ነጋሪ መጽሔት 27ኛ ዕትም - ኢዜአ ነጋሪ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016
ምክክር የሀገር መድኅን
ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ማውጫ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አዲስ መልክ
06
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በየሁለት ወሩ የምትታተም መጽሔት መስከረም 2009 ዓ.ም ተመሰረተች
አድራሻ፦
አራዳ ክፍለ ከተማ
ስልክ ቁጥር
+251-11-55-00-11
+251-11-56-39-31
+251-11-56-52-21
ፋክስ ቁጥር
+251-11-55-16-09
enanegari@gmail.com
ካፒታል ገበያ ምን ይዞ ይመጣል?
16
ለዘመናት ጥያቄ ምላሽ ሰጪው ጭላንጭል ተስፋ
24
መጪውን ወረርሽኝ አስቀድሞ ለመከላከል. . .
32
አገልግሎቱ ለማኅበረሰብ ጤና መጠበቅ. . .
36
ምክክር የሀገር መድኅን!!
40
Peace Building: Bedrock for Ethiopia’s Bright Future
52
የዜጎች ግልጋሎት ዝማኔ
60
ፈር ቀዳጁ የድንገተኛ ሕክምና ሆስፒታል
70
የሽግግር ፍትሕ ለምን?
76
መልዕክት
ውድ አንባቢያን ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረስ። ነጋሪ እንደ ወትሮው ሁሉ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ሰንዳ ቀርባለች። በዚህ ዕትሟ ኢትዮጵያ የተሸከመቻቸውን፤ ዘመናትን የተሻገሩ ቁርሾና የታሪክ ስብራቶች ለመጠገንና ትውልዱም ካለፈው የወረሰውን ዕዳ ለማቃለል የጀመረችውን ሀገራዊ የምክክር ሂደት ዓቢይ ጉዳይዋ አድርጋለች።
በዚህ ጽሑፍ ምላጭ በሚያስውጥ እልህ፣ በመጠፋፋት እና በብሽሽቅ ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ፤ ኢትዮጵያ አሁን የያዘችው ቅርፅ እንዲኖራት መሰረት በጣለው እና ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያና የ20ኛው ክፍል ዘመን መባቻ ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባሕል ዑደት፤ ሀገራዊ አለመግባባቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ዓለም አቀፍ ተመራጭነቱ እየጨመረ የመጣውን ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ ኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም የጀመረችው ሂደት እንዲሁም ቀጣይ ክንውኖች በስፋት ይዳሰሳሉ።
ለአዲስ አበባ ውበትም፣ ወረትም እንደሚሆን ተስፋ የተሰነቀበት፣ የመዲናዋን ስድስት ክፍለ ከተሞች የሚያካልለውና በመገባደድ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የነጋሪ አንዱ ጉዳይ ነው። ልማቱ ለነዋሪዎቿ ምቹ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር የሚያስገኘው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይተነተናል።
በማኅበረሰብ የሥርዓት እና የዘመን ምዕራፍ ሽግግር ወቅት የሚተገበር እና በዓለም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ ተቋማት እንዲሁም በአገራት መንግሥታት ሰነዶች ተቀራራቢ ትርጓሜና አንድምታ የተሰጠው ፅንስ ሃሳብ እና እርምጃ ስለሆነው ‘የሽግግር ወቅት ፍትሕ’ የሚያትተው ጽሁፍ ሌላው የነጋሪ ርዕሰ ጉዳይ ነው።
ከፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት በኋላ በኢትዮጵያ ጎልቶ መሰማት የጀመረውና ረቂቅ ፖሊሲ የተዘጋጀለት፤ በሚያዚያ 2016 ዓ.ም ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ስራ ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የሽግግር ፍትህ አንኳር ይዘቶች፣ የሂደቱ ተስፋዎችና ምክረ ሃሳቦች በጽሑፉ ይብራራሉ።
በአንድ ወቅት አንድ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል “ለመሆኑ መንግሥት በተቀያየረ ቁጥር የሚለዋወጥ ሲቪል ሰርቪስ ይዘን የምንቀጥለው እስከመቼ ይሆን? ሲሉ ላነሱት ቁጭት አዘል ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “በጣም ትክክለኛና የምጋራው ሃሳብ ነው” ሲሉ ምልከታቸውን እና የመንግሥታቸውን መሻት ያስረዱበት ነው - የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት። ለመሆኑ ሲቪል ሰርቪሱና አገረ-መንግሥቱ ምንና ምን ናቸው? ነጋሪ የምትለው አላት።
የኢትዮጵያ መንግሥት የገበያውን ተፈላጊነት በማጤን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን በአዋጅ ካቋቋመ ሰንበትበት ብሏል። በአዋጅ የተቋቋመው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንም የካፒታል ገበያን እውን ለማድረግ ዘመኑን በዋጁ አሠራሮች፣ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የሕግ ማዕቀፎች በመመራት ወደ ትግበራ ገብቷል። የካፒታል ገበያውን የማደራጀት ሥራዎችን እያከናወነም ይገኛል። የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣቱን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በመቋቋም ላይ ነው። ነጋሪ የድርሻ ገበያ በመባል የሚጠራውን የካፒታል ገበያ ፅንሰ ሃሳብና ምንነት፣ ገበያው ለሕዝብና ለአገር የሚኖረውን ፋይዳ ይዛለች።
በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚመጥን የመሠረተ ልማት አውታር ግንባታ አለመኖርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት በርካቶችን ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ የጤና እክል እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል። በመንገዶች ላይ የቁም እና የወለል ምልክቶች አለመኖር፤ በሕንፃዎች ላይ አካል ጉዳተኞችን የሚደግፉ መወጣጫዎች እጥረት፤ የመፀዳጃ እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች ላይ አካል ጉዳተኞች ተደጋጋሚ ቅሬታ ያነሳሉ፤ በዚህ ረገድ አካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብለው የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሬት ላይ ወርደው በተጨባጭ ምን ለውጥ አመጡ? አፈፃፀማቸውስ? የሚለውን የበርካቶች ጥያቄ ለመመለስ ምን እየተሰራ ነው? ስትል ነጋሪ ትጠይቃለች። ነጋሪ እነዚህንና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮችን ይዛለች።
መልካም ንባብ!
ዋና አዘጋጅ
አብዱራህማን ናስር
ም/ ዋና አዘጋጅ
የሺመቤት ደመቀ
ከፍተኛ አዘጋጅ
ፍቅርተ ባልቻ
አዘጋጅ
መንገሻ ገ/ሚካኤል
አርት ዳይሬክተር
ነብዩ መስፍን
nebiyou1st@gmail.com
ፎቶግራፍ
አሸናፊ ገ/ሥላሴ
ሙሉቀን ገረመው
እርምት ባለሙያ
ትዝታ ሁሴን
ኢኮኖሚ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ
አዲስ መልክ
በአህመድ መሀመድ
መግቢያ
ከተሞች የዘመን መስታወቶች ናቸው። የሥልጣኔ መልክና ልክ ማሳያ ጭምር። የመልከ- ብዙ ባሕል፣ ወግና ትውፊት መድመቂያ፣ የሉላዊ እሳቤ መታያ፣ የሥራ እና ሥራ ፈጣሪዎች መናኸሪያ እና የዕድገት መስፈንጠሪያ ናቸው። ብዝሃ የኑሮ ደረጃ ያዝላሉ፤ አዲስ ትውፊት ይወልዳሉ፤ የከተሜዎችን የነገ የጋራ ትዝታ በሕብረት ይቀርጻሉ። ለአያሌ ምዕተ ዓመታት የዓለም ታሪክ ከተሞች ለሥልጣኔ ማማ፣ የባሕል፣ የንግድና የአስተዳደር መልኮች አውድማ ናቸው። ድሮም ሆነ ዘንድሮ የኑሮ መሻትን ለማርካት በሚደረግ ግርግር ይታወቃሉ።
የሥነ-ከተማ አጥኚዎች እንደሚሉት ከተሞች የተወጠኑት ወንዝ ተከትለው ነው። በነዋሪዎች ጥግግት፣ በተማከለ አስተዳደር፣ አብያተ መንግሥታት እና አብያተ መቅደሶች በቤተ- መቅደሶቻቸው ይታወቃሉ። የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን አሰፋ (ዶ/ር) ከተሞች በየዘመናቱ የንግድ፣ የኪነ-ጥበብ እና የሃይማኖት ማዕከላት እንዲሁም የሥልጣኔ መሰረት ናቸው።
ለአብነትም በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ኃይል የመነጨው፤ ፋብሪካና የባቡር ሀዲድ የተዘረጋው በከተሞች ነው። ከተሞች በፈጠራ ጥበባቸው የሕዝብ ስበት ማዕከል ሆነዋል። ከድሕረ 20ኛው ክፍለ ዘመን እስከ ዛሬው የዲጂታላይዜሽን አብዮት ዘመንም ከተሞች የአዳዲስ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ግኝት፣ የቴክኖሎጂና የዲጂታላይዜሽን አስኳል ሆነው ቀጥለዋል። በዚህም የኢንቨስመንት፣ የፋይናንስ፣ የባሕል እና የዕውቀት ሜዳ ናቸው። ዘመኑን የዋጁ ኪነ ሕንጻዎች፣ መንገዶች እና የትንሿ ዓለም መልክ መገለጫዎችም ናቸው። ከጥንት እስከዛሬ ከተሞችን የዘመን መመልከቻ መስታወቶች እና አሻራ ማንበሪያ ሰሌዳዎች ሊባሉ ይችላል።
አዲስ አበባ እንደ ከተማ
የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤቷ ኢትዮጵያ በጥንተ ታሪክ ገጾቿ የራሷን ከተሞች መፍጠሯ ዕሙን ነው። የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን አሰፋ (ዶ/ር) እንደሚሉት ሞሶፖታሚያ፣ ግብጽ፣ ፋርስ እና መሰል ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤቶች እንደነበሩ ሁሉ ኢትዮጵያም አክሱምን መሰል ከተሞች ነበሯት። እስከዛሬዋ አዲስ አበባ ድረስ በየዘመን ሕዳጉ ከተማ የሚሰኙ ማዕከላት ተመስርተዋል።
በ1879 ዓ.ም የተከተመችው የዛሬዋ የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መናኸሪያ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት። ከባሕር ጠለል በላይ ከ2 ሺህ 300 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ፣ 527 ስኲዬር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ያላትና አምስት በመቶውን የአገሪቷን ሕዝብ ያቀፈች ግዙፍ ከተማ ነች። የከተሜነት ምጣኔውም በየዓመቱ 3 ነጥብ 7 በመቶ ይጨምራል። ዳሩ የከተማዋን ስፋትና ዕድገት የሚመጥን የከተሜነት መሰረተ ልማት፣ ገጽታ እና የኑሮ ጥራት እንደሚጎድላት ይነሳል። የመዲናዋ ዕምብርት የሚሰኙ በርካታ አካባቢዎች ገጽታ ከዛሬ 70 እና 80 ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር የተራራቀ አለመሆኑም ለዚህ አስረጂ ነው።
በ1920ዎቹ አዲስ አበባን የጎበኘው እንግሊዛዊው አልኸንድሮ ዲል ባዮ(ኮሎኔል) ‘ቀይ አንበሳ’ በተሰኘው ስለ ኢትዮጵያ የሚያትት የጉዞ ማስታወሻው “አዲስ አበባ የገጠር ከተማ ነች። ከሌሎቹ የአቢሲኒያ ከተሞች አንጻር አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ዘመናዊ ቤቶችና የመገናኛ አውታሮች መዘርጋት ለዋና ከተማነት አብቅቷታል። ከውጭ ለሚጎበኝ የውጭ ዜጋ ግን ሁኔታዋ ከሌሎች ከተሞች እምብዛም አይለይም” ሲል ገልጿታል። በተመሳሳይ ዘመን ኢትዮጵያን የጎበኘው ቼካዊው ዜጋ አዶልፍ ፓርላሳክ ‘የሃበሻ ጀብዱ’ (ተጫነ ጆብሬ እንደተረጎመው) በተሰኘው መጽሐፉ፤“መሀል ከተማ ላይ ሁለት ፎቅ የድንጋይና የእንጨት መኖሪያ ቤቶች እና የግሪክ ነጋዴዎች ሱቆች እንዲሁም ሌሎች አውሮፓዊያን መኖሪያ ቤቶች ተሰርተውበት ደመቅመቅ ብሏል” በማለት የአዲስ አበባን ለጋነት ይተርካል።
የሁለቱ አውሮፓዊያን ትዝብት የሚተርከው የፒያሳን የዘመን መልክ ነው። ከ80 ዓመታት በፊት የነበሩ ትዝብቶች ከበርካታ ትውልድ መተላለፍ በኋላ ዛሬም ቢቃኙት የፒያሳ የከተሜነት መልኳ ምን ያህል ተለውጧል ቢባል ምላሹ ግር ማሰኘቱ አይቀርም። ፒያሳና መሰል ቀደምት መንደሮች ታሪክ፣ ስምና ዕድሜቸውን የሚመጥን እድሳት አልተደረገላቸውም። ከጌጥነት ይልቅ ማኅበራዊ ጠንቅነታቸው የሚያደሉ ነታባ መንደሮች ሆነዋል። ጣሪያና ግድግዳቸው፣ በርና መስኮታቸው የተቦዳደሰ፣ ዛኒጋባዎች የተዛዘሉ፣ መንገዳቸው የፈራረሰ ለዓይን የሚቀፉ፣ ለአፍንጫ የሚረብሹ ስሜቶች ነበሩባቸው።
ልከኞቹ የአዲስ ኮሪደሮች
ኮሎኔል አልኸንድሮ ዲል ባዮ “የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት ለጅቦች እና ለጥንብ አንሳ አሞራዎች የተተወ ይመስላል፡፡ እነኚህ አውሬዎች በየሜዳው የወደቁትን እና የተጣሉትን ቆሻሻዎች
በመመገብ የከተማዋን ንጽህና ይቆጣጠራሉ። በግልጽ በሕዝብ መተላለፊያዎች እና መንገዶች ላይ የወደቀውን ለመጋራት ሲጣሉና ሲናከሱ ይታያሉ” በማለት ነበር ትዝብቱን ያሰፈረው። ይህ ስሜት ለዚህ ዘመኗ አዲስ አበቤዎች ለአፍንጫና ለዓይናቸው የቀረበ ዕውነት ሆኖ ኖሯል።
አዲስ አበባን ከመልከ ብዙ ጉድፎቿ በማንጻት ስምና ክብሯን የሚመጥን ገጽታ ማላበስ ያለሙ ፕሮጀክቶች አሁን ተግባራዊ መሆን ጀምረዋል።
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት አንዱ ነው። የመዲናዋን ስድስት ክፍለ ከተሞች የሚያካልለው የኮሪደር ልማቱ ለአዲስ አበባ ውበትም፣ ወረትም እንደሚሆን ትልቅ ተስፋ ተሰንቆበታል። በፕሮጀክቱ ከተጀመሩ ኮሪደሮች መካከል አምስቱ ግንባታቸው እየተጠናቀቀ ነው።
የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ገጽታዋን ማስዋብ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነዋሪዎች ለኑሮ የምትመች የጸዳችና የተዋበች መዲና ማድረግን ያለመ ነው። አምስቱ ኮሪደሮች ከፒያሳ-አድዋ ድል መታሰቢያ- አራት ኪሎ፣ ከአራት ኪሎ አደባባይ-መገናኛ፣ ከሜክሲኮ-ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር፣ ከአራት ኪሎ-መስቀል አደባባይ- ቦሌ ድልድይ እንዲሁም ከመገናኛ እስከ አዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲሆኑ 48 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ይሸፍናሉ።
ኮሪደር ልማቱ አይነተ ብዙ ልማቶችን ያቅፋል። የተሽከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶችን በማስፋትና ምቹ በማድረግ ለትራፊክ ፍሰት እየተመቻቹ ነው። ጎዳናዎች በዘመናዊ የኤሌክትሪክ መብራት እና የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት ተውበዋል። ዘፈቀዳዊ ፍሳሽ አወጋገድ ዘመኑን በዋጀ አግባብ በሥርዓት ይተካል። ለዓይን የማይመቹ ሕንፃ ግንባታዎች ተጠግነው ሳቢና ማራኪ ውበት እየተላበሱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ዘላቂነት ባለው አግባብ ለነዋሪዎቿ ኑሮ የተመቸችና የላቀች፣ ውብ መኖሪያ ከተማ የማድረግ ዘመን ተሻጋሪ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው ነበር።
የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን (ዶ/ር) የታቀፉ ሰፈሮች ለኑሮም ሆነ ለንግድ አገልግሎት የተጨናነቁ፣ ለሥራም ሆነ ለኑሮ የማይመቹ፣ በጽዳት አገልግሎት ዕጦት የታወኩ መንደሮች በኮሪደር ልማቱ ታቅፈው ወደ ልማት እንዲገቡ መደረጉን ትክክለኛ ውሳኔ ይሉታል።
በአሥር ዓመት የልማት ዕቅዱ ውስጥ የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ፤ አሳታፊና ዘላቂ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ ከተሞችን መገንባት ትኩረት ተሰጥቶታል። ለኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ አካባቢያዊና ሥርዓተ ምህዳር ተጽዕኖዎች የማይበገሩ ከተሞችን ማልማት ላይ ያተኮረ ነው። ይኸውም የመሬትና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ማሻሻል፣ የተቀናጀ መሠረተ ልማትና የአገልግሎት አቅርቦት ማሳለጥ፣ የጽዳት እና የአረንጓዴ ልማት ሽፋንን ማሳደግ በጥቅሉ ለኑሮ ምቹና ተስማሚ ማድረግ ነው። የኮሪደር ልማቱ ከዚህ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ ነው። ከትራፊክ ፍሰት እና ውበቱ ባሻገር ጤናማነትን ጨምሮ ተጓዳኝ ማኅበራዊ አበርክቶ እንዲኖራቸው ያስችላል።
ዘላቂ ክትመት
ዘላቂ ክትመት ማለት ለአካባቢ ተስማሚ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ያላቸው ከተሞች መፍጠርን ያነገበ ሰፊ ጽንሰ- ሃሳብ መሆኑን መዛግብት ይጠቁማሉ። የዚህ ዓይነቱ የከተማ ልማት ዓላማ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሐብቶች እና ሥነ-ምህዳሮችን በመጠበቅ የአሁኑን እና የመጪውን ትውልድ ፍላጎቶች ሊያሟላ የሚያስችል ነው። የዘላቂ ክትመት እንቅስቃሴ ከተሞች የሥራ ዕድልን በስፋት እንዲፈጥሩ በማድረግ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ልማት እንዲሁም የብልጽግና ጉዞን ለማፋጠን ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል ነው።
በተጨማሪም ከተሞችን ማልማት ለሥራና ለኑሮ ሳቢ በማድረግ ለመዋቅራዊ ሽግግሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ከዚህ አኳያ በአስር ዓመት የልማት ዕቅዱ፤ ‘ለልማት የሚሆኑ የመሬት አቅርቦቶችን ማሻሻልና በመልሶ ማልማት ሂደት ዘላቂ የከተማ ልማትን ማረጋገጥ፣ ከተሞችን በዙሪያቸው ካለ ልማት ጋር በማስተሳሰርና ከሌሎች የልማት ማዕከላት ጋር በማቆራኘት ምርታማነትን ማሳደግ፣ የመንግሥት እና የግል አጋርነትን በመጠቀም የቤቶችን ዕጥረት መፍታት፣ ያልተማከለ የከተማ ልማትን ማጠናከር እንዲሁም የከተሞችን የመሠረተ ልማት ፍላጎት ማሟላት ይገኙበታል’።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በመንግሥት የሚደረገው ክትትል እና ቁጥጥር አናሳ መሆን እና የኅብረተሰቡ ቸልተኝነት ከተማዋን በሚገባት መንገድ እንዳታድግ አድርጓት ቆይቷል ነው ያሉት። በመዲናዋ በየትኛውም አካባቢ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚቀጠሉት ላስቲኮች እና ቆርቆሮዎች፣ ሥርዓት በሌለው መንገድ እና ዲዛይን በሌለበት ሁኔታ የሚቀጠሉ የኤሌክትሪክ መብራቶች እና የውሃ አገልግሎቶች ለከተማዋ አስቸጋሪ ሆነው ቆይተዋል።
ከተሞች የስራ ዕድል የሚፈጠርባቸው፣ ፈጠራ እና ግኝቶች የሚያድጉባቸው፣ የካፒታል ዝውውር የሚደረግባቸው ልዩ ማዕከላት ናቸው። የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን አሰፋ (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ‘ከተሞች ሰው እንደሚተነፍሰው ሁሉ የመተንፈሻ ሥርዓት ሊኖራቸው ይገባል። የሰው ልጅ በሕይወት ለመቆየት የደም ዝውውር እንደሚያስፈልገው ሁሉ ከተሞችም እንዲያድጉ የዘመነ የመብራት፣ የመንገድ፣ የኢንተርኔት፣ የውሃ መስመር፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ሥርዓት ሊኖራቸው ይገባል።’ ከተሞች መሰረተ-ልማታቸው ሲሟላ የኢኮኖሚ ዕድገት ይፈጥራሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉት የልማት ኮሪደሮች ከጊዜው ጋር የሚራመዱ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ የሚከሰቱ የዓለም የፈጠራ ውጤቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ ቀጣይነት ያለው መሠረተ ልማት በመፍጠር የነዋሪዎቿን እና የአካባቢውን ደህንነት የሚደግፉ ዘላቂ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ማድረጉን ያነሳሉ። በተለይ የከተማዋን መጨናነቅ እና የአዕምሮ ማደሻ ቦታ ጥበት በሚፈታ ሁኔታ የመዝናኛ፣ የብስክሌት መንቀሳቀሻ መንገድ እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ለሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች ምቹ የሆኑ የእግረኛ መንገዶችን ያካተቱ ናቸው ይላሉ።
ከዚህ ቀደም ሲከናወኑ የቆዩ ግንባታዎች፣ የመሰረተ-ልማት ሥራዎች በተቋማት አለመናበብ ምክንያት በተፈለገው ጊዜና ጥራት ከመጠናቀቅ አኳያ ችግር ሲገጥማቸው ቆይቷል። በዚህ ሳቢያም በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሱ የኖሩ መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። አንዱ ተቋም ገንብቶ የጨረሰውን ሌላኛው ሲያፈርስ፣ አንድ እና ሁለት ዓመት ሳያገለግሉ መልሰው ሲፈርሱ የኖሩ ፕሮጀክቶች በርካቶች ናቸው። ይህም ቀደም ሲል የነበሩ ግንባታዎች ዘላቂ ክትመት እንደ ግብ ላለመቆጠሩ ማሳያ ሆኖ የሚቀርብ ነው። በአሁኑ የልማት ኮሪደር የሥራ ስምሪት ወቅት እነዚህ እና መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ተቋማት በመናበብ እና ኃላፊነታቸውን ወስደው በመተግበር ላይ ይገኛሉ። የኮሪደር ልማቱ የመዲናይቱን ገጽታ በተሻለ መልኩ የሚቀይር መሆኑን የሚገልጹት አቶ ጃንጥራር፤ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተጀመረና የተለያዩ አካላት በቅንጅት የሚመሩት መሆኑን በዋቢነት ጠቅሰዋል።
በኮሪደር ልማቱ የመንገድ፣ የመብራት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የውሃ እና መሰል ተቋማት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛሉ። በመሬት ውስጥ የሚሰሩ ሥራዎች እና አጠቃላይ የመሰረት ሥራ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡ ፡ የጎርፍ ማስወገጃ ቱቦዎች ዝርጋታ፣ የመብራት እንዲሁም የአፈር ሙሌት እና የኮንክሪት ሥራዎችም በአግባቡ እየተከናወኑ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሪደር ልማት የኤሌክትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ሥራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን እና በመስመር ማዛወር ሥራው ወቅት የልማት ተነሺ ለነበሩ 2 ሺህ 700 ደንበኞች አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ እንደተከናወነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያሳያል።
አዲስ የሥራ መንፈስ
ለረጅም ጊዜያት መደበኛ ባልሆነ መልኩ በመስፈር የተጎሳቆለ የአኗኗር ዘይቤ እየተከተለ የሚገኘውን ነዋሪ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል፣ እያደገና ከተማዋን እያጨናነቀ ለመጣው የትራፊክ ውጥረት መፍትሔ መንገዶችን ለማስፋት፣ ለእግረኞች ሰፋፊ መንገዶችን ለማበጀት፣ የቅርስ ቦታዎችን ለመጠገን ብሎም ሕንፃዎችን በከተማዋ የሕንፃ ሥነ-ውበት ደረጃ ልክ ለማድረስ ሠራተኞች እዚህም እዚያም በትጋት እና በፍጥነት እየሰሩ ነው።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን እየተለመደ የመጣ አዲስ የሥራ ባሕል ተፈጥሯል። 24/7 ተሰርተው ያለቁ ፕሮጀክቶች ለምስክርነት የቆሙ ህያው ሃውልቶች ናቸው። በተለይም በመንግሥት የተገነቡት አዳዲስ ፓርኮች፣ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ እና የእግረኛ መንገዶች ፕሮጀክቶች በትኩረት ከተሰሩ በፍጥነት መጠናቀቅ እንደሚችሉ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።
ይህ የኮሪደር ልማት በተያዘለት አጭር የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል ያሉ አመራሮች ከሠራተኞች ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን እና ግንባታው በስኬት እየተከናወነ አንደሆነ ምክትል ከንቲባው አቶ ጃንጥራር ዓባይ ገልጸዋል። በኮሪደር ልማቱ የሚካሄዱት የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገዶች፣ የታክሲና የአውቶቡስ መናኸሪያዎች ከተማዋን በሚመጥን መልኩ እየተገነቡ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ፍጥነትን ከውበት አቀናጅተው ሁሉንም ኮሪደሮች በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በግስጋሴ ላይ ናቸው።
የኮሪደር ልማቱ ሠራተኞች 24/7 በትጋት ላይ ናቸው። ያላቸው ጊዜ ዛሬ ብቻ ሳይሆን ‘አሁን’ ብቻ ይመስላል። ለአፍታ ቆሞ የሚታይ ሠራተኛ አይስተዋልም። ሁሉም እንቅስቃሴ ላይ ነው። ፕሮጀክትን በጊዜው እና በጥራት ከማድረስ አኳያ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሆን በሚችል መልኩ ሌት ከቀን በመስራት ላይ ናቸው። ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እየተስተዋለ ያለው አዲስ የሥራ ባሕል ማቆጥቆጥ በመላው አገራችን ሊቀዳ እና ሊባዛ የሚገባው መሆኑን ያስገነዘቡት። አመራሮች ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በየዕለቱ እንደሚከታተሉ እና ሠራተኞችም ሌሊቱን ሙሉ ሥራ ላይ ሆነው መታዘባቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያን ዕድገት እውን ለማድረግ ይህ መንገድ ብቸኛው አማራጭ ነው፤ በሣምንት አምሥት ቀን፣ በቀን ስምንት ሠዓት ብቻ በመስራት ኢትዮጵያን የሚያህል አገር መለወጥ አይቻልም ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም መንግሥት ‘የገጠር መንግሥት ነኝ፣ ከተማው አይመለከተኝም’ ሲል የኖረው ከተማ መምራት ከባድ በመሆኑ ነው፤ ይሁን እንጂ አሁን በተጀመረው ስኬታማ ጉዞ ‘እኛም ከተማ መምራት እንደምንችል ያሳየንበት፤ ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ለማዛመት የሚያስችል ልምድ እና እውቀት የተገኘበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።
ከውበት ባሻገር
ባለፉት ጥቂት አሥርት ዓመታት የሰዎች ወደ ከተሞች የሚደረግ የጉዞ ፍላጎት በመጨመር ላይ ይገኛል። ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ መንገደኞች ልዩ የሆኑ የባሕል፣ የታሪክ እና የመዝናኛ ትዕይንቶችን ለማየት ወደ ዓለም ከተሞች ይጎርፋሉ።
የከተማ ቱሪዝም ዕድገት የጉዞ እና የከተሞችን ልምድ ለውጦታል። ይህ አዝማሚያ እየተሻሻለ ሲመጣ የከተማ ቱሪዝም መንገደኞችንም ሆነ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ በከተማ ቱሪዝም የሚቀርቡትን ዕድሎች ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ለዜጋው ብሎም ለቀጣዩ ትውልድ የተሻሉ፣ የሚያምሩ እና ወጥነት ያላቸውን ከተሞች መፍጠር እንደሚቻል የዘርፉ ምሁራን በጥናቶቻቸው ያትታሉ።
የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) እንደገለጸው ባለፉት አሥርት ዓመታት የከተማ ቱሪዝም በከፍተኛ ደረጃ አድጓል። እ.ኤ.አ በ2019፤ በከተሞች ውስጥ የሚገኙ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻዎች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በሚሆን ድግግሞሽ ተጎብኝተዋል። እነዚህ የከተማ መዳረሻዎች ከጠቅላላው የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ፍሰት ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነውን ይሸፍናሉ። የከተማ ቱሪዝም በሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት በአማካይ ከ5 እስከ 6 በመቶ በየዓመቱ እንደሚያድግ ይገመታል።
ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ የዘመን ስሌት በ2021 በድምሩ 518 ሺህ ቱሪስቶችን በማስመዝገብ ከዓለም በ67ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ወርልድ ዴታ አስነብቧል። በዚሁ ዓመት ከቱሪዝም ዘርፍ ብቻ 2 ነጥብ 60 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ይህም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 2 ነጥብ 1 በመቶውን ይሸፍናል። እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ የዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻዎች 31 በመቶ ድርሻ ይዟል።
አዲስ አበባ 138 ዓመታትን ያስቆጠረች ጥንታዊት ከተማ ነች። ባሳለፈችው የዕድገት ጎዳና፣ በጠረገችው የልማት ትልም ሳቢያ በርካታ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ሆናለች። በተጨማሪም አዲስ አበባ የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች፣ ቆንስላዎችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ መቀመጫ ድንቅ እና ውብ ከተማ ብትሆንም እንደ ዕድሜዋ ያልዘመነች፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ ያልሆነች ከተማ እየተባለች ትተቻለች። በዚህ ሳቢያ ቱሪስቶች እንደ መሸጋገሪያ እንጂ እንደ መዳረሻ ሳይቆጥሯት ለረጅም ጊዜ የቱሪዝም ባይተዋር ሆና ከርማለች።
ቱሪስቶች ወደ ሌሎቹ የአገሪቷ የቱሪስት መዳረሻዎች ሲያልፉ ሆቴሎቿን ለማረፊያነት ቢጠቀሙም፣ ምግቦቿን ለመሰንበት ቢቀማምሱም እሷነቷን ፈልጎ የሚመጣ ቱሪስት የላትም ሲሉ አስጎብኚ ድርጅቶች ጭንቀታቸውን ሲገልጹ ከራርመዋል። ይህም ለሥራቸው ውጤታማነት እና ቅልጥፍና እንከን እንደፈጠረባቸው ሲያስረዱ ይደመጣሉ። ይሁን እንጂ በቅርቡ ከተማዋን ለማዘመን፤ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማ አስተዳደሩ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማዋ ካንቀላፋችበት እንድትነቃ፣ ማለፊያ ብቻ ሳትሆን ማረፊያ እንደሚያደርጋት ተስፋ ተጥሎበታል።
አዲስ አበባ አሁን ጎዳናዎቿን ገላልጣ፣ በፓርኮቿ፣ በሙዚየሞቿ እና በምቹ ጎዳናዎቿ ለሚመለከቷት ሀሴት የምትፈጥር አዲስ አበባ ሆናለች። በጅምር ላይ ያሉት የልማት ኮሪደሮች ሲጠናቀቁም አዲስ ውበት፣ አዲስ ሕይወት እንደምትፈጥር ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ መንግሥታዊ እንግዶች ወደ መዲናይቱ ሲመጡ፤ እንደ መንግሥት ለአንድ ሠዓት እንኳን ከሸራተን ውጭ እንዲያዩ እና እንዲጎበኙ የሚያስችል መዳረሻ እንዳልነበረ አንስተው፤ አሁን በመዲናዋ በሁለት እና ሦስት ቀን ተጎብኝተው የማያልቁ መዳረሻዎች መኖራቸውን ነው የገለጹት።
የመልሶ ግንባታው አንዱ ገጽታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማስፋት፣ የሕዝብ መገልገያ ቦታዎችን ማሻሻልን ያለመ ጭምር ነው። በከተማዋ የተገነቡት ፓርኮች፣ የታዳጊዎች መዝናኛ ቦታዎች፣ የስፖርት መጫወቻ ሜዳዎች እና ሌሎች የጋራ መጠቀሚያ ስፍራዎች በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች ማኅበረሰባዊ እርካታ መፍጠር ያስቻሉ ናቸው። ይህም የከተማዋን ውበት ከማሻሻል ባለፈ ማኅበራዊ መስተጋብርና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚያበረታታ ነው።
አዲስ አበባ ውብ እና ፅዱ ከሆነች፤ የቱሪዝም ኮንፈረንስ መቀመጫነቷ ይቀጥላል። እንጦጦን
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ያለማችው አዲስ አበባ፤ ሸገር ፓርክን፣ አንድነት ፓርክን፣ አድዋ ሙዚየምን ለውበቷ ተጨማሪ ጌጥ ያደረገችው አዲስ አበባ፤ የልማት ኮሪደሮቿን ስታጠናቅቅ አብዛኞቹ የልማት እንቅስቃሴዎች የልኬት ደረጃቸውን የጠበቁ እንደሚሆኑ አቶ ጃንጥራር አመላክተዋል። ቱሪስቶች በከተማዋ እንዲቆዩ የሚያስችል ዕድል ይፈጠራል፤ በዚህም የነዋሪው የኑሮ ደረጃ የተቃና መስመር ይይዛል።
ለቱሪስት መዳረሻነት የሚሆኑ በርካታ ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ ሐብቶችን የያዘችው አዲስ አበባ፤ በተለይም ታሪካዊ ቦታዎች፣ ቴአትር ቤቶች እና ሙዚየሞች፣ ሆቴሎች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች እንዲሁም የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎችን በጉያዋ አቅፋለች። ይሁን እንጂ እነዚህ ብቻቸውን የጎብኚዎችን ቀልብ አይስቡም። ንጹህ እና በቂ የትራንስፖርት መንገዶች፣ ምቹ እና ውብ የእግረኛ ጎዳናዎች ከሌሏት የቱሪዝም ፍሰቱ ፈተና እንጂ ‘መና’ ሊወርድለት አይችልም። ጥራት ያለው መሰረተ ልማት ለቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። ይሁን እንጂ አዲስ አበባ ለእዚህ ሳትታደል ለረጅም ጊዜያት ቆይታለች። ምቹ ያልሆኑት መንገዶቿ፣ የቆሸሹት የጎዳና መልኮቿ ዓይንም ልብም መሳብ ሳይችሉ ቀርተዋል።
አሁን ይህን መልኳን ለመቀየር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የቱሪዝም ዕድገቱንም እያፋጠኑት ይገኛሉ። ኢትዮጵያ እምብዛም ተጠቃሚ ያልሆነችበት የአገር ውስጥ ቱሪስት መፍጠር መነቃቃት እያሳየ ነው። የከተማዋ አስተዳደር የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን፤ ባለፉት አሥር ወራት ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች የሕዝብ መዝናኛ ፓርኮችን መጎብኘታቸውን ገልጿል። በቅርቡ በተሰሩ እና በተጠናቀቁ ውስን ሐብቶች ከ800 ሺህ በላይ የአገር ውስጥ ቱሪስት መፍጠር ከተቻለ፤ የልማት ኮሪደሮቹ ሲጠናቀቁ ከአገር ውስጥ ባሻገር አሃዙ ከፍ ያለ የውጭ አገር ጎብኚ መፍጠር እንደሚችሉ ይታመናል።
አዲስ አበባ ከጄኔቫ እና ኒው ዮርክ ቀጥላ ሦስተኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል ነች። ከ130 በላይ ኤምባሲዎች፣ የበርካታ አገራት ቆንጽላ ጽ/ቤቶች የሚገኙባት፣ እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ ኢጋድ ዋና መስሪያ ቤቶቻቸውን ያሳረፉባት ከተማ መሆኗን የሚገልጹት የከተማ ፕላን ባለሙያው አማን አሰፋ (ዶ/ር)፤ ይሁን እንጂ መዲናዋ እነዚህን ሁሉ ዕድሎች በጉያዋ ብትይዝም ከቱሪዝም የምታገኘው ገቢ እምብዛም ነው ይላሉ። ይሁንና አሁን የቆሸሹ የነበሩ ቦታዎች ለምተው ማረፊያ ስፍራዎች እየሆኑ፤ በእነዚህ አካባቢዎችም የከተማ ጽንሰ-ሃሳብ እየተፈጠረ መምጣቱን ያብራራሉ።
‘በሁሉም፣ ከሁሉም እና የሁሉም’
አካታች ከተሞችን መገንባት በዘላቂ ክትመት ውስጥ ቁልፍ ከሆኑ መርሆዎች አንዱ የሆነውን ማኅበራዊ ውህደት እና ፍትሃዊነትን ያመጣል። ይህም ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የመኖሪያ ቤት፣ የጤና እንክብካቤ፣ ትምህርት እና የሕዝብ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡ ከዚህ አኳያ በኮሪደር ልማቱ እንደ ግብ የተወሰደው ምቹ ከባቢዎች በመፍጠር እና በማሻሻል የገቢ አለመመጣጠንን እና ሰፊ የማኅበራዊ ልዩነቶችን የሚፈቱ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነዋሪዎች የአገርን እንዲሁም የዜጎችን ሕይወት በሚቀይሩ የኢኮኖሚ ልማቶች ውስጥ እንዲሳተፉ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የባለቤትነት ስሜት እና የኅብረተሰቡን አንድነት ማጎልበት የሚያስችሉ ናቸው።
በተጨማሪም ለተለያዩ ባሕሎች፣ የአስተሳሰብ ዳራዎች እና ማንነቶች አካታች እንዲሆኑ የሚያስችል ነው። የኮሪደር ልማቱ የመድብለ ባሕላዊ ዝግጅቶችን ለመደገፍ፣ ባሕላዊ ውይይቶችን ለማስተዋወቅ እና የሁሉንም ማኅበረሰብ ባለቤትነት በማግዘፍ ብዝሃነት እና ውህደትን የሚያዳብሩ ይሆናሉ። አካታች የሕዝብ ቦታዎችን፣ የባሕል ተቋማት እና የማኅበረሰብ ማዕከላትን መፍጠር ነዋሪዎች እንዲገናኙ፣ እንዲማማሩ እና እርስ በእርስ እንዲተሳሰቡ ዕድሎችን ያሰፋል። ከተሞች ብዝሃነትን በማክበር የሁሉንም ነዋሪዎች ሕይወት የሚያበለጽግ የበለጠ ንቁ እና የተቀናጀ ማኅበራዊ ትስስር መፍጠር ይችላሉ።
የእግረኛ መንገድ ባለመኖሩ በየቀኑ ዜጎችን በትራፊክ አደጋ ማጣት የተለመደ ነው። በአዲስ አበባ እ.አ.አ ከ2018-2020 ብቻ፤ 8 ሺህ 458 የመንገድ ትራፊክ አደጋዎች መመዝገባቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። ከእነዚህ አደጋዎች መካከል 1 ሺህ 274 አደጋዎች ዜጎችን ለሕልፈት ሲዳርጉ፣ 7 ሺህ 184 አደጋዎች ደግሞ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
ነገን የሚመሩ ሕፃናት፣ የአገር ተስፋ የሆኑ ልጆች፣
ባለ ራዕይ ወጣቶች፣ በካበተ ልምዳቸው አገር የሚያንጹ ጎልማሶች እና አዛውንቶችን በየቀኑ በዚህ አስከፊ አደጋ እናጣቸዋለን። ለአደጋው በከፍተኛ ደረጃ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለው ምቹ የእግረኛ መንገድ እና መተላለፊያ አለመኖሩ መሆኑን የወርልድ ባንክ ቡድን አባል የሆነው ዓለም አቀፍ የመንገድ ደህንነት ተቋም (GRSF) ገልጿል።
በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ ባለው የኮሪደር ልማት በአግባቡ እየተሰሩ ያሉ ምቹ እና አካታች የእግረኛ መንገዶች፤ ለአገር የሚበጁ ዜጎችን የመታደግ ሚናቸው ከፍተኛ እንደሆነ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ይህንን በተመለከተ ባነሱት ሃሳብ፤ “በየቀኑ ከምናጣቸው ወገኖች አንጻር፤ ለዚህ የእግረኛ መንገድ የምናወጣው ወጪ እና ድካም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም” ሲሉ የእግረኛ መንገዱን በአካታችነት መገንባት የሰው ሕይወት ማዳን መሆኑን አመላክተዋል።
በአጠቃላይ የኮሪደር ልማት ሥራው ብዙ ትምህርት የተወሰደበት፣ ማድረግ እንደሚቻል የታየበት፣ የኅብረተሰቡ የልማት ጥማት እና ተባባሪነት የታየበት፣ ኢትዮጵያ በራሷ ልጆች፣ በራሷ ሐብት አገር መቀየር የሚያስችል አቅም እንዳላት የታየበት አጋጣሚ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
አሳታፊነት
የማኅበረሰብ ተሳትፎ የማንኛውም የከተማ ልማት ፕሮጀክት ወሳኝ ገጽታ መሆኑ ይታመናል። በተለይ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ መልክ ያላት አድርጎ ለመገንባት የየአካባቢዋ ነዋሪዎች ፍላጎቶች ቅድሚያ ግምት ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ኅብረተሰቡን በዕቅድ እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ማሳተፍ አስፈላጊ ነው።
በመሆኑም የልማት ኮሪደር ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከነዋሪዎች ጋር ምክክር መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ መረጃ ይጠቁማል። በተለይም በመንግሥት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ለነበሩ ነዋሪዎች ፅዱ እና ምቹ የሆኑ የመኖሪያ ቤቶች ተገንብተው መተላለፋቸውን፣ የንግድና የመስሪያ ቦታ ለነበራቸው ነዋሪዎች በተገቢ ቦታ የተሻለ የንግድ ቦታ እንዲሁም የግል ይዞታ ለነበራቸው ነዋሪዎች ካሳ እና ምትክ ቦታ ተሰጥቷል። የልማት ኮሪደሩ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በሙሉ የተነሱ ሲሆን፤ ለሁሉም ምትክ መኖሪያ ተሰጥቷቸዋል። ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ አንድም መኖሪያ ቤት ሳይረከብ የወጣ ነዋሪ አለመኖሩን ነው የገለጹት።
በመልሶ ማልማት ውስጥ፤ በአካባቢው የነበሩ ነዋሪዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻቸው በማይጎዳበት መልኩ ወደ ሌላ አካባቢ ማዘዋወር ውስብስብ እና ጥንቃቄ የሚጠይቅ ክስተት ነው፤ ከተነሺ ነዋሪዎች ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት ዕቅድ፣ ምክክር እና ቅንጅት ይጠይቃል። እንደ ልማት ኮሪደር ያለ መጠነ ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ ፕሮጀክት በሚከናወንበት ጊዜ በለውጥ የሚነሱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ደህንነትና መብት ቅድሚያ ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት የገለጹት ምክትል ከንቲባው፤ በዚህ የግምገማ ሂደት ውስጥ የኅብረተሰቡ አባላት፣ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ድምፃቸውን፣ ስጋታቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ከግምት በማስገባት መከናወኑን አስረድተዋል።
የልማት ተነሺዎች ወደ ሌላ ስፍራ በሚዘዋወሩበት ጊዜ አስተማማኝ፣ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የቤት አማራጮች ከመቅረባቸው በተጨማሪ ንብረቶቻቸውን ወደ አዲሱ መኖሪያቸው ማጓጓዣ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶቻቸው እንዳይቋረጡ፣ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ፣ የትምህርት አገልግሎት እንዳያጡ፣ ነዋሪዎች በአዲስ ማኅበረሰብ ውስጥ ሕይወታቸውን እንዲገነቡ በሚያስችል መልኩ መከናወኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
አካታች እና ቀጣይነት ያለው ሁለገብ ከተማ ለመገንባት ከአስተዳደራዊ ሥራ በተጓዳኝ የሁሉንም ነዋሪዎች ደህንነት እና ክብር ማስቀደም አስፈላጊ ነው። ነዋሪዎች ፍላጎቶቻቸው እና ስጋቶቻቸው በልማት ሂደት ውስጥ እንዲፈቱ ኅብረተሰቡን ማሳተፍ ግዴታም ጭምር ይሆናል። በተለይም ማኅበረሰቡ በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ሲሳተፍ በአካባቢው በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማው ያደርጋል።
በልማት ኮሪደር ሥራዎች ውስጥ ኅብረተሰቡ የልማቱ አጋር መሆኑን አሳይቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንዳሉት፤ “እነዚህ ሁሉ የልማት ሥራዎች ሲሰሩ ኅብረተሰቡ ቆሞ የሚመለከተው፣ ሱቁ ሳይዘጋበት፣ ጥቅሙ ሳይነካበት ቀርቶ አይደለም። ይልቁንስ እየተሠራ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ያለው ሥራ የለበጠ ሳይሆን ትልቅ መሆኑን በመረዳቱ ነው” ብለዋል።
ከራስ ለራስ የተሰጠ ስጦታ
መሠረተ ልማት የአንድን ከተማ ዕድገትና ስኬት በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ከተሞች እንደ አዲስ በሚገነቡበት ጊዜ የመሠረተ ልማት አውታሮች የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ያላቸው እንዲሆኑ እና ከተሜነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆን እንዳለባቸው አማን አሰፋ (ዶ/ር) ይናገራሉ። የከተማ ሕይወት የጀርባ አጥንት የሆኑት የመጓጓዣ ሥርዓቶች፣ የሕዝብ መገልገያዎች እና የመገናኛ አውታሮች በመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ውስጥ መካተት እንዳለባቸውም እንዲሁ።
ከሌሎች የአገሪቷ ክፍሎች የተሻለ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን በመሻት የሚመጣው ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም እያደገ የሚሄደውን የሕዝብ ፍላጎት ለማሟላት መሠረተ ልማትን ማሻሻል፣ ማስፋፋት እና በየጊዜው ከከተማ ዕድገት ጋር እየፈጠነ ያለውን የቴክኖሎጂ ዝማኔ መለዋወጥ የመዲናዋን ቀጣይ ስኬት ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። የኮሪደር ልማቱ እነዚህን ሁሉ ፍላጎቶች ሊያሟላ በሚችል መልኩ በመከናወን ላይ ይገኛል።
የትራፊክ መጨናነቅን ለማቃለል፣ ዘላቂነት ያለው እንቅስቃሴ ለማስፋፋት እና በከተማ ውስጥ ያለውን መስተጋብር ለማጎልበት የትራንስፖርት ሥርዓቶችን ማሻሻል ወሳኝ መሆኑን የሚገልጹት አማን አሰፋ (ዶ/ር)፤ በሕዝብ ማመላለሻ፣ በብስክሌት መንገድ እና ለእግረኛ ተስማሚ መሠረተ ልማት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ የነዋሪዎችን አጠቃላይ የሕይወት ጥራት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ያብራራሉ።
ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይም፤ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የፍጆታ አገልግሎቶችን እንደ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ እና የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት መዘመን ለአንድ ከተማ የዕለት ተዕለት ተግባር አስፈላጊ በመሆኑ የኮሪደር ልማቱ እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች በሚገባ ይመልሳል ብለዋል።
ከተሞች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ዕድገትን የሚያመቻቹ መሆን አለባቸው። በዘላቂነት እንዲለሙ ማድረግ ደግሞ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑንም የሚጠራጠር አይኖርም። ከተሞችን በማደስ ሐብት የማፍራት፣ የኑሮ ጥራትን የማሳደግ፣ ጎብኝዎችን በዘላቂነት የማስተናገድ ሥልጣን ሁሉም ዜጋ የሚጋራው ነው።
የበርካታ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምርትና ፍጆታ ማዕከሏ አዲስ አበባ፤ ሐብትና ዕድል ይዘው የመጡ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ በረከቶችን በውስጧ ይዛለች። በአንጻሩ በሽታ፣ ወንጀል፣ ብክለትና ድህነትንም በጉያዋ አቅፋ አስቀምጣለች። ይህን ኢ-ፍትሃዊነት፣ ያልተደላደለ ሕይወት፣ ያልተገራ ዕድገት፣ በውበት ያልታጀበ ኑሮ፣ በእኩልነት ያልባረከ ጉዞ ለማስቀረት የከተማዋ ሁለንተናዊ ዕድገት ለአንድ አካል የማይተው፤ የሁሉንም ዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚሻ ጉዳይ ነው።
መንግሥት የኮሪደር ልማቱን ሲያቅድ፣ ዕቅዱን ወደ ተግባር ለመቀየር ሲነሳ፣ ዲዛይኑን ወረቀት ላይ ሲያሰፍር ይህን ፕሮጀክት ተፈጻሚ እንደሚያደርግ በሙሉ እምነት ነው። ከዚህ ቀደም የተሰሩ መዝናኛዎች፣ ሙዚየም፣ ፓርኮች በራስ ኃይል እና አቅም ማሳካት እንደሚቻል ያስመሰከሩ፤ ይህኛውም እንዲሳካ ቀድመው የተጠረጉ መንገዶች፣ መሻገሪያ ድልድዮች፣ የክህሎት ማበልጸጊያ ትምህርት ቤቶች፣ ለስኬት አቅጣጫ ጠቋሚዎች ሆነው ያገለግሉታል። ትናንት ያልነበረው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ለዛሬ እውነት እንደበቃው ሁሉ፣ ትናንት ያልታሰቡት ፓርኮች ለዛሬ ማረፊያዎች እንደሆኑት ሁሉ፤ የኮሪደር ልማቱ ሲጠናቀቅ ለዓይን የሚማርክ ውስጥን በሀሴት የሚሞላ ውበት ይሆናል።
መውጫ
የበርካታ ከተሞች የከተማነት መስፈርት እና ገጽታ የሕዝብ ቦታዎች እና መሠረተ ልማት አስፈላጊነት ከግምት ገብተው ሲሰሩ አይስተዋልም። ይህም የከተማ ፕላን ከግለሰቦች የኑሮ ጥራት፣ ከማኅበራዊ ልማትና ከሌሎች የሰው ልጅ ደህንነት አካላት ጋር ያለውን ዝምድና ሙሉ በሙሉ ካለመረዳት የሚመጣ መሆኑን የከተማ ፕላን ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በተመሳሳይ መልኩ ማራኪ ከተሞች የሥራ ፈጠራ፣ የአዳዲስ ፈጠራዎች መነሻ እና የሠለጠነ የሰው ኃይል ባለቤቶች በመሆናቸው የከተማ ኢኮኖሚ ሊያሳድጉ የሚችሉ ኢንቨስትመንቶችን የመሳብ ዕድላቸው ሰፊ ነው። ይሁን እንጂ የከተሞች ብሎም የአገራት የፋይናንስ አቅም በማነሱ ሳቢያ፤ የከተማ ዲዛይኖች የከተማ ልማት፣ ውበት፣ ጽዳት እና ምቹነትን ሲያሳኩ አይታይም።
ከዓለም አገራት ከ90 በላይ ከሚሆኑት ጋር በአጋርነት የሚሰራው UN-HABITAT እ.አ.አ ከ1998 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር በርካታ ፕሮጀክቶችን ተፈጻሚ አድርጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈትነው ውጤታማ የሆኑ መመሪያዎችን በማዳበር የተሻሻሉ፣ ዘላቂነት ያላቸው፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊነትን ያነገቡ ከተሞች እንዲፈጠሩ የዲዛይን እና የዕቅድ ንድፎችን በማዘጋጀት አባል አገራቱን ያግዛል።
ትልልቅ ከተሞች ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የተጠጋጋ የማኅበረሰብ አኗኗር ያላቸው በመሆናቸው የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ማዕከልነትን ይዘዋል። በትልልቅ ከተሞች፤ የከተማ ፕላንን ዛሬ ላይ ችላ ማለት ወደፊት ችግሩን ለመፍታት የበለጠ ወጪ የሚጠይቅ ሁኔታን ይፈጥራል። የUN- HABITAT ጥናቶች በአጠቃላይ ከከተማ ዲዛይን ማነቆዎች ዋነኛው በአገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ በቂ ማዕቀፎችና ሕጎች አለመኖራቸው መሆኑን ያሳያል።
የኢትዮጵያ ከተሞች በመሰረተ ልማት ኮሪደሮች ዙሪያ እንዲያድጉ የሚያስችሉ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ሐብት ባለቤቶች ናቸው። ከአዲስ አበባ ባሻገር ሌሎች ከተሞችም እንደ አዲስ የዕድገት ሞተር በመሆን ብቅ እያሉ ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የከተሞች ዕድገት ቀድሞም ያልታቀደ እና ያልተቀናጀ በመሆኑ ሰፊ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ዕድሎችን እንዲያጡ ሲያደርጋቸው ቆይቷል። አዲስ አበባም በዚህ ሳቢያ ስሟን ሳትመስል ለዘመናት አንቀላፍታለች።
በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ዜጎች ፍላጎቶታቸውን እና መሻቶቻቸውን የሚያሟሉባቸው በየደረጃው በፍትሃዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሉ የገቢ አቅምና ጥሪቶች እንዲሁም እነዚህን ጸጋዎች ለመፍጠር በሚያግዙ ቁሳዊ፣ ሰብዓዊና ተቋማዊ አቅሞች፤ በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች መኖራቸውን ያትታል። ሁሉም ዜጎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ፈቀደም አልፈቀደም ለመኖር መሰረታዊ የሆኑትን እንደ ተመጣጣኝ ምግብ፣ መጠለያ፣ ንጹህ የመጠጥ ውኃ፣ መሰረታዊ የጤናና የትምህርት አገልግሎቶች ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው ማድረግ በዕቅዱ የሰፈረ ሃቅ ነው። ይህ የሚሆነው በዘላቂነት የሚለማ፣ አካታች፣ ጽዱ እና ጤናማ አካባቢ ሲኖር ነው።
በመዲናዋ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለው የኮሪደር ልማት የUN-Habitatን መስፈርቶች ባሟላ መልኩ የተመጣጠነ እና ፍትሃዊ አከታተምን በማረጋገጥ በየደረጃው የተለያዩ
ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው ከባቢዎች ተመጋጋቢ ሆነው እንዲያድጉ በማድረግ የከተማዋን የዕድገት ዕድል ማስፋት እና የሕዝቦችን የልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ በተቀናጀ መንገድ በመከናወን ላይ ይገኛል።
አዲስ አበባን መልሶ በመገንባት ሂደት ከዚህ ቀደም መንግሥት ስሟን የሚመጥን፣ ‘እንደ ስሟ አዲስ እናደርጋታለን፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እንሰራለን’ በማለት የገባውን ቃል የመፈጸም ሂደት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ይህንን መፈጸም መቻል የተፈለገውን የብልጽግና እና የዕድገት ጉዞ ለማሳካት የሚያስችል አቅም መኖሩን የሚያሳይ መሆኑንም እንዲሁ።
አዲስ አበባ ፒያሳ ያስፈልጋታል። ከተማዋ እሷን የሚመጥን መሀል ፒያሳ ያስፈልጋታል። የኮሪደር ልማቱ ከሚያልፍባቸው አካባቢዎች አንዷ የሆነችው ፒያሳ ውብ መሆን ይኖርባታል። የኮሪደር ልማት ሥራው ሲጀመር ትችቶች ተሰንዝረዋል። ሥራውን የሚያጣጥሉ ሃሳቦች ተነስተዋል። ፒያሳን ደብዛውን የማጥፋት ሥራ ነው ተብለው ተኮንነዋል። በሥራ ሳይሆን በወሬ የተጠመዱ፣ በተግባር ሳይሆን በአሉባልታ የነጎዱ፣ መፍረሱን እንጂ መገንባቱን፣ መውደቁን እንጂ መነሳቱን ለመናገር አይደፍሩም።
ፒያሳ አዲስ አበባን መስላ የተሰራች መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሰዎች ሊያይዋት የሚናፍቁ፣ ሊጎበኟት የሚጓጉላት ፒያሳ እየተገነባች ነው፤ የልማት ኮሪደር ሥራው ቀድሞ የተጠና እና ብዙ ውይይቶች ያለፉበት ሃሳብ የነበረ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ፒያሳን ለአብነት አነሳን እንጂ የመዲናዋ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ቀደም ሲል የለሙ አካባቢዎችን ካልለሙት ጋር በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ከተማ ለማድረግ ታስቦ የተተገበረ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህም ማማር በአንድነት፣ ውበት በኅብረት፣ ምቹነትን እና ቅልጥፍናን በማንገብ የUN-Habitatን ጽንሰ- ሃሳብ አጉልቶ የሚያሳይ ነው።
የኮሪደር ልማት ሥራው መነሻ እና መድረሻ ከሕዝብ ፍላጎት ጋር የተዋሃደ ነው። ከሕዝብ ጋር የተቆራኘ መሰረት አለው። የአዲስ አበባ መልክ ሲያምር፣ በነዋሪዎቿ ፊት ላይ የሚነበብ እርጋታን ይፈጥራል። የመዲናዋ ምቹነት የማኅበረሰቡን ድሎት የሚወስን ነው። የከተማዋ ጽዳት እና ውበት የነዋሪው አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤና እንዲጠበቅ የሚያስችል ነው። የአዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻነት የማኅበረሰቡን የኢኮኖሚ ሁኔታ የሚያሻሽል ቅመም ይሆናል። አዲስ አበባ ስትደምቅ፤ ነዋሪዎቿም አብረው ይደምቃሉ።
ኢኮኖሚ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ካፒታል ገበያ ምን ይዞ ይመጣል?
ምን ይዞ ይመጣል?
በመንገሻ ገ/ሚካኤል
ምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት ማለት ምንድነው? ምን ሲሟላ ነው ዕድገቱ መጣ የሚባለው? በሚለው ጉዳይ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አንስቶ በጉምቱዎቹ የምጣኔ ኃብት ጠበብቶች በርካታ ሙግቶች ቢካሄዱም በሚያነሷቸው መላምቶች ላይ ግን ድምዳሜ የለም። እንዲያም ሆኖ አብዛኞቹ የመስኩ ተንታኞች እንደሚያስቀምጡት፤ ምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት ማለት ኢንቨስትመንትን ማስፋትና ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ነው በሚል ጠበብ ያለ ድምዳሜ መከራከሪያቸውን ያቀርባሉ። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች አጠቃላይ ምጣኔ ኃብታዊ እንቅስቃሴውን በአዎንታዊ መልኩ ይቀይሩታል ተብሎም ታምኖባቸዋል። ለዚህም ደግሞ በተለምዶ Economic Factors የተባሉትን መሬት፣ ካፒታልና የሰው ኃይል በዋና ግብዓትነት ያቀርባሉ። አሁን አሁን ግን ከዚህ ቀደም በመስኩ ተንታኞች (Classical Economists) ለዕድገት አስፈላጊ ናቸው ከተባሉት ጉዳዮች በተጓዳኝ የምጣኔ ኃብት ዕድገት ያለ ጠንካራ የፋይናንስ ዘርፍ ታሳቢ አለመሆኑን ብዙዎች በወል ይስማሙበታል። በተለይም ለረጅም ጊዜ የሚካሄድ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን በፋይናንስ ለመደገፍና ውጤታማ ለማድረግ ጠንካራ የዘርፉ ተቋም እንደሚያስፈልግ ነው የሚያስረግጡት። ለዚህም ይመስላል በርካታ አገራት የካፒታል ገበያ በማቋቋም ዘላቂ ምጣኔ ኃብታዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የሚረባረቡት።
ይህንን ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያም በቀደሙት ጊዜያት በተበጣጠሰ አኳኋን የካፒታል ገበያ ሥርዓት ማከናወኗን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ያም ሆኖ በተፈለገው መልኩ ተግባራዊ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ባለመደረጉና በተያያዥ ችግሮች የተፈተነው ገበያው የኋላኋላ ሊከስም ችሏል። በቅርቡም መንግሥት የገበያውን ተፈላጊነት በማጤን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንን በአዋጅ ቁጥር 1248/2013 አቋቁሟል። በአዋጅ የተቋቋመው የካፒታል ገበያ ባለሥልጣንም የካፒታል ገበያን እውን ለማድረግ ዘመኑን በዋጁ አሠራሮች፣ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ የሕግ ማዕቀፎች በመመራት ወደ ትግበራ ገብቷል። የካፒታል ገበያውን የማደራጀት ሥራዎችን እያከናወነም ይገኛል። የካፒታል ገበያ አዋጅ መውጣቱን ተከትሎ የተማከለ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በመቋቋም ላይ ነው። በዚህ ፅሁፍ የድርሻ ገበያ በመባል የሚጠራውን የካፒታል ገበያ ፅንሰ ሃሳብና ምንነት፣ ገበያው ለሕዝብና ለአገር የሚኖረው ፋይዳ እንደሚከተለው ተዳስሶ ቀርቧል።
ቅድመ-ታሪክ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሕግ አማካሪ አቶ በእሱፈቃድ ተረፈ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥርዓት በዳግማዊ ምኒልክ ሥርዓተ መንግሥት እንደተጀመረ የተለያዩ የታሪክ ድርሳናትን ዋቢ በማድረግ ያስረዳሉ። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1897 የኢትዮ- ጅቡቲ የምድር ባቡር ሐዲድ ለመዘርጋት የ40 ሚሊዮን የፈረንሣይ ፍራንክ አክሲዮን በፈረንሣይ አገር መሸጣቸውን የታሪክ ድርሳናቱ ያመላክታሉ ይላሉ። በዚያ ዘመን በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው አቢሲኒያ ባንክ ሲመሠረት አክሲዮኖቹ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በኒውዮርክ፣ በፓሪስ፣ በለንደን እና በቪየና ተሸጠዋል። ይህም “በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ጅማሮ ተደርጎ ይወሰዳል” ይላሉ።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት እ.አ.አ በ1956 የኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጅት ለሕዝብ ሽያጭ ወጥቷል። እሱን ተከትሎ እ.አ.አ ከ1957 እስከ 1963 ባለው ጊዜ የኢትዮጵያ ጠርሙስ ፋብሪካ (Ethiopian Bottling Company)፣ ኢንዶ-ኢትዮጵያን ጨርቃ ጨርቅ፣ ኤች.ቪ.ኤ ኢትዮጵያ፣ ሳባ ጠጅ፣ ተንዳሆ ተክል እና የአዲስ አበባ ባንክ ለሕዝብ ሽያጭ ቀርበዋል። እንዲሁም እ.አ.አ በ1959 ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ለሕዝብ ሽያጭ ቀርቦ ከአክሲዮን ሽያጭ በሦስት ወራት 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር መሰብሰብ ተችሏል። አብዛኛውን አክሲዮን የገዛው ደግሞ ኤች.ቪ.ኤ የተባለው የኔዘርላንድስ ኩባንያ ነው። ጄዲቮን ፒስኬ “አክሲዮን እና የአክሲዮን ግብይት በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ ባሳተመው መጽሐፉ በአክሲዮን ግብይቱ ሕዝቡ ቀላል ሊባል በማይችል ደረጃ ተሳትፎ አክሲዮን ገዝቶ ባለድርሻ መሆኑን ሰንዶት ይገኛል።
በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በ1960 ዓ.ም በኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ (State Bank of Ethiopia) ውስጥ የአክሲዮን ግብይት መምሪያ መቋቋሙ የአክሲዮን ግብይቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። መምሪያውን ማደራጀቱ የአክሲዮን ገበያን ለማስፋፋት በመንግሥት የተወሰደ የመጀመሪያው ተቋማዊ አደረጃጀት እርምጃ እንደሆነም ይነገራል።
እ.አ.አ ከ1959 እስከ 1963 ለሕዝብ ሽያጭ በወጡ ድርጅቶች በተደረገው የአክሲዮን ግብይት 61 ሚሊዮን ብር ያህል ሲሸጥ፤ ኤች.ቪ.ኤ የተባለው የኔዘርላንድስ ኩባንያ 41 ሚሊዮን ብር አክሲዮን በመግዛት ከላይ በተጠቀሱት ድርጅቶች ለሽያጭ ከቀረበው አክሲዮን 67 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤት መሆኑን አቶ አርዓያ ደበሳይና አቶ ታዴዎስ ሐረገወርቅ “የካፒታል ገበያ ዕድገት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቁት መጽሔት ላይ ሰፍሯል።
በኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ በወቅቱ በመምሪያ
ደረጃ ሲመራ የነበረው የአክሲዮን ግብይት በ1963 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መቋቋሙን ተከትሎ፣ እ.አ.አ በ1965 የአዲስ አበባ የአክሲዮን ንግድ ማኅበር (Addis Aba- ba Share Dealing Group) በሚል ተደራጅቶ ነበር። ማኀበሩ በብሔራዊ ባንክ የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገለት በሰባት ድርጅቶች መካከል የአክሲዮን እና የቦንድ ግብይት ሲያካሂድ ቆይቷል። ድርጅቶቹም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የአዲስ አበባ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ባንክ፣ ሳቢያን ዩቲሊቲ ኮርፖሬሽን እና አልፍሬድ አቤል የሚባሉ ግለሰብ እንደነበሩ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።
የአክሲዮን እና የቦንድ ግብይቱ በድርጅቶቹ መካከል ከመካሄዱ በተጨማሪ ድርጅቶቹ ለደንበኞቻቸውም ግዥ/ሽያጭ ይፈጽሙ ነበር። ማኅበሩ ከላይ የተጠቀሱትን ድርጅቶች ጨምሮ 15 ኩባንያዎችን መዝግቦ (List- ing) አክሲዮኖቻቸውን እና የመንግሥት ቦንዶችን ሲያገበያይ ቆይቷል። ግብይቱ በግልጽ ጨረታ ይከናወን የነበረ ሲሆን፤ በማኅበሩ አባላት ኮሚቴዎች ዋጋ በየሣምንቱ እየተወሰነ የሚፈጸም፤ የግብይት ዓይነቱም ወዲያውኑ የሚፈጸም ግብይት (Spot Trade)፣ ወደፊት የሚፈጸም ግብይት (Forward Trade) እና ያለግዴታ የመግዛት ወይም የመሸጥ መብት ለገዥው የሚሰጥ የሰነድ ግብይት (Options Trade) ነበሩ። ከታሪክ መዛግብት ለመረዳት እንደሚቻለው ሁሉም የማኅበሩ አባል ድርጅቶች አክሲዮኖቻቸውን ለሕዝብ የመሸጥ ሥራ በተሳካ መልኩ አከናውነዋል። ሕዝቡ ስለ አክሲዮን ግብይት ዕውቀት ከማግኘት ባለፈ ከዘርፉም ተጠቃሚ ነበር። በዚህ ሒደት በ1960 ዓ.ም የንግድ ሕግ መውጣቱ ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ ሚና የተጫወተ ቢሆንም፤ በ1975 ማኀበሩ በሽግግር ወቅት በደርግ መንግሥት እንዲፈርስ ተደርጓል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት የተማከለ የካፒታል ገበያ ለማቋቋም ያልተሳኩ ሙከራዎች ቢደረጉም በአሁኑ ወቅት በላቀ መነሳሳት ከፍተኛ ቁርጠኝነት በማሳየትና የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ረገድ መንግሥት ብዙ ርቀት ተጉዞ የተማከለ የካፒታል ገበያ በአገራችን ሊጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች አየተሰሩ ይገኛሉ ሲሉ ያብራሩት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሕግ አማካሪ አቶ በእሱፈቃድ ተረፈ ናቸው።
የካፒታል ገበያ ምንድን ነው?
የስቶክ ማርኬትና ኢንቨስትመንት መጽሐፍ ደራሲ አቡሽ አያሌው (ዶ/ር)፤ ካፒታል ገበያ ስንል የምንጠራው በተለምዶ “ስቶክ ማርኬት” የምንለው ሲሆን፤ ካፒታል ማርኬት ገንዘባቸውን ለጊዜው ለሌላ ሰው በመሸጥ (በማከራየት) ተጨማሪ ጥቅም የሚያገኙ ሻጮች ያሉበት ነው። በሌላኛው በኩል ደግሞ ገንዘቡን ከአቅራቢዎች ማለትም ከሻጮች (አከራዮች) አስፈላጊውን ተጨማሪ ተመን በመክፈል ሌላ ሥራ ላይ በማዋል ከገዙበት ዋጋ በላይ ከፍ ያለ ጥቅም (ትርፍ) የሚያገኙ ገዥዎችን የያዘ ነው ሲሉ ያስረዳሉ። የካፒታል ገበያ ዋና ዓላማው ገንዘቡን የሚወክሉ ሰነዶችን በመሸጥ እና በመግዛት ውስጥ ተጨማሪ ገንዘብ የማግኘት ትልምን የያዘ መሆኑ ለየት የሚያደርገው ነው። ከሌሎች የሸቀጣሸቀጥ ምርቶች የሚያመሳስለውም ገንዘብ እንደ ሸቀጥ የሚገዛና የሚሸጥ መሆኑ ነው ይላሉ።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሕግ አማካሪ አቶ በእሱፈቃድ ተረፈ በበኩላቸው የካፒታል ገበያ ኩባንያዎች የረጅም ጊዜ የገንዘብ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የአክሲዮን ወይም የዕዳ ሰነድ የሚያወጡበት አሠራር ነው ይሉታል። እነዚህ ሰነዶች በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (Securities Exchange) ወይም ባልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ (Over-the- Counter Market) በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ቁጥጥርና ድጋፍ እየተደረገለት የሚገበያዩበት አሠራር ነው። አሠራሩን በመመሪያ በመደንገግ ግብይት የሚደረግበት የኤሌክትሮኒክ (የዲጂታል) መሠረተ ልማትም ተዘርግቷል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አካል የሆነው የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ተቋቁሟል የሚሉት አቶ በእሱፈቃድ፤ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ በሌሎች አገራት ካለውና በተለምዶ የስቶክ ወይም የአክሲዮን ገበያ ከሚባለው ጋር ተመሳሳይ ነው። የሰነደ መዋዕለ ንዋይ (Securities) ማለት በገንዘብ ሊተመን የሚችል ባለቤትነትን የሚገልፅ ሰነድ ማለት ሲሆን፤ ሊሸጥ፣ ሊለወጥ ወይም በዋስትና ሊያዝ የሚችል መብት የሚያቋቁም ሰነድ መሆኑን ይገልጻሉ። በእኛ አገር የሚታወቁት የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ዓይነቶች አክሲዮን፣ ቦንድ እና የግምጃ ቤት ሰነድ ናቸው።
ባደጉት አገራት የተለያዩ ዓይነት የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ይገበያያሉ። እነዚህም አክሲዮኖችን (Shares)፣ የዕዳ ሰነዶችን (Debt Instru- ments)፣ ብድሮችን (Loans)፣ ቦንዶችንና ሌሎች ወደ ኩባንያ ካፒታልነት ሊቀየሩ የሚችሉ ስምምነቶችን ያካትታል። በተጨማሪም ሁሉም በመንግሥት ወይም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የወጡና ለግብይት የሚውሉ የሕዝብ የብድር ሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን፣ ለወደፊት የሚፈጸሙ የውል ዓይነቶችን (Fu- tures)፣ ያለ ግዴታ የመግዛት ወይም የመሸጥ መብት ለገዥው የሚሰጡ ሰነዶችን (Op- tions)፣ ተዛማጅ (Derivatives) እና በጋራ የኢንቨስትመንት ፈንድ ውስጥ ያለ የድርሻ ክፍልፋይን (Units in a Collective Invest- ment Scheme) የያዙ ናቸው።
የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከማቋቋም ባሻገር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችለውን መመሪያ ወደ ትግበራ አስገብቷል። ለሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ ለተዛማጅ ውሎችና ለያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች ፈቃድ የሚሰጥበትና የሚቆጣጠርበትን “የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎች እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች የፈቃድ አሰጣጥ፣ የአሰራር እና የቁጥጥር መመሪያ” በፍትህ ሚኒስቴር በማስመዝገብ፤ “የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች፣ የተዛማጅ ውሎችና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያዎች የፈቃድ አሰጣጥ፣ የአሰራር እና የቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1009/2016
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ከሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ አውሏል።
መመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች የተዛማጅ ውሎች እና ያልተማከለ የጠረጴዛ ዙሪያ ገበያ ፈቃድ ለማውጣት መሟላት ስለሚገባቸው መስፈርቶች፣ ገበያው አባላቱን መቆጣጠር የሚያስችለው የውስጥ ደንብ በባለሥልጣኑ አስፀድቆ ማውጣት እንደሚገባው፣ ለባለሥልጣኑ እንዴት ሪፖርት እንደሚያቀርብና በአጠቃላይ አሰራሩ ምን መምሰል እንዳለበት ደረጃዎችን አስቀምጧል።
የመንግሥትና የግል ድርጅቶች ገበያውን በመጠቀም የድርጅቶችን የድርሻ እና የብድር ሰነዶች በመሸጥ እና ገንዘብ በመሰብሰብ ፕሮጀክቶችን ለመሥራት አቅም ለመፍጠር እንዲሁም የድርሻ ወይም የብድር ሰነድ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ባለሃብት ፈቃድ ካለው ገበያ አስፈላጊው ቁጥጥርና ግልጸኝነት በተሟላበት የግብይት አሰራር ፈቃድ ባለው ተገበያይ አማካኝነት የተፈቀዱ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለመግዛት እና ለመሸጥ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። ይህም በተበታተነ መልኩ የሚደረገውን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ወደ አንድ ፈቃድ ወደሚሰጠው እና ቁጥጥር ወደሚደረግበት ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በማምጣት ዘርፉ ለተዋናዮች እና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ መመሪያ በመቋቋም ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ አክሲዮን ማኅበር አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች ሲያሟላ ፈቃድ በመስጠት ሥራ ማስጀመር የሚያስችል መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።
የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አሰራር
የካፒታል ገበያ እንደየአገሩ ሁኔታ ግብይቱንና ገበያውን ለመቆጣጠርና ለመደገፍ በመንግሥት በተቋቋመ አካል ቁጥጥር የሚደረግበት ነው። አሠራሩን በተመለከተም ዓለም አቀፍ የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ተቆጣጣሪዎች ድርጅት (In- ternational Organization of Securities Commissions-IOSCO) የሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን የቁጥጥር ዓላማዎች መሠረት በማድረግ የሚከናወን ነው። የባለሥልጣኑ የሕግ አማካሪ አቶ በእሱፈቃድ ተረፈ እንዳብራሩት፤ የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 በግልፅ ተቀምጧል። ባለሥልጣኑ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ግብይት ለሚከናወንበት ገበያና ለገበያው ተዋናዮች ፈቃድ መስጠት፣ ፈቃድ መሰረዝና ማገድ፣ ሰነደ መዋዕለ ንዋይን መመዝገብ (Securities Registration)፣ በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ የሚከናወነውን የምዝገባና ከምዝገባ የመሰረዝ ሥራ መቆጣጠር (Supervise Listing & Del- isting)፣ የገበያ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ በገበያው ተሳታፊዎች በሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል ትስስር መፍጠር የሚያስችል የመረጃ ቴክኖሎጂ አውታሮችን በማበልፀግ የገበያ መረጃ ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍና እንዲሠራጭ ማድረግ በአዋጁ ከተዘረዘሩት መካከል ይጠቀሳሉ።
እንዲሁም ለሽያጭ የሚቀርቡ አክሲዮኖችና ቦንዶችን ለግብይት ምቹ እንዲሆኑ በኤሌክትሮኒክ ዓይነት የሚያዙበትንና የሚተላለፉበትን መንገድ ማመቻቸት፣ የካፒታል ገበያ ተሳታፊዎችን ሒሳብ የሚሠሩ ኦዲተሮችን መሥፈርት በማውጣትና በመለየት መመዝገብ፣ የኢንቨስተሮችን ንቃት ማሳደግ፣ አስተዳደራዊ ዕርምጃ መውሰድን ጨምሮ አዋጁን ለማስፈጸም የሚያስችሉ መመሪያዎችን የማውጣትና የማስፈጸም ሥልጣን ተሰጥቶታል።
የአክሲዮን ገበያ እንደ ማንኛውም ንግድ በጥንቃቄ እና በዕውቀት ካልተመራ ኪሳራ ሊያመጣ የሚችል ነው የሚሉት የሕግ አማካሪው፤ ለምሣሌ በምሥረታ ላይ ከሚገኝ ወይም ካፒታሉን ለማሳደግ ከወሰነ አንድ የሕዝብ ኩባንያ (Public Company) አክሲዮን ሊገዛ የሚፈልግ ሰው አስቀድሞ ድርሻ ስለሚገዛበት ድርጅት በቂ መረጃ ሊኖረው ይገባል። አክሲዮን ገዥው ይህን መረጃ ሊያገኝ የሚችለው ከአክሲዮን ማኅበሩ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ነው። መግለጫው በካፒታል ገበያ አዋጅና በረቂቅ መመሪያው መሠረት ባለሥልጣኑ ፈቃድ በሰጠው ባለሙያ የተዘጋጀና ስለአውጪው ድርጅት አጠቃላይ ቁመና፣ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ፣ ኦዲት ሪፖርት፣ ትርፍ፣ ዕዳና ሌሎች መሠረታዊ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ ሆኖ ድርጅቱ ይህንኑ ለባለሥልጣኑ አቅርቦ ያስፀደቀና ያስመዘገበ መሆን አለበት። ይህም በባለሥልጣኑ ፀድቆ ሲመዘገብ ለሕዝብ ይፋ የሚወጣ በመሆኑ አክሲዮን ገዥዎች ግብይት ከመፈጸማቸው በፊት ስለሚገዙት ሰነድ ሙሉ መረጃ ኖሯቸው ግብይት መፈጸም እንዲችሉ ዕድል ይፈጥርላቸዋል።
ከዚህ በፊት ለሽያጭ የቀረቡና አሁን ገበያ ላይ የሚገኙ ነባር አክሲዮኖች የሚመዘገቡበት ሁኔታ ከላይ በተጠቀሰው ረቂቅ መመሪያ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል። ረቂቅ መመሪያው ነባር በገበያው የሚገኙ የሕዝብ ኩባንያ አክሲዮኖች ይህ ረቂቅ መመሪያ በፀደቀ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአውጪው ድርጅት በኩል በባለሥልጣኑ መመዝገብ እንዳለባቸው ይደነግጋል። ነባር አክሲዮን ያላቸው የሕዝብ ኩባንያዎች ሰነዶቹን ሲያስመዘግቡ በምሥረታ ላይ እንዳሉ፣ ወይም ካፒታላቸውን ለማሳደግ እንደወሰኑ የሕዝብ ኩባንያዎች የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። ይልቁንም የማቋቋሚያ ሰነዶቹን፣ የተቋቋመበትን ዓላማ፣ አጠቃላይ በድርጅቱ የወጡ ሰነዶችንና የተከፈለ ካፒታል፣ የድርጅቱን አመራሮች ቁመና፣ የሰነዶቹን አጭር መግለጫ፣ የአክሲዮን መደቦቹን (Class of Shares) ዓይነት፣ አጠቃላይ ካፒታል፣ ባለ አክሲዮኖቹን፣ ያለፉት ሦስት ዓመታት የኦዲት ሪፖርትና ሌሎች መሠረታዊ መረጃዎችን ያካተተ የነባር አክሲዮን ደንበኛ ሳቢ መግለጫ (Non-Offering Prospectus) በማዘጋጀት ለባለሥልጣኑ አቅርቦ ማስፀደቅና ማስመዝገብ ይጠበቅበታል። ይህ መግለጫ በዓይነቱ ከደንበኛ ሳቢ መግለጫ የተለየና አነስተኛ ግዴታዎችን የሚጥል ሲሆን፤ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 447 ከተገለጸው ዝቅተኛ መመዘኛዎችን ከሚያስቀምጠው መግለጫ በተጨማሪ ከላይ የተዘረዘሩትን ሌሎች የአውጪው ድርጅት መረጃዎችን የሚያካትት ነው።
የምዝገባ ሥርዓቱ የአውጪውን መረጃዎች ባለማወቅ አክሲዮን በሚገዙ ሰዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ሊያስቀር ይችላል። ይህ ሥርዓት ግልጽነትን በመፍጠር በአጠቃላይ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያውንና ተዋናዮቹን ከጉዳትና ከውድቀት ለመጠበቅ ይረዳል። በመሆኑም ሕዝቡ የምዝገባ መሥፈርቶችን ሳያሟሉና የደንበኛ ሳቢ መግለጫቸውን በባለሥልጣኑ ሳያስፀድቁ ለሕዝብ አክሲዮን ለመሸጥ ካወጡ ድርጅቶች አክሲዮን በመግዛት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይላሉ አቶ በእሱፈቃድ ተረፈ።
የካፒታል ገበያና ምጣኔ ኃብታዊ አንድምታው
የዓለም ባንክ በቅርቡ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያን ጨምሮ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ለውስጥ የልማት ፍላጎት ከሚያስፈልጋቸው ፋይናንስ በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦችን በቀጣይ ስድስት ዓመታት ለማሳካት ከ8 እስከ 10 ትሪሊዮን ዶላር ፈሰስ ማድረግ እንዳለባቸው ያሳያል። ይህንን ተከትሎ አገራት ለልማት ሥራዎች የሚውሉ አስተማማኝና
ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ፍሰት እንዲኖር የሚያስችሉ ሥልቶችን መቀየስ እንዳለባቸው ገልጿል። በተለይም የግሉ ዘርፍ የፋይናንስ ፍሰትን ለማጠናከር የሚያስችለውን የካፒታል ገበያ መዘርጋት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን ነው ባንኩ ምክረ ሃሳብ ያቀረበው። በኢትዮጵያ አሁን ሥራ ለመጀመር በመንደርደር ላይ ያለውን የካፒታል ገበያ የፋይናንስ ፍሰት በማሳለጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል። ያም ብቻ ሳይሆን በድምሩ በኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት ላይ በርካታ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ነው የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልጹት።
ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ መፍጠር
የካፒታል ገበያ ከሚያመጣቸው በርካታ ጥቆሞች አንዱ በዘርፉ ጠንካራ ሥርዓት በመዘርጋት የሰነደ መዋዕለ ነዋይ (Securities) ግብይትን የተሳለጠ ማድረግ ነው። የተዘረጋው ሥርዓት በተለይም በገበያው የሚሳተፉ ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት (disclosure) መግለጫ እንዲያመጡ መገደዳቸው ኢንቨስተሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያሳልፉ ከማድረጉ ባሻገር የገበያ መጭበርበርን ይቀንሳል። በተመሳሳይ በገበያ ለሚሳተፉ ኢንቨስተሮች ሥርዓቱ ሕጋዊ ከለላ መስጠቱ ኢንቨስተሮች በገበያው ያላቸው ተሳትፎ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጡበት ሌላኛው ምክንያት ነው። በሌላ በኩል በተበጣጠሰ አኳኋን የሚካሄደውን የአክሲዮንና መሰል ሽያጮች በተማለከ አኳኋን ለማስኬድና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚጋጥሙ ወጪዎችን ለመቀነስም ያስችላል።
ዶክተር አቡሽ ይህንን ሃሳብ በማጠናከር፤ በአገራችን በግለሰቦች እጅ የሚገኘው ገንዘብ ተሰብስቦ ትልቅ ኃይል መሆን የሚችል ነው። ይሁን እንጂ በተቀናጀና የሕግ ተጠያቂነት ባለው መልኩ የሚሠሩ ኮርፖሬሽኖች እንደ ልብ ስለሌሉ ይህን ሀብት አሰባስቦ ከፍተኛ የካፒታል እጥረት ላለበት ለግሉ ዘርፍ (sector) እንዲደርስ ማድረግ አልተቻለም ይላሉ። የተደራጀ ስቶክ ማርኬት ባለመኖሩ በርካታ ሰዎች ከኮርፖሬሽኖች አክሲዮን ገዝተው ሀብታቸውን ለማሳደግ ተስፋ ይቆርጣሉ። ከዚህም በተጨማሪ ኢንሹራንሶች የመንግሥትና የግል የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲዎች ያሉት ደግሞ በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ጥሬ ብር ታቅፈው ገንዘቡን ለግሽበት (Inflation) እያስመቱት ነው። በአንፃሩ ገንዘቡን ቢያገኙት የማደግና የመስፋፋት ዕድሉ ያላቸው በርካታ አነስተኛ የግል ድርጅቶች በአገራችን እንደ መኖራቸው ስቶክ ማርኬትን በማቋቋም ይህን ሀብት አስተሳስሮ ወደ ተሻለ ልማት መቀየር አልተቻለም ይላሉ። የስቶክ ማርኬትን ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ እነዚህን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከመፍታት አኳያ ሁነኛ አማራጭ ነው። በመሆኑም፤ የካፒታል ገበያው በተለያዩ የዘርፉ ተዋናዮች መካከል አስተማማኝ የፋይናንስ አመቻች አካል በመሆኑ የፋይናንስ ፍሰቱን ጤናማና ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ ያደርገዋል።
በተመሳሳይ አቶ በእሱፈቃድ የስቶክ ማርኬትን አስፈላጊነት ሲያስረዱ፤ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የሚታወቀው በምሥረታ ላይ ያለ ማንኛውም የአክሲዮን ማኀበር አክሲዮኖቹን ለሕዝብ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ለመሸጥ ሲፈልግ በንግድ ሕጉ መሠረት በአደራጆች ወይም በመሥራቾች አስተባባሪነት ሽያጭ በመፈጸም ድርጅቱን ለማቋቋም የሚያበቃ ገንዘብ ለመሰብሰብ ይሞክራል። ይህም በመጀመሪያ ደረጃ ገበያ (Primary Market) እና በሁለተኛ ደረጃ ገበያ (Second- ary Market) ይካሄዳል። በመጀመሪያ ደረጃ ገበያ የሚካሄደው ግብይት የሰነደ መዋዕለ ንዋይ አውጪዎች በውክልና ሻጮች (Invest- ment Bank/Underwriter) በኩል ድርሻ ለሕዝብ የሚሸጡበት ገበያ ነው። በዚህ ገበያ አክሲዮኖች፣ ቦንዶችና ሌሎች በገንዘብ ሊተመኑ የሚችሉ ሰነዶች ለመጀመሪያ ጊዜ በማውጣት (Intial Public Offering) እና በመሸጥ አዲስ ካፒታል የሚሰበስቡበት ገበያ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ገበያ የተደረገው የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ግብይት በሰነደ መዋዕለ ንዋይ ደላላዎች አማካኝነት በባለቤትነት ከያዘው ሰው ወደ ሕዝብ የሚሸጥበት መድረክ የሁለተኛ ደረጃ ገበያ ይባላል። በእኛ አገር በመጀመሪያም ሆነ በሁለተኛ ደረጃ የሚከናወነው የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ግብይት የተማከለ ካለመሆኑም ባሻገር በሁለተኛ ደረጃ ግብይት ትክክለኛውን የሰነዶች ዋጋ ማወቅ የሚቻልበት አግባብ የለም። ይህም ግብይቱ ግልፅነት እንዳይኖረው ከማድረጉ በላይ የአክሲዮን ማኀበራትን ሀብት በትክክል ከማወቅና ዘርፉ ለአገር ዕድገት ሊያበረክት ከሚችለው አስተዋጽኦ አንፃር አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል።
በተጨማሪም በዘርፉ ሀብታቸውን በከንቱ ያፈሰሱ እንዳሉ ይታወቃል። ይህም እውነታ ዘርፉ የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ቁጥጥርና ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ ሁነኛ አመላካች ነው። በሁለቱም ደረጃ ገበያዎች በአገራችን የተቋቋመ ተቆጣጣሪ ተቋምና የተማከለ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለመኖሩ ግብይቱና ሂደቱ በተደራጀና ቁጥጥር በሚደረግበት መልኩ እየተከናወነ ባለመሆኑ የዘርፉ ዕድገት የተገደበ እንዲሆን አድርጎታል። ይህም ቀደም ሲል ባልተማከለ መንገድ የሚደረገውን የአክሲዮን ግብይት ሕግ፣ ሥርዓትና ቁጥጥር ወደሚደረግበት ግብይት በማምጣት አገርም ሆነ የገበያው ተዋንያን ከዘርፉ የሚያገኙትን ጥቅም ያሳድጋል ተብሎ ይታመናል። የስቶክ ማርኬት አለመኖር በድርጅቶች መካከል ውድድርና ፈጠራ እንዳይዳብር ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ስቶክ ማርኬት በተገበሩ አገራት ውስጥ የውድድር እና የፈጠራ አቅም በፍጥነት እንዲጎለብት የራሱ የሆነ ድርሻ አለው። ለዚህ ዋነኛው ምክንያት የስቶክ ዋጋቸው በውድድርና በፈጠራ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ነው። ብዙ ሰው ገንዘቡን ባንክ ከማስቀመጥ፣ ባንክ በስቶክ ማርኬት ውስጥ ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ድርጅቶችን የባለቤትነት ዕድል መጋራት ያስችላል የሚሉት አቡሽ አያሌው (ዶ/ር) ናቸው። በአጠቃላይ ሥርዓቱ ግብይቱ ግልጽና ፍትሃዊ እንዲሁም የተረጋጋና ተዓማኒ ገበያ በመፍጠር ግለሰቦች ወይንም ኩባንያዎች በገበያው እንዲሳተፉ መተማመን ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ በገበያው የሚሳተፉ ተዋንያን በሙሉልብ እንዲሳተፉ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ያጠናክራል፤ የፋይናንስ ግኝትን ወይንም ፍሰትን ይጨምራል።
የካፒታል ገበያ ዋነኛ ግቡ በአንድ አገር ላይ በተለያዩ አካላት ሥር የሚገኙ የፋይናንስ አቅሞችን በማሰባሰብ ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ፍላጎቶች ማዋል ነው። በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ምሁራን፤ የካፒታል ማርኬት በተለይም ለረጅም ጊዜ ለሚካሄድ ኢንቨስትመንት የሚውል ፋይናንስ ለማግኘት አስቻይ ሁኔታ ይፈጥራል። ዶክተር አቡሽ፤ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ መጀመሩ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት ያስችላል ይላሉ። ያም ብቻ ሳይሆን የካፒታል ገበያ በዋናነት አክሲዮን ማኀበራት የሰነደ መዋዕለ ንዋዮችን በማውጣትና በመሸጥ ለሥራ የሚያስፈልጋቸውን ካፒታል በመሰብሰብ ድርጅታቸውን ማስፋፋት የሚችሉበትን ዕድል ይዞ መጥቷል። ሌላው የካፒታል ገበያ ፋይዳ መንግሥት የዕዳ ሰነዶችን አውጥቶ በመሸጥ ከዚህ በፊት ከሌሎች አገሮችና ዓለምአቀፍ ተቋማት በሚገኝ ብድር የሚሠሩትን ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶች በራስ አቅም መሥራት ያስችለዋል።
በተጨማሪም መንግሥት የልማት ድርጅቶቹን ድርሻ በካፒታል ገበያ በኩል ለሕዝብ በመሸጥ ከዚህ ቀደም በብድር የሚሠሩ አገራዊ ፕሮጀክቶችን በመደጎምና ሥራ ላይ በማዋል የሚፈጠረውን የካፒታል አቅም ክፍተት ሊሞላ ይችላል። የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታ ለማዞር በሚፈለግበት ጊዜ የካፒታል ገበያ የድርጅቶች አክሲዮን ዋጋ በመቀመርና ሕዝቡ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በግዥ ሒደቱ እንዲሳተፍና ወደ ግል ይዞታነት እንዲዘዋወሩ ያደርጋል። ሕዝቡም ከዚህ ድርሻ በመግዛት የባለቤትነት ወይም የትርፍ ክፍፍልና ሌሎች ጥቅሞችን ያገኛል። በሌላ በኩል ካፒታል ማርኬት የብድር ሰነድ በሁለተኛ ገበያ የሚሸጡበት ዕድል በመፍጠሩ ኢንቬስተሮች በቀላሉ ገንዘብ የሚያገኙበት ሁኔታ (liquid) በቀላሉ ይመቻቻል። ይህም ከዚህ ቀደም ያልነበረና አሁን በአዲስ መልኩ የሚጀመር ሲሆን አንድ ግለሰብ የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ገዝቶ የግድ የመመለሻ ጊዜውን ሳይጠብቅ በቀላሉ
በሁለተኛ ገበያው ላይ ዋጋውን አውርዶ ለሌላ አካል መሸጥ የሚችልበት ዕድል ተፈጥሯል።
የካፒታል ገበያና የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት
በመስኩ ጥናት ያደረጉት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፤ ተቋማት ወይንም ኩባንያዎች የሚፈልጉትን ፋይናንስ በወቅቱ ማግኘት ከቻሉ ለኩባንያው ምርታማነትና ዕድገት ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያደርጋል። የፋይናንስ ፍሰቱ ለአዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎችና ለበርካታ ጥቃቅን ድርጅቶች የማደግ ዕድል ይፈጥራል። መሰል የተቋማት ዘላቂ ዕድገት መረጋገጥ፤ ተቋማት ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ዕድል ይዞ ይመጣል። ይህም የአገሪቱ ዋነኛ የምጣኔ ኃብት ችግር የሆነውን የሥራ አጥ ቁጥር በመቀነስና ያለውን የሰው ኃይል ወደ ሥራ በማስገባት ትልቅ ሚና ይጫወታል። ሌላው በካፖታል ገበያውም ሆነ ካፒታል ገበያውን ተከትሎ በሚኖረው ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ፤ በአገሪቱ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያስችላል። ይህም የውጭ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በመሰማራት አንድም የቴክኖሎጂ ሽግግር በማሳለጥ፣ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የሥራ ዕድል በመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህም ብቻ ሳይሆን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መጠናከር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማስፋት የዘርፉን ሚዛን (Balance of Payment) በማስጠበቅ የራሱ ደርሻ እንደሚኖረው ይታመናል።
በሌላ በኩል ተቀማጭ ገንዘቦች ወደ ኢንቨስትመንት ተለውጠው ግለሰቦችን ትርፋማ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ፤ አሁን ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለውን የቁጠባ ባሕል በማሳደግና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች የማሰማራት ዝንባሌ ከፍተኛ ይሆናል። ይህም በተለይም በፋይናንስ ዘርፍ ውጭ የሚቀመጠውን የገንዘብ መጠን ወደ ሕጋዊ ተቋማት በማስገባት እንዲሁም የጥሬ ገንዘብ ችግር (Liquid- ity Crisis) በመቀነሰም የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል። ጎን ለጎንም የካፒታል ገበያ መጀመር የመንግሥት ገቢ በግብር መልክ በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ እንዲል ያደርጋል። “በግብር አሰባሰብ ምጣኔ ከአፍሪካ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን” የሚሉት (ዶ/ር) አቡሽ ለዚህ እንደ አንድ ምክንያት የሚታየው ራሱ የአገር ውስጥ ገቢ የአቅም ውስንነትና የንግዱ ማኅበረሰብ ግብር የመክፈል ባሕል አለመዳበር ቢሆንም፤ በኮርፖሬሽን ደረጃ በሕግና ሥርዓት የዳበሩ የንግድ ድርጅቶች በብዛት ባለመኖራቸው ነው።
የካፒታል ገበያ መኖር በርካታ ድርጅቶች በኮርፖሬሽን የመደራጀት ዕድላቸው ከፍተኛ ይሆናል። ይህ ደግሞ መንግሥትን ትክክለኛ ግብር ለመሰብሰብ ያስችለዋል። ኮርፖሬሽኖችም ሆኑ ማኅበረሰቡ ወደ ስቶክ ማርኬት በመሄድ ድርሻቸውን ሲሸጡና ሌላ ድርሻ ሲገዙ እንዲሁም ኮርፖሬሽኖች ትርፋቸውን ለባለቤቶች ሲያከፋፍሉ መንግሥት ከኃብት ዕድገት እና ከትርፍ ክፍፍል ከፍ ያለ ግብር መሰብሰብ ያስችለዋል። ይህም መንግሥት የሚያጋጥመውን የፊሲካል ክፍተት ወይም የወጪና ገቢ አለመመጣጠን ችግር በማቃለል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ያነሱት። እነዚህ ትሩፋቶች የማክሮ ኢኮኖሚው እንዲረጋጋና ጤናማ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ምቹ ከባቢ ለመፍጠር እንደሚያስችሉ ነው የመስኩ ባለሙያዎች የሚያስረዱት።
ለካፒታል ገበያ ውጤታማነት ምን መደረግ አለበት?
የካፒታል ገበያን ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መሰራት ይኖርባቸዋል። በተለይ አስፈላጊውን መሰረተ-ልማት ማሟላት ለነገ የማይባል ተግባር ነው። በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ መጀመሩ ጥቅሞች እንዳሉት ሁሉ በአግባቡ ለማስኬድና ውጤታማ ለማድረግ ተግዳሮቶችም እንደሚኖሩ ይጠበቃል የሚሉት ዶ/ር አቡሽ ከተግዳሮቶቹ መካከል ካፒታል ገበያን በአግባቡ ለመከወን ከሚረዳን መሠረተ ልማት አንዱ የሆነው የመረጃና ተግባቦት ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት /Information Communication Technology Infrastruc- ture/ ነው። ይህን መሠረተ ልማት ለማሟላት ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል።
የካፒታል መሠረተ ልማት በሚፈለገው መጠን አለማሟላት፣ በአገሪቱ የሒሳብ መዝገብ አያያዝና የኦዲት ሙያ በሚፈለገው መጠን ዓለም አቀፍ ደረጃን አለማሟላታቸው፣ የካፒታል ገበያን በተመለከተ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ያልዳበረ ግንዛቤና ዕውቀት፣ የሕዝቡ የቁጠባ ባሕል በሚፈለገው መጠን አለማደጉ በዋናነት ሲጠቀሱ እነኚህንና ሌሎች ተግዳሮቶችን በማስወገድ አገሪቱ እንደ ሌሎች አገሮች ከካፒታል ገበያ ተጠቃሚ ሆና ዕድገቷን የበለጠ ታሳድግ ዘንድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ይጠበቃል። ከዚህ አኳያ መንግሥት እነዚህን እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን በማጥናት ተገቢውን ዘላቂ ምላሽ በመስጠት ለገበያው ተግባራዊነት በትኩረት መሥራት እንዳለበት ነው ምከረ ሃሳባቸውን የሰጡት።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ለዘመናት ጥያቄ ምላሽ ሰጪው
ጭላንጭል ተስፋ
በትንሳኤ ገመቹ
የዛሬው የ76 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ያኔ በለጋነታቸው፤ ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ሜዳ ሳይመርጡ እንዳሻቸው በሚቦርቁበት፣ ሮጠው በማይጠግቡበት፣ ገና ታዳጊ ሳሉ በ13 ዓመት ዕድሜያቸው በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ነው ሁለት እግሮቻቸውን ያጡት። ይሁንና ይህ ጉዳታቸው ሳይበግራቸው በብዙ ውጣ ውረድና እልህ አስጨራሽ ትግል በትምህርታቸው እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ መዝለቅ ችለዋል።
እኚህ ሰው ካለሙበት ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፈዋል። ትውልድና ዕድገታቸው በአዲስ አበባ መሆኑ በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ድጋፍ ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ ዕድልን ሰጥቷቸዋል፤ የሥራ ዓለምንም ተቀላቅለዋል። ይህ ስኬታቸው ግን እንዲሁ እንደዋዛ የተገኘ አልነበረም።
የመዲናዋ የእግረኛም ሆኑ የተሽከርካሪ መሄጃ አስፓልት መንገዶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረጉ፤ ለዊልቼር መንቀሳቀሻ በቂ ቦታ የሌላቸውና አስቸጋሪ መሆናቸው እንቅስቃሴያቸውን በእጅጉ አክብዶባቸዋል፤ ለዓመታት በዊልቼር የተመላለሱባቸው ለእግረኛ እንኳን የማይመቹ የተቦረቦሩ፣ ወጣገባ፣ ዳገታማና ቁልቁለታማ መንገዶች ተጨማሪ የሕይወት ፈተናዎቻቸው ነበሩ። አዛውንቱ በታዳጊ፣ በወጣትነት እና በጉልምስናም ዕድሜያቸው በእጅጉ የፈተኗቸውን
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
እነዚያን የስቃይ ጊዜያት “መቼም አልረሳቸውም” ሲሉ እንደ እርሳቸው የአካል ጉዳት የገጠማቸውን ሰዎች የዕለት ተዕለት ተግዳሮቶች ይገልጻሉ፤ አቶ አለበል ሞላ።
ዓለም አቀፋዊ የአካል ጉዳተኝነት ሁኔታ
በዓለም-አቀፉ የአካል ጉዳተኞች መብት ኮንቬንሽን አንቀፅ አንድ እንደተመለከተው አካል ጉዳተኝነት ከረጅም ጊዜ የአካል፣ የአዕምሮ ወይም የስሜት ህዋሳት እክል ጋር የሚኖሩና በአመለካከትና በአካባቢያዊ ጋሬጣዎች ምክንያት በማኅብረሰቡ ውስጥ ሙሉና ትርጉም ያለው ተሳትፎ በእኩልነት ማድረግ የማይችሉ ሰዎችን ያጠቃልላል።
አካል ጉዳት ማለት፤ የአካል ክፍልን ማጣት ወይም የተግባር መገደብን የሚያመላክት ፅንሰ-ሀሳብ ነው። አካል ጉዳተኝነት ማለት ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል ተሳትፎ እንዳያደርጉ የሚያደርግ የአካል ጉዳት፣ የአመለካከት ችግርና አካባቢያዊ መሰናክሎች ድምር ውጤት ነው።
በዓለም ላይ የተለያየ አይነት አካል ጉዳተኝነት የሚያጋጥም ሲሆን፤ ዓይነ-ስውርነት፣ መስማት መሳን፣ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት፣ ማየትና መስማት መሳን እንዲሁም ተደራራቢ የአካል ጉዳት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር 2023 ያወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ያህል ሰዎች የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት ያጋጥማቸዋል። ይህ አሃዝ 16 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ ቁጥር የሚወክል ነው። ይህም የአካል ጉዳት ከስድስት ሰዎች በአንዱ ላይ አለ ማለት ነው። እነዚህ ዜጎች ከአካል ጉዳተኝነት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ተያያዥ የጤና እክሎች የሚያጋጥማቸው መሆኑንም መረጃው ያሳያል። ድብርት፣ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ስትሮክ፣ አላስፈላጊ የሰውነት ክብደት መጨመር፣ የአፍ ጤና እክልና ሌሎችም ተያያዥ በሽታዎች ከአካል ጉዳተኝነት ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱት መካከል ይጠቀሳሉ።
በዓለም ላይ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው ስያሜ የተለያየ ነው። ለምሣሌ በተለያዩ አገራት ያለው ቴክኖሎጂ፣ የሰዎች አመለካከት፣ ከድጋፍ አሰጣጥና ከመሰረተ ልማት ተደራሽነት ጋር ተያይዞ ለአካል ጉዳተኝነት የሚሰጠው ስያሜ እንዲለያይ አድርጓል። ለአብነት ለዓይነስውራን ልዩ የዓይን መነፅርና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማቅረብ በሚችሉ አገራት ዓይነስውራን እንደ አካል ጉዳተኛ አይታዩም። የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ሕፃናት ወደ ትምህርት ቤት የማይሄዱት በወላጆቻቸው የተዛባ አመለካከትና ትምህርት ቤቶች ለልዩ ፍላጎት ማስተማሪያ ተገቢውን ቁሳቁስ ማሟላት ባለመቻላቸው እንጂ ሕፃናቱ መማር ስለማይችሉ ወይም ቢማሩ ስለማይለወጡ አይደለም። ይህን ማሟላት በቻሉ አገራት የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እንደ አካል ጉዳተኛ ሊቆጠሩ አይችሉም።
በሌላ በኩል በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ለሚንቀሳቀስ ሰው ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ የሚያዳግተው አካል ጉዳቱ ሳይሆን፤ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ሳይፈጠርለት ሲቀር ብቻ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) መረጃ እንደሚያሳየው በታዳጊ አገራት 90 በመቶ አካል ጉዳተኛ ልጆች ትምህርታቸውን አይከታተሉም። እ.ኤ.አ 1998 ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥናት የአካል ጉዳተኛ ጎልማሶች ዓለም አቀፋዊ የማንበብ ደረጃ ሦስት በመቶ ሲሆን የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ደግሞ አንድ በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።
አካል ጉዳተኝነት በአፍሪካ
በአፍሪካ ከ80 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የተለያየ አይነት የአካል ጉዳት እንዳለባቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያሳያል።
በአህጉሪቱ በተለይም በየጊዜው የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች፣ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች በርካቶችን ለአካልና ለአዕምሮ ጤና ጉዳት የሚዳርጉ ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ። የአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት ፈተናዎች የሆኑት የምጣኔ ሀብት እና የመሠረተ ልማት ችግሮች አካል ጉዳተኞችን የበለጠ ጫና ውስጥ የሚከቱ ከመሆናቸው ባሻገር ተገቢውን ድጋፍ እንዳያገኙ ተግዳሮት ሆነው ቆይተዋል።
አካል ጉዳተኝነት በኢትዮጵያ
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ዜጎች ከተለያየ ዓይነት የአካል ጉዳት ጋር እንደሚኖሩ ግምት አስቀምጠዋል። ይሁንና የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ከተካሄደ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ምን ያህል አካል ጉዳተኞች እንዳሉ ትክክለኛ መረጃ ማግኘትን አዳጋች አድርጎታል። እነዚህ ዜጎች በጎጂ ልማዶችና በተዛባ አመለካከት እንዲሁም በሕግጋት እና በአፈጻጸማቸው ክፍተት ሳቢያ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እየተጋፈጡ እንደሆነም ይጠቁማሉ። በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች የሚመጥን የመሠረተ ልማት አውታር ግንባታ አለመኖርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት በርካቶችን ለከፍተኛ እንግልትና ለተጨማሪ የጤና እክል እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል። በመንገዶች ላይ የቁም እና የወለል ምልክቶች አለመኖር፤ በሕንፃዎች ላይ አካል ጉዳተኞችን የሚደግፉ መወጣጫዎች እጥረት፤ የመጸዳጃ እና ሌሎችም ተያያዥ አገልግሎቶች ላይ አካል ጉዳተኞች ተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲያነሱም አድርጓል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ስምምነትን (Convention) ተቀብላ የሕጓ አካል አድርጋለች። የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት እና የሕንፃ አዋጆች ጸድቀው ወደ ስራ ተገብቷል። ከ60 በመቶ በላይ አካል ጉዳተኞችን ለቀጠረ ድርጅት ከታክስ እና ከቀረጥ ነፃ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ስራ ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ አካል ጉዳተኞችን እኩል ተሳታፊና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብለው የወጡ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መሬት ላይ ወርደው በተጨባጭ ምን ለውጥ አመጡ? አፈፃፀማቸውስ? የሚለው አሁንም ድረስ የበርካቶች ጥያቄ ነው።
በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 5 እንደተደነገገው “መንግሥት የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞችን፣ አረጋዊያንና ያለ ወላጅ ወይም ያለ አሳዳጊ የቀሩ ሕፃናትን ለማቋቋምና ለመርዳት የአገሪቱ የኢኮኖሚ አቅም በፈቀደው ደረጃ እንክብካቤ ያደርጋል” የሚል ድንጋጌ ተቀምጧል። መንግሥት አካል ጉዳተኞችን በሚችለው አቅም መርዳት እንዳለበት የሚገልጸው ይህ ድንጋጌ በራሱ ትችት የሚቀርብበት ነው። ድንጋጌው አካል ጉዳተኞች አምራች እንዳልሆኑ እንዲሰማቸው የሚያደርግ መሆኑን ከሚተቹት መካከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎትና የአካቶ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ተክለማርያም (ዶ/ር) አንዱ ናቸው።
እንደ እርሳቸው፤ በዚህ አንቀፅ አካል ጉዳተኞችን ዕድሜያቸው ካልደረሱ ሕፃናት እንዲሁም ስራ ሰርተው ከጨረሱ አረጋዊያን እኩል ቦታ መስጠቱ ተገቢ አይደለም። አካል ጉዳተኞች በውክልና ካልሆነ ንብረታቸውን ማውረስ እንደማይችሉ በሕገ መንግሥቱ መደንገጉ አካል ጉዳተኞች “አልችልም” የሚል የበታችነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። አካል ጉዳተኞች ሁኔታዎች ከተመቻቹላቸውና ዕድሉ ከተሰጣቸው ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ይህ ለትርጉም ተጋላጭ የሆነውን አንቀፅ ማስተካከልና የኅብረተሰቡን አመለካከት መቀየር ካልተቻለ አካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የመሆን ዕድላቸው የሚፈለገውን ያህል አይሆንም። የአካል ጉዳት ያለባቸውን ዜጎች የተመለከቱ ሕጎች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርጉ አመራሮችና ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ የሚጠቁሙት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ ሕጉን አስገዳጅ ማድረግ እስካልተቻለ ድረስ ክፍተቱ ሊፈታ አይችልም።
ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አካቶ ትምህርትን የሚደግፉ ቢሆኑም፤ በየትምህርት ቤቶቹ ያለው አተገባበር ላይ ክፍተት መኖሩን አመልክተው፤ ይህም ከአመራር አካላት በጎ ፈቃደኝነትና ግንዛቤ ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ነው ይላሉ። በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ቀደም ካሉት ዓመታት ከነበረው የተሻለ ግንዛቤ ቢፈጠርም፤ አሁንም 90 በመቶ የሚሆኑት ከትምህርት ውጭ ከመሆናቸውም ባለፈ አንዳንድ የሚወጡ ሕጎች አካል ጉዳተኞችን የዘነጉ ናቸው። አካል ጉዳተኞች የትምህርት ዕድል ማግኘታቸው በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል። ይህም ካላቸው ከፍተኛ ቁጥር አኳያ ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገትና ለድህነት ቅነሳ የድርሻቸውን እንዲወጡ ያስችላል ሲሉም ያክላሉ።
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲግሪ ተማሪዎች የአካቶ ትምህርትን እንዲወስዱ መደረጉ አበረታች ውጤት መሆኑን የሚጠቅሱት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፤ “መሰል አስገዳጅ ሁኔታዎች የተዛባ አመለካከትን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላሉ” ይላሉ።
በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 9/4/ ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቷ ሕግ አካል እንዲሆኑ ይደነግጋል። ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች (Conventions) ውስጥ አንዱ ዓለም-አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብት ስምምነት ሲሆን፤ በዚህ የሕገ መንግሥት ድንጋጌ መሰረት ኮንቬንሽኑ የአገሪቷ የሕግ አካል ሆኗል ማለት ነው።
በተጨማሪም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 25 ስለእኩልነት መብት ሲዘረዝር ሁሉም ሰዎች በዘር፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ አመጣጥ፣ በሃብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግባቸው እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። በዚህ አንቀፅ በአካል ጉዳት ምክንያት ልዩነት መደረግ እንደሌለበት በግልፅ ባያስቀምጥም “በሌላ አቋም ምክንያት” የሚለው ሐረግ አካል ጉዳትንም እንደሚጨምር ታሳቢ ይደረጋል ማለት ነው።
በሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 5 ስለአካል ጉዳተኞች መብት በግልፅ ያስቀመጠ ሲሆን፤ አንቀፁ “መንግሥት የአካልና የአዕምሮ ጉዳተኞችን ለማቋቋምና ለመርዳት የአገሪቷ ኢኮኖሚ በሚፈቅደው መጠን እንክብካቤ ያደርጋል” ይላል። ይህ አንቀፅ አካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የሰጠው መብት ቢኖርም ወደ መሬት ወርዶ ተጨባጭ ለውጥ ከማምጣት አኳያ በርካታ ቀሪ ስራዎች አሉ።
ሀገሪቷ ከምትከተለው እኩል የሥራ ዕድል መርሆ ጋር የሚጣጣም፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታ የሚፈጥርና በሥራ ሥምሪት የሚደርስባቸውን አድልዎ በፍርድ መድረኮች በቀላሉ ለማስረዳት የሚያስችል አሠራር መዘርጋት ወሳኝ በመሆኑ ስለ አካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት መብት የሚደነግግ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብት አዋጅ ቁጥር 568/2000 ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል።
በዚህ አዋጅ ላይ እንደተመላከተው፤ የሥራው ጠባይ የማይፈቅድ ካልሆነ በቀር የተፈላጊ ችሎታ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
መመዘኛዎችን አሟልቶ የተገኘና በውድድር ውጤቱ ብልጫ ነጥብ ያገኘ ማንኛውም የአካል ጉዳተኛ በምንም ዓይነት መልኩ መድልዎ ሳይደረግበት፣ በማንኛውም መሥሪያ ቤት ወይም ድርጅት ውስጥ የሚገኝን ክፍት የሥራ ቦታ በቅጥር፣ በዕድገት፣ በድልድል ወይም በዝውውር የመያዝ መብት አለው።
በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሚሰጥ የሥልጠና ፕሮግራም የመሳተፍ መብት እንዳለውና የተፈላጊ ችሎታ መመዘኛዎችን አሟልቶ የተገኘና ለውድድር ውጤት እኩል ወይም ተቀራራቢ ነጥብ ያገኘ ማንኛውም አካል ጉዳተኛ በምንም ዓይነት መልኩ መድልዎ ሳይደረግበት የተመደበበት የሥራ መደብ የሚያስገኘውን ደመወዝና ሌሎች ጥቅሞች የማግኘት መብት እንዳለው አዋጁ ያትታል።
የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮንቬንሽን ስምምነት አዋጅ ቁጥር 676/2002 ላይ እንደተመላከተው፣ የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ ሁሉም አካል ጉዳተኞች በሁሉም ዓይነት ሠብዓዊ መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች ረገድ ሙሉ እና እኩል ተጠቃሚነት ያላቸው ስለመሆኑ ማረጋገጥ፣ ማሳደግና ለነዚሁ ጥበቃ ማድረግ፣ ብሎም ተፈጥሯዊ ክብራቸውን ከፍ ማድረግ ነው።
በዚሁ አዋጅ ስለ ሥራ እና ቅጥር በተቀመጠው አንቀፅ 27 ንዑስ አንቀፅ (ሀ) ላይ ምልመላን፣ ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ ቅጥርን፣ በቋሚ ስራ ላይ መቀጠልን፣ የሙያ ዕድገትን፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ሁሉ አስመልክቶ በአካል ጉዳት ላይ የተመሰረተ ማናቸውም አይነት አድልዎ እንዳይፈፀም ይከለክላል።
የዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (ለ) ደግሞ ከወከባ መጠበቅንና ለቅሬታዎች የመፍትሄ ምላሽ ማግኘትን ጨምሮ እኩል ዋጋ ላለው ሥራ እኩል ዕድሎችንም ሆነ እኩል ክፍያ የማግኘት፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታዎችን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩል ደረጃ ለአካል ጉዳተኞች ትክክለኛና ምቹ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት መስጠቱን ያትታል።
ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (አይ. ኤል.ኦ) እ.ኤ.አ በ2021 ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው በዓለማችን ዕድሜያቸው ለሥራ ከደረሰ ዜጎች 386 ሚሊዮን የሚገመቱት የአካል ጉዳት አለባቸው። በአንዳንድ ታዳጊ አገራትም የአካል ጉዳተኞች ሥራ አጥነት እስከ 80 በመቶ ይደርሳል። ይህም የሚያሳየው አሰሪዎች አካል ጉዳተኞችን የመቅጠር ፍላጎት እንደሌላቸውና ‘አካል ጉዳተኞች መስራት አይችሉም’ የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ መያዛቸውን ነው።
አካል ጉዳተኝነት ያልበገራቸው ብርቱዎች
በጽሑፉ መግቢያ የተዋወቅናቸው የ76 ዓመቱ የዕድሜ ባለፀጋ አቶ አለበል ሞላ ገና የ13 ዓመት ታዳጊ እያሉ በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ሁለት እግሮቻቸውን አጥተዋል።
አቶ አለበል አዲስ አበባ ተወልደው ማደጋቸው በተሽከርካሪ ወንበር (ዊልቼር) ድጋፍ ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ስራ ተመላልሰው ለመማርና ለመስራት የሰጣቸው ዕድል ቢኖርም የከተማዋ የእግረኛም ሆኑ የአስፓልት መንገዶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረጉ፤ ለዊልቼር መንቀሳቀሻ በቂ ቦታ የሌላቸው መሆናቸው እንቅስቃሴያቻውን በእጅጉ አክብዶባቸዋል። ከመኖሪያቸው ወደ ትምህርት ቤትና ወደ ስራ ቦታቸው በዊልቼር በሚመላለሱበት ጊዜ በመንገዱ ወጣገባነት ይገጥማቸው የነበረውን ፈተና እና ያሳለፉት ስቃይ እጅግ ከባድ እንደነበር ያስታውሳሉ።
ይሁንና አቶ አለበል በርካታ ውጣ ውረዶችና ተግዳሮቶችን አልፈው ትምህርታቸውን በመከታተል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን መያዝ ችለዋል። በመንግሥት መሥሪያ ቤት ተቀጥረው ለ25 ዓመታት አገልግለዋል። ሥራ ለመቀጠር አጋጥሟቸው የነበረውን እልህ አስጨራሽ ትግል አሁንም ድረስ በቁጭት ነው የሚያስታውሱት። ያንን ጊዜ “አስከፊና ተስፋ አስቆራጭ” ሲሉ ይገልፁታል።
በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ለአካል ጉዳተኞች የሚጠበቁ የሥራ ሁኔታዎችን በተመለከተ እንደተቀመጠው አካል ጉዳተኞች በቅጥር፣ በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር፣ በድልድል፣ በትምህርትና ሥልጠና አፈጻጸም የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው። ማንኛውም የመንግሥት መስሪያ ቤት የሥራ አካባቢው ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞቹ ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ለሥራ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችንና ቁሳቁሶችን ማሟላትና ስለአጠቃቀማቸው አስፈላጊውን ሥልጠና
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
እንዲያገኙ ማድረግ አለበት።
በሌላ በኩል ማንኛውም የመንግሥት መስሪያ ቤት ረዳት ለሚያስፈልገው የአካል ጉዳተኛ የመንግሥት ሠራተኛ ተገቢውን ድጋፍ የሚሰጥ ረዳት እንዲመደብለት የማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት ሲሆን፤ በሌሎች ሕጎች ለአካል ጉዳተኞች የተሰጡ መብቶች ለዚህ አዋጅ አፈጻጻም ተግባራዊ እንደሚሆኑ ያስቀምጣል።
ይሁን እንጂ ለአቶ አለበል ይህ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ በወረቀት ላይ ብቻ የሰፈረ የህልም እንጀራ ነው። “ስራ ለመቀጠር ማስታወቂያ በወጣባቸው የመንግሥትና የግል ተቋማት አካል ጉዳት ከሌለባቸው ጋር ተወዳድሮ ማለፍ ትልቅ ፈተና ነበር፤ ፈተናውን በጥሩ ነጥብ አልፌ እንኳን ለቃለ-መጠይቅ ዊልቸሬን እየገፋሁኝ ስገባ ከጠያቂዎቹ ፊት ላይ ያለውን ስሜት በመረዳት ነበር ስራውን እንደማላገኝ እርግጠኛ የምሆነው’’ይላሉ።
የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመረቁ ከአራት ዓመታት በኋላ በአንድ የመንግሥት ተቋም ውስጥ በጀማሪ ባለሙያነት የመቀጠር ዕድል ማግኘታቸውንና ይህን ዕድል በመጠቀም አካል ጉዳተኝነት ምንም አይነት ስራ ከመስራት ወደኋላ እንደማያስቀር ለማሳየት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ይናገራሉ።
ይሁንና እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም ሆነ ነገ ሁሉም አካል ጉዳተኞችን የሚመለከትበትን መነፅር መጥረግ እንዳለበት አጽንኦት የሚሰጡት አቶ አለበል በተለይም እውቀትና ችሎታው ኖሯቸው እኩል ዕድል ባለማግኘታቸው በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ አካል ጉዳተኞችን ለመታደግ እያንዳንዱ ዜጋ በሰብዓዊነት ስሜት ሊንቀሳቀስ፣ መንግሥትም ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ያስገነዝባሉ።
አቶ አለበል ያለፉበትን የሕይወት ውጣ ውረድ መንገድ ዛሬም በርካታ አካል ጉዳተኞች ይመላለሱበታል። የ12ኛ ክፍል ተማሪዋ ዓይናለም መክብብ ከእነዚህ መካከል አንዷ ነች። ዓይናለም ስትወለድ ጀምሮ ዓይነስውር ናት።
ዩኒቨርሲቲ ገብታ ሕግ የመማር ከፍተኛ ፍላጎት ያላት ዓይናለም ለምን ሕግ ማጥናት እንደፈለገች ስትጠየቅ “በሀገራችን ዓይነስውራንን ጨምሮ የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸው ዜጎች አካል ጉዳት ከሌለባቸው እኩል የትኛውንም አገልግሎት የማግኘት መብታቸው በአግባቡ ተከብሮ ከፍተኛ በሚባሉ የሥራ ቦታዎች ላይ በኃላፊነት እንዲመጡ ካለኝ ፅኑ ፍላጎት ነው” ትላለች።
ዓይናለም የምትማርበት ትምህርት ቤት ከብሬል አቅርቦት ጀምሮ የተለያዩ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም፤ እርሷ ግን በትምህርቷ ከዓይናማዎች እኩል፤ አንዳንዴም ከእነርሱም በላይ የላቀ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። ለዚህ ስኬቷም “እችላለሁ’’ የሚል ጠንካራ ሥነ-ልቦና እንዲኖራት ወላጆቿ ያሳደሩባትን አዎንታዊ ተጽዕኖ በምክንያትነት ትጠቅሳለች።
በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎች በትክክል አይፈፀሙም የሚለውን ቅሬታ ዓይናለምም ትጋራዋለች። ለምን አይፈፀሙም የሚል ጥያቄ ሲነሳም “ሰሚ ጆሮ እና ተመልካች ዓይን” የለም ነው ምላሿ። አካል ጉዳተኞች በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ላይ ሆነው አገራቸውን እና ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ የሚያግዝ አረንጓዴ መብራት አይታይም።
“በፈተና ውስጥም ቢሆን፤ በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ሕግ አጥንቼ በጥሩ ውጤት እንደምመረቅና ያሰብኩትን እንደማሳካ እርግጠኛ ነኝ” የምትለው ዓይናለም፤ እንደ አገር ለአካል ጉዳተኞች ያለውን ሁለንተናዊ አመለካከት ማስተካከል በተለይም የሕግ ተፈጻሚነትን ማሻሻል የቅድሚያ ቅድሚያ የስራ ትልሟ ስለመሆኑ ትገልፃለች።
የሕጎች የተፈጻሚነት ክፍተት
በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች ያለው አመለካከት የተንሸዋረረ ነው በሚል የሚነሳውን ቅሬታ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይነህ ጉጆም ይስማሙበታል። በአገሪቷ አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች በትክክል አካል ጉዳተኞችን እየደገፉ ካለመሆኑ ባሻገር አካል ጉዳተኞችን ብቻ አስመልክቶ የወጣ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖሩንም አጥብቀው ይተቻሉ።
አካል ጉዳተኞች ለሚያነሷቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የሚሰጥ አሰራር መዘርጋት የግድ ስለመሆኑ አፅንኦት የሚሰጡት አቶ ዓባይነህ “አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የሚወጡ ሕጎችና አሰራሮች በ’እኔ አውቅልሃለሁ’ እሳቤ የወጡና አካል ጉዳተኛውን የማይወክሉ ናቸው” ይላሉ።
በአጠቃላይ በሀገሪቷ አካል ጉዳተኞችን አስመልክተው የሚወጡ ሕጎች ተፈጻሚነታቸው ዝቅተኛ ነው። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በአካል ጉዳተኛው ቦታ ሆኖ ችግሩን አለመረዳትና የተቆርቋሪነት ስሜት አለመኖሩ ነው ሲሉም ያክላሉ።
በኢትዮጵያ ሕንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 በሀገሪቷ የሚገነቡ ሕንፃዎች ማሟላት ስለሚገባቸው አጠቃላይ ግዴታዎች ያስቀመጠ ሲሆን፤ በአንቀፅ 36 ስር የሚገነቡ ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ሊሆኑ እንደሚገባ አስፍሯል።
የሕንፃ አዋጁ ይውጣ እንጂ አብዛኞቹ የሚገነቡ ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ያላማከሉ ናቸው። ሕጉ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርጉ የማያስገድድ በመሆኑ ሕንፃ ገንቢዎቹ ስለአካል ጉዳተኞች መብት ግድ እንዳይሰጣቸው አድርጓል።
መንግሥት አካል ጉዳተኞችን በሀገሪቷ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ለማድረግ ጉዳታቸውን ታሳቢ ያደረገ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለበት በአፅንኦት የሚገልጹት አቶ ዓባይነህ ፌዴሬሽኑ አካል ጉዳተኞች በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ወጥነት ያለው የአካል ጉዳተኞች ሕግ እንዲወጣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ነው ያስረዱት።
በኢትዮጵያ የሚገነቡ ሕንፃዎችና መንገዶች ከዲዛይን ጀምሮ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ ማኅበሩ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን እና ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የዚህ ስምምነት ዋና ዓላማ አዳዲስ የሚገነቡ መንገዶችና ሕንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርጉ እንዲሁም ነባር ሕንፃዎችንም ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የማድረግ ሁኔታን መፍጠር ነው።
አካል ጉዳተኞች በሀገሪቷ ሁለንተናዊ ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ሁሉንም ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንደሚያሳድግ የሚገልጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለአብነትም ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ስራ ውጤታማነት አካል ጉዳተኞች የድርሻቸውን መወጣት እንዲችሉ በንቃት የሚሳተፉበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን በመዲናዋ ለዓይነስውራን እና ዊልቼር ለሚጠቀሙ አካል ጉዳተኞች ታስበው የተገነቡ የእግረኛ መንገዶች መኖራቸውን ይናገራሉ። ይሁንና ሁሉም ቦታ ላይ ያሉ መንገዶች የተገነቡት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ተደርገው ነው ማለት ግን አይቻልም። ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ጋር በጋራ
እየተሰራ ነው ይላሉ።
ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አካባቢ መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ግዴታ ስለመሆኑ ያነሱት አቶ እያሱ በተለይ የእግረኛን ጨምሮ የመንገድ መሰረተ ልማቶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉም በአፅንኦት ይገልፃሉ።
ቀደም ባለው ጊዜ በተቋማቸው የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ከሌሎች የሥራ ዘርፎች ጋር ተቀናጅቶ ይሰራ እንደነበር በማስታወስ ይህም ጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዳያገኝ ከማድረግ ባለፈ አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል የሚሉት ደግሞ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች ግንዛቤ ማስጨበጥ ዴስክ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ብርሃኑ ናቸው።
አቶ ሲሳይ አክለውም ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ብቻ የሚከታተል የሥራ ክፍል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱን እና በዚህም ለውጦች መምጣታቸውን ይገልጻሉ። ቀደም ባሉት ዓመታት ስለ አካል ጉዳተኞች የነበረው የተዛባ አመለካከት አሁን አሁን የተወሰኑ መሻሻሎችን ቢያሳይም፤ በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አልሸሸጉም።
አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች ተፈጻሚነት ላይ ጉልህ ክፍተቶች አሉ በሚለው አስተያየት አቶ ሲሳይ ይስማማሉ። በተለይ ኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች መብት ኮንቬንሽንን ተቀብላ ያጸደቀች ቢሆንም፤ ወደ ተግባር ከመቀየር አኳያ በርካታ ክፍተቶች ይስተዋላሉ። እንደ አቶ ሲሳይ ገለፃ እያንዳንዱ የመንግሥት ተቋም አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራት እንዳለበት በኮንቬንሽኑ ተቀምጧል። ይሁንና በየተቋማቱ ከአመራር እስከ ባለሙያ ድረስ አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ ሊያደርግ የሚችል አገልግሎት ከመስጠት አኳያ ገና ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ።
ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት ከመስጠት አኳያ በርካታ ተቋማት ተደራሽ አይደሉም። በዊልቼር ለሚንቀሳቀሱ፣ ለዓይነስውራን እና መስማት ለተሳናቸው ዜጎች የተቋማት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ብዙ ሊሰራ ይገባልም ይላሉ።
ጭላንጭሉ ተስፋ…
አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ በአንዳንድ ሕጎች ላይ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ድክመቶችን የማረም ጥረት ተጀምራል። ለአብነት በኢትዮጵያ የሚገነቡ ሕንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ አለመሆናቸው ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል። ይህን ችግር ለመፍታት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የሕንፃ አዋጁ እንዲሻሻል በጋራ እየሰራ ነው። በማሻሻያ አዋጁ ላይ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉና አስፈላጊውን ግብዓት እንዲጨምሩም ተደርጓል።
አካል ጉዳተኞች ከቀረጥ ነፃ ተሽከርካሪ ማስገባት የሚያስችላቸው መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን የአካል ጉዳተኞችን መረጃ የማደራጀት ሥራ እንዲከናወንና በተሰጣቸው ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው። አካል ጉዳተኞች በፌዴራልና በክልል ደረጃ በጉዳት አይነታቸው ተደራጅተው የእኩል ዕድል ተጠቃሚነታቸውና ተሳትፏቸው እንዲጨምር ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል። ያም ሆኖ አሁንም አንድ ትልቅ ችግር አለ፤ “በኢትዮጵያ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ከተካሄደ ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ ምን ያህል አካል ጉዳተኞች እንዳሉ ትክክለኛው መረጃ አይታወቅም” ይላሉ። ይህም አካል ጉዳተኞችን እንደ ጉዳት አይነታቸው ለይቶ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ከባድ ፈተና ሆኗል።
አካል ጉዳተኞችን አስመልክቶ የሚወጡ ሕጎች በአግባቡ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑት ተቋማት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ፤ ራሳቸው አካል ጉዳተኞችም ለመብቶቻቸው መከበር ይበልጥ መታገል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ይህም ብቻ አይደለም የአካል ጉዳተኞች እኩል ተጠቃሚነት ጉዳይ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ የሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል ድጋፍ ይሻል።
ጤና
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
መጪውን ወረርሽኝ አስቀድሞ ለመከላከል.......
በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
መጪውን ወረርሽኝ አስቀድሞ ለመከላከል.......
የበሽታ አምጪ ተህዋስያንን በዘረመል ደረጃ ለመለየትና ለመመርመር የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው። በሁለት ቃላት ውህደት የተመሰረተው ሳይንሳዊ ስያሜው ኢፒጅን (EpiGen) ይሰኛል። ኢፒ የሚለው ኢፒዶሞሎጂን የሚወክል፤ ትርጉሙም የበሽታዎች ጥናት ሲሆን ጂኖሚክ ደግሞ ዘረመል ማለት ነው። ጽንሰ ሀሳቡ የበሽታዎችን ምንነት ከስር መሰረቱ መለየት ነው፤ የበሽታዎችን ምንነት ብቻም ሳይሆን በሽታዎች በቆይታቸው የሚያመጡትን ለውጥ የዘረመል ክትትል (Genom- ic Sequence) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የበሽታ አምጪ ተህዋስያንን በዘረመል ደረጃ መለየትና መመርመር የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
ኢፒጂን (EpiGen) በበለጸጉ አገራት እየተሰራበት የቆየ ቴክኖሎጂ ቢሆንም በኢትዮጵያ በአግባቡ የተዋወቀው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት በኋላ ነው። የዚህ ቴክኖሎጂ አስፈላጊነት የላቀ ሆኖ በመገኘቱ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም ለመገንባት ኢፒጂን ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ ተደርጓል።
የፕሮጀክቱ ማጠንጠኛ ተላላፊ በሽታዎች ከመከሰታቸው በፊት ወይም በሽታ በተከሰተ በ24 ሰዓት ውስጥ ጥልቅ የዘረመል ምርምር በማድረግ መረጃውን በአፋጣኝ ለውሳኔ ሰጪ አካል ማለትም ለጤና
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ሚኒስቴር ማሳወቅና በጤናው ዘርፍ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ማስተላለፍ የሚያስችል አቅም መገንባት ነው።
የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት
የቅርብ ጊዜ ክስተት የሆነውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጨምሮ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም ላይ የወረርሽኞች ክስተት ጨምሯል (ዚካ፣ ዴንጊ፣ ኢቦላ፣ SARS)ን መጥቀስ ይቻላል። ባለፉት ጥቂት አሥርት ዓመታት በርካታ ተላላፊ በሽታዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የኅብረተሰብ ጤናን ለመጠበቅ በሽታ አምጪ የዘረመል ጥናት መረጃዎችን የማመንጨት አስፈላጊነት ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ሆኗል።
የኢፒጂን ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የሕዝብ ጤና መርሃ ግብሮች እና ከአውሮፓ ኅብረት አጋሮች የተውጣጣ መሆን፤ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ የቀረበው አካሄድ ኢትዮጵያ የተላላፊ በሽታዎችን ስጋት ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ያጎለብታል።
ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል በአገር አቀፍ ደረጃ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ክትትል መደረጉ በኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው አገራት የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መርሃ ግብሮች ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት
ለኅብረተሰብ ጤና መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
የፕሮጀክቱ ጠቀሜታ
የኢፒጂን ዋነኛ ጠቀሜታ ማንኛውም አይነት አዲስ የተከሰተ ተላላፊ በሽታ ጉዳት ከማድረሱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ነው። የኅብረተሰብን ጤና የሚያጓድል የበሽታ ወረርሽኝ መቼ፣ የት እና እንዴት እንደሚከሰት አይታወቅም። ስለሆነም ኢፒጅን ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ሊከሰቱ የሚችሉ ወረርሽኞችን የመለየት አቅም መገንባት የሚያስችል መሆኑ ተጠቃሽ ነው።
በሽታዎችን በዘረመል ደረጃ ለመመርመር፤ የቤተ-ሙከራ (ላቦራቶሪ) አቅምን ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችለው ይህ ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ ይደረግ እንጂ፤ ጤና ሚኒስቴር የተለያዩ በሽታዎች በአገር ውስጥ እንዳይከሰቱ ጥንቃቄ በማድረግ እና የመከላከል ስራዎችን በመስራት፤ ከተከሰቱም በኅብረተሰቡ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ በፍጥነት ለመቆጣጠር የተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን ሲተገብር ቆይቷል።
በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍ ያለ የአገር ውስጥ አቅም ለመፍጠር፣ በቤተ-ሙከራ (ላቦራቶሪ)፣ በሰው ኃይል፣ የበሽታዎችን ቅኝት ከማሳደግ አንጻር ጤና ሚኒስቴር በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን ነው የቆየው። ይሁን እንጂ በአገር ውስጥ አቅም በሽታዎች መከሰታቸውን አስቀድሞ መረዳትና መረጃውንም ማሳወቅ የሚያስችል ሙሉ አቅም አልነበረም።
የኢፒጂን ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት፤ የአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የበሽታዎችን ቅኝት የሚያዘምን፣ ሳይንቲስቶች ምርምር የሚያካሂዱበት፣ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ከፍተኛ የትምህርት ዕድል የሚያገኙበት እና ጥናትና ምርምር የሚያደርጉበት እንዲሁም የመመርመሪያ መሣሪያዎችን በአገር ውስጥ የማምረት አቅምን ማሳደግ የሚያስችል ነው።
በአውሮፓ ኅብረት የሚደገፈው ይህ ፕሮጀክት የአውሮፓ አባል አገራት የሆኑት የጀርመን፣ የስፔን እና የኔዘርላንድስ ዩኒቨርሲቲዎች፤ ከአገር ውስጥ ደግሞ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት እና አምስት የአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች ተካተውበታል።
በአገሪቷ በሚገኙ በተመረጡ ሆስፒታሎች የሚተገበር ሲሆን ከሦስት መቶ ሆስፒታሎች መረጃዎችን በመሰብሰብ ችግሮችን በመለየት እና መፍትሄ በማስቀመጥ አቅጣጫ
የሚሰጥበት፤ የ300 ጤና ተቋማት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ለአምስት ዓመታት የሚዘልቅም ነው - ኢፒጅን ኢትዮጵያ ፕሮጀክት።
የፕሮጀክቱ ግቦች
የፕሮጀክቱ ቀዳሚ ግብ፤ የኅብረተሰብ ጤና የውሳኔ አሰጣጥን ማሳደግ የሚያስችሉ የሕክምና ምርምሮችና ናሙናዎች እንዲሁም የአንድ አካባቢን ማኅበረሰብ የጤና ሁኔታን የተመለከቱ መረጃዎችን መሰብሰብ እና ትንተና ማቅረብ ነው። የቤተ-ሙከራ (Laborato- ry መሠረተ ልማት ማጠናከር፣ የሰው ኃይል ማሰልጠን፣ በሽታ አምጪ የዘረመል መረጃ ትንተና እንዲሁም መረጃ ለማጠናቀር የሚረዱ ነጥቦችን ከዘረመል ጥናት መረጃዎች ጋር ማቀናጀትን ጨምሮ በኢትዮጵያ በሽታ አምጪ የዘረመል ቅደም ተከተል አቅምን ማሳደግ ሌላው ግብ ነው።
አዳዲስ የዲጂታል መመርመሪያ ዘዴዎችን ማዘጋጀትና መተግበር፤ ለሕዝብ ጤና እና ለፖሊሲ ውሳኔዎች የሚሆኑ የሞባይል ስልክ መተግበሪያዎችን መፍጠር ከፕሮጀክቱ ግቦች መካከል ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም በተላላፊ በሽታዎች፣ በበሽታ አምጪ ተህዋስያን ዘረመል ክትትል ውስጥ የአፍሪካ ትብብር እና ትስስርን በማጎልበት የልምድ ልውውጥ እና የክትትል/ የምርምር ዕድሎችን መክፈትም ከፕሮጀክቱ ይጠበቃል።
የፕሮጀክቱ አፈጻጸም
ሊሳኩ የሚችሉ ዓላማዎችን በማስቀመጥ የተጀመረው ፕሮጀክቱ፤ ክሊኒካል መረጃዎችን መሰብሰብ እና መተንተን፤ የአገር ውስጥ የዘረመል ጥናት አቅምን ማሳደግ፣ የዲጂታል ምርመራ አቅምን በማጎልበት ለኅብረተሰብ ጤና ውሳኔ ሰጪዎች ወቅታዊ መረጃ ማቅረብ፣ በአፍሪካ አገራት መካከል የልምድና የዕውቀት ልውውጥ የሚደረግበትን መንገድ የማመቻቸት ዓላማዎችን አንግቧል።
የፕሮጀክቱ ዋና ተልዕኮ ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል አገር አቀፍ የዘረመል ጥናትና የመረጃ ክትትልን ማዳበር ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ በሽታዎችን መከላከል እና መቆጣጠርን ያካትታል።
ኢፒጂን በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት፤ በ Amsterdam Institute for Global Health & Development (AIGHD) እየተመራ፤ ከአውሮፓ አጋሮች Pharm Access Inter- national፣ Heinrich-Heine University Dusseldorf፣ The Barcelona Institute for Global Health፤ ከአገር ውስጥ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ አርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት፣ አርሲ፣ ባህር ዳር እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመተባበር የሚተገብሩት ይሆናል።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
አገልግሎቱ ለማኅበረሰብ ጤና መጠበቅ. . .
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
ጤና መጠበቅ. . .
በኢትዮጵያ ጤናው የተጠበቀ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር፤ የእናቶችና ሕፃናትን ሞት ለመቀነስ፤ ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ የሣምባ ነቀርሳ፣ የወባ እንዲሁም ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፤ በዚህም ጤናማ ማኅበረሰብ ለማፍራት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያበረከታቸውና የሚያበረክታቸው አስተዋጽኦዎች በርካቶች ናቸው።
በጤናው ዘርፍ ከተቀመጡ ስትራቴጂያዊ ግቦች አንፃር በአገራችን የሚገኙ የጤና ተቋማት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ፤ እንዲሁም በርካታ አዳዲስ አገልግሎቶች ከመስፋፋታቸው ጋር ተያይዞ የመድኃኒት እና የሕክምና መገልገያዎች ፍላጎት በዓይነትም በመጠንም ከዓመት ወደ ዓመት በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ነው።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጤና ተቋማትን ፍላጎት ታሣቢ በማድረግ በዓለምአቀፍ መስፈርት መሠረት ከውጭ እና ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች መድኃኒቶች፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እንዲሁም ሪኤጀንቶችን ግዥ በመፈፀም፤ በድጋፍ የሚቀርቡ ግብዓቶችንም አክሎ ለጤና ተቋማት በማሠራጨት የማኅበረሰቡን ጤና ከማስጠበቅ አንፃር ጉልህ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል።
አገልግሎቱ የመድኃኒት አቅርቦት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ II ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሦስት ዓመታትም ጉልህ ስኬቶችን አስመዝግቧል። በዋናነት የደንበኞችን እርካታ በ2013
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ዓ.ም ከነበረበት 67 ነጥብ 8፣ በ2015 ዓ.ም ወደ 74 በመቶ፤ የባለድርሻ አካላት እርካታ ከ72 ነጥብ 5 ወደ 91 ነጥብ6 በመቶ፤ የተገላባጭ ፈንድ መድኃኒቶች ትንበያ ትክክለኛነት መጠን ከ51 ወደ 60 በመቶ ያደጉ ሲሆን፤ የመድኃኒት የግዥ ቀናት ከ241 ወደ 194 ቀናት፤ የመድኃኒት ብክነት መጠን ከ2 ነጥብ 67 ወደ ዜሮ ነጥብ 72 በመቶ መቀነስ ተችሏል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተፈቀደ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ማረጋገጫ፤ አገልግሎቱን መልሶ ማቋቋሚያ አዋጅ ዝግጅት፤ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፤ የIFRS አተገባበር፤ የአገር ውስጥ አምራቾችን አፈፃፀም ለማሻሻል የተወሠዱ እርምጃዎች፤ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ማሻሻያ፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻል፤ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ያከናወናቸው ተግባራት በተቋሙ የአመራር አካላት ቁርጠኝነት እና በሠራተኞች ትጋት የተመዘገቡ የአገልግሎቱ ስኬቶች ናቸው።
በሌላ በኩል ባለፉት ሦስት የትግበራ ዓመታት ከተስተዋሉ ድክመቶች መካከል የሜጋ መጋዘን ኘሮጀክት፣ የመረጃ ጥራት መጓደል፣ የመረጃ አጠቃቀም ባሕል፤ የክፍያ አሰባሰብ ጊዜ መዘግየት፣ የመጋዘን ኪራይ እና የዋጋ ውድመት፣ በቂ ያልሆነ የአቅርቦት ሰንሠለት፣ የተቀናጀ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት መጓደል፣ ደካማ የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ሥርዓት መኖር፤ ጠንካራ የውስጥ ጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት አለመኖር ከታዩ ክፍተቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው። እነዚህ ድክመቶች በመካከለኛው ዘመን ዕቅድ እንደ ቅድመ ሁኔታ በማገልገል የሚተገበሩ ይሆናሉ።
የመካከለኛው ዘመን ዕቅድ (ከ2016 – 2018) ዓ.ም
በመካከለኛው የዕቅድ ዘመን ዘጠኝ ስትራቴጂክ ዓላማዎችን እና ስምንት ዋና ዋና ኘሮጀክቶች ተካተዋል፡-
• ስትራቴጂያዊ አጋርነትን ማሣደግ፣የግዥ ሂደትን ማዘመን፣
• የመጋዘን አያያዝና የሥርጭት ሂደትን ማሻሻል፣
• የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓትንና ቅልጥፍናን ማጎልበት፣
• በSCM ቴክኖሎጂ እና የመረጃ ሥርዓት ማጎልበት፣
• የተቋሙን አስተዳደራዊ አመራር
ማጎልበት፣
• የተቋሙን ስትራቴጂክ የስጋት አስተዳደር እና ተፅዕኖን የመቋቋም አቅም ማሳደግ፣
• የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን ማሻሻል፣
• የተቋሙን አሠራር፣ ስታንዳርድ እና መመሪያዎችን ትግበራ ማጠናከር ናቸው።
የተዘረዘሩት ዓላማዎች፤ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር፣ የሕክምና መሣሪያዎች አስተዳደር፣ የቀጥታ ሥርጭት ተደራሽነት፣ ስትራቴጂያዊ ግዥ፣ የመጋዘን የልህቀት ማዕከል፣ የፋይናንስ ዘላቂነት፣ ስልታዊ የውል አቅርቦት እና የኢንተርኘራይዝ ግብዓት ዕቅድ ኘሮጀክቶች በስትራቴጂክ ጊዜ ውስጥ የሚካተቱ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው።
በእነዚህ ተግባራት ስትራቴጂያዊ ዓላማዎችን እና ተነሳሽነቶችን ለመለካትና ለመከታተል ግቦች ተቀምጠዋል።
ግቦች፡-
• የደንበኞችን እርካታ መጠን ከ74 ወደ 92 በመቶ ማሳደግ፣
• የፋርማሲዩቲካል አቅርቦቶችን ከ83 ነጥብ 4 ወደ 92 በመቶ ማሳደግ፣
• የመድኃኒት ግዥ ጊዜን ከ194 ቀናት ወደ 160 ቀናት መቀነስ፣
• የአገር ውስጥ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎችን ከ12 ነጥብ 7 ወደ 47 በመቶ ማሳደግ፣
• የመድኃኒት ብክነትን ከዜሮ ነጥብ 72 ወደ ዜሮ ነጥብ 66 በመቶ መቀነስ፣
• የጥሬ ገንዘብ ኡደትን (cash to cash cy- cle) ከ371 ወደ 180 ቀናት መቀነስ፣
• ብቃት ያለው የሠው ኃይልን 75 በመቶ ማድረስ፣
• የሠራተኞችን እርካታ ከ48 ወደ 65 በመቶ ማሳደግ እንዲሁም
• የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ትግበራዎችን ከ86 ወደ 100 በመቶ ማድረስ ናቸው።
ለመካከለኛው ዘመን ዕቅድ. . .
ለዕቅድ ዘመኑ 33 ሚሊዮን 310 ሺህ 374 ዶላር አጠቃላይ በጀት የተያዘለት ሲሆን ከላይ ለተዘረዘሩት ስምንት ኘሮጀክቶች 16 ሚሊዮን 363 ሺህ 481 ዶላር ግምት ተቀምጦላቸዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ዘጠኝ ስትራቴጂክ ዓላማዎች እና ስምንት ተፈፃሚ ኘሮጀክቶችን ይዞ ለአፈፃፀም ዝግጁ ሆኗል።
ፖለቲካ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ምክክር የሀገር መድኅን!!
በቁምልኝ አያሌው
እንደ መግቢያ
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ የፖለቲካ ባሕላችን መልኮች
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ባሕል ምላጭ በሚያስውጥ እልህ፣ መጠፋፋት እና ብሽሽቅ ምዕተ ዓመታትን ተሻግሯል። ኢትዮጵያ አሁን የያዘችው ቅርፅ እንዲኖራት መሰረት በጣለው እና ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያና የ20ኛው ክፍል ዘመን መባቻ ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ ዑደት በአራት ከፍለን እንመልከተው።
የመጀመሪያው የፖለቲካ ምዕራፍ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ እስከ 1966 ዓ.ም የቆየው የፖለቲካ ሥርዓት ነው። በወቅቱ የነበረው ሥርዓት በነገሥታት የሚመራ የፊውዳል ሥርዓት እንደነበር የፖለቲካና የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ። ይህ ሥርዓት የራሱ በጎ መልኮች ያሉትን ያህል ኋላቀር፤ “ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ” በሚል ብሂል የሚመራ አብዛኛውን ሕዝብ ውስን ባላባቶች የሚመዘብሩበትና የዴሞክራሲ ልምምድ ያልነበረበት ነው። ለዓመታት ታምቀው የቆዩና የተጠራቀሙ ቅሬታዎች የወለዱት የ1966ቱ አብዮትም የፊውዳል ሥርዓቱን ከማሻሻል ይልቅ ጠራርጎ አስወግዶታል፤ የነገሥታቱ ዘመን እና ሥርዓታቸውም አክትሟል።
"ጦርነትን ኖረንበታል።የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈትተንበታል። አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል። በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው። ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም። ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው። ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል። ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል።"
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ሁለተኛው የፖለቲካ ምዕራፍ የፊውዳል ሥርዓት መገርሰሱን ተከትሎ የመጣው የ1966ቱ አብዮት ነው። የአብዮቱን መምጣት ተከትሎ በሀገሪቷ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ ዕይታዎችን ያነገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብቅ ያሉበትን አዲስ አውድ አስከትሏል። ይህም ብዝኃ የፖለቲካ ሥርዓት መወለድን ያበሰረ ቢመስልም፤ በወቅቱ ሀገር የሚመራው የደርግ ሥርዓት ለብዝሃ የፖለቲካ ሥርዓት የማይመቹ ሁኔታዎች ነበሩት። አንደኛው የአብዮቱ መሪዎች ግራ ዘመም የፖለቲካ አመለካከትን ያራምዱ ነበር፤ ደርግ ለሀገር ግንባታ የጣላቸው በጎ መሰረቶች ቢኖሩትም የትኛውንም የፖለቲካ እሳቤ በኃይል የማስፈጸም እሳቤን ያራምድ ስለነበር ብዙ የታጠቁ ቡድኖች በከተማና በገጠር እንዲፈለፈሉ ምክንያት ሆነ፤ አብዮቱ በሰከነ መንገድ ሀገር ከመምራት ይልቅ የእልህ፣ የመጠፋፋት፣ የፖለቲካ ልዩነትን በኃይል የማስፈጸም አካሄድን በመከተሉ ምክንያት በትጥቅ ትግል ተወግዷል።
ሦስተኛው ምዕራፍ በ1983 ዓ.ም የደርግ ሥርዓት ማክተምን ተከትሎ ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበትና እስከ 2010 የቆየበትን የፖለቲካ ዑደት ይዳስሳል። ኢህአዴግ ወደ መንበረ ሥልጣኑ ሲመጣ የሀገሪቷ ፖለቲካ ላይ የተወሰኑ ለውጦች መጥተዋል፤ ለምሣሌ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ጥያቄ የነበረው የብሔሮች እኩልነት የብዝሃ ማንነት ጉዳይ በሕገ-መንግሥቱ ምላሽ አግኝቷል፤ በአንጻሩ ለ1966ቱ አብዮት መነሻ የነበረው የዴሞክራሲ ጥያቄ በኢህአዴግ መራሹ ሥርዓት መጀመሪያ አካባቢ ልምምድ የነበረ ቢሆንም እየቆየ ግን ምላሽ ሳያገኝ እየተድበሰበሰ ወደ አፈና ሥርዓት ተሸጋግሯል። በተለይም ከአንድነት ይልቅ የልዩነት ፖለቲካ ተለጥጦ ተሰብኳል፤ በቀደሙት ሥርዓቶች የነበሩ የፍጹማዊ አንድነት ስህተቶችን ለቅሞ በመውሰድ በተቃራኒው ሀገራዊ አንድነትን አደጋ ላይ የሚጥል ጠርዝ የነካ የልዩነት ትርክት እንዲሰራጭ ተደርጓል፤ የዴሞክራሲ ባሕል ልምምድ በየጊዜው እየዳበረ መሄድ ሲገባው እየተዳከመ ቀጥሎ የልምምድ በሩ እየጠበበ መጥቷል፤ በዚህም ምክንያት ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ለ27 ዓመታት የተጠራቀሙ ችግሮች የ2010ሩን ሕዝባዊ የለውጥ ንቅናቄ አዋልደዋል።
አራተኛው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርዓት ምዕራፍ የሚጀምረውም በዚሁ ጊዜ ነው፤ በለውጡ ማግስት የዴሞክራሲ ልምምድን ባሕል ለማድረግ ምህዳሩን የመክፈት እርምጃዎች ተወስደዋል፤ መገናኛ ብዙኃን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ተደርጓል፤ በውጭ ያሉና በትጥቅ ወይም በሌላ የፖለቲካ አማራጭ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወደ ሀገራቸው ገብተዋል፤ ባለፉት ሥርዓቶች የተፈጠሩ ችግሮች በይቅርታ፣ በፍቅር እና በሠላማዊ መግባባት በዘላቂነት መፍታት ላይ ትኩረት ሰጥቷል፤ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን የፖለቲካ ጠርዝ ወደ መሀል በማምጣት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ማጠንከር አለብን የሚል አዲስ አካሄድ ማራመድ ተጀምሯል፤ ሆኖም ለዓመታት የተጠራቀሙ ችግሮችን በመፍታት ሂደት ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተዋል፤ የፖለቲካ ሥርዓቱን የማሻሻል ሂደቱንም ፈትነዋል።
የነበረው ኋላቀር የፖለቲካ ባሕል የልዩነት ሃሳብን በአፈሙዝ የበላይነት የመፍታት ዝንባሌ የተጠናወተው፣ የሃሳብ ልዕልናን የማይፈልግ፣ የአሸናፊና ተሸናፊነት፣ የጠላትና የወዳጅ ፍረጃ የሚስተዋልበት ነው። ይህ የፖለቲካ ባሕል የትርክት መዛባትን ፈጥሮ በልሂቃን መካከል
የነበረው መቆራቆስ ወደ ማኅበረሰቡ ወርዶ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲመለከት አስገድዷል፤ በየአካባቢው ግጭቶች እንዲፈጠሩ፣ ግጭትና መፈናቀል እንዲኖር፣ አለመረጋጋት እንዲቀጥል፣ ከሁሉም በላይ ዘላቂና አስተማማኝ ሠላም እየተገነባ እንዳይሄድ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ሕዝብም በሀገሩ እፎይታ አግኝቶ በሠላም ሰርቶ ለመኖር እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ ሲወተውት ዓመታት ተቆጥረዋል። ባለፉት የሀገሪቷ የፖለቲካ ዑደት ምዕራፎች ትውልዱ ያጋጠሙትን መልካም ዕድሎች በአግባቡ ባለመጠቀሙ ኢትዮጵያን እቶን ላይ የጣዱ ችግር እና ፍዳ አሽክሟታል። የዛሬው ትውልድም አንድ ዕድል መዳፉ ላይ ነው፤ ለዚህም ይመስላል ከለውጡ በኋላ የመጣው መንግሥት የሕዝቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የታመመውን የፖለቲካ ባሕል ለማከምና አገራዊ ስብራቱን መጠገን የሚያስችሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር “ሀገራዊ ምክክር”ን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የችግሮች መፍቻ ቁልፍ አድርጎ ለመተግባር ገለልተኛ ኮሚሽን የማቋቋም እርምጃን ወስዷል። እዚህ ጋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተናገሩትን ዋቢ እናንሳ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፥
“ጦርነትን ኖረንበታል። የተወሰኑ ችግሮቻችንን ፈተንበታል። አብዮትን ደጋግመነዋል። የተወሰኑ ችግሮችን ፈትተንበታል። በሁለቱም ያልተፈቱትን ችግሮች ለመፍታት የቀረን መንገድ ምክክር ነው። ምክክርን ግን አልተጠቀምንበትም። ጦርነትና አብዮት የተሟላ መፍትሔ የማያመጡት አሸናፊ እና ተሸናፊ ስለሚያስከትሉ ነው። ቢዘገይም የተሸነፈው ለማሸነፍ ይታገላል። ያሸነፈውም ድሉን ለመጠበቅ ይዋጋል። ምክክር ግን ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል። ከተሸነፍንም ሁላችንም ለአገራችን ብለን ነው የምንሸነፈው። ይሄ የምክክር ሂደት ሦስት ነገሮች ያስገኝልናል።
• ሁሉንም ባይሆን እንኳን ዋና ዋና ችግሮችን ይፈታል
• ከጦርነት ይልቅ ምክክር ባሕል እንዲሆን ያደርጋል
• በተቃራኒ ኃይሎች መካከል መቀራረብና መግባባት ይፈጥራል።
ይሄንን መቀራረብ በመጠቀምም ወደፊት በጉዳዮች እየተነጋገርን ለመቀጠል ያስችለናል።
በመሆኑም ይኽንን ዕድል ሳናበላሽ ወደ ተሟላ ድል እንድናሸጋግረው እጠይቃለሁ″ የሚል ነው።
ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን መልዕክት ተመርኩዘን ወደ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ስንንደረደር ምንነቱን አስቀድሞ ግልፅ ማድረግ የግድ ይላል።
ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው?
በሀገራዊ ምክክር ላይ ብያኔ የሰጡ አጥኚዎች የንድፈ ሃሳብ አፍላቂዎች ሁሉ የየራሳቸው የአገላለፅ ቅርጽ ቢኖራቸውም ዋና ጭብጣቸው ለሀገር ሠላም፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ እና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጠንቅ የሆኑ አለመግባባቶችን ቅንነት በተሞላበት ሀገራዊ ውይይት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ያሳያል። በሀገራዊ ውይይቶች የሚቀመጡ የመፍትሔ አቅጣጫዎችም የሀገርን የወደፊት ዕጣ ፋንታ በመወሰን ዜጎች በጋራ ማንነት ላይ የተመሰረተ ብሩህ እይታ እንዲኖራቸው ያስችላል ማለት ነው።
ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቁርሾን ለመፍታትም መንግሥት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የማኅበረሰብ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ተቋማት እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች በአንድ መድረክ ተሰይመው የሚመካከሩበት ግልጽ የዜጎች መድረክ እንደሆነ ይወሰዳል። የምክክር ሂደቱም አለመግባባትን ለመፍታት ሁነኛ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል። ብሔራዊ መግባባትን በመፍጠር ቀጣይነት ላለው የተረጋጋ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ከፍተኛ ትርጉም ይሰጠዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶችም ሀገራት ያጋጠሟቸውንና እያለፉበት የየሚገኘውን ፈታኝ ሁኔታ ለመቋጨት ብሔራዊ ምክክር ቀዳሚ መንገድ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ሀገራዊ አለመግባባቶችን ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ዓለም አቀፍ ተመራጭነቱ እየጨመረ የመጣውን ብሔራዊ ምክክር ሀገራት እንደየ ነባራዊ ሁኔታቸው አካሂደውታል። የምክክር ሂደትን በሚገባ የተጠቀሙበት ሀገራትም ግጭትና ፖለቲካዊ ቁርሾን በብሔራዊ መግባባት በመቋጨት በዕድገት ጎዳና በመገስገስ ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን የሀገራት መሪዎች የምክክር ሂደትን ባልተገባ መንገድ ሥልጣን ለማራዘም ሲጠቀሙበትና የውጭ ኃይላት ጣልቃገብነት ካለ የመክሸፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን የሀገራት ተሞክሮ ያሳያል። በዚህም ብሔራዊ ምክክር ያካሄዱ ሀገራት አንዳንዶቹ ስኬትን ሲጎናጸፉ ሌሎቹ ደግሞ ወደማይወጡት የባሰ አዘቅት ተዘፍቀዋል።
ብሔራዊ ምክክር የተደረገባቸው ክፍለ ዓለማት ተዛምዶ ሊለያይ ይቻል እንጂ አዲስ ክስተት አይደለም።
ለአብነት፡-
• የመጀመሪያው፡- የኮሙኒዝም ሥርዓት ከምስራቅና መካከለኛው አውሮፓ መንኮታኮት ጋር የተያያዘ ነው። እ.አ.አ. በ1989 የኮሙኒዝም ሥርዓት መፈራረስን ተከትሎ የተፈጠሩ ዋና ዋና የፖለቲካ ስንጥቃቶችን ለመቋቋም ተጠቅመውበታል። ፖላንድ፣ ሀንጋሪ፣ ቼኮዝሎቫኪያ፣ ምስራቅ ጀርመን እና ቡልጋሪያ በሠለጠነ የጠረጴዛ ላይ ውይይት ብሔራዊ ምክክር አካሂደው መግባባትን ፈጥረው ያለፉ ሀገራት ናቸው።
• ሁለተኛው፡- እ.አ.አ በ1990ዎቹ መባቻ ላይ በአህጉረ አፍሪካ ብሔራዊ ምክክር እንደ ማዕበል የተካሄደበት እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። በበርካታ ፈረንሣይኛ ተናጋሪ ሀገራት የተካሄደው ብሔራዊ ምክክርም ሥልጣን በጨበጡ ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ መሪዎችና ዜጎች መካከል የተካሄደ ነበር። የመጀመሪያው ሂደትም መሪዎች ምክክር እንዲያደርጉ የተገደዱበት ክስተት እንደሆነ ይገለፃል።
• ሦስተኛው፡- በርካታ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት በ1990ዎቹ ሕገ-መንግሥታዊ እና አሳታፊ የአስተዳደር ሥርዓት በመመስረት ልማትን ማጠናከር የሚያስችል መግባባት ለመፍጠር ያደረጉት ብሔራዊ የምክክር ሂደት ነው። ከዚህ አኳያም የደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሆኑት ቦሊቪያ እና ኮሎምቢያ በሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት የደረሱባቸው ጉዳዮች የብሔራዊ ምክክር ቁልፍ ነጸብራቅ ተደርገው ይወሰዳሉ።
• አራተኛው፡- በቅርቡ ከተካሄደው የዓረብ አብዮት ጋር የሚያያዝ የምክክር ሂደት ነው። በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ ሀገራት የተቀጣጠለው የዓረብ አብዮት ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላኛው በከባድ ፍጥነት በመስፋፋቱ የፖለቲካ ሥርዓቱ ላይ አዲስ መንገድ አመላክቷል፤ ብሔራዊ ምክክርን ማካሄድ ሁነኛ የመፍትሔ አካል ተደርጎ ተወስዷል። ሞሮኮ፣ ሊቢያ፣ ቱኒዚያ እና ግብጽም በተመሳሳይ ወቅት ብሔራዊ ምክክር አካሂደዋል። በተጨማሪም ሱዳን፣ ሊባኖስ፣ ባህሬን እና የመን ብሔራዊ ምክክር በማካሄድ አሁን ካሉበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የስኬትና የውድቀት ማሳያ የሆኑ ሂደቶችን አስተናግደዋል።
በሌላ መልኩ ደቡብ አፍሪካ፣ ላይቤሪያ እና ሊባኖስ ባካሄዱት ብሔራዊ ምክክር ቁርሾን በማስቀረት በዜጎቻቸው መካከል መግባባትን የፈጠሩ ተምሣሌት ሀገራት ሆነው ይጠቀሳሉ።
ደቡብ አፍሪካ፡- ጨቋኝና አግላይ የሆነውን የአፓርታይድ ሥርዓት በመገርሰስ ባካሄደችው ብሔራዊ ምክክር መግባባት በመፍጠር ያስመዘገበችው ስኬታማ ውይይት የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ ሀገር አሰኝቷታል።
ላይቤሪያ እና ሊባኖስ፡- ለተከታታይ ዓመታት በትውልድ ጨራሽ የእርስ በእርስ ጦርነት የቆዩ ሀገራት ነበሩ። ሀገራቱ ባካሄዱት አሸናፊነት የሌለው ጦርነት በዜጎች መካከል ተበጣጥሶ የነበረውን ማኅበራዊ ትስስር ለመጠገን ብሔራዊ ምክክርን ሁነኛ የመፍትሔ አማራጭ አድርገው ተጠቅመውበታል።
በተለያዩ ዓለማት እንደየሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታ የተካሄዱ ብሔራዊ ምክክሮችም በተቀናቃኝ
የአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚያስማማ መፍትሔ በማምጣት የመገዳደልና መጠፋፋት መጥፎ ጠባሳን በብሔራዊ መግባባትና ቀጣይነት ባለው ሀገረ መንግሥት የመተካት ግብን የሰነቁ ናቸው። የብሔራዊ ምክክር ግንባር ቀደም ዓላማም ፍትሃዊ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍል በማድረግ ሀገራዊ ሠላምና ዕድገትን ማስቀጠል ነው።
በተጨማሪም በሀገራዊ ምክክር ሂደት ያለፉ ሀገራት ውጤቶችን አስገኝቶላቸዋል። የምክክር ሂደት ውስጥ እንዲገቡ ያስፈለገበት ምክንያት የሚለያይ ቢሆንም በብዙ ሀገራት የተደረጉ የምክክር ሂደቶች ተቀራራቢ ውጤት አምጥተዋል። በሂደቱ ያለፉትም በፓለቲካ ሥርዓት፣ በሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች፣ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ፣ በሰብዓዊ መብት አያያዝና ቀደም ሲል በተፈፀሙ በደሎች ላይ መፍትሔ በማበጀት ወሳኝ የሚባሉ ዋና ዋና ውጤቶች ማስመዝገብ ያስቻሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ወስደዋል።
በፓለቲካ ሥርዓት መስክ፡- በምክክር ሂደት የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ አዳዲስ የፓለቲካ አስተሳሰብና አሰላለፍ እንዲከተሉ አስችሏቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በመንግሥታት ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚና ሕግ ተርጓሚ አካላት ላይ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጡ ዕድል አምጥቶላቸዋል።
በሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች፡- ሀገራዊ ምክክር ከሚያስገኛቸው ውጤቶች አንዱ ሕገ-መንግሥትን ማሻሻል ነው፡፡ ሀገራት ሕገ- መንግሥታቸውን በመሻር በአዲስ መቅረፅን ጨምሮ በተመረጡ አንቀፆች ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸውን ያለፉበት የምክክር ሂደት ተሞክሮ ያሳያል።
በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስክ ፡ በምክክር ሂደት ያለፉ ሀገራት ዜጎቻቸው ያነሷቸውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች መጠገን ያስቻሉ ድሎችን ተጎናጽፈዋል። ይህም መንግሥት ከመልካም አስተዳደር፣ ከትምህርት፣ ከጤና ፣ ከፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉበትን የለውጥ እርምጃ እንዲወስድ ዕድል ይሰጣል።
በሠብዓዊ መብት አያያዝ፡- የሰው ልጅ ከሚያነሳቸው መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የሠብዓዊ መብት መጠበቅ አንዱ ነው። በሀገራዊ ምክክር ሂደትም በሕይወት የመኖር፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የሴቶችና ሕፃናት መብቶችን የሚያስጠብቁ የማሻሻያ እርምጃዎች ተጠቃሽ ውጤቶች ሆነው እናገኛቸዋለን።
ቀደም ሲል ለተፈጸሙ በደሎች መፍትሔ በማበጀት፡- በምክክር ሂደት ወቅት በግጭት የቆዩ ሁለት ምድቦች ያሳለፉትን አስከፊ የቅራኔ ሂደት በግልጽ በመነጋገር መፍትሔ እንዲያበጁ ዕድል ይሰጣቸዋል። ሀገራት በሂደቱ የተፈጸሙ በደሎች እልባት የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት አካታችና ጤናማ ግንኙነት መመሰረት ችለዋል።
ምክክር ከሌሎች የልዩነት እና የግጭት መፍቻ መንገዶች በምን ይለያል?
ምክክር ልዩነቶችና አለመግባባቶችን ወይም ግጭቶችን ለማስወገድ ጥቅም ላይ ከሚውሉ አማራጮች መካከል አንዱ እንጂ ብቸኛው አማራጭ እንዳልሆነ ይነሳል። ከሚታወቁት ሠላማዊ የልዩነት ወይም የግጭት መፍቻ መንገዶች መካከል ውይይት፣ እርቅ፣ ድርድር ወይም ክርክር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምክክርም ውይይት፣ ክርክር፣ እርቅ አሊያም ድርድር ማለት እንዳልሆን መገንዘብ ያስፈልጋል። ተቀራራቢነታቸውን በመውሰድ አንድና ተመሳሳይ ተደርገው ሲታዩ ይስተዋላል። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ሃሳቦች ከምክክር አኳያ የየራሳቸው ትርጉምና ምንነት እንዳላቸው
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
አንረዳለን።
ድርድር (Negotiation) ተቀናቃኝ ኃይሎች በቀጥታ የሚሳተፉበት ሂደት ነው። በዚህ ያለ ሶስተኛ ወገን አስማሚነት ስምምነት ላይ ለመድረስ በሚደረገው ጥረት የውሳኔ ሃሳቦችን የሚያፈልቁበት ሂደት እንደሆነ ይነሳል። በሂደቱ ለድርድር የሚቀመጡት ወገኖች ተቀባይነት ያለው ታዛቢ በመሰየም በድርድሩ ወቅት አንዱ አካል ከሌሎች ልቆ ለመውጣት ይጥራል።
ሽምግልና (Mediation) ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በፈቃዳቸው ተቀባይነት ባለው ሶስተኛ ወገን (አሸማጋይ/ሽማግሌ) አማካይነት በመካከላቸው የተፈጠሩ ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚደረግ የግጭት ወይም ያለመግባባት መፍቻ አንድ መንገድ ነው። የግጭቱ ወይም የልዩነቱ ዋና ባለድርሻ አካላትን የሚያካትት ሲሆን የሌሎች ባለድርሻ አካላትን አስተያየት እና ፍላጎቶች በተለያዩ የተሳትፎ መንገዶች ወደ ሂደቱ እንዲቀላቀሉ ያደርጋል። ባለድርሻ አካላቱ ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ካልቻሉ የመሸምገል ወይም የማስታረቅ ሚና ያለው ወገን ለማስማማት የመወሰን አቅም የለውም። ነገር ግን ያስማማሉ የሚላቸውን ሃሳቦች የሚያቀርብበት መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል።
ክርክር ወይም ሙግት (Argument) የሃሳብ ፉክክር ነው። የሚደግፉት ሃሳብና አቋም አሸናፊ እንዲሆን ማድረግ ላይ ትኩረት ያደርጋል። ሌሎች የሚያራምዱትን የሃሳብ አመክንዮ ”ስህተት“ መሆኑን ለማስረዳትና ለማረጋገጥ ጥረት ይደረግበታል። የሌሎችን ድክመቶች በመፈለግ አቋማቸውን ይተቻል። የመደማመጡ ግብም የሌላውን ወገን ሃሳብ ለመረዳት ሳይሆን ድክመትን ለመፈለግ ጥረት የሚደረግበት የትችት አካሄድ ነው። በግጭትና በልዩነት ላይ ማተኮርን እንደ ልዩ ጥቅም በመመልከት ለጋራ ጉዳይና ለመልካም ግንኙነት ቦታና ዋጋ የለውም።
ውይይት (Discussion) የትኩረት መስኮቹ በፅንሰ-ሃሳቦች ላይ መነጋገር ነው። መረጃንና ዕውቀትን የማካፈል ዓላማ አለው፡ ፡ በማጠቃለያውም ”ገለልተኛ ሆኖ“ የመቆየትና የመታየት አዝማሚያ ይታይበታል። ለተነሱ ጉዳዮች መፍትሔና ምላሽ ለማፈላለግ፤ ግጭትና ልዩነት ሊፈጥሩ ወይም ሊያባብሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለማስወገድ ጥረት ያደርጋል። ከክርክር በተለየ መልኩ ለጋራ ጉዳዮችና መልካም ግንኙነቶች ዋጋ ይሰጣል።
የግልግል ዳኝነት (Arbitration) ተቀናቀኝ ኃይሎች ችግራቸውን ለግልግል ዳኞች በማቅረብ ውሳኔ የሚያገኙበት መንገድ ነው። ለዳኞች የሚቀርቡ ጉዳዮችም በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የጋራ የሆኑ ስምምነቶች ናቸው። ተቀናቃኝ ኃይሎች በጋራ ባደረጉት ስምምነት ፍርድ የሚሰጧቸውን ዳኞች ይመርጣሉ። የግልግል ዳኞች በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል ውሳኔ የማሳለፍ ሙሉ ሥልጣን አላቸው።
ምክክር (Dialogue) በአንድ ሀገር ውስጥ በመሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ እና ስር የሰደዱ ልዩነቶች ሲያጋጥሙ በበርካታ ሀገራዊ ባለድርሻ አካላት መካከል መግባባት ለመፍጠር ያለመ ሂደት ነው፡፡ የሀገራዊ ምክክር መድረኮች በአመለካከት፣ በእምነት፣ በብሔር፣ በዕድሜ፣ በፆታ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ሁኔታ የሚለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እንዲሁም የፖለቲካ መሪዎችን በማገናኘትና በልዩነቶቻቸው ዙሪያ እንዲመካከሩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር የሚያስችል ሁነኛ መሳሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።
ሀገራዊ ምክክር እንደ ክርክር የኔ ሃሳብ ወይም አቋም ትክክል ነው በሚል የሌላውን ሃሳብ ወይም አቋም በማጣጣልና በመድፈቅ የራስን ሃሳብ የበላይነት ለማሳመንና ለማንገሥ ጥረት የሚደረግበት አይደለም። እንደ ድርድርም በሰጥቶ መቀበል መርህ በጉዳዮች ላይ ተስማምቶና ለተግባራዊነቱ አሳሪ ሕጎችን በማውጣት የሚተገበር አይደለም።
ምክክር እንደ ውይይትም በጉዳዮች ላይ ተወያይቶና መረጃ ተለዋውጦ መለያየት አይደለም። ይልቁንም በመደማመጥ፣ አንዱ የሌላውን አቋምና እውነት ለመረዳት ጥረት በማድረግ ወይም አንዱ በሌላው ጫማ ውስጥ ሆኖ በማሰብ ለሕዝብ እና ለሀገር የሚበጅ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚደረግ አሳታፊ፣ አካታች፣ የአብዛኛው ማኅበረሰብ ጉዳዮች በሆኑ አጀንዳዎች ላይ የሚያተኩር፣ ግልጽ የሆነ አካሄድና ገለልተኛ አመቻችን የሚጠይቅ ሂደት ነው።
በአብዛኛው የሀገራዊ ምክክር ባለቤትም ሆነ ዋነኛ ፈጻሚ ሰፊው ሕዝብ መሆኑ ከሌሎች ግለሰቦች ወይም ውስን ቡድኖች ከሚገኙባቸው የልዩነት ወይም የግጭት መፍቻ መንገዶች የተለየ ያደርገዋል። የውጭም ሆኑ የአገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ለምክክሩ የተሳካ መሆን አስቻይ ሁኔታዎችን ከመፍጠር በዘለለ ውጤቱ ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ አይፈቅድም።
በምክክር እና በሌሎች የግጭት መፍቻ መንገዶች ጽንሰ ሃሳቦች ዙሪያ የተገለጹት ልዩነቶች ቢኖሩም በአተገባበር ግን ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማስገኘት ሲባል በጥምረት ጥቅም ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። ለምሣሌ የተካረሩ ልዩነቶችን ወይም ደም አፋሳሽ ግጭቶችን በቅድሚያ በድርድር ወይም በሽምግልና በመፍታት መሰረታዊ ልዩነቶችን በሀገራዊ ምክክር ዘላቂ መፍትሄ ወደማስገኘት ማሸጋገር ይቻላል።
ሀገራዊ ምክክሮች እንደ ሌሎቹ ውጤት ላይ ብቻ ሳይሆን በሂደቱ ላይ ጭምር የሚያተኩሩና ለሂደቱ አካታችነት፣ አሳታፊነት፣ ግልጽነትና ፍትሃዊነት ትኩረትና ላቅ ያለ ዋጋ የሚሰጡ ናቸው። ከሚያስገኙት ውጤት እኩል ወይም በበለጠ ሁኔታ የሂደታቸው ቅቡልነት፣ አካታችነት አና ተዓማኒነት ወሳኝ ነው።
ይህ ሲባል ሀገራዊ ምክክሮች ተጨባጭ ውጤቶች የሏቸውም ማለት አይደለም፡ ፡ በተጨባጭ የሚያስገኟቸው ውጤቶች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህ ውጤቶች የተገኙባቸው ሂደቶች ግን መለያ ባሕሪያቸው ናቸው። በሌላ አነጋገር ሀገራዊ ምክክሮች ዘላቂ መግባባት እና መተማመንን ለመፍጠር ሂደትን ማዕከል ያደረጉ መድረኮች ይሆናሉ።
ሂደቱን በጥንቃቄ በማለፍ ውጤታማ መሆን ግን በቀላሉ የሚታሰብ አይደለም። በማኅበረሰቡ የተለመዱ፣ በብቸኝነት ትክክል መስለው ለዘመናት የኖሩ ወይም ለፖለቲካና ለልዩ ልዩ ጥቅም ሲባል እንዳይነኩ የሚፈለጉ ነባር አውዶችንና አመለካከቶችን ሊነካ የሚችል በመሆኑ ከተለምዷዊ አውዱ ጋር ፊት ለፊት መገናኘትን ወይም መጋጨትን፣ ለዘመናት የቆዩ ቁስሎችን መነካካትን ይጠይቃል። ይህም ከልዩነት ይልቅ የሚያግባቡ ጉዳዮችን ሊያጠናክር ወይም ልዩነቶቹ ይበልጥ እንዲከሩና አለመግባባቱ ጎልቶ እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል። ይሁን እንጂ ሀገራዊ ምክክሮች ሰፊ መሰረት ያላቸውና አሳታፊ ሂደቶች በመሆናቸው ለበለጠ የትብብር ተሳትፎ እና መከባበር መሠረት የመጣል ሰፊ ዕድልና አቅም አላቸው። ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ወደ አካታች ሀገራዊ ምክክር ገብታለች።
ኢትዮጵያ እየመከረች ነው ሲባል. . .
በመግቢያችን ላይ እንደጠቀስነውና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳነሱት ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገሩ ቁርሾና የታሪክ ስብራቶችን የተሸከመች፤ ትውልዷም የውርስ ባለዕዳ ነው። ስብራቱን ለመጠገን እና ትውልድ ካለፈው የወረሰውን ዕዳ ለማቃለል ሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ ትገኛለች። መነሻውም
ከግጭት አዙሪትና አለመግባባት በመላቀቅ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ብሔራዊ መግባባት የተፈጠረባት ሠላማዊት ሀገር መገንባት ነው። ይህንን ስራ በገለልተኛነት እንዲያሳልጥም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ዓ.ም ተቋቁሞ በ11 ኮሚሽነሮች እንዲመራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደስራ ገብቷል። በአዋጁ መግቢያ “በሀገራችን በተለይም በፖለቲካ ልሂቃን መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተፈጠረና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ልዩነት መፍታት ለሀገራዊ አንድነት መሰረታዊ ነገር ነው። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ብቻ የተፈጠሩ ሳይሆኑ በሽግግር ላይ በነበሩ በርካታ ሀገራት ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ፈተናዎችን አልፈው ስኬታማ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ያደረጉ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው፤ አካታች ሀገራዊ ምክክሮችን ማድረግ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሻለ መግባባት እንዲኖር እና በሂደትም የመተማመን እና በወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ባሕልን ለማጎልበት ጠቃሚ እንደሆነ ያረጋግጣል” የሚል ጠንካራ ብያኔ ተቀምጧል።
አዋጁ አክሎም ሀገራዊ ምክክሩ “በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል እንዲሁም በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመን የሰፈነበት አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት ለመፍጠር፣ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በውይይት መፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባሕል ለማዳበር እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል ለመፍጠር፤ ወቅታዊ ችግሮች ዘላቂነት ባለው መንገድ ተፈትተው አስተማማኝ ሠላም የሚረጋገጥበትን የፖለቲካ እና ማኅበራዊ መደላድል ለማመቻቸት እንዲሁም ለሀገራዊ መግባባት እና ጠንካራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት“ የሚከናወን ሂደት መሆንኑን በግልጽ አመላክቷል።
የሀገራዊ ምክክር ከአዋጅ ቁጥር 1265/2014 አንፃር
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 አካታች ሀገራዊ ምክክርን፣ ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታን ታሳቢ በማድረግ ተመራጭ ግጭት መፍቻ ዘዴ መሆኑን ደንግጓል። ሀገራዊ ምክክር አንድ ወገን ብቻ የሚመክርበት ሳይሆን የተለያዩ ሃሳቦች፣ ጥቅሞች፣ ፍላጎቶችና መብቶች የሚወከሉበትና ምክክር የሚደረግበት ሂደት እንደሆነም ያብራራል። የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚወከሉበት የብዝኅነት መድረክ በመሆኑ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችንና ልዩነቶችን ወደ ሠለጠነ የጠረጴዛ ምክክር በማምጣት የጋራ መፍትሔ ለማምጣት የተመረጠና ጥቅም ላይ እንዲውል የተሰናዳ ሂደት እንደሆነም ተመላክቷል።
ሀገራዊ ምክክር በዋናነት ግጭትን ለማስወገድ (Peace Building)፣ የፖለቲካና ዴሞክራሲ ሽግግርን ለማሳለጥ አይነተኛ ጠቀሜታ አለው። በተለይ ግጭትን ለመከላከል፣ ለማስተዳደር (Conflict Management) እና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ሁነኛ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፡ ፡ ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ምክክር ሁሉንም አሸናፊ ያደርጋል” ያሉት። ለዚህም በሀገራዊ ምክክር የትኛውም ኢትዮጵያዊ ይሳተፋል፤ የትኛውም ዓይነት ሃሳብ ይስተናገዳል። የምክክሩ ሂደትም አካታችና አሳታፊ ነው።
የሀገራዊ ምክክር አካታችነት እና አሳታፊነት
አንድ ሀገራዊ ምክክር አሳታፊና አካታች ነው ለመባል ስምምነት የተደረሰባቸው አሃዛዊ መግባባቶች ወይም ወሰኖች እንደሌሉት መረጃዎች ያሳያሉ። ይሁንና ምክክር እንደሚደረግባቸው አጀንዳዎች ስፋትና ጥልቀት የተሳታፊ ብዛትና ተካታችነት ውስን፣ መካከለኛ ወይም ብዛት ያለው ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
የሀገራዊ ምክክር ሂደት አስፈላጊ የሆነበትን ውጤት ለማስገኘት የአሳታፊና የአካታችንትን ሚዛን የመጠበቅ እና ወሳኝ አጀንዳዎች ተገቢ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ትኩረት እንዲያገኙ የማድረግ መሠረታዊ መስፈርቶች አሉት። አካታች ሆኖ የማያሳትፍ፣ ወይም አሳታፊ ሆኖ አካታች ያልሆነ ወይም መሰረታዊ አጀንዳዎችን በጥልቀት ወደ ምክክር መድረኩ የማያመጣ ወይም የሃሳብ ልዩነት ያላቸውን ወገኖች ፊት ለፊት የማያገናኝ ሀገራዊ ምክክር በስኬት የመቋጨት ዕድሉ ጠባብ ነው።
ሀገራዊ ምክክር በምን ያህል መጠን አካታችና አሳታፊ ይሁን ወይም የትኞቹ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ይደረግ የሚሉ ጉዳዮችን ለመወሰን የቀደመ ተሞክሮ ያላቸው ሀገራት የተለያዩ አካሄዶችን ተከትለዋል፡፡ አንዳንዶቹ የምክክር ሂደቱን ለመምራትና ለማከናወን ባወጧቸው አዋጆችና ሕጎች በግልጽ አስቀምጠው ለመተግበር ሞክረዋል። አንዳንዶቹ ደግሞ የመወሰን መብቱን ሀገራዊ ምክክሩን እንዲመራ ለሰየሙት ተቋም ወይም አካል ሰጥተው የሂደቱ አንድ አካል እንዲሆን ማድረጋቸውን የታሪክ ማኅደራቸው ያስረዳል።
ኢትዮጵያ የምክክር ሂደቱን በበላይነት እንዲመራ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥልጣንና ኃላፊነት ሰጥታለች። ኃለፊነት የተሰጠው ኮሚሽንም በተቀመጡ መሠረታዊ ዓላማና መርሆዎች ላይ ተመርኩዞ ይሰራል። ይህ መሆኑም ኮሚሽኑ በአጠረ ጊዜ እንዲያከናውናቸው ከሚጠበቁ ተግባራትና ኃላፊነቶች አኳያ በምክክር ሂደቱ ስፋትና ባሕሪይ ላይ ጫና ይፈጥራል። ሆኖም በተለያየ ደረጃ ሰፊ ሕዝብ በማሳተፍ የምክክር አጀንዳዎች እንዲሰጥና በስፋት የሚመከርበትን ዕድል በመፍጠር ሰፊ መሰረትና ዘመን ተሻጋሪ ውጤት ያስገኛል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን በማጥበብ መግባባትን ለመፍጠር፣ በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከልና ከመንግሥት ጋር ያለን ግንኙነት ለማሻሻል፣ መተማመንን ለማጎልበት፣ የመነጋገር የፖለቲካ ባሕልን ለማጎልበት፣ ዘላቂ ሠላም ለማምጣት፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ መንግሥት በጋራ ለመገንባት፣ ልዩነቶችን በሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ ለመፍታት፣ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ሽግግር (Transforma- tion) ለማስቻል፣ ልማትን ለማፋጠን የሚሉ ተጠቃሽ ዓላማዎችን ሰንቋል።
በተጨማሪም በሚለዩ መሰረታዊ አለመግባባቶች፣ ልዩነትና የግጭት ምክንያቶችን (Root cause) በሠለጠነ መንገድ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ እና የግጭት መንስኤ ልዩነትን ለማጥበብ በዴሞክራሲያዊ፣ ሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ መፍታት የሚቻልበትን ዘዴ በጋራ በመቀየስ ተግባራዊ ለማድረግ ለመግባባት የጋራ ጥረት የሚደረግበትን መድረክ ለማመቻቸት አልሟል።
በሀገራዊ ምክክር ሂደቱም አካታችነት፣ ግልፅነት፣ ተዓማኒነት፣ መቻቻል፣ መከባበር፣ ምክንያታዊነት፣ የምክረ ሃሳቦች ተግባራዊነት፣ አውድ ተኮርነት፣ ገለልተኛ አመቻች፣ የአጀንዳ ጥልቀትና አግባብነት፣ ዴሞክሲያዊነት እና የሕግ የበላይነት በአዋጁ የተቀመጡ ዓለማዎችን ለማሳካት የተጠቀሱ መርሆች ናቸው። በተጨማሪም ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ የሚሳተፉ ዜጎች በቅን ልቦና መሳተፍ የሚያስችላቸውን ፍትሃዊ መርሆን ሊያካትት እንደሚችል ሥልጣን ተሰጥቶታል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የእስካሁን ሥራዎች በወፍ በረር
ኮሚሽኑ ከ2014 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት፣ የዝግጅት፣ የምክክር እና የትግበራና ክትትል በሚል ሥራዎችን በአራት ምዕራፎች ከፍሎ እያከናወነ ይገኛል። በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ለሥራዎቹ አመቺነትም በሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ከተባባሪና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ነው ሥራውን የጀመረው። በዝግጅት ምዕራፍ የአሰራር ሰነዶችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተባባሪ አካላት ሥልጠናዎች፣ በአጀንዳ ልየታ የሚሳተፉ የኅብረተሰብ ተወካዮች መረጣን ሲከውን ቆይቷል። ይህንን ሥራውን ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች በስተቀር በሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች አጠናቅቆ አሁን የምክክር ምዕራፍ አካል ወደ ሆነው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ ምዕራፍ ገብቷል። በቅርቡ በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት አካሂዷል። በዚሁ ጊዜ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ሳይበገር መቀራረብ እና መግባባትን ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
እንደ ዋና ኮሚሽነሩ ገለጻ ከተሳታፊነት አንፃር እስከ አሁን በ10 ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ከአንድ ሺህ በሚልቁ ወረዳዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ የሚሳተፉ ተወካዮች ተመርጠዋል። ፕሮፌሰር መፍስን በዚሁ ጊዜ፤ ″ከስብራት ሕይወት በመውጣት ወደ ተሻለ ሕይወት ለመሸጋገር ወጣቱ ችግሩን በአጀንዳ ቀረፃ፤ ጠብመንጃውን ወደ ሐሳብ መንጃና ማንሸራሸሪያ መቀየር ይጠበቅበታል″ ሲሉ ጠይቀዋል። በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አጀንዳውን በግልም ሆነ በጋራ ማቅረብ ይችላል። ምክክሩ አካታች፤ ሂደቱም ግልፅና ተዓማኒ በሆነ መልኩ የሚከናወን መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በምክክር ኮሚሽኑ በተቀመጠው መርህ መሰረት አካታችነት ግንባር ቀደም ነው። አካታችነት ከሕግ ዝግጅት እስከ ኮሚሽነሮች ምርጫ ድረስ የአካታችነት ተሳትፎን ለማረጋገጥ ጥረት የተደረገበት እንደሆነም ይታወቃል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ብሔራዊ የምክክር ሂደቶች የተቀመረና ወጥ የሆነ አካሄድ እንደሌለ ልብ ይሏል። ከዚህ ይልቅ ሕዝባዊ ተቀባይነት፣ የመንግሥት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት፣ አካታችነት፣ አሳታፊነት፣ ግልጽነት፣ ተዓማኒነት፣ ገለልተኝነት እና ተግባራዊነት የምክክር ሂደትን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ዋና ዋና መሠረታዊ መርሆች መሆናቸው ይታመናል። ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን በስኬት ለመቋጨትም የሚከተሉትን ዋና ዋና የምክክር ሂደት መርሆች መከተል አስፈላጊ ይሆናል።
የምክክር ሂደቱ መሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማካተት ሃሳብና ጥቅሞችን የሚወክሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲሳተፉበት እየተደረገ ይገኛል። በአዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ የኀብረተሰብ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሦስቱ የመንግሥት አካላት (ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ)፣ የተቋማትና የማኅበራት ተወካዮች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳትፈውበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በጦርነት እያለፈች እና በርካታ ስብራቶች እየገጠሟት ያለች ሀገር ነች በማለት ከዚህ የጦርነት እና የስብራት ታሪክ ለመውጣት ምክክር ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን አስምረውበታል። ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ በሆነው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ኢትዮጵያዊያን በንቃት በመሳተፍ ከተቃርኖ ይልቅ ተዛምዶን በማጠናከርና መጓደልን በመሙላት ኢትዮጵያን ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትና ተስፋ ያላት ሀገር ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል። ከዚህ አኳያ በጫካ የሚገኙና ነፍጥ ያነሱ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳዎቻቸውን በሠላማዊ መንገድ በምክክሩ በማቅረብ ለጋራ ሀገር የጋራ መፍትሔ ለማበጀት እንዲቀርቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ሀገራዊ ምክክርን በስኬት መከወኛ መንገዶች
በኢትዮጵያ በሂደት ላይ የሚገኘው ሀገራዊ ምክክር በአራት የቅድመ ዝግጅት (Initiation)፣ የዝግጅት (Preparation)፣ የምክክር ሂደት (Di- alog Process) እና የትግበራና ክትትል (Im- plementation & Follow Up) ምዕራፎችን ለማለፍ እየሰራ ይገኛል። ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ ከመገባቱ በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አከናውኗል፡ ፡ በዝግጅት ምዕራፍም የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶቸ በገለልተኝነትና በነፃነት ማከናወኑን አሳውቋል።
የምክክር አጀንዳዎችን፣ አወያይና ተወያይ አመራረጥን፣ የምክክር ሥነ-ስርዓትን እና መሰል ጉዳዮችን በነፃነትና በገለልተኝነት አከናውኗል። በሶስተኛው የምክክር ሂደት ምዕራፍም ሀገራዊ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትን ያስጀመረ ሲሆን በአዲስ አበባ አጀንዳ የመለየቱ ሥራ ተጠናቋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዓላማና መርህን በስኬት ለመቋጨት የመንግሥት አካላት፣ ማኅበራዊና የግል አደረጃጀቶች፣ የዜጎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠበቃል።
ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት መሰረታዊ ጉዳዮች
በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ብሔራዊ የምክክር ሂደቶች የተቀመረና ወጥ የሆነ አካሄድ እንደሌለ ልብ ይሏል። ከዚህ ይልቅ ሕዝባዊ ተቀባይነት፣ የመንግሥት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት፣ አካታችነት፣ አሳታፊነት፣ ግልጽነት፣ ተዓማኒነት፣ ገለልተኝነት እና ተግባራዊነት የምክክር ሂደትን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ዋና ዋና መሠረታዊ መርሆች መሆናቸው ይታመናል። ሀገራዊ የምክክር ሂደቱን በስኬት ለመቋጨትም የሚከተሉትን ዋና ዋና የምክክር ሂደት መርሆች መከተል አስፈላጊ ይሆናል።
ሕዝባዊ ተቀባይነት፡- የምክክሩ አስፈላጊነትና የውጤቱ ተጠባቂነት በአብዛኛው ኅብረተሰብ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል።
የመንግሥት ቁርጠኝነት፡- መንግሥት በቅድሚያ መግባባት ሊፈጠርባቸው የሚገቡ ልዩነቶች መኖራቸውን ከመቀበል ጀምሮ ልዩነቶችን በምክክር መፍታት እንዲቻል የፖለቲካ ተነሳሽነቱን መውሰድ ይጠበቅበታል። ለሂደቱ መሳካትና ለምክረ ሃሳቦቹ ተፈፃሚነት ከፍተኛና የማያቋርጥ ድጋፍ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ መያዝ ይኖርበታል።
አካታችነት፡- የተለያየ አመለካከት፤ ፆታ፣ የዕድሜ ክልል፣ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ያላቸውን ሰዎች በበቂ መጠን ማሳተፍ ያስፈልጋል። ይህም የምክክር ሂደትን በፍትሃዊነትና በዕኩልነት የመመልከት መርህ ተደርጎ እንዲወሰድ ያስችላል። አካታችነት በሁሉም የምክክር ሂደቶችና ተግባራት ላይ ሊንጸባረቅ የሚገባው ወሳኝ መርህ ተደርጎም ይወሰዳል።
አሳታፊነት፡- የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች (Constituencies) በንቃትና ገንቢ ሁኔታ የሚሳተፉበት የምክክር ሂደት የመርህ አይነት ነው። አሳታፊነት የምክክር ምንነት፣ ፋይዳና ሂደትን ማስገንዘብ የሚችል አቅም በመገንባት ትርጉም ያለው ተሳትፎን የሚያረጋገጥ የምክክር ሂደት ቁልፍ ጉዳይ ተደርጎ መታየት አለበት።
ግልጽነት፡- በምክክር ሂደት የተግባራት ክዋኔና ሁኔታ ግልጽና በቀላሉ ግንዛቤን መፍጠር የሚችል መርህ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሰራር በማዘጋጀት፣ በመተግበር እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ግልጽነት መፍጠር ወሳኝነት ይኖረዋል።
ተዓማኒነት፡- በምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎችና ፈፃሚዎች እንዲሁም በኀብረተሰቡ ዘንድ አመኔታና ተቀባይነት የማግኘት መርህ አይነት ነው። በሀገራዊ ምክክር ሂደትና ውጤት ላይ የተለያዩ አካላት ፍላጎት ጎልቶ የሚንጸባረቅበትና
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
በጥርጣሬዎች የታጀበ በመሆኑ ተዓማኒነትን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠይቃል።
ገለልተኝነት፡- ለየትኛውም ሃሳብ፣ አመለካከት ወይም አቋም የተለየ ድጋፍና እገዛ አለማድረግና ያለማንጸባርቅ ሁኔታ የማሳየት ኃላፊነት ነው። በተለይም የምክክር ሂደቱን የሚመሩ አካላት ገለልተኝነት መሰረታዊ ጉዳይ ይሆናል። በሂደቱም ሰዎችን ከመምረጥ ጀምሮ የአሰራር መመሪያና የሥነ-ምግባር ደንብ ዝግጅቶችን በጥብቅ ክትትል መፈጸም ያስፈልጋል።
ተግባራዊነት፡- በምክክር ሂደቱ መግባባቶች የተደረሰባቸው ጉዳዮች የሚፈጸሙበት የመርህ አይነት ነው፡፡ ተግባራዊነትም በሀገራዊ ምክክር ሂደት ትልቅ የሽግግር ፍኖተ ካርታ አካል ተደርጎ ይታያል። በኢኮኖሚ፣ በመዋቅር፣ በፖለቲካ እና በፍትሕ ማሻሻያ ሂደቶች መታጀብም ይኖርበታል።
ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክር መርሆዎች አካታችነት፣ ግልፅነት፣ ተዓማኒነት፣ መቻቻል እና መከባበር፣ ምክንያታዊነት፣ የምክረ ሃሳቦች ተግባራዊነት እና አውድ ተኮርነት፣ ገለልተኛ አመቻችነት፣ የአጀንዳዎች ጥልቀት እና አግባብነት፣ ዴሞክራሲ እና የሕግ የበላይነት፣ ብሔራዊ ጥቅም እና ሀገራዊ ባሕላዊ እውቀቶችንና እሴቶችን መጠቀም የሚሉትን መርሆች በመሰነቅ እየሰራ ይገኛል።
ለዚህም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው “ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉ አጽንኦት የሰጡት። በመድረኩ የተገኙት የሴቶች ድምጽ ተወካይ ኛቦር ባንዳክ በበኩላቸው፤ በግልጽነት ተነጋግረን መነጣጠልን፣ ጥላቻንና ሞትን በይቅርታ በመሻር በጋራ አገራችንን ከፍ እናድርጋት ያሉትም የምክክርን የግልፅነት አካሄድ ወሳኝነት ቁልጭ አድርጎ ያመላክታል።
በኢትዮጵያ ያለውን የግጭት፣ የልዩነት አዙሪት በመፍታት ጠንካራና አንድነቷ የተጠበቀ ለአፍሪካ በሁሉም በጎ ነገር ሁሉ ምሣሌ የምትሆን ሀገር መገንባት ይገባል። ከዚህ አኳያ የአሁኑ ትውልድ ጠንካራ ሀገር የመፍጠር ዕድል አግኝቷል፤ ይኸውም በማያግባቡ ጉዳዮች ላይ ቁጭ ብሎ በመመካከር ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠር ዕድል ነው። በመሆኑም ይህ ዕድል እንዳያመልጠን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን በማገዝ ለስኬቱ መትጋት ይገባል። ከአብዮቱ በፊት የነበሩ ነገሥታት ብዙ መልካም ዕድሎች አምልጠዋቸዋል፤ የ1966ቱ ትውልድም በርዕዮተ ዓለም ልዩነት ሲላጋ መዳፉ ላይ ያለውን ዕድል ነፋስ ነጥቆታል። የ1983ቱ ትውልድም ብዙ ዕድሎችን አባክኗል፤ አሁን ያለው ትውልድ ወሳኝ ዕድል እንዳያመልጠው ቆም ብሎ ማሰብ አለበት፤ ይህን አጋጣሚ በአግባቡ መጠቀም ካልተቻለ ጉዳቱ አንድ ወገን ላይ ብቻ ሳይሆን ጥቅል ሀገራዊ ጉዳት ነው የሚያደርሰው።
እዚህ ጋ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ “ትችት ብቻ ሀገር አይቀይርም፣ መወቃቀስ ብቻ ሀገር አይቀይርም፤ መወነጃጀል ብቻ ሀገር አይቀይርም፤ መጠፋፋት ሀገር አይቀይርም፤ እነዚህ ሀገር የሚቀይሩ ቢሆኑ ኖሮ እኛ ዛሬ ከበለጸጉ ሀገራት ተርታ ከፊት እንሆን ነበር፤ አሁን ዕድል ተፈጥሯል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራዊ ምክክር እናድርግ ብለን ወደ ሥራ ገብተናል” ያሉትን ሃሳብ ማንሳት ወደናል።
ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መንግሥት የማያሻማና ግልፅ አቋም ይዟል፤ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ ለዘመናት ያጋጠሟትን ችግሮች በተለይም ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት የሚፈጥር ምህዳር በገለልተኝነትና በነጻነት እንዲያመቻች ምልዑ ሥልጣን ተሰጥቶታል። አሁን አጀንዳ ወደማሰባሰብ ወሳኝ ምዕራፍ ገብቷል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነፍጥ አንግበው የፖለቲካ ጥያቄዎቻቸውን በኃይል ለማስመለስ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ቡድኖች በሠላማዊ መንገድ በምክክሩ እንዲሳተፉ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቧል። የመንግሥት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ እንደሚሉትም መንግሥት ከታጠቁ አካላት ጋር ችግሮችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነቱን በተዳጋገሚ አሳይቷል፤ የሰሜኑ ጦርነትም የተፈታው በሠላማዊ አማራጭ ነው፤ አሁንም የትኛውም አጀንዳ ያላቸው የታጠቁ ቡድኖች ጥያቄያቸውን በሠላማዊ መንገድ ወደ ጠረጴዛ አምጥተው ለውይይት ሊቀርቡ ይገባቸዋል። መንግሥት ለሠላማዊ ውይይት ሁልጊዜም በሩ ክፍት ነው። ከዚህ አኳያ ምክክሩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በገባበት በዚህ ወሳኝ ጊዜ የተፈጠረው ዕድል እንዳይከሽፍ ከሁሉም ወገን በጎ ሚና ይጠበቃል።
ከከተማ እስከ ገጠር ያለው መላው ሕዝብ፣ መንግሥት፣ ገዥው ፓርቲ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ ምሁራን፣ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ እና የትኛውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህ ዕድል እንዳያልፍ ማድረግ ይጠበቅበታል። ምክንያቱም ትናንት ብዙ ዕድሎች አጋጥመው የነበረ ቢሆንም በእልህ፣ በብሽሽቅ፣ በመጠፋፋት ፖለቲካ ከሽፈዋል። ዛሬም የተፈጠረውን ዕድል ሊያደናቅፉ የሚችሉ ስጋቶች አሉ፤ አንደኛው ፅንፈኝነት ነው፤ ይህ የመጓተት ፖለቲካ ሀገርን ወደኋላ የሚስብ በመሆኑ በመደማመጥ፣ በመነጋገር፣ ከራስ ፍላጎት የጋራና የሀገርን ጉዳይ በማስቀደም፣ ከጊዜያዊ ይልቅ የወደፊቱን አሻግሮ ማየት ላይ ማተኮር ያስፈልጋል። ለዚህም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ቁጭ ብሎ ለመነጋገር የተፈጠረውን ሀገራዊ ምክክር በአግባቡ መጠቀምና ለስኬቱ መትጋት ወሳኝ ነው።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ “ሀገራዊ ምክክር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ እና ደግሞ የማይገኝ ዕድል በመሆኑ ገለልተኛነቱን ጠብቆ አካታች የሆነ ምክክር እንዲካሄድ በአግባቡ ማገዝና በባለቤትነት በመስራት ዕድሉን መጠቀም ያስፈልጋል” ያሉትን ለአጽንኦት አንስተናል።
ትናንት የመጣንበት ኋላቀር የፖለቲካ ባሕል አያዋጣንም፤ በመሆኑም የሠለጠነ የፖለቲካ ሥርዓት ለመገንባት መገዳደልን ማቆም በሰጥቶ መቀበል መርህ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ሂደት ውስጥ መግባት አለብን፤ ለኢትዮጵያዊያን ፍቱን መድኃኒት ይህ ነው።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ መንግሥት ከሚያደርግላቸው ማበረታቻና ክትትል ውጭ ሥራቸውን ያለ አንዳች ጣልቃ ገብነት በገለልተኝነት እየመሩ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት፤ በመሆኑም ወጣቶች በዘመናዊና በሠለጠነ መንገድ ከግጭት ነጻ ሆነው የፖለቲካ ባሕልን በመቀየር፣ ለሁሉም የምትመች ሀገር እንድትሆን ጉልህ ሚና ይጠበቅባቸዋል። የወጣቶች ድምጽ ናትናኤል ባሕሩ የዚህ ዘመን ትውልድ በእጁ ላይ ያለውን አንድ ዕድል በመጠቀም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በምክክር መፍትሔ በመስጠት “የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና” የሚለውን አባባል እውን እናድርግ ሲል ያስተላለፈው መልዕክት የጽሑፋችን መደምደሚያ ይሁን።
"ሀገራዊ ምክክር፤ ለሀገራዊ መግባባት"
Politics
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
Peace Building: Bedrock for Ethiopia’s Bright Future
By Getnet Shenkute
Peaceful resolution of the conflict that flared up in the northern part of the country is one of the unique features of the body politics in Ethiopia. Evidently, Ethiopian history is a history of war. Even though this ancient African country has a renowned history in repulsing back the aggression from foreign powers, in the course of her history, Ethiopia has rarely succeeded in ending internal conflicts through negotiations. That is the reason why the AU brokered Pretoria peace deal would be considered as successful breakthrough.
Need for Concrete Moves
From the outset, the government of Ethiopia under the leadership of Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) utterly opposed any attempts to plunge the country into undesirable and unfortunate conflict. The federal government had even pleaded for peace by sending a group of elders to Tigray region in its effort to prevent the conflict. However, the conflict
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
erupted following the attack against the Northern Command of the Ethiopian National Defense Force (ENDF) based in Tigray at midnight of 4th November 2020.
Beyond the internal conflict, the East African nation became under immense unjustified pressure from some corners of the world. The pressures attempted to infringe on Ethiopia’s sovereignty by imposing draconian sanctions. However, the government and people of Ethiopia fended off the unwarranted foreign pressure through various means. They were even able to end the conflict peacefully through their own means with the support from the African Union. This is a manifestation of Ethiopia`s firm belief in “African solutions to Africa`s problems.”
On the 2nd of November 2022, the Federal Government of Ethiopia and the TPLF signed a Cessation of Hostilities Agreement in South Africa also known as the Pretoria Agreement. The announcement of this peace deal was certainly a surprise to the global community. The international community hailed it as a chance to secure peace after a devastating war of two years. Most notably, the deal has reaffirmed Ethiopia’s shift in its contemporary history to end such internal conflicts through dialogue. Many described the Pretoria Peace Agreement as a monumental step in moving Ethiopia forward on the path to a far-reaching reform initiated six years ago.
The federal government has been reiterating its determination not to waste a single day for ensuring a sustainable peace for the people of Tigray and Ethiopia in general. The government is pragmatic and firmly believes that full implementation of the Pretoria Agreement is the foundation to lasting solutions to sustainably resolving the problem in northern Ethiopia. This is why the federal government commenced implementing the deal almost right the next day following the signing of the agreement.
There are numerous instances in which the Government of Ethiopia has shown its unwavering commitment to the implementation of the agreement through bold and decisive measures it took to build trust in the negotiation process. The government has taken several constructive measures in this regard including toning down hostile political rhetoric during the execution of the peace deal process. After the immediate silencing of guns in the region, the federal government has halted any military operation, rehabilitated all essential public infrastructures and social services, and ensured unfettered humanitarian supplies by facilitating ways to open all humanitarian corridors. The government has been the major actor in supplying the necessary humanitarian aid to its people in Tigray.
The humanitarian access has
continued unabated along with the rehabilitation programs on social and infrastructural facilities heavily damaged and destroyed in the advent of the war. The government is also delivering on its commitment by restoring services, repairing damages made on major electricity substations connecting the Tigray region with the national grid. In fact, the swift measures taken by the federal government has tendentiously helped the people of Tigray getting out of a looming crisis as a result of war.
Right after the signing of the agreement, the Federal government dispatched a high-level delegation to Tigray region that included leadership of various institutions led by the Speaker of the House of People’s Representatives, Tagesse Chafo. On the occasion, federal institutions and all regions of the country immediately showed their unreserved and practical support for the people of Tigray. Moreover, regional chief administrators were present in the regional capital Mekele to demonstrate their solidarity with the people of Tigray and provided their support in kind and financial donations.
To provide basic services to the people of Tigray, officials in charge of banking, telecom, road, health,
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
education and aid were present in Tigray and discussed with the officials of the region. The federal government expended more than 37 billion Birr towards the rehabilitation and restoration of social and infrastructural facilities until the end of March 2024.
Based on the Pretoria Agreement, the House of Peoples’ Representatives has delisted TPLF from the list of terrorist organizations. The federal government also gave more opportunities that allowed the TPLF and armed leaders to establish the interim administration. In this way, the government has gone an extra mile to deliver on its responsibility to end the suffering of the people of Tigray and to ensure a durable peace in the region.
The other unparalleled response from the federal government is the endeavors to relocate the displaced and reinstate their normal lives in partnership with pertinent local and international actors. In some areas displaced persons have already returned to their homes. Furthermore, a consensus was reached among the federal government, the Amhara and Tigray regional states in order to sustainably resolve the issues related to disputed administrative borders through a referendum in accordance with the constitution.
Over the past two years the federal government has gone above and beyond what is required of it in the process of the implementation of the Pretoria Agreement for the sake of peace, development and security that eventually the people in Tigray region and Ethiopians in general would enjoy. As a result of the peace deal and the unwavering commitment of the federal government, the people of the region have been witnessing concrete changes and enjoying peace.
The people of Tigray now live in peace and lead regular lives thanks to the federal government’s various initiatives carried out in accordance with the Pretoria peace deal. Everything Tigray is back to normal because of the peace agreement. For the benefit of the local population, a number of development initiatives are now in progress. The federal government still believes that there is no other alternative than focusing on actionable measures that could help the Pretoria agreement fully implemented so as to ensure sustainable peace and development in the region and beyond.
Persistent Challenges
Despite all these constructive moves by the federal government, the writer believes that the TPLF has not been fully delivering on its responsibility and taking decisive actions on the major binding provisions of the peace deal. In fact, it seems, there are elements within the TPLF that are not remorseful about their misadventure but who rather enjoy cascading misery to the people of Tigray.
With all honesty, the agreement should be taken as an important step in efforts to silence the guns and provide a solid foundation for the preservation of Ethiopia’s sovereignty and territorial integrity. This was duly provided in the articles of the Agreement in terms of the immediate cessation of hostilities, the resumption of unhindered humanitarian access, the restoration
of services as well as healing wounds from the war and prevalence of reconciliation. However, the other side of the signing party has to meet its obligations including full disarmament.
It is to be noted that disarming ex-combatants is a key part of the agreement signed two years ago. For instance, the deal underlined that the disarmament of heavy weapons of the TPLF forces would take place immediately and should be completed within 30 days of the signing of the deal. Yet, TPLF has remained reluctance to uphold its commitments.
Even though TPLF handed over some light weapons initially, the group has stalled on the withdrawal of its heavy artillery and armored vehicles as required by the peace deal. This undermines the spirit and letter of the Pretoria Agreement and clearly contradicts the constitution of Ethiopia. The Pretoria peace accord further provide that the signing parties have agreed and recognize that the Federal Democratic Republic of Ethiopia has only one defense force.
Thus, the successful undertaking of Disarmament, Demobilization, and Reintegration is a key element of the Pretoria Peace Agreement that should be fully and urgently implemented in order to sustain the peace which is seriously needed by the people of Tigray. The people in Tigray are very much fade-up of sacrificing their children for no reason and engulfed by an unimaginable suffering. The people of Tigray have been demonstrating its detest to wat in various ways.
The peace agreement strongly demands constructive engagement among the signing parties through dialogue and reconciliation which is instrumental for addressing the political differences. This is a pivotal approach to Ethiopia to heal the country’s deep political divisions and a move towards lasting peace.
However, there are some elements that are engaged in obstructing the above mentioned central guiding principle of the peace agreement. These elements have still been pursuing antagonized rhetoric against the government in particular that would obstruct the endeavors for lasting peace. Despite this, the government has been trying to tame such ill attempts through peaceful mechanisms.
Thus, Ethiopia’s partners and international actors should encourage the efforts of the government to realize sustainable peace and stability in Ethiopia while trying to pressure the other side to abide by the principles of the agreement and discharge its responsibilities.
Bold Actions to Tackle Centuries Old Predicaments
Due to the country’s political culture, which is shaped by the barrel of the gun not the ballot box, Ethiopia experienced deep seated resentments and distrust perpetuated over the past several decades. One of the major problems in the contemporary political history of Ethiopia is the country has repeatedly missed golden opportunities for democratic transition. Historically, the country witnessed various political revolutions and struggles since the early 19th. Unfortunately, almost all attempts have not yet borne fruit to bring about democratic political orders.
Now Ethiopia has embarked on another golden opportunity with a far-reaching political reform. Since it has come to power in 2018, the new government is trying to defuse a winner-takes-all-approach of political practice by the Ethiopian elites rather than a negotiated transition based on elite bargains and win-win principled approaches. Regrettably, we have not yet learnt from the ordeals of our history. Even the ongoing political reform is facing the same challenges as an extension of authoritarian political elites who have continued to impose their will by having complete control over everything available to them.
The other challenge in recent times is ethnic polarization in Ethiopian body politic. I believe the ethnic based and divisive political discourse has to end somewhere to resolve the inherent problem in Ethiopian politics. The extreme focus on ethnic cleavages and ethnicized politics is yielding us nothing but ethnic-out bidders and their self-servicing approaches. In the case of our country we are all citizens of the state of Ethiopia. We have to discuss and debate the best policy for future generations of our great nation rather than keeping the ongoing contradictions based on ethnic bloodlines. This does not mean to say that we shall undermine the cultures, languages and values of our ethnic groups across the country. We shall cherish our diversity and utilize it to cement our bond and unity. We shall believe that we are many in languages and one as a nation.
Amidst of all the challenges, the
current government has decided to take bold actions to amend centuries old predicaments Ethiopians are facing. The House of Peoples Representative had approved a proclamation to establish a National Dialogue Commission to rectify age old problems, misgivings, mistrusts and grievances, unhealed wounds injustices through a nationwide inclusive, participatory, free and democratic dialogue. This has been hailed by all Ethiopians and international partners.
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
Dialogue in Action
Ethiopia has now embarked on the actual task of the long awaited national dialogue and reconciliation as the nation seeks to put an end to historical and contemporary contradictions in this ancient African country. At the end of last month, Ethiopia officially started the first- ever phase of national dialogue by conducting consultations in the capital Addis Ababa to set critical national agenda that would be discussed at the grand dialogue to be held at national level. The Addis Ababa chapter of the dialogue has been concluded successfully. Similar consultations are expected to be carried out in all regional states in the coming months.
In response to the challenging political situation of Ethiopia, this first-ever inclusive national dialogue involves all segments of the society with a view to resolving centuries old predicaments that the country has been facing to date. The National Dialogue is expected to heal resentments and wounds caused during the heinous acts of former political systems. The government has been intensifying its full support and commitment to the successful conduct of the inclusive dialogue that aims at correcting major fault lines paving the way for creating consensus on basic national issues through the
representatives of the participants of the national dialogue who are expected to voice the concerns and hopes of the people of Ethiopia.
The government has demonstrated the emergence of a new political culture through a national election that showed the desires of the people and formed a government that is based on the will of the people. Moreover, the government has demonstrated that this nation is a common home for the citizenry. To this effect, the government engaged leaders and members of other political parties into the state nomenclature, which is a new political venture in the history of Ethiopia.
Towards rectifying rampant mistakes inherited from the past, the government initiated the establishment of an independent National Dialogue Commission with 11 commissioners who have proven to be scholarly, independent, impartial and enthusiastic to see a peaceful, democratic and prosperous Ethiopia.
The commissioners of the National Dialogue, who are appointed to serve their country, are of high caliber and rich experience. The law has empowered them with extensive power to conduct their duties of coordinating and conducting an inclusive national dialogue. They have now charted out extensive outlines on how the inclusive dialogue should be conducted by consulting with pertinent stakeholders.
Transitional Justice: Viable Solution for Ethiopia’s Unsettled Past
The transitional justice mechanism has become another integral part of Ethiopia’s efforts to address historical human rights violations, ensure accountability, and reform and strengthen democratic institutions in order to lay the groundwork to sustain political stability and consolidate democracy. As many previous practices show, transitional justice is imperative as a tool for conflict resolution in the political landscape of severely divided post-conflict societies like Ethiopia.
As numerous political backlogs of Ethiopia have caused protracted disputes, misunderstandings, and instability, the country should come up with a viable mechanism which could change the nation’s modus operandi on the affairs of democratic system and human rights. Therefore, transitional justice is the only option for Ethiopia at this moment in time to properly confront unaddressed miscarriage of justice in the country over the past decades. .
To this effect, the reformist government of Ethiopia has adopted a Transitional Justice Policy as a viable mechanism to heal the wounds of the victims and avoid resentment which has been the main causes to the instability and underdevelopment of the country. This mechanism has been seen as the best way for Ethiopia to confront its unsettled past and break the cycle of violence through healing past wrongs and overcoming inherited challenges.
In conclusion, one can predict that a bright future is on the horizon for Ethiopia. As long as, these mechanisms and reconciliation platforms availed by the government, it can be used to effectively address age old challenges the country had to grapple with. The East African nation will hopefully lay the foundation for stronger nation- state building process and realize a shared narrative over division and hatred.
The federal government’s decision to support the creation of the aforementioned frameworks is a clear indication of its strong commitment to end the legacy of winners and losers, marred by resentment and hatreds, from passing down to future generations. Ethiopia will certainly proceed to the national reconstruction process. The whole country is going to embark on accelerated economic growth to become an African economic giant. However, it needs to be stressed that all Ethiopians regardless of their ethnic groups should be part of the national consultation project.
ማኅበራዊ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የዜጎች ግልጋሎት ዝማኔ
በአየለ ያረጋል
ቅምሻ…
በአንድ ወቅት አንድ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል “ለመሆኑ መንግሥት በተቀያየረ ቁጥር የሚለዋወጥ ሲቪል ሰርቪስ ይዘን የምንቀጥለው እስከመቼ ይሆን? ሲሉ ላነሱት ቁጭት አዘል ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) “በጣም ትክክለኛና የምጋራው ሃሳብ ነው” ሲሉ ነው ምልከታቸውን እና የመንግሥታቸውን መሻት ያስረዱት። ለመሆኑ ሲቪል ሰርቪሱና አገረ-መንግሥቱ ምንና ምን ናቸው?
ፅንሰ ሃሳባዊ ዳራ
አገረ-መንግሥት በሥርዓት ይበጃል፤ መንግሥትም በተዋቀረበት ምሰሶዎች ይቆማል። በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በሙያቸው ተወዳድረው ለመንግሥት መከታ የሆኑ ባለሙያዎች አሉ። መዝገበ ቃላቱም ሆነ የመስኩ ምሁራን ይህን የመንግሥት ግልጋሎት ሥርዓት ‘ሲቪል ሰርቪስ’ ይሉታል። ‘ሲቪል ሰርቫንት’ የሚለው ቃል ደግሞ “ባለሙያ የመንግሥት ሠራተኛ” ተብሎ ይተረጎማል። የአገልጋይ ሙያተኞች ሲባል “በሙያ ብቃቱና በንጹህ ኅሊናው ለዜጎች መንግሥታዊ አገልግሎቶችን የሚሰጥ በብቃትና ችሎታው ብቻ ተመርጦ የሚቀጠረው ሠራተኛ ነው” ሲሉ ይፈትቱታል።
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ”የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው። ሆኖም ሚኒስትር ዴኤታዎችን፣ ዋና እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን፣ በተመሣሣይ ደረጃና ከዚያ በላይ የሆኑ የመንግሥት ተሿሚዎችን አይጨምርም ይላል። እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን፤ የፍርድ ቤት ዳኞችንና ዐቃቢያነ ሕግን፤ የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወይም በመከላከያና በፖሊስ ደንብ የሚተዳደሩ ሠራተኞችን አያካትትም።
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ፍኖተ ካርታ የዜጎች አገልግሎት (civil Service) እና የሕዝብ አገልግሎት (Public Service) አሰጣጥ ልዩነትና ተደጋጋፊነትን ያወሳል። በዚህም የዜጎች አገልግሎት በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በዜጋ ባለሙያ ሠራተኞች ለዜጎች ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የሕዝብ አገልግሎት ደግሞ በአገሪቱ ለሚኖሩ ሁሉ በዜጋና በውጭ ባለሙያ ሠራተኞች በተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት እንደሆነ ያብራራል። የመንግሥት ዋነኛ ተግባርና ኃላፊነት የዜጎችን ሰብዓዊ ልማት በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ነው።
የመንግሥት አገልግሎት ተቋማዊ ዳራ
ሲቪል ሰርቪስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ አገልግሎት ላይ የዋለው በእንግሊዝ የሕንድ አስተዳደር ነው። ይህም የምስራቅ ሕንድ ኩባንያ ኮሌጅ የድርጅቱን አስተዳዳሪዎች ለመገምገምና ለማሰልጠን ያለመ እንደነበር ታሪክ ይናገራል። የዘመናዊ ሲቪል ሰርቪስ ጅማሮ ደግሞ በ17ኛው፣ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮፓና በአሜሪካ ከነበረው የአገረ-መንግሥትና የብሔረ-መንግሥት ግንባታ ጋር ይያያዛል። አንዳንዶች ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ማቆጥቆጥን ከዘውዳዊ ሥርዓተ መንግሥታት መንኮታኮትና ከብሔረ-መንግሥት ዕድገት ጋር ያቆራኙታል።
የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስረዱት በጥንት ዘመን ሲቪል አገልጋዮች የንጉሣዊያን ቤተሰብ የዘውዳዊ ሥርዓት አገልጋዮች አካል ነበሩ። ዘውዳዊ ሥርዓት ሲከስም በሚኒስትሮችና በሌሎች ባለሥልጣናት መልካም ፈቃድ የሚመረጡ ሰዎች ሆኑ። ይህ አሰራር ከሙስና፣ ከፖለቲካ ጥገኝነትና ከደመወዝ ጋር ተያይዞ በደረሰበት ተቃውሞ በሂደት ቦርድ መቋቋምን ጨምሮ የአሰራር ማሻሻያዎች መደረግ ጀመሩ። በሂደትም ገለልተኛ አሰራር ዘርግተው የሲቪል ሰርቪሱን የሰው ኃይል የሚያስተዳድሩ የሲቨል
ሰርቪስ ኮሚሽኖች በየአገራቱ መቋቋም ቀጠሉ። የሠራተኞች ምልመላ ከትምህርት ሥርዓት ጋር ተጣመረ፤ ምደባው በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በውድድር እንዲሆን ተደረገ።
የዜጎች አገልግሎት (ሲቪል ሰርቪስ) ሥርዓት አስፈላጊነት
የሥነ-መንግሥት ምሁራን ‘መንግሥት’ የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ የአንድ ሕዝብ ደህንነት፣ ግዛታዊ አንድነትና ምጣኔ ሃብታዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሕዝብ፣ ለሕዝብ የተደራጀ ሕጋዊ ሥልጣን ያለው አካል ያደርጉታል። በአጭሩ ‘ሕዝብ ለመምራት በሕዝብ የቆመ ተቋም’ ማለት ነው። እናም ይህ በሕዝብ የቆመ ተቋም የፖለቲካ ስራውን ገቢራዊ ማድረጊያ፣ የግለሰብና የቡድኖች ፍላጎት ማንፀባረቂያ፣ የመብትና ግዴታ መዳኛ ነውና ውስብስብ አሰራሮችን፣ ሂደቶችን፣ ግንኙነቶችንና ተቋማትን ያዘለ ገፀ- ብዙ ሃሳብ የያዘ አስተዳደር ሥርዓት ይዘረጋል።
ሕዝቡ መሠረታዊ ፍላጎቶች አሉት፤ ለፍላጎቱ ስኬት የዜጎች ሰብዓዊ ልማትን ይሻል። ሰብዓዊ ልማት ደግሞ አካላዊና አካባቢያዊ ጤንነትን፣ ዕውቀትን፣ ክህሎትን፣ የእሴቶች እምርታን፣ ቁሳዊና የተፈጥሮ ሀብቱን የማስተዳደርና የመጠቀም እንዲሁም በሰላም፣ በፍትሕና በእኩልነት ተጋግዞ የመኖር አቅምን ማበልፀግን ያካትታል። አልኪሬ የተባሉ የዘርፉ ምሁር የአንድ አገር ሕዝብ ሕልውናም ሆነ የዕድገት ደረጃው የሚለካው ‘የሕዝብ፣ በሕዝብ፣ ለሕዝብ’ የሆነ የዜጎች ሰብዓዊ ልማት ልክ ነው ይላሉ። መንግሥትን ደግሞ ሕዝቡ ፈልጎና ፈቅዶ የሚያደራጀው የሰብዓዊ ልማት መዳረሻ መሳሪያ ያደርጉታል።
የመንግሥት አስተዳደር፤ በማኅበረሰቡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ
እንቅስቃሴዎች ላይ ተመርኩዞ በሚያወጣው ፖሊሲ ማኅበረሰቡን ማገልገልና ሁለንተናዊ ልማቱን ለማረጋገጥ መልካም አስተዳደር ያሻዋል። ዜጎች መንግሥትን በራሳቸው ሥልጣን ሰጥተው የሚሾሙት ሰብዓዊ ልማታቸውን በዘላቂነት እንዲያረጋገጥ ነው።
የአንድ አገር ሥርዓተ መንግሥት ያለ ሲቪል ሰርቪስ ከንቱ ነው። የዘርፉ ምሁራንም ሲቪል ሰርቪስ የሥርዓተ መንግሥቱ ነፀብራቅ ነው ይሉታል። የትኛውም አገር ያለሲቪል ሰርቪስ ዕድገቱን ከፍ ማድረግ አይቻለውም። የመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ገቢራዊ የሚደረጉት ብርቱና ታታሪ ሲቪል ሰርቪስ ሲገነባ ነው። የመንግሥት አገልግሎት ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ለተገልጋዩ ሕዝብ የሚደርሰው በሕግ አስፈጻሚው አካል በኩል ነው።
የሕግ አስፈጻሚው አካል አደረጃጀት እንደየፖለቲካ ሥርዓቱ የሚለያይ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን አቅጣጫ ከወቅታዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ አንጻር የሚወስንና አተገባበሩን የሚከታተል የፖለቲካ ጉዳዮች አስፈጻሚ እና የፖለቲካ አቅጣጫውን ተከትሎ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን በተገቢው የሀብት ግብዓት የሚያሳልጥ የአስተዳደራዊ ሥራዎች አስፈጻሚ ተብለው በሚታወቁ የሥራ ክፍሎች የተዋቀረ ነው። የሥራ ክፍሎቹም የፖለቲካ ሹመኞችን ጨምሮ በበርካታ የሕዝብ አስተዳደር በየደረጃው ያሉትን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞችን የሚያካትት ነው። ሲቪል ሰርቪስ መንግሥት ፖሊሲውን፣ ስትራቴጂውን እና ፕሮግራሙን ለመንደፍ፣ ለማዘጋጀት በአጠቃላይ የስራ ዑደት ለማስቀጠል ብሎም ገቢራዊ የማድረጊያ መሳሪያው ነው። ውጤታማ የመንግሥትን አስተዳደርና ልማት አቅጣጫን ይወስናል።
በአገረ-መንግሥት ግንባታው የሲቪል ሰርቪሱ ሚና የማይተካ ነው። ማዕከላዊ መንግሥት በየደረጃው ባለው አስተዳደር ወጥነት ያለው ሥርዓት ለማንበርና የኃይል ምንጭን ለመቆጣጠር ረድቷል። እያደገ የመጣውም የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያዎች ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን እንደየአገሩ ነባራዊ እውነታ አጣጥሞ ለመቀመር አስችሏል።
ሺያቮ ካምፖ እና ሱንዳራም የተባሉ ምሁራን ስለ ቪሲል ሰርቪስ አስፈላጊነት ሲጠቅሱ ቀዳሚ ፋይዳው መልካም አስተዳደርን ማስፈን ነው። ለዚህ ደግሞ የሰለጠነ፣ ታታሪና ብቁ፣ ሙያዊ ሥነ ምግባር የተላበሰ ሙያተኛ ያስፈልጋል። ሁለተኛው ደግሞ ምርትና አገልግሎት በጥራትና በብዛት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ በክህሎት የሚመራ ሠራተኛ ማስፈለጉ ነው። ሦስተኛው ለምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ በፖለቲካ ይሁንታ የሚወጡ ፖሊሲዎችን ለማስፈጸም የመንግሥት ሠራተኛ የግድ ይላል። መንግሥት ወጭና ገቢን ለማስተዳደርና ሀብት ለማመንጨት የዘርፉ ሠራተኛ ያስፈልጋል። ሲቪል ሰርቪስ ለተቋማዊ ልማትም ወሳኝ ነው።
ሲቪል ሰርቪስ ለዘላቂ ልማት ለመልካም አስተዳደር የማይተካ ሚና አለው። በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ገለልተኛ የአስተዳደር መዋቅር የሚሸከመው ሲቪል ሰርቪስ በመሆኑ የዴሞክራሲ ሁነኛ አካል ይሰኛል። በዚህ ሚናው አገራት ሲቪል ሰርቪስ ከፍ ያለ የሙያና የሥነ ምግባር ደረጃዎች ሊኖረው ይገባል ሲሉ ይመክራሉ። ሲቪል ሰርቪሱ ፖሊሲውን፣ ሕጎችን፣ የአሰራር ሂደቶችን፣ ሥርዓቶችንና
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ድርጅታዊ አወቃቀርን ያካትታል። ሲቪል ሰርቫንቱ በመንግሥት ተቋማት አስተዳደራዊ መሳሪያዎችን የሚያንቀሳቅስ፣ መንግሥታዊ ውሳኔዎችን የሚያስፈፅም ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ አስተዳደር መምህር የነበሩት ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ ሲቪል ሰርቪስ የሙያተኞች ማህደር ነው፤ የሥርዓተ መንግሥቱ ምሰሶ በማለት ይገልጹታል። ሲቪል ሰርቪሱ በሕግ ምንጭነት፣ በሕግ አስፈፃሚነት ያገለግላል። የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የሚሳለጠው በመንግሥት ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ነው። በጥቅሉ ሲቪል ሰርቪስ የዘላቂ መንግሥታዊ አስተዳደር ቀኝ ክንድ ይሰኛል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ከሠራተኞች፣ ከአማካሪዎች ጀምሮ የፕሮግራምና የፖሊሲ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የዕለት ከዕለት ተግባራት ከዋኞችኝ ያጠቃልላል ይላሉ።
ሲቪል ሰርቪሱ በምን መልክ መደራጀት አለበት?
ዓለም የሄደበትና ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ የገነባበት መንገድ ዓለም አቀፋዊ እሳቤን የያዘ ነው። ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ የሚገነባው አቅምን፣ ችሎታን፣ ቁርጠኝነትን እና ለሕዝብ ተቆርቋሪነትን መሠረት አድርጐ ነው። ሲቪል ሰርቫንቱ በችሎታው ተወዳድሮ እንዲመደብ፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል። አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደወትሮው አገልግሎታቸውን መቀጠል እንጂ የምርጫ ውጤትን ተከትሎ በሚመጡ የፖለቲካ አለመግባባቶች መታወክ የለባቸውም። በብዙ አገራትም በችሎታና በልምድ ሥርዓት በፈተና ይቀጠራሉ።
የአንድ መንግሥት ሁለንተናዊ ሥራ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አሠራር ገለልተኛ ሆኖ ብቃት ባለው የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ታግዞ ሕዝብ ማገልገል ይጠበቅበታል። በዘርፉ ምሁራን ብያኔም በመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት የተሰማራ የመንግሥት ሠራተኛ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አሠራር ገለልተኛ መሆን መሠረታዊ ቅድመ-ሁኔታ ሆኖ ተቀምጧል። የሠራተኛው ገለልተኝነት የመንግሥት ተቋም ዴሞክራሲያዊ ቅቡልነት መሠረት ይሆናል።
የመንግሥት ሠራተኞች የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸውን መንግሥታት ለማገልገል የሚያስችል ዝግጁነትና ብቃት ሊኖራቸው ይገባል። በሕዝብ የተመረጠው መንግሥት ያወጣቸውን ፖሊሲዎች ሳይሸራርፉ በታማኝነትና በቅንነት የመተግበር፤ ከፖለቲካ እምነትና ፕሮግራም ባሻገር ያሉ ሙያዊ ምክሮችንና አስተያየቶችን የማቅረብና እንደአስፈላጊነቱም በምክንያት መሞገትም አለባቸው። በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥትም ቀድሞ ከነበረው መንግሥት የወረሰውን የካበቱ ፈርጀ ብዙ ወረቶችን ቀጥሎ ለሚመጣው የመንግሥት አስተዳደር ማውረስ አለበት። በየትኛውም ሁኔታ መንግሥት ሲለወጥ ሙያዊ ብቃትን መሰረት ያደረገ ሲቪል ሰርቪስ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ የመንግሥትን ግቦች የሚያስፈጽም ፋይዳ አለው። “ፖለቲከኞች ይቀየራሉ፤ አስተዳደሩ (ሲቪል ሰርቪሱ) ግን ይዘልቃል” ይሰኛል። ሙያውን የጠበቀና ገለልተኛ ሲቪል ሰርቪስ መንግሥት ቢለወጥም ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ሳያዛባ ይቀጥላል።
ብቁ በሆነ የሲቪል ሰርቪስ ማዕቀፍ የሚመራ ተቋም ስራውን በትክክል ቆጥሮ መከወን ይችላል። ምሁራኑ በጥቅል ሲቪል ሰራተኞች የፖለቲከኞችን ውሳኔና ኃላፊነቶች ይከውናሉ። የሕዝብ አስተዳደር ተግባራትን የሚከውነው የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓቱ ነው።
የሲቪል ሰርቪስ ጥቅሞችን በቀላሉ ለማሳየት አሜሪካን ማንሳት ይቻላል። የአሜሪካ ልዕለ ኃያል ሆኖ የመቀጠል አንዱ ጉዳይ የተዋጣለት ሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት መንበሩ ነው። ፕሬዚዳንታዊ ሥርዓት በምታራምደው አሜሪካ የሪፐብሊካንም ሆነ የዴሞክራት ፓርቲዎች መንበረ መንግሥቱን ሲቆጣጠሩ ሲቪል ሰርቪሱ በምርጫ ሳይናወጥ፤ ሥርዓቱ ሳይወዘወዝ ይቀጥላል። ይህ የሆነው በአሜሪካ በ1880ዎቹ ገዳማ የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ለውጥ ንቅናቄ ከፖለቲካ ጥገኝነት አላቆ ወጥ ሥርዓት በማንበሩ ነው። የሰው ኃይል አስተዳደሩ ከጥቅም መራሽ ወደ ችሎታ መራሽ ሠራተኛ ምልመላና ምደባ፣ ከፖለቲካ ወገንተኝነት ወደ ቴክኒካዊ ብቃት ማሸጋገር ችሏል። በዚህም የሲቪል ሰርቪሱ የሰው ኃይል ሙያውን የጠበቀ እንዲሆን፣ አዎንታዊ ሚናው አገራዊ ፋይዳ እንዲያበረክት አድርጎታል።
ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ እንደሚሉት ሲቪል ሰርቫንቱ በሳይንሳዊ ዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት በችሎታው የሚጠበቅበትን መወጣት እንዲችል የተደራጀ ቴክኒካዊና ሙያዊ አቅም ሊኖረው ይገባል። የተቀጣሪ ሠራተኞች የሥራ ዕድገት በፖለቲካ ውግንና ሳይሆን ባሳዩት ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ ለሕዝብ ጥቅም ባላቸው ተቆርቋሪነት መለኪያዎች ተመዝነው መሆን አለበት። ሲቪል ሰርቫንቱ የሚመለመለው በብቃቱና በችሎታው እንጂ በፖለቲካ ዝንባሌው ወይም በአባልነት መሆን የለበትም። የአሸናፊውን የፖለቲካ ኃይል ፖሊሲና ፕሮግራም አስፈጻሚ ቢሆንም ደጋፊና ነቃፊ መሆን አይገባውም።
አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በብቁ ባለሙያዎች መሙላት ይገባል። አንድ ባለሙያ በተመደበበት ቦታ ሆኖ የሚነቅፈውን የፖለቲካ ፕሮግራም እያስፈፀመ ከሆነና ፖለቲካውን ለመጉዳት ስራውን የሚበድል ከሆነ ሕዝብን እየጐዳና እያማረረ ስለሚሄድ ይህ ባህል መታከም አለበት። የአገልግሎት ቃል ኪዳንን መብላት ነው። የሲቪል ሰርቪስ ተቋም በየጊዜው እየተገነባ የሚሄድ ነው።
በሌላ በኩል ሲቪል ሰርቪሱ የአሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ ፖሊሲና ፕሮግራም ማስፈጸም አለበት። የፖለቲካ አባልነትን ከሲቪል ሰርቪሱ ማስፈጸም ጋር አቀላቅሎ ማየት አይገባም። የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ የፓርቲ አባል የፓርቲውን ፕሮግራም መሥሪያ ቤት የመንግሥትን ሃብትና ጊዜ ተጠቅሞ መፈጸም አይችልም።
ዶክተር ፋንታ እንዳሉት የአገልግሎት አሠጣጥ ደካማነት ሕዝብን ለአመፅ ይገፋፋል። ለሀገራዊ ለውጡ ምክንያት የሆነው አመፅ የፖለቲካ ጥያቄ ብቻ አልነበረም። ዜጎች የሚፈልጉትን ጥራት ያለው አገልግሎት የማግኘት ችግርም ጭምር ነው። የዜጋው ጥረት ፍሬ የሚያፈራው ሲቪል ሰርቪሱ ሲስተካከል ነው። ካለመልካም
ሲቪል ሰርቪስ አገር አያድግም።
የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት አመሰራረት ሂደት በኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በሥርዓተ መንግሥት ምስረታ ቀደምት ብትሆንም ቅሉ ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ጅማሮና በመተግበር ረገድ ከአውሮፓና ከሌሎች አገራት አንጻር ስትታይ ዘግይታ ነው ወደ ሥርዓቱ የገባችው። ሀገረ መንግሥቷን ስትመራ የቆየችው በባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት ነው።
እንደ ሪቻርድ ፓንክረስት ጥናት የዘመናዊ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የጀመረው በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1900 አካባቢ ነው። በወቅቱ የመንግሥትን ስራዎች በቀልጣፋ አደረጃጀትና ትዕዛዝ ለማስፈጸም ዘጠኝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተቋቋሙ። እነሱም የሥራ፣ የፍትሕ፣ የግብርና እና ኢንዱስትሪ፣ የአገር ግዛት፣ የግቢ፣ የንግድና ውጭ ጉዳይ፣ የገንዘብ፣ የጦርና የጽህፈት ሚኒስቴሮች ነበሩ።
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመናዊት ኢትዮጵያን የመገንባት ራዕይ እውን ለማድረግ የአገር ደኅንነትን፣ የግብር አሰባሰብን እና ዘመናዊ ጦሩን ለመደገፍ ያቋቋሙት ካቢኔ የኢትዮጵያ የመንግሥት አስተዳደር እና የዘመናዊ አገልግሎት ሥርዓትም ጅማሬ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደትን ለማስቀጠል ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነበር። ከዚህ ቀደም ሲል የነበሩት ዘውዳዊ ሥርዓቶች ምንም እንኳ ሥልጣናቸውን ቢያስጠብቁም ምንም አይነት የአስተዳደር ማዕቀፍ አልዘረጉም ነበር። ለመንግሥት አስተዳደር ሥርዓቱ ብቃት-ተኮር መረጣና ምልመላ፣ የሥራ ስምሪት የአሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋለት በመሆኑ ከንጉሣዊ ወገን መወለድ፣ ትውውቅ፣ ቅርርብ፣ ለንጉሣዊ ሥርዓቱ ታማኝነት፣ ዝምድና፣ ጋብቻና አምቻ የመሳሰሉት ዋነኛ የመመዘኛ መስፈርቶች ሆነው ቆይተዋል።
እንደ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ጥናት ኢትዮጵያ ከትምህርት በፊት ያቋቋመችው የመንግሥት ተቋማትን ነው። በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ በመሳፍንትና በቤተ ክህነት ሊቃውንት መተዳደር የግድ ብሏቸዋል። ዘመናዊ አስተዳደሩም በግለሰብ መልካም ፈቃድ አስተዳደርና ቁጥጥር ላይ የተመሰረተ ነበር። በተቋማቱ አገልግሎት አሰጣጥ ያልተሟላ አወቃቀር፣ ብቁና በቂ ያልሆነ አገልግሎት፣ ሙስና እና የልዑላን ጣልቃ ገብነት ችግሮች ነበሩበት። በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ሚኒስትሮች በጦርነት ጊዜ በሚያንቀሳቅሱት ጦር ብዛትና ታማኝነታቸው ተመዝኖ የሚሾሙና አለደመወዝ ያገለግሉ ስለነበር የሲቪል ሰርቫንቱ ቁጥር እዚህ ግባ የማይባል ከመሆኑም ባሻገር በዋናነት በሕግ ማስከበር ሥራ ላይ ያተኮረ ነበር።
ሄኖክ ስዩም አሰፋ የተባሉ ተመራማሪ በ2017 ዓ.ም “Advance Research and Devel- opment” በተሰኘ ዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔት ባሳተሙት ጥናት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ በዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት ዝርጋታ ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል። በዘውዳዊው ሥርዓት ማክተሚያ ላይ ወጥነት ባለው ሕግ የሚመራ፣ ብቃት ያለው ውጤታማ የሆነ የመንግሥት አስተዳደር ማደራጀትን ታሳቢ ያደረጉ ተቋማትን እንደገና የመመሥረትና የማዋቀር ተከታታይ ተግባራትን አከናውነዋል። የአገር ማዕከላዊነት እና ዘመናዊነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰው አፄ ኃይለሥላሴ ተከታታይ የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት አሰራሩ ተቋማዊ እንዲሆን ማድረጋቸው እንደሆነ የታሪክ ምሁራን ጽፈዋል። የሠራተኛ ማሰልጠኛ፣ ማማከርና ጥናት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የዘውዳዊ ሕዝብ አስተዳደር ኢንስቲትዩት በ1944 ዓ.ም መቋቋሙ በአብነት ይነሳል። እ.ኤ.አ 1962 የመንግሥት አገልግሎት መመሪያ እንዲሁም በ1972 የሠራተኛ ሥራ መደብ ዝርዝርና እርከን ደንብ ወጥቷል።
በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መበራከትና የሠራተኛው ብዛት በዓይነትና በመጠን በመጨመሩ፣ እንዲሁም የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ዓለም አቀፍ ግንኙነት በመስፋፋቱ፣ የሠራተኛውን አስተዳደር ዘመናዊ መልክ ማስያዝ የግድ ብሎ እንደነበር አቶ ተፈራ ኃይለሥላሴ በኢትዮጵያ ጥናት መድረክ ባሳተሙት ጥናት አመላክተዋል። በተለይም በቅኝ ግዛት አስተዳደር ስር የቆዩ አገራት የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርን በኃላፊነት
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የሚመሩ መሥሪያ ቤቶችና ሠራተኞችን የሚያስተዳድሩባቸው ደንቦች ሲኖሯቸው፣ በነፃነት የኖረችው ኢትዮጵያ ያለደንብ ሠራተኞቿን ማስተዳደሯን የአፄ ኃይለሥላሴ መንግሥት የሚቀበለው እውነታ አልነበረም። መንግሥት ይህን ክፍተት ለመሸፈን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሙያዎች እና በኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች አስጠንቶ በ1954 ዓ.ም የመንግሥት ሠራተኞች ማስተዳደሪያ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ስለማቋቋሙም ይገልጻሉ። በመቀጠልም የሠራተኞች ማስተዳደሪያ ዝርዝር ድንጋጌዎችን የያዘ ደንብ በ1955 ዓ.ም ወጥቷል። የመንግሥት ሠራተኞች ማስተዳደሪያ ደንብ መውጣቱ፣ በተለይ የሠራተኛ ቅጥርን፣ ዕድገትን፣ ደመወዝን፣ ዝውውርን፣ ልዩ ልዩ ፈቃድን፣ ቅጣትን፣ ሥልጠናን፣ ወዘተ በመሳሰሉት የአሰራር ሥርዓቶች ላይ ሥር ነቀል ለውጥ አምጥቷል። ሠራተኛውም ተግባሩንና ኃላፊነቱን፣ እንዲሁም መብትና ግዴታውን በመረዳት ሥራውን የሚያከናውንበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል።
በ1954 ዓ.ም የተጀመረው በሕግና ደንብ የሚመራ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት በመንግሥት የአገልግሎት ሥርዓቱ ታሪክ ውስጥ ብቃትን መሠረት ያደረገ የሠራተኞች ምልመላ፣ መረጣና ስምሪት ሥርዓት ማቆጥቆጥ የጀመረበት ጊዜ ነበር ማለት ያስችላል። ደንቦቹን ተከትለው ተግባራዊ የሆኑት አሠራሮች በዘመኑ ከበለፀጉት ሀገሮች ጋር ሲነጻጸሩ የአስተዳደር ሥርዓቱን ዘመናዊ ከሚባሉት አገሮች ተርታ ማስቀመጥ የቻሉ ነበሩ። በእነዚህ ደንቦች አማካይነት የመንግሥት ሠራተኞች ምልመላ፣ መረጣ፣ የሥልጠና አካሄድ፣ የሥራ አፈጻጸም ምዘና፣ የደመወዝ ጭማሪ ሥርዓት፣ የመንግሥት ሥራዎች የሚኖሯቸው እንደ ጥበቃና ጉልበት (ጥጉ)፣ እጅ ጥበብ (እጥ)፣ የፅህፈት ሥራ (ፅሂ)፣ አስተዳደር (አስ)፣ መለስተኛ ፕሮፌሽናል (መፕ) እና ፕሮፌሽናል ሣይንስ (ፕሣ) የመሳሰሉት ደረጃዎች እና የደመወዝ ስኬል ሥርዓት ተዘርግቷል። ይህ ወቅት የመንግሥት ሠራተኞች የዲሲፕሊን ሥርዓትና የአስተዳደር ፍርድ ቤት አሠራሮች የተቋቋሙበት፣ ዘመናዊና ወጥነት ያለው የሰው ሀብት አስተዳደር፣ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ የሠራተኞች ሥራ አፈጻጸም ምዘና፣ እና ሌሎች የመንግሥት አስተዳደር ሕጎችና አሠራሮች ተግባራዊ የሆኑበት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የመንግሥት ሠራተኞች ማስተዳደሪያ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት የተቋቋመበት ዓላማ የመንግሥት አስተዳደር ሠራተኞች በአንድ ወጥ ደንብና የአሰራር (የሠራተኛ ቅጥርና ስንብት፣ ደመወዝ፣ የደረጃ ምደባና ዕድገት፣ ፈቃድ፣ የሥራ ሰዓት፣ ወዘተ) የአሰራር ሥርዓት (ዲሲፕሊን) ማስከበሪያ ሥርዓትን፣ የሠራተኛ ማሰልጠኛ ደንቦችን እና መመሪያዎችን የተመለከቱ ጉዳዮችን እያጠና ለመንግሥት አቅርቦ ማስፈቀድና አፈጻጸማቸውንም መከታተል ነበር። መሥሪያ ቤቱ በንጉሡ በሚሾሙ የበላይ ኮሚሽነር እና በሁለት ኮሚሽነሮች የሚመራ ሆኖ ተጠሪነቱ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነበር። የመሥሪያ ቤቱ ማንኛውም ጉዳይ የሚወሰነው በኮሚሽነሮች ጉባዔ ነበር።
የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መራሹ መንግሥት ደግሞ ከ1984 ዓ.ም እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት በቀደሙት ሥርዓቶች የነበሩትን የሰው ሀብት አስተዳደር ደንቦች በማሻሻልና ሌሎችም የአሠራር ዘዴዎችን በመተግበር ሥርዓቱን ለማዘመን ጥረት አድርጓል። ሥርዓቱ በተነጻጻሪነት ካስተናገዳቸው መሠረታዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ጋር የተጣጣመ የአገልግሎት ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የለውጥና የማሻሻያ መርሃግብር ነድፎ የተለያዩ ተግባራትን አከናውኗል። እንደቀደሙት መንግሥታት ሁሉ የመንግሥት አስተዳደሩንም ሆነ የአገልግሎት ሥርዓቱን የኃላፊነትና የሥራ መደቦች ለፓርቲው ፍጹም ታማኝ በሆኑ ሠራተኞች የሚሞላበትን አሠራር ቀጥሎበት ቆይቷል። ሥርዓቱም በፓርቲው ቀጥታ ጣልቃ ገብነት የሚመራበትን አቅጣጫ ለማጠናከርም አበክሮ ሠርቷል።
ታሪካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ እውነታዎች በሲቪል ሰርቪሱ ሙያዊ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ አሳድረውበታል። ፖለቲካው በሰው ኃይል አስተዳደርና ውሳኔዎች ላይ ቁልፍ ሚና ይጫወት ነበር። በዚህም ሲቪል ሰርቪሱ በከፍተኛ ሁኔታ የፖለቲካ ተቋም ሆኗል ሲል የአቶ ተፈራ ኃይለሥላሴ ጥናት ይደመድማል። የሰራተኛ ምልመላ ሂደቶች በሕግና ሥርዓት አለመመራታቸው፣ አድሎ፣ ጉቦ፣ ፖለቲካዊ ታማኝነት የሲቪል ሰርቪሱን ሙያ ሲበድል ኖረዋል፤ በተለይም በመካከለኛና ከፍተኛው አመራር አካባቢ። በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር
በ1962 የተቋቋመው የማዕከላዊ የሰው ኃብት ኤጀንሲ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ምስረታ መሰረት ሆኗል። ዓላማውም ብቃትን መሰረት ያደረገ ብቁ፣ ውጤታማ፣ ቋሚ ሲቪል ሰርቪስ መዘርጋት ነበር። በእርግጥ ቢሮክራሲውና አወቃቀሩ የአውሮፓ ተዕጽኖ ነበረበት። በግሉ ዘርፍ ያለው የገበያ ውድድር እና የሲቪል ሰርቫንቱ አነስተኛ ክፍያ በመንግሥት አገልግሎት ተቋማት ብቁ የሆኑ ባለሙያዎች በየሙያ መስኩ እንዳይቆዩ ማድረጋቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ።
የአገልጋይነት ተልዕኮ እና ሥነ-ምግባር
ለኢትዮጵያዊያን የጋራ በሆነችው ኢትዮጵያ ሁሉም በእኩልነትና በፍትሃዊነት ሠርተው የሚለወጡባት አገር ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ነው። አገልግሎት የሁላችንም ነው፤ በአንድ ተቋም ያለ አገልጋይ በሌላው ተቋም ተገልጋይ ነው። የሲቪል ሲርቪስ ተልዕኮ ከከሸፈ ራሱ ሲቪል ሰርቫንቱ ተጎጂ ይሆናል። የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ትኩረት ሰጥቶ ሊያጠናክራቸውና ሊሰራባቸው ከሚገቡ አበይት ዕሴቶች መካከል ዜጋና ውጤት ተኮር ሰብዓዊ ብልፅግና፣ በራስ የመተማመንና ራስን የመምራት ብቃትን ማረጋገጥ፣ ፈጠራና ሰላማዊነት (ለሰላም ዘብ መቆም) የሚሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ናቸው። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሥነ- ምግባር ዕሴቶች በአራት ይከፈላሉ። እነሱም:-
1. ሥነ-ምግባራዊ ምሉዕነት (ሰብዓዊ ታማኝነት እና ፍትሃዊነት)፤
2. ዴሞክራሲያዊነት (ግልፅነት፣ተጠያቂነት፣ ሕጋዊነት እና ተወካይነት)፤
3. ሙያዊ ብቃት (አገልግሎት፣ ጥራት፣ አመራር እና ፈጠራ) እና ፤
4. ሰብዓዊ ዕሴት (መቻቻል፣ ርህራሄ፣ መልካም ምግባር፣ ድፍረት፡ ደግነት፣ እና ፍትሃዊነት) ናቸው።
እነዚህ ዕሴቶች የመንግሥት ዘርፍ ሥነ-ምግባር በዕለት ተዕለት ሥራ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ የመንግሥት ሠራተኛው (ሲቪል ሰርቫንቱ) ሊላበሳቸውና አበክሮ ሊተገብራቸው ይገባል። የሥነ መግባር እሴቶች ሳይኖሩ አገልግሎት አሰጣጥን ማሳለጥ፣ መልካም አስተዳደርን ማረጋገጥና የሕዝብ አመኔታን ማግኘት አይቻልም።
የሰው ሀብት አስተዳደር ፍልስፍና በብቃትና ችሎታ “ምሉዕ ስብዕና” ያለውን ሰው የመንግሥት ሠራተኛ አድርጎ በማሰማራት የዜጎች አገልጋይ እንዲሆን ማድረግ ነው። በአንድ አገር የአስተዳደር ሥርዓት ውስጥ መልካም አስተዳደር የማስፈን ጉዳይ ችሎታ፣ ብቃት፣ ምሉዕ ሰብዕና እና ቁርጠኝነት ያላቸውን ሰዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ ወደ መንግሥት ዘርፍ ከማስገባት ወይም ካለማስገባት ጋር በቀጥታ ይያያዛል። “ምሉዕ ስብዕና” በመንግሥታዊ አገልግሎት ዘርፍ ከራስ በፊት አገርንና ሕዝብን ማስቀደምን፣ ታማኝነትን፣ የዓላማ ፅናትን፣ ዝቅ ብሎ ማገልገልንና በቃል መገኘትን ተላብሶ በአእምሮና በአካል ለሥራ ዝግጁ መሆንን የሚያስገነዝብ ገዥ ሃሳብ ነው። በመንግሥት ሥራ በመሪነትም ሆነ በሠራተኛነት የ”ምሉዕ ስብዕና” ባለቤት ሳይሆኑ በኃላፊነት ቦታዎች መቀመጥ እንደ ቀላል ስህተት የማይታለፍ ጥፋት ነው። የሀገራችን የአስተዳደር ሥርዓት ከዚህ ገዥ ባህርይ አንጻር ሲገመገም እያሽቆለቆለ የመጣ ማንነት ያለው መሆኑን በዘርፉ የተካሄዱ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።
የኢትዮጵያ የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂም ዋና ትኩረቱን ያደረገው ማገልገል ክብር የሆነበት ሥርዓት መገንባት ተገቢነት ላይ ነው። የመንግሥት ዘርፍ የሰው ሀብት ልማት የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ዘርፉን የሚቀላቀሉት አገርንና ሕዝብን ማገልገል ሀገረ መንግሥትንና ሉዓላዊነትን የማስቀጠል ጉዳይ መሆኑን በውል መገንዘብ ያሻቸዋል። የመንግሥት ሠራተኞች ከመንግሥት ሥራ የሚያገኙት ጥቅም በገንዘብና በንብረት የሚለካ ሳይሆን ዜጎችን አክብሮ ከሚሰጥ የላቀ አገልግሎትና ከተገልጋይ እርካታ በሚመነጭ አንፀባራቂ ክብር የሚገለፅ ነው። ስለሆነም የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ አገርንና ሕዝብን ማገልገል ድርብ ክብር የሚያስገኝ መሆኑን ከሕፃንነት ጀምሮ በትምህርት ቤት በሚሰጡ ትምህርቶችና የሞራል አስተምህሮዎች ተደግፎ የሚሰርጽ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታ ችግሮች
ጥናቶች እንደሚያስረዱት አፄ ኃይለሥላሴ በሕግና ሥርዓት የሚመራ፣ ብቃት ያለው ውጤታማ የሆነ የመንግሥት አስተዳደር ማደራጀትን ታሳቢ ያደረጉ ተቋማትን እንደገና የማቋቋምና የማዋቀር ተከታታይ ተግባራት እንዲከናወኑ ያደረጉት በተቋማቱ አደረጃጀት የመሣፍንቱን አቅም ለመገደብና የንግሥናቸውን ማዕከላዊ ሥልጣን ለማጠናከር ነበር። የመንግሥት ሥራዎችን በሰው ኃይል በማስያዝ ረገድ ለፖለቲካ ታማኝነት የተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት፤ በመመሪያዎች አወጣጥና አተገባበር ላይ የነበረው ቀጥተኛ የፖለቲካ ጣልቃገብነት የመመሪያዎቹን ውጤታማነት ጎድቶታል።
በኢትዮጵያ ሠርቶ አደሮች ፓርቲ (ኢሠፓ) ብቸኛና ግንባር ቀደም መሪነት የቆየው ወታደራዊው የደርግ መንግሥትም ለሚከተለው የማርክሲስት-ሌኒኒስት ርዕዮተ-ዓለም ፍጹም ታማኝ የሆነ ሠራተኛ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱ ውስጥ በስፋት እንዲካተት፤ ፓርቲው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እንዲኖረው፣ በመንግሥት አስተዳደር እና በፓርቲው አሰራር መካከል ሊኖር የሚገባው መሠረታዊ ልዩነት እንዲደበዝዝ አድርጓል። ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ የደርግ ርዕዮተ-ዓለም ማራመጃ ሆኖ የቆየ በመሆኑም ነፃና ገለልተኛ አልነበረም። በጊዜው ቁልፍ የመንግሥት ውሳኔዎች የሚተላለፉባቸው የኃላፊነት ቦታዎች በፓርቲ አባላት እንዲያዙ ተደርጓል። ሥርዓቱ እንደቀደሙት ሁሉ የተማከለ አስተዳደርን በመከተሉ፣ በርካታ ነባር ደንቦች በደብዳቤ በመሻራቸው፣ አምራች ያልሆነ የሰው ኃይል በመሰባሰቡ፣ ለብዝሃነት ዋጋ ባለመስጠቱ እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ባለማካተቱ የመንግሥት ሠራተኞች ክብር በኢኮኖሚም ሆነ በማኅበራዊ ይዞታው እያሽቆለቆለ መምጣቱንም አቶ ተፈራ ያስረዳሉ።
ከወታደራዊው ደርግ ቀጥሎ አገር የማስተዳደር ሥልጣን የተረከበው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መራሹ መንግሥት የመድብለ ፖለቲካ ፓርቲ ሥርዓትን የተከተለ ነበር። “በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ” አስተሳሰብ እየተመራ ሀገሪቱን ያስተዳደረው ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥትም እንደቀደሙት የመንግሥታት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ለፖለቲካ ፓርቲው ፍጹም ታማኝ በሆኑ ሰዎች በማሲያዝ የፓርቲውን ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት አስፍኗል። አንዳንድ ወገኖች መንግሥት ለዘመናት የተንሰራፋውን የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች መደበላለቅ መለየት እንዳለበት ይገልጻሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ“መደመር” መጽሐፋቸው እንዳመለከቱት ገዥ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለዋወጡ ቁጥር የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ተቋማትን ከመሠረታቸው አፍርሶ የመገንባት ልማድ የሀገራችንን የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ሁሌም ለጋ እና የቀጨጨ እንዲሆን አድርጎታል። በመንግሥት ፖለቲካ ሥራዎችና በአስተዳደራዊ ተግባራት መካከል ሊኖር
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የሚገባው በመደጋገፍ ላይ የተመሠረተ የሥራ ግንኙነት ፈሩን ስቶ በሥልጣን ላይ ያለው የፖለቲካ ፓርቲ በተቀያየረ ቁጥር ሀገረ- መንግሥቱ የተዋቀረባቸው ተቋማት ፈርሰው ፍጹም እንደ አዲስ የሚገነቡበት፤ ያም ሆኖ ከማኅበረሰቡ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ባህሎች ዘላቂ ለውጥ ጋር በንቃት ለመጓዝ ራሳቸውን ማደስ የሚችሉ አልሆኑም።
በ2013 ዓ.ም የታተመው የመንግሥት አገልግሎት ፍኖተ ካርታ ባለፉት አሥርት ዓመታት በሀገራችን የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓትን ለማጠናከርና የማስፈጸም አቅምን ለማጎልበት እንዲቻል የተለያዩ የማሻሻያ ፕሮግራሞች ቢነደፉም፤ ወቅቱ በሚፈልገው ልክ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በመምራት የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካ መንግሥታዊ መዋቅር እንዳልተገነባ ያትታል። የአገልግሎት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተተገበሩ የለውጥ መሳሪያዎችም ለውጥ እንዳላመጡ ይልቁንም ተቋማት የሕዝብን ፍላጎት ከማርካት ይልቅ ለቅሬታ የዳረጉ፤ የመንግሥት ፖሊሲ አስፈጻሚ የሆነውን የመንግሥት ሠራተኛ የሕዝብ አገልጋይነት ስሜት ያሳጡ፤ ሕዝቡ ለሲቪል ሰርቫንቱ ያለው አመለካከት የተዛባ እንዲሆን ምክንያት መሆናቸውንም አመላክቷል።
ሕዝብን ከመምራት ጋር በተያያዘ ኃላፊነት የተጣለበትን አንድ ተቋም ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ተጽዕኖ ውጪ ማድረግ ፈጽሞ ባይቻልም፤ ከፖለቲካ ፓርቲ ቀጥተኛ ቁጥጥር የራቀ እንዲሆን ማድረግ እንደሚቻል ጥናቶች ያመለክታሉ። በመንግሥት የአስተዳደራዊ ሥራዎች ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና ባለሙያዎችን የማግለል አሰራር በዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ተቀባይነት የለውም። ካዩዚያ የተባለ የዘርፉ ምሁር የፖለቲካ ሥራዎችን ከመንግሥት አስተዳደራዊ ሥራዎች ለያይቶ ማየት ፈጽሞ ባይቻልም ሁለት የሚደጋገፉ የሕግ አስፈጻሚው የሥራ ክፍሎች እንጂ አንድ አይደሉም ይላሉ። አንዱ በሌላው አሰራር ውስጥ ዘልቆ በመግባት በሚወስንበት ጊዜ የፖለቲካና የመንግሥት አስተዳደራዊ ሥራዎች ሚዛናዊ መደጋገፍ ይዛነፋል። በዚህም የመንግሥት ውጤታማነት፣ አካታችነትና ተጠያቂነት ያለበት ተቋማዊ አሰራር መገለጫ የሆነው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ በሁሉም ገፅታው የተዛባ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ“መደመር” መጽሐፋቸው “ሀገረ-መንግሥቱ በደቀቁ፣ ሙያዊ ብቃታቸው ዝቅተኛ በሆኑ፣ እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ ባልሆኑ ተቋማት የተደራጀ ሆኗል” ይላሉ። በዚህም በርካታ ሰዎች ደረጃቸው ከፍተኛ በሆኑ የመንግሥት ሥራ መደቦች ላይ የፖለቲካ ምደባ ተደርጎላቸው ሥልጣንን ለግል ብልፅግና የሚያውሉ፣ በባለሥልጣናቱና በባለሀብቶች መካከልም የእንካ-በእንካ ግንኙነቶች በመንግሥት አገልግሎት መስኮች እንዲጎላ ሰበብ መሆኑን አመላክተዋል።
ወርቁ ታደሰ ከሦስት ዓመት በፊት “የፐብሊክ ሰርቪስ ለውጥ በኢትዮጵያ ተግዳሮትና የአፈጻጸም ክፍተቶች” በሚል ርዕስ በዓለም አቀፍ የምርምር መጽሔት ያሳተሙት ጥናት የለውጥ መሳሪያዎችን ተግባራዊነት እና ክፍተትን ዳሷል። የጥናቱ ግኝት የፐብሊክ ሰርቪሱ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች ከሀገሪቷ የልማት ስትራቴጂ ጋር አብረው የማይራመዱ፣ የኢትዮጵያን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገቡና ከሌሎች አገራት በቀጥታ የተቀዱ መሆናቸውን አመላክቷል። አተገባበራቸውም በፖለቲካዊ ግፊት በቀጥታ ከላይ ወደታች መውረዳቸው ውጤታቸው በወረቀት ትርክት ተንጠልጥሎ ከግባቸው መራቃቸውን በጥናቱ አሳይተዋል። ለውጡ ከፍተኛ የሠራተኛ ፍልሰት በማስከተሉ ተቋማት ልምድ ያላቸውን ሠራተኞች እንዲያጡና እንዲዳከሙ መደረጋቸውን እና ፖለቲካና ዘውግ ዘመም ሲቪል ሰርቪስ እንዲፈጠር ማድረጋቸው፤ በጥቅሉ የለውጥ ሥራዎቹ በሲቪል ሰርቪሱ መዋቅር አገልግሎት አሰጣጥ ተጨባጭ ለውጥ እንዳላመጡ ይደመድማሉ።
ተክላይ ተስፋይ እ.አ.አ በ2016 በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናታቸውን በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ሥነ ምግባር ላይ አካሂደዋል። ጥናቱ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች የሥነ ምግባር እሴቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸሩ መምጣታቸውን አመላክቷል። ወጣቱ ትውልድ ኢ-ሥነ ምግባራዊና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በአቋራጭ መክበርን ምርጫው ስለማድረጉ፣ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት በሥርዓተ ትምህርቱ ቢካተትም የወጣቱ የሥነ ምግባር ጥሰት እየተባባሰ ስለመሄዱም አንስቷል።
ባጫ ከበደ እና ሌሎች አጥኚዎች ባካሄዱት ጥናት የመንግሥትን አመኔታ ለማትረፍና የዜጎችን አገልግሎት እርካታ ለማሳደግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ይገልጻሉ። የመንግሥት ተቋማት የማስፈጸም አቅም ማነስ፣ የምዕራቡ ዓለምና የአገር በቀል ሥርዓት አለመጣጣምና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች የዘርፉ ችግር እንዲባባስ ሰበብ መሆናቸውን ያነሳሉ። በጥቅሉ እነዚህና መሰል መንስኤዎች ሕዝብ በመንግሥትና በሕዝብ አስተዳደር ተቋማት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርገው እ.አ.አ ከ2014 እስከ 2018 በሕዝባዊ ማዕበል መመታቱን ይገልጻሉ።
አጥኚዎቹ እንደሚሉት በሰው ኃይል ረገድ ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የተደረገው
ተቋማዊና የፖለቲካ አስተዳደር ማሻሻያ በክልልና በፌዴራል የነበረውን የሰው ኃይል ሥራ አመራር ለውጦታል። የሰው ሀብት ምልመላ፣ አቅም ግንባታና ዕድገት ሙያ መር የፖለቲካ ጥገኝነት የተቀላቀለበት ነበር። ሲቪል ሰርቪሱ ከንጉሣዊውና ከአብዮቱ ዘመን የፋሽን ለውጥ አድርጓል። ፖለቲካና አቅም መር መመዘኛዎች ተደበላልቀዋል። አተገባበሩም ከላይ ወደታች መሆኑ ሲቪል ሰርቫንቱ የፖለቲካ ማስፈጸሚያ እንዲሆን አስገድዶታል።
የዘውዳዊው ሥርዓት ማዕከላዊ ሥልጣንን ለማጠናከር ታልሞ የተሠራ እንደነበረ መረጃዎች ያስረዳሉ። የመንግሥት ሥራዎችን በሰው ኃይል በማስያዝ ረገድ ለፖለቲካ ታማኝነት የተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት፣ በመመሪያዎች አወጣጥና አተገባበር ላይ ፖለቲካው የነበረው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት የነፃና ገለልተኛ ሥርዓት ግንባታውን ውጤታማነት ተፈታትኖታል።ሥርዓቱ የራሱ ጥንካሬዎች እንዳሉት ሁሉ በርካታ ችግሮችም ነበሩት። ለአብነትም የወጡትን ሕጎች ከሀገሪቱ ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር ፈትሾ አለማሻሻሉ፣ ሥራን አቅዶ የአፈጻጸሙን ውጤት በአግባቡ አለመመዘኑ፣ በሀብት አጠቃቀሙ ብክነትን ተከላክሎ ውጤታማ አለመሆኑ፣ አገልግሎቱ የተማከለ አሠራርን መከተሉና ዜጋው ለአንድ አገልግሎት በርካታ ቢሮዎችን በማዳረስ እንዲንከራተት መንሥኤ መሆኑ ይጠቀሳሉ። የመንግሥት ሠራተኛውም ለግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ የሚገባውን ክብር አለመስጠቱ፣ ሌብነትን አምርሮ የማይጸየፍ መሆኑና አልፎ ተርፎም በድርጊቱ ተጠርጣሪ ሆኖ መታየቱ ሠራተኛውም ሆነ ዘርፉ በደበዘዘ ክብር እንዲዘቅጥ አድርጎታል።
የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ችግሮች ሥር የሰደዱ መሆናቸው፣ ሲቪል ሰርቫንቱ የፖለቲካ አራማጅና የፓርቲውን የደንብ ለብሶ የፓርቲ አባል እንዲሆን የተጀመረው በደርግ ሥርዓት እንደነበር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ይገልጻሉ። ይህም ቀደም ሲል የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ባሕል አበላሽቶታል። ይህ ባሕል ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላም ቀጥሎ ጉዳት አድርሷል። ኢሕአዴግ በወቅቱ ከደርግ ሥርዓት ጋር ወግኗል ያለውን ከሲቪል ሰርቪሱ አስወጥቶ ተጎጂ አድርጓል።
የመንግሥት የዘርፉ ትኩረት
የዜጎች ግልጋሎት ጉዳይ ዝማኔ ያሻዋል። ወጥ ሆኖ ደረጃውን ጠብቆ ሊዘረጋ ይገባዋል። የመንግሥት አገልግሎትን ጉዳይ የመንግሥትን አቋም የማገልገል ጉዳይ አድርጎ መመልከት አይገባም። የሕዝብና የአገር አገልግሎት ነው፤ ስኬታማ ልማትና አገር የሚገነባው በስኬታማ ሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ነው።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለፉት ዘመናት የግሉ ዘርፍ ለሲቪል ሰርቫንቱ መበላሸት አስተዋጽኦ አድርጓል። የሚገባውን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት ሲችል ገንዘብ ስላለው ብቻ በገንዘቡ አገልግሎትን ሲገዛ ነበር። ስለዚህ ገንዘብና አገልግሎት መራራቅ አለባቸው። ሲቪል ሰርቪሱን በሙያተኛ የማደራጀትን ተግባር ይጠይቃል።
በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው መንግሥት የሲቪል ሰርቪስን ዘመን ተሻጋሪና በመንግሥት መለዋወጥ የማይዛባ መዋቅር እንዲሆን ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
አዲሱ የሰው ኃብት ልማት ፖሊሲ ከሚገዛባቸው መርሆዎች ዋናው ከስትራቴጂዎችና ከአደረጃጀት፣ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችና መሳሪያዎች በላይ ለሰዎች ዕውቀትና የአስተሳሰብ ልህቀት አብልጦ ትኩረት ማድረጉን በ2013 ዓ.ም የታተመው የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ-ካርታ አመላክቷል። ከሰው ኃብት ልማት መስኮች መካከልም በመንግሥት ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት ፖሊሲ ለሰዎች የፈጠራ ችሎታ፣ ምጡቅ አስተሳሰብ እና ሃሳብ የማመንጨት ችሎታ ከዕውቀትና ከክህሎት በላይ ዋጋ የሚሰጠው “ቅድሚያ ችሎታ ላላቸው” የሚለው መርህ አንዱ ነው።
ለመንግሥት ሠራተኛነት የሚመለመሉ ሰዎች ‘ምሉዕ ስብዕና’ን ተላብሰው ዘርፉን እንዲቀላቀሉ፣ ለዜጎች የላቀ ውጤት ሊያስመዘግቡ የሚችሉ፣ ፈጠራን የሚያመነጭ ብሩህ አዕምሮ፣ ምጡቅ አስተሳሰብና የአዲስ ሐሳብ ባለቤቶች ሊሆኑ ይገባል። ስለሆነም በጥንቃቄ መቅጠር፤ ጥፋትን ፈጥኖ ማረም፣ ውጣ ውረድ የበዛበት የሥራ ሰንሰለትን ማሳጠር፣ አሠራርን ማቅለል፣ ችግር-ፈቺዎች፣ ለሠራተኞች ግልፅ ዕቅድ የሚሰጡ፣ አዳዲስ የሥራ ሂደቶችን የሚቀርጹና በተግባር ደግፈው ለሠራተኛው የሚያስተዋውቁ ብቁ የሥራ መሪዎችን ማፍራት፣ ማገልገል ክብር የሆነበት ሥርዓት መገንባት በተለይም የመንግሥት ሠራተኞች አገልግሎታቸው በገንዘብና በንብረት ጥቅም የሚለካ ሳይሆን፤ ዜጎችን አክብሮ ከሚሰጥ የላቀ አገልግሎትና ከተገልጋይ ዜጎች እርካታ በሚመነጭ አንጸባራቂ ክብር መሆኑን ማሳመንን ትኩረት አድርጓል።
በፍኖተ-ካርታው እንደተመላከተው ሙያዊ ብቃት ያለው ነፃ፣ ገለልተኛ የመንግሥትና የሕዝብ አገልጋይ ከማድረግ ባሻገር የአደረጃጀቶችን ምክንያታዊነት ማረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነትን ማስከበር፣ ለውጤት ተኮር አፈጻጸም ትኩረት መስጠት፣ ግልፅነት፣ ተደራሽነትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ላይ በትኩረት ይሰራል። የመንግሥት ዘርፍ የሰው ኃብት ልማቱ በተለዋዋጭ ሁኔታዎችና ለውጦች የሚያልፍ በመሆኑ፤ ከሌሎች ዘርፎች በተለየ በማያቋርጥ ለውጥ ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። በዚህም ምክንያት ከዘመን ዘመን የሚለዋወጥ ቁመናውን የሚወስኑ “ዕሴቶችን” ዜጎች/ተገልጋዮች ከሚፈልጉት ውጤት ጋር የሚጣጣሙ አድርጎ መላበስና ለየዘመኑ ጥያቄ ምላሽ ሰጪ የሆኑ አሠራሮችን ቀርጾ መተግበርን ይጠይቃል።
የመንግሥት ሠራተኛን ከፖለቲካዊ ርዕዮተ- ዓለምና ወገንተኛነት ጋር አዛምዶ በመንግሥት ሥራዎች ላይ መመደብ የብልሹ መንግሥታዊ ሥርዓት መገለጫ ነው። የመንግሥት አገልግሎት ዘርፉ ተለውጦ በሁለንተናዋ የበለፀገች ኢትዮጵያ ተፈጥራ በተለወጠ ሥርዓትም ትውልድ በቅብብሎሽ ሊኖርባት እንዲችል ተስፋና እምነት ሰንቆ መራመድ የግድ ይላል። ነባሩን የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ዘመኑን የዋጀ፣ ከፖለቲካ ጋር ያልተዛመደ፣ ለሀገረ መንግሥቱ ሕልውና የወገነ እንዲሆን ሁለንተናዊ ለውጥ እንደሚያስፈልገው ብዙዎች ያነሳሉ። ሰብዓዊ ልማትን ማዕከል ያደረገ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሆኖ መዘርጋት አለበት።
በመሆኑም ከፖለቲካ ፓርቲ ተጽዕኖ እና አላስፈላጊ ጣልቃገብነት ነፃና ገለልተኛ የሆነ፣የመፈጸም ብቃት ያለው የአገልግሎት ሥርዓት ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ተጨማሪ ጉልበት ነው። ስለሆነም “አርቆ በማሰብ፣ እንደገና ከአድማስ አቆራርጦ በማሰብ” በሥርዓቱ ግንባታ ዳግም ምልከታና ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል።
በማንኛውም የመንግሥት አገልግሎት ዘርፍ የሚሰማራ የሰው ኃይል በብቃትና በችሎታው ተመልምሎና ተመርጦ ከተሰማራ፣ የአገልጋይነት አስተሳሰብና ዕምነት በሕዝብ ውስጥ ከሰረጸ፣ ንቃተ ኅሊና ካደገና በአዲስ ዕውቀት ከበለጸገ በእርግጠኝነት የአገልግሎት ዘርፉ ችግር ይወገዳል። ሥርዓቱ በማይናወጥ ማዕዘን ላይ ከተሰራ ደግሞ ‘መንግሥት በተቀያየረ ቁጥር የሚቀያየር ሲቪል ሰርቫንት ይዘን እስከመቼ ነው የምንዘልቀው’ የሚለው ተጠየቅ ገቢራዊ ምላሽ ያገኛል።
ማኅበራዊ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ፈር ቀዳጁ የድንገተኛ ሕክምና ሆስፒታል
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ
ፈር ቀዳጁ የድንገተኛ ሕክምና ሆስፒታል
በመንገሻ ገ/ሚካኤል
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በሕክምናው ዘርፍ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስጀመር ትልቅ ድርሻ ያለው የሕክምና ተቋም ነው። በአገር ውስጥ የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና ባለሙያ ከመፈጠሩ ከ14 ዓመታት በፊት የድንገተኛ ሕክምና ክፍል ራሱን ችሎ ለብቻው እንዲገነባ በማድረግና አገልግሎት በማስጀመር በኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ነው። የሕሙማን ፍሰት ባልነበረበት እና በዘርፉ በቂ የሠለጠነ የሰው ኃይል በሌለበት ሁኔታ ከጤና ሚኒስቴር ጋራ በመሆን በወቅቱ ለሌሎች የሕክምና ተቋማት ተምሣሌት ሊሆን የሚችል የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና አገልግሎት ማስጀመሩ ለድንገተኛ ሕክምና ልዩ ትኩረት የሚሰጥ ተቋም ያደርገዋል።
የድንገተኛና ፅኑ ሕክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና የአቤት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ወልደሰንበት ዋጋ፤ የሕክምና ኮሌጁ በቅድመ ሆስፒታልና በአምቡላንስ አገልግሎት ተንቀሳቃሽ የሕክምና ማዕከል በማስጀመር በአገሪቷ ቀዳሚ መሆኑን ይናገራሉ። የድንገተኛ ሕክምናው ባልተቋቋመበትና ባልተደራጀበት ጊዜ ከኮርያ መንግሥት ጋር በመተባበር የሞባይል ክሊኒክ ማቋቋም ችሏል። በዚህም ሕክምና በሆስፒታል ብቻ ሳይታጠር በጦርነት ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው፣ ድንገተኛ በሽታዎች (ወረርሽኞች) በሚከሰቱባቸው አካባቢዎች የሕክምና ባለሙያዎች ተንቀሳቅሰው አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉት ሁለት የተደራጁ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ የሕክምና ማዕከላት ወይም ሞባይል ክሊኒኮች ባለቤት በመሆን በአገሪቷ የመጀመሪያው የሕክምና ተቋም ነው።
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በቅድመ ሆስፒታል አገልግሎቱ ባለሙያዎች አደጋ በደረሰበት እና ችግሮች ባሉባቸው ክልሎች ኤክስሬይ፣ አልትራ ሳውንድ እና ላቦራቶሪ የመሳሰሉትን የሕክምና መሣሪያዎች ጨምሮ መድኃኒቶችን ጭኖ በመሄድ ተጎጂዎችን ባሉበት ማከም የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር ችሏል። ሞባይል ክሊኒኮቹ እንደ ኮቪድ-19 ያሉ ወረርሽኞች ሲከሰቱ፣ ጦርነት በተከሰተባቸው የተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ትልቁን ድርሻ ወስዶ ከሆስፒታል በማይተናነስ መልኩ የድንገተኛ ሕክምና ሙሉ መሣሪያዎችን ይዞ በመንቀሳቀስ የሕክምና አገልግሎት ሰጥቷል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በሞባይል ክሊኒኮቹ አማካኝነት ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ትልልቅ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉባዔዎች በሚካሄዱ ጊዜ ሊከሰት የሚችልን የሕክምና እርዳታ የሚሻ አደጋ ታሳቢ በማድረግ አንድ ሺህ እና ከዚያ በላይ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች ላይ ባለሙያዎቹን አንቀሳቅሶ የሕክምና አገልግሎት የመስጠት፣ አክሞም ሕይወት የማዳን ተግባሩን ያሳየ ተቋም ነው።
በጥምቀት፣ በኢሬቻ እና በመሳሰሉት ሃይማኖታዊና አገራዊ ታላላቅ በዓላት አከባበር ላይ የሕክምና ባለሙያዎችን በማንቀሳቀስና በመምራት፤ እንዲሁም በቤኒሻንጉል፣ በጅግጅጋና በአሶሳ ግጭቶች ተከስተውባቸው በነበሩ አካባቢዎች የሕክምና ኮሌጁ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች በማደራጀትና በማስተባበር አገራዊ የድንገተኛ እና የአጣዳፊ (የጅምላ አደጋ ሕክምና)ን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በመምራት ፈር ቀዳጅ መሆኑን ነው ዶ/ር ወልደሰንበት የገለጹት።
በኢትዮጵያ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ይህን አገልግሎት ከመጀሩ ቀደም ባለው ጊዜ የብዙኃን ስብሰባ ሲኖር ሕክምና የሚሻ አደጋ ቢከሰት በቶሎ አክሞ ማዳን የሚያስችል የድንገተኛ ሕክምና አልነበረም ማለት ይቻላል። የተፈጥሮ አደጋዎችን ጨምሮ አተትና የመሳሰሉ ወረርሽኞች እንዲሁም ጦርነት ቢከሰት፣ ሆስፒታሎች አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ሁኔታ ስለሚፈጠር በእነዚህ አካባቢዎች የሕክምና ባለሙያ አንቀሳቅሶ መስራት አዳጋች ይሆናል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በድንገተኛ ሕክምና የሆስፒታል ሕክምናን ማሻሻል የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሆኖ የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት በሆስፒታሎች ብቻ ታጥሮ እንዳይቀር ተንቀሳሳቃሽ የድንገተኛ ሕክምናዎችን የሕክምና አገልግሎት አካል በማድረግ በኢትዮጵያ የሕክምና ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ማስቀመጥ የቻለ ነው።
የድንገተኛ አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመርን ተከትሎ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የድንገተኛ ሕክምናን በተለየ ሁኔታ መስጠት የሚያስችለውን ከዋናው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በተጨማሪ በአገሪቷ ብቸኛና የመጀመሪያ የሆነውን የአዲስ አበባ ቃጠሎ ድንገተኛ አደጋ ሕክምና ማዕከል (አቤት ሆስፒታል) የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል በመገንባት ተወዳዳሪ የሌለው ተቋም በመሆኑም ይታወቃል፡፡ የዚህ ማዕከል መከፈት እንደ አለርት፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ የመሳሰሉት ሆስፒታሎች የአደጋ ሕክምና ማዕከላትን እንዲገነቡ ተምሣሌት ሆኗል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ከሕክምና አገልግሎት ባሻገር በዘርፉ ባለሞያዎችን በማፍራት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል እያበረከተም ይገኛል፡፡ በድንገተኛ ሕክምና ስፔሻሊቲ ትምህርት የተጀመረው እ.አ.አ በ2010 ዓ.ም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሲሆን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመቀጠል ሁለተኛው የስፔሻሊቲ ማስተማሪያ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ እንዲሁም ባለሙያው የትምህርት ዕድል እንዲያገኝ ለምሣሌ የጽኑ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊቲን እንደ አገር ፈር ቀዳጅ በመሆን ከድንገተኛ ሕክምና ቀጥሎ ለባለሙያው የትምህርት ዕድል እንዲኖር በማመቻቸት የመጀመሪያ መባል የሚችል ነው ይላሉ ዶ/ር ወልደሰንበት።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅን ለየት የሚያደርገው ሌላው ነገር ሕክምና ለሚማሩ የመጀመሪያ ሥርዓተ ትምህርት የሚሆን ሜዲካል ዶክተር ለመሆን ሙያውን በአግባቡ እንዲለምዱ ትምህርቱ ከመጀመሪያ እንዲኖር በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ በማካተትም ከጥቁር አንበሳ በመቀጠል የሚቀድመው አይኖርም፡፡ ባለሙያዎች ወደ ስፔሻላይዜሽን እንዲመጡ ቅርፅ ከማስያዝ ጀምሮ የተደራጀ የድንገተኛ ሕክምና ማዕከል እንዲኖራቸው የራሱ አስተዋጽኦ አለው።
እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2017/18 የድንገተኛ እና የአጣዳፊ (ጅምላ አደጋ) የሚባለው ሕክምና በአገር ውስጥ
በመንግሥት በተመደበ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው ባለ አሥራ አምስት ወለል ሕንፃ፤ ከወለሎች አራቱ ከምድር በታች ናቸው።
ባልተጀመረበትና በማይታወቅበት ጊዜ ጀምሮ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ጤና ሚኒስቴር የሰጠውን ተልዕኮ በመውሰድ በመላ አገሪቷ ባለሙያ በማሰልጠን ድንገተኛ ጅምላ አደጋዎችን ማከም የሚያስችሉ እንዲሆኑ ጤና ሚኒስቴርን ወክሎ ኃላፊነቱን በመውሰድ ከ700 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችን በሁሉም ክልሎች ላይ በማሰልጠንና በማደራጀት የላቀ አበርክቶ ያለው ተቋም ነው።
የሕክምና ኮሌጁ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንደ አገር ያመጣውን አደጋ ለመጋፈጥ የሕክምና ባለሙያዎቹን አስቀድሞ በማዘጋጀትና በማሰልጠን ከተቋሙ ባሻገር ሚሊኒየም አዳራሽን ወደ ሆስፒታልነት በመቀየር የወረርሽኙን ስርጭት በመቀነስ እና በመቆጣጠር፤ በአገር አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው የሚኒስትሮች አማካሪ ቡድን ሦስት ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለጤና ሚኒስቴር በመስጠት የመሪነት ሚና በመጫወት እንዲሁም በኮቪድ-19 እና በሌሎች ድንገተኛ ወረርሽኞች ሕክምና ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በጤና ትምህርት ዘርፍም በየዓመቱ የሚመረቁ የድንገተኛ ሕክምና ስፔሻሊስቶችን በቁጥርና በጥራት የተሻለ በማድረግ በአገሪቷ ብቁ የድንገተኛና ፅኑ ሕክምና ባለሙያዎችን በማፍራት በክልሎችም ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል። በዚህ ረገድ በነርሲንግ በቢ.ኤስ.ሲ፣ በማስተርስና በፒ.ኤች.ዲ ደረጃ ትምህርቱን በማስጀመር ፈር ቀዳጅ ነው። የድንገተኛና ፅኑ ሕክምና ነርሶች የሚሰሩባቸው አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉ በማደረግ፣ ትምህርትና ሥልጠና በማመቻቸት፤ ሐኪም ብቻ ሳይሆን ነርሶችም ወደ ሙያው እንዲመጡ የማድረግ ሚናውም ተጠቃሽ ነው።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ አምቡላንስ ላይ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሙያተኞችን እንደ አገር በማስተርስ ሕክምና ያስጀመረ የመጀመሪያ ተቋም ስለመሆኑ መጥቀስ ይገባል። “ተቋሙ እና ድንገተኛ ሕክምና የተቆራኙ ናቸው” የሚሉት ዶ/ር ወልደሰንበት፤ በአገር ደረጃ ሆስፒታሎችን በሟቋቋም፣ በማደራጀትና በማብቃት ተቋማትን በመሳሪያና በሰው ኃይል በማገዝ፣ በትምህርትና ሥልጠና በማብቃት ረገድም እንዲሁ ድንገተኛና ፅኑ ሕክምና ላይ ጉልህ ድርሻ አለው ይላሉ።
የድንገተኛ ሕክምና መስጫ ተቋማትን
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
በመገንባት፣ አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት፣ የሰው ኃይል ማብቃትና ትምህርትን በአጭርና በረጅም ጊዜ በማሰልጠን እንዲሁም በድንገተኛ ሕክምና ፈር ቀዳጅ በመሆን አዳዲስ ያልተጀመሩ የድንገተኛ ሕክምና ዘርፎችን በመጀመር እና በማላመድም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ተጠቃሽ ነው።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በአዋቂዎች የድንገተኛ ሕክምና ክፍሉ ብቻ በየዕለቱ በአማካይ ከ90 እስከ 110 ለሚደርሱ ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የገለጹት የክፍሉ ኃላፊ ዶ/ር እሱባለው ገበየሁ ናቸው፡፡ ከ10 ዓመት በፊት በአንድ ባለሙያ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የሕክምና ክፍሉ በአሁኑ ወቅት ከሕክምና አልፎ ከተለያዩ ተቋማት የሚመጡትን ሳይጨምር በየዓመቱ እስከ 25 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።
የሕክምና ክፍሉ በሌሎች ተቋማት የማይገኙ እንደ ሜካኒካል ቬንትሌተር (አርቴፊሻል መተንፈሻ እና ካርዲያክ ሞኒተር (የልብ መከታተያ) የማሳሰሉ የሕክምና መሳሪያዎች ያሉት ሲሆን በእነዚህ መሣሪያዎች በመታገዝ በአደጋ፣ በእሣት ቃጠሎ፣ በመመረዝ፣ በሕክምና ችግር (Medical Com- plication) ሳቢያ ወደ ሆስፒታሉ ለሚመጡ ታካሚዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡ ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ሆስፒታሎች መካከል የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው የሚሉት ዶ/ር እሱባለው በከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎች ስብጥር 23 ስፔሻሊስቶችን በመያዝ በሌሎች የሕክምና ተማቋት የማይገኙ እንደ ፅኑ ሕሙማን ክትትል (Critical care) ዲፓርትመንት ማቋቋሙ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።
የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና ዘርፍ በአገራችን አዲስ ነው የሚሉት ዶ/ር ወልደሰንበት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ70 ዓመት የማይበልጥ ዕድሜ እንዳለው በመጥቀስ የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና አገልግሎት በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ ሲገልጹ ራሱን ችሎ እንደ ሕክምና ዘርፍ ከወጣ አጭር ጊዜ ቢሆንም ከሌሎች የሕክምና ዘርፎች ጋር ሲነፃፀር በ10 ዓመታት ዕድሜ የደረሰበት ደረጃ የሚበረታታ ነው ይላሉ፡፡ ዘርፉ መሻሻል ባለበት ፍጥነት መሻሻል ያሳየ ቢሆንም ማኅበረሰባችን ከሚፈልገው የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና አንጻር ግን የሚቀሩ ዳገቶች በመኖራቸው በትጋት መስራትና በፍጥነት መቀየር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የተደራጀና የተቀናጀ የቅድመ ሆስፒታል ትስስር ባላቸው አገራት ሰዎች ጤንነታቸው በየትኛውም ሁኔታ እክል ሲገጥመው መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በሚቀርብ አምቡላንስና በባለሙያ እገዛ ፈጣን ሕክምና ያገኛሉ የሚሉት ዶ/ር ወልደሰንበት፤ በአገራችን ሰዎች ሲታመሙ ከቤታቸው መውሰድ የሚችል የአምቡላንስ አገልግሎት በሚፈለገው ልክ የተደራጀ አለመሆኑን በመግለፅ
ባለድርሻ አካላት እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ ሁሉ ድርሻቸውን ወስደው መስራት ይጠበቅባችዋል ብለዋል።
የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና አገልግሎቱን በማስፋት ለታካሚዎች፣ ለአስታማሚዎች እና ለባለሙያዎች ምቹ ማድረግ የሕክምና ክፍሉ ቅድሚያ የተሰጠው ዕቅድ መሆኑን ዶ/ር እሱባለው ተናግረዋል። የሕክምና ባለሙያዎች ፈጣን የድንገተኛ ሕክምና መስጠት የሚያስችል አቅም እንዲኖራቸው ተከታታይ ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግም የስራ ክፍሉ እተገብረዋለሁ ያለው ጉዳይ ነው።
ኮሌጁ በድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና የላቀ የአገልግሎት ማዕከል በመሆን እየሰራ ሲሆን፤ በመስኩ በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ዘመናዊ ማዕከል መሆን የሚያስችለውን እንቅስቃሴም ከወዲሁ ጀምሯል።
ዶ/ር ወልደሰንበት እንደሚሉት በመንግሥት በተመደበ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ በጀት ዘመናዊ እና ለድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና አገልግሎት ተብሎ ዲዛይን የተደረገ ባለ አሥራ አምስት ወለል (ከወለሎች አራቱ ከምድር በታች የሆኑ) ሕንፃ ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 9 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ተረክቧል።
ሊገነባ የታቀደው ሕንፃ በየትኛውም የአገሪቷ ክፍል ለሚከሰት አደጋ፤ የአደጋ መከላከል ሠራተኞች ከቤት ውጪ ዝግጅት የሚያደርጉበት ስፍራ ይኖረዋል፡፡ በአደጋ ጊዜ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች በቀጥታ ወደ ማዕከሉ በሄሊኮፕተር በማጓጓዝ አፋጣኝ የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት መስጠት በሕንጸው አናት ላይ ሄሊኮፕተር ማሳረፍ እንዲችል ሆኖ ይሰራል፡፡ ማዕከሉ 963 የሕሙማን አልጋዎች እንዲሁም 40 የቀዶ ሕክምና ክፍሎች፣ 48 የጽኑ ሕሙማን (ICU) ክፍሎችን ይይዛል፡፡ ሕንጻው የትምህርትና የምርምር ማዕከላት ይኖሩታል፡፡ የቃጠሎ፣ የፕላስቲክ ቀዶ ሕክምና፣ የነርቭ እና የተለያዩ በአደጋ ጊዜ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች በላቀ መልኩ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
በተጨማሪም የላቀ ሕክምና የሚሰጥባቸው ልዩ ልዩ ክሊኒኮች ይኖሩታል፤ የዳሌና የጉልበት ሎሚ ቅየራ እና የስፖርት ሜዲስንን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሕንጻው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ ሁለት ሺህ ሠራተኞች ይኖሩታል።
ይህ በድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና የላቀ የሕክምና አገልግሎት ማዕከል በመስኩ የልህቀት ማዕከል ይሆናል። አሁን ያለውን የድንገተኛና ፅኑ ሕሙማን ቅበላ በ10 እጥፍ እንሚደሚያሳድገው ዶ/ር ወልደሰንበት ተናግረዋል። ይህም በሆስፒታሎች ተኝቶ ለመታከም ያለውን እጥረት እና የሕሙማን እንግልት በእጅጉ ይቀንሳል።
ኮሌጁ ከአገር ውስጥ አልፎ በምስራቅ አፍሪካ የድንገተኛ እና ፅኑ ሕክምና የልህቀት ማዕከልነቱን እውን ለማድረግ የጀመረው ውጥን ዳር ደርሶ ለኅብረተሰቡ እፎይታን የሚሰጥ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።
ፖለቲካ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የሽግግር ፍትሕ ለምን?
የሽግግር ፍትሕ ለምን?
በአየለ ያረጋል
መንደርደሪያ....
‘ፍትሕ’ ረቂቅ ጽንሰ ሃሳብ ነው-የተቀደሰ። ከሰው ልጅ ዘፍጥረት ይቀዳል። ተፈጥሯዊም፣ ኑባሬያዊም አንድምታ አለው። የሥነ ምግባር፣ የሥነ ሕግ እና የሥነ ሥርዓት መልክና ልክ ማንጸሪያ ነው። በአምላካዊ አስተምህሮ የተደነገገ፣ በሰብዓዊ እሳቤ በጣሙን የተፈለገ፣ የግብረ-ዕኩይ ማርከሻ፣ የብሩሕ ፍኖት ማሰሻም ጭምር ነው። “ፍትሕ አይጓደል፤ ደሃ አይበደል” እንዲል ሀገሬው በትውፊቱ፣ ፍትሕ ለሰው ልጆች የተስተካከለ ኑሮ፣ ለቀና የሕይወት ጎዳና፣ ከተሰናከለ ትናንት ማካካሻ፣ ወደ ተሻለ ነገ መሻገሪያ ድልድይ ነው። በቀል የሚያሽር፣ ሠላምና አብሮነት የሚያጸና፣ ሕይወት የሚያስተምር፣ የተዛነፈ ድርጊት በአመክንዮ መዝኖ የሚያቃና፣ ዕኩልነትና ክብርን ያጣመረ፣ የፍርድ ሚዛንን ያዘለ፣… ጽንሰ ሃሳብ ነው። የፍትሕ አስተኔ እና ክዋኔ የተለያየ መልክ ሊኖረው ይችላል። እሳቤው ግን ይኸው ነው። በዚህ ፅሁፍ ከፍትሕ አስተኔዎች መካከል የ‘ሽግግር ፍትሕን” (የሽግግር ወቅት ፍትሕን) ይቃኛል።
የሽግግር ፍትሕ ምንነት እና ታሪካዊ ዳራ
የሽግግር ወቅት ፍትሕ ትርጓሜ ከስያሜው ይነሳል። በማኅበረሰብ የሥርዓት እና የዘመን ምዕራፍ ሽግግር ወቅት የሚተገበር እና በዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ ተቋማት እንዲሁም በአገራት
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
መንግሥታት ሰነዶች ተቀራራቢ ትርጓሜና አንድምታ የተሰጠው ፅንስ ሃሳብ እና እርምጃ ነው። ይኸውም በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ግጭትን ጨምሮ በአያሌ መነሻዎች በደል፣ ሰቆቃ፣ ጭቆና፣ ግፎች እና ሌሎች መልከ ብዙ የሠብዓዊ መብት ጥሰትን ያስተናገዱ ወገኖች እንዲካሱ፣ በዳዮች እንዲክሱ እና ዕርቅና ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን ማስቻል የሚል ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ሰነዶች እንደሚያስረዱት የሽግግር ወቅት ፍትሕ ሂደት ከበደልና ጭቆና ተላቆ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ወሳኝ አማራጭ ነው። የተሻለ ነገ ለመገንባት በተንሸዋረረ ትናንት ላይ ፍትሕና ተጠያቂነት ማስፈን ሁነኛ ስንቅ ነው። በተለይም በመደበኛ የሕግ ሥርዓት መዳኘት ላልቻሉ፤ በታሪክ አጋጣሚ ለተፈጸሙ አይነተ ብዙ ችግሮች በዘላቂነት ዕልባት ለመስጠት አይነተኛ መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።
የዓለም አቀፉ የሽግግር ፍትሕ ማዕከል “አገራት በድሕረ ግጭት፤ በመደበኛ የፍትሕ ሥርዓታቸው አጥጋቢ ወይም በቂ ዳኝነት ወይንም ፍትሕ ላልተሰጣቸው ከፍተኛ፣ የተደራጁና በርካታ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች ምላሽ የሚሰጡባቸው መንገዶች” ይላቸዋል። ይኸውም ዘላቂ ሠላምና ልማት ዕውን ይሆን ዘንድ ቅድሚያ ‘የበደለ ክሶ፣ የቀማ መልሶ’ አይነት የሦስተኛ ወገን ዳኝነት እንደሚያሻ ያስረዳል። የተመድ ከፍተኛ የሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ደግሞ “ከአቅም በላይ ለሆኑና ልዩ ባሕሪይ ባላቸው የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ” በማለት ያብራራል።
በተመሳሳይ የአፍሪካ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲም በተለይ አፍሪካዊ አገራት በቅኝ ግዛት፣ በአፓርታይድ፣ በባርነት፣ በእርስ በእርስ ግጭቶችና መሰል አስከፊ የታሪክ በደሎች ፈውስ ለማግኘት ሲባል የሽግግር ፍትሕ ሂደት ገቢራዊ ስለመደረጉ ያትታል። ይህም ለተፈፀሙ ጥፋቶች ዕውቅና መስጠት፣ የወንጀል ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና ዘላቂ ሠላምና ደህንነት የማረጋገጥ ግቦች የያዙ ናቸው።
በአፍሪካ የሽግግር ወቅት ፍትሕ ፖሊሲ ላይ እንደተጠቀሰው የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ዓላማዎች ዕውነትን መፈለግና ማወቅ፣ ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም፣ የወንጀል ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እና የደረሰው በደል ዳግም እንዳይከሰት ዘላቂ የማሻሻያ መፍትሔ/ እርምጃ መውሰድ ነው። ከሠብዓዊ መብቶች አኳያ የሽግግር ወቅት ፍትሕ ከአጀንዳ 2063 ግቦች ጋር እንደሚጣጣም የፖሊሲ ሰነዱ ያስረዳል።
በሌላ በኩል የሽግግር ፍትሕ ለጉዳት ሰለባዎች ዕውቅና ከመስጠት ባሻገር በሠብዓዊ መብት መከበርና የሕግ የበላይነት መረጋገጥ ብሎም በሕዝቦች መካከል ዕርቅ ለመፍጠር ያግዛል።
የሽግግር ፍትሕ ሂደት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት (በፈረንጆች የዘመን ቀመር ከ1939- 1945) ወቅት በአውሮፓ የተፈጸሙ ሥርዓታዊ ግፎችን መነሻ በማድረግ እንደተጀመረ ታሪክ ያስረዳል። ለአብነትም የጀርመን ናዚ መሪዎች በጦርና በዘር ማጥፋት ወንጀሎች ተከሰው ታሪካዊ ውሳኔ አግኝተዋል። በጃፓን የተቋቋመው የቶኪዮ ወታደራዊ ችሎትም በተመሳሳይ ለሽግግር ፍትሕ እሳቤ መጠንሰስ እርሾ ሆኗል። በአውሮፓዊያን አቆጣጠር 1945 በግሪክ፣ በ1983 በአርጀንቲና መሰል የፍርድ ሂደቶች ተከናውነዋል። የሽግግር ፍትሕ በ1970 እና 1980ዎቹ በሠብዓዊ መብቶች ጥበቃ ላይ በማተኮር ዓለም አቀፍ የሠብዓዊ መብት የሕግ ማዕቀፎች እንዲወጡ አድርጓል። በካናዳ፣ በአውስትራሊያና በኒውዚላንድ ነባር የኅብረተሰብ ክፍሎች ለተፈፀመባቸው ጭቆና በዚህ ሂደት ምላሽ ለመስጠት ተሞክሯል። የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮዎች አገራትን ከነበሩበት ቀውስ ወደ ተሻለ ሠላም በማምጣት፣ መረጋጋት እና የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲያሰፍኑ አግዟል። ኮሎምቢያን፣ ደቡብ አፍሪካን፣ ዩጋንዳና ሴራሊዮንን ዋቢ ማድረግ ይቻላል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ሕብረት ‘ማኅበረሰቡ ያለፉ መጠነ ሰፊ ጥሰቶችን፣ ክፍፍሎችን እና አለመመጣጠኖችን ለማስወገድ፤ ፍትሕ ለማስፈን እና እርቅ ለማውረድ፤ ለደኅንነትም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሥርዓት ግንባታ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት’ የሚል ትርጓሜ ሰጥተውታል። ለዚህም መደበኛ ወይም ኢ-መደበኛ (ባሕላዊ) የፖሊሲ እርምጃዎች የሚወሰዱበትና ተቋማዊ አሠራሮች የሚተገበሩበት ሂደት እንደሆነ የተቋማቱ ሰነዶች ይገልጻሉ።
ሂደቱ ዕውነትን ማፈላለግ እና ይፋ ማውጣት፣ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ለተጎጂዎች ማካካሻ መስጠትና ተቋማዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ የሚሉ መሰረታዊ ስልቶችን ይከተላል። በዋናነትም የተፈጸሙ ጥሰቶች ድጋሚ እንዳይከሰቱ ዋስትና መስጠት ናቸው።
የሽግግር ፍትሕ ከአምባገነን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሸገጋሪያ ምቹ መደላድል ይፈጥራል። ላለፉ ቁርሾዎችና ላልሻሩ ቁስሎች መፍትሔ ያበጃል። ለችግሮች መፍቻ የዳኝነት ሥርዓት ያነብራል። በባህል ዕርቆች የተሟላ ካሳ ያሰጣል። ተጠያቂነትን ያሰፍናል። ቁርሾን ፈቶ፣ የሕግ ተጠያቂነትን አረጋገጦ፣ በዜጎችና በመንግሥታት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሰምርና ዴሞክራሲያዊ ተቋማት እንዲገነቡም ያስችላል።
በሽግግር ፍትሕ ሂደት ውጤታማነት የዕውነት አፈላላጊ ኮሚሽኖች ተቋቁመው ይተገበራሉ። ለምሣሌ በ1983 (እ.ኤ.አ) በአርጀንቲና፣ በ1990 (እ.ኤ.አ) በቺሊ እንዲሁም በ1995 (እ.ኤ.አ) በደቡብ አፍሪካ የተቋቋሙ የሐቅ አፈላላጊዎቸ በአርዓያነት ይጠቀሳሉ።
የሽግግር ፍትሕ በኢትዮጵያ
የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ በኢትዮጵያ ጎልቶ መሰማት የጀመረው ከፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት በኋላ ነው። በተለይም በ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ እንዲወጣ እንቅስቃሴ ተጀመረ። በሌላ በኩል የሠብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ) በተደጋጋሚ ድሕረ ጦርነት የሽግግር ፍትሕ ተግባራዊ እንዲደረግ ምክረ ሃሳብ ሲያቀርቡም ተደምጠዋል።
ያም ሆነ ይህ ግን እንደ አገር ኢ-ፍትሃዊነት በዕርቅና ይቅርታ መፍትሔ ለመስጠት በቅድሚያ አስቻይ የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት ታምኖበት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ የማዘጋጀት ቀዳሚ እርምጃ መስመር ያዘ። በወርኃ ጥር 2015 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስቴር ስር የተቋቋመ ገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ተደራጅቶ ወደ ሥራ ገባ። የባለሙያዎቹ ቡድን ከመላ አገሪቱ ተወካዮች ጋር ውይይቶች አካሄደ፤ ግብዓት አሰባሰበ። ከ15 ያላነሱ የዝግጅት ወራትን ፈጅቶ ረቂቅ ፖሊሲውን አዘጋጀ። በቅድመ- ፖሊሲ ማርቀቅ ሂደቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ እና የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የዓለም አቀፍ፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ተቋማት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
በሚያዚያ 2016 ዓ.ም ረቂቅ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ስራ ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቋል። ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የትግበራ ምዕራፍ ማስጀመሪያ መርሐ ግብርም ተካሂዷል። የፖሊሲው ዓላማም የኢትዮጵያን ዓውድ ያገናዘበ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ
ፕ/ር ቲም ሙርቲ
ቄስ ደረጀ ጀምበሩ
ሂደት በመተገበር ዘላቂ ሠላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር ነው። ፖሊሲው ከትናንት የተሻገሩ ተደራራቢና መጠነ ሰፊ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን በዕውነት፣ በዕርቅ፣ በምሕረት፣ በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ በሆነ መንገድ እንዲተገበሩ ግብ ይዟል።
የፖሊሲውን አስፈላጊነት በተመለከተ በመግቢያው ላይ “የሽግግር ፍትሕ ትግበራው በዓለም አቀፍ እና አህጉር−አቀፍ ሰነዶች ላይ የተመላከቱ መርሆዎችን በተከተለ አግባብ የሚካሄድበትን አሰራር ለማረጋገጥ፣ በአጠቃላይ ወጥነት ያለው፣ ግልጽ፣ ተጠያቂነት እና ፍትሕን የሚያሰፍን የሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደትን ለመምራት እንዲቻል ይህን የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል” ይላል።
የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በተለያዩ ወቅቶች ካነጋገራቸው የባለሙያዎች ቡድን አባላት መካከል ማርሸት ታደሰ (ዶክተር)፤ የሽግግር ፍትሕ ለፖለቲካና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውጤታማነት ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የሽግግር ፍትሕ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ በደሎችና ቁርሾዎችን በዕውነት፣ በፍትሕና በዕርቅ በመሻገር ዘላቂ ሠላምና ፍትሕ ለማስገኘት ያግዛል ሲሉ ያነሳሉ። የሽግግር ፍትሕ ሰነዱ ዓላማ ምሕረት መስጠትን፣ የሕግና ተቋማት ማሻሻያ ማድረግን፣ ማካካሻ መስጠትን፣ ዕውነት ማፈላለግ እና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሆነም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በአምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ የደረሰባትን ቁስል፣ በደልና የሠብዓዊ መብት ጥሰት በሽግግር ፍትሕ እንድትፈታም ነባራዊ ሁኔታዋን የዋጀ የሽግግር ፍትሕ መተግበር ያሻታል።
ሌላው የባለሙያዎች ቡድን አባል አዲስ ጌትነት በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ መስተጋብር እየሸረሸሩ የአገር ሕልውናን ሲፈታተኑ ተስተውለዋል ይላሉ። የፖሊሲ ሰነዱም ዓለም አቀፍ ተሞክሮን ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ችግሮችን በሽግግር ፍትሕ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንደሚረዳ ይናገራሉ።
የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው አንኳር ይዘቶች
የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ሦስት ክፍሎችን አቅፏል። የፖሊሲው ዓላማ፣ መርሆዎች፣ የተፈጻሚነት ወሰንና መሰል ጉዳዮች ጠቅላላ በሚል በክፍል አንድ ተካተዋል። ስለ ወንጀል ተጠያቂነት፣ ዕውነትን ማፈላለግ፣ ዕርቅ፣ ምሕረት፣ ማካካሻ፣ ተቋማዊ ማሻሻያና ስለ ፖሊሲው ትግበራ የጊዜ ወሰንና መሰል ነጥቦች ደግሞ የፖሊሲ ጉዳዮችና አቅጣጫዎች በሚል በሁለተኛው ክፍል ተብራርተዋል። በሦስተኛው ክፍል ደግሞ የመንግሥት እና የባለድርሻ አካላት ሚና እና የድጋፍ ሥርዓትን ይዳስሳል።
የፖሊሲው አጠቃላይ ዓላማ “የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አውድ መሰረት ያደረገ፣ የተቀናጀ እና የተናበበ የሽግግር ፍትሕ ሂደት የሚመራበት እና የሚተገበርበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዘላቂ ሠላም፣ ዕርቅ፣ የሕግ የበላይነት፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበትን መደላድል መፍጠር ነው” ይላል።
የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ “የወንጀል ምርመራ በማካሄድ እና ክስ በመመስረት አጥፊዎች ተጠያቂ የሚሆኑበትን ሥርዓት የሚዘረጋ ይሆናል” በማለት ያብራራል። ምርመራና ክስ የሚከናወነው ‘በጉልህ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ብቻ ያተኮረ’ እንደሚሆንም እንዲሁ።
በዚህ ረገድ ፖሊሲው “ጉልህ የሠብዓዊ መብት ጥሰት ማለት መጠነ ሰፊ፣ ስልታዊ፣ ወይም ተከታታይነት ባለው ሁኔታ፣ ዓለም- አቀፍ የሠብዓዊ መብት ሕጎችን፣ ዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግን ወይም የሠብዓዊነት ሕግን በመጣስ የሚፈጸም/ጥሰት ሲሆን በወንጀሉ
ፕ/ር አህመድ ዘከሪያ
የሥነ-ልቦና ባለሙያዋ ሠብለ ኃይሉ
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
ዓይነት እና በደረሰው የጉዳት መጠን መሰረት ተደርጎ የሚለይ ሌላ ወንጀልን ያካትታል” ሲል ይተረጉመዋል።
ክስ የሚመሰረትባቸውን አጥፊዎች ማንነት በተመለከተም “ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታዎች አንጻር በሁሉም አጥፊዎች ላይ ምርመራ ማካሄድ እና ክስ መመስረት ተመራጭ አካሄድ አይሆንም…. በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ ባላቸው አጥፊዎች ላይ ብቻ ይሆናል” ሲል ያትታል።
የወንጀል ምርመራ እና ክስ የሚከናወንበትን ተቋማዊ አሰራር በተመለከተ ደግሞ ክስና ምርመራው የሚከናወነው ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ ራሱን ችሎ በሚቋቋም ልዩ ዐቃቤ ሕግ ተቋም ሲሆን የፍርድ ሂደቱም በመደበኛው ፍርድ ቤቶች ስር “የተለየ የራሱ አደረጃጀት የሚኖረው ልዩ ፍርድ ቤት የሚደራጅ ይሆናል” በሚል ይገልጸዋል። “በአገር ውስጥ የማይገኙ ከፍተኛ ደረጃ የወንጀል ተሳትፎ ያላቸው አጥፊዎች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ከሚገኙበት አገር ተላልፈው እንዲሰጡ ለማድረግ ተገቢ ስራ ይሰራል” በማለትም ያክላል።
ከወንጀል ተጠያቂነት፣ ተፈጻሚነት ወሰን አኳያም የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ከጸደቀበት ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሆነ አስቀምጧል።
ፖሊሲው “ዕውነትን የማፈላለግ፣ ይፋ የማውጣት እና የዕርቅ ተግባራት ከተጽዕኖ እና ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ እና ገለልተኛ ሆኖ በሚቋቋም አዲስ የዕውነት አፈላላጊ ኮሚሽን አማካኝነት እንዲከናወኑ ይደረጋል” ሲል ያትታል። በፖሊሲው መሰረት በጉልህ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ያላቸው አጥፊዎች የምሕረት ተጠቃሚዎች አይሆኑም።
ከማካካሻ አኳያ በሠብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ኢ-ፍትሐዊ አሰራሮች ምክንያት ተጎጂ የሆኑ ግለሰቦች እና ማኅበረሰቦች የጉዳቶችን ዓይነት እና መጠን መሰረት በማድረግ የማካካሻ ሥርዓት እንደሚተገበር ይገልጻል።
የትግበራ ሂደቱ ልዩ ትኩረት ለሚሹ እና ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለሴቶች፣ ለሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአረጋዊያን እና ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ልዩ ፍላጎት እና ጥቅም ትኩረት በሚሰጥ አግባብ እንደሚከናወንም እንዲሁ።
ከባሕላዊ የፍትሕ ሥርዓቶች አኳያም “በሽግግር ፍትሕ ሂደት ከሌሎች የሽግግር ፍትሕ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እውነትን በማፈላለግ፣ ዕርቅ በማስፈን፣ በማካካሻ እና በምሕረት መስጠት ተግባራት እንዲሁም ማኅበረሰባዊ ሠላም ለማስፈን በሚደረጉ ስራዎች ማዕቀፍ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ይደረጋል” ይላል።
ፖሊሲው የመንግሥትና የባለድርሻ አካላትን ሚና በተመለከተ የሽግግር ፍትሕ ስልቶቹን በተቀናጀ መንገድ በመደጋገፍ እና በትብብር ለመተግበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚኖራቸውን ተሳትፎና ሚና በግልጽ አመላክቷል። ፍትሕ ሚኒስቴርን ጨምሮ የመንግሥት ተቋማት “የሽግግር ፍትሕ ስልቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚቋቋሙ ወይም የሚደራጁ ተቋማት ሊያጋጥማቸው የሚችል የሰው ኃይል፣ የበጀት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮችን ለመቅረፍ የሚያስችል እገዛ ማድረግ አለባቸው” በማለት ደንግጓል።
መንግሥትዊ ካልሆኑ ተቋማት መካከል ደግሞ የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና ከሽግግር ፍትሕ ሥርዓት አተገባበር ጋር በተያያዘ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሚና የሚኖራቸው አካላት ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ያትታል። ለምሣሌ ከጉዳዩ ጋር ጥብቅ ትስስር ካለው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ጋር በተያያዘ “የሽግግር ፍትሕ የትግበራ ሂደትና አገራዊ ምክክሩ ተመጋጋቢ በሆነ መልኩ ተግባራዊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ
ዶ/ር ባባ ጋሌህ ጃሎው
ይሰራል።” ይላል ፖሊሲው።
የሽግግር ፍትሕ . . .
የሽግግር ፍትሕ ከዓለም አቀፋዊ ጽንሰ ሃሳብና ግቡ አኳያ ለኢትዮጵያ የሚኖረው አስፈላጊነት አያጠራጥርም። ለምን ቢሉ በኢትዮጵያ ከትናነት እስከ ዛሬ የእርስ በእርስ ግጭት፣ ጦርነት እና መልከ ብዙ የሠብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተስተናገዱ መሆኑ እሙን ነውና። በታሪክ አጋጣሚ አይነተ ብዙ በደልና ሰቆቃዎች ተፈጽመዋል። ኢትዮጵያ የቁርሾ እና የቂም በቀል አዙሪት አልተለያትም። ፖለቲካዋ በጨቋኝና ተጨቋኝ ስሁት ትርክት የተለወሰ ነው። ስለዚህ በደሎችን ለማከም፣ ሠላምና ዴሞክራሲ የሰፈነበት ሥርዓት ለመገንባት የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ቅንጦት ሳይሆን መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ የማኀበራዊ ጉዳይ ምሁራን ይናገራሉ። የተራዘሙና የተሻገሩ ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት፣ በሕዝቦች መካከል መተማመንን መፍጠር፣ ለተፈጸሙ መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶች እና ወንጀሎች ምላሽ መስጠት፣ ፍትሕን ማስፈን እና ዕርቅን መተግበር አንዱ አማራጭ ነው።
በተለይ ከትናንት ችግሮች እያመረቀዙ ለሌላ ግጭትና ደም መፋሰስ የሚዳርጉ ቁስሎችን በዚህ አገባብ ማከም ግድ ይላል። ያለፉ አገራዊ በደሎችንና ቁርሾዎችን የአገሪቷን ተጨባጭ ሁኔታና ባሕሪይ ባገናዘበ አግባብ ኢ-ፍትሃዊነትን በፍትሕ፣ በእርቅና በይቅርታ መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ የዘርፉ ምሁራን ሲናገሩ ይደመጣል። ዘላቂ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ያመጣልና።
በእርግጥ ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ የበዳይ ተበዳይን አዙሪት ለመስበር የሽግግር ፍትሕ አንዱ ተመራጭ ሥልት መሆኑን ጠቅሷል። የመንግሥት ቁርጠኝነት መኖሩ ደግሞ ለሽግግር ፍትሕ ትግበራውና ሂደቱ መሳለጥ እንደሚበጅ ይታመንበታል።
በተለያዩ ጊዜያት በሽግግር ፍትሕ አስፈላጊነትና ትግበራ ዙሪያ አስተያየታቸውን የሰጡ የሥነ-ልቦና፣ የታሪክና የባሕል ባለሙያዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች የየራሳቸውን ምልከታ ያነሳሉ። የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ዋና ፀሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የፍትሕ ጉዳይ በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው፣ የዕርቅና የምሕረት ምንጭ እንደሆነ ይናገራሉ።
የሥነ-ልቦና ባለሙያዋ ሠብለ ኃይሉ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ያላባሩ ግጭቶችና ቀውሶች አንዱ መንስኤ ቀደም ሲል በአገሪቷ ለተፈጸሙ ጥፋቶች ዕልባት ባለመሰጠቱ እንደሆነ ያነሳሉ። የሽግግር ፍትሕ ለማካሄድ መወሰኑ ከግለሰብ እስከ አገር ወሳኝ ሚና በማንሳት፣ በሽግግር ፍትሕ ሂደት ችግሮችን በማከም መሻገር ይገባናል ይላሉ።
የቀድሞ የዕርቀ ሠላም ኮሚሽን አባል ልዑል በዕደማርያም መኮንን እና የኢትዮጵያ አገር ሽማግሌዎች መማክርት ጉባዔ አባል ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ የሽግግር ፍትሕ ማስፈጸሚያ ፖሊሲ መዘጋጀቱን እንደ ትልቅ እርምጃ ይወስዱታል። ፖሊሲው በማኅበረ-ኢኮኖሚው ዘርፍም ሁነኛ አገራዊ ሚና እንደሚኖረው እምነታቸውን ገልጸዋል።
በአስተያየት ሰጪዎቹ ገለጻ የሽግግር ፍትሕን ሁሉንም ያሳተፈ በማድረግ ለሕዝብ እፎይታ በሚሰጥ አግባብ መከወን ይገባል። የትናንትናን ችግር ፈትሾ በሽግግር ፍትሕ መፍትሄ በመስጠት የተሻለ ነገን መገንባት ላይ ማተኮር እንደሚያሻም አንስተዋል። የሽግግር ፍትሕ ወሳኝ በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡም ጠይቀዋል።
በአጠቃላይ ፖሊሲው የኢትዮጵያን የተራዘሙና የተወሳሰቡ ችግሮች በሽግግር ፍትሕ አማራጭ የመውጣቱን ፋይዳ እና ትግበራ በተመለከተ ፖሊሲው እንዲህ አስቀምጦታል።
“በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ሕዝባዊ ምክክሮች የተገኙ ግብዓቶችን ታሳቢ በማድረግ በተለያዩ ጊዜያት በአገሪቱ የተፈጠሩ ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል አሳታፊ፣ አካታች፣ ከዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት መርሆዎችና ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ፣ መሰረታዊ የሽግግር ፍትሕ መርሆዎችን የተከተለ፣ የአገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ፣ እንዲሁም አፈፃፀሙን አሳታፊ እና ሠብዓዊ መብት ተኮር በሆነ አካሄድ በመምራት እና ስልቶችን በተሰናሰለ መልኩ በመተግበር ዘላቂ ሠላም፣ የሕግ የበላይነት እና ፍትሕን ለማረጋገጥ የሚያስችል የሽግግር ፍትሕ ሂደት በአገር-አቀፍ ደረጃ መተግበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ወጥቷል”።
ለሒደቱ ተስፋዎችና ምክረ ሃሳቦች
የሽግግር ፍትሕ ሂደት ውጤታማ ለመሆን ደግሞ ሁሉን አሳታፊ፣ የሕግ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ እርቅ እና ካሳን ጭምር ታሳቢ ያደርጋል። ሂደቱ የይቅርታና የምሕረት ጉዳዮችን ያቅፋል።
የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍን
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም
በተመለከተ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች ማክበር ያለባቸውን መርሆዎች አስቀምጧል።
• ዐውድ-ተኮር፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ እና ሕጋዊ አደረጃጀት፣ ታሪክ፣ ባሕል እና ፍላጎቶች እንዲሁም ጥያቄዎች ላይ በመመሥረት በየአካባቢው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በመለየት ተፈጻሚነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ደንቦችን ያከበረ ሊሆን ይገባል።
• ሥርዓተ-ጾታን ያማከለ ፡- በሁሉም ሂደቶች ሴቶችን ማካተት፣ ጾታዊ እኩልነትን ማስፈን፣ በጾታዊ ጥቃቶች እና በሥርዓተ- ጾታ ላይ የተመሠረቱ ጥሰቶች እና ዋና መንስኤዎቻቸው ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት።
• ሁሉንም ኅብረተሰብ የሚለውጥ ፡- የሽግግር ፍትሕ ሂደት የተጎጂዎችን ፍላጎቶች በማሟላት እና አለመመጣጠኖችን ጨምሮ ፍትሐዊ ያልሆኑ የሥልጣን መዋቅሮችን፣ ሥር የሰደዱ አድልዎ እና አግላይ አሠራሮችን፣ ተቋማዊ ጉድለቶችን እና ለሌሎች መሰል የመብቶች ጥሰት ዋና መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት እንዲሁም ሠላም እና ደኅንነትን አደጋ ላይ ለሚጥሉ ሁኔታዎች መፍትሔ በማበጀት ጉልህ ማኅበረሰባዊ ለውጥን ለማምጣት የሚያስችል ዕድል ተደርጎም ሊወሰድ ይገባል።
• የሽግግር ፍትሕን የማስፈጸም ኃላፊነት፡- የኢትዮጵያ መንግሥት በሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተደገፈ ከአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ መልኩ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶችን የማስፈጸም ኃላፊነት አለበት።
• የሽግግር ፍትሕ አካሎችን ማቀናጀት፡ - የሽግግር ፍትሕ ተግባራትን የማቀናጀት ምርጫ፤ የሠላምና የዕርቅ እንዲሁም የፍትሕና የተጠያቂነት ዓላማዎችን ተደጋጋፊነትና አካታች ልማትን ለማረጋገጥ መጣር አለበት።
• ትብብር እና ቅንጅት፡- ሠላም ፍትሕ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ያለው ግፊት እንዲሁም የበርካታ ተዋናዮች መገኘት እና የሁሉም አካላት ትብብር እና ቅንጅት እጅግ አስፈላጊ ነው። የአገራዊ ባለቤትነትን፣ የአፍሪካዊ አመራርን፣ ሕጋዊነትን እና ተጠያቂነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ማብራራት እና መግለጽ ያስፈልጋል።
• የአቅም ግንባታ ለዘላቂነት፡- ኅብረተሰቡ አገራዊ ሂደቶች እና ተቋማትን የሚደግፍበትና የሚያሳድግበትን አቅም ከማጠናክር አኳያ ፤ ሁሉም የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የአቅም ግንባታ አካል ሊኖራቸው ይገባል።
በርካታ የዓለም አገራት በሽግግር ፍትሕ ዕውነትን ፈልገው፣ የወንጀል ተጠያቂነትን አስፍነው፣ ካሳን አስክሰው፣ ዘላቂ ሠላም፣ ፍትሕና ዕርቅ ለመፍጠር ሂደቱን ተጠቅመውበታል። ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ደቡብ አፍሪካ፣ ሴራሊዮን፣ ላይቤሪያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጋምቢያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጎዝላቪያ፣ ቺሊ፣ እንዲሁም ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል።
አገራቱ የሽግግር ፍትሕን ከነበሩበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ተላቀው የተሻለ ነገን ለመገንባት የተጠቀሙበት ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ ደቡብ አፍሪካና ጋምቢያ ተጠቃሾች ናቸው። እንደ ዕድል ሆኖ በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ጥልቅ ምርምር ያደረጉ የሁለቱ አገራት ምሁራንን በአካል አግኝቼ የማነጋገር ዕድል ገጥሞኝ ነበር። ምሁራኑ ደቡብ አፍሪካ እና ጋምቢያ በሽግግር ፍትሕ ሂደት ያለፉበት መንገድ ለኢትዮጵያ የተሻለ ተሞክሮ እንደሚሰጥ አውስተውኛል።
በደቡብ አፍሪካው ፍሪታውን ዩኒቨርሲቲ የፍትሕና ዕርቅ ኢንስቲትዩት ኃላፊ እና በአፍሪካ ጥናትና ምርምር የካበተ ልምድ ያላቸው ፕሮፌሰር ቲም ሙሪቲ በአፍሪካ የሽግግር ፍትሕ ዙሪያ ጥልቅ ምርምር አካሂደዋል። ታሪካዊና የአፍሪካ ተምሣሌት አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ከገጠማት አዙሪት ለመውጣት የጀመረችውን የሽግግር ፍትሕ አማራጭ ሂደቱን መጀመሯን አድንቀዋል። የሽግግር ፍትሕ መልከ ብዙ ግጭትና ግፎችን ላሳለፉ ማኅበረሰቦች ትናንትን በይቅርታ የነገውን በተስፋ ለመሻገር አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን በማንሳት።
በቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜህ ዘመነ መንግሥት ለ22 ዓመታት የተፈጸሙ ግፎችን በሽግግር ፍትሕ ሂደት የፈቱት የዕውነት፣ ዕርቅና ካሳ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ፤ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ተባባሪ አባል እና በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ዴቪስ ምሩቁ ጋምቢያዊው ዶክተር ባባ ጋሌህ ጃሎው፤ የሽግግር ፍትሕ አስፈላጊነት በተለይም ኢትዮጵያን ለመሰሉ አገራት አጠያያቂ አይደለም ይላሉ።
ሁለቱ ምሁራን የየአገራቸው የሽግግር ፍትሕ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ የተሻለ ልምድ እንደሚሰጥ ያምናሉ። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ፣ ባርነት እና ቅኝ ግዛት የጭቆና ሥርዓት ነጻ ስትወጣ ሥርዓቱ በጥቆሮች ላይ የፈጸመውን ግፍ፣ በማኅበራዊ ኢኮኖሚ መገለልና ብዝበዛ መልክ ለማስያዝ ሽግግር ፍትሕ ሂደት ተግብራለች።
ፕሮፌሰር ሙሪቲ እንደሚሉት፤ የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ በጥቁሮች ላይ የተፈጸሙ በደሎችን በሽግግር ፍትሕ ሂደት መልክ ለመስጠት ብሎም ሕዝባዊ አብሮነት እንዲቀጥል በሊቀ-ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ መሪነት የዕውነትና ዕርቀ ሠላም ኮሚሽን መቋቋሙን ያስታውሳሉ። እንደ ፕሮፌሰሩ ገለጻ የሽግግር ፍትሕ ሂደቱ ከአፈጻጸም ጋር የተያያዙ ክፍተቶች ቢኖሩበትም አካታችና የአገሪቱን ቀጣይ ጉዞ ለመቀየስ መሰረት የጣለ ነበር።
በተመሳሳይ በጋምቢያ አምባገነን መንግሥት የተፈጸሙ በደሎችን መልክ ለማስያዝ የተቋቋመው የዕውነት፣ ዕርቀ ሠላምና ካሳ ኮሚሽን ዜጎች ዕውነቱን እንዲረዱ፣ በዳዮች እንዲጠየቁና ተበዳዮች እንዲካሱ የሚያስችል ሰነድ ለአገሪቷ መንግሥት ማቅረቡን ዶክተር ባባ ጋሌህ ይገልጻሉ።
ምሁራኑ ኢትዮጵያ ለማድረግ ያሰበችው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ፍትሕ ፖለሲ እና የአገራትን ልምድ የቀመረ፣ አካታች፣ ተበዳዮችን የሚክስና አገርና ሕዝብን ወደፊት በሚያሻግር አግባብ እንዲፈጸም በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል።
ስለዚህ የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት ትግበራ ዘላቂ ሠላም ያለው ነገ ለመገንባት ለልማት የተነሳ፤ ከቅራኔ የራቀ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ተስፋ ይሰጣል። ለትግበራው ውጤታማነት ደግሞ ግለሰብ፣ ማኅበረሰብ፣ ልሂቃን እና ተቋማት አገራዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ግድ ይላል።
ትግበራው በፖሊሲው ላይ እንደተመላከተው የሠብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ያከበረ፣ ተጎጂን ማዕከል ያደረገ እና የፖሊሲውን መርሆዎች ያከበረ መሆኑን በመከታተልና በመደገፍ፤ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች በማሳተፍ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላምና ልማት እንዲያመጣና ዜጎች ነገን በተስፋ እንዲጠብቁና በአገራቸው ላይ ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸው በተሟላ መልኩ መተግበር አለበት። ለዚህም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ነው። የሽግግር ሂደቱን ምሉዕ ለማድረግ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ትልቁ ቁምነገር እንደሆነ በምሁራን ይነሳል።
ነጋሪ 6ኛ ዓመት ቁጥር 27 ነሐሴ 2016 ዓ.ም