክሎችን በማስፋፋት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ አገሪቷ በዘርፉ የልህቀት ማዕከል እንድትሆን ሊያደርግ ይችላል።

ይህንንም በማጠናከር ወደፊት ከጎረቤትና ሌሎች አገሮች ጋር የአየር ንብረት ዲፕሎማሲን በማጠናከር ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር የምትችልበትን ተጨማሪ እድል ይከፍታል። በመሆኑም ከልማቱ ጎን ለጎን አሁን የተጀመረውን ጎረቤት አገሮችን የማሳተፍ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ኢትዮጵያ ካላት ከፍተኛ የውሃ ሀብት አኳያ የአፍሪካ የውሃ ማማ ስትባል ኖራለች። ይህንን ከፍተኛ የውሃ ሀብትም ከእርሻ በተጨማሪ ለኃይል ማመንጫነት ለማዋል የሚያስችል አመቺ መልክአ ምድር ያላት በመሆኑ በዘርፉ ልማት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት በርካታ የኃይል ማመንጫዎች ለአገሪቷ የኤሌትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ ሲሆኑ፤ ለጎረቤት አገሮችም በተወሰነ ደረጃ ኃይል በማቅረብ ላይ ትገኛለች።

በቀጣይም የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በግንባታ ላይ የሚገኙ ኃይል ማመንጫዎች ወደ ስራ ሲገቡ አገሪቷ ከራሷ አልፎ ለጎረቤት የምታቀርበው ኃይል መጨመር ትችላለች። ይህም በሰጥቶ መቀበል መርሕ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መደራደርያ አቅም ሊፈጠር ይችላል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከነዚህ በተጨማሪ “በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እየተፈጠሩ ያሉ ነጻ የንግድ ቀጣናዎችን ለማቋቋም የሚካሄዱ ስምምነቶች እንዲሳኩ የምታደርጋቸውን ጥረቶች አጠናክራ መቀጠል አለባት” ሲሉ አቶ ዮሃናን ይመክራሉ። ምክንያቱም የነዚህ የኢኮኖሚ ጥምረቶች መፈጠር ለአገሪቷ የሚያስገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው።



55



56

የወርቃማው ዘመን ፈርጦች

ማህበራዊ



57

በፍቅርተ ባልቻ

የወርቃማው ዘመን ፈርጦች

ከራስ ባሻገር …

“ከአስራ ሁለት ዓመት በፊት ከኢሊባቦር ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። በወቅቱ ካርል ሄልዝ የሚመራው ‘ሰዎች ለሰዎች’ የሚባል ድርጅት ውስጥ የማስታወቂያ ስራ በመስራት የአዲስ አበባ ኑሮዬን አሃዱ ብዬ ጀመርኩ።

ስራውን ስሰራ የነበረው በቅጥር አይደለም፤ በግል እየወሰድኩ ነበር። ይህም አጋጣሚ በውስጤ ከጥበብ (አርት) ጋር የተያያዘ አቅም እንዳለኝ እንድረዳ አደረገኝ። የህትመት እና የማስታወቂያ ስራ ፍላጎት (ገበያ) እንዳለ ማየት ቻልኩ። ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማውጠንጠን ጀመርኩ” ይላል ታሪኩን ያካፈለን ስራ ፈጣሪው አቶ ኃብታሙ መንገሻ።

አቶ ኃብታሙ እንደሚለው እግሩ ላይ የአካል ጉዳት ስለአለበት እንደፈለገ ከቦታ ከቦታ መንቀሳቀስ ይፈታተነዋል። ብዙ የእግር ጉዞ በማድረጉ እና ምቹ ሁኔታም ባለመኖሩ የሚጠቀምበት ክራንች ከአንዴም ሁለት ጊዜ ተሰብሮበታል።



58

ከዚህ በላይ ኑሮን ለማሸነፍ የመጣባት አዲስ አበባ ሁሉን ነገር አልጋ በአልጋ አላደረገችለትም። ከበርካታ ችግሮች እና ውጣ ውረዶች ጋር አጋፍጣዋለች። ከገጠሙት ተግዳሮቶች መካከል ከፍተኛ ጫና የፈጠረበት የመስሪያ ቦታ ማጣት ነው። በየአካባቢው የኪራይ ዋጋ ከፍተኛ መሆን ተከራይቶ ለመስራት አላስቻለውም። እርሱ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ነው መንግሥት የጥቃቅን እና አነስተኛ ስትራቴጂን ነድፎ ወደ አፈጸጸም የገባው።

“ዕድሉን ለመጠቀም ወሰንኩ። እኔ ይህን ውሳኔ ስወስን ብዙዎች ፖሊሲውን እና እንቅስቃሴውን እንደፖሊቲካ በሩቁ ያዩት ነበር። ‘ለምን ከችግሬ ጋር አላገናኘውም? ለምን እንጀራ አላደርገውም?’ ብዬ ቆርጩ ተነሳሁ። በእርግጥም ተሳክቶልኛል፣ አሁን ላይ ሳየው ለእኔ እንጀራ ማድረግ ችያለሁ፣ ለእኔ ፖለቲካ አይደለም።” በማለት ነው የገለጸው።

ጥቃቅን እና አነስተኛን ከተቀላቀለ በኋላ ከሳምንት እስከ ሳምንት የመስሪያ ቦታ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ተመላልሷል። ከአንድ ዓመት ውጣ ውረድ እና ያላሰለሰ ጥረት በኋላ መስሪያ ቦታ አገኘ። 32 ካሬ ስፋት ያለው የመስሪያ ቦታ የተሰጠው በ2006 ዓ.ም ነው። በዚያን ወቅት በመስሪያ ቦታው የተደራጀ ነገር አልነበረም።

“አንድ እግሯ ሰባራ ጠረጴዛ ነበረች፣ ከግድግዳው ጋር አስደግፌ ነበር የተጠቀምኩባት። የመስሪያ ቦታ ከተሰጠኝ በኋላ ነው ብዙው ነገር የተቀየረው” ብሏል።

አቶ ኃብታሙ በ2007 ዓ.ም አጋማሽ ላይ አዲስ ካፒታል

ሊዝ ፋይናንሲንግ እንደተጀመረ ሰማ። (ይህ አሰራር የተወሰነ ቅድመ ክፍያ በመክፈል የመስሪያ ማሽን በማስከፈል መንግሥት በብድር የሚያቀርብበት ነው።) ‘ለምን አልሞክረውም?’ የሚል ቁጭት በውስጡ አደረ። ከዚህም ከዚያም በማለት 15 በመቶውን ቅድመ ክፍያ አመቻቸ። “የራሴ የምላቸውን ነገሮች ሁሉ በመሸጥ 33ሺ500 ብር ቅድመ ክፍያ አሟላሁ። መንግሥት ዘጠኝ መቶ ሺ ብር የሚያወጡ አራት ማሽኖችን በብድር ሰጠኝ። ማሽኖቹን ይዤ ከገንዘብ ሚኒስቴር የአንድ ሚሊየን ብር ስራ ወሰድኩ።” በማለት ይገልጻል።

የመጀመሪያውን ስራ በስኬት አጠናቀቀ። ከዚህ በኋላ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ያሉትን የገንዘብ ሚኒስቴር ስራዎች በሙሉ በተከታታይ ለማከናወን እድል አገኘ። “ከዚህ ቀደም ያለኝን ልምድ በመጠቀም ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ደረሰኞች፣ መጽሐፍት እና መጽሔቶችን እያተምኩ ነው። የህትመቱን ስራ የተቀላጠፈ ለማድረግ ዘመናዊ ማሽኖችን እጠቀማለሁ፤ በስራው ላይ ያሉትንም ባለሙያዎች እንዲሰለጥኑ አደርጋለሁ።” ሲል ከምን ተነስቶ፣ እንዴት እና በምን ሁኔታ ማደግ እንደቻለ ነው አቶ ኃብታሙ ታሪኩን ያካፈለን።

10ሺ 440 ብር ካፒታል ብቻው የጀመረውን ስራ አሳድጎ አሁን ላይ ከ35 በላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ ነው። አሁን ያለው ካፒታል ማሽነሪዎችን እና ሌሎች ተንቀሳቃሽ ነገሮች ጨምሮ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ተሻግሯል።

አቶ ኃብታሙ ከራሱ ባሻገር ለሌሎችም መትረፍ የቻለ፣ ለአካል ጉዳተኞች ተምሳሌት በመሆን፣ በርካታ

ሽልማቶችን፣ እውቅናዎችን ለማግኘት የበቃ፣ ለዜጎች በህትመት ስራ ሙያን እንዲቀስሙ በማሰልጠን ወደ ስራ ያስገባ፣ ለቀጣይም ትልቅ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ስራ ፈጣሪ ነው።

እልፍ ሲሉ - እልፍ ይገኛል አንዳንዶች ከእናት ከአባታቸው፣ ከአያት ከቅድመ አያቶቻቸው በወረሱት ኃብት እና ንብረት ተዝናንተው ሕይወታቸውን ይመራሉ። ሌሎች ደግሞ በራሳቸው ገቢ እና እውቀት በሚያገኟት አነስተኛ ገቢ ‘ከእጅ ወደ አፍ’ የሆነ ኑሮን ይጋፈጣሉ። ጥቂቶች አዲስ አሰራር፣ አዲስ ምርት፣ አዲስ አገልግሎት የሚያስጀምር ሃሳብ አፍልቀው ወደ ተግባር ይቀይሩታል፤ ብዙ ኃብት ንብረት ከማፍራትም አልፈው ባለ ራዕይ በመሆን ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የገቢ ምንጭ እና መተዳደሪያ የሚሆን የስራ ዕድል ይፈጥራሉ። እነዚህን ሰዎች ነው ኢንተርፕረነር የምንላቸው።

ዶ/ር ወሮታው በዛብህ “ኢንተርፕረነርሺፕ በቀላሉ የማይቆጠር፣ የማይለካ፣ ውጤቱ በኋላ የሚታይ፣ በሰዎች አዕምሮ የተደበቀ፣ የሚፈልጉ፣ የሚያስቡ፣ የሚያልሙ ሰዎች ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸውና ለአገራቸው የሚጠቀሙበት ስራ እና ኃብት መፍጠሪያ ጥበብ ነው።” ሲሉ ‘በኢንተርፕረነርሽፕ መበልጸግ በተሰኘው እና በ2003 ዓ.ም ለንባብ በበቃው መጽሐፋቸው ከትበዋል።

ኢንተርፕረነርሺፕ መሬት፣ የሰው ኃይል፣ ካፒታል እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በተለየ መንገድ አዋህዶ



59

ክፍተትን የሚሸፍን፣ ችግሮችን የሚፈታና ለባለጸግነት የሚያበቃ የባለ ራዕዮች ጠንካራ የስራ መፍጠሪያ መሳሪያ ስለመሆኑ በመጽሐፉ ተመላክቷል። ኢንተርፕረነርሺፕ በጥቅሉ ሲገለጽ በውስጣችን የተቀመጠ የስራ ፈጠራ ጥበብ እና የአስተሳሰብ ኃይል፣ ፈጣን የማያቋርጥና ተጨማሪ ኃብት የመፍጠር፣ የስራ ፈጠራ እና የቢዝነስ ማሻሻያ የአስተሳሰብ ጥበብ ነው።

ኢንተርፕረነርሺፕ በእያንዳንዳችን አዕምሮ ውስጥ ተቀብሮ ያለውን ተሰጥኦ በጥበብ አውጥቶ ወደ ትላልቅ ስራዎች እና ኃብት የመቀየር ሂደት ነው። ዶ/ር ወሮታው በመጽሐፋቸው በእያንዳንዱ ሰው አዕምሮ ውስጥ ከሦስት ሺህ በላይ የሚሆኑ የፈጠራ ችሎታዎች እንዳሉ ጥናቶች ዋቢ አድርገው ጽፈዋል። “እነዚህ ኃብት የሚፈጥሩ ችሎታዎች በአብዛኛው ከባለቤቶቻቸው ጋር አርጅተው ይቀበራሉ።” ይሉናል ጸሐፊው። “ከሁሉም ቦታዎች በኃብት የሚበልጡት የቀብር ቦታዎች ናቸው።” የሚባለው ለዚህ ሳይሆን ይቀራል?

ዶ/ር ወሮታው ‘ኢንተርፕረነርሺፕ ራስን እና አገርን ለማበልጸግ’ በሚል ርዕስ በ1998 ዓ.ም ያሳተሙት ሌላው መጽሐፋቸው ኢንተርፕረነርሺፕ ራሱን እንደቻለ ጽንሰ ሃሳብ እና የምርት ግብዓት መታየት ከጀመረ 200 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ጠቅሰዋል። በወቅቱ ኢንተርፕረነርሺፕ የሚገለጸው በተለይ አንድ ትርፋማ አካባቢ ላይ የተመረተን ምርት ወዳነሰበት (ምርት ወደሌለበት) አካባቢ ወስዶ ከማከፋፈል ጋር በተያያዘ ነበር። ይህም ኢንተርረነርሺፕ በየዘመናቱ የተለያየ መልክ እና ገጽታ እንደነበረው ያሳያል።

ይኸው መጽሐፍ ኢንተርፕረነርሺፕን ሲያብራራ የስራ ፈጠራ ጥበብ ወይም ችሎታ ነው ይለዋል። ፈጠራ አዲስ ሃሳብን አዕምሮ ውስጥ የማመንጨት እና የመነጨውን አዲስ ሃሳብ ወደ ምርት ወይም አገልግሎት ለውጦ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚው ኅብረተሰብ እንዲገለገልበት የማድረግ ችሎታ እንደሆነም መጽሐፉ አስነብቧል።

ኢንተርፕረነርሺፕ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከነበረው ‘ኢንተርፕራንደር’ ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ እንደሆነ ያስነበበው መጽሐፉ (በ1998 ዓ.ም የታተመው) ኃላፊነት (Risk) መውሰድ፣ አንድን ነገር ከሌላው በተለየ መንገድ ማድረግ ብለው እንደሚተረጉሙትም ጠቅሷል። ሌሎች የሚፈሩትን ኃላፊነት ወስዶ መስራት ነው። ኢንተርፕረነርሺፕ ቋሚና ፈጣን የሆነ አዳዲስ ተጨማሪ ኃብት የመፍጠር ሂደት ወይም ችሎታ ነው። አዳዲስ ምርቶችና አገልግሎቶችን ቢዝነስ ከመፍጠር ጋር ይያያዛል።

ዶ/ር ወሮታው በመጽሃፋቸው “ሁልጊዜም አንድን ስራ ለመስራት የሚያስችሉ የተሻሉ ዘዴዎች መፍጠር ይቻላል። ኢንተርፕረነርሺፕ ነባር አሰራሮችን በአዲስና በተሻሉ ዘዴዎች የመተካት ሂደት ነው። ኢንተርፕረነርሺፕ ኃላፊነትን በግል የመውሰድ እና ስኬታማ የመሆን ሂደት ነው።” የሚለውን የጆሴፍ ሹምፕረነርን ሃሳብ በአስረጂነት አቅርበዋል።

ከተለመደው ነገር ውጥቶ ኃላፊነት ወስዶ አዲስ አሰራርን በመተግበር በመንግሥትም ሆነ በግሉ ዘርፍ እሴት መጨመር ለውጥ ማምጣት የቻለ ሰው ኢንተርፕረነር እንደሆነ የሚናገሩት በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት

ኢንስቲትዩት የአቅም ግንባታ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ቦሩ ሻና ናቸው። አቶ ቦሩ “ኢንተርፕረነርሺፕ ንግድ ከፍቶ መስራት ብቻ አይደለም” ይሉናል። በመንግሥት ኃላፊነት ደረጃ ያሉ ሰዎች ሕዝብ ተኮር፣ ሰው ተኮር የሆነን አሰራር አምጥተው በሚሰሩበት ሙያ እና የስራ መስክ ኃላፊነት ወስው ውጤት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል አመለካከት መሆኑን ነው የሚያስረዱት።

የኢንተርፕረነርን መለያ ባሕሪያት ኃላፊው ሲገልጹም “ኢንተርፕረነር የሚወደውን ስራ ወዶ እና ፈቅዶ፣ ኃላፊነትም ወስዶ፣ እሴት በመጨመር ይሰራል። ኢንተርፕረነር በአካባቢው ያለውን ችግር እና መልካም አጋጣሚ፣ ብዙዎች የማይመለከቷቸውን ነገሮች የማየት እና መፍትሔ የማምጣት አቅም አለው። ያልተሟላ ፍላጎት እና ችግርን አይቶ ያንን ለማሟላት ድርጅት በማቋቋም ወይም በግሉ መፍትሔ መሆን የሚችል አገልግሎት ወይም ምርት ያቀርባል፤ ለራሱም ትርፍ ያገኛል፣ የማኅበረሰቡንም ችግር ይፈታል።” ነው ያሉት። ኢንተርፕረነርሺፕ እና ስራ ፈጠራ ይለያያሉ የሚሉት አቶ ቦሩ ስራ ፈጠራ የኢንተርፕረነርሺፕ ውጤት መሆኑን ይጠቅሳሉ። ለዚህም ነው የስራ ዕድል የሚፈጥሩት ኢንተርፕረነሮች ናቸው የሚባለው።

ዛሬ የዓለማችን የተለያዩ አገሮች የዕድገት እና የብልጽግና ልዩነት ዋናው ቁም ነገር ያለው የኢንተርፕረነርሺፕ ጥሬ ኃብት መጠንና ይዞታ ላይ እንደሆነ በልበ ሙሉነት መግለጽ ይቻላል። ኢንተርፕረነርሺፕ ሁሉንም ጥሬ ኃብቶች ለተሻለ ዕድገት ያበቃልና።

ባለራዕይ የቢዝነስ ሰዎች ከትንሽ ተነስተው ሰማይ ጠቀስ



60

የሚታይ ክስተት ነው። ምናልባት ልዩነቱ የዕድገቱ መጠን ይሆናል። በሁሉም የዓለም አገሮች የስራ ፈጣሪዎች ቁጥር ጨምሯል። ከቢዝነስ ፈጣሪዎች ውስጥ ኢንተርፕረነሮች ስንት እንደሆኑ ለመግለጽ ጥናት ቢፈልግም የቢዝነስ ፈጣሪዎቻቸው ቁጥር አድጓል።

ከእያንዳንዱ ቤተሰብ የሚፈለገው የሚበሉ እና የሚጠጡ ነገሮች ብቻ ሳይሆኑ የሚሸጡ ግብዓቶችንም እንዲያመርቱ ነው። ከውጭ የሚመጣን ምርት መጠቀም ብቻ ሳይሆን በአገሩ አምርቶና ለገበያ አቅርቦ በሚፈጥረው ኃብት ከሌላው ለመግዛት የሚያስችለውን የተሻለ አቅም እንዲገነባ በቤተሰቦች እየተመረተ ወደ ገበያ የሚወጣ የቤት ውስጥ ምርት ስራ ላይ የተመሰረተ (Home Based) ኢንተርፕረነርሺፕን ማስፋፋት ጭምር ነው። በአንጻሩ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ስለ ኢንተርፕረነርሺፕ በቂ ግንዛቤ አልተፈጠረም።

“በዓለም ላይ ከሚጀመሩ ቢዝነሶች 50 በመቶዎቹ አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ይዘጋሉ። 25 በመቶዎቹ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት፣ 15 በመቶዎቹ ደግሞ በቀጣዮቹ 10

ዓመታት ሲዘጉ፣ ቢዝነሳቸው ከአስር ዓመት በላይ ቀጥሎ የሚገኙት 10 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው።” ይላል ኢንተርፕረነርሺፕ ራስን እና አገርን ለማበልጸግ የተሰኘው የዶ/ር ወሮታው መጽሐፍ።

መጽሐፉ በአንድ አገር ውስጥ ኢንተርፕረነርሺፕ መኖሩን ለማረጋገጥ ሦስት መሰረታዊ አካሄዶችን መመልከት እንደሚገባ ይመክራል። የመጀመሪያው አዲስ ሃሳብና አዲስ ቢዝነስ የሚለው አካሄድ ነው። ኢንተርፕረነሮች አዲስ ሃሳብ፣ ምርትና አገልግሎት ይዘው ወደ አዲስ ገበያ ይገባሉ። ሁለተኛው በነባር አስተሳሰብ አዳዲስ ቢዝነስ መጀመር ነው። ይህም አንድን ችግር በአንድ መንገድ ብቻ ከማቃለል በአዳዲስ መንገዶች የማቃለል ጥረት ነው። ሦስተኛው መንገድ ባለው አስተሳሰብና ነባር ቢዝነሶች ላይ የሚሰራ ስራ መጀመር ነው። ይህም በሌላ ቦታ የሌሉ ነባር ስራዎችን ማስፋፋት ነው። ከዚህ በመነሳት በአገራችን ብሎም በአካባቢያችን ኢንተርፕረነሮች መኖር አለመኖራቸውን መፈተሽ እንችላለን።

“እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል” ይላል የአገሬ ሰው።

ፎቆች የሚገነቡበት፣ ሰፋፊ እርሻዎች የሚያቋቁሙበት ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚከፍቱበት የአስተሳሰብ ኃይል ነው። ስኬታማ ሰዎች ሰፊውንም ጠባቧንም መሬት በአግባቡ ይዘው ለእድገትና ለብልጽግና ይጠቀሙባታል። ሌሎች ግን ያባክኗታል።

ጃፓን ጠባብ፣ በተፈጥሮ ውሃማ እና ድንጋያማ መሬት ይዛ ኢኮኖሚዋን አበርትታለች። ለስራ ምቹ ያልነበረ መሬቷን፣ የሕዝቧን እና የመሪዎቿን በሳል ጥበብ ተጠቅማ ስራ እና ኃብት እንደፈጠረችበትና እንደበለጸገችበት እናያለን። በብዙ አገሮች የኢንተርፕረነርሺፕ ኃብት እንዲያድግ በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ ነው። ባደጉት አገሮች ብዙ ኮሚሽኖች ማቋቋማቸው እና ስለ ኢንተርፕረነርሺፕ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ ትምህርት እንደሚሰጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

እ.አ.አ ከ1970 ወዲህ የበለጸጉ አገሮች ኢንተርፕረነርሺፕን የማሳደግ ልዩ ዘመቻ ጀምረዋል የሚሉት ዶ/ር ወሮታው ዓለም በስራ ፈጠራ አነስተኛና መካከለኛ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች ትልቅ ዋጋ ያገኘበት ጊዜ መሆኑን በምክንያትነት ያነሳሉ።

የበለጸጉ አገሮች ለዕድገት ያበቋቸው ኢንተርፕረነሮች መሆናቸውን ስለሚያምኑ ለኢንተርፕረነርሺፕ ከፍተኛ ከበሬታ፣ እንክብካቤ እና ድጋፍ አላቸው። የምስራቅ አውሮፓ የሶሻሊስት ሥርዓት አራማጅ የነበሩ አገሮች የኢኮኖሚ ሥርዓታቸውን ቀይረው ወደ ነጻ ገበያ ሲገቡ ትልቁ ትኩረታቸው የሕዝባቸውን የቢዝነስ ፈጠራ ችሎታ ተጠቅመው ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ መድረስ ነው። እንደ ፖላንድ ያሉ አገሮች እያስመዘገቡ ያሉት ዕድገት ከሕዝባቸው ፈጠራ ጋር በቀጥታ የተያያዘ እንደሆነ ምሁራን ይገልጻሉ።

ጀርመን ወጣቶቿን ከዘጠነኛ ክፍል ጀምራ በኢንተርፕረነርሺፕ ታሰለጥናለች። በቂ ፋይናንስ፣ የገበያ ጥናት፣ የምክር አገልግሎት የሚሰጡ ዘርፎች አቋቁማለች። ለወጣቶች ስራ ፈጠራ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ቢዝነሶች ለይታለች። በዚህ መሰረት ቢያንስ ለአምስት ዓመት የራሳቸውን ካፒታል እስከሚያሳድጉ ከግብር ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ፈቅዳለች። በተለይ በቴክኖሎጂ፣ በወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ለሚሰሩ ወጣቶች ከባንክ የሚሰጠው ብድር ላይ ልዩ ትኩረት ታደርጋለች። በዚህ መሰረት ስራ ፈጠራን ከወጣትነት ጀምሮ ታበረታታለች።

በአሜሪካ ኮሌጆች ወጣቶች ትምህርታቸውን ከመጨረሳቸው በፊት በሚያቀርቧቸው የስራ ፈጠራ ጥናቶች ብድር እያገኙ የራሳቸውን ስራ መፍጠር እየጀመሩ ነው። እነዚህ ልምዶች የሚያሳዩን ወጣቱ የስራ ፈጠራ አቅሙን ተጠቅሞ ራሱን ሲያሳድግ አገሮች ፈጥነው እንደሚያድጉ ነው።

ዛሬ ባደጉት አገሮች ብዙ ስራ ፈጣሪዎች አሉ። የኢንተርፕረነሮች ቁጥር መጨመር በመላው ዓለም

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን



61

በኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብ ሁሉም ሰው አሁን ካለበት ወደ ላቀ ከፍታ መሸጋገር ይችላል፤ እግረ መንገዱንም የማኅበረሰቡን ችግር ያቃልላል። ይህ ሲሆን የአገር፣ የአህጉር እና የዓለም ገጽታ እና አኗኗር ይቀየራል፣ ይዘምናል፣ ያድጋል። በውጤቱም ዓለም ለሰዎች ምቹ፣ ተስማሚ እና ቀላል ትሆናለች።

ኢንተርፕረነርሺፕ ለኢኮኖሚው ኢትዮጵያ በዓለምም ሆነ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛታቸው ከሚታወቁ አገሮች መካከል ነች። ከሕዝቧ 70 በመቶው ደግሞ ዕድሜው ከ30 በታች እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህም ኢትዮጵያን የወጣቶች አገር የሚል ስያሜ አሰጥቷታል።

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን እንደሚገልጹት፤ ከኅብረተሰቡ ውስጥ ከ25 በመቶ በላይ የሚሆነው በተለያዩ ደረጃዎች ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኝ ነው።

ይህ አሃዝ በቴክኒክ እና ሙያ፣ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመረቁትን እንዲሁም ትምህርታቸውን የሚያቋርጡትን እንደሚጨምር ጠቅሰዋል። ስለሆነም ከአገራችን ሕዝብ አብዛኛው መስራት/ማምረት በሚችልበት የወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ነው። በአገራችን ያለው አጠቃላይ የስራ አጥነት ምጣኔ ከፍተኛ ነው። “በኢትዮጵያ የስራ አጥነት ችግር የኢኮኖሚው አንዱ ስብራት ነው።” በማለት ነው ሚኒስትር ዴኤታው የስራ አጥነቱን ደረጃ የገለጹት። አያይዘውም “የስራ አጥ ምጣኔው በኢኮኖሚው ውስጥ ዕድሜው ለስራ የደረሰ ነገር ግን በዘላቂ እና አርኪ የስራ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ ያልቻለው የኅብረተሰብ ክፍል ከፍ ያለ ነው” ብለዋል። ይህን በከተማ እና በገጠር ስናወዳድረው በተለይ በከተሞች ያለው ምጣኔ ከፍተኛ ነው፤ በጾታ ስናየው ደግሞ የሴቶች ምጣኔ ይበልጣል።

“ኢትዮጵያ ወጣቶች የሚበዙባት አገር ናት። ይህን ኃብት አቅጣጫ አስይዞ፣ ራዕይ አስቀርጾ፣ አስፈላጊውን የፋይናንስ፣ የገበያ ጥናት አገልግሎት እና የመስሪያ አካባቢዎች አመቻችቶ ወጣቱን ባለሃብት ማድረግ ይቻላል።” ይሉናል ዶ/ር ወሮታው በመጽሐፋቸው ባሰፈሩት ሃሳብ። እንደ እርሳቸው እምነት “በኢትዮጵያ ወጣቱ ስራ ፈጣሪ ሲሆን አገራችን በአጭር ጊዜ ከድህነት እና ኋላቀርነት መውጣቷ እውን ይሆናል።”

በኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የአቅም ግንባታ ፕሮግራም አስተባባሪው አቶ ቦሩ ሻና በበኩላቸው በአገራችን የኢንተርፕሩነርሺፕ ሥነ- ምህዳር እንዲጠነክር፣ እንዲጎለብት እና ስኬታማ የሆኑ ኢንተርፕረነሮች የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ ማገዝ ከኢንስቲቱዩቱ ዓላማዎች መካከል እንደሆነ ጠቅሰው የራሳቸውን ስራ መጀመር የሚፈልጉ ኢንተርፕረነሮች

ሃሳባቸውን መሬት ላይ አውርደው ወደ ትልቅ ደረጃ መሸጋገር የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

የኢንተርፕረነርሺፕን አስተሳሰብ በመላበስ የስራ ዕድል የመፍጠር ጉዳይ ለአገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ ነው። ሚኒስትር ዴኤታው ኢንተርፕረነርሺፕ ለአገሪቷ ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋጽኦ “የስራ አጥነት የኢኮኖሚው አንዱ ማነቆ ነው ካልን፣ የስራ ፈጠራ ጉዳይ ደግሞ ማነቆውን የሚፈታ ነው። ለዚህ ደግሞ የኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብ ግንባታ በእጅጉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የአገራችንን ኢኮኖሚ ሊያነቃቃ የሚችል ቁልፍ ጉዳይ ነው።” በማለት ነው የገለጹት።

ከስራ አጥ ምጣኔው ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ነው። “ወጣቱ በአግባቡ ከተደገፈ፣ ያላየውን ጸጋ እንዲያይ ከተደረገ፣ ስልጠና እና የመንግሥት ድጋፍ ካገኘ የስራ አጥ ምጣኔውን በመቀነስ አምራች መሆን ይችላል” ሲሉም አብራርተዋል። አቶ ንጉሱ አያይዘውም በዋጋም በጥራትም ተወዳዳሪ ምርት በማምረት ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የምናስገባቸውን ምርቶች ማስቀረት ይቻላል። ከዚህ ባሻገርም ወደ ውጭ አገሮች የሚላክ ምርት በማምረት የኢኮኖሚው ትልቁ ትኩሳት እና ችግር የሆነውን የዋጋ ንረት እና ግሽበት የመቆጣጠር እና የማስቀረት ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ስለሆነም የስራ ዕድል ፈጠራ ዜጎች ለዕለት ተዕለት ጉርሳቸው እና ቀለባቸው የሚውል እና የሚያኖራቸው ብቻ አይደለም። ከዚህ በላይ ኃብት ከመፍጠር፣ ምርት እና ምርታማነትን ከማሳደግ ጋር ጭምር የተያያዘ ነው። ይህ እውን ሲሆን አንድም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከማስቀረት ባሻገር ምርቶቹን ለዓለም ገበያ ማቅረብ ይቻላል። የዚህ ውጤት ደግሞ የኢኮኖሚው ማነቆ የሆነውን የዋጋ ንረት በመቀነስ ኢኮኖሚው እንዲረጋጋ ያግዛል።

“ሃሳብ ይዘው ለሚመጡ ሰዎች ሃሳባቸውን እንዴት ነው ወደ ቢዝነስ መቀየር የሚቻለው የሚለው ላይ ትኩረት ማድረግ መልካም ነው። የሰዎች ሃሳብ ተመዝግቦ ቁጭ ከሚል እሱን ተግባራዊ ለማድረግ መስራት ያስፈልጋል።” የሚሉት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የፖርት ፎሊዮ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ተገኘ ትልቁ ስራ ፈጠራ ይህ እንደሆነ ይገልጻሉ። የዚህ ፋይዳ ትልቅ እንደሆነ ጠቅሰው የሃሳብ ባለቤትነት መብታቸው ተከብሮላቸው፣ በግለሰብም ይሁን በመንግሥት ደረጃ የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ስራ መቀየር እንደሚገባም ይመክራሉ።

በተያያዘም ኢንተርፕረነርሺፕ እና የስራ ዕድል ፈጠራ በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ቁልፍ ተግባሩ አድርጎ እንደያዛቸው ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።

የመንግሥት እና የአጋር አካላት እንቅስቃሴ

ቀደም ሲል እንደተገለጸው ኢንተርፕረነርሺፕ ለኢትዮጵያ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው። ይህ ከሆነ ታዲያ ስራውን የሚመሩት አካላት እንዴት እየተንቀሳቀሱ እንደሆ መመልከት ተገቢ ነው። መንግሥታዊ ከሆኑ ተቋማት መካከል ስራውን በበላይነት እንዲመራ፣ እንዲያስተባብር እና እንዲደግፍ ኃላፊነት የተሰጠው የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ነው። በአገራችን የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት መዋቅር ማሻሻያ ሲደረግ እንደ አዲስ ከተዋቀሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል አንዱ ሆኖ እንዲደራጅ ተደርጓል።

አቶ ንጉሱ ይህን አስመልክተው ሲገልጹ “አዲስ አደረጃጀት ሲፈጠር የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ዕድል ፈጠራን፣ የክህሎት ግንባታን፣ የአሰሪ እና ሠራተኛ ግንኙነትን በማዕከል ሆኖ እንዲከታተል፣ እንዲያስተባብር፣ እንዲደግፍ፣ እንዲመራ እና እንዲቆጣጠር ስልጣን ተሰጥቶት በተቋማዊ ቁመና ተደራጅቶ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል።” ነው ያሉት።

የኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብ አለመዳበር ከስራ ዕድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለዩት እንቅፋቶች አንዱ ነው። ከዚህም ባሻገር ገበያው የሚፈልገውን ብቃት፣ ክህሎት፣ አመለካከት አለመላበስ እና በአቅርቦትም ረገድ ሰፊ ውስንነቶች መኖራቸው ይታወቃል።

ዜጎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት ሰርቶ ማደግ እንደሚቻል፣ ጸጋን እንዴት መለየት እንደሚችሉ፣ የሥራ ዕድል ከፈጠሩ በኋላ ስራቸውን እንዴት ሊመሩ ይችላሉ፣ ገበያ ያፈላልጋሉ፣ ከሰው (ከደንበኞቻቸው) ጋር እንዴት ይግባባሉ፣ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና አጠቃቀማቸው ምን መሆን አለበት የሚሉት ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ አንደኛው ተግባሩ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የስራ ፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች ሃሳባቸው ወደ አደባባይ እንዲወጣ፣ ከተወዳደሩ በኋላ አሸናፊዎቹ ባለ ሃሳብ (ከአጋር አካላት ጋር በመሆን) መነሻ ካፒታል እንዲያገኙ ይደረጋል። ባለ ሀሳብ እየተከታተሉ በመደገፍ ደረጃ በደረጃ ራሳቸውን እንዲችሉ እየተሰራ ነው። ከዚህም በሻገር ያደጉ እና የለሙ ኢንተርፕራይዞች እንዲሆኑ እና ለበርካቶች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ፣ ምርታቸውም በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን በማድረግ የተጀመረ ስራም አለ።

በዚህም ወደ 13 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች በቡድን እና በግል ሃሳቦቻቸውን አቅርበዋል። በተለያዩ ዙሮች ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ አሸናፊዎቹ የሚለዩበት አሰራርም ተዘርግቷል። እስከ አሁን አንድ ሺህ ያህል ሃሳቦች



62

ለውድድር ቀርበዋል። እስከ አሁን በአምስት ዙር ወደ 300 ባለ ሃሳቦች መነሻ ካፒታል ተሰጥቷቸው ሃሳቦቻቸውን ወደ ስራ እንዲቀይሩ ለማስቻል እየተሰራ ነው። ቁጥሩን የገደበው የአቅም ውስንነት መሆኑን የሚናገሩት አቶ ንጉሱ ግለሰቦች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የፋይናንስ እና የኢንሹራንስ ተቋማት፣ አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቀው በጎ ምላሽ እየተገኘ መሆኑን ጠቅሰዋል። በአንድ ዓመት ውስጥ ከ100 በላይ ሃሳቦችን አወዳድሮ ሽልማት ለመስጠት፣ መስሪያ እና መሸጫ ቦታም ለማመቻቸት ዕቅድ ተይዟል።

የፋይናንስ፣ የመስሪያ እና የመሸጫ ቦታ አቅርቦት፣ የገበያ ትስስር፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ከመንግሥታዊ ድጋፎች መካከል ናቸው። በአገር አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 184 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በማዕከላቱ ስራ አጥ ወጣቶችን የመለየት፣ የመመዝገብ፣ ለስልጠና የማመቻቸት ተግባራት ይከናወናሉ። በእነዚህ ማዕከላት ሌሎች 13 የሚሆኑ አገልግሎቶችም ይሰጣሉ።

ይህን የመንግሥት ድጋፍ ተጠቅመው ትልቅ ደረጃ የደረሱ በርካቶች ናቸው። ከእነዚህም መካከል አቶ ኃብታሙ መንገሻ አንዱ ነው። አቶ ኃብታሙ “ወደ ጥቃቅን እና አነስተኛ ስራ ለመግባት ምን አነሳሳህ?” ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ “ወደዚህ ስራ እንድገባ ያነሳሳኝ ስራ አጥነቴ ነው። ለአካል ጉዳተኛ ተደራሽ የሆነ ስራ ብዙም አልነበረም። ስለዚህ የግድ ውስጤ ያለውን ነገር መፈለግ ነበረብኝ።” ሲል ነው ምላሽ የሰጠው። ስራ ፈጣሪው “የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት ጥረት ይጠይቃል፤ እኔን መንግሥት

የመስሪያ ቦታ እና ብድር በመስጠት ባይደግፈኝ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሴ የሚታሰብ አይሆንም ነበር” ሲል እገዛው ምን ያህል እንደጠቀመው ይናገራል።

የሥራ ዕድል ለመፍጠር የመጀመሪያው ጉዳይ ሃሳብ እንደሆነ ግልጽ ነው። አዳዲስ አስተሳሰብ ለማፍለቅ ደግሞ ኢንተርፕረነርሺፕን ማስፋፋት ይጠይቃል። “የስነ-ልቦና ውቅር ለውጥ ማምጣት ወሳኝ እንደሆነ ታምኖበት፤ ይህን ሊመራ የሚችል ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆነ የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (ቀደም ሲል ማዕከል የነበረ) ተቋቁሟል።” ሲሉ በመንግሥት በኩል የተሰጠውን ትኩረት ያስረዳሉ አቶ ንጉሱ። ኢንስቲትዩቱ የኢንተርፕረነርሺፕን አመለካከትና አስተሳሰብ የማዳበር ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ሰዎችን የማብቃት፣ የማሰልጠን፣ የማነቃቃት፣ የመደገፍ፣ የንግድ ስራ አመራር ጥበብ እና እውቀት በማስጨበጥ ተነሳሽነትን ለመፍጠር ይሰራል።

አቶ ቦሩ በበኩላቸው የኢንተርፕረነርሺፕ አመለካከት በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲሰርጽ፤ የአገራችን ባሕል እንዲሆን እንድንሰራ ኃላፊነት ተሰጥቶናል ይላሉ። እንደ እርሳቸው ገለጻ “ሰው በሚሰራበት ቦታ ላይ ውጤት አምጥቶ ማለፍ እንዳለበት እና በተለመደው አሰራር አልሰራም ብሎ ማሰብ ሲጀምር የኢንተርፕረነርሺፕ ባሕል ዳብሯል” በየትኛውም ዘርፍ (በመንግስት፣ በግል) የሚሰራ ዜጋ ተጨማሪ እሴት ፈጥሮ ኃብት ማምጣት የሚያስችል ስራ ለራሱም፣ ለአገሩም ሲሰራ ነው ለውጥ መጣ የምንለው።

አቶ ቦሩ “ስራ ፈጣሪዎች ስራ ሲጀምሩ ብዙ ተግዳሮቶች

ይገጥሟቸዋል። ተግዳሮቶቹ በአንድ ተቋም ብቻ የሚፈቱ ስላይደሉ በአገር ደረጃ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል። በኢንተርፕረነርሺፕ ስኬታማ ለመሆን በአገራችን ያለውን ስነ-ምህዳር ተስማሚ ማድረግ ያስፈልጋል” ይላሉ። ስነ- ምህዳሩን ሲያብራሩም “የመንግስት የፖሊሲ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል። ሰው ብዙ ወጪ ሳያወጣ ንግዱን ከፍቶ የሚሰራበት ቀለል ያለ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግም ይጠይቃል” ነው ያሉት።

የኢንስቲትዩቱ አንደኛው አብይ ተግባር ለስራ ፈጣሪዎች ምቹ እና ተስማሚ ከባቢ እንዲኖር መስራት ነው። “ለዚህም እንዲረዳ ለባለድርሻ አካላት፣ ለመንግስት ሠራተኞች፣ ለባለስልጣናት እና ለኢንተርፕረነሮች የሚሰጡት ድጋፎች የሚመቹ እንዲሆኑ መንገድ የሚያሳዩ ስልጠናዎችን እየሰጠን ነው።” የሚሉት አቶ ቦሩ ሻና ናቸው። ከ150 ሺህ በላይ ኢንተርፕረነሮችን አሰልጥነናል ሲሉም ገልጸዋል። ከ250 በላይ አሰልጣኞች እና ከ600 በላይ የንግድ አማካሪዎችን ማብቃታቸውን ይህም የኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብን እና ስራ ፈጠራን ለማስፋት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቅሰዋል።

የሰለጠኑት ወደ ስራ ከገቡ በኋላ በንግድ ስራቸው ላይ ስኬታማ እንዲሆኑ የማማከር አገልግሎት ያገኛሉ። ተቋሙ ያሰባሰበው መረጃ እንደሚያሳየው ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት አግኝተው ንግዳቸውን ስላስፋፉ በሚፈጥሩት የሥራ ዕድል ላይ የ4 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት ታይቷል። ይህ መረጃ አመለካከት እና የስራ ባሕል ላይ ከተሰራ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አመላካች ነው።



63

የቀጣይ ውጥኑን “ብዙ አካል ጉዳተኛ ባሉባት አገር ብልጽግናን ለማምጣት፣ ልማቱን ለማሳካት ይህን የኅብረተሰብ ክፍል ማሳተፍ ይጠይቃል። እኔም በምሰራቸው ስራዎች እነሱን ለማካተት እጥራለሁ። ከዚህ ባሻገርም ተቋማትን ይዘው መምራት እንደሚችሉ ማሳየት እፈልጋለሁ። አንድ ፕሮጀክት ለልማት ባንክ አስገብቼ እየታየ ነው። ወደ ስራው ስገባ ለ500 ሰው የሥራ ዕድል ይፈጥራል። ትልቁ ሕልሜ ይህን ፕሮጀክት ማሳካት ነው። አካል ጉዳተኞች ቁጭ ብለው ሊሰሩት የሚችሉት ፕሮጀክት ነው።” ይላል ስራ ፈጣሪው ሐብታሙ።

“እኔ በሄድኩበት መንገድ ለመሄድ የሚጠይቀው ቁርጠኝነት ነው። እንደ እኔ ዓይነት ሰው እዚህ መድረስ ከቻለ ከእኔ የተሻሉ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ደረጃ ለመድረስ ምንም አያግዳቸውም፤ ራሳቸውን ማሳመን እና ጥረት ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው።” በማለትም ተሞክሮውን እና ለስራ ፈላጊ ወጣቶችም መልዕክቱን አስተላልፏል ኃብታሙ። ተምሮ የወጣውም ቢሆን የአገሪቷን ተጨባጭ ሁኔታ በማየት ዝቅ ብሎ ሙያ ተምሮ ራሱን ለማሳደግ መስራት እንደሚኖርበትም ይመክራል።

“በአገራችን በርካታ ስራ አጥ አለ፤ ለእነዚህ ስራ አጦች ተስማሚ የሆነ የስራ አካባቢ ለመፍጠር በመንግሥት በኩል የሚጠበቀው ትልቁ ነገር ኢንደስትሪውን ማስፋፋት ነው። ሰፋፊ ኢንደስትሪዎች ያስፈልጋሉ። ባለሃብቱም ህንጻ ገንብቶ ከማከራየት ይልቅ ወደ ኢንደስትሪው ዘርፍ እንዲገባ መሰራት አለበት። መንግሥት በጣም አስፍቶ ኢንደስትሪው ላይ ከሰራ በጣም ሰፊው የሰው ኃይል ወደዛው እንዲገባ ያደርጋል።” ሲል አስተያየቱን የሰነዘረው ስራ ፈጣሪው ባለኃብት ሐብታሙ መንገሻ ነው።

ነገን ወርቃማ ለማድረግ በአገር በቀል ኢኮኖሚው ትኩረት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች አንዱ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። በአገር በቀል ኢኮኖሚው አምስት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና አይሲቲ ዘርፎች ናቸው። በዚህም 11 ዘርፎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እምቅ አቅም እንዳላቸው ተለይተው እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ይህ በ10 ዓመቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ የድርጊት መርሃግብር ተለይቶ ተቀምጧል።

በ10 ዓመቱ መሪ ስትራቴጂክ፣ በአምስት ዓመቱ ስትራቴጂክ እንዲሁም የ10 ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ መሪ ዕቅዶች ተዘጋጅተዋል። በ2017 ዓ.ም ለ14 ሚሊዮን ዜጎች አዳዲስ የስራ ዕድሎች እንደሚፈጠሩ ታሳቢ የተደረገ ሲሆን በ2022 ዓ.ም ደግሞ ለ20 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በስትራቴጂው የድርጊት መርሃግብር ላይ ተመላክቷል።

“የት አካባቢ ምን ዓይነት ጸጋ አለ? በምን ሁኔታ ላይ ተመስርተን ብንሰራቸው ከፍተኛ የስራ ዕድል ሊፈጠር

ይችላል? የሚለው እየተለየ በንዑሳን ዘርፎች ጭምር በዕቅድ እንዲያዝ እየተደረገ ነው። በቀጣይም ለ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየሰራን ነው።” ሲሉ የትኩረት አቅጣጫውን ያብራሩት ሚኒስትር ዴኤታው ናቸው። ከዚህ ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነው በቅጥር፣ 60 በመቶ በኢንተርፕራይዝ በመደራጀት የሚፈጠር የሥራ ዕድል እንደሆነ ጠቁመዋል።

“የ2015 በጀት ዓመት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ በማቋቋም የሥራ ዕድል እንዲፈጠርባቸው፣ የተፈጠሩት የስራ ዕድሎች እንዲያንሰራሩ የምናደርግበት እና በመደበኛነት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የምንሰራበት ዓመት ነው።” ሲሉም የተያዘውን ውጥን አብራርተዋል።

በመንግሥትም ይሁን በየትኛውም የግል ድርጅት ያሉትን ክፍት ቦታዎች በመጠቀም ዜጎች በስራ ቅጥር ውስጥ እንዲሰማሩ ማድረግ አንደኛው አማራጭ ነው። ነባር የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ በማብቃት የስራ ዕድል የመፍጠር አቅማቸውን በማሳደግ የራሳቸው ስራ እየፈጠሩ እንደገና ለሌሎች ስራ ፈጥረው ቀጣሪ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው። ስለሆነም በሁለት መልኩ የስራ ዕድል ፈጠራው ይከናወናል።

ድጋፎቹን በተደራጀ ሁኔታ በመስጠት ኢንተርፕራይዝ እንዲያቋቁሙ፤ የተቋቋሙት ኢንተርፕራይዞች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ስራ ፈጣሪዎችን የማበረታታት ተግባር እንደሚያከናውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል። በጥቅሉ ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር የመንግሥት ሚና በማዕከል ሆኖ ማስተባበር፣ ማቀናጀት፣ መከታተል፣ መደገፍ ነው።

የስራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካላቸው መካከል ከዘጠኝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ተደርጓል። ከእነዚህም ውስጥ ግብርና፣ ኢንደስትሪ፣ ንግድ፣ መስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች፣ ቱሪዝም፣ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ይገኙበታል። ከዚህ ባሻገር ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከትላልቅ ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱንም እንዲሁ።

ከአመለካከት ጋር የሚያያዙ በርካታ ጉዳዮች ስላሉ ስራ አጥነት እንደዚህ በአንድ ጊዜ የሚቀረፍ ችግር አይደለም። ከአፀደ ሕጻናት ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ በየደረጃው የሚያድግ ስራ ለመስራት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቅሰዋል።

ከክልሎች ጋር፣ ክልሎች ከዞኖች ጋር፣ ዞኖች ከወረዳዎች ጋር ቁጭ ብለው ጸጋቸውን እና የስራ አጥ ቁጥራቸውን ይለያሉ። ስልጠና እና ከስልጠና ጋር ተያያዥ የሆኑ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይሰጣል። መንግሥትም የመስሪያ እና የመሸጫ ቦታ በማቅረብ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንደሚሰራ አስታውቋል። መንግሥት የቢዝነስ ልማት የገበያ ስራውን ለመደገፍ እና ፋይናንስ ለማቅረብ ያለውን

አቅም በማጣጣም እንደሚሰራ አቶ ንጉሱ አብራርተዋል። አያይዘውም ከሃሳብ ውድድር ጋር በተያያዘ የተጀመረውን ስራ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንዲደግፉ፤ ባለድርሻ አካላትም ይህንን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን ትልቅ ተጋድሎ እንዲያግዙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሥራ ዕድል ፈጠራው ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የቅንጅት ስራን የሚጠይቅ ነው። ስለሆነም የስራ አጥነት ምጣኔን ለመቀነስ መንግሥት፣ የግሉ ዘርፍር እና ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊረባረቡ ይገባል። ይህን በማድረግ ረገድ ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወተው መንግሥት ነው። የግሉ ዘርፍ የስራ ዕድል የመፍጠር ዋነኛ ተዋናይ ሲሆን አጋር አካላት ደግሞ በደጋፊነት የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ።

የመንግሥት ፖሊሲ ለኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብ ማደግ አንዱ ምክንያት ነው። መንግሥት ስራ ፈጣሪዎችን በተግባር የሚያበረታታ ሲሆን ኢንተርፕረነሮች ትልቅ ተነሳሽነት አግኝተው በመስራት ያድጋሉ። “የኤዢያን ታይገርስ የሚባሉት አገሮች ትልቅ ለውጥ ማምጣት የቻሉት መንግሥታቸው ከውጭ የሚመጣ ድጎማ እና እገዛ እኔን ይለውጠኛል ከሚል አስተሳሰብ ወጥቶ፣ ወደ ውስጤ ተመልክቼ ራሱን የሚቀይር ዜጋ መፍጠር አለብኝ ብለው ዜጋ ተኮር ስራ ሰርተው ነው።” የሚሉት አቶ ቦሩ ይህም ኢኮኖሚያቸው ካደጉት አገሮች ተርታ ለማሰለፍ እንዳስቻላቸው፤ ቻይናም በዓለም ላይ ኃያል ለመሆን የበቃችው የራሷን አቅም ስለተጠቀመች እንደሆነ አብነት በመጥቀስ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ መልክ መሰራት አለበት ይላሉ።

ሲጠቃለል የፈጠራ ሰዎችን ማበረታታት ከአስተዳደግ መጀመር አለበት። ወላጆች ልጆቻቸው መስማትና መናገር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ መልካም መልካሙን በአዕምሯቸው መመዝገብ አለባቸው። ኢንተርፕረነርሺፕ የሚፈጠርበት ሌላው ቦታ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤት የሰውን ልጅ ወደ ተሻለ ነገር ማድረስ የሚችል እውቀት የሚመግብ ማዕድ ነው። ስለሆነም ትምህርት ቤት ሁለገብ የሆነ እውቀት፣ ሙያ፣ ባሕሪይ የሚያስጨብጠን አካባቢ እንዲሆን መስራት ያሻል።

የስራ ፈጠራ ተነሳሽነት ኖሯቸው ለሚፍጨረጨሩ ልጆች እንደ ቤተሰብ አጋሮች፣ እንደ ኅብረተሰብ ብዙ አድገው ፈጥነው እንዲሄዱ ማበረታታት እንዳለብን ይመከራል። እነዚህን ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ከቻልን ስራ ፈጣሪዎች በርክተው ኢኮኖሚውን ያሳድጋሉ። ስራ ፈጣሪ ዜጎቿ የውበቷ፣ የዕድገቷ፣ የሁለንተናዋ ፈርጦች ናቸውና በስራ ፈጣሪ ወጣቶቿ ትጋት መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ብሎም ለኢትዮጵያዊያን ወርቃማ ይሆናል።



64

ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 22 ኅዳር 2015 ዓ.ምየጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ



65

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች የወባ በሽታ በስፋት ይታያል። በሽታው ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ ዋነኛ የጤና ጠንቅ ሲሆን፤ በተለይ ሰራተኛውን ኃይል ስለሚያጠቃ የማኅበራዊ ዕድገት ችግር መሆኑ በግልጽ ይስተዋላል።

ከኢትዮጵያ መልከዓ ምድር 75 በመቶ የሚሆነው ለወባ በሽታ ስርጭት ምቹ ሲሆን፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው 52 በመቶ ሕዝብ ለበሽታው የተጋለጠ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የወባ በሽታ በአብዛኛው የሚከሰተው የክረምት መውጫን ተከትሎ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ባለው ወቅት ነው። ይህም በመኸር ወይም በምርት መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ በሽታውን መከላከል ካልተቻለ ሰዎችን ለህመምና ለሞት ይዳርጋል። በተጨማሪ ገበሬዎች የግብርና ሥራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ፣ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ውጤታማ ሥራ እንዳይሰሩ፣ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ በማድረግ በማኅበራዊ መስተጋብርና በኢኮኖሚ እድገት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በተለይ የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ ሲከሰት በርካታ ሰዎችን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ለህመምና ለሞት ይዳርጋል። በዚህም የዕለት ተዕለት የግብርናን ስራ፣ የንግድና ቱሪዝም እንቅስቃሴ ያስተጓጉላል፤ በአገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

“ትንኝ ለመራባት . . . “

መንገሻ ገ/ሚካኤል



66

የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፤ በ2021 በዓለም አቀፍ ደረጃ የወባ ታማሚዎች ቁጥር በ2020 ከነበረው በአሥራ አራት ሚሊዮን ጨምሯል። ከ90 በመቶ በላይ ጭማሪ የተመዘገበው ደግሞ ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮች ውስጥ ነው።

ኢትዮጵያ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም ለማስወገድ የተለያዩ ስልቶችን ነድፋ ስትተገብር ቆይታለች። ከነዚህ ስልቶች መካከል የወባ ትንኝ ቁጥጥር ስራዎች ማከናወን አንዱ ነው። የመኝታ አጎበር ገዝቶ ማሰራጨት፣ የቤት ውስጥ የፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማካሄድና የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎችን መስራትን ያካትታል። የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መተግበር፣ የበሽታውን ቁጥጥር ቅኝት ማጠናከርና አስፈላጊውን እርምጃ በወቅቱ መውሰድ እንዲሁም፤ የወባ በሽታ ምርመራና ሕክምና አገልግሎት በየጤና ተቋማቶች በነፃ መስጠትም የወባን ስርጭት ለመቆጣጠር ያስችላሉ ተብሎ ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩ ስልቶች ናቸው።

በዚህም በወባ በሽታ ምክንያት የሚከሰተውን የህመምና የሞት መጠን በመቀነስ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር የወባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ጉዲሳ ወባን ለመከላከል በተደረገው የመድኃኒትና የአጎበር ስርጭት እንዲሁም ሕብረተሰቡ የወባን በሽታ ከመከላከል አንፃር ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የወባ ስርጭት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የወባ ህመም በ2012 ዓ.ም ከነበረው አንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ወደ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዝቅ እንዲል ተደርጓል። እንዲሁም በወባ ምክንያት የሚሞቱ ህሙማንን ምጣኔም ከ 0 ነጥብ 39 በመቶ ወደ 0 ነጥብ 28 በመቶ ለመቀነስ ተችሏል።

ይሁን እንጂ በ2014 በጀት ዓመት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች በተለይም በደቡብ (ከምባታ ጠምባሮ) ፣ ደቡብ ምዕራብና (ቤንች ሸኮ ዞን) ፣ ኦሮሚያ (ምዕራብ አርሲ፣ ኢሉባቦር፣ ምስራቅ ወለጋ) እንዲሁም በአማራ (ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር) ዞኖች በሚገኙ አካባቢዎች በተለያየ ምክንያቶች “በተለይ የበልግ ዝናብ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የወባ ህሙማን ቁጥር ሪፖርት ተደርጓል” ብለዋል አቶ ጉዲሳ።

አቶ ጉዲሳ እንደተናገሩት፤ በ2014 በጀት ዓመቱ የወባ ህመም ይዟቸዋል ተብሎ ለተጠረጠሩ 7 ሚሊዮን 545 ሺህ 420 ለሚሆኑ ሰዎች የላቦራቶሪና የፈጣን ምርመራ ተደርጓል። ከእነዚህ መካከል በወባ በሽታ መያዛቸው ለተረጋገጠ 1 ሚሊዮን 345 ሺህ 586 ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ተሰጥቷል። ከ2013 ዓ.ም ከተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በ10 ነጥብ 3 ከመቶ ጨምሯል።

አስተባባሪው የወባ ህሙማን ቁጥር መጨመር ምክንያት ያሏቸውን ሲያብራሩ ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ የሆነ የአየር ሁኔታ መኖሩ፣ ከአየር ንብረቱ ጋር ተያይዞ ድርቅ የነበረባቸው አካባቢዎች ዝናብ መዝነቡ፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የተሳለጠ የፕሮግራም አተገባበር ላይ ክፍተት መኖሩ፣ የማኅበረሰብና በግለሰብ ደረጃ የሚካሄዱ የወባ መከላከል ስራዎች መስራት ላይ በተለይም የአጎበር አጠቃቀምና የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች ላይ ክፍተትና መዘናጋት መፈጠሩ፣ በግብርና ልማት ስራዎች መስፋፋት ምክንያት ለወባ ትንኝ መራባት ምቹ የሆኑ ቦታዎች መኖራቸው በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

የተሰጡ ምላሾችና ቀጣይ ስራዎች አሁን የሚታየውን የወባ በሽታ ስርጭት መጨመር ለመግታት የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ የሚናገሩት አስተባባሪው አቶ ጉዲሳ፤ የበሽታው ወቅታዊ ስርጭትን አስመልክቶ በየሳምንቱ የሚመጡ መረጃዎችን “ለውሳኔ አሰጣጥ በሚረዳ መልኩ በመተንተን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል” ብለዋል።

እንደ አቶ ጉዲሳ ገለጻ፤ የወባ ስርጭት በጨመረባቸው አካባቢዎች የጤና ባለሙዎች ተመድበው ሙያዊ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ። እስከ አሁንም አምስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህሙማንን ለመመርመር የሚያስችል ፈጣን የወባ መመርመሪያ ኪት (RDT) እንዲሁም አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህሙማንን ማከም የሚያስችል የፀረ- ወባ መድኃኒት ስርጭት የተካሄደ ነው። ይህም የሕክምናና የምርመራ ግብዓት እጥረት አለመኖሩን እንደሚያሳይ ነው አስተባባሪው ያብራሩት።

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል በመጀመሪያ ዙር ሁለት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊያን አጎበር ተገዝቶ ተሰራጭቷል። በተጨማሪም 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን አጎበር በግዥ ሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በታቀደለት የጊዜ ገደብ ሲገባ ወዲያውኑ የሚሰራጭ ይሆናል።

“አንድ ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ቤቶችን ለመርጨት የሚያስችል የጸረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ተገዝቶ ወደ ወረዳዎች ተሰራጭቶ የርጭት ስራ ተሰርቷል” በማለት አቶ ጉዲሳ ገልጸዋል። የፕሮግራም አተገባበሩን ለማሻሻል ለሁሉም ክልሎች በበጀት ዓመቱ ከ280 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል።

“የበሽታውን ስርጭት በመቀልበስ፣ በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤቶች እየተገኙ ናቸው” የሚሉት አቶ ጉዲሳ፤ በቀጣይም በዋነኛው የወባ በሽታ መተላለፍያ ጊዜ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ የምላሽ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የወባ በሽታን ጨርሶ ለማጥፋት በጤና ሚኒስቴር የወባ በሽታን እ.ኤ.አ በ2030 ከኢትዮጵያ

ጨርሶ ለማጥፋት የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ ተነድፎ ወደ ተግባር መገባቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ”ወባን በምን መልኩ ማጥፋት ይቻላል የሚለውን አቅጣጫ የሚያሳይ” የወባ በሽታ ማጥፊያ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቷል። ፍኖተ ካርታው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለ ነው። በአንደኛ ምዕራፍ ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት ያሉባቸው ቦታዎች ላይ የወባን ጫና መቀነስ የሚል ግብ ይዟል። በሁለተኛው ምዕራፍ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር መቀነስ፣ በመጨረሻም ዝቅተኛ የወባ ስርጭት ያሉባቸው ወረዳዎችን ለይቶ ወደ ዜሮ በማድረስ ወባን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ግቡን ማሳካት ይሆናል።

ቅደመ ጥንቃቄ “ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ድረስ ያለው ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል” የሚሉት አስተባባሪው፤ ለወባ ትንኝ መራቢያነት ምቹ የሚሆኑ አካባቢዎችን ሕብረተሰቡ በመለየት የማፋሰስና የማዳፈን ተግባራት ማከናወን እንደሚኖርበት ነው የገለጹት። ሕብረተሰቡ የወባ መተላለፊያ ወቅትን በመገንዘብ ራሱንና ሕብረተሰቡን ከበሽታው መጠበቅ ይገባዋል።

ሕብረተሰቡ ውሃ የሚያቁሩና በተለይ በቤቶች አካባቢ ለትንኝ መራቢ የሚሆኑ የተከማቹ ውሃዎችን ማፋሰስ፣ በእንስሳትና ሌሎች መኖሪያ አከባቢዎች ያሉ ጉርጓዶች ውሃ እንዳይዙና ለትንኝ ምቹ እናዳይሆኑ መከታተል ያስፈልጋል። ሁልጊዜ የመኝታ አጎበርን መጠቀም መዘንጋት የለበትም።

ትንኝ ለመራባት ትንሽ ውሃ ብቻ እንደሚበቃት የሚናገሩት አቶ ጉዲሳ፤ በቤት አካባቢ የሚገኙ ኩሬዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራ ከሕብረተሰቡ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።

ሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አጎበር በአግባቡ መጠቀም ሌላው የወባ በሽታን ለመቆጣጠር ከሕብረተሰቡ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው። አንድ አጎበር በትንሹ ከሶስት እስከ አምስት ዓመት ያገለግላል። የተቀደዱ ካሉ እነዚያን ጠግኖ፣ የቆሸሹ ካሉ አጥቦ በወባ መተላለፊያ ወቅት ሁሌ በመኝታ ጊዜ መጠቀም ይጠበቅባቸዋል።

በሌላ በኩል አንድ ርጭት ከተካሄደ በትንሹ ለስድስት ወር ስለሚያገለግል “የተረጩ ቤቶች ላይ ምንም ዓይነት ቀለምም ሆነ ጭቃም ሆነ እበት መለቅለቅ፣ ጋዜጣ መለጠፍ አያስፈልግም” ብለዋል።

የወባ ምልክት ሲታይ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ መመርመርና መድኃኒትን ሳያቋርጡ መውሰድ ያስፈልጋል። የወባ በሽታ ሕክምና ከጤና ኬላ እስከ ሆስፒታል ደረጃ እንደሚሰጥ የሚያናገሩት አስተባባሪው፤ የወባ በሽታ ምልክት የሚታይባቸው ሰዎች ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ሕክምና ማግኘት እና የሚሰጡ መድኃኒቶቹን በትክክል መውሰድ ይኖርባቸዋል።

የ ጤ ና ባለሙያዎች የወባ በሽታ መተላለፊያ ወቅት መሆኑን አውቀው ሁልጊዜ የወባ ሕክምና ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረው፤ የወባ በሽታ መድኃኒቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ነው ያስረዱት።

ተግዳሮት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የገጠሙ አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ የሚያነሱት አቶ ጉዲሳ፤ የወባ በሽታ መከላከያና ማከሚያ ግብዓቶች (መድኃኒቶችና መመርመሪያ መሳሪያዎች) በበቂ ደረጃ የሚሰራጭ ቢሆንም፤ በአንዳንድ ጤና ተቋማት መቆራረጥ መኖሩ፣ የተሰራጩ አጎበሮችን በአግባቡና ሁልጊዜ አለመጠቀም፣ በየአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች ላይ የማኅበረሰቡ ተሳትፎ መቀነስ፣ የወባ በሽታ ማስወገድ ስራ ላይ “በሽታው ቀንሷል” በሚል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ትኩረት አለመስጠት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንቅፋት መሆን ከገጠሙ ተግዳሮቶች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።

ወባ በሽታን ለመከላከል በተደረገው የመድኃኒትና የአጎበር ስርጭት እንዲሁም ሕብረተሰቡ የወባን በሽታ ከመከላከል አኳያ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ወባ ቀንሷል” በሚል ምክንያት በሕብረተሰቡ ዘንድ መዘናጋት ይስተዋላል። በአንድ አንድ አካባቢዎች የአልጋ አጎበርን በትክክል አለመጠቀም እንዲሁም፤ ከተሰራበት ዓላማ ውጪ ለአላስፈላጊ አገልግሎት ማዋል ተስተውላል። ይህም በገጠራማ አካባቢዎች በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ፈታኝ ያደርገዋል።



67

የ ጤ ና ባለሙያዎች የወባ በሽታ መተላለፊያ ወቅት መሆኑን አውቀው ሁልጊዜ የወባ ሕክምና ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረው፤ የወባ በሽታ መድኃኒቶች መኖራቸውን ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ነው ያስረዱት።

ተግዳሮት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የገጠሙ አንዳንድ ተግዳሮቶች እንዳሉ የሚያነሱት አቶ ጉዲሳ፤ የወባ በሽታ መከላከያና ማከሚያ ግብዓቶች (መድኃኒቶችና መመርመሪያ መሳሪያዎች) በበቂ ደረጃ የሚሰራጭ ቢሆንም፤ በአንዳንድ ጤና ተቋማት መቆራረጥ መኖሩ፣ የተሰራጩ አጎበሮችን በአግባቡና ሁልጊዜ አለመጠቀም፣ በየአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች ላይ የማኅበረሰቡ ተሳትፎ መቀነስ፣ የወባ በሽታ ማስወገድ ስራ ላይ “በሽታው ቀንሷል” በሚል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በየደረጃው ትኩረት አለመስጠት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንቅፋት መሆን ከገጠሙ ተግዳሮቶች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።

ወባ በሽታን ለመከላከል በተደረገው የመድኃኒትና የአጎበር ስርጭት እንዲሁም ሕብረተሰቡ የወባን በሽታ ከመከላከል አኳያ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ወባ ቀንሷል” በሚል ምክንያት በሕብረተሰቡ ዘንድ መዘናጋት ይስተዋላል። በአንድ አንድ አካባቢዎች የአልጋ አጎበርን በትክክል አለመጠቀም እንዲሁም፤ ከተሰራበት ዓላማ ውጪ ለአላስፈላጊ አገልግሎት ማዋል ተስተውላል። ይህም በገጠራማ አካባቢዎች በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ፈታኝ ያደርገዋል።

ይህን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት የጤና ሚኒስቴር በጤና ኤክስቴንሽን ደረጃ የአጎበር አጠቃቀምና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ቤት ለቤት እንደሚሰራ ነው አቶ ጉዲሳ የተናገሩት። ዋነኛ የወባ መተላለፊያ ወቅትን በመለየት የወባ ሳምንት ተብሎ ከፍተኛ የወባ ስርጭት ባሉባቸው ቦታዎች አጎበር እንዴት እንደሚሰቀል፣ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የሚያሳይ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዘጋጀት “ሕብረተሰቡ በትክክል የሚጠቀምበትን ሁኔታ ለማዘጋጀት የንቅናቄ ስራ ይካሄዳል” ብለዋል።

የወባ በሽታ ምንድን ነው? ወባ በቀይ ደም ወይም በጉበት ውስጥ በጥገኝነት የሚኖሩ፣ የሚያድጉና የሚራቡ፣ በአጉሊ መነፅር (ማይክሮስኮፕ) ካልሆነ በስተቀር በዓይን የማይታዩ እና በእጅ የማይዳሰሱ፣ “ፕላስሞድየም” በመባል በሚታወቁ ረቂቅ ተህዋስያን አማካኝነት የሚመጣ በሽታ ነው። በተፈጥሮ በሰው አካል ውስጥ በመራባትና በማደግ ለበሽታው የሚያጋልጡት አራት የወባ ተህዋስያን ዝርያዎች ናቸው:: እነርሱም ፕላስሞዲየም ፋልሲፖረም፣ ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ፣ ፕላስሞዲየም ማላሪዬ እና ፕላስሞዲየም ኦቫሌ ናቸው።

ተህዋስያኑ ያላቸው ቅርጽ፣ እድገት፣ የትውልድ ብዛት፣ ለመራባት የሚወስዱት የጊዜ ፍጆታ፣ የበሽታው የጥቃት መጠን፣ በሰው ላይ የሚያሳዩት የግርሻ ዓይነትና ወቅት በመድኃኒቶች የመጠቃት ዝንባሌ፣ በአካል ውስጥ የሚያደርሱት የጉዳት ዓይነት የተለያየ ነው። ከእነዚሁ የወባ ተህዋስያን ዝርያዎች መካከል በአገራችን በዋናነት በሕብረተሰቡ ላይ ጥቃት የሚያደርሱት ፕላስሞዲየም ፋልሲፖረምና ፕላስሞዲየም ቫይቫክስ ናቸው።

የወባ በሽታ የሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆች በርካታ ናቸው። ለምሳሌ የቀይ ደም ህዋሳትን በማጥቃት ለደም ማነስ የሚያጋልጥ ሲሆን፤ የአእምሮ ማዳከም፣ ለጉበትና ለኩላሊት መታወክ፣ እና በአጠቃላይ ለአካል ጉስቁልናና ለሞት ሊያጋልጥ ይችላል። በተለይም ፕላስሞዲየም ፋልሲፖረም የተባለው የወባ ዝርያ በወቅቱ ተገቢው ሕክምና ካልተሰጠ በስተቀር ለሞት አደጋ ያጋልጣል። የወባ በሽታ በተለይ ነፍሰጡር ሴቶችንና እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናትን በይበልጥ የሚያጠቃ ሲሆን፤ በቀላሉ ለአካል ጉስቁልና ለሞት አደጋ ጭምር ያጋልጣል።

ምልክቶቹ የወባ በሽታ ተጠቂዎች ህመሙ ሲጀምራቸው ብርድ ብርድ የማለትና የማንቀጥቀጥ ስሜት ይከሰትባቸዋል። ጥርስ ማፋጨትና የሰውነት መወራጨት፣ ጥቂት ቆይቶ የትኩሳት እና የላብ መከሰት፣ የምግብ ፍላጎት ያለመኖርና ቢመገቡም ማስመለስ፣ ራስ ምታትና ውሃ ጥማት፣ በጀርባና በአካል መገጣጠሚያዎች የቁርጥማት ስሜት መኖርና የመሳሰሉ ምልክቶች ይታይባቸዋል።

የወባ በሽታ ስሜቶችና መለያ ምልክቶችን የወባ ተህዋስያን በቀይ ደም ህዋሳት ውስጥ የሚያደርጉትን የዕድገትና የመራባት ኡደት ከጨረሱ በኋላ በመጨረሻ ከቀይ ደም ህዋሳት ውስጥ በመውጣትና በመሰራጨት ሌሎች ጤነኛ የደም ህዋሳትን በሚያጠቁበት ጊዜ ወዲያውኑ ተመርምሮ አስፈላጊውን ሕክምና ካላገኘ በስተቀር እንደወባው ዝርያ የሚለያይ ቢሆንም፤ በየሁለትና ሶስት ቀናት ያገረሻል። የወባ በሽታ በደም ህዋሳት ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ከሚከሰቱት ምልክቶች በተጨማሪ ደም ማነስ፣ መገርጣት፣ ክብደት መቀነስ፣ የጣፊያ እብጠት እና የመሳሰሉት አዘውትረው ይታያሉ።

መተላለፊያ መንገዶች የወባ በሽታ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፈው “አኖፌሌስ” በመባል በምትታወቀው እንስት የወባ አስተላላፊ ትንኝ አማካኝነት ነው። የወባ አስተላላፊ ትንኝ የምትራባው በአብዛኛው ከዝናብ ወራት በኋላ በየአካባቢው ተጠራቅሞ በሚቆይ ውሃ ውስጥ ነው። የወባ ህመምተኛ ምንም ዓይነት ስሜት ሳይሰማው የተለመደ ተግባሩን እያከናወነ ከ10 እስከ 14 ቀናት ደህና ሆኖ ሊሰነብት ይችላል። ታዲያ በእነዚህ ቀናት ተህዋስያኑ ወደ ህመምተኛው ጉበት ውስጥ በመግባት የሚራቡ ሲሆን ተህዋስያኑ እድገታቸውን ጨርሰው ከጉበት ውስጥ በመውጣት ወደ ደም ቧንቧ በመሰራጨት ቀይ የደም ህዋሳትን ይወራሉ። ይህም የወባ በሽታ የመደላደያ ጊዜ ይባላል።

በመሆኑም ለመራቢያ የሚያመቿትን ያቆረ ውሃ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች የተጠራቀመን ውሃ መረበሽና በፕሮግራም አካባቢን በማፅዳት የወባ በሽታ መተላለፊያ መንገድን ማቋረጥ ያስችላል።

መከላከል መድኃኒት በተረጩ አጎበሮች ሥር መተኛትና የመኖሪያ ስፍራዎችን መድኃኒት መርጨት ዋናዎቹ የወባ መከላከያ መንገዶች ናቸው። እንዲሁም ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስና በማዳረቅና አጎበሮችን ለአላስፈላጊ አገልግሎቶች ከመጠቀም መቆጠብ ውጤታማ የወባ መከላከያ ዘዴዎች ናቸው።

በተለያየ ጊዜ መድኃኒቱን ከመርጨት ባሻገር ለሚጓዙ ሰዎች የሚዋጡ መድኃኒቶችን መውሰዱም በጣም ጠቃሚ የሆነ የወባ መከላከያ መንገድ እንደሆነ ይገለፃል። ከዚህ ባለፈ ጥርጣሬ ካለ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ በግማሽ ሰዓት ውስጥ ውጤቱን ማወቅ እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። በሽታውን በፍጥነት ለይቶ ማወቁ ወባው ከፍ ወዳለ ደረጃ ወይም ሞትን ወደ ማስከተል ሳይደርስ መከላከል ይቻላል።



68

“የሕሙማን እፎይታ” - ማንዚሎፋሻ ሰርጀሪ እና

የጥርስ ሕክምና

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከኢዜአ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ



69

በብርሃኑ አለማየሁ

ማንዚሎፋሻ (Maxillofacial) በአፍ ውስጥ፣ በፊትና በአፍንጫ ላይ የሚደርስን ጉዳትና በሽታ የማከም እንዲሁም የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሲሆን ዴንትስትሪ ደግሞ በጥርስ ሕክምና ዘርፍ ጥርስን፣ የጥርስ አቃፊዎችን፣ የአጥንትን እና ሌሎች ህዋሳት ሕክምና ዘርፍ ነው።

ማንዚሎፋሻ ሰርጀሪ እና የጥርስ ሕክምና (dentistry) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጥርስ፣ የአፍ ውስጥ እንዲሁም የፊት ቀዶ ሕክምና ትምህርት ክፍል በየዓመቱ ከ12 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሕይወት አድን ሕክምና እየሰጠ ይገኛል።

ክፍሉ ሕክምናውን እየሰጠ የሚገኘው ማንዚሎፋሻ ሰርጀሪ እና የጥርስ ሕክምና በሚባሉ ሁለት ዘርፎች ነው።

በዚህ ክፍል የጥርስና የአፍ ውስጥ ሕክምና የሚሰጥ ሲሆን፤ ከጥርስ ሕክምና ጋር በተያያዘ በስፔሻሊቲ ደረጃ የፊትና የአፍ ውስጥ አጥንቶችና ገጽታዎች ሕክምና (ማንዚሎፋሻ) ይከናወናል። በተቋሙ የጥርስ፣ የአፍ ውስጥ እና የፊት ቀዶ ሕክምና እና ትምህርት ክፍል ውስጥ ከ20 በላይ የሕክምና አገልግሎቶች ይሰጣሉ።



70

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የጥርስ እና ማንዚሎፋሻ ቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ጸጋነሽ በርታ እንደሚገልጹት፤ ክፍሉ በጥርስ፣ በአፍ ውስጥ እና በፕላስቲክ ሰርጀሪ ሕክምና በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በተለይም የጥርስ መለስተኛ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን፤ የጥርስ ሙሌት፣ የእጥበት እና የአርቴፊሻል ስራዎችን ለመጀመር የዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ በመሆኑ በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል።

በዚሁ ክፍል የድድ፣ የላንቃ፣ የመንጋጋ እና የከንፈር ሕክምናዎች እየተሰጡ ይገኛሉ። በተጨማሪም በከፍተኛ ቀዶ ሕክምና፣ በመድኃኒት መስጠት፣ በተመላላሽ ታካሚነትና በአስተኝቶ ማከም አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል እንደ ዶክተር ጸጋነሽ ገለጻ። ይህ የሕክምና አገልግሎት በሰባት የጥርስ ሐኪሞች፤ በተመሳሳይ የማንዚሎፋሻ ሕክምና ደግሞ በሶስት የውጭ አገር እና በአራት ኢትዮጵያዊያን ሐኪሞች ነው የሚሰጠው።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሁለት ዘርፎች እየተሰጠ የሚገኘው ሕክምና እና ትምህርት በ1986 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፤ የማንዚሎፋሻ ሰርጀሪ በ1995ዓ.ም መጀመሩን ነው ሰነዶች የሚያመለክቱት።።

የትምህርት ከፍሉ በኢትዮጵያዊያን ሚሊኒየም መባቻ አካባቢ መመስረቱን የሚናገሩት ዶክተር ጸጋነሽ፤ በትምህርት ክፍሉ የማንዚሎፋሻ (የአፍ ውስጥ፣ የፊት እና የአፍንጫ ሕክምና) ስፔሻሊቲ ትምህርት እንደሚሰጥ፤ በየዓመቱም አራት ተማሪዎችን እንደሚቀበል ነግረውናል።

ትምህርቱ በገለጻና በተግባር የሚሰጥ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች በልዩ ትኩረት የተግባር ትምህርት ይሰጣል። በጥርስ ሕክምና ዘርፍ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የሚመጡ ተማሪዎችን መቀበሉን በቦታ ጥበትና በሌሎች የአቅም ማነስ ችግሮች ሳቢያ ለጊዜው መቋረጡን ነው የገለጹት።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለአራት ዓመታት በሚሰጠው በዚህ የትምህርት ክፍል በአሁኑ ወቅት 16 የስፔሻሊቲ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ።

ዶክተር ጸጋነሽ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጥርስ፣ የአፍ ውስጥ እንዲሁም የፊት ቀዶ ሕክምና እና ትምህርት ክፍል ዋና ዓላማ የሆነውን የሕክምና አገልግሎት ዘርፍ “የህሙማን እፎይታ”

ይሉታል።

የጥርስና የአፍ ውስጥ በሽታዎች ለታማሚዎች ከሕመሙ ባሻገር ችግሩ በፊት ገጽታ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ትልቅ በመሆኑ ለሥነ-ልቦና ጉዳት እንደሚዳርግ የተናገሩት ዶክተሯ፤ “ሕሙማኑ በሕክምናው የሚያገኙት ፈውስ እረፍትና እፎይታ ይሰጣቸዋል” ይላሉ።

ታካሚዎች ወደ ሕክምና ክፍሉ መጥተው በሽታቸው ተለይቶ “የሕክምና አገልግሎቱን አግኝተው ሲፈወሱና እፎይታ ሲሰማቸው የሚያቀርቡት ምስጋና የላቀ ነው” የሚሉት ዶክተር ጸጋነሽ፤ የታካሚዎችን ሁኔታ መከታተልና ሕክምናቸውን እንዲጨርሱ ማድረግ ከሐኪሞች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ከሚመጡ ታካሚዎች በተጨማሪ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ሕሙማን በሕክምና ክፍሉ አገልግሎት ማግኘታቸውን ነው የተናገሩት። የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ነጻ ሕክምና ከፍለው የሚታከሙ ደግሞ በተመጣጣኝ ክፍያ ሕክምናውን ያገኛሉ።

አብዛኞቹ የሕክምና ክፍሉ ታካሚዎች በተሽከርካሪ እና በሌሎች አደጋዎች ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸውን የሚገልጹት ዶክተር ጸጋነሽ፤ አስተኝቶ ማከምና ከባድ ቀዶ ሕክምናን ሳይጨምር በየዓመቱ ከ12 ሺ ለሚልቁ “ሕሙማን የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው” ብለዋል።

በክፍሉ ከሚሰጡት ከ20 በላይ የሕክምና ዓይነቶች መካከል ታክመው የማይድኑ እንዲሁም አጥንት ውስጥ የተቀበሩ ጥርሶችን መንቀል፣ በመለስተኛ ቀዶ ሕክምና ናሙና መውሰድ፣ የአፍ ውስጥ እና የፊት ላይ መለስተኛ ቀዶ ሕክምና፣ በድንገተኛ ሁኔታ የሚመጣ የፊት ላይ መሰንጠቅ ቀዶ ሕክምና፣ የአፍንጫ ስብራት እንዲሁም የጉንጭ አጥንት ስብራት ሕክምናዎች ይጠቀሳሉ።

በአደጋ የተጎዱ ጥርሶችን፣ የላይ እና የታች የመንጋጋ አጥንቶች ስብራት፣ የመንጋጋ አጥንቶች መገጣጠሚያ ውልቃት መመለስ እና በሽታዎችን ማከም እንዲሁም

የአፍ ውስጥ እና የፊት ኢንፌክሽን፣ የአፍ ውስጥ እና የፊት ሕመሞች፣ የጥርስ ማጽዳት፣ የጥርስ ሙሌት፣ የጥርስ ስር ሕክምና፣ የአፍ ውስጥ እና የፊት ላይ እባጮች እና የካንሰር ከፍተኛ ቀዶ ሕክምና በዚሁ ክፍል ከሚሰጡት ሕክምናዎች መካከል ናቸው።

በተጨማሪም የአፍ ውስጥ እና የፊት ላይ አደጋዎች ከፍተኛ ቀዶ ሕክምና፤ በተፈጥሮ፣ በበሽታ እና በአደጋ የተዛቡ የአፍ ውስጥ እና የፊት ላይ ችግሮችን በቀዶ ሕክምና ማስተካከል፣ የመንጋጋ አጥንቶች መገጣጠሚያ በሽታዎችን በከፍተኛ ቀዶ ሕክምና ማከም፤ በተፈጥሮ የከንፈር፣ የላንቃ እና የፊት መሰንጠቅ ከፍተኛ ቀዶ ሕክምና፣ የምራቅ ዕጢዎች በሽታ ቀዶ ሕክምናም እንዲሁ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የሚገኘው የአፍ ውስጥ ካንሰር ሕክምና ሌላው በዚህ ዘርፍ በክፍሉ የሚሰጥ ሕክምና ነው። በዚህም በቀን እስከ ሃምሳ የሚደርሱ ከጨቅላ ሕጻናት እስከ አዛውንት ያሉ ተመላላሽ ታካሚዎች ሕክምና ሲያገኙ፤ በየቀኑ እስከ ሦስት የቀዶ ሕክምናዎች ይሰጣሉ።

እነዚህ የሕክምና አገልግሎቶች በሚሰጡበት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጥርስ፣ የአፍ ውስጥ እንዲሁም የፊት ቀዶ ሕክምና እና ትምህርት ክፍል ዋና የጥርስ እና የአፍ ውስጥ እንዲሁም የፊት ሕክምናዎች ስፔሻሊስት ሐኪሞች፣ ነርሶችና ሌሎችን ጨምሮ 67 ባለሙያዎች ይገኛሉ።

የሕክምና አገልግሎቱን በሚፈለገው ደረጃ ለማስኬድ የቦታ ችግር መኖሩንና ምቹም እንዳልሆነ የሚያነሱት ዶክተር ጸጋነሽ፤ የሕክምና አገልግሎቱን በበቂና ምቹ ቦታ በስፋት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት። በዚህም ችግሩ ይቃለላል የሚል እምነት አላቸው።

በሌላ በኩል በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለውን የአፍ ውስጥ እና የጥርስ በሽታዎችን ሳይታከሙ በቤት ውስጥ በማቆየት የሚታዩ የግንዛቤ እጥረቶችን ለማረም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በመሆን የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃ ግብሮችን ለማዘጋጀት መታቀዱን ነው አጽንኦት የሰጡት። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ የመጣውን የአፍ ውስጥ ካንሰር ቀድሞ ለመከላከል ከባለሙያዎች ጀምሮ የግንዛቤ ማሳደግ ስራ ለመስራት መታሰቡን አክለዋል።

የጥርስ፣ የአፍ ውስጥ እንዲሁም የፊት ጉዳት ወይንም ሕመም በሚያጋጥም ጊዜ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ችግሩ ስር ሳይሰድ ሕክምና ማግኘት እንደሚገባም ዶክተር ጸጋነሽ አስገንዝበዋል።

ጳውሎስ ሆስፒታል የጥርስ እና ማንዚሎፋሻ ቀዶ ሕክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ጸጋነሽ በርታ



71



72




የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም