ነጋሪ መጽሔት 26ኛ ዕትም - ኢዜአ ነጋሪ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 26 ሚያዚያ 2016 ዓ.ም ዋጋ 15 ብር
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
አድራሻ፦ አራዳ ክፍለ ከተማ
ስልክ ቁጥር +251-11-55-00-11 +251-11-56-39-31 +251-11-56-52-21
ፋክስ ቁጥር +251-11-55-16-09 enanegari@gmail.com
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት
ማውጫ
መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች
የዘመን አሻራ 6
ስብራቱን ለማከም...
24
የአገራዊ ምክክሩ ዋነኛ ባለቤት ኢትዮጵያዊያን
16
ዋና አዘጋጅ ገዛኸኝ ዳንጉል
ም/ ዋና አዘጋጅ የሺመቤት ደመቀ
ከፍተኛ አዘጋጅ ፍቅርተ ባልቻ
አዘጋጅ መንገሻ ገ/ሚካኤል
አርት ዳይሬክተር ነብዩ መስፍን nebiyou1st@gmail.com
ፎቶግራፍ ወርቅነህ ረጋሳ አሸናፊ ገ/ሥላሴ እርምት ባለሙያ ትዝታ ሁሴን
መልዕክት አንጋፋውን ለማዘመን 36
ዩኒቨርሲቲው ለማኅበረሰቡ
42 ከጨዋታም በላይ
50
ጠባቂነትን ታሪክ ያደረገው ቀበሌ
68 ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
74 በርካቶች የሚመኙት
ባለራዕዮች የሚጎናጸፉት 80
አገራዊ ለውጥ የሚያሳካ ተቋማዊ ዕቅድ
ነጋሪ እንደ ሁልጊዜው ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ሰንዳ ቀርባለች። በዚህ ዕትሟ
የኢትዮጵያዊያን የጋራ ታሪካዊ ገድል የሚዘከርበት፤ የ”አልገዛም” ባይነት የድል ዓርማ፤ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሣሌት፤ . . . ስለሆነውና ከ127 ዓመታት በኋላ የዓድዋ ጀግኖች አርበኞች እና ድሉ የተዘከረበትን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በምናብ ታስቃኛለች። ከዓድዋ ጀግኖች ምን እንውረስ? የእኛ አድዋስ ምን ይሁን? ስትል ትጠይቃለች፤ ምላሹንም አመላክታለች።
በዓቢይ ጉዳይዋ በአክሱም ዘመነ መንግሥት የጀመረው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ፤ ዘመናዊ ገጽታን ተላብሶ መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን የነበረውን ጉዞ፤ በተለይ ባለፉት አምሥት ዓመታት የተመዘገቡ ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን ዳሳለች።
የችግሮች ሁሉ መፍቻ ዋነኛ ቁልፍ ስለሆነው ‘ትምህርት’፤ የምታነሳው ነጋሪ ለመሆኑ የአገራችን የትምህርት ጥራት አሁናዊ ደረጃ ምን ላይ ነው? “የትምህርት ጥራት እየቀነሰ ነው፣ የተማሪዎች ውጤት እያሽቆለቆለ ነው” እየተባለ ከሚነገረው ባሻገር የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ብሎም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ምን እየተሰራ ነው? የስራው ባለቤቶችስ እነማን ሊሆኑ ይገባል፤ ስትል የችግሮቹን ምንጭ ትፈትሻለች፣ ከችግሮቹ መውጫውን መንገድ በማመላከት ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን ምክረ ሃሳብ ይዛለች።
የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) በጥር 2016 ዓ.ም በኢጣሊያ- ሮም ባካሄደው የዕውቅና መስጠት መድረክ በአገር በቀል የመደመር ፍልስፍና እና በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የአፍሪካ ብሎም የዓለም ተምሣሌት የሆነውን የኢትዮጵያን የብልፅግና ራዕይ ለማሳካት ቀን ከሌሊት እየተጉ ዘርፈ ብዙ አገራዊ ለውጦች እና ውጤቶችን ያስመዘገቡና እያስመዘገቡ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለተበረከተው የፋኦ የከበረ አግሪኮላ ሜዳሊያ ነጋሪ የምትለው አላት።
በኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ስለሚጠበቀው አገራዊ ምክክር ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ የሌሎች አገራት ተሞክሮ፣ የኮሚሽኑ የእስካሁን የዝግጅት ስራዎች ስለሚገኙበት ደረጃ እና የትኩረት አቅጣጫዎችም “የአገራዊ ምክክሩ ዋነኛ ባለቤት-ኢትዮጵያዊያን” ስትል ታብራራለች።
ነጋሪ የዘንድሮ (እ.አ.አ 2024) የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ቡድናቸው ውጤታማ እንዲሆን በአገር ፍቅር ስሜት፣ በአንድ ላይ በኅብረት መሰለፋቸውን፤ ሕልማቸው ተሳክቶም 34ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ በድል በማንሳት ከዓመታት በፊት አጋጥሟቸው የነበረውን ቀውስ ላይመለሱበት ረስተው በከረሙበት ፌሽታና ፈንጠዝያ በማዋዛት፤ ስፖርት ለዜጎች አብሮነትና አንድነት እንዲሁም ለአገር ፍቅር መነሳሳትና መነቃቀት ያለውን ሁለተናዊ ፋይዳ፤ ስፖርታዊ መድረኮችም ለአንድ አገር ልማትና ዕድገት እንዲሁም ሁሉም አበክሮ የሚሻው፣ እጅግ አስፈላጊ እና የሁሉም ነገር መሰረት የሆነውን ሰላም ለማስፈን ያለውን የላቀ አስተዋጽኦ ታስነብባለች።
መልካም ንባብ!
ስብራቱን ለማከም...
24
58
የዘመን አሻራ
ፖለቲካ
በየሺመቤት ደመቀ
ሙዚየሞች በዓለም ላይ በብዛት ከሚጎበኙ መስህቦች መካከል ግንባር ቀደም ሆነው ቀጥለዋል። በተለይ ታሪካዊ ሙዚየሞች ጎብኚዎች በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ባለው የበለጸገ ቀረፃ ውስጥ እንዲመሰጡ በማድረግ ያለፈን ዘመን ማሳያ መስኮቶች ናቸው።
እነዚህ ሙዚየሞች ከጥንት ሥልጣኔዎች እስከ ዘመናዊ ክስተቶች ድረስ ዓለማችንን የፈጠሩ ቅርሶችን፣ ሰነዶችን እና ታሪኮችን ጠብቀው ያኖራሉ፤ ለትውልድም ያሳያሉ። ምርጥ ታሪካዊ ሙዚየሞች ደግሞ ሰዎችን በምናባዊ ምልሰት ዘመናትን ወደኋላ መልሰው ልዩ እና ማራኪ ትዕይንት ውስጥ እንዲቆዩ የማድረግ አቅም አላቸው።
በዓለም ላይ የተለያዩ ዓይነት ሙዚየሞች ይገኛሉ። ከታሪካዊ እስከ ኪነ ጥበባዊ ሙዚየሞች፣ ከወታደራዊ እስከ ሳይንሳዊ ሙዚየሞችን ጨምሮ በርካታ ሙዚየሞች ልዩ ልዩ ቅርሶችን አቅፈው በስፋት ለዕይታ መብቃት ችለዋል።
ከዚህ ጽሑፍ ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ያለው ታሪካዊ፣ ወታደራዊና የጦር ሙዚየም እንደመሆኑ መጠን ስለ ሙዚየም ጥቂት አለማንሳት ንፉግነት ይሆናል። የጦርነት ሙዚየሞች በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ የወታደራዊ ታሪክን፣ የጦርነት ቅርሶችን ለማሳየት እና እውነተኛ የጦርነት ገጽታዎችን እና ልምዶችን ለማሳየት እንዲሁም በወደቁት ጀግኖች የተከፈለውን መስዋዕትነት ለማስታወስ የታሰቡ የሕዝብ ትውስታ ማሳያዎች ናቸው።
የጦር ሙዚየሞች ቅርስን ከመጠበቅ ባለፈ በግጭት ላይ የተመሰረቱ ውስብስብ ማኅበራዊ ችግሮችን ከግጭት መለስ እንዴት በብስለት መፍታት እንደሚገባ የሚያመላክቱ ሲሆኑ
ከማዝናናት ባሻገር የጥናትና ምርምር እንዲሁም የመማሪያ ማዕከላት ጭምር መሆናቸውን ድርሳናት ያስረዳሉ።
በዓለማችን ስመጥር ከሆኑት ወታደራዊና የጦር ሙዚየሞች መካከል በሎንዶን የሚገኘው የኢምፔሪያል የጦር ሙዚየም (Imperial War Museum) አንዱ ሲሆን፤ ሌላው በሞስኮ የሚገኘው ታላቁ የአርበኞች የጦርነት ሙዚየም (Museum of the Great Patriotic War) ተጠቃሽ ነው።
በተመሳሳይ በአሜሪካ ኒው ኦርሊየንስ የሚገኘው የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሙዚየም
(National WWII Museum)፣ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በንጉሥ ፍራንዝ ዮሴፍ ትዕዛዝ የተመሰረተው የኦስትሪያ ወታደራዊ ታሪክ ሙዚየም (Museum of Military History)፣ በፓሪስ የሚገኘውና በ1670 በንጉሥ ሉዊስ አሥራ አራተኛ የተቋቋመው ሌስ ኢንቫሊዴስ (Les Invalides) እና ሌሎችም ሙዚየሞችን መጥቀስ ይቻላል።
በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወታደራዊ ሙዚየሞች ከእርስ በርስ ጦርነት እስከ የዓለም ጦርነቶች ድረስ ያለውን የግጭት ታሪክ እንዲሁም ጥለውት የሚያልፉትን አዎንታዊና አሉታዊ ጠባሳዎች ለትውልድ ማቆየትና ነገ እንዳይደገም ግንዛቤ የሚሰጡ ናቸው።
እነዚህ ሙዚየሞች ከጦርና ጎራዴ እስከ መድፍና ሌሎች ተተኳሾች እንዲሁም ከተዋጊ አውሮፕላኖች እስከ ባሕር ሰርጓጅ የጦር መርከቦች፣ ከነጋሪት ጉሰማ እስከ የጦር ሜዳ ውሎዎች ትዕይንትን ይዳስሳሉ።
ከሁሉም በላይ ግን የጦርነት ሙዚየሞች በጦርነት ለተሰዉ መታሰቢያ ወይም የጦር መሣሪያን የቴክኖሎጂ ዕድገት ከማሳያነት በላይ፤ አገራዊ ታሪኮችን ለመቅረፅ እና የሕዝቦችን ባሕላዊ ማንነት ለማጎልበት የለውጥ ነፀብራቆች ጭምር ናቸው። እንዲህ ያሉ ሙዚየሞች በተለይ ታሪካዊ ንቃተ ሕሊናን ለመቀስቀስ ውጤታማ ተቋማት እንደሆኑ በመስኩ ጥናት ያደረጉ ምሁራን ይገልፃሉ።
እናም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ተገንብቶ በቅርቡ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚስማማበት ብቻ ሳይሆን ታላቅ (የወል) ትርክትን በመፍጠርና መልክ በማስያዝ በኩል በአፍሪካም ሆነ በዓለም ተጠቃሽ ሙዚየም የሚያደርገው ነው።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ-የትውልድ አሻራ
ኢትዮጵያዊያን 128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በድምቀት ለማክበር ዕለቱን በጉጉት እየጠበቁ ባሉበት በወርሃ የካቲት በሦስተኛው ቀን 2016 ዓ.ም፤ በዲፕሎማቲክ መዲናዋ አዲስ አበባ እምብርት፤ በታላቅ ጉጉት ሲጠበቅ የቆየ ትልቅ
ጉዳይ እየተከናወነ ነው። ከኹነቱ ብሥራት ቀደም ብሎ ከሁለት ለማያንሱ ሰዓታት በዕለቱ በስፍራው ለመታደም የታደሉት ከሁሉም የአገሪቷ ክልሎች የመጡ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጦር መኮንኖች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች (ከያንያን)፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ ሌሎችም በርካታ እንግዶች. . . የኢትዮጵያዊያንን ብዝሃነት በሚገልጹ፤ እጅግ በሚያምሩ፣ ኢትዮጵያን በሚያሳዩ፣ ኢትዮጵያን በሚመስሉ በብሔር ብሔረሰቦች አልባሳት ተውበውና ደምቀው ወደ ስፍራው ተመሙ። በስፍራው ተገኝተው ሥነ-ሥርዓቱን መታደም ያልቻሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ኹነቱን በቴሌቪዥን መስኮት ለመከታተል በያሉበት ተሰየሙ። ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተጠባቂውን ኹነት የተመለከቱ መርሃ ግብሮችን በየመሃሉ፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ወደ ስፍራው እየገቡ የሚገኙትን እንግዶች ማሳየቱን ቀጥሏል . . .
የዕለቱ የክብር እንግዳ ደረሱ. . . የብዙዎችን ቀልብ በጉጉት አንጠልጥሎ የቆየው ታላቅ ጉዳይ የኢትዮጵያዊያን፤ የጋራ ታሪካዊ ገድል የሚዘከርበት፤ የ”አልገዛም” ባይነት የድል ዓርማ፤ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሣሌት፤ ከታሪካዊ ቅርስነት ባሻገር የመላው ጥቁር አፍሪካዊያን
ንቅናቄ የሚታወስበት፤ ዓለምን ያስደነቀ፣ ይሆናል ተብሎ የማይታሰበውን እውን አድርጎ ያሳየ፣ የቅኝ ግዛት ትርክትን የቀየረ፤ ተቀድቶ የማያልቅ ምንጭ፤ የማሸነፍ ተምሣሌት፤ የድል ቀንዲል-ዓድዋ! ነበር።
በአፍሪካዊያንና በዲፕሎማቲክ መዲናዋ እምብርት. . . የድሉን ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርጎ፤. ከ127 ዓመታት በኋላ “የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም” እውን ሆነ - ዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር።
አገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ብሔራዊ ትርክትን የሚገነባ፤ ኢትዮጵያዊያን ልዩነቶቻችንን እያጎላን፣ አንድነታችንን እያሳነስን ያለንበትን አካሄድ ለማስወገድ ማለፊያ መንገዳችን፤ ኢትዮጵያን ለማፅናት ከምንጠቀምባቸው የትርክት መሰረቶች አንዱና ዋነኛው፤ የቀደመው፣ የዛሬው እና የነገው ትውልድ የሚተሳሰሩበት የቃልኪዳን ገመድ፤ የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት - ዓድዋ! የዕለቱ የክብር እንግዶች ከሙዚየሙ መግቢያ ጀምሮ ገለጻ እየተደረገላቸው ወደ ውስጥ ዘለቁ፤ ጉብኝቱ በአስጎብኚዎች የቅብብሎሽ ገለጻ ቀጠለ. . .፤
የሙዚየሙ ገፅታ በወፍ በረር
ኢትዮጵያዊያን ጀግኖችን፤ የዓድዋን መልክዓምድር በሚገልፅ መልኩ ታሪካዊ እሴቱን ጠብቆ በአምስት ሄክታር መሬት ላይ ባረፈው ሙዚየም ደረቱን ለምዕራብ ሰጥቶ የተሰደረው ደረጃ ኢትዮጵያዊያኑ ከአምሥት ወራት በላይ ተጉዘው የኢትዮጵያን ክብር፣ ልዕልና፣ አይደፈሬነት፣ ይልቁንም የገናናነቷን ታሪክ ለመዘከር ያለፉበትን ውጣ ውረዳቸውን፣ እንግልታቸውን ያሳያል።
ሙዚየሙ ከምድር በታች ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ አምሥት ወለል እና ስምንት በሮች ያሉት ሲሆን፤ ወደ ሙዚየሙ የሚያስገቡት አራት ዋነኛ መግቢያዎች፤ የተለያየ ገፅታ እና አገልግሎት ወዳላቸው የሕንፃው ክፍሎች ያደርሳሉ። ስያሜያቸው የደቡብ ጀግኖች፣ የሰሜን ጀግኖች፣ የምሥራቅ ጀግኖች እና የምዕራብ ጀግኖች የሚል ነው። ቀሪዎቹ በሮች የፈረሰኞች በር፣ የአርበኞች በር እና የፓን-አፍሪካኒዝም በር የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። በአራቱ አቅጣጫዎች የተሰየሙት በሮች ተምሣሌትነት የዓድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን ከአራቱም አቅጣጫ በመትመም በአንድነት የተቀዳጁት የጋራ ድል መሆኑን ያመላክታል። የበሮቹ ስያሜ ስሜቱም፣ ተምሳሌትነቱም እርሱ ነው።
የኢትዮጵያዊያንና የአፍሪካዊያን የነፃነት መገለጫ የሆነው የዓድዋ ድል መታሰቢያ
ሙዚየም መሃል ላይ ለሁሉም የሀገሪቷ ከተሞች ርቀት ልኬት መነሻ የሆነው የ‘ዓድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር’ ምልክት ይገኛል። በጦርነቱ ለዓድዋ ድል መገኘት አስተዋጽኦ የነበራቸው የጦር መሳሪያዎች፣ ወኔ መቀስቀሻ መሳሪያዎች፣ ለጦርነቱ መነሻ የሆኑ ስምምነቶች እና ሌሎችም የጦር መሳሪያዎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡
ወደ ሙዚየሙ ውስጥ በሚያስገባው በምዕራብ በር ላይ የፀረ ቅኝ ግዛት ጦርነቱ በድል እንዲቋጭ የመሪነቱን ሚና የተወጡት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሐውልት በክብር ቆሟል። በዓድዋ ጦርነት ወቅት ጠላት ለመጠጥነት ይጠቀምበት የነበረው የምንጭ ውሃ በእቴጌይቱ ብልሃት የታከለበት አመራር በኢትዮጵያ ሠራዊት እንዲከበብና ጠላት በውሃ ጥም እንዲዳከም በማድረግ ድል መንሳት የተቻለበትን የጦር ስትራቴጂ የሚዘክር የውሃ ፏፏቴ ከእቴጌ ጣይቱ ሐውልት ፊት ለፊት ተቀምጧል።
ጦርነቱን በታላቅ ጀግንነት በመምራት ለጥቁር ሕዝቦች ድል ያበሰሩት 12ቱ የጦር መሪዎች፤ ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ ጉርሙ:- በጀግንነት ስማቸው አባ ጎራው ይሰኛሉ፤ ከዓድዋ ጦርነት አስቀድሞ ከነበረው ከአምባላጌ እስከ ዓድዋ ድረስ ተጋድሎ ያደረጉ ናቸው። በጀግንነት ሲዋጉ ቆይተው በዓድዋ የመጨረሻ ቀን በክብር የተሰዉት እኚህ ጀግና የጦር መሪ፤ በመድፍ ተኳሽነታቸው ይታወቃሉ።
ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል:- (አባ ቃኘው) ከአምባላጌ ጀምሮ እስከ ዓድዋ ጦረኛ፣ ፈረሰኛ እና እግረኛ ጭምር በማዝመትና በመዋጋት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የጦር አመራር የሰጡ፤ ከውጫሌ ውል ጋር በተያያዘ መንግሥት የዲፕሎማሲ ፍትጊያ ውስጥ ሲገባ ነገሩ በሰላም እንዲፈታ ጥረት አድርገው ነበር፤ ይሁንና ጦርነቱ መካሄዱ ስላልቀረ ዘምተዋል።
ንጉስ ተክለኃይማኖት ተሰማ ጎሹ:- (አባ ጠና) በተለያየ አውደ ጦር ሲሳተፉ ቆይተዋል፤ በዓድዋ ጦርነትም ፈረሰኛን ከእግረኛ አዋህደው መርተዋል።
ንጉሥ ሚካኤል ዓሊ ሊበን:- (አባ ሻንቆ) ከዓድዋ ጦርነት ባሻገር በመቀሌ አምባላጌ ዋጋ
የከፈሉ፤ ጦር የመሩ ናቸው።
ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ ሮባ:- (አባ ጠለስ)፣ የፈረስ ስማቸው አባ ነፍሶ በንጉሥ ምኒልክ ግምጃ ቤት በጅሮንድ እንደነበሩ ይነገራል። በዓድዋ እና በመቀሌ ጦርነት ዋጋ የከፈሉ እግረኛውንም ፈረሰኛንም ጦር ያዋጉ ናቸው።
ራስ ወሌ ብጡል ኃይለማርያም:- (አባ ጠጣው) ታዋቂ ጦረኛ ናቸው፤ ጦር አዝምተው ራሳቸውም ዘምተው ለነፃነት ዋጋ ከፍለዋል።
ፊታውራሪ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ሁንዱል:- (አባ መቻል) በጦር አማካሪነታቸው የሚታወቁ ናቸው። ፊታውራሪ ገበየሁ በጦር ሜዳ ሲሰዉ የጦር አበጋዝ በመሆን በፊታውራሪነትን ቦታ ተሹመው ጦር ያዘመቱ ናቸው።
ራስ አሉላ እንግዳ ቁቢ:- (አባ ነጋ) በስለላ ስራ ጎበዝ የሆኑ የወራሪውን የኢጣሊያ ጦር አሰላለፍ ቀድመው በመረዳት የኢትዮጵያ ጦር የተሻለ ቦታ እንዲጠብቅ እና ወራሪው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንዲያደርስ አድርገዋል፤ በዓድዋ ጦርነት ተዋግተው አዋግተዋል።
ራስ መንገሻ ዮሐንስ ምርጫ:- (አባ ግጠም) በተለያዩ አውደ ውጊያዎች በተለይ ኩአቲት እና ሰናታ ግንባር ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ የነበራቸው፤ በዓድዋም አንደኛው የጦር አመራር ሆነው ዋጋ የከፈሉ የጦር መሪ ናቸው።
ዋግሹም ጓንጉል ብሩ ገብረመድህን:- (አባ መርከብ) የወራሪው የኢጣሊያ ጄኔራል አልቤርቶኒን እና ሌሎች ሠራዊቱን የማረኩ የጦር መሪ ናቸው።
ራስ አባተ ቧያለው ንጉሡ:- (አባ ይትረፍ) የሊቀ መኳስነት ማዕረግ የነበራቸው ናቸው። በመድፍ ተኳሽነታቸውም የታወቁ ነበሩ፤ የተለያዩ አውደ ግንባሮች ላይ ትልቅ ስም አትርፈዋል።
ራስ ቢትወደድ መንገሻ ቲከም ቢተርፉ:- (አባ ገድብ) በንጉሥ ምኒልክ የሚወደዱ ስለነበሩ በጦር ምክራቸው የራስ ቢትወደድነት ማዕረግን ያገኙ፤ በዓድዋ ድል እግረኛ ጦር አዝምተው ድል ያስመዘገቡ፤ ከዚያ ባሻገር የዓድዋን ድል ተከትሎ በተካሄደው የአዲስ አበባ ስምምነት
አንድም ኢትዮጵያ ነፃ ሉዓላዊት የሆነችበትን፤ ሁለትም የውጫሌን ውል የሰረዘው ስምምነት ላይ የሰላም ድርድሩን የተካፈሉ ናቸው።
እነዚህ ጀግኖች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ስማቸው በክብር ከፍ ብሎ፤ የጀግንነት መጠሪያቸውን አስከትሎ ሐውልት ቆሞላቸዋል።
ጦርነቱ የተካሄደበትን የዓድዋን ሰንሰለታማ ተራራ የሚያሳየው የአሸዋ ገበታም ሌላው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ውበትና ታሪክ ነው፡፡ የዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮችን መልክዓ- ምድር የሚሳየው የመሬት ላይ ንድፍ ስራ ኢትዮጵያዊያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነፃነት የከፈሉትን መስዋዕትነት ያሳያል። ከተራሮቹ አጠገብ ጣሊያን ስሪት የሆነና በጦርነቱ ወቅት ጥቅም ላይ የዋለ “ቶሪኖ 1883” የሚል ጽሁፍ የተቀረጸበት መድፍ ይገኛል።
የአርሶ አደሮችና ሌሎችም የጦርነቱ ተሳታፊዎች ውለታም አልተረሳም። ተዋጊዎችን ያጓጓዙ 45ሺህ ፈረሰኞች የፈጸሙትን ጀብድ ባልዘነጋው ሙዚየም ‘የዓድዋ ፈረሰኞች የድል ሐውልት’ ቆሟል፡፡ የዓድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያን ከወራሪው የኢጣሊያ ሠራዊት ለመታደግ ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ በአንድነት መሰባሰባቸውን የሚያሳይ ‘የአንድነት ድልድይ’ም ተገንብቷል።
በጦርነቱ ወቅት ሕዝብና አገርን በታማኝነት ሲያስተዳድሩ የቆዩ እንደራሴዎች ስዕላዊ መታሰቢያ፣ በጦርነቱ ወቅት የነበረውን የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚገልጹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና የመገልገያ ቁሳቁሶች፣ ስዕሎችና ቅርጾች፤ የግብርና ስራቸውን አቋርጠው አገር አናስደፍርም በማለት ታጥቀው ድል የተጎናጸፉ አርሶ አደሮች፤ በጦርነቱ ወቅት ሴቶች የቤት ኃላፊነትን ከመወጣት ባሻገር በአዋጊነት፣ በመረጃ ሰጪነት ቁስለኞችን በመንከባከብ ለፈጸሙት አኩሪ ተግባር የተሰየመ ማስታወሻ፤
በአንድ ጊዜ እስከ ሦስት ሺህ የሚደርሱ እንግዶችን ማስተናገድ የሚችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የስብሰባ አዳራሽ፣ መላው ሕዝብ የጦርነት ክተት አዋጅ ጥሪ ሲሰማ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው አገሩን ከወራሪ ለመታደግ በወኔ መነሳቱን፣ ወደ ጦር ግንባር መትመሙን እና በጀግንነት የመፋለሙን ትዕይንቶች የሚያሳዩ ስክሪኖች፤ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተባብረው አፍሪካን በራስ አቅም ማልማት እንደሚቻል ያሳዩበት፣ አፍሪካዊው ተምሣሌት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፏፏቴ፤ ኢትዮጵያዊያን ለጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ላደረጉት ተጋድሎ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የፓን- አፍሪካ ሐውልት . . . እነዚህና ሌሎችም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከትመዋል። ከሙዚየሙ ዋናው መግቢያ የጀመረው ጉብኝት ቀጥሏል፤ በውስጡ የሚታየው ሁሉም
ነገር የድል፣ የአሸናፊነት ኩራት ስሜት ውስጥ ይከታል፤ በጎብኚዎቹ ፊት ላይ የሚነበበውም ይኸው ነው፤ የአርበኞች ልጅነት ኩራት፤ የልማት አርበኝነት።
በሙዚየሙ መሐል ላይ፤ የዛሬ 128 ዓመት ኢትዮጵያዊያንን ከምስራቅ እስከ ምዕራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ለመቀስቀስ የክተት ጥሪ የተደረገበት ግዙፍ ነጋሪት ተገሽሯል፤ በነጋሪቱ ግራና ቀኝ ለጦርነቱ መንስኤ የሆነው የውጫሌው ውል አንቀጽ 17፣ የዓድዋ ታሪክ እንዲሁም ከድል ወደ ሰላም የሚለው የአዲስ አበባ ስምምነት ሰነድ ተዘርግቶ ይታያል።
የሙዚየሙ የትኩረት ማዕከል በሆነው ግዙፍ ነጋሪት ቀልባቸው የተሳበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአስጎብኚውን ገለጻ አቋርጠው ወደ ነጋሪቱ ተጠጉ፤ በላዩ ላይ የተቀመጠውን መምቻ አንስተው ጠበቅ አድርገው ያዙት ፊታቸው ላይ የሚታየው ብሩህ ፈገግታ አብረዋቸው በነበሩት ጎብኚዎችም ላይ ተጋብቷል፤ ነጋሪቱን ጎሰሙት፤ ድ . . . ም - ድ . . . ም - ድ . . . ም . . . አዋጅ፣ አዋጅ፣ አዋጅ . . .
128 ዓመት ወደኋላ . . .
ጊዜው አውሮፓዊያን አህጉረ አፍሪካን ለመቀራመት በእጅጉ የሚመኙበት፤ ጥቁር
አፍሪካዊያንን በቅኝ ግዛት ይዘው ያሻቸውን ለማድረግ የቋመጡበት ነበር፡፡ የመጀመሪያ ትኩረታቸው የምዕራብና የደቡቡ ክፍል ላይ የነበረ ቢሆንም በ1869 ዓ.ም ስዊዝ ካናል ሲከፈት ኢትዮጵያ ኢጣሊያ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ የሚራኮቱባት ቦታ ሆነች።
“በወቅቱ ስዊዝ ካናልን መቆጣጠር የዓለም ንግድን መቆጣጠር ነው” እየተባለ ይነገር ስለነበረ አስፈላጊነቱ ከፍ ብሎ ነበር። ስዊዝ ካናልን ለመቆጣጠር ደግሞ ዓባይን መቆጣጠር ያስፈልጋል የሚል እምነት ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ ኢጣሊያ አሰብን በትንሽ ስምምነት ያዘች፤ ከእንግሊዞች ሰምምነት በኋላ በነበረው ክፍተትም ምፅዋን ያዘች፤ ቀስ በቀስም ወደታች መውረድ ጀመረች፤ በዚህ ጊዜ ማንም ያልተቆጣጠራትን ኢትዮጵያን የሚወር ኃይል መጣ” ሲሉ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት 128ኛውን የዓድዋ ድል ለመዘከር “ዓድዋ የመደመር ተምሳሌታዊ ዓርማ” በሚል መሪ ሃሳብ ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ባቀረቡት ጽሑፍ ጠቅሰዋል።
ይህን ሁኔታ ለማርገብ በሚያዚያ 1881 ዓ.ም በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያ መካከል ሃያ አንቀጾችን የያዘ እና የሁለቱን አገራት ወዳጅነት ለማጠናከር በሚል “የውጫሌ ውል ስምምነት” ተፈራረሙ። ስምምነቱ ለሁለቱም አገራት
በሚያመች መልኩ በአማርኛ እና በጣሊያንኛ ቋንቋዎች ተፅፎ ተዘጋጀ። በስምምነቱ የኢጣሊያ ፍላጎት የነበረው ግን ንግድ እና ወዳጅነት ሳይሆን መቆጣጠር ነበር። ለዓድዋ ጦርነት መነሻ፤ የነገሮች መጠንሰሻው ከዚህ ነው የጀመረው። የኢጣሊያ መንግሥት በውጫሌው ስምምነት በኩል ኢትዮጵያን እንደፈለገ ለማድረግ ተመኘ።
ነገሩ እንዲህ ነው. . .፤
በዚህ ውል አንቀጽ 17 ላይ በጣሊያንኛ የሰፈረው ጽሑፍ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ በኩል መሆን እንዳለበት ሲያመለክት፤ የአማርኛው ትርጉም ግን ግንኙነቱን በኢጣሊያ በኩል ማድረግ ትችላለች ይላል።
ይህ የትርጉም ልዩነት እንደታወቀ በመጀመሪያ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የውሉን አንቀጽ አስራ ሰባት እንደማይቀበሉ አሳወቁ። ስምምነቱን አለመቀበላቸውንም በይፋ ለአውሮፖ ኃያላን ካሳወቁ በኋላ ቀጥለውም ሙሉውን የውጫሌን ውል ውድቅ አደረጉት። ይህም ኢጣሊያ ጦሯን በማዝመት ወረራ እንድትፈጽም ሊያደርጋት እንደሚችል የተረዱት ንጉሡ ዝግጅት ማድረግ ጀመሩ። ይህም ሆኖ ግን በአገራቱ መካከል ለስድስት ዓመት ሰፊ የዲፕሎማሲ ሂደት ነበር። ብዙ ውይይቶች፣ ክርክሮችና እሰጣገባ ነበረበት።
ከዚህ ሁሉ በኋላ የአንቀጹን ትርጓሜ ማሳሳትን ሆን ብላ የፈጸመችው ኢጣሊያ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ጀመረች፡፡ ይሄኔ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለሕዝባቸው ክተት አወጁ።
አዋጅ-አዋጅ-አዋጅ . . .
“እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፋፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም። ከእንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም። አሁንም አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ የሰዉንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር። አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። የአገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ። አልተውህም። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻየ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ።”
የንጉሡን የክተት ጥሪ ተከትሎ ከመላ ሀገሪቱ የተሰባሰበው ሠራዊት ሀገሩን ከኢጣሊያ ወረራ ለመከላከል ያለውን መሳሪያ ይዞ ወደ ሰሜን አቀና፤ በአፄ ምኒልክ የተመራው ሠራዊት እስከ ሃያ ሺህ የሚደርሱ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከአንድ መቶ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አርበኛ ወደ ዓድዋ ሲተም መነሻው አዲስ አበባ ነበር።
ሠራዊቱ ዓድዋ ለመድረስ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር አካባቢ በእግሩና በጋማ ከብት ተጉዞ (ዝግጅቱና ጉዞው ስድስት ወራትን ወስዷል) ዓድዋ ከደረሰ በኋላ ለፍልሚያ አመቺ ጊዜ ሲጠብቅ ቆይቶ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም 20 ሺህ ያህል ወታደሮችን ካሰለፈው አውሮፓዊ ኃይል ጋር ጦርነት ገጠመ።
ለግማሽ ቀን በተካሄደው ጦርነት አሸናፊ እና ተሸናፊው ተለየ። የኢትዮጵያ አርበኞች በሁሉም አቅጣጫ በኢጣሊያ ሠራዊት ላይ በሰነዘሩት ጥቃት ከባድ ጉዳት ስላደረሱበት በአንድ ላይ ተሰልፎ ኢትዮጵያዊያኑን መቋቋም ሳይችል ቀረ። በሺህዎች የሚቆጠሩ የኢጣሊያ ወታደሮች ሲገደሉ ሌሎች ሺህዎች ደግሞ ተማረኩ። አርበኞቹ መድፎችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ ማረኩ። የኢጣሊያን ሠራዊት ከመሩት መኮንኖች መካከል ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ ዋና አዛዥ የነበረው ጄኔራል ባራቴሪ ሸሽቶ አመለጠ።
እነዚያ ኢትዮጵያ የምትሰኝ ሀገር ዜጎች፤ ጀግኖች፣ ኩሩዎች፣ አገር ወዳዶች፣ አትንኩን ባይ ሕዝቦች ነፃነታቸውን ያወጁባት ብሎም ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን ድል ያስመዘገቡባት ልዩና ታሪካዊ ዕለት የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ዓድዋ ላይ ታላቅ ገድል ፈጸሙ፤ ለጥቁሮች ነፃነት የሆነ፤ ዓለምን ያስደነቀ ዜናም ተሰማ። ኢትዮጵያ ወራሪውን የኢጣሊያ ሠራዊት ድል በመንሳት አኩሪ ታሪክ አስመዘገበች።
ዓድዋ የፓን አፍሪካ እርሾ
በኢጣሊያ ላይ ሽንፈትን ያስከተለው የዓድዋ ድል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ከማፅናት ባሻገር አድማስ ተሻግሮ፣ አህጉራትን አቋርጦ የተሰማ፤ በዓለም ዙሪያም ጉልህ ተጽዕኖ ያስከተለ፤ በዘመናዊው ዓለም የፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ውስጥ የኢትዮጵያ ስም ተደጋግሞ ከሚነሳባቸው ክስተቶች መካከልም አንዱ ለመሆን የበቃ፤ በተለይ በጥቁሮች ዘንድ ለነፃነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ መነቃቃትና ተስፋን የሰጠ ክስተት ነው።
በዓድዋ ድል የተፈጠሩ ክስተቶችና ያስከተለውን ውጤት አስመልክቶ በታሪክ አጥኚዎች ከሰፈሩ የተለያዩ ነጥቦች መካከል አፍሪካን ተቀራምተዋት በነበሩት ቅኝ ገዥዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል፤ አፍሪካ ውስጥ አውሮፓዊያንን የሚገዳደር ወታደራዊ ኃይል እንዳለ አሳይቷል፤
ነጮች በጥቁሮች ላይ የነበራቸውን የኃያልነት ትርክት ከመሰረቱ ቀይሯል፤ ‘ዓድዋ’ ኢትዮጵያ ለጥቁሮች የነፃነት ቀንዲል ሆና እንድትታይ አድርጓታል። በሌላ በኩል የኢጣሊያን መስፋፋት ቀያሽ የነበረው የፍራንሲስኮ ክርስፒ አስተዳደር እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል፤ የዓድዋን ጦርነት የመራው የጄኔራል ባራቲየሪ ውድቀት ሆኖ ለሽንፈቱ ክስ ተመስርቶበታል። በመጨረሻም ኢጣሊያ የዓድዋ ጦርነት ምክንያት የነበረውን የውጫሌ ስምምነት ውድቅ ያደረገውንና የኢትዮጵያን ነፃ ሀገርነት የሚቀበለውን የአዲስ አበባውን ስምምነት እንድትፈርም አድርጓል።
ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለዓድዋ ድል አስተዋጽኦ ላበረከቱ የጦር መሪዎች መታሰቢያ ሐውልትና ተቋማትን በስማቸው ከመሰየም የዘለለ የራሱ ሙዚየም ሳይሰራለት ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ተቆጥሯል።
የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ ከዓድዋ ድል በኋላ የነበሩት ሰባት ዓመታት የሀዘን እንደነበሩ፤ ከዚያም በኋላ የዓድዋ ድል በመገናኛ ብዙሃን ለአንድ ቀን የሚዘከር ሆኖ መቆየቱን በማንሳት “የዓድዋን ትሩፋት ስንናገር ሰው ገብረን ማሸነፋችንን መርሳት የለብንም” ሲሉ በአጽንኦት ይናገራሉ።
“ዓድዋን ስናነሳ ብዙ የታሪክ ዘርፎችን የምናጠናበት፤ የጦርነት ደረጃውን ስናነሳ ዛሬም የጦር ትምህርት ቤቶች የሚማሩትን ስልት ያስገኘ መሆኑን፤ ዲፕሎማሲውን ስናነሳ ስድስቱ ዓመት ሰፊ የዲፕሎማሲ ጥናት የሚያስጠናን ነው፤ የኅብረተሰብ ታሪኩን ስናነሳ ከመቶ ሺህ ለሚልቅ ሰው ቀለብ፣ ስንቅ ዝግጅቱን ማሰብ ያስፈልጋል፤ ይህ አሁን እንኳን አስቸጋሪ ነው። ኅብረተሰቡ በሙሉ ነው የወጣው ተዋጊው ብቻ አይደለም ድጋፍ ሰጪውም የነበረበት የሴቶች ድርሻ፣ የአጋሰሶቹ ድርሻ ብዙ አካላት አስተዋጽኦ ያደረጉበት ጦርነት ነው። የመሪዎቹ ድርሻ እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ መሆኑን እየተረዳን ስንመጣ ነው የዓድዋን ክብር የምንገነዘበው” ይላሉ የታሪክ ምሁሩ።
ከዓድዋ ድል ማግሥት ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ቦታዋን አገኘች፤ አምባሳደሮች ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ ለማግኘት ወደ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተግተልትለው መጥተዋል። ኢትዮጵያ ማንም የማይወዳደረውን ቦታ አገኘች። አዲስ አበባ ዛሬ የኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካም መዲና ናት። ከዓለም የዲፕሎማቲክ ከተሞች ሦስተኛዋ ናት። ዓድዋ ባይኖር ኖሮ ይህ የሚታሰብ፣ የሚሆን
አይደለም። ዓድዋ በዲፕሎማሲው ያስገኘው ውጤት በጣም ብዙ ነው፤ ለጭቁን ሕዝቦችስ ብለን የጠየቅን እንደሆነ ‘ነጭ ይሸነፋል’ የሚለውን ኢትዮጵያ በተግባር አስመስክራለች።
የአፍሪካ ነፃነት የተገኘው፤ ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች የሆነችው፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አዲስ አበባ ውስጥ የተመሰረተው። በዓድዋ ተምሣሌትነት ነው።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለኢትዮጵያዊያን ሌላም አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል። የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን፣ በዓለም ላይ እጅግ ጥቂት አገራት ብቻ ባሳኩት የሆሎግራም ቴክኖሎጂ ሦስት ፎቶግራፎችና ጥራት በሌለው ድምፅ የተቀረፀ (የተቀዳ) የዳግማዊ አፄ ምኒልክን ንግግር በአዲስ መልዕክትና በዛሬ ምንነት ከመቶ ዓመት በፊት በሞት የተለዩትን ንጉሥ በታዳሚዎች ፊት ከስቶ አነጋግሯል።
ከሙዚየሙ ፋይዳዎች በጥቂቱ
ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ወረራ ያሳየችውን ተቃውሞና አልገዛም ባይነት ማስታወስ ብሎም ድሏን መዘከር የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን መገንባት ማዕከላዊ ሀሳቦች መካከል አንዱ ነው።
የመታሰቢያ ሙዚየሙ የአርበኞችን ድል ከመዘከርና ከማስታወስ ባሻገር የሀገር ፍቅርን፣ በሕብረት፣ በአንድነት መቆም ለድል እንደሚያበቃ፣ ድል ማድረግ በፈተናዎች መፅናትን እንደሚጠይቅ ለትውልድ ማስተማሪያነት የገዘፈ ፋይዳ አለው።
ለዓለም ሕዝብ በኩራት ልናስጎበኘው የምንችለው የድል ታሪክ በመሆኑ የቱሪስት መስህብም ነው። አዲስ አበባ ሦስተኛዋ ዓለም አቀፍ የኮንፍረንስ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን የቱሪዝም አቅምን የሚያሳድጉ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ አዳራሾች ጭምር በሙዚየሙ መገኘታቸው ፋይዳውን ያጎላዋል።
ሙዚየሙ በዓድዋ ጦርነት ከተመዘገበው ድል ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። የቀደመውን የአባቶችን ጥበብ፣ ጀግንነት፣ ትዕግሥት፣ ዲፕሎማሲ እና ለጠላት ትምህርት የመሆንን ተግባር በውስጡ የያዘ በመሆኑ በዓለም
ሕዝቦች የሚጎበኝ ግዙፍ የታሪክ ትምህርት ቤት (ሙዚየም) ያደርገዋል።
የዓድዋ ትሩፋት ለትውልዱ
የዛሬው ትውልድ ከዓድዋ የተሰጠው ጀግንነት ነው፤ መነሻው ብሔራዊ አንድነት የሆነ ጀግንነት፤ ጥያቄው ይህን የጀግንነት ታሪክ እየዘከርንና በእሱም እየተኩራራን እንቀጥል ወይንስ. . .? ረዳት ፕሮፌሰር ምሕረቱ ሻንቆ /በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ/ “ታሪክን ያልተማሩ ከታሪክ አይማሩም” ሲሉ ይጀምራሉ፤ ታሪክን መማር ያስፈልጋል ምክንያቱም ከስህተት ተምሮ መልካም ነገርን ያስቀጥላልና። አገራት ለምን ወደኋላ ቀሩ ለምን አላደጉም በሚል ብዙ አጥኚዎች ከታሪክና ከኢኮኖሚ አንጻር አጥንተው ሦስት ነገሮችን በሞዴል ደረጃ ማስቀመጣቸውን ያነሳሉ።
አንዳንድ አገራት በትዝታ ይነዳሉ፤ ትናንት የሆነ ማማ ላይ ደርሰው እሱን ብቻ እያወሩ ይኖራሉ፤ እንደ ምሣሌ የተጠቀሰ በቅርብ ጊዜ የሆነው እንግሊዝ ታላቋ ብሪቴን ስለነበርኩኝ የአውሮፓ ኅብረት የምትሉትን አልፈልግም ማለቷ በጥናቱ ተጠቅሷል። ትውስታ ተብሎ የተቀመጠው ለትውልድ ይጠቅማል፤ በትዝታ ብቻ የዛሬውን ዓለም መዋጀት ግን አይቻልም።
ዓድዋ ለኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም ለአሁኑ ትውልድ ምንድን ነው ካልን መነሻና መስፈንጠሪያ ነጥብ ነው። ረዳት ፕሮፌሰር ምሕረቱ ሻንቆ “ሌሎች አገራት ተሸንፈው ከዜሮ ተነስተዋል፤ እነ ጀርመን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዛሬ በኢኮኖሚ የአውሮፓ መሪ የሆኑት ከዜሮ ተነስተው ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ግን ከዜሮ አልተነሳንም፤ ሌሎች ከዘጠኝ ሚሊዮን ሕዝብ ስድስቱ ሚሊዮን አልቆ ሦስቱ ሚሊዮን ብቻ ገናና የሆኑበት ታሪክ አለ፤ እኛ ግን መነሻ አለን፤ ወረቱ ደግሞ ዓድዋ ለእኛ የሚያስተላልፈው ነው” ይላሉ።
በትዝታ የሚነዱት አገራት ዋጋ እየከፈሉ ነው። ዓድዋ ለእኛ በትዝታ የምንነዳበት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ለተግባር እንድንነሳ የሚያደርገን ‘እውነታ’ የሚባለው ሞዴል ጋር መምጣት አለበት። ሌላው ስኬታማ የሚያደርገው ሕልመኛ የሚባለው ሞዴል ጋር መምጣትም አለብን፤ (Memory driven, Reality driven, Dream driven) ዓድዋ ለእኛ የእነዚህ ሦስት ሞዴሎች ስራ መሆን አለበት። ትውስታ ብቻ ከሆነ
አይሆንም፤ ዛሬ ላይ እኛን የሚያሰራ፣ ለነገም እንድናቅድ የሚረዳ መሆን አለበት።
ትውልዱ ከዓድዋ እሴት ምን ይማር?
የአሁኑም ሆነ መጪው ትውልድ የወል ታሪካችን ከሆነው ከዓድዋ ድል ሊማራቸው የሚገቡ በርካታ ቁምነገሮች አሉ።
ረዳት ፕሮፌሰር ምሕረቱ ሻንቆ የአሁኑም ይሁን መጪው ትውልድ ሊማራቸው፣ ሊወርሳቸው ይገባሉ ያሏቸውን የዓድዋ ትውልድ መገለጫዎች እንዲህ ያብራራሉ፤ “አንደኛው መደማመጥ ነው፤ መደማመጥ ያልቻሉ አገራት ትልቅ ሕዝብ ሆነው ሳለ ትንሽ ሆነው ተከፋፍለዋል፤ ከአራቱም አቅጣጫ ተሰብስበው ወደ ጦርነቱ የሄዱት መደማመጥ ስለቻሉ ነው። የማይደማመጥ ሕዝብና አገር የትም አይደርስም፤ ለአንድ አገር ትልቁ ድልድይ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል መደረግ ያለበትም መደማመጥ ነው”።
ያለመገዛት ስሜት ሁለተኛው የዓድዋ ትውልድ መገለጫ ነው፤ ኢትዮጵያዊያን የማሸነፍና የድል ስሜት ይዘው አልተነሱም፤ ይዘው የተነሱት “አንገዛም” የሚል ስሜት ነው። አንዳንዴ ያለመገዛት ስሜት ከጊዜያዊ ድሎች ይበልጣል፤ አልገዛም የሚል ሰው ለጊዜው ቢሸነፍ እንኳን ሌላ ቀን ያሸንፋል።
ሦስተኛው የዓድዋ ትውልድ መገለጫ ይላሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ “ሀገር ትልቁ ስዕላቸው ነበረች፤ ከስሜታቸው፣ ከሰፈራቸው፣ ከሃይማኖታቸው፣ ከብሔራቸው በላይ ‘ሀገር’ የሚለውን ይዘው ነው የተነሱት፤ ዓድዋ የዚህ ነው የዚያ ነው አላሉም”።
የዛሬ 128 ዓመት የተሰራውን ታሪክ ዛሬ እኛ እንድንዘክር ያደረገው አባቶቻችን ለትውልድ ስለሰሩ ነው፤ ለመጪው ትውልድ ምን እናስተላልፍ ብለው ነው፤ ያንን ገድል የፈፀሙት ለመጪው ትውልድ ሲሉ ነው፤ ለራሳቸው ቢሆን አናስታውሳቸውም ነበር፤ ታሪካቸውም እዚህ አይደርስም ነበር፤ ይህ ሌላው መገለጫቸው ነው።
“መነሻ፣ አቅጣጫ እና መዳረሻውን የሚያውቅ ነው፤ የዘመናችን ችግር መነሻ አያስቸግረንም፤ አቅጣጫና መዳረሻ ግን ይጠፋብናል፤ ብዙዎች አገርን እንደ እግር ኳስ ደጋፊ ይሆኑታል ሲመቻቸው የሚደግፉ አገር ችግር ውስጥ
ስትሆን ወደሌላ ቦታ የሚሄዱ፤ ችግር ቢገጥመን እንኳን ከሀገራችን ጋር መቆም ነው ያለብን” ሲሉ ነው ረዳት ፕሮፌሰር ምሕረቱ የዓድዋ ትውልድ መገለጫዎችን ያብራሩት።
ለዛሬውም፣ ለመጪውም ትውልድ ታሪክ ከቶም የጥላቻ ምንጭ ሊሆን አይገባም፤ የታሪክን ክፉውንም ደጉንም አስቀምጠን የሚያስተምረንን እንወስዳለን፤ እንደ አገር የተሰራው ታሪክ፣ የዓድዋ ድልም የጋራችን ነው።
“የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የዓድዋን ትርክቶች የምንወያይበት ይሆናል፤ በመጨረሻም የኢትዮጵያዊያን ይሆናል የሚሉት የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ የእኔ፣ የአንተ መባባሉ ዓድዋን በሥርዓቱ እንዳንጠቀምበት አድርጎን ቆይቷል፤ አሁን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ማዕቀፍ ሆኖናል፤ የምክክር፣ የውይይት፣ የክርክር. . . ያለንን ትርክት ሁሉ አቅርበን እያመሳከርን ስምምነት የምንደርስበት ይሆናል። በሂደት ደግሞ የአፍሪካ ማድረግ፤ ወደ ተባበሩት መንግሥታት መውሰድ ያስችለናል ይላሉ።
መጪው ጊዜ ያሉብንን ጉድለቶች አስተካክለን ዓለምአቀፍ ማድረግ፤ ልማት፣ ቴክኖሎጂ፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ላይ ያሉብንን ደካማ ጎኖች እንደ አጀንዳ ወስደን ከቴክኖሎጂ ጋር የምንታረቅበት፣ ለውጥ የምናመጣበት ይሆናል።
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ብሔራዊ ትርክትን የሚገነባ፤ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ነው። የኅብረተሰቡን አንድነትና ተሳትፎ ያሳያል፤ ታሪካዊ ዳራው ሀገር እና አህጉርን የሚወክል ነው፤ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ መገንባቱ ደግሞ በአፍሪካዊያን መካከል ኅብረትን ይፈጥራል። በሌላ በኩል የከተማዋን ሥነ ጥበብ በማሳደግ የቱሪስት መስህብ ከማድረግ አንፃርም ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል። ሙዚየሙ የጠራ፣ ሁሉን ያካተተ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ተገንብቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየሙ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “አባቶቻችን እሴት ነበራቸው፤ ያን እሴት ለማሳካት የተጠቀሙበት እሣትም ነበራቸው፤ አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉበት ነፃነትና ክብር እሴት ነው፤ ነፃነትና ክብር ለመጎናጸፍ
የሄዱበት መንገድ ግን እሣት ነው። እኛ ልንወርስ የሚገባው ነፃነቱን፣ ክብሩን፣ አንድነቱን እንጂ ያን ሊያሳኩ የታገሉበትን ስልት እሳቱን መውረስ አይጠበቅብንም” ብለዋል።
ዘመን ተሻጋሪውን እሴት የወረስነው እኛ የጀግኖች አባቶቻችን ልጆች፤ የወረስነው እምቢኝ ማለት ለወራሪ፤ እምቢኝ ማለት ለድህነት፤ እምቢኝ ማለት ለልመና ስለሆነ ይህንን ለፃነትና ክብር የወረሰ ኢትዮጵያዊ ዛሬም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚተጋ መሆን አለበት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን አስመልክተው ሲናገሩ ስንዴ ሲባል፣ ሩዝ ሲባል፣ ሌማት ሲባል ዓድዋ የሚታሰበው መሆን አለበት ነው ያሉት። “ምክንያቱም የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ከቻልን ዓድዋ በሌላ መንገድ በሀገራችን ሊከወን ይችላል፤ ለማኝ ሀገር ነፃ መሆን ስለማትችል”።
የአየር ንብረት ለውጥ ዓለምን አስቸግሯል እኛን ደግሞ ድርቅ በተደጋጋሚ ጎብኝቶናል፤ ይህንን ለመከላከል አረንጓዴ አሻራ ሲባል ዓድዋ ሚታወሰው፣ የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያመጣው ጣጣ አልገዛም፣ እጅ ተጠቅሜ፣ ተባብሬ የከባቢ አየርን ልገዳደር እችላለሁ የሚል እንጂ እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ ችግር ሲመጣ ተቸገርኩ የሚል መሆን የለበትም። “እኛ ኢትዮጵያዊያን እሴት ከወረስን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመገዳደር በጋራ መቆም የምንችል መሆን
አለብን”
በተጨማሪም አባቶቻችን በዓድዋ በጋሻ እና በጦር፣ በፈረስ ተዋግተው፣ ደምተውና ሞተው ኢትዮጵያን ነፃ የጥቁር ሕዝቦች ምልክት አድርገዋታል፤ ዛሬ የዓድዋ እሴት በእኛ የተወረሰ የሚሆነው ቴክኖሎጂን ለማወቅ፣ ለመጠቀም ስንጥር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ቀደምት አባቶቻችን ለቴክኖሎጂ የነበራቸውም ጥማትና ፍላጎት ማሳያ የሆነችውን፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገጣጠመችውንና ከሀገር ወጥታ ከ88 ዓመት በኋላ ወደ አገሯ ተመልሳ ማረፊያዋን በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ያደረገችውን ፀሐይ አውሮፕላንን በአብነት ጠቅሰዋል።
“ኢትዮጵያን ከነክብሯ፣ ከነነፃነቷ ለልጆቻችን ለማስተላለፍ እንደዚህ ያለ መታሰቢያ በእጅጉ አስፈላጊ ነው። እኛ ጀምረነዋል ትውልድ ይጨርሰዋል” ብለው ሃሳባቸውን ከመቋጨታቸው በፊት ይህን አሉ “ኢትዮጵያ የተባለችው አውሮፕላን ዛሬ ሞተር እያሞቀች ነው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ማኮብኮብ ትጀምራለች፤ ከዚያም መብረር ትጀምራለች”።
ጎበዝ! አገሬን ያለ ሞተሯን አሙቃ ሳትጨርስ፣ ማኮብኮብ ሳትጀምር መሳፈር ቢችል መልካም ነው።
ፖለቲካ
የአገራዊ ምክክሩ ዋነኛ ባለቤት
ኢትዮጵያዊያን
የአገራዊ ምክክሩ ዋነኛ ባለቤት
በምክክሩ ሂደት መንግሥትና ፖለቲከኞች አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳርፉ መጠንቀቅ ይገባል ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የፖለቲካ እና የሀሳብ መሪዎች መካከል መሰረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች የሀሳብ ልዩነትና አለመግባባት ይታያል። ይህን ልዩነትና አለመግባባት በውይይት ለመፍታት አገራዊ ምክክርን ማካሄድ አስፈላጊ ነው። መንግሥት ሁሉን አቃፊ፣ አካታችና አሳታፊ አገራዊ ምክክር ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ የመተማመንና ተቀራርቦ የመስራት ባህልን ለማጎልበት፣ የተሸረሸሩ ማኅበራዊ ዕሴቶችን ለማደስ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲያስገነዝብ ቆይቷል። አገራዊ የምክክር ሂደትን ለማሳለጥ የሚያስችል ሕግና ሥርዓት አበጅቷል። አገራዊ ምክክሩ ተአማኒና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ከሚያስችሉ ጉዳዮች መካከል ምክክሩን የሚያመቻች፣ የሚያስተባብርና የሚመራው አካል ብቃትና ገለልተኛነት አንዱና ዋነኛው ነው። በመሆኑም መንግሥት አገራዊ ምክክሩን በብቃት የሚመራ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አቋቁሟል። ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት በብቃት በመወጣት አገራዊ ምክክሩን ውጤታማ ለማድረግ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። ነጋሪ መጽሔት በኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ስለሚጠበቀው አገራዊ
በምሕረት አንዷለም
ኢትዮጵያዊያን
ምክክር ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ የሌሎች አገራት ተሞክሮ፣ የኮሚሽኑ የእስካሁን የዝግጅት ስራዎች ስለሚገኙበት ደረጃ እና የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጋር ያደረገችው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል። ነጋሪ፦ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለቃለመጠይቁ ፈቃደኛ ስለሆኑ እናመሰግናለን! ፕሮፌሰር መስፍን፦ እንኳን ደህና መጣችሁ። ነጋሪ፦ የአገራዊ ምክክር ምንነትና ዓለም አቀፋዊ ዳራው ምን ይመስላል? ፕሮፌሰር መስፍን፦ አገራዊ ምክክር አንድ አገር ላይ አለመግባባቶችና ችግሮች ሲኖሩ፤ ወደ ግጭትና ጦርነት ሲገባ፤ የአገሪቱ ሕግና ደንብ በአግባቡ ሳይሰራ ሲቀር፤ ከጦርነት ለመውጣትና ሽግግር አድርጎ ወደ ሰላም ለመምጣት ሕዝቦች በጋራ ለችግሩ መፍትሔ የሚያበጁበት ሰላማዊ ሂደት ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን መልካም የሚሆነው አስፈላጊውን ምክክር አድርጎ ሁሉም በሃሳብ ልዕልና አሸናፊ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ነው። መከራ፣ ችግር፣ ቀውስ፣ የአዕምሮ ስብራት የደረሱ በደሎችን ለትውልድ እንዳይተላለፉ በምክክር ማከም ነው። ይህን የምክክር ሂደት አውሮፓዊያን ተጠቅመውበት አንጻራዊ ሰላምና የተሟላ አውሮፓዊ አገር ፈጥረው እየሄዱ ነው፤ አሜሪካኖች አገራቸውን ያነጹበት ዕድሜ ከሌሎች አንጻር ሲታይ ትንሽ ነው፤ ሦስት መቶና አራት መቶ ዓመት ቢሆን ነው። ሰሜነኞች ከደቡቦች፣ ከእንግሊዝ፣ ከአየርላንድ፣ ከስፔን እና ከሌሎቹም መጥተው እርስ በእርስ በጦርነት ተላልቀውና ተፋጅተው መጨረሻ ላይ በምክክር ጠንካራ የሆነ አገር መስርተው፣ ሕግና ሥርዓት አክብረው በመኖር ታላቅ አገር ገንብተዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የደረሰው ግፍ ሁሉ የታለፈው አውሮፓዊያን፣ እስያዊያን፣ አሜሪካዊያን በሰለጠነ መንገድ ምክክር በማድረግና የሽግግር ፍትሕን በማካሄድ የሚካሰውን ክሰው፣ የተበደለውን ይቅርታ ጠይቀው በአጠቃላይ ጥፋታቸውን አምነው ጠንካራ አገር ፈጥረው ሕዝባቸውን እየመሩ ይገኛሉ። እንዲሁም ቀረብ ባሉ ጊዜያት ደግሞ በባልካን፣ በሰሜን አፍሪካ፣ በላቲን አሜሪካ አገራዊ ምክክር አካሂደው የተሻለ አንጻራዊ ሰላምን ያገኙ አገራትም አሉ። ነጋሪ፦ የዓለምን ዳራ ካየን፣ ኢትዮጵያም አገራዊ ምክክር ለማካሄድ
በ 21 ኛው ክፍለ ዘመን መልካም የሚሆነው አስፈላጊውን ምክክር አድርጎ ሁሉም በሃሳብ ልዕልና አሸናፊ ሆነው እንዲወጡ ማድረግ ነው። መከራ፣ ችግር፣ ቀውስ፣ የአዕምሮ ስብራት የደረሱ በደሎች ለትውልድ እንዳይተላለፉ በምክክር
ማከም ነው።
ላለፉት 20 እና ከዚያ በላይ ዓመታት አኩርፎ ጫካ መግባት በዛ፤ ለምን አንመካከርም፤ ለምን ተመካክረን ወደ መግባባት አንደርስም፤ ለምን የመግባባት ተቋም አይኖረንም የሚሉ ጥያቄዎች በየጊዜው ሲነሱ ነበር። “ለሁሉም ጊዜ አለው” እንዲል ብሂሉ አሁን ጊዜው ደርሶ የግጭት ሂደት የማያዋጣ መሆኑን የአገራችን ሕዝቦች እና የፌዴራልና የክልል መንግሥታት በማመናቸው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በአዋጅ 1265/2014 እንዲቋቋም ተደርጓል። ነጋሪ፦ የምክክሩ ባለቤት ማን ነው? ፕሮፌሰር መስፍን፦ የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ ጠንካራ ድንጋጌዎች አሉት፤ መግቢያው ላይ እኛ ኢትዮጵያዊያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ሰላም ቢኖርም ባይኖርም አብረን ኖረናል፤ ቋንቋዎችና ባሕሎች በሚገባ ተከብረው ሁላችንም በያለንበት ተዘዋውረን መኖር ካስፈለገን ያሉብንን ክፍተቶች ለመሙላት ተመካክረን መግባባት ላይ መድረስ አለብን፤ በሁሉም አካባቢዎች ግጭቶች ተፈጥረዋል፤ ለዚህ ያደረሱን ያላግባቡን ምክንያቶች አሉ ማለት ነው፤ እነዚህን ለመፍታት ሕግና ድንጋጌዎችን፣ ሥርዓቶችን በትክክል ማውጣት አለብን፤ ባለቤቱም ሕዝቡ ነው። ላለመግባባት የዳረጉንን ምክንያቶች በተወሰኑ ጊዜያት ውስጥ ነቅሶ ለማውጣት መምከር አለብን፤ የምክክሩ ባለቤት ማን ነው የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ በአዋጁ ላይ ተቀምጧል። ነጋሪ፦ አገራዊ ምክክሩ ሲካሄድ የሚከተላቸው መሰረታዊ መርሆዎች ምንድን ናቸው? ፕሮፌሰር መስፍን፦ የመጀመሪያው መርህ አካታች መሆን አለበት፤ አካታች ሲባል ከምክክሩ የሚቀር ማንም የለም ማለት ነው። ሁለተኛው አሳታፊነት ነው፤ ይህም በምክክሩ የተካተቱት ሁሉ በሂደቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሃሳባቸውን ማዋጣትና ማንሸራሸር አለባቸው። አንዳንድ ጊዜ የዚህ አገር ችግር የምሁራን፣ የልሂቃን፣ የሀሳብ አመንጪዎች፣ የፖለቲከኞች ተደርጎ ይወሰዳል። ችግሩን ያመጡት እነሱ ናቸው፤ ተጠያቂዎችም ራሳቸው ስለሆኑ ተሰባስበው፤ ተወያይተው ወደ መግባባት መድረስ አለባቸው የሚሉ ሃሳቦች ይነሳሉ። ሆኖም እነዚህን የኅብረተሰብ ክፍሎች አይተናቸዋል፤ አሁንም ፖለቲከኞች አሉ፤ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ 65 የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፤ እስከዛሬ የሞከሩትንም አይተናል። ነገር ግን ሕዝብስ ችግርህ ምንድን ነው ተብሎ ተጠይቆ ያውቃል? በዚህች አገር ለብዙ ሺህ ዓመታት የኖረው
በዝግጅት ላይ ትገኛለች፤ ለመሆኑ እንደ አገር ምክክር ለማድረግ አስገዳጅ የሆኑ ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ኢትዮጵያዊያን ለብዙ ሺህ ዘመናት ተቻችለውና ተከባብረው፣ ተጋብተውና ተዋልደው ላይለያዩ እርስ በእርስ ተጋምደው፣ ቋንቋ ባህላቸውን አዋህደው አብረው ኖረዋል። ይሁን እንጂ በነበረው የአገረ መንግሥት ምስረታ ሂደት ውስጥ አጋጥመው በነበሩ ችግሮች አሁንም እየተጋጨን ነው። የሚያጋጩን ፖለቲከኞች፣ ልሂቃን ወዘተ. . . ናቸው ቢባልም፤ የግጭቱ መንስኤ የትኛውም ወገን ይሁን ሕዝቦች ለጉዳት መዳረጋቸው ግን አልቀረም። ስለሆነም ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አገራዊ ምክክር ማድረግ አስፈልጓል። አገራችን በተለይ ላለፉት 30 እና 40 ዓመታት አንዴ በሶሻሊዝም፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በግራ ዘመም ፖለቲካ በመሳሰሉት ስትታመስ ቆይታለች። ምንም እንኳን በሕዝቦች መካከል በነበረው ከፍታና ዝቅታ በሥርዓቱ አለመደሰት ቢኖርም፤ በዘውዳዊው አገዛዝ አንጻራዊ የሚመስል ሰላም ነበር። ሥርዓቱ በሕዝቦች መካከል ፈጥሮት የነበረው ከፍተኛ ልዩነት ወደ ተማሪዎችና ወደ ምሁራኑ መጥቶ በጊዜው የነበሩ ምሁራን በውጭ አገሮች ያስተዋሉትን በተለይ በምስራቁ ዓለም የነበረው የሶሻሊዝምና የኮሙኒዝም ርዕዮተ ዓለም በአገራችን ተግባራዊ ቢሆን የፊውዳሉ ሥርዓት ይወገዳል፤ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ይመሰረታል፤ በዚህም ገበሬው የመሬት ባለቤት ይሆናል፤ ሠራተኛው በአሠሪው አይበዘበዝም፤ እኩልነት ይሰፍናል፤ በሚል የምስራቅ አውሮፓን አስተምህሮ ለማምጣት የነበረው ትግል ምን እንደሆነ አይተናል። በወቅቱ ሕዝባዊ መንግሥት መቋቋም አለበት፤ ድህነት መጥፋት አለበት፤ አገራችን ለሁላችንም እኩል መሆን አለባት፤ የሚለው እሳቤ የወጣቱን ስሜት የሳበ ነበርና ዘውዳዊው አገዛዝ ተገርስሶ ወደ አብዮት መጣን። ከዚያ በኋላ የመጣው ወታደራዊው የደርግ መንግሥት አገርን አንድ አድርጌ ሶሻሊዝምን እተገብራለሁ በሚል ያከናወናቸው መልካም ስራዎች ያሉትን ያህል በዚያው ልክ ደግሞ የፈጸማቸው ብዙ ስህተቶች ነበሩ። በዘውዳዊው አገዛዝም ሆነ በወታደራዊው የደርግ አስተዳደር የተፈጸሙ ስህተቶችን በሚገባ በማረም ወደ ትክክለኛው ሁኔታ ለመምጣት አቅሙም ፍላጎቱም አልነበረም። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በየጊዜው የሚመጡት መንግሥታት ትክክል ነን ብለው ስለሚያምኑ
ነው። በዚህም ምክንያት ወታደራዊው የደርግ መንግሥት በሌሎች ኃይሎች ሊገረሰስ ግድ ሆኗል። በእርግጥ በደርግ ሥርዓት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ትልቅ የሚባለው መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ሆኗል፤ ጭሰኛ በመባል ይታወቅ የነበረው የገባርነት ሥርዓት ተወግዷል። ይህ ትልቅ ድል ቢሆንም፤ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ነው የሚለው ሙሉ በሙሉ የጠራና የለየለት ባለመሆኑ፣ በጉልበት የመጨፍለቅና አገርን አንድ አድርጎ ጠንካራ አሃዳዊ መንግሥት የመመስረት ሂደቱ ብዙ መከፋትን ፈጥሯል። ምንም እንኳ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በሚገባ ተጠንተው ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፤ የራሳቸውን መንግሥት ሳይሆን የጋራ መንግሥት መስርተው የሚሄዱበት አካሄድ ስለነበረ በብሔርና ብሔረሰብ ተደራጅተው ወታደራዊውን የደርግ መንግሥት አንፈልግም በማለታቸው፤ በደርግ መንግሥት ምስረታው ሂደት ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው እንደ ኢህአፓ፣ መኢሶን የመሳሰሉትን ፓርቲዎች በየደረጃው እያጠፋቸው በመሄዱ ብሶት ተፈጠረና ወደ ጫካ ገብተው ትግላቸውን ቀጠሉ። ዘውዳዊውን ሥርዓት የጣሉት ወታደሮች በአፍሪካ ግዙፍ ኃይል የሚባሉ ቢሆኑም፤ እነሱም ጫካ በገቡ ኃይሎች ተሸነፉ። በዚህም የአሸናፊና ተሸናፊ ሂደት ቀጠለ ማለት ነው። ቀጥሎ የመጣውም መንግሥት በደርግ መንግሥት የነበረውን በማጠናከር ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በሚል አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ባደረገ መልኩ ሁሉም የየራሳቸውን ክልላዊ መንግሥታት እንዲመሰርቱ እና የዞንና የወረዳ አስተዳደራዊ መዋቅሮችን እንዲዘረጉ በማድረግ መንግሥት መስርቶ ቀጠለ። ይህም በሕዝቦች መካከል የተለያዩ ስሜቶችን መፍጠር ጀመረ፤ ከፍና ዝቅ ተፈጠረ፤ ይህ መሆን የለበትም፤ ይህች አገር ለሁላችንም እኩል አልሆነችም፤ የሚል መከፋትን በመፍጠሩ ቀደም ባሉት መንግሥታት የነበረው ትግል ተጀመረ። በዚህ የአለመግባባትና የቅራኔ ጉዞ አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። ቅር የተሰኘ ሁሉ ጫካ ገብቶ ግጭትና ጦርነት በመፍጠር ምን አተረፈ የሚለው ሲታይ ግን ትርፉ ጉዳት ብቻ ነው። በመሆኑም ሕዝቦች ተነጋግረው፤ መክረውና ዘክረው፤ ምን ይሻላል የሚለውን አይተው፤ ያልተስተካከለውን አስተካክለው ወደ ፊት ለመሄድ ምክክር ማድረግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው።
ሕዝብ ነው። እያረሰም እየነገደም፤ በቋንቋ፣ በኃይማኖት፣ በባሕል ልዩነት ሳይገደብ ይህቺን አገር ጠብቆ ያኖረው ሕዝብ ነው። በኢትዮጵያ ገናና ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው ሕዝቡ ነው፤ ስለዚህ በአገራዊ ምክክሩ የአካታችነትና አሳታፊነት መርህ እንዲኖር የተፈለገው ሕዝቡ እንዲናገር ለማድረግ ነው። ነጋሪ፦ ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተቋቋመ በኋላ የመጀመሪያ ስራው ምን ነበር? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ኮሚሽኑን ለመምራትና ምክክሩን ለማስተባበር 11 ኮሚሽነሮች ተሹመናል፤ ስንጀምር የፖለቲካ ወገንተኝነት ሊኖረን እንደማይገባ በቃለመሃላ ያስረገጥነው ነው። ወደ ሥራ የገባነው ለየትኛውም ሃይማኖትና ብሔር አንወግንም፤ ይልቁንም የሁሉም ሕዝቦች ወገንተኝነት ሊኖረን ይገባል ብለን ተማምነን ነው። የምክክር ስራ ለኢትዮጵያ አዲስ ስለሆነ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍን የጀመርነው ቢሮ በማቋቋም፣ የአሰራር ደንቦችን በመቅረፅ፣ የሥነ-ሥርዓት መመሪያዎችን በማውጣት ነው። ሌላው በዚህ ምዕራፍ ያከናወንነው ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም ክልሎች በእያንዳንዱ ወረዳ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ስብጥር በአግባቡ የመለየት ስራ ነው። ለምሣሌ በአንድ ወረዳ አርሶ አደር፣ አርብቶ አደር ሊኖር ይችላል፤ በሌላው ደግሞ አሳ አጥማጅ ሊኖር ይችላል ስለዚህ ሁሉም የየራሱ የተለየ የማኅበረሰብ ዓይነት ይኖረዋል። እናም ከላይ ከክልሎች እስከ ወረዳ በመወያየትና በመግባባት የወረዳውን ማኅበረሰብ ስብጥር ለይተናል። ከዚህም ባሻገር አስራ አንድ ኮሚሽነሮች ወደ ስራ የገባነው በአራት ዘርፎች የሥራ ድልድል አድርገን ነው። አንደኛው አመራሩን የሚከታተል፣ ሁለተኛው የምክክር ሂደቱን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሚከታተል፣ ሦስተኛው የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን አጋርነትን የሚከታተል ሲሆን፤ አራተኛው ዘርፍ ደግሞ አዋጁን መነሻ ያደረጉ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን የሚያወጣ፣ ስልጠና የሚያስተባብር፣ የምርምር ስራዎችን የሚያካሂድ ነው። በዚህ መሰረት ላለፉት ሁለት ዓመታት ባከናወንናቸው ስራዎች ትልቅ ተቋም ፈጥረናል። ኮሚሽኑ ራሱን የቻለ፤ በቀጣይ ሌሎች ሰዎች ቢመጡ እያዳበሩ የሚሄዱት ተቋም እንዲሆን አድርገነዋል። ነጋሪ፦ አገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ አዲስ ከሆነ የሌሎች አገራትን ልምድ ቃኝታችሁ ይሆን? ፕሮፌሰር መስፍን፦ አዎን፤ ከስራዎቻችን አንዱና ዋነኛው አገራዊ ምክክር በሌሎች አገራት
ምን ይመስላል? እንዴት ተካሄደ? በስንት አገራት ተካሄደ? እነማን ተሳካላቸው? እንዴት ተሳካላቸው? እነማን ሳይሳካላቸው ቀረ? ለምን አልተሳካላቸውም? የሚሉትን ለይቶ ለመገንዘብ የተከተለው ሁለት አካሄዶችን ነው። አንዱ የአገራቱን ልምድ በአካል ሄዶ ማየት ነው። ይህኛው ከተቋቋምንበት ዓላማና ካለን ጊዜ አንጻር የማይቻል በመሆኑ ሁለተኛውን አካሄድ መርጠናል። በዚህም የየአገራቱን የምክክር ሰነዶች በማሰባሰብ በዝርዝር ፈትሸናል። የኬንያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የሱዳን፣ የማሊ፣ የቤኒን፣ የቱኒዚያ፣ የየመን፣ የኢራቅ፣ የጓቲማላ፣ የኮሎምቢያና የባልካንን ጨምሮ የበርካታ አገራትን ተሞክሮ አይተናል። ብዙ አገሮች ምክክር ያካሄዱት በምክንያት ነው። ለምሣሌ ኬንያ የምርጫ ሂደት ነበራቸው፤ በየጊዜው ፕሬዚዳንታቸውን የሚመርጡት በቀጥተኛ ዴሞክራሲ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ በአንድ ወቅት ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ የምርጫ ውጤት የተሰማበት ነበር፤ ያ አደገኛ ነበርና የነበረውን ግጭት ማስቆም አለብን፤ ለዚህም መመካከር አለብን ብለው ለውይይት ተቀመጡ። አጀንዳቸው የሽግግር መንግሥት ለማቋቋምም ይሁን የተመረጠውን መንግሥት ለማስቀጠል አገራዊ ምክክር ማካሄድ ነው። ለምክክር ደግሞ አወያይ ያስፈልጋል፤ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ጋናዊው ኮፊ አናን ዋና አወያይ ሆነው ሌሎች ከደቡብ አፍሪካ የመጡ አወያዮች ተመደቡ፤ ተወያዮቹም በድህረ ምርጫው ጦር የተማዘዙ ተቀናቃኝ ኃይላት ሲሆኑ፤ መሳሪያቸውን አስቀምጠው ለውይይት መጡ። ወደ ውይይት እንዲገባ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት እና ሌሎች የውጭ አካላት አዎንታዊ ተፅዕኖ ፈጠሩ። ውይይቱም አንድ ነጠላ አጀንዳ ያለው፣ ተወያዮች ፈቃደኛ የሆኑበት እና ገለልተኛ አወያዮች ያመቻቹት ስለሆነ ፍሬያማ ነበር። ሰላም ተፈጥሮ በመግባባት መርህ የመንግሥት ስልጣን ክፍፍል አድርገው ቀጠሉ። ቱኒዚያም ውስጥ እንዲሁ ፍራፍሬ የሚሸጠው ወጣት ሞሃመድ ቡአዚዚ ራሱን በእሣት ማቃጠሉን ተከትሎ በተፈጠረው የዓረብ ፀደይ አብዮት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ከአገር ጥለው በመጥፋታቸው የተነሳ መንግሥት ባለመኖሩ፣ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ገቡ። ቱኒዚያዊያን ስለ ዴሞክራሲ ባሕልና ስለ አገራዊ ምክክር ልምድ ያላቸው በመሆናቸው የንግድና የሠራተኞች ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፍትሕ አካላት በጋራ ተነሳሽነቱን ወስደው፤ አመቻቾችንና አወያዮችን ለይተው ወደ
ምክክር ገቡ። ሕገ መንግሥታቸውን በማሻሻል መንግሥታዊ ሥርዓት ፈጥረው የተረጋጋች ቱኒዚያ እንድትቀጥል አድርገዋል። በምክክር ሂደቱ የውጭና የውስጥ አሉታዊ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር በማድረጋቸው ተሳክቶላቸዋል። ለምክክር ራሳቸውን የሰጡ በሳል ተዋናዮች በመኖራቸው ውጤታማ ሆነዋል። በዚሁ ልክ አገራዊ ምክክር አካሂደው ያልተሳካላቸው አገራትም አሉ። ለምሣሌ የመን ከ30 ዓመታት በላይ ጦርነት ላይ ነው ያለችው፤ የመን መጀመሪያ አንድ አገር ነበረች፤ በኋላ ሰሜንና ደቡብ ተብላ ለሁለት ተከፈለች። እንደገና ተመልሰው አንድ ሆኑ፤ ሆኖም መጨረሻ ላይ ሊግባቡ ባለመቻላቸው መልሰው ወደ ጦርነት ገቡ። የመኖች አንድ ቋንቋ ተናገሪ፣ አንድ ሃይማኖት ተከታይ፣ አንድ ሕዝብ ቢመስሉም ብዙ ጎሳዎች ያሏቸው ናቸው። በዙሪያዋ ያሉ የባሕረ ሰላጤው አገራት ጣልቃ ገብነት በመኖሩ ጎራ ለይተው እየተጨፋጨፉ ነው። በመሀል አገራዊ ምክክር ማድረግ አለብን ብለው ጀምረው ጥሩ ሂደት ላይ ነበሩ፤ የምክክር ሂደቱ ሴቶችና ወጣቶችን ጭምር በጥሩ ሁኔታ ያሳተፈም ነበር። የኬንያ አሳታፊም አካታችም አልነበረም፤ በቱኒዚያ እውቀት አላቸው የተባሉ ተቋማት ዋና ተወያዮች ነበሩ። የመኖች ግን በመሰረታዊነት የሕዝብ ተሳታፊዎችን አካትተዋል። የጎሳ ተወካዮችም ተሳትፈዋል፤ ግን ውጤታማ አልሆኑም። የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዳይሆን ያደረጉ ሁለት ምክንያቶች አሉ፤ አንዱ ውስጣዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ሲሆን፤ ሁለተኛው ውጫዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ነው። ውጫዊ አሉታዊ ተፅዕኖው ከፍተኛ ነበር፤ ሁቲዎችን የሚደግፉ በአንድ ጎራ፤ ሌሎችን የሚደግፉ በሌላ ጎራ አሉ። በአንድ በኩል የገልፍ የትብብር ምክር ቤት የሚባለው ጥምረት ተፅዕኖው ጠንካራ ነው። በሂደቱ እጅ ጠምዝዞ የሚፈልገውን ሰው ለማስቀመጥ ይፈልግ ነበር። አጀንዳዎቻቸው አስቀድመው የተለዩ ቢሆኑም፤ ውጫዊ ተፅዕኖው ከፍተኛ በመሆኑ አገራዊ ምክክሩ ሳይሳካ ቀረ፤ ጦርነቱም ቀጠለ፤ የመንም ሰላም አልባ ሆና ቀጥላለች፤ ወደፊት ምን እንደምትሆን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። ሌላው በሱዳን የተደረገው አገራዊ የምክክር ሂደት ጥሩ ነበር፤ ከ990 በላይ አጀንዳዎች ቀድመው ተለይተው ነበር፤ የተሳታፊዎች አመራረጥም ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን ውስጣዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ነበር። የምክክር ሂደቱ የበላይ ተቆጣጣሪ የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር
ፓርቲዎችም እንዳይኖር ማድረግ ተገቢ ነው። ፖለቲካ ፓርቲዎች ተደራጅተው መጥተው እኛ የፈለግነውን መሆን አለበት ቢሉ አይ አይሆንም፣ ተጠሪነታችን ለሕዝባችን ነው። ስለዚህ እናንተ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማድረስ ትችላላችሁ፤ ይህም ማለት በምክክር መሳተፍና ተሳታፊዎቻችሁን በትክክል ለተሳትፎ እንዲመጡ ማስቻል ነው። የየራሳቸው ባለድርሻ አካል ተሳትፎ እንዲኖር ማድረግ ይችላሉ፤ ኢትዮጵያ የሁላችንም እኩል ትሁን ከተባለ፣ ሁላችንም እኩል እንጠቀምባት ከተባለ፣ ለአንዱ እናት ለሌላው የሩቅ ዘመድ መሆን የለባትም ካልን መንግሥት፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሕዝብና የአገር ደህንነትን የሚጠብቁ አካላት፣ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳቶች፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች እኩል የምክክር ባለድርሻዎች መሆን አለባቸው ብለን እየሰራን ነው። በምክክሩ የተወሰኑ አካላት ተፅዕኖ እንዳይኖር መጠበቅ ይገባል። ነጋሪ፦ ከቅድመ ዝግጅት ስራዎች በኋላ ወደ ተሳታፊ ልየታ ነው የገባችሁትና
ሀሰን አልበሽር ነበሩ። ስለዚህ እሳቸው የምክክር ሂደቱን መጠምዘዝ ፈለጉ፤ ምክክሩ እሳቸውንም በአጀንዳ ውስጥ የሚመለከት ስለነበር ሂደቱ ፈረሰ። በአገራዊ ምክክር ኮሎምቢያም ስኬታማ በመሆን ጥሩ ተምሣሌት ነች፤ የአገሪቱ መንግሥት ለምክክሩ ጥሩ ፍላጎትና ቁርጠኝነት በማሳየቱ ለዘመናት ጫካ ገብተው ሲጫረሱና ሲያጫርሱ የነበሩ የፋርክ ኃይሎች መሳሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ምክክር መጥተዋል። ብዙ ጉዳት አድርሰው ስለነበር የምክክር ሂደቱ የራሱ ሕመም ነበረው፤ ከምክክር በፊት የሽግግር ፍትሕ ያስፈልጋል እና ከጨረሱን ሰዎች ጋር እንዴት አብረን እንመካከራለን የሚሉ ሃሳቦች ነበሩ፤ ነገር ግን ጠንካራ ውስጣዊ አዎንታዊ ተፅዕኖ ስለነበር ውጤታማ ምክክር አድርገዋል። ከአፍጋኒስታን እስከ ዛምቢያ ድረስ የተካሄዱ በርካታ ምክክሮችን ተሞክሮ በመዳሰስ ስኬታማ የሆኑና ያልሆኑትን በመለየት ለአገር የሚጠቅሙትን ቀምረናል። ዋናው ነገር በምክክር ሂደቱ አሉታዊ የሆነ ውጫዊም ሆነ
ውስጣዊ ተፅዕኖ እንዳይኖር ማድረግ ነው። ነጋሪ፦ ውስጣዊ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይኖር ማድረግ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው? ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፦ ውስጣዊ አሉታዊ ተፅዕኖ ስንል መንግሥት ወይም ሌላ የውስጥ ኃይል በምክክር ሂደት በአሉታዊ መንገድ ጣልቃ ገብቶ እጅ እንዳይጠመዝዝ ማድረግ ነው። መንግሥት ለአገራዊ ምክክሩ ተነሳሽነት በመውሰድ ኮሚሽኑን አቋቁሟል፤ ምክክሩ የሚመራበትን አዋጅ አስጸድቋል፤ በዚህም እናመሰግናለን። ተጠሪነታችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ በጣም ጥሩ ነው። በየጊዜው ሪፖርት እናደርጋለን፤ በተለይ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በየጊዜው ሥራችንን ያያል፤ በቅርቡም የመስክ ምልከታ አድርጓል። ይህም ተገቢ ነው። ነገር ግን እዚህ ቦታ ስራ፣ ይህንን አስወጣ የሚል መብት የለውም። ስለዚህ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይኖር በሚገባ መጠበቅ ይኖርብናል። በሌላ በኩል ከፖለቲካ
እስካሁን ምን ሰራችሁ? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ከማዕከላዊ ስታትስቲክስና ከካርታ ስራዎች ድርጅት ያለን መረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ 1 ሺህ 400 ወረዳዎች እንዳሉ ነው። ይህን መሰረት አድርገን እያንዳንዱን ወረዳ ለመድረስ ሰባት ተባባሪ አካላትን ለየን። እነሱም የሃይማኖት ተቋማት፣ የመምህራንና የሲቪክ ማኅበራት፣ ዕድሮች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የወረዳ አስተዳደሮችና የወረዳ ዳኛ ናቸው። ከእነዚህ አካላት ጋር መስራት የሚያስችለንን መግባባትና ስምምነት ፈጥረን ወደ ስራ ገብተናል። በምክክር ፅንሰ ሀሳብና በአሠራሩ ላይ በቂ ስልጠና ተሰጥቷቸውና ተመዝነው ወደየመጡበት ወረዳዎች ተመልሰው ተሳታፊዎችን በተሰጣቸው ቀመር መሰረት የመለየት ስራ እያከናወኑ ነው። በወረዳ ደረጃ የተሳታፊ ብዛት ዘጠኝ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያካትታል። ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ራሳቸውን የሚገልጹበት መተዳደሪያ ያላቸው (አርብቶ እና አርሶ አደሮች) የንግድ ማኅበረሰብ፣ የመንግሥት/የግል ሠራተኞች፣ የማኅበረሰብ መሪዎች፣ መምህራን፣ በባሕልና በሙያቸው የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ተፈናቃዮች ካሉም ያካትታል። ተባባሪ አካላት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ በመሆናቸው የተሳታፊዎችን አካታችነት ለማረጋገጥ አመቺ ነው። በዚህ ስራ ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች በስተቀር ሁሉም ክልሎች እና የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች አስተዳደሮች በሙሉ ተሳታፊዎቻቸውን አስለይተዋል። በወረዳ ደረጃ ተሳታፊዎችን ለይተናል፣ ክልል ላይ አጀንዳ የሚሰጡ ሰዎች ተለይተዋል። በእርግጥ ስራው የደረሰበት ደረጃ ከክልል ክልል የተለያየ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ የአሰልጣኞች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፤ የተባባሪዎች ስልጠናም በአዳማ እና በጅማ ከተሞች ተሰጥቷል። በኦሮሚያ ክልል ዞኖች የተሳታፊዎች ልዩታ እየተከናወነ ነው በቅርቡ ይጠናቀቃል ። ስለዚህ ሁሉም ዞኖች ተሳታፊ ሆነዋል። ስልጠና የወሰዱ ተባባሪዎቻችን በቀጣይ የሚያከናውኑት በየወረዳዎች ተሳታፊዎቻቸውን የመለየትና የማስመረጥ ስራ ነው። በወረዳ ደረጃ 90 ተሳታፊዎች ይለያሉ፤ 90ዎቹ ተሰባስበው ወደ ክልል የሚሄዱ ሁለት ሁለት ሰዎችን ይመርጣሉ፤ ስለዚህ በአንድ ወረዳ ከ18 እስከ 20 ሰው ይመረጣል ማለት ነው። እነዚህ ከየወረዳው የተመረጡት ሰዎች ክልል ላይ ተገናኝተው አጀንዳቸውን ያሰባስባሉ። በሶማሌ ክልል የተባባሪዎች ስልጠና ተሰጥቶ
የተሳታፊዎች ልየታ በመከናወን ላይ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ቀጣይ ስራ እንገባለን። የተሳታፊዎችን ልየታ የምንጀምረው ተባባሪዎችን በሶማልኛ ቋንቋ አሰልጥነን ነው። አሰልጣኝ የምናሰለጥነው ደግሞ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ለይተን ወስደን ነው። የምክክር ፅንሰ ሀሳብን በአግባቡ ለማስረፅ የየአካባቢውን ቋንቋ በመጠቀም ለማሰልጠን ጥረት እያደረግን ነው። በአማራ ክልል ወረዳዎች በሚገባ ተለይተው የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፤ ነገር ግን የተባባሪዎች ስልጠና ወደፊት የምናየው ይሆናል። ትግራይ ክልል ወረዳዎችን ገና አልለየንም፤ ነገር ግን ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ተነጋግረናል። በቀጣይ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ተባባሪ አካላትን ለማግኘትና ሌሎች ስራዎችን ለመስራት ወደ ክልሉ እናቀናለን። ነጋሪ፦ ስለ አገራዊ ምክክሩ ለኅብረተሰቡ ምን ያህል ግንዛቤ ተፈጥሯል? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ከአገራችን ሕዝብ ስለ ምክክሩ ምንነትና አስፈላጊነት የማያውቅ የለም ማለት አይቻልም። ሕዝቡን ማስገንዘብ ላይ ጠንክረን አልሰራንም። ተደራሽነታችን ከዚህም በላይ መስፋት አለበት። ተደራሽነታችን የሚሰፋው ሁላችንም አጀንዳ ስናደርገው ነው። ክልሎች፣ ዞኖች፣ ወረዳዎች ምክክሩን ልክ እንደ አረንጓዴ አሻራ ብሔራዊ አጀንዳ አድርገው መስራት አለባቸው፤ ከአረንጓዴ ልማት እኩል ሰላም ያስፈልግናል፤ አገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያዊያን ለአንድንታችን እና ለቀጣይነታችን በጣም ወሳኝ ነው። ጠንካራ ሆነን ሕዝባችንን በስኬት ከፍ ማድረግ አለብን ከተባለ ሰላም ያስፈልጋል፤ ለዚህ ደግሞ ወሳኝ ሆኖ ያገኘነው አማራጭ አገራዊ ምክክር ነው። ስለዚህ ይህን ለመስራት ሀሳቡን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ይግባል። ለዚህ ደግሞ ኃላፊነቱ የሁላችንም ነው። የፌዴራልና የክልል መንግሥታት፣ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችም በየችሎታቸው በየቋንቋው ስለ አገራዊ ምክክር ምንነት፣ ሂደትና አስፈላጊነት ሕዝቡን ማስገንዘብ አለባቸው። ነጋሪ፦ ቀደም ብለው የተሳታፊዎች ልየታ በአብዛኛዎቹ ክልሎች መካሄዱን ጠቅሰዋል፤ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ስላለው የምክክር ዝግጅት ቢያብራሩልን? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ተስፋ የምናደርገው አማራ ክልል ሰላም ቢሆንልን እና ትግራይ
ክልል ሙሉ ፈቃዱን ሰጥቶን በክልሎቹ ወደ ስራ እንድንገባ ነው። ዋናው ስራችን አገራዊ ምክክር ማካሄድ ነው። አገራዊ እስከሆነ ድረስ፣ አማራን፣ ትግራይን ወይም ምዕራብ ኦሮሚያን ትተን ማካሄድ አንችልም፤ ለዚህ የሚያግዙን፣ መንግሥት፣ ሕዝቡና ሌሎችም ተዋናዮች ናቸው። መንግሥት ወላጅ ስለሆነ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡ አካላት አጀንዳ ኖሯቸው ስለሚሆን ወደዚያ የገቡት ትጥቃቸውን አስቀምጠው አጀንዳቸውን ይዘው ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ለማድረግ እጁን ዘርግቶ የሰላም ጥሪ በማድረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት። በሚፈጠሩ ግጭቶች መከራውን እያየ ያለው ሕዝብ ነው፤ ምክንያቱም የሰላም መጥፋት መጀመሪያ የሚጎዳው ሴቶችን፣ እናቶችን እና አቅመ ደካሞችን ነው፤ ስለዚህ ሕዝቡም ተነሳሽነቱን ማሳየት አለበት። ታጣቂዎችም በትግል ሂደት የሚደርሰው ጉዳት፣ የምናጣቸው ወጣቶች፣ በሰሜኑ ጦርነት የደረሰው ውድመት ሰፊ ነው። የእነዚያን ወጣቶች ሕይወት የምንመልሰው እንዴት ነው፤ ግጭቱ የሚያልፈው ርዝራዥ ጠባሳ ጥሎ ነው፤ በአማራም፣ በኦሮሚያም ነፍጥ ያነገቡ ኃይሎች ነፍጥ አውርደው ለዚህ ያነሳሳቸውን አጀንዳ ይዘው ወደ ምክክሩ መምጣት አለባቸው። ነጋሪ፦ ዋናውን የአገራዊ ምክክር ጉባዔ መቼ ነው የምታካሂዱት? ፕሮፌሰር መስፍን፦ በዚህ ጊዜ ነው የምናደርገው አልልም፤ እየሰራን እንቀጥላለን፤ ጊዜው ሲደርስ ዋናውን አገራዊ የምክክር ጉባዔ እናካሂዳለን። በምክክሩ ከወረዳ እስከ ፌዴራል የሚመጡ ተሳታፊዎች እና በውጭ አገራት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ይሳተፋሉ። ነጋሪ፦ በአገር ደረጃ በሚካሄደው ዋናው ምክክር ምን ያህል ሰዎች ይሳተፋሉ? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ቁጥሩን መወሰን ያለበት 11ዱም ኮሚሽነሮች ያሉበት ምክር ቤት ነው። ምን ያህል ቢሆን ይሻላል የሚለውን እናያለን፤ ለምሣሌ ሦስት ሺህ ቢሆን ያዋጣል ወይ የሚለውን እንቃኛለን። ምክክር ያካሄዱ አገራት በአማካይ ከ250 እስከ አንድ ሺህ ሰዎችን አሳትፈዋል። የእኛ አገር ሕዝብ ቁጥር ደግሞ በጣም ብዙ ነው፤ ስለዚህ ምን ያህል ተሳታፊ ብናደርግ ነው የሚሻለው የሚለውን እያየነው ነው። ምክክር የተወሰኑ ልሂቃንና ፖለቲከኞች ወይም የመንግሥት ኃላፊዎች ንግግር አድርገው በጭብጨባ የሚጠናቀቅ አይደለም። ምክክር መግባባት ነው። መግባባት እስኪደረስ ሰዓታት፣ ቀናት፣ ሣምንታት፣ ወራት፣ ዓመታት ሊወስድ
አሳታፊ ማድረግ ስላለብን ነው። ስለዚህ አሁን በግጭት ውስጥ ያሉ አካባቢዎችንም መጠበቅ አለብን። ሕዝቡ ለሁሉም የሚያዋጣው ምክክር ብቻ ነው እያለ ስራችንን እያበረታታ ነው። ነጋሪ፦ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ምን ዝግጅት አድርጋችኋል? ፕሮፌሰር መስፍን፦ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን እያሳተፍን ነው። እስካሁንም አራት ስብሰባዎችን አካሂደን በአውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአፍሪካ፣ በፓስፊክ፣ በእስያ እና በአሜሪካ አካባቢዎች ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በበይነ መረብ ተወያይተናል። የተሰጡን ግብረ መልሶች የሚያበረታቱ ናቸው፤ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮችን ፈትተናል፤ ስለ አገራዊ ምክክሩ ተዓማኒነትና ገለልተኝነት በአግባቡ እንዲረዱ አድርገናል። በውጭ ለሚኖረው ማኅበረሰብ መግለፅ የምፈልገው ኩርፊያም ብስጭትም ቢኖር ችግሩን ለመፍታት በግልፅ መነጋገርና መመካከር ነው። ነጋሪ፦ የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለዎት? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ስራችን ብዙ ነው፤ ሕዝባችን ከእኛ ብዙ ይጠብቃል፤ እኛም ከሕዝባችን ብዙ እንጠብቃለን፤ ከመንግሥት ብዙ እንጠብቃለን፤ በግጭት ውስጥ ያሉ ወደ ሰላም መጥተው ችግሮች በሰላማዊ መንገድ በምክክር እንዲፈቱ የድርሻቸውን እንዲወጡ ብዙ እንጠብቃለን፤ አገራችን ወደፊት እንድትራመድ የሚያዋጣን ይህ አገራዊ ምክክር ነው። በችግሮች ዙሪያ ቁጭ ብሎ በግልፅ መነጋገርና መግባባት እንጂ በራስ አቅጣጫ ብቻ መጓዝ አይጠቅመንም። ውብ የሆኑ ባሕሎች፣ ቋንቋዎች፣ ትውፊቶች፣ ሃይማኖት አሉን። ብዙ እርስ በእርስ አስተሳስረው የሚያጋምዱን ዘመን ተሻጋሪ ዕሴቶች አሉን። በመሆኑም ችግሮችን በጋራ ፈትተን ለመሻገር ወደ ልቦናችን ተመልሰን፣ በግልፅ እንመካከር፤ የፈረንጆቹ 2024 ወይም የራሳችን 2016 ቢያንስ የመጀመሪያውን አገራዊ ምክክር የምናደርግበት ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ለስኬቱም ፈጣሪ ይርዳን። ነጋሪ፦ በዝግጅት ክፍሉ ስም ለጊዜዎ በጣም እናመሰግናለን! ፕሮፌሰር መስፍን፦ እኔም አመሰግናለሁ!
ይችላል። አንዳንዶች ወደሚቀጥለው ትውልድ ሊተላለፉ ሁሉ ይችላሉ፤ አንዳንዶቹ የሕዝብ ውሳኔ ሊደረግባቸው ይችላሉ፤ አንዳንዶቹ በሕገ መንግሥት ታቅፈው ሊታዩ ይችላሉ፤ በዚህ ሂደት አወያዮች ይመረጣሉ፤ ይሰለጥናሉ፤ ምሁራን ተገቢውን ግንዛቤ ይሰጣሉ። ምክክር ክርክር በእጅ ብልጫ የሚወሰን አይደለም፤ ከየአካባቢው ወስኖ መጥቶ ይህ ካልሆነ ይፍረስ የሚባልበትም አይደለም፤ ወደ ምክክር ሲመጣ ሀሳብ ሊቀየር፣ ሊዳብር፣ ሊወሰድ ይችላል፤ ጥሩ ተናጋሪም ጥሩ አድማጭም መሆንን ይፈልጋል፤ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራን ነው ያለነው፤ ስራው በጣም አድካሚና እልህ አስጨራሽ ነው። ስለዚህ በዋናው በምክክር ጉባዔው የሚሳተፉትን ብዛት በሂደት እንወስናለን። ነጋሪ፦ ቀደም ሲል በምክክር ኮሚሽኑና በአገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ቅሬታ የነበራቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ነበሩ፤ ለመሆኑ ምን ያህል የፖለቲካ ፓርቲዎች ከእናንተ ጋር እየሰሩ ነው? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ከእኛ ውጭ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀስ በቀስ እየመጡ ነው። በቅርቡ ከአንድ ከሦስቱ ጋር የስምምነት ማዕቀፍ ተፈራርመናል። የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር እና የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ከእኛ ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል። ሶማሌዎች በጣም እየረዱን ነው። ከአፋር ሕዝቦች ፓርቲ ጋርም ተቀራርበን እየሰራን ነው። ወደ እኛ ያልመጡት ጥቂት ናቸው፤ ለምሣሌ ኦነግ፣ ኦፌኮ፣ ወላይታም ውስጥ አንድ ፓርቲ አልመጡም። ያልመጡት እንዲመጡ ጥሪ እያደረግን ነው። መንግሥትም በሰላም እንዲመጡ እገዛ ማድረግ አለበት። አንዳንዶች በፖለቲካዬ ምክንያት አባሌ እየታሰረ ነው የሚሉ ጥያቄዎችን ይዘው ይመጣሉ። አገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን በፖለቲካ ምክንያት በማረሚያ ቤት ካሉ ቢለቀቁና ጥያቄዎቻቸውን ይዘው ወደ ምክክሩ መጥተው መግባባት ላይ ቢደረስ ጥሩ ነው። ለመንግሥትም በየጊዜው ምክረ ሃሳብ እየሰጠን ነው። በመሆኑም ሁሉም ፓርቲዎች አጀንዳዎቻቸውን አቅርበው በሚገባ ምክክር ቢደረግባቸው የተሻለ ነው ብዬ ነው የማስበው። ነጋሪ፦ አገራዊ ምክክሩ የሚደረግባቸውን አጀንዳዎች የመለየት ሥራስ በምን ሂደት ላይ ነው? ፕሮፌሰር መስፍን፦ አጀንዳ የመሰብሰብ ስራ በቅርቡ እንጀምራለን፤ በአጀንዳ ስብሰባው ሂደት በዋናው አገራዊ የምክክር ጉባዔ የሚሳተፉትን በየክልሉ በሚሰጣቸው ቀመር መሰረት
እንዲመርጡ እናደርጋለን፤ ሁለት ስራ ሰርተን ነው የምንመጣው፤ አጀንዳ እንሰበስባለን፤ ለአገራዊ ምክክሩ የሚሆኑትን ተሳታፊዎቸ እንመርጣለን፤ የተሰበሰቡትን አጀንዳዎች እዚህ አምጥተን እንለያለን። አጀንዳዎቹን ስንለይ ብቻችንን አይደለም፤ አማካሪዎቻችን እና ሌሎች ታዛቢዎች ባሉበት ነው። አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራውን ከአዲስ አበባም መጀመር እንችላለን፤ በእርግጥ አዲስ አበባ በጣም ሰፊ ነው፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ድሬዳዋና ሐረሪ በአንድ ላይ መሰብሰብ እንችላለን። አጀንዳ ስብስባው በቅርቡ ይጀመራል። ነጋሪ፦ በእስካሁን ሂደት ምን ችግር አጋጠማችሁ፤ የተባባሪዎችስ ድጋፍ ምን ይመስላል? ፕሮፌሰር መስፍን፦ ስነ-ዘዴያችንን በየጊዜው እየፈተሽን እናስተካክላለን፤ ስንጀምር የወረዳ ተሳታፊዎች ቁጥር በጣም ሰፊ ነበር፤ የሄድነው ድሬዳዋ፣ ሐረርና ሲዳማ ነው፤ ተሳታፊው ብዙ ስለሆነ ክፍያ ላይ በጣም ፈታኝ ጊዜ ነበር። ለምሣሌ አምስት ወረዳ ቢሳተፍ የሚመጣው ተሳታፊ 2 ሺህ 250 ሰው ነው። ለዚህ ሁሉ ተሳታፊ ምግብ ማቅረብ፣ አዳራሽ አዘጋጅቶ የቀን አበል መክፈል ለእኛ የቀን ቅዠት ነበር። ክፍያውን ወዲያው መክፈል አለብህ፤ አብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች የባንክ ቁጥር የላቸውም፤ የአጎታቸውን የአክስታቸውን ይሰጣሉ፤ ያ ደግሞ ከባንክ ጋር ሲመሳከር ወራትን ይፈጃል፤ በተለይ ሲዳማ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር እንዲህ ዓይነት ችግሮች ገጥመውናል። ጀማሪዎች ስለነበርን በክልሎች ለተፈጠረው መስተጓጎል በኮሚሽኑ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ። አሁን ስነ-ዘዴያችንን አስተካክለናል፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የደህንነት ተቋማት፣ የክልል አስተዳዳሪዎች በሙሉ እየተባበሩን ነው። መጀመሪያ ሲያጋጥሙን የነበሩ ችግሮችን ፈትተናል። ነጋሪ፦ በየአካባቢው ስትሄዱ ሕዝቡ ለኮሚሽኑና ለአገራዊ ምክክሩ ያለው ዕይታ ምን ይመስላል? ፕሮፌሰር መስፍን፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምን ይፈልጋል። በአገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች ስንሄድ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ወዘተ. . . ሁሉም የሚጠይቀው ሰላምን ነው። ሕዝቡ በሄድንበት ሁሉ የሚነግረን አገራዊ ምክክሩ ይፋጠን የሚል ግፊት ነው። እኛ በሕዝቡ ፍላጎት ልክ ያልፈጠንነው ምክክሩን ሁሉንም አካታች እና
ስብራቱን ለማከም . . .
ማህበራዊ
በአንዱንሰው ሺፈራው ትምህርት በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት አንድ ብሎ የጀመረው እ.አ.አ 1908 በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዓላማው የምዕራባዊያንን ሐሳቦች እና ዘመናዊነትን የመማር ፍላጎት፤ የመንግሥት ባንክ ምስረታ፤ የድልድይ፣ የሆስፒታሎች፣ የሆቴሎችና የባቡር ሀዲድ ግንባታዎች፤ የፖስታ አገልግሎት፣ የስልክ እና የመሳሰሉ ፈጠራዎች አስፈላጊነት በመታመኑ ትምህርትን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ትምህርት ቤት ነው። በዚያን ጊዜ የተጀመረው ዘመናዊ ትምህርት ዘመናትን ተሻግሮ ዛሬ ላይ ደርሷል።
የትምህርት ፋይዳ
ትምህርት ለሰው ልጆች ኑሮ ቅልጥፍና፣ ለአገራት ዕድገትና ልማት፣ ባሕልንና ዕውቀትን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር ዋነኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። የዓለም የነፃነት ታጋይ ተምሣሌቱ የመጀመሪያው ጥቁር የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ በአንድ ወቅት
ስለትምህርት ሲናገሩ፣ “ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ ልትጠቀምበት የምትችለው በጣም ኃይለኛ መሣሪያ ነው” ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ (Universtiy of South Africa) መግቢያ በር ላይ በጉልህ የተፃፈው የኔልሰን ማንዴላ መልዕክት የትምህርትን ፋይዳ በጉልህ የሚያሳይ ነው። “ማንኛውንም አገር ለማፍረስ የአቶሚክ ቦምብ አልያም የረጅም ርቀት ሚሳኢሎችን መጠቀም አይጠይቅም። የትምህርት ጥራትን ዝቅ ማድረግ እና በተማሪዎች ፈተና ወቅት ኩረጃን መፍቀድ ብቻ በቂ ነው” ይላል። ይህ ከሆነ ህሙማን ታካሚዎች እንደዚህ ባሉ ዶክተሮች እጅ ይሞታሉ፤ ለሌሎች የሕክምና ስህተቶች ጭምር ይዳረጋሉ። በእንደዚህ ዓይነት መሐንዲሶች እጅ የተገነቡ ሕንፃዎች ተደርምሰው የበርካቶችን ሕይወት ይቀጥፋሉ፤ አካል ያጎድላሉ፤ ንብረት ያወድማሉ። በእንደዚህ ያሉ ኢኮኖሚስቶች እና የሂሳብ ባለሙያዎች እጅ ገንዘብ ይጠፋል። የሰው ልጅ በእንደዚህ ዓይነት የሃይማኖት ሊቃውንት እጅ መንፈሳዊ ሕይወቱ ይታወካል። ፍትሕ እንደዚህ ባሉ ዳኞች እጅ ትዛባለች. . . በጥቅሉ የትምህርት ውድቀት የአገር ውድቀት ነው። ስለሆነም የትምህርትን ጥራት ማስጠበቅ
በምንም መልኩ ሊሸራረፍ የማይገባው የነገዋ የተሻለች ኢትዮጵያ መሰረት የሚጣልበት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው።
በአገራችንም ትምህርት የዕድገት ሁሉ መሰረት ነው፤ የችግሮች ሁሉ መፍቻ ዋነኛ ቁልፍ ነው በሚል ለዓመታት ሲነገር ቆይቷል። የተማሩ ዜጎች በራሳቸው የሚተማመኑ፣ ብቁና በምክንያታዊ ትንተና የሚያምኑ፣ በሙያቸው ብቃት ያላቸው፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ አዳዲስ ግኝቶች አፍላቂዎች፣ ጠንካራ የሥነ ምግባር እና ግብረገባዊ እሴቶችን የተላበሱ፣ ለሕግ ዘብ የቆሙ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋ ሆነው ራሳቸውን ብሎም ቤተሰባቸውን እና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ይሆናሉ። ለመሆኑ የሀገራችን የትምህርት ጥራት አሁናዊ ደረጃ ምን ላይ ነው፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ብሎም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ምን እየተሰራ ነው? የሚለውን በዚህ ፅሁፍ ለመፈተሸ ወደድን።
በአገራችን እውን የትምህርት ጥራት ቀንሷል?
የኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት የት ደርሷል ያልን እንደሆነ ጥራቱ እየቀነሰ፣ የተማሪዎች ውጤት እያሽቆለቆለ ስለመምጣቱ ማሳያዎች እየተጠቀሱ መነገር ከጀመሩ ሰንበትበት ብሏል። በገሃድ እየታየ ያለውም ሃቅ የሚያሳየውም ይህንኑ ነው።
የትምህርት ሥርዓቱ በንድፈ ሀሳብ እንጂ በተግባር፣ በክህሎትና በፈጠራ ላይ ያተኮረ አለመሆኑ፤ የምዘና ሥርዓቱ ዕውቀትን ብቻ የሚመዝን መሆኑ ከትምህርት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ናቸው። በሂደትም ፈተናን በራስ አቅም ከመስራት ይልቅ ስርቆትና ኩረጃ እያደገ ስለመምጣቱ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ተፈሪ ንጉሤ እውን የትምህርት ጥራት ቀንሷል? ለሚለው ጥያቄ፤ አዎ የትምህርት ጥራት ቀንሷል ይላሉ፤ ለምላሻቸው አመላካቾች መኖራቸውንም ይጠቅሳሉ። “የትምህርት ጥራት አንዱና ዋነኛ ማሳያ የማንበብና የማስላት ብቃት አንዱ ውጤት ነው። ሁለተኛው የተማሪ ባህሪይ
የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ተፈሪ ንጉሤ፤
ነው። ነገር ግን አሁን አሁን በአንዳንድ ተማሪዎች ዘንድ የሚስተዋለው የትምርት ፍላጎት እየቀነሰ መምጣቱ ነው።
የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የፊዚክስ መምህር ደረጀ ኃ/ማርያም በእርግጥም የትምህርት ጥራት በየጊዜው እየቀነሰ መምጣት ችግር በጥናት መደገፍ እንዳለበት ቢያምኑም፤ ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ ስለመሆኑ በብዙዎች ዘንድ የሚነገረውን እውነታ እሳቸውም ይጋሩታል። “ከተማሪ ብንነሳ ተማሪው ለመማር ያለው ፍላጎት አነስተኛ ነው፤ አብዛኛው ተማሪ ለመማር በቂ ፍላጎት የለውም። ክፍል ውስጥ ስትገባ ደብተር፣ እስክሪቢቶ፣ የተሰጠውን የመማሪያ መሣሪያ አሟልቶ ይዞ የሚገባው ጥቂት ነው። ስንጠይቃቸው የተለያየ ምክንያት ነው የሚያነሱት። ተምረን የት እንደርሳለን፤ ከእኛ በፊት የተማሩት ወንድም እህቶቻችን በጣም ጎበዝ የነበሩት 12ኛ ክፍል ሲደርሱ እኛው ጋር ነው ያሉት ይላሉ፤ ጥቂቶች ካልሆኑ በስተቀር ይህን ነው የሚሉት”። ሲሉ ያስረዳሉ። የአንዳንድ ተማሪዎች ፍላጎት መቀነሱን ተከትሎ የመጨረሻ ግባቸው 12ኛን ጨርሶ ወደ ስራ ፈጠራ ስለመግባት እንደሆነ የሚያነሱት የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ኤፍሬም፤ ስራን መፍጠር የሚበረታታና ተፈላጊ መሆኑን፤ ነገር ግን ለዚህም ቢሆን ትምህርትን አጠንክሮ መያዝ ለቀጣይ ሕይወት ወሳኝ ስለመሆኑ ነው
የገለፁት። “የትምህርት ዋና ግቡ አዳዲስ ሀሳብ ማፍለቅን መጨመር ነው” ይላሉ።
ሰው ሲማር እይታው ይሰፋል። መፍትሔ ለማምጣት ራሱ አቅም ይኖረዋል። ለጊዜው ገንዘብ ሊያስገኝ ይችላል፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት ከዘመኑ ጋር ተፎካካሪ አያደርግም። ምክንያቱም የሸመቷት እውቀት ትንሽ ስለሆነች፣ ለተወሰነ ጊዜ ነው የምታኖረው” በማለት ትምህርት በመጪው ዘመን ለሚኖር ዓለምአቀፍ ተፎካካሪነት የላቀ ሚና እንዳለው አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህር አቶ ተፈሪ ንጉሤ በበኩላቸው ተማሪው ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በየደረጃው እየበቃ ካልመጣ፣ ሁለተኛ ደረጃ ሲደርስ የትምህርቱ ይዘት የታጨቀ ነው የሚሆነው። ከታችኛው ደረጃ ማንበብ፣ መሰረታዊ ስሌቶችን ማስላት ሳይችል ሁለተኛ ደረጃ የመጣ ተማሪ ለተስፋ መቁረጥ እና ለጭንቀት ይዳረጋል። የሁለተኛ ደረጃ መጽሐፍቶች በጊዜ ተገድበው የመጡና ሰፊ ይዘት ያላቸው ናቸው። በሌላ መልኩ ደግሞ ተማሪው ካላነበበ እና ካልፃፈ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ለመቀጠል ይቸገራል። ስለዚህ እንዲሁ ለማሟያ ብቻ፣ ወይም ወላጅ ስለሚያስገድደው፣ አልምያ 12ኛ ክፍልን ለመጨረስ ያክል ብቻ ነው ወደ ት/ቤት የሚመጣው። ይህንን ከመሰረቱ ካልሰራንበት እዚህ በምናደርገው የጥገና ሂደት ለውጥ ይመጣል ብዬ አላምን ይላሉ።
የኢኮኖሚ ችግር
ትምህርት በርካታ ግብዓቶችን የሚፈልግ፣ የዓመታት ወጥነት ያለው ስራን የሚሻ፣ በእጅጉ አድካሚ ነገር ግን ፍሬው እጅግ ጣፋጭ ነው። ወላጆች ባለባቸው ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት ለትምህርት የሚያስፈልጋቸው ግብዓት ሳይሟሉላቸው ወደ ት/ቤት የሚመጡ ተማሪዎች አሉ። ይህ በተማሪዎች የትምህርት አቀባበል ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል። መምህር ደረጀ ኃ/ማርያም የተማሪዎች ኢኮኖሚያዊ ችግር ሌላው የትምህርት ጥራት መጓደል መንስኤ ስለመሆኑ ያነሳሉ። እርሳቸው በሚያስተምሩበት ዳግማዊ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ሳይሟሉላቸው ለትምህርት የሚመጡ ተማሪዎች መኖራቸውን፤ ቤተሰቦቻቸው ድሆች በመሆናቸው ቁርስ ሳያገኙ እስከ 8ኛው ክፍለ ጊዜ ድረስ ለመቆየት እንደሚገደዱ ገልጸዋል።
የሚለካበት የመጨረሻ ውጤት ነው፤ ከእነዚህ አንፃር እውነትም የትምህርት ጥራቱ ወድቋል የሚያስብሉ አመላካቾች አሉ። በእኛ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በአግባቡ የማይፅፍ፣ መሰረታዊ ስሌቶችን የማያሰላ ተማሪ ቁጥሩ በርካታ ነው። ይሄ አንዱ አመላካች ነው” ሲሉ የትምህርት ጥራት ስለመቀነሱ ማሳያዎች ያሏቸውን ይጠቅሳሉ።
አቶ ተፈሪ አክለውም ለትምህርት ጥራት መቀነስ ምክንያቶች ናቸው ያሏቸው ደግሞ የማስተማሪያ ግብዓት በወቅቱ አለመሟላት እና ጭራሽ አለማግኘት፣ የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በሚገባ አለመወጣት እንዲሁም ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው ፍላጎት እየቀነሰ መሄድ፣ የመምህራን ተነሳሽነት መቀነስ፣ የወላጅ ክትትል ማነስ፣ የትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ አለመሆን መሆናቸውን አስረድተዋል።
የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ኤፍሬም አይተንፍሱ በበኩላቸው የትምህርት ጥራት ቀንሷል የሚለውን ሃሳብ ይጋራሉ። ለዚህም በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን በማሳያነት ያነሳሉ። አያይዘውም ተማሪዎች ፈተናውን የወደቁት ብቃት በሌለው መምህር ስለተማሩ፤ ለትምህርቱ መሳካት በቤተ ሙከራ የተደገፈ ትምህርት አለመሰጠቱን፤ የመማሪያ መጽሐፍት በወቅቱ አለመድረሳቸውን፣ ምቹ የትምህርት ቤት ከባቢ አለመፈጠሩን፤ ተማሪዎች በተለያዩ አዋኪ ነገሮች እየተሳቡ መሆኑን፣ ት/ቤትም ውጭም ያለው ማኅበረሰብ ለስብዕና ግንባታቸው የሚያደርገው አስተዋፅኦ አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ጥራት እንዲቀንስ፣ የተማሪዎች ውጤትም እንዲያሽቆለቁል ማድረጉን ያብራራሉ። በተጨማሪም ተማሪዎች ከታችኛው ደረጃ ጀምሮ በሚፈለገው ልክ ብቁ ሆነው ወደ ሁለተኛ ደረጃ ባለመላካቸው በውጤታማነታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማድረሱን አስረድተዋል።
የትምህርት ጥራት በየጊዜው እየቀነሰ ነው የሚሉት ደግሞ ለ18 ዓመታት በመምህርነት ያገለገሉት የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር ደረጃ ኃይለማርያም ናቸው። ለትምህርት ጥራት መቀነስ ምክንያቶች ናቸው ያሏቸውን የተማሪዎች ለትምህርት ያላቸው ተነሳሽነት መውረድ፣ የቤተሰብ ልጆቹን አለመከታተል፣ ከኢኮኖሚያዊ ችግር ጋር ተያይዞ ምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ሳይሟሉላቸው ወደ ት/ቤት የሚመጡ ተማሪዎች መኖር፣ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በአደንዛዥ ዕፅ ሱስ የተያዙ
መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በእርግጥም በሀገሪቷ እየተስተዋለ ስላለው የትምህርት ጥራት መውረድ የሚስማሙት የዘርፉ ባለሙያዎች የተለያዩ ምክንያቶችን ያንሱ እንጂ፤ ከምክንያቶቹ መካከል የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት በየጊዜው እየቀነሰ መምጣት በብዙዎች የሚጠቀስ ነው። በዚህ ጽሁፍ እየተስተዋለ ላለው የትምህርት ጥራት መቀነስ ምክንያቶችን፣ መፍትሔዎችና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ይዳሰሳሉ።
የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት
ተማሪዎች ትምህርት በመጀመሪያ ራሳቸውን፣ ቀጥሎም ቤተሰብን እና ሀገርን እንደሚለውጥ አምነው በንቃት መማር እንዳለባቸው እሙን
በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት አሁን የተማሪዎች ምገባ መኖሩ ችግሩን ቀለል እንዳደረገውና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አለመኖሩ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ሌላው እንቅፋት እንደሆነ ነው የገለፁት።
የመምህር ደረጀን ሃሳብ የሚጋሩት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተፈሪ በበኩላቸው በት/ ቤቱ ወላጅ የሌላቸው ወይንም ደግሞ በአንድ ወላጅ ብቻ የሚያድጉ፤ ከአያት፣ ከአክስት ጋር የሚያድጉ በርካታ ተማሪዎች እንደሚገኙና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ መሆን በአንድም በሌላም መልኩ የትምህርት ጥራት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ነው ያነሱት።
የተማሪዎች ምገባ
ምግብ ሳይመገብ ወደ ትምህርት ቤት የሚመጣ ተማሪ እንደምን ትምህርቱን ሊከታተል ይችላል? ጊዜ የማይሰጠውን ረሀብን ከማዳመጥ በዘለለ እንደምን የመምህሩን ገለፃ በትኩረት ሊያዳምጥ ይቻለዋል? ይህን ችግር በሚገባ የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃግብር በተለይ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም ተማሪዎች ቁርስ እና ምሳ እየተመገቡ ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እያደረገ ነው። ነገር ግን በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በምገባ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ የነበሩ
ተማሪዎች ወደ ሁለተኛ ደረጃ ሲሸጋገሩ የምገባ ፕሮግራሙ ይቋረጣል፤ ይህን ተከትሎም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች እየተራቡ ለመማር ይገደዳሉ። ለመሆኑ ይህ ችግር ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለፃል?
በወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ያለውን ሁኔታ ርዕሰ መምህሩ አቶ ኤፍሬም ሲገልፁ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተለመደው ምገባ፤ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ባለመኖሩ አንዳንድ ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸውን ላለማስቸገር የጉልበት ስራ ለመስራት ይገደዳሉ። ይህን ደግሞ የሚያከናውኑት ከትምህርት ሰዓታቸው ቀንሰው ጭምር ስለሆነ ሲረፍድባቸው ይስተዋላል። የተማሪዎች ምገባ ተግባራዊ ቢሆን መጠነ ማርፈድንና ማቋረጥን፤ በጥቅሉ የትምህርት ጥራት መጓደል የሚያመጡ ችግሮችን ይሰበስባቸዋል ይላሉ። “የሰው ልጅ ትምህርት ቤት ሄጄ ምን እበላለሁ፣ ትምህርት ቤት ሄጄ የት አድራለሁ። እነዚህ የሰውን ልጅ ዝቅ ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ናቸው። እየራበው ማዳመጥ፣ መፃፍ፣ እንዲሁም ከሰው መቀላቀል አይችልም። ጠዋት ከሚኒባስ ላይ እቃ አውርጄ ነው ወደዚህ የምመጣው። ቤተሰቤን የማግዘው በዚህ ሁኔታ ነው ይልሀል። እነዚህ በተማሪዎቻችን ላይ የከፋ ተጽዕኖ ያሳድራሉ” ነው ያሉት።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተማሪዎች ምገባን አስመልክቶ ለቀረበላቸው
ጥያቄ ሲመልሱ፤ ለተማሪዎች ምገባ የሚበጀት በጀት አለመኖሩን ነው የገለፁት። ”እኛ እንደ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን መመገቢያ በጀት የለንም። ከድጋፍ ሰጪ የውጭ ድርጅት እየጠበቅን አንድ ነገር እናሳካለን የምንለው ጊዜያዊ ነገር ያደርግ ይሆናል፤ ነገር ግን በዘላቂነት መፍትሔ መፈለግ ያለብን ራሳችን ነን። ሁልጊዜ የውጭ እርጥባን እየጠበቅን መኖር ቢሳካ እንኳን ውጤቱ ጥሩ አይሆንም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ እንዳሉት “አዲሱን ትምህርት ቤዝ ዲዛይን ስናደርግ እያንዳንዱ ት/ቤት ቢያንስ አንድ ሄክታር መሬት ሊኖረው ይገባል ብለናል። አሁን የምንሰራቸው ት/ ቤቶች በሙሉ በትንሹ አንድ ሄክታር መሬት፣ አንዳንዶቹ ከዚያም በላይ መሬት ግቢ ውስጥ ይተዋሉ። የምናስበው ለምግብ ጥቅም ላይ የሚውሉ ተክሎችን እንዲዘሩ ነው። አቮካዶ፣ ቲማቲም፣ ጎመን እነዚህን ነገሮች በአንድ በኩል
ትምህርት ይማሩባቸዋል እርሻ ምን እንደሆነ፤ ኮምፕርሄንሲቭ የሆነ ዕውቀት እንዲኖራቸው፤ ሁለተኛ ያንን ለት/ቤቱ ተማሪዎች ለመመገብ ይጠቀሙበታል። አዲሱ ሞዴል ትምህርት እርሻ ብቻ ሳይሆን ትንሽ የከብት ማርቢያ ጉሮኖ ነገር አለው፤ ዶሮ ለማርባትም እንዲሁ። ት/ቤቶችን በተቻለ መጠን ከውጭ እጅ ማውጣት፤ ዘንድሮ አሁን መሀል ሴሚስተር ላይ ብዙ ዕርዳታ ሰጪ የሚባሉት ገንዘብ የለንም በጀታችን አልቋል አሉ፤ ሁሉም ሊያቆም ነበር፤ እንደዛ መሆን የለበትም። እኛ በተቻለ መጠን በራሳችን ጥረት እነኚህን ነገሮች ማሳካት አለብን ብዬ ነው የማስበው። ወደዛ ነው እየሄድን ያለነው። አነስተኛም ቢሆን እርሻ እንዲጀምሩ፣ በአካባቢያቸው የወተት ላም፣ ዶሮ አርብተው እንቁላል ቢያገኙ የበለጠ ይሳካል። ዘላቂነት ያለውም ይሄ ነው” ሲሉ ማኅበረሰቡ ራሱን የሚችልበት መንገድ መከተል እንደሚገባ በማስገንዘብ ችግሩን በዘላቂነት በራስ አቅም ለመፍታት እየተደረገ ስለሚገኘው እንቅስቃሴ አስረድተዋል።
የተማሪዎች ምገባ ጅማሮ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች
በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያለው ምገባ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እየተተገበረ አይደለም። በዚህም የተነሳ በምገባ ታግዘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ በከፍተኛ ድህነት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እየተቸገሩ ስለመሆናቸው ያነጋገርናቸው መምህራንም ሆነ ተማሪዎች የገለጹት ሀቅ ነው።
ታዲያ በእነዚህ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ያሉ መምህራን በከፍተኛ ችግሮች ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን ስር የሰደደ ችግር አይተው ዝም አላሉም። ከመምህራን አቅም በፈቀደ ገንዘብ በማሰባሰብ ችግሩ ባስ ላለባቸው ጥቂት ተማሪዎች የምገባ መርሀ-ግብር ጀመሩ እንጂ። በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሆነውም ይኸው ነው። የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር 2ሺህ 251 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ባለው ት/ቤት፣ ያለማጋነን 50 በመቶው ምገባ እንደሚፈልግ ነው የሚናገሩት።
ርዕሰ መምህሩ ሲገልፁ ”የኢኮኖሚ ችግሩ የከፋባቸውን አንደኛ በጎ አድራጎት ክበብ አለ። ክበቡ ከመምህራን፣ ከሰራተኞች፣ በቋሚነት መዋጮ ሰብስቦ እዚሁ ሻይ ክበብ ይመግባቸዋል፣ በሻይ ሰዓት። እሱ ብቻ አይደለም፣ ቁጥራቸው ከፍተኛ ስለሆነ እንደ ትምህርት ቤት፣ አሁን ላይ ከ250 ተማሪ በላይ የከፋ ችግር ውስጥ ያሉ ከዚህ ከምገባ ጋር ተያይዞ ተለይተው፣ በአቅራቢያችን ከሚገኘው ዳግማዊ ምኒልክ አንደኛ ደረጃ ት/ ቤት ጋር ተነጋግረን ክፍለ ከተማውም አግዞን እዚያ ምሳ ሰዓት ላይ ወጥተው ይመገባሉ። ይሄ እንደ ትምህርት ቤት አንድ መፍትሔ ነው። የወሰድነው በጣም የባሰባቸውን ነው። እነዚህ የተለዩ ተማሪዎች 200 ቁርስ እና ምሳ በቋሚነት ይመገባሉ። በአጠቃላይ ከምንመግባቸው ጋር 250 ተማሪዎች መካከል 50ዎቹ ት/ቤቱ ውስጥ 200ዎቹ ውጭ ወጥተው በቋሚነት ይመገባሉ።
በወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ ት/ቤትም እንቅስሴዎች ስለመኖራቸው ነው የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር የገለፁት። በጣም ችግር ላለባቸው ልጆች ተብሎ ሆፕ ፎር ወርልድ የሚባል አንድ ሀገር በቀል ድርጅት 25 ልጆችን ከኢትዮጵያ ትቅደም ት/ቤት ጋር በማስተሳሰር የቁርስ እና ምሳ ድጋፍ ለማድረግ መጥተው መልምላ
ስለመደረጉ ነው ያነሱት። መሰል ጥረቶች ያለ ምግብ ወደ ት/ቤት ለሚመጡ ተማሪዎች ተስፋ ሰጪ፣ ረሃባቸውን ከማዳመጥ ወጥተው ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ጋን በጠጠር ይደገፋል እንደሚባለው አቅሙ ያላቸው የተለያዩ ባለሀብቶችም እነዚህን የነገ አገር ተረካቢዎች በብቃት የማስተማር ቅዱስ ተግባርን መደገፍ ላይ ሊረባረቡ ይገባል።
መምህር እና የትምህርት ጥራት
መምህርነት መሀይምነትን አርቆ ባለምጡቅ አዕምሮ፣ በአስተሳሰብ የበለፀገ ዜጋ የሚቀርፅ ሙያ ነው። መምህር የተለያየ ሐይማኖት፣ ባሕል፣ ወግ፣ ልማድ፣ እምነት እና የፖለቲካ ልዩነት ያላቸውን ተማሪዎች ያለምንም አድልዎ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመላበስ እኩል የሆነ ትምህርት የሚሰጥ ነው። እንደ ሻማ እየቀለጠ ለሌሎች የሚያበራ፣ የሰውን ልጅ አዕምሮ የሚገነባ ሀገር እና ዜጋ ወዳድ ነው። ለመሆኑ ይህ ሙያተኛ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን በተደጋጋሚ በሚነሳው የትምህርት ጥራት መጓደል ላይ ሚናው ምን ያህል ነው፤ ያሉበት ችግሮች ምንድን ናቸው ስንል ላነሳነው ጥያቄ ምላሽ አግኝተናል።
የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህሩ ደረጀ ኃ/ማርያም መምህራን ሙሉ ጊዜያቸውን ለስራቸው እንዳይሰጡ እንቅፋት ያሉትን ሲገልጹ “መማር ማስተማሩ ውጤታማ እንዲሆን መምህራን በተለይ በኑሯቸው፤ አብዛኛውን ደመወዛቸው ለቤት ኪራይ ነው። ልብስ ቀይሮ መምጣት አሁን ላይ ችግር ሆኗል። ይሄ በራሱ ተጽዕኖ አለው። በኑሮ ውድነቱ መኖር እየተቻለ አይደለም፤ ደመወዙ ባለበት ነው ያለው። የመግዛት አቅም የለውም። አቅም በፈቀደ በየጊዜው ቢታይ የተሻለ ይሆን ነበር” ነው ያሉት።
የወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዝኛ መምህር ሙሉጌታ ታደሰ ለትምህርት ጥራት መቀነስ የመምህራንም ድርሻ ስለመኖሩ ነው የሚያነሱት። “የመምህራን በቂ ዝግጅት ያለማድረግ፤ ተማሪዎች ደንበኞች ናቸው፣ ካንተ ቢያንሱም በሀሳብም በስሜትም ተዘጋጅተህ የሚጠበቅብህን ማቅረብ ነው። ያንን የሚያደርጉ ብዙ አይደሉም። መምህሩ ያንን እንዳያደርግ የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ። መምህሩ የኑሮውን ሁኔታ፣ የመኖሪያ ቤት
ችግሩን የመሳሰሉትን የግል ሕይወቱን ሲያስብ የተማሪዎቹን ጉዳይ እየዘነጋው ይመጣል” በማለት የመምህሩ ኢኮኖሚያዊ ችግር የፈጠረውን ተጽዕኖ ያስረዳሉ።
ለትምህርት ጥራት የመምህራን ብቃት እና ተነሳሽነት ወሳኝ ስለመሆኑ የሚናገሩት የዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተፈሪ ንጉሤ ዛሬ መምህር እየሆኑ ያሉት ባለፉት 30 ዓመታት በነበረ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተምረው ያለፉ መሆናቸው በራሱ የፈጠረው በከፍተኛ ደረጃ የሚገለጽ ክፍተት አለ ይላሉ። ክፍተቱ ከብቃት ማነስ የሚመነጭ እንደሆነም ይገልጻሉ። የመምህሩ ደመወዝ እና የኑሮ ሁኔታ አለመስተካከሉ ለስራው ያለውን ተነሳሽነት እንደሚቀንስ፤ ይህ ተደማምሮ የትምህርት ጥራት ላይ በተዘዋዋሪም በቀጥታም ችግሩን እያባባሰው መሆኑን ነው የገለፁት።
ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንን አቅም ለማጎልበት ሥልጠና ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ፤ የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የራሱን ሚና እንደሚወጣ የታመነበት ሥልጠና በዚሁ በመገባደድ ላይ ባለው የትምህርት ዘመን እንደሚሰጥ ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ስለዚሁ ጉዳይ ሲያብራሩ በሲቪል ሰርቪስ አሰራር ደመወዝ ለማግኘት የሚጠየቀውን የትምህርት ዝግጅት ደረጃ ሰርተፊኬት፣ ዲፕሎማ፣ ዲግሪ… ለማሟላት እንጂ መምህራን በሚያስተምሩት ትምህርት አይነት ብቃት እንዲኖራቸው የሚያደርግ የሥልጠና አግባብ እንኳን አለመኖሩን ገልጸዋል። ይህን ሁኔታ ለመቀየር መምህራንን ለሚያስተምሩት የትምህርት አይነት የትምህርት ሥርዓት መዘጋጀቱን፤ የመጀመሪያው ሥልጠናም በዚህ ዓመት መጨረሻ ለመምህራን መስጠት እንደሚጀመር አስረድተዋል።
ሥልጠናው ርዕሳነ መምህራንንም እንደሚያካትት የገለጹት ሚኒስትሩ የት/ ቤቶችን አስተዳደር የማሻሻል ሪፎርም በ2015 ዓ.ም መጀመሩንና 4ሺህ ርዕሳነ መምህራን መሠልጠናቸውን አስታውሰው፤ በቀጣይ የርዕሰ መምህራን ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ይቋቋማል ነው ያሉት።
የትምህርት ጥራት እና ግብዓት
አዲሱ ሥርዓት ትምህርት ወደ ትግበራ የገባው በ2015 ዓ.ም ቢሆንም በትምህርት ዘመኑ የመማሪያ መጽሐፍት በአብዛኛው ተደራሽ የሆኑት በሶፍት ኮፒ ነው። የመማሪያ መጽሐፍት ታትመው ለተማሪዎች እየደረሰ ያለው ዘግይቶ በመሆኑ ተማሪዎች የክፍል ውስጥ እና የቤት ስራዎቻቸውን ለመስራት እና ለማንበብ ተቸግረዋል።
መምህር ደረጀ ኃ/ማርያም ከመማሪያ መጽሐፍትና ሌሎች የትምህርት ግብዓቶች አቅርቦት ጋር በተያያዘ እየገጠማቸው ያለውን ችግር ያነሳሉ ”መጽሐፍት ተሟልተው በጊዜ አይቀርቡም። ብዙ ግዜ ሶፍት ኮፒዎች ናቸው። መጽሐፍ ታትሞ የመጣው በቅርቡ ነው፤ እሱም የሚሰጠው አንድ መጽሐፍ ለሦስት እና ለአራት ተማሪ ነው። ቤተ-ሙከራዎችም የመማር ማስተማር ስራውን የሚያግዙ የተሟላ ግብዓት የላቸውም። የግብዓቶች በሚፈለገው መጠን ተሟልተው አለመገኘት በመማር ማስተማሩ ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው“ ይላሉ።
ከመማሪያ መጽሐፍት ሕትመት ጋር በተያያዘ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የመማሪ መጽሐፍትን ማሳተም የክልሎች ድርሻ መሆኑንና የሁለተኛ ደረጃን ደግሞ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነት እነደሆነ ተቀምጧል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመጽሐፍት አቅርቦት ጋር በተያያዘ እንደ ሀገር ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ሚኒስቴሩ ትርጉም ያለው ስራ መስራቱን ገልጸው፤ 120 ሚሊዮን ሕዝብ ባለባት ሀገር በኢንዱስትሪ ደረጃ መሰራት ያለበት የመጽሐፍት ሕትመት አለመኖሩንም ያነሳሉ። መጽሐፍ በፈለግን ቁጥር ሕንድ፣ ዱባይ እየሄድን እያሳተምን እስከ መቼ ነው የምንዘልቀው በሚል ኢንዱስትሪያል ፕሪንቲንግ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቋቋም ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን፤ በዚህ ዓመት አስቸኳይ ስለነበር ውጭ ባሉ ኩባንያዎቻቸው በፍጥነት አትመው ማድረሳቸውን፤ በቀጣይ ግን ኮንስትራክሽን ጀምረው ፋብሪካውን በሀገር ውስጥ እንደሚተክሉና የመጽሐፍት ሕትመት ስራውን እንደሚያከናውኑ አብራርተዋል።
“ከዚህ በኋላ የመጽሐፍት ሕትመት ችግር ይጠፋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በሕትመት ዘርፉ በኢንዱስትሪ ደረጃ የሚሰሩ የውጭ አገር ባለሃብቶች መጋበዛቸው ተጨማሪ ዕድል ይዞ መምጣቱንም
ይገልጻሉ። ቀደም ሲል 40 ሚሊዮን መጽሐፍት ለማሳተም በወጣው ጨረታ ከተወዳደሩ የሀገር ውስጥ አታሚዎች በተገኘው ዝቅተኛው ወደ 29 ቢሊዮን ብር መጠየቁንና ይኸው ሕትመት በውጭ አታሚዎች ዋጋው ወደ ሰባት ቢሊዮን ብር መውረዱን ጠቅሰው፤ የኢንዱስትሪው መምጣትና በጥራት እዚህ ማተም መቻል ከመማሪያ መጽሐፍት በተጨማሪ ሌሎችም መጽሐፍቶች በጥሩ ዋጋ የሚታተሙበት ዕድል ይዞልን ይመጣል። ከዚህ ባሻገርም ሥርዓተ ትምህርት በየአምስትና በየሰባት ዓመት ልንቀይር እንችላለን፤ ከሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ለሚኖረውም የመጽሐፍት ሕትመት አስተዋጽኦ እንደሚኖረም ይገልጻሉ።
የትምህርት ቤቶች ርቀት
አንዳንድ ት/ቤቶች ከተማሪዎች የመኖሪያ አካባቢ በእጅጉ የራቁ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። የትራንስፖርት ችግር ስላለ ለረጅም ጊዜ ሰልፍ ጠብቀው፣ ትምህርት ቤት የሚመጡ ተማሪዎች አሉ። ችግሩ ባስ ሲል ታዲያ ማርፈድ እና ከትምህርት ገበታ ለመቅረት የሚገደዱ ተማሪዎች ቁጥር ቀላል አይደለም። የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ኤፍሬም አይተንፍሱ አንዳንድ ተማሪዎች ራቅ ካሉ አካባቢዎች ለአብነት ከሱሉልታ የሚመጡ መኖራቸውን ገልፀው፤ እነዚህ ተማሪዎች የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት ላይ እንደማይገኙ አንስተዋል። ሌሎችም በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት ዘመኑ ሳይጠናቀቅ የመኖሪያ አካባቢ የሚቀይሩ ተማሪዎች የዚህ ችግር ተጎጂዎች መሆናቸውን በመጥቀስ የትምህርት ቤት ለተማሪዎች መራቅ ለትምህርት ጥራት መጓደል አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዳለውም ይገልጻሉ።
የርዕሰ መምህር ኤፍሬምን አስተያየት የሚጋሩት አቶ ተፈሪ ንጉሴም በተለይ ጠዋት ላይ በትራንስፖርት ችግር እና በመንገዶች መዘጋጋት ምክንያት ከሩቅ አካባቢዎች የሚመጡ ተማሪዎች ረፍዶባቸው አብዛኛውን ጊዜ የመጀመሪያው የትምህርት ክፍለ ጊዜ እንደሚያመልጣቸው ገልጸው፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥት ተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን መክፈት እንደሚኖርበት ምክረ-ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።
በየጊዜው እየጨመረ ከመጣው የከተማ ነዋሪ ቁጥር አንፃር ተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/
ቤቶችን በጥራት መገንባት የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ የራሱ ሚና ስለሚኖረው በጥናት ላይ ተመስርቶ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ዕቅድ ቢሰራበት ሲሉም አክለዋል።
የመምህራን ዝግጁነት
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከሚረዱ ነገሮች አንዱ የመምህራን የትምህርት ዝግጅት ነው። በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከሚገኙ መምህራን 45 በመቶ ሁለተኛ ዲግሪ፤ 55 በመቶ የመጀመሪ ዲግሪ እንዳላቸው ከት/ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ከወ/ሮ ቀለምወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን መካከል 60 በመቶ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆኑ፤ የቀሩት ደግሞ የመጀመሪ ዲግሪ ያላቸው ናቸው።
በሁለቱም ት/ቤቶች መምህራኑ ተከታታይ የሙያ ላይ ሥልጠና፣ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና (ሲ.ፒ.ዲ) በቋሚነት ይሰጣቸዋል። ነገር ግን አንዳንድ መምህራን የሚሰጣቸው ሥልጠና ሙያቸውን አንደሚያሻሽል ያላቸው እምነት ዝቅተኛ እንደሆነ ነው ርዕሳነ መምህራኑ የሚገልፁት። ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናን በሙሉ ተነሳሽነት፣ ሙያውን ለማሳደግ፤ በሂደት ደግሞ የተማሪዎችን ውጤት እና መልካም ባህሪይ ለመቅረፅ እንደሚያግዝ በማመን የሚሰራበት አግባብ ውስንነት እንደሚስተዋልበትም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ባለድርሻ አካላት በሥልጠናው አስፈላጊነት ላይ የጋራ አቋም በመያዝ የመማር ማስተማር ስራውን ሊጠቅም በሚችል አግባብ መስራትን የቤት ስራ ሊያደርጉት ይገባል።
ምቹ የት/ቤት ከባቢ
ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩን ስራ ከሚያውኩ ነገሮች መጠበቅ ይኖርባቸዋል። በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ተማሪዎችን ከትምህርታቸው የሚያዘናጉና ወዳልተፈለገ መስመር የሚመሩ ሁኔታዎች ላይ ፈጣን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ነው። በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች የውስጥ ግቢ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ ቤተ-ሙከራ እና ሌሎችም ክፍሎች ምቹነት መረጋገጥ አለበት።
በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ በቀዳሚነት የሚነሳው የዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ
ደረጃ ት/ቤት በርካታ የሰው ኃይል አፍርቶ ለሀገር አበርክቷል። ት/ቤቱ የዕድሜውን ያህል ባይሆንም ግብዓት ለማሟላት የተደረገውን ጥረት ያህል ውስንነቶችም ስለመኖራቸው ነው የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር የሚገልጹት። የተደራጀ ቤተ-መጽሐፍት ያለው ሲሆን ቅጥር ግቢውን ለማስተካከል ተሞክሯል፤ ነገር ግን ከሚጎድሉ ነገሮች አንዱ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ /አይ.ሲ.ቲ/ አለመደራጀት፣ በቂ ኮምፒውተሮች አለመኖር፣ ያሉትም የማይሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎችን ምቹ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል። የክፍል-ተማሪ ጥምርታ አንድ ለ40 አይሞላም። ነገር ግን ከቤተ-መጽሐፍት ጋር በተያያዘ ት/ቤቱ ያለበት ችግር ዓመታትን የተሻገረና ምንም እልባት ያልተሰጠው ስለመሆኑ ርዕሰ መምህሩ ይናራሉ። የቤተ-መጽሐፍቱ ሕንፃ የአሰራር ችግር ያለበት፣ በውስጡ ተቀምጦ ለማንበብ የማይጋብዝ፣ ጣራው እያፈሰሰ መጽሐፍትን ከጥቅም ውጭ እያደረገ ያለ መሆኑንም እንዲሁ።
የዚሁ ትምህርት ቤት መምህር ሙሉጌታ ታደሰ የቤተ-መጽሐፍቱን ችግር የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ክፍለ ከተማው ጭምር የሚያቁት ቢሆንም በዚህ ዓመት ይስተካከላል
እየተባለ ብዙ ትውልድ ቤተ-መጽሐፍቱን ሳይጠቀምበት ት/ቤቱን ለቀው እንደሚሄዱ በመጥቀስ የችግሩን አሳሳቢነት በአጽንኦት ይገልጻሉ።
በትምህርት ቤቱ ለትምህርት ጥራት እገዛ የሚያደርጉት የአይ.ሲ.ቲ ክፍሎች በብቃት የተደራጁ አይደሉም፤ ቀደም ሲል አንድ ኮምፒውተር ለ15/20 ተማሪ ይደርስ ነበር፤ አሁን የተማሪ ቁጥር በመጨመሩ ወደ 30 ከፍ ብሏል። በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎች መልቲሚዲያ ይማራሉ። ኮምፒውተሮቹ ሶፍትዌር ለመጫን አቅም ስለሌላቸው አንዳንድ የትምህርት ክፍሎችን በተግባር ሳያዩ ያልፋሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሩ ስራ ምን ያህል ምቹ ናቸው? ሲል ባካሄደው ጥናት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የሚጠበቅባቸውን ያሟሉ ትምህርት ቤቶች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት የመንግሥት የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአራት ደረጃዎች ተመዝነው መስፈርቱን ሙሉ በሙሉ ያሟሉ በሚለው አራተኛ ደረጃ የተገኙት ስድስት ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው። በመቶኛ ሲሰላ 0 ነጥብ 02 ከመቶ ማለት ነው። በዚህ ደረጃ በሚገኝ ትምህርት ቤት የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የሚደረገው ሙከራ እንቅፋት
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ይገጥመዋል።
ይህን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር አንድ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ጀምሮ ወደ ተግባር መግባቱ ይታወቃል። መንግሥት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ሊያድስ ስለማይችል የኅብረተሰቡን አቅም በማሰባሰብ ት/ቤቶቹን ለማሻሻል የቀድሞ ተማሪዎችን፣ የአካባቢ ተወላጆችን፣ ከአገር ውጪም በአገር ውስጥም ያሉትን ወላጆች ጭምር እንዲሰሩት ተደረገ፤ ለዚህም በሀገሪቷ የሚገኙ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ምን እንደሚመስሉ የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል በማዘጋጀትና ስራውንም በአምስት ዓመት ለማጠናቀቅ ዘመቻው ተጀመረ። ይሁንና ዘመቻው በተጀመረ በሰባት ወራት ውስጥ 11 ሺህ 611 ትምህርት ቤቶች እድሳት ተደርጎላቸዋል በታቀደው መሰረት አሁን ያሉትን 50 ሺህ ገደማ ትምህርት ቤቶች በአምስት ዓመት ውስጥ ማሻሻልና ዕቅዱን ማሳካት እንችላለን፤ በዚህም የትምህርት ጥራትን ካበላሹብን ችግሮች አንዱን እናቃልላለን ብለዋል የትምህርት ሚኒስትሩ።
እሳቸው እንዳሉት የትምህርት ቤቶችን ገፅታ ለመቀየር የተሰራው ስራ ነባር ትምህርት ቤቶችን በማደስ ብቻ የተገታ አይደለም። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በነዋሪዎች አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን እና መማሪያ ክፍሎችን እስከ መገንባት የደረሰ ተሳትፎ ተድርጓል። በትምህርት ለትውልድ እቅስቃሴ 4 ሺህ 871 ት/ ቤቶች ተገንብተዋል። ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 180 ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ 1 ሺህ 390 አንደኛ ደረጃ 295 የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሕዝቡ መዋጮና ትብብር ተሰርተዋል።
በእርግጥም ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራው ምቹ እንዲሆኑ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ለዚህም ባለድርሻ አካላት ከአንድ ወቅት የዘመቻ ስራ ወጥተው ወጥነት ባለው መልኩ በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል። ይህ ሲሆን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እንቅፋት የሆነው ደረጃ በደረጃ እየተቃለለ መወገዱ የማይቀር ነው።
ኩረጃ
ኩረጃ የተማሪዎችን የማንበብ፣ የማገናዘብ እና በራስ መተማመንን ያሳጣል። በኩረጃ ከክፍል ወደ ክፍል ሲዘዋወር የመጣ ተማሪ በምንም መስፈርት በራስ መተማመን አይኖረውም።
በራሱ የማይተማመን ዜጋ ለራሱም ሆነ ለሀገር የሚጠቅም አይሆንም። የወ/ሮ ቀለመወርቅ ጥሩነህ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የኩረጃን አስከፊነት ሲገልፁ ”በኩረጃ የመጣ ሐኪም ይገድላል እንጂ አያድንም፤ በኩረጃ የመጣ ዳኛ ፍርድ ያዛባል፣ እንጂ ፍትሕ አያፀናም። በኩረጃ በማንኛውም የስራ መዋቅር ላይ የመጣ የሚሰራው ከተቀመጠበት የስራ ደረጃ በታች ነው። ውጤታማ አይደለም፤ ተገልጋዩንም አያረካም። ሁልጊዜ ቅሬታ ይመጣበታል። መንገድ ቢሰራ በአጭር ጊዜ የሚፈርስ ነው። መሰረተ ልማቱ የሕዝብን እርካታ አያሟላም።
ኩረጃ የትምህርት ጥራት ካንሰር ነው። በኩረጃ ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለመደ ተማሪ ራሱን ችሎ፣ መጽሐፍትን አንብቦ በሙሉ የራስ መተማመን የመስራት ልምዱ ዝቅተኛ ነው። በዚህም ሀገር ተረካቢ ዜጎች ብቃት የሌላቸው ይሆናሉ። በዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት የኩረጃን አስነዋሪነት በተማሪዎች ዘንድ ለማስረፅ አነቃቂ ንግግሮች እንደሚደረጉ፤ በሚኒሚዲያ ትምህርት እንደሚሰጥ እና የምክር አገልግሎትም መኖሩን ርዕሰ መምህሩ አቶ ተፈሪ ይናገራሉ። በትምህርት ቤቱ ሲኮርጅ የተገኘ ተማሪ እርምጃ የሚወሰድበት ሕግና ሥርዓትም ተበጅቷል።
ሱሰኝነት
ወጣትነት አዲስ ነገርን ለመሞከር መጓጓት የሚስተዋልበት ዕድሜ ነው። ጠቃሚ ወይንም በተቃራኒው የማይጠቅሙ ነገሮች ሊሞከሩ ይችላሉ። ይህ ሁኔታ በተለይ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ከዚያ በላይ ባሉ ተማሪዎች ዘንድ ይስተዋላል።
ችግሩ እንደ አገር በትኩረት እየተሰራበት ላለው የትምህርት ጥራትን የማሻሻል እንቅስቃሴ ትልቅ እንቅፋት ነው። ሲጀመር በተማሪ ደረጃ የሱስ ወጪን ማሟላት ለተማሪ ከባድ እንደሚሆን መገመት አይከብድም። ሱስን ለማሟላት ካልተቻለ ደግሞ ወደ ዘረፋ እና ወንጀል ወደመፈፀም ማምራት መከተሉ አይቀርም። የተማሪው የትምህርት አቀባበል ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖም ከባድ ነው። በሌሎች ተማሪዎች ላይ የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽዕኖ ሲታሰብ አጠቃላይ የመማር ማስተማሩን ስራ ከድጡ ወደማጡ እንደሚያደርገው እርግጥ ነው። በሱስ ውስጥ የተዘፈቁ ተማሪዎችን ይዞ የትምህርት ጥራትን ማሳካት የማይታሰብ ነው።
ስለሆነም ችግሩን ለማስወገድ ወጥነት ባለው አግባብ በቅንጅት መስራት ከትምህርት ቤቶች ማኅበረሰብ፣ ከወላጆች፣ ከፀጥታ አካላትና ከሚመለከታቸው ሁሉ የሚጠበቅ ቀዳሚ የቤት ስራ መሆን አለበት።
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት
አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በ2014 ዓ.ም ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በሙከራ ደረጃ ተጀምሮ በ2015 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱ ይታወቃል። በተመሳሳይ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ሥርዓተ ትምህርቱ በ2015 ዓ.ም በሙከራ ደረጃ፤ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ ገብቷል።
ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በተዘጋጁት አዳዲስ መጽሐፍት ውስጥ ያሉት እሴቶች አጓጊ እና ደስ የሚያሰኙ ስለመሆነቸው የሚናገሩት አቶ ተፈሪ ንጉሴ ይዘቱ ያስቀመጠው እሴት፣ ካለብን ችግርና ዓለም ከደረሰችበት ሁኔታ ችግር ፈቺ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ሲሉ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል።
ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የሚያያዝ ቴክኖሎጂ ያስፈልጋል የሚሉት አቶ ተፈሪ ከ90ዎቹ ጀምሮ ስኩል ኔት የሚባል ነገር ቢሰማም ተቋም ላይ ግን አለመኖሩን ያነሳሉ። ተቋሞቻችን በስኩል ኔት ተሳስረውና ዘምነው በዚያ ልክ ትምህርት እንዲሰጡ መንግሥት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሥርዓተ ትምህርቱን ተቀባይነት ባለው መንገድ በማዘጋጀት በኩል ምንም ችግር አለማጋጠሙን፤ ነገር ግን የሙከራ ትግበራ በሚደረግበት ጊዜ ያለቀው ወደ ሰኔ አካባቢ ስለነበር በመስከረም ለማዘጋጀት፣ ከዚያም በኋላ መጽሐፍትን ለማሳተም ጊዜ መውሰዱን ነው የገለፁት። በመምህራን ደረጃ አንዳንድ አዳዲስ ቦታዎችና አዳዲስ ትምህርቶች እጥረት በመኖሩ ሙሉ ለሙሉ ሊሰጡ የታሰቡ ትምህርቶች አሁን ላይ እየተሰጡ እንዳልሆነ ቀደም ብሎ ታውቆ የተገባበት መሆኑን አስረድተዋል።
የሰላም እጦት
የትምህርት ስራ ያለ ሰላም ከቶውንም የማይታሰብ ነው። የጥይት ድምፅ በሚሰማበት አካባቢ ሕፃናት አልያም ታዳጊዎች ተረጋግተው
ትምህርታቸውን ሊማሩ አይችሉም። በሀገራችን የተለያዩ ክልሎች ባለው የፀጥታ ችግር የመማር ማስተማር ስራው እንቅፋት ገጥሞት ነው ያለው። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ”በፊት ኦሮሚያ ውስጥ በተለይ ወለጋ ግጭት የነበረባቸው ቦታዎች ላይ የጎላ ተጽዕኖ ነበረው። አሁን እሱ እየተሻለ የሚመስልበት ሁኔታ አለ። አሁን አማራ ክልል ደግሞ ቁጥሩ በፊት ከነበረው የጨመረበት ሁኔታ አለ። ግጭት ሁልጊዜ የትምህርት ፀር ነው።
በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ባለፉት አምስት ዓመታት ያጋጠሙ ግጭቶች መሰረተ ልማት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያችን ብዙ ነገር አስከፍለውናል። እንዱ እየከፈልንበት ያለነው በትምህርት ዘርፍ ያለው ነው። የፖለቲካ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ሙከራ ተደርጎ ልጆቻችን ቢያንስ በትምህርት ገበታቸው ላይ የሚገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት የጋራ ኃላፊነት ነው። የወላጅ ኃላፊነት ነው። ግጭት ውስጥ የገቡትም የሚያስቡትን ለማግኘት ልጆቻችን እንዳይማሩ እንቅፋት በመፍጠር መሆን የለበትም” ብለዋል።
የባለድርሻ አካላት ሚና
የትምህርት ስራ የበርካቶችን ተሳትፎ የሚጠይቅ፣ ውጤቱን ለማየት ዓመታትን መጠበቅ የሚያስፈልገው ነው። ሀገር በትምህርት በበቁና ምክንያታዊ በሆኑ ትውልዶች ቅብብሎሽ መቀጠል እንድትችል ሁሉም ለትምህርት ጥራት በጋራ መረባረብ ይኖርበታል።
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ከታች ጀምሮ መስራት ሊተኮርበት ይገባል። ብዙ ተማሪዎችን ካላሳለፍኩ እገመገማለሁ በሚል ተለምዷዊና ትውልድ ገዳይ በሆነ አሰራር ያልበቁ ተማሪዎችን ወደ ቀጣይ ክፍል ማሻገር የትምህርት ጥራትን በእጅጉ የሚጎዳ ነው። ማንበብ፣ መፃፍ፣ መሰረታዊ የሂሳብ ስሌቶችን ማስላት የማይችልን ተማሪ ከክፍል ወደ ክፍል ማሳለፍ መቆም አለበት። ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የትምህርት ስራውን በቅርብ የሚቆጣጠሩ አካላትም ይህን በቅርብና ወጥነት ባለው መልኩ መከታተል አለባቸው።
ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራው ምቹና፣ ተማሪዎች የሚወዱት እንዲሆን ለማድረግ በትምህርት ሚኒስቴር አነሳሽነት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
ትምህርት ቤቶች ያሉባቸውን የግብዓቶች እጥረት ለማሟላት በበለጠ ተግቶ መስራት የግድ ይላል። እንደ ሀገር ካሉት ትምህርት ቤቶች ስንቶቹ ቤተ-መጽሐፍት አላቸው። ቤተ-መጽሐፍቶቹ ምን ያህል በቂ መጽሐፍት የተሟላላቸው ናቸው፣ ሕንፃው፣ ተማሪዎች ተቀምጠው የሚያነቡባቸው ወንበርና ጠረጴዛዎች ምን ያህል ምቹ ናቸው፣ ምን ያህል ዲጂታላይዝድ ሆነዋል የሚሉት ሁሉ ላይ መስራት ይገባል።
የአይ.ሲ.ቲ ክፍሎችን በአግባቡ ማደራጀት ያስፈልጋል። በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ ከሚመጣው የተማሪ ቁጥር ጋር የኮምፒውተሮችም ቁጥር መጨመር ይኖርበታል። ዘመኑን የዋጃቸው ፈጣን ኮምፒውተሮችም አቅም በፈቀደ ለትምህርት ቤቶች ለማሟላት መስራት ያስፈልጋል። ለዚህም መንግሥት የየትምህርት ቤቶቹን ወላጆች እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማሳተፍ ተነሳሽነቱን ሊወስድና በትምህርት ጥራት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጣ ስራ ሊሰራ ይገባል።
የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ የመምህራንን የኑሮ ደረጃ መቀየር ላይ ሊሰራበት ይገባል። በኑሮ ውድነት ሳቢያ ከወር ወር ለመድረስ የሚቸገር መምህር ይዞ ስለትምህርት ጥራት ስኬት ማውራት ያስቸግራል። በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው እውነታም የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ሰፊ ሰዓታትን ለትምህርት ስራ መስጠትን ለሚጠይቀው የትምህርት ስራ ስኬት የመምህራን ገቢ ቢያንስ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል። የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች የሚያገኙበት አግባብም መመቻቸት እንዲሁ። ይህ ሲሆን የትምህርት ጥራት የሚያስጨንቀው እና ሰፊውን ጊዜውን ለትምህርት ስራ የሚሰጥ፣ በሙሉ ተነሳሽነት የሚስራ መምህር ይኖራል። ይህ ሲሆን ትልቅ ፈተና የሆነብንን የትምህርት ጥራት ችግር ለመፍታት የሚደረገው ጥረት እንዲሳካ ትልቁን ስራ እንደመስራት ይቆጠራል፤ ምክንያቱም ዋናው የዘርፉ ሞተር መምህሩ ነውና።
ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት አቀባበል በቅርብ መከታተል እና ከትምህርት ቤቶች ጋር ተናበው በጋራ መስራት አለባቸው። የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ምሁራን፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ ታዋቂ ሰዎች ልምዶቻቸውን ሊያካፍሉ ይገባል። የነገዋን
ኢትዮጵያ ተረካቢዎች የዛሬዎቹ ተማሪዎች ናቸው። ስለሆነም ተማሪዎች ሀገራቸው ከሌሎች ያነሰች እንዳትሆን በትምህርታቸው ሊተጉ፣ የላቀ ብቃት ሊኖራቸው፣ ከሌላው ዓለም ተማሪዎች ጋር ብቁ ተፎካካሪ ሊሆኑ የግድ ይላቸዋል። ዓለም ወደ አንድ መንደርነት በመጣችበትና ውድድሩ ከምንጊዜውም በላይ በፈጠነበት በዚህ ዘመን የትምህርት ጥራትን አለማረጋገጥ አገርን ዋጋ ሊያስከፍል ስሚችል ቆም ብሎ ማሰብና ተግቶ መስራት ያስፈልጋል።
ትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለትምህርት ጥራት መጠበቅ የጀመሩትን ስራ አጠናክረው ማስቀጠል አለባቸው። ምሁራን በትምህርት ጥራት ዙሪያ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በማካሄድ ማገዝ ይኖርባቸዋል።
በሁሉም የትምህርት እርከኖች ከሚተገበሩ የሪፎርም ስራዎች እኩል የትምህርት ጥራትን ዋነኛ አጀንዳ ማድረግ ያስፈልጋል። የትምህርት ተደራሽነትና ፍትሃዊነት፣ የትምህርት ምዘናና ፈተና አሰጣጥን ማሻሻል፣ የትምህርት ዲጂታላይዜሽን ሪፎርም እንዲሁም ሙሉ በሙሉ እና ከፊል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን በማሳተፍ በፌዴራልና በክልሎች አቅም መልሶ ለመገንባት የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር ይገባል። እነዚህን ማሳካት ስንችል ለትምህርት ጥራት መደላድሉን እንፈጥራለን። በጥቅሉ በትምህርት ዘርፉ ያጋጠመውን ስብራት ማከም ለአንድ ወገን በተለይም ለመንግሥት ብቻ የሚተው ሳይሆን፤ የሁሉም ዜጋ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ።
ጤና
አንጋፋውን ለማዘመን
በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎትና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
ከምስረታው ጀምሮ የቆመለት ዓላማ ትልቅ ነው - ሕይወትን መታደግ፤ አገርና ሕዝብ ማገልገል። ከ75 ዓመታት በላይ የመድኃኒት ዕቃዎች፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ የሕክምና መሣሪያዎች እና አቅርቦቶችን ሥራ የሚከውን ግዙፍ መንግሥታዊ ተቋም ነው። በተለያዩ ጊዜያት መጠሪያውን ቢቀይርም ተግባሩን እያጎለበተ፤ የአገልግሎት ተደራሽነቱን እያሰፋ እስከአሁን ዘልቋል - የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት
ይህ አንጋፋ ተቋም ዛሬም ዘመነኛ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የሚገነባበትን፤ እኔም ወደ ትግበራ የገባሁበትን ፕሮጀክት ላስተዋውቃችሁ ይላል። ERP (Enterprise Resource Planning) ይሰኛል።
ERP ምንድነው?
ERP (Enterprise Resource Planning) በቻይና ፣ በሕንድ፣ በብራዚል፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ አገራት ከ50 ዓመት በላይ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት የደንበኞችን አገልግሎት ለማቀላጠፍ፤ የአቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም የገንዘብ ፍሰትን ለማሳለጥ፤
በየሺመቤት ደመቀ
የመረጃ ደህንነትን ለማስጠበቅ፤ የቢዝነስ ሪፖርቶችን ለማዘመን ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል።
የአንድን ድርጅት የስራ ሂደት ፍሰት በማስተካከል እንዲሁም ወጥነት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ በማድረግ ውጤታማነት እና የስራ ቅልጥፍናን የሚጨምር፤ የውስጥ እና የውጭ ግንኙነትን የሚያሻሽል እንዲሁም መረጃዎችን በአንድ ቋት በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል የተቀናጀ የመረጃ ሥርዓት (ሶፍትዌር) ነው።
በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥም በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እና አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ቴክኖሎጂ ሲሆን አገልግሎቱን በማቀላጠፍ ጊዜ፣ ጉልበትና ሃብትን በአግባቡ መጠቀም ያስችላል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት (ERP/SAP S4/HANA)ን ለትግበራው አመቺነት ሲል ሞጁሎችን (Tranche one) እና (Tranche Two) በማለት በሁለት በመክፈል ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።
በመጀመሪያው ክፍል የሚተገብራቸው 11 ሞጁሎች (Modules) ሲሆኑ በሁለተኛው ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉት ደግሞ 9 ሞጁሎች ናቸው። በአጠቃላይ በአገልግሎቱ 20 ሞጁሎች ተግባራዊ የሚደረጉ ሲሆን በእያንዳንዱ ክፍል የሚተገበሩ ስራዎችን በአምስት ምዕራፎች በመክፈል ወደ ትግበራ ገብቷል።
ERP ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት አንፃር
ወቅታዊ የተቀናጀ እና የተናበበ መረጃ ማየት የሚያስችል በመሆኑ ለውሣኔ አሰጣጥ ያግዛል፣ የዓመታት የስራ አፈፃፀምን ከበጀት ጋር ተንትኖ ያቀርባል፤ የቀጣይ ዕቅድ ትኩረትን ይጠቁማል፤ የተናበበ እና የተቀናጀ መረጃ ይሰጣል፤ ስራዎች በቴክኖሎጂ የታገዙ ስለሚሆኑ ቀድሞ ከነበረው ባጠረ ጊዜ እና በአነስተኛ ግብዓት መስራት በማስቻሉ ወጪ ቆጣቢ ነው። የስራ ድግግሞሽን በማስቀረት ሠራተኛው ስራዎችን በቀላሉ እና በፍጥነት መፈፀም ይችላል፣ ለስራው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ማየት ስለሚያስችል ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያሰፍናል፤ በራስ መተማመንን ይጨምራል፤ የስራ አፈፃፀምን
የሚያሣይ በመሆኑ ሠራተኛን ለማብቃት እንዲሁም ሥልጠና እና ማበረታቻ ለመስጠት ያስችላል፤ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው የአገልገሎቱን ስራ ያቀላጥፋሉ፤ የሠራተኞች ውጤታማነትም ይጨምራል።
የERP ጠቀሜታ ጠቅለል ሲል ፡-
ማቀላጠፍ - የተቋሙን የስራ ፍሰት በማቀላጠፍና በቴክኖሎጂ በማገዝ የመረጃዎችን ትክክለኛነት በማሻሻል ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ፤
መለካት - ሁሉንም መረጃዎች በማዋሃድና በቀላሉ በመተንተን የተቋሙን የዕለት ተዕለት ስራዎች ለመለካት፤
ፈጠራ - የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ሥራን ለሚያሻሽል አዳዲስ ፈጠራዎች በቂ ጊዜና ትኩረት እንዲሰጡ፤
መምራት - የተቋሙ አመራሮች ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች ላይ ተመርኩዘው ፈጣን ውሳኔ በመስጠት ተቋሙን እንዲመሩ፤
ማስቻል - ሠራተኞች ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ፣ ባገኙት መረጃ ላይ ተመስርተው ውሳኔ እንዲሰጡ ያስችላል።
ፕሮጀክት ስማይል
ፕሮጀክት ‘SMILE’ ለERP ትግበራ ከፕሮጀክቱ የሚጠበቁ ውጤቶችን የሚወክሉ ቃላትን በመውሰድ የተሰጠ የፕሮጀክት ስም ነው።
የፕሮጀክት ስማይል ዓላማ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የተሳለጠ የስራ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግ፣ ትክክለኛ እና የተተነተነ መረጃ ለማግኘት፣ ጊዜና ገንዘብ ለመቆጠብ፣ በትክክለኛ መረጃ ተመስርቶ ውሳኔ ለመስጠት በአጠቃላይ አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዘው ሶፍትዌር (The latest version SAP/S4HANA Enterprise tech- nology) እንዲተገበር ያደርጋል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ERP ፕሮጀክት በመጀመሪያው ክፍል (Tranche One) ተግባራዊ የሚያደርጋቸው 11 ሞጁሎች (Modules)፤ ሞጁሎቹ የሽያጭ እና የስርጭት አስተዳደር (O2C)፣ የሰው ሐብት አስተዳደር
(H2R)፣ የስራ አካባቢ ጤነነትና ደህንነት (EHS)፣ የፋይናንስ አስተዳደር (F2R), የግዥ ትንበያ (PI2Pr)፣ የትራንስፖርት ማኔጅመንት (TM)፣ የጥራት እና ቁጥጥር (I2R)፣ የግዥ አስተዳደር (P2P)፣ የመጋዘን እና የክምችት አያያዝ (S2S) እና የጥገና አስተደደር (In2Rep) ናቸው።
አገልግሎቱ እነዚህን ሞጁሎች የክምችት እና የመጋዘን አስተዳደር ስራዎችን የተቀላጠፈ እና ውጤታማ ለማድረግ፤ የክምችትና የመጋዘን አሰራሩን ለማዘመን፣ በቀላሉ ለማስተዳደር እና ለመቆጣጠር፤ ለስርጭት እና ለቆጠራ፤ የመጋዘን አቀማመጥን በማስተካከል ወጭ ቆጣቢ አሰራሮችን ለመጠቀም እና አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ፤
የአካባቢ፣ የጤና እና የደህንነት ፕሮግራሞችን እና የተሟላ የአደጋ መቆጣጠርና አስተዳደር ሥርዓትን በመዘርጋት በተቋሙ ሊደርሱ የሚችሉ የአደጋ ተጋላጭነትን ለመለየት፣ ለመተንተን፣ ለመከታተል፣ ለመከላከል እና ለመቀነስ፤ በተለይ ሠራተኞች በስራ ላይ እያሉ ሊደርስባቸው የሚችሉ ጉዳቶችን በመከላከል ለሠራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ክሶችና የተለያዩ ወጪዎችን ለመቀነስ፤
የደንበኞችን የመድኃኒትና ሌሎች የሕክምና ግብዓቶች ፍላጎት ለማወቅ፣ ዓለም እና አገር አቀፍ የግዥ ሥርዓቱን ግምት ውስጥ ለማስገባት፣ የበርካታ አገራት አቅራቢዎችን መረጃ በመተንተን የግዥ ትንበያ ስራዎችን ለመከወን፤
አገልግሎቱ የት አካባቢ ምን አይነት የሕክምና ግብዓት በምን ያህል መጠን እንደሚፈለግ እና ምን ያህል ወጪ እንደሚጠይቅ በመለየት እንዲሁም መቼ መቅረብ እንዳለባቸው በመወሰንና በመከታተል የአቅርቦት ዕቅድ ጥራትን ለማሻሻልና ብክነትን ለመቀነስ እያደረገ ያለውን ጥረት በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ከዚህ በፊት በማንዋል ሲሰራ የነበረውን ጊዜ በማሳጠር፣ ፍጥነት በመጨመር፣ ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል በማድረግ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማሻሻልና ወደ ትክክለኛ ፍላጎት በመጠጋት የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር ጥቅም ላይ ያውላቸዋል።
መድኃኒት ለሰው ልጅ የጤና ችግር ፈውስ ለመስጠት እና በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል የሚዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን የሚፈለገውን ጥቅም እንዲሰጥ ጥራቱ, ደህንነቱ እና ፈዋሽነቱ የተጠበቀ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ በአቅርቦት ሰንሰለት ሂደት ውስጥ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይታወቃል።
እነዚህ ጥራታቸው ተረጋግጦ አገር ውስጥ የገቡ መድኃኒቶችን ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማከማቸትና በማሰራጨት ለጤና ተቋማት እስከ ማስረከብ ድረስ ያለውን የጥራት ደረጃ ክትትል ማድረግ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሚና ነው። አገልግሎቱ ይህንን ሚና በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ተግባሩን በአግባቡ ለመፈጸም የሚጠቀመው የጥራትና ቁጥጥር አስተዳደር ይገኝበታል።
በአገልግሎቱ ተገዝተው የሚመጡ እና በአጋር ድርጅቶች በኩል በእርዳታ የሚቀርቡ የሕክምና እና ሌሎች ግብዓቶችን ከጥራት መለኪያዎች አንጻር መጋዘን ሲደርሱ፣ በክምችት ላይ እያሉ እና ለደንበኞች ሲሰራጩ እንዲሁም ከደንበኞች ሲመለሱ የጥራት ፍተሻ በማድረግ ዓለምአቀፍ የጥራት መለኪያዎችን ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ስራዎችን ለመፈጸም የሚያስችለውንም ሞጁል ጥቅም ላይ አውሏል።
የጥራት አስተዳደር በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚስተዋሉ የጥራት ጉድለቶች እና በተለያዩ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የሕክምና ግብዓቶች ተከታትሎ የእርምትና የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ለማድረግ፣ የጥራት ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከል፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት፣ ብክነትና ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የደንበኞችን የግብዓት እጥረት ቅሬታ ምላሽ በመስጠት እርካታ ለመጨመር ያግዛል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ካፒታል ከሚያንቀሳቅሱ የመንግሥት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ተቋሙ ንብረቶች ብልሽት እንዳይገጥማቸው አስቀድሞ ለመከላከልና ብልሽቶች ሲገጥሙም በፍጥነት ተጠግነው ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ ለማድረግ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን አሰራሩን ፈጣን እና ቀልጣፋ ለማድረግ ዓለም የደረሰበት የጥገና አሠራር ሂደቶችን ተግባራዊ በማድረግ ምቹ፣ የተቀላጠፈና ወጪ ቆጣቢ አሰራር ይተገብራል።
አገልግሎቱ ከሚተገብረው የተቀናጀ የመረጃ
ሥርዓት ከደንበኛ ትዕዛዝ ክፍያ አስከመፈጸም ድረስ ያለውን የሽያጭ እና የስርጭት ሂደት በቴክኖሎጂ ታግዞ የሚያስተዳድርበት፤ ደንበኞች ወደ ተቋሙ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ትዕዛዝ ለመላክ፣ የትዕዛዝ ሂደቱን ለመከታተል፣ የዱቤ እና የክፍያ ውሎችን ለማስተዳደር፣ ደረሰኞችን እንዲሁም ሌሎች ሰነዶችን በተቀላጠፈ መልኩ ለመለዋወጥ በአጠቃላይ የሽያጭ እና ስርጭት ሥርዓቱን ፈጣን እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ በማስተዳደር የደንበኞችን እርካታ የሚያሳድግበት ነው።
ይህ ሥርዓት የሽያጭ እና የክፍያ መጠየቂያ መረጃዎችን በቀላሉ ለማወቅና የተጠቃለለ ሪፖርት በማዘጋጀት ለባለድርሻ አካላት ለማቅረብ፤ የተቋሙን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ለማመላከት፣ ለማቀድና ለመተንበይም ያስችላል።
የአቅርቦት ሰንሰለት ስራዎችን በማዘመን በማዕከል በብቃት ለማስተዳደር ተገዝተው የመጡ ወይም በተለያየ መልኩ የገቡ የሕክምና ግብዓቶችን/እቃዎችን ተቀብሎ ከማከማቸት አስከ ማጓጓዝ ያለውን የስራ ፍሰት ለማቀላጠፍና በመጋዘን ያሉ ግብዓቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ ለመከታተል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓትም አለው። ይህም በአጠቃላይ የአቅርቦት ሰንሰለት እይታውን በመጨመር፣ አሠራሩን በማቀላጠፍ፣ ብክነትን፣ የጭነት፣ የመጓጓዣ እና የሰው ኃይል ወጪዎችን በመቀነስ የአቅርቦት ሰንሰለቱ ውጤታማ እንዲሆን ያግዘዋል።
ለመድኃኒት አቅርቦቱ ፈተና ከሆኑት ምክንያቶች አንዱ ከ80 በመቶ በላይ የሆነው የመድኃኒት ግዥ በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚፈፀምና በርካታ ባለድርሻ አካላት ተዋናይ መሆናቸው የግዥ ሂደቱን ረዥምና ውስብስብ በማድረጉ በአቅርቦት ሥርዓቱ ላይ የፈጠረውን ጫና በማቃለል የሚገዛውን የመድኃኒት ወይም የእቃ ዓይነትና መጠን በመለየት የግዥ ትዕዛዝ ለመስጠት፣ አቅራቢዎችን ለማወዳደርና አፈጻጸማቸውን ለመገምገም፤ ክፍያዎችን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ከማስቻሉም ባሻገር መሻሻል ያለባቸውን ቦታዎች መለየት የሚያስችል ትንታኔና ሪፖርት ለማቅረብ የሚረዳውም ሞጁል ይገኝበታል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የአቅርቦት ሰንሰለት
ለመገንባት በያዘው ዕቅድ መሰረት እያከናወነ የሚገኘው የተቀናጀ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት (ERP/SAP S4/HANA) በመጀመሪያው ክፍል (Tranche one) ከሚተገብራቸው 11 ሞጁሎች (Modules) መካከል አንዱ የፋይናንስ አስተዳደር SAP F2R (Finance to Report)) ይገኝበታል።
ሌላው የተቋሙን የፋይናንስ አሰራር ፈጣን፣ ቀላል እና እርስ በእርስ የተናበበ እንዲሆን የሚያደርገው ሞጁል ሲሆን የአገልግሎቱን አጠቃላይ ገቢ እና ወጭ በቀላሉ ለማወቅና ለማስተዳደር፣ የበጀት አጠቃቀሙን ለመከታተል፣ የወረቀት ስራዎችን እና የስራ ድግግሞሽን ለመቀነስ በአጠቃላይ ወጭ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ስራዎችን በማከናወን ውጤታማ የሚያደርገው ነው።
በተጨማሪም የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የፋይናንስ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ለማዘጋጀት፣ የድርጅቱን ቋሚ ንብረቶች በተቀመጡ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ ተመስርቶ ለመከታተልና ለማስተዳደር በአጠቃላይ የስራ ሂደቶችን በማስተሳሰር ወቅታዊ መረጃዎችን በመተንተን ሥራን ያቀላል።
ከቅጥር እስከ ስንብት ድረስ ያለውን የስራ ፍሰት የሚያዘምን፤ በተለይ የቅጥር ሥርዓቱን ለማቀላጠፍ፣ የሠራተኞችን የግል መረጃ በተደራጀና በግልጽ ለማስተዳደር፣ የሥልጠና ፍላጎቶችና የሙያ ዕድገቶችን ለመከታተልና ለመፈጸም፣ የሠራተኛን ክህሎትና ብቃት ለማሳደግ የሚረዳው፤ የወረቀት ስራዎችን፣ ስህተትና የመረጃ ድግግሞሽን የሚቀንሰው፣ የሠራተኞችን የእረፍት ጊዜ፣ የትርፍ ሰዓት እና የፈረቃ ሥርዓቶች ለማወቅና ሪፖርቶችን በፍጥነትና በቀላሉ ለማውጣት የሚያገለግለው የሰው ኃብት አስተዳደር ሞጁል ነው።
የትራንስፖርት አስተዳደር ሥርዓት ለላኪዎች፣ ለጭነት አስተላላፊዎችና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት ሰጪዎች ከጫፍ እስከ ጫፍ የትራንስፖርት አስተዳደር የሚሰጥ የላቀ የሎጂስቲክስ ሶፍትዌር ነው። የጭነት ስራዎችን ለማመቻቸት፣ ለማሰማራትና ለማሳለጥ የተነደፈ በመሆኑ የማስፈጸምና የማመቻቸት ብቃትን ያላብሳል።
ማህበራዊ
ዩኒቨርሲቲው ለማኅበረሰቡ . . .
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
በጌታቸው ሰናይ በመማር ማስተማር ሂደት ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፍ አንጋፋ ተቋም ነው። በየጊዜው በለውጥ ጎዳና እየተጓዘና አዳዲስ አሰራሮችን እያጠናከረ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲም ነው። 70 ዓመታት ባስቆጠረው የመማር ማስተማር ተግባሩ በርካታ ስመጥር ተመራማሪዎችን አፍርቷል። በአገሪቷ የልማትና የዕድገት ተግባራት ውስጥ የራሳቸውን የማይተካ ሚና የሚጫወቱና እየተጫወቱ ያሉ ምሁራንን ያስገኘ የትምህርት ተቋም ነው - ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ።
“ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታው ጀምሮ በርካታ ምሁራንን በማፍራት አገራቸውን ያገለገሉና ሕዝባቸው ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጣ ያገዙ በርካታ የሀገርና የወገን ባለውለታዎችን አፍርቷል” ሲሉ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ባሳለፍነው የካቲት ወር ባካሄደው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ፕሮፌሰር መንግሥቱ ኡርጌ የገለጹትን ሃሳብ እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በምርምር ዘርፍ ኢትዮጵያ ‘አሉኝ’ ብላ ከምትመካባቸውና በግንባር ቀደምነት ከምትጠቅሳቸው ጠንካራና አስተማማኝ ተቋማት መካከል ተጠቃሽ ነው። አገሪቷ በግብርናው ዘርፍ ባስመዘገበቻቸውና እያስመዘገበቻቸው በሚገኙ መልካም ውጤቶች ከመጀመሪያው ረድፍ የሚቀመጥ ታላቅ ተቋምም ነው። በተለይ በየጊዜው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለምታደርገው ጥረት የማይተካ ሚናውን በመጫወት ላይ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በግብርናው ዘርፍ አንደኛው ተግዳሮት የሆነውን የድህረ ምርት ብክነት ለመቀነስ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት በማስተዋወቅ ረገድ የዩኒቨርሲቲው ሚና ቀላል አይደለም።
ይህ አንጋፋ የትምህርት ተቋም በሰብል ልማት፣ በተፈጥሮ ሐብትና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፎች ሰፋ ያሉ ጥናትና ምርምሮች በማካሄድ አገር በቀል መፍትሔዎችን በመፈለግ ለአርሶ እና ለአርብቶ አደሩ የማስተዋወቅ ተግባር ሲያከናውን
ዓመታትን አስቆጥሯል፤ አሁንም ይህን ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም ለአገሪቷ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ሊያመጡ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችን በማፍለቅ አርብቶ አደሮችና አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል፤ እያደረገም ነው።
ዩኒቨርሲቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በዕውቀት የበለጸጉ ተግባራትን በማከናወን፣ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለሀገራዊ ፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በማስረፅ ላይ
እንደሚገኝ በዕድሜው ካስመዘገባቸው ድንቅ ውጤቶች መገንዘብ ይቻላል። ኢትዮጵያ በግብርና ምርምር ያላት አቅም እንዲጠናከር የበኩሉን የማይተካ ሚና ተጫውቷል። በአገር ደረጃ ጠንካራ የምርምር ሥርዓት እንዲፈጠር የማይተካ ወሳኝ ሚና ነበረው፤ አሁንም ይህን ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።
ለኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል። በግብርና መስክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር
የሆኑ ተመራማሪዎችንና ሳይንቲስቶችን አፍርቷል፤ አሁንም እያፈራ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዘርፎች የምርምር ውጤቶችን በማቅረብ በሀገሪቷ የለውጥ ሂደት ውስጥ አዎንታዊ ሚናውን አጉልቶ እያሳየ ነው። በተለይም የተለያዩ የምርምር ተግባራትን ከአገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መልካም ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል።
በተለይ በግብርናው ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች አስደናቂዎች ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በግብርና ዘርፍ በአገር ደረጃ የልህቀት ማዕከል በመሆን መጻኢ ዘመኑ ላይ ትልቁን ድርሻ ይወጣል። በግብርናው ዘርፍ ከአገር አልፎ በአፍሪካ ደረጃ የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይ ሰንቆ መስራት መጀመሩ በአብነት የሚጠቀሰው ለዚህ ነው።
በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማኀበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ይስሐቅ ዩሱፍ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ምርጥ ዘር ከ20 እስከ 25 በመቶ የሚሆነው ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
የወጣ ነው። ሰብል ላይ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው” ሲሉ ይገልጻሉ። ዩኒቨርሲቲው በግብርናው መስክ ያከናወናቸው በርካታ ተግባራት በአገር ደረጃ ያለውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ በጉልህ ያሳያል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማሩ እና በምርምር ሥራዎች ብቻ የተገታ አይደለም፤ የማኀበረሰብ አገልግሎት በመስጠትም ቀዳሚ ሆኗል። የአካባቢው ማኅበረሰብ “ከጎናችን ያለ የእኛ ተቋም ነው” በሚል በዩኒቨርሲቲው መተማመን ያደረባቸው በማኅበራዊ አገልግሎቱ እያከናወናቸው በሚገኙ ተግባራቱ ነውም ይላሉ። “ለኅብረተሰቡ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ያደርጋል ወይንም ደግሞ የማኅበረሰብ ተሳትፎ ስራዎችን ያከናውናል” ሲሉም መሰረታዊ ተግባራቱን ይገልጻሉ።
እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ዩኒቨርሲቲው በማኅበረሰብ ላይ ያተኮሩ ስድስት ዓበይት ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። አንደኛው በግብርና ውጤታማነት ላይ የሚሰራው ነው። ሌላው በትምህርት ጥራት፣ በተፈጥሮ ሐብት
አስተዳደር እንዲሁም በሕግ አገልግሎት ላይ የሚያከናውናቸውና ማኅበረሰቡን በእጅጉ እየጠቀሙ ያሉ ተግባራቱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ “ጤና ላይ እንሰራለን፣ ሌሎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ላይ እንሰራለን። ዩኒቨርሲቲውንና ኢንዱስትሪዎችን በማገናኘት የኢንዱስትሪዎችን ችግር በጋራ ለመፍታት እንቀሳቀሳለን። ተማሪዎች እዚያ ሆነው አብረው የሚሰሩባቸውን ሁኔታዎችም እናመቻቻለን” ሲሉ ዶክተር ይስሐቅ በስፋት ገልጸውታል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ባካሄደው የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ፕሮፌሰር መንግሥቱ ኡርጌ “በሥልጠና፣ በቁሳቁስና በመጻሕፍት ድጋፍ፣ በመሰረት ልማት ማስፋፋት፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን መቀነስ በሚያስችሉ ተግባራት፣ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎችን በማከናወን የአካባቢውን ማኅበረሰብ በመደገፍ ላይ ይገኛል”
ሲሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማኅበረሰብ ድጋፍ ስራውን እያሰፋ መሆኑን በንግግራቸው አጽንኦት ሰጥተውታል።
ዩኒቨርሲቲው የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በማከናወን የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል። በተለይም የንጹሕ መጠጥ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮና መስመር ዝርጋታ ስራዎችን በማከናወን የአካባቢውን ነዋሪዎች የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር ለማቃለል መስራቱ ከማኅበረሰቡ ጎን መቆሙን በተግባር ያረጋገጠበት ማሳያ ነው።
ማኅበረሰቡን በማስተባበር የሚያከናውናቸው የልማት ተግባራት ዘላቂ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡና የሕዝቡን ችግሮች የሚፈቱ መሆናቸውን ላለፉት አሥር ዓመታት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያከናወነው ተግባር ዓብይ ምስክር ነው።
“በአካባቢ ጥበቃ የሐረማያ ሐይቅ ተፋሰስን
በማልማት የጠፋው ሐይቅ እንደገና እንዲያገግምና እንዲመለስ ያስቻሉ ስራዎችን በተፋሰሱ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን በማስተባበር ላለፉት አሥር ዓመታት ሰርተናል፡፡ በዚህም ያገኘነውን ውጤት ለማስፋፋት ከሐይቁ ተፋሰስ ክልል በመውጣት ከኖርዌይ መንግሥት በፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በኩል ባገኘነው የገንዘብ ድጋፍ ደንገጎ አካባቢ ፕሮጀክት አስጀምረን ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያየን ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር መንግሥቱ ገልጸዋል።
ማኅበረሰቡን ከመጥቀምና አካባቢያዊ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ከማድረጊያ መንገዶች አንዱ የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን በማባዛት ማሰራጨት ነው። ምርጥ ዝርያዎችን በማውጣት ለማኅበረሰቡ ዩኒቨርሲቲው ተደራሽ እያደረገ ነው።
እነዚህን ዝርያዎች አባዝቶ ለማኅበረሰቡ በማሰራጨት ውጤታማ ስራ እንዲከናወን ያደርጋል። በተለይ ወጣቶች ተደራጅተው በመቅረብ ምርጥ ዘር በመውሰድ ይጠቀማሉ።
ይህም በስራቸውና በአካባቢያቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ለሚያደርጉት ጥረት የጀርባ አጥንት እንዲሆንላቸው የሚሰራ ነው። “አንደኛው መልኩ ራሳቸውን ላልቻሉና አዲስ ለተደራጁ ወጣቶችም ሆኑ አርሶ አደሮች ድጋፍ ማድረጊያ መንገዳችን ነው” በማለት ዶክተር ይስሐቅ ይናገራሉ።
ሌላው ለአርሶና ለአርብቶ አደሮች ቴክኖሎጂ በድጋፍ ወይም በክፍያ እንዲደርሳቸው መደረጉ ተጠቃሽ ነው። ይህ ማለት አቅም ያላቸው የማኅበረሰብ አባላት በግዥ እንዲያገኙ ይደረጋል፤ ሌሎቹን ደግሞ ዩኒቨርሲቲው ይደግፋቸዋል።
“የዶሮ እርባታ ጣቢያው እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ለማኅበረሰቡ ያቀርባል። ማቅረብ ብቻም አይደለም፤ በአካባቢው ለሚገኙ ሴት አርሶ አደሮች ያለ ክፍያ ይሰጣል። በተለይ ከምግብ እጥረት እና ከኢኮኖሚ ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮችን ለማቃለል የዶሮዎች አቅርቦት ይደረጋል” ይላሉ ዶክተር ይስሐቅ።
ዩኒቨርሲቲው ለሴት አርሶ አደሮች የሚሰጣቸው እንቁላል ጣይ ዶሮዎች የዕለት ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ይረዳቸዋል። በዚህ ዓይነት በየዓመቱ ሦስት ሺህ ያህል ዶሮዎች ወደ ማኅበረሰቡ እንዲደርሱ በማድረግ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራው ማኅበረሰቡን ወደተሻለ የኑሮ ደረጃ ሊያሻግር የሚችል በዕውቀት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት ስለመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በሚሰራባቸው አካባቢዎች የሚታዩ ለውጦችን በመፈተሽ መረዳት ይቻላል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የከብቶች ማደለቢያም
አለው። ለተማሪዎች መመገቢያ ቤት የስጋ አቅርቦት የሚውሉ ከብቶች ይደልቡበታል። ከዚህ በተጨማሪም ለማኅበረሰቡ የተሻለ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎችን ኮርማዎች ይሰጣል። በተለይ በተመረጡ ሰርቶ ማሳያዎችና ገበሬ ማህበሮች ውስጥ ኮርማዎቹን የአካባበቢው ማህበረሰብ እንዲጠቀምባቸው እያደረገ ነው። ዩኒቨርሲቲው ከንብ ማነቢያውም በየዓመቱ ከ20 እስከ 30 የንብ ቀፎዎችን ከንብ ጋር በሐረማያ ሐይቅ ተፋሰስ ውስጥ ለሚገኙና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ላይ ተሳትፎ ለሚያደርጉ አርሶ አደሮች ድጋፍ ያደርጋል።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎት
ከሚሰጥባቸው የተለያዩ ዘርፎች የጤና እና የሕግ አገልግሎቶች ይጠቀሳሉ፤ በእነዚህ አገልግሎቶቹ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ይሆናል። በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙና አገልግሎቶቹን በተፈለገው መጠን ማግኘት የማይችሉትን በማገዝ ለአካባቢው ማኅበረሰብ አጋርነቱን በተግባር አሳይቷል፤ እያሳየም ይገኛል።
ለአብነት በዩኒቨርሲቲው በኩል በሕግ ኮሌጅ የሚሰጠው ነፃ የሕግ አገልግሎት ድሆችን እና ጠበቃ ለመቅጠር አቅም የሌላቸውን የአካባቢውን ማኅበረሰብ አባላትን ማገልገልን ታሳቢ ያደረገ ነው። በዚህም በርካታ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ አዛውንቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና
ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ሆነዋል።
ነፃ የሕግ አገልግሎት የሚሰጠው በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች በሚገኙ ሁሉም የወረዳ ፍርድ ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች እንዲሁም በሐረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም የወረዳ ፍርድ ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች ነው። በተለይም ከመጀመሪያ ደረጃ፣ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት እስከ ኦሮሚያ እና ሐረሪ ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም እስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሕግ አገልግሎት ለሚሹ ድጋፍ በማድረግ የማኅበረሰቡን ችግር በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል። የኮሌጁ ተማሪዎችም ለማኅበረሰቡ ነፃ የሕግ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በተግባር ላይ የተመሰረተ የሕግ እውቀት እንዲገበዩ ይደረጋል። በሌላ በኩል
ደግሞ በችግር ምክንያት ፍትሕ ለማግኘት የተቸገሩ የማኅበረሰብ ክፍሎችም ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለማኅበረሰቡም ሆነ ለተቋሙ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ኢንተርፕራይዝ አቋቁሞ ለዓመታት ሲከውነው የነበረውን ተግባሩን በተቀናጀና አትራፊ በሆነ መንገድ ለመምራት በማሰብ ነው። በተለይም ኢንተርፕራይዙ ለዩኒቨርሲቲውና አካባቢው ማኅበረሰብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ የተዘጋጀ ነው። ለዚህም ውጤታማ የሚያደርገውን አደረጃጀት ይከተላል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል የሱፍ፤ “በዩኒቨርሲቲው ለተሽከርካሪዎች ተገቢውን የጥገና አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዘመናዊ
ጋራዥ ግንባታ መጠናቀቁን፣ ዘመናዊ ለጥገና ስራ የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች መኖራቸው፤ በአካባቢው የሚታየውን የተሽከርካሪዎች ጥገና ችግር ለመፍታት ያስችላል” ሲሉ የኢንተርፕራይዙን ዝግጅት በተመለከተ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተቀናጀ ትምህርት እንዲቀስሙ ዕድል ይሰጣል። ይህ በራሱ የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ፤ ተግባር ተኮር ትምህርት እጅግ ውጤታማ እንዲሆን ያደርጋል። የኢንተርፕራይዙ በዩኒቨርሲቲው መቋቋም ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት “ማኅበረሰቡም በአነስተኛ ክፍያ የሚፈልገውን አገልግሎት በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል። ለእኛም ትልቅ ገቢ የሚያስገኝ ይሆናል” ሲሉ ዶክተር ጀማል አስረድተዋል።
ፖለቲካ
ከጨዋታም በላይ
በቆንጂት ተሾመ በምዕራብ አፍሪካዊቷ አይቮሪኮስት ዋና ከተማ አቢጃን የሚገኘውና በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አላሳን ኡታራ ስም የሚጠራው ግዙፍ ስታዲየም ብርቱካናማ መለያ በለበሱ 60 ሺህ የአገሪቱ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ደምቋል። በሜዳቸው ያዘጋጁትን እና ከጥር 4 እስከ የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን 34ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ቡድናቸው እንዲያነሳ ያልተቋረጠ የድጋፍ ኅብረ ዜማ ሲያሰሙ ቆይተዋል። በመጨረሻም ተሳካላቸው! ባስታወሱት ቁጥር ፈገግ የሚሉበትን ደስታ ተጎናጸፉ። አይቮሪኮስታዊያኑ በአገር ጉዳይ አብሮነትና አንድነትን አሰናስሎ በትጋት መስራት የጥንካሬና የስኬት መገለጫ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል።
የአይቮሪኮስት ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎችም ሆኑ መላው የአገሪቱ ዜጎች ከአሥር ዓመት በፊት አጋጥሟቸው የነበረውን እና የአገራቸው መገለጫ ሆኖ ቆይቶ የነበረውን ክስተት ግን መቼም ሊያስታውሱት አይፈልጉም። ፖለቲካዊ ቀውስ ባመጣው የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ የሞትና የስደት ዜናዎች በየቀኑ የሚሰሙባት ነበረች-አይቮሪኮስት።
ከዘመንም ዘመን ገድ አለው እንዲሉ የፈረንጆቹ 2024 ለአይቮሪኮስታዊያን የሳቅና የሀሴት ዘመናቸው ሆኗል። በአንድነት እኩል የተጋሩትን ደስታ አግኝተዋል። በምድራቸው ባዘጋጁት 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፤ ብሔራዊ ቡድናቸው ውጤታማ እንዲሆን በአገር ፍቅር ስሜት በአንድ ላይ በሕብረት
ተሰልፈዋል። የአገር ፍቅር ስሜታቸውን በተግባር ማሳየት ችለዋል። ህልም ውጥናቸው ተሳክቶም 34ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ በድል ማንሳት ችለዋል።
በአገሪቷ በሚካሄደው ምርጫ በድጋሚ ለፕሬዝዳትነት ለመወዳደር በመወሰናቸው ተቃውሞና ትችት የገጠማቸው ፕሬዚዳንት አላሳን ኡታራ፤ ለአሸናፊው ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናቸው ዋንጫውን ለመሸለም በሥማቸው በተሰየመው ስታዲየም ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናቸውን ደግፎ ለማበረታታትና የጋራ ጥረትና ትጋት የሆነውን የድል ብስራት ዋንጫ በሕብረት ለማንሳት በስታዲየሙ ከታደመው ከ60 ሺህ ከሚልቀው ሕዝባቸው ፊት ሲቆሙ፤ የደስታ ጩኸት ነበር ያጀባቸው። የፖለቲካ ልዩነቱን ወይም በመንግሥት ላይ ያለውን ቅሬታ አስታውሶ በተቃውሞ የጮኸባቸው አንድም ዜጋ አልነበረም። ለምን ቢባል ጉዳያቸው ልዩነትን ወደ ጎን ትቶ በአንድነትና በሕብረት የቆሙበትና ለድልም የበቁበት የአገር ጉዳይ ነውና። የሕፃናትና የእናቶች ዋይታ ይሰማባቸው የነበሩት የአቢጃን ጎዳናዎችም ዜጎች በሆታ እና በደስታ የሚጨፍሩባቸው ሆኑ። በአይቮሪኮስት ምድር ይህ ይሆናል ብሎ ማንም አልገመተም ቢባል ማጋነን አይሆንም። አይቮሪኮስት የአብራኳ ክፋዮች አሁን በደስታ አንብተዋል።
አይቮሪኮስት በበርካታ ጉዳዮች ልዩነት ያላቸው ልጆቿ በስታዲየም ውስጥ አንድ ሆነው ታድመዋል። በዚሁ ለአንድ ወር ሲካሄድ በቆየው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የአገራቸውን ስኬት ብቻ በመሻት ብሔራዊ ቡድናቸውን በአንድነት ሲደግፉ ሰንብተዋል።
አይቮሪኮስታዊያኑን እንዲህ በአንድነት፣ በአንድ ድምፅ ሆ! ብለው እንዲቆሙ ያደረጋቸው ምንድን ነው? ያልን እንደሆነ፤ የነፃነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ “ስፖርት በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበብ አንድነትን ማምጣት የሚያስችል ኃያል መሳሪያ ነው” ሲሉ የተናገሩት ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ይሆነናል። ለአይቮሪኮስት የአፍሪካ ዋንጫው ከዚህም በላይ ነው። የአገሪቱ ሕዝቦች በአንድነት እንዲቆሙ ከማድረግ ባሻገርም የኢኮኖሚ ጥቅሟን ከፍ ያደረገ ሌላ ዕድልም ሆኗል።
አይቮሪኮስት ለ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ መስተንግዶ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋለች። ፕሬዝዳንት አላሳን ኡታራ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (International Mon- etary Fund) ከተበደሩት 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ግማሽ ያህሉን ለስፖርት ማዋላቸው
ብዙ ቢያስተቻቸውም ያተረፉት እንደሚበልጥ መናገር ይቻላል።
አይቮሪኮስት ለ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አራት አዲስ ዘመናዊ ስታዲየሞችን በመገንባትና ሁለት ነባር ስታዲየሞችን በማደስ፤ ሆቴሎችና የሕክምና ተቋማትን በማዘጋጀት፤ እንዲሁም የመንገድና የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት ዝግጁ ሆና እንግዶቿን አስተናግዳለች። እነዚህ ውድድሩን ታሳቢ በማድረግ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ለአገርና ለሕዝብ ዘለቄታዊ ሀብት ሆነው ያገለግላሉ። በሂደት ደግሞ አገሪቷ ከጠቅላላው ገቢዋ ዘጠኝ በመቶ የሆነው የቱሪዝም ገቢዋ እንዲጨምር እንደሚያደርጉ ይታመናል።
አይቮሪኮስት በዚህ አህጉራዊ የውድድር መድረክ አዘጋጅነቷ ያገኘችውን የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስላት ጊዜው ገና ቢሆንም፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት ተራዝሞ በ2014 ዓ.ም የተካሄደውን 33ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያስተናገደችውን ካሜሮንን ለአብነት መጥቀስ ተገቢ ነው። ካሜሮን 33ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታስተናግድ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብታወጣም፤ ከወጪዋ በ4 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብልጫ ያለው 6 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ማግኘቷ ነው የተነገረው።
ስፖርት ቱሪዝም
መሰል ስፖርታዊ መድረኮች ለአንድ አገር ልማትና ዕድገት እንዲሁም ሁሉም አበክሮ የሚፈልገውን፣ እጅግ አስፈላጊ እና የሁሉም ነገር መሰረት የሆነው ሰላም እንዲሰፍን ከማስቻል ባሻገር፤ የስፖርት ቱሪዝም ገቢን በማሳደግ ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው።
ስፖርት ቱሪዝም፤ በዋናነት ስፖርታዊ ውድድሮች የሚስተናገዱበት ሲሆን፤ የተለያዩ ጉዞዎች የሚደረግበትም ነው። ስፖርታዊ ውድድሮች ቡድኖችንም ሆኑ የደጋፊዎችን ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ፤ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መጓዝን ይጠይቃሉ። በዚህ የጉዞ ሒደት ውስጥ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ የሚፈጥረው ምጣኔ ሐብታዊ ፋይዳ ቀላል አይደለም። በተለይም ደግሞ ዓለም አቀፋዊ የስፖርት መድረኮችን ማዘጋጀት የውጭ ምንዛሬ ገቢንም በማስገኘት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው። በተጓዳኝም የጉብኝት መዳረሻዎችን የሚመለከቱበት አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ የውድድር መድረኮቹ አዘጋጅ አገር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል።
በዓለም ላይ ስፖርት ቱሪዝም አሁን አሁን በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የሚገኝ የቱሪዝም ዘርፍ ነው። አገራት ምጣኔ ሐብታቸውን ለመደገፍ ስፖርታዊ የውድድር መድረኮችን ማዘጋጀትን እንደ አንድ አማራጭ ይጠቀሙበታል።
አውሮፓ በስፖርት ቱሪዝም ከፍተኛውን የጥቅም
ድርሻ የምታገኝ ሲሆን፤ ይህ ጥቅም ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ከማዘጋጀት እንደሚመነጭ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በአንጻሩ አፍሪካ ከዘርፉ ለመጠቀም ገና ጅማሮ ላይ ናት። የተፈጥሮ ሀብቶቿን እና የመስህብ ስፍራዎቿን ለማሳየትና ከዚህም ገቢ ለማግኘት ስፖርት ቱሪዝም ላይ መስራት እጅጉን ያዋጣታል። ነገር ግን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እንደ ኦሊምፒክ እና የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (FIFA) ዓለም ዋንጫ መድረኮችን ለማዘጋጀት የመሰረተ ልማት እጥረትና የሰላም እጦት እንቅፋት ሆነውባታል።
ከምስራቅ አፍሪካ አገሮች ኬንያ ከፍተኛ የቱሪዝም ገቢ ባለቤት ናት። በ2023 ይፋ የሆነው መረጃ እንደተመላከተው ዓመታዊ የቱሪዝም ገቢዋን 2 ነጥብ 13 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ የቻለች ሲሆን፤ ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 83 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ ስፖርታዊ መድረኮች በማዘጋጀት ያገኘችው ገቢ የራሱ ድርሻ አለው። የረጅም ርቀት ሯጮች ባለቤት የሆነችው ኬንያ ዓለም አቀፍ የማራቶን፣ የራግቢ፣ የሆኪ እና የውሃ ዋና የመሳሰሉ ውድድሮችን በማዘጋጀት ወደ አገሯ የሚመጡ የውጭ አገር ጎብኝዎችን ቁጥር ማሳደግ ችላለች።
ስፖርት ቱሪዝምን ጉዳይ ወደ አገራችን አምጥተን
ስናየው ግን ኢትዮጵያ ፈጽሞ የዘነጋችው የቱሪዝም ዘርፍ ነው ማለት ይቻላል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአገሪቱ የቱሪዝም ገቢ ተመሳሳይ ከሆኑ ዘርፎች የሚገኝ ነው። በአብዛኛው የምታስመዘግበው ገቢ ከጥንታዊ ቅርሶችን ፍለጋ በተጨማሪ ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላትን ምክንያት አድርገው ከሚመጡ የውጭ አገራት ዜጎች የሚገኝ ነው። ከዚህ አኳያ ሲታይ ስፖርታዊ መድረኮች ላይ ገና አልተሰራም ለማለት ያስደፍራል።
የስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር መስፍን ቸርነት በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ። ነገር ግን በመንግሥት ደረጃ ውድድሮችን ከማዘጋጀት በፊት፤ መሰረተ ልማቶችን የማሟላት ስራዎች ቅድሚያ እንደተሰጣቸው ይገልጻሉ።
“መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ለማዘጋጀት ነው ቅድሚያ የሰጠው። አዳዲስ በመገንባትና ነባሮቹንም በማደስ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ለማሟላት እየሰራን ነው። በየክልሎቹ የሚገኙትን ጨምሮ የአዲስ አበባ ስታዲየምን እና አደይ አበባ ስታዲየምን ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግዱ ክትትል እያደረግን ነው። ይህንን ማሳካት ሲቻል ዓለም አቀፍ የስፖርት መድረኮችን ለማዘጋጀት እንጥራለን” ይላሉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የመሰረተ ልማቶችን ማሟላት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ነው ያስረዱት። በዚህ ረገድ ከሌሎች ተቋማት ጋር ተናቦ የመስራት ልምዱ እንደሌለ አልሸሸጉም። በቀጣይ ትኩረት ሊቸረው የሚገባ ጉዳይ ስለመሆኑ አስምረውበታል።
በእርግጥ አምባሳደር መስፍን እንዳሉት መሰረተ ልማቶችን ማሟላት አስፈላጊ ነው። መሰረተ ልማቶች እየተገነቡ፤ ባለው ነባራዊ ሁኔታም መስራት ግን ይቻላል። ምንም መሰረተ ልማት የማይፈልጉ እንደ ጎዳና ላይ ሩጫ ስፖርቶች አሉ። ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መድረክ ለዚህ ጥሩ ምሣሌ ነው። በዚህ መድረክ ላይ ለመሳተፍ በየዓመቱ ከውጭ አገር የሚመጡ የተለያዩ አገራት ዜጎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም።
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ እንደነገሩን በሩጫ መድረኩ ላይ ለመሳተፍ በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ በሩጫው ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ መኖራቸውን፤ እንዲሁም አመጣጣቸው ሩጫው ላይ ብቻ ተሳትፎ ለመመለስ እንዳልሆነም ነው የሚያስረዱት።
“ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከውጭ የሚመጡ ዜጎች 10 ኪሎ ሜትሩን ለማጠናቀቅ ከአንድ ሰዓት በላይ ላይፈጅባቸው ይችላል። 10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ብቻ አይደለም ወደ ኢትዮጵያ የሚያመጣቸው። ሩጫው መነሻ ምክንያታቸው ነው። ነገር ግን ከሩጫም በላይ ኢትዮጵያ ምርጫቸው እንድትሆን ያደረጋቸው ብዙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርስና ሐብቶች ስላለንም ነው። ከሩጫው በፊትም ሆነ በኋላ ወደ ሌሎች የጉብኝት ቦታዎች ሳይሔዱ አይመለሱም” ሲሉ ሩጫው ሌሎች የቱሪስት መዳረሻዎችም በውጭ ዜጎች እንዲጎበኙ አስተዋጽኦ ማድረጉን ያስረዳሉ።
በእርግጥም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም ገቢ ማስገኛ መድረክ ስለመሆኑ መናገር ይቻላል። መሰል መድረኮችን በብዛት ማዘጋጀት በተለይም የቱሪዝም ሐብቶች ባሏቸው አካባቢዎች ማዘጋጀት ከዘርፉ የሚገኘውን ሁለንተናዊ ትርፍ ይበልጥ ያሳድጋል።
በዚህ በኩል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዘንድሮ ሐዋሳ ላይ የተዘጋጀውን የግማሽ ማራቶን ሩጫ፤ በአዲስ የመሮጫ ቦታና ስያሜ ማከናወኑን መጥቀስ ተገቢ ነው። ዓመታዊው የሐዋሳ
ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ሲካሔድ የቆየ ሲሆን፤ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው በሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ነው። ስያሜውንም “የሐዋሳ ሐይቅ ዳር ሩጫ” ብሎታል። ውድድሩ በሐይቆች የታደለችውን የሐዋሳን ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ማሳየት አስችሏል።
ባለፈው ጥር 2016 ዓ.ም መጨረሻ የተካሔደው የሐዋሳ ሐይቅ ዳር ሩጫ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች የተሳተፉበትና በቀጣይም በብዛት የሚመጡበት እንደሚሆን ነው ዳግማዊት አማረ ያላቸውን እምነት የገለጹት።
ያልተሰራበት ታላቁ መድረክ በዓለም የአትሌቲክስ ስፖርት “አበበ ቢቂላ” የሚለው ስም ታላቅ ነው። አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፤ በመላው ዓለም እጅጉን የተከበረና የተደነቀ ታሪክ ሰሪ ጀግና ነው። በዚህ ታላቅ የማራቶን ጀግና ስም፤ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አማካኝነት የሚዘጋጅ ዓመታዊ ውድድር አለ። “የሻምበል አበበ ቢቂላ ኢንተርናሽናል የማራቶን ውድድር” የሚል ስያሜ ይዞ ይካሔዳል። የታላቁን የዓለም ጀግና አትሌት ስም እንደመያዙ ግን ታላቅ መድረክ መሆን አልቻለም። መድረኩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ አገራዊ ጥቅም ማግኘት ቢቻልም አልተሰራበትም።
አበበ ቢቂላ ካለው ታላቅ የሩጫ ስብዕና አንጻር ውድድሩ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ኖሮት፤ የውጭ አገር ዜጎች እንዲሳተፉ ማድረግ ቢቻልም፤ በውድድሩ የሚሳተፉት ግን የአገር ውስጥ ሯጮች ብቻ ናቸው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሌላም በኢንተርናሽናል ስያሜ የሚጠራውን የጃን ሜዳ አገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ያዘጋጃል። ይህ ቀደም ሲል ከአምስት ያላነሱ አገሮች አትሌቶቻቸውን የሚያሳትፉበት መድረክ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን አሁን ግን የውጭ አገር አትሌቶች የሚታዩበት አይደለም። ከዚህም ባሻገር አሁናዊ ቁመናው የአገር ውስጥ አትሌቶችንም በአግባቡ ለማወዳደር የሚችልበት የጥራት ደረጃ ላይ እንደማይገኝ ይነገራል።
ፌዴሬሽኑ ለሩጫ ውድድሮቹ ኢንተርናሽናል (ዓለም አቀፍ) የሚለውን ስያሜ እየተጠቀመ ቢሆንም፤ አሁንም ድረስ የውጭ አገር ዜጎችን እንዲሳተፉ ባለማድረጉ ሊገኝ የሚችለውን የስፖርት ቱሪዝም ገቢ መፍጠር አልቻለም። ይህ ለምን ሆነ? ስንል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ
እንግዳን ጠይቀናል። እርሳቸውም የፌዴሬሽኑ ዓላማ በዋናነት ብቁ አትሌቶችን በማፍራት በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማስቻል እንደሆነ ይገልጻሉ። በዚህ ሒደት ውስጥም በአገር ውስጥ የተለያዩ የውድድር መድረኮችን እንደሚያዘጋጅ ያክላሉ። መድረኮቹ ለዓለም አቀፍ ቀርቶ ለአገር አቀፍ እንኳ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዳልሆኑም ይስማማሉ። ለዚህ ደግሞ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ጥራት መጓደል እና የመወዳደሪያ ቁሶች አለመሟላታቸውን አንስተዋል።
“ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ቀርቶ ልምምድ ለመስራትም የምንችልበት የስፖርት ማዘውተሪያ ማግኘት ተቸግረናል። አንድም ትራክ ያለው ስታዲየም የለንም” ሲሉም ነው ፌዴሬሽኑ ራሱ ለአትሌቶቹ መለማመጃ መቸገሩን የገለጹት።
ባዶ ሜዳን ማዘጋጀት የሚፈልገውን የአገር አቋራጭ የውድድር መድረክም ሆነ የአስፓልት መንገዶችን ለይቶ መከለልን ብቻ የሚጠይቀውን የማራቶን ሩጫ፤ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀት አለመቻል ግን በእርግጥ ያስተቻል፤ እየተተቸም ነው።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዮሐንስ እንግዳ ግን ይህን ትችት አይቀበሉትም። የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በልማት ላይ እንጂ ገቢ የሚያስገኙ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን የማዘጋጀት ተልዕኮ እንደሌለው ይሞግታሉ።፡ ይልቁንም አገራት የሚሳተፉባቸው የአትሌቲክስ መድረኮችን ማዘጋጀቱ ብዙ ጥቅም እንዳለው በማስታወስ፤ ይህም በቀጣይ የሚሰራበት እንደሆነ ነው የተናገሩት። ይሁንና ቱሪዝም ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ ማናቸውም አካላት ጋር በትብብር ለመስራት ፌዴሬሽኑ ፈቃደኛ እንደሆነም ይገልጻሉ።
አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ በበኩሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ችግር ቢሆንም፤ ዓለም አቀፋዊ የውድድር መድረኮችን በማዘጋጀት ማትረፍ እንደሚቻል ይገልጻል። በአፍሪካ አገሮች በአካልም የተመለከታቸው የሩጫ ውድድሮችን በመጥቀስ ኢትዮጵያም ማዘጋጀት እንደምትችል ያምናል።
ጋዜጠኛ ተሾመ “ኬንያን ለምሣሌ ብንጠቅስ ዓመታዊ የማራቶን መድረኮችንም ሆነ የአገር አቋራጭ ውድድሮቿን፤ ኢትዮጵያም በተሻለ ደረጃ ለማዘጋጀት ትችላለች። በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለው የተለያየ አይነት የአየር ጠባይና መልክዓ ምድር ለዚህ ምቹ ነው። የውጭ አገር አትሌቶች እንደውም ፈተናውን
ይፈልጉታል። የሚመጡት ጥሩ ሆቴልና የተሟላ የስፖርት መሰረተ ልማት ፈልገው አይደለም። አፍሪካዊያን ያለብንን ችግር ያውቁታል” ይላል።
የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶች በቂ ነገር ሳይሟላላቸው አሸናፊ እንደሆኑ ያውቃሉ። ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች የታደሉትን የተፈጥሮ ፀጋ ተጠቅመው ውጤታማ እንደሆኑ ስለሚገነዘቡ ነውም ይላል።
ይህንን በመረዳትም አገር ከስፖርት ቱሪዝም ተጠቃሚ እንድትሆን ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ መስራት እንደሚገባ ነው የተናገረው። እነ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ የልምምድ ቦታ ማዘጋጀታቸው ከስፖርት ቱሪዝም ገቢ እንደሚገኝ ስለሚያውቁ እንደሆነም ይጠቅሳል። ሌሎች ባለሀብቶችም ስፖርት ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ያሉትን አማራጮችን ማሳየት እንደሚገባ ነው የገለጸው።
የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከጥቂት ዓመታት በፊት “ጉዞ ወደ ዓባይ ምንጭ” በሚል ስያሜ፤ የብስክሌት ወድድር አዘጋጅቶ ነበር። ከአዲስ አበባ ባሕር ዳር ድረስ የተደረገው የብስክሌት ውድድር፤ ከፉክክርም በላይ ኢትዮጵያ ያላትን ሐብት የማስተዋወቅ ዓላማን ያነገበ እንደነበር የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ረዘነ በየነ ያስታውሳሉ።
“ጉዞ ወደ ዓባይ ምንጭ” የብስክሌት ውድድር ከአዲስ አበባ ባሕር ዳር ድረስ ሲካሔድ፤ በምንደርስባቸው ከተሞች ሁሉ ያለውን የተፈጥሮ ሐብትና እሴቶች እየተመለከትን ነው። ውድድሩም የኢትዮጵያ ታላቅ የወንዝ ሐብት የሆነውን ዓባይን የሚያስተዋውቅ ነበር።
የኢትዮጵያ መገለጫዎች የሆኑ ስያሜዎችን በመስጠት ውድድሮችን ማካሔድና ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዲኖራቸው በማድረግ የውጭ ሀገር ዜጎችን በቀላሉ ማሳተፍ እንደሚቻልም ይገልጻሉ። በዚህም ሀገር የምታተርፈው ብዙ ነገሮች መኖራቸውንም አስረድተዋል። ይህም፤ የቱሪዝም ገቢን በከፍተኛ ደረጃ ከማሳደግ ባሻገር፤ ወጣቱ ስፖርታዊ ተሳትፎ እንዲኖረው በማድረግ ከጥፋት መንገድ መጠበቅ መቻሉንም ነው ያብራሩት።
በኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝምን በማስፋፋትና በማጎልበት ከዘርፉም የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ ከመንግሥት በተጨማሪ የግሉን ዘርፍ ባለሀብቶች ማሳተፍ አስፈላጊ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ግንዛቤ መፍጠሩ እንደሚቀድም የሚናገረው ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ፤ እንደ ኬንያ ያሉ ጎረቤት አገሮችን ተሞክሮ አምጥቶ ማካፈል ያስፈልጋል ይላል።
“ኬንያ የስፖርት ቱሪዝምን ገቢ ቀድማ በመረዳት ብዙ ባለሀብቶች የስፖርት ማዘውተሪያ
ሥፍራዎችን እንዲያለሙ አድርጋለች። ባለሀብቶች በዋናነት የውጭ ዜጎችን ማዕከል በማድረግ ብዙ የልምምድ ቦታዎችን ምቹ አድርገው ሰርተዋል። በዚህም የአውሮፓና የአሜሪካ አትሌቶች ለወራት ልምምድ የሚያደርጉባቸውን ማረፊያዎች በቀላሉ መርጠው ያገኛሉ። ይህን ተሞክሮ በማካፈል ግንዛቤ እንዲፈጠር ማድረግ ይቻላል”።
ኢትዮጵያ ካላት የሕዝብ ብዛት እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳየት ከምትችላቸው አያሌ ፀጋዎችና ሀብቶች አንጻር የሚዘጋጁ የስፖርት መድረኮች በቂ እንዳልሆኑ የገለጹት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳማዊት አማረ፤ ክልሎችም ሆኑ ሌሎች አካላት ቢሰሩበት አዋጭ እንደሆነ ነው ያስረዱት። እርሳቸው እንዳሉት ስፖርታዊ መድረኮች የተለያየ አስተሳሰብና ሃይማኖት ውስጥ ያለውን ሕዝብ በአንድ መድረክ በማገናኘት ሰላምና አንድነትን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ነው።
“ስፖርት ለጤንነት፣ ለፍቅር፣ ለወዳጅነት፣ ስፖርት ለአካል ማጎልመሻ፣ ለመንፈስ ማደሻ…” እያለ ያዜመው የአገራችን አቀንቃኝ ዛሬ ላይ ቢሆን ስፖርት - ለሰላም፣ ለቱሪስት መስህብ፤ ለአንድነት… የሚሉ ስንኞችን የሚያክልበት አይመስላችሁም? ቸር እንሰንብት!
ፖለቲካ
በስኬት የዘለቀው
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ
በስኬት የዘለቀው
ኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን በሚጠጋው የሕዝብ ብዛቷ ከሰሃራ በታች ሁለተኛ፤ ከዓለም ደግሞ 13ኛ አገር ስትሆን፣ የምትገኝበት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥም በምስራቅ አፍሪካ እስያና አውሮፓ የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂ ወሳኝ ሊባል የሚችል ስፍራ ነው። በዓለማችን በመጀመሪያ ተርታ ከሚጠቀሱ ሃይማኖቶች መካከል አይሁድ፣ ክርስትና እና እስልምና እምነቶችን በቀደምትነት የተቀበለችም አገር ነች። ይህም እነዚህ እምነቶች በተነሱባቸው አካባቢዎች ሕዝቦች እና መንግሥታት ዘንድ ያላትን ታዋቂነት፣ ተቀባይነት እና ጠንካራ ግንኙነት የሚመሰክር ነው። ከዚህም ባሻገር ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶቿ ማጠናከሪያ ሆኗል። አንድ አገር ከውጭው ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ጥንካሬ በዋናነት ከሚወስኑት ሁለት አበይት ጉዳዮች አንደኛው ውስጣዊ ጉዳይ ሲሆን፣ ሁለተኛው ውጫዊ ምክንያቶች እንደሆኑ የዘርፉ ምሁራን ያስረዳሉ። ውስጣዊ ሲባል አንድ አገር የሚገኝበት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲሁም መረጋጋት ሊሆን ይችላል። የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ተንታኙ አቶ አትክልት አጥናፉ እንደሚሉት የአንድ አገር የውጭ ጥንካሬ የሚመጣው በውስጥ ከፍተኛ አቅም ሲፈጠር ነው። ስለዚህ በኢኮኖሚ፣ በጦር ኃይል አቅምና ያልተገባ ዓለም አቀፍ ጫናን ተቋቁሞ ማለፍ እንደ አንድ ተቋማዊ አቅሞች ማሳያ እና አንድ አገር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እንዳለው ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
በማሕተመ ብሩ
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ
ከዚህ አንጸር ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርካታ ዓለምአቀፍ ተግዳሮቶችን ያሳለፈች ስትሆን በእነዚህ ተግዳሮቶች ሳትበገር አሁን ለምትገኝበት ደረጃ መድረስ የቻለችው ሕዝብና መንግሥት ችግሮቹን በጽናት እና በብልሀት በማለፋቸው እንደሆነ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአንድ ወቅት ይህን ብለዋል። “የመጀመሪያው የድሉ ምንጭ እና ሐብት የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናት፤ የኢትዮጵያ እንደ አገር ብርታት እና የተዋናዮቹ ጥበብና ብልሃት እንዲሁም የወዳጆቻችን አብሮ መቆም ነው። በእነዚህ አራት ጭብጦች ውህድ ውጤት ኢትዮጵያ ይህን ፈተና ተሻግራ ዋናውን መስመሯን ሳትለቅ በታሪክ በየዘመኑ የተሻገርንባቸውን የአገር ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ይህንን በረዶ ለመሻገር ችላለች። ይህ እንደ ትልቅ ድል እና ስኬት ሊወሰድና ዋናው ባለቤት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል”። አቶ አትክልት በበኩላቸው በዓለም አቀፍ ግንኙነት አገራት ከአገራት ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት ቋሚ ጥቅማቸውን በዘላቂነት ማስጠበቅ ላይ የተመሠረተ ነው። ይሁን እንጂ ትኩረት የሚሰጠው ከቋሚ ወዳጅ ይልቅ ቋሚ ጥቅም የሚባለው መርህ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ከዚያ ወጣ ባለ መንገድ አገራት የራሳቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አላቸው። ሕገ መንግሥታቸውን መሠረት ያደረገውን የውጭ ፖሊሲያቸውን ለማሳካት የአጭር እና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂም ይኖራቸዋል። ስትራቴጂው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ቅርበት፣ የንግድ፣ የፖለቲካ፣ የዜጋ ለዜጋ ግንኙነቶችን መሠረት ያደረገ ሊሆን ይችላል። እነዚህ እንዳሉ ሆነው በአንድ ጉዳይ ላይ አገሪቷ የውስጥ አቋሟ፣ የውስጥ ፍላጎቷ ወይም አገራዊ፣ ፖለቲካዊና በራሷ አስተዳደር ያለምንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ጫናዎችን ተቋቁማ መሰለፍ ስትችል፤ የአገሪቷን የውስጥና የተቋማት ጥንካሬ እንዲሁም የመተግበር አቅም ሲኖራት፤ በዲፕሎማሲ የመደራደር አቅሟን ጭምር የሚያሳይ ተቋማዊ አቅም ሲኖራት ጠንካራ ዲፕሎማሲ ገንብታለች ለማለት ያስደፍራል ይላሉ። አንድ አገር (መንግሥት) ምን ያህል ጠንካራና ተጽዕኖ ፈጣሪ ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ አንዳንድ የኢትዮጵያን ሁኔታዎች መዳሰስ አንዱ መንገድ ቢሆንም እነዚህ መመዘኛዎች ባሉበትም ሌሎች አገራት ለኢትዮጵያ እየሰጡት ያለውን
ቦታ ማየትም መልስ ሊሆን ይችላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ደመቀ መኮንን ሲያብራሩ በርካታ አገራት ውስብስብ ዓለምአቀፍ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟቸው ውሳኔ ከማሳለፋቸው አስቀድመው ኢትዮጵያን ማማከር ወይም የኢትዮጵያን አቋም ማየት እንደሚያዘወትሩ ያስረዳሉ። አያይዘውም “ብዙ አገራት አፍሪካዊያን፣ በታሪክ በመጣንባቸው በተለያዩ መልኮች ለኢትዮጵያ ያላቸው ክብርና ግምት በጣም የላቀ ነው። አንዳንድ ጊዜ እኛ በልዩ ልዩ አጀንዳ ተወጥረን ባለንበት ዓለምን የሚፈትኑ ጉዳዮች ሲመጡ በተባበሩት መንግሥታት አቋም የሚያዝባቸው፣ ድምጽ የሚሰማባቸው፣ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ኢትዮጵያ በራሷ ብዙ ችግርና ብዙ ጫና ያለባት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናት፣ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት፣ በአፍሪካ ኅብረት ትልቅ ቦታ ያላት አገር ናት። የኢትዮጵያ ድምጽ፣ የኢትዮጵያ መልዕክትና ተጽዕኖ ተባዥ ነው። ከዚህ አኳያ ነው ሚናችሁን መወጣት ያለባችሁ፣ ይህን አቋም ውሰዱ፣ እንዲህ ዓይነት እርምጃ ውሰዱ፣ እንዲህ ዓይነት ድምጽ አሰሙ በሚል ትልቅ ግምት ሰጥተው ነው የሚነግሩን።
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ምናለች ይባላል። አፍሪካዊያን፣ የላቲን አሜሪካ አገራት እና ብዙ የዓለም አገራት ለኢትዮጵያ ያላቸው አተያይና እይታ በጣም ከፍ ያለ ነው” ይላሉ። በጥቅሉ ውስጣዊ የሚባለው መመዘኛ የሚያተኩረው አንድ አገር (መንግሥት) በሌሎች አገራት ተፈላጊ ሊያደርገው የሚችለውን እና ይዞት የሚቀርበውን ጉዳይ አጠናክሮ የቤት ስራውን ሰርቶ መገኘት ማለት ነው። ውጫዊ የሚባለው ደግሞ ያ አገር ወይም መንግሥት የሚከተለው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ከየትኞቹ አገራት ጋር በምን አይነት መልኩ መዛመድና መወገን እንዳለበት የሚያሳይ ነው። የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት ንግሥት ሳባ ንጉሥ ሰለሞንን ለመጎብኘት ወደ እስራኤል ተጉዛ ነበር። ይህ ታሪካዊ ጉዞ እና ጉብኝትም የኢትዮጵያ ጥንታዊ የውጭ ግንኙነት ዲፕሎማሲ ጅማሮ እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል። በዚህ የተጀመረው የአገሪቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዛሬ በተቋም ደረጃ ተጠናክሮ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ተሰሚ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን አድርጓታል።
በንግሥት ሳባ ዘመን የተጀመረው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። በንጉሥ ዓፄ ፋሲለደስ ዘመን ንጉሡ የተከተሉት የዝግ በር ፖሊሲም በሩን ዘግቶ የነበረው ለአውሮፓዊያን እንጂ ከሌላው ዓለም ጋር ግንኙነቱ በጠበቀ መልኩ መቀጠሉን የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ። ኢትዮጵያ ምንም እንኳን እንደ በርካታ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች የተቀየደች ብትሆንም ቅሉ፤ ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች አሁን እያስመዘገበች ባለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊና ተጽዕኖ ፈጣሪ ልትባል የምትችል አገር ናት። በዚህ ረጅም ዕድሜ ባስቆጠረው ሚዛናዊ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ በተለያዩ ዘመናት ያጋጠሟትን በርካታ ውጣ ውረዶች አልፋ ዛሬ በዓለምአቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በቀጣናዊ ተቋማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጉልህ ሚና የምትጫወት አገር ሆናለች። አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ኢመሪተስ ባህሩ ዘውዴ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት የጀመረው በአክሱም ዘመነ መንግሥት ሲሆን፣
የውጭ ግንኙነቱም በንግድና በሃይማኖት ላይ የተመሰረተ እንደነበረ ያወሳሉ። አክሱም ከሌላው ዓለም ጋር በጣም ሰፊ የሆነ የንግድ ግንኙነት ነበራት። በተለይም በጊዜው በሜዲትራኒያን በኩል ከዓለም ጋር ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴ ታደርግ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ ሲሉ ይጠቅሳሉ። በወቅቱም በዓለም ትልቅ ዝና እና ዕውቅና ከነበራቸው ወደቦች መካከል የአዶሊስ ወደብ አንዱ ነበር። በተለይ አንድ በጉዞ ማስታወሻ መልክ የተጻፈ ዘገባ በዝርዝር እንዳተተው በአዶሊስ ወደብ ብዙ ሸቀጦች ይገቡና ይወጡ እንደነበር ነው። የንግድ ግንኙነቱ የኋላ ኋላ ለሃይማኖት ግንኙነት መሠረት ሆኗል። የእስልምና ሃይማኖት በተጀመረበት ወቅት የነበሩ የአካባቢው ገዥዎች እምነቱን ስላልተቀበሉት ነብዩ መሀመድ በንጉሥ ኢዛና ዘመን ተከታዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል። “ፍትህ የሚያውቅ ንጉሥ ሀበሻ ምድር አለና ወደ እርሱ ሄዳችሁ ጥገኝነት ጠይቁ” ባሉት መሰረት የመጀመሪያዎቹ የእምነቱ ተከታዮች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአክሱም ዘመን የመጨረሻዎቹ ዓመታት አካባቢ እንደነበር ይነገራል።
ከ13ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓዊያን በእስልምና እምነት ተከታይ መንግሥታት ቁጥጥር ስር የዋለችውን ኢየሩሳሌምን ለመያዝ የመስቀል ጦርነት የሚያካሂዱበት ወቅት ነበር። በዚህ ጦርነት የበላይነት ለማግኘት ያግዘናል ብለው ያመኑበትን ቄስ ዮሐንስ የተባለውን ንጉሥ ለማግኘት ባካሄዱት ፍለጋ ያገኙት ኢትዮጵያን እንደነበር ፕሮፌሰር ባህሩ ያብራራሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያና የአውሮፓ መንግሥታት ግንኙነት እያደገ፣ የተለያዩ ልውውጦች እና ድጋፎችም ሲደረጉ ቆይተው አሁን ለደረሰበት ባለ ብዙ መልክ የዲፕሎማሲ ግንኙነት በቅቷል። ዘመናዊው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ጅማሮ በርካታ ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ጠንካራ የውጭ ግንኙነት ዘመናዊ ገፅታን ተላብሶ መካሄድ የጀመረው የዛሬ 116 ዓመት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተቋቋመ በኋላ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ። ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መቋቋም መሰረት የሆነው ኢትዮጵያ በዓድዋ ጦርነት ያገኘችው ታሪካዊ ድል ነው። የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛታቸው ለማድረግ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም የመጨረሻው ወሳኝ ምዕራፍ ግን ከኢጣሊያ ጋር አድዋ ላይ የተደረገው ጦርነት ነበር። የኢጣሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ጋር ውጫሌ ላይ ያደረገውን ውል ሰበብ በማድረግ ኢትዮጵያን እንደ ቅኝ ግዛቱ ለማድረግ ቢሞክርም ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ይህን ሸር ተረድተው ከኢጣሊያ ጋር የተደረገው ጦርነት ዓድዋ ላይ በኢትዮጵያዊያን ድል አድራጊነት ተቋጭቶ የውጫሌ ውል ውድቅ ሆኖ ኢትዮጵያ ነፃና ሉዓላዊት አገር መሆኗን ለዓለም አስመሰከረች። በዓድዋ ድል አውሮፓዊያኑ ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛታቸው ማድረግ እንደማይችሉ ተገንዝበው ከኢትዮጵያ ጋር ሥርዓት ያለው የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አስገደዳቸው። ከዓድዋ ድል ማግስት ኢጣሊያ፣ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ በኢትዮጵያ ኤምባሲያቸውን ከፈቱ፤ ሌሎች ወዳጅ አገራትም ተከተሏቸው። ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያም እንደ ሌሎቹ አገራት የዲፕሎማሲ ስራዎችን የሚያከናውን መስሪያ ቤት ማቋቋም በማስፈለጉ በ1907 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ እና ንግድ ሚኒስቴር በሚል ስያሜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቋቋመ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተቋቋመ በኋላ
ኢትዮጵያ በርካታ እመርታዎችን አሳይታለች። በዚህም ለዘመናት ጠብቃ የቆየችውን ፖሊሲ በማስቀጠል፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ምስረታ በመሳተፍ እና አባል በመሆን፣ እንዲሁም ከተመሰረቱም በኋላ የተለያዩ ግዴታዎችን በመወጣት በአፍሪካ ግንባር ቀደም ምሣሌ ሆናለች፤ አሁንም እንደሆነች ቀጥላለች። ለአብነትም በ1923 የተቋቋመው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል መሆኗ አንዱ ማሳያ ነው። በርካታ የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር በሚማቅቁበት በዚያ ዘመን ኢትዮጵያ የሊጉ አባል መሆኗ ከታሪካዊ ዝናነት ባለፈ በፋሽስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ሊጉ ፍትሃዊ አቋም አለመያዙ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል። ያም ሆኖ ግን ኢትዮጵያ በቀጣይ ሊጉን ተክቶ የተቋቋመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል በመሆን ዓለም እና አህጉር አቀፍ ሚናዋን በመወጣት ከአፍሪካ ነፃና ቀደምት ሉዓላዊት አገር መሆን ችላለች። ሌሎች አገራት በግንባር ቀደምትነት በሚመሰርቷቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በቀዳሚነት አባል መሆን ብቻም ሳይሆን ኢትዮጵያ አፍሪካዊያን የራሳቸው አህጉር አቀፍ
ተቋም ኖሯቸው ለነፃነታቸውና ለመብታቸው እንዲታገሉም የላቀ አስተዋጽኦ አበርክታለች። ለአብነትም የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት ነው። ያለፉት አምስት ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ያጋጠሟትን ዓለም አቀፍ ጫናዎች ለመቋቋም፣ ኢኮኖሚያዊ ግቦቿን ለማሳካት እና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ዲፕሎማሲን እየተጠቀመችበት ትገኛለች። በእነዚህ ጊዜያት በተካሄዱ መልከ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ኹነቶች በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። ለተመዘገቡት ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች የውጭ ግንኙነትን አስመልክቶ በመንግሥት የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የአሰራር እና የአቅጣጫ እርምጃዎች በምክንያትነት ይጠቀሳሉ። ከስኬቶቹና ከድሎች መካከልም ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ተዳሰዋል። የኢትዮጵያ የብሪክስ (BRICS) አባልነት ጉዞ እና ስኬት ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የለውጥ ጎዳና መተግበር ከጀመረችበት ካለፉት አምስት
ዓመታት ወዲህ ካስመዘገበቻቸው ዲፕሎማሲያዊ ድሎች መካከል ዋነኛው እና ትልቁን ቦታ የሚይዘው የብሪክስ አባል አገር ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ነው። ይህም በተለያዩ ጊዜት ሲደርስባት የነበረውን ያልተገባ ኢኮኖያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለማስወገድ እያደረገች ላለው ብርቱ ጥረት ወሳኝ ከመሆኑ በላይ ለምታካሂዳቸው የልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስ፣ የቴክኒክ እና የገበያ ዕድል በማመቻቸት ረገድ ትልቅ ዕድል በመሆኑ ነው። ዓለማችን በአሁኑ ወቅት ስምንት ቢሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ይኖርባታል። እነዚህ ሕዝቦችም 200 በሚጠጉ ነፃና ሉዓላዊ አገራት እና ግዛቶች ይኖራሉ። ይሁን እንጂ አገራቱ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በቴክኖሎጂና በሌሎችም ወሳኝ በሆኑ መመዘኛዎች እኩል ወይም ተመጣጣኝ በሚባል ደረጃ የሚገኙ አይደሉም። ጥቂቶቹ በኢኮኖሚ የፈረጠሙ፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለጸጉ ሲሆኑ፤ የተወሰኑት በመካከለኛ ደረጃ፤ በርካቶቹ ደግሞ ዝቅተኛ በሚባል ደረጃ የሚገኙ ናቸው። በዚህም እነዚህ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ምዕራባዊያን አገራት በማደግ ላይ ያሉት አገሮች
በእነሱ ሁለንተናዊ ተጽዕኖ ስር ወድቀው ጉዳይ አስፈጻሚያቸው እንዲሆኑ አበክረው ይጥራሉ። እነዚህ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ምዕራባዊያን አገራት እጅ በመጠምዘዝ ይህን ዓላማቸውን ለማሳካት ከሚጠቀሙባቸው ስልቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ለታዳጊ አገራት በሚያደርጉት እርዳታና በሚሰጡት ብድር ሰበብ በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ መግባት በሚችሉባቸው ተቋማት በኩል ነው። ይህን ፖሊሲያቸውን የሚያስፈጽሙት ደግሞ በዓለም ባንክ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) አማካኝነት ነው። ይህን መመሪያ የማይቀበሉ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ለኢኮኖሚና ለማኅበራዊ ልማት የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ ድጋፍ አያገኙም። መመሪያውን ተቀብለው የሚተገብሩ ከሆነ ደግሞ በብዙ መስዋዕትነት ያስከበሩትን ነፃነት እና ሉዓላዊነታቸውን የሚገዳደር ይሆናል። ስለሆነም በማደግ ላይ ያሉ አገራት ነጻነታቸውን እና ሉዓላዊነታቸውን በማያስደፍር መንገድ ለዕድገታቸው ወሳኝ የሆነውን የገንዘብ ድጋፍና የገበያ ዕድል ማግኘት መቻል ትልቅ ስኬት ነው። ከዚህ አንጻር በማደግ ላይ ላሉ አገራት ትልቅ
የምስራች ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው የቅርብ ጊዜው ፍጻሜ ብሪክስ /BRICS/ በመባል የሚታወቀው ጥምረት ነው። “ብሪክስ” የሚለው ቃል የመጣው ጥምረቱን ለመጀመሪያ ጊዜ የመሰረቱትን አገራት ስም የመጀመሪያ ፊደል/ሆሄ በመያዝ ሲሆን እነርሱም ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው። ስያሜው ደቡብ አፍሪካ ጥምረቱን ከመቀላቀሏ በፊት እንደ አውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ2001 የፈጠሩት የጎልድማን ሳክስ ኦ’ኔል እንደሆኑ ይነገራል። በተለይም መስራቾቹ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ኢኮኖሚ ከፍተኛ እምርታ ማሳየቱን ተከትሎ የዓለምን ኢኮኖሚ የሚለውጥ አቅም እንዳለው በመገንዘባቸው በጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ግንዛቤ የተወሰደበት ነበር። የብሪክስ አባል አገራት የዓለምን ሕዝብ 42 በመቶ እንዲሁም የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት 31 ከመቶ ይሸፍናሉ። የብሪክስ ዋና ግቡ ቀጣይነት ያለውና ሁሉንም ፍትሃዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ዕድገት ለማስፈን በአባል አገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ ማስፋት እና ማሳደግ እንደሆነም ይነገራል:: ”የብሪክስ” አባል አገራት ኢኮኖሚያቸውን በከፍተኛ ደረጃ እያሳደጉ ስለሆነ የዓለምን የፖለቲካ ኃይል ሚዛን በመቀየር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ አላቸው። በማደግ ላይ ያሉ አገራት ኃያላን አገራት የሚሏቸውን “እሺ” ብሎ ከመቀበል ይልቅ በበርካታ ጉዳዮች በልዩነት የቆሙባቸው መድረኮች ነበሩ። ስለዚህ ጥምረቱ የአንድ ወገን የበላይነትን የመገዳደር ሚናው ከፍተኛ ነው። ከተመሰረተ 13 ዓመት ያስቆጠረው ብሪክስ የበርካታ አገራትን ትኩረት ስቦ “እኔንም አስገቡኝ፤ ተቀበሉኝ” ውትወታ ለማስተናገድ በቅቷል። ባለፈው ሐምሌ ደቡብ አፍሪካ ላይ የተካሄደው የብሎኩ ስብሰባ ከመካሄዱ በፊት የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ40 ያላነሱ አገራት የአባልነት ጥያቄ አቅርበዋል። እነዚህ አገራት አብዛኞቹ በኢኮኖሚ፣ በሕዝብ ብዛትም ሆነ በሌሎች መመዘኛዎች ከኢትዮጵያ ጋር አቻ አልያም ከፍ ያሉ የሚባሉ ናቸው። መስራቾቹም አዲስ አባል አገራትን በመቀበል ጥምረቱን የማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው አሳይተዋል። ዓለም አቀፍ ተቋማት ባስቀመጡት ግምት መሠረት ኢትዮጵያ በየዓመቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ነው። በጥምረቱ የብትካተት ጥያቄ ያቀረበችው ብሄራዊ ጥቅሟን ታሳቢ
ጥቅምን የማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ፣ የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በእርግጠኝነት የማሳደግ ጉዳይ ነው። በሁኔታዎች የማይበገር የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት ኢትዮጵያና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እ.ኤ.አ በ1971 ሲሆን፤ ግማሽ ምዕተ ዓመት በዘለለው ግንኙነታቸው በርካታ ድሎችን አስመዝግበዋል። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቶ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በትምህርትና ሥልጠና፣ በትራንስፖርትና በመሳሰሉ ዘርፎች ተምሣሌት በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛል። የቻይና ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማስመዝገብ ግንባር ቀደም ከሚባሉት ተርታ ይመደባሉ። የሁለቱ አገራት ዕድገት በተለያዩ ወቅቶች ያለፉባቸውን ዲፕሎማሲያዊ ውጣ ውረዶች አልፎ ዛሬ ላይ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ የሚባለውን በሁኔታዎች የማይበገር (All Weather Friend- ship) የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመመስረት በቅተዋል። የኢትዮ-ቻይና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ዓለም አቀፉ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር የማይለዋወጥ በጋራ ጥቅም ላይ በመተሳሰብ የሚወስኑበት ነው።
በበርካታ ዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟት ኢትዮጵያ እንደ ቻይና ካሉ ወዳጅ አገራት ጋር የመሰረተችው አጋርነት ተጽዕኖዎችን ተቋቁማ በማለፍ ዘላቂ ጥቅሟን ለማስከበር እያደረገች ያለውን ጥረት እውን ለማድረግ የጎላ ሚና ይኖረዋል። ይህ ደግሞ መንግሥት ካከናወናቸው ስኬታማ የዲፕሎማሲ አፈጻጸሞች በግንባር ቀደምትነት ሊጠቀስ ይችላል። በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 28) የተገኘው ድል ባለንበት ዘመን በምድራችንና በሰው ልጆች ህልውና ላይ የተጋረጠ ትልቁ አደጋ የሚባለው የአየር ንብረት ለውጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ በባህሪው ዓለም አቀፍ ሥጋት ቢሆንም ለውጡ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ከመቋቋምና የሚደርስባቸውን ውድመትና ኪሳራ ከማካካስ አንጻር ያደጉት ሀገራት የተሻለ የገንዘብና ቴክኖሎጂ አቅም አላቸው። በማደግ ላይ ያሉ አገራት በዚህ ረገድ ተጽዕኖውን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም ሰለሌላቸው ከፍተኛ ጉዳት ያጋጥማቸዋል። በዚህም ምክንያት አገራቱ በየዓመቱ በሚያካሂዱት የአየር ንብረት ለውጥ የባለድርሻ አካላት ጉባዔ (Conference of Parties, CoP) ላይ እየተገኙ ሊደረግላቸው
አድርጋ ነው። “የብሪክስ” ባንክ የሚባለው በአምስቱ የጥምረቱ አገራት በአንድ ዓመት የተለያዩ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ወጪ እንዲከናወኑ ማድረግ ችሏል። ስለዚህ “የብሪክስ” አባል መሆን ጥምረቱ ይዞት የሚመጣው ለአባል ሀገራቱ የሚሰጥ ማንኛውንም አይነት ጥቅም በሙሉ ይዞ የሚመጣ ነው። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ፍሰሐ ሻውል እንደሚሉት፤ ነባሩ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት እየተዳከመ በመሆኑ በዚህ ሽግግር ውስጥ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር የሚያግዛትን ማንኛውንም ዕድል ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለማግኘት አማራጭ የሰጠ ነው። አሁን ኢትዮጵያ “ብሪክስን” ስለተቀላቀለች በርካታ አገራት ለኢትዮጵያ ያላቸው አተያይ ከፍ እንደሚል አምባሳደሩ ይናገራሉ። “ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዘንድ ታዋቂ ከሆኑ አገራት ተርታ ትሰለፋለች፤ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ የነቃ ኢኮኖሚና ታታሪ ሕዝቦች ያሏት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ትዋሰናለች። ከኢትዮጵያ ጋር አጋር ለመሆን ለሚፈልጉ ሁሉ ትልቅ ዕድሎች ሊሆኑ ይችላሉ” ሲሉም ያክላሉ። ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ የርዕዮተ ዓለም ወይም የሕብረት መቀየር ሳይሆን፤ ብሔራዊ
ስለሚገባው ድጋፍ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጡን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያደርሱት አገራት የሚፈጽሙትን የበካይ ጋዝ ልቀት እንዲቀንሱ ይጠይቃሉ። በኮፕ ዓመታዊ ጉባኤዎች በማደግ ላይ ያሉ አገራትን ድምፅ በማሰማትና ተጽዕኖ በመፍጠር ረገድ ኢትዮጵያ የላቀ ሚና አላት። በቅርቡ በዱባይ በተካሄደው 28ኛው የኮፕ ጉባኤ በንቃት ተሳትፋ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን በማረጋገጥ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል እያደረገች ባለው ጥረት የተገኙ ተሞክሮዎችን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አካፍላለች። ይህን ተሞክሮዋን ለማስተዋወቅ ያዘጋጀችው ፓቪሊዮን ከፍተኛ እውቅና እና ምስጋና ተችሮታል። ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ማስመለስ ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች ለአንድ አገር ሕዝብ የማንነቱ መገለጫና ዘርፈ ብዙ ፋይዳ
አላቸው። እነዚህ ቅርሶች ለአውሮፓዊያንም ሆነ ለአፍሪካዊያን፣ ላደጉትም ሆነ በማደግ ላይ ላሉት ሕዝቦች ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጡ ናቸው። የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ የቅኝ ግዛታቸው አካል ለማድረግ ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢከሽፍም፤ ለቀን ቅዠት ቀቢፀ ተስፋቸው ስኬት ባደረጓቸው ሙከራዎች በተፈጠሩ አጋጣሚዎች እና ከዚያም በኋላ የተለያዩ ክፍተቶችን ተጠቅመው አያሌ ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች መዝረፋቸውን መረጃዎች ያስረዳሉ። የቅርስ ዘረፋው የተፈጸመው በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በቅኝ አስተዳደራቸው ስር በነበሩ አገራትም ጭምር ነው። አፍሪካዊያን የተዘረፉ ቅርሶቻቸውን ለማስመለስ እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረጉ ነው። ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ለመላቀቅ፤ ነፃነትና ሉዓላዊነታቸውን ለማወጅ ባካሄዱት እልህ አስጨራሽ መራራ ትግል ከከፈሉት መስዋዕትነት
ቀጥሎ ቅርሶቻቸውን የማስመለስ ትግላቸው ዋነኛው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ያም ሆኖ ግን የአብዛኞቹ ጥረት ባለሙትና ባሰቡት ልክ ስኬታማ ነው ለማለት አያስደፍርም። በአንጻሩ ኢትዮጵያ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተዘረፉ ቅርሶቿን ለማስመለስ ለዘመናት ባደረገችው ብርቱ ጥረት በተለያዩ ጊዜያት ንዋየ ቅድሳትንና ሌሎች ባሕላዊና ታሪካዊ ቅርሶቿን አስመልሳለች። በተለይ በ2000 ዓ.ም መገባደጃ ወደ እናት አገሩ ተመልሶ የተተከለው የአክሱም ሐውልት ይጠቀሳል። መንግሥት በተለያዩ አጋጣሚዎች የተዘረፉ የአገሪቱን ቅርሶች ከተቀመጡባቸው አገራት እንዲመለሱ ስኬታማ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ያገኛል። ለአብነትም በቅርቡ ወደ አገሯ የተመለሰችው “ፀሐይ” የተሰኘችውና እ.ኤ.አ 1935 በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የተሰራችውን አውሮፕላን ማንሳት ይቻላል። ፀሐይ በቅርቡ ለምረቃ በበቃው ኢትዮጵያዊያን
ጀግኖች አርበኞችን በሚዘክረውና የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት በሆነው በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በክብር ተቀምጣለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብሎም በዓለም የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ስመጥር የሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋም ባለቤት ነች። ከዚህ ጋር ተያይዞ “ፀሐይ” የተሰኘችው አውሮፕላን ወደ ባለቤቷ መመለስ ወቅቱ ከፈጠረው መነቃቃት ጋር ተያይዞ አሁንም ለቀጣዩ ትውልድ የመነቃቃት ተምሣሌት መሆኗ አይቀሬ ነው። ቅርሷ ከ80 ዓመታት ስደት በኋላ ወደ አገሯ እንድትመለስ በመንግሥት የተደረገው ብርቱ ጥረት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ድል ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የባሕር በር ስምምነት ኢትዮጵያ የታሪክ አጋጣሚ በፈጠረው ክስተት የባሕር በሯን አጥታ ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የባሕር በር ከሌላቸው አገራት አንዷ ሆናለች። በዚህም ገቢና ወጪ ምርትና ዕቃዎችን በጎረቤት አገራት ወደቦች በከፍተኛ ወጪ ስታጓጉዝ ቆይታለች። የአገሪቱ ኢኮኖሚ እያደገ የገቢና ወጪ ንግዷ ከጊዜ ወደ ጊዜ
በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ ለወደብ አገልግሎት ኪራይ የምታወጣው ወጪ በዚያው መጠን እየጨመረ መጥቷል። ከዚህም ባሻገር በቅርበት የምትገኝበት የቀይ ባሕር አካባቢ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድርባት ቢሆንም፤ በአካባቢው የባሕር በር ስለሌላት የቅርብ ሩቅ ተመልካች ብቻ ሆና ቆይታለች። ኢትዮጵያ ይህን ሁኔታ ለመለወጥ በተለያዩ አማራጮች ስታደርግ የቆየችው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እውን ሆኖ በቅርቡ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ የባሕር በር የማግኘት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርማ ለተፈጻሚነቱ በትጋት እየሰራች ትገኛለች። የመግባቢያ ስምምነቱ ዓላማ ኢትዮጵያ የትኛውንም አገር ሉዓላዊነት እና ዓለም አቀፍ ሕጎችን ሳትጥስ የራሷ የሆነ የባሕር በር በኪራይ መልክ በሰጥቶ መቀበል መርህ ማግኘት ነው። ከዚህም ባሻገር ስምምነቱ ኢትዮጵያ ስታካሂደው የቆየውን ቀጣናዊ ትስስር በማቀላጠፍ፣ አብሮ የመልማትና የማደግ ውጥኗን የሚያሳካ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ እመርታ ነው።
የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል አጋጥሞ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የኢንቨስትመንት ዘርፉ ተቀዛቅዞ ቆይቷል። በተለይ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት አጋር የሆኑ እንደ ቻይና ያሉ አገራት በወረርሽኙ መጠቃታቸው በተዘዋዋሪ መንገድ በዘርፉ ላይ የራሱን ጫና አሳድሯል። ስለዚህም ያለፉት ሁለት ዓመታት ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፈታኝ ጊዜዎች ነበሩ። በችግሩ ልክ ጠንካራ ሥራዎችን በቅንጅትና በትብብር በበለጠ ትጋት በመስራት ችግሮችን ተቋቁሞ በማለፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃዎች ያመለክታሉ። በ2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ 3 ነጥብ 31 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ያስመዘገበች ሲሆን፤ ይህም በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚዋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሳበች አገር አድርጓታል። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን ይዛለች። ይህም በብዙ ፈተና ውስጥ ጥሩ ውጤት መመዝገቡን የሚያሳይ ነው።
በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ የበጀት ዓመት 2 ነጥብ 95 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ታቅዶ 1 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ያህል የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ የተቻለ ሲሆን፤ ይህም የዕቅዱ 64 በመቶ እንደሆነ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ገልጿል። አፈጻጸሙ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ16 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለማምጣት ታቅዷል። በሰሜኑ የአገራችን ክፍል አጋጥሞ የነበረው ጦርነት በሰላም ስምምነት መቋጨቱ ለዘርፉ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እየጨመረ መጥቷል። ኢትዮጵያ አጋጥመዋት የነበሩ ተግዳሮቶችን ተቋቁማ በዘርፉ ያስመዘገበችው ውጤት ይበል የሚያሰኝ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። ለማክሮ ኢኮኖሚው ትልቅ አቅም እንደሚሆን የሚጠበቀው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተግዳሮቶችን እየተቋቋመ ተጨማሪ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚጠበቅበት በበጀት
ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ የዘርፎች ዕቅድ አፈፃፀም በተገመገመበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል። ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ከሚጠጋው ሕዝቧ አብዛኛው ወጣት ነው። ላለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ከአገሩ ርቆ ኑሮውን በተለያዩ አገራት ያደረገው ዜጋ ቁጥርም ከፍተኛ ነው። ይህ በተለያዩ የዓለም ከፍሎች ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከፊሉ በሕጋዊ፤ አብዛኛው ደግሞ በሕገወጥ መንገድ የወጣ ሲሆን በየደረሰበት አገርም ስፍር ቁጥር የሌለውን ችግር ሲጋፈጥ የኖረ ነው። በርካታ ዜጎች በዚህ ምክንያት ለእስር፣ ለግድያና ለሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተዳርገዋል። እንዲሁም በሕጋዊ መንገድ ከአገራቸው ወጥተው በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ወደ አገር ቤት ተመልሰው፤ በአገራቸው ሐብት ንብረት ለማፍራት፣ ቤተሰብ ለመጠየቅና በአገራቸው ልማት ላይ ለመሳተፍ በርካታ
ተግዳሮቶችን ሲጋፈጡ ኖረዋል። ይህም አገሪቱ በውጭ ለሚኖሩ ዜጎቿ መብትና ደህንነት መከበር የምታደርገውን ጥረት ደካማ ከማድረጉ ባሻገር በውጭ ከሚኖሩ ዜጎቿ ልታገኝ የምትችለውን ጥቅምም አሳጥቶ ወይንም አሳንሶት ቆይቷል። መንግሥት ይህን ሁኔታ ለመቀየር ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። ለአብነትም ቀደም ሲል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ይንቀሳቀስ የነበረው የዳያስፖራ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አሁን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በሚል ተቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ተቋም አንዱ ነው። ተቋሙ ባለፉት አምስት ዓመታት ካከናወናቸው ተግባራት መካከል በሕገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ አገራት ገብተው ይኖሩ የነበሩ፤ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉ በዋናነት የሚጠቀስ ነው። በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለአገራቸው የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እንዲያጎለብቱም አገልግሎቱ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ተመልሰው የወላጆቻቸውን አገር እንዲያውቁና እንዲያግዙ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት በርካታ የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ጎብኝተዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በዲፕሎማሲያዊ ጥረቷ ያሳካቻቸው ድሎች በርካቶች ናቸው። በሰሜኑ የአገራችን ክፍል አጋጥሞ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ አንዳንድ የምዕራቡ ዓለምና ዓለም አቀፍ ተቋማትን ጫና አክሽፋ የውስጥ ጉዳይዋን በሰላም ስምምነት የደመደመችበት፤ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ትኩረት የሳቡ ዲፕሎማሲያዊ ትግል የተካሄደባቸው እና በድል የተወጣቻቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና ሌሎች ተያያዥ ኹነቶችን መጥቀስ ይቻላል። በአጠቃላይ ያለፉት አገራዊ የለውጥ ዓመታት ያካሄደቻቸውን ፈታኝ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በአሸናፊነት የተወጣችባቸው ናቸው። ከውስጥም ከውጭም መንግሥትን በማዳከም አገር ለማፍረስ በሴራ የተቀናጁ ተልዕኮዎችን አክሽፋ፤ የኢትዮጵያን እውነት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቀው በማድረግ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳዎችን አምክና እና ያልተገቡ ጫናዎችን ተቋቁማ በድል የተሻገረችባቸው ናቸው ማለት ይቻላል።
ማህበራዊ
በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
ጠባቂነትን ታሪክ ያደረገው ቀበሌ
የንጹሕ ውኃ አቅርቦትን፣ የግልና የአካባቢ የንጽሕና አጠባበቅን በማሻሻል በዓመት በእነዚህ ለጤና መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ሳቢያ በሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ሊጎዱ የሚችሉ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል። ይሁን እንጂ ከዓለም ሕዝብ ግማሽ ያህል የሚሆኑት በቂ የንጹሕ ውኃ አቅርቦት እና የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ጉድለቶች አሉባቸው።
የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ጉድለት ለበርካታ ተላላፊ በሽታዎች ክስተትና ስርጭት መንስኤ እንደሚሆን እሙን ነው። ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን በቀላሉ መቆጣጠር የሚቻል ቢሆንም፤ በዕድገት ወደኋላ በቀሩ አገራት አሁንም የኅብረተሰብ ጤና ችግር ናቸው።
ኢትዮጵያ በግል እና በአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ጉድለት የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በርካታ ተግባራትን ስታከናውን ቆይታለች፤ በማከናወን ላይም ትገኛለች። ባለፉት ዓመታት በጤናው ዘርፍ የግልና የአካባቢ ንጽሕና (Hygiene and Sanitation) አጠባበቅ ፕሮግራምን በመተግበር አያሌ ተስፋ ሰጪና አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። የግልና የአካባቢ ንጽሕና የጤና አጠባበቅ ፕሮግራም ስር ሦስት ዋና ዋና ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች ተግባራዊ ማድረጓን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያሳያል። እነርሱም የከተማ የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ስትራቴጂ፣ የማኅረሰብና ትምህርት ቤት መር አጠቃላይ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የሳኒቴሽን ግብይት እና በጤናው ዘርፍ የአየር ንብረት
በመንገሻ ገ/ሚካኤል
ለውጥን የሚቋቋም ሥርዓት መዘርጋት ናቸው። በመርሃ ግብሩ በ500 ወረዳዎች የሳኒቴሽን ግብይት ማዕከላት ለማቋቋም ተወጥኖ በ370 ያህል ወረዳዎች ቢያንስ አንድ የሳኒቴሽን ግብይት ማዕከል ማቋቋም ተችሏል።
የሳኒቴሽን ግብይት ማዕከላት ያስፈለጉበት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ቤተሰቦች በራሳቸው አቅም የተሰራ የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚዎች ቢሆኑም መጸዳጃ ቤቶቹ የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ሊኖረው የሚገባውን ዝቅተኛ መስፈርት ያሟሉ ባለመሆናቸው ክፍተቱን ለመሙላት የሳኒቴሽን ግብይትን መጀመር/ ማስተዋወቅ በማስፈለጉ ብሔራዊ የሳኒቴሽን ግብይት መመሪያ እ.ኤ.አ በ2013 ሥራ ላይ ውሏል፡፡ ዓላማውም የሳኒቴሽን ግብይትን የአተገባበር፣ የክትትል እና ግምገማ ሥራዎች ወጥነት ባለው መንገድ ለማቀድና ለመተግበር፤ በአገሪቱ ለተሻሻለ የሃይጂንና ሳኒቴሽን ግብዓቶች የሚኖረውን ፍላጎትና አቅርቦት ለማሳደግ እንዲሁም ባለሀብቶች ሳኒቴሽንን እንደ ቢዝነስ ዘርፍ በመውሰድ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው፡፡
በግልና የአካባቢ ንጽሕና (Hygiene and San- itation) አጠባበቅ መርሃ ግብሩ በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች የታዩ ቢሆንም፤ አሁንም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ በርካታ ማነቆዎችም አሉ። ከማነቆዎቹ በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የሳኒቴሽን መገልገያዎች ሽፋን ዝቅተኛ መሆን፤ በቤተሰብ ደረጃ የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ትግበራ ደካማ መሆን፤ በግልና በአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ዙሪያ የማኅበረሰቡ አመለካከትና ባህሪ አለመዳበር፤ የንጽሕና አጠባበቅ ቁጥጥር ዝቅተኛ መሆን እና በዘርፎች መካከል የቅንጅታዊ አሰራር ውስን መሆን ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው።
የጤና ሚኒስቴር እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ መርሃ ግብር አውጥቶ ሰርቷል፤ እየሰራም ይገኛል። የግልና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብሩ የትኩረት አቅጣጫ የኅብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በሚወስኑ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ጤናን ማበልፀግ፣ በሽታን መከላከል እና የጤና አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል ነው። ይህ መርሃ ግብር በውስጡ ዘርፈ-ብዙ የአገልግሎት መስኮችን ያቀፈ ሲሆን፤ እነዚህም የተሟላና ደህንነቱ የተረጋጠ የንጽሕና (Sanitation) አጠባበቅ አገልግሎት፤ የግል ንጽሕና አጠባበቅ፤ የመጠጥ ውኃ ጥራትና ደህንነት፤ የምግብ
ሃይጂንና ደህንነት፤ የቤት ውስጥ አየር ብክለትን መቀነስ፤ ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን ማረጋገጥ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የጤና ሥርዓቱ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን መቋቋም የዚሁ አካል ሲሆን የውኃ፣ የሳኒቴሽን እና የሃይጂን (WASH) በጤና እና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ ዘርፎችን የተቀናጀ ድጋፍ የሚሹ ድንገተኛ ሁኔታዎችን ምላሽ መገንባትን ያካትታል።
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የግልና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብር አተገባበርና እንደ ሀገር የተገኘውን ውጤት በጥልቀት መዳሰስ አይደለም። ይልቁንም የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ያደረሰንን መረጃ የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ መርሃ ግብርን በአግባቡ
በመተግበር የተሻለ ተሞክሮ ያለውንና ለሌሎች አካባቢዎችም ዓርአያ ሊሆን የሚችልን የአንድ ቀበሌ መልካም ተሞክሮ በአጭሩ በመዳሰስ ለውድ ተደራሲያን ማቋደስ ነው።
የመልካም ተምሳሌት አርዓያ የሆነው ይህ ቀበሌ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደወላቡ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ 22 ቀበሌዎች አንዱ የሆነው ካራ ቆሬ ነው። የቀበሌው ማኅበረሰብ በንጹሕ ውኃ አቅርቦት እጥረት፣ በግልና በአካባቢ ንጽሕና ጉድለት ሳቢያ ያጋጥሙት የነበሩትን የጤና ችግሮች በማስወገዱ ሂደት የማንም አካል ጠባቂ ሳይሆን፤ የችግሩ መንስኤም የመፍትሔውም ቁልፍ አካል ሆኖ በትጋት በመስራቱ ከችግሩ ተላቋል። የካራ ቆሬ ቀበሌ 2ሺህ 300 አባና እማወራዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በግልና በአካባቢ ንጽሕና ጉድለት ሳቢያ ያጋጥሟቸው ከነበሩ ተላላፊ በሽታዎች ነፃ ሆነው የሚኖሩበት
ነው።
የጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት መረጃ እንደሚያመለክተው ከዚህ ቀደም በቀበሌው የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ በሚፈለገው ደረጃ ስላልነበረ ነዋሪዎቹ በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ሲቸገሩ ቆይተዋል። የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ጤናማ አምራች ማኅበረሰብ ከመፍጠር አኳያ ያለውን ሁለንተናዊ ፋይዳ በተሰጣቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመረዳታቸው ይህን የጤናውን ዘርፍ መርሃ ግብር በተገነዘቡት ልክ በመተግበራቸው ውጤታማ መሆን ችለዋል። አንዳንድ የቀበሌው ነዋሪዎች ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ለጤና ችግር መዳረጋቸውን፤ በዚህም ለከፍተኛ የሕክምና ወጪ ሲዳረጉ እንደነበር፤ ከዚህም ባሻገር lልማት ያውሉት የነበረውን ጊዜና ጉልበት ሕክምና ለማግኘት በውጣ ውረድ
ያባክኑት እንደነበር አስተያየት መስጠታቸውን ጭምር ነው።
የግልና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብርን ከመተግበራቸው በፊት የጤናቸው ሁኔታ አስቸጋሪ እንደነበረ ነዋሪዎቹ ማንሳታቸውን መረጃው ያክላል። የተለያዩ የጤና ችግሮች ሲያጋጥሟቸው የነበረው ከግልና ከአካባቢ ንጽሕና ጉድለት የተነሳ መሆኑን ዘግይተው መረዳታቸውንም አስተያየት ሰጪዎቹ መግለጻቸውን ያትታል። ነዋሪዎቹ አያይዘውም በአካባቢያቸው መፀዳጃ ቤትን የመጠቀም ልምዳቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ሜዳ ላይ የመፀዳዳት ልምድ በስፋት ይስተዋል እንደነበርና በዚህም ምክንያት ለአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) እና ኮሌራን ለመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች በተደጋጋሚ ሲጋለጥ መቆየቱን ይናገራሉ፤ ይላል የዳይሬክቶሬቱ መረጃ።
ከዚህም ባሻገር በአካባቢው የነበረው ልምድ ለቤት እንስሳት የተለየ ቤት ስለማይሰራ እንስሳቱ ከሰው ጋር በአንድ ላይ ያድሩ እንደነበር ነዋሪዎቹ አስታውሰው፤ ይህም የግልና የመኖሪያ አካባቢን ንጽሕና የመጠበቅ ሁኔታን በእጅጉ አስቸጋሪ አድርጎት መቆየቱን፣ በግንዛቤ ማነስ ሳቢያ በየደጃፋቸው እንዳሻቸው ያስወግዱት የነበረው የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻም ለአካባቢው ንጽሕና መጓደል ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ክስተትና ስርጭት ምክንያት ማኅበረሰቡ በቀላሉ ለጤና ችግር ተጋላጭ ሆኖ መቆየቱን ማስረዳታቸውን መረጃው አመላክቷል።
በግልና በአካባቢ ጤና አጠባበቅ መርሃ ግብሩ በቀበሌው የግልና የአካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ሥርዓት አለመጎልበቱ ማኅበረሰቡን ለከፋ የጤና ችግር እየዳረገው መሆኑን በእጅጉ ያሳሰባቸው በቀበሌው የተመደቡ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በተለይ መፀዳጃ ቤት አዘጋጅተው የማይጠቀሙ እማና አባወራዎችን ለይተው ሰርተው እንዲጠቀሙ እና ኅብረተሰቡ የሰውና የእንስሳት ቤቶችን ለይተው እንዲሰሩ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በማከናወን በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚፈለገውን ግንዛቤ መፍጠር ችለዋል ይላል።
መረጃው እንደሚያመለክተው ባለሙያዎቹ በቅድሚያ የሴቶች የልማት ቡድን አደረጃጀትን በመጠቀም 60 ግንባር ቀደም እማወራዎችን/ እናቶችን በመመልመል ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ሰጧቸው። ከቀበሌው አመራሮች ጋር በችግሩ ዙሪያ
በግልፅ በመነጋገርና በመምከር ቀበሌውን ከአይነ-ምድር ነፃ ለማድረግ ለኅብረተሰቡ ስልጠናዎችን በመስጠት ቀጣይ ስራዎችን በቅንጅት መስራትም ተጀመረ። ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ከወረዳው ጤና ጽሕፈት ቤት እና በአቅራቢያ ከሚገኘው ጤና ጣቢያ ጋር በመሆን ግንዛቤውን ለሁሉም የማስረጹን ሥራ ተቀናጅተው በትጋት የመተግበሩ ሥራ ተጠናክሮ ቀጠለ። በቀበሌው አንድ የልማት ቡድን በማደራጀት ዋና ትኩረታቸውን የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስልቶች እና የተሻለ የመፀዳጃ ቤት አዘገጃጀት ላይ ያደረጉ ተግባር ተኮር የግንዛቤ ማበልፀጊያ ስልጠናዎች ተሰጣቸው።
የግልና የአካባቢ ንጽሕናን በተገቢው መንገድ መጠበቅ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች ለመከላከልና መጠበቅ
መሆኑን ከስልጠናው በሚገባ መገንዘብ የቻሉት የቡድኑ አባላት የአካባቢያቸው ነዋሪዎች መፀዳጃ ቤቶችን፣ የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ጉድጓዶችን አዘጋጅተውና የሰውና የእንስሳት ማደሪያን ለይተው በመስራት የግልና የአካባቢያቸውን ንጽሕና በመጠበቅ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከንጽሕና ጉድለት ከሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ መከላከልና መጠበቅ መቻላቸውንም መረጃው አመላክቷል።
ከዚህም ባሻገር መፀዳጃ ቤት፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ጉድጓዶች ያላዘጋጁ እማና አባወራዎችን በማነሳሳት፣ በማነቃቃትና በመደገፍ አዘጋጅተው እንዲጠቀሙ በማድረግ የጤና ባለሙያዎችን ትምህርትና ምክር ወደ ተግባር መቀየራቸው ለጤናቸው እጅግ ጠቃሚ ሆኖ ያገኙት ስለመሆኑ ነዋሪዎቹ ምስክር መሆናቸውንም አክሏል።
እንደመረጃው ጥንቅር የካራ ቆሬ ቀበሌ ነዋሪዎች ሌላም መልካም ተሞክሮ አላቸው፤ ለአካባቢው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የመኖሪያ ቤት ገንብተዋል፤ የሚገለገሉበትን የጤና ኬላም በአጥር ከልለዋል። ነዋሪዎቹ በራስ ተነሳሽነት እነዚህን ተግባራት ያከናወኑት የቀበሌው የሴቶች ልማት ቡድን አደረጃጀቶች በጊዜ ሂደት በቁጠባ ባጠራቀሙት ገንዘብ ነው።
ይህም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎቹ ይኖሩበት የነበረው ከተማ ከካራ ቆሬ ቀበሌ ራቅ ያለ ከመሆኑም ባሻገር በአካባቢው በሚስተዋለው የትራንስፖርት ችግር የተነሳ ድንገተኛ የጤና እክል ሲያጋጥማቸው ባለሙያዎቹን ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ የቆየውን ችግርና ‘ድንገተኛ የጤና ችግር ቢከሰት ምን እንሆናለን’ የሚለውን ስጋታቸውን ማስወገድ አስችሏል።
እንደ ጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት መረጃ የኤክስቴንሽን ባለሙያዎቹም የመኖሪያ ቤት ችግራቸው ስለተቃለለላቸውና በጉዞ የሚያባክኑትን ጊዜ ለስራ ማዋል በመቻላቻው
ለቀበሌው ኅብረተሰብ መስጠት የሚገባቸውን አገልግሎት በአግባቡ እየሰጡ ነው።
እናም ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ በግልና በአካባቢ ንጽሕና ጉድለት ሳቢያ ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ጊዜ የኮሌራ ወረርሽኝ ይከሰትበት የነበረው የመደ ወላቡ ወረዳ በግልና አካባቢ ንጽሕና አጠባበቅ ስራ ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ተሸላሚ ሆኗል ይላል መረጃው።
የሴቶች የልማት አደረጃጀት እና በየደረጃው የሚገኘው የመንግሥት መዋቅር በአካባቢው ለተገኘው አመርቂ ውጤት ግንባር ቀደም ሚና እንደነበራቸው የዞኑና የወረዳው ጤና አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ሲልም ያክላል።
የዞኑና የወረዳው ጤና ጽሕፈት ቤቶች በመደወላቡ ወረዳ የተገኘውን ውጤታማ ተሞክሮ ወደ ሌሎች ወረዳዎችና አካባቢዎች፤ ወረዳው ደግሞ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ለማስፋት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የካራ ቆሬ ቀበሌ የጤናው ዘርፍ ተሞክሮ በዋናነት ኅብረተሰቡ ለችግሩ መፍትሔ ከሌላ አካል ከመጠበቅ ይልቅ ራሱ የችግሩ መንስኤም፤ የመፍትሔውም አካል መሆኑን ተገንዝቦ ከጠባቂነት ተላቆ በባለቤትነት ስሜት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ያስቻለ ነው። እንዲሁም በመንግሥት መዋቅር በተዋረድ ቅንጅታዊ ስራን በማጠናከር ለተጨባጭ ውጤት የበቃበት ጥረት የሚደነቅና ለሌሎች በዓርአያነት የሚጠቀስ ተምሳሌት ነው። በመሆኑም ይህን መልካም ተሞክሮ ወደሌሎቹ የሀገሪቱ ክፍሎች በማስረፅና በመተግበር ከግልና ከአካባቢ ንጽሕና ጉድለት ከሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ኅብረተሰቡን ለመከላከልና ለመጠበቅ እንዲሁም በሽታን አስቀድሞ በመከላከል ጤናማ አምራች ዜጋ የማፍራቱ ተግባር ለመንግሥት ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ጉዳይ በመሆኑ መልካም ተሞክሮን አስርጾ ለመተግበር ለተጀመረው ቅንጅታዊ ጥረት ስኬት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ የግድ ይላል።
ማህበራዊ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
በፍቅርተ ባልቻ የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማገልገል 80 ዓመታትን ሊያስቆጥር ተቃርቧል፡፡ የሕክምና አገልግሎት እና የነርሲንግ ትምህርት ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ ተቋም ከኢትዮጵያ ሚሊኒየም መባቻ ጀምሮ በአዲስ ምዕራፍ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር ሲሰጥ የነበረውን የነርሲንግ ትምህርት ወደ ሁለተኛ ዲግሪ እና በሕክምና ስፔሻላይዜሽን እና ሰብ ስፔሻሊቲ እና የፒ.ኤች.ዲ ትምህርት እየሰጠ ነው፡፡ በየጊዜው አገልግሎቱን እያዘመነና ወደፊትም ወደ ውጭ አገር ሄደው የሚታከሙ ኢትዮጵያውያን በኮሌጁ እንዲታከሙ ለማድረግ ከወዲሁ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ከኮሌጁ የትምህርት ክፍሎች መካከል ‘የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጉሮሮ፣ የአንገት፣ የራስ ቅል ሕክምና ትምህርት ክፍል በመማር ማስተማርና በሕክምና አገልግሎቱ የደረሰበትን ደረጃ እንመለከታለን፡፡ ለዚህም ከትምህርት ክፍሉ ባለሙያዎች ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ጅማሬው የጆሮ፣ የአፍንጫና የጉሮሮ ሕክምና በአገር ውስጥ በሙያው የሰለጠና ባለሙያ ስላልነበረ የተለያዩ ባለሙያዎች ከውጭ አገራት እየመጡ የሕክምና አገልግሎቱን ይሰጡ ነበር፡፡ “በ1960ዎቹ አካባቢ በቻይናውያን ባለሙያዎች እንደተጀመረ፤ ከእነርሱ ቀጥሎ በጀርመኖች እንዲሁም በቡልጋሪያውያን
ባለሙያዎች ሕክምናውን ይሰጥ እንደነበር በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የጆሮ፣ አፍንጫና ጉሮሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና መምህር ዶ/ር አለነ መሸሻ ያስረዳሉ። በሌላ በኩል በ1980 ዓ.ም መጀመሪያ አካባቢ ኩባ አገር ተምረው የመጡ ሐኪሞች ሆስፒታሉን ተቀላቅለው አገልግሎት ይሰጡ የነበረ ሲሆን፤ የሕክምና መሰጫ ቦታና የሕክምና ግብዓት ችግሮች ስለነበሩ አገልግሎቱ በተመላላሽ ሕክምና ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር ፡፡ 1983 ዓ.ም በኮሌጁ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ስፔሻሊስት የሕክምና አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ወቅት ነው፡፡ በመስኩ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ዳመኑ ዘለቀ ይባለሉ፡፡ ከእርሳቸው በኋላ ሌላው ኢትዮጵያዊ ዶክተር መሰለ ግዛው የሕከምና አገልግሎቱን እየሰጡ ቆይተዋል። ዶ/ር አለነ ሆስፒታሉን በ2006 ዓ.ም ሲቀላቀሉ ሦስተኛው ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው። ትርጓሜ በተለምዶ አጠራሩ ‘ከአንገት በላይ ሕክምና‘ ይባል እንጂ ትክክለኛ ስያሜው ‘የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጉሮሮ፣ የአንገት፣ የራስ ቅል ሕክምና ትምህርት ክፍል‘ ይሰኛል። ስያሜውን ለማሳጠር ”ከአንገት በላይ” ይባላል፡፡ የጆሮ፣ የአፍንጫና የጉሮሮ እንደ ሳይነስ ያሉ በሽታዎችን አንገትና የራስ ቅልን ያጠቃልላል፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት የጥርስ፣ የዓይን፣ የሥነ አዕምሮ ሕክምና የራሳቸው ስፔሻሊስት እንዳላቸውና በተለምዶ ከአንገት በላይ ከሚባለው ይለያል። ይህ ማለት የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጉሮሮ፣ የአንገትና የራስ ሕክምና፤ የጥርስ፣ የዓይን፣ የመንጋጭላ፣ የአንጎል እና የአዕምሮ ሕክምናዎችን ያካተተ አይደለም። እነዚህ ሕክምናዎች ከሆስፒታሉ ምስረታ ጋር የተጀመሩ እና በሂደት እያደጉ የመጡ ስለመሆኑ የተቋሙ ታሪክ ያስረዳል። አዲስ ምዕራፍ! ”ከሚሊኒየሙ በፊት እንደ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶ፣ የማስተማሪያ ሆስፒታል ሲሆን እየተስፋፉ የመጡ አገልግሎቶች አሉ። በእኛም የትምህርት ዘርፍ ተመሳሳይ ለውጦች መጥተዋል፡፡ ለአብነትም የባለሙያዎች ቁጥር ጨምሯል፣ ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎች ተደራጅተዋል፣ የትምህርት ክፍሉ አገልግሎት የሚሰጥበት የሕክምና መስጫ ክፍል ተስፋፍቷል፡፡ ለሕሙማን የሚሰጠው አገልግሎት
በብዛትም ሆነ በዓይነት ጨምሯል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም ችግር ፈቺ ጥናቶችም ይካሄዳሉ ይላሉ ዶ/ር አለነ፡፡ አገልግሎቱ እየተሻሻለ በመምጣት ከሚሰጠው ሕክምና በተጨማሪ በ2001 ዓ.ም ወደ ኮሌጅ ተሸጋግሮ የቅድመ ምረቃ ሥርዓተ ትምህርት ቀርፆ ትምህርት መስጠት ጀመረ፤ በመቀጠልም በ2007 ዓ.ም የድህረ ምረቃ ትምህርት መስጠት ጀምሮ አሁን ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ሆስፒታሉ ኮሌጅ ሲሆን ቀደም ሲል የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ሲሰጥ የቆየው ክፍል ራሱን ችሎ የትምህርት ክፍል ሆኖ ተቋቋመ። አገልግሎት እየሰጠ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን እያስተማረ ከቆየ በኋላ በ2008 ዓ.ም የድህረ ምረቃ ትምህርት መስጠት ጀመረ። በተቋሙም ሆነ በስራ ክፍሉ መሰረታዊ ለውጥ የመጣውና ፈጣን ዕድገት የተገኘው ከሚሊኒየሙ (2000 ዓ.ም) በኋላ እንደሆነ ይነገርለታል። ዕድገት እና አሁናዊ ቁመና ቀለል ያሉ የቀዶ ሕክምናን ያላካተቱ፤ በተገኙት የሕክምና መሳሪያዎች ሊሰሩ የሚችሉ አገልግሎቶች ሲሰጡ እንደነበር የሚያስታውሱት
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአፍንጫ፣ ጆሮ፣ ጉሮሮ፣ አንገትና የራስ ቅል ቀዶ ሕክምና ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ሣምሶን ድረስ ናቸው። ኃላፊው የስራ ክፍሉ የራሱ የሆነ ተመላላሽና የቀዶ ሕክምና የሚሰጥበት አስተኝቶ የሚያክምበት ቦታ እንኳ እንዳልነበረው ያስታውሳሉ። በዚህ ረገድ ትልቅ ለውጥ የተመዘገበበት ጊዜ የድህረ ምረቃ ትምህርት ከተጀመረ በኋላ እንደሆነም ይጠቅሳሉ። ከተቋሙ ጋር በአጋርነት የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ባደረጉት እገዛና ድጋፍ የተለያዩ ግብዓቶችን ማግኘት እንደተቻለ፤ ሌሎች የዓለም አገራት የሚጠቀሟቸውን መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የቀዶ ሕክምና እና ተያያዥ ሕክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም ዘመኑ ያፈራቸው የሕክምና መሳሪያዎች እንደ ማይክሮስኮፕ እና ኢንዶስኮፕ ያሉት በግዥ እንዲሟሉ መደረጉን ዶ/ር ሣምሶን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የሕክምና መሣሪያ አቅርቦቱና ቴክኖሎጂው በሚፈቅደው መጠን የጆሮ፣ የአፍንጫና የጉሮሮ ሕክምናዎችን ለመስጠት፤ ቀዶ ጥገናዎችን ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት አገልግሎቶቹ በቴክኖሎጂ
በመታገዝ በዓይነትም በብዛትም እየሰፉና እያደጉ ስለመምጣታቸው ነው ባለሙያዎቹ ምስክርነታቸውን የሚሰጡት። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአፍንጫ፣ ጆሮ፣ ጉሮሮ … ሕክምናዎች በአገራችን የዘመነ ሕክምና የሚሰጥበት ማዕከል መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ለአብነትም የትምህርት ክፍሉ በዘመናይ የሕክምና መሳሪያዎች መደራጀቱ፣ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የነርቭ፣ የመስማት ችግር ላለባቸው ሕሙማን በውስጠኛው የጆሮ ክፍል (ኮኪሊያ) ውስጥ የሚቀበር ማዳመጫ (cochlear implant) ሕክምና ቁጥራቸው ስድስት ለሚሆን ኢትዮጵያዊያን በተሳካ ሁኔታ አካሄዷል፡፡ ይህም የኮሌጁ ትልቅ እመርታ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የጆሮ እና የጆሮ ነርቭ ቀዶ ሕክምና (Otology –Nvetology unit) ተቋቁሟል፡፡ ይህም ክፍል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ በኢንዲስኮፒ የታገዘ የጆሮ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉም የትምህርት ክፍሉ ሌላው ስኬት ነው፡ ፡ በሕክምና ክፍሉ በስድስት ስፔሻሊስት ሐኪሞች እና በአምስት ነርሶች አማካኝነት
የተመላላሽ፣ የድንገተኛ፣ የአስተኝቶ ማከም እንዲሁም የተለያዩ ቀላልና ከባድ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን ዶ/ር ሳምሶን ያስረዳሉ፡፡ ”የጆሮ ምርመራና የድጋፍ መሳሪያዎችን የመግጠም አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር የሕክምና ኮሌጅ ላይ ሐኪምም ሆኖ ማስተማርም ይጠይቃል። በትምህርት ክፍሉ ያሉት ስድስት ስፔሻሊስት ሐኪሞች ለሕሙማን የሕክምና አገልግሎት ይሰጣሉ፤ ተማሪዎችንም ያስተምራሉ፡፡ ይህ ደሞ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆኖ ላለፉት 10 ዓመታት ዘልቋል፡፡ በኮሌጁ ባለሙያዎችን ለማፍራት በተሰራው ስራ በሕክምና ዘርፉ እስከ አሁን 20 ስፔሻሊስት ሐኪሞችን አስተምሮ አስመርቋል። እነዚህም በአምስት ዙር የአራት ዓመት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው። ሌሎች 12 ባለሙያዎችም በሥልጠና ላይ ይገኛሉ። እንደ ዶክተር ሣምሶን ገለጻ፤ የጆሮ፣ የአፍንጫና የጉሮሮ ሕክምና ተደራሽነት እንደ አገር በጣም ውስን ነው። በአጠቃላይ አገር ውስጥ የሚገኙ ስፔሻሊስቶች ቁጥር ከመቶ በታች ሲሆን ከእነዚህም አብዛኞቹ አዲስ አበባ ነው የሚገኙት። ”ባለፈው ዓመት ከአስራ ስድስት ሺህ በላይ
ታካሚዎችን አስተናግደናል። ከ1 ሺህ 400 በላይ ቀዶ ሕክምናዎችን ሰርተናል። በአንድ ሣምንት ውስጥ በአማካይ እስከ 400 ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። እየሰጠን ያለነው አገልግሎት ሰፊ ነው። ከጆሮ ምርመራ በተጨማሪም በአንድ ዓመት ውስጥ እስከ ሁለት ሺህ ለሚጠጉ ሕሙማን ምርመራ እናደርጋለን” ሲሉ ያለውን የስራ ጫና ይገልጻሉ፡፡ በኮሌጁ ከጨቅላ ሕፃናት ጀምሮ እስከ አዋቂ ድረስ የጆሮ ምርመራ ይደረጋል። ይህም እንደ አገር ውስንና በጥቂት ሆስፒታሎች ብቻ የሚሰጥ ስለመሆኑ ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት። አገር አቀፍ ጥናት በአገር አቀፍ ደረጃ የጆሮ የመስማት ችግር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ጫናውን የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት (National based popu- lation survey) ተሰርቶ ለጤና ሚኒስቴር መላኩንና ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ሣምሶን፤ የዳሰሳ ጥናቱ ብዙ ወጪ፣ ጊዜና አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ አፍሪካ ውስጥ ከአንድና ከሁለት አገራት በላይ ሊኖር እንደማይችል ጠቅሰዋል። ይህ ጥናት በኢትዮጵያ ያለው የመስማት ችግር አጠቃላይ መረጃዎች ተተንትነው የቀረቡበትና እንደ አገር ለሚዘጋጁ ፖሊሲዎች ግብዓት የሚሆን መረጃ እንደሚሰጥ ታምኖበታል። ኮሌጁ የዓለም የመስማት ቀን (የዓለም የጆሮ ጤና ቀን - march 3)ን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በየዓመቱ ያከብራል። የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፣ የአካል ጉዳት ያባቸው፣
መስማት የተሳናቸው፣ ማኅበራትና ሌሎችም የሚታደሙበት ሁነት በመሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች ይሰጣሉ። በዚህ ሁነት የተለያዩ መልዕክቶችን በዲጂታል፣ በሕትመት እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው። በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ድጋፍ ተደራሽነት ለማይኖራቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችና ወደ ክልሎች የሕክምና ቡድኖችን በመላክ ሕክምናው እየተሰጠ ነው። ለአብነት በቡታጅራ ከተማ የተሰጠው የሕክምና አገልግሎት ይጠቀሳል። ባለሙያዎች ወደ ቡታጅራ በመጓዝ የምርመራ እና የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሰጥተዋል። በተጨማሪም በትምህርት ተቋማት፣ በጤና ጣቢያዎች፣ ወዘተ … በመገኘት በተለይ የመስማት ችግር ልየታ በማድረግ ለማኀበረሰቡ በቅርበት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል። ውጣ ውረዶች እና ውጥን የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጉሮሮ፣ የአንገት፣ የራስ ቅል ሕክምና እና ትምህርት ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ሲል የተመላከቱትን ዋና ዋና ለውጦች በማድረግ አገልግሎቶቹን በዓይነትም፣ በተደራሽነትም በማስፋፋት በርካታ አበረታች ውጤቶች መገኘታቸው እሙን ነው። ከእነዚህ ስኬቶች ጀርባ በርካታ ውጣውረዶች መኖራቸው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ እና ኢኮኖሚያቸው በማደግ ላይ ለሚገኝ አገራት እንግዳ አይሆንም። በስራ ክፍሉ አንዱ ተግዳሮት የሕክምና ባለሙያዎችና የታካሚዎች ቁጥር አለመመጣጠን ነው። ዶክተር ሣምሶን ”ቀጠሮ
ተይዞላቸው የሚጠብቁ የሕፃናት ቀዶ ሕክምና ወረፋ ከዚህ በፊት ከነበረው የቀነሰ ቢሆንም አሁንም ከስድስት ሳምንት እስከ ሁለት ወር ድረስ ይጠብቃሉ። የካንሰር ሕክምና፣ የአፍንጫና ሳይነስ ቀዶ ሕክምና ከሆነ ከአንድ ወር አይበልጥም፤ በአንጻሩ የጆሮ ሕክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ብቸኛ ተቋም በመሆኑ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ያስጠብቃል። እኛ በቀን ለአምስትና ለስድስት ሕሙማን ሕክምናውን ስንሰጥ እስከ 30 ሰው ሕክምና ለማግኘት ይመዘገባል። የጆሮ ሕክምና ጫናው በጣም ከፍተኛ ነው፣ አገልግሎቱ ቢሰፋ ጫናው አይፈጠርም። ትልቁ ችግር የባለሙያ እጥረት ነው። ካለው ታካሚ አንጻር የስፔሻሊስትና የሰብ ስፔሻሊስቶች ቁጥር አነስተኛ ነው። ጥራትንም ለመጨመር የሰው ኃይል ያስፈልገናል። ይህ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ ነው” ብለዋል። የታካሚዎች ብዛት ከፍተኛ የሆነበት አንደኛው ምክንያት ሕክምናው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሚሰጥ መሆኑ ሲሆን ሌላው ምክንያት በተሻለ አገልግሎቱ ተመራጭ በመሆኑ ነው የሚሉት የሕክምና ክፍሉ ባለሙያዎች ለሚያጋጥሙ ችግሮች ጊዜያዊ መፍትሔ በመስጠት ስራቸውን እያከናወኑ ስለመሆኑ ነው የሚገልጹት። እንደማሳያም በዘርፉ ያለው ባለሙያ ውስን ስለሆነ አሁን ያሉት ባለሙያዎች መሰረታዊ እውቀት እንዲኖራቸው ለማስቻል እገዛ መደረጉን ጠቅሰዋል። የባለሙያ አያያዝ ችግር መኖሩን የሚገልጹት የመስኩ ባለሙያዎች፤ እስከ አሁን ሃያ ስፔሻሊስቶችን አሰልጥኖ ያስመረቀ ቢሆንም
በኮሌጁ በዘመናዊ መሣሪያዎች በመጠቀም ጥሩ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ሌላ የሕክምና ተቋማትን ሲቀላቀሉ እነዚህን ዘመናዊ የሕክምና መሣሪዎችና ግብዓቶች ስለማያገኙ እና በቀሰሙት ትምህርት ልክ ለመስራት ሁኔታዎች ስለማይፈቅዱላቸው ወደ ውጭ አገራት የመሄድ ዝንባሌዎች ይስተዋላሉ ይላሉ። ይህ እንደ አገር የሚያስከትለው ጉዳት ቀላል ስላልሆነ የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ ቢያበጅ መልካም ነው። ሌላው ተጠቃሽ ችግር የሕክምና መስጫ ቦታ ጥበት ነው፤ ይህ ችግር ከግንባታ መዘግየት ጋር የተያያዘ ሲሆን ኮሌጁ እያስገነባው ያለው ሕንጻ ሲጠናቀቅ መፍትሔ እንደሚያገኝ ይጠበቃል። የሕክምና ክፍሉ አላቂ እቃዎችን በአብዛኛው የሚያገኘው በበጎ አድራጊዎች ፈቃድ ሲሆን ድጋፉ ሲቋረጥ አገልግሎቱም ችግር ይገጥመዋል። ስለሆነም መንግሥት አላቂ ዕቃዎችን በቋሚነት ቢያቀርብ ተያይዞ የሚነሳውን ችግር ማቃለል ይቻላል።
ዶክተር አለነ ሌላው ማነቆ ሲሉ የገለጹት የሕክምና መሣሪያዎች ጥገና ነው፤ ትላልቅና ዋጋቸው ውድ የሆኑ ዕቃዎች ይገዛሉ፤ ብልሽት ሲያጋጥማቸው አይጠገኑም። ለዚህም በቁ የጥገና ባለሙያ እንዲኖር ቢሰራ አገልግሎቱን ያለመቆራረጥ ማስቀጠል ይቻላል። የአዳዲስ እና የዘመናዊ መሣሪያዎች ግዥ ሲፈጸም ጎን ለጎን ወይም ብልሽት ከማጋጠሙ በፊት የጥገና ባለሙያ ማብቃት (ማሰልጠን) ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። የትምህርት ክፍሉ በቀዳሚነት ከተጀመሩ የጤና አገልግሎቶች አንዱ ቢሆንም ዕድገቱ በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን ያነሱት ዶክተር አለነ በባለሙያ ቁጥር፣ በግብዓት አቅርቦት ከሚሰጠው አገልግሎት አንጻር ተገቢውን ትኩረት ያላገኘ ነው ይላሉ። በዚህ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስፔሻሊስቶችን ማምረት ከባድ ሆኖ መቆየቱን፤ አሁንም በመንግሥት እና በባለድርሻ አካላት በቂ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።
ማጠቃለያ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ቀጣይ ዓላማው የሕክምና ዩኒቨርሲቲ መሆን ነው። የአፍንጫ፣ የጆሮ፣ የጉሮሮ፣ የአንገት፣ የራስ ቅል ሕክምና እና ትምህርት ክፍልም ይህን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። ”ከስምንት ዓመት በፊት የተቋሙ አመራሮች፣ መንግሥትና አጋር አካላት በቅንጅት ውጤታማ ሥራ ሰርተው ለውጥ እንደተገኘው ሁሉ ቀጣይ ዓላማችን የልህቀት ማዕከል መገንባት በመሆኑ ይህንን ለማሳካት የምንተጋ ይሆናል። ያሉትን ክፍተቶች እየሞላን፣ የትምህርት ጥራቱን እያሻሻልን፣ አገልግሎቱም እየሰፋ እና ተደራሽነቱ እያደገ፣ ችግር ፈቺ ጥናቶችንም እየሰራን የተያዘውን ዓላማ እናሳካለን” ሲሉ ዶክተር ሣምሶን አስተያየታቸውን ቋጭተዋል።
ኢኮኖሚ
በርካቶች የሚመኙት ባለ ራዕዮች የሚጎናጸፉት
በገዛኸኝ ዳንጉል
መንደርደሪያ መቀመጫውን በኢጣሊያ መዲና ሮም ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ኤጀንሲ የ79 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ነው። ኤጀንሲው በመላው ዓለም ረሃብን ለማጥፋት፣ የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትን ለማሻሻል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ይመራል። ለዚሁ ዓላማ እ.ኤ.አ ጥቅምት 16 ቀን 1945 የተቋቋመው ይኸው ልዩ ኤጀንሲ የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (The Food and Agriculture of the United Nations (FAO) ነው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 176 የዓለም አገራትን በአባልነት አሰባስቦ የያዘው የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት፤ መንግሥታት እና የልማት ድርጅቶች የግብርና፣ የደን፣ የዓሣ፣ የመሬት እና የውሃ ሐብቶችን የማሻሻል እና የማልማት ተግባራቸውን አስተባብረው እንዲተገብሩ ይደግፋል። የምርምር ስራዎችን ያከናውናል፤ ለፕሮጀክቶች የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል። የትምህርትና የሥልጠና መርሃ-ግብሮችን ይተገብራል። የግብርና ምርት፣ የምርትና የልማት መረጃዎችንም ያሰባስባል። እንደ መረጃዎቹ ማብራሪያ የድርጅቱ አባል አገራት ሦስት አበይት ዓላማዎችን ለማሳካት ቃልኪዳን ገብተዋል። ዓላማዎቹ የሕዝቦቻቸውን ሥርዓተ ምግብና የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የሁሉንም የአመጋገብ
ባለ ራዕዮች የሚጎናጸፉት
ደረጃዎች፣ የግብርና ምርትና ስርጭትን ማሳደግ እና በገጠር የሚኖረውን ሕዝብ የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ናቸው። የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት በመደበኛ መርሃ ግብሩ አባል አገራቱ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት አከናውነው ስኬታማ መሆን እንዲችሉ የፖሊሲ እና የቴክኒክ ምክረ ሃሳብ ይሰጣል። በመስክ መርሃ ግብሩ አገራቱ የገጠር ልማትን ለማስፋፋት፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የመሬትና የውሃ አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ የደን እና የዓሣ ሀብት አጠቃቀምን ለማሳደግ የሚያደርጉት ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ያደርጋል። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ድርጅቱ (FAO) በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሰረት ለአባል አገራት የሕዝቦቻቸውን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ ስለሚያደርገው ድጋፍ ማስረዳት አይደለም። ይልቁንም ድርጅቱ ባለፈው ጥር መገባደጃ ባካሄደው የዕውቅና አሰጣጥ መድረክ ኢትዮጵያ በመሪዋ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራር የተጎናፀፈችውን ታላቅ ክብርና ሞገስ በአጭሩ መዳሰስ እንጂ። የፋኦ የከበረ አግሪኮላ ሜዳሊያ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም በኢጣሊያ ዋና ከተማ ሮም የዕውቅና መስጠት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። በመድረኩ የአገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ታድመዋል። ከታደሙት የአገራት መሪዎች መካከል በአገር በቀል የመደመር ፍልስፍና እና በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ የአፍሪካ ብሎም የዓለም ተምሣሌት የሆነውን የኢትዮጵያን የብልፅግና ራዕይ ለማሳካት ቀን ከሌሊት እየተጉ ዘርፈ ብዙ አገራዊ ለውጦች እና ውጤቶችን ያስመዘገቡና እያስመዘገቡ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አንዱ ናቸው። መድረኩን ኢትዮጵያ እጅግ ጎልታ፣ ደምቃና ልቃ የታየችበት ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሎም የዓለም የብልፅግና ተምሣሌት እንድትሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እየሰጡ ባሉት በሳል አመራር፣ ባሳዩት ቁርጠኝነትና ፅናት ባለፉት አምስት ዓመታት በምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን ላይ ትልቅ ስራ በመስራቷ ዓለም አቀፍ ዕውቅናን ተጎናፅፋለች።
በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ከፍተኛውን የከበረ ሽልማት አግሪኮላ ሜዳሊያ ተሸልመዋል። የዓለም አገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች እና ተወካዮች በታደሙበት የአገራችን የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ በእጅጉ በተደመሙበት በዚሁ የዕውቅና መድረክ የድርጅቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ኪዩ ዶንግዩን ለጠቅላያችን ሽልማቱን በልዩ አክብሮትና አድናቆት አበርክተውላቸዋል። አግሪኮላ ሜዳሊያ አግሪኮላ ሜዳሊያ ድህነትን ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ዘላቂነት ያለው የምግብ አቅርቦትን ለማሳደግ ለሠሩ፤ ለዓለም አቀፍ ትብብር ድጋፍ ቁርጠኝነት ላሳዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ የአገር መሪዎች እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች ዕውቅና የሚሰጥበት የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) የከበረ ከፍተኛ ሽልማት ነው። አግሪኮላ ሜዳሊያ ለእነማን? መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ይህን የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት የከበረ ከፍተኛ ሽልማት የሆነውን አግሪኮላ ሜዳሊያ መስጠት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1977 ነበር። ድርጅቱ የሕዝቦቻቸውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት ላከናወኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ የአገር መሪዎች እና ግለሰቦች አበርክቷል። ቀደም ሲል የፋኦን አግሪኮላ ከፍተኛውን የከበረ ሜዳሊያ ከተሸለሙት መካከል የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንሞሃን ሲንግ፣ የቀድሞ የታይላንድ ንጉሥ ባሁሚቦለ አዱለያዴጅ፣ የቀድሞ የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ፣ የቀድሞው የቻይና ፕሬዚዳንት ጂያንግ ዜሚኒ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዌን ጂያባኦ፣ የማላዊው ፕሬዝዳንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ ይጠቀሳሉ። አሁን በሕይወት የሌሉት የሳዑዲ ዓረቢያ ንጉስ አብዱላህ ቢን አብዱል አዚዝ አል ሳዑድ፣ የቀድሞ የግብፅ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ፣ የቀድሞ የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆዜ ማሪያ አዝናር፣ የቀድሞ የጀርመን ፕሬዚዳንት ዮሐንስ ራኡ እና የሮማ ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ጆን ፖል ሁለተኛ የከበረ የአግሪኮላ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ነበሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኪዩ
ዶንግዩን የተባባሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው መምራት ከጀመሩበት እ.ኤ.አ ከ2019 ወዲህ የፋኦ የከበረ ከፍተኛ አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት የተጎናጸፉ ብቸኛው ተጽዕኖ ፈጣሪ የአገር መሪ ናቸው። የኪዩ ዶንግዩን እማኝነት ስለ ኢትዮጵያ የለውጥ እመርታ የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ኪዩ ዶንግዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፋኦን የከበረ አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት ካበረከቱላቸው በኋላ ከሁሉ አስቀድሜ ክቡርነትዎ ለምግብ ሥርዓተ ለውጥ፣ ለገጠር ልማት መሻሻል ባሳዩት አመራር፣ ቁርጠኝነት እና ፍቅር ለተገኘው ትልቅ ታሪካዊ መሰረታዊ ለውጥ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል። በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተለይም በስንዴ ልማት እና በአረንጓዴ አሻራ ልማት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አውስተዋል። በእርስዎ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ተነሳሽነት ኢትዮጵያ በአሥር ዓመታት ውስጥ ብልፅግና ብቻ ሳይሆን አረንጓዴና ውብ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ ሲሉም አክለዋል። “በተለይ ሥልጣን ከያዝኩ በኋላ የፋኦን የከበረ አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት ስሰጥ እርስዎ የመጀመሪያው ነዎት። ሽልማቱ በእውነት ለእርስዎ እና ለአህጉርዎ የሚገባ ነው። ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካ ያለኝ የቅርብ ስሜት ነፀብራቅ ነው” ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል። ዳይሬክተር ጀኔራሉ ያስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልታና ደምቃ መታየት የአፍሪካዊያንም ድምቀት ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን ወኪል መሆኗን ጭምር የሚያረጋግጥ ነው። ዳይሬክተር ጀኔራል ኪዩ ዶንግዩን አያይዘውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ከተረከቡበት እ.ኤ.አ 2018 ጀምሮ አሳሳቢ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት አዳዲስ መፍትሔዎችን በመለየትና በመተግበር በኢትዮጵያና በሌሎችም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ለምግብ ሥርዓተ ለውጥ እና የኢኮኖሚ ልማት ራዕያቸውን ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል ሲሉ ነው ያብራሩት። ይህ ስኬት ምን ያህል አስደናቂ እንደነበር ማየት እንችላለን። ይህን ራዕይ እውን በማድረግ የሕዝቦቻችሁን ሕይወት ለማሻሻል ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ያደረጋችሁትን ጥረት እናደንቃለን፤
እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን ብለዋል። ኪዩ ዶንግዩን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሳል አመራርና ቁርጠኝነት በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ስላለው አገራዊ ለውጥም እማኝነታቸውን ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በምግብ ዋስትና እና በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት ላሳዩት ራዕይ፣ አመራርና ቁርጠኝነት የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅትን የከበረ፤ ከፍተኛ (Prestigious Award) አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት መጎናጸፋቸውን አስረድተዋል፡፡ ባለፉት አምስት ዓመታት አስቸጋሪ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ባሉበት ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ውጤታማ፣ ተጠያቂነት ያለው እና የተረጋጋ አመራር” የኢትዮጵያን አስደናቂ ዕድገት ተመልክተናል ሲሉ ነው ኪዩ ዶንግዩን በኢትዮጵያ እየተመዘገ ስላለው ሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ እማኝነታቸውን ለመድረኩ ታዳሚዎች የገለጹት። ሽልማቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተበረከተው የምግብ ዋስትና ደህንነትን ለማረጋገጥ፣ ድህነትን ለመቀነስ፣ በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት፣ በገጠርና በምጣኔ ሐብት ልማት ሥራዎቻቸው እና በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ላስመዘገቡት ስኬት ነው ሲሉ አብራርተዋል። ኪዩ ዶንግዩን በኢትዮጵያ የገጠር እና የምጣኔ ሐብት ልማት ሥራዎች እና የአረንጓዴ አሻራ ልማት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግል ጥረት ውጤቶች ናቸው ብለዋል። በኢትዮጵያ ውጤታማ ለሆነው የስንዴና በምግብ ራስን የመቻል መርሃ ግብር ስኬት ያደረጉት ብርቱ ጥረትና ያሳዩት ቁርጠኝነት በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የመነሳሳት ምንጭ መሆኑን ዳይሬክተር ጀኔራሉ ገልጸው፤ “ሁልጊዜ እንደምለው አፍሪካዊያን በአካባቢያችሁ ነባራዊ ሁኔታና ጥበብ ላይ በመመስረት የራሳችሁ መፍትሔዎች አሏችሁ” ሲሉ ተደምጠዋል። ኪዩ ዶንግዩን እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ለስንዴ ምርታማነት ዕድገት ባደረጉት ጥረት የተገኘው ውጤት፤ ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ እንዳለ ያረጋገጠ ነው። ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በየካቲት 2023 የመጀመሪያውን የስንዴ ምርት ለዓለም አቀፍ ገበያ አቅርባለች። ይህ ደግሞ ሌሎች የዓለም አገራት በዓርአያነት ሊከተሉት የሚገባ ስኬት ነው። አገሪቱ ፍላጎቷን አሟልታ ስንዴን ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንድትችል በማድረግ ምርጥ ተሞክሯቸውን በተግባር አሳይተዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራርና ቁርጠኝነት ኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ያስመዘገበችው ስኬት በአፍሪካዊያን ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትና መነሳሳት መፍጠሩን ጠቅሰው፣
ይህን ምርጥ ተሞክሯቸውን ለአፍሪካዊያን ወንድሞችና እህቶች ማካፈል አስፈላጊ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል። ኪዩ ዶንግዩን ባለፉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ሁለት ጊዜ መጎብኘታቸውን ገልጸው፤ በዚህም ከመሰረተ ልማት እስከ ግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በስንዴ ምርት ራስን ለመቻል በተደረገው ጥረት የመጡ ለውጦችን ተመልክቻለሁ ብለዋል። በመሰረተ ልማት፣ በመስኖ ሥርዓት፣ በግብይትና በሰብል ዘር ቴክኖሎጂዎች በላቀ ደረጃ የታየው መሻሻል በእውነት የሚደነቅ ነው ሲሉም አክለዋል። ኢትዮጵያን ማራኪ አረንጓዴ አገር የሚያደርጋትን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ተነሳሽነት (Initiative) የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን ከወዲሁ አይቻለሁ ብለዋል የፋኦ ዳይሬክተር ጄኔራል ኪዩ ዶንግዩን። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሽልማቱን ከተረከቡ በኋላ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው “ፋኦ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለምናደርገው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳሊያ ስላበረከተልኝ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል። ከፍተኛ ዋጋ ላላቸውና ለኢንዱስትሪ የሰብል ምርቶች የሰጠነው ትኩረት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስገኘ ስለሆነ አገራዊ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ለጀመርነው ጉዞ ስኬት ቁርጠኛ ነን ሲሉም አክለዋል።
በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የሚታረስ መሬት በ50 በመቶ እንዲጨምር መደረጉ፤ የስንዴ እና የሩዝ ምርት በከፍተኛ መጠን እንዲያድግ ማስቻሉን፤ እርሳቸው ሥልጣን ሲረከቡ ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ታስገባ እንደነበረ፤ አሁን ፍላጎቷን አሟልታ እ.ኤ.አ ከ2023 ጀምሮ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መጀመሯን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል። ስለ ሽልማቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የከበረ የፋኦ “አግሪኮላ ሜዳሊያ“ መሸለም አስተያየትና ማብራሪያ ከሰጡ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) አንዷ ናቸው። ሚኒስትሯ እንዳሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አመራር ኢትዮጵያ በምግብ ሥርዓት ለውጥ (transformation) ትልቅ ስራ በመስራቷ ዕውቅና አግኝታለች። ሽልማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች የተተገበሩት የሌማት ትሩፋት፣ የስንዴ ልማት እና የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ያሳየ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰጠው የአግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት
ከግብርናው ዘርፍ ባሻገር በቱሪዝም ልማትና በሌሎች መስኮች ሕዝቡን በማንቃትና በማሳተፍ ላሳኳቸውና ወደፊት ለሚያከናውኗቸው ሥራዎች ብርታት እንደሚሆንም ነው የገለጹት። ሽልማቱ ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል ላስቀመጠችው ራዕይ ስኬት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያነሳሳ ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የግብርናውን ዘርፍ ለመቀየር ላበረከቱት ድጋፍ ዕውቅና በመስጠቱ አድናቆታቸውን ገልጸው፤ “በእርግጥ የአርሶ አደሮች ሕይወት ሲሻሻል የአገሪቱም የግብርና ምርታማነት ያድጋል” ብለዋል። የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የከበረውን የፋኦን አግሪኮላ ሜዳሊያ የሸለማቸው ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት እና በስንዴ ልማት መርሃ ግብሮች ለተመዘገበው ውጤት ላሳዩት አመራርና ቁርጠኝነት ነው ሲሉ የገለጹት ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ
ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ናቸው። የክልል መንግሥታት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትን ለማሻሻል ላሳዩት ራዕይ፣ አመራርና ቁርጠኝነት እንዲሁም ፈጣን፣ ተለዋዋጭና ፈታኝ በሆነው ከባቢያዊ ሁኔታ በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በተከተሉት ፈጠራዊ መፍትሔ ከዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የተበረከተላቸው የከበረው የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማትና የተሰጣቸው ዕውቅና እንደ አገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተጨማሪ መነሳሳትን የሚፈጥር እንደሆነ በመግለጽ የእንኳን ደስ አለዎት! መልዕክት አስተላልፈዋል። ማጠቃለያ ከኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አምስት ምሰሶዎች (ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች) መካከል ግብርና አንዱ ነው። ግብርና የአብዛኛው ኢትዮጵያ ሕዝብ የሕይወት መሰረት ነው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ 85 በመቶ የሚሆነው በገጠር የሚኖርና ሕይወቱም በግብርና ላይ የተመሰረተ ነው። ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ዕድገት ወሳኝ ዘርፍ ነው፡፡ ከጠቅላላው የአገሪቱ ምጣኔ ሐብት 38 በመቶ ያህል ድርሻ አለው፤ ከወጭ ንግድ ዘርፍም 80 በመቶ ያህሉን ይሸፍናል። በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም 80 በመቶ ያህሉን የሰው
ኃይል በመያዝ አብላጫውን ድርሻ ይይዛል፡፡ መንግሥት ግብርናን በማዘመን፣ ዘርፉን ከዝናብ ባሻገር በመስኖ ልማት በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ በማልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። በዚህም በየዓመቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን የስንዴ ምርት በማስቀረት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምሯል። ይህ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ግብርናን በከተማ ደረጃ በማስፋፋት ኅብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤውን እንዲቀይር፣ በከተማ ግብርና ተሰማርቶ ከዕለታዊ ፍጆታው አልፎ ገበያ ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለማርገብ እየተደረገ ያለውን ሁሉን አቀፍ ጥረት እያገዘ ይገኛል። በመሆኑም በከተሞች በግለሰቦች፣ በመንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ተይዘው ጦም አዳሪ የሆኑ ቦታዎች እየለሙ የኅብረተሰቡ የምግብ ዋስትና ማረጋገጫና የገቢ ማሻሻያ መሰረት እየሆኑ ነው። ከዚህ ባሻገርም የግብርና ውጤቶችን እንዳለ ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ይልቅ እሴት ጨምሮ የዘርፉን የገቢ ምርቶች በወጪ ምርት ለመተካት የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋትና ለማጠናከር እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ኢትዮጵያ ከዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያገኘች ነው። በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን
የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ በርካታ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይገኛሉ። በተለይ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ውጤት እየተገኘ ነው። በግብርና ኢንቨስትመንት ሰፊ ስራ ተሰርቷል፤ እየተሰራም ነው። በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋትና በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብሮች በሕዝብ ተሳትፎ ጭምር የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማሳየት ጀምረዋል። ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘችበት የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዚህ ውጤት መገኘት ላሳዩት ራዕይ፣ አመራርና ቁርጠኝነት የሰጠው የከበረ አግሪኮላ ሜዳሊያ ሽልማት አንዱ ማሳያ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራርና ቁርጠኝነት በግብርናው ዘርፍ የተጎናጸፈችውን ዓለም አቀፍ ዕውቅና በሌሎቹም አገር በቀል የኢኮኖሚ ምሰሶዎች (ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች) በመድገም የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ የልማት፣ የዕድገትና የብልፅግና ራዕይ እውን ለማድረግ በሁሉም የሙያ ዘርፍ በተለወጠ አስተሳሰብና አመለካከት ተግቶ በመስራት የዜግነት ግዴታን መወጣት ይጠይቃል።
ኢኮኖሚ
አገራዊ ለውጥ የሚያሳካ ተቋማዊ ዕቅድ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ ዕቅዱ አገራዊ የኃይል ፍላጎትን ለማሳካት፤ በረጅም ጊዜ ዕቅዱ ደግሞ የአፍሪካን በተለይም የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሕዝቦችን በኃይል አቅርቦት ለማስተሳሰር የሚያስችል ራዕይ ሰንቆ እየሠራ ነው። ዘርፉ ተቋማዊ ትልሙን ዕውን ማድረግ የሚያስችሉትን የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶች ቀይሷል። በተለይ ዘመኑ ከደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎች ጋር እያጣጣሙ ማቀድና መተግበር ወይም ቀደም ሲል የነበረውን ተለምዷዊ አሠራር ወደ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ማሸጋገር ዘርፉ እየተከተላቸው ከሚገኙ የለውጥ ሥራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ተቋሙ ለኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭነት የሚውሉ ሐብቶችን በጂኦ-ስፓሻል መረጃ ታግዞ መገኛ ቦታቸውን፣ በምን ያህል መጠን እንደሚገኙ፣ ለምን ዓይነት ዓላማ እንደሚውሉ እና እንዴት ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ወዘተ. . . መረጃዎችን በሳተላይት እና በድሮን ቴክኖሎጂዎች በማሰባሰብ ለፖሊሲ አውጪ እና ለሌሎች ተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል። ዘርፉ የጀመረውን ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ይበልጥ ለማሳደግ እንዲያግዘውም ከተለያዩ አገራዊ እና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የትብብር ስምምነት አድርጓል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት የአገሪቱን እምቅ ሐብቶች በማልማት
መላውን ሕዝብ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ዕቅድ ነድፎ እየሰራ ይገኛል። በተለይ ከ95 በመቶ በላይ ከውኃ የሚያመነጨውን ኃይል ከፀሐይ፣ ከንፋስና ከከርሰ ምድር እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ከውኃ የሚገኘውን የማመንጨት ድርሻ ወደ 73 በመቶ በመቀነስ የኃይል ስብጥሩን ለማስፋት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ በዕቅዱ ተመላክቷል። ተቋሙ የአገሪቷ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የሚያመጣውን የኃይል ፍላጎት ጥያቄ መመለስ የሚያስችልና በኃይል ማስተላለፍ ወቅት የሚያጋጥመውን የ6 በመቶ የኤሌክትሪክ ብክነት ወደ 3 ነጥብ 5 በመቶ በመቀነስ በጥራት ተወዳዳሪና አስተማማኝ የኃይል አቅራቢ መሆንን ያለመ ነው። በዚህም መሠረት አገሪቱ ከአራት ዓመት በፊት የነበራትን 4 ሺህ 200 ሜጋ ዋት አገራዊ የኃይል ምርት በቀጣዮቹ ሰባት ዓመታት በአራት እጥፍ በማሳደግ 17 ሺህ ሜጋ ዋት ለማድረስ፤ ከኢነርጂ ተጠቃሚነት አንጻርም 15 ሺህ ጊጋ ዋት ሠዓት የነበረውን ዓመታዊ የኢነርጂ ምርት ወደ 65 ሺህ ጊጋ ዋት ሠዓት ለማድረስ ዕቅድ ይዟል። ለዚህ ትልም ስኬት በቀጣይ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶችን ሳይጨምር አገልግሎት እየሰጡ ካሉት 19 የኃይል ማመንጫዎች በተጨማሪ
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጨምሮ አምስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ግንባታ እያከናወነ ይገኛል። በተጨማሪም ተቋሙ ከ132 ኪሎ ቮልት በላይ አቅም ያላቸው 192 ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ቁጥር ወደ 265 ለማሳደግ፤ እንዲሁም 20 ሺህ 634 ኪ.ሜ ርዝመት ያለውን ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ወደ 33 ሺህ 497 ኪ.ሜ ለማድረስ የተለያዩ ቮልቴጅ መጠን ያላቸው የማስተላለፊያ መስመሮችንና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በመገንባት ላይ ነው። በተቋሙ ዕቅድ ትኩረት የተሰጠው ሌላው ጉዳይ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዘርፍ ማሳተፍ የሚለው ነው። ለዚህም እንዲያመች የግሉ ዘርፍ የሚሳተፍባቸውን አማራጮች በጥናት በመለየት የተለያዩ የሕግ ማሻሻያ ሥራዎች ተከናውነዋል። ይህን ተከትሎ በዘርፉ መሳተፍ የሚፈልጉ አልሚዎች በንፋስና በፀሐይ ኃይል የማመንጨት ሥራ ላይ ለመሰማራት ከወዲሁ ፍላጎት ማሳየታቸው ለዘርፉ አዲስ ምዕራፍ እየተከፈተ መምጣቱን ማሳያ አድርጎ መውሰድ ይችላል። በተጨማሪም አሁን ያለውን 300 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተቋም ገቢ ወደ 5 ነጥብ 32 ቢሊዮን ማሳደግ የሚለው ሌላው የተቋሙ
የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ነው። ለዚህ ዕቅድ ስኬት ከአገር ውስጥ ፍላጎት የሚተርፈውን የኃይል ምርት ለጎረቤት አገራት በመሸጥ በሚገኘው የውጭ ምንዛሬ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እና ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር በተቋሙ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው። በመሆኑም በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ቀዳሚ ከሆኑ ተቋማት ተርታ እንደሚያሰልፈው ተስፋ ተጥሎበታል። የተቋሙ አፈፃፀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ እያንዳንዱ ተግባር ከረጅም ጊዜ ዕቅድ ተቀድቶ የዓመት፣ የወርና የዕለት ተግባር ተለይቶ ትግበራ ጀምሯል። በዕቅዱ ላይ የተጠናከረ ክትትል እና የአፈፃፀም ግምገማ ስለሚካሄድ እንዲሁም ዕቅዱ በሚዛናዊ ውጤት ተኮር ሥርዓት ስለሚለካ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ አግዟል። የተጀመረው ተቋማዊ ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረው በየደረጃው የሚገኙ የመስተዳድር አካላት እና ኅብረተሰቡ ለሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን ጥበቃ በማድረግና የሕዝብ ሐብት እንዳይመዘበር በማድረግ አገርና ወገንን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንዳይደናቀፍ አገራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል።